ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦ በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ሩጫ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሙኒኬሽን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።



የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን  በኮፐንሃገን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ በማድረግ ሀገራችሁን አኩርታችኋል ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው አንድ የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም