ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነን
Jul 25, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተመራቂ መኮንኖች ገለጹ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖች አስመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ይመር መኮንን፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሃብታሙ፣ ጄኔራል መኮንኖች እና የሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። በዚህ ወቅት ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመራቂ መኮንኖች በስልጠናው ያገኙትን ንድፈ ሃሳብ ከተግባር ያጣመረ ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም የሀገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከተመራቂ መኮንኖቹ መካከል የዋንጫ ተሸላሚው ምክትል መቶ አለቃ ዳዊት አዱኛ አንደገለጹት፤ በሶስት ዓመታት ወታደራዊ ስልጠና ሀገራቸውን በብቃት ማገልገል የሚያስችል ዕውቀት ቀስመዋል። ከስልጠና ባገኙት እውቀትና ክህሎት መሰረትም ኢትዮጵያን ለማገልገል የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሌላው የሜዳሊያ ተሸላሚ ምክትል መቶ አለቃ ጌትነት አፈለ በበኩላቸው፤ በስልጠናው ኢትዮጵያን ሀገሬን በብቃት የማገለግልበትን ወታደራዊ ዕውቀት አግኝቻለሁ ብለዋል። በስልጠናው ያገኙትን የዕውቀት፣ የአስተሳሰብና ክህሎት ብቃት ለሀገራቸው መልሰው ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዕድገትና ብልፅግና ጎዳና ላይ በመሆኗ የሀገሪቱን ልማት ለማደናቀፍ የሚሹ የጥፋት ኃይሎችን ተልዕኮ ለማምከን ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቆይታቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ክብር ማስጠበቅ የሚያስችል ወታደራዊ ዕውቀት መቅሰማቸውን ያነሱት ደግሞ ምክትል መቶ አለቃ ኦብሳ ሰይፉ ናቸው። የሀገራቸውን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሀገረ መንግሥት ግንባታን ለማጠናከር እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ነው
Jul 25, 2026 148
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው አካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደት የሀገረ መንግሥት ግንባታን ለማጠናከር፣ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና የሕዝቦችን አንድነት ማረጋገጥ የሚያስችል ታላቅ ዕድል መሆኑን ተመካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ምክክር የሚደረግባቸውን ስምንት አጀንዳዎች በመለየት ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዋናውን ምክክር እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተጀመረው ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያውያን በመመካከር ሀገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን መሠረት የሚጥል ነው። በምክክር መድረኩ እየተመካከሩ የሚገኙና አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ፖለቲከኞች እንዳመለከቱት፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለሰላምና ለፍትህ በርካታ ትግሎች የተደረጉ ቢሆንም የሚፈለገው ሰላምና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት መገንባት አልተቻሉም። አሁን ላይ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ግን ዜጎች በነፃነት የሚወያዩበትና በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ነው የተናገሩት። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ጎበዜ አበራ እንደገለጹት፤ ይህ እጅግ አካታችና የመላዋን ኢትዮጵያ ስብጥርና ብዝሃነት ያከበረ መድረክ፣ በሀገራችን ባልተለመደ መልኩ ችግሮችን ተነጋግሮ የመፍታት አዲስ ባህልና ሥርዓት ለመገንባት ትልቅ ተስፋ ሰንቋል። በሂደቱ በዋና ዋና መዋቅራዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ መግባባት ይፈጠራል ብለን እንጠብቃለን ሲሉም ገልጸዋል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሀፊ ሙሉብርሃን ኃይሉ፤ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ አማካኝነት ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት እና ተቋማት እንደሚፈጠሩና በየደረጃው ያሉ መዋቅራዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ሀገሪቱ ወደ ሙሉ ሰላም፣ መረጋጋት እና ዘላቂ አንድነት እንደሚያሸጋግራት አክለዋል። የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ፕሬዚዳንት አላምረው ይርዳው እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ቀደምት ትውልዶች ያላገኙትን ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ ያመቻቸ ነው። መላው ሕዝብ ትውልድን ወደፊት በሚያሸጋግር የጋራ ዓላማ ላይ በትብብር ሊሠራ እንደሚገባም ነው ጨምረው የገለጹት።
ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የሚያግዝ ስምሪት ተደርጓል - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
Jul 25, 2026 193
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ለመገንባት የሚያግዝ ስምሪት ማድረጉን ገለጸ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን በተመለከተ ባካሄደው ግምገማዊ ውይይት ጠንካራና የተረጋጋ ሀገረ-መንግሥት ለመፍጠር በሚያግዝ መልኩ የተሳካ ስምሪት ማድረጉን ገልጿል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመገንዘብና ስጋቶችን አስቀድሞ በመተንተን ወደ ተግባር መገባቱን የጠቆመው የአገልግሎቱ መግለጫ፤ በተለይ የሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ደኅንነት ማዕከል በማድረግ የተዘጋጀውን የበጀት ዓመቱን ቁልፍ ግብ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በማሳካት የጸና ሀገረ-መንግሥት የመገንባት ሂደቱ ላይ ጉልህ ሚና መጫወት መቻሉን ጠቁሟል፡፡ ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅሞች መከበርና ማደግ እንዲሁም ለዜጎች ደኅንነት ስጋት በሆኑ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ መንገዶች በመሰብሰብ፣በማደራጀትና በመተንተን ለውሳኔ ሰጪ አካላትና ለኦፕሬሽናል ግዳጆች ማዋል መቻሉ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡ በዚህም የሽብርና ታጣቂ ቡድኖችን የመረጃ፣ የሎጂስቲክስ እና የሽብር መረብ በመበጣጠስና ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ በማካሄድ እንደ ሀገር ተደቅነው የነበሩ በርካታ ስጋቶችን ማክሸፍ መቻሉን አስታውቋል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ያስገኛቸውን ጥቅሞች በሚጻረር መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችንና የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመከላከል የዜጎችን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በተከናወኑ የመረጃ ስምሪቶችና ኦፕሬሽኖች በርካታ በሕገ-ወጥ ተግባር የተሰማሩ ሰዎች ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መደረጉንም መግለጫው ጠቅሷል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በውጭ መረጃ ስምሪቱ የሀገሪቷን ብሔራዊ ጥቅሞች በላቀ ደረጃ የሚያረጋግጡ ስኬቶችን ማስመዝገቡን መግለጫው አብራርቷል፡፡ በዚህ ረገድ በቀጣናው እና በዓለም-አቀፍ ደረጃ የሚስተዋሉ የኃይል አሰላለፍ ለውጦችንና ጂኦ-ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን በመረዳትና በመተንተን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነት፣ ጥቅምና ክብር የሚያረጋግጡ አቅጣጫዎች ለመከተል የሚያግዙ ስትራቴጂካል መረጃዎች መሰብሰብና ማሰራጨት መቻሉና ተጨባጭ ለውጥ መገኘቱንም አስታውቋል፡፡ ከውጭ አቻ ተቋማት ጋር መርህን በጠበቀ መልኩ የተከናወኑ የአጋርነትና ትብብር ሥራዎችም ሽብርተኝነትን፤ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችንና ሕገ-ወጥ የገንዘብና የጦር-መሣሪያ ዝውውሮችን በመከላከል ከፍተኛ ሚና እንዳበረከቱ አመልክቷል፡፡ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ በደኅንነት ስምሪት ማዕቀፉ፣ ቁልፍ የመንግሥት ተቋማትን፣ እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ስልታዊ መሰረተ-ልማቶችን እና ታላላቅ ሀገራዊ ኹነቶችን ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የመጠበቅ አቅም እንደገነባ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ አስተማማኝ በሆነ መንገድ በቴክኖሎጂ ጭምር ታግዞ የተገነባው ደኅንነትን የማረጋገጥ ስርዓት ኢትዮጵያ ተመራጭ የኮንፈረስ ቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን እገዛ ማድረጉም መግለጫው ገልጿል። የአቪዬሽን ደኅንነትን በማረጋገጥ ረገድ የተከናወኑ ሥራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተማማኝና ተመራጭ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽዖ እያደረገ መቀጠሉ በዓመታዊ ግምገማው ተነስቷል፡፡ ይህን ስኬት በአሠራርና በቴክኖሎጂ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትም ስኬታማ እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅትና የሌሎችም ምዘና ተቋማትን ኦዲቶችን ያለምንም ጉድለት ማጠናቀቅ መቻሉና የአቪዬሽን ደኅንነት አዋጅ ተሻሽሎ መጽደቁም በአብነት የሚጠቀሱ ስኬቶች መሆናቸው በመግለጫው ተብራርቷል። እንደ ሀገር የሚቃጡ የሥነ-ልቦና ጦርነቶችን ለመመከትና ለማጥቃት በተሰጡት የማስተባበር ሥራዎች ከጠላት ኃይሎች የሚቃጡ ሙከራዎችን ከማክሸፍ ባሻገር፤ ሀገራዊ አንድነትንና ሕብረትን የሚያፀኑ እንዲሁም የኢትዮጵያን ገፅታ የሚገነቡ ሰፋፊ ሥራዎች መከናወናቸውም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ ለመረጃ፣ ለደኅንነትና ለሥነ-ልቦና ጦርነት ስምሪት የሚውሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በራስ አቅም በማበልፀግ የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስ የተከናወኑ ሥራዎች ከፍተኛ ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸው መገምገሙ ተመላክቷል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መግለጫ እንዳመለከተው፤ በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ያለው ተቋም ለመገንባት የሚከናወኑትን ሥራዎች ለማጠናከር ሪፎርሙን በአዳዲስ ዕይታዎች የሚያበለፅጉ አቅጣጫዎች ተቀምጧል፡፡
የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 25, 2026 232
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ ሰራተኞች የቡና ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን በእምድብር ከተማ በሰሜ ቀበሌ አካሄደዋል ። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ በወቅቱ እንደገለፁት የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው፡፡ ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል። በዘርፉ በቅንጅት በተሰራው ስራ በቡና ምርታማነት ላይ የተገኘው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል፡፡ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ጁሃር የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት ስኬት እየተመዘገበ ነው ብለዋል። በዘንድሮ አመት በክልሉ 48 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በሽታ የሚቋቋሙ፣ በአጭር ጊዜ የሚደርሱና ምርታማ የሆኑ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በብልፅግና ፓርቲ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። ወጣቶች ቡና በስፋት እና በጥራት በማምረት እንዲሁም በፍራፍሬ ልማት ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን ያነሱት ደግሞ የእምድብር ከተማ ከንቲባ አቶ ግንባሩ በርጋ ናቸው ። የከተማው ወጣት ዳዊት ትእዛዙ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞች እያለማ መሆኑን ተናግሮ ዘንድሮም ይህን በማስፋት ከ2 ሺህ በላይ ችግኝ መትከሉን ተናግሯል፡፡ ሌላው በእምድብር ከተማ በቡና ልማት የተሰማሩት አቶ ሳሙኤል ፍራንሷ በበኩላቸው ባላቸው 3 ሄክታር ማሳ ላይ ቡና እያለሙ መሆኑን ጠቁመው ዘንድሮ ከ1 ሺህ በላይ የተሻሻለ የቡና ችግኝ መትከላቸውን ገልጸዋል፡፡
በብሄረሰብ አስተዳደሩ 34 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል
Jul 25, 2026 176
ሰቆጣ፤ ሃምሌ 18/2018(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 34 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለፁት አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በስፋት በመገንባት ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከ539 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ 34 የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል። የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶችም 820 ሄክታር መሬት በማልማት ከአራት ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። ፕሮጀክቶቹ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በበጋ ወቅት ጭምር በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል። ስራ የጀመሩት ፕሮጀክቶች አርሶ አደሩ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ አትክልትና ፍራፍሬ ጨምሮ እንዲያመርትና የስርዓተ ምግብ ችግር እንዲያቃልል የሚያደርግ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። የሰቆጣ ከተማ የ03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጉሱ አመረ እንዳሉት፤ በአካባቢያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ የማምረት አቅም እንድናገኝ የሚያደርግ ነው ። የጓሮ አትክልትና ፍሬፍሬ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ምርቶችን በማሳደግ አኗኗራቸውን ለመቀየር የሚያስችላቸው መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል። በአስተዳደሩ በጋዝጊብላ ወረዳ 03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አገኘሁ ጌታሁን፤በቀበሌያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በክረምት ዝናብ ብቻ የተመሰረተውን የግብርና ስራ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚነታችን እንድናሳድግ የሚያደርግ ነው ብለዋል። በብሄረሰብ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት በተገነቡ የመስኖ ተቋማት አራት ሺህ 885 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ፖለቲካ

መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ የጥፋት ኃይሎችን ተልዕኮ በማምከን ግዳጁን በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ ነው
Jul 25, 2026 296
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ የጥፋት ኃይሎችን ተልዕኮ በማምከን ግዳጁን በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖች እያስመረቀ ይገኛል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮንን፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጌታቸው ሃብታሙ፣ ጄኔራል መኮንኖችና የሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ባላት የጂኦ ፖለቲካ አቀማመጥና በተፈጥሮ ሃብቷ ምክንያት ለተለያዩ ፈተናዎች ስትጋለጥ የቆየች ሀገር ናት። አርበኞች በታሪክ የሀገራቸውን ህልውና በመጠበቅ የተጫወቱትን ሚና በማስታወስ፤ በአሁኑ ወቅት የሀገርን ሰላምና ደኅንነት ለመፈታተን የሚሞክሩ ኃይሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በልማትና በብልፅግና ጉዞ ላይ መሆኗን የማይወዱ የጥፋት ኃይሎች ሴራና ደባ ለመፈጸም እየሞከሩ መሆኑንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሀገር ፍቅር፣ በአርበኝነትና ሕዝብን የማገልገል ዕሴቶች በመላበስ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚቃጡ የጥፋት ሴራዎችን በብቃት እያመከነ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሚገጥማትን ፈተና በድል ለመወጣት ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ የወል ብቃት ያላት ሀገር መሆኗን በመጥቀስ። ይሁንና ዘመኑ የሚጠይቀውን የደኅንነት ፈተና ለመመከት የወል ብቃት ብቻ በቂ እንደማይሆን ጠቅሰው፤ ያለውን አቅም በሰው ኃይል ልማት፣ በትምህርትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የማሰልጠንና የማብቃት ተልዕኮውን በማጠናከር በርካታ የስልጠና ተቋማትን በማስፋፋት የሰው ኃይል ልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም የሠራዊቱ የሙያ ብቃት፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የተልዕኮ አፈጻጸም አቅም እየጎለበተና እየዘመነ መምጣቱን ጠቁመዋል። የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮንን በበኩላቸው፤ ዘመናዊ ሠራዊት ግንባታን እውን ማድረግ የሚያስችሉ የትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ተገንብተዋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና ሌሎች የሥልጠና ማዕከላት ዘመኑን የዋጀ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅ በቴክኖሎጂ፣ በአስተሳሰብ፣ በአሰራር የበቁ የሠራዊትና አመራር አባላት እየተፈጠሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው የ71ኛ መተማ ካዴት ዕጩ መኮንኖችም የዚህ ጥረት መገለጫዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሀብታሙ፤ ተመራቂዎቹ የወሰዱት ስልጠና ሁለንተናዊ የአመራር ጥንካሬን የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል። ዕጩ መኮንኖቹ ያገኙት ትምህርትና ስልጠና ማንኛውንም የሠራዊት የግዳጅ ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አቅም አጎናፅፏቸዋል ብለዋል። ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አፍሪካውያን ዕጩ መኮንኖችም ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸውን ተናግረዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ የሚበጅና አዋጭ መንገድ ነው - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ
Jul 25, 2026 250
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ በውይይትና መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሔ የማምጣት አዋጭ መንገድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ። ዋና ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሂደትን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ በተለያዩ ቡድኖች ሆነው ውይይት ማድረግ መቀጠላቸውን ገልጸዋል። ተመካካሪዎች በመከባበርና በመደማመጥ በነጻነት ሀሳባቸውን እያንሸራሸሩ እንደሚገኙም አመልክተዋል። በምክክሩ የተለያዩ ሀሳቦች መነሳታቸውና በጥልቀት መዳሰሳቸው በቀጣዩ ሀሳቦችን ወደ አንድ የመሰብሰብ ምዕራፍ ሂደት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል። የምክክር ጉባኤው የመጨረሻ ምዕራፍ የጋራ መግባባት እንደሆነ ጠቅሰው ለዚህም መሳካት አሁን እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች ወሳኝ አበርክቶ አላቸው ነው ያሉት። አጠቃላይ እስከ አሁን በጉባኤው ላይ የታዩ ነገሮች በጣም አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ። ዋና ኮሚሽነሩ ለኢትዮጵያ የምክክር ሂደቱ አዋጭና ዘላቂ መፍትሄን መምጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
Jul 25, 2026 283
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል። በምረቃ ሥነ-ሰርዓቱ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄነራል ይመር መኮንን፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው ሀብታሙ፣ የክብር ጄነራል መኮንኖች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። በመርሃግብሩ በስልጠናው ብልጫ ያመጡ ዕጩ መኮንኖች በጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የማዕረግ ማልበስ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው ሀብታሙ፤ ተመራቂዎቹ የወሰዱት ስልጠና ሁለንተናዊ የአመራር ጥንካሬን የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል። ዕጩ መኮንኖቹ ከትምህርትና ስልጠናው ያገኙት እውቀት እና ክህሎት ማንኛውምንም የሠራዊት የግዳጅ ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አቅም አጎናፅፏቸዋል ብለዋል። ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አፍሪካውያን ዕጩ መኮንኖችም ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸውን ተናግረዋል።
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በኢትዮጵያ አዲስ የመግባባትና የአንድነት ታሪክ እየተጻፈ ነው
Jul 24, 2026 415
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በኢትዮጵያ አዲስ የመግባባትና የአንድነት ታሪክ እየተጻፈ መሆኑን ዑስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ለምክክር የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በእነዚህ አጀንዳዎች ላይም 4ሺህ ተመካካሪዎች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተመካከሩ ይገኛሉ። ዑስታዝ ጀማል ለኢዜአ በሰጡት አስተያየትም፤ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ እየተጻፈበት መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በነበሩ ሥርዓቶች ውሳኔዎች ከላይ ወደ ሕዝብ የሚወርዱበት አሰራር እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ግን ሕዝቦች በመመካከር በጋራ ውሳኔ የሚደርሱበት አውድ ተፈጥሯል ብለዋል። የምክክር ጉባኤም ''ኢትዮጵያ እየመከረች ነው'' የሚለውን መሪ ሃሳብ በሚመጥን መልኩ በሕዝብ ወኪል በሆኑ ተመናካካሪዎች መካከል ግልፅና አሳታፊ ምክክር እየተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል። ከሂደቱም የሚጠበቁ ምክረ ሀሳቦች ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ዕድገት የሚያግዙ ውጤቶችን የሚያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። በዓለም ላይ በምክክር ችግሮቻቸውን የፈቱ ሀገራት ብዙ ናቸው ያሉት ተመካካሪው፤ የምክክር ጉባኤውም በኢትዮጵያውያን ግልጽ ተሳትፎ መመራቱ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስችል እንደሆነ አስረድተዋል። ከምክክሩ የሚወጡ ምክረ ሀሳቦች በባለድርሻ አካላት ተግባራዊ ሆነው የሕዝቦችን ተጠቃሚነትና የሀገርን የጋራ ጥቅም የሚያሳድጉ ውጤቶች እንደሚያመጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሀሳቦችን ወደ አንድ የጋራ መግባባት ለማምጣት የተከፈተ ታላቅ መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል። በምክክር የሚገነባው መግባባትም ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና የጋራ ብልፅግና መሰረት እንደሚሆን አንስተዋል።
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና የጸናች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው
Jul 24, 2026 413
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና የጸናች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና አራት ሺህ የሕዝብ ተወካይ ተመካካሪዎች በተገኙበት ዋናው የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መጀመሩ ይታወቃል። ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮም የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮችና በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን የሚወክሉ ተመካካሪዎች በንዑስ ቡድኖች ተከፋፍለው በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ እየተመካከሩ ይገኛሉ። ተመካካሪ ተስፋዬ አየለ እንድገለጹት፤ የምክክር ሂደቱ የጸናች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ሁነኛ መንገድ በመሆኑ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምክክር ጉባኤው ሁሉንም ያካተተ፣ ያሳተፈ እና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥር ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስተላለፍ እየመከሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ሊቀ-ካህናት ጌታሰው በላይ በበኩላቸው፤ በምክክሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች እና ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች በመመካከር ላይ መሆናቸውን አንስተዋል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተፈጠረው ታላቅ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው የበለጸገች ሀገርን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ዕድል በአግባቡ በመጠቀምና አንዱ የአንዱን ሃሳብ በመረዳት ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስተላለፍ እየመከርን ነው ብለዋል። በምክክሩ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገርን መጻኢ ዕድል ብሩህ ለማድረግ እየመከሩ መሆናቸውንም የገለጸው ደግሞ ወጣት ቸሩ በየነ ነው። የምክክር ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ተደራጅቶ መጀመሩንና አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልጾ ሁሉንም ያካተተ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋና ብሩህ መደላድል ይዞ እንደሚመጣ እምነቱን ተናግሯል፡፡ ሌላኛው አስተያያት ሰጪ ማርቆስ ገዛኸኝ ምክክሩ ትስስርን የሚያጠናክር፤ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ እንዲሁም መጻኢ ዕድልን የሚወስን በመሆኑ በንቃት አየተሳተፋ መሆኑን ገልጸዋል። ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚቆሙበትን የአንድነት ምዕራፍ ለመፍጠር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አመልክተው ሂደቱ ለጠንካራ የሀገር ግንባታ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

ማህበራዊ
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ አቅም የመልማት እድልን ይፈጥራል
Jul 25, 2026 195
ጎንደር ፤ሐምሌ 18 /2018(ኢዜአ)፡-የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀት በማስተባበር በራስ አቅም የመልማት እድልን የሚፈጥር ነው ሲሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ መድረክ በጎንደር ከተማ አካሂዷል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ትኩረት የተሰጠው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማቃለል የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በተያዘው ክረምትም የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ ችግኝ በመትከል፣ ደም በመለገስ፣ የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት የመገንባትና የማደስ እና ሌሎች ተግባራት እየተከናወነ ነው ብለዋል። ከ236 ሺህ በላይ ማህበረሰብን በማሳተፍ 136 ሺህ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የከተማ አስተዳደሩ አደረጃጅት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ እንዳርጌ ናቸው። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መከናወኑ ከመንግስት ካዝና ይወጣ የነበረውን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት በማዳን የልማት ስራዎችን ለማከናወን ያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። በስድስቱም ክፍለ ከተሞች እስካሁን በተካሄደው የደም ልገሳ ተግባርም ከሁለት ሺህ ዩኒት በላይ ደም ማሰባሰብ መቻሉን ጠቁመው 16 የአቅመ ደካማ ዜጎችን መኖሪያ ቤቶችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መገንባት ተችሏል ብለዋል። ከአራት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለማከናወን የታቀደውን ከ60 በመቶ በላይ በበጎ ፈቃድ ስራው መፈጸም መቻሉን አስገንዝበዋል። በመድረኩ ላይም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች በለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በክልሉ በጤና ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ተችሏል
Jul 25, 2026 212
ባህር ዳር፤ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ። የቢሮው የ2018 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር መድረክ በባህር ዳር ከተማተካሂዷል። የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን በኩል ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህም ዘላቂና የተደራጀ የጤና ስርዓት በመገንባት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን እየተቻለ መሆኑን ጠቁመው በህክምና ተቋማት ህሙማን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የጤና ተቋማትን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር እና ከወረቀት ነፃ አሰራርን በመዘርጋት የተገልጋዩን እንግልት የመቀነስ ስራም በትኩረት መከናወኑን አንስተዋል። በየደረጃው በሚገኙ የህክምና ተቋማት ዘመኑ ያፈራቸውን የህክምና መሳሪያዎችን በማሟላት ማህበረሰቡን በአቅራቢያው መሰረታዊ የጤና ህክምና የአገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ የተሻለ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ስርዓት በመገንባትም ሃብት መሰብሰብ እንደተቻለና በዚህም የህክምና አገልግሎቱን በራስ አቅም የመስጠት ሂደትን የማጠናከር ስራ መከናወኑን አመልክተዋል። በየደረጃው 109 የማህበረሰብ መድሃኒት ቤቶችን በማቋቋም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የማሳደግ ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል። በ2019 በጀት ዓመት በሁሉም መስክ የተሻለ ስራ ለመስራት ታቅዶ እየተተገበረ መሆኑን አስታውቀዋል። የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አባይ መላኩ በበኩላቸው፤ በክልሉ በሽታዎችን ከመከላከል ባለፈ አክሞ የማዳን አቅም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። የማህብረሰብ መድሃኒት ቤቶችን በመገንባት የመድሃኒት አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት እና ለህክምና የተመቹ ፅዱና ማራኪ የጤና ተቋማትን በማስፋት በኩልም አበረታች ስራ መሰራቱን ገልፀዋል። እንዲሁም ተቋሙ እያካሄደ ያለው የሪፎርም ስራ በተሻለ ጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በጤናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከርም የማህበረሰቡን የጤና ችግር በመሰረታዊነት መፍታት እስኪቻል ድረስ የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመድረኩ የክልልና በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Jul 25, 2026 163
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያመጡ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሔደ ነው። ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገንና ጥራትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዘርፉ ላጋጠሙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ በትምህርት ዘርፉ በቅንጅት ውጤታማ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን አንስተዋል። ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግና በግብአት ለማሟላትም በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። በዚሁ ወቅት ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ ሲሆን የመማሪያ ክፍሎች ዕድሳት መደረጉንም ነው የተናገሩት። ይህም የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት በመጨመር በትምህርታቸው ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲታይ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስረድተዋል። በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የታየውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሠራ አመልክተው ባለድርሻ አካላትም ለዚሁ ስኬት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ በበኩላቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የተከናወኑ ጠንካራ ሥራዎች ፍሬ እያፈሩ ነው። የህዝብን አቅም በመጠቀም ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና የመምህራንን አቅም ለመገንባት በተቀናጀ መንገድ የተሠሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ነው ያነሱት። የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተሳተፉበት ባለው መድረክ የትምህርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ ነው
Jul 24, 2026 263
ድሬደዋ፣ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦የድሬዳዋ አስተዳደር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በአል ድሬዳዋ ለመጡ ምዕመናንና እንግዶች አቀባበል አድርገዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በወቅቱ እንዳሉት፥ ከተማዋ በህብረ ብሔራዊ አንድነት የደመቀች በመሆኗ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለሚያጠናክሩ ተግባራት ትኩረት በመስጠት እየተከናወኑ ነው። ድሬዳዋ እንግዶችን በፍቅር የመቀበል ልምድ ያላት መሆኗም የዚሁ መገለጫ መሆኑን ጠቁመው የዛሬው አቀባበልም ይህንኑ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል። ከተማዋ የሰላም፣ የልማትና የፍቅር ተምሳሌት በመሆኗም ለኃይማኖታዊም ሆነ ሌሎች ሁነቶች ተመራጭነቷ እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል። ድሬዳዋ የዜጎች የርስ በርስ ትስስር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መጠናከር መሰረት መሆኑን በተግባር አሳይታለች ያሉት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው መምሪያው የቁሉቢ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በአል ታዳሚዎች በድሬዳዋ ቆይታቸው ሰላማዊ ጊዜ እንዲያሳልፉ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። ለኃይማኖታዊ ክብረ በአሉ ወደ ድሬዳዋ ከመጡ ምዕመናን መካከል አቶ ስዩም ታደሰ እና አቶ የፈቃዱ አስናቀ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች ያደረጉላቸው አቀባበልና መስተንግዶ አስደስቷቸዋል።
ኢኮኖሚ
የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 25, 2026 232
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ ሰራተኞች የቡና ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን በእምድብር ከተማ በሰሜ ቀበሌ አካሄደዋል ። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ በወቅቱ እንደገለፁት የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው፡፡ ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል። በዘርፉ በቅንጅት በተሰራው ስራ በቡና ምርታማነት ላይ የተገኘው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል፡፡ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ጁሃር የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት ስኬት እየተመዘገበ ነው ብለዋል። በዘንድሮ አመት በክልሉ 48 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በሽታ የሚቋቋሙ፣ በአጭር ጊዜ የሚደርሱና ምርታማ የሆኑ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በብልፅግና ፓርቲ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። ወጣቶች ቡና በስፋት እና በጥራት በማምረት እንዲሁም በፍራፍሬ ልማት ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን ያነሱት ደግሞ የእምድብር ከተማ ከንቲባ አቶ ግንባሩ በርጋ ናቸው ። የከተማው ወጣት ዳዊት ትእዛዙ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞች እያለማ መሆኑን ተናግሮ ዘንድሮም ይህን በማስፋት ከ2 ሺህ በላይ ችግኝ መትከሉን ተናግሯል፡፡ ሌላው በእምድብር ከተማ በቡና ልማት የተሰማሩት አቶ ሳሙኤል ፍራንሷ በበኩላቸው ባላቸው 3 ሄክታር ማሳ ላይ ቡና እያለሙ መሆኑን ጠቁመው ዘንድሮ ከ1 ሺህ በላይ የተሻሻለ የቡና ችግኝ መትከላቸውን ገልጸዋል፡፡
በብሄረሰብ አስተዳደሩ 34 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል
Jul 25, 2026 176
ሰቆጣ፤ ሃምሌ 18/2018(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 34 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለፁት አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በስፋት በመገንባት ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከ539 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ 34 የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል። የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶችም 820 ሄክታር መሬት በማልማት ከአራት ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። ፕሮጀክቶቹ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በበጋ ወቅት ጭምር በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል። ስራ የጀመሩት ፕሮጀክቶች አርሶ አደሩ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ አትክልትና ፍራፍሬ ጨምሮ እንዲያመርትና የስርዓተ ምግብ ችግር እንዲያቃልል የሚያደርግ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። የሰቆጣ ከተማ የ03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጉሱ አመረ እንዳሉት፤ በአካባቢያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ የማምረት አቅም እንድናገኝ የሚያደርግ ነው ። የጓሮ አትክልትና ፍሬፍሬ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ምርቶችን በማሳደግ አኗኗራቸውን ለመቀየር የሚያስችላቸው መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል። በአስተዳደሩ በጋዝጊብላ ወረዳ 03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አገኘሁ ጌታሁን፤በቀበሌያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በክረምት ዝናብ ብቻ የተመሰረተውን የግብርና ስራ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚነታችን እንድናሳድግ የሚያደርግ ነው ብለዋል። በብሄረሰብ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት በተገነቡ የመስኖ ተቋማት አራት ሺህ 885 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል
Jul 25, 2026 112
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሸገር ከተማ የግብርና ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ግርማ ኃይሉ ገለጹ። የሸገር ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛው ሩብ ዓመት የክትትልና አስፈጻሚ አካላት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። አቶ ግርማ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ አርሶ አደሩ የሚያካሒደውን የእርሻ ስራ በሜካናይዜሽን በማገዝ እና የግብርና ግብዓቶችን በወቅቱ በማቅረብ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል። በ2017/18 የምርት ዘመን በከተማዋ 81 ሺህ 538 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በመስኖ ስንዴ ልማት ከ42 ሺህ 613 ሄክታር መሬት በማረስ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱንም አክለዋል። በተያዘው የመኸር የምርት ዘመንም 95 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል። በተለይም የግብርና ሜካናይዜሽንን በማሳደግ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ነው የገለጹት። ከዚህ በተጨማሪ የከተማው አርሶ አደር የክረምቱን ዝናብ ብቻ ከመጠበቅ ወጥቶ በሁሉም ወቅቶች ማምረት እንዲችል የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውንም ገልፀዋል። ለዚህም 171 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የመስኖ ውኃ በማቅረብ 42 ሺህ 613 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ነው የተናገሩት።
በሸገር ከተማ በ2018 በጀት ዓመት በተከናወኑት የተለያዩ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል
Jul 25, 2026 124
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር )ገለጹ። የሸገር ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛው ሩብ ዓመት የክትትልና አስፈጻሚ አካላት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር ) ሪፖርቱንት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የከተማዋንና የማሕበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በተለይም የገቢ አቅምን ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን አንስተው፣ በ2018 በጀት ዓመት 40 ነጥብ 17 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል። የተሰበሰበው ገቢ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን፣ ተወዳዳሪና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል። የተገኘው ገቢ ከአምው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑንም ነው የጠቆሙት። በበጀት ዓመቱ 348 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የሕብረተሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት ። በከተማዋ በትምህርት ዘርፍ የተተገበሩ ኢኒሼቲቮችም በትምህርት ቤቶች ቁጥር፣ በትምህርት ዕድልና ተደራሽነት ረገድ ከፍተኛ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ነው የገለጹት። በዚሁ መሠረት 121 የቅድመ መደበኛ እና 15 የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ነው ያመለከቱት። ከዚህ በተጨማሪ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርም በ1 ሺህ 224 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ ሆነዋል፤በዚህም 382 ሺህ 176 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የተማሪዎችን መጠነ መቅረት ከማስቀረቱ ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ማገዙን አንስተዋል። በሸገር ከተማም የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራትም ሶስት የሚደርሱ ሆስፒታሎችን አገልግሎት ማስጀመር መቻሉ አክለዋል። በሕብረተሰብ አቀፍ የጤና መድህን በኩልም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የቤተሰብ አባላትን ማቀፍ የተቻለ ሲሆን 609 ሺህ በላይ ዜጎች የሕክምና አገለግሎት ማግኘታቸውንም ነው የተናገሩት። በተጠናቀቀው በበጀት ዓመት ንጹህ የመጠጥ ውሃን ተደራሽ በማድረግ 59 ነጥብ 9 በመቶ የነበረውን ሽፋን ወደ 71 በመቶ ለማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት። በዚህም 322 ሺህ በላይ የሚደርስ ሕዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። በሸገር ከተማ በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ደረጃ እና በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች 8 ሺህ በላይ መዝገቦች እልባት አግኝተዋል ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን የሚያፋጥን የሰው ኃይል እየተገነባ ነው
Jul 25, 2026 242
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን የሚያፋጥን የሰው ኃይል እየተገነባ መሆኑን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሰለጠኑ ስታርት አፖችን አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዲጂታል ሽግግር ጠንካራ የሰው ኃይል አቅም እንዲሁም አስተማማኝ መሠረተ ልማቶችን ይጠይቃል። ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል። በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲና ስትራቴጂ መቀረጹን፣ ችግር ፈቺ ውጤቶች መመረታቸውን፣ ለአለም ገበያ ብቁ የሆኑ ዲጂታል ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉን፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ዝርጋታና ሌሎች ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል። በሁሉም ዘርፎች በተለይም ቅድሚያ በሚሰጣቸው የፍትህና አስተዳደር፣ ስማርት ኮርት (ዘመናዊ ፍርድ ቤት)ና ስማርት ፖሊስ ጣቢያ፣ ጤና፣ የሕዝብ አገልግሎትና በሌሎች ዘርፎች በAI የታገዙ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ሥራ ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል። በዘርፉ ለተገኘው ስኬት በስታርታፕ፣ ሰመር ካምፕ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎች ተቋማት የሰው ኃይል ልማት ጠንካራ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በመከናወኑ ነው ብለዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑት ተመራቂዎች የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ የሆኑ፣ የተፈተሹ፣ ሥራ ላይ የዋሉና በገበያው ሊስፋፉ የሚችሉ ውጤቶች ማቅረባቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ውጤቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወደ ተግባር መሸጋገሩን እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። በዕለቱ በተዘጋጀው አውደ-ርዕይ ሰልጣኞቹ በጤና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት፣ በቋንቋ ቴክኖሎጂ፣ በስማርት ሲቲ፣ በፋይናንስ እና በሰብዓዊ ልማት ዘርፎች የሠሯቸውን ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የነገውን ዓለም ታሳቢ በማድረግ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅ የሰው ኃይል እያፈራች ነው
Jul 25, 2026 173
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የነገውን ዓለም ታሳቢ በማድረግ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅ የሰው ኃይል እያፈራች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባለፉት ስድስት ወራት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ያሰለጠናቸውን ስታርታፖች በይፋ አስመርቋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የነገውን ዓለም ጉዞ እየቃኘና እየወሰነ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን ዕድል ለብሔራዊ ጥቅም ለማዋልና የነገውን ዓለም ጉዞ በብቃት ለመቃኘት ተተኪውን ትውልድ በዘርፉ የማብቃትና የማንቃት ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሰልጥነው ለምረቃ የበቁት ስታርታፕ ሰልጣኞችም ትልቅ ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል። መመረቅ የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን ለረጅም ጉዞ የመጀመሪያ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስልጠና ቆይታቸው ዕውቀትና በራስ መተማመን አቅም መገንባታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በታማኝነት በማሳደግ ለሀገር የሚጠቅሙ መፍትሔዎችን እንዲያቀርቡና ኢትዮጵያን በዘርፉ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ አምባሳደሮች እንዲሆኑ አስገንዝበዋል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም የኢንስቲትዩቱን አርዓያነት ያለው ጉዞ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በስታርታፕ ልማት ለራሷ አልፎ ለመላው አፍሪካውያን ወጣቶች የምትተርፍ እንድትሆን ቀጣይነት ያለው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በመጨረሻም ለተመራቂ ስታርታፖች መልካምና ስኬታማ የሥራ ዘመን ተመኝተዋል። በዕለቱ በተዘጋጀው አውደ-ርዕይ ሰልጣኞቹ በጤና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት፣ በቋንቋ ቴክኖሎጂ፣ በስማርት ሲቲ፣ በፋይናንስ እና በሰብዓዊ ልማት ዘርፎች የሠሯቸውን ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ አቅርበዋል።
የሀገራችንን መዳረሻ በራሳችን ዕውቀትና ጥበብ እንቀርጻለን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jul 25, 2026 124
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋንና መዳረሻዋን ሌሎችን ጣልቃ ሳታስገባ በራሷ ዕውቀት እና ጥበብ ትቀርጻለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አማካኝነት በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዎቹን የኤአይ ስታርትአፕ ሠልጣኞች በሳይንስ ሙዚየም ዛሬ በድምቀት ማስመረቃቸውን ጠቁመዋል። እኛ የወደፊቱን ዕጣ ፈንታችንን እና መዳረሻችንን ሌሎች እንዲወስኑ አንጠብቅም አንፈቅድም፤ ይልቁንም በሀገራችን ጥበብ፣ በራሳችን ዕውቀት እንቀርጸዋለን ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዘርፉ የሰጡት ልዩ ትኩረትና የቅርብ ክትትል ፍሬ፣ እንዲሁም ሀገራችን በልጆቿ ጥረት ያስመዘገበችው ትልቅ የስኬት ምዕራፍ ማሳያ ነው ብለዋል። ወጣት ፈጣሪዎች በጤና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት፣ በስማርት ሲቲ፣ በፋይናንስና በሌሎችም ዘርፎች የተሠማሩ መሆናቸውን አብራርተዋል። በቴክኒክና የምርት ልማት ክሂሎት፣ ትክክለኛ ችግር ፈቺ የቢዝነስ አስተሳሰብ፣ ደረጃውን የጠበቀ የኤአይ ወርክሾፕ፣ የክላውድ ዳታ ማዕከል እና ከፍተኛ የኮምፒዩቲሽናል ሪሶርስ ድጋፍ ማግኘታቸውንም ነው የገለጹት። አንድ ስታርትአፕ ሲደገፍ የላቀ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ለብዙዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፤ መንግሥታችን ለዚህ ትኩረት ሰጥቷል። የዛሬ ተመራቂዎችም ተጨባጭ ማሳያ ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በኦሮሚያ ክልል አገልግሎቶችን ከብልሹ አሰራር የፀዱ ማድረግ የሚያስችል ሪፎርም እየተተገበረ ነው
Jul 25, 2026 111
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ለሕብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዱ ማድረግ የሚያስችል ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ተናገሩ። ''የአገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና'' በሚል መሪ ሀሳብ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር)፣ የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ኮከቤ ዲዳ፣ የመንግስት ከፍተኛ የቢሮ ኃላፊዎችና አመራሮች ተገኝተዋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው በማድረግ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ሪፎርም እየተተገበረ ይገኛል። ከዚህ ውስጥም በክልሉ ከቀበሌ ጀምሮ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ ማድረግ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም የተለያዩ አልግሎቶችን በዲጂታል ስርዓት በመደገፍ የህዝቡን እንግልት፣ ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። በየደረጃው የሚገኘው የክልሉ አመራርና ሰራተኛም ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ ሰፊ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም አመልክተዋል። በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር የማድረግ ስራ ልዩ ትኩረት እንደሰጠውም ነው የገለጹት። በአሁኑ ወቅትም የመንግስት ሰራተኞች አቅምን የማሳደግ፣ አዎንታዊ የስራ ባህልን መገንባት እና የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ የሚያስችል ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። በለውጡ ዓመታት በክልሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተው በአዲሱ በጀት ዓመትም የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በተሟላ መልኩ የሚተገበር ይሆናል ብለዋል። የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ዲዳ በበኩላቸው፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን አሰራር የማዘመንና የሰው ኃይሉን አቅም መገንባት የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም የአገልግሎት አሰጣጥን በዲጂታል መንገድ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 58 የመሶብ አንድ ማዕከል መስጫ ተቋማት አገልግሎት መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
ስፖርት
የርገን ክሎፕ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
Jul 24, 2026 170
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የርገን ክሎፕን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል። የ59 ዓመቱ ጀርመናዊ የአራት ዓመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱ አሰልጣኙን እስከ 2030 የዓለም ዋንጫ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸው ነው። ክሎፕ በቦታው የተኩት በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጀርመን በ32ቱ ዙር በፓራጓይ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ከሆነች በኋላ ከኃላፊነታቸው የለቀቁትን ጁሊያን ናጌልስማንን በመተካት ነው። ከሊቨርፑል የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የሬድ ቡል ሳልስበርግ የዓለም እግር ኳስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ክሎፕ፣ የጀርመን እግር ኳስን እንደገና ወደ ቀደመ ገናናነቱ የመመለስ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ክሎፕ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም. በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ (Uefa Nations League) ከኔዘርላንድስ ጋር ያደርጋሉ።
የዓለም አትሌቲክስ የአትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን አፀደቀ
Jul 23, 2026 196
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ የኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ (women’s only) የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዛሬ ማፅደቁን ይፋ አድርጓል። አትሌት ትዕግስት እ.አ.አ አፕሪል 26 / 2026 በለንደን ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በመግባት እ.አ.አ በ2025 በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በዘጠኝ ሴኮንድ በማሻሻል አሸንፋለች። የዓለም አትሌቲክስ የአትሌቷን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረ ወሰን ዛሬ ማፅደቁን አስታውቋል። የሴቶች ብቻ (women’s only) የዓለም ክብረ ወሰን ሴቶች ብቻ በሮጡበት ውድድር ብቻ የተመዘገበ የዓለም ፈጣን ሰዓት ማለት ነው። የዚህ የዓለም ክብረ ወሰን አመዘጋገብ በሴቶች ውድድር ላይ የወንድ አሯሯጮች ወይም ወንዶች ተቀላቅለው ሲሮጡ (አጠቃላይ ሩጫ) ከሚመዘገበው የዓለም ክብረ ወሰን ጋር የሚለያይ ነው። ወንዶች በሴቶች ውድድር ላይ መኖራቸው የውድድሩን አዝማሚያ እና ሴቶች የሚያስመዘግቡት ሰዓት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። ሴት እና ወንድ ተደባልቀው በሚሮጡበት አጠቃላይ የሴቶች ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን (Overall women's world record) የያዘችው ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕጌቲች ናት። ሩት እ.አ.አ በ2024 በቺካጎ ማራቶን 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ጨብጣለች። የዓለም አትሌቲክስ ከአትሌት ትዕግስት በተጨማሪ ሰባት የዓለም ክብረ ወሰኖችን ማጽደቁን አስታውቋል። እውቅናና ፈቃድ በተሰጣቸው ውድድሮች ላይ ማሸነፍ፣ የውድድር ሜዳዎቹ የሚፈለገውን መስፈርት ያሟሉ መሆንና አትሌቶች በአበረታች ቅመም ምርምራ ውጤት ጤነኛ መሆናቸው መረጋገጥ አትሌቶች የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት የሚሆኑባቸው ዋነኛ ቅደመ-ሁኔታዎች ናቸው።
የስፔኑ ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
Jul 20, 2026 605
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተጠናቋል። በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የኮከብ ተጫዋቾች ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በዚሁ መሰረት የስፔኑ አምበል ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች በመባል ተመርጧል። የስፔኑ ተከላካይ ፓዎ ኩባርሲ የወጣት ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አግኝቷል። ኡናይ ሲሞን (ስፔን ) የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኗል። ፈረንሳዊው ኪሊያን እምባፔ 10 ግቦች በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሽልማት ወስዷል።
ስፔን አርጀንቲናን በመርታት የዓለም ዋንጫን አነሳች
Jul 20, 2026 461
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ መርሐ ግብር ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የአርጀንቲና የአማካይ ተጫዋች ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ93ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በ90 ደቂቃ አሸናፊ ባለመገኘቱ ቡድኖቹ ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርቷል። ተቀይሮ የገባው ፌራን ቶሬስ በ106ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ስፔን ፍጹም የበላይነት ወስዳለች። የአርጀንቲናው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በርካታ ያለቀላቸው ኳሶችን አድኗል። ተጋጣሚዋ አርጀንቲና በጨዋታው ደካማ እንቅስቃሴ አድርጋለች። ቡድኑ የግብ እድል መፍጠር ተስኖታል። ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ለሁለተኛው የዓለም ዋንጫን አንስታለች። አውሮፓዊቷ ሀገር እ.አ.አ በ2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 19ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ እንደነበረች ይታወሳል። አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ክብሯን ማስጠበቅ አልቻለችም። ለአራተኛ ጊዜ ዋንጫ የማንሳት ህልሟ አልተሳካም።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስኬታማነት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
Jul 25, 2026 109
ጋምቤላ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ እየተካሄደ ላለው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስኬታማነት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የ2018 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ማስጀመሪያ ስነ ስርአት በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ ተካሂዷል። ርዕሰ መስተዳድሯ በወቅቱ እንዳሉት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎችን በማጠናከር ለግብርና ልማቱ ስኬታማነት ልንተጋ ይገባል። በክልሉ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ ባለፉት አመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች በርካታ ስኬቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል። ባለፉት የለውጥ አመታት በተከናወኑት የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በርካታ የተራቆቱ አካባቢዎች ከማገገማቸው ባለፈ የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉን ገልፀዋል። በቀጣይም የተጀመረውን ልማት በማሳለጥ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለተያዘው ግብ መሳካት ያላሰለሰ ጥረት ልናደርግ ይገባል ብለዋል። በዘንድሮው ዓመት እየተከናወነ ላለው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የክልሉ ህዝብ ተሳትፎና ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሯ አሳስበዋል። የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኡጁሉ ኡሞድ በበኩላቸው እንደገለጹት የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት በመቀነስና የአፈር ለምነትን በመጨመር የአርሶና አርብቶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ ረገድ የማይተካ ሚና አበርክቷል። በክልሉ ባለፉት አመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ከ50 ሺህ ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት በደን መሸፈኑን ጠቅሰዋል። በአረንጓዴ ሻራ ልማት የለሙ የፍራፍሬና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በህብረተሰቡ ህይወት ላይ አወንታዊ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን ገልፀዋል። ዘንድሮም ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ትሩፋትና የሕብረብሔራዊ አንድነት የልማት ምልክት ነው
Jul 25, 2026 245
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ትሩፋትና የሕብረብሔራዊ አንድነት የልማት ምልክት መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) አመራር አባላት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሃሳብ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትርና የኢዜአ ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ አረንጓዴ ዐሻራ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስምና ዝና ከፍ እያደረገ የሚገኝ ሀገራዊ ተነሳሽነት ነው። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በኢትዮጵያ በርካታ ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ሀገር ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገው ሽግግር እየሰመረ መሆኑን በተግባር እንደሚያሳይ ገልጸዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ከሀገር ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ባሻገር በቀጣናዊ ትብብር ውስጥም አዲስ የዲፕሎማሲ መልዕክት እያስተላለፈ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኝ በማቅረብና የአካባቢ ጥበቃ ተሞክሮዎችን በማካፈል ቀጣናዊ ትስስርን እያጠናከረች ነው፤ ይህም በርካታ የዲፕሎማሲ ትሩፋቶችን እያስገኘ ነው ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የወሰድነው ተግባራዊ እርምጃ ዓለም እንደ ተሞክሮ እየተመለከተው መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዕውቅናና አድናቆት እንድታገኝ እንዳስቻላት አብራርተዋል። በሀገር ውስጥም አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎችን የጋራ ተሳትፎ በማሳደግ ኃይማኖት፣ ዕድሜና ጾታ ሳይገድባቸው ኢትዮጵያውያንን በአንድ ዓላማ ያሰባሰበ ሀገራዊ የልማት አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ በሀገር ጉዳይ በጋራ መሥራት ያለውን ጠቀሜታ ያሳየና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ያጠናከረ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከኢኮኖሚ አኳያም አረንጓዴ ዐሻራ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የገጠርና የከተማ ኢኮኖሚን ለማጠናከር እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ የተሻለ ኑሮ ለመፍጠር አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ ኢዜአ እንደ ተቋም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። በቢሾፍቱ ከተማ የተካሄደው የችግኝ ተከላም በዚህ ክረምት ኢዜአ ያካሄደው ሁለተኛው የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባር ሲሆን፤ በቀጣይም በክልሎች የተለያዩ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮችን እንደሚያካሂድ ገልጸዋል። ኢዜአ ዜጎች በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማስገንዘብና የማንቃት ሥራውን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማስገኘት ለገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Jul 25, 2026 105
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን በማስገኘት ለገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ''ፅዱ ኢትዮጵያ፤ ለትውልድ'' በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ሦስተኛው ዙር ሀገራዊ የከተማ አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ በይፋ ተጀምሯል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማስገኘት ለገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋትኦ እያበረከቱ ነው። በዚህም የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የስነ-ምኅዳር ደኅንነትን በመጠበቅ ዜጎች ጤናማና ፅዱ ከባቢ የሚኖሩበትን አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በሦስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄም በመጀመሪያው ወር የፕላስቲክ፣ በሁለተኛው ወር የአደገኛና ኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ፣ በሦስተኛው ወር የድምፅ ብክለትን የመከላከል ሥራዎች እንደሚከናወኑ አብራርተዋል። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው፤ በከተማዋ የሚከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የመሠረተ ልማት ሥራዎች የሥነ-ምኅዳር ከባቢን ከዜጎች ጤና ጥበቃ ጋር ተስናስለው የተገነቡ ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 44 በማሳደግ የመዲናዋን የፍሳሽ ማጣሪያ ሽፋን ወደ 43 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ በተሰራው ስራም 600 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ 76 ወንዞችን ከብክለት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ፅዳትና ንጽህና የከተማ ስልጣኔ መገለጫ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) ሲሆኑ መላው ሕብረተሰብም በንቅናቄው ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በማስተካከል ዕድገትን በማፋጠን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው
Jul 23, 2026 230
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የሥነ-ምኅዳር ደኅንነት በማስተካከል ዕድገትን የሚያፋጥን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን "ተስፋን እንትከል" መሪ ሃሳብ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። በዚሁ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይም፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልጽግና የሚያረጋግጥ ብሔራዊ የልማት ትልም መሆኑን ገልጸዋል። በዘንድሮው መርሃ ግብር ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ሁሉም የማኅብረሰብ ክፍል በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል። በዚሁ መሠረትም የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በየአካባቢያቸው ችግኝ በመትከል ዐሻራቸውን እያኖሩ ይገኛል። የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አመራርና ሠራተኞችም በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጎሮ የወንዝ ዳርቻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል። በዚሁ ወቅት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የሥነ-ምኅዳር ደኅንነት በማጠናከር ዘላቂ ልማትን የሚያፋጥን ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መርሃ ግብሩ በ2011 ዓ.ም ከተጀመረ ወዲህ ባሉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት በርካታ ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል። መርሃ ግብሩ የሥነ-ምኅዳር ሚዛንን ከማስጠበቅ ባለፈ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። እንዲሁም ዛፍ መትከል ለሰው ልጆች የአዕምሮ እርካታና የልብ ደስታን በመፍጠር ተስፋን የማለምለም አቅም እንዳለው ጠቁመዋል። በተጨማሪም የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ መንከባከብና በቀጣይነት መከታተል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ በበኩላቸው፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከሰው ልጆች ሕይወት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው የልማት ተግባር ነው ብለዋል። በዚህ ብሔራዊ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ አሻራ ማኖር፣ በሀገር ልማትና በትውልድ ተስፋ ላይ አሻራ የማኖር ዕድል መሆኑንም ገልጸዋል። ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መሳተፋቸውን የገለፁት ደግሞ ሌላኛዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የመንግሥታት ግንኙነት፣ የብዝኅነትና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር መንደሪን ማርቆስ ናቸው። መርሃ ግብሩ ለቀጣዩ ትውልድ ልምላሜን የተላበሰች ኢትዮጵያ ለማስረከብ ያለመ በመሆኑ፣ እስካሁን የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል። የምክር ቤቱ የትራንስፖርት ባለሙያ አቶ ኬኔዲ መላኩ በበኩላቸው፣ ከልጅነት ጀምሮ ችግኝ የመትከል ልምድ እንዳላቸው ገልጸዋል። ይህም ለተፈጥሮ ጥበቃና ለችግኝ እንክብካቤ ያላቸውን ግንዛቤ የበለጠ እንዲጎለብት አስችሎኛል ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 20380
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 13225
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 12016
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 11917
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ምግቤን ከደጄ፤ የከተማ ግብርና አዲሱ የምግብ ዋስትና መሰረት
Jul 25, 2026 106
በመቅደስ ወልዴ መግቢያ፡- ዛሬ ዓለም በፈጣን የከተሜነት ሽግግር ውስጥ ትገኛለች። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ፣ ከተሞችን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የኑሮ ማዕከላት እያደረጓቸው ነው። ይህ ሽግግር አዳዲስ የልማት ዕድሎችን ቢፈጥርም፣ ከምግብ አቅርቦት እስከ የኑሮ ውድነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ እስከ የሥራ ፈጠራ ድረስ ያሉ አዳዲስ ፈተናዎችንም አስከትሏል። በተለይም በታዳጊ ሀገራት የከተሞች መስፋፋት የምግብ ዋስትናን ከልማት ፖሊሲዎች ማዕከል ላይ አስቀምጦታል። በ2050 ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሦስተኛው በከተሞች እንደሚኖር የሚጠበቀው እውነታ፣ ከተሞች ምግባቸውን ለማረጋገጥ አዳዲስና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል። ኢትዮጵያም ከዚህ ዓለም አቀፋዊ ሽግግር ውጭ አይደለችም። የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የገበያ መረጋጋትና የኑሮ ውድነት አዳዲስ የፖሊሲ ጉዳዮች ሆነው ተነስተዋል። በዚህ ዐውድ ውስጥ የከተማ ግብርና ባዶ ቦታን ወደ ምርት፣ ቆሻሻን ወደ ማዳበሪያ፣ ሸማቹን ወደ አምራች የሚቀይር ዘመናዊና ዘላቂ የልማት መንገድ ሆኖ እየጎለበተ ነው። የከተማ ግብርና፤ ምንነቱና ጠቀሜታው የከተማ ግብርና በከተማ ውስጥ በሚገኙ አነስተኛ ቦታዎች፣ በመኖሪያ ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በበረንዳ ስፍራዎች ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ቀላል የምርት ዘዴዎችን በመጠቀም አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንስሳት፣ ዓሳና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን የማምረት ሥርዓት ነው። ቀደም ሲል ግብርና የገጠር ብቻ ተደርጎ ይታሰብ የነበረው አመለካከት ዛሬ በእጅጉ ተለውጧል። በከተሞች የሚገኙ ጠባብ ስፍራዎች እንኳን ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የልማት መስኮች ሆነዋል። በቤት ዙሪያ ይደረግ የነበረው ቀላል የጓሮ አትክልት ልማትም ዛሬ ለሺዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ ገበያን የሚያረጋጋና የሀገር ኢኮኖሚን የሚደግፍ ዘርፍ ሆኗል። ከተሞችን ውብና አረንጓዴ ከማድረጉ ባሻገር፣ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ፣ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙና ለአካባቢ ጥበቃ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። እንዲሁም የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብና ሌሎች አነስተኛ የግብርና ሥራዎች የቤተሰብን ምግብ ከማሟላት ባለፈ ገበያውን በማረጋጋት ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የከተማ ግብርና ለምን አስፈለገ? የግብርና ልማት ዛሬ በገጠር አርሶ አደሮች ጥረት ብቻ የሚገደብ አይደለም። የከተሞችን እምቅ ሀብት በመጠቀምና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማቀናጀት የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የሚቻልበት ውጤታማ መንገድ መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ተሞክሮዎችም የከተማ ግብርና የከተሞችን ገበያ በማረጋጋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የከተማ ቆሻሻን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየርና የከተሞችን አረንጓዴነት በማጎልበት ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ በተግባር አሳይተዋል። የከተማ ግብርና፤ ከጓሮ ልማት ወደ ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ቀደም ሲል በቤት ጓሮ የሚከናወን ቀላል የአትክልት ልማት ተደርጎ ይታይ የነበረው የከተማ ግብርና፣ ዛሬ የምግብ ዋስትናን፣ የገበያ መረጋጋትን፣ የሥራ ፈጠራንና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን የሚያጠናክር ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ሆኖ ተቀይሯል። በአነስተኛ ቦታዎች፣ በቤት ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በባዶ መሬቶች ላይ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ሀብት፣ የንብ እርባታና ሌሎች የግብርና ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ። "ምግቤን ከደጄ" የሚለው ሀገራዊ ንቅናቄም የከተማ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እስከ የገበያ መረጋጋት የከተማ ግብርና ከሚያስገኛቸው ትልልቅ ጥቅሞች መካከል ዋነኛው የምግብ ምርትን ለተጠቃሚው በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪና በተሻለ ጥራት ማድረስ መቻሉ ነው። በከተማ ውስጥ የሚመረቱ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ እንቁላልና ወተት ረጅም ርቀት ሳይጓዙ በቀጥታ ለገበያ ስለሚቀርቡ ትኩስነታቸውን ይጠብቃሉ፤ የመጓጓዣ ወጪንም በእጅጉ ይቀንሳሉ። በሌላ በኩል ቤተሰቦች በጓሯቸው የሚያመርቱት ምርት የዕለት ተዕለት የምግብ ወጪያቸውን በመቀነስ የምግብ ዋስትናቸውን ያጠናክራል። ከቤተሰብ ፍጆታ በላይ የሚተርፈው ምርት ደግሞ ወደ ገበያ በመግባት የምግብ አቅርቦትን ያሳድጋል፤ በዚህም የዋጋ ንረትን በመቀነስ የገበያ መረጋጋትን ለማስፈን የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። የአረንጓዴ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ የከተማ ግብርና የምግብ ምርትን ከማሳደግ ባለፈ፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የከተማ ኢኮኖሚን የሚያነቃቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሠረትን የሚያጠናክር ዘርፍ ሆኗል። በአዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ሀብትና በንብ ማነብ የተሰማሩ በርካታ ወጣቶችና ሴቶች ቋሚ የገቢ ምንጭ እያገኙ ይገኛሉ። ይህም የከተማ ግብርና የቤተሰብ የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር የሥራ አጥነትን ለመቀነስና የከተማ ኢኮኖሚን ለማጠናከር እያበረከተ ያለውን ጉልህ አስተዋፅኦ ያሳያል። አካባቢን ከመጠበቅ እስከ የከተሞችን ውበት የከተማ ግብርና የሥነ-ምህዳር ጠቀሜታውም ከፍተኛ ነው። ከቤት የሚወጡ ኦርጋኒክ ቆሻሻዎችን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየር የአፈር ለምነትን ያሻሽላል፤ በተመሳሳይ ጊዜም የከተማ ጽዳትን ያጠናክራል። ከዚህ በተጨማሪ የአረንጓዴ ስፍራዎች መስፋፋት የከተሞችን የሙቀት መጠን በመቀነስ፣ የአየር ጥራትን በማሻሻልና ለነዋሪዎች ጤናማና ምቹ የኑሮ አካባቢ በመፍጠር ለከተማ ዘላቂነት የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ማጠቃለያ የከተማ ግብርና የኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት የልማት አቅጣጫ መሆኑን በተግባር አረጋግጧል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጀምሮ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የሥራ ፈጠራን ማስፋፋት፣ የከተሞችን ውበት ማጎልበትና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ድረስ ያለው ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ ነው። ስለሆነም ለከተማ ግብርና የሚስማሙ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍን ማጠናከር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻልና በከተማ ፕላን ውስጥ ለግብርና ተስማሚ ቦታዎችን በቋሚነት መመደብ ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው። ከተሞች የምግብ ፍጆታቸውን በራሳቸው የማምረት አቅም እያዳበሩ ሲሄዱ፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ዋስትና፣ ጠንካራ አረንጓዴ ኢኮኖሚና ተወዳዳሪ የከተማ ልማት ስኬታማ ትልም ይበልጥ ይፋጠናል። ከደጃችን የሚጀምረው ምርት፤ ለሀገር ዕድገት የሚሆን ትልቅ አቅም ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ፤ ከሥነ-ምኅዳር ዘብ እስከ ዓለም የልማት ተምሳሌት
Jul 23, 2026 409
በመጽሔት አንለይ በወሳኝ ሀገራዊ የልማት ውይይቶች ላይ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸው፣ በዚህም በርካታ ሚሊየን ሄክታር መሬት መታደሱ እንዲሁም የተመዘገበ የደን ሽፋን በአበይት ጉዳይነት ይነሳሉ። ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአርሶ አደሩ ምርታማነት ማደግ፣ የወጣቱ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን፣ የእናቶች የኑሮ መሻሻልና የተፈጥሮ ሃብት መጠበቅ መቻሉ እንዲሁም የአየር ንብረት መዛባትን ማስተካከልና የደን ሽፋንን ማሳደጉ ለመርሃ ግብሩ ውጤታማነት በአብነትነት ይጠቀሳሉ። በዚህ አተያይ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከተራ የችግኝ ተከላ ዘመቻ ባሻገር በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ልማት ዘርፎች መዋቅራዊ ለውጥ በማምጣት አንጸባራቂ ውጤት እያሰገኘ ነው። የዓለም አየር ንብረት ጉዳይ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ አፍሪካ የችግሩ ተጠቂ ብቻ ሳትሆን ለመፍትሄውም የራሷን ልምድና አቅም ማበርከት እንደምትችል እያሳየች ይገኛል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ንቅናቄም ለአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት አዲስ የተግባር ልምድ እየሆነ መጥቷል። የአረንጓዴ ዐሻራው ልዩነት በተተከሉ ችግኞች ቁጥር ብቻ አይለካም። በተራቆቱ መሬቶች ላይ የተመለሰው ሕይወት፣ በገጠር የተፈጠሩ የኢኮኖሚ ዕድሎች፣ የተጠበቁ የውሃ ሀብቶችና ለወደፊት ትውልድ የተገነባው የአካባቢ መሠረት ዋናው ውጤቱ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፤ ከርዕይ ወደ ተግባር!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በሀገራዊ ለውጥ ማግስት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሕዝባዊ ተሳትፎ የተጀመረ ሲሆን፤ እስካሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። ከዚህ በፊት የነበረው የተፈጥሮ ሃብት መራቆት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ብቻ ሳይሆን በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይም ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ ነበር። የአፈር መሸርሸር፣ የደን መጥፋትና የድርቅ ተጋላጭነቶችም የገጠር ሥነ-ምኅዳራዊ ሕይወትን ሲፈታተኑ ቆይተዋል። ይህን ምላሽ ለመስጠትም የአረንጓዴ ዐሻራ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማትና የደን ሽፋንን ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የአረንጓዴ አሻራ የኢኮኖሚ ዐሻራ፡- የአረንጓዴ ዐሻራ ትርጉም በአካባቢ ጥበቃ ብቻ አይወሰንም። በኢኮኖሚውም ውስጥ አዲስ የልማት መንገድ እየፈጠረ ይገኛል። በጥምር ግብርና (Agroforestry) አማካኝነት ቡና፣ ፍራፍሬና ሌሎች የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ከደን ልማት ጋር እንዲሰናሰሉ አድርጓል። ይህም የገቢ ምንጭን ከማስፋት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ አስተዋፅዖ አድርጓል። በተለይ የቡና ዘርፍ ከሚሊዮን ወደ ቢሊዮን ዶላር ደረጃ መሻገሩ የዚህ ጥምረት ውጤት አንዱ ማሳያ ነው። የአቮካዶ ምርት ለወጪ ንግድ የፈጠረው ዕድልም አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ውጤታማነት አብነት ሆኗል። በሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች ላይ የመጣው ዕድገት ኢትዮጵያን በዓለም ገበያ የተሻለ ተወዳዳሪ የምትሆንበትን ዕድል ፈጥሯል። ከአፈር ጥበቃ እስከ ምግብ ዋስትና፡- የአረንጓዴ ዐሻራ በአፈር ጤናማነት ላይ ያመጣው ለውጥ የግብርና ምርታማነትን ከፍ አድርጓል። የአፈር ኦርጋኒክ ካርቦን መጨመር፣ የውሃ ማቆየት አቅም መሻሻልና የተፋሰስ ልማት በኢትዮጵያ የመስኖ ልማትና የምግብ ምርት ዕድገት መሠረት ጥለዋል። የስንዴ ምርታማነት ዕድገት እና የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስኬታማ ጉዞም የአረንጓዴ ዐሻራ ተጠቃሽ ውጤቶች ናቸው። የተፈጥሮ ጋሻነት፡- ኢትዮጵያ ለድርቅ፣ ለጎርፍና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ዛፎችና ስሮቻቸው አፈርን በመያዝ መሸርሸርን ይቀንሳሉ፤ የውሃ ሃብቶችን ጠብቆ በማቆየትና በማሻሻል የድርቅ ተጋላጭነትን የመቋቋም አቅም እየገነባ ነው። በተለይም በርካታ የኃይል ማመንጫ ግድቦችንና የውሃ ሃብቶችን ከደለል አደጋ ለመጠበቅ የደን ልማት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቀልበስ የተፈጥሮ ጋሻነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። የትውልድ ሐውልትና የልማት ውርስ የሆነው አረንጓዴ ዐሻራ!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በአንድ ወቅት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻም፣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፈውበታል። ይህም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ታሪክ በመፃፍ በልማት መስክ አስደናቂ የትብብር መንፈስ እንዲገነቡ አስችሏል። የመርሃ ግብሩ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ የደን ውድመትን በመከላከል የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ፣ የድርቅና የበረሃማነት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተፅዕኖ መቋቋም አዲስ የዲፕሎማሲ ሚና!! በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የአፍሪካ ዋና ጥያቄ የአየር ንብረት ፍትሐዊነት ነው። አህጉሪቱ በአነስተኛ የካርቦን ልቀት ላይ ብትገኝም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከባድ ጫናን እየተጋፈጠች ይገኛል። በዚህ አውድ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራን እንደ ሀገራዊ ፕሮጀክት በመውሰድ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር የሚጋራ ተሞክሮ ፈጥራለች። የአፍሪካ አህጉራዊ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱም ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎና አመራር ያሳየ ክስተት ነው። ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት ማዕከል እንድትሆን ከማገዙም በላይ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረኮችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም በተግባር አሳይቷል። ማጠቃለያ፡- የተተከለ ችግኝ፣ የተገነባ ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ ''ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በዚህ ዓመት ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምቷል። በዚሁ ወቅትም ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ወደ 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በፅናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ዘንድሮም የተያዘውን የስምንት ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት በሚደረገው ብሔራዊ የንቅናቄ ስራ ላይ በሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ የወደፊት የዕድገትና ብልፅግና ማሳኪያ የልማት ትልም እንጂ። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም ከአንድ ችግኝ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የደረሰ የሀገር ተሞክሮ ነው። የተተከሉት ችግኞች ዛሬ የአካባቢ ጥበቃ ዘብ ሲሆኑ፣ ነገ ደግሞ የኢኮኖሚ ዕድል፣ የምግብ ዋስትና፣ የኃይል ዘላቂነትና የትውልድ ተስፋ ይሆናሉ። የተተከለው ችግኝ ነገ የሚሆነው ዛፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ጋሻና ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሕያው ቅርስ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ ዛሬ የሚተከል ተስፋ፣ ነገ የሚሰበሰብ ብልፅግና ነው፤ ተስፋን እንትከል!!!
የሌማት ትሩፋት፡ የኢትዮጵያ ግብርና በአዲስ ምዕራፍ
Jul 22, 2026 352
በሳባ ስለሺ መግቢያ ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ የምግብ ዋስትና ለመቀየር ተግዳሮት ሆኖባት የቆየ ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግስት በተጀመረው ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ጉዞ የዘርፉ ታሪክ በተጨባጭ እየተቀየረ ነው። የዚህ ለውጥ አብይ ማሳያ የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ የሆነው "የሌማት ትሩፋት" መርሃ ግብር አንዱ ነው። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ልማት ጉዞ በአዲስ ምዕራፍ የቃኘ ነው። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ሲሆን፣ በዋናነት በእንስሳት ሀብት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኩራል።በእንስሳት ሀብት ልማት ረገድ የወተት ላሞችን፣ የዶሮ (ሥጋ እና እንቁላል)፣ የንብ ማነብ (ማር) እና የዓሣ እርባታን በስፋት የሚያካትት ነው።የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ከምግብ ሸማችነት ወደ አምራችነት በማሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው። በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የኑሮ ውድነትን በማቃለል፣ የአርሶና አርብቶ አደሩን ገቢ በማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ ያለመ ነው። የሌማት ትሩፋት ለምን አስፈለገ? ፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል በመጠቀም፣ ለዘመናት የዘለቀውን የምግብና ሥነ-ምግብ ዋስትና ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተነደፈ ነው። መንግስት ለዚህ መርሃ ግብር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የሚገኘውም፣ ሀገሪቱ ያላትን ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተጨባጭ እሴትና የሀገር ውስጥ ተጠቃሚነት ለመቀየር እንዲሁም የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ነው። ባለፉት አራት ዓመታት ምን ተከናወነ?፡- ባለፉት አራት ዓመታት በተተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወተት፣ የእንቁላል፣ የሥጋ፣ የዓሣ እና የማር ምርቶችን ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ተከናውኗል። ለዚህ ስኬት በቂና ጥራት ያለው የእንስሳት ተዋጽኦ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሰፊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና የማዳቀል ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ የአዳቃይ ቴክኒሻኖችን አቅም መገንባት፣ የፈሳሽ ናይትሮጂን አቅርቦትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለዘርፉ ተዋናዮች ማስተላለፍ ተችሏል። እንዲሁም የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የእንስሳት እርባታ ደህንነታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ እና አስፈላጊውን መሰረተ ልማት በማሟላት ረገድ ላለፉት አራት ዓመታት ቅድሚያ ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል። በመስኩ ምን ተጨባጭ ውጤት ተገኘ ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገሪቱን የምግብና ስነ-ምግብ ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በዜጎች ዘንድ የቆየውን አመለካከት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግቧል። በተለይም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ተወስኖ የነበረውን የግብርና እንቅስቃሴ ወደ ከተሞች በማስፋት፣ ህጻናት፣ እናቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከእንስሳት ተዋጽኦ ማግኘት የሚገባቸውን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እንዲያገኙ አስችሏል። ይህ ተነሳሽነት የከተማ ግብርናን በማስተዋወቅ ዜጎች በቤታቸው እንስሳትን በማርባት ከራስ ፍጆታ ባለፈ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በመሆኑም፣ ባለፉት ዓመታት በመስኩ የተመዘገቡት ስኬቶች እንደሚያሳዩት፣ መርሃ ግብሩ ዜጎች በተቋማት ተቀጥረው ከመስራት ይልቅ በዘርፉ ተሰማርተው የራሳቸው ስራ ኖሯቸው ለሌሎችም የስራ እድል እንዲፈጥሩ አድርጓል። ይህ የመንግስት ያላሰለሰ ጥረት፣ የዜጎችን የስነ-ምግብ ፍላጎት ከማሟላት አልፎ፣ ጤናማ እና ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ትውልድ በመገንባት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በአሀዛዊ መረጃ የተደገፉ የዘርፉ ስኬቶች ፡- የግብርና ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው አኃዛዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተጀመረ በአራት ዓመታት (2014 ዓ.ም -2018 ዓ.ም) ውስጥ በእንስሳት ምርታማነት አስደናቂ ለውጥ ተመዝግቧል። በወተት ምርት፦ መርሃ ግብሩ ሲጀመር የነበረው 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር አድጓል። በእንቁላል ምርት፦ ከነበረበት 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ፣ ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ከፍ ብሏል። በዶሮ ሥጋ ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 90 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 253 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በማር ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 146 ነጥብ 7 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 428 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በአሳ ምርት፦ የውሃ አካላትንና ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በአግባቡ በመጠቀም የተከናወነው የአሳ ጫጩት ስርጭት፣ ከ300 ሺህ ወደ 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን አድጓል። ይህ ውጤት ሀገሪቱ በእንስሳት ተዋጽኦ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንዴት ማጎልበት እንደተቻለ በግልጽ ያሳያል። ዘርፉ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ምን አበረከተ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገር ውስጥ የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ኢትዮጵያ ከእንስሳት ተዋፅኦ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ብቻ 24 ነጥብ 2 ሺህ ቶን የተቀነባበረ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ 128 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል። ማጠቃለያ፦ በዘርፉ የተመዘገበውን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ አርብቶ አደር እና አርሶ አደሩ ከተለመደው ባህላዊ የእንስሳት አረባብ ዘዴ ለማላቀቅ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ጤና አገልግሎትን የማዘመን፣ እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማምረት አቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው። በተጨማሪም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የማህበረሰቡን ቅንጅት ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አሰራር መዘርጋት፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያለው የገበያ ትስስር መፍጠርና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ እንዲሁም አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ጠንካራ መሰረት ማኖር ይቻላል። በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ ሀገራዊ ብልፅግና ለመቀየር የተጀመረ ውጤታማ መንገድ መሆኑን ባለፉት አራት ዓመታት አሳይቷል። ይህ ከተጠናከረ ሀገሪቱ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥ ያለመችውን ትልም ከማሳካት የሚያስቆማት ነገር እንደማይኖር አመላካች ነው።
ሀገራዊ ምክክር፡ለተሻለች ኢትዮጵያ የተከፈተ በር
Jul 22, 2026 235
በኢትዮጵያ ለዓመታት የቆዩ አለመግባባቶችና ችግሮች ብዙ ናቸው።እነዚህ አለመግባባቶች የሀገር ሰላም፤አንድነት፤ልማት እድገትና የዜጎችን የወደፊት ተስፋ የሚፈታተኑ ሆነው ቆይተዋል። አለመግባባቶችን በኃይል ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ አልቻሉም። ስለዚህ የጥላቻን፣የበቀልንና የመከፋፈልን ዑደት ለማቆም የሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ውይይት፣መደማመጥና መግባባት መሆኑ በስፋት እየታመነ መጥቷል። በዚህ መነሻ፣ኢትዮጵያ በታሪኳ ታላቅ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ እያካሄደች ትገኛለች።ይህ ምክክር ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበትና የጋራ መፍትሄ የሚፈልጉበት መድረክ ሆኗል። የሀገራዊ ምክክሩ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር ሳይሆን፣ የሁሉንም ወገን ድምጽ በማዳመጥ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። ይህ ምክክር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተወከሉ ዜጎች ድምጽ የሚሰማበት፣አመለካከቶች የሚተነተኑበትና የጋራ መፍትሄዎች የሚፈለጉበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኗል። ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ ወገኖችን በአንድነት በማሰባሰብ፣የከረሙ ችግሮችን በተቀናጀ መንገድ በመፍታት፣ የፖለቲካዊ፣የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ለውጦችን ለማምጣት ይረዳል። እንዲሁም ኢትዮጵያን ወደ አንድነት፣ሰላምና ብልጽግና ለማሸጋገር የሚያገለግል ታላቅ መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ብለው ያመኑ ኢትዮጵያዊያንም ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ እና ከውጭ ጭምር በመምጣት በአዲስ አበባ ተገናኝተው ስለሀገራቸው እየመከሩ ይገኛል። በሁሉም ክልሎች፣በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች ሕዝብ የወከላቸው ተመካካሪዎችም በንዑስ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል። በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ሂደት ጠንካራ መግባባትን የሚፈጥር ግልፅና ተስፋ ሰጪ ምክክር እያደረግን ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች በበኩላቸው ገልጸዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ጋር የሚያያዝ ነው። ዛሬ በምክክር የምንገነባው መግባባት፣ነገ ለመጪው ትውልድ የተረጋጋች፣የተባበረች፣ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን የሚያስረክብ መሠረት ይሆናል። ይህ ሀገራዊ ምክክር የጋራ መግባባት ባህልን ለማጠናከር፤ለፀናችና ለተሻለች ኢትዮጵያ የተከፈተ ትልቅ በር ነው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 361
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 542
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4527
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 3662
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 10720
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20899
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 13932
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 19685
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 7054
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ
Jun 26, 2026 4848
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ፍኖቷ ለአፍሪካ አርአያ ሆና አሳይታለች... የአፍሪካውያን ቀንዲል ናት። የክፉ ቀን መሸሸጊያቸው፣ የመከራ ጊዜ መጽናኛቸው፣ የነጻነት ተምሳሌትና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በረጅም ዘመናት ታሪካዊ መስተጋብር የተፈጠረ የሀገረ መንግሥት መዋቅር ባለቤት ናት። በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ ምድሯን ሰንጥቀው በሚያልፉ ወንዞቿ የምትታወቅ አገር ናት። የተለያዩ ማዕድናት በብዛት የሚገኙባት ከመሆኗም በላይ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች ሕብር ሠርተው፣ ተስማምተው የሚኖሩባት የታሪክ ማህደር ናት። ይሁን እንጂ ይህ ታሪካዊ ግርማ ሞገስና የነጻነት አርማነት፣ በውስጣዊ የፖለቲካ ጉዞዋ ውስጥ ካጋጠሟት መዋቅራዊ ስብራቶችና የሥልጣን ፍትጊያዎች ሊታደጋት አልቻለም። ለዘመናት በሀገሪቷ የሰፈነው የሥልጣን ሥርዓት የሰፊውን ሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ፣ በጥቂት የሕብረተሰብ ክፍሎችና ልሂቃን ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር። ይህ አካሄድ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አንዱን ሥርዓት በሌላው እየተካ፣ የተተካው አገዛዝ ደግሞ የባሰ ጭቆናን ይዞ የሚመጣበትን አዙሪት ፈጥሯል። ከብዙ መቶ ዓመታት የዘውድ አገዛዝ በኋላ የመጣው ወታደራዊ ሥርዓት፣ በመቀጠልም ለ30 ዓመታት ገደማ የዘለቀው የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀገሪቱንና ዜጎቿን ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርገው አልፈዋል። ይህ ዓይነቱ የመከራና የጭቆና ሰንሰለት ግን በ2010 ዓ.ም በተቀጣጠለው ሀገራዊ ለውጥ ተገርስሶ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምሕዳር ተሸጋግሯል። ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ስንመረምር፣ ሀገሪቷ ከአሮጌውና ከተለመደው የአፈና ሥርዓት ወጥታ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ አቅም ይዛለች። ይህ ወቅት የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት በተግባር የተረጋገጠበትና የሐሳብ ብዝኃነት የተስተናገደበት ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም የሥልጣን ማራዘሚያ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ዋና ዋና ተቋማት ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲደራጁ መደረጉ የለውጡ ትልቁ ስኬት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የለውጡ የመጀመሪያ ፍሬ የታየው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቆቁሞ ሕዝቡ ያሳየው የባለቤትነት ስሜት የዴሞክራሲ ናፍቆቱን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህንን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ፣ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ የነቃ አስደናቂ የፖለቲካ ተሳትፎ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ታሪካዊ መድረክ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን የማይናወጥ አቋም አሳይተውበታል። ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ረጅም ሰዓታትን ተሰልፈው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችንና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በሙሉ በትዕግሥት በመሻገር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህ ሂደት የሚያሳየው ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭነቱን በተግባር የተረዳበትና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞና የውስጥ መረጋጋት ሁልጊዜም በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ጉዳይ ነው። ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችና የጂኦፖለቲካ ጫናዎች ቢኖሩም፣ ይህ በስኬት የተጠናቀቀው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቷን የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊነት በተግባር ያስመሰከረ ሆኗል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነፃነትና በሰላም ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳይ በራሷ ዜጎች ፍላጎት የመወሰን ሙሉ አቅም እንዳላት ለዓለም አሳይቷል። ምርጫው ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት አስከብሯል። የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በሁከት ሳይሆን በሕዝብ የላቀ ውሳኔ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካለፈችባቸው የፖለቲካ ስብራቶች በላይ ከፍ ብላ እንድትቆም አድርጓታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተደማጭነትና የድርድር አቅም ከፍ የሚያደርግ ነው። የምርጫው ዝርዝር ስኬቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ስንመለከት፦ 👉የአፈሙዝ ድምፅንና የጽንፈኛ ዛቻን ያሸነፈው የሕዝብ ጽናት ግንቦት 24 ታሪካዊ ቀን ናት። በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ በየምርጫ ጣቢያው በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠው ሕዝብ ያሳየው የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጽናት ማረጋገጫ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍና ሕዝቡን ለማስፈራራት የተቃጡ የአፈሙዞች ድምፆችና የሁከት ዛቻዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ሕዝብ ከመምረጥ አላፈገፈገም። መራጮች የጽንፈኛ ኃይሎችን ዛቻ ወደ ጎን ትተው፣ የአካላቸውን ሕመም፣ የበሽታን ሥቃይ፣ አልፎ ተርፎም የወሊድ ምጥንና የቅርብ ዘመድ ሞት ያመጣውን ጥልቅ ሐዘን በሕሊናቸውና በሥጋቸው ተሸክመው ነበር ረጅሙን ሰልፍ ተሰልፈው ይበጀኛል ያሉትን በካርዳቸው የመረጡት። ይህ የሚያሳየው እውነት ለኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ሰላማቸውን የሚገዙበት፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚወስኑበት ብቸኛ የነጻነት አዋጃቸው መሆኑን ነው። ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ፣ በኃይል ወይም በሁከት ሥልጣን ለመያዝ ምኞትና የቆየ የሥልጣን ናፍቆት ላላቸው ወገኖች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግልጽና የማያሻማ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይልና የሁከት አካሄድን እንደማይቀበል፣ በድምፅ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሕጋዊ ሥርዓትን ለማፅናት እንደሚታገል አረጋግጧል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአፅንኦት ሲያነሱ፤ "የዘመናችን ዲሞክራሲ አስተምህሮቱ ሰላምና ዕድገት፣ ቋንቋው ደግሞ መምረጥና መመረጥ ብቻ በመሆኑ የፖለቲካ ቅኝታችሁንና አካሄዳችሁን ከዚሁ ስልጡን መስመር ጋር ማስተካከል ይበጃችኋል። ካሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ መሆኑን እነሆ እንዳየነው መሠረት የጣለ ስለሆነ ይህኑ ስልጡን መንገድ ለመቀበል የማትፈቅዱ ሁሉ ግን ግፋ ቢል የዘመናችን የፖለቲካ ድርሳን ሲጻፍ ልትሆኑ የምትችሉት የግርጌ ማስታወሻ ብቻ ነው።" ብለዋል። ስለሆነም ከዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ አካሄድ ውጭ የሚደረግ ሙከራ የጥፋት ተዋናይ ከመሆን ባሻገር ለሀገር የሚያተርፈው አንዳች ነገር እንደሌለ በዚህ ስሑት መንገድ ላይ የሚገኙ አካላት ሊገነዘቡ ይገባል። 1. ምርጫው በቁጥሮች ሲገለጽ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጉልህ የሚጠቀሱ አኃዛዊ መረጃዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በውጭ ሀገር አሳትሞ ካስመጣ በኋላ፣ ከምርጫው 4 ቀናት በፊት በሀገሪቱ ባሉት ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በታማኝነትና በጥንቃቄ ማድረስ ተችሏል። ይህንን እጅግ ግዙፍና ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑት የቦርዱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ብቻ መሆናቸው ተቋማዊ አቅሙ ምን ያህል እንደጎለበተ ማሳያ ነው። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ እንደተናገሩት፤ የቦርዱ ሠራተኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎች በዕረፍት ቀናትና በሌሊት በመጋዘን ውስጥ ጭምር እያደሩ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራዎችን በትጋት አከናውነዋል። ሩቅና ተደራሽነታቸው አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳቁሶችን በእግር፣ በእንስሳት ጀርባና በጀልባ ጭምር በማጓጓዝ፣ ወንዞችን ለመሻገር የራሳቸውን የፕላስቲክ ጀልባ ሠርተው ሀገራዊ አደራቸውን ተወጥተዋል። በድምፅ መስጫ ቀን ሥራቸውን ከንጋት እስከ ንጋት በልዩ ብርታት ፈጽመዋል። ይህ ልብ የሚነካ እውነታ የሚያሳየው፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የተናጥልና የጋራ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ሰፊ ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 80 የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል። 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች ተወዳድረዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲዎች ፖሊሲዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት የክርክር መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ፓርቲዎች ከምርጫው ውጭም ራሳቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበትን ባህል ያዳብራል። የመራጮችና አስፈጻሚዎች ቁጥር፦ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ምርጫውን ለማስፈጸም ከ350 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ታዛቢዎችና ወኪሎች፦ ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያሰማሯቸው ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ እንዲሁም 63 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል። ለመራጩ ሕዝብ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት መስፈርቱን ላሟሉ 169 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። እንዲሁም 21 ሚሲዮኖችና አንድ የውጭ ሀገር የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ምርጫውን ተመልክተዋል። የአየር ሰዓት አጠቃቀም፦ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ነፃ የአየር ሰዓት የማግኘት መብት ስለነበራቸው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 752.5 ነፃ የሬዲዮ ሰዓት፣ 57.5 ነፃ የቴሌቪዥን ሰዓትና 576 የጋዜጣ ኮለምን በዘመናዊ የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ተደልድሎ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። መገናኛ ብዙኃን፦ 73 የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን የወከሉ 1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥና 45 የውጭ ጋዜጠኞች ለዘገባ ሥራ ተሰማርተዋል። የሕግ ማሻሻያ እና ዲጂታላይዜሽን፦ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ተሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተተክቷል። ቦርዱ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚመራ፣ እያንዳንዳቸው 2 ሰዓት የሚወስዱ 19 የክርክር መድረኮች በቦርዱ ተዘጋጅተዋል። 14ቱ በአማርኛ፣ 5ቱ በክልል ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ አፋርኛ) ተካሂደው በሰባት መገናኛ ብዙኃን በፕራይም ታይም ተላልፈዋል። አካታችነት፦ 28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ከ20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ተደርጓል። የቅሬታ አፈታትና ክትትል፦ የቅድመ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት (Early Warning System) ተዘርግቷል። 663 የምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ልዩ የአጣሪ ጉባኤ ተደራጅተው 129 አቤቱታዎችን መርምረዋል። የሕግ ጥሰት በተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል። 2. ጠንካራና ገለልተኛ ተቋም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሀገር ውስጥ አቅም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠነ ሰፊ ተቋማዊና ሕጋዊ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ከመሆኑም በላይ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ሀገራዊ አቅምን በተግባር ያሳየ ነበር። የዚህ ምርጫ ትልቁ ትርፍ ጠንካራና የማይናወጡ ብሔራዊ ተቋማትን መገንባት መቻላችን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳየው ፍጹም ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ብቃት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተግበር አቅም፣ ተቋማት ከግለሰቦችና ከፖለቲካ ጫና በላይ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው። ይህም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አስተማማኝ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ነው። ለምርጫው ስኬት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮችን በትዕግሥት በማስተናገድ፣ ብቁ አስፈጻሚዎችን በማሰማራትና ሂደቱን በታማኝነት በመምራት ረገድ ቦርዱ አድናቆት የተቸረው ሥራን ፈጽሟል። የሠራተኞቹ ቀንና ሌሊት መትጋት እንዲሁም በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት አመራር አባላት ያሳዩት ቁርጠኝነት የላቀና ለሀገር ኩራት የሆነ ተግባር ነው። በዚህ ምርጫ ውስጥ ትልቁን ትኩረት የሳበውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት ነው። ይህ ዘመናዊ አሠራር ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መጓዝ ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በነፃነት እንዲመዘገቡ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው የመራጮችን ማንነት በፎቶግራፍ ጭምር በማረጋገጡ በድምፅ መስጫ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ ግድፈቶችንና ማጭበርበሮችን በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል። የዚህ ሥርዓት ዋነኛውና ትልቁ ድል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የዚህን የቴክኖሎጂ ስኬት አስፈላጊነት ሲያብራሩ፤ "እነዚህ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቶች በውጭ ሀገር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የለሙ ሳይሆን በራሳችን ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው። ይህም ተቋሙን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነት ነፃ በማድረግ በራሱ አቅም እንዲቆምና ለወደፊቱ ማሻሻያዎችን በራሱ እንዲያከናውን መሠረት ጥሏል።" ይህ እርምጃ ቦርዱ የውጭ የቴክኒክ ጥገኝነትን በመቀነስ የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባትና የሉዓላዊነትና የደኅንነት ዋስትናን በራስ ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ የቻለበትን ስትራቴጂካዊ አካሄድ በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በውጭ ዜጎች ይሠራ የነበረው የቴክኒክ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መተካቱ የተሳካ የእውቀት ሽግግር መኖሩን አሳይቷል። 3. ሕጋዊ ማሻሻያዎች፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ዴሞክራሲ እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ዜጎች፣ በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ያለ ፍርሃትና ጫና፣ ደኅንነታቸው ተጠብቆ በፖለቲካዊ ሂደቶች እኩል መሳተፍ ሲችሉ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በታዛቢነት በመሳተፍ፣ ሴቶች የዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዲጠቀሙና በሂደቱ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል። ቦርዱ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም በላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አቋቁሟል። በተጨማሪም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ቀድሞ የነበረው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፣ ቦርዱ ይህንን መነሻ በማድረግ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። በነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ዋና መርህ የተወሰደ ነው። 4. ፈተናዎችን መጋፈጥና ገለልተኝነትን ማስከበር ይህ ሁሉ ስኬት ግን ያለ ፈተና አልመጣም። ምርጫው በተያዘለት ጊዜ አይካሄድም የሚሉ ጥርጣሬዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ተቋሙን ፈትነውት ነበር። ሆኖም ቦርዱ ጫናዎችን በመቋቋም ሕግና መርህን ብቻ ተከትሎ በመሥራት ምርጫውን ለስኬት ማብቃቱን ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ያረጋግጣሉ። ቦርዱ በምርጫው ወቅት የተቋሙን ነፃነት ከማንኛውም ዓይነት ጫናና ጣልቃገብነት በመጠበቅ በሕግና በመርህ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል። በምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ግድፈቶች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች በድምፅ መስጫው ቀን ጭምር አስፈጻሚዎችን አሰናብቷል፤ በምርጫ ውጤቶች ላይም ውሳኔ ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ ለሕግ የበላይነትና ለምርጫ ታማኝነት ያለውን ጽኑ አቋም ያሳያል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአንድ ተቋም ወይም በጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች በፀሐይና በዝናብ ሳይበገሩ በትዕግሥት የሰጡት ድምፅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች (እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ) እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው። 5. የምርጫው ግልጽነትና ዓለም አቀፍ እውቅና የምርጫውን ታሪካዊ ሂደትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል። ሂደቱን ለመዘገብ 73 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1 ሺህ 827 ጋዜጠኞች የዘገባ ሥራቸውን አከናውነዋል። ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እና ከ64 ሺህ በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። በተለይም በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 60 ሺህ 277 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን፤ 169 ድርጅቶች ደግሞ ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። በአህጉር ደረጃም የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና 26 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ታዛቢዎች ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ግልጽ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት መካሄዱንም አረጋግጠዋል። 👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምስክርነት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው ዕለት ሰላማዊ፣ ሥነ ሥርዓት የሰፈነበት እና ግልፅነት የታየበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ መተግበሩ ወጣቶችን መሳቡን፣ ዜጎች በትዕግሥት ሰልፍ በመያዝ ጥልቅ ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን፣ የሎጂስቲክስ ዝግጅቱ የተሟላ መሆኑንና የምርጫ ሰዓት መራዘሙ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በመስተንግዶ ረገድም ወንበሮችና የምግብ አቅርቦቶች መኖራቸው ረጅሙን ሰልፍ ታጋሽ እንዳደረገውና ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት "ቅኝ ግዛትን በአንድነት የተከላከለች Couch፣ ለአፍሪካ ነፃነት የቆመች እና የአህጉሪቱ ዋና ከተማ በሆነች ሀገር ውስጥ የተደረገው ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሊኮሩ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድም በሕዝቦች መካከል ያለውን የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ውይይት ይበልጥ ማሳደግ፣ ወደ ኋላ የተተዉ የሚሰማቸውን አካላት ወደ መድረኩ በማምጣት እና አካታችና የተባበረች ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የኡጋንዳ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 28 ጣቢያዎችን በመጎብኘት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቡድኑ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው መከፈታቸውን፣ በቂ ቁሳቁስና አስፈጻሚዎች እንደነበሩ፣ የሳጥኖች አስተሻሸግ የድምፅ ምስጢራዊነትን ያረጋገጠ መሆኑንና የድምፅ አሰጣጡ ያለምንም መሰናክል በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመታዘብ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ለአረጋውያን፣ ሕፃናት ለያዙ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱንና መራጮች የሚቀመጡባቸው ወንበሮች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማዘጋጀትና በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ኦፕሬሽናል አቅም ማሳየቱን አጉልቷል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት ያደነቀ ሲሆን፣ "ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ በተለይም የምርጫ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ አካታችነትን እና ተዓማኒነትን ለማሳደግ የተነደፉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂያዊ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተስተዋሉበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲል ቡድኑ ምስክርነታቸውን በአፅንኦት የገለጹት። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ "ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመዘገብ አብረን ለመሥራት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ሲሉ ነው የተደመጡት። 6. የምርጫው ውጤት፣ የሕዝቡ ጽናትና የአሸናፊው ፓርቲ ከባድ ሸክም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎችም በምክር ቤቶቹ ወንበሮችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስድስት፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሦስት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሦስት፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሦስት፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለት ወንበሮችን አሸንፈዋል። በሌላ በኩል ኦብነግ፣ ጉህዴን፣ አርጎባ አንድነት ጀበርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ኅብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ የጌዴዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው አንድ ወንበር ሲያገኙ 8 የግል ተወዳዳሪዎችም ምክር ቤት ለመግባት አሸንፈዋል። ይህን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች ጊዜያት ለየት የሚያደርገው ታላቅ ክስተት፣ መራጩ ሕዝብ በታጋሽነት ተሰልፎ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ወደር የለሽ ጽናት ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ይህንን የሕብረተሰብ አደራ "አሸናፊው ፓርቲ ትልቅ ሀገራዊ ሸክም የተጣለበት መሆኑን ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል። ፓርቲያችን በማኒፌስቷችንና በአጠቃላይ በምርጫ ቅስቀሳችን ወቅት ለሕዝብ ቃል የገባናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል" ብለዋል፡፡ 👉የፉክክርና የትብብር ሚዛን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር በቀጣይነት ሊመራበት የሚገባው ስልጡን መስመር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሀገር ግንባታ ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር በብሔራዊ ጥቅም ላይ በትብብር ለመሥራት ያለው አቋም የጸና መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በሰጡት አስተያየት፤ "ባለፉት ዓመታት የጀመርነውን በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ የሚሄድ ጥረታችንን በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሕዝቡን በማሳተፍ፣ በየጊዜው የሕዝቡን ግብረ መልስ በመስማት፣ ያንን እንደ ግብዓት ተጠቅመን የእቅድ አካል አድርገን ወደ ተግባር ለመተርጎም በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን።" ብለዋል። ይህ ዕይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሕዝብን ድምፅና ግብረ መልስ በየጊዜው የሚያዳምጥ፣ እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሀገር ጥቅም በጋራ የመሥራትን ስልጡንና አካታች የአሠራር ሥርዓት መከተል መጀመሩን ያሳያል። 7. ዴሞክራሲና ምርጫው የሚገለጽባቸው አራቱ ምሰሶዎች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማለት አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይና የሁለንተናዊ ብልጽግናችን መሠረት ነው። ብዝኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው በዴሞክራሲያዊ ምሰሶዎች ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። መንግሥት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና የማይተካና አዎንታዊ ሚና አላቸው። መራጩን ሕዝብ ከማስተማር፣ ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም ከማስቻል፣ እስከ ሰላም እሴት ግንባታና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የዜጎችን ባለቤትነት ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንደገለጹት፣ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። አንደኛው ምሰሶ፦ ምርጫ የሰላም ዋስትና መሆኑን መረዳት ነው። ሕዝቡ ልዩነቶችን በፀብና በአምባጓሮ ከመፍታት አዙሪት ተላቆ፣ በሰላማዊ መንገድ የመሻገር ባህልን መርጧል። በነቂስ ድምፁን መስጠቱ ኋላ ቀር የአመፃ መንገድን ለሚከተሉ ሁሉ "በቃችሁ" የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የሰፊው ሕዝብ ማዕበላዊ ድምፅ ከአሮጌው የብጥብጥ ባህል መላቀቅ እንደሚፈልግ ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛው ምሰሶ፦ የምርጫ ውግንና ከሕዝብ ጋር መሆኑን ማወቅ ነው። የምርጫ ተዓማኒነትና ክብሩ የሚገለጠው ሥልጣን ከሚመነጭበት ከሰፊው ሕዝብ ሉዓላዊ መብትና ፍላጎት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። ምርጫ ከሚሰጠው ኃላፊነት በላይ ለእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ሕይወት መሻሻልና ከሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል ተገንዝቧል። ሦስተኛው ምሰሶ፦ የምርጫው የፖሊሲ ሐሳቦችና አማራጮች ከፍታ የታየበት ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረኮች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያነሷቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሕዝቡ በጥንቃቄ አዳምጧል። እነዚህ ሐሳቦች ለሀገር ዕድገት፣ ለጠንካራ መንግሥትና ለሰከነ የፖለቲካ ባህል ግንባታ መሠረት እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕሊና ማስረፅ፣ በሰነድ በማዘጋጀትም መተግበር ይገባል። አራተኛው ምሰሶ፦ ምርጫ እንደ ማኅበራዊ ሀብት፤ ምርጫ ፖለቲካዊ ኩነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማኅበራዊ ሀብት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የዚህን ማኅበራዊ እሴት አንድምታ ሲያብራሩም "ሕዝባችን ስለ ኢትዮጵያዊ ቀናነቱና ፍቅሩ ጩኸቱን ሳይሆን የምርጫ ካርድ ድምፁን፣ ስላቅና ሃኬትን ሳይሆን ትሑትነቱን፣ የትኛውንም የፖለቲካ ሐሳብ ቢያራምድ እንኳን ማኅበራዊና ሀገራዊ ፍቅሩን ከጎኑ ላለው ወገኑ አለመንፈጉን ያየንበት እጅግ የተዋበ መድረክ ነበር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ምርጫ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ባልተናነሰ ሁኔታ ማኅበራዊ ፋይዳውም ከፍ ያለ ትልቅ የማኅበራዊ መሠረትን የሰጠው ነው።" ብለዋል። 8. የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ሚና፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስብራቶች የመፈወስ ዕድል ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት ጉዞዋ ውስጥ በርካታ አኩሪ ታሪኮችን ብታስመዘግብም፣ በሂደቱ ውስጥ የተፈጠሩና ዛሬም ድረስ ሀገራዊ አንድነቷን፣ ሰላሟንና የዴሞክራሲ ግንባታዋን እየተፈታተኑ ያሉ ሥር የሰደዱ የፖለቲካ ስብራቶች መኖራቸው አይካድም። እነዚህን ለዘመናት የዘለቁ ስብራቶች በመጠገን ረገድ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግር የሚችል ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ዕድል ይዞ መጥቷል። ምርጫው በበሰለና አካታች መንገድ በመመራቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ጉልህና አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ የሚችልባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አሉት። እነዚህም፦ የቅቡልነት ስብራትን ማከም፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመንግሥታት ሥልጣን አመጣጥ አብዛኛውን ጊዜ ከኃይል ፖለቲካ ወይም ሙሉ በሙሉ ነፃ ካልሆኑ ምርጫዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ለግጭቶች መነሻ ሲሆን ቆይቷል። ይህ ምርጫ ነፃና ታማኝ ሆኖ መካሄዱ አሸናፊው አካል ከሕዝብ የሚሰጠው እውነተኛ የሥልጣን አደራ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ይህም በገዥው አካልና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን በማደስ ረገድ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ባህልን መገንባት፦ ሥልጣንን በአፈሙዝ የመያዝ ልምድ ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ለድቀት የዳረጋት መሆኑ ብዙ ትምህርት ሰጥቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁሉም ወገኖች የሕዝብን ድምፅ አክብረው የሚቀበሉበት ድባብ መፈጠሩ ምርጫን ብቸኛ የሥልጣን መያዣና መልቀቂያ መንገድ የማድረግ አዲስና ጤናማ የፖለቲካ ባህል በሀገሪቷ ውስጥ እንዲለመድ ያደርጋል። በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ ማደስ፦ ሕዝቡ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት ባሉ ገለልተኛ መሆን በሚገባቸው ተቋማት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ሌላው ስብራት ሲሆን፣ ይህንንም ምርጫ በስኬትና በገለልተኝነት ማካሄድ መቻሉ የተቋማቱን ነፃነትና ብቃት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቷ የሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት መልሶ እንዲያገግም ያደርጋል። ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፦ አካታች የሆነ ምርጫ ማካሄድ መሣሪያ ያነሱ ወይም በሰላማዊ መንገድ የሚያምፁ የፖለቲካ ኃይሎች ቅሬታቸውን በሕዝብ ድምፅ እንዲፈትሹ በር ይከፍታል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶች ለመፈወስ የራሱ አሻራ ሊያኖር የሚችለው ሂደቱ ፍትሐዊ፣ ግልጽና በርካታ የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በንቃት የተሳተፈበት በመሆኑ ነው። በዚህም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ በራሱ ወደ ሰፊው ብሔራዊ ምክክር ለመሻገር እንደ ትልቅ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ማጠቃለያ፦ ምርጫው ለአፍሪካ ዴሞክራሲ የብርሃን ፍኖት አፍሪካ በፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፣ በወታደራዊ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ኢ-ሕገመንግሥታዊ መንገድ መምራት፣ የመንግሥት ግልበጣዎች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ስልጡን መንገድ ምርጫዋን ማጠናቀቋ ለአህጉሪቱ አዲስ ፍኖተ ዴሞክራሲ ሆና እንድትወጣ አድርጓታል። 'የአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካውያን መፍትሔዎች' የሚለውን መርህ በተግባር በማሳየት፣ የራሳችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በራሳችን አቅም መቅረጽ እንደምንችል ለዓለም አሳይተናል። በዚህ አስቸጋሪ አህጉራዊ ድባብ ውስጥ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከልና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ፍትሐዊ መንገድ በስኬት ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ለጫናዎች ሳትበገር፣ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ መድረክ ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ አህጉሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዲሞክራሲ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ ሰላምና ልማት ሊመጡ የሚችሉት በጠመንጃ ኃይል ሳይሆን ሕዝብ በነፃነት የራሱን መሪ በሚመርጥበት ስልጡን መንገድ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፦ "አህጉራችን ከዲሞክራሲ ውጭ ሌላ ምርጫ የላትም። ወደፊት ለመራመድ፣ ዕድገትን ለማረጋገጥና በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ዴሞክራሲ ብቻ ነው" ሲሉ በአፅንኦት ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና ሕጋዊ መሠረቷን በማጠናከር ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የተሻገረችበት እና የጋራ የትብብር አቅምን ያሳየችበት አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል። ለዚህም ስኬት በየሚናቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ታዛቢ ድርጅቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል። በምርጫው ወቅት የተሰጠው የሕዝብ አመኔታና ድምፅ ለተመራጮች ትልቅ አደራና ኃላፊነትን ጥሏል። ያሸነፉ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በመሸከም ለሕዝብ ፍላጎት ቅርብ የሆነ አገልግሎት በመስጠት፣ በታማኝነት፣ በቅንነትና ንጹሕ በሆነ ሕሊና በመሥራት የሕዝቡን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ግዴታ አለባቸው። የምርጫው ትልቁና የመጨረሻው ስኬት የሚለካው በተመራጮችና በሕዝብ መካከል በሚገነባው መተማመን፣ በሚረጋገጠው ዘላቂ ሰላምና ለሁሉም ተጠቃሚነትን በሚያሰፍነው ሀገራዊ ዕድገትና ብልጽግና ብቻ ነው።