ቀጥታ፡

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና ወደ መንግስት ገቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13 /2019 (ኢዜአ)፦የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የሕወሃት ነባር አመራር ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮና የጦርነት አባዜን በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግስት ገብተዋል።

ጀነራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃና ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ህፃናትን አስገድዶ በመመልመል ለጦርነት በመማገድ ፣ የትግራይ ህዝብን ስቃይ እያበዛ ያለውን የህወሃት እኩይ ሴራ በመቃወም ጀኔራሉ ከድርጅቱ መለየታቸውም የህገ - ወጡን የህውሀት ቡድን ህልውና ማክተሙን በተግባር ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም