አርእስተ ዜና
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የብሔራዊ ባንክ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ገለጹ
Mar 30, 2023 65
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የብሔራዊ ባንክ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያካሄደው ሰፋ ያለ ጥናት ዛሬ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ሆኗል። የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ የቀረበው ጥናት በዘርፉ ያሉ ችግሮችንና የተለያዩ የውጭ ሀገራትን ተሞክሮዎችም ጭምር በጥልቀት የዳሰሰ ነበር።   የጥናቱን ግኝቶች መነሻ በማድረግ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና የገንዘብ ዝውውርን ሰንሰለት ለመበጠስ እንዲሁም የድርጊቱ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የፖሊስ፣ የሥርዓትና የተጠያቂነት መፍትሄዎችን የሚጠቁሙ ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል። በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አመላክቷል። በጥናቱ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የውጭ ምንዛሬ ገበያዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣ የኑሮ ውድነትን በማናርና ሙስናን በማስፋፋት ሀገርን ለከፋ አደጋ እያጋለጡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡ በህገ-ወጥ ተግባራቱ መንግሥታዊና የግል ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር የሚሳተፉ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ ከውጭ ሀገራት እስከ መሀል ሀገር የተዘረጋው ህገ-ወጥ የጥቅም ትስስር በደላሎች፣ በድርጅቶች፣ በኩባንያዎችና በባንክ ሥርዓቱም ጭምር እንደሚደገፍ አመልክቷል። ይህም በሀገራችን እየታየ ላለው ቅጥ ያጣ የዋጋ ንረትና ማህበራዊ ችግር አንዱ ቁልፍ ምክንያት መሆኑን አሳይቷል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት፤ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ የሀገርን ህልውናና የህዝብን ጥቅም እየተፈታተነ ያለ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን በመረዳት አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብና ህዝቡ በትብብርና በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡   በጥናቱ የተለዩና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች፣ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እርምጃ በቀጣይነት የሚወሰድ መሆኑን ነው የገለፁት። ህገ-ወጥነትን በመቆጣጠር፣ የሀገርንና የህዝብን ህልውና በመታደግ ትግሉ ውስጥ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የህግ አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ተቀናጅተውና ተናበው ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳስበዋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከብሔራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀትና ሌሎች አካላትን በማሳተፍ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ ባንኩ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳይችል እንቅፋት ሆነዋል፣ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ ነው።   የውጭ ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን የብር እንቅስቃሴውም ከባንክ ሥርዓት ውጭ በመዘዋወር ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለ መሆኑ ተደርሶበታል ያሉት አቶ ማሞ በርካታ የብር ኖቶችን ከባንክ ሥርዓት ውጭ በማንቀሳቀስ ላልተፈለገ ዓላማ በሚያውሉ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። በቀረበው ጥናት ላይ ውይይት ያደረጉ የብሄራዊ ባንክ ገዢን ጨምሮ የመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበው ጥናት አጠቃለይ ችግሩን፣ የችግሩን ተዋንያን እና የመፍትሄ ሐሳቦችን በሚገባ ያመላከተ በመሆኑ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ምስጋና ማቅረባቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኅን በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ዕውቅናና ሽልማት አበረከቱ
Mar 30, 2023 45
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን/ኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ዕውቅናና ሽልማት አበረከቱ። ዶክተር ወርቅነህ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ኃይል ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱራህማን አሊ ካህን ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል።   ዶክተር ወርቅነህ ዕውቅናና ሽልማቱ ያበረከቱት ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች የሁለቱን ፖሊስ ተቋማት በማስተባበር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በቀጠናው የሚስተዋለውን የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።   በተጨማሪም በህገ-ወጥ የሰዎች፣ የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ እንዲሁም አሸባሪዎችን፣ የፀረ-ሰላም እንቅስቃሴዎችንና የጸጥታ ስጋቶችን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት ሊሆን በሚችል መልኩ የጋራ ግብረ-ኃይል በማቋቋም የድንበር ደህንነት ለመቆጣጠር የላቀ ሚና ስላበረከቱ እንደሆነም ታውቋል።   የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የጋራ ግብረ ኃይል የድንበር ደህንነትን በጋራ ለመጠበቅ የቴክኒክ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማሟላት የሚያስችላቸውን ዝክረ-ሀሳብ ለኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ያቀረቡ ሲሆን ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ግብረ ኃይሉን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። በቀጣይ ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት ያቋቋሙትን የጋራ ግብረ-ኃይል የበለጠ በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ የድንበር ደህንነትን ለማረጋገጥ በላቀ ተነሳሽነትና ትብብር እንደሚሰሩ ቃልገብተዋል።
በግለሰብ ቤት የተከማቸ የተበላሸ ቴምር ከወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን ፖሊስ ገለጸ
Mar 30, 2023 30
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ በግለሰብ ቤት የተከማቸና ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ንፅህናውን ያልጠበቀና የተበላሸ በርካታ ቴምር ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ታይዋን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። ግለሰቦቹ በመኖሪያ ግቢያቸው በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የተበላሸና በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል በርካታ ቴምር ንጽህና በጎደለው ሁኔታ አስቀምጠው ለአትራፊ ነጋዴዎች በፌስታል አሽገው የ92ሺህ ብር ከሸጡላቸው በኋላ የተበላሸ መሆኑን የተገነዘቡት ገዢዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ሊያዙ ችለዋል፡፡   መረጃው የደረሰው በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የእፎይታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያም ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማወጣትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ግቢ መጋዘን ውስጥ ባደረገው ፍተሻ መጥፎ ጠረን ያለው የተበላሸ በርካታ ቴምር ተከማችቶ ተገኝቷል። በክፍለ ከተማው የወረዳ 10 አስተዳደር የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብቱ መካ በበኩላቸው በቁጥጥር ስር የዋለው ቴምር ወደ ህብረተሰቡ ቢሰራጭ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።   ተበዳዮቹ ከተጠርጣሪዎቹ የገዙትን የተበላሸ ቴምር ለህዝብ ሳይሸጡ እና የግል ጥቅም ሳያጓጓቸው ለሰዎች ጤና በማሰብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ጊዜና ወቅትን እየጠበቁ ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ነጋዴዎችም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ተገንዝበው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ኢዜአ በአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል-ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ
Mar 30, 2023 41
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚና ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ገለጸ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለጋዜጠኞቹ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ሙያዊ ዘገባ መስራት የሚያስችል ለሶስት ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።   የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለጋዜጠኞቹ ሙያዊ ልምዱንና የዘገባ ንድፈሀሳቦችን ለጋዜጠኞች አጋርቷል። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚዲያ ተቋም ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ስም ያለው ተቋም መሆኑን አውስቷል። የዜና አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ አልፎ በቅኝ ግዛት ዘመን ድምፅ አልባ ለነበሩ አፍሪካውያን ድምፅ በመሆን ለነጻነታቸው እንዲታገሉ መረጃዎችን ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል። በአፍሪካ ቀዳሚው የዜና አገልግሎት የሆነው ኢዜአ፤ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መሪዎችን እና የነጻነት ታጋዮችን ታሪክ በመሰነድም ኢትዮጵያን በጉልህ ማስጠራቱን ጠቅሷል። ጋዜጠኛ ጥበቡ እንደሚለው በአፍሪካ ትልቅ ታሪክ እና ስም ያለው ይህ የዜና አገልግሎት በአህጉሪቱ ወደነበረበት ከፍታ እንዲመጣ መስራት ይጠበቅበታል። አገልግሎቱ በአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ፣ በሰው ኃይልና በሌሎች መስኮች የጀመረውን ሁለንተናዊ ተቋማዊ ማሻሻያ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መክሯል። ለአገልግሎቱ ቀጣይ ስራ መሳካት አመራሩና ጋዜጠኞቹ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝቧል። ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ጋዜጠኝነት ሁሌም እየተማሩ የሚኖሩት ስራ በመሆኑ በየጊዜው ለዘጋቢዎች የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱም ባለሙያዎችን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቁሟል።   የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነትና የስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወንዲራድ ኢዜአ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የአቅም ግንባታ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ ገጽታን በመገንባት እንዲሁም የመረጃ ምንጭነቱን አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችል ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በስልጠናው የተሳተፉ የኢዜአ ጋዜጠኞች በበኩላቸው ስልጠናው ለቀጣይ ስራዎቻቸው ተጨማሪ እውቀት የሚገበዩበት መሆኑን ገልጸዋል። ኢዜአ ለሌሎች መገናኛ ብዙሃን የዜና ምንጭ በመሆኑ ጥራት ያለውና አስተማማኝ መረጃ ለማድረስ በየወቅቱ አቅማቸውን የሚያሳድጉ መሰል ስልጠናዎች መሰጠታቸው ተገቢ ነው ብለዋል።    
በሲዳማ ክልል ያሉ የቱሪስት መስህቦችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል--የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
Mar 30, 2023 31
ሀዋሳ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎችን ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሀላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለኢዜአ እንደገለጹት ገቢው የተገኘው ባለፉት ሰባት ወራት ክልሉን ከጎበኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ነው። ገቢው ከቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች በደረሰኝ የተሰበሰበ ገቢን ጨምሮ ከሆቴልና ሌሎች የቱሪስት አገልግሎቶች የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል። ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተገኘው መረጃ መሰረት ባለፉት ሰባት ወራት ክልሉን ለመጎብኘት ከመጡ ቱሪስቶች መካከል 20ሺህ የሚሆኑት የውጪ ሀገር ጎብኚዎች መሆናቸውን አቶ ጃጎ ገልጸዋል። ወደ ክልሉ በመደበኛነት ከሚመጡ የሀገር ውሰጥና የውጪ ጎብኚዎች በተጨማሪ በሀዋሳ የሚከናወኑ ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊና ህዝባዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚመጡ ጎብኚዎች ለቱሪስት ፍሰቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን አውስተዋል።   በክልሉ ያሉትን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ የመስህብ ስፍራዎችን በጥናት በመለየትና በአራት ማዕከል በማደራጀት ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አቶ ጃጎ አስረድተዋል። በሀዋሳ ከተማ ማዕከል ስር የሀዋሳ የፍቅር ሀይቅ፣ የዓሳ ገበያ፣ የታቦር ተራራ፣ የወንዶ ገነት የተፈጥሮ ደንና ፍል ውሀን የያዘ የመስህብ ስፍራ እንደሚገኝበት ጠቅሰዋል። የመስህብ ስፍራዎቹን በድረ-ገጽ በሀገር ውስጥና በውጪ መገናኛ ብዙሀንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አብዛኞቹ በሀዋሳ ከተማ መገኘታቸው በሌሎች አካባቢዎች ጎብኚዎች እንዳይቆዩ ማድረጉን ጠቁመዋል። ይህንን ችግር ለማቃለል በቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍና በሆቴል ስራ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የሚታይ

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በህዝቡ ትብብር እየተገነቡ ያሉ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ እንደሚያሳድጉ ተገለጸ
Mar 30, 2023 40
ድሬደዋ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በህዝቡ ትብብር እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በእጅጉ ሊያሳድጉ የሚችሉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ያዘጋጁት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝት ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።   በዛሬው እለት የድሬዳዋ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ የድሬዳዋ ስታዲየም ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት እና የሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ መዳረሻዎች መካከል በ9ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውንና በ307 ሚሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የድሬዳዋ ስፖርት አካዳሚ አንዱ ነው። ዓለም አቀፍ ደረጃን ባሟላ መልኩ እየተገነባ የሚገኘው የድሬዳዋ ስፖርት አካዳሚ የወጣቶችን ሰብእናና አካል ብቃት ለመገንባት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። የኦሎምፒክ መወዳደሪያ መስፈርትን ጠብቆ እየተገነባ የሚገኘው ብቸኛው የቤት ውስጥ መዋኛ የሚገኘውም እዚሁ አካዳሚ ውስጥ ነው።   በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታዲየም የማሻያያ ፕሮጀክት ሥራ የስታዲየም ሥራው ተጠናቆ በቀጣዩ ዓመት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ብቁ እንዲሆን የአርቴፊሻል ሳር የማልበስ ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡ የድሬዳዋ ምድር ባቡር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ቡድኑ የተጎበኘው ሌላው ተቋም ነው። የ127 ዓመታት እድሜ ያለው አንጋፋው ተቋም ለ25 ዓመታት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ቢቆይም በ2014 ዓ.ም መንግስት በከተማ አስተዳደሩ እንዲተዳደር በፈቀደው መሰረት በጥቂት ወራት ውስጥ ሶስት ባቡሮችን ጠግኖ ወደ ሥራ አስገብቷል። በቀጣዮቹ ወራትም ተጨማሪ ባቡሮችን በመጠገን በአመቱ መጨረሻ ሰባት ባቡሮችን ወደ ስራ የማስገባት እቅድ እንዳለው በጉብኝቱ ተገልጿል።   ሌላው በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ቡድኑ የተጎበኘው በሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀውና በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር የተገለጸው የኩላሊት ሕመምተኞች የዲያሊሲስ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው። ማዕከሉ በድሬዳዋ ብሄራዊ ሲሚንቶ ፋብሪካና በከተማው ወጣቶች ተሳትፎ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሕንጻ ግንባታው ተጠናቋል። በአንድ የከተማው ነዋሪ በጎ ፈቃደኛ ልገሳ ደግሞ 10 የዲያሊሲስ ማሽኖች ተገዝተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። በዚህም ማዕከሉ በቅርቡ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመርና በከተማው በአንድ የግል ሆስፒታል ብቻ እየተሰጠ ያለውን የዲያሊሲስ አገልግሎት እጥረት እንደሚፈታም ታምኖበታል።
በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሃት ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ
Mar 30, 2023 56
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል። በዚህ መሰረትም በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሃት ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ በማቋረጥ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የፍትህ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመላክቷል። ስለዚህም በተገለፀው አግባብ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት ክሳቸው የተነሳ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ማስታወቂያ
ፖለቲካ
የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ዕውቅናና ሽልማት አበረከቱ
Mar 30, 2023 45
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን/ኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ዕውቅናና ሽልማት አበረከቱ። ዶክተር ወርቅነህ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ለጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ኃይል ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱራህማን አሊ ካህን ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል።   ዶክተር ወርቅነህ ዕውቅናና ሽልማቱ ያበረከቱት ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች የሁለቱን ፖሊስ ተቋማት በማስተባበር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በቀጠናው የሚስተዋለውን የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።   በተጨማሪም በህገ-ወጥ የሰዎች፣ የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ እንዲሁም አሸባሪዎችን፣ የፀረ-ሰላም እንቅስቃሴዎችንና የጸጥታ ስጋቶችን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት ሊሆን በሚችል መልኩ የጋራ ግብረ-ኃይል በማቋቋም የድንበር ደህንነት ለመቆጣጠር የላቀ ሚና ስላበረከቱ እንደሆነም ታውቋል።   የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የጋራ ግብረ ኃይል የድንበር ደህንነትን በጋራ ለመጠበቅ የቴክኒክ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማሟላት የሚያስችላቸውን ዝክረ-ሀሳብ ለኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ያቀረቡ ሲሆን ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ግብረ ኃይሉን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። በቀጣይ ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት ያቋቋሙትን የጋራ ግብረ-ኃይል የበለጠ በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ የድንበር ደህንነትን ለማረጋገጥ በላቀ ተነሳሽነትና ትብብር እንደሚሰሩ ቃልገብተዋል።
መንግስት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመልሶ ግንባታ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ነው-የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ
Mar 30, 2023 79
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦መንግስት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመልሶ ግንባታ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ ገለጹ። በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት "ድህረ-ግጭት መልሶ ማቋቋምና የሰላም ግንባታ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም" በሚል አገር አቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።   የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታዋ ማርታ ሉዊጂ በዚሁ ወቅት መንግስት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም፣ የሽግግር ፍትህና ሌሎች የዘላቂ ሰላም ማሳለጫ መንገዶችን በመዘርጋት ለሁለንተናዊ ሰላም መረጋገጥ እየተሰራ ነው" ብለዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት የተፈጠሩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮችን ለማስተካከልም የመልሶ ማቋቋም ተግባር ውስጥ መገባቱን አንስተዋል። በጦርነት የተጎዱ መሰረተ-ልማቶችን እና ተቋማትን መልሶ የመገንባትና የልማት ስራዎችን ማፋጠን ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል። በዚህም ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። መንግስት ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና በመልሶ ግንባታ እያከናወነ ያለውን ተግባር ምሁራን በእውቀታቸው፣ ባለሀብቱ በገንዘቡና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ሚኒስትር ዲኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል የፀጥታ ኃይሉ ከማንኛውም ጸረ-ሰላም ኃይል የሚቃጣን ትንኮሳ በብቃት በመመከት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የሚችልበት ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱን በአቅም፣ በሞራልና በቴክኖሎጂ በብቃት የመገንባት ስራም በስኬት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። የሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም በማስከበር ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኗን ገልጸዋል። በፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ለአካባቢው አገራት ጭምር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰው፤ ስምምነቱን በሙሉ አቅም በመተግበር ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት መንግስት፣ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል። የሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ኮማንዳንት ብርጋዴር ጄነራል ሰብስቤ ዱባ ኢንስትቲዩቱ ከትምህርትና ስልጠና ጎን ለጎን የሰላምና ግጭት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን እንደሚያዘጋጅ ተናግረዋል። በዛሬው እለት የተካሔደው መድረክም በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል። በሲምፖዚየሙ ጄነራል መኮንኖች፣ ምሁራንና ሌሎች በሰላም ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል። በውይይቱ ላይ በድህረ-ግጭት መልሶ ማቋቋምና ሰላም ግንባታ የሲቪል ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሚና ላይ ያተኮሩ የመወያያ ፅሑፎች በምሁራን ቀርበዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
Mar 30, 2023 67
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ):- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። ምክር ቤቱ በዛሬው 12ኛ መደበኛ ስብሰባው በተጨማሪ በኢፌዴሪ መንግስትና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት እንዲሁም ስለ ራስ--ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።   ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በቀዳሚነት ተወያይቶ በአብላጫ ድምጽ ያጸደቀው የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን ነው።   የረቂቅ አዋጁን የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡት በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ፤ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሁሉን አቀፍ፣ ወጥና አስተማማኝ በሆነ መልኩ የአገሪቱ ነዋሪዎች የሚመዘገቡበትን ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል። መታወቂያውን በመጠቀም በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የግልጽነትና ተጠያቂነት ስርዓት እንዲዘረጋና የተሳለጠ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ሲሉም አክለዋል። አዋጁ ረዘም ላለ ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ያሉት ሰብሳቢዋ ግለሰቦችና ተቋማት የተጭበረበረ መታወቂያ ሰጥተው ከተገኙ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጥልም ገልጸዋል። ምክር ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አድርጎ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። ምክር ቤቱ በመቀጠል ተወያይቶ ያጸደቀው በኢፌዴሪ መንግስትና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ነው።   የስምምነቱን የውሳኔ ሃሳብ እና ሪፖርቱን የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ አቅርበዋል። በዚህም የብድር ስምምነቱ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮጀክትን በማስፈጸምና የመሬት ልማት ስራዎችን ለመስራት፣ ዘመናዊ የመሬት አያያዝን ለማስፈን ወሳኝ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። የተራቆቱ መሬቶችን ለማልማት፣ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ስራዎችን ለማጠናከር እንዲሁም የመሬት ምርትና ምርታማነት እድገትን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ገቢ እና አኗኗር እንደሚያሻሽል አመልክተዋል። ምክር ቤቱም የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርቱን ካዳመጠ በኋላ የብድር ስምምነቱን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ ስለ ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይም ውይይት አድርጓል።   በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ናቸው። በማብራሪያቸውም ዩኒቨርሲቲዎቹ ራስ-ገዝ እንዲሆኑ መታሰቡ ለተቋማት ውጤታማነት፣ አካዳሚያዊና ተቋማዊ ነጻነት እንዲኖራቸው፣ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲያስፋፉ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል። ምክር ቤቱ በአዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየበት በኋላ ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 16/2015 ሆኖ ለዝርዝር እይታ ለሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት መተዳደሪያ ደንብን ለማዘጋጀት የቀረበ መነሻ ሃሳብን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ
Mar 30, 2023 67
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መተዳደሪያ ደንብን ለማዘጋጀት የቀረበ መነሻ ሀሳብን ለዝርዝር እይታ ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ምክር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ስብስባውን ዛሬ አድርጓል። መነሻ ሃሳቡን ያቀረቡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በተለያዩ ወቅቶች ከአደረጃጀት ጋር በተያያዘ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር አውስተው፤ አገልግሎቱ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠርና አገራዊ ገጽታን የመገንባት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።   ይሁን እንጂ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ያለውን የተለያየ ጫና ተቋቁም በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ በየጊዜው ሲደረግ ከነበረው ጥገናዊ ለውጥ ወጥቶ ተወዳዳሪና ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አመልክተዋል። ምክር ቤቱም ማብራሪያውን ካዳመጠ በኋላ ረቂቅ ደንብ ቁጥር 02/2015 አድርጎ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የሶማሌ ክልል ህዝብ ጽንፈኝነትን በጋራ በመዋጋት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን ማስቀጠል አለበት- ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ
Mar 30, 2023 66
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ)፦የሶማሌ ክልል ህዝብ ጽንፈኝነትን በጋራ በመዋጋት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን ማስቀጠል እንዳለበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ገለጹ፡፡ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሀመድ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ፤ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ/ አገዛዝ ወቅት የሰብዓዊ ጥሰትና የመብት ረገጣ ከተፈፀመባቸው ኢትዮጵያውያን መካከል የሱማሌ ክልል ህዝብ ቀዳሚው ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በአገዛዙ ከፍተኛ በደልና ሰቆቃ እንደደረሰባቸው አስታውሰው ፤ የሶማሌ ክልል ህዝብም በቀዬው በሰላም ተረጋግቶ እንዳይኖርና የክልሉን ሀብት አልምቶ እንዳይጠቀም ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል። ንጹሃንን መጨቆን፣ የሀብት ዘረፋና ምዝበራ፣ አስገድዶ መድፈር፣ እስራትና ግርፋት የስርዓቱ መገለጫዎች ሆነው የሱማሌን ህዝብ በሀገሩ ባይተዋር እንዲሆን አድርገውት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ከለውጡ በፊት የነበሩ አስር ዓመታት ለሶማሌ ክልል ህዝብ በንብረቱ የማያዝበት፣ ከቤት ወጥቶ በሰላም የማይመለስበት አስከፊ ጊዜ ማሳለፉን ጠቁመዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም፣ ከለውጡ በኋላ የሱማሌ ክልል መንግስት ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት፣ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በውይይት ልዩነቶችን በመፍታት፣ የተፈናቀሉትን በማቋቋም በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ተደርጓል ብለዋል፡፡ በክልሉም ሆነ በፌዴራል ተቋማት ለቁጥር ማሟያ ብቻ ሲደረግ የቆየውን የአመራር ስምሪት በማስቀረት በብቃታቸው ተወዳድረው ኢትዮጵያን ማገልግል የሚችሉ ብቁ አመራሮችን ማፍራት መቻሉንም እንዲሁ። የሶማሌ ክልል ህዝብ በአካባቢው በሰፈነው ሰላምና መረጋጋት በተለያዩ የልማት ዘርፎች ተሰማርቶ የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለአብነት የክልሉን ህዝብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት ከተገነቡ 18 ሆስፒታሎች መካከል ዘጠኙ የተሰሩት ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ 260 ጥልቅ የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ መለስተኛ ግድቦችን በመስራት፣ ስምንት ከተሞችን የውሀ አቅርቦት እንዲኖራቸው በማድረግና ብዙ መንደሮችን የሚያገናኝ የውሃ መስመር ዝርጋታ በማከናወን የክልሉን የውሃ ሽፋን በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡ የሶማሌ ክልል ህዝብ "በንብረቱ የማያዝዝበት፤ ሰብዓዊ መብቱ የሚረገጥበት ዘመን አሁን አክትሟል ያሉት" ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ "በግብርና እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችን ለማስጠቀል የክልሉን ሰላም በንቃት መጠበቅ እንዳለበት" አሳስበዋል፡፡ ከለውጥ በኋላ በፍትህ አካላት፣ በህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲሁም በዲሞክራሲ ተቋማት ላይ በርካታ ማሻሻያዎች ተደርገው ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቋንቋን፣ ሃይማኖትን እና ዘርን ሽፋን ያደረገ የአክራሪነትና የፅንፈኝነት አካሄድ ህዝቡ ታግሎ ያመጣውን ለውጥ እየፈተነ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች አቀንቃኝነት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን እረፍት እየነሳ ያለውን የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እኩይ አስተሳሰብና ድርጊት በጋራ መከላከል አለብን ነው ያሉት።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት በሙሉ መተማመን እየደገፈ ነው-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Mar 30, 2023 80
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት በሙሉ መተማመን እየደገፈ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለፁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከሳዑዲ ዜጎችን የማምጣት ተግባር ከተጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ 125ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት መመለስ መቻሉንም ተናግረዋል። ሳምንቱ በሰላም፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ጠንካራ እንቅስቃሴ የተደረገበት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት በሙሉ መተማመን እየደገፈ መሆኑንም ተናግረዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት በዘላቂነት ለማቆም በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በመፈጸም ረገድ መንግሥት በርካታ ስራዎችን ማከናወኑንም ነው ያነሱት። መሰረታዊ አገልግሎችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ እንዲሁም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም እንዲሁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሰላምና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን አስተሳስሮ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት በማስፈን በጋራ ለመልማት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር ትሰራለች ብለዋል። በተለይም ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችሉ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል-የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ
Mar 30, 2023 62
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመለወጥ ለዜጎች የምትመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ኢትዮጵያ በቅድመ 2010ዓ.ም በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በርካታ ፈተናዎች ገጥመዋት በቁልቁለት ጉዞ ላይ እንደነበረች" አስታውሰዋል። በተለይም የሥራ አጥነት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የፕሮጀክቶች መጓተትን ጨምሮ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በከፍተኛ ደረጃ የሚጣሱበት ሁኔታ እንደነበር ገልጸዋል። የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የታፈነበትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ጭላንጭል ጠፍቶ የነበረበት አጋጣሚ እንደነበርም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። የዜግነት ዲፕሎማሲ የተገፋበት፣ የሀገር ጥቅም ቅድሚያ የማይሰጥበት፣ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተዛባ ግንኙነት የነበረበት አገርና ህዝብን የሚጎዳ አካሄድ እንደነበርም ገልጸዋል። በእነዚህ እና በሌሎችም ተደራራቢ ችግሮች ኢትዮጵያ በቁልቁለት ጉዞ ላይ ትገኝ ነበር ብለዋል አቶ አደም። አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ግን ባለፉት አምስት አመታት በርካታ ውስብስብ አገራዊ ችግሮችን በመፍታት ለዜጎች የምትመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጥረት ተደርጓል ብለዋል። በሂደቱ በርካታ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች ቢያጋጥሙም ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመለወጥ በተለያዩ መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች መምጣታቸውን አብራርተዋል። በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው መስክ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ አካታችና ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሥርዓት በመከተል የተሳካ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል። የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትም የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች ተደርገው ሁሉንም አሳታፊ የሆነ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ማኖር ተችሏል ነው ያሉት። ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመለወጥ ስልትም በኢኮኖሚው መስክ የዕዳ ጫናን በማቃለልና ምርታማነትን በማሳደግ የላቀ አፈፃፀም መመዝገቡን አንስተው፤ በተለይም በስንዴ ልማት፣ በቡና፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ የተገኙትን ውጤቶች ለአብነት ጠቅሰዋል። የቱሪዝም አቅምን የመጠቀም፣ በሌማት ቱርፋት፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የተመዘገበው ስኬትም ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል። በፖለቲካው መስክ የሀሳብ ብዝሃነት እንዲከበር፣ ስልጣን በሀሳብ ልዕልና እንዲያዝ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረው በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የታየውን ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደትም አንስተዋል። በዲፕሎማሲው መስክ ጎረቤት ሀገራትን ያስቀደመ የትብብር ግንኙነትና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመከተል የኢትዮጵያን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም፣ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ጥረት መደረጉን ገልጸዋል። በቀጣይም የተጀመሩ ስኬታማ ሥራዎችን በማስቀጠል ፈተናዎችን ተጋፍጦ በማሸነፍ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑን አቶ አደም አረጋግጠዋል። የተቋማት ግንባታና የዴሞክራሲ ባህልን ማጠናከር፣ ምርታማነትን መጨመር፣ ሌብነትና ጽንፈኝነትን መታገል፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ በቀጣይም ቁልፍ ሥራዎች ሆነው ይቀጥላሉ ብለዋል። በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት መፍጠር፣ አገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን መሥራትና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሥራ ላይ ውሎ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ በማድረግ ሂደት የመንግስት ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከስራ አሰናበተ
Mar 30, 2023 134
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ። ምክር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።   በስብስባው ላይ በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የስራ ስንበት የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል። አቶ ፋንታሁን የዳኞች የስነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ክስ ስነ-ስርዓት ደንብ በመተላለፍና የሐቀኝነት ተነጻጻሪ ግዴታ በመተላለፍ ከአመልካች ብር 100ሺህ መደለያ መቀበላቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል። ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የአቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የስራ ስንብት የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 13/2015 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ማህበራዊ
በግለሰብ ቤት የተከማቸ የተበላሸ ቴምር ከወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን ፖሊስ ገለጸ
Mar 30, 2023 30
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ በግለሰብ ቤት የተከማቸና ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ንፅህናውን ያልጠበቀና የተበላሸ በርካታ ቴምር ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ታይዋን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። ግለሰቦቹ በመኖሪያ ግቢያቸው በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የተበላሸና በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል በርካታ ቴምር ንጽህና በጎደለው ሁኔታ አስቀምጠው ለአትራፊ ነጋዴዎች በፌስታል አሽገው የ92ሺህ ብር ከሸጡላቸው በኋላ የተበላሸ መሆኑን የተገነዘቡት ገዢዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ሊያዙ ችለዋል፡፡   መረጃው የደረሰው በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የእፎይታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያም ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማወጣትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ግቢ መጋዘን ውስጥ ባደረገው ፍተሻ መጥፎ ጠረን ያለው የተበላሸ በርካታ ቴምር ተከማችቶ ተገኝቷል። በክፍለ ከተማው የወረዳ 10 አስተዳደር የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብቱ መካ በበኩላቸው በቁጥጥር ስር የዋለው ቴምር ወደ ህብረተሰቡ ቢሰራጭ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።   ተበዳዮቹ ከተጠርጣሪዎቹ የገዙትን የተበላሸ ቴምር ለህዝብ ሳይሸጡ እና የግል ጥቅም ሳያጓጓቸው ለሰዎች ጤና በማሰብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ጊዜና ወቅትን እየጠበቁ ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ነጋዴዎችም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ተገንዝበው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ኢዜአ በአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል-ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ
Mar 30, 2023 41
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚና ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ገለጸ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለጋዜጠኞቹ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ሙያዊ ዘገባ መስራት የሚያስችል ለሶስት ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።   የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለጋዜጠኞቹ ሙያዊ ልምዱንና የዘገባ ንድፈሀሳቦችን ለጋዜጠኞች አጋርቷል። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚዲያ ተቋም ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ስም ያለው ተቋም መሆኑን አውስቷል። የዜና አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ አልፎ በቅኝ ግዛት ዘመን ድምፅ አልባ ለነበሩ አፍሪካውያን ድምፅ በመሆን ለነጻነታቸው እንዲታገሉ መረጃዎችን ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል። በአፍሪካ ቀዳሚው የዜና አገልግሎት የሆነው ኢዜአ፤ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መሪዎችን እና የነጻነት ታጋዮችን ታሪክ በመሰነድም ኢትዮጵያን በጉልህ ማስጠራቱን ጠቅሷል። ጋዜጠኛ ጥበቡ እንደሚለው በአፍሪካ ትልቅ ታሪክ እና ስም ያለው ይህ የዜና አገልግሎት በአህጉሪቱ ወደነበረበት ከፍታ እንዲመጣ መስራት ይጠበቅበታል። አገልግሎቱ በአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ ለመሆን በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ፣ በሰው ኃይልና በሌሎች መስኮች የጀመረውን ሁለንተናዊ ተቋማዊ ማሻሻያ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መክሯል። ለአገልግሎቱ ቀጣይ ስራ መሳካት አመራሩና ጋዜጠኞቹ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝቧል። ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ጋዜጠኝነት ሁሌም እየተማሩ የሚኖሩት ስራ በመሆኑ በየጊዜው ለዘጋቢዎች የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱም ባለሙያዎችን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቁሟል።   የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነትና የስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወንዲራድ ኢዜአ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የአቅም ግንባታ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ ገጽታን በመገንባት እንዲሁም የመረጃ ምንጭነቱን አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችል ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በስልጠናው የተሳተፉ የኢዜአ ጋዜጠኞች በበኩላቸው ስልጠናው ለቀጣይ ስራዎቻቸው ተጨማሪ እውቀት የሚገበዩበት መሆኑን ገልጸዋል። ኢዜአ ለሌሎች መገናኛ ብዙሃን የዜና ምንጭ በመሆኑ ጥራት ያለውና አስተማማኝ መረጃ ለማድረስ በየወቅቱ አቅማቸውን የሚያሳድጉ መሰል ስልጠናዎች መሰጠታቸው ተገቢ ነው ብለዋል።    
የወላይታ ዞን አስተዳደር በአበላ አበያ ወረዳ በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
Mar 30, 2023 36
ሶዶ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ)፦ የወላይታ ዞን አስተዳደር በአበላ አባያ ወረዳ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ሚስማር፣ የግድግዳና ማገር እንጨትና ሌሎች ቁሳቁችን ያካተተ ነው።   ድጋፉን የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ ለአበላ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል መና አስረክበዋል። ድጋፉ የዞኑ አስተዳደር፣ የወረዳና ከተማ መዋቅሮችን በማስተባበር መሰብሰቡ ተገልጿል። የተፈናቀሉ ዜጎችን ከጊዜያዊ ሰብአዊ ድጋፍ ባለፈ በዘላቂነት ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ አሊያም ወደ ተሻለ ቦታ በማዛወር ለማቋቋም አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዋና የመንግስት ተጠሪው ገልጸዋል።   በዞኑ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል በበኩላቸው ተፈናቃዮች በዘላቂነት ሕይወታቸውን የሚመሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የአበላ አበያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል መና ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በዘላቂነት ቋሚ ቤት እንዲሰራላቸው ቦታ ማመቻቸትን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።   ከዞኑ የአስተዳደር መዋቅሮች ለተደረገው ድጋፍም አቶ ሳሙኤል መና ምስጋና አቅርበው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በአበላ አባያ ወረዳ በሚገኙ ጮካሬ፣ ሰላም ጓድ፣ አባያ ጉርቾና አባያ ማራጫ በሚባሉ አራት ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎች የብላቴ ወንዝ ሙላት ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ምክንያት መፈናቀላቸው ይታወቃል።
በድሬዳዋ ህብረተሰቡ ከድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ራሱን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት---ማዕከሉ
Mar 30, 2023 36
ድሬዳዋ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ) በድሬዳዋና ዙሪያዋ እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ የሚከሰት ጎርፍ በሰውና በንብረት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅና መካከለኛ ኦሮሚያ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳሰበ። ባለፉት አራት ሳምንታት በድሬዳዋና በዙሪያው በሚገኙ ወረዳዎች እየጣለ ያለው ዝናብ ጎርፍ እያስከተለ ይገኛል።   የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ትዕዛዙ ገረመው ለኢዜአ እንደተናገሩት፣ በድሬደዋና በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በአሁኑ ወቅት እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ መጠናከር ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል። በጎርፍ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ገልጸው፣ በተለይ ከጎርፍ መውረጃ አካባቢዎች በመራቅ ራሱን መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። የሚመለከታቸው ተቋማትም አደጋውን ቀድሞ መከላከል እንዲቻል ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የለውጥና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ በበኩላቸው ሰሞኑን የጣለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ አደጋ አስከትሏል።   በተለይ በድሬዳዋ አሸዋ በተባለው የደቻቱ ጎርፍ መውረጃ ስፍራ ላይ ተኝቶ የነበረ አንድ ግለሰብ በጎርፍ ምክንያት ህይወቱ ማለፉን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በጎርፍ መውረጃው አሸዋ ላይ የነበረውን ልባሽ አልባሳት በጎርፍ ተጠርጎ መውሰዱን ገልጸዋል። ከአምስት ቀናት በፊትም ከድሬዳዋ ተጎራባች አካባቢዎች ድንገት በቀን የመጣው ጎርፍ በቀፊራ የገበያ አካባቢ የአትክልትና ፍራፍሬ ንብረት መውሰዱን አስታውሰዋል። እንደኮማንደር ገመቹ ገለፃ አንዳንድ ነዋሪዎች በአሸዋው ላይ የሚያልፈውን ጎርፍ ለማቋረጥ የሚያደርጉት ሙከራ ለአደጋ እያጋለጠ ይገኛል። ፖሊስ ከገጠር ቅርንጫፎች ጭምር የደረሰውን መረጃ ለህብረተሰቡ ከማሳወቅ ባለፈ ሰዎች ከቦታው እንዲነሱ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። በቀጣዮቹ ቀናት መሰል ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ የራሱን ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ በጎርፍ መውረጃ ሥፍራ ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ማከናወን እንደሌለበት አሳስበዋል። በድሬዳዋ አስተዳደር የአደጋ ስጋት አመራር ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር አቶ አብዱልሰላም ዩሱፍ በበኩላቸው፤ በጉዳዩ ላይ ለህብረተሰብ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። "በተለይ የጎርፍ አደጋ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎችና በጎርፍ መውረጃዎች ላይ የሚኖሩና የሚነግዱ ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው" ብለዋል። የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በድሬዳዋ ገጠር የተሰሩ የግንብና የጎርፍ መውረጃ ቦዮች በአግባቡ እየተጠገኑ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ወርቅነህ ናቸው። ባለስልጣኑ ከድሬዳዋ ሥራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት፣ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ ከጽዳትና ውበት ኤጀንሲ እንዲሁም ከድሬዳዋ ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት የጎርፍ አደጋን የመከላከልና ውሃውን ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ የጎርፍ መከላከያ አዲስ ግንቦችን የመገንባትና ነባሮቹን የመጠገን፣ የጎርፍ መውረጃ ትቦዎችን ከደለል የማፅዳት እንዲሁም በገጠር የጎርፍ መውረጃ አካባቢዎች ላይ የድንጋይ ክትሮችና የተፋሰስ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው ያስታወቁት። ጎርፍ የሚፈስበትን ስፍራ ለተለያዩ አገልግሎቶች ማዋል ተገቢ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት መቆጠብ እንዳለበትም አሳስበዋል።  
ኢኮኖሚ
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የብሔራዊ ባንክ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ገለጹ
Mar 30, 2023 65
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የብሔራዊ ባንክ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያካሄደው ሰፋ ያለ ጥናት ዛሬ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ሆኗል። የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ የቀረበው ጥናት በዘርፉ ያሉ ችግሮችንና የተለያዩ የውጭ ሀገራትን ተሞክሮዎችም ጭምር በጥልቀት የዳሰሰ ነበር።   የጥናቱን ግኝቶች መነሻ በማድረግ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና የገንዘብ ዝውውርን ሰንሰለት ለመበጠስ እንዲሁም የድርጊቱ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የፖሊስ፣ የሥርዓትና የተጠያቂነት መፍትሄዎችን የሚጠቁሙ ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል። በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አመላክቷል። በጥናቱ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የውጭ ምንዛሬ ገበያዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣ የኑሮ ውድነትን በማናርና ሙስናን በማስፋፋት ሀገርን ለከፋ አደጋ እያጋለጡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡ በህገ-ወጥ ተግባራቱ መንግሥታዊና የግል ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር የሚሳተፉ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ ከውጭ ሀገራት እስከ መሀል ሀገር የተዘረጋው ህገ-ወጥ የጥቅም ትስስር በደላሎች፣ በድርጅቶች፣ በኩባንያዎችና በባንክ ሥርዓቱም ጭምር እንደሚደገፍ አመልክቷል። ይህም በሀገራችን እየታየ ላለው ቅጥ ያጣ የዋጋ ንረትና ማህበራዊ ችግር አንዱ ቁልፍ ምክንያት መሆኑን አሳይቷል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት፤ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ የሀገርን ህልውናና የህዝብን ጥቅም እየተፈታተነ ያለ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን በመረዳት አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብና ህዝቡ በትብብርና በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡   በጥናቱ የተለዩና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች፣ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እርምጃ በቀጣይነት የሚወሰድ መሆኑን ነው የገለፁት። ህገ-ወጥነትን በመቆጣጠር፣ የሀገርንና የህዝብን ህልውና በመታደግ ትግሉ ውስጥ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የህግ አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ተቀናጅተውና ተናበው ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳስበዋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከብሔራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀትና ሌሎች አካላትን በማሳተፍ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ ባንኩ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳይችል እንቅፋት ሆነዋል፣ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ ነው።   የውጭ ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን የብር እንቅስቃሴውም ከባንክ ሥርዓት ውጭ በመዘዋወር ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለ መሆኑ ተደርሶበታል ያሉት አቶ ማሞ በርካታ የብር ኖቶችን ከባንክ ሥርዓት ውጭ በማንቀሳቀስ ላልተፈለገ ዓላማ በሚያውሉ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። በቀረበው ጥናት ላይ ውይይት ያደረጉ የብሄራዊ ባንክ ገዢን ጨምሮ የመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበው ጥናት አጠቃለይ ችግሩን፣ የችግሩን ተዋንያን እና የመፍትሄ ሐሳቦችን በሚገባ ያመላከተ በመሆኑ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ምስጋና ማቅረባቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኅን በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
በሲዳማ ክልል ያሉ የቱሪስት መስህቦችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል--የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
Mar 30, 2023 31
ሀዋሳ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎችን ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሀላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለኢዜአ እንደገለጹት ገቢው የተገኘው ባለፉት ሰባት ወራት ክልሉን ከጎበኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ነው። ገቢው ከቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች በደረሰኝ የተሰበሰበ ገቢን ጨምሮ ከሆቴልና ሌሎች የቱሪስት አገልግሎቶች የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል። ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተገኘው መረጃ መሰረት ባለፉት ሰባት ወራት ክልሉን ለመጎብኘት ከመጡ ቱሪስቶች መካከል 20ሺህ የሚሆኑት የውጪ ሀገር ጎብኚዎች መሆናቸውን አቶ ጃጎ ገልጸዋል። ወደ ክልሉ በመደበኛነት ከሚመጡ የሀገር ውሰጥና የውጪ ጎብኚዎች በተጨማሪ በሀዋሳ የሚከናወኑ ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊና ህዝባዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚመጡ ጎብኚዎች ለቱሪስት ፍሰቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን አውስተዋል።   በክልሉ ያሉትን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ የመስህብ ስፍራዎችን በጥናት በመለየትና በአራት ማዕከል በማደራጀት ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አቶ ጃጎ አስረድተዋል። በሀዋሳ ከተማ ማዕከል ስር የሀዋሳ የፍቅር ሀይቅ፣ የዓሳ ገበያ፣ የታቦር ተራራ፣ የወንዶ ገነት የተፈጥሮ ደንና ፍል ውሀን የያዘ የመስህብ ስፍራ እንደሚገኝበት ጠቅሰዋል። የመስህብ ስፍራዎቹን በድረ-ገጽ በሀገር ውስጥና በውጪ መገናኛ ብዙሀንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አብዛኞቹ በሀዋሳ ከተማ መገኘታቸው በሌሎች አካባቢዎች ጎብኚዎች እንዳይቆዩ ማድረጉን ጠቁመዋል። ይህንን ችግር ለማቃለል በቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍና በሆቴል ስራ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለፍጻሜ ለማድረስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉም ዜጋ ተሳትፎውን ሊያጠናክር ይገባል--የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት
Mar 30, 2023 37
ሆሳዕና መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለፍጻሜ ለማድረስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉም ዜጋ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ተጠየቀ። ለግድብ ግንባታ የሚሆን ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በሆሳዕና ከተማ ተጀምሯል። በመርሀ ግብሩ ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ መኮንን መንገሻ እንዳሉት በዜጎች የተቀናጀ ርብርብ የተጀመረው የግድቡ ግንባታ በመገባደድ ላይ ይገኛል። የግድቡን ስራ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ የሁሉንም ህብረተሰብ ጠንካራ ድጋፍና ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።   የግድቡ ግንባታ ከፍፃሜ መድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የግብርና ልማት እንቅስቃሴውን ለማሳለጥና ቱሪዝምን በማስፋፋት ረገድ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች እንዳሉት ገልጸዋል። ለመጪው ትውልድ አሻራ ለማኖርና የሀገሪቱን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ስላለው ህብረተሰቡ እስካሁን ሲያደርግ የነበረውን ተሳትፎ በማጎልበት ግድቡን ለስኬት እንዲያበቃ ተወካዩ ጥሪ አቅርበዋል። በደቡብ ክልል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚልክያስ እስራኤል በበኩላቸው ግድቡ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ተሻግሮ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ መድረሱን አንስተው፤ ለዚህም ህዝቡና መንግሥት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ተናግረዋል።   በደቡብ ክልል የሀዲያ ዞን ህዝብ እስካሁን ለግድቡ 100 ሚሊዮን 613ሺህ ብር በቦንድ ግዥና በድጋፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታውሰው፤ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል። “ግድቡ የአሁኑ ትውልድ አሻራ የመጪው ትውልድ ቅርስ” ነው ያሉት የ50ሺህ ብር ድጋፍ ያበረከቱት የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው አቶ ደበበ ኤርመኮ ግድቡ እዚህ ደረጃ ላይ በመድረሱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ በከተማው ዛሬ በነበረው ቆይታ የቦንድ ሽያጭን ጨምሮ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ያካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በዲላ ከተማ 7ሺህ 935 ነዋሪዎች በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ
Mar 30, 2023 52
ዲላ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ 7ሺህ 935 የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ነዋሪዎች በሰፍቲኔት ፕሮግራም ወደ ሥራ መግባታቸውን የከተማው ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በፕሮግራሙ በተፈጠረላቸው የሥራ እድል ኑሯቸውንና የከተማውን ገጽታ ለመለወጥ እንደሚተጉ ተጠቃሚዎቹ ገልጸዋል። የከተማው ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት በበኩሉ፤ ፕሮግራሙ የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ችግር ከማቃለል ባለፈ የከተማውን ልማትና ዕድገት ከማገዝ አንጻር ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን አመልክቷል።   የጽህፈት ቤቱ ሐላፊ አቶ እድሉ ታደሰ የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ባንክ ባወጡት መሰፈርት መሰረት የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው 7ሺህ 935 ነዋሪዎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ሆነዋል። "ተጠቃሚዎቹ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ በተፋሰስ ልማትና በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እንዲሁም በአነስተኛ መሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች በመሳተፍ ኑሯቸውን የሚደግሙ ይሆናል" ብለዋል። ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ለሚካሄደው ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከዓለም ባንክ ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ጠቅሰዋል።   ተጠቃሚዎቹ ቆይታቸው ሲጠናቀቅ ወደ ቀደሞ ሕይወታቸው እንዳይመለሱ በየወሩ በሚቆጥቡት ገንዘብ ላይ ተጨማሪ ሀብት በማከል ወደ ተሻለ የሥራ መስክ የሚሰማሩበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን ሐላፊው አስታውቀዋል። "የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ወገኖች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ወደ ሚደጉሙበት ሥራ መግባታቸው ለነዋሪውና ለከተማው ልማት ጠቀሜታው ድርብ ነው" ያሉት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ ናቸው። በተለይ በከተማው ስር የሰደደ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ችግር ከማቃለል ባለፍ ለማህበራዊ ለውጥ በተለይ በልጆች ትምህርትና ጤና ላይ መሻሻል ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።   ተጠቃሚዎች እድሉን በመጠቀም የሚያገኙትን ገቢ በመቆጠብና በአግባቡ በመጠቀም ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ለሌሎች ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል። ተጠቃሚዎች በበኩላቸው በተሰማሩት የስራ መስክ ጠንከረው በመስራት ከራሳቸው አልፈው ለከተማው ልማት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል ወይዘሮ አይናለም አለሙ እንደገለጹት፤ መንግስት የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ ችግራቸውን እንደሚያቃልልላቸው ገልጸዋል። በተሰማሩበት የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥራ ጠንከረው በመሥራት ኑሯቸውንና የከተማውን ገጽታ ለመቀየር ዝግጁ መሆናቸውን አመልክተዋል።   ባለባቸው የአቅም ችግር ልጆቻቸውን ለማስተማር ይቸገሩ እንደነበር ያነሱት ደግሞ ወይዘሮ ፋጤ የሱፍ ናቸው። መንግስት ችግራቸውን ተረድቶ የሥራ እድል ተጠቃሚ ስላደረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ያገኙትን እድል በአግባቡ በመጠቀም ኑሯቸውን ለማሻሻልና ከተማቸውን ለመለወጥ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። በከተማው የዛሬዎቹን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ10ሺህ በላይ ነዋሪዎች በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሐ-ግብር ወደ ሥራ በመግባት ተጠቃሚ መሆናቸውን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እኤአ በ2025 ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሊያጡ ይችላሉ- ተመድ
Mar 27, 2023 142
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እኤአ በ2025 ከአገር ውስጥ ዓመታዊ ምርታቸው ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሊያጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ "የፈጠራና ቴክኖሎጂ ለፆታ እኩልነት" በሚል መሪ ሃሳብ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ውይይት አካሂዷል።   የድርጅቱ የሰብአዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ፤ የዲጂታል ዘመን ሥራዎችን ቀላል በማድረግ በተለይም ሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ዕድሎችን ይዞ መጥቷል ብለዋል። በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ተደራሽነቱን ማስፋት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አካታች የዲጂታል ስትራቴጂ ተግባራዊ አለማድረግ በማኅበራዊና የምጣኔ ሃብት እድገት ላይ ተጽዕኖው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ አገሮች በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት። አፍሪካን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ባለፉት አሥርት ዓመታት ለአካታች ኢንተርኔት ትኩረት ባለመስጠታቸው ከዓመታዊ የአገር ውስጥ ምርታቸው 1 ትሪሊየን ዶላር ማጣታቸውን ተናግረዋል። በመሆኑም መንግሥታት ክፍተቱን ለመሙላት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እ.ኤ.አ በ2025 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር ሊያጡ ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የክህሎትና እውቀት ክፍተት፣ የኢንተርኔት ዋጋ አቅምን ያገናዘበ አለመሆን፣ ፆታዊ ትንኮሳ፣ የመጠቀሚያ መሳሪያዎች እጥረት የዘርፉ ፈተናዎች መሆናቸውን ዶክተር ካትሪን ገልጸዋል። በ2025 ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዋን የተሳካ ለማድረግ ስትራቴጂ ቀርፃ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው፤ ዕቅዱ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፤ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ የለውጥ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል። በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የዲጂታል ተጠቃሚነት ዕድልና ክህሎት ልዩነት ለማጥበብ እንደ አገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይም መሰል ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ይሆናል ብለዋል።
አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ ላይ እየተሰራ ነው
Mar 27, 2023 149
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ። አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሴቶችን የዲጂታል ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ ተከብሯል።   በዚሁ ጊዜ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለችው ዲጂታል 2025 መርሃ-ግብር ሴቶች ቴክኖሎጂን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጠቀሙ ካደረጉ ችግሮች ውስጥ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ማነስ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን አካታች ምጣኔ ሀብትን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል የዲጂታል ዕውቀት ልዩነትን ለማጥበብ እንደ ሀገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይ በጥናቱ ግኝት መሰረት እስትራቴጂ በመቅረጽ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 የያዘቻቸውን እቅዶች ለማሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመድረኩ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ተወካይ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አካታች ዲጅታል መርሃ ግብሮችን ባለመተግበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ እንደሆኑ በመድረኩ ተነግሯል።
የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገለጸ
Mar 25, 2023 233
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015(ኢዜአ)፦ የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ.ኤች.ዲ.) ከቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ዋና ሊቀመንበር ሰር ቶኒ ብሌር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ትብብርና በቀጣይ ለመስራት ባቀዷቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 (ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን) ስትራቴጂ ከዝግጅት ወቅት አንስቶ እስከ ማስፈጸም ሂደት በቴክኒክ(ባለሙያ)፣በኢ-ሰርቪስ ትግበራ ላይ ጥናት በማድረግ፣የማስፈጸም አቅም እንዲሁም የአደረጃጀትና የስራ ሂደትን ለማሻሻል የሚያስችል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል። ኢንስቲትዩቱ ከዲጂታል መሰረተ ልማት አኳያ በዳታ ሴንተር፣በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ በክላውድና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ በቀጣይ ሊያደርገው በሚችለው ድጋፍ ውይይት መደረጉ ተመላክቷል። በሌላ በኩል የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ለሰር ቶኒ ብሌር የዲጂታል መታወቂያን አገልግሎቶች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ለአገልግሎቱ የሚያደርገውን ድጋፍ እና ከመሰረተ ልማት ጋር ያሉ ተግዳሮቶች ላይም ገለጻ አድርገዋል። የ69 ዓመቱ የእንግሊዝ የቀድሞ ፖለቲከኛ አገሪቷን ከእ.አ.አ 1997 እስከ 2007 በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የመሪነቱን ሚና እየተወጣ ነው-ፍሬህይወት ታምሩ
Mar 24, 2023 226
አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015 (ኢዜአ) ኢትዮ- ቴሌኮም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የመሪነቱን ሚና እየተወጣ መሆኑን የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ መልክ ያበለጸገውን ቴሌ ብር "ሱፐር አፕ" የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል። መተግበሪያው ደንበኞች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማቅለልና በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስራዎችን ለማሳለጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በአንድ ጊዜ ፈርጀ ብዙ የዲጂታል ግብይት አገልግሎቶችን እንዲያገኙና ለማንኛውም የግዢ ሂደት እንዲጠቀሙ የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑም ተመላክቷል። ይህ አዲሱ መተግበሪያ አሁን በስራ ላይ ካለው የቴሌብር መተግበሪያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአፈጻጸም፣ የሴኩሪቲ ሲስተም፣ የስልክ ዳታ የመያዝ አቅም ውስንነትንና ሌሎች የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል። እንዲሁም የማይ- ኢትዮ- ቴል መተግበሪያንና ሌሎች መተግበሪያዎችን በአንድ በማካተት የተቀናጀ፣ ብቁ እንዲሁም አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የኢትዮ -ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኩባንያው አገልግሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ይገኛል። የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን የማድረግ ሥራን አጠናክሮ በመቀጠል ኢትዮ-ቴሌኮም በዘርፉ የመሪነት ሚናውን እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፤ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነውም መተግበሪያ ይህንኑ እንደሚያጎለብት ተናግረዋል። ሌላኛው የስማርት ስልክ አጠቃቀም መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ በኔትወርክ ላይ ከተመዘገቡት 81ሚሊየን ቀፎዎች ውስጥ 46 በመቶ የሚሆኑት የስማርት ቀፎዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው መተግበሪያ ቴሌ ብር ሱፐር አፕ ለተለያዩ አገልግሎት የምንጠቀምባቸው አፕሊኬሽኖችን በአንድ መተግበሪያ ላይ ሁሉንም መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ጊዜንና ወጭን በመቆጠብ ረገድ መተግበሪያው ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።        
ስፖርት
12 የመደመር ትውልድ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት በመጪው ሰኔ ወር ለአገልግሎት ይበቃሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 30, 2023 45
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ) በመዲናዋ ከ “መደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ የሚገነቡት 12 የሕጻናትና ወጣቶች የመጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ግንባታቸው በመጪው ሰኔ ወር ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በአዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከል ግንባታ የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ ተከናውኗል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቆሼ አካባቢ ቴኒስ ሜዳ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፈረንሳይ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከላት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከ“መደመር ትውልድ” መጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ለወጣቶችና ሕጻናት የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መፅሐፉን በስጦታ ማበርከታቸውን አስታውሰዋል፡፡ መጽሐፉ ትውልድ ቀረጻ ላይ ያተኮረ መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፤ ሽያጩ የሚካሄደውም በሚሰበሰበው ገቢ ትውልድ የሚቀረፅባቸውን ማዕከላት ለመገንባት ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለትም 12 የመደመር ትውልድ የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከላት ግንባታ መጀመሩን ጠቅሰው፤ በመጪው ሰኔ ወር ግንባታቸው እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል። ያለፉት ትውልዶች በዘመናቸው ከፈጸሟቸው መልካም ተግባራትና ጉድለቶች የተሻለች ሀገር የሚገነባ ትውልድ ለመፍጠር ሃሳብና ምቹ ስፍራ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በአእምሮና በአካል የዳበረ ሀገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት በተጀመረው ፕሮጀክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም በመደመር እሳቤ በሀገሩ የሚኮራ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነቱን የሚያስጠብቅ ትውልድ ለማፍራት ከአምስት ሺህ ያላነሱ የስፖርት እና የመዝናኛ ስፍራዎችን እንሰራለን ብለዋል፡፡ ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ሁሉም በትኩረት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን በበኩላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው ትኩረት 235 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንበተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹም የፋት-ሳል፣ እግር ኳስ፣ እጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቮሊቦልና ጠረጴዛ ቴኒስን ያካተቱ ናቸው ብለዋል።      
በአዲስ አበባ ከተማ የ “መደመር ትውልድ” የወጣቶችና ሕጻናት የመጫወቻና ስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተካሄደ ነው
Mar 30, 2023 92
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ ከ “መደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ ለሚገነቡ የሕጻናትና ወጣቶች የመጫዎቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐግብር በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። በመርሐግብሩ አማካኝነት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በተመሳሳይ አንድ የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐግብር ተከናውኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቆሼ አካባቢ ቴኒስ ሜዳ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፈረንሳይ እየሱስ ሜዳና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከላት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ከ “መደመር ትውልድ” መጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ለወጣቶችና ሕጻናት የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በስጦታ ማበርከታቸውን ከንቲባ አዳነች አስታውሰዋል፡፡   “የመጽሐፉ ሽያጭ የሚካሄደው ገቢ ማግኛ ብቻ ሳይሆን ትውልድ የሚገነባበት ታላላቅ ሃሳቦች በውስጡ የያዘ ነው” ብለዋል። ያለፋት ትውልዶች የሰሩት መልካም ተግባርና ጉድለቶች አሉ ያሉት ከንቲባዋ ከእነሱ የተሻለውን በመማር አገር የሚገነባ ትውልድ ለመፍጠር ሃሳብና ምቹ ስፍራ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሚገነቡት የወጣቶችና ሕጻናት የመጫወቻና ስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት በሶስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ተገልጿል። በመርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች፣ ነዋሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሶስተኛው የኢትዮጵያ ፓራኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና መክፈቻ አራት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል
Mar 29, 2023 70
አዲስ አበባ መጋቢት 20/2015(ኢዜአ)፦ በሶስተኛው የኢትዮጵያ ፓራኦሊምፒክ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መክፈቻ ቀን አራት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል። የኢትዮጵያ ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ያዘጋጀው ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዛሬ ተጀምሯል። በውድድሩ ላይ ከአምስት ክልሎችና ሁለት ከተማ መስተዳደሮች የተወጣጡ ወንድ 254 ሴት 126 በድምሩ 380 ስፖርተኞች ተሳታፊ ናቸው። በተጨማሪ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚና የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ክለብ በውድድሩ ተሳታፊ መሆናቸው ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ጊዮን ሰይፋ (ዶ/ር) ውድድሩ ተቀዛቅዞ የቆየውን የፓራኦሊምፒክ ስፖርት ማነቃቃትና በቀጣይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፋ ስፖርተኞችን ለመምረጥ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በውድድሩ መክፈቻ አራት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል። በሴቶች 100 ሜትር የእጅ ጉዳት በሴቶች 100 ሜትር የእጅ ጉዳት የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሀያት ይማም ከአማራ ክልል አሸንፋለች። አትሌት ዝናሽ አሳይ ከኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሉባባ ዘውዴ ከአማራ ክልል ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በወንዶች 100 ሜትር አይነስውራን ጭላንጭል አትሌት ኤርሚያስ ቱሉ ከኦሮሚያ ክልል አሸናፊ ሆኗል። አትሌት ይሄነው ካሳሁን ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሁለተኛ ሲወጣ አትሌት ልዑል መረሳ ከአዲስ አበባ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በሴቶች አሎሎ ውርወራ የእግር ጉዳት አትሌት ሀዳስ ምሩፅ ከአዲስ አበባ አንደኛ ወጥታለች። አትሌት ሚሚ ሚካኤል ከሲዳማ ክልልና አትሌት አዳነች ፍቃዱ ከኦሮሚያ ክልል በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በወንዶች 800 ሜትር የዊልቸር አትሌት ደምስ አበራ ፣ አትሌት ምህረት ባዜና አትሌት ፀሐይነህ ተፈራ ሁሉም ከአዲስ አበባ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በላይነት አጠናቀዋል። ከፍጻሜ ውድድሮች በተጨማሪ በተለያዩ ርቀቶች የማጣሪያ ውድድሮች ተከናውነዋል። ሶስተኛው የኢትዮጵያ ፓራኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ መጋቢት 24 2015 እንደሚቆይ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ዊቶልድ ባንካ ጋር ተወያዩ
Mar 29, 2023 93
አዲስ አበባ መጋቢት 20/2015(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ(ዋዳ) ፕሬዝዳንት ዊቶልድ ባንካ ጋር ኢትዮጵያና ኤጀንሲው ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባችው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ዋዳ ለኢትዮጵያ የሚያደርጋቸውን ድጋፎች የተመለከተ ምክክር መደረጉንም ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።   ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላትና አትሌት አበበ ቢቂላ በሮም ማራቶን ድል ካደረገ ጊዜ ጀምሮ በዓለም መድረክ እውቅናዋ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። ዋዳ በፀረ- አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ዙሪያ ለሚያደርጋቸው የቴክኒክ ድጋፎች ምስጋና አቅርበዋል። የዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ዊቶልድ ባንካ ከቀናት በፊት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
አካባቢ ጥበቃ
በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱ ተገለጸ
Mar 26, 2023 149
መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ) በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155 ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በዞኑ ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ መጠናቀቁን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት እንደገለጸው ባለፉት ሁለት ወራት በተከናወነው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ 155ሺህ ሄክታር መሬት የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ ተከናውኗል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ይሳቅ በተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃ የተከናወኑ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን በመቀነስ በኩል ጉልህ አስታዋጽኦ እያበረከቱ ነው። በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ከ155ሺህ ሄክታር መሬትን በመሸፈን በተከናወነው በዚህ ሥራ 3ሺህ ሄክታር መሬትን ከእንስሳት ንክኪ ማካለልን ጨምሮ የችግኝ ዝግጅት፣ 20ሺህ ኪሎ ሜትር የማሳና የተራራ ላይ እርከን ስራ፣ የግጦሽ መሬት ልማትና ሌሎች የድርቅ ተጋላጭነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ከድር እንዳሉት፣ በዞኑ በተደጋጋሚ እየተሰሩ የሚገኙ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን ከመቀነስ በተጓዳኝ የሥራ ዕድል ምንጭ እንዲሆኑ ከ4ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን በዘርፉ ማደራጀት ተጀምሯል። በዞኑ የዳዌ ቃቸን ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ አሚን እንዳሉት፣ በአካባቢያቸው በተደጋጋሚ እያጋጠመ የሚገኘውን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ ለተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቷል። በወረዳው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የተከናወነባቸው ተፋሰሶች በዘላቂነት እንዲጠበቁ ከ30 የሚበልጡ ወጣቶችን በተፈጥሮ ኃብት ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል ብለዋል። ወጣቶቹ ከእንስሳት ንክኪ በተከለሉና በተፈጥሮ ኃብት በተሸፈኑ አካባቢዎች ውስጥ የንብ ማነብ፣ የእንስሳት መኖ ልማት፣ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ነው የገለጹት። በዳዌ ቃቸን ወረዳ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከተሳተፉ ነዋሪዎች መካከል አቶ ያህያ አብዱልወሃብ በሰጡት አስተያየት፣ የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን እንደሚቀንሱ በማመን በስራው መሳተፋቸውን ተናግረዋል። በተለይ ዘንድሮ በአካባቢያቸው በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ወጣቶች እንዲደራጁ መደረጉ ሥራውን ውጤታማ ያደርገዋል ነው ያሉት። ወጣት ሙክታር መሐመድ በበኩሉ፣ በሰው ሰራሽ ተጽእኖ የተነሳ አካባቢያቸው ተራቁቶ እንደልብ ይፈሱ የነበሩ ወንዞች በመድረቃቸው ለድርቅ መጋለጣቸውን አስታውሰዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የተራቆተው አካባቢ አረንጓዴ እየለበሰ መምጣቱ ተስፋ እየሰጣቸው መሆኑን ነው የገለጹት። በአሁኑ ወቅት ከሌሎች 15 የአካባቢያቸው ወጣቶች ጋር የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ማህበራት በመደራጀት በንብ ማነብና የእንስሳት መኖ እየተሳተፈ መሆኑን አመልክቷል።  
በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ ተከናውኗል - የክልሉ ግብርና ቢሮ
Mar 24, 2023 256
ሰቆጣ መጋቢት 15 ቀን 2015(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ መከናወኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በበጋው ወቅት የተከናወኑ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎችን እንዲጠብቁ ለአርሶ አደሮች በባለቤትነት የማስረከብ መርሐግብር በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ ሽመላ ቀበሌ ጋውሳ ተፋሰስ ዛሬ ተካሂዷል።   የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አልማዝ ጊዜው የክልሉን የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የዞንና ቀበሌ ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱንና 34 ሺህ የሚደርሱ የስራ መሳሪያዎች ለዞኖች መከፋፈላቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል። በክልሉ 8 ሺህ 548 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ለማከናወን ታቅዶ፤ በ8 ሺህ 596 ተፋሰሶች ላይ ስራዎቹ መካሄዳቸውን አመልክተዋል። በልማቱ በ331 ሺህ ሄክታር ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውንና በስራዎቹ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት በዘላቂነት በማከናወን የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን መታሰቡን ነው ዶክተር አልማዝ ያስረዱት። በቀጣይም የለሙ ተፋሰሶችን በስነ ሕይወታዊ ዘዴዎች የመሸፈንና የኢኮኖሚ ምንጭ የሚሆኑትን የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ እንዳሉት፤ በአስተዳደሩ በ277 ተፋሰሶች ውስጥ የሚገኝ 4 ሺህ 927 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ተካሄዷል።   በልማቱም ከ82 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንና በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት ተፋሰሶች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እንዳሳደጉትም ገልጸዋል። በተለይም በተራራ ላይ የተሰሩ የጠረጴዛ እርከኖች ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንና ስራዎቹን በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች በመሳተፍ የእርሻ መሬታቸውን ለም አፈር በማሳ ውስጥ በማስቀረት ምርታማነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ገልጸዋል።   ዘንድሮ የተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች በአግባቡ እንዲጠበቁና እንዲያገግሙ በየአካባቢያቸው የተፈጥሮ ሃብት ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። በአማራ ክልል በዘንድሮው ዓመት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ሶስት ቢሊዮን ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል'።  
በአማራ ክልል የ2015 የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የሽግግርና ርክክብ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 24, 2023 202
ሰቆጣ መጋቢት 15/2015(ኢዜአ) የአማራ ክልል የ2015 የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የሽግግርና ርክክብ መርሃ ግብር በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ እየተካሄደ ነው። በወረዳው እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለውን ጨምሮ የክልልና የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።   በክልሉ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራው ከጥር 17 ቀን 2015 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። ሽግግርና ርክክቡም በህዝብ ንቅናቄ የለማውን ተፋሰስ በየአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች በማስረከብ በስነ ህይወታዊ ዘዴ በዘላቂነት እንዲለማ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። "ይህም ተፋሰሱን በመጠበቅና በማልማት በቋሚ አትክልትና ፍራፍሬ፣ በንብ ማነብና መሰል የሥራ ዘርፎች ተደራጅተው ለሚገቡ ወጣቶች የኢኮኖሚ ምንጭ ለመሆንም ያስችላል" ብለዋል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በዞኑ ስድስት ወረዳዎች በ119 ቀበሌዎች በህዝብ ተሳትፎ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። በዚህም በ 2 ሺህ 775 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የተሰራ ሲሆን፣ በ2 ሺህ 152 ሄክታር መሬት ላይ ደግሞ ነባር የለሙ ተፋሰሶች ጥገና መደረጉን አስታውቀዋል። በልማት ሥራው ከ82 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ በሥራዎቹ ከ147 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከት ተችሏል ብለዋል።  
የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Mar 23, 2023 220
አዲስ አበባ መጋቢት 14/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያና የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ62ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃም ለ42ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተከብሯል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ሃይለማርያም በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ተዳራሽ በማድረግ ደኅንነት ለማስጠበቅና ልማትን ለማፋጠን እየተሰራ ነው። ትክክለኛ የአየር ትንበያ መረጃዎች ለጥናት ምርምር ጭምር እንደሚያግዙ ጠቁመው ትክክለኛ የአየር ትንበያ መረጃ እንዲኖር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ጎርፍና ድርቅ ያሉ ክስተቶች በአገሪቷ እየተበራከቱ መሆናቸውን አንስተው እነዚህን ለመቋቋምም የተጠናከረ የአየር ሁኔታ መከታተያ፣ መተንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በመገንባትና በመዘመን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለዚህም በሰው ሃብትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሱን በማሻሻል ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር ዶክተር አግነስ ኪጃዚ በበኩላቸው የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ መረጃ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመታገዝ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች የግብርና ሥራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ከማድረጉም ባለፈ ምርቶች በጊዜ ተሰብስበው ለተፈለገላቸው ዓላማ እንዲውሉ ከማገዝ አንጻር ሰፊ ጠቀሜታ አላቸው።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 595
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተገለጸ
Dec 20, 2022 593
አዲስ አበባ ታኅሳስ 11/2015 (ኢዜአ) አህጉራዊው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፍሪካ ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተመላከተ። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ትስስር ከባህረ-ሰላጤው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት እንደሚጠቀስም ተገልጿል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዊሊያም ስቴንሀውስ ከሲ ጂ ቲ ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በተለይም ዱባይ የአፍሪካን ንግድና ኢንቨስትመንት በተመለከተ ዋና ማዕከል ሆናለች ብለዋል። በዱባይ 25ሺህ ገደማ የአፍሪካ ካምፓኒዎች እንደሚንቀሳቀሱ አመልክተው ይህም ሀገሪቱ በነጻ የንግድ ቀጣናው የቢዝነስ አጋር እንድትሆን አስችሏታል ነው ያሉት። አፍሪካውያን ባለሃብቶች የግብይት ማዕከላቸውን በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በማድረግና ምርቶችን ወደ አህጉሪቷ በማስገባት በነጻ ንግድ ቀጣናው ስር የገልፍ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደጉት እንደሚገኝም አስገንዝበዋል። የዱባይ ወደብ በአፍሪካ ያለው ተደራሽነት መስፋፋትም አፍሪካ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የሚኖራትን የሎጀስቲክስ አቅርቦት እንደሚያሳድግ በመረጃው ተመላክቷል። ከገልፍ ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ ዲፕሎማሲያዊና ወንድማማችነትን መሠረት ያደረገ ነው ያሉት ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ናቸው። አምባሳደሩ እንደሚሉት ከመካከለኛው ምስራቅ መነሻቸውን ያደረጉ ባለሃብቶችና የቢዝነስ ሰዎች ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር በልዩ ልዩ ዘርፎች ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ይገኛል። እ.አ.አ በጥር 2021 ተግባራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ከአጀንዳ 2063 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቱን ወሳኝ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የዲጂታል ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ትስስርና ሌሎች የንግድ ግንኙነቶችን በነጻ የንግድ ቀጣና ለማከናውን የተካሄደ ስምምነት ነው።
ሐተታዎች
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 100
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ውጣ ውረድ የማይበግረው አጋርነት
Mar 17, 2023 343
በሰለሞን ተሰራ ኢትዮጵያ በሥልጣኔ ቀደምትና ታሪካዊት ሀገር ነች። ቅሉ ከውጭ ሀገራት ያላትን ዘመናዊው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቅኝት የጀመረችው በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑ በታሪክ ይጠቀሳል። በተለይም ኢጣሊያ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1896 በአድዋ እንዲሁም በድጋሚ በ1935 ያደረገችው የግፍ ወረራ ኢትዮጵያ የዓለምን ፖለቲካ በቅጡ አሰላለፍ ተረድታ አጋር ሀገራትን እንድትሻ ዐይኗን ገልጦላታል። በዚህም ድኅረ-አድዋ ድል በርካታ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርተዋል። የወቅቱ ልዕለ-ኃያል ሀገር አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ የተመሰረተውም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና በፕሬዝዳንት ሩዝቬልት መንግሥት ተወካይ ሮበርት ስኪነር መካከል በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1903 በተደረሰው የንግድ አጋርነት ስምምነት ነበር። ድኅረ-ስምምነቱም በፈረንጆቹ በ1909 የአሜሪካ ሌጋሲዮን በአዲስ አበባ የተመሰረተ ሲሆን ሆፍማን ፊሊፕ የተባሉት ቋሚ መልዕክተኛ የአሜሪካ ቆንስላ ተሿሚ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፄ ምኒልክ አቅርበዋል፡፡ ከ120 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጽኑ ወዳጅነትና የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ እንደነበር ይወሳል፡፡ ሀገራቱ ጥቅማቸውን በጠበቀ መልኩ የመሰረቱት ግንኙነት ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም አይዘነጋም፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራን ተከትሎ ቆንስላዋን የዘጋችው አሜሪካ፤ ኢትዮጵያ በአርበኞቿ ትግል ነፃነቷን ስታረጋግጥ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በነኅሴ 1943 በድጋሚ ቆንስላዋን በመክፈት ግንኙነቷን አስቀጥላለች። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የቆንስላ ቢሮ ከፍታ ዕውቁን ዲፕሎማት ብላታ ኤፍሬም ተወልደመድኅንን በቋሚ መልዕክተኛነት ሾማለች። በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1952 የተደረገው 'ፖይንት ፎር' የተሰኘው የተቋማት ቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ለሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ መሰረት የጣለ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ስምምነትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአውራ ጎዳና ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅት በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ተቋቁመዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱ አድማሱን እያሰፋ፣ ሥር እየሰደደ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ጦር ሠራዊቷን እንድታጠናክር በአነስተኛ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችና ወታደራዊ ሥልጠናዎች ተጨባጭ አጋርነት አሳይታለች። የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን በተቆጣጠረ ማግስት ግን በዘመኑ በነበረው ዓለም አቀፋዊ ርዕዮተ- ዓለም ልዩነት ሳቢያ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሮ ሌላ መልክ ያዘ። በተለይም የደርግ ሊቀ-መንበር የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ሶቪየት ሕብረት አቅንተው የጦር መሳሪያ ድጋፍ መፈራረማቸው አለመግባባቱን ይበልጥ አባባሰው። በዚህም አሜሪካ በኤርትራ የነበረውን የቃኘው ሻለቃ ጣቢያዋን ዘግታ ወጣች። ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ከአምባሳደር ደረጃ በማውረድ በጉዳይ አስፈጻሚ ሲገናኙ ቆይተዋል፡፡ ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የሀገራቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት የአምባሳደር ደረጃ በመመለስ ከአሜሪካ ጋር የነበረው ግንኙነት መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጎታል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት አሜሪካ በጤና፣ በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ በምታደረገው ድጋፍ በመታገዝ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አሜሪካ መርህን ያልተከተለ አካሄድ በሀገራቱ መካከል የነበረውን ወዳጅነትና አጋርነት ላይ ጥቁር ጥላ ማጥላቱ አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሻክሮ የቆየውን ግንኙነት በማደስ የነበረውን ጠንካራ ወዳጅነት በድጋሚ የሚያጸኑ ጅማሮዎች ተስተውለዋል። በተለይም ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተደረሰውን የሰላም ሰምምነት ተከትሎ የሀገራቱ መቃቃር እየረገበ ሲሆን የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እየጎበኙ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተነጋግረዋል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ያደረጉት ውይይት ዘርፈ-ብዙ አጋርነትን ለማጠናከር መግባባት የተደረሰበት እንደነበርም በሁለቱም ወገኖች ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱ በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነና በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት የተደረሰበት እንደሆነ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት ማግኘቱንም ጠቅሰዋል። በኢኮኖሚው መስክ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ባተኮሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት መነጋገራቸውን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ አንቶኒ ብሊንከን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሚኒስትሮቹ ለረዥም ዘመን የዘለቀውን የኢትዮ-አሜሪካ ትብብር እና አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ተነጋግረዋል። በኢትዮጵያ አዲስ የመረጋጋትና የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አብራርተውላቸዋል። የሰላም ምዕራፍ የበለጠ እንዲጠናከርና የሰመረ እንዲሆን ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱን በጎ ገጽታ እንዲላበስ መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እምርታ እንዲመጣ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት መንግሥት አሁንም ቁርጠኛና ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው፤ በመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ተግባር የአሜሪካ መንግሥት እንዲደግፍም ጠይቀዋል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው፤ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር አሜሪካ በትብብር መንፈስ እንደምትሰራ እና አሜሪካ ሁለንተናዊ ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል። አሜሪካ ለድርቅ ተጎጂዎች እና ለስደተኞች የምታደርገው ድጋፍ አለመቋረጡ የሁለቱ ሀገራት አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ይጠቁማል፡፡ የብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መጀመሩም ዛሬም ኢትዮጵያ በአሜሪካ መንግሥት ዐይን ያላትን ቀዳሚ ሥፍራ ያመለክታል። አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ትግበራ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የበለጠ እንዲጠናከር የአሜሪካ መንግሥት ሁለገብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረገች ያለውን ጥረት አሜሪካ በአድናቆት እንደምትመለከተውና የሚበረታታ መሆኑን ብሊንከን ገልጸዋል። የብሊንከንን ጉብኝት ተከትሎ አሜሪካ 331 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ አረጋግጣለች። ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ነፍስ አድን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።  
የሴቶች ቀን ሲታሰብ
Mar 8, 2023 529
የሴቶች ቀን ሲታሰብ የሰው ልጅ ሕይወትን ቀላል ባደረጉ የፈጠራ ስራዎቻቸው የምናስባቸው እንስቶች በቀዳሚነት ይነሳሉ። በተለያዩ መስኮች አሻራቸውን ያሳረፉ እንስቶች ቁጥራቸው ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ጽሑፋችን ግን በኬሚስትሪና ፊዚክስ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት አስተዋጽኦ በኖቤል ሽልማት እውቅና የተሰጣቸውን የየዘመኑ ፈርጦች እንዳስሳለን። ከነዚህ ፈርጦች መካከል በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማትን ከሴቶች ቀዳሚ በመሆን በቀዳሚነት ያሸነፉት ሜሪ ኩሪ ይወሳሉ። ይልቁንም እ.አ.አ በ1903 በኬሚስትሪ ዘርፍ የተቀበሉትን የኖቤል ሽልማት በድጋሚ በ1911 በመሸለም ብቸኛነት ስማቸው ይነሳል። በ1967 በፖላንድ ዋርሶ የተወለዱት ማሪ ኩሪ ለዘመናዊው የሳይንስና ኬሚስትሪ ዘርፍ ውለታን ከዋሉ ስመጥር ተመራማሪዎችና በጨረራ ህክምና ፈጠራ የዘርፉ ፈር ቀዳጅ በመሆን የአለምን የራዲዮአክቲቪቲ እይታን የቀየሩ ጀግና ናቸው።   የሜካኒካልና ኤሮስፔስ ተመራማሪዋ ፍራንሲስ አርኖልድ ደግሞ በህክምናናና በታዳሽ ኃይል ዘርፍ አሻረቸውን በጉልህ ካኖሩ ተመራማሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ። አሜሪካዊቷ ፍራንሲስ ለታዳሽ ኃይል እና ለፋርማሲ አገልግሎት የሚውል አዲስ ኢንዛይም በምርምር በማግኘት በዘረፉ አሻራቸውን አኑረዋል። ለዚህም አስተዋጽኦዋ እ.አ.አ በ2018 በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል። የኤድስን ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሰፊ አበርክቶ ያላቸው የህክምና ተመራማሪዋ ፍራንሶዝ ባሪሲኖሲም የሴቶች ቀን ሲታሰብ ከሚወሱ አንስቶች አንደኛዋ ናቸው። ባሪሲኖሲ የኤች አይቪ ኤድስን ከገዳይ በሽታነት መታከምና መቆጣጠር ወደ ሚችል በሽታነት ለመቀየር የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራን በማላቅ ረገድ ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ይወሳል። በ1947 በፓሪስ ከተማ የተወለዱት ባሪሲኖሲ “ሳይንስን ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል እንሰራለን” በሚለው አባባላቸው ይታወቃሉ። ኤድስን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦም በፊዚዮሎጂ/ሕክምና ዘርፍ እ.አ.አ በ2008 የኖቤል ሽልማትን አግኝተዋል። ያለ ህክምና ትምህርት የሚሊዮኖችን ሕይወት በታደገው የወባ በሽታ መከላከያ ፈጠራቸው አለም እውቅና የተሰጣቸው ቱ ዩዩ በሴቶች ቀን የምናመሰግናቸው ሌላኛዋ ተመራማሪ ናቸው። ቻይናዊቷ ቱ ዩዩ ባህላዊውን የወባ በሽታ መከለከያ ህክምና ወደ ዘመናዊ በመቀየርና በማስተዋወቅ ነው ስመ ገናና የሆኑት።   የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዙፍ አሻራቸውን ላስቀመጡት ተመራማሪ ባለውለታነት እ.አ.አ በ2015 በፊዚዎሎጂ/ ህክምና ዘርፍ ሳይንስ ምድብ የመጀመሪያዋ ቻይናዊት በመሆን የኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የሰው ልጆችን ሕይወት ካቀለሉ አለም አቀፍ ፈጠራዎች መካከል የተጠቀሱትን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ መሆኑ ይታወቃል።
ሴትነት እና እናትነት
Mar 8, 2023 795
(አየለ ያረጋል) እስኪ መላ ስጪኝ መላ ካንቺ ይገኛል እኔማ ወንድ ነኝ ይደናገረኛል… (የማኅበረሰቡ ቃላዊ ግጥም) ሴትነት እናትነትን ለመግለጽ ቀርቶ በጥቂቱ ለመረዳት የ’እናት ልብ’ መታደል የሚሻ ይመስላል። ጥቂት ወንዶች ይህን ጸጋ ይቸራሉ። ልክ እንደ ዶክተር ይሁኔ አየለ። የስነ-ምግብ ሳይንቲስቱ ዶክተር ይሁኔ አየለ ‘እናት’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፍ የሴትነት እና እናትነትን ከፍታ በ’ኩርሽም’ ቃላት ተራቀውበታል። የሴቶች ቀንን (ማርች-8) ሰበብ በማድረግ ይህን ጽሑፍ ሳዘጋጅ መታሰቢያነቱ እናትን አስበው በ‘እናትነት’ ቅን ልቦና ‘እናትን’ ላበረከቱልን ዶክተር ይሁኔ አየለ ነው። ‘እናት፤ የሴት ልጅ ስንክሳር፤ ከቤተሰባዊ ሕይወት እስከ ሐልዮመንበርት’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባሳተሙት (በ406 ገፆች በተቀነበበ) አርበ ጠባብ መጽሐፍ ሴትነትን ከዘፍጥረት እስከ አሁን ዘመናትን ዋጅተው፣ እናትነትን ከሴትነት ዘንቀው፣ የእናትነት ጸጋን ከነባራዊ ሃቅ ጋር አሰነናስለው፣ የእናትነትን ልዕለ-ተፈጥሮ አርቅቀው፣ የዓለምን ክብር-ነሽነት ከነገረ-ሃይማኖት እስከ ነገረ-ባህልና ፍልስፍና ፈትተው፣ የማኅበረሰቡን ምልከታ ዝንፈት እና ሚዛን ጉድለት ከማኅበራዊ እስከ ፖለቲካዊ መገለጫዎች አዛምደው አቅርበውታል። ዶክተር ይሁኔ አየለ “እናት” በተሰኘ እናት የሆነ መጽሐፋቸው እናትነትን በልኩ ነጽረውታል። ሴትነት በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ሰለባነቱን፣ ነገረ-ሴትነትን ከንጽረተ-ሴትነት ቃኝተውታል። በእሳቤ ሚዛን ሰለባነት ዓለም ውስጥ ከንግስት ማክዳ እስከ ንግስት ፉራ፣ ከሰብለ ወንጌል እስከ ድል ወንበራ፣ … ብርቱ ኢትዮጵያዊት ሴቶችን ሕይወት ጨልፈውታል። የሴትነትን ጸጋዎች ጨልፈው በሴትነት ላይ የሚፈጸሙ የሀበሻ ግፎችን ተንትነውበታል። ሴቶች የማኅበረሰቡ ግፍ ሰለባዎች፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጉድለት ሰለባዎች እንደሆኑ በቅጡ ገልጸውታል። ዳሩ ሴትነት ጀግና እና ብልህ፣ የቤተሰብ መሰረት፣ የደስታና እልልታ እናት፣ ቃል ኪዳንና ክብር ጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል። “ሴት ልጅ ባለብዙ ጸጋዎች ናት። ከጸጋዎቿ መካከል ጀግንነት እና ብልሃት ይጠቀሳሉ። … ሴት ልጅ ባህልን ፈጥራ የማኅበራዊነትን ማስተሳሰሪያ ገመዶች ገምዳ አስተሳስራ ማኅበረሰብን የተከለች ሥርዓት ናት። … ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ የመጀመሪያ ተቋም ነው። የተቋሙ ባለሥልጣን (እመቤት) ሴት ናት። ያቺ ሴት እናት ናት። ቤተሰብ የስብዕና መሰረት የሚባለው እናትን ምሰሶ አድርጎ ነው” (ገጽ-285) ሴት ልጅ መለኛ መሆኗን ማኅበረሰባችን ቢያምንም ሴትነትን ግን እንዳላከበረ አሉታዊ ይትባህልና ኪነተ- ቃሉን ዘይቤ ያወሳሉ። በእርግጥ የእናትን ምቹነት እና ዋጋ ከፋይነት የሚያትቱ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችም አሉ። ለምሳሌ ዳንኤል አበራ “የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች” በሚለው መጽሐፋቸው “እናት ትረገጣለች እንደመሬት፤ እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ፤ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ፤ እናት የሌለው ልጅ እንደ ጌሾ፤ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ…” የሚሉ ምሳሌያዊ ንግግሮችን አስፍረዋል። መላኩ ይርዳው የተባሉ ጸሐፊ ‘ደቦ ቅጽ-፩’ ከተሰኘው የ60 ደራሲያን ሥራዎችን ያካተተ መጽሐፍ ውስጥ ‘የሴትነት ጸጋ’ በሚል በጻፉት መጣጥፍ ሴትነትን ከፍቅር፣ ከጥበብ፣ ከብልሃትና ልዕልና ጋር አቆራኝተውታል። “ሴት ልጅ ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አልታዩኝም። የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የተረዳነው አይመስለኝም።… ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለሴት ልጅ የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንስብኛል” ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስለሴት ልጅ ጭቆና የታገለ እና ስለክብሯ የዘመረ ምሁር ነው። ስለሴት ልጅ ስቃይና ሰቆቃ አትቷል። ‘በናቴኮ ሴት ነኝ’ በሚለው መጽሐፉ ስንኞች እንምዘዝ! …. ግማሽ አካሏ ወንድ በትምክህት ቢከዳት ጧ! ብላ አለቀሰች አዛኝ ቢደርስላት፣ … ብሶት ተጫጭኗት ምንም ሰው አልሆነች በቀቢጸ ተስፋ ሕላዌንም ጠላች ያገሬ ጭቁን ሴት መድኅን መላ ያጣች….! ‘ሔዋንያት የትውልድ ፋብሪካዎች ናቸው፤ እነሱ ባይኖሩ ዓለም ባዶ ትሆን ነበር’ እንዲል ፈላስፋው ሶቅራጥስ። ስለሴት (ግማደ ሰቧ ፍጡር) ግፍና በደል ገሞራው እንዲህ ይላል። “መራራ ጭቆና በሰፈነበት ምዝብር ሕብረተሰብ ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ሔዋንያት ብሶታቸው፣ ፍዳቸው፣ በደላቸው፣ ጭንቀታቸውና መከራቸው እንደ ሰማዕታት ገድል እጥፍ ድርብ ነው…. አጉል ልማድ፣ ኋላቀር ባሕልና አድሃሪ ሕገ-ማኅበረሰብ ከከንቱ አስተሳሰቦች ጋር ተዳምሮ በአንድነት በመመሳጠር ዘርዓ ሔዋንን ሲጫወቱባቸው ሲያሾፉባቸው ኑረዋል” (ገጽ-23) በሥነ-ሕይወት ሳይንስና በትምህርተ-ጄነቲክስ (አካለ ሕላዌ) ሴቶችን ከወንዶች የሚያሳንስ ምንም አይነት አካላዊ ተሰጥኦ እንደሌለ ተረጋግጧል። ታሪክና ተረክ ግን ወገንተኛ መሆኑን ገሞራው ይናገራል። ተረክና ተረት አልባሌ ታሪክ የሚፈጥሯቸው አርበኞች ሁሉ በፆታቸው ተባዕት በመሆናቸው፤ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ሊኖራቸው የሚችለው ዕድገት ላይ ትልቅ ደንቃራ ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። “የታሪክን ሁኔታዎችን የመመንዘር ትርጓሜያዊ አንጻር የታሪክን ትዕይንቶች ብንመረምር አንደርድሮ የሚያደርሰን ሴቶች ከወንዶች የከፋ ባህሪያዊ ድክመት እንዳለባቸው ከሚያሳይ ሥዕል ላይ ነው።” በሚት(ተለጣጭ ተረክ) ላይ የሚራቀቁት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፎክለር መምህር) ‘ተረኮች እማዊ ሳይሆን አባዊ ናቸው’ በማለት ይህን ጉዳይ ያጠናክሩታል። “በሚት ውስጥ ገነው ከሚታዩ አበይት ማኅበራዊና ባህላዊ እውነታዎች መሃል አንዱ ፆታዊ ወገንተኝነት ነው። የሰማናቸው፣ ያነበብናቸው ሚታዊ ተረኮች በእጅጉ አባዊ ለሆኑ ሥርዓቶች (ፓትሪያርካል ሲስተምስ) ያደሩ፣ በአብዛኛው በተባዕት ተጋዳሊያን የተሞሉ ናቸው” ይላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ይሁኔ (በገፅ-401) ስለሰው ማንነት ቀረጻ በተመለከተ ከጥንት እስከ ዛሬ አከራካሪ የሆኑ ፈላስፎችን ክርክር ያነሳሉ። ይኸውም የሰው ልጅ ‘ማን ቀረጸኝ? ተፈጥሮ ወይስ ተሞክሮ?’ የሚለውን መከራከሪያ ጽንሰ-ሃሳብ ይፈትሻሉ። በዚህም “ሰዎች ሲፈጠሩ የሰውየውን ችሎታ ይዘው ነው” እና “የሰዎች ማንነት የሚቀረጸው ከውልደት በኋላ በተሞክሮ ወይም ከአካባቢ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ነው” የሚሉትን ሃሳቦች ወስደው ከእናት ሚና ጋር ያዛምዱታል። እናም እናት ‘በየትኛውም መደብ ልጅን አሳምራ ትቀርጻለች’ የሚል ድምዳሜ ሰጥተዋል። “በየትኛውም መንገድ በሰው ልጅ ላይ የእናት ቀራፂነት ስለሚኖር ከተጽዕኖዋ ማምለጥ የሚቻል አይመስለኝም።… አካባቢም ሰውን ይሰራዋል የሚሉትም ከውልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር የሚደረገው ውስብስብ መስተጋብር ‘ሰው’ በመሆን ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል” ይላሉ። በዚህ እሳቤ ሰው የወላጆቹም፤ የአካባቢውም ውጤት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን” ይላሉ። ሴቶች ከጥንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ማኅበረ-ባህላዊ እንዲሁም ለሰላምና ዕርቅ እሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው። ሴቶች ያልተሳተፉበት ዘርፍ የለም። ከመሪነት፣ ጥበበኝነት፣ ከአገር ድንበር ጠባቂነትና የዲፕሎማሲያዊ ሚና… መጥቀስ ይቻላል። ሴቶች በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ በሰላምና ግጭት አፈታት ግንባር ቀደም ተሰሚነት አላቸው። ለአብነትም ሀደ ሲንቄ፣ በሶማሌ-ሔር፣ በሲዳማ-ያካ፣ በራያ ማኅበረሰብ ዱበርቲዎች፣ በስልጤ-ሴረን ባህል መጥቀስ ይቻላል። ከሰሞኑ ባከበርነው የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሴቶች ውለታ በወፍ በረር ማውሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ ሴቶች ከሌላው ዓለም ሴቶች በተለየ የራሳቸው ቀለም ያላቸው፣ የአመራር ልምድ ያዳበሩ፣ የመወዳደሪያ ስነ-ልቦና ያላቸው፣ ችለው አሸንፈው ያሳዩ ናቸው። ሴቶች ድሉን በማስመዝገብ የተጫወቱትን ሚና ያህል፣ ገድላቸው በታሪክ በሚገባ አልተወሳም። ዶክተር አልማው ክፍሌ የተባሉ የታሪክ ምሁር በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ሲሉ ሰምቻለሁ። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች በርካታ ናቸው። ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡- “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችዎን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) ዶክተር ይሁኔ (በገጽ-14) በበኩላቸው እናቶችን ሩህሩሆች፣ አጉራሽና አልባሽ፣ የችግር ቤዛዎች፣ ሕይወት ዑደት አስቀጣዮች፣ የሕይወት መድኅኖች፣ ባለብዙ ጸጋዎች፣ መልካም ባህሪ አውራሾች፣… በማለት ገልጸውታል። መላ ሴቶችንም በእናቶች አተያይ ማየት እንደሚገባም እንዲሁ። “እናትነት መልካም ገጽታዎችን ደራርቦ የያዘ የሴት ልጅ ትልቅ መገለጫ ነው። እናትነት ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። እናትነት ጥልቅና ሰናይ ባህሪያት የሚፈልቁበት ምንጭ ነው። እናትነት የደግነት፣ የጥራት፣ የልህቀትና ተፈላጊነት ማሳያ ተምሳሌት ነው። እናትነት ሞት የማያደበዝዘው ኃያል መንፈስ ነው። እናትነት ከባድ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። … እናትነት የሰላም፣ የመልካም ግንኙነትና እንክብካቤ መፍለቂያ አድባር ናት። እናትነት ሰፊና ጥልቅ የሕይወት ትምህርት ቤት ነው። እናትነት ሌሎች ከስቃይ ነፃ እንዲሆኑ፣ ምቾት እንዲሰማቸው በሚደረግ ትግል ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ መኖር ነው” በመቀጠልም የኢትዮጵያ እናቶችን ‘ጠቃሚ ነገር ሰጪዎች’ ይላቸዋል። “እናቶች ሰው የመሆኛ ቅመሞች የሚጨለፍባቸው ባህር ናቸው። … ሕይወታዊ ስሪታችን ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የወሰደው ከእናት ነው። ከእናት የምናገኘው ‘ማይቶኮንድሪያ’ (ማይቶኮንድሪያ የኃይል ማመንጫ ክፍል ሲሆን የምንመገበው ምግብ እየተቃጠለና ወደ አስፈላጊው ኃይል እየተቀየረ ሕይወትን ያንቀሳቅሳል) የምግብ ማቃጠያ ምድጃ ወይም ኃይል ማመንጫ ቤት ሆኖ ያገለግላል። … ብዙ መልካም ስብዕና መገለጫዎች ምንጫቸው የእናት ፍቅር፣ የመልካም ስብዕና እና የርህራሄ ምንጭ ነው” (ገጽ- 61) ኢያሱ በካፋ ‘የኢያሱ በካፋ ወጎች’ በተሰኘው መጽሐፉ እናትነትን ማህጸንን፣ ምግብን፣ ትንፋሽን፣ ደም፣ ሥጋን እና ነፍስን ሰጥተው በረቂቅ ተፈጥሮ ሰውን ከመውለድ ባለፈ ፍቅራቸውን ዘላለማዊ ገደብ አልባ እና ዕልቆ-ቢስ እንደሆነ እንዲህ ገልጾታል። “እናትነት ነፍስን ማካፈል ነው፤ እናትነት የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር መስጠት ነው፤ እናትነት ከራስ ሕልውና ይበልጥ ለልጅ ማሰብ ነው፤ እናትነት ፍፁም ወረት አልባ መሆን ነው። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር አይነጥፍም፤ አይለወጥም። ለእናት ልጇ ሁሌም ልጇ ነው” (ገጽ-4) እናትነት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ፤ በውለታ ማካካስ ይከብዳል። የእናት ውለታዋን መክፈል የሚችል ልጅ የለም። የእናት ፍቅርን ለመግለጽም በርካቶች አንደበታቸው ይተሳሰራል፤ ቃላት ይነጥፍባቸዋል፤ ስሜታቸውን መግራት ይሳናቸዋል። ድምፃዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) ‘ይናገራል ፎቶ’ በሚል እናትና አባቱን በገለጸበት ሙዚቃ የመጨረሻው ማጠንጠኛው ‘እወድሻለሁ/እወድሃለሁ’ ያለው፤ እንዲሁም ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ‘እናት ውለታዋ’ በተሰኘ ዘፈኗ ውስጥ (ዜማና ግጥም ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ)፤ “ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ” እያለች በሚስረቀረቅ ድምጿ የምታንጎራጉረው ለዚህ ይመስላል። ዕውቁ የቋንቋ ሊቅ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) ‘የጥቁር አፈር ትሩፋቶች’ በተሰኘው መጽሐፉ (ገጽ-79) ‘መቀነትሽን አጥብቂ’ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ረዘም ያለ ግጥም ሁለት አንጓዎች ብቻ ስንመዝ የእናትነት ውለታን መመለስ እንደሚሳን፤ የእናትነት ግብሯ ‘እናት’ የሚለው ቃል በራሱ እንደሚያንስባት ያትታል። … “ለዚህ ወሮታሽ አጸፋ፤ እናት ይልሻል አገሩ፤ እኔም እናቴ ብልሽ መች ሊመጥንሽ ዳሩ። … እናትነት ምጡቅ ነው፤ እናት ከመባል ይልቃል፤ የግብርሽ ስንክሳር ዚቁ፤ በስያሜ መች ያልቃል”… በማለት ይገልጸዋል። መውጫ ዶክተር ይሁኔ የሴት እና እናትን የነገዋን መንገድ ከሳይንስ አተያይ አንጽረው፤ ከማኅበረ-ፖለቲካ፤ ከማኅበረ-ባህል ከፍታዋ አመሳክረው፤ እናትና ሀገርን መጋመድ አመስጥረው መልእክታቸውን እንደ መውጫ አስፍረዋል። ለስንበት አንድ አንቀጽ እንወርውር!! “የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። የሰመረ ትውልድ ሊቀጠል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው። የእናቶች አቅም ሲገነባ የራሳቸውን አቅም ያውቃሉ፤ ምርጫቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እንዲሁም ለሚመጣው ማኅበራዊ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ። ስለሆነም የእናቶችን አቅም ማጎልበት ትውልድን ማጎልበት ነው። እናቶች ላይ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት ነው”  
ትንታኔዎች
የአየር ንብረት ፋይናንስ-አፍሪካውያን ገፍተው ያልሄዱበት መንገድ
Feb 18, 2023 615
/በገዛኸኝ ደገፉ/ የአፍሪካ ቀንድ ከ40 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ አያቅም የተባለለትን የድርቅ አደጋ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊ ሆነዋል። የድርቁ አደጋ የከፋበት የአፍሪካ ቀንድ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ተሸክመዋል። በተጨማሪም የከተሞች መስፋፋትና የከተሜነት የኑሮ ዘይቤን እያስተናገደች ባለችው አፍሪካ የኃይል እጥረት፣ በቂ የመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ አለመኖር፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት፣ ሥራ አጥነት ብሎም የወንጀሎች መስፋፋት አሕጉሪቱን ክፉኛ እየፈተኗት ይገኛሉ። የገጠር መሬት ምርታማነት መቀነስ ከገጠር ወደ ከተማ ለሚደረገው ፍልሰት አንደኛው ገፊ ምክንያት ሲሆን ለመሬቱ ምርታማነት መቀነስ ሰበብ ተደርጎ በዋናነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት የሚወልዳቸው የውኃ ኃብት መቀነስና ለተከታታይ ዓመታት የሚዘልቁት የድርቅ አደጋዎች መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አወሳስቦታል። እንደ አህጉር ከ4 በመቶ ያነሰ የካርቦን ልቀት ያላት አፍሪካ 65 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ የችግሩ ቀጥተኛ ገፈት ቀማሽ መሆን ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከዚህ ችግር ሙሉ ለሙሉ መውጣት ባይቻልም ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ እንዲቻል አህጉሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ኃብትና ወጣት የሰው ኃይል በማስተሳሰር ለውጥ ማምጣት ግድ ይላታል። በአፍሪካ የማይቀረውን የከተሞች መስፋፋትም ሆነ የህዝቦቿን የመልማትና የመለውጥ ፍላጎት ማሟላት ካለባት የአየር ንብረት ፋይናንስን የበለፀጉ ሀገራት ገቢራዊ ሊያደርጉት ይገባል። የአየር ንብረት ፋይናንስ (Climate Finance) የአካባቢ፣ ብሔራዊ ወይም ድንበር ተሻጋሪ ፋይናንስን የሚመለከት ሲሆን ከሕዝብ፣ ከግል እና ከአማራጭ የገንዘብ ምንጮች የተውጣጣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው። የኪዮቶ ፕሮቶኮል እና የፓሪስ ስምምነት ደግሞ ሰፊ የገንዘብ አቅም ካላቸው አገራት አነስተኛ የኃብት አቅም ላላቸው እና ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ አገራት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ስምምነት ነው። ስምምነቱ “የጋራ ግን ደግሞ ልዩነት ያለው ኃላፊነትና አቅም” በሚለው መርህ መሰረት ያደጉ አገሮች አዳጊ አገራትን ለመርዳት የገንዘብ ምንጮችን እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። ፋይናንሱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ወሳኝ ድጋፍ እንደሚሆን ታምኖበታል። ምክንያቱም ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ላቅ ያለ የኢንቨስትመንት አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ። በተመሳሳይ ከአሉታዊ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች ጋር ለመላመድ እና ተለዋዋጭ ጫናዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። ከጥቂት አሥርት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተዘጋጅቶ የቀረበው የምእተ ዓመቱ የልማት ግብ ሰነድም ሆነ በቅርቡ በሚጠናቀቀው ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ለጉዳዩ ከፍ ያለ ትኩረት ቢሰጠውም እስካሁን ግን የፈየደው ነገር የለም። አፍሪካ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመላመድ ዓመታዊ 41 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ክፍተት ይገጥማታል። ይህን ክፍተት ለመሙላት አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለችው 36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ የአየር ንብረት ፋይናንስ ገቢራዊ ማድረግን ቀዳሚ ትኩረታቸው መሆን እንዳለበት የአንድ ዘመቻ (ONE Campaign) አጽንኦት ሰጥቶ ምክረ ሃሳቡን ሰንዝሯል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የአንድ ዘመቻ ዳይሬክተር ዶሪን ኒኒናሃዝዌ የአፍሪካ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመላመድ ፋይናንስ ድጋፍን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተጽዕኖ የመቋቋም አቅም እንዲገነቡ መክረዋል። አፍሪካ ባልፈጠረችው የአየር ንብረት ለውጥ ህዝቦቿ ለከፋ ጥቃት እየተዳረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች የበለጸጉ አገሮች የገቡትን የማላመድ ፋይናንስ ድጋፍ ቃል እንዲፈጽሙ ከማግባባት ባለፈ ማሳሰብ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይህ ማለት እኤአ ከ2020 እስከ 2025 በዓመት 100 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመተውን ግብ የማሳካት ተግባር የሚጠይቅ ነው። ከዚህ ባሻገር በቀጣዮቹ ዓመታት በተጨመሩ መዋጮዎች የሚስተዋሉ ጉድለቶችን መፍታት እና በግብጿ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ባስተናገደችው COP-27 ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ለመላመድ በእጥፍ ፋይናንስን የማቅረብ ቁርጠኝነት የማቅረቢያ ዕቅድ ሊነድፉ ይገባል ነው ያሉት። የአፍሪካ አገሮች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እና ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ጋር ሲታገሉ ቢቆዩም አሁን ላይ “አፍሪካ በአፈፃጸሙ ላይ መጠነኛ መሻሻል አሳይታለች” ብለዋል። እናም በ36ኛው የመሪዎቹ ጉባዔ የተገኙ ስኬቶች እና የጠፉ ዕድሎች እንዲሁም የድርጅቱን ዓላማዎች ለማሳካት በአየር ንብረት ፋይናንስ በጥልቀት መክረው ለተሻለ ስኬት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ በአየር ንብረት ምክንያት የሚፈጠሩ መፈናቀልን ለመግታት የተሻሻሉ የመላመድ እና የተጽዕኖ ቅነሳ ተነሳሽነት ገቢራዊ ለማድረግ በአገራት መካከል ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ያሰምሩበታል። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በተፈጥሮ ሃብት ላይ ኑሯቸውን መሰረት ባደረጉ ህዝቦች ላይ አውደ-ተኮር መላመድ እና የመቋቋም አቅም ግንባታ መፍጠር ይገባል። ለዚህ ደግሞ መላመድን የሚደግፉ ፋይናንስ ለማግኘት የሚረዱ መመሪያዎች ይበልጥ የተፍታቱ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ቪቶሪኖ ይሞግታሉ። ከ 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በተጓዳኝ በተካሄደው ከፍተኛ የውይይት መድረክ (High-Level Forum) ላይ ዳይሬክተሩ እንዳሉት በሻርም ኤል ሼክ በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ መላመድን፣ መከላከልን እና ዝግጁነትን ለማሻሻል ዓለም አቀፍ ትብብር ማጎልበት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አውስተዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ያወጣቸው የስምምነት ማዕቀፎች (United Nations Framework Convention on Climate Change (UNFCCC)) በርካታ ዝርዝርና ሚዛናዊ አካሄዶችን የያዙ ናቸው። ያም ሆኖ አተገባበራቸው እዚህ ግባ የማይባል በመሆኑ የሚታሰበውን ያህል ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቷል። በዚህም ቦረና ዞንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። የአየር ንብረት መዛባት፣ የሙቀትና የባህር ጠለል መጨመር፣ ጎርፍ፣ ድርቅ እንዲሁም ያልተገመቱ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማሙበታል። ዳሩ ግን አገራትን፣ አህጉርን፣ ዓለምን እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ግዙፍ ኩባንያዎችን ያስተሳስራል የተባለለት የአየር ንብረት ፋይናንስ በቅጡ ገቢራዊ ማድረግ ባለመቻሉ የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ በርካታ ህዝቦች ዳፋውን ለመጋፈጥ ተገደዋል። የአየር ንብረት ፋይናንስን በመተግበር በመስኩ የተጎጂዎችን ቁጥር ሊቀንሱና የዓለምን ሥነ-ምህዳር ከተቻለ ወደ ቀድሞው ሊመልሱ አሊያም አሁን ባለበት አረጋግተው ሊያቆዩ የሚያስችሉ በርካታ አማራጮች ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል። ለአብነትም ለድሃ ሃገራት አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተገቢውን ዋጋ በመክፈል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን እንዲቋቋሙ ማድረግ ከአማራጮቹ መካከል አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለሚያስወግዷቸው በካይ ጋዞች ተመጣጣኝ የጤና ሥርዓት በመዘርጋት የታዳጊ ሃገራት ዜጎችን የጤና አገልግሎት ማሻሻል ሌላው አማራጭ ነው። የተፈጥሮ ኃብቶችን የሚጎዱ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተፈጥሮን በሚንከባከቡ ዘዴዎች መተካት እንዲሁም ብክለትን የሚያስቀሩ የምርት ሂደቶች መለማመድ ጥቂቶቹ የመፍትሄ አማራጮች ተደረገው የሚወሰዱ ናቸው። በፓሪስ ከተደረሰውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ቀደም ብሎ በፈረንጆቹ 1994 ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (Global Environment Facility-GEF) COP-16 ዓለም አቀፍ ጉባዔ በኋላ በ2010 አረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund-GCF) እንዲሁም በ2001 ደግሞ ልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (Special Climate Change Fund-SCCF) እና የመላመድ ፈንድ (Adaptation Fund-AF) የተባሉ ማዕቀፎች የተዘጋጁ ቢሆንም ስለጉዳዩ የሚያስረዱ ተከታታይ ስብሰባዎች ከማዘጋጀት በዘለለ ብዙ ርቀት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። በቅርቡ በአለም ባንክ አሰባሳቢነት በኬንያ ናይሮቢ ተዘጋጅቶ በነበረው የአህጉሪቱን መሪዎች ባለሃብቶችንና ምሁራንን ባካተተውና “One Planet Summit” በተሰኘ መሰል ጉባዔ ላይም አፍሪካውያን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚገጥማቸውን ችግሮች ተከላክለው ሁለንተናዊ ዕድገታቸውን እንዲያፋጥኑ ካስፈለገ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ አዘጋጅተው መተግበር እንደሚኖርባቸው መግባባት ላይ የተደረሰ ቢሆንም አሁንም ጥያቄ ያስነሳው አፈጻጸሙ ስለመሆኑ ብዙ ተብሎለታል። ክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ የተባለ ድርጅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያመለክተው አፍሪካ እንደ ፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር ከ 2020 እስከ 2030 ባሉት አሥር ዓመታት 2 ነጥብ 8 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር አሊያም በየዓመቱ ከ2 መቶ ሃምሳ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያስፈልጋት ሲሆን አህጉሪቱ ከዘርፉ እያገኘችው ያለው ገንዘብም ከሚያስፈልጋት 12 በመቶውን ወይም 30 ቢሊየን ዶላር ብቻ ስለመሆኑ አስነብቧል። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ተቋቁመው ሊሰሩ የሚችሉ በርካታ ተግባራት እንዳሏት የሚያትተው ሪፖርቱ ከአየር ንብረት ፋይናንስ የሚገኘው ገንዘብ በትራንስፖርት፣ በኃይል ልማት፣ በኢንዱስትሪ ብሎም በግብርና፣ በአፈርና በደን ኃብት አጠቃቀም ውጤታማ በሆነ መንገድ ከዋለ የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ኃብቶች መንከባከብ ከማስቻሉም ባለፈ ላቅ ያለ ፋይዳ ይኖራዋል ብሏል። ይህ ሲሆን የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ ለአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖው ያስረዳል። ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራን የማስፋፋትና የተጎዱ አካባቢዎችን የማከም ሥራ እንዲሁም አይቀሬ የሆኑትን ከተሜነትና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ታሳቢ ያደረጉ የአየር ንብረት ፖሊሲዎች ተግባራዊ መደረጋቸው ለአፍሪካ ሃገራት እየፈጠረው ያለው በጎ ተጽዕኖ በግልጽ እየታየ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ጥረት ግን በአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲደገፍ አገራዊና የተቀናጀ አሕጉራዊ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። ከአጠቃላይ የአፍሪካ አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ግብጽ ብቻ 151 ቢሊየን ዶላር ከአየር ንብረት ንብረት ፋይናንስ ማግኘት እንደሚኖርባቸው የክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ ሪፖርቱ ይገልጻል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በመጭው የCOP-28 ጉባዔ የራሷንና የአፍሪካን ፍላጎት የሚያስጠብቁ የፋይናንስ ትልሞችን የመንደፍ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ የ COP-27 ጉባዔ ለአፍሪካ ያስገኘውን ውጤት እና አንድምታ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የመሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አስተባባሪ በሆኑት በኬንያው ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት በኅብረቱ የአዲስ አበባ ጉባዔ ላይ በጥልቀት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል። እዚህ ላይ ኢትዮጵያ ጥረቷን የሚያጎለብት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ጠንካራ ተሳትፎ ልታደርግ ይገባል። የአፍሪካ አገራት ገፍተው ረጅም ርቀት ያልሄዱበት የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ሌሎች የድጋፍ አማራጮችን በፍትሃዊነትና በምክንያታዊነት በመጠቀም የአየር ንብረት ተጽዕኖን የሚቋቋሙበት ጠንካራ አቅም ሊገነቡ ግድ ይላቸዋል። በእርግጥም አፍሪካውያን መሪዎች በሚያደርጉዋቸው ስብሰባዎች በየማዕዝናቱ በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጦት የተዳረጉ ህዝቦቻቸውን የሚታደጉበት ሁነኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበትን ዘዴ ነድፈው ረጅም ርቀት ሊጓዙ ይገባል። ”
ዛሬ የሚጀመረው 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል
Feb 18, 2023 573
"የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መቀላጠፍ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የዘንድሮ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ወደ ሥራ የገባውንና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ሕዝብ በንግድ ለማስተሳሰር የታለመውን የንግድ ቀጣና ይበልጥ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራል። በተለይም ደግሞ የጋራ የጉምሩክ ሥርዓትና ወጥ የታሪፍ አስተዳደር በአህጉሪቷ ለመተግበር ትኩረት ይደረግበታል ተብሏል። ሌሎችም የእርስ በርስ የንግድ ግንኙነትን የሚያቀጭጩ አሰራሮች ነቅሶ በማውጣት የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት ለመፍጠር ምክክር አድርገው አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል። የአፍሪካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ እንዲሁም በዩክሬንና በሩስያ ጦርነት ምክንያት አደጋ ላይ የወደቀው የአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ችግር እልባት በሚሰጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሏል። በተለይም ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና ሥራ ለማሳለጥና በአህጉሪቱ ዘመናዊ የእርሻ ሥራ በሚስፋፋባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል። ይህም በዘላቂነት የአህጉሪቱን የምግብ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል ተብሏል። በመሆኑም የዛሬው ጉባዔ ትኩረቱ በዚሁ የምግብ ዋስትና ሁኔታ ላይ እንደሚሆን ብዙ ግምት ተሰጥቶታል። የአፍሪካ የ2063 አጀንዳ አፈጻጸም ባለፉት አሥር ዓመታት በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የተጣለውን የረዥም ጊዜ ዕቅድ ከግምት በማስገባት የተሰሩ ሥራዎች ይገመግማል ተብሏል። ለቀጣይ አሥር ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚችሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጎ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ ዋና ዋና የሚባሉ ስኬቶችን በመገምገምና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት መጪውን አሥር ዓመት የተሻለ ለመፈጸም የሚያስችል የትግበራ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል። ከዚህም ባሻገር አፍሪካ በፋይናንስ ራሷን እንድትችል እየተደረገ ያለውን ጥረትም ትልቅ ሥፍራ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። ለአብነትም የኅብረቱ ሰላም ፈንድ የሚደረገው የአባል አገራት መዋጮና አገራት ከታክስ ገቢያቸው ለኅብረቱ በማዋጣት አጠቃላይ የኅብረቱን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውም ጉዳይ ምክክር ሊደረግበት የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በቻድ፣ በካሜሮን፣ ኒጀር፣ በናይጄሪያ አካባቢው ከጽንፈኝነት ጋር በተያያዘ በርካታ የጸጥታ ችግሮች እየተከሰቱ ሲሆን ይህም ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍልም የትጥቅ ትግል መቀስቀሱ የተዘገበ ሲሆን ይህም አገሪቱን ከሚያዋስኑ አገራት ጋርም አለመረጋጋት ፈጥሯል። በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው የጸጥታ ችግርም አሁንም እልባት ያላገኘ ጉዳይ ነው። ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ሂደት ላይ ናቸው፤ ሱዳን ሕዝባዊ አስተዳደር ለመመሥረት የሽግግር ትግበራ ላይ ናት። በመሆኑም የአፍሪካ ኅብረት በእነዚህና በሌሎች የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ - የአፍሪካ የዘመናት ፈተና
Feb 13, 2023 581
በረከት ሲሳይ በርካታ የአፍሪካ አገራት ነፃነታቸውን ከተቀዳጁበት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስካሁን እልባት ካልተገኘላቸው አፍሪካዊ ጉዳዮች መካከል ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አንዱ ነው። ለዚሁ ጉዳይ በርካታ መነሾ ቢኖሩትም ቅኝ ግዛቱ የፈጠራቸው ፖለቲካዊ ስንጥቃቶች፣ ድህነትና ሌሎች ማኅበራዊ ምስቅልቅሎሽ ለእነዚህ የጸጥታ ችግሮች በአብዛኛው የሚነሱ ምክንያቶች ናቸው። በአህጉሪቱ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት መቋጫ በሌለው መልኩ እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶችና ጦርነቶች ለአያሌዎች ሞትና የአካል ጉዳተኝነት ለገሚሱ ደግሞ ለዘመናት ከኖረበት ቀዬ እንዲሰደድ ምክንያት ሆነዋል። በብዙ ጥረት የተገነቡ መሰረተ-ልማቶች ወደ ፍርስራሽነት እንዲለወጡና በሂደት ላይ ያሉ የዘመናዊ አገር ግንባታ ሂደቶች እንዲስተጓጎሉና በፈተናዎች እንዲታጀቡ አድርጓል። ይህንኑ ኢኮኖሚያዊ ኪሣራ በሚያሳይ መልኩ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ከሁለት ዓመታት በፊት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ በአፍሪካ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች በየዓመቱ የአገራቱን አጠቃላይ አገራዊ ምርት (ጂ ዲ ፒ) እድገት ከ4 በመቶ እስከ 6 በመቶ እንዲቀንስ ያደርገዋል ይላል። በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚው ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ተጽዕኖ ዓመታትን የሚዘልቅ በመሆኑ ተደራራቢና ድግግሞሽ ያሏቸው ችግሮች እንዲበራከቱ በር ከፍቷል። በእነዚህ ድርብርብ ውጥንቅጦች በአህጉሪቱ በከባድ ድህነት የሚኖሩ ዜጎች ህይወት ይበልጡኑ እንዲወሳሰብባቸውና ለከፋ ማኅበራዊ ችግር እንዲጋለጡ እያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ የጸጥታ ችግሮች በአፍሪካ ሳያባሩ መቀጠላቸው ዛሬም ጉዳዩን በአንክሮ እንድንመለከተው ያስገድደናል። ይህንን በሚያስረግጥ መልኩ ያለፈው የፈረንጆች ዓመት (2022) ግጭቶች የተስተዋሉበት ዓመትና በዘንድሮ ዓመት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ተመላክቷል። በሰላም ስምምነት የተቋጨውን በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ጦርነት ጨምሮ እስካሁን እልባት ያልተገኘላቸው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ችግሮች ተጠቃሽ መሆናቸውን ነው የአፍሪካ የደኅንነት ተቋም ሪፖርት የሚያሳየው። ከዚህ ጎን ለጎን በሳሀል፣ በቻድ ሃይቅ ሸለቆ፣ በምስራቅ አፍሪካና በሰሜን ሞዛምቢክ ጸጥታን የሚያውክ የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ መኖሩንም አመላክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን በቡርኪና ፋሶ፣ በጊኒ፣ ማሊ፣ ሱዳን፣ ቻድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጅቡቲ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማዳጋስካርና ኒጀር የተሳካና ያልተሳካ የመፈንቅለ-መንግሥት (ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ) ሙከራ መካሄዱንና የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደተስተዋለባቸው ነው ሪፖርቱ ያወሳው። መንግሥታዊ የአስተዳደር ግድፈቶች፣ ምርጫን ተከትሎ የሚቀሰቀስ አለመግባባትና ሌሎችም በአህጉሪቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት የተከሰቱ የጸጥታና የደኅንነት ችግሮች ለተያዘው የፈረንጆች ዓመትም ትልቅ ሥጋት መሆኑን ነው ያነሳው። አፍሪካ ኅብረት በበርካታ አገሮች የጸጥታ ችግሮች እንዲቆሙና እንዲረጋጉ በማድረግ አዎንታዊ ሚና መጫወቱ ተገልጿል። ለአብነትም በኢትዮጵያ በዘላቂነት ግጭትን ለማቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠቃሽ ሲሆን በሌሎችም አገራት ወደ ተሻለ ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲመጡ ትልቅ ሥራ ሰርቷል። ይህም ሆኖ አሁንም ድረስ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ በኩል በርካታ ሥራ እንደሚቀር ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ በምዕራብ ሳሀል ያለው ከአልቃይዳና ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ጽንፈኛ ቡድን በአካባቢው የፈጠረው አለመረጋጋት፣ ከማሊ የፈረንሳይ ጦር መውጣትና ማሊ ራሷ ከሳሀል ቡድን አምስት የጸጥታ መዋቅር መውጣቷም ሌላው የአህጉሪቷና የአካባቢው ራስ ምታት ሆኗል። የቻድ ሃይቅ ሸለቆ አካባቢ (በኒጀር፣ ቻድ፣ በካሜሮንና ናይጄሪያ) የሚስተዋለው የቦኮሃራምና ሌሎች የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ፣ በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ራሱን ኤም23 በማለት የሚጠራው ቡድን ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ጦር መማዘዙ እንዲሁም በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው በመንግሥትና በተቃዋሚ መካከል የተቀሰቀሰው የሽምቅ ውጊያ አሁንም አለመቆሙ፤ የአፍሪካ ኅብረት ጸጥታን በተመለከተ በዚህ ዓመት ትኩረት ሊያደርግበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው የእንግሊዙ ቻም ሃውስ የተሰኘው የጥናት ተቋም መረጃ የሚያመለክተው። በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በተለያዩ ደረጃ የሚካሄዱ 17 ብሔራዊ ምርጫ መኖራቸውንና ይህንንም ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የድኅረ-ምርጫ ፖለቲካዊ ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ አፍሪካ ኅብረት አዎንታዊ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበትም ተመላክቷል። የአፍሪካ ኅብረት ቀጣይ አቅጣጫስ? አፍሪካ ኅብረት በበርካቶች አይን ሲታይ ምንም እንኳን የፖሊሲና የስትራቴጂ ችግር ባይኖርበትም ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ተስተውሎበታል። ለዚህም ተቋሙ ካለበት የፋይናንስና ሌሎች ተያያዥ የቴክኒክ ችግሮች በተጓዳኝ በዋነኛነት አባል አገራት በኅብረቱ ቻርተር በመመራት ረገድ በርካታ ክፍተቶች መኖራቸው መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይም በጸጥታና ደኅንነት ምክር ቤት በኩል የሚወስናቸው ስምምነቶች ገቢራዊ አለመሆናቸው ትልቅ ክፍተት ሲሆን ምክር ቤቱም በቅርቡ ያደረገው ስብሰባ ይህንኑ አጋልጧል። ይህም አፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አመላክቷል። ለአብነትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የጥይት ድምፅ የማይሰማባት አህጉር ለመፍጠር ያቀደው ዕቅድ ምንም እንኳን ዕቅዱ ከጅምሩም ቢሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታና የግጭቶች የመስፋፋት አዝማሚያ ከግምት በማስገባት ሊሳካ እንደማይችል በርካታ የመስኩ ተንታኞች ቢናገሩም ኅብረቱ በዚህ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አልቻለም። ለዚህም ደግሞ በቀዳሚነት ምንም እንኳን የአባል አገራት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ትልቁን ድርሻ ቢይዝም የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ነው የሚያሳዩት። በአፍሪካ በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎች በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል። በተለይም ደግሞ አፍሪካ ኅብረት በቅርቡ ዳግም የከለሰውን በአህጉሪቱ የጥይት ድምፅ ለማጥፋት የወጣውን ፍኖተ- ካርታና እንዲሁም የክትትልና የግምገማ ማዕቀፍ ፈጥኖ ወደ ሥራ ማስገባት ይኖርበታል። ይህንንም ተከትሎ በጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤቱ ያቋቋመውን የባለሙያዎች ቡድን የያዘ ማዕቀብ ለመጣል የሚሰራው ንዑስ ኮሚቴም በአግባቡ መጠቀም አለበት። አሁን ላይ በአህጉሪቱ ለጸጥታ መስፈን ሥጋት በሚሆኑና በሚያቆጠቁጡ ጉዳዮች ላይ እልባት ለመስጠት መረባረብ እንዳለበት ነው የሚጠቀሰው። በተመሳሳይ የሚወስዳቸው እርምጃዎችም በባህሪያቸው ተከታታይነትና ወጥነት ያላቸው እንዲሁም ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ሳይሆን ከመፈጠራቸው በፊት አስቀድሞ መከላከልና ማክሸፍ ላይ ሊረባረብ እንደሚገባ ነው የሚያነሱት። ከዚህ በተጓዳኝ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችሉ የአገራትን የፖለቲካ እንቅስቃሴ መደገፍና በዘላቂነት ዴሞክራሲ ባህል እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎችን መደገፍ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። በተለይም ደግሞ ወጣቶችን ያሳተፉ የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎች በስፋት መሠራት እንዳለበት ነው የሚጠቀሱት። ከዚህ ጎን ለጎንም የአፍሪካ የእርስ በርስ መገማገሚያ መድረክም (ፒር ሪቪው ሜካኒዝም) በተለይም መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲጎለብት በማድረግ ረገድም አበርክቶው ከፍ እንዲል መሠራት ይጠይቃል። የሰላም ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የሰላም ፈንድም ማሰባሰብ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ላይ የሰላም ፈንዱ አጠቃላይ ገቢ 328 ሚሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 22 አባል አገራት ሙሉ በሙሉ እንዲሁም አምስት አገራት ደግሞ በከፊል የሚጠበቅባቸውን መዋጮ አዋጥተዋል። በሌላ በኩል 28 አባል አገራት ደግሞ መዋጮውን መክፈል አለመቻላቸውን ነው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ሪፖርት የሚያመለክተው። በመሆኑም አፍሪካ ኅብረት አባል አገራት የሚያዋጡትን ገንዘብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጨርሱ ቅስቀሳ ማድረግን በአፍሪካ ጥላ ሥር በተለያዩ አገራት የሚያንቀሳቅሰውን የሰላም ሥራ ውጤታማ ማድረግ ይገባዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተ.መ.ድ) የጸጥታ ምክር ቤት ጉዳይ ላለፉት 15 ዓመታት በአፍሪካ መሪዎች በስፋት የተቀነቀነው አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል የሚለው ጉዳይም አፍሪካ ኅብረት በዘንድሮ ጉባዔው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት አፍሪካን የተመለከቱ መሆናቸውና ይህም ሆኖ በምክር ቤቱ ውስጥ አፍሪካ አለመወከሏ የፍትሃዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል። በርካታ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም ኅብረቱን በሊቀ-መንበርነት የመሩት እስከ ወቅቱ ሊቀ-መንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ድረስ ጥሪያቸውን በተለያዩ መድረኮች አሰምተዋል። አሁን አሁን ላይም ጥያቄውን ምንም እንኳን የሩቅ ምስራቆቹ ጃፓንና ቻይና እንዲሁም ሕንድ አስቀድመው ቢቀበሉትም በተለይም አንዳንድ የምዕራብ አገራት ያሏቸውን የሃሳብ እቀባ በማንሳት ጉዳዩን እንዲጋሩት በማድረግ አፍሪካ ትልቅ ስኬት አግኝታለች። ይህም ሆኖ አሁንም አፍሪካ ስንት መቀመጫ ይኑራት? እንዲሁም ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ይሰጣት ወይስ አይሰጣት? የሚለው ጉዳይ ላይ ክርክሮቹ እንደቀጠሉ ነው። በዘንድሮ ጉባዔው ኅብረቱ በእነዚህ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚደረስበትን ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንንም ማድረግ ከተቻለ በአፍሪካ ቀደምት መሪዎች ሲቀነቀን የቆየውን "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች" የሚለውን ብሂል እውን ለማድረግና አህጉሪቷ ላይ ዘላቂ ሰላምና ደኅንነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ አዎንታዊ አበርክቶ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ጠንካራ አንድነት - ለዘላቂ ሰላም መሰረት!
Feb 3, 2023 524
በእንግዳው ከፍያለው (ባህር ዳር ኢዜአ) በረጅም እንጨት ጫፍና ጫፍ በገመድ ታስረው የተንጠለጠሉ ቋጠሮዎችን ተሸክማ ከጓደኞቿ ጋር ገበያ እየሄደች ነበር የተገናኘነው። ወጣት ማሪማ ሜካ ትባላለች፤ ዕድሜዋ ከሃያ ዓመት አያልፍም። በእንጨቱ አንደኛው ጫፍ 10 ሊትር አረቄ የያዘ ጀሪካን፤ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ሌላ ቋጠሮ በማንጠልጠል ተሸክማለች። ሸክሙን በትካሸዋ ላይ ጣል እድርጋ ፈጠን እያለች ስትራመድ ላየ በፊቷ ላይ አንዳች የብርታትና የጽናት መንፈስን ያነባል። እንደእኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው “ሴት ልጅ እንዴት ይህን ያህል ክብደት ተሸክማ ትጓዛለች?” ብሎ ራሱን ሊጠይቅ ይችላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዋ ወጣት ማሪማ ግን ሸክሙ እንደ ኩበት ቀሏት ይሁን ጽናቱን ፈጣሪ ሰጥቷት ባላውቅም በደስታ ወደ ፊት መራመዷን ቀጥላለች። “የኛ ችግር የምንይዘው ሸክም ሳይሆን የጸጥታ ስጋት ነበር” የምትለው ወጣቷ ባለፉት ዓመታት በኛ ላይ የደረሰው አስከፊ ሰቆቃና መከራ ለጠላትም እንዲገጥመው አልመኝም በማለት ትናገራለች። ባለፉት ዓመታት በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ሲከሰት የነበረው ግጭት የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለሞት፣ ለስደት፣ ለንብረት መውደም እንዲሁም ለተለያዩ ችግሮች ዳርጓቸው መቆየቱ የቅርብ ትውስታ ነው። አካባቢው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገነባበት፣ ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት፣ የስኳር ፕሮጀክቶችና ሌሎች የኢንዱስትሪ ልማቶች ያሉበትና ለመተግበር የታቀደበት በመሆኑ የውጭ ሃይሎች ግጭት እንዲነሳ እጃቸውን ሊያስገቡ እንደሚፈልጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ወጣት ማሪማ ግጭት በተከሰተባቸው በነዚያ አስከፊ ጊዜያት የነበረውን ሁኔታ፣ የደረሰውን ጉዳት፣ በተከፈለው መስዋዕትነት የመጣውን ሰላም በሚያስታውስ የተስፋ ስሜት "ጸረ ሰላም ሃይሎች ያስነሱት ግጭት ለዘመናት በአንድነት የኖረውን የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ተስፋ አጨልሞት ነበር፤ በሰላም እጦት ሁሉም ህዝብ ጫካ ገብቶ ኑሮውን ከዱር አውሬ ጋር ያደረገበት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው" ትላለች። በአሁኑ ወቅት ጸረ ሰላም ሃይሎችና ተባባሪዎቻቸው የፈጠሩት ሰው ሰራሽ ችግር ሊፈታ መቻሉ እፎይታን መፍጠሩን ትገልጻለች። በወቅቱ ሕክምና፣ መድሃኒትና ሌሎች የጤና መጠበቂያ ቁሶች ባለመኖራቸው ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በወባ እና ሌሎች በሽታዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች እንዳሉ በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላትና ሰላም ፈላጊ የአካባቢው ተወላጆች ከመንግሰት ጋር በመሆን ባደረጉት ጥረት የነበረው ግጭት ተወግዶ በአካባቢው ሰላም ሰፍኗል። ይህም ለማሪማና ለአካባቢው ነዋሪዎች እፎይታን በማጎናጸፉ በጣም ደስተኛ ናቸው። የተገኘውን ሰላም ተከትሎ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ ተነስታ በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ በመምጣት ለመገበያየት በቅታለች። ከጓደኞቿ ጋር ከቻግኒ ከተማ የሚፈልጉትን ገዝተው ወደ አካባቢያቸው ወስደው በትርፍ ለመሸጥ ምቹ ሁኔታም ተፈጥሮላቸዋል። በቻግኒ ከተማ የቅዳሜ ገበያ የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ። በርበሬ፣ የተለያዩ የጥራጥሬ፣ የቅባትና የአገዳ ምርቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ። አልባሳት፣ የሴቶች ጌጣጌጥ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች እንዲሁም ሌሎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች ንግድ ልወውጥ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗን በነበረኝ የአጭር ጊዜ ቆይታ አስተውያለሁ። ገበያተኛው የተፈጠረውን ሰላም በማጣጣም ላይ መሆኑን በገበያው ውስጥ ከሚያሳየው መስተጋብር መረዳት ቀላል ነው። እኔም ይሄን በተደጋጋሚ ታዝቢያለሁ። ከህዝቡ ፊት ያነበብኩት በግጭቱ የተነሳ በደረሰው ችግር ምክንያት ቁርሾና ቂም በቀል ውስጥ መግባትን ሳይሆን የሰላምና እርስ በርስ መዋደድና የመደጋገፍ ስሜትን ነው። ይሄን ደግሞ በቻግኒ ከተማ በሚካሄደው የቅዳሜ ገበያ መስተጋብር ላይ ተገኝቶ ማረጋገጥ ይቻላል። ገበያው የሁለቱም ክልሎች ህዝቦች ያላቸውን ይዘው መጥተው በነጻነት የሚገበያዩበት ነው። አሁን በሰላም ተገበያይቶ ወደ ቤት የሚመለስበት ሁኔታ በመፈጠሩ ለወጣት ማሪማ እና እንደ እሷ ላሉ ወጣቶች ደስታና እፎይታን ሰጥቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንዱራ ሚሊሻ የሆኑት አንመይ አልቤም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም መታጣት ችግር ዛሬ መፈታት በመቻሉ በነጻነት ያለስጋት ለመገበያየት መብቃቱን አስረድቷል። "ያ አሰቃቂና የእልቂት ጊዜ አልፎ ተገናኝተንና እርስ በርስ ተገበያይተን በሰላም ወደየቤታችን እንመለሳለን ብሎ ማሰብ እንደ ከንቱ ህልም ነበር" ይላል የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውስ። “ሚሊሻ እንደመሆኔ ከፌዴራልና ከክልሎች የጸጥታ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ ግጭት ቀስቃሾችን ለመፋለም ጨካ ለጫካ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም አይረሳኝም” ያለው ሚሊሻ አንመይ፣ ስንቶች በሕክምና፣ በመድሃኒትና ምግብ እጦት ህይወታቸው ማለፉን አንስቷል። "አማሟቴን አሳምረው" እንደሚባላው በወጉ መሞትና መቅበር ትልቅ ጸጋ መሆኑን የገለጸው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጥ በመግባት ነው። አሁን ላይ ሁሉም የደረሰውን ጉዳት በመርሳት የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ ነው። የሁለቱ ክልል ህዝቦች ቂም በቀልን ትተን በጋራ የምንሰራበት ወቅት ላይ መድረሳችን ህዝቡ ከጥንት ጀምሮ ያለው የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና አንድነት የመንፈሰ ጠንካራነት ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጸው። በእርግጥም የማንዱራ ሚሊሻው እንዳለው በአካባቢያቸው ትምህርት ቤቶች በመከፈታቸው ህጻናት ያለስጋት በመማር ላይ ናቸው። የጤና ተቋማትም የተለመደውን የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው። በሰላም እጦት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች በመከፈታቸውም ሁሉም ተሯሩጦ ኑሮውን ለማሸነፍ ላይ ታች እያለ ነው። ባለሃብቶችም በክረምቱ በግብርናው መስክ ተሰማርተው ማልማት ችለዋል። የጸጥታ ስጋት ተወግዶ ሌሎች የልማት ሥራዎች ሲተገበሩ ማየት ትልቅ ስኬት ነው። በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የቻግኒ ከተማ ነዋሪ አቶ ሲራጅ አዲስ እንዳሉት ግጭት በነበረበት ወቅት በአካባቢው የኢንቨስትመንትና የንግድ እንቅስቃሴ ተዳክሞ ነበር። እሱ ቀርቶ በሰላም ውሎ ለማደር ጊዜው ከባድ ነበር ይላሉ። "የተገኘው ሰላም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት በመሆኑ ሰላሙ አስተማማኝና ዘላቂ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል" ብለዋል። አሁን ላይ ያለፈውን የመከራ ጊዜ፣ በሞት የተለየውን ወገን፣ የወደመውን ሀብትና ንብረት በመርሳት በተገኘው ሰላም በጋራ ሰርቶ ራስንና አካባቢውን ለመለወጥ መትጋት እንደሚገባ ነው የመከሩት። ያለፈን በደልና ቅሬታ በእርቅና በይቅርታ በማለፍ ነገን ብሩህ ለማድረግ መትጋት አለብን በማለትም ነው ያስገነዘቡት። አቶ ሲራጅ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የጉሙዝ ማህበረሰብ ወደ ቻግኒ መጥቶ ያለውን ሽጦ የሚፈልገውንም ገዝቶ ይሄዳል፤ እነሱም ወደ መተከልና ማንዱራ በመሄድ ያላቸውን ይሸጣሉ፤ የፈለጉትንም ገዝተው የሚመጡበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይሄን አብሮነት በማጠናከር ሁለንተናዊ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላምን ማጽናት ላይ ጠንክሮ መስራት ይገባል። በአማራም ሆነ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ወንጀለኞችን አጋልጦ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። አሁንም የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትን አደብ እንዲገዙ ማድረግ ተገቢ ነው። ወንጀለኛን ለህግ አጋልጦ መስጠትን ከተለማመድን ነገም አካባቢውን የጦር ቀጣና ለማድረግ የሚፈልጉ የጥፋት ሃይሎች መግቢያ ቀደዳ አይኖራቸውም ይላሉ። ሃገር በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጎች የተባበረ ክንድ ትገነባለች፤ ደህንነቷም ድንበሯም ይጠበቃል። ለዛሬው ትውልድ የደረሰችውም የብዙዎች ዋጋ ተከፍሎባት እንደመሆኑ በጋራ በሰላምና በአብሮነት ይሄንኑ ማስቀጠል የግድ ይላል። በተለይም የሰላም ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት የሚወስድ እንደመሆኑ አካበቢን የመጠበቅ የነቃ ተሳትፎን ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ልታለማውና ልትጠቀምበት የምትችለው ገና ብዙ ያልሰራችበት ሃብት ባለቤት መሆኗ የአንዳንድ ሃይሎችን ቀልብ መሳቡ የሚጠበቅ ነው። ሰላሟ ሲረጋገጥ የዜጎች ደህንነት ሲከበር የተጀመረው የእድገት ጉዞ መፋጠኑ የማይቀር በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 150
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 328
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 452
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 635
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ሴቶችን በዘላቂነት በማቋቋም መሆን አለበት
Mar 8, 2022 2396
የካቲት 29/2014 (ኢዜአ) ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ሴቶችን በዘላቂነት በማቋቋም መሆን አለበት ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገሩ፡፡በዓለም ለ111ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ እለቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራትን እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የሴቶች አደረጃጀቶች ተቀናጅተው የሴቶችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሰሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ይሁንና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት በተለይ ሴቶች ይበልጥ ተጎጂዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በርካታ ሴቶች ለጾታዊና አከላዊ ጥቃት መዳረጋቸውንም ጠቅሰዋል። በመሆኑም ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ውስጥ የሚገኙ እናትና እህቶቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም ድጋፍ በማድረግ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። ከየካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ ማድረግን ዓላማ ያደረገ አገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚተገበር እቅድ በማውጣት ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን እየደገፉ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የተሃድሶ ስራዎች ደግሞ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ በዚህም ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በቀላሉ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ስፖርታዊ ውድድሮችን ለቱሪዝም ዕድገት ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ
Feb 26, 2023 1219
ሀዋሳ (ኢዜአ) የካቲት 19/2015 በኢትዮጵያ ከተሞች ስፖርታዊ ውድድሮችን በማስፋፋት ለቱሪዝም ዕድገት ጉልህ ሚና እንዲጫወት እየተሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። አትሌቶችን ጨምሮ 3 ሺህ 500 ሰዎች የተሳተፉበት 11ኛው የሶፊ ማልት ግማሽ ማራቶን ውድድር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በውድድሩ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሠላማዊት ዳዊት እንዳስታወቁት፤ የተለያዩ ኩነቶችን በማዘጋጀት ቱሪዝምን ለማነቃቃትና ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል። እስካሁን ከአዲስ አበባ ውጭ በሀዋሳና በቆጂ ስፖርታዊ ውድድር ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በሌሎች የክልል ከተሞች መሰል ውድድሮችን በማስፋፋት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋ ለስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ትላልቅ ኩነቶች ምቹ በመሆኗ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተስተናገደባትና ቱሪዝሙም እየተነቃቃ እንደሆነ ተናግረዋል። ስፖርታዊ ውድድሩ ለከተማዋ የቱሪስት ፍሰት ጉልህ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እያገዘ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በየዘርፉ ያሉ ስፖርተኞችን ለሀገር በማበርከት የምትታወቀው ሀዋሳ አገርን የሚወክሉ ስፖርተኞች ለማፍራት የምትሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅ ዳግማዊት አማረ ውድድሩን ስናዘጋጅ በዋናነት የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን የትኩረት ማዕከል በማድረግ ነው ብለዋል። ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በጋራ እየሰራን ነው ያሉት አዘጋጇ፤ ከተሳታፊዎች መካከል እጣ የደረሳቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የሚጎበኙበት ዕድል መመቻቸቱን ገልጸዋል። በውድድሩ ከግማሽ ማራቶን በተጨማሪ የስምንት ኪሎ ሜትር እንዲሁም የህፃናትና አዋቂዎች ውድድር መካሄዱን ጠቁመዋል። በ21 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች አንድ ሰዓት ከአንድ ደቂቃ 52 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ አንደኛ የወጣው አትሌት አበባው ደሴ ለኢዜአ በሰጠው አስተያየት ውድድሩ ብርቱ ፉክክር የታየበት መሆኑን ተናግሯል። የሀዋሳ አየር ንብረት ፀባይ ለውድድሩ ምቹ እንደሆነ ጠቅሶ በከተማዋ ተመሳሳይ ውድድሮች ሊስፋፉ እንሚገባ ጠቁሟል። በሴቶች አንድ ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ አንደኛ የወጣችው አትሌት የኔነሽ ደጀኔ ውድድሩ የመጀመሪያዋ እንደሆነ ተናግራለች። እንዲህ አይነት ኩነት ለተተኪ አትሌቶች መፍለቅ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ በሌሎች ከተሞችም ተጠናክሮ ቢቀጥል መልካም እንደሆነ አመልክታለች። በውድድሩበ አንደኝነት ላጠናቀቁ ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር እንዲሁም በወንዶች ከአንድ ሰዓት በፊት በሴቶች ደግሞ ከ70 ደቂቃ በፊት ውድድሩን ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ተጨማሪ ሽልማት ተዘጋጅቶ እንደነበርም ተጠቁሟል።
የካራማራ ድል የኢትዮጵያ ጦር በዜያድባሬ ጦር ላይ ታሪካዊ ገድል የፈጸመበት ነው ... በውጊያው የነበሩ የጦር መኮንኖች
Mar 5, 2021 1009
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2013(ኢዜአ) የካራማራ ጦርነት ድል የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ የወራሪው የዜያድባሬ ጦር ላይ ታሪካዊ ገድል የፈጸመበት ነው ሲሉ በአውደ ውጊያው ላይ የነበሩ የጦር መኮንኖች ገለጹ። ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሉዓላዊነት ሁልጊዜ ዘብ መቆም አለባቸው ብለዋል።  የካራማራ ጦርነት 43ኛ ዓመት የድል በዓል መታሰቢያ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት አደባባይ ተከብሯል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 ግልጽ ወረራ ኢትዮጵያ ላይ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኩባ ወታደሮችም የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል በማድረጉ የኢትዮጵያ አሸናፊነት በአደባባይ ታወጀ። በካራማራ ጦርነት በአውደ ውጊያው ላይ የነበሩ የቀድሞ የሠራዊት አባላት ብርጋዴል ጀኔራል ሃይለመለኮት ማሞ፣ ሻምበል ባሻ ሁሴን ጎበና እና መቶ አለቃ በቀለ በላይ ድሉን አስመልክቶ የምስክርነት ቃላቸውን ለኢዜአ ሰጥተዋል። ጦርነቱ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባውን ወራሪውን የሶማሊያ ጦር ከአገር ለማስወጣትና ድል ለማድረግ የሕይወት መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑንና ኢትዮጵያም በድሉ ክብሯ መጠበቁን ገልጸዋል። በምድርና በአየር ወራሪ የሶማሊያ ጦርን በመደምሰስ የኢትዮጵያ ሠራዊት ታሪካዊ፣ አስደናቂ ገድልና ጀብድ መፈጸሙንም ተናግረዋል። በወቅቱ የነበሩ የሠራዊቱ አባላት ሕይወቴ ከአገሬ አይበልጥም ብለው ያሳዩት ተጋድሎ የማይረሳ ነው ብለዋል የጦር መኮንኖቹ። ኢትዮጵያዊያን ሁልግዜ አገራቸውን ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸውና ለሉዓላዊነቷ ዘብ መቆም እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስ የካራማራው ጦርነት ኢትዮጵያ በውጭ ወራሪ ኃይል ላይ ያስመዘገበችው ድል መሆኑን ገልጸዋል። በጦርነቱ ላይ የኩባ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጎን በመሆን መዋጋታቸውንና 163 ኩባዊያን ወታደሮች የሕይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውን ተናግረዋል። "የተገኘው ድል በኢትዮጵያና በኩባ ሕዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት ትስስር የሚያሳይ ምስክር ነው" ብለዋል። "ኢትዮጵያና ኩባን ከ43 ዓመት በፊት ያስተሳሰረ የወዳጅነትና ትብብር መንፈስ አሁንም አለ" ያሉት አምባሳደር ቪልማ፤ አገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለማጠናከር እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን አገሮች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ቤኩማ መርዳሳ ፣ "የካራማራ ድል ኢትዮጵያዊያን የዚያድ ባሬ ወራሪ ኃይል በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመውን ወረራ በመመከት ድል የተጎናጸፉበት ታሪክ ነው" ብለዋል። ድሉ ኢትዮጵያ ወራሪ ሃይልን በማሸነፍ ዳግም ነጻነቷን ያወጀችበትና ኢትዮጵያዊያን የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለው ሉዓላዊነታቸውን ያስጠበቁበት እንደሆነም አክለዋል። ኩባ በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ያሳየችው አጋርነት ኢትዮጵያ ሁሉጊዜ የምታወሳውና የምትዘክረው እንደሆነም አመልክተዋል። የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበበ አያሌው ማህበሩ በአጥንትና በደም የተሳሰረውን የኢትዮጵያና ኩባ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ኩባ ከኢትዮጵያ ጎን ሆና ላሳየችው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ታማኝ በየነ "የካራማራ ድል ኢትዮጵያዊያን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ኢትዮጵያን ያቆዩበት ታሪካዊ ገድል ነው" ብለዋል። ኢትዮጵያዊያን በታሪክ ከተገኙ ድሎች በመማር አሁንም ቢሆን ከልዩነታቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም አገራቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያን ሁልጊዜም ታሪክ ለሰሩ ወታደሮችና የጦር ሠራዊት አባላት ክብር መስጠት አለባቸው ብለዋል። በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ በተከበረው የድል በዓል የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በጦርነቱ ለተሰው ጀግኖች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። ከኢትዮጵያዊያን የየካቲት ወራት ድሎች አንዱ የሆነው የካራማራ ድል 43ኛ ዓመቱን አስቆጥሮ የድል በዓሉ በኢትዮጵያዊያን ዛሬም እየተከበረ ይገኛል።
ባለፉት ስድስት ወራት በሀገራዊ ዕድገትና ገጽታ ግንባታ ላይ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ተሰርቷል--የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Mar 4, 2023 869
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 25 ቀን 2015 በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት በአገራዊ ዕድገትና ገጽታ ግንባታ ላይ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መከናወኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተዘጋጀው የፌዴራልና ክልል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።   የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ በጫናዎች ውስጥ ሆናም በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት፣ በመልካም አስተዳደር ሥራዎች፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እንደ አገር የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ለእነዚህ ስኬቶች የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አስተዋፅኦ ድርሻ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። በመንግስት እና ሕወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዲዝ እንዲሁም በሌሎች አገራዊ ስኬቶች ላይ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ጠንካራ ስራ አከናውኗል ነው ያሉት። "በኢትዮጵያ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ውስብስብ ችግሮችን በመፍጠር ተጽእኖ አሳድረዋል" ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይሄንን በመመከትም አበረታች ስራ መሰራቱን አመልክተዋል። "የዜጎች ሰላም ወጥቶ በሰላም መመለስ እረፍት የሚነሳቸው የውስጥና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማመስ የሚያደርጉትን እኩይ ሙከራ ማክሸፍ ይገባል" ብለዋል። "ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል ተወጥታ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን እንድታደርግ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በተናበበ አኳኋን መምራት የሚጠበቅብን ወቅት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ለገሰ፤ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ በዘርፉ የሚከናወኑት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። በቀጣይም አክራሪነትና ፅንፈኝነትን በቅንጅት በመመከት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚመጥን የሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባም ሚኒስትሩ አሳስበዋል።    

የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ ነው -ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ
Mar 3, 2023 802
ባህር ዳር (ኢዜአ) የካቲት 24/2015 የግብርናው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ። የክልሉ ግብርና ቢሮ ዛሬ 241 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረክቧል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት አመታት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት የተሰጠ ቢሆንም አሰራሩ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ በኩል ለውጥ ሳይመጣ ቆይቷል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በተግባር የታገዘ ለውጥ የሚያመጣ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በስንዴና አኩሪ አተር ምርት በክልሉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ጊዜ የሚቆጥቡና የምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በረጅም ጊዜ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ የማዘመንና በረጅም ጊዜ ክፍያ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እንዲያገኝ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በተለመደው መንገድ መሄድ እንደማያዋጣ የገለጹት ደግሞ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ናቸው። የግብርና ምርታማነትን በፍጥነት ለማሳደግ ዘመኑ ያፈራቸውን ጊዜ ቆጣቢና የአርሶ አደሩን ድካም የሚቀንሱ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ባለፉት ዓመታት መንግስት የግብርናውን ዘርፍ የሚያዘምኑ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የእርሻ ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥ ነጻ እያስገባ መሆኑን ተናግረዋል። በሃገር አቀፍ ደረጃ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርታማነትን በማሳደግ በኩል ብዙ እንደሚቀር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከሚታረሰው መሬት 22 በመቶው ብቻ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ገልጸዋል። አርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታዎች መቅደም እንዳለባቸው አመልክተው፤ ለዚህም አንዱና ዋነኛው መሬትን በኩታ ገጠም ማረስ እንደሆነ አብራርተዋል። ለዚህም ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ዶክተር ግርማ፤ አሁን ላይ እንደ ሀገር 6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ተደራጅቷል ብለዋል። ''አርሶ አደሩ በቴክኖሎጂ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው'' ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማሪያም ከፍያለው ናቸው። በክልሉ ለዓመታት የነበሩት ትራክተሮች ከ800 ያልበለጡ እንደነበሩ አስታውሰው፣ ባለፉት ሁለት ዙሮች ብቻ ከ700 በላይ ትራክተሮች ለአርሶ አደሮች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ በዘር በመሸፈን ላይ ከሚገኘው 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር የእርሻ መሬት 11 በመቶው ብቻ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚታረስ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ለአርሶ አደሮች ትራክተሮችን የማቅረብና ሌሎች የማዘመን ጅምር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የክልሉ መንግስት በረጅም ጊዜ ክፍያ የትራክተር ባለቤት እንዲሆኑ ማድረጉ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ደግሞ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደንብያ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አሰፋ አያሌው ናቸው። አርሶ አደሮቹ የተረከቧቸው የእርሻ ትራክተሮች የተለያየ የፈረስ ጉልበት እንዳላቸው ተገልጿል። በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል"-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Feb 26, 2023 798
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 19/2015 ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል። በማጠቃለያው ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን የመከላከል ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አገልግሎት አሰጣጥን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ ለማስቻል በርካታ ዘርፎችን የማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ የነዋሪውን ችግር እንዲያቀሉ የተጀመሩት የእሁድ ገበያ እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል። በእሁድ ገበያ ለመሰረታዊ ፍጆታ የሚሆኑ ምርቶች በቀላሉ ህብረተሰቡ ጋር እንዲደርሱ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል። አስተዳደሩ ከተማዋን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ውብና ምቹ ከማድረግ ባሻገር ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ከተማነቷን የምትመጥን ለማድረግ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ተግባራዊ እያደረገ ነውም ብለዋል። “ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር አመራራችን ፅንፈኝነትን፣ ጥላቻን፣ የህብረተሰቡን አንድነት የሚንዱ አስተሳሰቦችን፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረጉ የሚዲያ ዘመቻዎችንና ሌሎች የፓርቲያችን እሳቤ ያልሆኑ አመለካከቶችን በመዋጋት ረገድ እየተሰራ መሁኑ ተናግረዋል። “አሁንም ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት እና በህቡእ አደረጃጀት የሚደረግ ህገ-ወጥነት ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል” ሲሉ መግለጻቸውን ከንቲባ ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል። በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት ያልተከናወኑ ተግባራት ተለይተው በእቅድ ክለሳ እንዲካተቱ በማድረግ የህዝቡን ኑሮ የሚያቀሉ ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰሩም ከንቲባ አዳነች አክለው ገልጸዋል።
ሴትነት እና እናትነት
Mar 8, 2023 795
(አየለ ያረጋል) እስኪ መላ ስጪኝ መላ ካንቺ ይገኛል እኔማ ወንድ ነኝ ይደናገረኛል… (የማኅበረሰቡ ቃላዊ ግጥም) ሴትነት እናትነትን ለመግለጽ ቀርቶ በጥቂቱ ለመረዳት የ’እናት ልብ’ መታደል የሚሻ ይመስላል። ጥቂት ወንዶች ይህን ጸጋ ይቸራሉ። ልክ እንደ ዶክተር ይሁኔ አየለ። የስነ-ምግብ ሳይንቲስቱ ዶክተር ይሁኔ አየለ ‘እናት’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፍ የሴትነት እና እናትነትን ከፍታ በ’ኩርሽም’ ቃላት ተራቀውበታል። የሴቶች ቀንን (ማርች-8) ሰበብ በማድረግ ይህን ጽሑፍ ሳዘጋጅ መታሰቢያነቱ እናትን አስበው በ‘እናትነት’ ቅን ልቦና ‘እናትን’ ላበረከቱልን ዶክተር ይሁኔ አየለ ነው። ‘እናት፤ የሴት ልጅ ስንክሳር፤ ከቤተሰባዊ ሕይወት እስከ ሐልዮመንበርት’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባሳተሙት (በ406 ገፆች በተቀነበበ) አርበ ጠባብ መጽሐፍ ሴትነትን ከዘፍጥረት እስከ አሁን ዘመናትን ዋጅተው፣ እናትነትን ከሴትነት ዘንቀው፣ የእናትነት ጸጋን ከነባራዊ ሃቅ ጋር አሰነናስለው፣ የእናትነትን ልዕለ-ተፈጥሮ አርቅቀው፣ የዓለምን ክብር-ነሽነት ከነገረ-ሃይማኖት እስከ ነገረ-ባህልና ፍልስፍና ፈትተው፣ የማኅበረሰቡን ምልከታ ዝንፈት እና ሚዛን ጉድለት ከማኅበራዊ እስከ ፖለቲካዊ መገለጫዎች አዛምደው አቅርበውታል። ዶክተር ይሁኔ አየለ “እናት” በተሰኘ እናት የሆነ መጽሐፋቸው እናትነትን በልኩ ነጽረውታል። ሴትነት በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ሰለባነቱን፣ ነገረ-ሴትነትን ከንጽረተ-ሴትነት ቃኝተውታል። በእሳቤ ሚዛን ሰለባነት ዓለም ውስጥ ከንግስት ማክዳ እስከ ንግስት ፉራ፣ ከሰብለ ወንጌል እስከ ድል ወንበራ፣ … ብርቱ ኢትዮጵያዊት ሴቶችን ሕይወት ጨልፈውታል። የሴትነትን ጸጋዎች ጨልፈው በሴትነት ላይ የሚፈጸሙ የሀበሻ ግፎችን ተንትነውበታል። ሴቶች የማኅበረሰቡ ግፍ ሰለባዎች፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጉድለት ሰለባዎች እንደሆኑ በቅጡ ገልጸውታል። ዳሩ ሴትነት ጀግና እና ብልህ፣ የቤተሰብ መሰረት፣ የደስታና እልልታ እናት፣ ቃል ኪዳንና ክብር ጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል። “ሴት ልጅ ባለብዙ ጸጋዎች ናት። ከጸጋዎቿ መካከል ጀግንነት እና ብልሃት ይጠቀሳሉ። … ሴት ልጅ ባህልን ፈጥራ የማኅበራዊነትን ማስተሳሰሪያ ገመዶች ገምዳ አስተሳስራ ማኅበረሰብን የተከለች ሥርዓት ናት። … ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ የመጀመሪያ ተቋም ነው። የተቋሙ ባለሥልጣን (እመቤት) ሴት ናት። ያቺ ሴት እናት ናት። ቤተሰብ የስብዕና መሰረት የሚባለው እናትን ምሰሶ አድርጎ ነው” (ገጽ-285) ሴት ልጅ መለኛ መሆኗን ማኅበረሰባችን ቢያምንም ሴትነትን ግን እንዳላከበረ አሉታዊ ይትባህልና ኪነተ- ቃሉን ዘይቤ ያወሳሉ። በእርግጥ የእናትን ምቹነት እና ዋጋ ከፋይነት የሚያትቱ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችም አሉ። ለምሳሌ ዳንኤል አበራ “የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች” በሚለው መጽሐፋቸው “እናት ትረገጣለች እንደመሬት፤ እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ፤ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ፤ እናት የሌለው ልጅ እንደ ጌሾ፤ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ…” የሚሉ ምሳሌያዊ ንግግሮችን አስፍረዋል። መላኩ ይርዳው የተባሉ ጸሐፊ ‘ደቦ ቅጽ-፩’ ከተሰኘው የ60 ደራሲያን ሥራዎችን ያካተተ መጽሐፍ ውስጥ ‘የሴትነት ጸጋ’ በሚል በጻፉት መጣጥፍ ሴትነትን ከፍቅር፣ ከጥበብ፣ ከብልሃትና ልዕልና ጋር አቆራኝተውታል። “ሴት ልጅ ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አልታዩኝም። የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የተረዳነው አይመስለኝም።… ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለሴት ልጅ የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንስብኛል” ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስለሴት ልጅ ጭቆና የታገለ እና ስለክብሯ የዘመረ ምሁር ነው። ስለሴት ልጅ ስቃይና ሰቆቃ አትቷል። ‘በናቴኮ ሴት ነኝ’ በሚለው መጽሐፉ ስንኞች እንምዘዝ! …. ግማሽ አካሏ ወንድ በትምክህት ቢከዳት ጧ! ብላ አለቀሰች አዛኝ ቢደርስላት፣ … ብሶት ተጫጭኗት ምንም ሰው አልሆነች በቀቢጸ ተስፋ ሕላዌንም ጠላች ያገሬ ጭቁን ሴት መድኅን መላ ያጣች….! ‘ሔዋንያት የትውልድ ፋብሪካዎች ናቸው፤ እነሱ ባይኖሩ ዓለም ባዶ ትሆን ነበር’ እንዲል ፈላስፋው ሶቅራጥስ። ስለሴት (ግማደ ሰቧ ፍጡር) ግፍና በደል ገሞራው እንዲህ ይላል። “መራራ ጭቆና በሰፈነበት ምዝብር ሕብረተሰብ ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ሔዋንያት ብሶታቸው፣ ፍዳቸው፣ በደላቸው፣ ጭንቀታቸውና መከራቸው እንደ ሰማዕታት ገድል እጥፍ ድርብ ነው…. አጉል ልማድ፣ ኋላቀር ባሕልና አድሃሪ ሕገ-ማኅበረሰብ ከከንቱ አስተሳሰቦች ጋር ተዳምሮ በአንድነት በመመሳጠር ዘርዓ ሔዋንን ሲጫወቱባቸው ሲያሾፉባቸው ኑረዋል” (ገጽ-23) በሥነ-ሕይወት ሳይንስና በትምህርተ-ጄነቲክስ (አካለ ሕላዌ) ሴቶችን ከወንዶች የሚያሳንስ ምንም አይነት አካላዊ ተሰጥኦ እንደሌለ ተረጋግጧል። ታሪክና ተረክ ግን ወገንተኛ መሆኑን ገሞራው ይናገራል። ተረክና ተረት አልባሌ ታሪክ የሚፈጥሯቸው አርበኞች ሁሉ በፆታቸው ተባዕት በመሆናቸው፤ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ሊኖራቸው የሚችለው ዕድገት ላይ ትልቅ ደንቃራ ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። “የታሪክን ሁኔታዎችን የመመንዘር ትርጓሜያዊ አንጻር የታሪክን ትዕይንቶች ብንመረምር አንደርድሮ የሚያደርሰን ሴቶች ከወንዶች የከፋ ባህሪያዊ ድክመት እንዳለባቸው ከሚያሳይ ሥዕል ላይ ነው።” በሚት(ተለጣጭ ተረክ) ላይ የሚራቀቁት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፎክለር መምህር) ‘ተረኮች እማዊ ሳይሆን አባዊ ናቸው’ በማለት ይህን ጉዳይ ያጠናክሩታል። “በሚት ውስጥ ገነው ከሚታዩ አበይት ማኅበራዊና ባህላዊ እውነታዎች መሃል አንዱ ፆታዊ ወገንተኝነት ነው። የሰማናቸው፣ ያነበብናቸው ሚታዊ ተረኮች በእጅጉ አባዊ ለሆኑ ሥርዓቶች (ፓትሪያርካል ሲስተምስ) ያደሩ፣ በአብዛኛው በተባዕት ተጋዳሊያን የተሞሉ ናቸው” ይላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ይሁኔ (በገፅ-401) ስለሰው ማንነት ቀረጻ በተመለከተ ከጥንት እስከ ዛሬ አከራካሪ የሆኑ ፈላስፎችን ክርክር ያነሳሉ። ይኸውም የሰው ልጅ ‘ማን ቀረጸኝ? ተፈጥሮ ወይስ ተሞክሮ?’ የሚለውን መከራከሪያ ጽንሰ-ሃሳብ ይፈትሻሉ። በዚህም “ሰዎች ሲፈጠሩ የሰውየውን ችሎታ ይዘው ነው” እና “የሰዎች ማንነት የሚቀረጸው ከውልደት በኋላ በተሞክሮ ወይም ከአካባቢ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ነው” የሚሉትን ሃሳቦች ወስደው ከእናት ሚና ጋር ያዛምዱታል። እናም እናት ‘በየትኛውም መደብ ልጅን አሳምራ ትቀርጻለች’ የሚል ድምዳሜ ሰጥተዋል። “በየትኛውም መንገድ በሰው ልጅ ላይ የእናት ቀራፂነት ስለሚኖር ከተጽዕኖዋ ማምለጥ የሚቻል አይመስለኝም።… አካባቢም ሰውን ይሰራዋል የሚሉትም ከውልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር የሚደረገው ውስብስብ መስተጋብር ‘ሰው’ በመሆን ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል” ይላሉ። በዚህ እሳቤ ሰው የወላጆቹም፤ የአካባቢውም ውጤት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን” ይላሉ። ሴቶች ከጥንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ማኅበረ-ባህላዊ እንዲሁም ለሰላምና ዕርቅ እሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው። ሴቶች ያልተሳተፉበት ዘርፍ የለም። ከመሪነት፣ ጥበበኝነት፣ ከአገር ድንበር ጠባቂነትና የዲፕሎማሲያዊ ሚና… መጥቀስ ይቻላል። ሴቶች በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ በሰላምና ግጭት አፈታት ግንባር ቀደም ተሰሚነት አላቸው። ለአብነትም ሀደ ሲንቄ፣ በሶማሌ-ሔር፣ በሲዳማ-ያካ፣ በራያ ማኅበረሰብ ዱበርቲዎች፣ በስልጤ-ሴረን ባህል መጥቀስ ይቻላል። ከሰሞኑ ባከበርነው የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሴቶች ውለታ በወፍ በረር ማውሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ ሴቶች ከሌላው ዓለም ሴቶች በተለየ የራሳቸው ቀለም ያላቸው፣ የአመራር ልምድ ያዳበሩ፣ የመወዳደሪያ ስነ-ልቦና ያላቸው፣ ችለው አሸንፈው ያሳዩ ናቸው። ሴቶች ድሉን በማስመዝገብ የተጫወቱትን ሚና ያህል፣ ገድላቸው በታሪክ በሚገባ አልተወሳም። ዶክተር አልማው ክፍሌ የተባሉ የታሪክ ምሁር በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ሲሉ ሰምቻለሁ። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች በርካታ ናቸው። ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡- “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችዎን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) ዶክተር ይሁኔ (በገጽ-14) በበኩላቸው እናቶችን ሩህሩሆች፣ አጉራሽና አልባሽ፣ የችግር ቤዛዎች፣ ሕይወት ዑደት አስቀጣዮች፣ የሕይወት መድኅኖች፣ ባለብዙ ጸጋዎች፣ መልካም ባህሪ አውራሾች፣… በማለት ገልጸውታል። መላ ሴቶችንም በእናቶች አተያይ ማየት እንደሚገባም እንዲሁ። “እናትነት መልካም ገጽታዎችን ደራርቦ የያዘ የሴት ልጅ ትልቅ መገለጫ ነው። እናትነት ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። እናትነት ጥልቅና ሰናይ ባህሪያት የሚፈልቁበት ምንጭ ነው። እናትነት የደግነት፣ የጥራት፣ የልህቀትና ተፈላጊነት ማሳያ ተምሳሌት ነው። እናትነት ሞት የማያደበዝዘው ኃያል መንፈስ ነው። እናትነት ከባድ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። … እናትነት የሰላም፣ የመልካም ግንኙነትና እንክብካቤ መፍለቂያ አድባር ናት። እናትነት ሰፊና ጥልቅ የሕይወት ትምህርት ቤት ነው። እናትነት ሌሎች ከስቃይ ነፃ እንዲሆኑ፣ ምቾት እንዲሰማቸው በሚደረግ ትግል ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ መኖር ነው” በመቀጠልም የኢትዮጵያ እናቶችን ‘ጠቃሚ ነገር ሰጪዎች’ ይላቸዋል። “እናቶች ሰው የመሆኛ ቅመሞች የሚጨለፍባቸው ባህር ናቸው። … ሕይወታዊ ስሪታችን ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የወሰደው ከእናት ነው። ከእናት የምናገኘው ‘ማይቶኮንድሪያ’ (ማይቶኮንድሪያ የኃይል ማመንጫ ክፍል ሲሆን የምንመገበው ምግብ እየተቃጠለና ወደ አስፈላጊው ኃይል እየተቀየረ ሕይወትን ያንቀሳቅሳል) የምግብ ማቃጠያ ምድጃ ወይም ኃይል ማመንጫ ቤት ሆኖ ያገለግላል። … ብዙ መልካም ስብዕና መገለጫዎች ምንጫቸው የእናት ፍቅር፣ የመልካም ስብዕና እና የርህራሄ ምንጭ ነው” (ገጽ- 61) ኢያሱ በካፋ ‘የኢያሱ በካፋ ወጎች’ በተሰኘው መጽሐፉ እናትነትን ማህጸንን፣ ምግብን፣ ትንፋሽን፣ ደም፣ ሥጋን እና ነፍስን ሰጥተው በረቂቅ ተፈጥሮ ሰውን ከመውለድ ባለፈ ፍቅራቸውን ዘላለማዊ ገደብ አልባ እና ዕልቆ-ቢስ እንደሆነ እንዲህ ገልጾታል። “እናትነት ነፍስን ማካፈል ነው፤ እናትነት የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር መስጠት ነው፤ እናትነት ከራስ ሕልውና ይበልጥ ለልጅ ማሰብ ነው፤ እናትነት ፍፁም ወረት አልባ መሆን ነው። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር አይነጥፍም፤ አይለወጥም። ለእናት ልጇ ሁሌም ልጇ ነው” (ገጽ-4) እናትነት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ፤ በውለታ ማካካስ ይከብዳል። የእናት ውለታዋን መክፈል የሚችል ልጅ የለም። የእናት ፍቅርን ለመግለጽም በርካቶች አንደበታቸው ይተሳሰራል፤ ቃላት ይነጥፍባቸዋል፤ ስሜታቸውን መግራት ይሳናቸዋል። ድምፃዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) ‘ይናገራል ፎቶ’ በሚል እናትና አባቱን በገለጸበት ሙዚቃ የመጨረሻው ማጠንጠኛው ‘እወድሻለሁ/እወድሃለሁ’ ያለው፤ እንዲሁም ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ‘እናት ውለታዋ’ በተሰኘ ዘፈኗ ውስጥ (ዜማና ግጥም ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ)፤ “ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ” እያለች በሚስረቀረቅ ድምጿ የምታንጎራጉረው ለዚህ ይመስላል። ዕውቁ የቋንቋ ሊቅ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) ‘የጥቁር አፈር ትሩፋቶች’ በተሰኘው መጽሐፉ (ገጽ-79) ‘መቀነትሽን አጥብቂ’ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ረዘም ያለ ግጥም ሁለት አንጓዎች ብቻ ስንመዝ የእናትነት ውለታን መመለስ እንደሚሳን፤ የእናትነት ግብሯ ‘እናት’ የሚለው ቃል በራሱ እንደሚያንስባት ያትታል። … “ለዚህ ወሮታሽ አጸፋ፤ እናት ይልሻል አገሩ፤ እኔም እናቴ ብልሽ መች ሊመጥንሽ ዳሩ። … እናትነት ምጡቅ ነው፤ እናት ከመባል ይልቃል፤ የግብርሽ ስንክሳር ዚቁ፤ በስያሜ መች ያልቃል”… በማለት ይገልጸዋል። መውጫ ዶክተር ይሁኔ የሴት እና እናትን የነገዋን መንገድ ከሳይንስ አተያይ አንጽረው፤ ከማኅበረ-ፖለቲካ፤ ከማኅበረ-ባህል ከፍታዋ አመሳክረው፤ እናትና ሀገርን መጋመድ አመስጥረው መልእክታቸውን እንደ መውጫ አስፍረዋል። ለስንበት አንድ አንቀጽ እንወርውር!! “የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። የሰመረ ትውልድ ሊቀጠል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው። የእናቶች አቅም ሲገነባ የራሳቸውን አቅም ያውቃሉ፤ ምርጫቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እንዲሁም ለሚመጣው ማኅበራዊ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ። ስለሆነም የእናቶችን አቅም ማጎልበት ትውልድን ማጎልበት ነው። እናቶች ላይ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት ነው”  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን ተደራሽ የሚያድረግ ድረ-ገጽ አስጀመረ
Mar 4, 2023 745
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 25/2015፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ መረጃዎችን በፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች ተደራሽ የሚያደርግ አዲስ ድረ-ገጽ አስጀመረ። አዲሱን ድረ-ገጽ በይፋ ስራ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ትዕግስት ሀሚድ ናቸው። የተቋሙ ዌብ አድሚኒስትሬተር ሄኖክ አብይ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት አዲሱ ድረ-ገጽ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች በእኩል ጥራት ለማድረስ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ነው።   የተቋሙን ብራንድ መሰረት ባደረገ መልኩ የተዘጋጀው ድረ-ገጹ ከመረጃ ጥራትና ደኅንነት አንጻርም አስተማማኝ ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አማካኝነት መገንባቱንም ገልጸዋል። ድረ-ገጹ ከዚህ ቀደሞ በተቋሙ ሲሰራባቸው የነበሩትን እንግሊዝኛ ፣ አረብኛ ፣ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞን ጨምሮ በአዲስ መልኩ በቅርቡ የተጀመሩትን ፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎችን በማካተት አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መደራጀቱን አስታውቀዋል። የኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ እንዳሉት ኢዜአ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገነቡ ሀገራዊ ጉዳዮችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ የሚያደርጉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ። አሁን ይፋ የሆነው አዲስ የድረ-ገጽ ይሀንኑ አላማ ለማስፈጸም የሚያግዝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው አስተማማኝነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ ዘመናዊ አገልግሎት ማቅረብ እንዲያስችል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መገንባቱን ተናግረዋል። በቀጣይም ኢዜአ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዘርፉ ልማት ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው ተቋማቸው የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከኢዜአ ጋርም በዘርፉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል በጋራ ከመስራት ባለፈ በቀጣይም በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንኙነት የሚያሳድጉ ተግባራትን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። በድረ-ገጹ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።  
መጣጥፍ
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 592
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ)
Jan 25, 2023 627
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ) አየለ ያረጋል (ኢዜአ) መዳረሻዬ ሽሬ እንዳስላሴ ነው። ለዘገባ ሥራ ከባህርዳር- ጎንደር- ደባርቅ- ሸሬ መንገድ ከሚዲያ ባልደረቦች ጋር እየተጓዝኩ ነው። የጥምቀት ሙሽራዋ ጎንደር እየተኳኳለች ነበር። ደባርቅ ከመድረሴ በፊት ዳባት ትገኛለች-የደጃች አያሌው ብሩ ቁርቁር ከተማ። ደጃች አያሌው ትውልዳቸው በጌምድር ጋይንት ቢሆንም ግዛታቸውና ኑሯቸው ዳባት ነበር። ሞገደኛው ደጃዝማች አያሌው ብሩ በጎንደር ማኅበረሰብ ዘንድ ዝናቸው የናኘ ነው። ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ (ከልጅ ኢያሱ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት) ታሪካዊ ክንውኖች ጉልህ ተሳትፎ አላቸው። አንዷን ብቻ ልምዘዝ። ራስ ተፈሪ ‘ንጉሠ-ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ’ ደጃች አያሌው የቅርብ ዘመዳቸውን ራስ ጉግሳ ወሌ ብጡልን (የንግሥት ዘውዲቱን ባለቤት) ወግተው የጎንደር ግዛት ‘ራስ’ ተብለው ለመሾም ቃል ቢገባላቸውም፤ ተልዕኳቸውን ተወጥተው ቃሉ ባለመፈጸሙ ደጃዝማቹ ከአጼው ጋር መቀያየማቸው አልቀረም። በዚህም:- "አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፣ የአያል ጠመንጃ፣ ስሟን እንጃ ስሟን እንጃ…” በማለት የጎንደር አዝማሪ አዚሟል። ዛሬም ይህ ግጥም የብዙ ባህላዊ ዘፈኖች አዝማች ነው። ደጃች አያሌው ብሩ ደፋር ናቸው ይባላል። ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር ቢቀያየሙም በ1928 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲመጣ ቅድሚያ ለአገሬ ብለዋል። ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘው የዶክተር ሀራልድ ናይስተሮም (ትርጉም ገበየሁ ተፈሪ እና ደሳለኝ አለሙ) መጽሐፍ እንደተጠቀሰው ደጃች አያሌው “ንጉሡ እንደኛ ሰው ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሁላችንም ናት" ብለው ጦራቸውን መርተው በሽሬ ግንባር ዘምተዋል። ጉዟችን ቀጥሏል። ደባትን እያለፍን ነው። ‘እንኳን ደህና መጡ፤ ወደ ጭና ታሪካዊቷ ሥፍራ’ የምትለዋን ታፔላን በስተግራ እያየን ወደ ደባርቅ ገሰገስን። የሰሜን ተራሮች የብርድ ወጨፎ ያረሰረሳትን ደባርቅን ከማለፋችን ሊማሊሞ ጠመዝማዛ ቁልቁለት ተቀበለን። አስፈሪ የሊማሊሞ መልክዓ ምድር የደጋው ሰሜን ውርጭ እና የተከዜ በርሃ ኬላ ነው። ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን “የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ አይበገር የዐለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ ሊማ-ሊሞ አድማስ ሰበሩ፣ በጎማ ፈለግ ይፈታ? በትሬንታ እግር ይረታ?…” ብሎ የመኪና መንገድ ተገንብቶበት በማየቱ ግርምቱን የተቀኘለትም ለዚህ ይመስላል። ከሊማሊሞ ቁልቁለት በኋላ አዲ-አርቃይ፣ ዛሪማ፣ ማይፀብሪ እና ሌሎች የጠለምት ወረዳ ከተማዎችን አልፈን፤ የዋልድባ ረባዳማ አካባቢዎችን ተሻግረን ተከዜ ወንዝ ደረስን። የዚህን መንገድ እና ተከዜ ወንዝን ሳስብ የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ አስተከዘኝ። የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር የወገንን ጦር ፊት ለፊት መቋቋም ሲሳነው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማያውቅ መርዝ በጅምላ የፈጀበት አሳዛኝ ታሪክ ነበር። በተከዜ ወንዝ ውሃን በመመረዝ የወገን ጦር ያለቀበት ሥፍራ ነው። የተከዜ ሸለቆ በኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በአንድ ዕለት የተመለከቱትን እንዲህ ጽፈውታል። “የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ላይ ሰፊና ፀጥ ያለ ነው። ታዲያ ያ ሰፊ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት ቀይ ቀለም በከባዱ የተበጠበጠ ይመስላል። “ምን ነገር ነው፤ ምን ጉድ ነው?” እየተባባልን ቀረብ ስንል መሻገሪያው በቁሙም በወርዱም ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶበት የዚያ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው። የሰው ሬሳ፣ የፈረስ እና የበቅሎ ሬሳ፣ ያህያ ሬሳ፣ ያውሬ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከእግር እየተመሰቃቀለ እየተደራረበ ሞልቶበት፥ የዚያ ሁሉ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው”። ይሉናል። ቀጥለውም “በእውነቱ እንዲህ ያለውን መሳሪያ ምንም ጠላት ቢሆን በሰው ላይ ለማዋል የሚጨክን ሰው፥ ሰብዓዊ ስሜት የሌለው፣ አለት ድንጋይ የተፈጠረበት መሆን አለበት፤ እንዲህ ያለውን መሳሪያ በሰው ላይ ማዋል ሰብዓዊ ህሊና ሊሸከመው የማይችል እጅግ ከባድ መሆኑን ዓለም ሁሉ ያወቀውና ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከማድረጉ በቀር “ሌላ መንግሥት በሌላ አገር ላይ አደረገ’ ሲባል ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል። ከተከዜ ባህር ማዶ ጉዞዬ ያገኘኋት ሌላዋ ታሪካዊ ሥፍራ እንዳባጉና ናት። እንዳባጉና የወገን ጦር ትልቅ ገድል የፈጸመበት ነው። ጀግኖች አባቶቻችን የጠላት ታንክ ሳያስፈራቸው የጠላት ጅምላ ጨራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተቋቁመው ጠላትን ድባቅ የመቱበት፤ ወደ አክሱም እንዲያፈገፍግ ያደረጉበት ሥፍራ ነው። “የጠላት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በጦር ሜዳው ትንንሽ ቦምቦች አውቶማቲክ ጠመንጃ ይተኩስ ነበር። አቢሲኒያኖች ደግሞ ከጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው ጉዳይም አልሰጡትም ነበር…” ይላል ዶክተር ሀራልድ ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘ መጽሐፉ። ይህ አካባቢ በሀገር ፍቅር የነደዱ ኢትዮጵያዊያን ደም ያፈሰሱበት፣ አጥንት የከሰከሱበት፤ ለኢትዮጵያ መስዕዋትነት የከፈሉበት ነው። ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ቀጣና ነው። ቀኑ ተገባዷል። ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። እኔም የማሽላ ማሳዎችን ግራ ቀኝ እየተመለከትኩ ለዕለቱ መዳረሻችን ወደሆነችው ሽሬ ከተማ ገባን። ሽሬ በትግርኛ ‘ሽረ’ ሲሉት ይደመጣሉ። በእርግጥ ሽሬን ለመጀመሪያ ጊዜ መርገጤ ነው። ዕለቱም ጥር ሥላሴ ነው። ሽሬ በጥር ሥላሴ ትደምቃለች፤ ሙሉ ስሟም ሽረ እንዳስላሴ ነው። የሽሬ ሥላሴ ጠበል ሽሬ ደርሰን ማረፊያችንን ያዝን። ጊዜው በጣም አልመሸምና ከተማዋን በቀላሉ መቃኘት ይቻላል። ሽሬ ሰፊና ደማቅ የዞን ከተማ ናት። ከመካከላችን የአንደኛው ባለሙያ ቤተሰቦች ሽሬ ነበሩና አስጠሩን። ለሥላሴ ጠበል ግብዣ። ባል እና ሚስቱ ከልክ በላይ መስተንግዶ አደረጉልን። ‘ጠብ እርግፍ አድርገው አስተናገዱን’ ማለት ይቀላል። እንግዳ መቀበል ነባር ኢትዮጵያዊ እሴታችን ቢሆንም ጦርነት ውስጥ ለቆየ አካባቢ የተለየ መልክ ነበረው። እንግዳ አቀባበላቸው በእርግጥም የመሃል አገር ሰው የናፈቃቸው ይመስላል። የተትረፈረፈ እህልና ውሃ አቅርበው በ’ብሉልን፤ ጠጡልን’ ተማጽኗቸው የተነፋፈቀ ቤተ-ዘመድ ግብዣ አስመሰሉት። የሥላሴው ጠበል የሸሬ ጠላ ቀረበ። የሸሬ ጠላ ሳስታውስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ታወሱኝ። የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሀሩ ፕሮፌሰር ሽብሩ በዘመነ ደርግ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ሽሬ ዘምተው ነበር። በወቅቱ ታዲያ የሸሬ ጠላ ፍቅር ይዟቸው በየጊዜው ሲኮመኩሙ የተመለከቱ ሰዎች ‘ፕሮፌሰሩ ከጠፉ የሚገኙት ጠላ ቤት ነው’ ሲባሉ እንደነበር ‘ከጉሬ ማርያም እስከ አዲስ አበባ’ በተሰኘው ግለ ታሪካቸው አስፍረዋል። ከግብዣ መልስ ከማረፊያ ሆቴል ላይ ሆኜ ከተማዋን ስቃኛት ከጦርነት ድባቴ የተላቀቀች ይመስላል። የአመሻሽ ሕዝቡ እንቅስቃሴም ሆነ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ የሚሰሙ የመዝናኛ ቤቶች ሙዚቃዎች የከተማዋን አሁናዊ መልክ የገለጠልኝ ነበር። ንጋት ላይ በቁርስና ቡና ሰዓታት ከሰዎች ጋር መስተጋብሬ ጀመረ። በጦርነት አዙሪት የከረመችው ሽሬና አካባቢው ኑሮ እጅጉን የከበደ ነበር። መልከ-ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች አስተናግደዋል። አሁናዊ ምላሻቸው “ተመስገን፤ ያ ሁሉ አለፈ” የሚል ነው። ገበያው ተረጋግቷል፤ ማህበራዊ ኑሮ ተመልሷል። ድህረ-ሰላም ስምምነት ለሽሬ ነዋሪዎች ሁለንተናዊ እፎይታን አንብሯል። ከቀናት በኋላ በአክሱም የታዘብኩትም እንዲህ ነው። ኑሮን ያቀለለው የተቋማት አገልግሎት ጅማሮ በመጀመሪያ ዘገባ ስራዬ መሰረተ ልማትን አገልግሎት ቃኘሁ። ባንክ፣ ቴሌ፣ ሆስፒታል… መሰሎቹን። ተጠቃሚዎችንም፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ሃላፊዎችንም አነጋገርሁ። ከሰላም ስምምነቱ ማግስት ጀመሮ ተቋማቱ ወደስራ መመለሳቸው ከሁለንተናዊ ችግር እንደታደጋቸው ያነሳሉ። በትራንስፖርት እየተንቀሳቀሱ፣ በኤሌክተሪክ ስራዎቻቸውን እየከወኑ ነው። ለሁለት ዓመታት የተቋረጠው አገልግሎት አቅርቦት እና የአገልግሎት ፈላጊዎች ፍላጎት ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የተጠቃሚዎችም፤ የአገልግሎት ሰጭዎችም ሀሳብ ነው። በሽሬ ስሁል ሆስፒታል የተመለከትኳቸው፤ ያነጋገርኳቸው፤ ከታዳጊዎች እስከ አዛውንት ዕድሜ ያሉ ህሙማን የሰላም አየር ማግኘታቸው የሕይወታቸው ዑደት እንዲቀጥል አድርጓል። ድንገተኛም ሆነ ነባር ህመም ያለባቸው ሰዎች በነጻ እየታከሙ ነው ያገኘኋቸው። ሰላም ከሌለ መታከም ቀርቶ በቅጡ ማስታመም፤ በወጉ መቀበርም እንደማይቻል ገልጸውልናል። የጤና፣ የባንክና የቴሌኮም አገልግሎት የግብዓት ክፍተቶች የማሟላት ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በፌዴራል ደረጃ በየተቋማቱ የተመደቡ አስተባባሪዎች አረጋግጠውልኛል። የጸጥታ አካሉና የህብረተሰቡ ትብብርም የሚያስቀና እንደሆነ ግለሰቦችም፤ የጸጥታ አካላትም ነግረውኛል። አክሱም ጺዮን ማርያም፣ ሽሬ ስላሴ ንግስ፣ የጥምቀት በዓላት ከሶስት ዓመታት በኋላ በአደባባይ ታቦት ወጥቶ ተከብሯል። የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮችም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልኝ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ የሆኑ ይመስላል። እንቅስቃሴያቸውም የሰላማዊ ቀጠና መልክ ያለው ነው፤ ዩኒፎርም ከመልበሳቸው በስተቀር ጀሌያቸውን ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ደግሞ መተማመን ከመፍጠር ባለፈ ጦርነት ውስጥ ለቆየ ማህበረሰብ ከስነ ልቦና ጫና እንዲላቀቅ አይነተኛ ሚና እንደላው ይሰማኛል። ኢ-መደበኛ የሽሬና አክሱም ወጎች ያረፍኩበት ሆቴል ባለቤት ‘አደይ’ ተግባቢ ናቸው። ደግ እናት ይመስላሉ። ከገባን ጀምሮ ‘ጠላ ተጎንጩ፤ ቡና ጠጡ’ ጭንቃቸው ነው። ሁለት ቀን ቡና አስፈልተውልናል፤ ጠላ አቅርበው ዘክረውናል። ይህ ሁሉ ሲሆንም ለከተማው እንግዳ መሆናችንን እንጂ ስለሙያችንም ሆነ ስለሌላ ማንነታችን አያውቁም ነበር። ብዙ መጨዋወትና ውሎ አዳር በኋላ ነው ጋዜጠኛ ስለመሆናችን ያወቁት። አደይ ተጨዋች ናቸው። አማርኛ ያዝ ቢያደርጋቸውም ጨዋታቸው ‘ኩርሽም’ ነው- ተሰምቶ የማይሰለች። በአጋጣሚ ‘ሰለክላካ’ ስለምትባለዋ ታሪካዊ ሥፍራ ጠይቄያቸው እያወጋን ነበር። ‘እንደእናንተ ወጣቶች ሳለን ‘ሰለክላካን ያላዬ ሸዋን ያመሰግናል’ ይባል ነበር። ታዲያ አንድ የሸዋ ሰው መጣና ሰለክላካን አየና ‘በቃ ይቺ ናት’ ሰለክላካ’ ብሎ ተገረመ” ብለው አሳቁን። (የፍቅር እስከ መቃብር መሪ ገጸ-ባህሪው ‘በዛብህ’ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄዶ ‘የዲማ መልኳ እና ዝናዋ’ ተጣርሶበት እንደተገረመበት ቅጽበት መሆኑ ነው)። አደይ የተጀመረው ሰላም ፍጹም ምሉዕ ሆኖ ወደ ቀደመ ኢትዮጵያዊ መልካችን የምንመለስበት ጊዜ እንዲመጣ ይሻሉ። ከጦር-ነት ወደ ሰላም-ነት! ቆንጂዬዋ ፊዮሪ የኮሌጅ ተማሪ ነበረች። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጀምሮ በኋላም በጦርነት ሳቢያ ትምህርቷን ካቆመች ሦስት ዓመታት ሆኗታል። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የጀበና ቡና ጀምራለች። ደንበኞቿ ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን። ፊዮሪ ከስኒ ማቅረቢያዋ ላይ አነስተኛ ጀበናዋን፤ የሚያማምሩ ስኒዎቿን እና መዓዛው ከሚያውድ የዕጣን ማጨሻዋ ጋር ሰድራ ይዛ ትቀርባለች። ከመካከላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጥና እርሷም ወንበር ይዛ ከመካከላችን ትቀመጣለች። ቡናው እስኪሰክን ጨዋታዋን ታስኮመኩመናለች። ቡናው ከሰከነ በኋላ ቡናዋን ቀድታ ለእያንዳንዳችን በእጃችን እያነሳች ትሰጣለች። በሽሬ ቡና የሚቀርበው በዚህ መልክ ነው። ለፊዮሪ እና መሰሎቿ ጦርነቱ ክፉ ጠባሳ መጣሉ፤ ተስፋቸው ላይ መጥፎ አሻራ ማስቀመጡን ታነሳለች። አሁን ግን ብሩህ ተስፋ ሰንቃለች። ስለነገዋም “ሰላሙ ይዝለቅልን፤ ትምህርቴን ለመቀጠል እመኛለሁ” ትላለች። አክሱም ከሽሬ በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ከሽሬ አክሱም ስንንቀሳቀስ ከጥምቀት ዕለት በስተቀር ገበሬው የግብርና ሥራዎቹን እየከወነ ነበር። አርሶ አደሩ ያርሳል፤ መስኖውን ያለማል። የተዘራውን ውሃ ያጠጣል። የበቀለ ቡቃያውን ይኮተኩታል። ከጦርነት ወደ ልማት መዞሩን ዐይኔ ታዝቧል። በጥምቀት ዋዜማ፤ የከተራ በዓል ዕለት ሁለት ጎራማይሌ የረፋድ ትዕይንቶችን ላንሳ። ከአክሱም ከተማ ወደ አድዋ እና ሽሬ መገንጠያ አካባቢ ሰፊ የቀንድ ከብት ገበያ ነበር። እውነተኛ የዓመት በዓል ገበያ መልክ ያለው ትዕይንት ነበር። በተለይም የፍየል ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታሪካዊቷን አክሱም ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ የረገጥኳት/የተሳለምኳት ከአራት ዓመት በፊት በ2011 ዓ.ም ይመስለኛል። ከገበያው ቀጥሎ በታቦተ-ጽዮን መገኛዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ደጅ፣ በጥንታዊያኑ የአክሱም ሐውልት መገኛ አደባባይ ነበር። ከጽዮን በስተምዕራብ በአርባቱ እንሰሳ በኩል፤ በቅዱስ ያሬድ ዋርካ… አድርጌ በጽዮን ዋናው በር ደረስኩ። ማራኪ የአክሱም የኮብልስቶን መንገዶች ኦና ናቸው። የወትሮው ግርግር ናፍቋቸዋል። ከጽዮን ቅጥር ግቢ በዋናው በር በስተውጭ አነስተኛ እና ብቸኛ ዋንዛ በኮብልስቶን መሃል ነበረች። ዛሬም ለምልማ አለች። በዚህ አካባቢ ድሮ የነጭ ጎብኚ ጋጋታ፣ የጽዮን ደጅ ጠኚ ምዕመን… የተጨናነቀ ነበር። እንደ ድሮው የፎቶ አንሺ ግርግር፣ የአክሱም መስቀል ቀርጸው የሚሸጡ ወጣቶች ጫጫታ የለም። ይልቁንም እርጥባን የሚሹ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ነበሩ። ጦርነት የሥፍራዋን መልክ አጠይሞታል። ያም ሆኖ ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በኩሉሄ ባይባልም ወደነበረበት እየተመለሰ ነው። የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኰች ሥራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከአክሱም ሐውልት ወደ ሌላ ሰፈር አቀናሁ። ትርሐስ ገና ታዳጊ ልጅ ነች። ጠይም፤ ስርጉድ፣ ሳቂታና ተረበኛ አይነት ልጅ ነች። እንደ ሽሬዋ ፊዮሪ መንገድ ዳር የጀበና ቡና እየሰራች ነው። ከሩቅ የመጣን እንግዶች መሆናችንን ስታውቅ፤ ደስታዋ ከገጿ ይነበብ ነበር። ያለፉ ጊዜያትን ሰቆቃ አጫወተችን። ስለቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እና ዕቅዷ ስታወራ ትቆይና “የሰው ልጅ ግን በጣም ከሃዲ ነው። ከወራት በፊትኮ ስለቢዝነስ አላስብም ነበር። መቼ እሞታለሁ እንጂ” ብላ ራሷን ትወቅሳለች። ወደ ሰማይ አንጋጣ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ጦርነት ተራውንም ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ቀውስ ዳርጎት እንደቆየ ታነሳለች። ዛሬ ሁሉ አልፎ ሰላም መውረዱ ለመጨዋወት መብቃቷ ለእርሷ ትልቅ ብሥራት ነው። ይህ ለትርሐስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አክሱማዊያን መሆኑ እሙን ነው። አክሱም ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በሻለቃ አዛዥነት የተሰማራ የፌደራል ፖሊስ አባልም ያጋጠመውን አሳዛኝ ገጠመኞች አጫውቶኛል። ጦርነቱ ቢራዘም ኖሮ በተራው ሕዝብ ላይ ምን ያህል የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር በአሳዛኝ ሁኔታ ገልጾልኛል። አክሱሞች ያን ሁሉ አልፈው ሰላም አየር ነፍሶ፣ ከስጋት ቆፈን ተላቀው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል። የዛሬ ሳምንት ሰርክ(11 ሰዓት) ላይ አክሱም የከተራ በዓል በድምቀት አክብራለች። ታቦተ-ጽዮን ወደ ባህረ- ጥምቀቱ ስትወርድ፤ ወግና ሥርዓቱ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ በሀበሻ ነጫጭ አልባሳት፣ ካህናት በልብሰ ተክህኖ ደምቀው … እየተከወነ ነበር። አንዲት እናት ለአማርኛ ተናጋሪ በቀረበ አነጋገር እያለቀሱ ታቦት እየሸኙ ነው። ትኩር ብዬ ሳያቸውም ዕንባቸው ዱብ ዱብ ይላል። “ከዚያ ሁሉ መከራ አልፎ ለዚህ በቃን፤ ተመስገን” እያሉ እልልታውን ያቀልጡታል። በደስታ እያነቡ ነበር። ይህ ስሜት የብዙኃኑ አክሱማዊያን እናቶች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። አክሱም በኮቪድ እና በኋላም በጦርነቱ ምክንያት ባህረ-ምቀት ታቦት ወጥቶ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከወትሮው በተለየ ድምቀትና ውበት በሰላምና በደስታ፤ በአደባባይ እልልታና ሆታ በማክበራቸው ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋልና! እናም በአክሱም የከተራ ሆነ የበዓለ-ጥምቀት ክብረ-በዓላት በሰላም ስምምነቱ ማግስት በድምቀት ተከውኖ አለፈ። የሃይማኖት አባቶቹም ሆኑ ምዕመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅም የዘንድሮው ክብረ-በዓል ካለፉት ዓመታት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸሩ፤ ትልቅ ብሥራትና መልክ እንዳለው ገልጸዋል። ሰላም እንዲጸና፤ ነባር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተባበር እንዲመለስ ጽኑ መሻታቸውን ነግረውናል። በበጎ ቀን የማውቃትን አክሱም፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ አሁናዊ መልኳን ታዝቤ፤ የነገ ትዝታ ሰንቄ ተመለስኩ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም