የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ማካሄድ ይጀምራል

ሀዋሳ ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ዘመን 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ማካሄድ እንደሚጀምር የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ገለጹ።

ምክር ቤቱ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚያካሄደው ጉባኤ በ11 አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይም ተመልክቷል።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ለኢዜአ እንዳሉት ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ማካሄድ ይጀምራል።

ምክር ቤቱ ከነገ ጀምሮ በሚያካሂደው 6ኛ ምርጫ ዘመን 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውም በ11 አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ተናግረዋል።

ከአጀንዳዎቹ መካከልም የምክር ቤቱን የ8ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ የ2017 አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2018 ረቂቅ ዕቅድና በጀት ማፅደቅ እንደሚገኙበትም አፈ-ጉባኤዋ አመልክተዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኦዲት መስሪያ ቤቱ የ2017 ዓ/ም አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ ዕቅድና በጀት ቀርቦ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።

እንዲሁም በምክር ቤቱ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና ሹመቶች ቀርበው እንደሚፀድቁም ዋና አፈ-ጉባኤዋ ተናግረዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም