የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጁባ ደርሷል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጁባ ደርሷል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 /2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ዋልያዎቹ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከሱዳን ጋር ይጫወታሉ።
በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን እና ሴኔጋል ለሚያደርገው የማጣሪያ ጨዋታ ከአንድ ወር በላይ በሀገር ቤት ዝግጅቱን አድርጓል።
ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን ከሴኔጋል ጋር መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም በባህር ዳር ስታዲየም ታከናውናለች።
በምድብ 10 የምትገኘው ኢትዮጵያ በማጣሪያው ከሱዳን፣ ሴኔጋል እና ሞዛምቢክ ጋር ተደልድላለች።