ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣መስከረም 12 /2019 (ኢዜአ):- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች ከ81ኛ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በቀጣናው የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ዋና ጸኃፊው የኢትዮጵያን የዘላቂ ልማት ጉዞ በማድነቅ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ትብብር እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።