በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሁለት የሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠበቃሉ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሁለት የሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
ናይጄሪያ ከአልጄሪያ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም፣ ቱኒዚያ ከቦትስዋና በፔሬ-ጄጎ ስታዲየም በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በስድስት ነጥብ ወደ ሩብ ፍጻሜ መግባቷን ማረጋገጧ ይታወሳል። ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት የምድቡ መሪ ሆና እንድታጠናቅቅ ያስችላታል።
በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አልጄሪያ ማሸነፍ በቀጥታ ወደ ሩብ ፍጻሜው ያስገባታል።
ተሸንፋም ወይም አቻ ወጥታ ሁለተኛ ሆና ወይንም ምርጥ ሶስተኛ ሆና ልታልፍ ትችላለች።
በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቱኒዚያ ወደ ሩብ ፍጻሜው ለመግባት ማሸነፍ ግድ ይላታል።
ለሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አራት ነጥብ በናይጄሪያና አልጄሪያ ጨዋታ ውጤት ላይ ተመስርታ ሁለተኛ ወይም ምርጥ ሶስተኛ ሆና ልታልፍ ትችላለች።
ሁለት ሽንፈት አስተናግዳ ያለ ምንም ነጥብ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን የያዘችው ቦትስዋና ማሸነፍ ምርጥ ሶስተኛ ሆና እንድታልፍ የሚያደርግ እድል ሊሰጣት ይችላል።