ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ዕድገትና ትብብር ያጠናክራል- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አስተማማኝ የባህር በር ማግኘት የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ዕድገትና ትብብር  እንደሚያጠናክር  ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ  ገለጹ።  
 
81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ መካሄዱን ቀጥሏል።
 
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ  ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ንግግር አደርገዋል።
 
ፕሬዝዳንት ታዬ  በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገው ጥረት አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ሳይኖር ዘላቂ ልማት ማምጣት እንደማይቻል  ገልጸዋል።
 
በመሆኑም የኢትዮጵያ ባህር በር የማግኘት ጉዳይ ለሁሉም የቀጣናው ሀገራት ከሚያስገኘው የጋራ ጥቅም እና ዕድገት ጠቀሜታ አንጻር መመልከት እንደሚገባ ተናግረዋል።
 
በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ የባህር በር  የማግኘት ፍላጎቷን  እውን ለማድረግና ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ለመተሳሰር  ሁሉንም የዲፕሎማሲ አማራጮች ተጠቅማ እየሰራች መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም