ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የሜዳ ጨዋታቸውን በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- በአህጉራዊ የክለቦች ውድድሮች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ቀን እና ቦታ ይፋ ሆኗል።
 
በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የቻዱን ኤጌሎን በድምር ውጤት 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈው ሲዳማ ቡና፤ ከሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን ጋር የሚያደርገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም  ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ  ስታዲየም ያደርጋል።



በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የሱዳኑን ሂሊል አል ሳህል በመለያ ምት ያሸነፈው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጋር ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም  ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ያከናውናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም