ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም የቻይና ባለሀብቶችን ይበልጥ እየሳበ ነው-አምባሳደር ቼን ሃይ
Aug 26, 2026 293
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና እየተሻሻለ የመጣው የኢንቨስትመንት ከባቢ ይበልጥ የቻይና ባለሀብቶችን እየሳበ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ። አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ግዙፍና ፈጣን እድገት ካላቸው ኢኮኖሚዎች አንዷ መሆኗን ገልጸዋል። ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ የንግድ አጋሮችና ባለሀብቶች ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን እያቀረበች እንደምትገኝም አመልክተዋል። አምባሳደሩ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የከተሜነት መስፋፋት እና የግብርና ዘመናዊነት አሰራሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን አድንቀዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ ትስስር ለሀገራዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ከማበርከት ባለፈ፣ የማህበረሰቡ ኑሮ እንዲሻሻል መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አንስተዋል። ቻይናና ኢትዮጵያ ሀገራዊ ዕድገትና የመዘመን ራዕይን እውን ለማድረግ የጋራ የሆነ መሻት እንዳላቸውም አብራርተዋል። አምባሳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ በቆዩበት ጊዜ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምህዳርና የንግድ ከባቢ ላይ ግልጽ ለውጦች እንደተመለከቱም ተናግረዋል። በዚህም የቻይና ባለሀብቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ አዳዲስ ፋብሪካዎችና ማምረቻዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን አንስተዋል። የኢንቨስትመንት ከባቢው እንዲሻሻል በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የተደረጉ ማሻሻያዎች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፣ እነዚህ እርምጃዎች ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንዳስቻሉም አክለዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እየሰፋ መሄዱን፣ በተለይም የቻይና ሸማቾች ለኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። እንደ ቡናና ሰሊጥ ያሉ የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች በቻይና ገበያ ያላቸው ተወዳጅነት ማደጉን ጠቅሰው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የኢንዱስትሪና እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችም ጭምር በቻይናውያን ሸማቾች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት እያገኙ መምጣታቸውን አመልክተዋል። አምባሳደሩ በቻይና ንግድ ተቋማትና በኢትዮጵያ መንግሥት አካላት መካከል በቀጣይ የሚኖረው ትብብር የሀገሪቱን የንግድ ምህዳር ይበልጥ እንደሚያጠናክረውና ለንግድና ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የንግድና ኢንቨስትመንት ጠንካራ ትብብር የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከማፋጠን ባለፈ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ እንደሚያጎለብተውም ተናግረዋል። የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት (all-weather strategic partnership) ደረጃ ከፍ ማለት፣ የሁለቱን ሀገራት ለሰፊ ትብብርና ለጋራ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይና የቻይና-አፍሪካን የኢኮኖሚ ግንኙነት አጠቃላይ ፋይዳ አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በዞኑ በማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት የተሰባሰቡ የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች እየተሰራጩ ነው
Aug 26, 2026 293
ደብረ ብርሃን፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በክረምት የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት የተሰባሰቡ 75 ሺህ ደርዘን ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ“ በሚል መሪ ሀሳብ በበጎ ፈቃደኞች የተሰባሰቡ የትምህርት ቁሳቁስ ወላጆቻቸው አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች እየተሰራጨ ነው።   የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በማቃለል በኩል ጉልህ አስተዋጾ እያደረገ ነው።   በተያዘው ክረምትም በዞኑ 985 ሺህ 759 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ ትምህርት፣ ግብርናና ጤናን ጨምሮ በ17 የሥራ ዘርፎች የማህበራዊ መደጋገፍን የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። የመንግስት ሠራተኞች ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ውጤታማ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ በበኩላቸው እንዳሉት በዞኑ በ2019 የትምህርት ዘመን 612 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ሥራ ተጀምሯል።   ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ በማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት 75 ሺህ ደርዘን ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሶችን በማሰባሰብ የማሰራጨት ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል። በዛሬው ዕለትም ለ1 ሺህ 255 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ደርዘን ደብተር እና 12 እስክርቢቶ በድጋፍ መሰጠቱን ነው የተናገሩት። የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑም አመልክተዋል። የደብተርና የእስክርቢቶ ድጋፍ ካገኙ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ወንጌላዊት ይልማ የተደረገላት ድጋፍ ለቤተሰቦቿ እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን ተናግራለች። ሌላው ተማሪ ኪሩቤል ንጋቱ በበኩሉ የተደረገለት ድጋፍ ለማህበረሰቡ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንደጨመረለት ገልጿል።
የሪፎርም ስራዎች የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲያድግ አስችለዋል
Aug 26, 2026 298
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ባለፉት ዓመታት የተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎች የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲያድግ ማስቻላቸውን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፉም ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት አራት ዓመታት የተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎችን በትኩረት አከናውኗል። ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል አቅርቦትን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማሸጋገር፣ የግዥ ሥርዓቱን ማዘመንና ግልጽ ማድረግ፣ የክምችትና ሥርጭት አሠራርን ማስተካከል እንዲሁም የምርቶች አቅርቦት ሰንሰለት ቅንጅትን ማጠናከር ይገኙበታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ሪፎርሙ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማስቻሉንም አመልክተዋል። በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አጠቃላይ የግዥና የክምችት ሥርዓቱን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ማዘመን መቻሉ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንደጨመረው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበሩ አሠራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀው ይህም የደንበኞችን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሳደጉ ባሻገር አሠራሩን ወጪ ቆጣቢ ማድረጉንም ገልጸዋል። ይህም በአገልግሎቱ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አህጉራዊ እውቅናም እያስገኘለት መሆኑን ጠቁመዋል። የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ ዕውቅና ያገኘ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፍ መቻሉንም አስታውቀዋል። ይህ ሽልማት አገልግሎቱ የሕክምና አቅርቦት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ለማስደገፍና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሠራቸው ስኬታማ ሥራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ እውቅና ወደፊት አገልግሎቱን አህጉራዊ ተወዳዳሪና ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትልቅ ብርታት እንደሚሆን አክለዋል።      
ኢትዮጵያ የጤና ሥርዓቱን በፋይናንስ በመደገፍ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በመጠንና በጥራት እያሳደገች ትገኛለች
Aug 26, 2026 399
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የጤና ሥርዓቱን በፋይናንስ በመደገፍ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በመጠንና በጥራት እያሳደገች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ። በአፍሪካ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ከአባል ሀገራት ጋር በትብብር ትሰራለችም ብለዋል። 76ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄዱን ቀጥሏል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ብቁና ሥነ ምግባር የተላበሰ የጤና ባለሙያ ማፍራት የሚያስችል ስትራቴጂ ገቢራዊ አድርጋለች። ኢትዮጵያ የጤና ሰራተኞች ስትራቴጂ ገቢራዊ በማድረግ የጤናውን ዘርፍ የሰው ኃይል አቅም ከ50 በመቶ በላይ ማሳደግ ችላለች ብለዋል። በዚህም በገጠርና ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ላሉ የጤና ሰራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠርና ድጋፍ በማድረግ እንዲበረታቱ መደረጉን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 የሚተገበረውን የአፍሪካ የጤና ሰራተኞች ስትራቴጂ በመደገፍ ለተግባራዊነቱ ከአባል ሀገራቱ ጋር በትብብር ትሰራለች ብለዋል። በአፍሪካ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው የጤና ሰራተኞች ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከሕብረቱ አባል ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።   በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሥርዓትና አገልግሎት ክላስተር ዳይሬክተር ዶክተር አደልሄድ ኦንያነጎ በበኩላቸው፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአፍሪካ የጤና ሰራተኞች ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅዕኖ ቢያሳድርም እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2017 በኋላ መሰረታዊ ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል። በአሕጉሪቱ ቀጣይና የጤና ዘርፍ ስትራቴጂዎችን፣ ፖሊሲዎችንና ዓለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂዎችን ገቢራዊ በማድረግ የአፍሪካን የጤና ሰራተኛ በ2013 ከነበት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በ2024 ወደ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ በባለሙያዎች ፍልሰት፣ በአካላዊ ጫናና ከሥራ በማቋረጥ ሳቢያ በጤናው ዘርፍ ላይ አደጋ እንዲደቀንበት ማድረጉ አልቀረም ብለዋል። በመሆኑም የጤና ሥርዓቱን ጠንካራና ዘላቂነት ያለው ለማድረግ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 የሚቆይ የአፍሪካ የጤና ሰራተኞች አጀንዳ ገቢራዊ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም እስከ 2035 ጠንካራ የጤና ተቋማትን ከመገንባት ባለፈ አሕጉሪቱ ቢያንስ ከ3 ሚሊዮን ያላነሰ ተጨማሪ የጤና ሰራተኛ ያስፈልጓታል ብለዋል። ይህን ግብ ለማሳካት ጠንካራ የአስተዳደር ሥርዓት መገንባት፣ የስልጠና ማዕከላት ማስፋፋት፣ የተጠያቂነትን ሥርዓት ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።    
የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል
Aug 26, 2026 382
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግ ገለፁ። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩትን አምባሳደር ጃንግ ካንግን አሰናብተዋል።   በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው የስንብት መርሃ ግብር ተሰናባቹ አምባሳደር ጃንግ ካንግ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት በጠንካራ ታሪካዊ መሠረት ላይ የተገነባ ነው። የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱንም ጨምረው ገልጸዋል። በተለይም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚደረጉ ጉብኝቶች፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ዓመታትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን አምባሳደሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ማሳደግ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል። በተጨማሪም በሕዝቦች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ የበለጠ ማጎልበት ይገባል ነው ያሉት። የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በኢትዮጵያ በነበራቸው መልካም የስራ ጊዜ ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና አ
የሚታይ

የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 26, 2026 377
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ የተከናወኑ ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ እውን ለማድረግ በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት የተገነቡ የተቀናጁ የትራንስፖርት ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎችና የንግድ ማዕከላት ምረቃ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።   ከተማ አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት የሚያገኝባቸውን በርካታ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል። ዛሬው ለምረቃ የበቁት የታክሲና የአውቶቡስ አገልግሎት ትራንስፖርት የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ዐረፍ ብሎ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ የጀመረችውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎች መካተታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎች ከነሙሉ አገልግሎታቸው ተዘጋጅተው ለሕዝብ ጥቅም ክፍት ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ከመመለስ ባሻገር የአካባቢ ጥበቃን ያማከሉ አረንጓዴ የትራንስፖርት አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡ በዚህም በመዲናዋ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለመገንባት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ከተማዋ ወደ አረንጓዴ ትራንስፖርት የምታደርገውን ሽግግር ያፋጥናሉ ብለዋል፡፡   በአሁኑ ወቅት የህዝብ ትራንስፖርትንና የግል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የመኪና ማቆሚያ አቅም ከ180 ሺህ በላይ መድረሱን ከንቲባዋ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ በእነዚህ የትራንስፖርትና የመኪና ማቆሚያ መሰረተ ልማቶች ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ብቻ እስከ አሁን ከ20 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማሪያም በበኩላቸው፤ ቢሮው ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፍጥነትና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡ መሰረተ ልማቶቹ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፉና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በውስጣቸው የንግድ ሱቆች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ አሳንሰሮችና የቲኬት መቆረጫ ቢሮዎች እንደተገነባላቸውም ገልጸዋል።      
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር አሰናበቱ
Aug 26, 2026 396
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግን አሰናብተዋል። በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው የስንብት መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት በጠንካራ ታሪካዊ መሠረት ላይ የተገነባ ነው። የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።   በተለይም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚደረጉ ጉብኝቶች፣በኢኮኖሚ ትብብርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች አበረታች እድገት መመዝገቡን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ዓመታትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን አምባሳደሩ ገልጸዋል። በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ማሳደግ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። በተጨማሪም በሕዝቦች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ የበለጠ ማጎልበት እንደሚገባ አምባሳደሩ ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸው፣ በኢትዮጵያ ላሳለፉት መልካም ጊዜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል
Aug 26, 2026 382
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግ ገለፁ። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩትን አምባሳደር ጃንግ ካንግን አሰናብተዋል።   በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው የስንብት መርሃ ግብር ተሰናባቹ አምባሳደር ጃንግ ካንግ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት በጠንካራ ታሪካዊ መሠረት ላይ የተገነባ ነው። የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱንም ጨምረው ገልጸዋል። በተለይም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚደረጉ ጉብኝቶች፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ዓመታትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን አምባሳደሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ማሳደግ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል። በተጨማሪም በሕዝቦች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ የበለጠ ማጎልበት ይገባል ነው ያሉት። የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በኢትዮጵያ በነበራቸው መልካም የስራ ጊዜ ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና አ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር አሰናበቱ
Aug 26, 2026 396
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግን አሰናብተዋል። በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው የስንብት መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት በጠንካራ ታሪካዊ መሠረት ላይ የተገነባ ነው። የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።   በተለይም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚደረጉ ጉብኝቶች፣በኢኮኖሚ ትብብርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች አበረታች እድገት መመዝገቡን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ዓመታትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን አምባሳደሩ ገልጸዋል። በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ማሳደግ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። በተጨማሪም በሕዝቦች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ የበለጠ ማጎልበት እንደሚገባ አምባሳደሩ ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸው፣ በኢትዮጵያ ላሳለፉት መልካም ጊዜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ የገለጹት የኢትዮጵያ እውነት
Aug 26, 2026 437
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሔድ የቆየው የሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ማጠቃለያ በስኬት ማለቁ ተበስሯል። የውጭና የሃገራት እንግዶች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶች ኮሚሽነሮችና ተመካካሪዎች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቱ ያሰሙት ድምጽ ጆሮ ገብ ነበር። የሁሉንም ትኩረት የሳበ። ለመሆኑ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምን ብለው ነበር? በዚህ ንግግራቸውስ ምን መልዕክት አስተላለፉ? የሀገራዊ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ የማይታወቀውና ያልተለመደው የሆነበት ነው ። ይህ ምከክር ልዩነቶችን ከምክክር ይልቅ በኃይል ለመፍታት የመሞከር አባዜም ወደ ታሪክነት መሸጋገሪያው ነው ። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተረክ /political discourse/ ውስጥ በዘፈቀደ ሲገለጹ የሚሰሙት “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ፣ “ኢትዮጵያ ልትበተን ነው” ፣ “ኢትዮጵያ ልትፈርስ” ነው የሚሉና መሰል አገላለጾች የፖለቲከኞች እንጀራ መብያ እንጂ የኢትዮጵያ መንገድ መገለጫ እንዳልሆነ ያነሳሉ። ይልቁንም ኢትዮጵያን የማይገልጹና ከፍላጎታችን፣ ከሀገራዊ መሻቶቻችን ጋር አብረው የማይሄዱት እነዚህ አገላለጾች መነሻቸው ዝንታለም በሌሎች ሀሳብና ርዕይ የሚነግዱ የሀሳብ ተከታዮች እንጂ ኢትዮጵያውያን ፈጽሞ የሚናገሩት ቃል አይደለም ይላሉ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚሆነው መስቀለኛ ሳይሆን ቀጥ ያለ፣ ርቱዕ የእድገትና የህብረት መንገድ ብቻ መሆኑንም አስምረውበታል። ምክክር ማህበራዊ ባህላችን ውስጥ ያለንና የቆየ ሀብታችን ቢሆንም ይሄንን ነባር ባህል የፈተናዎቻችን መድህን የሀገር ግንባታችን ካስማ እንዲሆን መልክና ቅርጽ ተበጅቶለት ይፈጸም ዘንድ ቢያንስ በርሳቸው እድሜ እንደማያስታውሱ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የዚህን ሂደት ታሪካዊ ዋጋና ሀገራዊ ፋይዳ በማሰላሰል ለሀሳቡ እውንነት ለተጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ውጥንና ዓላማ ኢትዮጵያን ማዕከል በማድረግ ዘመንን ሊያሻግሩና ሀገርን ሊያጸኑ በሚችሉ የሀሳብ አውዶች ዙሪያ መወያየት እንደመሆኑም በመድረኩ የታየው ይሄው ነበር። በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎች፦ በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎችም መነሻቸው ይሄንኑ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ። የጋራ መሻትን ማጎልበት ቀዳሚው ሲሆን ልዩነቶችን በመሻገር የጋራ እጣፈንታንና ራዕይን የሚያጸና እውቀት የተንሸራሸረበት መድረክ መፍጠሩ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ምክክሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ስክነትና እርጋታ እንዲሸጋገሩ ያስቻለ፣ የፖለቲካ ውይይቱም ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ አስተዋይ በሆነ መንገድ እንዲመራም ያስቻለ መሆኑን ነው። ፕሬዝዳንቱ በሦስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ትልቁ ፋይዳ ደግሞ የይቅርታ እና የስርየት ጎዳና እንዲፈጠር መሰረት መጣሉ ሲሆን ከደመኝነት እና ከተቃርኖ ፖለቲካ በመውጣት በይቅርታና በመተሳሰብ የጋራ ጉዞን ለመቀጠል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ነው። የተለመደው የፖለቲካ ማጠንጠኛ ከሆነው ከአምባጓሮና ከነፍጥ በዘላቂነት በመላቀቅ የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላምና በመደማመጥ ላይ እንዲመሰረት ሃገራዊ ምክክሩ በር መክፈቱ በአራተኛነት ያነሱት ነጥብ ነው። ሌላኛው በአምስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳም በመከባበርና በሰመረ ቋንቋ፣ ከኃይለ ቃል በፀዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን ያሳየንም ነው። እንደ ሀገር ፈተና ባጋጠመን ጊዜ አንዳንድ ወዳጅ ሀገራት ከናንተ የተማርነው በህብረት ቆማችሁ ቀኝ ገዢዎችን ማንበርከክ ሆኖ ሳለ ለምን የውስጥ ጉዳያችሁን ለመፍታት ወደ ነፍጥ ታደላላችሁ? የሚል የወዳጅ ጥያቄ አዘውትሮ እንደሚቀርብም አንስተዋል። መንግስት የነበረ አካል ፣ ወደ ሽፍትነት የተለወጠበትን አጋጣሚ ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ውጥንቅጥ ችግር ሲያጋጥማቸው መቼውንም ቢሆን መውጫ መንገድ አጥተው እንደማያውቁም ጠቅሰዋል። ለዚህም ህልውናችንን የሚፈታተኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ሀገር እየጠበቅንም፣ እየመከርንም ኢትዮጵያችንን ማፅናት መቻላችን ነው ብለዋል። የዚህ መሰረቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ስልጣኔ፣ እውቀትና እውነትን አጋምዳ የያዘች በመሆኗ ችግር ሲያጋጥመን በጋራ ቆመን ጠላትን የምንመክተው የዳበረ፣ የጥንት ሀገር ስልጣኔ ባለቤት በመሆናችን ነው ይላሉ። እንደኛ የፖለቲካ እይታ ቢሆን ሌላ ድርሳን ነበረ። አጋምዶ የያዘን ግን አንዱ ጥንታዊ ሀገር ባለቤቶች በመሆናችን ነው። ሀገር ደግሞ የጋራ ላብ፣ የጋራ ደም፣ ተከሻና ጉልበት ውጤት ናት ሲሉም ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የውስጥ ችግር ባጋጠመን ወቅት፣ በአለም አቀፍ መድረክ እጅግ የማይመቹ ቃላት በኢትዮጵያ ላይ ተነጣጥረው እንደነበረ አንስተው የጋራችንን ሳይሆን የተወሰኑ የክፋት መንገድን የመረጡ ኃይሎችን ብቻ በመመልከት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ተበጥሷል፣ ወደነበረበት ለመመለስም ኢትዮጵያውያን ተስኗቸዋል በማለት ለማስተከዝ የሞከሩ እንደነበሩም አስታወሰዋል። አንዳንዶቹማ በዚህ ሀገራዊ የሀሳብ ጉባኤ ወቅት ሳይቀር የእንመካከር እንወያይ ሀሳብ ለሀሳብ እንለዋወጥ የሚለውን ጥሪ እንደ ትልቅ አጋጣሚ ከመውሰድ ይልቅ፣ ለክፋት መጠንስሻና ግጭት ማውጠንጠኛ ሊያደርጉ ሲባዝኑ መታዘባቸውን አንስተዋል። እነዚህን የመሰሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የሺህ ዓመታት ጥብቅ ማህበራዊ ሸማችንን በቅጡ ያልተረዱ፣ የህዝባችንን የውስጥ ጥንካሬ ያላወቁ ናቸው ይሏቸዋል ፕሬዝዳንቱ። እኛ ኢትዮጵያውያን የተራሮች፣ የሸለቆዎች፣ የደጋዎች፣ የወንዞች ልጆች ነን። የኢትዮጵያ ህዝብ ወንዞቹን ለመሻገርና ለመግራት የሚያስፈልገውን ትዕግስት ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። በእርግጥም አባይን የሚያቋርጥ ብቻ ሳይሆን ታሪክን የሚያሻግር ሁሉ ከነፋስና ወጀብ የበረታ ታላቅ የትዕግስት መከተሪያ ሊኖረው እንደሚገባ ያወቀ ብልህ ህዝብም ነው። ትዕግስት ስንቁ ነው። የሚሻገረውም በትዕግስተኛነትና በብርታት ነው።
ሀገራዊ ምክክሩ በሀገር ጉዳይ በጋራ በመምከር ዘላቂ ሰላም እና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በተግባር ያየንበት ነው- የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች
Aug 26, 2026 375
አምቦ ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡-ሀገራዊ ምክክሩ በሀገር ጉዳይ በጋራ በመምከር ዘላቂ ሰላም እና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በተግባር ያየንበት ነው ሲሉ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ሁለንተናዊ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር አሳታፊ የሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቅ ችሏል። በተለይም የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ችግሮችን በኃይል የመፍታት የፖለቲካ ባህል በመቀየር፣ ልዩነቶችን በንግግርና በውይይት ብቻ መፍታት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ታሪካዊ ሁነት ሆኗል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች፤ ሀገራዊ ምክክሩ የዚህ ትውልድ ጉልህ አሻራ ያረፈበትና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ጠንካራ መሰረት ያኖርንበት ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ በሀገር ጉዳይ በጋራ በመምከር ዘላቂ ሰላም እና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በተግባር ያየንበት ነው ሲሉም ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ደለሳ ሚዴክሳ፤ የምክክር ጉባኤው ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችን በኃይል ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀራርበን ለመፍትሄው የተመከረበት ታሪካዊ ሁነት መሆኑን አንስተዋል። ለዘመናት የተሻገሩ የፖለቲካና ማህበራዊ ስብራቶችን በምክክር በመፍታት ለሁላችንም የምትመች ሀገር ለመገንባት መሰረት ያኖርንበት ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል። ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ወይዘሮ ቶለሺ ፈይሳ እና አቶ ደበላ ጌታሁን፤ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ ተሰባስበው በሀገራቸው ጉዳይ የመከሩበት ሀገራዊ የምክክር ሂደት አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል።   ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ተቀራርበው በመምከር የጋራ መፍትሄ የተለሙበት፣ ዘላቂ ሰላም እና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በተግባር ያየንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ለአርባ ስድስት ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረው የምክክር ጉባኤ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑም ይታወቃል።  
የሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ያሸጋግራል -የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች
Aug 26, 2026 400
ቦንጋ፣ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡-የሀገራዊ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ከሀምሌ 8 ጀምሮ በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡ በጉዳዩ ለይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች የምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ችግሮችን በጋራ ፈትቶ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ወጣት ትዕግስቱ ጴጥሮስ እንዳለው ላለመግባባትና ለግጭት መንስኤ የሆኑ የቆዩ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የተጀመረው ሂደት ሃገርን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው፡፡ ሂደቱ እኔ አውቅልሀለው በሚል ፍላጎትን በሃይል ለማስፈጸም ሲደረግ የነበረን አካሄድ በመቀየር ዜጎች በሀገራቸው ላይ በጋራ መክረው በአንድነትና ተግባብተው ለመኖር ያላቸውን ፍላጎት ያሳዩበት ነው ብሏል፡፡ ሀገራዊ ምክክር ችግሮችን በውይይትና በምክክር የመፍታት ባህልን ከማዳበር ባለፈ በብዙ መልኩ የሀገራችንን መፃኢ ዕድል ያሳምረዋል ሲልም ገልጿል። ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ጥላሁን ደሳለኝ በበኩላቸው ሐገራዊ የምክክር ጉባኤው ዜጎች ልዩነት በፈጠሩና ሳያግባቡ በቆዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ ምክረሀሳብ ያስቀመጡበት ምቹ ምህዳር መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ከዚህ ቀደም ንግግር ተደርጎባቸው የማያውቁ ሃገራዊና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር ውጤታማ ውይይት በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ ሀገራዊ ምክክሩ እርስ በእርስ የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማዳበር ለሀገር ዘላቂ ሰላምና አንድነት ትልቅ መሰረት መጣሉን የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ ነቢላ አህመድ ናቸው። ከዚህ ቀደም ላለመግባባት መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ለይ ቁጭ ብለን ባለመነጋገራችን እንደሀገር ብዙ ዋጋ ከፍለናል ያሉት አስተያየት ሰጪዋ ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወጣት አለማየሁ ወልደሚካል የተባለ ነዋሪ በበኩሉ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቁ ችግሮቻችንን በውስጥ አቅም በመፍታት ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ ትልቅ መሠረት ይጥላል ብሏል፡፡ ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን ውይይት ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መሰረት መጣሉንና ይህን ለማስቀጠል ከታች ጀምሮ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ አመልክቷል። ሀገራዊ ምክክሩ ተቀራርቦ መነጋገር፣ መከባበርና መደማመጥ ካለ የማይፈቱ የሚመስሉ ችግሮችን በመፍታት ሀገርን በጋራ ማስቀጠል እና ዕድገቷን ማፋጠን እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ነው ሲልም ገልጿል።      
ሀገራዊ ምክክሩ የሁሉንም ወገን ድምፅ ያዳመጠና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ መድረክ ነው
Aug 26, 2026 449
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የተካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የሁሉንም ወገን ድምፅ ያዳመጠ እና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ገለጹ። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለአርባ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። በጉባኤው ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የዘለቁ የአለመግባባት ስብራቶችን በሐሳብ የበላይነትና በጥበብ መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተግባር አሳይቷል፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ለአርባ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አሳታፊና አካታች መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤው ከአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተውጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በመሳተፍ ለኢትዮጵያ የሚበጁ ምክረ ሐሳቦችን ማዋጣት የቻሉበት መሆኑን ተናግረዋል። ከነዋሪዎች መካከል መልካም በንቲ እንደገለጸችው፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝቡ እኩል እንዲመክርና እንዲወከል በማድረጉ ከፍተኛ ሀገራዊ ስሜትን የሚያነቃቃና ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስታውቀዋል። በታሪካችን ውስጥ የነበሩ የታሪክ ስብራቶችን ለማቃናት፣ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የቆዩ ችግሮችን ለማስተካከል ሂደቱ ወሳኝ እንደነበረም አመልክታለች፡፡ ጉባኤው ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሻገርና ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ለማስቀጥል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፃለች።   ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ሱራፌል ዳርጌ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮችን በራሳችን አቅምና በጋራ ውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታሪካዊና ከፍተኛ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ጉባኤው ዘላቂ ሰላሟ የተጠበቀና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል። በተለይም በሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና የጋራ እሴቶችን በማጠናከር ረገድ ወደ ተሻለ አንድነት የሚያመጣ መንገድ መሆኑን አመልክተዋል።   የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር የሁሉንም ወገን ድምፅ በማደመጥ የኢትዮጵያ አሸናፊነትና የበላይነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑን የገለጸው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት አላዛር ረዘነ ነው። ጠንካራና የጸና ሀገራዊ አንድነት እንዲፈጠር ሲንከባለሉ የቆዩ መሠረታዊ ችግሮችን በጥቅል የመፍታትና ለጥያቄዎችም ዘላቂ ምላሽ የመስጠት በኩል መድረኩ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። በተለይም ችግሮችን በተበታተነና በተነጠለ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ፣ በጋራ በመቆምና በአንድነት በመካከር ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት ምቹ ሁኔታንና አዲስ ተስፋን የፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል።   ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በራስ አቅም የመፍታት ከፍተኛ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የገለፀው ደግሞ ሌላኛው የመዲናዋ ነዋሪ ወጣት እዮብ ተኬ ነው። ሀገራዊ ምክክሩ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያስቀጥሉና የሚያጠናክሩ ወሳኝ ምክረ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት መድረክ መሆኑን አስታውቋል። በመሆኑም በምክክሩ የመጡ መልካም አጋጣሚዎችንና ውጤቶችን ለማጽናት እንዲሁም ወደ ተግባር ለመቀየር ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል።  
በክልሉ በፓርቲው መሪነት በተለያዩ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Aug 24, 2026 962
ሳውላ፤ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በተለያዩ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው።   በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በፓርቲው መሪነት የተከናወኑ የልማት ኢንሼቲቮችና የንቅናቄ አጀንዳዎች የተሳኩና ውጤት የተገኘባቸው ናቸው። በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየውን ስኬት ለአብነት ጠቁመው በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብርም አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል ። በተመሳሳይ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሀገር ውስጥ ምርትን በመተካት እንዲሁም ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡን አመልክተዋል ። በክልሉ ከተሞች የኮሪደር ልማት በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በተመሳሳይ መልኩ የገጠሩን ሕብረተሰብ የኑሮ ዘይቤ በዘላቂነት ለመቀየር የተጀመረው ሞዴል የገጠር ኮሪደር ልማት ስራም ውጤታማ መሆኑን አንስተዋል ። ባጠቃላይ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ባስገኛቸው ውጤቶች ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በማህበራዊ ልማት በኩል በትምህርትና በጤና ዘርፎች ጥራትን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውንም አንስተዋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአረጋውያንና አቅም ለሌላቸው ወገኖች የተደረጉ የቤት አድሳትና የድጋፍ ስራዎች ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ ባህልን ያጎሉ፣ የእርሰ በርስ መስተጋብርን ያጠናከሩ ናቸዉ ብለዋል።   የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸዉ በፓርቲዉ መሪነት በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። ይህም በዞኑ ዜጎችን በተለያየ መልኩ ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቁመው በህዝብ ተሳትፎ ውጤቱን ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል ። በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የክልል፣ የዞኖችና የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሀገራዊ ምክክሩ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በመመካከር ወደ መግባባት መሸጋገር የተቻለበት ነው – ተመካካሪዎች
Aug 24, 2026 892
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የልዩነት ምንጭ በነበሩ አጀንዳዎች ላይ በግልጽነት በመመካከር የጋራ መፍትሔ ሀሳቦች የተቀመጡበትና ወደ የጋራ መግባባት መምጣት የተቻለበት ወሳኝ መድረክ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋና ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ባለፈው ቅዳሜ ተከናውኗል። ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ማጠቃለያ በኋላ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች እንዳሉት፤ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በመመካከር ዘላቂ ልማትና ሰላምን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦችን በማፍለቅ ምክክራቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ከሶማሌ ክልል የተወከሉት ተመካካሪ አብዱልቃድር መሐመድ እንዳሉት፤ ምክክሩ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተመካካሪዎች በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንዲያነሱና እንዲመካከሩ ዕድል ፈጥሯል። መሰል የምክክር ሂደት በቀጣይም ሊገጥሙን ለሚችሉ ችግሮች መፍቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በምክክር ሂደቱ የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበው ልዩነቶችን በምክክር በማቀራረብ ወደ የጋራ መግባባት መምጣት ተችሏል ብለዋል።   ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብን በመወከል የተመካከሩት መቶ አለቃ ዘለቀ ጮቅሬ፤ ምክክሩ የሀገሪቱን ሰላምና አንድነት ዘላቂ በማድረግ ለሁለንተናዊ ዕድገት የሚያግዝ ሂደት እንደነበር ገልጸዋል። በምክክር ጉባኤው የልዩነት ምንጭ በነበሩ አጀንዳዎችና ኢትዮጵያ ወደፊት በሰላም እንዴት መቀጠል እንዳለባት በሰፊው መመካከራቸውንም አክለዋል። በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግና ሰላሟንና ልማቷን በዘላቂነት ማስቀጠል የሚያስችል ግልጽና አሳታፊ ምክክር አድርገናል ብለዋል።   ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕናን የወከሉት ተመካካሪ ጌታቸው ዮሐንስ በበኩላቸው፣ ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የተስፋ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ገልጸዋል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ሂደት ኢትዮጵያውያን ስለሀገራቸው የወደፊት አቅጣጫ በመመካከር፣ ችግሮቻቸውን ግልጽና አሳታፊ በሆነ መልኩ በማንሳት መፍትሔ የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀረቡበት መሆኑን ጠቁመዋል። በምክክሩ የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ለቀጣይ ሀገራዊ ሥራዎች ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆኑ ጠቁመዋል። መንግሥትም ምክረ ሀሳቦቹን እንደግብዓት በመጠቀም የሕዝቦችን አንድነት የሚያጎለብቱና ለጋራ ራዕይ የሚያነሳሱ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተመካካሪው ገልጸዋል።  

ማህበራዊ
በዞኑ በማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት የተሰባሰቡ የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች እየተሰራጩ ነው
Aug 26, 2026 293
ደብረ ብርሃን፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በክረምት የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት የተሰባሰቡ 75 ሺህ ደርዘን ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ“ በሚል መሪ ሀሳብ በበጎ ፈቃደኞች የተሰባሰቡ የትምህርት ቁሳቁስ ወላጆቻቸው አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች እየተሰራጨ ነው።   የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በማቃለል በኩል ጉልህ አስተዋጾ እያደረገ ነው።   በተያዘው ክረምትም በዞኑ 985 ሺህ 759 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ ትምህርት፣ ግብርናና ጤናን ጨምሮ በ17 የሥራ ዘርፎች የማህበራዊ መደጋገፍን የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። የመንግስት ሠራተኞች ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ውጤታማ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ በበኩላቸው እንዳሉት በዞኑ በ2019 የትምህርት ዘመን 612 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ሥራ ተጀምሯል።   ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ በማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት 75 ሺህ ደርዘን ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሶችን በማሰባሰብ የማሰራጨት ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል። በዛሬው ዕለትም ለ1 ሺህ 255 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ደርዘን ደብተር እና 12 እስክርቢቶ በድጋፍ መሰጠቱን ነው የተናገሩት። የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑም አመልክተዋል። የደብተርና የእስክርቢቶ ድጋፍ ካገኙ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ወንጌላዊት ይልማ የተደረገላት ድጋፍ ለቤተሰቦቿ እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን ተናግራለች። ሌላው ተማሪ ኪሩቤል ንጋቱ በበኩሉ የተደረገለት ድጋፍ ለማህበረሰቡ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንደጨመረለት ገልጿል።
የሪፎርም ስራዎች የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲያድግ አስችለዋል
Aug 26, 2026 298
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ባለፉት ዓመታት የተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎች የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲያድግ ማስቻላቸውን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፉም ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት አራት ዓመታት የተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎችን በትኩረት አከናውኗል። ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል አቅርቦትን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማሸጋገር፣ የግዥ ሥርዓቱን ማዘመንና ግልጽ ማድረግ፣ የክምችትና ሥርጭት አሠራርን ማስተካከል እንዲሁም የምርቶች አቅርቦት ሰንሰለት ቅንጅትን ማጠናከር ይገኙበታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ሪፎርሙ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማስቻሉንም አመልክተዋል። በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አጠቃላይ የግዥና የክምችት ሥርዓቱን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ማዘመን መቻሉ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንደጨመረው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበሩ አሠራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀው ይህም የደንበኞችን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሳደጉ ባሻገር አሠራሩን ወጪ ቆጣቢ ማድረጉንም ገልጸዋል። ይህም በአገልግሎቱ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አህጉራዊ እውቅናም እያስገኘለት መሆኑን ጠቁመዋል። የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ ዕውቅና ያገኘ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፍ መቻሉንም አስታውቀዋል። ይህ ሽልማት አገልግሎቱ የሕክምና አቅርቦት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ለማስደገፍና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሠራቸው ስኬታማ ሥራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ እውቅና ወደፊት አገልግሎቱን አህጉራዊ ተወዳዳሪና ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትልቅ ብርታት እንደሚሆን አክለዋል።      
ኢትዮጵያ የጤና ሥርዓቱን በፋይናንስ በመደገፍ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በመጠንና በጥራት እያሳደገች ትገኛለች
Aug 26, 2026 399
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የጤና ሥርዓቱን በፋይናንስ በመደገፍ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በመጠንና በጥራት እያሳደገች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ። በአፍሪካ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ከአባል ሀገራት ጋር በትብብር ትሰራለችም ብለዋል። 76ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄዱን ቀጥሏል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ብቁና ሥነ ምግባር የተላበሰ የጤና ባለሙያ ማፍራት የሚያስችል ስትራቴጂ ገቢራዊ አድርጋለች። ኢትዮጵያ የጤና ሰራተኞች ስትራቴጂ ገቢራዊ በማድረግ የጤናውን ዘርፍ የሰው ኃይል አቅም ከ50 በመቶ በላይ ማሳደግ ችላለች ብለዋል። በዚህም በገጠርና ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ላሉ የጤና ሰራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠርና ድጋፍ በማድረግ እንዲበረታቱ መደረጉን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 የሚተገበረውን የአፍሪካ የጤና ሰራተኞች ስትራቴጂ በመደገፍ ለተግባራዊነቱ ከአባል ሀገራቱ ጋር በትብብር ትሰራለች ብለዋል። በአፍሪካ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው የጤና ሰራተኞች ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከሕብረቱ አባል ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።   በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሥርዓትና አገልግሎት ክላስተር ዳይሬክተር ዶክተር አደልሄድ ኦንያነጎ በበኩላቸው፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአፍሪካ የጤና ሰራተኞች ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅዕኖ ቢያሳድርም እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2017 በኋላ መሰረታዊ ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል። በአሕጉሪቱ ቀጣይና የጤና ዘርፍ ስትራቴጂዎችን፣ ፖሊሲዎችንና ዓለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂዎችን ገቢራዊ በማድረግ የአፍሪካን የጤና ሰራተኛ በ2013 ከነበት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በ2024 ወደ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ በባለሙያዎች ፍልሰት፣ በአካላዊ ጫናና ከሥራ በማቋረጥ ሳቢያ በጤናው ዘርፍ ላይ አደጋ እንዲደቀንበት ማድረጉ አልቀረም ብለዋል። በመሆኑም የጤና ሥርዓቱን ጠንካራና ዘላቂነት ያለው ለማድረግ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 የሚቆይ የአፍሪካ የጤና ሰራተኞች አጀንዳ ገቢራዊ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም እስከ 2035 ጠንካራ የጤና ተቋማትን ከመገንባት ባለፈ አሕጉሪቱ ቢያንስ ከ3 ሚሊዮን ያላነሰ ተጨማሪ የጤና ሰራተኛ ያስፈልጓታል ብለዋል። ይህን ግብ ለማሳካት ጠንካራ የአስተዳደር ሥርዓት መገንባት፣ የስልጠና ማዕከላት ማስፋፋት፣ የተጠያቂነትን ሥርዓት ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።    
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የገጠሩ ክፍል የአኗኗር ዘይቤ እንዲዘምን እያስቻሉ ነው
Aug 26, 2026 450
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እየጎለበቱ መምጣታቸው የገጠሩ የሀገራችን ክፍል የአኗኗር ዘይቤ እንዲዘምን እያስቻሉ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) ገለጹ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በጋራ በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ሸወዴ ቀበሌ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን በይፋ አስጀምረዋል።   የተቋማቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በምስራቅ ባሌ ዞን የሚገኘውን አስደናቂውን የሶፍ ዑመር ዋሻም ጎብኝተዋል፡፡ ተቋማቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ለመደገፍ ዓላማ አንግበው መነሳታቸው ተጠቁሟል። የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንደገለጹት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየጎለበቱ መምጣታቸው የገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል የአኗኗር ዘይቤ እንዲዘምን እያስቻሉ ነው። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልምድ እየዳበረ መምጣቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን ማጠናከሩንም አብራርተዋል። በከተማም ሆነ በገጠር የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለዚህ በአበይት ማሳያነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ ሁሉም በየተሰማራበት መስክ ህዝቡንና ሀገሩን በቀናነት ማገልግል እንደሚገባውም አስገንዝበዋል። ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር በዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ሸወዴ ቀበሌ የሚከናወኑ አጠቃላይ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ማከናወን ጀምረናል ብለዋል። ከበጎ ፈቃድ ተግባራት መካከል ከሀገራዊው የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተቀናጀ መልኩ 20 መኖሪያ ቤቶችና አንድ መዋለ ሕፃናት እንዲገነቡ የመሠረተ ድንጋይ መቀመጡን ጠቅሰው፤ ከሚገነቡት መኖሪያ ቤቶች መካከል አምስቱ ቤቶች በምስራቅ ባሌ ዞን አስተዳደር እንደሚገነቡም ገልጸዋል።   540 ለሚሆኑ ተማሪዎች ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንና የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር መከናወኑንም አክለዋል። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሀሰን በበኩላቸው፤ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ኮሚሽኑ እየተሳተፈ ይገኛል ብለዋል። ሁለንተናዊ ልማቷ የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማሻገር የበጎ ፈቃድ ተግባራት ወሳኝ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።   በመሆኑም ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በምስራቅ ባሌ ዞን ማከናወን ጀምረናል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ግስጋሴ ለማፋጠን የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።   የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጃርሶ ቦሩ በዞኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤት እድሳት፣ የትምህርት ተቋማት ግንባታ፣ ደም ልገሳ እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በተቋማቱ የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ነዋሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ በርካታ ፋይዳዎች እንዳሉትም ጨምረው ገልጸዋል።    
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም የቻይና ባለሀብቶችን ይበልጥ እየሳበ ነው-አምባሳደር ቼን ሃይ
Aug 26, 2026 293
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና እየተሻሻለ የመጣው የኢንቨስትመንት ከባቢ ይበልጥ የቻይና ባለሀብቶችን እየሳበ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ። አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ግዙፍና ፈጣን እድገት ካላቸው ኢኮኖሚዎች አንዷ መሆኗን ገልጸዋል። ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ የንግድ አጋሮችና ባለሀብቶች ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን እያቀረበች እንደምትገኝም አመልክተዋል። አምባሳደሩ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የከተሜነት መስፋፋት እና የግብርና ዘመናዊነት አሰራሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን አድንቀዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ ትስስር ለሀገራዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ከማበርከት ባለፈ፣ የማህበረሰቡ ኑሮ እንዲሻሻል መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አንስተዋል። ቻይናና ኢትዮጵያ ሀገራዊ ዕድገትና የመዘመን ራዕይን እውን ለማድረግ የጋራ የሆነ መሻት እንዳላቸውም አብራርተዋል። አምባሳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ በቆዩበት ጊዜ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምህዳርና የንግድ ከባቢ ላይ ግልጽ ለውጦች እንደተመለከቱም ተናግረዋል። በዚህም የቻይና ባለሀብቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ አዳዲስ ፋብሪካዎችና ማምረቻዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን አንስተዋል። የኢንቨስትመንት ከባቢው እንዲሻሻል በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የተደረጉ ማሻሻያዎች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፣ እነዚህ እርምጃዎች ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንዳስቻሉም አክለዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እየሰፋ መሄዱን፣ በተለይም የቻይና ሸማቾች ለኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። እንደ ቡናና ሰሊጥ ያሉ የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች በቻይና ገበያ ያላቸው ተወዳጅነት ማደጉን ጠቅሰው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የኢንዱስትሪና እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችም ጭምር በቻይናውያን ሸማቾች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት እያገኙ መምጣታቸውን አመልክተዋል። አምባሳደሩ በቻይና ንግድ ተቋማትና በኢትዮጵያ መንግሥት አካላት መካከል በቀጣይ የሚኖረው ትብብር የሀገሪቱን የንግድ ምህዳር ይበልጥ እንደሚያጠናክረውና ለንግድና ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የንግድና ኢንቨስትመንት ጠንካራ ትብብር የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከማፋጠን ባለፈ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ እንደሚያጎለብተውም ተናግረዋል። የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት (all-weather strategic partnership) ደረጃ ከፍ ማለት፣ የሁለቱን ሀገራት ለሰፊ ትብብርና ለጋራ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይና የቻይና-አፍሪካን የኢኮኖሚ ግንኙነት አጠቃላይ ፋይዳ አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በሰሜን ጎንደር ዞን 29 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል ለምቷል
Aug 26, 2026 362
ጎንደር ፤ነሐሴ 20 /2018 (ኢዜአ)፡- በሰሜን ጎንደር ዞን በያዝነው ክረምት 29 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬትን በስንዴ ሰብል መሸፈን መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ፋሲካ መርሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የስንዴ ልማቱን በማስፋት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓትና ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት እየተቻለ ነው፡ በ2018/19 የመኸር ምርት ዘመንም 35 ሺህ 290 ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል በማልማት ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። እስካሁን በተደረገ ጥረትም 29 ሺህ 439 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን የአረምና የተባይ መከላከል ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንዲሁም ምርጥ ዘር በአግባቡ እንዲጠቀም በማድረግ፣ ምርታማነቱን በሄክታር በአማካይ 31 ኩንታል ለማድረስ እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል። በተጨማሪም በመካናይዜሽን በመታገዝ በኩታ ገጠምና በመስመር አሠራር በመዝራት የታቀደውን ምርት ለመሰብሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። የዘር ሥራው አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው፤ ይህም የታቀደውን መሬት ሙሉ በሙሉ ለማልማት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። በዞኑ በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን በአጠቃላይ ከ156 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት እየተሠራ እንደሚገኝ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በጋምቤላ ክልል የልማት አቅሞችን ለይቶ ተግባራዊ የማድረግ ስራ ቀዳሚ ትኩረት ይሰጠዋል-ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Aug 26, 2026 94
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 20/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የጋምቤላ ክልል ሕዝብን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል በየዘርፉ ያሉ የልማት አቅሞችን አውጥቶ ተግባራዊ የማድረግ ስራ ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሰጠው ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በጋምቤላ ክልል በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች በአዲሱ በጀት ዓመት ለሚያስፈጽማቸው የልማት ስራዎች የሚሆን ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በክልሉ ስቲሪንግ ኮሚቴ አጽድቋል።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ወደ ክልሉ የሚመጡ አጋዥ የልማት ፕሮጀክቶችን ከልማት እቅዶች ጋር አጣጥሞ በመተግበር የህዝቡን ህይወት ለመለወጥ በትኩረት መስራት ይገባል። በክልሉ እየተተገበረ ያለው የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረጉንም ገልጸዋል። አክለውም በዘንድሮው በጀት ዓመት በትምህርት፣ በግብርና፣ በመንገድና በሌሎች የኑሮ ማሻሻያ ዘርፎች የታቀዱት ስራዎች የህዝቡን ህይወት ሊያሻሽሉ የሚችሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። ለፕሮጀክቶቹ ስኬታማነት የስትሪንግ ኮሚቴውና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ፣ ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ሊጎለብት እንደሚገባ አመልክተው ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የፕሮጀክቱ የጋምቤላ ክልል አስተባባሪ ዶክተር ቤል ቢቾክ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚለውጡ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል። በዘንድሮው በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ተግባራትን ለማከናወን ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ወደ ተግባር ምዕራፍ መግባቱን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ 35 የትምህርት ቤት፣ የእንስሳት ጤና ኬላ፣ የመንገድ ግንባታና ዲዛይን እንዲሁም ሌሎች የህዝቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል። ለእነዚሁ ተግባራት ስኬትም የባለድርሻ አካላትን ድጋፍና ትብብር እንደሚያስፈለግ ነው የተናገሩት። የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ስር በሰባት ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 120 ወረዳዎች የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እየተተገበረ የሚገኝ መሆኑ መረጃ ያመለክታሉ ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ልማትን ለማቀላጠፍ ቅንጅታዊ ሥራ ተግባራዊ ተደርጓል
Aug 26, 2026 102
ድሬዳዋ፣ነሐሴ 20/2018(ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢን በአግባቡ ሰብስቦ ልማትን ለማቀላጠፍ ቅንጅታዊ ሥራ ተግባራዊ መደረጉን የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልሰላም መሐመድ (ዶ/ር) ተናገሩ ። በዘንድሮ በጀት ዓመት በአስተዳደሩ 15 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቅንጅታዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው ተመላክቷል።   የድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልሰላም መሐመድ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ አስተዳደሩ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ የግብር ከፋዮችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ በቴክኖሎጂ ታግዘው ግብራቸውን በመክፈል ግዜና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ እያደረገ ነው። የከተማዋ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች 15 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ሥራው ተጀምሯል ብለዋል። ስራውንም በንቅናቄ በመምራት ሐምሌ ወር ብቻ ከ934 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ890 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቁመዋል። በእዚህም የዕቅዱን ከ95 በመቶ በላይ ለማሳካት እንደተቻለና ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ685 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል። በሚሰበሰብ ገቢም የህዝብ የመንገድ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የአነስተኛ መስኖ አውታሮች፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በማስፋፋት የነዋሪውን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ይሰራል ብለዋል።   በድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን ግብራቸውን በመክፈል ላይ ከነበሩት መካከል ወይዘሮ ሂዩስቲና ስዩም እና አቶ ዮሴፍ አለባቸው ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በባለስልጣኑ የተዘረጋው ቀልጣፋ አገልግሎት ግብራቸውን በወቅቱ ለመክፈል አግዟቸዋል።   የሚከፍሉት ግብር ለድሬዳዋ ዕድገት እና ለነዋሪው ተጠቃሚነት እንደሚውል በማመን ግብራቸውን በወቅቱና በታማኝነት መክፈላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ያመጣቻቸውን ለውጦች ለሀገራት አካፈለች
Aug 26, 2026 117
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለተሻለ የህክምና ውሳኔ አሰጣጥ በመጠቀም ያመጣቻቸውን ለውጦች ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈል መቻሏን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ። ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለተሻለ የህክምና ውሳኔ አሰጣጥ በሰፊው እየተጠቀመች መሆኑንም ገልጸዋል። በአምስት የጤና ዘርፍ ምሰሶዎች ላይ በማተኮር ለአራት ቀናት የሚቆየው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። የመድረኩ ዋና ዋና የጤና ምሰሶዎች ዘላቂ የጤና ፋይናንስና የዲጂታል ጤና ሥርዓት፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና የሀገር ውስጥ ምርቶች አቅም ማሳደግ ናቸው። በዛሬው እለትም የጉባኤው አካል የሆነ በጤናው ዘርፍ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚና በሚል በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በርካታ የዲጂታላይዜሽንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶችን እየተጠቀመች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ለህክምና ውሳኔ አሰጣጥ ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ የወረቀት አሰራሮች በዲጂታል መተካታቸውን ገልጸው በመድረኩ ኢትዮጵያ ተሞክሮዋን አካፍላለች ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ የጤና ኤክስቴንሽን ፐሮግራም እየተገበረች መሆኑንና ይህንንም ተሞክሮ ማካፈሏን ጠቁመዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በአምስት ቋንቋ ከአንድ መቶ በላይ መመሪያዎችን ባለሙያዎች በስልክ እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በራስ የሚሰሩ እና የሚተዳደሩ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ማዋሏን አንስተው ለረጅም ጊዜ በተበታተነ መንገድ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ሲስተሞች ወደ አንድ ማምጣት መቻሉንም አክለዋል። በዚህም በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡንና አገልግሎት አሰጣጡንም ማቀላጠፉን ሚኒስትር ዴኤታዋ ጨምረው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ አገልግሎት ላይ የዋሉ የዲጂታላይዜሽንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች በህክምና ውሳኔ አሰጣጥ ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽአ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። እነዚህ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች በዘርፉ የተጠቃለሉ መረጃዎችን ለውሳኔ ሰጭ አካላት ማቅረብ እያስቻሉ መሆኑንና አጠቃላይ በጤና ስርዓቱ ላይ ትልቅ አቅም እየፈጠሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል።  
የመድሀኒትና ህክምና መሣሪያዎች አቅርቦት አገልግሎት ዲጂታል ሪፎርም እውቅና አገኘ
Aug 26, 2026 211
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦‎የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ለሀገሪቱ የመድሀኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ እውቅና ማግኘቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ገለጹ። አገልግሎቱ በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፉም ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት አራት ዓመታት በተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎች በትኩረት አከናውኗል። ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል አቅርቦትን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማሸጋገር፣ የግዥ ሥርዓቱን ማዘመንና ግልጽ ማድረግ፣ የክምችትና ሥርጭት አሠራርን ማስተካከል እንዲሁም የምርቶች አቅርቦት ሰንሰለት ቅንጅትን ማጠናከር ይገኙበታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ሪፎርሙ የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማስቻሉንም አመልክተዋል። በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አጠቃላይ የግዥና የክምችት ሥርዓቱን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ማዘመን መቻሉ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንደጨመረው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበሩ አሠራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀው ይህም የደንበኞችን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሳደጉ ባሻገር አሠራሩን ወጪ ቆጣቢ ማድረጉንም ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ይህ በአገልግሎቱ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አህጉራዊ እውቅናም እያስገኘለት መሆኑን ጠቁመዋል። የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ ዕውቅና ያገኘ ሲሆን በቅርቡም በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፍ መቻሉንም አስታውቀዋል። ይህ ሽልማት አገልግሎቱ የሕክምና አቅርቦት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ለማስደገፍና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሠራቸው ስኬታማ ሥራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ እውቅና ወደፊት አገልግሎቱን አህጉራዊ ተወዳዳሪና ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትልቅ ብርታት እንደሚሆን አክለዋል።  
የመደመር መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ቴክኖሎጂን እንደ ቁልፍ መሣሪያ በመጠቀም እመርታዊ ለውጦችን እያመጣ ይገኛል
Aug 26, 2026 131
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ቴክኖሎጂን እንደ ቁልፍ መሣሪያ በመጠቀም እመርታዊ ለውጦችን እያመጣ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣የዜጎችን እንግልት በመቀነስና የመንግሥት አሰራርን በማዘመን ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አሰራርን በአንድ ቦታ ላይ በማቅረብ፣ዜጎች የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች በአንድ ቦታ ፈጣን፣ጥራት ያለውና ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲያገኙ አድርጓል። ይህም የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ከማሳለጡ ባለፈ፣ አጠቃላይ አሰራሩን ግልጽ በማድረግ ብልሹ አሰራርን በከፍተኛ ሁኔታ መከላከል ችሏል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ አለማየሁ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ በሂደት መቀየርና መሻሻል የሚገባው ትልቅ ክፍተት በመሆኑ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መቋቋሙን ገልጸዋል። አገልግሎቶቹን ዲጂታላይዝድ ከማድረግ ባሻገር ተበታትነው የሚገኙ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የተሳለጠ እና ውጤታማ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ማዕከሉ የተበታተኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን አቀናጅቶ ለዜጎች በአንድ ማዕከል መስጠት ሲሆን ይህም ስኬታማ ነበር ብለዋል። አገልግሎቶቹን በማቀናጀት ብቻ ሳይወሰን ለዜጎች የሚሰጠው አገልግሎት እርካታን የሚያመጣ እንዲሆን ማድረግ ሌላው የማዕከሉ ዋና ዓላማ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ረገድም ውጤታማ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ110 በላይ ማዕከላት መድረሱንና እስካሁን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን ጠቅሰዋል። የዜጎችን የአገልግሎት ፍላጎት በፍጥነትና በቅልጥፍና ለማሟላት የተለያዩ የአገልግሎት ሞዳሊቲዎችን ተግባራዊ እያደረገ እንዳለም ገልጸዋል። በአካል ወደ ማዕከሉ መምጣት የማይችሉ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ የሞባይልና የተንቀሳቃሽ አገልግሎት መጀመሩን ጠቁመዋል። በዚህም በፌደራል ደረጃ ሁለት እና በአዲስ አበባ ከተማ አንድ በድምሩ ሦስት ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎቶች ሥራ መጀመራቸውን ጠቅሰዋል። በተጨማሪ የኦንላይን አገልግሎትና የአፕሊኬሽን ሞዳሊቲዎችን በመጠቀም አገልግሎቶችን እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለቀጣዩ የዲጂታል ሽግግር ጠንካራ መሠረት ጥሏል–ምሁራን
Aug 26, 2026 217
ጅማ፤ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ለሀገሪቱ ቀጣይ የዲጂታል ሽግግር ጠንካራ መሠረት መጣሉን የጅማ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን አስታወቁ። የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንጆቹ 2020 ይፋ ያደረገው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠንና አገልግሎቶችን ዘመናዊ ለማድረግ የተነደፈ ብሔራዊ መርሃ-ግብር ነው። ስትራቴጂው በተለይም በግብርና፣በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ነበር። ምሁራኑ በ2025 የተከናወነው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ምዕራፍ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበትና በውጤታማነት የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል። በዋና ዋና ስኬትነት ከተጠቀሱት መካከል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስፋፋት፣ የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ፣የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ-መረብ መስጠት እና ለሚሊዮኖች የተሰጠው የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እንደሚገኙበት ምሁራኑ ጠቁመዋል። በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሜካኒካል ትምህርት ክፍል መምህር ሸዋንግዛው ወርቃገኘሁ፤የአገሪቱ የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ በስፋት እያደገ መምጣቱን ገልጸው፣ በርካታ ስኬቶች ከመመዝገባቸው ባለፈ በርካታ የዘርፉን ባለሙያዎች ማፍራት መቻሉን ጠቁመዋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት በተለያዩ ተቋማት የመረጃ አያያዝን ከማዘመኑ ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን ማቀላጠፉን አብራርተዋል። ይህም ዜጎች አገልግሎቶችን ያለ እንግልት እንዲያገኙ፣ እንዲሁም ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ እያስቻላቸው መሆኑን አስረድተዋል። በተለይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአገልግሎት አሰጣጥና በመልካም አስተዳደር በኩል የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል። የዲጂታል አገልግሎቶች የግልጽነት መርህን በማጠናከር ሙስናን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ዳይሬክተር ኢንጂነር ጃርሚያ ባይሳ ናቸው። ተቋማት መዘመናቸውና መገንባታቸው፣የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መስፋፋቱ፣ እንዲሁም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከምዝገባ ጀምሮ የመረጃ አያያዙ ዘመናዊና ስኬታማ መሆኑ የዲጂታል ሽግግሩ አበይት ውጤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። ሆኖም የተመዘገቡት ስኬቶች በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ በቀጣይ ይበልጥ መጠናከር እንዳለባቸው ኢንጂነር ጃርሚያ አስገንዝበዋል። በተለይም ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ከግብ እንዲደርስ የተጀመሩ የዲጂታል ልማት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ማስፋፋት፣እንደ ኢትዮ-ኮደርስ ያሉ የቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን ማጠናከር እና በዘርፉ በርካታ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት ለቀጣዩ የዲጂታል ሽግግር ስኬት ወሳኝ መሆኑን ኢንጂነር ጃርሚያ ተናግረዋል። የበለጸጉ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማጠናከር ከተጠቀሙባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የግል ተቋማት ቴክኖሎጂን በመጠቀምና በማስፋፋት ረገድ ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ መሆኑን የጠቀሱት ምሁሩ፤መንግሥትም የግል ተቋማትን በዘርፉ የማሳተፍ ሥራውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አክለው ገልጸዋል።
ስፖርት
ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት ሲፈልገው የነበረውን ካርሎስ ባሌባን አስፈረመ
Aug 25, 2026 288
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ዩናይትድ የካሜሮኑን አማካይ ካርሎስ ባሌባን ከብራይተን በ70 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን ዛሬ አስታውቋል። የ22 ዓመቱ ተጫዋች በኦልድ ትራፎርድ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት የተፈራረመ ሲሆን፣ እስከ እ.አ.አ 2031 በሚቆየው በዚህ ውል ላይ የክለቡ ተጨማሪ የ12 ወራት የማራዘም አማራጭ ተካቷል። ባሌባ ወደ አዲሱ ክለቡ መቀላቀሉን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፣ ለረጅም ጊዜ ለመቀላቀል ሳልመው በነበረው ማንችስተር ዩናይትድ መፈረም በመቻሌ ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል ብሏል። ከአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ጋር በመስራት እና የእሱን ልምድ በመጠቀም ብቃቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚፈልግም ገልጿል። ባሌባ በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር በክረምቱ የዝውውር መስኮት የፈረመ ሶስተኛው የአማካይ ተጫዋች ሆኗል። ዩናይትድ ቀደም ሲል አንድሬ ሳንቶስን ከቼልሲ በ48 ሚሊዮን ፓውንድ እና ዩሪ ቲሊማንስን ከአስቶንቪላ በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙ ይታወቃል።
ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል
Aug 24, 2026 314
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ቼልሲ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፏል። ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ኮል ፓልመር የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ጆአኦ ፔድሮ በ31ኛው ሴኮንድ ያስቆጠረው የዓመቱ ፈጣን ጎል ሆኖ ተመዝግቧል። ጆሹዋ ኪንግ እና ጎንዛሎ ጋርሺያ የፉልሃምን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ከአስቶንቪላ ወደ ቼልሲ የተዘዋወረው ሞርጋን ሮጀርስ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታው ጎል አስቆጥሯል። ከሪያል ማድሪድ ፉልሃምን የተቀላቀለው ጎንዛሎ ጋርሺያም የመጀመሪያ የሊግ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ጨዋታው እጅግ አዝናኝና በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ነበር። የቼልሲው አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ቀንቶታል። በአንጻሩ አዲሱ የፉልሃም አዲሱ አሰልጣኝ አርቫሎ አርቤሎአ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግዷል። ጨዋታውን ተከትሎ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል። የሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ከአርብ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ሽንፈትን አስተናገደ
Aug 24, 2026 190
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት መርሐ ግብር የዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አግነስ ናቡኬንያ በ11ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ግቧን አስቆጥራለች። በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽንፈቱን ተከትሎ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ እድሉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ንግድ ባንክ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታው የጅቡቲውን ኡጄኮን 11 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስን በኡጄኮ መሸነፍ ይኖርበታል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ረቡዕ ነሐሴ 2018 ዓ.ም በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይካሄዳል። ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ በጨዋታው ካሸነፈ ወይም አቻ ከወጣ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያልፋል። የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ላይ 10 ክለቦች በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድሩን ያሸነፈው ክለብ ዞኑን ወክሎ በሻምፒዮንስ ሊጉ መሳተፉን ያረጋግጣል። የሴካፋ ማጣሪያ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 26, 2026 377
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ የተከናወኑ ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ እውን ለማድረግ በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት የተገነቡ የተቀናጁ የትራንስፖርት ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎችና የንግድ ማዕከላት ምረቃ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።   ከተማ አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት የሚያገኝባቸውን በርካታ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል። ዛሬው ለምረቃ የበቁት የታክሲና የአውቶቡስ አገልግሎት ትራንስፖርት የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ዐረፍ ብሎ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ የጀመረችውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎች መካተታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎች ከነሙሉ አገልግሎታቸው ተዘጋጅተው ለሕዝብ ጥቅም ክፍት ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ከመመለስ ባሻገር የአካባቢ ጥበቃን ያማከሉ አረንጓዴ የትራንስፖርት አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡ በዚህም በመዲናዋ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለመገንባት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ከተማዋ ወደ አረንጓዴ ትራንስፖርት የምታደርገውን ሽግግር ያፋጥናሉ ብለዋል፡፡   በአሁኑ ወቅት የህዝብ ትራንስፖርትንና የግል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የመኪና ማቆሚያ አቅም ከ180 ሺህ በላይ መድረሱን ከንቲባዋ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ በእነዚህ የትራንስፖርትና የመኪና ማቆሚያ መሰረተ ልማቶች ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ብቻ እስከ አሁን ከ20 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማሪያም በበኩላቸው፤ ቢሮው ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፍጥነትና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡ መሰረተ ልማቶቹ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፉና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በውስጣቸው የንግድ ሱቆች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ አሳንሰሮችና የቲኬት መቆረጫ ቢሮዎች እንደተገነባላቸውም ገልጸዋል።      
በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ጥበቃ ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያገዙ  ነው
Aug 24, 2026 249
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ጥበቃ ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያገዙ እንደሚገኙ የክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት አስታወቀ። በክልሉ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የካርበን ሽያጭ በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተገልጿል። የኦሮሚያ ክልል ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አራርሳ ረጋሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ክልሉ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በተለይም የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን በመቀነስ የምድር ሙቀትን ለመግታትና የደን ሽፋን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመላክተዋል።   በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉት ችግኞች መካከል አብዛኞቹ ጸድቀው ወደ ደንነት በመሸጋገራቸው የአካባቢውን አየር ንብረት በመጠበቅና የካርቦን ልቀትን በመቀነስ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበሩከቱ ይገኛሉ ብለዋል። ህብረተሰቡም ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ዘላቂ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር ተዘርግቶ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም አቅምን የማጠናከሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። አቶ አራርሳ ጨምረው እንደገለጹት፤ ክልሉ የደን ካርበን ንግድን በማስፋፋት በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በተደረገው ሳይንሳዊ ጥናት መሠረት አንድ ሄክታር የደን መሬት ከ10 እስከ 20 ቶን የሚደርስ ካርቦን ዳይኦክሳይድ በውስጡ የመያዝ እና የማመቅ ከፍተኛ አቅም እንዳለው አብራርተዋል። ይህም ክልሉ የሚያካሂደው የደን ልማት ለአለም አቀፉ የካርቦን ልቀት ቅነሳ ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሆነ አብራርተዋል። አቶ አራርሳ ኢትዮጵያ ከካርቦን ገበያ ገቢ ማግኘት የጀመረችበትን ታሪካዊ ሂደት ሲያብራሩ፤ የመጀመሪያው የደን ካርበን ሽያጭ እ.ኤ.አ በ2012 በባሌ ደን መጀመሩን አውስተዋል። እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥም 9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን ለገበያ በማቅረብ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል።   ከሽያጩ የተገኘው ገቢም ደኑን ለጠበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ለቀጣይ የደን ልማት ስራዎች በመዋሉ የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። ድርጅቱም ከአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር በመቀናጀት እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት የተመዘገበውን 13 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የካርቦን መጠን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጁ ሆኗል። በቀጣይም የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን በሳይንሳዊ መንገድ በመንከባከብና የካርቦን ንግድን በመተግበር የአካባቢ ጥበቃውን እንዲሁም ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን የማሳደግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።    
ውበትን ከስልጣኔ ጋር ያቆራኙ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች
Aug 23, 2026 278
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በኮሪደር እና በወንዝ ዳር ልማቶች የተገነቡት ቤተ መጽሐፍት እና የተለያዩ የመዝናኛ ስፈራዎች ለመጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋን የሰነቁ የስልጣኔ ማሳያዎች መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መዲናዋን ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ዘመናዊ ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘው ግዙፍ የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። ይህ በዋና ዋና አደባባዮች፣ መናፈሻዎች፣ መንገዶችና የወንዝ ዳርቻዎች ላይ ያተኮረው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፤ ውበትን ከጥቅም ጋር አዋህዶ የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ለውጦችን እያመጣ ነው። ኢዜአ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሉት፤ የተገነቡት የመጫወቻና የማንበቢያ ስፍራዎች የከተሜነት ምህዳሩን ከማሻሻላቸው ባሻገር ለወጣቶች የማሰላሰያና አዳዲስ ሐሳቦችን ማፍለቂያ ማዕከላት እየሆኑ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ጺዮን ጌታቸው፤ በቅርብ ዓመታት የተከናወኑት የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች አዲስ አበባን ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጋቸው ባሻገር፣ ነዋሪው አእምሮውን እያዝናና እውቀት እንዲገበይበት መንገድ መክፈታቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ግርማ አለሙ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቶቹ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉና ለአዲሱ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይም የተዘጋጁት የንባብ ማዕከላት ለተለያዩ ጥናትና ምርምሮች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ተናግረዋል።   የመዲናዋ ነዋሪ ወጣት ፍራኦል ናትናኤል በበኩሉ የኮሪደር ልማቱ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በመገንባት በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብሏል።   ይህም ለአገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጿል።   አቶ እንዲሪስ ተሾመ እና አቶ ግርማ ንጉሴ የተባሉ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ የመዝናኛ ስፍራዎች ተገንብተዋል ብለዋል። አሁን ላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የእረፍት ጊዜ ለማሳለፍ እነዚህን አካባቢዎች ምርጫቸው ማድረጋቸውን ተናግረዋል።   የወንዝ ዳርቻ ልማቶቹ፣ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍትና የመዝናኛ ስፍራዎቹ የከተማዋን ውበትና የህዝቡን የማህበራዊ ህይወት ደረጃ ያሳደጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።    
አካባቢን ከብክለት በመጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራቱ ተግባር ይጠናከራል
Aug 21, 2026 364
ገንዳውሃ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ህብረተሰቡ አካባቢውን ከብክለት በመጠበቅና በማፅዳት ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራት ተግባርን አጠናክሮ እንዲቀጥል የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የሀገራዊ እንቅስቃሴ አካል የሆነ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ ተካሄዷል።   የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መልካም ዋሲሁን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ፅዱና ውብ አካባቢን መፍጠር ለጤናማ ማኅበረሰብ ግንባታ መሠረት ነው። አካባቢን ከፕላስቲክና ከሌሎች ደረቅ እንዲሁም ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ በማድረግ ፅዱ አካባቢን መፍጠር አምራች፣ ጤናማና ውጤታማ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ለዚህም ማኅበረሰቡ የአካባቢ ፅዳት ሥራን የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳያደርግ የዘወትር ተግባርና የኑሮ ባህሉ በማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጉርባ በበኩላቸው፣ ከአካባቢ ንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሕብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንፅህና ዘወትር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል። አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ እንደ ወባ፣ ኮሌራና መሰል ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ የግልና የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ ባህል ሊደረግ ይገባል ነው ያሉት። የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ አዳነ ሀሰን እንዳሉት፣ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ለባለሀብቶች ሳቢ ለማድረግ በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብና የወጣት አደረጃጀቶች አካባቢያቸውን ሰላም ከመጠበቅ ጎን ለጎን ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። "ለነገው ሀገር ተረካቢ ሕፃናት ፅዱ ከተማን ማስረከብ የእኛ የወጣቶች ኃላፊነት ነው" ያለው ደግሞ በፅዳት ዘመቻው የተሳተፈው ወጣት ሃብታሙ አክሊሉ ነው። ከተማዋን ከፕላስቲክና ከሌሎች መርዛማ ኬሚካሎች በማፅዳት ማራኪና ለነዋሪዎቿ የምትመች ተመራጭ ከተማ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት በቀጣይም የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል። በፅዳት ዘመቻው የከተማዋ የመንገድ ዳርቻዎች፣ የገበያ ስፍራዎችና የሕዝብ መዝናኛ አካባቢዎችን ከቆሻሻ ፅዱ የማድረግ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ በየሳምንቱም የፅዳት ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል። በተካሄደው የፅዳት ዘመቻም የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1287
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1049
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1324
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1912
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 332
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል።   ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች።   ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል።   ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 346
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 554
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ
Aug 19, 2026 454
ቡሄ በወርሃ ነሐሴ በ13ኛው ቀን ህፃናት ሆያ…. ሆዬ….! ሆ…. በሚል ዜማና ጅራፍ እያጮሁ የሚያከብሩት፤ እናቶች ለህፃናቱ ሙል ሙል ዳቦ በመስጠት እንኳን አደረሳችሁ እያሉ በድምቀት የሚያከብሩት በዓል ነው። ቡሄ ትርጓሜውም ብርሃን፣ብራ፣ ወጋግን ማለት ሲሆን ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገሪያ የተስፋ ምልክት ነው። በሀይማኖታዊ አንድምታው በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ብርሃን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ መገለጡ የሚታሰብበት ነው፤ በዚህም ደብረ ታቦር ይባላል፡፡ የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ የብርሃን ወጋገን የሚታይበት ሕፃናትና ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ «ሆያ ሆዬ» በማለት በረከትና ምርቃት የሚያፍሱበት የደስታና የፍቅር መግለጫ ነው። ህፃናትና ወጣቶች በየዕድሜያቸው ጅራፍ እያጮሁ በሕብረ ዝማሬዎች እየደመቁ በአብሮነት እና በደስታ የሚያከብሩት ትውፊታዊ በዓል ነው ቡሄ። የወጣቶችን ጉርብትና እና ማኅበራዊ ትስስር የሚያጎለብት እሴት ነው፤ በአከባበሩ ወቅት የሚንጸባረቀው የመረዳዳትና ያለውን የመካፈል ባህል ፋይዳውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሸጋገር ያስችላል። የቡሄ በዓል ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅ፣ ትውልድን በማቀራረብ እና ማኅበራዊ ትስስርን ይበልጥ በሚያጠናክር ተምሳሌትነቱ እልፍ ነው። በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከፍተኛ የቅርስ ጥናት ተመራማሪ መምህር መክብብ ገብረማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ የቡሄ በዓል የብርሃን ዘመን መምጣቱን የተስፋ ጎህ መቅደዱን ማብሰሪያ ነው፡፡ ቡሄ ከጨለማ ወደ ብርሃን ሽግግር መምጣቱን የሚያበስር በታዳጊዎች የሚዘከር የፍቅር፣ የአንድነትና የበረከት መገለጫና ተስፋ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ታዳጊዎችና ወጣቶች በበዓሉ ወቅት የሚያዜሙት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የ«ሆያ ሆዬ» ሕብረ ዜማ ለጋራ ትርክት ግንባታ ገንቢ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ በመሆኑ ማኅበራዊ ትስስርና የጋራ ዕሴቶችን ማጠናከር ያስችላል ብለዋል።   ታዳጊው በሱፈቃድ አስሜ ቡሄ ከጓደኞቹ እና ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክርበት የደስታና የተስፋ በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ ቡሄ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠብቀውና ቀጣይ ሕይወቱን በአዲስ መንፈስ ለመምራት አቅም የሚፈጥርለት የብሩህ ዘመናትን ማለሚያ መሆኑን ይገልፃል። ቡሄ ከታላላቆቹ የወረሰው ከእኩዮቹ ጋር በፍቅርና በደስታ የሚያከብረው ነገን በተስፋ የሚያይበት ውብ በዓል እንደሆነ የሚናገረው ደግሞ ታዳጊው በረከት ምናለ ነው፡፡   የተጣሉ ጓደኛሞች እርቅ የሚያወርዱበት በዓል በመሆኑ ለትውልድ አንድነት እና አብሮነትን በማስተማር ረገድ ትልቅ ድርሻ አለውም ብሏል። ወጣት ያብስራ ጸጋዬ በበኩሉ ቡሄ በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጣ፤ ተራርቀው ከሚኖሩ የተለያዩ አካባቢ እኩዮቹ ጋር በአንድነት የሚያከብሩት በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡   ከሁሉም ዓይነት ሕብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ታዳጊዎች የሚሰባሰቡበት፤ ሕብረ ብሔራዊነትን የሚያጠናክር የጋራ በዓል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ በኃይሉ ሞገስ ናቸው።      
ትንታኔዎች
ፕሬዝዳንቱ የገለጹት የኢትዮጵያ እውነት
Aug 26, 2026 437
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሔድ የቆየው የሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ማጠቃለያ በስኬት ማለቁ ተበስሯል። የውጭና የሃገራት እንግዶች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶች ኮሚሽነሮችና ተመካካሪዎች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቱ ያሰሙት ድምጽ ጆሮ ገብ ነበር። የሁሉንም ትኩረት የሳበ። ለመሆኑ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምን ብለው ነበር? በዚህ ንግግራቸውስ ምን መልዕክት አስተላለፉ? የሀገራዊ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ የማይታወቀውና ያልተለመደው የሆነበት ነው ። ይህ ምከክር ልዩነቶችን ከምክክር ይልቅ በኃይል ለመፍታት የመሞከር አባዜም ወደ ታሪክነት መሸጋገሪያው ነው ። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተረክ /political discourse/ ውስጥ በዘፈቀደ ሲገለጹ የሚሰሙት “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ፣ “ኢትዮጵያ ልትበተን ነው” ፣ “ኢትዮጵያ ልትፈርስ” ነው የሚሉና መሰል አገላለጾች የፖለቲከኞች እንጀራ መብያ እንጂ የኢትዮጵያ መንገድ መገለጫ እንዳልሆነ ያነሳሉ። ይልቁንም ኢትዮጵያን የማይገልጹና ከፍላጎታችን፣ ከሀገራዊ መሻቶቻችን ጋር አብረው የማይሄዱት እነዚህ አገላለጾች መነሻቸው ዝንታለም በሌሎች ሀሳብና ርዕይ የሚነግዱ የሀሳብ ተከታዮች እንጂ ኢትዮጵያውያን ፈጽሞ የሚናገሩት ቃል አይደለም ይላሉ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚሆነው መስቀለኛ ሳይሆን ቀጥ ያለ፣ ርቱዕ የእድገትና የህብረት መንገድ ብቻ መሆኑንም አስምረውበታል። ምክክር ማህበራዊ ባህላችን ውስጥ ያለንና የቆየ ሀብታችን ቢሆንም ይሄንን ነባር ባህል የፈተናዎቻችን መድህን የሀገር ግንባታችን ካስማ እንዲሆን መልክና ቅርጽ ተበጅቶለት ይፈጸም ዘንድ ቢያንስ በርሳቸው እድሜ እንደማያስታውሱ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የዚህን ሂደት ታሪካዊ ዋጋና ሀገራዊ ፋይዳ በማሰላሰል ለሀሳቡ እውንነት ለተጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ውጥንና ዓላማ ኢትዮጵያን ማዕከል በማድረግ ዘመንን ሊያሻግሩና ሀገርን ሊያጸኑ በሚችሉ የሀሳብ አውዶች ዙሪያ መወያየት እንደመሆኑም በመድረኩ የታየው ይሄው ነበር። በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎች፦ በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎችም መነሻቸው ይሄንኑ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ። የጋራ መሻትን ማጎልበት ቀዳሚው ሲሆን ልዩነቶችን በመሻገር የጋራ እጣፈንታንና ራዕይን የሚያጸና እውቀት የተንሸራሸረበት መድረክ መፍጠሩ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ምክክሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ስክነትና እርጋታ እንዲሸጋገሩ ያስቻለ፣ የፖለቲካ ውይይቱም ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ አስተዋይ በሆነ መንገድ እንዲመራም ያስቻለ መሆኑን ነው። ፕሬዝዳንቱ በሦስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ትልቁ ፋይዳ ደግሞ የይቅርታ እና የስርየት ጎዳና እንዲፈጠር መሰረት መጣሉ ሲሆን ከደመኝነት እና ከተቃርኖ ፖለቲካ በመውጣት በይቅርታና በመተሳሰብ የጋራ ጉዞን ለመቀጠል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ነው። የተለመደው የፖለቲካ ማጠንጠኛ ከሆነው ከአምባጓሮና ከነፍጥ በዘላቂነት በመላቀቅ የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላምና በመደማመጥ ላይ እንዲመሰረት ሃገራዊ ምክክሩ በር መክፈቱ በአራተኛነት ያነሱት ነጥብ ነው። ሌላኛው በአምስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳም በመከባበርና በሰመረ ቋንቋ፣ ከኃይለ ቃል በፀዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን ያሳየንም ነው። እንደ ሀገር ፈተና ባጋጠመን ጊዜ አንዳንድ ወዳጅ ሀገራት ከናንተ የተማርነው በህብረት ቆማችሁ ቀኝ ገዢዎችን ማንበርከክ ሆኖ ሳለ ለምን የውስጥ ጉዳያችሁን ለመፍታት ወደ ነፍጥ ታደላላችሁ? የሚል የወዳጅ ጥያቄ አዘውትሮ እንደሚቀርብም አንስተዋል። መንግስት የነበረ አካል ፣ ወደ ሽፍትነት የተለወጠበትን አጋጣሚ ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ውጥንቅጥ ችግር ሲያጋጥማቸው መቼውንም ቢሆን መውጫ መንገድ አጥተው እንደማያውቁም ጠቅሰዋል። ለዚህም ህልውናችንን የሚፈታተኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ሀገር እየጠበቅንም፣ እየመከርንም ኢትዮጵያችንን ማፅናት መቻላችን ነው ብለዋል። የዚህ መሰረቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ስልጣኔ፣ እውቀትና እውነትን አጋምዳ የያዘች በመሆኗ ችግር ሲያጋጥመን በጋራ ቆመን ጠላትን የምንመክተው የዳበረ፣ የጥንት ሀገር ስልጣኔ ባለቤት በመሆናችን ነው ይላሉ። እንደኛ የፖለቲካ እይታ ቢሆን ሌላ ድርሳን ነበረ። አጋምዶ የያዘን ግን አንዱ ጥንታዊ ሀገር ባለቤቶች በመሆናችን ነው። ሀገር ደግሞ የጋራ ላብ፣ የጋራ ደም፣ ተከሻና ጉልበት ውጤት ናት ሲሉም ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የውስጥ ችግር ባጋጠመን ወቅት፣ በአለም አቀፍ መድረክ እጅግ የማይመቹ ቃላት በኢትዮጵያ ላይ ተነጣጥረው እንደነበረ አንስተው የጋራችንን ሳይሆን የተወሰኑ የክፋት መንገድን የመረጡ ኃይሎችን ብቻ በመመልከት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ተበጥሷል፣ ወደነበረበት ለመመለስም ኢትዮጵያውያን ተስኗቸዋል በማለት ለማስተከዝ የሞከሩ እንደነበሩም አስታወሰዋል። አንዳንዶቹማ በዚህ ሀገራዊ የሀሳብ ጉባኤ ወቅት ሳይቀር የእንመካከር እንወያይ ሀሳብ ለሀሳብ እንለዋወጥ የሚለውን ጥሪ እንደ ትልቅ አጋጣሚ ከመውሰድ ይልቅ፣ ለክፋት መጠንስሻና ግጭት ማውጠንጠኛ ሊያደርጉ ሲባዝኑ መታዘባቸውን አንስተዋል። እነዚህን የመሰሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የሺህ ዓመታት ጥብቅ ማህበራዊ ሸማችንን በቅጡ ያልተረዱ፣ የህዝባችንን የውስጥ ጥንካሬ ያላወቁ ናቸው ይሏቸዋል ፕሬዝዳንቱ። እኛ ኢትዮጵያውያን የተራሮች፣ የሸለቆዎች፣ የደጋዎች፣ የወንዞች ልጆች ነን። የኢትዮጵያ ህዝብ ወንዞቹን ለመሻገርና ለመግራት የሚያስፈልገውን ትዕግስት ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። በእርግጥም አባይን የሚያቋርጥ ብቻ ሳይሆን ታሪክን የሚያሻግር ሁሉ ከነፋስና ወጀብ የበረታ ታላቅ የትዕግስት መከተሪያ ሊኖረው እንደሚገባ ያወቀ ብልህ ህዝብም ነው። ትዕግስት ስንቁ ነው። የሚሻገረውም በትዕግስተኛነትና በብርታት ነው።
ፋይዳ- ሌላው የኢትዮጵያ ዲጂታል ራዕይ የስኬት ጉዞ ማሳያ
Aug 26, 2026 109
ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዲጂታል ሥርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያም ይህን ዓለም አቀፋዊ ግስጋሴ ተቀላቅላ በዲጂታል ዘርፉ እመርታ እያሳየች ትገኛለች። በዚህም በዘመናዊ የለውጥ ጉዞ እንደ ዋና ምሰሶ የሚያገለግለው ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ አሁን ላይ የሀገሪቱ ዲጂታላይዜሽን ስኬት ጉልህ ማረጋገጫ ለመሆን በቅቷል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግር ስራ የማገዝ እና ዘመናዊ የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማት መገንባትን መነሻ በማድረግ በ2013 ዓ.ም በሙከራ ደረጃ ተጀምሯል። መንግስት እያንዳንዱ ነዋሪ በአካልም ሆነ በኦንላይን ማንነቱን በተአማኒነት ማረጋገጥ የሚችልበት ሥርዓት እንደሚያስፈልግ በመረዳት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን አስጀምሯል። ፕሮግራሙ የቅድመ-ሙከራ ስራዎችን ሲጀምር ቀደም ሲል የነበሩትን የተበታተኑ፣ ለአጭበርባሪዎች የተጋለጡ እና አንዱ ድርጅት ከሌላው ጋር መረጃ የማይለዋወጥባቸውን የቆዩ አሰራሮች በአንድ ማዕከላዊ የባዮሜትሪክ ስርዓት መተካት ዋነኛ ግብ አደረገ። ስርዓቱ ጠንካራ ህጋዊ መዋቅር እንዲኖረውም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን አስመልክቶ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይዳ መታወቂያን ተራ መለያ ሰነድ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ክብርና መብት ማረጋገጫ እንዲሁም ዘመናዊ የኢኮኖሚ ነጻነትን የሚያፋጥን የሉዓላዊነት መሣሪያ አድርገው ገልጸውታል። በተለይም በመንግስት መስሪያ ቤቶችና በግል ተቋማት ውስጥ የሚስተዋለውን የመረጃ መጭበርበር፣ አድካሚ ቢሮክራሲ እና ሙስናን ሙሉ በሙሉ በማስወገድ ረገድ ይህ ዲጂታል መሠረተ-ልማት የመፍትሔው ዋነኛ ቁልፍ መሆኑን በተደጋጋሚ አጽንኦት ሰጥተውበታል። ይህ የፋይዳ መታወቂያ ጉዞ ከኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የዲጂታል ስትራቴጂ 2030 ራዕይ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ሀገሪቱ እስከ 2030 .ድረስ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ፣ የተቀናጀ የኤሌክትሮኒክስ መንግስት አሰራር የሰፈነባት እና በዲጂታል ክፍያ የምትመራ የኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን ያቀደችውን ግብ ለማሳካት ፋይዳ እንደ ዋና የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል። ማንኛውም የዲጂታል አገልግሎት፣ የኦንላይን ንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ያለምንም እንከንና በተገቢው ፍጥነት መተግበር የሚችለው እያንዳንዱ ዜጋ ሊጭበረበር የማይችል አስተማማኝ የዲጂታል ማንነት ሲኖረው ብቻ በመሆኑ የፋይዳ ሚና ለስትራቴጂው ስኬት ወሳኝ ነው። በአሁኑ ወቅት የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም ከቀላል የፓይለት ፕሮጀክትነት ተሻግሮ፣ ወደ ትልቅ ሀገራዊ ተቋምነት ተቀይሯል። ተቋሙ ይበልጥ በራሱ እንዲንቀሳቀስና አገልግሎቱን እንዲያሰፋ «ፋይዳቨርስ» በሚል ስያሜ ራሱን የቻለ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በይፋ ተዋቅሯል። በዲጂታል መታወቂያ ስርዓ የተመዘገቡት ጠቅላላ የሰዎች ቁጥር ከ49 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘረጉ ከ12 ሺህ በላይ የባዮሜትሪክ መመዝገቢያ መሣሪያዎችን (Registration Kits) በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል የተመዘገበ ታላቅ ስኬት ነው። ከተመዘገቡት ነዋሪዎች መካከልም ከ14 ነጥብ 3 በመቶ በላይ የሚሆኑት የፕላስቲክ ካርድ ህትመታቸው ተጠናቆ በቀጥታ ማግኘት ችለዋል። ይህ የዲጂታል መታወቂያ አሰራር አሁን ላይ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር በጥብቅ በመተሳሰር የዕለት ተዕለት አገልግሎት ማረጋገጫ እየሆነ ይገኛል። እስከ አሁን ድረስ 150 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል የልማት ድርጅቶች (Integrated Agencies) የአሰራር ስርዓታቸውን ከፋይዳ ጋር ያቀናጁ ሲሆን፣ ይህም ተቋማቱ የደንበኞቻቸውን ማንነት በሴከንዶች ውስጥ በዲጂታል መንገድ እንዲያረጋግጡ አስችሏቸዋል። በዚህም ምክንያት እስከ አሁን ድረስ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ማለትም ከ194 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ማንነት ማረጋገጫ (eKYC) ፍተሻዎች በተሳካ ሁኔታ ተከናውነዋል። በፋይናንስ ዘርፍ ባንኮች አዳዲስ ደንበኞችን ለመመዝገብና የቆዩ አካውንቶችን ከፋይዳ ጋር ለማገናኘት ይህንን ቴክኖሎጂ በስፋት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ይህ የፋይዳ ዲጂታል አሰራር በሀገሪቱ ማኅበራዊ እና ፍትሃዊ አካታችነት ላይ የሚያሳድረው በጎ ተፅዕኖ እጅግ የጎላ ነው። ቀደም ሲል የመታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት በጂኦግራፊያዊ ርቀት፣ በወረቀት ቢሮክራሲ ወይም በሌሎች ማኅበራዊ ምክንያቶች ይገለሉ የነበሩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም በገጠር የሚኖሩ ዜጎች፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችና አሁን ላይ እኩል በሆነ መንገድ የመንግስትና የግል አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን በር ከፍቶላቸዋል። የዲጂታል ማንነት የዜግነት ክብርና ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ ማህበራዊ ፍትሕን የሚያሰፍን ሀገራዊ ድልድይ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። በሌላ በኩል፣ ከሀገራዊ ደህንነትና የፋይናንስ ዘርፍ ጥራት አንጻር የፋይዳ አስተዋፅኦ ወደር የለውም። የህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውርን (Money Laundering) እና ህገ-ወጥ ደላሎችን ለመግታት በባንኮችና በፋይናንስ ተቋማት የሚደረጉ ቁጥጥሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ማዕቀፍ ቀይሮታል። እያንዳንዱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከተረጋገጠ ግለሰብ ማንነት ጋር ብቻ የሚገናኝ በመሆኑ፣ የኢኮኖሚው ዘርፍ ግልፅነትና ተአማኒነት እንዲኖረው አድርጓል። ይህም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባበት ወቅት በራስ መተማመንን የሚፈጥርና ሀገሪቱን ለዓለም አቀፍ አሰራር ዝግጁ የሚያደርግ ትልቅ የቴክኖሎጂ እርምጃ ነው። የፋይዳቨርስ የወደፊት ራዕይ ይበልጥ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ ነው። ተቋሙ እድሜያቸው ለምዝገባ የደረሱ ተመዝጋቢዎችን ቁጥር 90 ሚሊዮን ለማድረስ እና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ከወላጆቻቸው መታወቂያ ጋር አገናኝቶ የመመዝገብ ልዩ አሰራርን ለማስፋት እየሰራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውንም አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት፣ ሲም ካርድ ለመግዛት፣ ፓስፖርት ለማደስ፣ የመንጃና የንግድ ፈቃድ ለማውጣት የፋይዳ ቁጥርን ብቸኛ እና ግዴታ የማድረግ ሂደትን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ተጠቃሚዎች የትኛው ተቋም የትኛውን መረጃቸውን ማየት እንዳለበት ራሳቸው መቆጣጠር የሚችሉበትን የሉዓላዊ ማንነት ቴክኖሎጂን ማጎልበት እና የግል መረጃዎችን ፍጹም ደህንነት ማረጋገጥም የስትራቴጂው አካል ነው። በአጠቃላይ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያሳየው ፈጣን እድገት፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ስኬታማነት ማሳያ ነው። ከግለሰቦች አልፎ ለባንኮች፣ ለትምህርት ተቋማት እና በሀገሪቱ ለሚኖሩ ስደተኞች ጭምር እኩል መብትና አገልግሎትን በዲጂታል መንገድ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል። ፋይዳ የኢትዮጵያን ዲጂታል ስትራቴጂ 2030 ራዕይን በማሳካት፣ ሁሉንም ዜጎች ያካተተ ፍትሃዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በዲጂታል ክፍያ የሚመራ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ ታምርት እና የኢንዱስትሪው ትንሳኤ
Aug 26, 2026 103
ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ጉዞ ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መዋቅራዊ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሀገር ውስጥ ምርትን ለማዘመን የታለመ ታላቅ ሀገራዊ መርሐ ግብር ነው። ንቅናቄው በአጭር ዓመታት ውስጥ በኢኮኖሚ ደህንነት፣ የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ አምጥቷል። ይህ ንቅናቄ በይፋ የተጀመረው በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። የንቅናቄው አላማ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ይስተዋል የነበረውን የቅንጅት ማጣት፣ የፋብሪካዎችን መዘጋት እና እጅግ ዝቅተኛ የነበረውን የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅም ለማሻሻል እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቀነስ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንቅናቄው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ትንሣኤና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት በተግባር የሚያረጋግጥ ዋና መሣሪያ ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች ላይ ገልጸዋል። አምራች ዘርፉን ማሳደግ የፖሊሲ ምርጫ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ነጻነት የማስከበር ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል። የምርት ማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከ2015 ዓ.ም አንስቶ ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመካሄድ ላይም ይገኛል። አራተኛው ዙር ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዝያ 24 እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል። በዚህ ኤክስፖ ላይ ከ270 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገበያ ትስስር ውል ተፈርሟል። በአሁኑ ወቅት ንቅናቄው ከተጀመረ ወዲህ ተዘግተው የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ፋብሪካዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የተመለሱ ሲሆን፣ ከ14 ሺህ 500 በላይ አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ እንዲሁም ከ350 በላይ አዳዲስ ግዙፍ ፋብሪካዎችም ወደ ምርት ገብተዋል። ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም 67 በመቶ የተሻገረ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ አምራቾች የምርት ድርሻም ከ30 በመቶ ወደ 45 በመቶ አድጓል። ከፋይናንስና ከምርት ዕድገት ባሻገር፣ ንቅናቄው ብዙ ቁጥር ላላቸው ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። በተጨማሪም ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በተደረገ ቅንጅት የኢንዱስትሪዎችን የቴክኖሎጂ ፍላጎት የሚያሟላ የሰለጠነ የሰው ኃይል የማፍራት ሥራ ጎን ለጎን እየተከናወነ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ የኢንዱስትሪ ምርቶችን፣ አልባሳትን እና የግብርና ማቀነባበሪያ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እስካሁን ድረስ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከንቅናቄው መጀመር አንስቶ በየዓመቱ በሚዘጋጁት የገበያ ትስስሮችም በአምራቾች እና በገዢዎች መካከል ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውል ተፈጽሟል። የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተወዳዳሪ ለማድረግ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስትቲዩትና በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አማካኝነት ለአምራቾች የቴክኒክና የሎጅስቲክስ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል። ይህም የሀገር ውስጥ ምርቶች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነትና እምነት እንዲጨምር አድርጓል። ወደፊት የመንግስት ትኩረት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢንዱስትሪ መንደሮችና የረጅም ጊዜ ብድር ማመቻቸት ላይ ያተኩራል። ለመንግስት ሰራተኞች የሚቀርቡ አልባሳት፣ ደብተሮችና የቢሮ ቁሳቁሶች በመቶ በመቶ ከሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲገዙ የሚያስገድደው አሰራር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ምርቶችን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ማድረግ የወደፊቱ ዋና አቅጣጫ ነው። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከመሸመት ወደ ማምረት እና ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል የተደረገ ትልቅ የኢኮኖሚ አብዮት በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚዋ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደሚያደርጋት ጥርጥር የለውም።
ኢትዮጵያ-የቀይ ባሕር ደህንነትና የቀጣናዊ መረጋጋት ዋስትና!
Aug 23, 2026 384
ኢትዮጵያ-የቀይ ባሕር ደህንነትና የቀጣናዊ መረጋጋት ዋስትና! የቀይ ባሕር ቀጣና በዓለም አቀፍ የንግድ ዝውውር፣ በጂኦፖለቲካዊ ትስስር እና በባሕር ላይ ደህንነት ረገድ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ቦታ የሚይዝ ቀጣና ነው።ሆኖም በአሁኑ ወቅት አካባቢው የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች መራኮቻ፣የባሕር ላይ ወንበዴነት፣ የሕገ-ወጥ ንግድና የሽብር ስጋቶች የተጋረጡበት በመሆኑ፣ዘላቂ ሰላምና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ጠንካራና አስተማማኝ አቅም ያለው ቀጣናዊ አጋር ያስፈልገዋል።ኢትዮጵያ በ130 ሚሊዮን ሕዝቧ፣ በገነባችው ግዙፍ ኢኮኖሚ፣በጠንካራ የመከላከያና የባሕር ኃይል አቅሟ እንዲሁም ቅድሚያ ለጎረቤት በሚለው የመደመር ዲፕሎማሲያዊ መርህዋ የቀይ ባሕርና የመላው ቀጣናው ደህንነት ዋስትና ሆና ወጥታለች። ኢትዮጵያ ከራሷ ባለፈ ሀገራት ግጭት ሲያጋጥማቸው፣ለችግር ሲጋለጡ ቀድማ የምትደርስ፣ ሰላምን በማስከበርና መረጋጋትን በመፍጠር በጽኑ መሠረት እንዲቀጥሉ በማስቻል የምትታወቅ ሀገር ናት።በ1950ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ወቅት የተባበሩት መንግሥታትን ጥሪ በመቀበል ከ3 ሺህ 500 በላይ ወታደሮቿን በመላክ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የፈጸመችው ገድል የቃኘው ሻለቃ በጦር ሜዳ ላይ ያሳየው ጀግንነትና የከፈለው መስዋዕትነት እስከ ዛሬ በዓለምና በደቡብ ኮሪያ ሕዝብ ዘንድ በከፍተኛ አክብሮት ይታወሳል። ይህ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ኢትዮጵያ አፍሪካን ጭምር ያኮራችበት ነበር። ከዚያ በኋላም በኮንጎ፣በሩዋንዳ፣ በላይቤሪያ፣ በቡሩንዲ፣ በዳርፉር፣ በአብዬ እና በደቡብ ሱዳን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደር የለሽ ሀገር ያደርጋታል። በሶማሊያ ደግሞ ኢትዮጵያ የደም ዋጋ ከፍላ ሀገሪቱን በአሸባሪዎች ከመበታተንና ከመፍረስ ታድጋለች። የአልሸባብን ስጋት በመግታትና የሶማሊያን መንግሥት በመደገፍ ለቀጣናው ደህንነት የማይተካ ሚና ተጫውታለች። ዛሬም በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዋነኛዋ ሀገር ሆና ቀጥላለች።ይህ የካበተ ልምድ ኢትዮጵያን የቀጣናው የደህንነት ዋስትና እንድትሆን አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር እሳቤያቸው እንዳመላከቱት፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት ከሁሉም የውጭ ግንኙነቶች ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው። መደመር ከአጎራባች ሀገራት ጋር የምናደርገው ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅምን በአብዛኛው በጋራ ጥቅም ላይ ተመሥርቶ የሚመራ መሆን ይኖርበታል የሚል የጸና አቋም ያራምዳል። ዕጣ ፈንታችን የተሳሰረ ስለሆነ የጋራ ጥቅሞቻችንን መሠረት ያደረገ ትብብርና መተጋገዝ ያስፈልገናል የሚለው መርህም ኢትዮጵያ አሁን እየተራመደችበት ያለው የገቢር ነበብ ዲፕሎማሲ መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ በመደመር እያንዳንዱ የልማት እርምጃዋ፣ ቀጣናዊ መሻቷ ጎረቤቶቿን የሚያግዝና ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ጎረቤቶቿ ለችግር በተዳረጉ ጊዜም ቀድማ ደራሽ ናት። የሰላማቸው አምባ፣ የሀዘናቸው አጽናኝ ናት። ለአብነትም ሱዳን ከባድ ቀውስ ውስጥ በገባች ጊዜ 15 ሚሊዮን ዶላር በመደገፍ የችግር ጊዜ የአብሮነት መርሗን በተግባር አሳይታለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞችን በሯን ከፍታ ተቀብላ በማስጠለል ሰብዓዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች ነው።ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ የጎረቤቶቿ ሕመም የሚያማት፣ እንደ ዋርካ ሆና የምታሳርፍ፣ ለጋራ ጥቅም ቀድማ የምትሰለፍ መሆኗን በግልጽ ያሳያል። ኢትዮጵያ ወንዞቿና ጅረቶቿ የቀጣናውን ሀገራት የሚያለሙ፣ ለም አፈሯ ምግብ የሆናቸው ሀገር መሆኗም የማይታበል ሐቅ ነው። የመደመር መንግሥት ይህንን ተፈጥሯዊ ሚዛን በእሴት የጨመረ የትብብር ድልድይ አጽንቷል። በዓባይ ወንዝ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በመገንባት የቀጣናው የብርሃን ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል። ግድቡ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር የጋራ ልማትን እውን እያደረገ ነው። ኢትዮጵያ ሌሎች የኃይል ማመንጫዎችን በመገደብ የቀጣናውን የኃይል ዋስትና የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኝነቷን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። ይህ በመደመር መንግሥት የሚተገበር ራዕይ ኢትዮጵያ የቀጣናው የጋራ የኢነርጂ ደህንነት ምሰሶ መሆኗን ያረጋግጣል። የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የምግብ ሉዓላዊነትና የቀጣናው ተስፋ የመደመር መንግሥት በተከተለው የጠራ እሳቤ ኢትዮጵያ ግዙፍ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው። ይህም ትሩፋቱ ለቀጣናው ሀገራት ጭምር እየተትረፈረፈ ነው። በመሠረተ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፍ የተከናወኑት ስኬቶች ሀገሪቱ የምግብ ዋስትናን በቀጣና ደረጃ ለማረጋገጥ ምሳሌ አድርጓታል። የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በጀመረችው የስንዴ ልማት ኢኒሼቲቭ እመርታዊ ስኬት አስመዝግባለች። ለዓመታት በድርቅና በሌሎች ችግሮች የሚያጋጥማትን ሰብዓዊ ድጋፍ በእርዳታ ስትሸፍን የነበረችውና ለፍጆታ የሚሆን ስንዴንም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ስታስገባ የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ላይ በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ስንዴን በበጋ መስኖና በክረምት በማልማት በዓመት 33 ሚሊዮን ቶን ስንዴ የምታመርት ሀገር ሆናለች። በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር፣ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ በራሷ ምርት የተካች ሀገር፣ ለሌሎች ጎረቤት ሀገራት ስንዴ የምትልክ ሀገር በመሆንም እየተጠቀሰች ነው። የምግብ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ ጉዞዋ በመስኖ የሚለሙ መሬቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በማስፋፋት፣ የክላስተር እርሻን በማጠናከር ኢትዮጵያ ከተረጂነት ራሷን ወደመቻል ተሸጋግራለች። ይህ የኢትዮጵያ ስኬት ለቀጣናው የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ተምሳሌት ሆኗል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ድርቅን መቋቋም የሚችል የግብርና ሥርዓት በመገንባትና በረሃዎቿን በማልማት ምርትና ምርታማነትን አሳድጋለች። በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ ተጋላጭ ለሆነው ቀጣና ተግባራዊ ምሳሌን በአረንጓዴ አሻራ አሳይታለች። ባለፉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ሀገርን አረንጓዴ አልብሳለች። አረንጓዴ አሻራዋ ድንበር ተሻግሮ የቀጣናው የተስፋ ምንጭም ሆኗል። የቀይ ባሕር ባለቤትነት ታሪካዊ መብትና የቀጣናው ደህንነት ኢትዮጵያ ለሺህ ዓመታት ቀይ ባሕርን ተፈጥሯዊ ወሰኗ በማድረግ የአዱሊስ፣ የምጽዋና የአሰብ ወደቦችን ስታስተዳድርና የንግድ ዝውውሩን ስታስጠብቅ የቆየች ሀገር ናት። በታሪካዊ አጋጣሚዎች ምክንያት ከባሕር ተገልላ የቆየች ቢሆንም፣ ለ130 ሚሊዮን ሕዝቧ፣ ለግዙፍ ኢኮኖሚዋ እና ለቀጣናው ደህንነት ሲባል የባሕር በር ማግኘት የህልውና ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ዳግም በጥንካሬ በማደራጀት ስትራቴጂካዊ እርምጃ ወስዳለች። ይህ ዝግጁነት የቀይ ባሕርን የንግድ መስመር ከባሕር ወንበዴዎች ለመጠበቅ፣ የሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውርን እንዲሁም የሽብር እንቅስቃሴዎችን ከሥር ለማምከን የሚረዳ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷን በሰላማዊ መንገድ፣ በዲፕሎማሲና በጋራ ጥቅም መርህ ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የመላው ቀጣናው አሸናፊነት ማረጋገጫ ይሆናል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም፣ ልማትና መረጋጋት ቀዳሚ ሚናዋን ስታበረክት የቆየች የምስራቅ አፍሪካ ምሰሶ ናት።የኢትዮጵያ አቅምና ዝግጁነት ለቀይ ባሕር ቀጣና ደህንነት ዋስትና የሚሰጥ እንጂ ማንንም ሀገር የሚጎዳ አይደለም። በጋራ ጥቅም እና በቅድሚያ ለጎረቤት መርህ የሚሳካው የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ለቀጣናው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሎጂስቲክስ ቅልጥፍና እና ለጋራ ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ድርሻ ይጫወታል። ዛሬም በመደመር እሳቤ፣ በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በጠንካራ የመከላከያ ኃይልና በቅድሚያ ለጎረቤት በሚሰጥ ጠንካራ ዲፕሎማሲ የቀጣናውን የተሻለ ነገ እየገነባች ነው። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሳየችውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ የቀይ ባህር ባለቤትነት መብቷን በማሳካትም ትደግመዋለች። የልማት ተስፋና የቀጣናው የደህንነት ዋስትናነቷን በገቢር ነበብነት ታረጋግጣለች።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 12369
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 21962
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14996
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20738
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105194
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 79840
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58193
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55800
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 39877
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 39775
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39251
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37738
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105194
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 79840
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58193
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55800
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 654
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።   በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።   በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 622
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም