ቀጥታ፡

በአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ የሚሳተፉ ልዑካን አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ

‎አዲስ አበባ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦‎በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

‎በዚሁ መሠረት የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዶክተር ኤድዋርድ ቢዚማና አዲስ አበባ ገብተዋል።




‎አምባሳደር ዶክተር ኤድዋርድ ቢዚማና ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም መላኩ በዳዳ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

‎49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ከሐምሌ 21 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

‎በጉባኤው ለመሳተፍ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድን አባላትም አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም