ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚዎቹን አውቋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2018 (ኢዜአ)፦ የ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተካሄዷል።

በማጣሪያው ላይ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ እና ብሩንዲ ጋር ተደልድላለች።

አዘጋጇ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን በምድብ አንድ የሚገኙ ሀገራት ናቸው።

ታንዛንያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ በምድብ ሶስት ተደልድለዋል።

የማጣሪያ ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሩዋንዳ ይካሄዳል።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።

17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም