አርእስተ ዜና
ሀገርን የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ በጋራ መስራት ይገባናል - ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው
Mar 27, 2023 31
ሀዋሳ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ስብራትን እንደ መማሪያና መስፈንጠሪያ ምዕራፍ በመጠቀም ሀገርን የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት ይገባናል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስገነዘቡ። የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዝቅተኛ የመሆን መንስኤ እና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በወቅቱ እንዳሉት ተማሪዎች የነገ ሀገርን የመገንባት ዕድልና ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ተማሪዎች ነገ ሀገርን የሚያሻግሩ ሥራዎችን ለመስራት ከወዲሁ በትጋትና በውጤት መታጀብ እንዳለባቸው አመልክተዋል ። የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንደ ሀገር እጅግ ዝቅተኛ እንደነበር ጠቅሰው "ይህንን የውጤት ስብራት እንደ መስፈንጠሪያ ምዕራፍ በመጠቀም ሀገርን የሚያሻግርና የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ በቁጭት መስራት ያስፈልጋል" ብለዋል። "በመሆኑም ውጤታማ ሥራ ለመስራት በጋራ መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው" ሲሉም አስገንዝበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው "በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራት በእጃችን ያሉ እድሎችን አሟጠን መጠቀም ያስፈልገናል" ብለዋል። ለትምህርት ጥራትና ውጤታማነት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የተማሪዎችና የመምህራን ትጋትና ሥነ-ምግባርም ከፍተኛ ድርሻ የሚሰጠው እንደሆነ ተናግረዋል። በ2014 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ባልተመቻ ቸ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው በትጋት በመስራታቸው ያገኙት መሆኑን አመልክተዋል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው" ለውጤት ውድቀት በዋናነት ሰባት የሚደርሱ መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች መኖራቸውን በጥናት አረጋግጠናል" ብለዋል። በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ኃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት፣ የመምህራን ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ከሚጠበቀው በታች መሆን፣ የተማሪው ትጋት ማነስና አላማ ይዞ አለመማርን ለአብነት ጠቅሰዋል። ተከታታይ ምዘና አለመኖር፣ በታችኛው ደረጃ ላይ ያለው የትምህርት አሰጣጥ ሥርዐት ክፍተት፣ የወላጆች ክትትል ማነስ እንዲሁም የትምህርት ቤት አካባቢ ምቹ አለመሆንና ሌሎች ምክንያቶች መሆናቸውን በጥናት መለየታቸውን ጨምረው አመልክተዋል። በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና የታየውን እጅግ ዝቅተኛ ውጤት ለመቀየር የተጠቀሱ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ቢሮው በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከመፍትሄዎቹ መካከል የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት ወሳኝ ሚና እንዳለው አመልክተዋል። "የንቅናቄ መድረኩ እስከ ታችኞቹ የትምህርት መዋቅሮች እንደሚቀጥል ጠቅሰው የትምህርት አመራሮች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከትምህርት ሥራ ጋር ትሥሥር ያላቸው ሴክተሮች የየራሳቸውን የሀላፊነት ድርሻ ወስደው በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ይደረጋል" ብለዋል። "ተማሪዎች በግላቸው ከሚያደርጉት ጥረት ባሻገር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችላቸው ሁኔታ በዙሪያቸው ሊፈጠርላቸው ይገባል" ሲሉም አስገንዝበዋል ። ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ሠላምና ፀጥታን በማስፈን የተረጋጋ የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር ማድረግ፣ ትምህርት በጤና መታወክ ምክንያት እንዳይስተጓጎል መከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ሥርዐት መዘርጋት ከትምህርት ሥራ ጋር በቀጥታ የሚቆራኙ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ አንጻር የሴክተር መስሪያ ቤቶች ቅንጅታዊ አሰራር በተማሪው ውጤት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ወደር የሌለው እንደሆነ አስረድተዋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ብዛት ያላቸው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ላሳለፉ ትምህርት ቤቶች የዕውቅናና የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።    
ለትንሳኤ በዓል ከ7 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ገለጸ
Mar 27, 2023 42
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ ለመጪው የትንሳኤ በዓል ከ7 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አስታወቀ።   የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንያው ዋሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በማህበሩ ስር ያለው የምግብ ዘይት ፋብሪካ የፓልም እና የሱፍ ዘይቶችን ለሃገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ወራትም ከ100 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም ዘይት በማምረት መንግስት በሚያቀርበው ድልድል መሰረት ለተለያዩ ክልሎች ማሰራጨቱን ተናግረዋል።   ለመጭው የትንሳኤ በዓልም ለህብረተሰቡ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም እና ከ4 ሚሊዮን ሊትር በላይ የሱፍ ዘይት ለማቅረብ ከወዲሁ እየተዘጋጀ መሆኑን ኢንጂነር እንያው ገልጸዋል። የፓልም ዘይቱ በአከፋፋዮች በኩል ለክልሎች እንደሚሰራጭ ጠቅሰዋል። ፋብሪካው አሁን ላይ ከ1ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠሩን ኢንጂነር እንያው አያይዘው ገልጸዋል።   በአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የንግድ ውድድር ሸማቾች ጥበቃና መሰረታዊ የንግድ እቃዎች አቅርቦት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ታፈረ ይመር እንዳሉት፣ ከጥቂት ወራት በፊት በክልሉ የዘይት አቅርቦት ሰፊ ጉድለት ነበረው። "መንግስት በዘይት ዋጋ ላይ ያደረገው ድጎማ እንዳለ ሆኖ የፊቤላ ዘይት ወደ ገበያ መግባት የምርት ችግር እንዳይኖርና ዋጋውም እንዲረጋጋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል" ብለዋል። ፋብሪካው ለበርካታ ወጣት ምሩቃን የሥራ ዕድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በፋብሪካው የሥራ ዕድል ያገኙት ኢንጂነር ትንሳኤ ተስፋ እና ወጣት ስመኝ ክንዴ ናቸው።   በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ የተመረቀውና በፋብሪካው የሰሊጥ ክፍል ማቀነባበሪያ ሃላፊ የሆነው ኢንጂነር ትንሳኤ ተስፋ ከፋብሪካው መቋቋም ጀምሮ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።   ወጣት ስመኝም በፋብሪካው ተቀጥራ መስራት ከጀመረች ከሁለት ዓመት በላይ እንደሆናት ጠቅሳ፣ "ፋብሪካው እሷን ጨምሮ ብዙ ወጣቶችን ሥራ በማስያያዝ ከተስፋ መቁረጥ ታድጓል" ብላለች።   የፌቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወደ ሥራ ከገባ ሁለት ዓመታት ማስቆጠሩ ታውቋል።
አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ ላይ እየተሰራ ነው
Mar 27, 2023 42
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ። አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሴቶችን የዲጂታል ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ ተከብሯል።   በዚሁ ጊዜ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለችው ዲጂታል 2025 መርሃ-ግብር ሴቶች ቴክኖሎጂን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጠቀሙ ካደረጉ ችግሮች ውስጥ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ማነስ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን አካታች ምጣኔ ሀብትን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል የዲጂታል ዕውቀት ልዩነትን ለማጥበብ እንደ ሀገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይ በጥናቱ ግኝት መሰረት እስትራቴጂ በመቅረጽ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 የያዘቻቸውን እቅዶች ለማሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመድረኩ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ተወካይ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አካታች ዲጅታል መርሃ ግብሮችን ባለመተግበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ እንደሆኑ በመድረኩ ተነግሯል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ  ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ
Mar 27, 2023 54
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የግብርና ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ኒ ሆንግሺንግ እንዲሁም በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል የምዕራብ እስያና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሊዩ ጂያንግ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ቻይና በግብርናው መስክ በትብብር ለመስራት የፈረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሊተገበሩ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶች በመቀየር ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።   ሁለቱ ወገኖች በግብርና ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር አስመልክቶ መደበኛ የሆነ የምክክር ጊዜ ለማዘጋጀት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያና ቻይና በግንቦት 2014 በግብርና፣ኢንዱስትሪ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማትና ጤና መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የኢንቨስትመንት ስምምነቶች መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።
የሚታይ

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት የውሃ ሀብትን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው--የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Mar 27, 2023 41
አዳማ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት የውሃ ሀብትን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና እንዳለው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዕቅድ ትግበራ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ አደራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብረሃ አዱኛ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ሀብቱን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። ሀብቱን ውጤታማ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና አገልግሎቶች ለማዋል እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ለዚህም የ10 ዓመት መሪ ዕቅድና የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው። ሰፊ የውሃ ሀብት የሚገኝበትና በሀገሪቷ ከሚገኙ 12 ተፋሰሶች ውስጥ ሰባቱ የሚገኙት በኦሮሚያ ክልል መሆኑን ዶክተር አብረሃ ጠቅሰው የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት እውን ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል። በተለይ በክልሉ ያሉ ወንዞችና ሃይቆች ላይ እየደረሰ ያለው ብክነትን፣ ብክለትንና መመናመንን ለመታደግ የተቀናጀ የውሃ ሀብት ስርዓት እውን በማድረግ የውሃ ሀብት በዘላቂነትና በፍትሃዊነት ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።   ይህንን ማድረግ ካልቻልን የውሃ ሀብቱን ለህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል አንችልም ሲሉም ገልጸዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በተፋሰሶች ውስጥ እየተከናወነ ያለው የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት ፍትሃዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑንም አመልክተዋል። በአባይ፣ አዋሽና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የኦሞ፣ ጊቤ፣ ገናሌ፣ ዳዋና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶችን ወደ ተቀናጀ የውሃ አስተዳደር ስርዓት ለማስገባት በዘርፉ ሙሁራኖች ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ተወካይ ተሻለ በቃና በበኩላቸው የውሃ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ውጤታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። በክልሉ የውሃ ብክነትና ብክለት በመቀነስና የውሃ ሀብት ደህንነትን በመጠበቅ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የውሃ አስተዳደር ስርዓት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል። የተቀናጀ የከርሰ-ምድርና ገፀ-ምድር የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት በክልሉ ወንዞች፣ ሃይቆችና ተፋሰሶች የውሃ ሀብት ልማቱን ለማበልፀግ የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ ከኦሮሚያ ሁሉም ዞኖች የዘርፉ ሙያተኞችና ሃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ማስታወቂያ
ፖለቲካ
"በቀጣይ የብልጽግና ፓርቲ ዋናው የቤት ሥራ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር ላይ መሥራት ነው"-የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ
Mar 27, 2023 54
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ)፦ "በቀጣይ የብልጽግና ፓርቲ ዋናው የቤት ሥራ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር ላይ መሥራት ነው" ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡ "ድሎችን ማፅናት እና ፈተናዎችን መሻገር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ወቅታዊ እና ታሪካዊ የአመራር ተልእኮ መድረክ በሀገራዊ የሰላም፣ የፀጥታ እና የልማት ጉዳዮች ላይ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ውይይት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።   በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ከተሳታፊ አመራሮች ለተነሡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኑሮ ውድነትን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮችን በሚመለከት ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እንደሚሠራ አበክረው ገልጸዋል።   ብልጽግና ፓርቲ አስቀድሞ የጀመራቸውን መርህን መሠረት ያደረጉ ተቋማዊ አሠራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል የፓርቲውን ሕዝባዊ ቅቡልነት ማሳደግ እና ጠንካራ መንግሥታዊ አቅም መፍጠር እንደሚገባም ጠቅሰዋል። ይህንንም ለማጠናከር አመራሩ የአመለካከት እና የተግባር አንድነቱን በማጠናከር በኅብረ ብሔራዊ አንድነት በተሰናሰለ ወጥ ሀገራዊ እሳቤ አቅም መሆን እንደሚገባው አንሥተዋል።   የብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካዊ እሳቤዎች ኢትዮጵያዊ መሠረት ያላቸው እና የሀገራችንን እና የሕዝባችንን ችግር ፈቺዎች እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ማሳደግ እና የሕዝቡን ፖለቲካዊ ሞጋችነት እና የልማት ተሳትፎ እንዲሁም ተጠቃሚነት በማሳደግ ቅቡልነትን ማሳገድ እንደሚገባም ማብራሪያ ሰጥተዋል።   በአጠቃላይ ብልጽግና ፓርቲ መላ መዋቅራዊ አቅሙን ፈትሾ የሚታዩ የአመራር የአቅም ጉድለቶችን አርሞ፣ ውስጣዊ ብልሽቶችን አክሞ እና መርሕን መሠረት ባደረገ አግባብ ተግባራት በማሳለጥ የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ እና ዕድገት በማስቀጠል ሕዝባዊ ቅቡልነትን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደ ሀገር የመጣውን ነፃነት ከመጠቀም ጋር ሰፊ ክፍተት እንዳለ እና ነፃነትን ማክበር እና ማስከበር በሚመለከት ብልጽግና ፓርቲ የሚደራደርበት ጉዳይ እንዳልሆነ አሳስበዋል።   እንደመሪ ፓርቲ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር ላይ መሥራት እንደሚገባም አክለው ገልጸዋል። በተመሳሳይ ነፃነትን በፓርቲው ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ እና የፓርቲው አመራር እና አባል ተገቢ ነፃነት ተጎናፅፎ ሐሳቡን ያለተፅዕኖ እያራመደ መቀጠል እንዳለበት በአፅንኦት አስቀምጠዋል። እንደ ሀገር የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ እና የዳኝነት ተቋማት በነፃነት እና በገለልተኝነት ሥራቸውን አጠናክረው መሥራት እንደሚገባቸውም ለተሳታፊ አመራሮች ማንሣታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የመደመር እሳቤ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለምን መጻዒ ዘመን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ሊተገብረው የሚገባ መርህ ነው...የህንድ ባለሃብቶች
Mar 25, 2023 131
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015 (ኢዜአ) የመደመር እሳቤ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለምን መጻዒ ዘመን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ሊተገብረው የሚገባ መርህ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የሕንድ ባለሃብቶች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የአስደናቂ ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያ በመምራት ሂደት በተለይ የትውልድ ቀረጻ ላይ ማተኮራቸውን አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን እና የትውልዱን መጻዒ ብሩህ ተስፋ የሚተልሙ መደመር፣ የመደመር መንገድ እና የመደመር ትውልድ የተሰኙ ሦስት መጻሕፍትን አበርክተዋል። ሦስቱም መጻሕፍት ማጠንጠኛ 'መደመር' ቢሆንም የመደመር እሳቤው ምንነት፣ ስለትግበራ መንገዱ እና ስለትውልዱ ትግበራ ወሰን በተለያዬ ዐውድ የሚያትቱ ናቸው። በቅርቡ የተመረቀው 'የመደመር ትውልድ' የተሰኘው ሶስተኛ መፅሓፋቸው የእንግሊዝኛ ቅጂ ለዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እና ለውጭ ባለሃብቶች በታደሙበት የማስተዋወቅ መድረክ ተካሂዷል። በኢትዮጵያ የሕንድ ባለሃብቶች ፎረም ምክትል ሰብሳቢ ራጂቭ ሻርማ እንዳሉት፤ መፅሐፉ የመደመር ትውልድ ከትናንት እንዲማርና የራሱን አቅሙን አሰባስቦ የተሻለች ሀገር እንዲገነባ መንገድ ያሳያል። የመደመር እሳቤ ዓለም አቀፋዊ መርሆን የሚያስተጋባ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ዓለም የሚበጅ መሆኑንም እንዲሁ። አፍሪካውያን ከቀደመ ታሪካቸው እንዲማሩ፣ እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ብሎም ወደ ፊት ጠንካራ አህጉር መገንባት የሚያስችል አቅማቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጡ መንገድ የሚጠቁም መሆኑንም ተናግረዋል።   የህንድ የቢዝነስ ፎረም አባል ካውሸል ሼድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ጥንታዊትና አኩሪ ታሪክ ያላት እና መልከ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፈች ሀገር መሆኗን አውስተዋል። የዘመኑ ትውልድም ከትናንት ታሪክ ቁም ነገሮችን ቀስሞ፤ በመደመር እሳቤ የተሻለ ነገን መገንባት እንደሚችል መመላከቱን ጠቁመዋል። ከቅደመ አያቶቻቸው ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን የሚናገሩት ሕንዳዊ ባለሀብት ሀርሺ ኮታሪ፤ መደመር በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሀብቶችን አሰባስቦ በመጠቀም ሀገርን መለወጥ እንደሚቻል የሚያሳይ እሳቤ ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲሱ የመደመር ትውልድ መፅሐፋቸው የትናንት፣ የዛሬ እና የነገ ትውልዶች ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜና ጥበባቸውን ለጋራ ዓላማ ማዋል እንደሚገባቸው አሳይተዋል ነው ያሉት። የነገ ትውልድ ጥበብና አቅሙን አዳብሮ ሀገሩን በዓለም ላይ ከፍ ያለች ኢትዮጵያን ዕውን እንዲያደርግ መንገድ ጠቁሟል ብለዋል። የመደመር ትውልድ የዓለም አንድ አካል በመሆኑ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን ትስስር እንዲያጎለብትና ሀብቱን አሟጦ እንዲጠቀም የአደራ መልዕክት ያስተላለፈ መፅሐፍ ነውም ብለዋል። ሌላኛው ባለሃብት ባህበሽ ኢንዳሪያ ብዝሃነት በሞላባት ዓለም ውስጥ ብዝሃ ጸጋን በአግባቡ ተጠቅሞ አካታች ዕድገትና ስልጣኔን ለማረጋገጥ የመደመር እሳቤ የወቅቱ መፍትሔ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ'መደመር ትውልድ' መፅሐፋቸው ትውልዱ ለጋራ መዳረሻውን ውስጣዊ አቅሙን ይፈትሽ ዘንድ የዕውቀት ብልጭታ እንደሰጡ ጠቁመዋል። ባለሃብቶቹ አፍሪካዊያን ሀገር በቀል ጥበብ እንዳላቸው ጠቅሰው፤ የሀገራት መሪዎች ትውልድ ግንባታ በመጻፍና ሰርቶ በማሳየት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አርዓያ ሊከተሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የመደመር እሳቤ በራስ መተማመንና የማሳካት አቅም ያዳበረ ትውልድ በመገንባት የኢትዮጵያን፣ የአፍሪካ እና የዓለምን በርካታ ችግሮች መቅረፍ እንደሚቻልም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ መሪነት ሚናዋ፣ ለመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂክ ስፍራነቷ እንዲሁም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ላይ ከሚገኙ ሀገራት ተራ የተሰለፈች ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም ያለው የመደመር ትውልድ ይበልጥ የበለጸገች፣ የታፈረች እና የተከበረች ኢትዮጵያን የመገንባት ማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።        
መንግስት የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ለሚያነሷቸው የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት ይሰራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
Mar 25, 2023 171
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015( ኢዜአ)፦መንግስት የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ለሚያነሷቸው የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ ከጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ የልማት ጉዳዮች ተወያይተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች የሰላም፣ የልማትና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።   ነዋሪዎቹ በጥያቄዎቻቸው በዞኑ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት ተደራሽነት ችግር መኖሩን ተናግረዋል። ይህም በዞኑ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል። በመሆኑም የጉራጌ ዞን ራሱን ችሎ በክልልነት በመደራጀት የልማት ጥያቄዎቹን ለመፍታት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል የሚል ጥያቄ ተነስቷል። ነገር ግን የክልልነት ጥያቄን እንደሽፋን በመውሰድ በዞኑ አብረው በጋራ የኖሩ ህዝቦችን ለማጋጨት የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን የጠቀሱት ነዋሪዎቹ፣ እነዚህ አካላት ተለይተው ለህግ እንዲያቀርቡም ጠይቀዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ በምላሻቸው በሁሉም አካባቢዎች በርካታ የመልማት ጥያቄዎች መኖራቸውን ገልፀው፤ መንግስት ያሉትን አቅሞች በማሰባሰብ ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ መንግስት የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ላነሷቸው የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። ከህዝቡ ለተነሱት የልማት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ ባለሃብቶችም የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። አስተዳደራዊ አደረጃጀት ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ መስጫ መፍትሔ አለመሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ከአጎራባች ዞኖች ጋር ያላቸውን አብሮነት በማጠናከር በጋራ ለመልማት መስራት አለባቸው ብለዋል። የሚነሱ ጥያቄዎችን በሰለጠነና በሰከነ አግባብ መፍታት እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል።
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ዘመናዊ ሰራዊት ለመገንባት የምታስገባቸውን ቴክኖሎጂዎች በአገር ውስጥ ለመተካት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር አለበት -የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Mar 25, 2023 139
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢትዮጵያ ዘመናዊ ሰራዊት ለመገንባት ከውጭ የምታስገባቸውን ቴክኖሎጂዎች በአገር ውስጥ ለመተካት የጀመረው ጥረት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳሰቡ። ዩኒቨርሲቲው በምህንድስናና ጤና ሳይንስ የትምህርት መርሐ-ግብሮች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን አስመርቋል። በምርቃት መርሐ-ግበሩ ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ከፍተኛ መኮንኖችና የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል ። የአገር መከላከያ ሰራዊት የሚገጥሙ ፈተናዎችን በብቃት እያለፈ እንደሚገኝና ለዚህም እንደ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ አይነት የትምህርት ተቋማት ትልቅ ሚና መጫወታቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ገልጸዋል። ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ ላይ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል። “መከላከያን የማዘመኑ ሂደት ቴክኖሎጂን ይፈልጋል ይህን ደግሞ ከውጭ በማስገባት ብቻ አይቀጥልም” ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹሙ ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባው ቴክኖሎጂ መተካት ላይ የጀመረውን ጥረት እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከ75 በላይ መደበኛ መርሐግብሮች እንዳሉት ገልጸዋል። በነዚህ መርሐ-ግብሮች ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ ሰራዊት በማፍራት ላይ እንደሚገኝና በጥናትና በምርምር ዘርፍም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማፍለቅ ዘመናዊ ሰራዊት እንዲገነባ እየሰራ ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በሶስተኛ ዲግሪ መርሐግብር መስጠት መጀመሩን ገልጸው በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማሻሻል የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ነው ብርጋዴር ጀኔራሉ ያብራሩት። በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በግዳጅ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆች ነጻ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በምርቃት መርሐ-ግብሩ ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ሽልማት ተበርክቷል።
መንግሥት የገባውን ቃል ገቢራዊ እያደረገ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ገለጸ
Mar 24, 2023 182
አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015(ኢዜአ)፦ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ቀውስ በዘላቂነት ለመፍታት በፕሪቶሪያ በተደረሰው ሥምምነት መሰረት የፌዴራል መንግሥት የገባውን ቃል እየተገበረ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት 52ኛ ስብሰባውን በዚህ ሣምንት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ አካሂዷል። በስብሰባው የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት የባለሙያዎች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ዝርዝር ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ መሐመድ ቻንዴ ኦትማን በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ኮሚሽኑ ባለፈው ዓመት መስከረም ላይ የመጀመሪያውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ ካቀረበ በኋላ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል አሳይቷል። በደቡብ አፍሪካ ፕሮቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት ተከትሎ ጉልህ የሆነ እና እስከ አሁን ድረስ ቀጣይነት ያለው መሻሻል መታየቱን በሪፖርታቸው ይፋ አድርገዋል። በፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ሥምምነት ጠቃሚ መሻሻሎች እያሳየ መምጣቱን ተናግረዋል። የፌዴራሉ መንግሥት በፕሪቶሪያ ሥምምነት የገባውን ቃል ተፈፃሚ ማድረጉ በመስኩ ለታየው መሻሻል ዓይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው መሀመድ ቻንዴ ኦትማን የገለጹት። ሥምምነቱን ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት በገባው ቃል መሰረት ወደ ሽግግር የፍትህ ሂደት የሚወስዱ ተከታታይ እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩን በአዎንታ ገልጸውታል። በውይይቱ አስተያየቱን የሰጠው የአውሮፓ ኅብረትም በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል ግጭትን የማስወገድ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በአገሪቱ የታየውን መሻሻል አድንቋል። የሰላም ስምምነቱና ሥምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉትን እርምጃዎች እንደሚያደንቅ ኅብረቱ ጨምሮ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ የሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ቀርፆ ገቢራዊ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት አወድሶ ኅብረቱ በዚህ ረገድ ልምዱን ለማካፋል ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። በአምባሳደር ሚቸል ቴይለር በውይይቱ የተሳተፈችው አሜሪካም በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ግጭትን የማስቆም ስምምነት ከተፈረሙ በኋላ የታየውን ከፍተኛ መሻሻል በአዎንታ መቀበሏን ገልጻለች። በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የአሜሪካ ቋሚ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ቴይለር እንዳሉት ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህን ለመተግበር እያደረገች ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው ብለውታል።

ማህበራዊ
ሀገርን የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ በጋራ መስራት ይገባናል - ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው
Mar 27, 2023 31
ሀዋሳ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ስብራትን እንደ መማሪያና መስፈንጠሪያ ምዕራፍ በመጠቀም ሀገርን የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት ይገባናል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስገነዘቡ። የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዝቅተኛ የመሆን መንስኤ እና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በወቅቱ እንዳሉት ተማሪዎች የነገ ሀገርን የመገንባት ዕድልና ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ተማሪዎች ነገ ሀገርን የሚያሻግሩ ሥራዎችን ለመስራት ከወዲሁ በትጋትና በውጤት መታጀብ እንዳለባቸው አመልክተዋል ። የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንደ ሀገር እጅግ ዝቅተኛ እንደነበር ጠቅሰው "ይህንን የውጤት ስብራት እንደ መስፈንጠሪያ ምዕራፍ በመጠቀም ሀገርን የሚያሻግርና የሚገነባ ትውልድ ለማነፅ በቁጭት መስራት ያስፈልጋል" ብለዋል። "በመሆኑም ውጤታማ ሥራ ለመስራት በጋራ መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው" ሲሉም አስገንዝበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው "በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራት በእጃችን ያሉ እድሎችን አሟጠን መጠቀም ያስፈልገናል" ብለዋል። ለትምህርት ጥራትና ውጤታማነት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የተማሪዎችና የመምህራን ትጋትና ሥነ-ምግባርም ከፍተኛ ድርሻ የሚሰጠው እንደሆነ ተናግረዋል። በ2014 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ባልተመቻ ቸ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው በትጋት በመስራታቸው ያገኙት መሆኑን አመልክተዋል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው" ለውጤት ውድቀት በዋናነት ሰባት የሚደርሱ መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች መኖራቸውን በጥናት አረጋግጠናል" ብለዋል። በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ኃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት፣ የመምህራን ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ከሚጠበቀው በታች መሆን፣ የተማሪው ትጋት ማነስና አላማ ይዞ አለመማርን ለአብነት ጠቅሰዋል። ተከታታይ ምዘና አለመኖር፣ በታችኛው ደረጃ ላይ ያለው የትምህርት አሰጣጥ ሥርዐት ክፍተት፣ የወላጆች ክትትል ማነስ እንዲሁም የትምህርት ቤት አካባቢ ምቹ አለመሆንና ሌሎች ምክንያቶች መሆናቸውን በጥናት መለየታቸውን ጨምረው አመልክተዋል። በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና የታየውን እጅግ ዝቅተኛ ውጤት ለመቀየር የተጠቀሱ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ቢሮው በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከመፍትሄዎቹ መካከል የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት ወሳኝ ሚና እንዳለው አመልክተዋል። "የንቅናቄ መድረኩ እስከ ታችኞቹ የትምህርት መዋቅሮች እንደሚቀጥል ጠቅሰው የትምህርት አመራሮች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከትምህርት ሥራ ጋር ትሥሥር ያላቸው ሴክተሮች የየራሳቸውን የሀላፊነት ድርሻ ወስደው በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ይደረጋል" ብለዋል። "ተማሪዎች በግላቸው ከሚያደርጉት ጥረት ባሻገር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችላቸው ሁኔታ በዙሪያቸው ሊፈጠርላቸው ይገባል" ሲሉም አስገንዝበዋል ። ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ሠላምና ፀጥታን በማስፈን የተረጋጋ የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር ማድረግ፣ ትምህርት በጤና መታወክ ምክንያት እንዳይስተጓጎል መከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ሥርዐት መዘርጋት ከትምህርት ሥራ ጋር በቀጥታ የሚቆራኙ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ አንጻር የሴክተር መስሪያ ቤቶች ቅንጅታዊ አሰራር በተማሪው ውጤት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ወደር የሌለው እንደሆነ አስረድተዋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ብዛት ያላቸው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ላሳለፉ ትምህርት ቤቶች የዕውቅናና የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።    
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
Mar 26, 2023 113
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገለጹ።   ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።   በውይይቱም “ስኬቶቻችንን አስጠብቀን፣ ጉልበት የሚሆኑ ገንቢ ሃሳቦች እና ሊታረሙ በሚገቡ እንዲሁም ትኩረት በሚፈልጉ ጉድለቶቻችን ላይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል“ ሲሉም አክለዋል።   ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን የሚመጥን አስተሳሰብ ማሰረፅ፣ ፅንፈኝነት፣ ጥላቻንና ህዝብን የሚከፋፍሉ የሴራ ፖለቲካን በጋራ ለመከላከል መግባባት መደረሱን ገልጸዋል።   በተጨማሪም “የኑሮ ውድነት ጫናን መቀነስ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት፣ እንዲሁም ከህዝባችን የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት መሆኑን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።
የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየተሰራ ነው - የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት አወሉ አብዲ
Mar 26, 2023 206
አዳማ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚደንት አወሉ አብዲ ገለጹ። በክልሉ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቀነስና በአገልግሎት ማሻሻል ላይ በተሰሩ ስራዎች 40ሺህ በሚጠጉ አመራሮችና ሙያተኞች ላይ የተለያየ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት የክልሉ መንግሥት የተገልጋዩን ህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታትና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ በትኩረት እየሰራ ነው። በተለይም ባለፉት ሰባት ወራት የመልካም አስተዳደር ችግር የሚስተዋልባቸውን ተቋማት ለመለየት በክልሉ ፕሬዚደንት የቅርብ ክትትል የሚደረግበት ልዩ ግብረ-ሃይል በማደራጀት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በምክትል ፕሬዚደንት የሚመሩ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱን አቶ አወሉ አብዲ ገልጸዋል። ኮሚቴውም የመጀመሪያ ስራው ችግሮችን መለየት ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰራቱ በክልሉ መስሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መለየት ተችሏል ብለዋል። በዚህም በሁሉም መስሪያ ቤቶች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መኖራቸውን በማረጋገጥ ወደ መፍትሄ ዕቅድ ዝግጅት መገባቱን ተናግረዋል። የመንግስት ስራ ሰዓት ካለማክበር ጀምሮ ብዙ ችግሮች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ አወሉ ''አብዛኛው ሰራተኛ አራት ሰዓት ቢሮ ገብቶ ዘጠኝ ሰዓት እንደሚወጣ በተለያየ ጊዜ ከተገልጋዮች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ማረጋገጥ ተችሏል'' ብለዋል። በዚህም አገልግሎት ፈላጊው ህዝብ ከመጉላላት ባለፈ 'እጅ መንሻ' ጭምር እየተጠየቀ መሆኑን መረዳት እንደተቻለ ተናግረዋል። እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለፃ አንዳንድ አመራሮችም ስብሰባዎችን ጨምሮ የኮሚቴና ሌሎች ጉዳዮችን ሽፋን በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠሩ መሆናቸው መረጋገጡን ጠቅሰዋል። ችግሮቹ ከተለዩ በኋላም በየመስሪያ ቤቱ መፍትሄ ማምጣት የሚያስችሉ ሪፎርሞች እንዲካሄድ በመደረጉ የተወሰኑ ለውጦች ታይተዋል ብለዋል። በተለዩት ችግሮች መነሻ በማድረግ ችገሮቹን ለመቀነስና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል 40ሺህ በሚጠጉ አመራሮችና ሙያተኞች ላይ የተለያየ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች በሙስናና 'እጅ ማንሻ' በመጠየቅ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ውስጥ በመሳተፍ መረጃ የተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል። የተወሰደው እርምጃም ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ከቦታ ማንሳት፣ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ማድረግ፣ ከስራ ማሰናበትና በህግ ተጠያቂ ማድረግ ጭምር የሚያካትት መሆኑንም አስረድተዋል። እርምጃ ከመውሰድ ጎን ለጎን በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም ንግድ፣ መሬት፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ የህዝቡ የዕለት ተዕለት አገልግሎት የሚበዛባቸው ተቋማት ላይ አገልግሎቱን ወደ 'ዲጂታል' የማስገባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ከመዝገብ ቤት ጀምሮ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለመለወጥና ከሰው ንክኪ ነፃ ለማድረግ የቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን አገልግሎት መጀመራቸውን አክለዋል። በተጨማሪም እያንዳንዱ አመራር በሳምንት ሶስት ቀን ቀኑን ሙሉ ቢሮ ሆኖ ህዝቡን እንዲያገለግል የክልሉ መንግስት ወስኖ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ በክልል ደረጃ በምክትል ፕሬዝዳንቱ የሚመራ የተለያየ ኮሚቴ ተደራጅቶ ክትትልና ቁጥጥር በማድረጉ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከወረዳ ጀምሮ በከተሞችና በዞኖች መሻሻሎች መኖራቸውን አመልክተዋል። ይሁንና ችግሮቹን በመሰረታዊነት ለመቅረፍ ሪፎርምና ማሻገር ላይ በቀጣይ ስራ የሚፈልጉ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ አወሉ አብዲ ጠቁመዋል።
"የመደመር ትውልድ (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የማስተዋወቅ ስነ-ስርዓት ተካሄደ
Mar 26, 2023 90
ሐረር መጋቢት 17/2815 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ” (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የማስተዋወቅና ሽያጭ መርሃ ግብር ተካሄደ። የማስተዋወቅ መርሃግብሩ እየተካሄደው በሐረር ከተማ በሚገኘው የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድን ጨምሮ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በክልሉ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው የ"መደመር ትውልድ" (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።  
ኢኮኖሚ
ለትንሳኤ በዓል ከ7 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ገለጸ
Mar 27, 2023 42
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ ለመጪው የትንሳኤ በዓል ከ7 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አስታወቀ።   የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንያው ዋሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በማህበሩ ስር ያለው የምግብ ዘይት ፋብሪካ የፓልም እና የሱፍ ዘይቶችን ለሃገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ወራትም ከ100 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም ዘይት በማምረት መንግስት በሚያቀርበው ድልድል መሰረት ለተለያዩ ክልሎች ማሰራጨቱን ተናግረዋል።   ለመጭው የትንሳኤ በዓልም ለህብረተሰቡ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም እና ከ4 ሚሊዮን ሊትር በላይ የሱፍ ዘይት ለማቅረብ ከወዲሁ እየተዘጋጀ መሆኑን ኢንጂነር እንያው ገልጸዋል። የፓልም ዘይቱ በአከፋፋዮች በኩል ለክልሎች እንደሚሰራጭ ጠቅሰዋል። ፋብሪካው አሁን ላይ ከ1ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠሩን ኢንጂነር እንያው አያይዘው ገልጸዋል።   በአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የንግድ ውድድር ሸማቾች ጥበቃና መሰረታዊ የንግድ እቃዎች አቅርቦት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ታፈረ ይመር እንዳሉት፣ ከጥቂት ወራት በፊት በክልሉ የዘይት አቅርቦት ሰፊ ጉድለት ነበረው። "መንግስት በዘይት ዋጋ ላይ ያደረገው ድጎማ እንዳለ ሆኖ የፊቤላ ዘይት ወደ ገበያ መግባት የምርት ችግር እንዳይኖርና ዋጋውም እንዲረጋጋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል" ብለዋል። ፋብሪካው ለበርካታ ወጣት ምሩቃን የሥራ ዕድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በፋብሪካው የሥራ ዕድል ያገኙት ኢንጂነር ትንሳኤ ተስፋ እና ወጣት ስመኝ ክንዴ ናቸው።   በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ የተመረቀውና በፋብሪካው የሰሊጥ ክፍል ማቀነባበሪያ ሃላፊ የሆነው ኢንጂነር ትንሳኤ ተስፋ ከፋብሪካው መቋቋም ጀምሮ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።   ወጣት ስመኝም በፋብሪካው ተቀጥራ መስራት ከጀመረች ከሁለት ዓመት በላይ እንደሆናት ጠቅሳ፣ "ፋብሪካው እሷን ጨምሮ ብዙ ወጣቶችን ሥራ በማስያያዝ ከተስፋ መቁረጥ ታድጓል" ብላለች።   የፌቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወደ ሥራ ከገባ ሁለት ዓመታት ማስቆጠሩ ታውቋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ  ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ
Mar 27, 2023 54
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የግብርና ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ኒ ሆንግሺንግ እንዲሁም በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል የምዕራብ እስያና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሊዩ ጂያንግ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ቻይና በግብርናው መስክ በትብብር ለመስራት የፈረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሊተገበሩ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶች በመቀየር ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።   ሁለቱ ወገኖች በግብርና ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር አስመልክቶ መደበኛ የሆነ የምክክር ጊዜ ለማዘጋጀት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያና ቻይና በግንቦት 2014 በግብርና፣ኢንዱስትሪ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማትና ጤና መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የኢንቨስትመንት ስምምነቶች መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።
የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት የውሃ ሀብትን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው--የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Mar 27, 2023 41
አዳማ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት የውሃ ሀብትን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና እንዳለው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዕቅድ ትግበራ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ አደራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብረሃ አዱኛ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ሀብቱን ከብክነትና ከብክለት በፀዳ መልኩ ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። ሀብቱን ውጤታማ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና አገልግሎቶች ለማዋል እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ለዚህም የ10 ዓመት መሪ ዕቅድና የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው። ሰፊ የውሃ ሀብት የሚገኝበትና በሀገሪቷ ከሚገኙ 12 ተፋሰሶች ውስጥ ሰባቱ የሚገኙት በኦሮሚያ ክልል መሆኑን ዶክተር አብረሃ ጠቅሰው የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት እውን ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል። በተለይ በክልሉ ያሉ ወንዞችና ሃይቆች ላይ እየደረሰ ያለው ብክነትን፣ ብክለትንና መመናመንን ለመታደግ የተቀናጀ የውሃ ሀብት ስርዓት እውን በማድረግ የውሃ ሀብት በዘላቂነትና በፍትሃዊነት ለመጠቀም ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።   ይህንን ማድረግ ካልቻልን የውሃ ሀብቱን ለህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል አንችልም ሲሉም ገልጸዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በተፋሰሶች ውስጥ እየተከናወነ ያለው የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት ፍትሃዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑንም አመልክተዋል። በአባይ፣ አዋሽና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የኦሞ፣ ጊቤ፣ ገናሌ፣ ዳዋና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶችን ወደ ተቀናጀ የውሃ አስተዳደር ስርዓት ለማስገባት በዘርፉ ሙሁራኖች ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ተወካይ ተሻለ በቃና በበኩላቸው የውሃ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ውጤታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። በክልሉ የውሃ ብክነትና ብክለት በመቀነስና የውሃ ሀብት ደህንነትን በመጠበቅ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የውሃ አስተዳደር ስርዓት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል። የተቀናጀ የከርሰ-ምድርና ገፀ-ምድር የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት በክልሉ ወንዞች፣ ሃይቆችና ተፋሰሶች የውሃ ሀብት ልማቱን ለማበልፀግ የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ ከኦሮሚያ ሁሉም ዞኖች የዘርፉ ሙያተኞችና ሃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በተከናወነ “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን የማስተዋወቅ እና ሽያጭ መርሐ-ግብር ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ
Mar 26, 2023 204
ሐረር/ጭሮ/አዳማ መጋቢት 17/2015(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ እንዲሁም በምስራቅ ሸዋ ዞኖች በተከናወነ “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን የማስተዋወቅ እና ሽያጭ መርሐ-ግብር ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ። በተመሳሳይ በባሌ ዞን መጽሐፉን የማስተዋወቅ እና ከሽያጭ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግዢ ለመፈጸም ቃል ተገብቷል።   በምስራቅ ሀረርጌ በተከናወነው መርሃ-ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰአዳ አብዱረህማን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተፃፈው “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ ለትውልድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ ለትውልዱ እውቀትን ከማሳደግ ባለፈ የቱሪዝም ሃብትን አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በዞኑ የሚገኙ ባለሃብቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ባደረጉት ተሳትፎ ከመፅሃፉ ሽያጭ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ነው ያሉት፡፡ ካሁን ቀደም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፃፉት መፅሃፍት ለትምህርት ቤት እና መሰረተ-ልማት ግንባታዎች መዋላቸውን አፈ-ጉባኤዋ አስታውሰዋል፡፡ አያይዘውም ከ”መደመር ትውልድ” መፅሃፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በክልሉ የሚገኙ እንደ ሶፍ ኡመር ዋሻ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶችን አልምቶ ለመጠቀም እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ የሶፍ ኡመር ዋሻ ታድሶ ለቱሪዝም ክፍት መደረጉ የቱሪዝም ፍሰቱን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግና ቅርሱን ለትውልድ ከማስተላለፍ አንፃር ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡   የምስራቅ ሃረርጌ ዞን አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሃመድ በበኩላቸው ከመፅሃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለአገር መሰረተ-ልማት ግንባታ የሚውል መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በየግላቸው የአንድ አንድ ሚሊዮን ብር የመፅሃፉን ግዢ የፈጸሙት ባለሀብቶች ደግሞ አቶ መሃመድ ሳለህ እና አቶ ማህዲ አብዱረህማን መፅሃፉ ከትውልድ ግንባታ ባለፈ የቱሪስት ስፍራዎችን ለማልማት የሚውል በመሆኑ በበጎ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን ተናግረዋል። የውጭ ዜጎች ጭምር መፅሐፉን እየገዙት እንደሚገኝ በመጠቆም ለሶፍ ኡመር ዋሻ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚውል በመሆኑ ወደ ፊትም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡   በተመሳሳይ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን “የመደመር ትውልድ” የተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መጸሐፍን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መርሐ-ግብር 25 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የዞኑ አስተደዳር ገልጿል፡፡   በዛሬው እለት በተካሄደው “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ የማስተዋወቅ ስነ-ስርዓት ላይ ከባለሀብቶች፣ ከዞኑ፣ ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች 25 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የዞኑ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ኢክራም ጣሃ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ ሸዋ ዞን በተከናወነ “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ ማስተዋወቅና ሽያጭ መርሃ-ግብር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።   የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ እንደገለፁት “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን ለዞኑ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ በተካሄደው ፕሮግራም ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ሽያጭ መከናወኑን ተናግረዋል። በመፅሃፉ ማስተዋወቅ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኦሮሚያ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ሚሊዮን በቀለ ”የመደመር ትውልድ” መጸሐፍ ስለ መጪው ትውልድና በመጪው ጊዜያችን ምን መስራት እንደሚገባን በግልጽ ያስቀመጠ ነው” ብለዋል። ለአሁኑና ለነገ ትውልድ የተሻለ ተስፋን ያመላከተ ነው ያሉት ሃላፊዋ ከመጸሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የክልሉን ታሪካዊ ቦታና የቱሪዝም ሀብቱን ለማልማት ትልቅ ሚና ያለው ነው ብለዋል።   በዚህም የሶፍ ዑመር ዋሻን ጨምሮ ታሪካዊ ቦታዎች ለምተው ለቱሪዝም ዕድገቱ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከማስቻሉም ባለፈ ለትውልድ እንዲተላለፉ የሚያስችል አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የዞኑ ነዋሪዎች መፅሐፍን በመግዛት የልማት አጋርነታቸውን በተግባር በማረጋጣቸው አመስግነዋል። በተመሳሳይ "የመደመር ትውልድ” (Dhaloota Ida'amuu) መጸሐፍ በባሌ ዞን ደረጃ የማስተዋወቅና ሽያጭ መርሃ-ግብር የተካሄደ ሲሆን ነዋሪዎች እና ባለሀብቶች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግዢ ለመፈጸም ቃል ገብተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መጸሐፉ ትውልድ ትክክለኛውን ታሪክ እንዲረዳ ከማድረግ በተጓዳኝ በሽያጩ የሚገኛው ገቢ ለልማት ወዋሉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ ላይ እየተሰራ ነው
Mar 27, 2023 42
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ። አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሴቶችን የዲጂታል ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ ተከብሯል።   በዚሁ ጊዜ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለችው ዲጂታል 2025 መርሃ-ግብር ሴቶች ቴክኖሎጂን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጠቀሙ ካደረጉ ችግሮች ውስጥ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ማነስ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን አካታች ምጣኔ ሀብትን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል የዲጂታል ዕውቀት ልዩነትን ለማጥበብ እንደ ሀገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይ በጥናቱ ግኝት መሰረት እስትራቴጂ በመቅረጽ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 የያዘቻቸውን እቅዶች ለማሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመድረኩ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ተወካይ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አካታች ዲጅታል መርሃ ግብሮችን ባለመተግበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ እንደሆኑ በመድረኩ ተነግሯል።
የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገለጸ
Mar 25, 2023 138
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015(ኢዜአ)፦ የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ.ኤች.ዲ.) ከቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ዋና ሊቀመንበር ሰር ቶኒ ብሌር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ትብብርና በቀጣይ ለመስራት ባቀዷቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 (ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን) ስትራቴጂ ከዝግጅት ወቅት አንስቶ እስከ ማስፈጸም ሂደት በቴክኒክ(ባለሙያ)፣በኢ-ሰርቪስ ትግበራ ላይ ጥናት በማድረግ፣የማስፈጸም አቅም እንዲሁም የአደረጃጀትና የስራ ሂደትን ለማሻሻል የሚያስችል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል። ኢንስቲትዩቱ ከዲጂታል መሰረተ ልማት አኳያ በዳታ ሴንተር፣በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ በክላውድና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ በቀጣይ ሊያደርገው በሚችለው ድጋፍ ውይይት መደረጉ ተመላክቷል። በሌላ በኩል የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ለሰር ቶኒ ብሌር የዲጂታል መታወቂያን አገልግሎቶች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ለአገልግሎቱ የሚያደርገውን ድጋፍ እና ከመሰረተ ልማት ጋር ያሉ ተግዳሮቶች ላይም ገለጻ አድርገዋል። የ69 ዓመቱ የእንግሊዝ የቀድሞ ፖለቲከኛ አገሪቷን ከእ.አ.አ 1997 እስከ 2007 በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የመሪነቱን ሚና እየተወጣ ነው-ፍሬህይወት ታምሩ
Mar 24, 2023 153
አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015 (ኢዜአ) ኢትዮ- ቴሌኮም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የመሪነቱን ሚና እየተወጣ መሆኑን የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ መልክ ያበለጸገውን ቴሌ ብር "ሱፐር አፕ" የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል። መተግበሪያው ደንበኞች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማቅለልና በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስራዎችን ለማሳለጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በአንድ ጊዜ ፈርጀ ብዙ የዲጂታል ግብይት አገልግሎቶችን እንዲያገኙና ለማንኛውም የግዢ ሂደት እንዲጠቀሙ የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑም ተመላክቷል። ይህ አዲሱ መተግበሪያ አሁን በስራ ላይ ካለው የቴሌብር መተግበሪያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአፈጻጸም፣ የሴኩሪቲ ሲስተም፣ የስልክ ዳታ የመያዝ አቅም ውስንነትንና ሌሎች የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል። እንዲሁም የማይ- ኢትዮ- ቴል መተግበሪያንና ሌሎች መተግበሪያዎችን በአንድ በማካተት የተቀናጀ፣ ብቁ እንዲሁም አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የኢትዮ -ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኩባንያው አገልግሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ይገኛል። የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን የማድረግ ሥራን አጠናክሮ በመቀጠል ኢትዮ-ቴሌኮም በዘርፉ የመሪነት ሚናውን እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፤ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነውም መተግበሪያ ይህንኑ እንደሚያጎለብት ተናግረዋል። ሌላኛው የስማርት ስልክ አጠቃቀም መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ በኔትወርክ ላይ ከተመዘገቡት 81ሚሊየን ቀፎዎች ውስጥ 46 በመቶ የሚሆኑት የስማርት ቀፎዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው መተግበሪያ ቴሌ ብር ሱፐር አፕ ለተለያዩ አገልግሎት የምንጠቀምባቸው አፕሊኬሽኖችን በአንድ መተግበሪያ ላይ ሁሉንም መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ጊዜንና ወጭን በመቆጠብ ረገድ መተግበሪያው ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።        
ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ መልክ ያበለጸገውን ቴሌ ብር "ሱፐር አፕ"ይፋ አደረገ 
Mar 23, 2023 205
አዲስ አበባ መጋቢት 14/2015 (ኢዜአ) ፦ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ መልክ ያበለጸገውን ቴሌ ብር "ሱፐር አፕ" የሞባይል መተግበሪያ ዛሬ ይፋ አደረገ። ተቋሙ የቴሌ-ብር አገልግሎት ባቀረበ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለትራንስፎርሜሽንና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገልጿል። የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በማቅለል ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱም እንዲሁ። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው መተግበሪያም ከዚህ ቀደም ከነበረው መተግበሪያ ተጨማሪ አገልግሎቶች ተካተውበት በአዲስ መልኩ መበልጸጉ ተገልጿል። መተግበሪያው ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ መሆኑም ተጠቅሷል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኩባንያው አገልግሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ መምጣቱን ተናግረዋል። ኩባንያው ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን የማድረግ ሥራን አጠናክሮ በመቀጠል ኢትዮ-ቴሌኮም በዘርፉ የመሪነት ሚናውን እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ኃብትን በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ፤በዛሬው እለት ይፋ የሆነውም መተግበሪያ ይህንን ያሳልጣል ነው ያሉት። መተግበሪያው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የሚውሉ መተግበሪያዎች በአንድ የተካተቱበት መሆኑን ገልጸዋል። ጊዜንና ወጭን በመቆጠብ ረገድ መተግበሪያው ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል። አገልግሎቱን ከፕሌይ ስቶር፣ ከአፕ ስቶርና ከአፕ ጋለሪ በማውረድ መጠቀም እንደሚቻል ተመላክቷል።
ስፖርት
“በዛሬው ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይዞ መውጣት የሚያስችል የስነ-ልቦና ዝግጅት አድርገናል”-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
Mar 27, 2023 41
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ)፦ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር ሁለተኛውን የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ታደርጋለች። የሁለቱ አገራት ጨዋታ በሞሮኮ ራባት በሚገኘውና 45ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ልዑል ሙላይ አብደላ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሰዓት ይካሄዳል። በምድብ አራት የሚገኙት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም ባደረጉት ጨዋታ ጊኒ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል። የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዛሬውን ጨዋታ አስመልክቶ በሰጠው አስተያያት “ከመጀመሪያው ጨዋታ በኋላ አብዛኛው ትኩረት የነበረው ተጫዋቾቹን ከሽንፈቱ በኋላ ከነበረው ስሜት ወጥተው ለዛሬው ጨዋታ በስነ ልቦናና አዕምሮ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ነው” ሲል ገልጿል። በጊኒ ለተወሰደብን ብልጫ መልስ ለመስጠትና ጨዋታውን ለመቆጣጠር ከአዕምሮ ዝግጁነት ይልቅ አካላዊ ፍልሚያና ስሜታዊነት ላይ ትኩረት ማድረጋችን ለነሱ ይበልጥ እንዲመቻቸው ማድረጉን ተናግሯል። ይህም ተጫዋቾቹ ከጨዋታው ውጤት ለማግኘት ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉትና በአዕምሯቸው ስለው የገቡትና ሜዳ ላይ የነበረው ነባራዊ እውነት የተለያዩ ከመሆናቸው እንደሚመነጭ አመልክቷል። “በታዩት ክፍተቶች ላይ ውይይት መደረጉንና ከዛሬው ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይዞ ለመውጣት ዝግጅታችንን ጨርሰናል” ነው ያለው አሰልጣኝ ውበቱ። የአማካይ ተጫዋቹ ጋቶች ፓኖም በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት በቅጣት በዛሬው ጨዋታ የማይሰለፍ ሲሆን የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ምኞት ደበበ ከአንድ ጨዋታ ቅጣት መልስ ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ የ36 ዓመቱ ቻዳዊ ኢንተርናሽናል ዳኛ አልሀጂ አላው ማህማት በዋና ዳኝነት ይመሩታል። ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ አራት ማላዊ ከግብጽ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት በቢንጉ ናሽናል ስታዲየም ይጫወታሉ። በምድብ አራት ግብጽ እና ጊኒ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኢትዮጵያ በሶስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ እድላቸውን ለማስፋት የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት መዲና ኢሳ በአንደኝነት አጠናቀቀች
Mar 26, 2023 92
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት መዲና ኢሳ በአንደኝነት አጠናቀቀች።   አትሌት መዲና ኢሳ በመሪነት በማጠናቀቋ የ70ሺህ ብር ተሸላሚ ስትሆን በተጨማሪም በውድድሩ አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገቧ የ50ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላታል። በውድድሩ አትሌት ፅጌ ገብረ ሰላማ 2ኛ እንዲሁም አትሌት መልክናት ውዱ 3ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው እንደቅደም ተከተላቸው የ45ሺህ ብር እና የ30ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። በውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ የተለያዩ አትሌቶችና እንግዶች ተገኝተዋል። የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎሜትር ሩጫ ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ ውድድር አትሌቶች፣ 15 ሺህ የጤና ሯጮች፤ እንዲሁም አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።
20ኛው የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
Mar 26, 2023 88
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጀው 20ኛው የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው። ውድድሩ መነሻና መድረሻውን አዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ አድርጎ እየተካሄደ ነው።   የዘንድሮው ዓመት ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። በዚህ ውድድር ላይ በአትሌቶች፣ የጤና ሯጮች፣ እንዲሁም አምባሳደሮች ይሳተፋበታል።   በውድድሩ በሴት አትሌቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር በአንደኝነት ለምታጠናቅቀው አትሌት የ70ሺህ ብር ሽልማት መዘጋጀቱም ታውቋል። እንዲሁም ውድድርን ሁለተኛ ሆና ለምታጠናቅቅ 45ሺህ ብር፤ 3ኛ ሆና ለምታጠናቅቅ ደግሞ የ30ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱም ተጠቁሟል።   ክብረ-ወሰን የሚያሻሽሉ አትሌቶች ተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል። በውድድሩ በአትሌቶች መካከል ከሚደረገው ውድድር በተጨማሪ 15ሺህ የጤና ሯጮች እየተሳተፉ ነው።   በሩጫ ውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር እና አትሌት ለተሰንበት ግደይ ተገኝተዋል።
መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሜ ተመርጡ
Mar 25, 2023 99
አዲስ አበባ (ኢዜአ) መጋቢት 16/2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ላለፉት ሶስት ዓመታት የመሩት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሜ ተመርጡ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል። በጉባኤው ቀጣይ ሶስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበርን የሚመሩ የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ምርጫ አካሂዷል ። በዚህም ከ15 ክለቦች እጩዎችን የቀረቡ ሲሆን ሰባቱ በአባልነት ተመርጠዋል። ሊጉን ላለፉት ሶስት ዓመታት የመሩት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፤ ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ጌቱ ደጉ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ ንዋይ በየነ፣ መንግስቱ መሀሩ፣ አብዮት ብርሃኑ፣ አሰፋ ሆሲሶ እና ልዑል ፍቃዱ የቦርድ አባል ሆነው ተመርጠዋል። በቀጣይ ሶስት ዓመት ፕሪሚየር ሊጉ የተሻለ ገቢ እንዲያመነጭና ምስራቅ አፍሪካ ላይ ጥሩ ሊግ እንዲሆን የሚሰሩ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሜ የተመርጡት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ገልጸዋል። ከሱፐር ስፖርት ጋር ውል በመግባት የቀጥታ ስርጭት ገቢ የማመንጨት ጅምሮች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው ለሊጉ እድገት የሚያግዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ይሰራል ብለዋል። የእግር ኳስ ሜዳ ችግር ለዘርፉ እድገት ፈታኝ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁሉንም ትኩረት እንደሚሻ ተናግረዋል። የእግር ኳስ ሜዳዎች መገንባት የፌደራል መንግስትና የክልሎች ሃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው በጅምር ላይ ያሉ የስታዲሞች ግንባታ እንዲጠናቀቅ መስራት ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ፤ አክሲዮን ማህበሩ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የፕሪሚየር ሊጉን የገቢ ምንጭና አቅሙን ማጠናከር ላይ በርብርብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።  
አካባቢ ጥበቃ
በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱ ተገለጸ
Mar 26, 2023 74
መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ) በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155 ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በዞኑ ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ መጠናቀቁን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት እንደገለጸው ባለፉት ሁለት ወራት በተከናወነው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ 155ሺህ ሄክታር መሬት የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ ተከናውኗል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ይሳቅ በተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃ የተከናወኑ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን በመቀነስ በኩል ጉልህ አስታዋጽኦ እያበረከቱ ነው። በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ከ155ሺህ ሄክታር መሬትን በመሸፈን በተከናወነው በዚህ ሥራ 3ሺህ ሄክታር መሬትን ከእንስሳት ንክኪ ማካለልን ጨምሮ የችግኝ ዝግጅት፣ 20ሺህ ኪሎ ሜትር የማሳና የተራራ ላይ እርከን ስራ፣ የግጦሽ መሬት ልማትና ሌሎች የድርቅ ተጋላጭነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ከድር እንዳሉት፣ በዞኑ በተደጋጋሚ እየተሰሩ የሚገኙ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን ከመቀነስ በተጓዳኝ የሥራ ዕድል ምንጭ እንዲሆኑ ከ4ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን በዘርፉ ማደራጀት ተጀምሯል። በዞኑ የዳዌ ቃቸን ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ አሚን እንዳሉት፣ በአካባቢያቸው በተደጋጋሚ እያጋጠመ የሚገኘውን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ ለተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቷል። በወረዳው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የተከናወነባቸው ተፋሰሶች በዘላቂነት እንዲጠበቁ ከ30 የሚበልጡ ወጣቶችን በተፈጥሮ ኃብት ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል ብለዋል። ወጣቶቹ ከእንስሳት ንክኪ በተከለሉና በተፈጥሮ ኃብት በተሸፈኑ አካባቢዎች ውስጥ የንብ ማነብ፣ የእንስሳት መኖ ልማት፣ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ነው የገለጹት። በዳዌ ቃቸን ወረዳ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከተሳተፉ ነዋሪዎች መካከል አቶ ያህያ አብዱልወሃብ በሰጡት አስተያየት፣ የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን እንደሚቀንሱ በማመን በስራው መሳተፋቸውን ተናግረዋል። በተለይ ዘንድሮ በአካባቢያቸው በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ወጣቶች እንዲደራጁ መደረጉ ሥራውን ውጤታማ ያደርገዋል ነው ያሉት። ወጣት ሙክታር መሐመድ በበኩሉ፣ በሰው ሰራሽ ተጽእኖ የተነሳ አካባቢያቸው ተራቁቶ እንደልብ ይፈሱ የነበሩ ወንዞች በመድረቃቸው ለድርቅ መጋለጣቸውን አስታውሰዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የተራቆተው አካባቢ አረንጓዴ እየለበሰ መምጣቱ ተስፋ እየሰጣቸው መሆኑን ነው የገለጹት። በአሁኑ ወቅት ከሌሎች 15 የአካባቢያቸው ወጣቶች ጋር የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ማህበራት በመደራጀት በንብ ማነብና የእንስሳት መኖ እየተሳተፈ መሆኑን አመልክቷል።  
በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ ተከናውኗል - የክልሉ ግብርና ቢሮ
Mar 24, 2023 163
ሰቆጣ መጋቢት 15 ቀን 2015(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ መከናወኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በበጋው ወቅት የተከናወኑ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎችን እንዲጠብቁ ለአርሶ አደሮች በባለቤትነት የማስረከብ መርሐግብር በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ ሽመላ ቀበሌ ጋውሳ ተፋሰስ ዛሬ ተካሂዷል።   የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አልማዝ ጊዜው የክልሉን የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የዞንና ቀበሌ ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱንና 34 ሺህ የሚደርሱ የስራ መሳሪያዎች ለዞኖች መከፋፈላቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል። በክልሉ 8 ሺህ 548 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ለማከናወን ታቅዶ፤ በ8 ሺህ 596 ተፋሰሶች ላይ ስራዎቹ መካሄዳቸውን አመልክተዋል። በልማቱ በ331 ሺህ ሄክታር ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውንና በስራዎቹ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት በዘላቂነት በማከናወን የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን መታሰቡን ነው ዶክተር አልማዝ ያስረዱት። በቀጣይም የለሙ ተፋሰሶችን በስነ ሕይወታዊ ዘዴዎች የመሸፈንና የኢኮኖሚ ምንጭ የሚሆኑትን የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ እንዳሉት፤ በአስተዳደሩ በ277 ተፋሰሶች ውስጥ የሚገኝ 4 ሺህ 927 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ተካሄዷል።   በልማቱም ከ82 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንና በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት ተፋሰሶች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እንዳሳደጉትም ገልጸዋል። በተለይም በተራራ ላይ የተሰሩ የጠረጴዛ እርከኖች ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንና ስራዎቹን በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች በመሳተፍ የእርሻ መሬታቸውን ለም አፈር በማሳ ውስጥ በማስቀረት ምርታማነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ገልጸዋል።   ዘንድሮ የተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች በአግባቡ እንዲጠበቁና እንዲያገግሙ በየአካባቢያቸው የተፈጥሮ ሃብት ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። በአማራ ክልል በዘንድሮው ዓመት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ሶስት ቢሊዮን ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል'።  
በአማራ ክልል የ2015 የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የሽግግርና ርክክብ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 24, 2023 128
ሰቆጣ መጋቢት 15/2015(ኢዜአ) የአማራ ክልል የ2015 የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የሽግግርና ርክክብ መርሃ ግብር በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ እየተካሄደ ነው። በወረዳው እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለውን ጨምሮ የክልልና የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።   በክልሉ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራው ከጥር 17 ቀን 2015 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። ሽግግርና ርክክቡም በህዝብ ንቅናቄ የለማውን ተፋሰስ በየአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች በማስረከብ በስነ ህይወታዊ ዘዴ በዘላቂነት እንዲለማ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። "ይህም ተፋሰሱን በመጠበቅና በማልማት በቋሚ አትክልትና ፍራፍሬ፣ በንብ ማነብና መሰል የሥራ ዘርፎች ተደራጅተው ለሚገቡ ወጣቶች የኢኮኖሚ ምንጭ ለመሆንም ያስችላል" ብለዋል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በዞኑ ስድስት ወረዳዎች በ119 ቀበሌዎች በህዝብ ተሳትፎ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። በዚህም በ 2 ሺህ 775 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የተሰራ ሲሆን፣ በ2 ሺህ 152 ሄክታር መሬት ላይ ደግሞ ነባር የለሙ ተፋሰሶች ጥገና መደረጉን አስታውቀዋል። በልማት ሥራው ከ82 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ በሥራዎቹ ከ147 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከት ተችሏል ብለዋል።  
የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Mar 23, 2023 148
አዲስ አበባ መጋቢት 14/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያና የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ62ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃም ለ42ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተከብሯል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ሃይለማርያም በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ተዳራሽ በማድረግ ደኅንነት ለማስጠበቅና ልማትን ለማፋጠን እየተሰራ ነው። ትክክለኛ የአየር ትንበያ መረጃዎች ለጥናት ምርምር ጭምር እንደሚያግዙ ጠቁመው ትክክለኛ የአየር ትንበያ መረጃ እንዲኖር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ጎርፍና ድርቅ ያሉ ክስተቶች በአገሪቷ እየተበራከቱ መሆናቸውን አንስተው እነዚህን ለመቋቋምም የተጠናከረ የአየር ሁኔታ መከታተያ፣ መተንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በመገንባትና በመዘመን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለዚህም በሰው ሃብትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሱን በማሻሻል ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር ዶክተር አግነስ ኪጃዚ በበኩላቸው የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ መረጃ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመታገዝ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች የግብርና ሥራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ከማድረጉም ባለፈ ምርቶች በጊዜ ተሰብስበው ለተፈለገላቸው ዓላማ እንዲውሉ ከማገዝ አንጻር ሰፊ ጠቀሜታ አላቸው።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 531
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተገለጸ
Dec 20, 2022 535
አዲስ አበባ ታኅሳስ 11/2015 (ኢዜአ) አህጉራዊው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፍሪካ ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተመላከተ። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ትስስር ከባህረ-ሰላጤው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት እንደሚጠቀስም ተገልጿል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዊሊያም ስቴንሀውስ ከሲ ጂ ቲ ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በተለይም ዱባይ የአፍሪካን ንግድና ኢንቨስትመንት በተመለከተ ዋና ማዕከል ሆናለች ብለዋል። በዱባይ 25ሺህ ገደማ የአፍሪካ ካምፓኒዎች እንደሚንቀሳቀሱ አመልክተው ይህም ሀገሪቱ በነጻ የንግድ ቀጣናው የቢዝነስ አጋር እንድትሆን አስችሏታል ነው ያሉት። አፍሪካውያን ባለሃብቶች የግብይት ማዕከላቸውን በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በማድረግና ምርቶችን ወደ አህጉሪቷ በማስገባት በነጻ ንግድ ቀጣናው ስር የገልፍ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደጉት እንደሚገኝም አስገንዝበዋል። የዱባይ ወደብ በአፍሪካ ያለው ተደራሽነት መስፋፋትም አፍሪካ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የሚኖራትን የሎጀስቲክስ አቅርቦት እንደሚያሳድግ በመረጃው ተመላክቷል። ከገልፍ ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ ዲፕሎማሲያዊና ወንድማማችነትን መሠረት ያደረገ ነው ያሉት ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ናቸው። አምባሳደሩ እንደሚሉት ከመካከለኛው ምስራቅ መነሻቸውን ያደረጉ ባለሃብቶችና የቢዝነስ ሰዎች ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር በልዩ ልዩ ዘርፎች ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ይገኛል። እ.አ.አ በጥር 2021 ተግባራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ከአጀንዳ 2063 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቱን ወሳኝ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የዲጂታል ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ትስስርና ሌሎች የንግድ ግንኙነቶችን በነጻ የንግድ ቀጣና ለማከናውን የተካሄደ ስምምነት ነው።
ሐተታዎች
ውጣ ውረድ የማይበግረው አጋርነት
Mar 17, 2023 279
በሰለሞን ተሰራ ኢትዮጵያ በሥልጣኔ ቀደምትና ታሪካዊት ሀገር ነች። ቅሉ ከውጭ ሀገራት ያላትን ዘመናዊው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቅኝት የጀመረችው በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑ በታሪክ ይጠቀሳል። በተለይም ኢጣሊያ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1896 በአድዋ እንዲሁም በድጋሚ በ1935 ያደረገችው የግፍ ወረራ ኢትዮጵያ የዓለምን ፖለቲካ በቅጡ አሰላለፍ ተረድታ አጋር ሀገራትን እንድትሻ ዐይኗን ገልጦላታል። በዚህም ድኅረ-አድዋ ድል በርካታ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርተዋል። የወቅቱ ልዕለ-ኃያል ሀገር አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ የተመሰረተውም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና በፕሬዝዳንት ሩዝቬልት መንግሥት ተወካይ ሮበርት ስኪነር መካከል በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1903 በተደረሰው የንግድ አጋርነት ስምምነት ነበር። ድኅረ-ስምምነቱም በፈረንጆቹ በ1909 የአሜሪካ ሌጋሲዮን በአዲስ አበባ የተመሰረተ ሲሆን ሆፍማን ፊሊፕ የተባሉት ቋሚ መልዕክተኛ የአሜሪካ ቆንስላ ተሿሚ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፄ ምኒልክ አቅርበዋል፡፡ ከ120 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጽኑ ወዳጅነትና የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ እንደነበር ይወሳል፡፡ ሀገራቱ ጥቅማቸውን በጠበቀ መልኩ የመሰረቱት ግንኙነት ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም አይዘነጋም፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራን ተከትሎ ቆንስላዋን የዘጋችው አሜሪካ፤ ኢትዮጵያ በአርበኞቿ ትግል ነፃነቷን ስታረጋግጥ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በነኅሴ 1943 በድጋሚ ቆንስላዋን በመክፈት ግንኙነቷን አስቀጥላለች። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የቆንስላ ቢሮ ከፍታ ዕውቁን ዲፕሎማት ብላታ ኤፍሬም ተወልደመድኅንን በቋሚ መልዕክተኛነት ሾማለች። በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1952 የተደረገው 'ፖይንት ፎር' የተሰኘው የተቋማት ቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ለሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ መሰረት የጣለ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ስምምነትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአውራ ጎዳና ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅት በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ተቋቁመዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱ አድማሱን እያሰፋ፣ ሥር እየሰደደ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ጦር ሠራዊቷን እንድታጠናክር በአነስተኛ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችና ወታደራዊ ሥልጠናዎች ተጨባጭ አጋርነት አሳይታለች። የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን በተቆጣጠረ ማግስት ግን በዘመኑ በነበረው ዓለም አቀፋዊ ርዕዮተ- ዓለም ልዩነት ሳቢያ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሮ ሌላ መልክ ያዘ። በተለይም የደርግ ሊቀ-መንበር የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ሶቪየት ሕብረት አቅንተው የጦር መሳሪያ ድጋፍ መፈራረማቸው አለመግባባቱን ይበልጥ አባባሰው። በዚህም አሜሪካ በኤርትራ የነበረውን የቃኘው ሻለቃ ጣቢያዋን ዘግታ ወጣች። ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ከአምባሳደር ደረጃ በማውረድ በጉዳይ አስፈጻሚ ሲገናኙ ቆይተዋል፡፡ ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የሀገራቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት የአምባሳደር ደረጃ በመመለስ ከአሜሪካ ጋር የነበረው ግንኙነት መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጎታል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት አሜሪካ በጤና፣ በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ በምታደረገው ድጋፍ በመታገዝ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አሜሪካ መርህን ያልተከተለ አካሄድ በሀገራቱ መካከል የነበረውን ወዳጅነትና አጋርነት ላይ ጥቁር ጥላ ማጥላቱ አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሻክሮ የቆየውን ግንኙነት በማደስ የነበረውን ጠንካራ ወዳጅነት በድጋሚ የሚያጸኑ ጅማሮዎች ተስተውለዋል። በተለይም ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተደረሰውን የሰላም ሰምምነት ተከትሎ የሀገራቱ መቃቃር እየረገበ ሲሆን የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እየጎበኙ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተነጋግረዋል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ያደረጉት ውይይት ዘርፈ-ብዙ አጋርነትን ለማጠናከር መግባባት የተደረሰበት እንደነበርም በሁለቱም ወገኖች ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱ በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነና በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት የተደረሰበት እንደሆነ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት ማግኘቱንም ጠቅሰዋል። በኢኮኖሚው መስክ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ባተኮሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት መነጋገራቸውን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ አንቶኒ ብሊንከን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሚኒስትሮቹ ለረዥም ዘመን የዘለቀውን የኢትዮ-አሜሪካ ትብብር እና አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ተነጋግረዋል። በኢትዮጵያ አዲስ የመረጋጋትና የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አብራርተውላቸዋል። የሰላም ምዕራፍ የበለጠ እንዲጠናከርና የሰመረ እንዲሆን ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱን በጎ ገጽታ እንዲላበስ መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እምርታ እንዲመጣ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት መንግሥት አሁንም ቁርጠኛና ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው፤ በመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ተግባር የአሜሪካ መንግሥት እንዲደግፍም ጠይቀዋል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው፤ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር አሜሪካ በትብብር መንፈስ እንደምትሰራ እና አሜሪካ ሁለንተናዊ ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል። አሜሪካ ለድርቅ ተጎጂዎች እና ለስደተኞች የምታደርገው ድጋፍ አለመቋረጡ የሁለቱ ሀገራት አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ይጠቁማል፡፡ የብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መጀመሩም ዛሬም ኢትዮጵያ በአሜሪካ መንግሥት ዐይን ያላትን ቀዳሚ ሥፍራ ያመለክታል። አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ትግበራ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የበለጠ እንዲጠናከር የአሜሪካ መንግሥት ሁለገብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረገች ያለውን ጥረት አሜሪካ በአድናቆት እንደምትመለከተውና የሚበረታታ መሆኑን ብሊንከን ገልጸዋል። የብሊንከንን ጉብኝት ተከትሎ አሜሪካ 331 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ አረጋግጣለች። ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ነፍስ አድን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።  
የሴቶች ቀን ሲታሰብ
Mar 8, 2023 469
የሴቶች ቀን ሲታሰብ የሰው ልጅ ሕይወትን ቀላል ባደረጉ የፈጠራ ስራዎቻቸው የምናስባቸው እንስቶች በቀዳሚነት ይነሳሉ። በተለያዩ መስኮች አሻራቸውን ያሳረፉ እንስቶች ቁጥራቸው ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ጽሑፋችን ግን በኬሚስትሪና ፊዚክስ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት አስተዋጽኦ በኖቤል ሽልማት እውቅና የተሰጣቸውን የየዘመኑ ፈርጦች እንዳስሳለን። ከነዚህ ፈርጦች መካከል በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማትን ከሴቶች ቀዳሚ በመሆን በቀዳሚነት ያሸነፉት ሜሪ ኩሪ ይወሳሉ። ይልቁንም እ.አ.አ በ1903 በኬሚስትሪ ዘርፍ የተቀበሉትን የኖቤል ሽልማት በድጋሚ በ1911 በመሸለም ብቸኛነት ስማቸው ይነሳል። በ1967 በፖላንድ ዋርሶ የተወለዱት ማሪ ኩሪ ለዘመናዊው የሳይንስና ኬሚስትሪ ዘርፍ ውለታን ከዋሉ ስመጥር ተመራማሪዎችና በጨረራ ህክምና ፈጠራ የዘርፉ ፈር ቀዳጅ በመሆን የአለምን የራዲዮአክቲቪቲ እይታን የቀየሩ ጀግና ናቸው።   የሜካኒካልና ኤሮስፔስ ተመራማሪዋ ፍራንሲስ አርኖልድ ደግሞ በህክምናናና በታዳሽ ኃይል ዘርፍ አሻረቸውን በጉልህ ካኖሩ ተመራማሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ። አሜሪካዊቷ ፍራንሲስ ለታዳሽ ኃይል እና ለፋርማሲ አገልግሎት የሚውል አዲስ ኢንዛይም በምርምር በማግኘት በዘረፉ አሻራቸውን አኑረዋል። ለዚህም አስተዋጽኦዋ እ.አ.አ በ2018 በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል። የኤድስን ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሰፊ አበርክቶ ያላቸው የህክምና ተመራማሪዋ ፍራንሶዝ ባሪሲኖሲም የሴቶች ቀን ሲታሰብ ከሚወሱ አንስቶች አንደኛዋ ናቸው። ባሪሲኖሲ የኤች አይቪ ኤድስን ከገዳይ በሽታነት መታከምና መቆጣጠር ወደ ሚችል በሽታነት ለመቀየር የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራን በማላቅ ረገድ ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ይወሳል። በ1947 በፓሪስ ከተማ የተወለዱት ባሪሲኖሲ “ሳይንስን ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል እንሰራለን” በሚለው አባባላቸው ይታወቃሉ። ኤድስን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦም በፊዚዮሎጂ/ሕክምና ዘርፍ እ.አ.አ በ2008 የኖቤል ሽልማትን አግኝተዋል። ያለ ህክምና ትምህርት የሚሊዮኖችን ሕይወት በታደገው የወባ በሽታ መከላከያ ፈጠራቸው አለም እውቅና የተሰጣቸው ቱ ዩዩ በሴቶች ቀን የምናመሰግናቸው ሌላኛዋ ተመራማሪ ናቸው። ቻይናዊቷ ቱ ዩዩ ባህላዊውን የወባ በሽታ መከለከያ ህክምና ወደ ዘመናዊ በመቀየርና በማስተዋወቅ ነው ስመ ገናና የሆኑት።   የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዙፍ አሻራቸውን ላስቀመጡት ተመራማሪ ባለውለታነት እ.አ.አ በ2015 በፊዚዎሎጂ/ ህክምና ዘርፍ ሳይንስ ምድብ የመጀመሪያዋ ቻይናዊት በመሆን የኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የሰው ልጆችን ሕይወት ካቀለሉ አለም አቀፍ ፈጠራዎች መካከል የተጠቀሱትን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ መሆኑ ይታወቃል።
ሴትነት እና እናትነት
Mar 8, 2023 689
(አየለ ያረጋል) እስኪ መላ ስጪኝ መላ ካንቺ ይገኛል እኔማ ወንድ ነኝ ይደናገረኛል… (የማኅበረሰቡ ቃላዊ ግጥም) ሴትነት እናትነትን ለመግለጽ ቀርቶ በጥቂቱ ለመረዳት የ’እናት ልብ’ መታደል የሚሻ ይመስላል። ጥቂት ወንዶች ይህን ጸጋ ይቸራሉ። ልክ እንደ ዶክተር ይሁኔ አየለ። የስነ-ምግብ ሳይንቲስቱ ዶክተር ይሁኔ አየለ ‘እናት’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፍ የሴትነት እና እናትነትን ከፍታ በ’ኩርሽም’ ቃላት ተራቀውበታል። የሴቶች ቀንን (ማርች-8) ሰበብ በማድረግ ይህን ጽሑፍ ሳዘጋጅ መታሰቢያነቱ እናትን አስበው በ‘እናትነት’ ቅን ልቦና ‘እናትን’ ላበረከቱልን ዶክተር ይሁኔ አየለ ነው። ‘እናት፤ የሴት ልጅ ስንክሳር፤ ከቤተሰባዊ ሕይወት እስከ ሐልዮመንበርት’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባሳተሙት (በ406 ገፆች በተቀነበበ) አርበ ጠባብ መጽሐፍ ሴትነትን ከዘፍጥረት እስከ አሁን ዘመናትን ዋጅተው፣ እናትነትን ከሴትነት ዘንቀው፣ የእናትነት ጸጋን ከነባራዊ ሃቅ ጋር አሰነናስለው፣ የእናትነትን ልዕለ-ተፈጥሮ አርቅቀው፣ የዓለምን ክብር-ነሽነት ከነገረ-ሃይማኖት እስከ ነገረ-ባህልና ፍልስፍና ፈትተው፣ የማኅበረሰቡን ምልከታ ዝንፈት እና ሚዛን ጉድለት ከማኅበራዊ እስከ ፖለቲካዊ መገለጫዎች አዛምደው አቅርበውታል። ዶክተር ይሁኔ አየለ “እናት” በተሰኘ እናት የሆነ መጽሐፋቸው እናትነትን በልኩ ነጽረውታል። ሴትነት በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ሰለባነቱን፣ ነገረ-ሴትነትን ከንጽረተ-ሴትነት ቃኝተውታል። በእሳቤ ሚዛን ሰለባነት ዓለም ውስጥ ከንግስት ማክዳ እስከ ንግስት ፉራ፣ ከሰብለ ወንጌል እስከ ድል ወንበራ፣ … ብርቱ ኢትዮጵያዊት ሴቶችን ሕይወት ጨልፈውታል። የሴትነትን ጸጋዎች ጨልፈው በሴትነት ላይ የሚፈጸሙ የሀበሻ ግፎችን ተንትነውበታል። ሴቶች የማኅበረሰቡ ግፍ ሰለባዎች፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጉድለት ሰለባዎች እንደሆኑ በቅጡ ገልጸውታል። ዳሩ ሴትነት ጀግና እና ብልህ፣ የቤተሰብ መሰረት፣ የደስታና እልልታ እናት፣ ቃል ኪዳንና ክብር ጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል። “ሴት ልጅ ባለብዙ ጸጋዎች ናት። ከጸጋዎቿ መካከል ጀግንነት እና ብልሃት ይጠቀሳሉ። … ሴት ልጅ ባህልን ፈጥራ የማኅበራዊነትን ማስተሳሰሪያ ገመዶች ገምዳ አስተሳስራ ማኅበረሰብን የተከለች ሥርዓት ናት። … ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ የመጀመሪያ ተቋም ነው። የተቋሙ ባለሥልጣን (እመቤት) ሴት ናት። ያቺ ሴት እናት ናት። ቤተሰብ የስብዕና መሰረት የሚባለው እናትን ምሰሶ አድርጎ ነው” (ገጽ-285) ሴት ልጅ መለኛ መሆኗን ማኅበረሰባችን ቢያምንም ሴትነትን ግን እንዳላከበረ አሉታዊ ይትባህልና ኪነተ- ቃሉን ዘይቤ ያወሳሉ። በእርግጥ የእናትን ምቹነት እና ዋጋ ከፋይነት የሚያትቱ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችም አሉ። ለምሳሌ ዳንኤል አበራ “የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች” በሚለው መጽሐፋቸው “እናት ትረገጣለች እንደመሬት፤ እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ፤ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ፤ እናት የሌለው ልጅ እንደ ጌሾ፤ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ…” የሚሉ ምሳሌያዊ ንግግሮችን አስፍረዋል። መላኩ ይርዳው የተባሉ ጸሐፊ ‘ደቦ ቅጽ-፩’ ከተሰኘው የ60 ደራሲያን ሥራዎችን ያካተተ መጽሐፍ ውስጥ ‘የሴትነት ጸጋ’ በሚል በጻፉት መጣጥፍ ሴትነትን ከፍቅር፣ ከጥበብ፣ ከብልሃትና ልዕልና ጋር አቆራኝተውታል። “ሴት ልጅ ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አልታዩኝም። የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የተረዳነው አይመስለኝም።… ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለሴት ልጅ የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንስብኛል” ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስለሴት ልጅ ጭቆና የታገለ እና ስለክብሯ የዘመረ ምሁር ነው። ስለሴት ልጅ ስቃይና ሰቆቃ አትቷል። ‘በናቴኮ ሴት ነኝ’ በሚለው መጽሐፉ ስንኞች እንምዘዝ! …. ግማሽ አካሏ ወንድ በትምክህት ቢከዳት ጧ! ብላ አለቀሰች አዛኝ ቢደርስላት፣ … ብሶት ተጫጭኗት ምንም ሰው አልሆነች በቀቢጸ ተስፋ ሕላዌንም ጠላች ያገሬ ጭቁን ሴት መድኅን መላ ያጣች….! ‘ሔዋንያት የትውልድ ፋብሪካዎች ናቸው፤ እነሱ ባይኖሩ ዓለም ባዶ ትሆን ነበር’ እንዲል ፈላስፋው ሶቅራጥስ። ስለሴት (ግማደ ሰቧ ፍጡር) ግፍና በደል ገሞራው እንዲህ ይላል። “መራራ ጭቆና በሰፈነበት ምዝብር ሕብረተሰብ ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ሔዋንያት ብሶታቸው፣ ፍዳቸው፣ በደላቸው፣ ጭንቀታቸውና መከራቸው እንደ ሰማዕታት ገድል እጥፍ ድርብ ነው…. አጉል ልማድ፣ ኋላቀር ባሕልና አድሃሪ ሕገ-ማኅበረሰብ ከከንቱ አስተሳሰቦች ጋር ተዳምሮ በአንድነት በመመሳጠር ዘርዓ ሔዋንን ሲጫወቱባቸው ሲያሾፉባቸው ኑረዋል” (ገጽ-23) በሥነ-ሕይወት ሳይንስና በትምህርተ-ጄነቲክስ (አካለ ሕላዌ) ሴቶችን ከወንዶች የሚያሳንስ ምንም አይነት አካላዊ ተሰጥኦ እንደሌለ ተረጋግጧል። ታሪክና ተረክ ግን ወገንተኛ መሆኑን ገሞራው ይናገራል። ተረክና ተረት አልባሌ ታሪክ የሚፈጥሯቸው አርበኞች ሁሉ በፆታቸው ተባዕት በመሆናቸው፤ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ሊኖራቸው የሚችለው ዕድገት ላይ ትልቅ ደንቃራ ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። “የታሪክን ሁኔታዎችን የመመንዘር ትርጓሜያዊ አንጻር የታሪክን ትዕይንቶች ብንመረምር አንደርድሮ የሚያደርሰን ሴቶች ከወንዶች የከፋ ባህሪያዊ ድክመት እንዳለባቸው ከሚያሳይ ሥዕል ላይ ነው።” በሚት(ተለጣጭ ተረክ) ላይ የሚራቀቁት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፎክለር መምህር) ‘ተረኮች እማዊ ሳይሆን አባዊ ናቸው’ በማለት ይህን ጉዳይ ያጠናክሩታል። “በሚት ውስጥ ገነው ከሚታዩ አበይት ማኅበራዊና ባህላዊ እውነታዎች መሃል አንዱ ፆታዊ ወገንተኝነት ነው። የሰማናቸው፣ ያነበብናቸው ሚታዊ ተረኮች በእጅጉ አባዊ ለሆኑ ሥርዓቶች (ፓትሪያርካል ሲስተምስ) ያደሩ፣ በአብዛኛው በተባዕት ተጋዳሊያን የተሞሉ ናቸው” ይላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ይሁኔ (በገፅ-401) ስለሰው ማንነት ቀረጻ በተመለከተ ከጥንት እስከ ዛሬ አከራካሪ የሆኑ ፈላስፎችን ክርክር ያነሳሉ። ይኸውም የሰው ልጅ ‘ማን ቀረጸኝ? ተፈጥሮ ወይስ ተሞክሮ?’ የሚለውን መከራከሪያ ጽንሰ-ሃሳብ ይፈትሻሉ። በዚህም “ሰዎች ሲፈጠሩ የሰውየውን ችሎታ ይዘው ነው” እና “የሰዎች ማንነት የሚቀረጸው ከውልደት በኋላ በተሞክሮ ወይም ከአካባቢ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ነው” የሚሉትን ሃሳቦች ወስደው ከእናት ሚና ጋር ያዛምዱታል። እናም እናት ‘በየትኛውም መደብ ልጅን አሳምራ ትቀርጻለች’ የሚል ድምዳሜ ሰጥተዋል። “በየትኛውም መንገድ በሰው ልጅ ላይ የእናት ቀራፂነት ስለሚኖር ከተጽዕኖዋ ማምለጥ የሚቻል አይመስለኝም።… አካባቢም ሰውን ይሰራዋል የሚሉትም ከውልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር የሚደረገው ውስብስብ መስተጋብር ‘ሰው’ በመሆን ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል” ይላሉ። በዚህ እሳቤ ሰው የወላጆቹም፤ የአካባቢውም ውጤት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን” ይላሉ። ሴቶች ከጥንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ማኅበረ-ባህላዊ እንዲሁም ለሰላምና ዕርቅ እሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው። ሴቶች ያልተሳተፉበት ዘርፍ የለም። ከመሪነት፣ ጥበበኝነት፣ ከአገር ድንበር ጠባቂነትና የዲፕሎማሲያዊ ሚና… መጥቀስ ይቻላል። ሴቶች በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ በሰላምና ግጭት አፈታት ግንባር ቀደም ተሰሚነት አላቸው። ለአብነትም ሀደ ሲንቄ፣ በሶማሌ-ሔር፣ በሲዳማ-ያካ፣ በራያ ማኅበረሰብ ዱበርቲዎች፣ በስልጤ-ሴረን ባህል መጥቀስ ይቻላል። ከሰሞኑ ባከበርነው የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሴቶች ውለታ በወፍ በረር ማውሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ ሴቶች ከሌላው ዓለም ሴቶች በተለየ የራሳቸው ቀለም ያላቸው፣ የአመራር ልምድ ያዳበሩ፣ የመወዳደሪያ ስነ-ልቦና ያላቸው፣ ችለው አሸንፈው ያሳዩ ናቸው። ሴቶች ድሉን በማስመዝገብ የተጫወቱትን ሚና ያህል፣ ገድላቸው በታሪክ በሚገባ አልተወሳም። ዶክተር አልማው ክፍሌ የተባሉ የታሪክ ምሁር በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ሲሉ ሰምቻለሁ። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች በርካታ ናቸው። ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡- “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችዎን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) ዶክተር ይሁኔ (በገጽ-14) በበኩላቸው እናቶችን ሩህሩሆች፣ አጉራሽና አልባሽ፣ የችግር ቤዛዎች፣ ሕይወት ዑደት አስቀጣዮች፣ የሕይወት መድኅኖች፣ ባለብዙ ጸጋዎች፣ መልካም ባህሪ አውራሾች፣… በማለት ገልጸውታል። መላ ሴቶችንም በእናቶች አተያይ ማየት እንደሚገባም እንዲሁ። “እናትነት መልካም ገጽታዎችን ደራርቦ የያዘ የሴት ልጅ ትልቅ መገለጫ ነው። እናትነት ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። እናትነት ጥልቅና ሰናይ ባህሪያት የሚፈልቁበት ምንጭ ነው። እናትነት የደግነት፣ የጥራት፣ የልህቀትና ተፈላጊነት ማሳያ ተምሳሌት ነው። እናትነት ሞት የማያደበዝዘው ኃያል መንፈስ ነው። እናትነት ከባድ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። … እናትነት የሰላም፣ የመልካም ግንኙነትና እንክብካቤ መፍለቂያ አድባር ናት። እናትነት ሰፊና ጥልቅ የሕይወት ትምህርት ቤት ነው። እናትነት ሌሎች ከስቃይ ነፃ እንዲሆኑ፣ ምቾት እንዲሰማቸው በሚደረግ ትግል ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ መኖር ነው” በመቀጠልም የኢትዮጵያ እናቶችን ‘ጠቃሚ ነገር ሰጪዎች’ ይላቸዋል። “እናቶች ሰው የመሆኛ ቅመሞች የሚጨለፍባቸው ባህር ናቸው። … ሕይወታዊ ስሪታችን ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የወሰደው ከእናት ነው። ከእናት የምናገኘው ‘ማይቶኮንድሪያ’ (ማይቶኮንድሪያ የኃይል ማመንጫ ክፍል ሲሆን የምንመገበው ምግብ እየተቃጠለና ወደ አስፈላጊው ኃይል እየተቀየረ ሕይወትን ያንቀሳቅሳል) የምግብ ማቃጠያ ምድጃ ወይም ኃይል ማመንጫ ቤት ሆኖ ያገለግላል። … ብዙ መልካም ስብዕና መገለጫዎች ምንጫቸው የእናት ፍቅር፣ የመልካም ስብዕና እና የርህራሄ ምንጭ ነው” (ገጽ- 61) ኢያሱ በካፋ ‘የኢያሱ በካፋ ወጎች’ በተሰኘው መጽሐፉ እናትነትን ማህጸንን፣ ምግብን፣ ትንፋሽን፣ ደም፣ ሥጋን እና ነፍስን ሰጥተው በረቂቅ ተፈጥሮ ሰውን ከመውለድ ባለፈ ፍቅራቸውን ዘላለማዊ ገደብ አልባ እና ዕልቆ-ቢስ እንደሆነ እንዲህ ገልጾታል። “እናትነት ነፍስን ማካፈል ነው፤ እናትነት የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር መስጠት ነው፤ እናትነት ከራስ ሕልውና ይበልጥ ለልጅ ማሰብ ነው፤ እናትነት ፍፁም ወረት አልባ መሆን ነው። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር አይነጥፍም፤ አይለወጥም። ለእናት ልጇ ሁሌም ልጇ ነው” (ገጽ-4) እናትነት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ፤ በውለታ ማካካስ ይከብዳል። የእናት ውለታዋን መክፈል የሚችል ልጅ የለም። የእናት ፍቅርን ለመግለጽም በርካቶች አንደበታቸው ይተሳሰራል፤ ቃላት ይነጥፍባቸዋል፤ ስሜታቸውን መግራት ይሳናቸዋል። ድምፃዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) ‘ይናገራል ፎቶ’ በሚል እናትና አባቱን በገለጸበት ሙዚቃ የመጨረሻው ማጠንጠኛው ‘እወድሻለሁ/እወድሃለሁ’ ያለው፤ እንዲሁም ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ‘እናት ውለታዋ’ በተሰኘ ዘፈኗ ውስጥ (ዜማና ግጥም ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ)፤ “ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ” እያለች በሚስረቀረቅ ድምጿ የምታንጎራጉረው ለዚህ ይመስላል። ዕውቁ የቋንቋ ሊቅ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) ‘የጥቁር አፈር ትሩፋቶች’ በተሰኘው መጽሐፉ (ገጽ-79) ‘መቀነትሽን አጥብቂ’ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ረዘም ያለ ግጥም ሁለት አንጓዎች ብቻ ስንመዝ የእናትነት ውለታን መመለስ እንደሚሳን፤ የእናትነት ግብሯ ‘እናት’ የሚለው ቃል በራሱ እንደሚያንስባት ያትታል። … “ለዚህ ወሮታሽ አጸፋ፤ እናት ይልሻል አገሩ፤ እኔም እናቴ ብልሽ መች ሊመጥንሽ ዳሩ። … እናትነት ምጡቅ ነው፤ እናት ከመባል ይልቃል፤ የግብርሽ ስንክሳር ዚቁ፤ በስያሜ መች ያልቃል”… በማለት ይገልጸዋል። መውጫ ዶክተር ይሁኔ የሴት እና እናትን የነገዋን መንገድ ከሳይንስ አተያይ አንጽረው፤ ከማኅበረ-ፖለቲካ፤ ከማኅበረ-ባህል ከፍታዋ አመሳክረው፤ እናትና ሀገርን መጋመድ አመስጥረው መልእክታቸውን እንደ መውጫ አስፍረዋል። ለስንበት አንድ አንቀጽ እንወርውር!! “የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። የሰመረ ትውልድ ሊቀጠል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው። የእናቶች አቅም ሲገነባ የራሳቸውን አቅም ያውቃሉ፤ ምርጫቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እንዲሁም ለሚመጣው ማኅበራዊ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ። ስለሆነም የእናቶችን አቅም ማጎልበት ትውልድን ማጎልበት ነው። እናቶች ላይ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት ነው”  
አድዋ የፓን አፍሪካዊነት እርሾ..
Mar 1, 2023 559
(አየለ ያረጋል) መንደርደሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የዛሬው አፍሪካ ሕብረት) ከተመሰረተ ዘንድሮ 60 ዓመታት ደፈነ። አፍሪካ ሕብረት በ2063 ለማሳካት ያቀዳቸው አህጉር አቀፍ ግቦች ትግበራ 10ኛ ዓመታት ሞልቶታል። 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባዔ 'የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን' በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱ በርካታ ፓን አፍሪካዊያን ዘንድ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል። ይሄውም የቀደምት አፍሪካዊያን ፖለቲካዊ ግቦች ወደ አፍሪካ አቀፍ ምጣኔ ሀብታዊ ሕልሞች ስኬት መንገድ ይመራል የሚል ብሩህ ተስፋ በማሳየቱ ነው። ቀደምት ፓን አፍሪካዊያን መሪዎች ሲሰባሰቡ አፍሪካን ከቅኝ ገዝዎች መንጋጋ ፈልቅቀው ነጻነቷ የተረጋገጠ፣ የዳበረችና ሕብረቷ የተጠበቀ አፍሪካን ዕውን ለማድረግ በመሻት ነበር። በዚህም ከአውሮፓዊያን ቅኝ ግዛት ቀድመው ነጻነታቸውን ያወጁ ሀገራት፤ ይህን ሕልማቸውን ዕውን ለማድረግ ድርጅት ሲጠነስሱ የሀሳብ ሜዳና መዳረሻቸው ኢትዮጵያ ነበረች። ለምን ቢሉ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻነት ዘፍጥረት ነጸብራቅ ናትና። ይሄ የሆነው ታዲያ በአድዋ እርሾ ላይ ተመስርቶ ነው። "አድዋ ድል የአፍሪካ ድል ነው። የኢትዮጵያ ትንሳኤ የአፍሪካ ትንሳኤ ነው" እንዲሉ የፓን አፍሪካዊነት አቀንቃኙ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት። አፍሪካ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መልከ ብዙ ፈተናዎች እየተናጠች ቀጥላለች። በየጊዜው ወደ አስከፊ ድህነትና ውስጣዊ መከፋፈል ቀውስ እያመራች ባለበት አሁናዊ መልኳ የአፍሪካ ሕብረት ህልሞች ይሳካሉ ወይ የሚለው የብዙሃኑ ስጋት ነው። እናም የፓን አፍሪካዊነት (Pan Africanism) እርሾ የሆነውን አድዋ ድልን ተጠቅሞ መነጋገር፤ የአፍሪካ እንጀራዋን መጋገርና ዕቅዷን መተግበር ሳያሻት አይቀርም። የአድዋ ድል የፓን አፍሪካዊነት እርሾነት (…) “አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲልአድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደልላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክልለዛሬም ታሪክ ነው፣ ‘ነገም ሌላ ቀን ነው’ ለሚል…”(ከደራሲና ጋዜጠኛ ነብይ መኮነን ‘ስውር ስፌት’ ከተሰኘው የግጥም መድብል የተቀነጨበ) የአድዋ ጦርነት ሰበብ የውጫሌ ውል ነው የሚለው ታሪካዊ ዕይታ ሰፊ ቦታ ይዟል። ዳሩ አሳማኙ የጦርነቱ መንስኤ ከውጫሌ ውል ይልቅ አፍሪካን በይፋ የመቀራመት ውሳኔ የተደረገበት በርሊን ጉባዔ ነው የሚል ምሁራዊ አተያይ አለ። ጉባዔው አፍሪካዊያንን ለዘመናት በባርነት ሲያግዙ የኖሩ አውሮፓዊያን አፍሪካዊያንን እንደ ሸቀጥ ከመጠቀም ባሻገር ሁለመና አንጡራ ሀብት ለመበዝበዝ የሜድትራኒያንን ባህር ተሻግረው አፍሪካን ለመቀራመት በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ያደረጉት ስምምነት ነበር። የኢትዮጵያ ዕጣም ለኢጣሊያ መንግስት ወጥቷል። አንዳንድ የታሪክ አተያዮች አጼ ዮሐንስ መተማ ላይ በተሰው በጥቂት ቀናት ልዩነት የተፈረመው የውጫሌ ውል ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዙፋን ከተረከቡ በኋላ ራሳቸውን እስኪያደራጁ ለጊዜ መግዣ ያደረጉት ውል እንጂ ጦርነቱ አይቀሬነት ንጉሱ መጠርጠራቸው አልቀረም ይላሉ። ለዚህ ደግሞ የአድዋ ጦርነት የተደረገው የውጫሌ ውል ከተፈረመ ከአምስት ዓመታት በኋላ መሆኑ፤ በርግጥም አድዋ ጦርነት የበርሊን ጉባዔ ውሳኔ ጦስ እንጂ የውጫሌ ብቻ አይደለም የሚለው ሃሳብ ገዥነት ይኖረዋል። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪ የአፍሪካ ቀን በተከበረበት በአንድ ወቅት "ከአድዋ ድል 11 ዓመታት ቀደም ብሎ በርሊን ላይ በተደረገው አፍሪካን የመቀራመት ጉባዔ፤ ከአድዋ ድል ማግስት ፉርሽ ሆነ። የበርሊን ጉባዔ ውሳኔ ወደ ግጭት እንዲያመሩ አደረጋቸው። አፍሪካ ቅኝ መገዛት አለባት የሚለውን እሳቤ ኢትዮጵያ በእምቢተኝነት ተቃወመች፤ በገቢርም አሳካቸው። ከተባበሩ ማንንም ሃይል ማሸነፍ እንደሚቻል ለአፍሪካዊያን ግልጽ መልዕክት አስተጋባች" በማለት አብራርተው ነበር። ቅድመ አድዋ የኢጣሊያን ጦር አዝማች ጄነራል ባራቴሪ ምኒልክን ጉሮሮውን አንቆ ወደ ኢጣሊያ ሀገር እንስሳት ማቆያ እንደሚያመጣው ለሀገሪቷ ምክር ቤትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ክሪስፒ ፊት ቃል ገብቶ ነበር። ከወራት በኋላ በተደረገው የአድዋ ጦርነት ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ነበር። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር አድዋ ላይ የሽንፈት ካባ ተከናንቦ ተመለሰ። ጀኔራል ባራቴሪም ‘ጽድቁ ቀርቶ በቅጥ በኮነነኝ’ እንዲሉ በጦርነቱ ተዋርዶ የጀኔራል መኮነንነት ማዕረጉ ተገፎ የተጠያቂነት ፍርድ ተፈረደበት። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ኤምሬትስ ፕሮፌሰሩ ባህሩ ዘውዴ በአንድ ወቅት የአድዋ ክብረ በዓል ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ “ጥቁር ሕዝቦች ከነጮች ጋር ያደረጓቸው ጦርነቶች ብዛት የትየሌለ ነው። አንድም ጦርነት ግን በነጮች ላይ ድል አልተጎናጸፈም፤ ከወርቃማው የአድዋ ድል በስተቀር” ማለታቸውን አስታውሳለሁ። በፕሮፌሰሩ አተያይ አድዋ አዲስ የታሪክ ምዕራፉ ሲከፍት በአንጻሩ ነባር አስተሳስብ ሰብሯል፤ የጥቁሮች የበታችነት ስሜትና የነጮች የበላይነት አስተሳስብ ለመጀመሪያ ጊዜ በአድዋ ተራሮች ግርጌ ተሽሯል። ፕሮፌሰሩ ‘ኢትዮጵያዊያን ለምን አሸነፉ’ የሚለው አመክንዮ ሲፈትቱም ቅድመ አድዋ ጦርነቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለልዩነት ህብረት መቆሙ፤ የአጼ ምኒልክ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት የነበረው የኢትዮጵያዊያን ታክቲካዊ የበላይነት እንደሆነ ይገልጻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአንድ ወቅት “ታሪክን ለሚመረምር ትውልድ ዓድዋ ውስጥ ሕልውናን አፅንቶ የመኖር፣ ዓድዋ ውስጥ ዲፕሎማሲ፣ ዓድዋ ውስጥ ወታደራዊ ስትራቴጂ፣ ታላቅ ውስጣዊ የሕዝቦች ኅብረትና አንድነት፣ ጥበብና ተግባቦት፣ ፍቅርና መስጠት፣ ክብርና ጀግንነት ሞልቶና ሰፍቶ የነበረ መሆኑን እናያለን” ብለው ነበር።የአድዋ ድል ቱርፋቶች መልከ ብዙ፣ ቀለመ ደማቅ፣ አድማስ ዘለል ናቸው። አድዋ አገራዊ፣ አህጉራዊና ሉላዊ እሳቤን ለውጧል። በዚህ ጽሁፍ ግን የአድዋ ድል ቱርፋትን ከፓን አፍሪካዊነት አተያይ እንቃኛለን። አድዋ ድል ከኢትዮጵያዊያን ባለፈ ለለቀረው አፍሪካ፣ ሰፋ ሲልም ለመላው ጥቁር ሰብዓ ዘር ምን ፈየደ፤ ምንስ አተረፈ፣ ለኋላው ፓን አፍሪካዊነት ምን አበርክቶ ነበረው የሚሉ ተጠየቆች ሲፈተኙ ለዛሬዋና ለነገዋ አፍሪካ የሚበጁ ቁም ነገሮችን ነቅሶ ማውጣት ይቻላል። የአሜሪካው ሞርጋን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ዶክተር ጌታቸው መታፈሪያ የአድዋ ድል “አንድም ቅኝ ገዥዎች ኃያልነታቸው በአፍሪካዊያን እንደሚፈተን የተገነዘቡበት፤ ሁለትም የአፍሪካ ዳያስፖራዎች የተስፋ ስንቅ የታጠቁበት ነው። ባርነት፣ ጭቆና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ብዝበዛዎች እልባት እንዲያገኙ ደወል አቃጭሏል። ልክ ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያዊያንን ካለአንዳች ልዩነት አሰባስበው ጠላትን ድል እንደነሱት ሁሉ አርቆ አሳቢ አመራር ካለ አፍሪካዊያን እኩልነት፣ ፍትሕና የህልም እንጀራ የሆነባቸውን ሁለንተናዊ አህጉራዊ ሠላም ማግኘት እንደሚችል ወኔ ቆሰቆሰባቸው” ብለዋል። ዕውቁ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት “የአድዋ ድል ዜና በአውሮጳ ኃያላን ዘንድ የጦር አደጋ ጋረጠ፤ ሮምን በመሰሉ የአውሮጳ ከተሞች የፖለቲካዊ ቀውስ ምጽዓት ቀረበ፤ የእንግሊዛዊያንን ሸውራራ እሳቤም በአንድ ሌሊት ቀየረ” ይላሉ። እንደ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ጥናት አድዋ ከትግል ባሻገር በደቡብ አፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ ‘ኢትዮጵያዊነት’ የሚል ሃይማኖት አስተምሮ እንቅስቃሴ ያስጀመረ ታሪካዊ ከስተትም ነው። በአድዋ ድል ማግስት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኢትዮጵያ ስም አያሌ አብያተ- ክርስቲያናት መታነጻቸውን ይዘረዝራሉ። ለአብነትም የተባበሩት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ተልዕኮ በደቡብ አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ፣ የቅዱስ ፍሊፕ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ የምህላ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ ሰብዓ-ገነት የእግዚአብሄር መመስገኛ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚሉት ይገኙበታል። በተመሳሳይ የሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር ሃሮልድ ማርክስ “ለጥቁር ዳያስፖራዎች የኢትዮጵያ ድል ጮራ የወቅቱ ክብርና ለነጋቸው የይቻላል መንፈስ ያስታጠቃቸው ልዩ ክስተት ሆነም” ይላሉ። ምዕራባዊያኑ በጥቁሮች ላይ ለዘመናት ያሳደሩትን ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ንቀት እንዲያጤኑ፤ ማድረጉን ይጠቅሳሉ። በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በበኩላቸው አድዋን ልዕለ አውራጃዊ ምልከታ፣ ልዕለ ዘውግ አስተሳስብ የታየበት የጋራ ነጻነት ዓርማ ሲያደርጉት፤ ዕውቁ የታሪክ ሰው ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦም አድዋን 'ኢምፔሪያሊዝምን ያሸነፈ ድል' በማለት ገልጸውታል። ‘የአድዋ ጦርነት’ በተሰኘው መፅሀፋቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰሩ ሬሞንድ ጆናስ አንዳንድ የምዕራባዊያን አገራት የአድዋን ድል ለማንኳሰስ ቢሞክሩም ሙከራው ወንዝ እንዳላሻገራቸው ይጠቅሳሉ። ‘ታሪክ የተለየ ክስተትን ይወዳል’ የሚሉት ፕሮፌሰሩ አድዋ ተለምዷዊ ጉዞ የቀየሰ፣ ነባር ንግርን የለወጠ፣ ለአፍሪካዊያን ቅኝ ተገዥዎች የራስ መተማመን ጉልበት ያጎናጸፈ፣ በአጠቃላይ አድዋን የታሪክ ዑደትን የጨዋታ ሕግ የቀየረ ዕውነታ አድርገውታል። ፕሮፌሰሩ አክለውም ከአድዋ ድል ቱርፋት ሀተታቸው አድዋ አፍሪካን በዝባዥ ወራሪ ሃይልን ያስተማረ፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች በመላው ዓለም በበረቱበት በዛ ወቅት አጼ ምኒልክ ለምርኮኞቻቸው ያሳዩትን ርህራሄና ህዝቡን አስተባብሮ የመምራት ብልሀተቻው የታየበት ከዚህም ባሻገር ግን ለአፍሪካውያን ብሎም ለአፍሪካ አሜሪካውያን የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ምልክት እና ለፓን አፍሪካን ራዕይ አቀንቃኞች ተምሳሌት ድል መሆኑን ጠቅሰዋል። የካናዳው ማክጊል ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ምሁር ዶክተር ሜማይሬ ሜናሴማይ፤ አድዋ የማይቻል መሰል እውነት በገሃድ የታየበት ሁነት ነው፤ አዲስ ፖለቲካዊ ተጠየቅ የፈለቀበት፤ ታሪካዊ አድማስ የተከፈተበትም ዕለት እንደሆነ የሌሎች ምሁራንን ሃሳብ ይጋራሉ። በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ፣ ባሕልና አወቃቀር ጥናታቸው በስፋት የሚታወቁት ፕሮፌሰር ዶናልድ ሊቨን የአድዋ ዘመቻ ድል ፍሬ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የሚሊዮን ጥቁሮች የኩራትና ወኔ ፏፏቴ ቅርስ እንደሆነ ይገልጻሉ። አድዋ ከአፍሪካዊያን ንቅናቄ መነሻነቱ ባሻገርም ለጥቁሮች መብት ታጋዩ ማርክስ ጋርቬይ “ኢትዮጵያ እውነተኛዋ የአባቶቻችን ምድር” በማለት ለ‘የምልሰተ አፍሪካ ንቅናቄ’ ቅስቀሳው ተጠቅሞበታል። እውቅ የጥቁር መብት ተሟጋቾች የሃይቲው ቤንቶ ሲልቫን፣ የምዕራብ ኢንዲያኖች ጆሴፍ ቪታሌን፣ እንዲሁም ቡከር ዋሽንግተን፣ ኢዳ ዌልስ፣ ዲ ቦይስ ‘የጺዮን ንጉስ’ ምልክት በማድረግ ለፀረ ቅኝ ግዛትና ዘረኝነት ትግል ቀስቅሰውበታል። በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ከነበሩ የአፍሪካና የላቲን አሜሪካ አገራት የነጻነት ታጋዮች መካከልም የናይጄሪያው ናምዲ አዝኪዌ፣ የጋናው ክዋሜ ንኩርማን፣ የኬንያው ጆሞ ኬንያታ፣ የጀማይካው ጆርጅ ፓድሞሬ በአድዋ ድል ዜጎቻቸውን በመቀስቀስና ከጎናቸው በማሳለፍ፣ ተከታዮችን አፍርተዋል። በአጠቃላይ ድሕረ አድዋ ድል ኢትዪጵያ ውስጥ ዘመናዊነት እንዲስፋፋ፣ የባቡር፣ ስልክ፣ ትምህርት፣ ፖስታ፣ ቴሌ፣ መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንዲዘረጉ፤ ኢትዮጵያ የትኛውም አፍሪካዊ አገር ያላገኘውን የራሷን የፖለቲካ ኢኮኖሚ እንድትመራ አስችሏታል። ታላቁ የአድዋ ድል ዘመናዊት ኢትዮጵያን ከጥንታዊ ታሪኳ ጋር ያዋደደ፤ የጥንቶቹን አባቶቻችን ጀግንነትና ለአገር ያላቸውን ፍቅር ያስመሰከረ፣ የነጻነት አይበገሬነት ወኔን ያሳዬ፣ የህዝቦች አንድነት ህያው ማሳያ ታሪካዊ ሁነት ነው። እናም አድዋ ለ’ፓን አፍሪካዊነት’ ጉዞ መሰረት ሆኗል፤ ቅኝ ግዛት እጣፈንታ አለመሆኑን አብስሯል። በርካታ የአፍሪካ አገራት ከቅኝ ግዛት ቀንበር ሲላቀቁ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማትን ተሻምተዋል። አድዋ በሌሎች አገሮች ሕዝቦች የነጻነት ትግል ተምሳሌት ሆኖ በተለይም የጥቁር ዓለም ህዝቦችን ያነሳሳ፣ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲቀነቀን ያስቻለ ድል ነው።ኃያላኑ የምዕራብ አገራት ኤምባሲዎቻቸውን በአዲስ አበባ ከፍተው ለኢትዮጵያ ነጻና ሉዓላዊነት ‘አሜን’ ብለው ዕውቅና ሰጥተዋል። በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ ፖሊሲያቸውን ጭምር እንዲመረምሩ አድርጓል። አድዋ ከድሉ ማግስት ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር መሆኗ እንዲረጋገጥ እና ድንበሯን እንድትካለልም አስችሏታል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች እንድትታወቅ፣ ዝናዋ እንዲናኝና እንድትከበር ምክንያት ሆኗል፤ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት እርሾ ሆኗል። በዲፕሎማሲ ማዕከልነት ረገድ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ትሆን ዘንድ አድዋ ወሳኙ እርሾ ነበር። ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር፣ ለተቀረው አፍሪካ የነጻነት ትግል ፋና ወጊ እንድትሆን በማድረጉ ትልቅ ሚና ነበረውና!! አፍሪካ ሕብረት እና ፓን አፍሪካዊነት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ1955 ዓ.ም በ32 ሃገራት አባልነት ተመሰረተ። በቅርቡ በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ግቢ የመታሰቢያ ሃውልት የቆመላቸው (በ32ኛው የሕብረቱ መሪዎች ጉባኤ ወቅት) ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴና ካቢኒዎቻቸው ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ትልቅ ሚና ነው። ሕብረቱ ንጉሰ ነገስቱ ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነት ላደረጉት ድጋፍና ለሕብረቱ መመስረት ለተጫወቱት ሚናን ታሳቢ በማድረግ መታሰቢያ ሐውልት አቁሞላቸዋል።የአፍሪካ ሕብረት የአህጉሪቷ ሁለንተናዊ ጉዳይ የበላይ ጠባቂ ነው። የፓን አፍሪካዊነት ውጤት የሆነው ይህ ተቋም ካሉት ተልዕኮዎች መካከል አህጉራዊ ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ማረጋገጥ ዕድገትና ብልጽግናን ማበረታታት ነው። በእስካሁኑ እርምጃው ለአህጉሪቷና ሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ደህንነትና ልማት አበርክቶቱ የሚተቸው ሕብረቱ በቅርብ ዓመታትም አፍሪካን ወደ በለጸገች አህጉር ለማሸጋገር የ2063 አጀንዳ ነድፎ ጉዞ መጀመሩ ይታወቃል። ይህን ሕልም ዕውን ለማድረግ “የሰላምና ደህንነት መዋቅሩን በበላይነት መምራት ይገባዋል” የሚሉ ወገኖች ግን ሕብረቱ ከአፍንጫው ሥር ያለውን ክፍለ አህጉራዊ ሰላምና ደህንነት መምራት ተስኖታል በማለት ይሞግታሉ። “ደጅ አስከባሪነቱን ተነጠቀ?” እንዴ ሲሉም ይጠይቃሉ።በአፍሪካ ጸጥታና ደህንነት ለማረጋገጥ መሪዎቹ በማህበረሰባቸው ውስጥ የፖለቲካን መነጣጠል ያጠበበ አካባቢ መፍጠር እንዳለባቸው ምሁራን ይመክራሉ። የምርጫ ኮሚሽኖችን በራስ ፍላጎት መቀየድ፣ በፓለቲካዊ ሐሳብ ልዩነቶች ሁሉን ማግለል ለአምባገነን መሪዎች መፈጠር ምክንያት ይሆናል። እናም በአህጉሪቷ የግጭት መንስኤ የሚያጠኑ ጠንካራ ተቋማት መገንባት አካታች ዴሞክራሲያዊ ምህዳር በመፍጠር አህጉራዊ ቁልፍ ጉዳዮችን ዕልባት ከተበጀላቸው የ2063 የአህጉራዊ መዋቅራዊ ሽግግር አጀንዳ ማሳካት ይቻላል። እናም የአፍሪካ መንግስታት ከህዝብ ጋር በተዋዋሉት ፖለቲካዊ ውል መሰረት በቅድሚያ መታደስ ያሻቸዋል። የወቅቱ ነባራዊ ሁናቴ የአፍሪካ ሕብረት ጸጥታና ደህንነቱን በበላይነት የመቆጣጠር ተስፋ ፓን አፍሪካን እንደ አካል ከመጠየቅ በላይ ይጠጥራል። የመሪዎች ጉባዔ እና ፓን አፍሪካዊነት የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ "የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን" በሚል መሪ ሀሳብ የካቲት 11 እና 12 በአዲስ አበባ ተደርጓል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ስለዘንድሮው ጉባዔ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግር ወጥታ ጉባዔውን በስኬት መስተናገዷ ብቻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት የተፈታበት መንገድ ኢትዮጵያ አሁንም የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ የመፍታት አርዓያነቷን ያሳዬ አጋጣሚ መሆኑን ጉባኤው በአድናቆት አውስቶታል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ በዘንድሮው መሪዎች ጉባዔ በኢትዮጵያ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ትልቅ አድናቆት የተቸረ እንደነበር ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የሰላም ሂደት ተሞክሮ በ2063 የአፍሪካ የልማት አጀንዳ ውስጥ አንዱ በሆነው የተኩስ ድምፅ የማይሰማበት አፍሪካን ዕውን የማድረግ ግብ ማሳያ መሆኑንም እንዲሁ። ኢትዮጵያ ተመራጭ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን ያሳየችበት፣ በአንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይሰራጩ የነበሩ የተዛቡ ዘገባዎች ትክክለኛ መልክ የያዙበት እንደነበር በመግለጫው ተወስቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመሪዎቹ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው ከ60 ዓመታት በፊት የአፍሪካን ትብብር ለማረጋገጥ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የመሰረቱ ቀደምት አፍሪካውያንን ራዕይ አድንቀው የአፍሪካን መፃኢ ዕድል ብሩህ ለማድረግ ከቀደምት አባቶች አንድነት መማር እንደሚያሻ የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴን ንግግር አውስተው ነበር። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የአህጉሪቱን ፈተናዎች በአፍሪካዊ ትብብር መቋቋምና መፍታት እንደሚቻል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጠቅሰዋል። በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ መጠየቃቸውና የዓለም አቀፉን ሚዲያ የተንሸዋረረ አተያይ ለመቀልበስ አፍሪካ አቀፍ ሚዲያ ማቋቋም እንደሚያስፈልጋት መጠቆማቸው ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ አምባሳደር ታዬ ያነሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጰያ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ መገንባቷ፣ ዘንድሮም ለመጀመሪያ ጊዜ የፓን አፍሪካ ጉባዔ ማዘጋጀቷ፣ የፓን አፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ መመስረት እንዳለበት መጠየቋም ሌላው የፓን አፍሪካዊነት መሪነቷን አሁኑም ማስቀጠሏን ማሳያ እንደሆነ አምባሳደር ታዬ ጠቅሰውታል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ አፍሪካ የሰላምና ፀጥታን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በመንግስታቱ ድርጅት በኩል በቂና ተመጣጣኝ የፋይናንስ ድጋፍ እንደምትሻ፣ የሰላም ማስከበር ስምሪቶች ስኬታማነት ፋይናንስና በጀት ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠውና እንደ ፀጥታ ምክር ቤት አፍሪካም የራሷ አቅሙ የጎለበተ ተቋም መገንባት እንደሚጠበቅባት፣ መፈንቀለ መንግስትን ጨምሮ ኢ-ሕገ መንግስታዊ አካሄዶችን ህብረቱ አሁንም በፅኑ እንደሚያወግዝ ጠቁመው ነበር። በአፍሪካ ግጭት አፈታት ሂደቶች ጥበብና ብልሃት ያላቸውን አፍሪካዊ ወጣቶችን ጨምሮ ሁሉንም ህብረተሰብ ክፍል ማሳተፍ፣ አሳቢያንንና ምሁራንን ጥምረት በመፍጠር ተግባርና ንድፈ ሀሳብን በማጣጣም ውጤታማ ስራ ማከናወንና ዲፕሎማሲያዊ ስራን ማፋጠን እንደሚያም እንዲሁ። በተመሳሳይ ከኢኮኖሚ አንጻር የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሾነር ዶክተር አቡ ዘይድ አማኒ ደግሞ በሃይል፣ በትራንስፖርትና በዲጂታላይዜሽን ረገድ አፍሪካን እድገት ለማሳለጥ ስርዎችን አንስተዋል። ለአብነትም በአፍሪካ ሁለንተናዊ ዕድቷን ለማረጋገጥ አፍሪካ አቀፍ አንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ እንዲኖርም ፍኖተ ካርታ መቀረፁን፣ ለአፍሪካዊያን ትስስር ለማሳለጥ በትራንስፖርት ዘርፍም በ35 ሀገራት የአንድ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መፈጠሩን፤ በዲጂታላይዜሽን በኩልም በሁለም መስክ አፍሪካ አቀፍ የጋራ ገበያ እንዲፋጠን የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። እነዚህ ተግባራትም ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ለማፋጠን የሚኖራቸውን ሁነኛ አስተዋጽኦ አብራርተዋል። በጉባዔው መዝጊያ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት እና ተመራጩ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የኮሞሮሱ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በሰጡት መግለጫ፤ በ2023 አፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸው ነበር። አፍሪካ ያላት የተፈጥሮ ሀብት ማልማትና የንግድ ትስስሯን በማጠናከር ሁለንተናዊ ልማቷን ለማረጋገጥ፣ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናውን ትግበራን ማሳለጥ፣ የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይሰማ ዘንድ በፀጥታው ምክር ቤት አባል እንድትሆን መጎትጎትን ጠቃቅሰዋል። አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየሰጠ ያለው የገንዘብ ድጋፍ ኢ-ፍትሃዊነት መስተካከል እንዳለበትም የሰራ ኅላፊዎቹ በተደጋጋሚ አንስተዋል። አፍሪካ ለነገዋ የአድዋ ድልን ፓን አፍሪካዊነት እርሾ ብትጠቀምስ ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲልነቷ በታሪክ መዛግብት ሰፍሯል። ለአፍሪካና ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክና ሥልጣኔ፣ ቅርስና ባህል፣ ነጻነትና መብት ያደረገችውን ተጋድሎ ጉምቱ ፓን አፍሪካዊያኑ ይስማሙበታል። ከደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እስከ ኦሊቨር ታምቦና ታቦ ምቤኪ፣ ከዚሙባቡዌው ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ እስከ ሴኔጋላዊው ሴዳር ሴንጎር፣ የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታና ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች ኢትዮጵያ ‘‘የአፍሪካ እናት” ሲሉ ደጋግመው ገልጸዋታል። ኔልሰን ማንዴላ የነጻነት ረጅሙ ጉዞ (Long Walk to Freedom) በተሰኘ ግለ ታሪካቸው ‘‘ኢትዮጵያ በልቤ ውስጥ ሁልጊዜም ልዩ ቦታ አላት፤ የፈረንሳይን፣ እንግሊዝንና አሜሪካንን በጥምር ከምጎበኝ ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ኢትዮጵያን መጎብኘት የበለጠ ይስበኛል፣ ትልቅ ደስታንም ይሰጠኛል” ብለዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የታሪክና የሥልጣኔ መሠረት ናት ብለው ያምናሉ። የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት እሁሩ ኬኒያታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢህ አህመድ በዓለ ሲመት ወቅት ‘‘ኢትዮጵያ የአፍሪካ እናት’ ብለዋታል። የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በአንድ ወቅት በአድዋ ድል ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው "የአድዋ መሬት የተቀደሰ ነውና ጫማዬ ላወልቅ ግድ ይለኛል" ብለው ነበር። አድዋ የአፍሪካ ቅዱስ መሬት፣ ለቅኝ ግዛት አቀንቃኞች ሃፍረት ምንጭ እንደሆነ አስረድተው ነበር። መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ሚድራድ ከተማ ያደረገው የፓን አፍሪካኒዝም ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፎርቹን ቻሩምቢራ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ሕብረት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞቾ ትግበራ መከታተልና የአፈፃፀም ክፍተቶችን መጠቆም፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የዴሞክራሲ ባህል ማጎልበት፣ የአፍሪካዊያን ድምፅ የሚሰማባቸውን የጋራ መድረኮች ማመቻቸትና ሀሳብ የማንሸራሸር ዕድል በመፍጠር የተሰበሰቡ ምክረ ሀሳቦችን ለሕብረቱ አስፈፃሚ አካል የማቅረብ ተልዕኮ ይዞ እንደሚሰራ ይገልጻሉ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአውሮፓዊያኑ 1963 ሲቋቋም ዋናው ዓላማው ፖለቲካዊ ትብብር እንደነበር ገልፀው፣ አሁናዊ አፍሪካውያን ግን ከፖለቲካው ባለፈ በመካከላቸው ኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያስፈልጋቸው ይጠቅሳሉ። ለዚህ ደግሞ ከቅኝ ገዥዎች አዕምሯዊ እስር ቤት ወጥተው በፖን አፍሪካዊነት እሳቤ መራመድ እንደሚገባቸው አንስተዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሀገራት ከቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ጉያ ከመርመጥመጥ፣ ባህልና ኩራታቸው ከቅኝ ገዥዎቻቸው እሳቤ ከመቅዳት በበይነ አፍራካ አካሄድ፣ በፓን አፍሪካዊነት መርህ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ያነሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓን አፍሪካ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በአፍሪካ ወጣት መሪዎችን ለማፍራትና ለፓን አፍሪካዊነት መጠናከር ዐይነተኛ ሚነ እንዳለው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያም ለፓን አፍሪካዊነት ማንሰራራት የነበራትን ታሪካዊ የመሪነት ሚና አሁንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠው ነበር። ፎረሙ የፓን አፍሪካ መንፈስ እና የአፍሪካ አንድነትን እንደ አዲስ ትንሳዔው እንደሚያበስርም እንዲሁ። ሀገራት ከሰው ሰራሽ መልክዓ ምድራዊ የወሰን ሃሳብ መስመሮች፣ ከርዕዮተ ዓለም አጥሮች ወጥተው የተባበረች እና የበገለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ አጀንዳ የሚቀርጽ፣ ተሻጋሪ ሃሳብ የሚያፈልቅ ችግር ፈች አፍሪካዊ ትውልድ መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪም የቀጣይ አፍሪካ መጻዒ ዕድልን በአድዋ ድል እርሾዎችን ተጠቅሞ መወሰን እንደሚያስፈልግ፣ የጥቁሮች አኩሪ ታሪኮችን ለትውልድ ማስተማር፣ ወጣቱን በፓን አፍሪካዊ ቅኝት መቅረጽ እንደሚያስፈልግ ይጎተጉታሉ። የአድዋ የኢትዮፐያ ትንሳዔ የአፍሪካ ትንሳኤ መሆኑን የገለጹትም ለዚህ ነው። “ኢትዮጵያዊያን እንዳደረጉት መላ ህብረተሰቡን ካንቀሳቀስን እናሸንፋለን። ግን ምን ያህሎቻችን የተማርን ሰዎች ስለ አድዋ እና ኢትዮጵያ ታሪክ እናውቃለን። በ2004 ሃይቲ 200ኛ 'ዓመቷን የነጻነት ቀኗን አክብራ ነበር። የሃይቲ ዜጎች ከአፍሪካ በባርነት የተወሰደዱ ሰዎች ናቸው። ሶስት ግዛተ አጼዎችን /ስርዓት መንግስታትን/ አሸንፈዋል። የብሪታኒያን፣ ስፔን እና በመጨረሻም ፈረንሳይን ሶስት ስርዓተ መግስታትን ያሸነፉ ጥቁሮች ታሪክ ነውና። ይህን ታሪክ መተረክ አለብን። በ18ኛው ክፍል ዘመን የሃይቱ፣ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የአድዋና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የደቡበ አፍሪካ አፓርታይድ ትግል የተገኙ ድሎች ታሪክ መንገር አለብን። እርስ በርስ የተሳሰሩ የአፍሪካዊያን የነጻነት ታሪኮች ናቸው። ትልቁ እንደ አህጉር ያለብን ከፍተት እኛ አፍሪካዊያን ወጣቶች ስለራሳቸው እንዲያውቁ እና እንዲነሳሱ ማስቻል ላይ ነው። ስለራሳቸው እንድንኮራና ስለማንነታቸው ያላቸው ስሜት በማነሳሳት አፍሪካዊያን ወጣቶች አህገሪቱ ሁለንተናዊ ሽግግር እንድታመጣ ማስቻል ይገባል። አድዋ ተጠቂዎች ሳይሆን አሸናፊዎች እንደምንሆን አሳይቶናል። አድዋን መዘከር የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው" ነበር ያሉት።
ትንታኔዎች
የአየር ንብረት ፋይናንስ-አፍሪካውያን ገፍተው ያልሄዱበት መንገድ
Feb 18, 2023 552
/በገዛኸኝ ደገፉ/ የአፍሪካ ቀንድ ከ40 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ አያቅም የተባለለትን የድርቅ አደጋ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊ ሆነዋል። የድርቁ አደጋ የከፋበት የአፍሪካ ቀንድ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ተሸክመዋል። በተጨማሪም የከተሞች መስፋፋትና የከተሜነት የኑሮ ዘይቤን እያስተናገደች ባለችው አፍሪካ የኃይል እጥረት፣ በቂ የመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ አለመኖር፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት፣ ሥራ አጥነት ብሎም የወንጀሎች መስፋፋት አሕጉሪቱን ክፉኛ እየፈተኗት ይገኛሉ። የገጠር መሬት ምርታማነት መቀነስ ከገጠር ወደ ከተማ ለሚደረገው ፍልሰት አንደኛው ገፊ ምክንያት ሲሆን ለመሬቱ ምርታማነት መቀነስ ሰበብ ተደርጎ በዋናነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት የሚወልዳቸው የውኃ ኃብት መቀነስና ለተከታታይ ዓመታት የሚዘልቁት የድርቅ አደጋዎች መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አወሳስቦታል። እንደ አህጉር ከ4 በመቶ ያነሰ የካርቦን ልቀት ያላት አፍሪካ 65 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ የችግሩ ቀጥተኛ ገፈት ቀማሽ መሆን ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከዚህ ችግር ሙሉ ለሙሉ መውጣት ባይቻልም ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ እንዲቻል አህጉሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ኃብትና ወጣት የሰው ኃይል በማስተሳሰር ለውጥ ማምጣት ግድ ይላታል። በአፍሪካ የማይቀረውን የከተሞች መስፋፋትም ሆነ የህዝቦቿን የመልማትና የመለውጥ ፍላጎት ማሟላት ካለባት የአየር ንብረት ፋይናንስን የበለፀጉ ሀገራት ገቢራዊ ሊያደርጉት ይገባል። የአየር ንብረት ፋይናንስ (Climate Finance) የአካባቢ፣ ብሔራዊ ወይም ድንበር ተሻጋሪ ፋይናንስን የሚመለከት ሲሆን ከሕዝብ፣ ከግል እና ከአማራጭ የገንዘብ ምንጮች የተውጣጣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው። የኪዮቶ ፕሮቶኮል እና የፓሪስ ስምምነት ደግሞ ሰፊ የገንዘብ አቅም ካላቸው አገራት አነስተኛ የኃብት አቅም ላላቸው እና ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ አገራት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ስምምነት ነው። ስምምነቱ “የጋራ ግን ደግሞ ልዩነት ያለው ኃላፊነትና አቅም” በሚለው መርህ መሰረት ያደጉ አገሮች አዳጊ አገራትን ለመርዳት የገንዘብ ምንጮችን እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። ፋይናንሱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ወሳኝ ድጋፍ እንደሚሆን ታምኖበታል። ምክንያቱም ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ላቅ ያለ የኢንቨስትመንት አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ። በተመሳሳይ ከአሉታዊ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች ጋር ለመላመድ እና ተለዋዋጭ ጫናዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። ከጥቂት አሥርት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተዘጋጅቶ የቀረበው የምእተ ዓመቱ የልማት ግብ ሰነድም ሆነ በቅርቡ በሚጠናቀቀው ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ለጉዳዩ ከፍ ያለ ትኩረት ቢሰጠውም እስካሁን ግን የፈየደው ነገር የለም። አፍሪካ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመላመድ ዓመታዊ 41 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ክፍተት ይገጥማታል። ይህን ክፍተት ለመሙላት አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለችው 36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ የአየር ንብረት ፋይናንስ ገቢራዊ ማድረግን ቀዳሚ ትኩረታቸው መሆን እንዳለበት የአንድ ዘመቻ (ONE Campaign) አጽንኦት ሰጥቶ ምክረ ሃሳቡን ሰንዝሯል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የአንድ ዘመቻ ዳይሬክተር ዶሪን ኒኒናሃዝዌ የአፍሪካ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመላመድ ፋይናንስ ድጋፍን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተጽዕኖ የመቋቋም አቅም እንዲገነቡ መክረዋል። አፍሪካ ባልፈጠረችው የአየር ንብረት ለውጥ ህዝቦቿ ለከፋ ጥቃት እየተዳረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች የበለጸጉ አገሮች የገቡትን የማላመድ ፋይናንስ ድጋፍ ቃል እንዲፈጽሙ ከማግባባት ባለፈ ማሳሰብ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይህ ማለት እኤአ ከ2020 እስከ 2025 በዓመት 100 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመተውን ግብ የማሳካት ተግባር የሚጠይቅ ነው። ከዚህ ባሻገር በቀጣዮቹ ዓመታት በተጨመሩ መዋጮዎች የሚስተዋሉ ጉድለቶችን መፍታት እና በግብጿ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ባስተናገደችው COP-27 ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ለመላመድ በእጥፍ ፋይናንስን የማቅረብ ቁርጠኝነት የማቅረቢያ ዕቅድ ሊነድፉ ይገባል ነው ያሉት። የአፍሪካ አገሮች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እና ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ጋር ሲታገሉ ቢቆዩም አሁን ላይ “አፍሪካ በአፈፃጸሙ ላይ መጠነኛ መሻሻል አሳይታለች” ብለዋል። እናም በ36ኛው የመሪዎቹ ጉባዔ የተገኙ ስኬቶች እና የጠፉ ዕድሎች እንዲሁም የድርጅቱን ዓላማዎች ለማሳካት በአየር ንብረት ፋይናንስ በጥልቀት መክረው ለተሻለ ስኬት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ በአየር ንብረት ምክንያት የሚፈጠሩ መፈናቀልን ለመግታት የተሻሻሉ የመላመድ እና የተጽዕኖ ቅነሳ ተነሳሽነት ገቢራዊ ለማድረግ በአገራት መካከል ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ያሰምሩበታል። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በተፈጥሮ ሃብት ላይ ኑሯቸውን መሰረት ባደረጉ ህዝቦች ላይ አውደ-ተኮር መላመድ እና የመቋቋም አቅም ግንባታ መፍጠር ይገባል። ለዚህ ደግሞ መላመድን የሚደግፉ ፋይናንስ ለማግኘት የሚረዱ መመሪያዎች ይበልጥ የተፍታቱ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ቪቶሪኖ ይሞግታሉ። ከ 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በተጓዳኝ በተካሄደው ከፍተኛ የውይይት መድረክ (High-Level Forum) ላይ ዳይሬክተሩ እንዳሉት በሻርም ኤል ሼክ በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ መላመድን፣ መከላከልን እና ዝግጁነትን ለማሻሻል ዓለም አቀፍ ትብብር ማጎልበት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አውስተዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ያወጣቸው የስምምነት ማዕቀፎች (United Nations Framework Convention on Climate Change (UNFCCC)) በርካታ ዝርዝርና ሚዛናዊ አካሄዶችን የያዙ ናቸው። ያም ሆኖ አተገባበራቸው እዚህ ግባ የማይባል በመሆኑ የሚታሰበውን ያህል ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቷል። በዚህም ቦረና ዞንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። የአየር ንብረት መዛባት፣ የሙቀትና የባህር ጠለል መጨመር፣ ጎርፍ፣ ድርቅ እንዲሁም ያልተገመቱ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማሙበታል። ዳሩ ግን አገራትን፣ አህጉርን፣ ዓለምን እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ግዙፍ ኩባንያዎችን ያስተሳስራል የተባለለት የአየር ንብረት ፋይናንስ በቅጡ ገቢራዊ ማድረግ ባለመቻሉ የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ በርካታ ህዝቦች ዳፋውን ለመጋፈጥ ተገደዋል። የአየር ንብረት ፋይናንስን በመተግበር በመስኩ የተጎጂዎችን ቁጥር ሊቀንሱና የዓለምን ሥነ-ምህዳር ከተቻለ ወደ ቀድሞው ሊመልሱ አሊያም አሁን ባለበት አረጋግተው ሊያቆዩ የሚያስችሉ በርካታ አማራጮች ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል። ለአብነትም ለድሃ ሃገራት አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተገቢውን ዋጋ በመክፈል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን እንዲቋቋሙ ማድረግ ከአማራጮቹ መካከል አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለሚያስወግዷቸው በካይ ጋዞች ተመጣጣኝ የጤና ሥርዓት በመዘርጋት የታዳጊ ሃገራት ዜጎችን የጤና አገልግሎት ማሻሻል ሌላው አማራጭ ነው። የተፈጥሮ ኃብቶችን የሚጎዱ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተፈጥሮን በሚንከባከቡ ዘዴዎች መተካት እንዲሁም ብክለትን የሚያስቀሩ የምርት ሂደቶች መለማመድ ጥቂቶቹ የመፍትሄ አማራጮች ተደረገው የሚወሰዱ ናቸው። በፓሪስ ከተደረሰውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ቀደም ብሎ በፈረንጆቹ 1994 ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (Global Environment Facility-GEF) COP-16 ዓለም አቀፍ ጉባዔ በኋላ በ2010 አረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund-GCF) እንዲሁም በ2001 ደግሞ ልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (Special Climate Change Fund-SCCF) እና የመላመድ ፈንድ (Adaptation Fund-AF) የተባሉ ማዕቀፎች የተዘጋጁ ቢሆንም ስለጉዳዩ የሚያስረዱ ተከታታይ ስብሰባዎች ከማዘጋጀት በዘለለ ብዙ ርቀት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። በቅርቡ በአለም ባንክ አሰባሳቢነት በኬንያ ናይሮቢ ተዘጋጅቶ በነበረው የአህጉሪቱን መሪዎች ባለሃብቶችንና ምሁራንን ባካተተውና “One Planet Summit” በተሰኘ መሰል ጉባዔ ላይም አፍሪካውያን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚገጥማቸውን ችግሮች ተከላክለው ሁለንተናዊ ዕድገታቸውን እንዲያፋጥኑ ካስፈለገ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ አዘጋጅተው መተግበር እንደሚኖርባቸው መግባባት ላይ የተደረሰ ቢሆንም አሁንም ጥያቄ ያስነሳው አፈጻጸሙ ስለመሆኑ ብዙ ተብሎለታል። ክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ የተባለ ድርጅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያመለክተው አፍሪካ እንደ ፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር ከ 2020 እስከ 2030 ባሉት አሥር ዓመታት 2 ነጥብ 8 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር አሊያም በየዓመቱ ከ2 መቶ ሃምሳ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያስፈልጋት ሲሆን አህጉሪቱ ከዘርፉ እያገኘችው ያለው ገንዘብም ከሚያስፈልጋት 12 በመቶውን ወይም 30 ቢሊየን ዶላር ብቻ ስለመሆኑ አስነብቧል። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ተቋቁመው ሊሰሩ የሚችሉ በርካታ ተግባራት እንዳሏት የሚያትተው ሪፖርቱ ከአየር ንብረት ፋይናንስ የሚገኘው ገንዘብ በትራንስፖርት፣ በኃይል ልማት፣ በኢንዱስትሪ ብሎም በግብርና፣ በአፈርና በደን ኃብት አጠቃቀም ውጤታማ በሆነ መንገድ ከዋለ የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ኃብቶች መንከባከብ ከማስቻሉም ባለፈ ላቅ ያለ ፋይዳ ይኖራዋል ብሏል። ይህ ሲሆን የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ ለአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖው ያስረዳል። ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራን የማስፋፋትና የተጎዱ አካባቢዎችን የማከም ሥራ እንዲሁም አይቀሬ የሆኑትን ከተሜነትና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ታሳቢ ያደረጉ የአየር ንብረት ፖሊሲዎች ተግባራዊ መደረጋቸው ለአፍሪካ ሃገራት እየፈጠረው ያለው በጎ ተጽዕኖ በግልጽ እየታየ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ጥረት ግን በአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲደገፍ አገራዊና የተቀናጀ አሕጉራዊ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። ከአጠቃላይ የአፍሪካ አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ግብጽ ብቻ 151 ቢሊየን ዶላር ከአየር ንብረት ንብረት ፋይናንስ ማግኘት እንደሚኖርባቸው የክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ ሪፖርቱ ይገልጻል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በመጭው የCOP-28 ጉባዔ የራሷንና የአፍሪካን ፍላጎት የሚያስጠብቁ የፋይናንስ ትልሞችን የመንደፍ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ የ COP-27 ጉባዔ ለአፍሪካ ያስገኘውን ውጤት እና አንድምታ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የመሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አስተባባሪ በሆኑት በኬንያው ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት በኅብረቱ የአዲስ አበባ ጉባዔ ላይ በጥልቀት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል። እዚህ ላይ ኢትዮጵያ ጥረቷን የሚያጎለብት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ጠንካራ ተሳትፎ ልታደርግ ይገባል። የአፍሪካ አገራት ገፍተው ረጅም ርቀት ያልሄዱበት የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ሌሎች የድጋፍ አማራጮችን በፍትሃዊነትና በምክንያታዊነት በመጠቀም የአየር ንብረት ተጽዕኖን የሚቋቋሙበት ጠንካራ አቅም ሊገነቡ ግድ ይላቸዋል። በእርግጥም አፍሪካውያን መሪዎች በሚያደርጉዋቸው ስብሰባዎች በየማዕዝናቱ በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጦት የተዳረጉ ህዝቦቻቸውን የሚታደጉበት ሁነኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበትን ዘዴ ነድፈው ረጅም ርቀት ሊጓዙ ይገባል። ”
ዛሬ የሚጀመረው 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል
Feb 18, 2023 516
"የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መቀላጠፍ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የዘንድሮ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ወደ ሥራ የገባውንና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ሕዝብ በንግድ ለማስተሳሰር የታለመውን የንግድ ቀጣና ይበልጥ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራል። በተለይም ደግሞ የጋራ የጉምሩክ ሥርዓትና ወጥ የታሪፍ አስተዳደር በአህጉሪቷ ለመተግበር ትኩረት ይደረግበታል ተብሏል። ሌሎችም የእርስ በርስ የንግድ ግንኙነትን የሚያቀጭጩ አሰራሮች ነቅሶ በማውጣት የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት ለመፍጠር ምክክር አድርገው አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል። የአፍሪካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ እንዲሁም በዩክሬንና በሩስያ ጦርነት ምክንያት አደጋ ላይ የወደቀው የአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ችግር እልባት በሚሰጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሏል። በተለይም ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና ሥራ ለማሳለጥና በአህጉሪቱ ዘመናዊ የእርሻ ሥራ በሚስፋፋባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል። ይህም በዘላቂነት የአህጉሪቱን የምግብ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል ተብሏል። በመሆኑም የዛሬው ጉባዔ ትኩረቱ በዚሁ የምግብ ዋስትና ሁኔታ ላይ እንደሚሆን ብዙ ግምት ተሰጥቶታል። የአፍሪካ የ2063 አጀንዳ አፈጻጸም ባለፉት አሥር ዓመታት በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የተጣለውን የረዥም ጊዜ ዕቅድ ከግምት በማስገባት የተሰሩ ሥራዎች ይገመግማል ተብሏል። ለቀጣይ አሥር ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚችሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጎ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ ዋና ዋና የሚባሉ ስኬቶችን በመገምገምና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት መጪውን አሥር ዓመት የተሻለ ለመፈጸም የሚያስችል የትግበራ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል። ከዚህም ባሻገር አፍሪካ በፋይናንስ ራሷን እንድትችል እየተደረገ ያለውን ጥረትም ትልቅ ሥፍራ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። ለአብነትም የኅብረቱ ሰላም ፈንድ የሚደረገው የአባል አገራት መዋጮና አገራት ከታክስ ገቢያቸው ለኅብረቱ በማዋጣት አጠቃላይ የኅብረቱን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውም ጉዳይ ምክክር ሊደረግበት የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በቻድ፣ በካሜሮን፣ ኒጀር፣ በናይጄሪያ አካባቢው ከጽንፈኝነት ጋር በተያያዘ በርካታ የጸጥታ ችግሮች እየተከሰቱ ሲሆን ይህም ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍልም የትጥቅ ትግል መቀስቀሱ የተዘገበ ሲሆን ይህም አገሪቱን ከሚያዋስኑ አገራት ጋርም አለመረጋጋት ፈጥሯል። በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው የጸጥታ ችግርም አሁንም እልባት ያላገኘ ጉዳይ ነው። ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ሂደት ላይ ናቸው፤ ሱዳን ሕዝባዊ አስተዳደር ለመመሥረት የሽግግር ትግበራ ላይ ናት። በመሆኑም የአፍሪካ ኅብረት በእነዚህና በሌሎች የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ - የአፍሪካ የዘመናት ፈተና
Feb 13, 2023 522
በረከት ሲሳይ በርካታ የአፍሪካ አገራት ነፃነታቸውን ከተቀዳጁበት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስካሁን እልባት ካልተገኘላቸው አፍሪካዊ ጉዳዮች መካከል ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አንዱ ነው። ለዚሁ ጉዳይ በርካታ መነሾ ቢኖሩትም ቅኝ ግዛቱ የፈጠራቸው ፖለቲካዊ ስንጥቃቶች፣ ድህነትና ሌሎች ማኅበራዊ ምስቅልቅሎሽ ለእነዚህ የጸጥታ ችግሮች በአብዛኛው የሚነሱ ምክንያቶች ናቸው። በአህጉሪቱ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት መቋጫ በሌለው መልኩ እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶችና ጦርነቶች ለአያሌዎች ሞትና የአካል ጉዳተኝነት ለገሚሱ ደግሞ ለዘመናት ከኖረበት ቀዬ እንዲሰደድ ምክንያት ሆነዋል። በብዙ ጥረት የተገነቡ መሰረተ-ልማቶች ወደ ፍርስራሽነት እንዲለወጡና በሂደት ላይ ያሉ የዘመናዊ አገር ግንባታ ሂደቶች እንዲስተጓጎሉና በፈተናዎች እንዲታጀቡ አድርጓል። ይህንኑ ኢኮኖሚያዊ ኪሣራ በሚያሳይ መልኩ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ከሁለት ዓመታት በፊት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ በአፍሪካ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች በየዓመቱ የአገራቱን አጠቃላይ አገራዊ ምርት (ጂ ዲ ፒ) እድገት ከ4 በመቶ እስከ 6 በመቶ እንዲቀንስ ያደርገዋል ይላል። በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚው ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ተጽዕኖ ዓመታትን የሚዘልቅ በመሆኑ ተደራራቢና ድግግሞሽ ያሏቸው ችግሮች እንዲበራከቱ በር ከፍቷል። በእነዚህ ድርብርብ ውጥንቅጦች በአህጉሪቱ በከባድ ድህነት የሚኖሩ ዜጎች ህይወት ይበልጡኑ እንዲወሳሰብባቸውና ለከፋ ማኅበራዊ ችግር እንዲጋለጡ እያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ የጸጥታ ችግሮች በአፍሪካ ሳያባሩ መቀጠላቸው ዛሬም ጉዳዩን በአንክሮ እንድንመለከተው ያስገድደናል። ይህንን በሚያስረግጥ መልኩ ያለፈው የፈረንጆች ዓመት (2022) ግጭቶች የተስተዋሉበት ዓመትና በዘንድሮ ዓመት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ተመላክቷል። በሰላም ስምምነት የተቋጨውን በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ጦርነት ጨምሮ እስካሁን እልባት ያልተገኘላቸው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ችግሮች ተጠቃሽ መሆናቸውን ነው የአፍሪካ የደኅንነት ተቋም ሪፖርት የሚያሳየው። ከዚህ ጎን ለጎን በሳሀል፣ በቻድ ሃይቅ ሸለቆ፣ በምስራቅ አፍሪካና በሰሜን ሞዛምቢክ ጸጥታን የሚያውክ የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ መኖሩንም አመላክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን በቡርኪና ፋሶ፣ በጊኒ፣ ማሊ፣ ሱዳን፣ ቻድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጅቡቲ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማዳጋስካርና ኒጀር የተሳካና ያልተሳካ የመፈንቅለ-መንግሥት (ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ) ሙከራ መካሄዱንና የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደተስተዋለባቸው ነው ሪፖርቱ ያወሳው። መንግሥታዊ የአስተዳደር ግድፈቶች፣ ምርጫን ተከትሎ የሚቀሰቀስ አለመግባባትና ሌሎችም በአህጉሪቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት የተከሰቱ የጸጥታና የደኅንነት ችግሮች ለተያዘው የፈረንጆች ዓመትም ትልቅ ሥጋት መሆኑን ነው ያነሳው። አፍሪካ ኅብረት በበርካታ አገሮች የጸጥታ ችግሮች እንዲቆሙና እንዲረጋጉ በማድረግ አዎንታዊ ሚና መጫወቱ ተገልጿል። ለአብነትም በኢትዮጵያ በዘላቂነት ግጭትን ለማቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠቃሽ ሲሆን በሌሎችም አገራት ወደ ተሻለ ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲመጡ ትልቅ ሥራ ሰርቷል። ይህም ሆኖ አሁንም ድረስ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ በኩል በርካታ ሥራ እንደሚቀር ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ በምዕራብ ሳሀል ያለው ከአልቃይዳና ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ጽንፈኛ ቡድን በአካባቢው የፈጠረው አለመረጋጋት፣ ከማሊ የፈረንሳይ ጦር መውጣትና ማሊ ራሷ ከሳሀል ቡድን አምስት የጸጥታ መዋቅር መውጣቷም ሌላው የአህጉሪቷና የአካባቢው ራስ ምታት ሆኗል። የቻድ ሃይቅ ሸለቆ አካባቢ (በኒጀር፣ ቻድ፣ በካሜሮንና ናይጄሪያ) የሚስተዋለው የቦኮሃራምና ሌሎች የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ፣ በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ራሱን ኤም23 በማለት የሚጠራው ቡድን ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ጦር መማዘዙ እንዲሁም በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው በመንግሥትና በተቃዋሚ መካከል የተቀሰቀሰው የሽምቅ ውጊያ አሁንም አለመቆሙ፤ የአፍሪካ ኅብረት ጸጥታን በተመለከተ በዚህ ዓመት ትኩረት ሊያደርግበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው የእንግሊዙ ቻም ሃውስ የተሰኘው የጥናት ተቋም መረጃ የሚያመለክተው። በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በተለያዩ ደረጃ የሚካሄዱ 17 ብሔራዊ ምርጫ መኖራቸውንና ይህንንም ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የድኅረ-ምርጫ ፖለቲካዊ ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ አፍሪካ ኅብረት አዎንታዊ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበትም ተመላክቷል። የአፍሪካ ኅብረት ቀጣይ አቅጣጫስ? አፍሪካ ኅብረት በበርካቶች አይን ሲታይ ምንም እንኳን የፖሊሲና የስትራቴጂ ችግር ባይኖርበትም ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ተስተውሎበታል። ለዚህም ተቋሙ ካለበት የፋይናንስና ሌሎች ተያያዥ የቴክኒክ ችግሮች በተጓዳኝ በዋነኛነት አባል አገራት በኅብረቱ ቻርተር በመመራት ረገድ በርካታ ክፍተቶች መኖራቸው መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይም በጸጥታና ደኅንነት ምክር ቤት በኩል የሚወስናቸው ስምምነቶች ገቢራዊ አለመሆናቸው ትልቅ ክፍተት ሲሆን ምክር ቤቱም በቅርቡ ያደረገው ስብሰባ ይህንኑ አጋልጧል። ይህም አፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አመላክቷል። ለአብነትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የጥይት ድምፅ የማይሰማባት አህጉር ለመፍጠር ያቀደው ዕቅድ ምንም እንኳን ዕቅዱ ከጅምሩም ቢሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታና የግጭቶች የመስፋፋት አዝማሚያ ከግምት በማስገባት ሊሳካ እንደማይችል በርካታ የመስኩ ተንታኞች ቢናገሩም ኅብረቱ በዚህ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አልቻለም። ለዚህም ደግሞ በቀዳሚነት ምንም እንኳን የአባል አገራት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ትልቁን ድርሻ ቢይዝም የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ነው የሚያሳዩት። በአፍሪካ በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎች በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል። በተለይም ደግሞ አፍሪካ ኅብረት በቅርቡ ዳግም የከለሰውን በአህጉሪቱ የጥይት ድምፅ ለማጥፋት የወጣውን ፍኖተ- ካርታና እንዲሁም የክትትልና የግምገማ ማዕቀፍ ፈጥኖ ወደ ሥራ ማስገባት ይኖርበታል። ይህንንም ተከትሎ በጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤቱ ያቋቋመውን የባለሙያዎች ቡድን የያዘ ማዕቀብ ለመጣል የሚሰራው ንዑስ ኮሚቴም በአግባቡ መጠቀም አለበት። አሁን ላይ በአህጉሪቱ ለጸጥታ መስፈን ሥጋት በሚሆኑና በሚያቆጠቁጡ ጉዳዮች ላይ እልባት ለመስጠት መረባረብ እንዳለበት ነው የሚጠቀሰው። በተመሳሳይ የሚወስዳቸው እርምጃዎችም በባህሪያቸው ተከታታይነትና ወጥነት ያላቸው እንዲሁም ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ሳይሆን ከመፈጠራቸው በፊት አስቀድሞ መከላከልና ማክሸፍ ላይ ሊረባረብ እንደሚገባ ነው የሚያነሱት። ከዚህ በተጓዳኝ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችሉ የአገራትን የፖለቲካ እንቅስቃሴ መደገፍና በዘላቂነት ዴሞክራሲ ባህል እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎችን መደገፍ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። በተለይም ደግሞ ወጣቶችን ያሳተፉ የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎች በስፋት መሠራት እንዳለበት ነው የሚጠቀሱት። ከዚህ ጎን ለጎንም የአፍሪካ የእርስ በርስ መገማገሚያ መድረክም (ፒር ሪቪው ሜካኒዝም) በተለይም መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲጎለብት በማድረግ ረገድም አበርክቶው ከፍ እንዲል መሠራት ይጠይቃል። የሰላም ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የሰላም ፈንድም ማሰባሰብ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ላይ የሰላም ፈንዱ አጠቃላይ ገቢ 328 ሚሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 22 አባል አገራት ሙሉ በሙሉ እንዲሁም አምስት አገራት ደግሞ በከፊል የሚጠበቅባቸውን መዋጮ አዋጥተዋል። በሌላ በኩል 28 አባል አገራት ደግሞ መዋጮውን መክፈል አለመቻላቸውን ነው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ሪፖርት የሚያመለክተው። በመሆኑም አፍሪካ ኅብረት አባል አገራት የሚያዋጡትን ገንዘብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጨርሱ ቅስቀሳ ማድረግን በአፍሪካ ጥላ ሥር በተለያዩ አገራት የሚያንቀሳቅሰውን የሰላም ሥራ ውጤታማ ማድረግ ይገባዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተ.መ.ድ) የጸጥታ ምክር ቤት ጉዳይ ላለፉት 15 ዓመታት በአፍሪካ መሪዎች በስፋት የተቀነቀነው አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል የሚለው ጉዳይም አፍሪካ ኅብረት በዘንድሮ ጉባዔው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት አፍሪካን የተመለከቱ መሆናቸውና ይህም ሆኖ በምክር ቤቱ ውስጥ አፍሪካ አለመወከሏ የፍትሃዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል። በርካታ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም ኅብረቱን በሊቀ-መንበርነት የመሩት እስከ ወቅቱ ሊቀ-መንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ድረስ ጥሪያቸውን በተለያዩ መድረኮች አሰምተዋል። አሁን አሁን ላይም ጥያቄውን ምንም እንኳን የሩቅ ምስራቆቹ ጃፓንና ቻይና እንዲሁም ሕንድ አስቀድመው ቢቀበሉትም በተለይም አንዳንድ የምዕራብ አገራት ያሏቸውን የሃሳብ እቀባ በማንሳት ጉዳዩን እንዲጋሩት በማድረግ አፍሪካ ትልቅ ስኬት አግኝታለች። ይህም ሆኖ አሁንም አፍሪካ ስንት መቀመጫ ይኑራት? እንዲሁም ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ይሰጣት ወይስ አይሰጣት? የሚለው ጉዳይ ላይ ክርክሮቹ እንደቀጠሉ ነው። በዘንድሮ ጉባዔው ኅብረቱ በእነዚህ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚደረስበትን ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንንም ማድረግ ከተቻለ በአፍሪካ ቀደምት መሪዎች ሲቀነቀን የቆየውን "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች" የሚለውን ብሂል እውን ለማድረግና አህጉሪቷ ላይ ዘላቂ ሰላምና ደኅንነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ አዎንታዊ አበርክቶ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ጠንካራ አንድነት - ለዘላቂ ሰላም መሰረት!
Feb 3, 2023 467
በእንግዳው ከፍያለው (ባህር ዳር ኢዜአ) በረጅም እንጨት ጫፍና ጫፍ በገመድ ታስረው የተንጠለጠሉ ቋጠሮዎችን ተሸክማ ከጓደኞቿ ጋር ገበያ እየሄደች ነበር የተገናኘነው። ወጣት ማሪማ ሜካ ትባላለች፤ ዕድሜዋ ከሃያ ዓመት አያልፍም። በእንጨቱ አንደኛው ጫፍ 10 ሊትር አረቄ የያዘ ጀሪካን፤ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ሌላ ቋጠሮ በማንጠልጠል ተሸክማለች። ሸክሙን በትካሸዋ ላይ ጣል እድርጋ ፈጠን እያለች ስትራመድ ላየ በፊቷ ላይ አንዳች የብርታትና የጽናት መንፈስን ያነባል። እንደእኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው “ሴት ልጅ እንዴት ይህን ያህል ክብደት ተሸክማ ትጓዛለች?” ብሎ ራሱን ሊጠይቅ ይችላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዋ ወጣት ማሪማ ግን ሸክሙ እንደ ኩበት ቀሏት ይሁን ጽናቱን ፈጣሪ ሰጥቷት ባላውቅም በደስታ ወደ ፊት መራመዷን ቀጥላለች። “የኛ ችግር የምንይዘው ሸክም ሳይሆን የጸጥታ ስጋት ነበር” የምትለው ወጣቷ ባለፉት ዓመታት በኛ ላይ የደረሰው አስከፊ ሰቆቃና መከራ ለጠላትም እንዲገጥመው አልመኝም በማለት ትናገራለች። ባለፉት ዓመታት በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ሲከሰት የነበረው ግጭት የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለሞት፣ ለስደት፣ ለንብረት መውደም እንዲሁም ለተለያዩ ችግሮች ዳርጓቸው መቆየቱ የቅርብ ትውስታ ነው። አካባቢው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገነባበት፣ ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት፣ የስኳር ፕሮጀክቶችና ሌሎች የኢንዱስትሪ ልማቶች ያሉበትና ለመተግበር የታቀደበት በመሆኑ የውጭ ሃይሎች ግጭት እንዲነሳ እጃቸውን ሊያስገቡ እንደሚፈልጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ወጣት ማሪማ ግጭት በተከሰተባቸው በነዚያ አስከፊ ጊዜያት የነበረውን ሁኔታ፣ የደረሰውን ጉዳት፣ በተከፈለው መስዋዕትነት የመጣውን ሰላም በሚያስታውስ የተስፋ ስሜት "ጸረ ሰላም ሃይሎች ያስነሱት ግጭት ለዘመናት በአንድነት የኖረውን የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ተስፋ አጨልሞት ነበር፤ በሰላም እጦት ሁሉም ህዝብ ጫካ ገብቶ ኑሮውን ከዱር አውሬ ጋር ያደረገበት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው" ትላለች። በአሁኑ ወቅት ጸረ ሰላም ሃይሎችና ተባባሪዎቻቸው የፈጠሩት ሰው ሰራሽ ችግር ሊፈታ መቻሉ እፎይታን መፍጠሩን ትገልጻለች። በወቅቱ ሕክምና፣ መድሃኒትና ሌሎች የጤና መጠበቂያ ቁሶች ባለመኖራቸው ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በወባ እና ሌሎች በሽታዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች እንዳሉ በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላትና ሰላም ፈላጊ የአካባቢው ተወላጆች ከመንግሰት ጋር በመሆን ባደረጉት ጥረት የነበረው ግጭት ተወግዶ በአካባቢው ሰላም ሰፍኗል። ይህም ለማሪማና ለአካባቢው ነዋሪዎች እፎይታን በማጎናጸፉ በጣም ደስተኛ ናቸው። የተገኘውን ሰላም ተከትሎ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ ተነስታ በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ በመምጣት ለመገበያየት በቅታለች። ከጓደኞቿ ጋር ከቻግኒ ከተማ የሚፈልጉትን ገዝተው ወደ አካባቢያቸው ወስደው በትርፍ ለመሸጥ ምቹ ሁኔታም ተፈጥሮላቸዋል። በቻግኒ ከተማ የቅዳሜ ገበያ የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ። በርበሬ፣ የተለያዩ የጥራጥሬ፣ የቅባትና የአገዳ ምርቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ። አልባሳት፣ የሴቶች ጌጣጌጥ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች እንዲሁም ሌሎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች ንግድ ልወውጥ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗን በነበረኝ የአጭር ጊዜ ቆይታ አስተውያለሁ። ገበያተኛው የተፈጠረውን ሰላም በማጣጣም ላይ መሆኑን በገበያው ውስጥ ከሚያሳየው መስተጋብር መረዳት ቀላል ነው። እኔም ይሄን በተደጋጋሚ ታዝቢያለሁ። ከህዝቡ ፊት ያነበብኩት በግጭቱ የተነሳ በደረሰው ችግር ምክንያት ቁርሾና ቂም በቀል ውስጥ መግባትን ሳይሆን የሰላምና እርስ በርስ መዋደድና የመደጋገፍ ስሜትን ነው። ይሄን ደግሞ በቻግኒ ከተማ በሚካሄደው የቅዳሜ ገበያ መስተጋብር ላይ ተገኝቶ ማረጋገጥ ይቻላል። ገበያው የሁለቱም ክልሎች ህዝቦች ያላቸውን ይዘው መጥተው በነጻነት የሚገበያዩበት ነው። አሁን በሰላም ተገበያይቶ ወደ ቤት የሚመለስበት ሁኔታ በመፈጠሩ ለወጣት ማሪማ እና እንደ እሷ ላሉ ወጣቶች ደስታና እፎይታን ሰጥቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንዱራ ሚሊሻ የሆኑት አንመይ አልቤም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም መታጣት ችግር ዛሬ መፈታት በመቻሉ በነጻነት ያለስጋት ለመገበያየት መብቃቱን አስረድቷል። "ያ አሰቃቂና የእልቂት ጊዜ አልፎ ተገናኝተንና እርስ በርስ ተገበያይተን በሰላም ወደየቤታችን እንመለሳለን ብሎ ማሰብ እንደ ከንቱ ህልም ነበር" ይላል የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውስ። “ሚሊሻ እንደመሆኔ ከፌዴራልና ከክልሎች የጸጥታ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ ግጭት ቀስቃሾችን ለመፋለም ጨካ ለጫካ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም አይረሳኝም” ያለው ሚሊሻ አንመይ፣ ስንቶች በሕክምና፣ በመድሃኒትና ምግብ እጦት ህይወታቸው ማለፉን አንስቷል። "አማሟቴን አሳምረው" እንደሚባላው በወጉ መሞትና መቅበር ትልቅ ጸጋ መሆኑን የገለጸው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጥ በመግባት ነው። አሁን ላይ ሁሉም የደረሰውን ጉዳት በመርሳት የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ ነው። የሁለቱ ክልል ህዝቦች ቂም በቀልን ትተን በጋራ የምንሰራበት ወቅት ላይ መድረሳችን ህዝቡ ከጥንት ጀምሮ ያለው የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና አንድነት የመንፈሰ ጠንካራነት ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጸው። በእርግጥም የማንዱራ ሚሊሻው እንዳለው በአካባቢያቸው ትምህርት ቤቶች በመከፈታቸው ህጻናት ያለስጋት በመማር ላይ ናቸው። የጤና ተቋማትም የተለመደውን የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው። በሰላም እጦት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች በመከፈታቸውም ሁሉም ተሯሩጦ ኑሮውን ለማሸነፍ ላይ ታች እያለ ነው። ባለሃብቶችም በክረምቱ በግብርናው መስክ ተሰማርተው ማልማት ችለዋል። የጸጥታ ስጋት ተወግዶ ሌሎች የልማት ሥራዎች ሲተገበሩ ማየት ትልቅ ስኬት ነው። በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የቻግኒ ከተማ ነዋሪ አቶ ሲራጅ አዲስ እንዳሉት ግጭት በነበረበት ወቅት በአካባቢው የኢንቨስትመንትና የንግድ እንቅስቃሴ ተዳክሞ ነበር። እሱ ቀርቶ በሰላም ውሎ ለማደር ጊዜው ከባድ ነበር ይላሉ። "የተገኘው ሰላም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት በመሆኑ ሰላሙ አስተማማኝና ዘላቂ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል" ብለዋል። አሁን ላይ ያለፈውን የመከራ ጊዜ፣ በሞት የተለየውን ወገን፣ የወደመውን ሀብትና ንብረት በመርሳት በተገኘው ሰላም በጋራ ሰርቶ ራስንና አካባቢውን ለመለወጥ መትጋት እንደሚገባ ነው የመከሩት። ያለፈን በደልና ቅሬታ በእርቅና በይቅርታ በማለፍ ነገን ብሩህ ለማድረግ መትጋት አለብን በማለትም ነው ያስገነዘቡት። አቶ ሲራጅ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የጉሙዝ ማህበረሰብ ወደ ቻግኒ መጥቶ ያለውን ሽጦ የሚፈልገውንም ገዝቶ ይሄዳል፤ እነሱም ወደ መተከልና ማንዱራ በመሄድ ያላቸውን ይሸጣሉ፤ የፈለጉትንም ገዝተው የሚመጡበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይሄን አብሮነት በማጠናከር ሁለንተናዊ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላምን ማጽናት ላይ ጠንክሮ መስራት ይገባል። በአማራም ሆነ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ወንጀለኞችን አጋልጦ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። አሁንም የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትን አደብ እንዲገዙ ማድረግ ተገቢ ነው። ወንጀለኛን ለህግ አጋልጦ መስጠትን ከተለማመድን ነገም አካባቢውን የጦር ቀጣና ለማድረግ የሚፈልጉ የጥፋት ሃይሎች መግቢያ ቀደዳ አይኖራቸውም ይላሉ። ሃገር በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጎች የተባበረ ክንድ ትገነባለች፤ ደህንነቷም ድንበሯም ይጠበቃል። ለዛሬው ትውልድ የደረሰችውም የብዙዎች ዋጋ ተከፍሎባት እንደመሆኑ በጋራ በሰላምና በአብሮነት ይሄንኑ ማስቀጠል የግድ ይላል። በተለይም የሰላም ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት የሚወስድ እንደመሆኑ አካበቢን የመጠበቅ የነቃ ተሳትፎን ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ልታለማውና ልትጠቀምበት የምትችለው ገና ብዙ ያልሰራችበት ሃብት ባለቤት መሆኗ የአንዳንድ ሃይሎችን ቀልብ መሳቡ የሚጠበቅ ነው። ሰላሟ ሲረጋገጥ የዜጎች ደህንነት ሲከበር የተጀመረው የእድገት ጉዞ መፋጠኑ የማይቀር በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 72
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 254
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 392
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 565
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ሴቶችን በዘላቂነት በማቋቋም መሆን አለበት
Mar 8, 2022 2291
የካቲት 29/2014 (ኢዜአ) ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ሴቶችን በዘላቂነት በማቋቋም መሆን አለበት ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገሩ፡፡በዓለም ለ111ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ እለቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራትን እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የሴቶች አደረጃጀቶች ተቀናጅተው የሴቶችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሰሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ይሁንና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት በተለይ ሴቶች ይበልጥ ተጎጂዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በርካታ ሴቶች ለጾታዊና አከላዊ ጥቃት መዳረጋቸውንም ጠቅሰዋል። በመሆኑም ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በችግር ውስጥ የሚገኙ እናትና እህቶቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም ድጋፍ በማድረግ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። ከየካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ ማድረግን ዓላማ ያደረገ አገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚተገበር እቅድ በማውጣት ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን እየደገፉ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የተሃድሶ ስራዎች ደግሞ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ በዚህም ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በቀላሉ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ስፖርታዊ ውድድሮችን ለቱሪዝም ዕድገት ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ
Feb 26, 2023 1065
ሀዋሳ (ኢዜአ) የካቲት 19/2015 በኢትዮጵያ ከተሞች ስፖርታዊ ውድድሮችን በማስፋፋት ለቱሪዝም ዕድገት ጉልህ ሚና እንዲጫወት እየተሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። አትሌቶችን ጨምሮ 3 ሺህ 500 ሰዎች የተሳተፉበት 11ኛው የሶፊ ማልት ግማሽ ማራቶን ውድድር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በውድድሩ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሠላማዊት ዳዊት እንዳስታወቁት፤ የተለያዩ ኩነቶችን በማዘጋጀት ቱሪዝምን ለማነቃቃትና ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል። እስካሁን ከአዲስ አበባ ውጭ በሀዋሳና በቆጂ ስፖርታዊ ውድድር ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በሌሎች የክልል ከተሞች መሰል ውድድሮችን በማስፋፋት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋ ለስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ትላልቅ ኩነቶች ምቹ በመሆኗ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተስተናገደባትና ቱሪዝሙም እየተነቃቃ እንደሆነ ተናግረዋል። ስፖርታዊ ውድድሩ ለከተማዋ የቱሪስት ፍሰት ጉልህ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እያገዘ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በየዘርፉ ያሉ ስፖርተኞችን ለሀገር በማበርከት የምትታወቀው ሀዋሳ አገርን የሚወክሉ ስፖርተኞች ለማፍራት የምትሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅ ዳግማዊት አማረ ውድድሩን ስናዘጋጅ በዋናነት የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን የትኩረት ማዕከል በማድረግ ነው ብለዋል። ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በጋራ እየሰራን ነው ያሉት አዘጋጇ፤ ከተሳታፊዎች መካከል እጣ የደረሳቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የሚጎበኙበት ዕድል መመቻቸቱን ገልጸዋል። በውድድሩ ከግማሽ ማራቶን በተጨማሪ የስምንት ኪሎ ሜትር እንዲሁም የህፃናትና አዋቂዎች ውድድር መካሄዱን ጠቁመዋል። በ21 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች አንድ ሰዓት ከአንድ ደቂቃ 52 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ አንደኛ የወጣው አትሌት አበባው ደሴ ለኢዜአ በሰጠው አስተያየት ውድድሩ ብርቱ ፉክክር የታየበት መሆኑን ተናግሯል። የሀዋሳ አየር ንብረት ፀባይ ለውድድሩ ምቹ እንደሆነ ጠቅሶ በከተማዋ ተመሳሳይ ውድድሮች ሊስፋፉ እንሚገባ ጠቁሟል። በሴቶች አንድ ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ አንደኛ የወጣችው አትሌት የኔነሽ ደጀኔ ውድድሩ የመጀመሪያዋ እንደሆነ ተናግራለች። እንዲህ አይነት ኩነት ለተተኪ አትሌቶች መፍለቅ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ በሌሎች ከተሞችም ተጠናክሮ ቢቀጥል መልካም እንደሆነ አመልክታለች። በውድድሩበ አንደኝነት ላጠናቀቁ ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር እንዲሁም በወንዶች ከአንድ ሰዓት በፊት በሴቶች ደግሞ ከ70 ደቂቃ በፊት ውድድሩን ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ተጨማሪ ሽልማት ተዘጋጅቶ እንደነበርም ተጠቁሟል።
የካራማራ ድል የኢትዮጵያ ጦር በዜያድባሬ ጦር ላይ ታሪካዊ ገድል የፈጸመበት ነው ... በውጊያው የነበሩ የጦር መኮንኖች
Mar 5, 2021 931
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2013(ኢዜአ) የካራማራ ጦርነት ድል የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ የወራሪው የዜያድባሬ ጦር ላይ ታሪካዊ ገድል የፈጸመበት ነው ሲሉ በአውደ ውጊያው ላይ የነበሩ የጦር መኮንኖች ገለጹ። ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሉዓላዊነት ሁልጊዜ ዘብ መቆም አለባቸው ብለዋል።  የካራማራ ጦርነት 43ኛ ዓመት የድል በዓል መታሰቢያ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት አደባባይ ተከብሯል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 ግልጽ ወረራ ኢትዮጵያ ላይ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኩባ ወታደሮችም የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል በማድረጉ የኢትዮጵያ አሸናፊነት በአደባባይ ታወጀ። በካራማራ ጦርነት በአውደ ውጊያው ላይ የነበሩ የቀድሞ የሠራዊት አባላት ብርጋዴል ጀኔራል ሃይለመለኮት ማሞ፣ ሻምበል ባሻ ሁሴን ጎበና እና መቶ አለቃ በቀለ በላይ ድሉን አስመልክቶ የምስክርነት ቃላቸውን ለኢዜአ ሰጥተዋል። ጦርነቱ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባውን ወራሪውን የሶማሊያ ጦር ከአገር ለማስወጣትና ድል ለማድረግ የሕይወት መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑንና ኢትዮጵያም በድሉ ክብሯ መጠበቁን ገልጸዋል። በምድርና በአየር ወራሪ የሶማሊያ ጦርን በመደምሰስ የኢትዮጵያ ሠራዊት ታሪካዊ፣ አስደናቂ ገድልና ጀብድ መፈጸሙንም ተናግረዋል። በወቅቱ የነበሩ የሠራዊቱ አባላት ሕይወቴ ከአገሬ አይበልጥም ብለው ያሳዩት ተጋድሎ የማይረሳ ነው ብለዋል የጦር መኮንኖቹ። ኢትዮጵያዊያን ሁልግዜ አገራቸውን ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸውና ለሉዓላዊነቷ ዘብ መቆም እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስ የካራማራው ጦርነት ኢትዮጵያ በውጭ ወራሪ ኃይል ላይ ያስመዘገበችው ድል መሆኑን ገልጸዋል። በጦርነቱ ላይ የኩባ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጎን በመሆን መዋጋታቸውንና 163 ኩባዊያን ወታደሮች የሕይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውን ተናግረዋል። "የተገኘው ድል በኢትዮጵያና በኩባ ሕዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት ትስስር የሚያሳይ ምስክር ነው" ብለዋል። "ኢትዮጵያና ኩባን ከ43 ዓመት በፊት ያስተሳሰረ የወዳጅነትና ትብብር መንፈስ አሁንም አለ" ያሉት አምባሳደር ቪልማ፤ አገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለማጠናከር እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን አገሮች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ቤኩማ መርዳሳ ፣ "የካራማራ ድል ኢትዮጵያዊያን የዚያድ ባሬ ወራሪ ኃይል በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመውን ወረራ በመመከት ድል የተጎናጸፉበት ታሪክ ነው" ብለዋል። ድሉ ኢትዮጵያ ወራሪ ሃይልን በማሸነፍ ዳግም ነጻነቷን ያወጀችበትና ኢትዮጵያዊያን የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለው ሉዓላዊነታቸውን ያስጠበቁበት እንደሆነም አክለዋል። ኩባ በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ያሳየችው አጋርነት ኢትዮጵያ ሁሉጊዜ የምታወሳውና የምትዘክረው እንደሆነም አመልክተዋል። የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበበ አያሌው ማህበሩ በአጥንትና በደም የተሳሰረውን የኢትዮጵያና ኩባ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ኩባ ከኢትዮጵያ ጎን ሆና ላሳየችው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ታማኝ በየነ "የካራማራ ድል ኢትዮጵያዊያን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ኢትዮጵያን ያቆዩበት ታሪካዊ ገድል ነው" ብለዋል። ኢትዮጵያዊያን በታሪክ ከተገኙ ድሎች በመማር አሁንም ቢሆን ከልዩነታቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም አገራቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያን ሁልጊዜም ታሪክ ለሰሩ ወታደሮችና የጦር ሠራዊት አባላት ክብር መስጠት አለባቸው ብለዋል። በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ በተከበረው የድል በዓል የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በጦርነቱ ለተሰው ጀግኖች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። ከኢትዮጵያዊያን የየካቲት ወራት ድሎች አንዱ የሆነው የካራማራ ድል 43ኛ ዓመቱን አስቆጥሮ የድል በዓሉ በኢትዮጵያዊያን ዛሬም እየተከበረ ይገኛል።
ባለፉት ስድስት ወራት በሀገራዊ ዕድገትና ገጽታ ግንባታ ላይ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ተሰርቷል--የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Mar 4, 2023 803
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 25 ቀን 2015 በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት በአገራዊ ዕድገትና ገጽታ ግንባታ ላይ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መከናወኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተዘጋጀው የፌዴራልና ክልል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።   የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ በጫናዎች ውስጥ ሆናም በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት፣ በመልካም አስተዳደር ሥራዎች፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እንደ አገር የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ለእነዚህ ስኬቶች የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አስተዋፅኦ ድርሻ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። በመንግስት እና ሕወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዲዝ እንዲሁም በሌሎች አገራዊ ስኬቶች ላይ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ጠንካራ ስራ አከናውኗል ነው ያሉት። "በኢትዮጵያ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ውስብስብ ችግሮችን በመፍጠር ተጽእኖ አሳድረዋል" ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይሄንን በመመከትም አበረታች ስራ መሰራቱን አመልክተዋል። "የዜጎች ሰላም ወጥቶ በሰላም መመለስ እረፍት የሚነሳቸው የውስጥና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማመስ የሚያደርጉትን እኩይ ሙከራ ማክሸፍ ይገባል" ብለዋል። "ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል ተወጥታ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን እንድታደርግ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በተናበበ አኳኋን መምራት የሚጠበቅብን ወቅት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ለገሰ፤ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ በዘርፉ የሚከናወኑት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። በቀጣይም አክራሪነትና ፅንፈኝነትን በቅንጅት በመመከት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚመጥን የሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባም ሚኒስትሩ አሳስበዋል።    

የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ ነው -ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ
Mar 3, 2023 740
ባህር ዳር (ኢዜአ) የካቲት 24/2015 የግብርናው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ። የክልሉ ግብርና ቢሮ ዛሬ 241 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረክቧል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት አመታት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት የተሰጠ ቢሆንም አሰራሩ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ በኩል ለውጥ ሳይመጣ ቆይቷል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በስትራቴጂ የታገዘ ስራ እየተከናወነ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በተግባር የታገዘ ለውጥ የሚያመጣ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በስንዴና አኩሪ አተር ምርት በክልሉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ጊዜ የሚቆጥቡና የምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በረጅም ጊዜ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ የማዘመንና በረጅም ጊዜ ክፍያ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እንዲያገኝ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በተለመደው መንገድ መሄድ እንደማያዋጣ የገለጹት ደግሞ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ናቸው። የግብርና ምርታማነትን በፍጥነት ለማሳደግ ዘመኑ ያፈራቸውን ጊዜ ቆጣቢና የአርሶ አደሩን ድካም የሚቀንሱ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ባለፉት ዓመታት መንግስት የግብርናውን ዘርፍ የሚያዘምኑ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የእርሻ ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥ ነጻ እያስገባ መሆኑን ተናግረዋል። በሃገር አቀፍ ደረጃ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርታማነትን በማሳደግ በኩል ብዙ እንደሚቀር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከሚታረሰው መሬት 22 በመቶው ብቻ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ገልጸዋል። አርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታዎች መቅደም እንዳለባቸው አመልክተው፤ ለዚህም አንዱና ዋነኛው መሬትን በኩታ ገጠም ማረስ እንደሆነ አብራርተዋል። ለዚህም ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ዶክተር ግርማ፤ አሁን ላይ እንደ ሀገር 6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ተደራጅቷል ብለዋል። ''አርሶ አደሩ በቴክኖሎጂ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው'' ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማሪያም ከፍያለው ናቸው። በክልሉ ለዓመታት የነበሩት ትራክተሮች ከ800 ያልበለጡ እንደነበሩ አስታውሰው፣ ባለፉት ሁለት ዙሮች ብቻ ከ700 በላይ ትራክተሮች ለአርሶ አደሮች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ በዘር በመሸፈን ላይ ከሚገኘው 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር የእርሻ መሬት 11 በመቶው ብቻ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚታረስ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ለአርሶ አደሮች ትራክተሮችን የማቅረብና ሌሎች የማዘመን ጅምር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የክልሉ መንግስት በረጅም ጊዜ ክፍያ የትራክተር ባለቤት እንዲሆኑ ማድረጉ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ደግሞ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደንብያ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አሰፋ አያሌው ናቸው። አርሶ አደሮቹ የተረከቧቸው የእርሻ ትራክተሮች የተለያየ የፈረስ ጉልበት እንዳላቸው ተገልጿል። በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል"-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Feb 26, 2023 727
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 19/2015 ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል። በማጠቃለያው ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን የመከላከል ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አገልግሎት አሰጣጥን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ ለማስቻል በርካታ ዘርፎችን የማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ የነዋሪውን ችግር እንዲያቀሉ የተጀመሩት የእሁድ ገበያ እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል። በእሁድ ገበያ ለመሰረታዊ ፍጆታ የሚሆኑ ምርቶች በቀላሉ ህብረተሰቡ ጋር እንዲደርሱ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል። አስተዳደሩ ከተማዋን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ውብና ምቹ ከማድረግ ባሻገር ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ከተማነቷን የምትመጥን ለማድረግ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ተግባራዊ እያደረገ ነውም ብለዋል። “ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር አመራራችን ፅንፈኝነትን፣ ጥላቻን፣ የህብረተሰቡን አንድነት የሚንዱ አስተሳሰቦችን፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረጉ የሚዲያ ዘመቻዎችንና ሌሎች የፓርቲያችን እሳቤ ያልሆኑ አመለካከቶችን በመዋጋት ረገድ እየተሰራ መሁኑ ተናግረዋል። “አሁንም ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት እና በህቡእ አደረጃጀት የሚደረግ ህገ-ወጥነት ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል” ሲሉ መግለጻቸውን ከንቲባ ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል። በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት ያልተከናወኑ ተግባራት ተለይተው በእቅድ ክለሳ እንዲካተቱ በማድረግ የህዝቡን ኑሮ የሚያቀሉ ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰሩም ከንቲባ አዳነች አክለው ገልጸዋል።
ሴትነት እና እናትነት
Mar 8, 2023 689
(አየለ ያረጋል) እስኪ መላ ስጪኝ መላ ካንቺ ይገኛል እኔማ ወንድ ነኝ ይደናገረኛል… (የማኅበረሰቡ ቃላዊ ግጥም) ሴትነት እናትነትን ለመግለጽ ቀርቶ በጥቂቱ ለመረዳት የ’እናት ልብ’ መታደል የሚሻ ይመስላል። ጥቂት ወንዶች ይህን ጸጋ ይቸራሉ። ልክ እንደ ዶክተር ይሁኔ አየለ። የስነ-ምግብ ሳይንቲስቱ ዶክተር ይሁኔ አየለ ‘እናት’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፍ የሴትነት እና እናትነትን ከፍታ በ’ኩርሽም’ ቃላት ተራቀውበታል። የሴቶች ቀንን (ማርች-8) ሰበብ በማድረግ ይህን ጽሑፍ ሳዘጋጅ መታሰቢያነቱ እናትን አስበው በ‘እናትነት’ ቅን ልቦና ‘እናትን’ ላበረከቱልን ዶክተር ይሁኔ አየለ ነው። ‘እናት፤ የሴት ልጅ ስንክሳር፤ ከቤተሰባዊ ሕይወት እስከ ሐልዮመንበርት’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባሳተሙት (በ406 ገፆች በተቀነበበ) አርበ ጠባብ መጽሐፍ ሴትነትን ከዘፍጥረት እስከ አሁን ዘመናትን ዋጅተው፣ እናትነትን ከሴትነት ዘንቀው፣ የእናትነት ጸጋን ከነባራዊ ሃቅ ጋር አሰነናስለው፣ የእናትነትን ልዕለ-ተፈጥሮ አርቅቀው፣ የዓለምን ክብር-ነሽነት ከነገረ-ሃይማኖት እስከ ነገረ-ባህልና ፍልስፍና ፈትተው፣ የማኅበረሰቡን ምልከታ ዝንፈት እና ሚዛን ጉድለት ከማኅበራዊ እስከ ፖለቲካዊ መገለጫዎች አዛምደው አቅርበውታል። ዶክተር ይሁኔ አየለ “እናት” በተሰኘ እናት የሆነ መጽሐፋቸው እናትነትን በልኩ ነጽረውታል። ሴትነት በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ሰለባነቱን፣ ነገረ-ሴትነትን ከንጽረተ-ሴትነት ቃኝተውታል። በእሳቤ ሚዛን ሰለባነት ዓለም ውስጥ ከንግስት ማክዳ እስከ ንግስት ፉራ፣ ከሰብለ ወንጌል እስከ ድል ወንበራ፣ … ብርቱ ኢትዮጵያዊት ሴቶችን ሕይወት ጨልፈውታል። የሴትነትን ጸጋዎች ጨልፈው በሴትነት ላይ የሚፈጸሙ የሀበሻ ግፎችን ተንትነውበታል። ሴቶች የማኅበረሰቡ ግፍ ሰለባዎች፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጉድለት ሰለባዎች እንደሆኑ በቅጡ ገልጸውታል። ዳሩ ሴትነት ጀግና እና ብልህ፣ የቤተሰብ መሰረት፣ የደስታና እልልታ እናት፣ ቃል ኪዳንና ክብር ጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል። “ሴት ልጅ ባለብዙ ጸጋዎች ናት። ከጸጋዎቿ መካከል ጀግንነት እና ብልሃት ይጠቀሳሉ። … ሴት ልጅ ባህልን ፈጥራ የማኅበራዊነትን ማስተሳሰሪያ ገመዶች ገምዳ አስተሳስራ ማኅበረሰብን የተከለች ሥርዓት ናት። … ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ የመጀመሪያ ተቋም ነው። የተቋሙ ባለሥልጣን (እመቤት) ሴት ናት። ያቺ ሴት እናት ናት። ቤተሰብ የስብዕና መሰረት የሚባለው እናትን ምሰሶ አድርጎ ነው” (ገጽ-285) ሴት ልጅ መለኛ መሆኗን ማኅበረሰባችን ቢያምንም ሴትነትን ግን እንዳላከበረ አሉታዊ ይትባህልና ኪነተ- ቃሉን ዘይቤ ያወሳሉ። በእርግጥ የእናትን ምቹነት እና ዋጋ ከፋይነት የሚያትቱ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችም አሉ። ለምሳሌ ዳንኤል አበራ “የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች” በሚለው መጽሐፋቸው “እናት ትረገጣለች እንደመሬት፤ እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ፤ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ፤ እናት የሌለው ልጅ እንደ ጌሾ፤ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ…” የሚሉ ምሳሌያዊ ንግግሮችን አስፍረዋል። መላኩ ይርዳው የተባሉ ጸሐፊ ‘ደቦ ቅጽ-፩’ ከተሰኘው የ60 ደራሲያን ሥራዎችን ያካተተ መጽሐፍ ውስጥ ‘የሴትነት ጸጋ’ በሚል በጻፉት መጣጥፍ ሴትነትን ከፍቅር፣ ከጥበብ፣ ከብልሃትና ልዕልና ጋር አቆራኝተውታል። “ሴት ልጅ ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አልታዩኝም። የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የተረዳነው አይመስለኝም።… ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለሴት ልጅ የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንስብኛል” ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስለሴት ልጅ ጭቆና የታገለ እና ስለክብሯ የዘመረ ምሁር ነው። ስለሴት ልጅ ስቃይና ሰቆቃ አትቷል። ‘በናቴኮ ሴት ነኝ’ በሚለው መጽሐፉ ስንኞች እንምዘዝ! …. ግማሽ አካሏ ወንድ በትምክህት ቢከዳት ጧ! ብላ አለቀሰች አዛኝ ቢደርስላት፣ … ብሶት ተጫጭኗት ምንም ሰው አልሆነች በቀቢጸ ተስፋ ሕላዌንም ጠላች ያገሬ ጭቁን ሴት መድኅን መላ ያጣች….! ‘ሔዋንያት የትውልድ ፋብሪካዎች ናቸው፤ እነሱ ባይኖሩ ዓለም ባዶ ትሆን ነበር’ እንዲል ፈላስፋው ሶቅራጥስ። ስለሴት (ግማደ ሰቧ ፍጡር) ግፍና በደል ገሞራው እንዲህ ይላል። “መራራ ጭቆና በሰፈነበት ምዝብር ሕብረተሰብ ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ሔዋንያት ብሶታቸው፣ ፍዳቸው፣ በደላቸው፣ ጭንቀታቸውና መከራቸው እንደ ሰማዕታት ገድል እጥፍ ድርብ ነው…. አጉል ልማድ፣ ኋላቀር ባሕልና አድሃሪ ሕገ-ማኅበረሰብ ከከንቱ አስተሳሰቦች ጋር ተዳምሮ በአንድነት በመመሳጠር ዘርዓ ሔዋንን ሲጫወቱባቸው ሲያሾፉባቸው ኑረዋል” (ገጽ-23) በሥነ-ሕይወት ሳይንስና በትምህርተ-ጄነቲክስ (አካለ ሕላዌ) ሴቶችን ከወንዶች የሚያሳንስ ምንም አይነት አካላዊ ተሰጥኦ እንደሌለ ተረጋግጧል። ታሪክና ተረክ ግን ወገንተኛ መሆኑን ገሞራው ይናገራል። ተረክና ተረት አልባሌ ታሪክ የሚፈጥሯቸው አርበኞች ሁሉ በፆታቸው ተባዕት በመሆናቸው፤ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ሊኖራቸው የሚችለው ዕድገት ላይ ትልቅ ደንቃራ ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። “የታሪክን ሁኔታዎችን የመመንዘር ትርጓሜያዊ አንጻር የታሪክን ትዕይንቶች ብንመረምር አንደርድሮ የሚያደርሰን ሴቶች ከወንዶች የከፋ ባህሪያዊ ድክመት እንዳለባቸው ከሚያሳይ ሥዕል ላይ ነው።” በሚት(ተለጣጭ ተረክ) ላይ የሚራቀቁት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፎክለር መምህር) ‘ተረኮች እማዊ ሳይሆን አባዊ ናቸው’ በማለት ይህን ጉዳይ ያጠናክሩታል። “በሚት ውስጥ ገነው ከሚታዩ አበይት ማኅበራዊና ባህላዊ እውነታዎች መሃል አንዱ ፆታዊ ወገንተኝነት ነው። የሰማናቸው፣ ያነበብናቸው ሚታዊ ተረኮች በእጅጉ አባዊ ለሆኑ ሥርዓቶች (ፓትሪያርካል ሲስተምስ) ያደሩ፣ በአብዛኛው በተባዕት ተጋዳሊያን የተሞሉ ናቸው” ይላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ይሁኔ (በገፅ-401) ስለሰው ማንነት ቀረጻ በተመለከተ ከጥንት እስከ ዛሬ አከራካሪ የሆኑ ፈላስፎችን ክርክር ያነሳሉ። ይኸውም የሰው ልጅ ‘ማን ቀረጸኝ? ተፈጥሮ ወይስ ተሞክሮ?’ የሚለውን መከራከሪያ ጽንሰ-ሃሳብ ይፈትሻሉ። በዚህም “ሰዎች ሲፈጠሩ የሰውየውን ችሎታ ይዘው ነው” እና “የሰዎች ማንነት የሚቀረጸው ከውልደት በኋላ በተሞክሮ ወይም ከአካባቢ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ነው” የሚሉትን ሃሳቦች ወስደው ከእናት ሚና ጋር ያዛምዱታል። እናም እናት ‘በየትኛውም መደብ ልጅን አሳምራ ትቀርጻለች’ የሚል ድምዳሜ ሰጥተዋል። “በየትኛውም መንገድ በሰው ልጅ ላይ የእናት ቀራፂነት ስለሚኖር ከተጽዕኖዋ ማምለጥ የሚቻል አይመስለኝም።… አካባቢም ሰውን ይሰራዋል የሚሉትም ከውልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር የሚደረገው ውስብስብ መስተጋብር ‘ሰው’ በመሆን ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል” ይላሉ። በዚህ እሳቤ ሰው የወላጆቹም፤ የአካባቢውም ውጤት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን” ይላሉ። ሴቶች ከጥንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ማኅበረ-ባህላዊ እንዲሁም ለሰላምና ዕርቅ እሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው። ሴቶች ያልተሳተፉበት ዘርፍ የለም። ከመሪነት፣ ጥበበኝነት፣ ከአገር ድንበር ጠባቂነትና የዲፕሎማሲያዊ ሚና… መጥቀስ ይቻላል። ሴቶች በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ በሰላምና ግጭት አፈታት ግንባር ቀደም ተሰሚነት አላቸው። ለአብነትም ሀደ ሲንቄ፣ በሶማሌ-ሔር፣ በሲዳማ-ያካ፣ በራያ ማኅበረሰብ ዱበርቲዎች፣ በስልጤ-ሴረን ባህል መጥቀስ ይቻላል። ከሰሞኑ ባከበርነው የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሴቶች ውለታ በወፍ በረር ማውሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ ሴቶች ከሌላው ዓለም ሴቶች በተለየ የራሳቸው ቀለም ያላቸው፣ የአመራር ልምድ ያዳበሩ፣ የመወዳደሪያ ስነ-ልቦና ያላቸው፣ ችለው አሸንፈው ያሳዩ ናቸው። ሴቶች ድሉን በማስመዝገብ የተጫወቱትን ሚና ያህል፣ ገድላቸው በታሪክ በሚገባ አልተወሳም። ዶክተር አልማው ክፍሌ የተባሉ የታሪክ ምሁር በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ሲሉ ሰምቻለሁ። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች በርካታ ናቸው። ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡- “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችዎን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) ዶክተር ይሁኔ (በገጽ-14) በበኩላቸው እናቶችን ሩህሩሆች፣ አጉራሽና አልባሽ፣ የችግር ቤዛዎች፣ ሕይወት ዑደት አስቀጣዮች፣ የሕይወት መድኅኖች፣ ባለብዙ ጸጋዎች፣ መልካም ባህሪ አውራሾች፣… በማለት ገልጸውታል። መላ ሴቶችንም በእናቶች አተያይ ማየት እንደሚገባም እንዲሁ። “እናትነት መልካም ገጽታዎችን ደራርቦ የያዘ የሴት ልጅ ትልቅ መገለጫ ነው። እናትነት ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። እናትነት ጥልቅና ሰናይ ባህሪያት የሚፈልቁበት ምንጭ ነው። እናትነት የደግነት፣ የጥራት፣ የልህቀትና ተፈላጊነት ማሳያ ተምሳሌት ነው። እናትነት ሞት የማያደበዝዘው ኃያል መንፈስ ነው። እናትነት ከባድ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። … እናትነት የሰላም፣ የመልካም ግንኙነትና እንክብካቤ መፍለቂያ አድባር ናት። እናትነት ሰፊና ጥልቅ የሕይወት ትምህርት ቤት ነው። እናትነት ሌሎች ከስቃይ ነፃ እንዲሆኑ፣ ምቾት እንዲሰማቸው በሚደረግ ትግል ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ መኖር ነው” በመቀጠልም የኢትዮጵያ እናቶችን ‘ጠቃሚ ነገር ሰጪዎች’ ይላቸዋል። “እናቶች ሰው የመሆኛ ቅመሞች የሚጨለፍባቸው ባህር ናቸው። … ሕይወታዊ ስሪታችን ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የወሰደው ከእናት ነው። ከእናት የምናገኘው ‘ማይቶኮንድሪያ’ (ማይቶኮንድሪያ የኃይል ማመንጫ ክፍል ሲሆን የምንመገበው ምግብ እየተቃጠለና ወደ አስፈላጊው ኃይል እየተቀየረ ሕይወትን ያንቀሳቅሳል) የምግብ ማቃጠያ ምድጃ ወይም ኃይል ማመንጫ ቤት ሆኖ ያገለግላል። … ብዙ መልካም ስብዕና መገለጫዎች ምንጫቸው የእናት ፍቅር፣ የመልካም ስብዕና እና የርህራሄ ምንጭ ነው” (ገጽ- 61) ኢያሱ በካፋ ‘የኢያሱ በካፋ ወጎች’ በተሰኘው መጽሐፉ እናትነትን ማህጸንን፣ ምግብን፣ ትንፋሽን፣ ደም፣ ሥጋን እና ነፍስን ሰጥተው በረቂቅ ተፈጥሮ ሰውን ከመውለድ ባለፈ ፍቅራቸውን ዘላለማዊ ገደብ አልባ እና ዕልቆ-ቢስ እንደሆነ እንዲህ ገልጾታል። “እናትነት ነፍስን ማካፈል ነው፤ እናትነት የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር መስጠት ነው፤ እናትነት ከራስ ሕልውና ይበልጥ ለልጅ ማሰብ ነው፤ እናትነት ፍፁም ወረት አልባ መሆን ነው። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር አይነጥፍም፤ አይለወጥም። ለእናት ልጇ ሁሌም ልጇ ነው” (ገጽ-4) እናትነት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ፤ በውለታ ማካካስ ይከብዳል። የእናት ውለታዋን መክፈል የሚችል ልጅ የለም። የእናት ፍቅርን ለመግለጽም በርካቶች አንደበታቸው ይተሳሰራል፤ ቃላት ይነጥፍባቸዋል፤ ስሜታቸውን መግራት ይሳናቸዋል። ድምፃዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) ‘ይናገራል ፎቶ’ በሚል እናትና አባቱን በገለጸበት ሙዚቃ የመጨረሻው ማጠንጠኛው ‘እወድሻለሁ/እወድሃለሁ’ ያለው፤ እንዲሁም ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ‘እናት ውለታዋ’ በተሰኘ ዘፈኗ ውስጥ (ዜማና ግጥም ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ)፤ “ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ” እያለች በሚስረቀረቅ ድምጿ የምታንጎራጉረው ለዚህ ይመስላል። ዕውቁ የቋንቋ ሊቅ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) ‘የጥቁር አፈር ትሩፋቶች’ በተሰኘው መጽሐፉ (ገጽ-79) ‘መቀነትሽን አጥብቂ’ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ረዘም ያለ ግጥም ሁለት አንጓዎች ብቻ ስንመዝ የእናትነት ውለታን መመለስ እንደሚሳን፤ የእናትነት ግብሯ ‘እናት’ የሚለው ቃል በራሱ እንደሚያንስባት ያትታል። … “ለዚህ ወሮታሽ አጸፋ፤ እናት ይልሻል አገሩ፤ እኔም እናቴ ብልሽ መች ሊመጥንሽ ዳሩ። … እናትነት ምጡቅ ነው፤ እናት ከመባል ይልቃል፤ የግብርሽ ስንክሳር ዚቁ፤ በስያሜ መች ያልቃል”… በማለት ይገልጸዋል። መውጫ ዶክተር ይሁኔ የሴት እና እናትን የነገዋን መንገድ ከሳይንስ አተያይ አንጽረው፤ ከማኅበረ-ፖለቲካ፤ ከማኅበረ-ባህል ከፍታዋ አመሳክረው፤ እናትና ሀገርን መጋመድ አመስጥረው መልእክታቸውን እንደ መውጫ አስፍረዋል። ለስንበት አንድ አንቀጽ እንወርውር!! “የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። የሰመረ ትውልድ ሊቀጠል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው። የእናቶች አቅም ሲገነባ የራሳቸውን አቅም ያውቃሉ፤ ምርጫቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እንዲሁም ለሚመጣው ማኅበራዊ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ። ስለሆነም የእናቶችን አቅም ማጎልበት ትውልድን ማጎልበት ነው። እናቶች ላይ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት ነው”  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን ተደራሽ የሚያድረግ ድረ-ገጽ አስጀመረ
Mar 4, 2023 684
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 25/2015፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ መረጃዎችን በፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች ተደራሽ የሚያደርግ አዲስ ድረ-ገጽ አስጀመረ። አዲሱን ድረ-ገጽ በይፋ ስራ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ትዕግስት ሀሚድ ናቸው። የተቋሙ ዌብ አድሚኒስትሬተር ሄኖክ አብይ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት አዲሱ ድረ-ገጽ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች በእኩል ጥራት ለማድረስ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ነው።   የተቋሙን ብራንድ መሰረት ባደረገ መልኩ የተዘጋጀው ድረ-ገጹ ከመረጃ ጥራትና ደኅንነት አንጻርም አስተማማኝ ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አማካኝነት መገንባቱንም ገልጸዋል። ድረ-ገጹ ከዚህ ቀደሞ በተቋሙ ሲሰራባቸው የነበሩትን እንግሊዝኛ ፣ አረብኛ ፣ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞን ጨምሮ በአዲስ መልኩ በቅርቡ የተጀመሩትን ፈረንሳይኛና ትግሪኛ ቋንቋዎችን በማካተት አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መደራጀቱን አስታውቀዋል። የኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ እንዳሉት ኢዜአ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገነቡ ሀገራዊ ጉዳዮችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ የሚያደርጉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ። አሁን ይፋ የሆነው አዲስ የድረ-ገጽ ይሀንኑ አላማ ለማስፈጸም የሚያግዝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው አስተማማኝነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ ዘመናዊ አገልግሎት ማቅረብ እንዲያስችል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መገንባቱን ተናግረዋል። በቀጣይም ኢዜአ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዘርፉ ልማት ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው ተቋማቸው የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከኢዜአ ጋርም በዘርፉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል በጋራ ከመስራት ባለፈ በቀጣይም በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንኙነት የሚያሳድጉ ተግባራትን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። በድረ-ገጹ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።  
መጣጥፍ
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 525
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ)
Jan 25, 2023 567
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ) አየለ ያረጋል (ኢዜአ) መዳረሻዬ ሽሬ እንዳስላሴ ነው። ለዘገባ ሥራ ከባህርዳር- ጎንደር- ደባርቅ- ሸሬ መንገድ ከሚዲያ ባልደረቦች ጋር እየተጓዝኩ ነው። የጥምቀት ሙሽራዋ ጎንደር እየተኳኳለች ነበር። ደባርቅ ከመድረሴ በፊት ዳባት ትገኛለች-የደጃች አያሌው ብሩ ቁርቁር ከተማ። ደጃች አያሌው ትውልዳቸው በጌምድር ጋይንት ቢሆንም ግዛታቸውና ኑሯቸው ዳባት ነበር። ሞገደኛው ደጃዝማች አያሌው ብሩ በጎንደር ማኅበረሰብ ዘንድ ዝናቸው የናኘ ነው። ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ (ከልጅ ኢያሱ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት) ታሪካዊ ክንውኖች ጉልህ ተሳትፎ አላቸው። አንዷን ብቻ ልምዘዝ። ራስ ተፈሪ ‘ንጉሠ-ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ’ ደጃች አያሌው የቅርብ ዘመዳቸውን ራስ ጉግሳ ወሌ ብጡልን (የንግሥት ዘውዲቱን ባለቤት) ወግተው የጎንደር ግዛት ‘ራስ’ ተብለው ለመሾም ቃል ቢገባላቸውም፤ ተልዕኳቸውን ተወጥተው ቃሉ ባለመፈጸሙ ደጃዝማቹ ከአጼው ጋር መቀያየማቸው አልቀረም። በዚህም:- "አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፣ የአያል ጠመንጃ፣ ስሟን እንጃ ስሟን እንጃ…” በማለት የጎንደር አዝማሪ አዚሟል። ዛሬም ይህ ግጥም የብዙ ባህላዊ ዘፈኖች አዝማች ነው። ደጃች አያሌው ብሩ ደፋር ናቸው ይባላል። ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር ቢቀያየሙም በ1928 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲመጣ ቅድሚያ ለአገሬ ብለዋል። ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘው የዶክተር ሀራልድ ናይስተሮም (ትርጉም ገበየሁ ተፈሪ እና ደሳለኝ አለሙ) መጽሐፍ እንደተጠቀሰው ደጃች አያሌው “ንጉሡ እንደኛ ሰው ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሁላችንም ናት" ብለው ጦራቸውን መርተው በሽሬ ግንባር ዘምተዋል። ጉዟችን ቀጥሏል። ደባትን እያለፍን ነው። ‘እንኳን ደህና መጡ፤ ወደ ጭና ታሪካዊቷ ሥፍራ’ የምትለዋን ታፔላን በስተግራ እያየን ወደ ደባርቅ ገሰገስን። የሰሜን ተራሮች የብርድ ወጨፎ ያረሰረሳትን ደባርቅን ከማለፋችን ሊማሊሞ ጠመዝማዛ ቁልቁለት ተቀበለን። አስፈሪ የሊማሊሞ መልክዓ ምድር የደጋው ሰሜን ውርጭ እና የተከዜ በርሃ ኬላ ነው። ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን “የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ አይበገር የዐለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ ሊማ-ሊሞ አድማስ ሰበሩ፣ በጎማ ፈለግ ይፈታ? በትሬንታ እግር ይረታ?…” ብሎ የመኪና መንገድ ተገንብቶበት በማየቱ ግርምቱን የተቀኘለትም ለዚህ ይመስላል። ከሊማሊሞ ቁልቁለት በኋላ አዲ-አርቃይ፣ ዛሪማ፣ ማይፀብሪ እና ሌሎች የጠለምት ወረዳ ከተማዎችን አልፈን፤ የዋልድባ ረባዳማ አካባቢዎችን ተሻግረን ተከዜ ወንዝ ደረስን። የዚህን መንገድ እና ተከዜ ወንዝን ሳስብ የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ አስተከዘኝ። የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር የወገንን ጦር ፊት ለፊት መቋቋም ሲሳነው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማያውቅ መርዝ በጅምላ የፈጀበት አሳዛኝ ታሪክ ነበር። በተከዜ ወንዝ ውሃን በመመረዝ የወገን ጦር ያለቀበት ሥፍራ ነው። የተከዜ ሸለቆ በኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በአንድ ዕለት የተመለከቱትን እንዲህ ጽፈውታል። “የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ላይ ሰፊና ፀጥ ያለ ነው። ታዲያ ያ ሰፊ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት ቀይ ቀለም በከባዱ የተበጠበጠ ይመስላል። “ምን ነገር ነው፤ ምን ጉድ ነው?” እየተባባልን ቀረብ ስንል መሻገሪያው በቁሙም በወርዱም ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶበት የዚያ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው። የሰው ሬሳ፣ የፈረስ እና የበቅሎ ሬሳ፣ ያህያ ሬሳ፣ ያውሬ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከእግር እየተመሰቃቀለ እየተደራረበ ሞልቶበት፥ የዚያ ሁሉ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው”። ይሉናል። ቀጥለውም “በእውነቱ እንዲህ ያለውን መሳሪያ ምንም ጠላት ቢሆን በሰው ላይ ለማዋል የሚጨክን ሰው፥ ሰብዓዊ ስሜት የሌለው፣ አለት ድንጋይ የተፈጠረበት መሆን አለበት፤ እንዲህ ያለውን መሳሪያ በሰው ላይ ማዋል ሰብዓዊ ህሊና ሊሸከመው የማይችል እጅግ ከባድ መሆኑን ዓለም ሁሉ ያወቀውና ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከማድረጉ በቀር “ሌላ መንግሥት በሌላ አገር ላይ አደረገ’ ሲባል ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል። ከተከዜ ባህር ማዶ ጉዞዬ ያገኘኋት ሌላዋ ታሪካዊ ሥፍራ እንዳባጉና ናት። እንዳባጉና የወገን ጦር ትልቅ ገድል የፈጸመበት ነው። ጀግኖች አባቶቻችን የጠላት ታንክ ሳያስፈራቸው የጠላት ጅምላ ጨራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተቋቁመው ጠላትን ድባቅ የመቱበት፤ ወደ አክሱም እንዲያፈገፍግ ያደረጉበት ሥፍራ ነው። “የጠላት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በጦር ሜዳው ትንንሽ ቦምቦች አውቶማቲክ ጠመንጃ ይተኩስ ነበር። አቢሲኒያኖች ደግሞ ከጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው ጉዳይም አልሰጡትም ነበር…” ይላል ዶክተር ሀራልድ ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘ መጽሐፉ። ይህ አካባቢ በሀገር ፍቅር የነደዱ ኢትዮጵያዊያን ደም ያፈሰሱበት፣ አጥንት የከሰከሱበት፤ ለኢትዮጵያ መስዕዋትነት የከፈሉበት ነው። ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ቀጣና ነው። ቀኑ ተገባዷል። ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። እኔም የማሽላ ማሳዎችን ግራ ቀኝ እየተመለከትኩ ለዕለቱ መዳረሻችን ወደሆነችው ሽሬ ከተማ ገባን። ሽሬ በትግርኛ ‘ሽረ’ ሲሉት ይደመጣሉ። በእርግጥ ሽሬን ለመጀመሪያ ጊዜ መርገጤ ነው። ዕለቱም ጥር ሥላሴ ነው። ሽሬ በጥር ሥላሴ ትደምቃለች፤ ሙሉ ስሟም ሽረ እንዳስላሴ ነው። የሽሬ ሥላሴ ጠበል ሽሬ ደርሰን ማረፊያችንን ያዝን። ጊዜው በጣም አልመሸምና ከተማዋን በቀላሉ መቃኘት ይቻላል። ሽሬ ሰፊና ደማቅ የዞን ከተማ ናት። ከመካከላችን የአንደኛው ባለሙያ ቤተሰቦች ሽሬ ነበሩና አስጠሩን። ለሥላሴ ጠበል ግብዣ። ባል እና ሚስቱ ከልክ በላይ መስተንግዶ አደረጉልን። ‘ጠብ እርግፍ አድርገው አስተናገዱን’ ማለት ይቀላል። እንግዳ መቀበል ነባር ኢትዮጵያዊ እሴታችን ቢሆንም ጦርነት ውስጥ ለቆየ አካባቢ የተለየ መልክ ነበረው። እንግዳ አቀባበላቸው በእርግጥም የመሃል አገር ሰው የናፈቃቸው ይመስላል። የተትረፈረፈ እህልና ውሃ አቅርበው በ’ብሉልን፤ ጠጡልን’ ተማጽኗቸው የተነፋፈቀ ቤተ-ዘመድ ግብዣ አስመሰሉት። የሥላሴው ጠበል የሸሬ ጠላ ቀረበ። የሸሬ ጠላ ሳስታውስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ታወሱኝ። የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሀሩ ፕሮፌሰር ሽብሩ በዘመነ ደርግ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ሽሬ ዘምተው ነበር። በወቅቱ ታዲያ የሸሬ ጠላ ፍቅር ይዟቸው በየጊዜው ሲኮመኩሙ የተመለከቱ ሰዎች ‘ፕሮፌሰሩ ከጠፉ የሚገኙት ጠላ ቤት ነው’ ሲባሉ እንደነበር ‘ከጉሬ ማርያም እስከ አዲስ አበባ’ በተሰኘው ግለ ታሪካቸው አስፍረዋል። ከግብዣ መልስ ከማረፊያ ሆቴል ላይ ሆኜ ከተማዋን ስቃኛት ከጦርነት ድባቴ የተላቀቀች ይመስላል። የአመሻሽ ሕዝቡ እንቅስቃሴም ሆነ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ የሚሰሙ የመዝናኛ ቤቶች ሙዚቃዎች የከተማዋን አሁናዊ መልክ የገለጠልኝ ነበር። ንጋት ላይ በቁርስና ቡና ሰዓታት ከሰዎች ጋር መስተጋብሬ ጀመረ። በጦርነት አዙሪት የከረመችው ሽሬና አካባቢው ኑሮ እጅጉን የከበደ ነበር። መልከ-ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች አስተናግደዋል። አሁናዊ ምላሻቸው “ተመስገን፤ ያ ሁሉ አለፈ” የሚል ነው። ገበያው ተረጋግቷል፤ ማህበራዊ ኑሮ ተመልሷል። ድህረ-ሰላም ስምምነት ለሽሬ ነዋሪዎች ሁለንተናዊ እፎይታን አንብሯል። ከቀናት በኋላ በአክሱም የታዘብኩትም እንዲህ ነው። ኑሮን ያቀለለው የተቋማት አገልግሎት ጅማሮ በመጀመሪያ ዘገባ ስራዬ መሰረተ ልማትን አገልግሎት ቃኘሁ። ባንክ፣ ቴሌ፣ ሆስፒታል… መሰሎቹን። ተጠቃሚዎችንም፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ሃላፊዎችንም አነጋገርሁ። ከሰላም ስምምነቱ ማግስት ጀመሮ ተቋማቱ ወደስራ መመለሳቸው ከሁለንተናዊ ችግር እንደታደጋቸው ያነሳሉ። በትራንስፖርት እየተንቀሳቀሱ፣ በኤሌክተሪክ ስራዎቻቸውን እየከወኑ ነው። ለሁለት ዓመታት የተቋረጠው አገልግሎት አቅርቦት እና የአገልግሎት ፈላጊዎች ፍላጎት ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የተጠቃሚዎችም፤ የአገልግሎት ሰጭዎችም ሀሳብ ነው። በሽሬ ስሁል ሆስፒታል የተመለከትኳቸው፤ ያነጋገርኳቸው፤ ከታዳጊዎች እስከ አዛውንት ዕድሜ ያሉ ህሙማን የሰላም አየር ማግኘታቸው የሕይወታቸው ዑደት እንዲቀጥል አድርጓል። ድንገተኛም ሆነ ነባር ህመም ያለባቸው ሰዎች በነጻ እየታከሙ ነው ያገኘኋቸው። ሰላም ከሌለ መታከም ቀርቶ በቅጡ ማስታመም፤ በወጉ መቀበርም እንደማይቻል ገልጸውልናል። የጤና፣ የባንክና የቴሌኮም አገልግሎት የግብዓት ክፍተቶች የማሟላት ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በፌዴራል ደረጃ በየተቋማቱ የተመደቡ አስተባባሪዎች አረጋግጠውልኛል። የጸጥታ አካሉና የህብረተሰቡ ትብብርም የሚያስቀና እንደሆነ ግለሰቦችም፤ የጸጥታ አካላትም ነግረውኛል። አክሱም ጺዮን ማርያም፣ ሽሬ ስላሴ ንግስ፣ የጥምቀት በዓላት ከሶስት ዓመታት በኋላ በአደባባይ ታቦት ወጥቶ ተከብሯል። የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮችም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልኝ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ የሆኑ ይመስላል። እንቅስቃሴያቸውም የሰላማዊ ቀጠና መልክ ያለው ነው፤ ዩኒፎርም ከመልበሳቸው በስተቀር ጀሌያቸውን ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ደግሞ መተማመን ከመፍጠር ባለፈ ጦርነት ውስጥ ለቆየ ማህበረሰብ ከስነ ልቦና ጫና እንዲላቀቅ አይነተኛ ሚና እንደላው ይሰማኛል። ኢ-መደበኛ የሽሬና አክሱም ወጎች ያረፍኩበት ሆቴል ባለቤት ‘አደይ’ ተግባቢ ናቸው። ደግ እናት ይመስላሉ። ከገባን ጀምሮ ‘ጠላ ተጎንጩ፤ ቡና ጠጡ’ ጭንቃቸው ነው። ሁለት ቀን ቡና አስፈልተውልናል፤ ጠላ አቅርበው ዘክረውናል። ይህ ሁሉ ሲሆንም ለከተማው እንግዳ መሆናችንን እንጂ ስለሙያችንም ሆነ ስለሌላ ማንነታችን አያውቁም ነበር። ብዙ መጨዋወትና ውሎ አዳር በኋላ ነው ጋዜጠኛ ስለመሆናችን ያወቁት። አደይ ተጨዋች ናቸው። አማርኛ ያዝ ቢያደርጋቸውም ጨዋታቸው ‘ኩርሽም’ ነው- ተሰምቶ የማይሰለች። በአጋጣሚ ‘ሰለክላካ’ ስለምትባለዋ ታሪካዊ ሥፍራ ጠይቄያቸው እያወጋን ነበር። ‘እንደእናንተ ወጣቶች ሳለን ‘ሰለክላካን ያላዬ ሸዋን ያመሰግናል’ ይባል ነበር። ታዲያ አንድ የሸዋ ሰው መጣና ሰለክላካን አየና ‘በቃ ይቺ ናት’ ሰለክላካ’ ብሎ ተገረመ” ብለው አሳቁን። (የፍቅር እስከ መቃብር መሪ ገጸ-ባህሪው ‘በዛብህ’ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄዶ ‘የዲማ መልኳ እና ዝናዋ’ ተጣርሶበት እንደተገረመበት ቅጽበት መሆኑ ነው)። አደይ የተጀመረው ሰላም ፍጹም ምሉዕ ሆኖ ወደ ቀደመ ኢትዮጵያዊ መልካችን የምንመለስበት ጊዜ እንዲመጣ ይሻሉ። ከጦር-ነት ወደ ሰላም-ነት! ቆንጂዬዋ ፊዮሪ የኮሌጅ ተማሪ ነበረች። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጀምሮ በኋላም በጦርነት ሳቢያ ትምህርቷን ካቆመች ሦስት ዓመታት ሆኗታል። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የጀበና ቡና ጀምራለች። ደንበኞቿ ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን። ፊዮሪ ከስኒ ማቅረቢያዋ ላይ አነስተኛ ጀበናዋን፤ የሚያማምሩ ስኒዎቿን እና መዓዛው ከሚያውድ የዕጣን ማጨሻዋ ጋር ሰድራ ይዛ ትቀርባለች። ከመካከላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጥና እርሷም ወንበር ይዛ ከመካከላችን ትቀመጣለች። ቡናው እስኪሰክን ጨዋታዋን ታስኮመኩመናለች። ቡናው ከሰከነ በኋላ ቡናዋን ቀድታ ለእያንዳንዳችን በእጃችን እያነሳች ትሰጣለች። በሽሬ ቡና የሚቀርበው በዚህ መልክ ነው። ለፊዮሪ እና መሰሎቿ ጦርነቱ ክፉ ጠባሳ መጣሉ፤ ተስፋቸው ላይ መጥፎ አሻራ ማስቀመጡን ታነሳለች። አሁን ግን ብሩህ ተስፋ ሰንቃለች። ስለነገዋም “ሰላሙ ይዝለቅልን፤ ትምህርቴን ለመቀጠል እመኛለሁ” ትላለች። አክሱም ከሽሬ በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ከሽሬ አክሱም ስንንቀሳቀስ ከጥምቀት ዕለት በስተቀር ገበሬው የግብርና ሥራዎቹን እየከወነ ነበር። አርሶ አደሩ ያርሳል፤ መስኖውን ያለማል። የተዘራውን ውሃ ያጠጣል። የበቀለ ቡቃያውን ይኮተኩታል። ከጦርነት ወደ ልማት መዞሩን ዐይኔ ታዝቧል። በጥምቀት ዋዜማ፤ የከተራ በዓል ዕለት ሁለት ጎራማይሌ የረፋድ ትዕይንቶችን ላንሳ። ከአክሱም ከተማ ወደ አድዋ እና ሽሬ መገንጠያ አካባቢ ሰፊ የቀንድ ከብት ገበያ ነበር። እውነተኛ የዓመት በዓል ገበያ መልክ ያለው ትዕይንት ነበር። በተለይም የፍየል ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታሪካዊቷን አክሱም ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ የረገጥኳት/የተሳለምኳት ከአራት ዓመት በፊት በ2011 ዓ.ም ይመስለኛል። ከገበያው ቀጥሎ በታቦተ-ጽዮን መገኛዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ደጅ፣ በጥንታዊያኑ የአክሱም ሐውልት መገኛ አደባባይ ነበር። ከጽዮን በስተምዕራብ በአርባቱ እንሰሳ በኩል፤ በቅዱስ ያሬድ ዋርካ… አድርጌ በጽዮን ዋናው በር ደረስኩ። ማራኪ የአክሱም የኮብልስቶን መንገዶች ኦና ናቸው። የወትሮው ግርግር ናፍቋቸዋል። ከጽዮን ቅጥር ግቢ በዋናው በር በስተውጭ አነስተኛ እና ብቸኛ ዋንዛ በኮብልስቶን መሃል ነበረች። ዛሬም ለምልማ አለች። በዚህ አካባቢ ድሮ የነጭ ጎብኚ ጋጋታ፣ የጽዮን ደጅ ጠኚ ምዕመን… የተጨናነቀ ነበር። እንደ ድሮው የፎቶ አንሺ ግርግር፣ የአክሱም መስቀል ቀርጸው የሚሸጡ ወጣቶች ጫጫታ የለም። ይልቁንም እርጥባን የሚሹ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ነበሩ። ጦርነት የሥፍራዋን መልክ አጠይሞታል። ያም ሆኖ ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በኩሉሄ ባይባልም ወደነበረበት እየተመለሰ ነው። የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኰች ሥራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከአክሱም ሐውልት ወደ ሌላ ሰፈር አቀናሁ። ትርሐስ ገና ታዳጊ ልጅ ነች። ጠይም፤ ስርጉድ፣ ሳቂታና ተረበኛ አይነት ልጅ ነች። እንደ ሽሬዋ ፊዮሪ መንገድ ዳር የጀበና ቡና እየሰራች ነው። ከሩቅ የመጣን እንግዶች መሆናችንን ስታውቅ፤ ደስታዋ ከገጿ ይነበብ ነበር። ያለፉ ጊዜያትን ሰቆቃ አጫወተችን። ስለቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እና ዕቅዷ ስታወራ ትቆይና “የሰው ልጅ ግን በጣም ከሃዲ ነው። ከወራት በፊትኮ ስለቢዝነስ አላስብም ነበር። መቼ እሞታለሁ እንጂ” ብላ ራሷን ትወቅሳለች። ወደ ሰማይ አንጋጣ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ጦርነት ተራውንም ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ቀውስ ዳርጎት እንደቆየ ታነሳለች። ዛሬ ሁሉ አልፎ ሰላም መውረዱ ለመጨዋወት መብቃቷ ለእርሷ ትልቅ ብሥራት ነው። ይህ ለትርሐስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አክሱማዊያን መሆኑ እሙን ነው። አክሱም ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በሻለቃ አዛዥነት የተሰማራ የፌደራል ፖሊስ አባልም ያጋጠመውን አሳዛኝ ገጠመኞች አጫውቶኛል። ጦርነቱ ቢራዘም ኖሮ በተራው ሕዝብ ላይ ምን ያህል የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር በአሳዛኝ ሁኔታ ገልጾልኛል። አክሱሞች ያን ሁሉ አልፈው ሰላም አየር ነፍሶ፣ ከስጋት ቆፈን ተላቀው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል። የዛሬ ሳምንት ሰርክ(11 ሰዓት) ላይ አክሱም የከተራ በዓል በድምቀት አክብራለች። ታቦተ-ጽዮን ወደ ባህረ- ጥምቀቱ ስትወርድ፤ ወግና ሥርዓቱ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ በሀበሻ ነጫጭ አልባሳት፣ ካህናት በልብሰ ተክህኖ ደምቀው … እየተከወነ ነበር። አንዲት እናት ለአማርኛ ተናጋሪ በቀረበ አነጋገር እያለቀሱ ታቦት እየሸኙ ነው። ትኩር ብዬ ሳያቸውም ዕንባቸው ዱብ ዱብ ይላል። “ከዚያ ሁሉ መከራ አልፎ ለዚህ በቃን፤ ተመስገን” እያሉ እልልታውን ያቀልጡታል። በደስታ እያነቡ ነበር። ይህ ስሜት የብዙኃኑ አክሱማዊያን እናቶች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። አክሱም በኮቪድ እና በኋላም በጦርነቱ ምክንያት ባህረ-ምቀት ታቦት ወጥቶ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከወትሮው በተለየ ድምቀትና ውበት በሰላምና በደስታ፤ በአደባባይ እልልታና ሆታ በማክበራቸው ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋልና! እናም በአክሱም የከተራ ሆነ የበዓለ-ጥምቀት ክብረ-በዓላት በሰላም ስምምነቱ ማግስት በድምቀት ተከውኖ አለፈ። የሃይማኖት አባቶቹም ሆኑ ምዕመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅም የዘንድሮው ክብረ-በዓል ካለፉት ዓመታት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸሩ፤ ትልቅ ብሥራትና መልክ እንዳለው ገልጸዋል። ሰላም እንዲጸና፤ ነባር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተባበር እንዲመለስ ጽኑ መሻታቸውን ነግረውናል። በበጎ ቀን የማውቃትን አክሱም፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ አሁናዊ መልኳን ታዝቤ፤ የነገ ትዝታ ሰንቄ ተመለስኩ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም