ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ይቀጥላል
Aug 6, 2026 13
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ገለጹ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሙስና፣ በብልሹ አሰራር እና በህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመለክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መንግሥት ከህዝብ የቀረቡለትን ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች መነሻ በማድረግ በልዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕቀፎች እና የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ያካሄዳቸውን ጥልቅ ፍተሻዎች፣ የምርመራ ውጤቶች እና የተወሰዱ የህግ ተጠያቂነት እርምጃዎችን አስመልክተው ነው ዝርዝር መግለጫ የሰጡት፡፡ በመግለጫቸው እንደጠቆሙት፤ የመደመር መንግሥት ያልተገባ ሀብት እና ጥቅም የመፈለግ አዝማሚያዎችን የሀገር እድገት አደጋ አድርጎ በመውሰድ ገና ከጠዋቱ ቀይ መስመር በማስመር ህጋዊ እና ተቋማዊ ሪፎርሞችን ሲያካሂድ ቆይቷል ብለዋል። ይህ መረጃ በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ በፌደራል ፖሊስ እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በጋራ የተቀናጀ ስልታዊ ጥናት፣ ክትትል እና ህጋዊ ፍተሻ የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ እርምጃዎች ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን የብዙሃን ዘርፍ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የህዝቦቿን ህይወት የመቀየር ሂደት ከሚያጋጥሙ እንቅፋቶች ለመጠበቅ ያለሙ ናቸው ብለዋል። በዚህም በትልቁ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ አደጋ ለመፍጠር፣ ምርቶችን በመጋዘን በመሸሸግ እና በመደበቅ የምርት እጥረት እንዲከሰት ያደረጉ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በመፍጠር በህብረተሰቡ ላይ የኑሮ ጫና እና ምሬት እንዲፈጠር ያደረጉ አካላት ላይ ሰፊ ኦፕሬሽን መካሄዱን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ የንግድ ተቋማት፣ ሱቆች እና መጋዘኖች በህግ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ እንዲዘጉም ተደርገዋል ብለዋል። ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመቀመር፣ በጥቁር ገበያ እና በህገ-ወጥ ሐዋላ በመሰማራት፣ እንዲሁም ነጋዴዎች ከባንክ ማግኘት የሚገባቸውን የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ እንቅፋት በሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬን በስውር በማንቀሳቀስ እና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት የተጠረጠሩ 169 ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት በህግ አግባብ ተጠያቂ ሆነዋል ብለዋል። በተጨማሪም በፋይናንስ ተቋማት፣ ኤቲኤም ማሽኖች እና በግለሰቦች አካውንት ላይ የሳይበር ማጭበርበር የፈጸሙ እና ያለፈቃድ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ የነበሩ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል። በሌላ በኩል፣ ያለፈቃድ በመንቀሳቀስ በማህበረሰቡ እና በወጣቶች ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ያመጡ፣ ግብር የሚሸሹ 36 ህገ-ወጥ የቤቲንግ ድርጅቶች እና በበየነ መረብ የሚሰሩ ተቋማት እንዲዘጉ እና በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል። ከሀገሪቱ አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው የማዕድን ዘርፍ በተለይም በወርቅ ምርት ላይ የሚከናወነውን የኮንትሮባንድ ዝውውር እና ድለላ ለማስቆም በተደረገ ተደራጅቶ የመስራት ምርመራ፣ ምርቱን ወደ ብሔራዊ ባንክ ከማስገባት ይልቅ ለማሸሽ የሞከሩ አምራቾች፣ አዘዋዋሪዎች እና ደላሎችን ጨምሮ 138 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል። መንግሥት ህዝቡን ከጫና ለመጠበቅ ከፍተኛ በጀት በሚመድብበት የነዳጅ አቅርቦት ላይ የሎጂስቲክስ እና የስርጭት አሻጥር በመፍጠር፣ ነዳጅን ወደ ጎረቤት ሀገራት በማሸሽ፣ መጋዘን ውስጥ በመደበቅ እና ኮታን ለግል ጥቅም በማዋል የቀውስ አዝማሚያ የፈጠሩ አካላት ተለይተዋል። በዚህ የተደራጀ ጥቅም ትስስር ውስጥ የተሳተፉ የመንግሥት አካላት፣ ነጋዴዎች እና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ስርዓቱን ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ጥብቅ መመሪያ ወጥቷል ብለዋል። አርሶ አደሩ ግብአቱን በወቅቱ እንዳያገኝ ያደረጉ፣ የኮንትራክተሮች እና የደላሎች አሻጥር ያለበት የተጋነነ ዋጋ ያለው ግዢ እንዲፈጸም ያደረጉ እና ግዢው እንዲጓተት ያደረጉ አካላት በጥልቀት ተመርምረዋል ብለዋል። በዚህም ድርጊት የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ደላሎች እና ግለሰቦች በህግ አግባብ ተጠያቂ ሆነዋል። በተቋሙ የፕሮጀክት ስራዎች ላይ የተጋነነ ዋጋ በመጠየቅ፣ የኃይል መሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲጓተቱ በመመሣጠር ሀገር ላይ የኢኮኖሚ ጫና ለማሳደር የሞከሩ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ ተባባሪ ኮንትራክተሮች እና ነጋዴዎች በጥናት ተደርሶባቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል። በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ማዕቀፍ የሚከናወነውን ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና የዜጎችን ደህንነት የሚያዛቡ፣ ህጋዊ ውል ከሌላቸው ሀገራት ጋር አየር በአየር እና በህገ-ወጥ ኤጀንሲዎች ውል በማስመሰል ሲላኩ የነበሩ፣ 8 ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ኤጀንሲዎች እና ደላሎች በህግ ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሊቢያ፣ በጅቡቲ እና በሞያሌ ድንበሮች በኩል በህገ-ወጥ መንገድ ዜጎችን ሲያሸሹ በነበሩ ደላሎች ላይ የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በጉምሩክ እና ገቢዎች ዘርፍ የተዛባ የግብር ግምት በማድረግ፣ የታክስ ስወራ እንዲኖር በር በመክፈት፣ የገቢ እቃዎችን ዋጋ በመቀነስ እና ሀገሪቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገቢ እንድታጣ ከነጋዴዎች ጋር በመመሣጠር የሙስና መረብ የዘረጉ ባለሙያዎች እና አመራሮች ላይ የማጥራት እና የህግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። መንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል በማስደገፍ፣ አሰራሮችን በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን የጀመረውን የተቀናጀ ፀረ-ሙስና ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል። ህዝቡም ጥቆማዎችን በመስጠት እና ከጸጥታና ፍትህ ተቋማት ጎን በመቆም የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ከምክክር ጉባኤው የሚወጡ ውሳኔዎች የተሻለች ሀገርን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ ያስችላሉ
Aug 6, 2026 17
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ከምክክር ጉባኤው የሚወጡ ውሳኔዎች ለዘመናት የቆዩ ስብራቶችን በመጠገን የተሻለች ሀገርን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ እንደሚያስችሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህል ሽማግሌዎች ገለፁ። የባህል ሽማግሌዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ከምክክር ጉባኤው የሚወጡ ውሳኔዎች ለዘመናት የቆዩ ስብራቶችን በመጠገን የተሻለች ሀገርን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል። የሀዲያ የባህል ሽማግሌ ዳኛ ብርሃኑ ጡሞሮ፣ የምክክር ሂደቱ የልዩነት እሳቤዎችንና ጎታች አመለካከቶችን በመቅረፍ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። ጉባኤው የተሻለች ሀገርን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ የሚረዱ ውሳኔዎች የሚቀመጡበት መሆኑን ተከትሎ ወቅቱን በተስፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት። ከምክክር ጉባኤው የሚወጡ ውሳኔዎች ኢትዮጵያ የተደመረ አቅሟንና የውስጥ ጸጋዎቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ዕድገቷን እንድታረጋግጥ እንደሚያስችላት ተናግረዋል። የስልጤ ባህል ሽማግሌ ሼህ ሙዘይን ሰይድ በበኩላቸው፤ አለመግባባቶችን በመፍታት በአብሮነት ለመጓዝ የምክክር ሂደቱ ፍቱን መፍትሔ እንደሚያመጣ ተናግረዋል። በምክክሩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ተመካካሪዎች ከመላ ሀገሪቱ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ በመሆኑ ሙሉ ውክልና እንዳላቸው አመልክተዋል። እየተካሄደ ከሚገኘው የምክክር ጉባኤ በዜጎች መካከል ለልዩነት መንስኤ ሆነው የቆዩ ስብራቶችን በመጠገንና አብሮነታትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እንደሚጠብቁም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር የኢትዮጵያውያን በቅንጅት መጓዝ ቀዳሚው አማራጭ ነው ያሉት ደግሞ የጠምባሮ የባህል ሽማግሌ ታሪኩ በርገኖ ናቸው። ለዚህም ስኬት ያደሩ ችግሮችን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጠረጴዛ ዙሪያ በምክክር የጋራ ተግባቦት መፍጠር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል
Aug 6, 2026 35
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026/27 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በግብጽ ካይሮ ተካሄዷል። በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፈው ሲዳማ ቡና ከቻዱ ክለብ ኤግሎንስ ጋር ይጫወታል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ድል ከቀናው በቀጣዩ ዙር ከቡሩንዲው ኤግሌ ኖይር እና ከሱዳኑ አል ሂላል አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሱዳኑ አል ሂላል አልሳሂል ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። ወልዋሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፈ ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ባለቤት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን በነሐሴ 2018 ዓ.ም እና መስከረም 2019 ዓ.ም ያከናውናሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ
Aug 6, 2026 31
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም ከተማዋ ያላትን እምቅ አቅምና ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የታየ ሲሆን፤ እነዚህ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎች የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም ከተማዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ሚና ይበልጥ የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ነው የገለጸው። በተጨማሪም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ ድጋፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምም ለማየት መቻላቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ጎን ለጎን በአደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በደም ልገሳ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
Aug 6, 2026 41
አዳማ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ጎን ለጎን በአደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በደም ልገሳ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የአዳማ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ አሰታወቀ። ኤጀንሲው ከአዳማ ደም ባንክና ከከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ''በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ደም እንለግስ'' በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በወቅቱም የአዳማ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መኩሪያ ሹሚ እንዳስታወቁት፤ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ኤጀንሲው እያካሄደው ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል ነው። ኤጀንሲው በዋናነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ለተለያዩ አካላት ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ፣ በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በደም ልገሳ ለመድረስ የትራንስፖርት ተዋናዮችን በማስተባበር እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ለ5ኛ ጊዜ በአዳማ መናኸሪያ በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ 150 ዩኒት ደም ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልጸዋል። እሳቸውም ደም መለገሳቸውን ጠቁመው፤ ደም መለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት መታደግ በመሆኑ የሕሊና እርካታ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የአዳማ ደም ባንክ ኃላፊ አቶ ከተማ ደቀባ በበኩላቸው፤ በተሽከርካሪ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ድንገተኛ ሕክምና መስጠት የሚቻለው በቂ ደም ሲገኝ በመሆኑ ሁላችንም ደም መለገስን ባህል ልናደርግ ይገባል ነው ያሉት። ደም በመለገስ የወገንን ሕይወት መታደግ ሰብዓዊ አገልግሎት በመሆኑ ሕብረተሰቡ ይህን ተግባር ሊደግፍ ይገባል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ ደም ከለገሱት መካከል በአዳማ ደምበላ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ግንዛቤና ደኅንነት ክትትል ኃላፊ ኢንስፔክተር እሸቱ መሸሻ ለ15ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን ገልጸዋል። በዚህም በትራፊክ አደጋም ሆነ በወሊድ ወቅት የደም እጥረት ላጋጠማቸው ወገኖች በመድረሳቸው ደስታ እንደሚሰማቸውም ተናግረዋል። ሌላኛዋ ደም ለጋሽ የባጃጅ ትራንስፖርት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሳዲያ አብዲሪያ በበኩሏ፤ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በበጎ ፈቃደኝነት ደም መለገሷን ገልጻለች። በቀጣይም በየሦስት ወሩ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ደሟን ለመለገስ ማቀዷን ገልጻለች።
ፖለቲካ

በምክክሩ የተተገበረው የተመካካሪዎች አደረጃጀት ሁሉም ለሀገር ይበጃል የሚለውን ሀሳብ እንዲሰጥ ዕድል ፈጥሯል
Aug 6, 2026 109
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተግባራዊ የተደረገው የተመካካሪዎች አደረጃጀት ሁሉም ለሀገር የሚበጀውን ሀሳብ እንዲገልጽ ከማስቻሉም በላይ አሳታፊነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎችን በማሳተፍ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል። ተመካካሪዎቹ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረጋቸው ስምንት አበይት የመመካከሪያ አጀንዳዎች ላይ እየተመካከሩ ሲሆን አሳታፊነትንና የሀሳብ ብዝሃነትን ማስተናገድ በሚያስችል መልኩ በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተዋል። ይህም አስር፣ ሃምሳ፣ ሁለት መቶ ሃምሳ እና አምስት መቶ ሰዎችን በሚይዙ ቡድኖች ተደራጅተው እየተመካከሩ መሆኑ ይታወቃል። ተመካካሪ መሰረት ማቲዎስ ለኢዜአ እንደገለጹት ተመካካሪዎች በተፈጠረላቸው አደረጃጀት ሀሳባቸውን በነጻነት እየገለጹና በተቀራረቡ ሀሳቦች ወደ መግባባት እየመጡ መሆኑን ተናግረዋል። ምክክሩ ለሀገር አንድነትና ሰላም መጽናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሌላኛው ተመካካሪ አስቻለው አደራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተመካካሪዎች ትልቁን ሀገራዊ ማዕቀፍ በማሰብ ለሀገር የሚበጁ ሀሳቦች ላይ ወደ መግባባት እየደረሱ መምጣታቸውንና ምክክሩ በበጎ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ምክክሩ የሚደረግበት የቡድን አደረጃጀትም ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲያነሱ እና አሳታፊነቱንም ለማጠናከር ጥሩ ዕድል ፈጥሯል ነው ያሉት። ተመካካሪዎች ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ሃሳብ በነጻነትና አሳታፊ በሆነ መልኩ ማቅረብ በሚችሉባቸው ቡድኖች መደራጀታቸው የሁሉንም ተመካካሪዎች ሀሳብ ማስተናገድ የሚያሰችል ዕድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ ሀይለእየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ናቸው። የምክክር ሂደቱ አስር፣ ሃምሳ፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ከዛም አምስት መቶ ሰዎችን በያዙ ቡድኖች ተደራጅቶ መከናወኑ አሳታፊነትን መተግበር ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲያነሱ እንዳስቻለም ገልጸዋል። በመሆኑም ከምክክሩ የሚገኙ ምክረ ሃሳቦች ለበርካታ ዓመታት የልዩነት ምንጭ ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን ለመፍታት ያስችላሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን በመወከል የምክክር ሂደቱን እየታዘቡ መሆኑን የተናገሩት ለሚ ስሜ ምክክሩ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በማካተት ተመካካሪዎች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲያነሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የገለጹት። ተመካካሪዎች በንቃት እየተሳተፉ መሆንና በምክክሩም ደስተኛ መሆናቸውን መታዘባቸውን ገልጸው፤ ምክክሩ ሀገር መገንባት የሚያስችል የጋራ መፍትሔ ለማመላከት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
ምክክሩ ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመፍታት ለሀገራዊ መግባባት መሠረት የሚጥል ነው
Aug 6, 2026 89
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ አካታችና አሳታፊ የሆነው ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመፍታት ለሀገራዊ መግባባት መሠረት የሚጥል ነው ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍና ስምንት የምክክር አጀንዳዎችን በመለየት ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የምክክር ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል። በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው ምክክር አራት ሺህ ተመካካሪዎች እየመከሩ ይገኛሉ። ተሳታፊዎቹ ምክክሩ ልዩነቶችን በምክክር በመፍታት፣ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡ ተመካካሪ አቶ መሳሪያው ተንጎ ምክክሩ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች በማሳተፍ አካታችነቱ የተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡ በሂደቱ ሁሉም ተመካካሪዎች ሃሳባቸውን በነፃነት እያቀረቡ መሆናቸውን ጠቅሰው ለሀገር ዕድገት የሚበጁና ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት የሚያስችሉ ሃሳቦች እየተንሸራሸሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ከምክክሩ በኋላ ሀገራዊ መግባባቷ የተጠበቀና አንድነቷ የተረጋገጠባት ጠንካራ ሀገር እንደሚገነባም ጠቁመዋል፡፡ ተመካካሪ ወይኒቱ አዱኛ የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት አሳታፊነቱን በጠበቀ መልኩ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። ሂደቱ አካታችና ነፃ የሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑን አንስተዋል። አክለውም ከዚህ ምክክር በኋላ አንድነቷ የተጠናከረና ሰላሟ የበዛ ኢትዮጵያ እንደምትገነባም ተስፋቸውን ተናግረዋል። ተመካካሪ ሻም አሜ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ በመሆኗ ሂደቱም በፍቅር፣ በሰላምና በመግባባት የሕዝቦችን አንድነት ለማጠናከር እጅግ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባካሄደው ክትትልና ድጋፍ ውጤታማ አፈፃፀም እንዲመዘገብ አድርጓል
Aug 6, 2026 103
ወልቂጤ፤ ሐምሌ 30/2018(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባካሄደው ክትትልና ድጋፍ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ዕቅዶች ተግባራዊ ሆነው ውጤታማ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ማድረጉን ገለጸ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባካሄደው ክትትልና ድጋፍ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ዕቅዶች ተግባራዊ ሆነው ውጤታማ አፈፃፀም እንዲመዘገብ አድርጓል። ለዚህም የምክር ቤቱ አባላትም በቋሚ ኮሚቴዎች አማካይነት በአካል ክትትል ማድረጉንና ዕቅድና ሪፖርቶችን በማመሳከር የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ የልማት ሥራዎች እንዲሳኩ ክትትል በማድረግ ግብረ መልስ ከመስጠት ባለፈ፣ ተጠያቂነትን በማስፈን የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣቱን አስረድተዋል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤም በ2018 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ዕቅድ አፈጻጸም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በዋና ኦዲተር እና በምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አፈጻጸም እንዲሁም በያዝነው በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅዶች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል። በተጨማሪም የክልሉ የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ማስፈጸሚያ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንደሚጸድቅም ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ምክክሩ ለዘላቂ ሰላምና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ነው
Aug 6, 2026 124
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ምክክሩ ለዘላቂ ሰላምና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ነው ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱ ቀጥሏል። በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛል። ተመካካሪ አቶ ምስጋናው ስማቸው ለኢዜአ እንዳሉት በምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት የሚያነሱበት መሆኑን ገልጸው፤ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚያስችል ሂደት ላይ ነው ብለዋል። ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሁም የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑንም ተናግረዋል። ሌላኛዋ ተመካካሪ ወይዘሮ ጸጋነሽ በቀለ በበኩላቸው በምክክር ሂደቱ ሀሳቦች በነጻነት የሚስተናገዱና መግባባት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤው ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠ፣ ለልማትና ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ሀገርን ለመገንባት ወሳኝ መድረክ ነው ብለዋል። የምክክር መድረኩ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተወጣጡ ተመካካሪዎች በአንድ ሆነው ሃሳባቸውን የሚገልጽበት ትልቅ ሃገራዊ ጉባኤ ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ አቶ ሃብታሙ አስፋው ናቸው። ተመካከሪዎች ሀሳባቸውን ያለምንም ስጋት በነጻነት እያነሱ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በምክክር በመፍታት ለዘላቂ ሰላምና እድገት መሰረት ይጥላል
Aug 6, 2026 150
ሚዛን አማን፣ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፡-ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችና ልዩነቶችን በምክክር በመፍታት ሰላምና እድገትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ጠንካራ መሰረት እንደሚጥል የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ እየተካሄደ ያለውና የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰው ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል። ኢዜአ በሚዛን አማን ከተማ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች መካከል አቶ እጅጉ ጉርሜሳ እንዳሉት አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታት የማህበረሰቡን እሴቶች ወደ አደባባይ በማውጣት ለቆዩ ሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሀገራዊ ምክክሩ የሄደበት ርቀት ተሰፋ ሰጪ ነው። በኮሚሽኑ ለውይይት የተለዩ አጀንዳዎች የህዝብ አጀንዳ እንደሆኑና ለዘላቂ ሰላምና የህዝቦች አንድነት መፍትሄ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት አቶ እጅጉ፣ በተለይ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በምክክሩ እልባት ያገኛሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። በመተማመን ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅና ሀገራዊ ምክክሩ በዚህ ሂደት ያለፈ መሆኑን ያመለከቱት ደግሞ ወይዘሮ ማርታ ሽቢ የተባሉ ነዋሪ ናቸው። ህዝብን ወክለው በሀገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ አካላት በተለዩ አጀንዳዎች ላይ በሀላፊት ስሜት በመወያየት ለሁሉም የምትመች ሀገርን በመገንባት ረገድ ያላቸውን ሚና በአግባቡ እንደሚወጡ እምነታቸውን ገልጸዋል። በኮሚሽኑ ለውይይት የተለዩ አጀንዳዎች የኢትዮጵያ ህዝብ አጀንዳ ስለመሆናቸውና በምክክሩ ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸው፣ በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸው በሰለጠነ መንገድ በመወያየት ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት የተጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሁሉም ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ መንግሥቱ ሻምበል እና አቶ ግርማ አይነታ ናቸው። ችግሮችን በመሰረታዊነት በምክክር ለመፍታት ኮሚሽኑ በገለልተኛነትና ሁሉን አሳታፊ በሆነ መንገድ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ልምድ የሚወሰድባቸው ናቸው ብለዋል። ለምክክሩ በአጀንዳነት የለያቸው ጉዳዮችም በየደረጃው ህዝብ የተወያየባቸውን ሀሳቦች በአግባቡ አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ የምክክሩን ስኬት እንደሚያጎላው ጠቁመዋል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 4ሺህ የሕዝብ ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። ተመካካሪዎቹ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን የሚወክሉ ሲሆን ለውይይት በተለዩ ስምንት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይም ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ።
የምክክር ጉባዔው ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ዕድል የፈጠረ ነው
Aug 5, 2026 393
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ዕድል የፈጠረ መሆኑን የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪሎችም በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛል። በብሪታንያ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የጋራና አካታች በመሆኑ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው። በብሪታኒያ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባት ኡስታዝ ሙክታር ጀማል እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ኢትዮጵያ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ያስፈልጋት የነበረ ታላቅ እርምጃ ነው። ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ሂደት ነው ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባት ፓስተር አረጋ ሽፈራሁ በበኩላቸው፤ የምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ መሆኑንና እያንዳንዱ ተመካካሪ ሃሳቡን ያንፀባረቀበት ሁሉም በኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላምና ልማት እየመከረ ይገኛል ብለዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የሚያስችል ነው
Aug 5, 2026 344
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ የሚያስችል ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ስምንት የምክክር አጀንዳዎችን በመለየት ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የምክክር ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል። በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው ምክክር አራት ሺህ ተመካካሪዎች እየመከሩ ይገኛሉ። በምክክር ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ያስችላል። የምክክር ሂደቱ ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ የድርሻውን የሚያበረክትበት ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን በመግለጽ፣ ለሀገር ግንባታ የሚረዱ ሀሳቦችን እያንሸራሸሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ተመካካሪ ከተማ ባህሩ እንደገለጹት፣ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው በአጀንዳዎች ዙሪያ ላይ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ጠንካራ መድረክ ሆኖ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ መድረኩ የሀሳብ ብዝሃነትን በአግባቡ የሚያስተናግድና ሁሉም ተመካካሪዎች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲያንሸራሽሩ ሰፊ ዕድል ያመቻቸ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም ሂደቱ ሁሉንም የህብረተሰቡን ክፍሎች ያሳተፈና አካታች በመሆኑ ለሀገራዊ አንድነትና ውይይት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ተመካካሪ እቴነሽ ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ የምክክር ሂደቱ አካታች መሆኑን በመግለጽ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ትልቅ ዕድል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክክሩ አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን በመጠቆም፣ ሁሉንም ያሳተፈ መሆኑንና በሁሉም ጉዳዮች ላይ በግልጽ እየተወያዩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ እያካሄድነው ያለው ሀገራዊ ምክክር ለመጭው ትውልድ ደህንነቷ የተጠበቀ እና ሰላሟ የተረጋገጠች ሀገር ለማስረከብ የሚያስችል ነው ያለው ተመካካሪ ደግሞ አብዱላዚዝ አብዲ ነው፡፡ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባት የተፈጠረባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ ተስፋ እንዳለውም ተናግሯል።

ማህበራዊ
የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ጎን ለጎን በአደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በደም ልገሳ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
Aug 6, 2026 41
አዳማ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ጎን ለጎን በአደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በደም ልገሳ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የአዳማ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ አሰታወቀ። ኤጀንሲው ከአዳማ ደም ባንክና ከከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ''በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ደም እንለግስ'' በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በወቅቱም የአዳማ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መኩሪያ ሹሚ እንዳስታወቁት፤ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ኤጀንሲው እያካሄደው ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል ነው። ኤጀንሲው በዋናነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ለተለያዩ አካላት ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ፣ በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በደም ልገሳ ለመድረስ የትራንስፖርት ተዋናዮችን በማስተባበር እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ለ5ኛ ጊዜ በአዳማ መናኸሪያ በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ 150 ዩኒት ደም ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልጸዋል። እሳቸውም ደም መለገሳቸውን ጠቁመው፤ ደም መለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት መታደግ በመሆኑ የሕሊና እርካታ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የአዳማ ደም ባንክ ኃላፊ አቶ ከተማ ደቀባ በበኩላቸው፤ በተሽከርካሪ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ድንገተኛ ሕክምና መስጠት የሚቻለው በቂ ደም ሲገኝ በመሆኑ ሁላችንም ደም መለገስን ባህል ልናደርግ ይገባል ነው ያሉት። ደም በመለገስ የወገንን ሕይወት መታደግ ሰብዓዊ አገልግሎት በመሆኑ ሕብረተሰቡ ይህን ተግባር ሊደግፍ ይገባል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ ደም ከለገሱት መካከል በአዳማ ደምበላ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ግንዛቤና ደኅንነት ክትትል ኃላፊ ኢንስፔክተር እሸቱ መሸሻ ለ15ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን ገልጸዋል። በዚህም በትራፊክ አደጋም ሆነ በወሊድ ወቅት የደም እጥረት ላጋጠማቸው ወገኖች በመድረሳቸው ደስታ እንደሚሰማቸውም ተናግረዋል። ሌላኛዋ ደም ለጋሽ የባጃጅ ትራንስፖርት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሳዲያ አብዲሪያ በበኩሏ፤ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በበጎ ፈቃደኝነት ደም መለገሷን ገልጻለች። በቀጣይም በየሦስት ወሩ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ደሟን ለመለገስ ማቀዷን ገልጻለች።
በከተማ አስተዳደሩ የጤና ተቋማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ምቹና ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ ነው
Aug 6, 2026 36
ጎንደር ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የጤና ተቋማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር በመዘርጋት የህክምና አገልግሎቱን ምቹ፣ ጥራት ያለውና ፈጣን ማድረግ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ አስታወቀ። በከተማ አስተዳደሩ የሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ጤና ጣቢያ የዲጂታል አገልግሎት አሰራር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ተካሂዷል። የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰኢድ የሻው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በከተማዋ የሚገኙ የጤና ተቋማትን ዲጂታላይዝ በማድረግ ከወረቀት ነፃ የሆነ፣ ፈጣንና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ተችሏል። በከተማዋ ከሚገኙ ስምንት ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አምስቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር እውን በማድረግ ይነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ መቻላቸውን ገልጸዋል። በዚህም የመረጃ አያያዝን በማዘመን፣ የሕሙማንን እንግልት በመቀነስና የባለሙያዎችን ጊዜ በመቆጠብ ፈጣንና ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት መስጠት መቻሉን አስረድተዋል። መምሪያውም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 77 ሚሊዮን ብር ለጤና ተቋማቱ በመደገፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንባታና የግቢ ማስዋብ ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ማገዙን ተናግረዋል። በተጨማሪም የአጋር አካላትንና የማህበረሰቡን አቅም በማቀናጀት ሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ከማቀላጠፍ ባሻገር የሕክምና መሣሪያዎችና የመድኃኒት አቅርቦት የማሟላት ሥራ መሠራቱን አውስተዋል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር የቅዱስ ገብርኤል ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ታጀበ ታዬ እንደገለጹት፣ የወረቀት አልባ አሰራር የታካሚዎችን ምልልስና እንግልት ያስቀረ ነው። ታካሚዎች በየቦታው ወረፋ በመጠበቅ የሚያባክኑትን ጊዜና የሚደርስባቸውን እንግልት በማስቀረት አስተማማኝ ሕክምና እንዲያገኙ ማስቻሉንም ተናግረዋል። ይህም ደንበኞች በሕክምና አሰጣጡ ላይ ያነሱት የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ማስቻሉን አስረድተዋል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ እንደገለጹት፣ የከተማ አስተዳደሩ የሕክምና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ጥራትን ለማሻሻል በቅንጅት እየሠራ ይገኛል። በተጠናቀቀው ዓመት ብቻ አስተዳደሩ ለስምንቱም ጤና ጣቢያዎች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በጀት በመመደብ ዘመናዊ አሰራርን እንዲተገብሩ መደገፉን ገልጸዋል። ይህም የጤና ተቋማቱን ግቢና አካባቢውን ጽዱ፣ ውብና ማራኪ በማድረግ በከተማዋ ከተገነባው የኮሪደር ልማት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የሕክምና ተቋማቱን አሰራር ሳይንሳዊና ዘመናዊ በማድረግ ለኅብረተሰቡ ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ ሕክምና እንዲሰጡ ለማስቻል እንደሚሠራ አመላክተዋል።
መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው
Aug 6, 2026 97
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ። የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል ። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው ከውስጥም ከውጪም ያሉ በርካታ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው። እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል። በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል። በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል። በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል። ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል። በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፤ በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡ የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡ በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል። በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡ በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡ ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል። በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡ የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን በተለያዩ ዘርፎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ነው
Aug 6, 2026 41
ደብረ ማርቆስ፤ ሃምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፡-በምስራቅ ጎጃም ዞን በተለያዩ ዘርፎች በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መከናወናቸውን የዞኑ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ አሞኘሽ መሀመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ አብሮነትን የሚያጠናክሩና የዜጎችን የትብብር ባህል የሚያሳድጉ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በክረምቱ የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ተደራሽ ለማድረግ ተችሏል ብለዋል ። እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለውም ከ460 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እንደሆነ ተናግረዋል። ከተከናወኑት ተግባራት መካከልም ከ47 ሺህ በላይ ችግኝ መትከል፣ ከ240 በላይ የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በአዲስ መገንባትና መጠገን፣ እንዲሁም ከ21 ሺህ ሄክታር በላይ የአቅመ ደካሞች መሬትን በዘር የመሸፈን ስራ ይገኙበታል ነው ያሉት። በተጨማሪም የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ፣ የደም ልገሳና ሌሎች ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ጠቁመው፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉን አብራርተዋል። በዞኑ የአዋበል ወረዳ የወጀል ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ሙላት ጤናው በበኩሉ፣ በዚህ ክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገንና ደም በመለገስ ስራ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተናግሯል። ለወደፊትም ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል አቅመ ደካሞችን በጉልበቱ፣ በእውቀቱና በገንዘቡ ለመርዳት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። የአነደድ ወረዳ የአንበር ከተማ ነዋሪ ወጣት ሳሙኤል ሁነኛው በበኩሉ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አራት ዓመት እንደሆነው ገልጿል። በበጎ ፈቃድ ስራው በመሳተፉም አቅመ ደካሞችን ከመርዳት ባሻገር ከማህበረሰቡ ልምድና እውቀት በማግኘት ተጠቃሚ መሆኑን አስረድቷል። በዞኑ ባለፈው ዓመት ክረምት በተካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የልማት ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢኮኖሚ
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ይቀጥላል
Aug 6, 2026 13
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ገለጹ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሙስና፣ በብልሹ አሰራር እና በህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመለክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መንግሥት ከህዝብ የቀረቡለትን ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች መነሻ በማድረግ በልዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕቀፎች እና የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ያካሄዳቸውን ጥልቅ ፍተሻዎች፣ የምርመራ ውጤቶች እና የተወሰዱ የህግ ተጠያቂነት እርምጃዎችን አስመልክተው ነው ዝርዝር መግለጫ የሰጡት፡፡ በመግለጫቸው እንደጠቆሙት፤ የመደመር መንግሥት ያልተገባ ሀብት እና ጥቅም የመፈለግ አዝማሚያዎችን የሀገር እድገት አደጋ አድርጎ በመውሰድ ገና ከጠዋቱ ቀይ መስመር በማስመር ህጋዊ እና ተቋማዊ ሪፎርሞችን ሲያካሂድ ቆይቷል ብለዋል። ይህ መረጃ በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ በፌደራል ፖሊስ እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በጋራ የተቀናጀ ስልታዊ ጥናት፣ ክትትል እና ህጋዊ ፍተሻ የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ እርምጃዎች ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን የብዙሃን ዘርፍ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የህዝቦቿን ህይወት የመቀየር ሂደት ከሚያጋጥሙ እንቅፋቶች ለመጠበቅ ያለሙ ናቸው ብለዋል። በዚህም በትልቁ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ አደጋ ለመፍጠር፣ ምርቶችን በመጋዘን በመሸሸግ እና በመደበቅ የምርት እጥረት እንዲከሰት ያደረጉ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በመፍጠር በህብረተሰቡ ላይ የኑሮ ጫና እና ምሬት እንዲፈጠር ያደረጉ አካላት ላይ ሰፊ ኦፕሬሽን መካሄዱን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ የንግድ ተቋማት፣ ሱቆች እና መጋዘኖች በህግ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ እንዲዘጉም ተደርገዋል ብለዋል። ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመቀመር፣ በጥቁር ገበያ እና በህገ-ወጥ ሐዋላ በመሰማራት፣ እንዲሁም ነጋዴዎች ከባንክ ማግኘት የሚገባቸውን የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ እንቅፋት በሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬን በስውር በማንቀሳቀስ እና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት የተጠረጠሩ 169 ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት በህግ አግባብ ተጠያቂ ሆነዋል ብለዋል። በተጨማሪም በፋይናንስ ተቋማት፣ ኤቲኤም ማሽኖች እና በግለሰቦች አካውንት ላይ የሳይበር ማጭበርበር የፈጸሙ እና ያለፈቃድ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ የነበሩ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል። በሌላ በኩል፣ ያለፈቃድ በመንቀሳቀስ በማህበረሰቡ እና በወጣቶች ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ያመጡ፣ ግብር የሚሸሹ 36 ህገ-ወጥ የቤቲንግ ድርጅቶች እና በበየነ መረብ የሚሰሩ ተቋማት እንዲዘጉ እና በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል። ከሀገሪቱ አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው የማዕድን ዘርፍ በተለይም በወርቅ ምርት ላይ የሚከናወነውን የኮንትሮባንድ ዝውውር እና ድለላ ለማስቆም በተደረገ ተደራጅቶ የመስራት ምርመራ፣ ምርቱን ወደ ብሔራዊ ባንክ ከማስገባት ይልቅ ለማሸሽ የሞከሩ አምራቾች፣ አዘዋዋሪዎች እና ደላሎችን ጨምሮ 138 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል። መንግሥት ህዝቡን ከጫና ለመጠበቅ ከፍተኛ በጀት በሚመድብበት የነዳጅ አቅርቦት ላይ የሎጂስቲክስ እና የስርጭት አሻጥር በመፍጠር፣ ነዳጅን ወደ ጎረቤት ሀገራት በማሸሽ፣ መጋዘን ውስጥ በመደበቅ እና ኮታን ለግል ጥቅም በማዋል የቀውስ አዝማሚያ የፈጠሩ አካላት ተለይተዋል። በዚህ የተደራጀ ጥቅም ትስስር ውስጥ የተሳተፉ የመንግሥት አካላት፣ ነጋዴዎች እና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ስርዓቱን ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ጥብቅ መመሪያ ወጥቷል ብለዋል። አርሶ አደሩ ግብአቱን በወቅቱ እንዳያገኝ ያደረጉ፣ የኮንትራክተሮች እና የደላሎች አሻጥር ያለበት የተጋነነ ዋጋ ያለው ግዢ እንዲፈጸም ያደረጉ እና ግዢው እንዲጓተት ያደረጉ አካላት በጥልቀት ተመርምረዋል ብለዋል። በዚህም ድርጊት የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ደላሎች እና ግለሰቦች በህግ አግባብ ተጠያቂ ሆነዋል። በተቋሙ የፕሮጀክት ስራዎች ላይ የተጋነነ ዋጋ በመጠየቅ፣ የኃይል መሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲጓተቱ በመመሣጠር ሀገር ላይ የኢኮኖሚ ጫና ለማሳደር የሞከሩ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ ተባባሪ ኮንትራክተሮች እና ነጋዴዎች በጥናት ተደርሶባቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል። በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ማዕቀፍ የሚከናወነውን ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና የዜጎችን ደህንነት የሚያዛቡ፣ ህጋዊ ውል ከሌላቸው ሀገራት ጋር አየር በአየር እና በህገ-ወጥ ኤጀንሲዎች ውል በማስመሰል ሲላኩ የነበሩ፣ 8 ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ኤጀንሲዎች እና ደላሎች በህግ ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሊቢያ፣ በጅቡቲ እና በሞያሌ ድንበሮች በኩል በህገ-ወጥ መንገድ ዜጎችን ሲያሸሹ በነበሩ ደላሎች ላይ የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በጉምሩክ እና ገቢዎች ዘርፍ የተዛባ የግብር ግምት በማድረግ፣ የታክስ ስወራ እንዲኖር በር በመክፈት፣ የገቢ እቃዎችን ዋጋ በመቀነስ እና ሀገሪቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገቢ እንድታጣ ከነጋዴዎች ጋር በመመሣጠር የሙስና መረብ የዘረጉ ባለሙያዎች እና አመራሮች ላይ የማጥራት እና የህግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። መንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል በማስደገፍ፣ አሰራሮችን በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን የጀመረውን የተቀናጀ ፀረ-ሙስና ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል። ህዝቡም ጥቆማዎችን በመስጠት እና ከጸጥታና ፍትህ ተቋማት ጎን በመቆም የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ
Aug 6, 2026 31
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም ከተማዋ ያላትን እምቅ አቅምና ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የታየ ሲሆን፤ እነዚህ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎች የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም ከተማዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ሚና ይበልጥ የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ነው የገለጸው። በተጨማሪም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ ድጋፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምም ለማየት መቻላቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሰሶ ነው
Aug 6, 2026 61
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሰሶ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የአየር መንገዳችን ደማቅ የስኬት ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ ዘመናዊ ተርሚናል ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ፈርጀ ብዙ ኢኮኖሚያው ፋይዳ ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ከተማዋን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቀጥሎ የሁለተኛው ትልቅ የዓለም አቀፍ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚና እንዲኖራት የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ የላቀ ጥራትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከፍተኛ የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባው ይህ ደረጃውን የጠበቀ ተርሚናል፣ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶችን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን በቀጥታና በምቾት ለማስተናገድ በዕጅጉ እንደሚረዳም ነው የተናገሩት። በተጨማሪም የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በመጨመር ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ፣ በአቪዬሽን፣ በሆቴልና በትራንስፖርት ዘርፎች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም ባሕር ዳርን የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ሁነቶች ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ አቅምን እንደሚፈጥር አመልክተዋል። ፕሮጀክቶችን አቅዶ መጀመር፣ በጥራት ፈጽሞ ለህዝብ አገልግሎት ማብቃት የመደመር መንግሥት ባህልና መገለጫ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ የትጋትና የመፈጸም ጉዟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የውበት፣ የልምላሜና የፀዳል ተምሳሌት የሆነሽው ውቧ ባሕር ዳርና የአካባቢው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ! ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በባህር ዳር የተጀመሩ የኢኮኖሚና የመሰረተ ልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Aug 6, 2026 75
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ባህር ዳር የልማትና የእድገት ምሳሌ ሆና እንድትቀጥል የተጀመሩ የኢኮኖሚና የመሰረተ ልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር ከተማ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባህርዳር በተፈጥሮ ውበቷና በታሪካዊ እሴቶቿ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው የአፍሪካ አህጉር የልማትና የእድገት ምሳሌ መሆን የምትችል ከተማ መሆኗን ገልጸዋል። ከተማዋ ከመቶ ዓመታት በፊት በሸዋ፣በወለጋ እና በጎንደር መካከል ይደረግ ለነበረው ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ እንደ ዋና መሸጋገሪያ ድልድይ ሆና ስታገለግል መቆየቷን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም ታሪካዊ አሰፋፈር ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ትልቅ መነሻ መሆኑን አስረድተዋል። በጎርጎራ እና በባህርዳር መካከል የነበረውን ጥንታዊ የንግድና የቱሪዝም ትስስር ለማጠናከር በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣የጎርጎራ ሪዞርት እና የፈለገ ግዮን ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። በተጨማሪም እንደ ጣናነሽ ያሉ ትላልቅ መርከቦች በጣና ሀይቅ ላይ እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ በሁለቱ አካባቢዎች ያሉ ታሪካዊ ደሴቶችንና ቅርሶችን ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ ከመንግስት አልፎ በግሉ ዘርፍም በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል ነው ያሉት። ባህርዳር ከቱሪዝም በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ እቅም ያላት በመሆኗ የኢንዱስትሪ ፓርክ እንደተገነባላትም ነው የጠቀሱት። ከተማዋ በሀገር ደረጃ በምሳሌነት የሚጠቀስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ያላት መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም በአካባቢው የተገነባው ታላቅ ድልድይ እና በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን የበለጠ ውብና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምቹ የሚያደርጋት መሆኑን አብራርተዋል። በከተማዋ እየተገነባ ያለው ስታዲየም ሲጠናቀቅ ከሀገር ውስጥና ከአፍሪካ በርካታ ሰዎችን የሚስብ እንደሚሆንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወነውን የሪፎርም ስራ አድንቀዋል። የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ከቢሯቸው ሆነው በመላው ክልሉ የሚደረጉ ችሎቶችን በቨርቹዋል ለመከታተልና የህዝብን ቅሬታ ለመስማት የሚያስችል ዘመናዊ አሰራር በመዘርጋታቸው ምስጋና አቅርበውላቸዋል። አዲሱን የአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ግንባታ በተመለከተም፣ ቀድሞ የነበረው አሮጌ ተርሚናል በግጭት ምክንያት ጉዳት ቢደርስበትም፤ በችግሩ ከመበሳጨት ይልቅ አጋጣሚውን ወደ እድል በመቀየር ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገር የተሻለና የላቀ ተርሚናል መገንባት መቻሉን ተናግረዋል። ይህ አሰራርና ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ የመቀየር ባህል ወደፊትም ሊደገምና ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። አዲሱ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ከአብዛኞቹ የአፍሪካ ዋና ከተሞች ኤርፖርቶች የተሻለ አቅምና ደረጃ ያለው መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ታላቅ እቅም ወደ ሙሉ ስኬት ለመቀየር የህዝቡ ትጋት፣ ጥረትና የጋራ ስራ አስፈላጊ በመሆኑ፣ህዝቡ ጊዜውንና እድሉን ተጠቅሞ ለልማት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ሰላም ውድ ስጦታ፣ጊዜ ደግሞ ትልቅ ሀብት መሆኑን በማስገንዘብ፣ ህዝቡ በህብረት እንዲቆምና ሀገሩን እንዲያለማ ጠይቀዋል። ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች ቢኖሩ እንኳ እንደ ጨዋ ህዝብ በንግግርና በውይይት መፍታት እንደሚገባ፤ ነገር ግን በግጭት ጊዜ ማባከን እንደማይገባ በአፅንኦት አሳስበዋል። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ክልሉና ባህርዳር ከተማ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ የሚያስተዳድሩበት የተሟላ እድል አግኝተው እንደማያውቁ አውስተዋል። አሁን ግን በህግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት መስራትና ማሰራትን የሚችሉ የክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሉ ገልጸው፣ሁሉም ተባብሮ ባህርዳርን እንዲያለማ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የሲቪል ምዝገባ የዲጂታል ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ ነው
Aug 6, 2026 150
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጀመረው ዲጂታል የአሰራር ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሰራሩን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ አገልግሎቶቹን በኦንላይን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የኦንላይን አገልግሎቱ ገፅ ለ ገፅ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል፣ በላፕቶፕና በሌሎች ዲጂታል መሳሪያዎች በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ተቋሙ በአጠቃላይ ከሚሰጣቸው ሰባት ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል በአሁኑ ወቅት የመታወቂያ፣ የልደት እና ያላገባ ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በኦንላይን እየሰጠ ይገኛል። እስከ አሁን ከ15 ሺህ በላይ ተገልጋዮች በኦንላይን ሥርዓቱ አገልግሎት ማግኘታቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አዲሱ አሰራር የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ ከመቆጠቡም በላይ እንግልትን እያስቀረ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም አሰራሩ ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር የሥራ ቅልጥፍናንና ውጤታማነትን ማሳደጉን ገልጸዋል። ኤጀንሲው መረጃዎችን በዲጂታል ሥርዓት በማደራጀት ዘመናዊ የኦንላይን አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በቀጣይም የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የሞትና የጉዲፈቻ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎቶች ወደ ኦንላይን ሥርዓት በማስገባት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከጤና ተቋማትና ከፍርድ ቤቶች ጋር በመቀናጀት እንደ ልደትና ሞት ያሉ ኩነቶች በተከሰቱበት ቦታ ላይ በቀጥታ እንዲመዘገቡ የሚያስችል አሰራር እየተጠናከረ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። በኤጀንሲው እየተከናወነ ያለው ይህ የዲጂታል ሽግግር የኢትዮጵያን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ እና የከተማዋን የስማርት ከተማ ግንባታ ግብ እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡ አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በመገናኛ ብዙኃንና በተለያዩ አማራጮች ህብረተሰቡ ስለ ኦንላይን አገልግሎቱ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት ያሳያል
Aug 5, 2026 362
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን የቤኒን የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ገለጹ፡፡ በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትና በፋይዳ ቨርስ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ፈጣን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር እየተደረገ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ አስገራሚ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባትና ፈጣን የመንግሥት አገልግሎት ስርዓት ላስመዘገቡት ዕምርታ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያና ቤኒን መካከል ያለው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክፍተት በጋራ መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ልምድ መለዋወጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት በግልጽ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዲጂታል መሰረተ ልማት እያደገች መሆኑን መታዘባቸውን በመጥቀስ፤ ከዚህ መማር አጀንዳችንን ለማቀላጠፍ ያግዘናል ብለዋል፡፡ ቤኒን በሳይበር ደህንነት ያላትን ጠንካራ አቅም ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማሳደግ በአቅም ግንባታና በዕውቀት ልውውጥ በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ የፋይዳ ቨርስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ በበኩላቸው፤ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ለዲጂታል ዲፕሎማሲ አቅም ግንባታ የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ብዙ የተለመደው ከአውሮፓ ወይም ከኤዥያ የሚመጣን ስርዓት ማስተዳደር ነው ያሉት አቶ ዮዳሔ፤ ቴክኖሎጂን በራስ አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ሁሉም መገንዘቡን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የራሷን ቴክኖሎጂዎች በማፍለቅ ለሌሎች ትምህርት መስጠቷ አፍሪካውያን በራሳቸው እንዲተማመኑና ዕምነት እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ስያሜውንና ተልዕኮውን በመቀየር ራሱን ችሎ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር መካተቱን አንስተዋል፡፡ ይሄውም አገልግሎቱን ከኢትዮጵያ ውጪ በማስፋት በአፍሪካ ሀገራት ጭምር የማማከርና ስርዓት የመገንባት ዕድሎችን የምናገኝበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ የኢፌዴሪ የመሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ፤ መሶብ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን አሻሽሏል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ 108 የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በመክፈት ከ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ማገልገል ተችሏል ብለዋል፡፡ ከ220 በላይ አገልግሎቶችን በላቀ ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊ አሰራር በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ 98 በመቶ ማድረስ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡ መሶብ የኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመሻገር ህልም መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካ ሀገራት ልምድ የሚወስዱበትና የዲፕሎማሲ ተግባቦት የሚፈጠርበት ነው ብለዋል፡፡ የቤኒን ብቻ ሳይሆን የሌሎች ዓለም ሀገራት ጭምር አይተው የሚደነቁበት መሆኑን በማንሳት ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ብዙ ርቀት መጓዟን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን ኢንጂነሮችና በኢትዮጵያ ሀብት የለማ መሆኑ ኢትዮጵያውያን እውቀትና አቅማችንን አስተባብረን መስራት እንደምንችል አሳይቷል ብለዋል፡፡
ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት አስተማማኝ የልኬትና የካሊብሬሽን ሥርዓት መገንባት ወሳኝ ጉዳይ ነው - ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
Aug 5, 2026 216
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት አስተማማኝ የልኬትና የካሊብሬሽን ሥርዓት መገንባት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። 19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (ሜትሮሎጂ) ጠቅላላ ጉባዔ "ሥነ-ልክ ለዲጂታል ሽግግር፤ ተዓማኒ ልኬቶች ለአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በጠቅላላ ጉባዔው የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሙሉጌታ ደርበው (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (AFRIMETS) ፕሬዚዳንት ሔነሪ ኪበት ሮቲች (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የዘርፉ ተወካዮች ተገኝተዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በአንድ የአፍሪካ ሀገር የተመረቱ ምርቶች ተደራራቢ የጥራትና የልኬት ፍተሻዎችን አልፈው ወደ ሌላ ሀገር በነፃነት እንዲዘዋወሩ የተቀናጀ የልኬት ስታንዳርድ መዘርጋት አስፈላጊ ነው። አህጉራዊ የንግድ ትስስሩ ውጤታማ ሊሆን የሚችለውም ሀገራት ወጥና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የልኬት ቁጥጥር ሥርዓት ሲኖራቸው እንደሆነ አስረድተዋል። አክለውም የሜትሮሎጂ ሥርዓትን ማዘመንና ዲጂታላይዝ ማድረግ አፍሪካ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ለላቀ ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂዎች ዝግጁ እንድትሆን እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ከመደበኛ የሥነ-ልክ ሥርዓቶች ጋር በማጣመር የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤቶች አህጉራዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ የንግድ እንቅፋቶችን እንደሚያስወግድም ጠቁመዋል። የላቦራቶሪ ምርመራዎችንና የካሊብሬሽን አቅምን ማሳደግ የንግድ እንቅፋቶችን ከመቅረፉ ባሻገር፣ አህጉሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር በታማኝ የልኬት መረጃ ለማስደገፍ እንደሚያስችልም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዋ ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰራች መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር በመተባበር የሜትሮሎጂ ስታንዳርዶችን ለማጠናከርና የአፍሪካን የኢኮኖሚ ትስስር እውን ለማድረግ ሙሉ ቁርጠኝነቷን አረጋግጣለች።
የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎበኙ
Aug 5, 2026 259
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎብኝተዋል። የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ጉብኝት እያደረገ ነው። በኢፌዴሪ የመሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ ለልዑኩ ገለፃ አድርገውላቸዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው በገለፃቸው በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ዓመቱ ውስጥ ከ200 በላይ የመንግሥት አገልግሎት በተሟላ መሰረተ ልማት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማት እንደሆነ በመግለጽ ቅሬታ የሚበዛበትን የመንግስት አገልግሎት ግልፅና ቀልጣፋ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። አገልግሎቱ የመንግስት ተቋማትን በማቀናጀት ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎት በፍትሐዊነት መስጠት አስችሏል ብለዋል። የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን ሚኒስትሩና ልዑካቸው በቆይታቸው ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ። በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ኢኖቬሽንና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ላይ ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስፖርት
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል
Aug 6, 2026 35
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026/27 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በግብጽ ካይሮ ተካሄዷል። በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፈው ሲዳማ ቡና ከቻዱ ክለብ ኤግሎንስ ጋር ይጫወታል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ድል ከቀናው በቀጣዩ ዙር ከቡሩንዲው ኤግሌ ኖይር እና ከሱዳኑ አል ሂላል አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሱዳኑ አል ሂላል አልሳሂል ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። ወልዋሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፈ ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ባለቤት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን በነሐሴ 2018 ዓ.ም እና መስከረም 2019 ዓ.ም ያከናውናሉ።
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች
Aug 6, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና ትናንት ማምሻውን በአሜሪካ ኦሬጎን ተጀምሯል። ዛሬ ማለዳ ላይ በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ሽቶ ጉሚ 15 ደቂቃ ከ07 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈችው አትሌት እመቤት ጥላሁን 15 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ ከ51 ማይክሮ ሴኮንድ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ዩጋንዳዊቷ አትሌት ቻሪቲ ቼሮፕ 15 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ ከ88 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥታለች። ኬንያዊቷ ጆይሊን ቼፕኬሞይ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዳምጠው ከበደ 13 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ38 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በርቀቱም የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማማሩ ጎዴ 13 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ ከ41 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ኬንያዊው አትሌት ፍራንክሊን ኪቤት 13 ደቂቃ ከ28 ሴኮንድ ከ27 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል። ሌላኛው ኬንያዊ ኔሄሚያ ኪፕጌንዮ ሁለተኛ ወጥቷል። ከፍጻሜው በተጨማሪም በሻምፒዮናው መክፈቻ የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል። በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የመጀመሪያ ማጣሪያ አትሌት አልማዝ ዮሀንስ 9 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ ከ45 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜ አልፋለች። አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ ከ36 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍጻሜው ውድድር ተሸጋግራለች። የፍጻሜው ውድድር ነገ ይካሄዳል። በወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈው አትሌት ነጋሄ እያሱ 1 ደቂቃ ከ51 ሴኮንድ ከ16 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል። በሌላኛው የወንዶች 800 ሜትር የማጣሪያ ምድብ የተሳተፈው የሮሰን ግርማ 1 ደቂቃ ከ47 ሴኮንድ ከ57 ማይክሮ ሴኮንድ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈችው ደራርቱ ሽብሩ 2 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜው አልፋለች። እንዲሁም በሴቶች 800 ሜትር ምድብ አራት የተወዳደረችው ሀብታም ገበየሁ 2 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ ከ66 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተሸጋግራለች። የ800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ ውድድሮች ነገ ይካሄዳሉ።
በዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የመክፈቻ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ
Aug 5, 2026 187
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ኦሬጎን ይካሄዳል። ዛሬ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም በሚጀመረው ሻምፒዮና ላይ ከ147 ሀገራት የተውጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ። ኢትዮጵያም በሻምፒዮናው ላይ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እንዲሁም በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) ትሳተፋለች። በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ኦሬጎን ደርሷል። በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን በሁለቱም ጾታዎች የ5000 ሜትር የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ንጋት 11 ሰዓት ከ53 ላይ በ5000 ሜትር ሴቶች አትሌት ሽቶ ጉሜ እና አትሌት እመቤት ጥላሁን ይወዳደራሉ። በአጠቃላይ 27 አትሌቶች በፍጻሜው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። ነገ ጠዋት 12 ሰዓት ከ20 ላይ በሚደረገው የወንዶች የ5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዳምጠው ከበደ እና አትሌት ማማሩ ጎዴ የሚሳተፉ ይሆናል። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ። ምሽት 4 ሰዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው የ800 ሜትር ወንዶች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ነጋሄ እያሱ እና የሮሳን ግርማ ይሳተፋሉ። በአምስት ምድቦች ተከፍሎ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡ አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያው በቀጥታ ያልፋሉ። ምርጥ ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት ተጨማሪ አትሌቶች ግማሽ ፍጻሜ ይገባሉ። ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ በሚደረገው የ800 ሜትር ሴቶች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ደራርቱ ሽብሩ እና ሀብታም ገበየሁ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። በአምስት ምድቦች በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር፣ ከእያንዳንዱ ምድብ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ የሚወጡ አትሌቶች በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያልፋሉ። ከዚህ በተጨማሪ፣ የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት ተጨማሪ አትሌቶች ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ። 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። እ.አ.አ በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ በመሆን ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
በበጀት ዓመቱ ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ተግባራት ተከናውነዋል
Aug 5, 2026 146
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለፁ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እና የቀጣይ ሶስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን እና ዓመታዊ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት፤ በጉባኤው የባህል፣ የጥበባት እና ስፖርት ለሀገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በሳይንሳዊ መንገድ ለመደገፍና በቀጣይ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያነሱት ሚኒስትሯ፤ በበጀት ዓመቱ 47 የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት እና 5 ሀገር አቀፍ ክብረ በዓላት በተሳካ መንገድ መከበራቸውን ተናግረዋል። በነዚህ በዓላት ላይ ከ46 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በመሳተፍ ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከሩን አስረድተዋል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ባለፉት 28 ዓመታት ስራ ላይ የነበረው የስፖርት ፖሊሲ መሻሻሉን ገልጸው፤ ፖሊሲው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት ሙሉ ተቋማዊ ሪፎርም የማድረግና አሰራሮችን የማዘመን ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚከናወኑ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ ስፖርት ቱሪዝምን ማስፋፋት የሚያስችሉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለሃብቶች ወደ ስፖርቱ ዘርፍ በብዛት እንዲገቡ የማበረታታት ስራ መሰራቱን ጠቅሰው 29 ዓለም አቀፍ የስፖርት ኮንፈረንሶችና ውድድሮች በኢትዮጵያ መካሄዳቸውን አብራርተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን እያጎለበተ ነው
Aug 6, 2026 37
ሮቤ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን ከማጎልበት ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ አሻራ ማኖርን ያስተማረ ነው ሲሉ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህም ሀገሪቱ ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ ለመሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል። የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አንድምታ በተመለከተ ኢዜአ ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ጋር ቆይታ አድርጓል። ምሁራኑ እንዳሉት፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን ከማጎልበት ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ አሻራ ማኖርን ጭምር ያስተማረ ነው። ከዩኒቨርሲቲው ምሁራን መካከል የውኃና አካባቢ ጥበቃ ረዳት ፕሮፌሰር አለማየሁ አባታ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ ተአምር መስራት እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ነው። በሀገሪቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየጊዜው በሚተከሉ ችግኞች የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ እያገዘ መምጣቱንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግና የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አብራርተዋል። የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለተመሳሳይ ዓላማ ሲቆሙ ተአምር መስራት እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ነው ያስረዱት። በሀገሪቱ ዜጎች በ"ይቻላል" መንፈስ እውን የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዚሁ ህብረትና የተደመረ ሀገራዊ አቅም ማሳያ እንደሆነ አውስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ሳይንስ መምህርና የደን ዘርፍ ተመራማሪው አቶ ኡመር አብደላ በበኩላቸው፣ ሀገሪቱ እያሳካችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ዘለቄታዊና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት የአፈር ለምነትን በመጠበቅና የመሬት መራቆትን በመከላከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን አክለዋል። እንዲሁም ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅን በመቋቋም የግብርና ምርታማነትን ማሳደጉን አመልክተዋል። በተጨማሪም በደንና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ በተሰሩ ሥራዎች ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ከመቻሉም ባሻገር፣ ህዝቡ ለአንድ ሀገራዊ ግብ በጋራ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ የህብረትና የአብሮነት ባህሉን የሚያጠናክርበት ትልቅ መድረክ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። ምሁራኑ እንዳመለከቱት፣ እነዚህ ስኬቶች ኢትዮጵያውያን በራሳቸው እቅድ፣ አቅምና በጸና ህብረት ከተንቀሳቀሱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጡ ማሳያዎች ናቸው።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የብዝሃሕይወት መመናመንን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው
Aug 6, 2026 97
አሶሳ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን እና የብዝሃሕይወት መመናመንን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ንቅናቄው የህብረተሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እያሳደገ መምጣቱም ተመላክቷል። የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢ፣ ደን ሃብት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋር በመተባበር "ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛውን ዙር የአካባቢ ብክለት መከላከል የ6 ወራት ንቅናቄ አስጀምሯል። የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ እንደተናገሩት፤ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሥራን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ አበረታች ውጤት አስገኝቷል። የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን፣ የብዝሃሕይወት መመናመን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP-32) በፈረንጆቹ ህዳር 2027 ለማዘጋጀት መመረጧ በአገር አቀፍ ደረጃ ለምታከናውናቸው ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች የተሰጠ ትልቅ ዓለም አቀፍ እውቅና መሆኑንም ጠቁመዋል። ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ በትኩረት መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢ፣ ደን ሃብት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሉቅማን አብዱልቃድር ናቸው። የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን አካባቢን ውብ እና ጹዱ ከማድረግ ባለፈ ጤናማ ማኅበረሰብን ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንዳስቻለም ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ-ግብር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ የልማት ግቦች በማሳካት በኩል ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው
Aug 6, 2026 86
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የልማት ግቦች በማሳካት በኩል ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አመራር አባላት እና ሰራተኞች በቢሾፍቱ ፍጥነት መንገድ ዳርቻ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን እያስገኘ ነው። መርሃ-ግብሩ የአመራር እና የህዝብ ቁርጠኝነት የታየበት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት ተጨባጭ ለውጦችን ያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። አረንጓዴ ዐሻራ የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ ከማስቻል ባለፈ የደን ሽፋን እንዲጨምር በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተጽዕኖ መከላከል ማስቻሉንም ጠቅሰዋል። የካርቦን ሽያጭን በማጠናከር ኢትዮጵያ ከካርቦን ሽያጭ የምታገኘው ገቢ እንዲያድግም መርሃ-ግብሩ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመርሃ-ግብሩ ለምግብነት የሚውሉ በርካታ የፍራፍሬ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህም የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ የውጭ ምንዛሬ እንዲገኝ እያስቻለ ነው ብለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የልማት ግቦችን በማሳካት በኩል ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ መሆኑንም ተናግረዋል። በሚኒስቴሩ የመሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ መልካሙ ተሰማ በበኩላቸው፤ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ለቀጣዩ ትውልድ ቅርስ ነው፤ በመርሀ ግብሩ በመሳተፌ ደስተኛ ነኝ ብለዋል። በችግኝ ተከላ ላይ በተለያዩ ጊዚያት መሳተፋቸውን የገለጹት ወይዘሮ ጸሀይ በቀለ በበኩላቸው፤ ዛሬ የምንተክለው ለትውልዱ አርአያ ለመሆንም ጭምር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በቀጣይም ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ በኩል የሚጠበቅብኝን ሃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል።
የመደመር ፍሬ፡አረንጓዴዋ ኢትዮጵያ
Aug 5, 2026 357
በሙሴ መለሰ የመደመር እሳቤ ዋና መሠረቱ እውቀትን፣ጉልበትን፣ሀብትንና አቅምን አስተባብሮ ለአንድ የጋራ ዓላማ በጋራ ማቆምን ያመለክታል። ይህን የሃሳብ ልዕልና በተግባር ፈትሾ ተጨባጭ ውጤት የታየበት ላለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነው። አረንጓዴ ዐሻራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም ጅማሮውን አግኝቷል። የአረንጓዴ ዐሻራ ትልቁ ማሳያ የህዝብ ህብረት የታየበት መሆኑ ነው። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እድሜ፣ ጾታ እና ልዩነት ሳይበግራቸው በነቂስ በመውጣት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አኩሪ ታሪክ የሰሩበት ህዝባዊ ንቅናቄ የመደመርን አስተሳሰብ በተግባር ያረጋገጠ ነው። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ ከተካሄደው የአንድ ጀምበር መርሃ ግብር እንደታየው፣መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ምንም ክፍያ በሙሉ ፈቃደኝነት እና በዝናብ ውስጥ ውሎ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ሰርቷል። በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላው 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን ተደምረው ለነገ ልጆቻቸው መሰረት ለመጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ ያሳዩበት ህያው አብነት ነው። የመደመር እሳቤ በቃላት ሳይሆን በተጨባጭ ውጤት የሚለካ ነው፤ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ዘመቻ እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ቀሪው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ደግሞ በቀጣይ ጊዜያት ይተከላል። በአንድ ወቅት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፋን የነበራት ኢትዮጵያ ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሃብትና የመሬት አጠቃቀም ምክንያት የደን ሽፋኗ ወደ 3 በመቶ ወርዶ ነበር። አረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ የደን ሽፋን ከነበረበት 17.2 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ችግኝ ተከላው ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ከምግብ ዋስትና እና ከሀገር ኢኮኖሚ ጋርም የተሳሰረ ነው። በፍራፍሬ እንደ አቮካዶ፣ማንጎ እና ቡና ባሉ ምርታማ ችግኞች ላይ በማተኮሩ የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር፣ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የምትበለጽግ፣የማትለምን እና ለተቸገሩት የምትደርስ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል የዜጎችን ገቢ የማሳደግ ድርሻ አለው። ኢትዮጵያ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ያከናወነቻቸው የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስራዎች የመደመር እሳቤ ድንበር አቋርጦ ለአህጉራዊ ትስስር እና ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ የሚሆን ድንበር ተሻጋሪ እሴት እንዳለው ያሳያል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዋ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል። ይህም የኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቷል። በአጠቃላይ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በቀና እሳቤ እና በትብብር በመቆም ተስፋን ለልጆቻቸው መዝራት እንደሚችሉ በተግባር፣በስራና በውጤት ያረጋገጡበት ትልቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 280
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 337
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 649
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1107
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
ያቀደችውን በተግባር የምታሳካ ታላቅ ሀገር
Aug 3, 2026 606
የአንድ ሀገር ታላቅነት ከሚለካባቸው ጉዳዮች አንዱ የተያዙ ሀገራዊ እቅዶችን በተግባር የመለወጥ አቅም ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አዲስ ታሪካዊ ስኬት፣ ሀገሪቱ ያቀደችውን በተግባር ማሳየት የምትችልና ትልልቅ ህልሞችን የመተርጎም አቅም ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ ነው። ይህ በአንድ ጀምበር የተከናወነ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በርካታ ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ነው፡ በአንድ ጀንበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ግዙፍ የሎጂስቲክስ፣ የዝግጅትና የህዝብ ንቅናቄ ስራን ይጠይቃል። ይህ ስኬት ሀገሪቱ ማንኛውንም ታላቅ አገራዊ እቅድ አቅዳ እስከ መጨረሻው የትግበራ ምዕራፍ ድረስ በብቃት የመምራትና የማስተባበር ተቋማዊና ህዝባዊ አቅም እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዕድሜ፣ ጾታ፣ ወይም ልዩነት ሳይለያያቸው በአንድ ቀን ለተመሳሳይ አገራዊ ዓላማ መቆማቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለጋራ እድገታቸውና ለሀገራቸው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና አንድነት አሳይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት ዋና ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ እርምጃ ለችግሩ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የዓለም አቀፍ መሪነቷን ያስመሰከረችበት አጋጣሚም ጭምር ነው። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የገጠሟትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ተሻግራ፣ አቅሟን አስተባብራ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደምትችል ለዜጎቿም ሆነ ለውጭው ዓለም የሰጠችው ትልቅ የራስ መተማመንና የተስፋ መልእክት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ጀምበር የተከናወነው ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ አርቆ የማሰብና የማቀድ ችሎታዋን ብቻ ሳይሆን፣ ያቀደችውንም በአንድነትና በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሀገር መሆኗን በግልጽ ያረጋገጠ አኩሪ ተግባር ነው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ትንሳኤ ብስራት!!
Aug 2, 2026 427
በሐዊ አጫሉ መግቢያ፡- የኢንዱስትሪ ዘርፍ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬን ከሚወስኑ ዋነኛ የብልፅግና ማረጋገጫ ምሰሶዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ዘርፉ ምርትን ከማሳደግ ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን የሚያፋጥን የልማት ሞተር ነው። ኢትዮጵያም ከግብርና መሠረት የተነሳ ኢኮኖሚዋን ወደ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን አቀፍ የምርት ሥርዓት ለማሸጋገር ከምታደርገው ጥረት መካከል ኢንዱስትሪውን በቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶነት በማካተት እየሰራችበት ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ አምስት ዐበይት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ምሰሶዎች ተመሥርቶ እየተመራ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ ኢንዱስትሪው የምርት አቅምን በማሳደግ የግብርና ምርቶችን ወደ ተጨማሪ እሴት በመቀየርና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ እያስገኘ ነው። ይህንን ሽግግር እውን ለማድረግ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ የቀድሞ ገጽታ፤ ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ለውጥ መንገድ!! በቀደሙት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተለያዩ ዕድሎችንና ፈተናዎችን በማስተናገድ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። ሀገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር በተደረጉ ጥረቶች የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል። እነዚህ ፓርኮችም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በግብርና ምርት ማቀነባበር ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሞከረበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ጉዞ በበቂ መሠረተ ልማት፣ በተሟላ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና በተቀናጀ የምርት ሰንሰለት እጥረት ምክንያት በበርካታ ፈተናዎች ለመውደቅ ተገዶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ውስንነት፣ ዕውቅትና ክህሎትን የተሰላበሰ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የፋይናንስ እጥረት፣ ውስብስብና አስቸጋሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትና የገበያ ትስስር እጥረት የዘርፉን እድገት ገድበው የነበሩ ሁነኛ ተግዳሮቶች ናቸው። ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ምርታማነት፤ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የለውጥ ፍኖት!! ባለፉት ዓመታት በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተስተዋሉ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታትና የሀገሪቱን የማምረት አቅም ለማሳደግ አዳዲስ የለውጥ አቅጣጫዎች ተነድፈው ተተግበረዋል። በተለይም ኢንዱስትሪን ከተለመደው የምርት ሥርዓት በማሻገር ወደ ተወዳዳሪ ዘመናዊና ውጤታማ የማምረቻ ማዕከል ለመቀየር የተለያዩ የፖሊሲማሻሻያዎች ተደርገዋል። የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ማስፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን፣ የሰው ኃይል አቅምን ማሳደግና የግብርና-ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር በዘርፉ የተወሰዱ ሁነኛ የለውጥ እርምጃዎች ናቸው። በዚህም የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ከሀገር ውስጥ ገበያ እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ድረስ ውጤት እያስገኘ ነው። የግል ባለሃብቱ ሚና፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሞተር!! የኢንዱስትሪ ልማት በመንግሥት ጥረት ብቻ የሚሳካ አይደለም። የግል ዘርፉ በካፒታል፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂና በአስተዳደር ብቃት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። በዚህ ረገድ የግል ባለሃብቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዋና አጋር እንዲሆን የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተሻሽለው እየተሰራባቸው ይገኛል። ይህም የግሉን ዘርፍ የኢንቨስትመንት በማሻሻል፣ የንግድ ሥራ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የምርት አቅምን በማሳደግ የግሉን ዘርፉ የምርታማነት አቅም እያጎለበተ ነው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ የትንሳኤ ብስራት!! በሀገራችን የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ የምርትና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀናጀት አዲስ ምዕራፍ ከከፈቱ ዐበይት ሀገራዊ መርሃ-ግብሮች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት ባህልን በማሳደግ ዘርፉ ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ የሚሸጋገርበት ሁነኛ ዕድልን ፈጥሯል። ንቅናቄው የማምረት አቅምን በማሳደግ ሥራ ያቆሙ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ መመለስ፣ የአምራቾችን ችግሮች በፍጥነት መፍታትና አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ በመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል። በዚህ ሂደት በፋይናንስ፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬና በተቋማዊ ቅንጅት ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎች የአምራች ዘርፉን የምርታማነት አቅም በማጎልበት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲያንሰራራ በማድረግ የምርታማነት አብዮት እንዲቀጣጠል እያደረገ ይገኛል። የንቅናቄው ዋና ዓላማ በአምራች ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ማሳደግ ነው። ይህም ሥራ ያቆሙ ወይም በአቅማቸው ልክ ያልሠሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሙሉ ምርት በመመለስ የአምራቾችን ችግር በተቀናጀ መንገድ መፍታት፣ የፋይናንስና የግብዓት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጓል። በዚህ ሂደት የማምረቻ ዘርፉ በአዲስ የሥራ ባህል፣ በተቋማዊ ቅንጅትና በፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እየተመራ መሆኑ የለውጡን ፍጥነት እያሳደገው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ተደራሽነትን ማሻሻልና የምርት ጥራትን ማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ትንሳኤ ዋና ማሳያዎች ናቸው። ለአብነትም፡- የፋይናንስ አቅምና የብድር አቅርቦት ማሻሻል፡- የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብ፣ የብድር አቅም ቀደም ሲል ከነበረበት 40 ቢሊዮን ብር ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል በማድረግ ለአምራቾች ሰፊ የካፒታል አቅም መፍጠር ተችሏል። የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የግብዓት ድጋፍ ማደግ፡- ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ይቀርብ የነበረው የውጭ ምንዛሬ መጠን አሁን ላይ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህም ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች እንዲሠሩ ያስገድድ የነበረውን የምርት ውስንነት በከፍተኛ ደረጃ አቃሎታል። የምርት ዕድገት፣ ተኪ ምርትና የኤክስፖርት አፈጻጸም፡- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከነበረበት 348 ሚሊዮን ዶላር ወደ 5.9 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል ተመዝግቧል። እንዲሁም በኤክስፖርት ገበያ የሚገኘው ገቢ ከ385 ሚሊዮን ዶላር ወደ 607 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለት ችሏል። ተቋማዊ ቅንጅትና አዲስ የሥራ ባህል ማዳበር፡- በክልሎችና በፌዴራል ተቋማት መካከል የነበረውን የቢሮክራሲ ጫና በመቀነስ ፈጣን ውሳኔዎች እንዲሰጡ መደረጉ፤ እንዲሁም ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርትን በኩራት የመጠቀም እና የሀገር ፍቅር ስሜትን ከአምራችነት ጋር የማስተሳሰር ትልቅ ማህበራዊ ንቃተ-ህሊና መገንባት ተችሏል። የወደፊት ተስፋ፤ ኢትዮጵያ አዲሲቷ አፍሪካዊት የኢንዱስትሪ ምርታማነት ተምሳሌት ሀገር!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ በቀጣይ ዓመታት ከተለመደው ማምረት ወደ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ሥርዓት እንዲሸጋገር ይጠበቃል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የፈጠራ ሥርዓቶችን ወደ ማምረቻ ዘርፉ ማስገባት የወደፊቱ ትኩረት ይሆናል። በተመሳሳይም ጠንካራ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስር፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአህጉራዊ ገበያ ተደራሽነት የሀገሪቱ ቀጣይ የኢንዱስትሪ ግቦች ናቸው። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ማጠቃለያ፡- ማምረት፤ የኢትዮጵያ የብልፅግና ቁልፍ መሳሪያ!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል፣ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ተጨማሪ እሴት ያለው ምርት አቅራቢነት በማምራት እመርታዊ ውጤቶችን እያስገኘ ነው። የኢንዱስትሪውን አቅም ማሳደግ ማለት ፋብሪካዎችን ብቻ ማስፋፋት ሳይሆን የሀገርን ምርታማነት፣ የወጣቶችን ዕድል፣ የኢኮኖሚ ነፃነትንና የልማት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን የዛሬ ልማት ብቻ ሳይሆን የነገውን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚገነባ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር
Aug 2, 2026 314
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ) የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል። በክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5 ዓመት 3ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አንስተዋል። የሜካናይዜሽን እርሻም ተግባራዊ በመደረጉ ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም ጠቅሰዋል። ከማዕድን ዘርፍም በበጀት ዓመቱ ከ 8 ሺህ 900 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል። ኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት በማድረግ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሪፎርም እየተተገበረ ይገኛል። ለዚህም የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ይፋ የማድረጊያ መርሃ ግብር ''የአገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና'' በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል እስከ ቀበሌ የደረሰ አሰራር መዘርጋቱን በወቅቱ አንስተዋል። አልግሎቶችን በዲጂታል ስርዓት በመደገፍ የህዝቡን እንግልት፣ ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። ይህም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ሲዳማ ክልል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ ማድረግና በግብአት ለማሟላት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ በማድረግ በትምህርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲታይ መደረጉንም አስረድተዋል። ጋምቤላ ክልል የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ ያስጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። በክልሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች በህዝብ ተሳትፎ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል ። ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ ከማድረጋቸው ባለፈ የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልፀዋል። አማራ ክልል በአማራ ክልል የግብርናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪዎች ግብአት ማምረት ተችሏል። የዚሁ አካል የሆነው በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ 837 አርሶ አደሮች በማህበር በመደረጃት “የጅሩ-አግሮ ቢዝነስ“ ኩባንያን መስርተዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ኩባንያው የአርሶ አደሮችን ምርት በማቀነባበር ለገበያ የሚያቀርብ ነው። የአግሮ-ቢዝነስ ኩባንያውም ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከጥሬ ግብአት አቅራቢነት ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስተርነት በማደግ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል። ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳዳር ዙሪያ ጨታ ቀበሌ የተገነባውን የባቾ ገጠር ሞዴል መንደር መርቀው ለነዋሪዎች አስረክበዋል። በወቅቱም የሞዴል የገጠር መንደሩ መገንባት የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ብሎም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል። በሌላ በኩል በክልሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በተለይም የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በመገንባት የወረዳና ቀበሌዎች ማህበራዊ ትስስር እንዲጠናከርና የግብይት ሰንሰለትም እንዲቀላጠፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ለአብነትም በክልሉ ኮንታ ዞን በአመያ ዙሪያ ወረዳ በኡማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናት ችግር ያቃለለና ለመሰረተ ልማት ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። በመልእክታቸውም በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ስለመሆኑ ተናግረዋል። በ2019 በጀት ዓመትም በክልሉ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ለዚህም በህግና የአሠራር ስርአት በመታገዝ የገቢ አቅምን በማስፋት የክልሉን ዕድገት ዘላቂነት በማረጋገጥ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል ። በ2019 በጀት አመትም የክልሉን የገቢ አቅም ለይቶ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ የግብር እቅድን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል። በዚህም በበጀት አመቱ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ገቢውን ለማሳካትም የህግና የአሠራር ስርአት በመዘርጋት የክልሉ ዕድገት በዘላቂነት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። አፋር ክልል በአፋር ክልል የእንሰሳትና ዓሳ ሀብትን በማልማት ለወጣቶች የስራ እድልን ለማስፋት የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ የእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ገልጸዋል። ለዚህም ስምንት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሐይቆች ላይ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ አሳ ልማት ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል። ለአብነትም በአፋምቦ ሐይቅ ላይ 200 ወጣቶች በዓሳ ሀብት ልማት ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን አስረድተዋል። በዓሳ ሀብት ልማቱ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች እንዳሉት የአሳ ሀብትን አልምተው ተጠቃሚ ለመሆን በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ ናቸው። ስራውንም ለማሳካት ክልሉ እያደረገ ያለው የሙያ ስልጠናና ድጋፍ የማይተካ ድርሻ አለው ብለዋል። ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "ሁሉ አቀፍ እመርታ ፣ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። ርዕስ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል። የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ክልሉን የህብረ ብሄራዊነት ተምሳሌት ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከርና የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የመድረኩ ዋና ዓላማ ስለመሆኑም ገልጸዋል። ሐረሪ ክልል የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር እንደገለፀት፤ በክልሉ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ስራ በገጠር ወረዳዎች የመስኖ ልማት በስፋት ተከናውነዋል። ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ የ2018 የግብርና ልማት እቅድ አፈጻጸምና የ2019 የግብርና ልማት መሪ እቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የእንስሳት ተዋጽኦና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ትልቅ እመርታ የተገኘበት ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባሻገር የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል። ሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን ሲያካሂድ ርእሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ሙሀመድ፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የሰላምና የልማት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስራዎችና የመጡ ውጤቶችን አብራርተዋል። የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው፤ የፍትህ አካላትን አቅም ለመገንባት በተደረገ ጥረት የፍትህ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን መቻሉንም አንስተዋል። በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በድህነት ቅንሳ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የሚመጡ አደጋዎች ቅነሳም ከፍተኛ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
ከሀገር አቀፍ ንቅናቄ እስከ ዓለም አቀፍ እውቅና፦የአረንጓዴ አሻራ ውጤታማ አበርክቶ
Jul 30, 2026 642
በታዋቂ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሔቶች ላይ የታተሙ ተከታታይ ጥናቶች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በደን መልሶ ማልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተዕፅኖን በመከላከል ፣ የካርበን ክምችት በማሳደግ እና በማህበረሰብ ተሳትፎ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን አረጋገጡ። የጥናቱ ግኝቶች ከስምንት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመረው የአረጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር፣ በአፍሪካ ግዙፍ እና እጅግ ውጤታማ ወደሆነ የመሬት ገጽታ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ማደጉን የሚያሳይ ጠንካራ ሳይንሳዊ ማስረጃ አቅርበዋል። ኔቸር ፖርትፎሊዮ (Nature Portfolio)፣ ኤልሴቪየር (Elsevier) እና ስፕሪንገር (Springer)ን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው አሳታሚዎች እ.ኤ.አ. በ2026 የወጡ አምስት ጥናቶች፤ የሳተላይት ምስሎችን፣ የመስክ የዳሰሳ ጥናቶችን፣ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የመርሐ-ግብሩን አካባቢያዊ ፋይዳ ገምግመዋል። ከፍተኛ የችግኝ ጽድቀት ምጣኔ - የውጤታማ መልሶ ማልማት ማሳያ በኤልሴቪየር 'ትሪስ፣ ፎረስስ ኤንድ ፒፕል' (Trees, Forests and People) መጽሔት ላይ የታተመ ጥናት (አሰፋ እና ሌሎች፣ 2026) እንዳመለከተው፣ በደቡብ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ የዛፍ ችግኞች 80 በመቶ የሚገመት የጽድቀት ምጣኔ አስመዝግበዋል፤ ይህም ከሌሎች በርካታ ሰፊ የደን ልማት ፕሮግራሞች ልቆ የተገኘ ነው። ተመራማሪዎቹ ለዚህ ስኬት በዋነኛነት የጠቀሷቸው የተሻሻሉ የመልሶ ማልማት ልምዶችን ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል በዋናው የክረምት ወቅት መትከል፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የቦታ ምርጫ፣ እንዲሁም በቴክኒክ ስልጠና የታገዘ ጠንካራ ማህበረሰብ አቀፍ እንክብካቤ ይገኙበታል። የጥናቱ መሪ ዶ/ር ታደሰ አሰፋ እንደገለጹት፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ከሳይንሳዊ የደን አያያዝ ጋር ማቀናጀት አዳዲስ ተከላ የተካሄደባቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ የችግኝ መትከያ ቦታዎች ብቻ ሆነው ከመቅረት ይልቅ ዘላቂ ወደሆነ ደንነት እንዲያድጉ አስችሏል። የማህበረሰብ ተሳትፎ ለስኬቱ ሞተር ነው በስፕሪንገር 'ዲስከቨር ኢንቫይሮመንት' (Discover Environment) ላይ የታተመ ሌላ ጥናት ደግሞ ሰፊው የማህበረሰብ ተሳትፎ የመርሐ-ግብሩ ታላቅ ጥንካሬ መሆኑን አመልክቷል። የጥናቱ መሪ ዶ/ር አብዱረዛቅ ሀጂ እንዳስገነዘቡት፣ እያደገ የመጣው የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እና በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የህዝብ ተነሳሽነት፣ አባወራዎች ችግኝ መትከልን የአካባቢን የመቋቋም አቅም ለመገንባት፣ ለዘላቂ ግብርና እና ለወደፊት የኑሮ መሰረት እንደተደረገ ኢንቨስትመንት እንዲመለከቱት አድርጓል። የህዝብ ተሳትፎ የመርሐ-ግብሩ የረጅም ጊዜ ስኬት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ጥናቱ በማጠቃለያው አስቀምጧል። የደን ሽፋን ማደግ የአካባቢን አየር ንብረት ያሻሽላል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ቡኖ በደሌ ዞን የተካሄደ ጥናት በስድስት ዓመታት ውስጥ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን፣ ማለትምከ27.64 በመቶ ወደ 38.24 በመቶ ከፍ ማለቱን አስመዝግቧል። ጥናቱ የመሬት ገጽ የሙቀት መጠን እስከ 1.16 ዲግሪ ሴልሺየስ መቀነሱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ይህም የደን ሽፋን መስፋፋትየአካባቢውን አየር ንብረት እያሻሻለ እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን እያጠናከረ መሆኑንያሳያል። እነዚህ ለውጦች የስነ-ምህዳር አገልግሎቶችን እንደሚያሳድጉ እና የግብርና ምርታማነትን እንደሚደግፉ ይጠበቃል ሲሉ ተመራማሪዎቹተናግረዋል። ጥናቶች ከፍተኛ የካርበን ክምችት አቅም መኖሩን አጉልተዋልበኔቸር ፖርትፎሊዮ (Nature Portfolio) ሥር በ'ሳይንቲፊክ ሪፖርትስ' መጽሔት ላይየወጣ ሌላ ጥናት፣ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች እና የግብርና-ደን ሥርዓቶች ከፍተኛ መጠንያለው የካርበን ዳይኦክሳይድ ክምችት የመያዝ አቅም እንዳላቸው አረጋግጧል። አንዳንድ መልመው ያገገሙ መሬቶች በሄክታር ወደ 500 ሜጋግራም የሚጠጋ የካርበን ዳይኦክሳይድ መጠን የያዙ መሆናቸው የተረጋገጠሲሆን፣ ይህም መርሐ-ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥን በማቃለል ረገድ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያሳያል። የደን መልሶ ማልማት ስራውን ማስፋፋት የኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ተሳትፎ የበለጠ እንደሚያጠናክርናበማደግ ላይ ባለው የዓለም አቀፍ የካርበን ገበያ ላይ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የደን ዕድገቱ እንደሚቀጥል ተንብዮአል ማሽን ለርኒንግ፣ የሳተላይት ምስሎች እና የጂኦስፓሻል ትንታኔዎችን በመጠቀም በስፕሪንገር 'ኢንቫይሮመንታል ሞኒተሪንግ ኤንድአሴስመንት' (Environmental Monitoring and Assessment) መጽሔት ላይ የታተመ ሌላ ጥናት እንዳመላከተው፣አሁን ያለው የመልሶ ማልማት ጥረት ከተቀጠለ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ቢያንስ እስከ 2035 ድረስ መስፋፋቱን እንደሚቀጥልተንብዮአል። በመሬት ገጽታ መልሶ ማልማት ላይ የሚደረገው ተከታታይ ኢንቨስትመንት የደን ሽፋንን የበለጠ እንደሚያሳድግ፣ የካርበን ክምችትንእንደሚያጠናክር እንዲሁም የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የዘላቂ ልማት ግቦችን እንደሚደግፍ ጥናቱ ያሳያል። ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ እውቅና በአጠቃላይ ሲታይ፣ አምስቱ ገለልተኛ ጥናቶች የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ሁለንተናዊ ሳይንሳዊ ግምገማ በማቅረብ፤በደን መልሶ ማልማት፣ በካርበን ክምችት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና በህዝብ ተሳትፎ ረገድ የሚለኩና ተጨባጭ ውጤቶችንማምጣቱን ደምድመዋል። እነዚህ ግኝቶች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የሰፊ ሥነ-ምህዳር መልሶ ማልማት ቀዳሚ ሞዴል በማድረግ ያስቀመጡትሲሆን፤ ዘላቂ የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ ሳይንሳዊ ዕቅድ እና አገር አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ እንዴት ተጨባጭ የአካባቢ ጥበቃ ውጤቶችንማምጣት እንደሚችሉና፣ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመሬት መራቆትን ለመከላከል ለሚደረጉ ጥረቶች ከፍተኛ አስተዋጽዖእንደሚያበረክቱ በጉልህ አሳይተዋል።
ትንታኔዎች
የመደመር ፍሬ፡አረንጓዴዋ ኢትዮጵያ
Aug 5, 2026 357
በሙሴ መለሰ የመደመር እሳቤ ዋና መሠረቱ እውቀትን፣ጉልበትን፣ሀብትንና አቅምን አስተባብሮ ለአንድ የጋራ ዓላማ በጋራ ማቆምን ያመለክታል። ይህን የሃሳብ ልዕልና በተግባር ፈትሾ ተጨባጭ ውጤት የታየበት ላለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነው። አረንጓዴ ዐሻራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም ጅማሮውን አግኝቷል። የአረንጓዴ ዐሻራ ትልቁ ማሳያ የህዝብ ህብረት የታየበት መሆኑ ነው። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እድሜ፣ ጾታ እና ልዩነት ሳይበግራቸው በነቂስ በመውጣት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አኩሪ ታሪክ የሰሩበት ህዝባዊ ንቅናቄ የመደመርን አስተሳሰብ በተግባር ያረጋገጠ ነው። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ ከተካሄደው የአንድ ጀምበር መርሃ ግብር እንደታየው፣መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ምንም ክፍያ በሙሉ ፈቃደኝነት እና በዝናብ ውስጥ ውሎ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ሰርቷል። በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላው 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን ተደምረው ለነገ ልጆቻቸው መሰረት ለመጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ ያሳዩበት ህያው አብነት ነው። የመደመር እሳቤ በቃላት ሳይሆን በተጨባጭ ውጤት የሚለካ ነው፤ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ዘመቻ እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ቀሪው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ደግሞ በቀጣይ ጊዜያት ይተከላል። በአንድ ወቅት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፋን የነበራት ኢትዮጵያ ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሃብትና የመሬት አጠቃቀም ምክንያት የደን ሽፋኗ ወደ 3 በመቶ ወርዶ ነበር። አረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ የደን ሽፋን ከነበረበት 17.2 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ችግኝ ተከላው ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ከምግብ ዋስትና እና ከሀገር ኢኮኖሚ ጋርም የተሳሰረ ነው። በፍራፍሬ እንደ አቮካዶ፣ማንጎ እና ቡና ባሉ ምርታማ ችግኞች ላይ በማተኮሩ የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር፣ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የምትበለጽግ፣የማትለምን እና ለተቸገሩት የምትደርስ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል የዜጎችን ገቢ የማሳደግ ድርሻ አለው። ኢትዮጵያ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ያከናወነቻቸው የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስራዎች የመደመር እሳቤ ድንበር አቋርጦ ለአህጉራዊ ትስስር እና ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ የሚሆን ድንበር ተሻጋሪ እሴት እንዳለው ያሳያል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዋ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል። ይህም የኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቷል። በአጠቃላይ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በቀና እሳቤ እና በትብብር በመቆም ተስፋን ለልጆቻቸው መዝራት እንደሚችሉ በተግባር፣በስራና በውጤት ያረጋገጡበት ትልቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
በተቃርኖ የተሞላው ሕገ ወጡ ሕወሓት የጥፋት ጉዞ
Jul 30, 2026 629
የሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የፖለቲካ ጉዞ በበርካታ መሠረታዊ ተቃርኖዎችና የፖለቲካ ስህተቶች የተሞላ ነው። ቡድኑ በትግል ጊዜም ይሁን ሀገርን በመምራት ባደረገው የፖለቲካ ተሳትፎ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ስህተቶችን ፈጽሟል። ከሁሉም በላይ የትግራይን ሕዝብ ለዘመን ተሻጋሪ መከራና ስቃይ ዳርጓል። የወጣቶችን ተስፋ እና ሕልም አጨልሟል። የሕገ ወጡ ቡድን በተቃርኖ የተሞላ ጉዞ በጨረፍታ እንመልከት። ተቃርኖ አንድ፦ የሀገር ገዥነት እና የነጻ አውጪነት መንፈስ ሕገ ወጡ ሕወሓት ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንባር ፈጥሮ ሀገር በመራበት ዘመንም ጉዞው በተቃርኖ የተሞላ ነበር። በዚህ የሥልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን፤ ከኅብረት ይልቅ መነጠልን ሥር እንዲሰድ አድርጓል። በስም ደረጃ ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት እንደሚያራምድ ቢናገርም ለኢትዮጵያውያን የተለያየ የዳቦ ስም በመስጠት እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩ በማድረግ የጥላቻ ፖለቲካን አንግሷል። የሕግ የበላይነት እና የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት በአንዱ ቡድን ላይ የማይተገበር ሌላው ላይ ግን ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል። ከቡድኑ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ቡድኖች ለሕግ የማይገዙ፣ ከኮንትሮባንድ እስከ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ውስጥ የሚሳተፉ ነበሩ። ሌላው ጽንፈኛ፣ አክራሪ እና ተስፋፊ ተደርጎ በሽብር እየተወነጀለ በየማረሚያ ቤቱ እንዲንገላታ ተደርጓል። በጥቅሉ ሕገ-መንግሥት እና የፌዴራል ሥርዓትን ለራሱ በሚያመች መልኩ ሲጠቀምበት ቆይቷል። ከዚህም ባለፈ ሕገ ወጡ ቡድን ሀገርን እየመራ እንደ አንድ የክልል ነጻ አውጪ ድርጅት በብሔሮች መካከል ጥርጣሬና ልዩነት እንዲሰፋ የሚያደርጉ የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካዎችንም አንግሷል። ‘እኛ እና እነሱ’ የሚል ፖለቲካን ከማካሄድ ባለፈ ‘ልዩ ኃይል’ በሚል ወታደራዊ አደረጃጀት ፈጥሮ መንግሥት መስሎ ሀገርን የማፍረስ እና የማዳከም ተግባር ውስጥ ተሳትፏል። ተቃርኖ ሁለት፦ ሰሜን እዝን ባጠቃበት ጊዜ ሕገ ወጡ ቡድን ራሱ ያደራጀውን እና ሲያሞካሸው የቆየውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 2013 ዓ.ም. በማጥቃት የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን አረጋግጧል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ የትግራይ ሕዝብ ጋሻና መከታ፣ የችግር ጊዜ ደራሽ እና ከሻዕቢያ ተከላካይ ሆኖ ላቡንና ደሙን ገብሯል። ሕገ ወጡ ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትና የሕገ-መንግሥት ጠባቂ ነኝ ሲል ቆይቶ፣ ለ20 ዓመታት በትግራይ ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ላይ የነበረውን እና የትግራይ ተወላጆችንም በሠራዊቱ ውስጥ ያቀፈውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አጥቅቷል። ሴረኛው እና በተቃርኖ የተሞላው ቡድን የማይመርዝና የማይለውጠው መሆኑን ያረጋገጠበትን ድርጊት ፈጽሞ የሀገር ጋሻና መከታን አዋርዷል። ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳፋሪ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። የተቃርኖው ውጤት ግን መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልተጠበቀ ሁኔታ አንድ ላይ አስተሳሰረ፤ ለሉዓላዊነትና ለግዛት አንድነት የአባቶቹን ታሪክ እንዲደግም ዕድል ፈጠረ። ተቃርኖ ሦስት፦ የሰላም ውል እና የውስጥ ክፍፍል ሕገ ወጡ ቡድን የሥልጣን ጥመኝነቱን ለማርካት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የትግራይ ክልል ተስፋ የሆኑ ወጣቶችን በጦርነት ከማገደ በኋላ የሰላም ስምምነት ተፈረመ። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገ ወሳኝ እርምጃ ነበረ። ነገር ግን ከስምምነቱ በኋላ አሁንም ከስህተቱ የማይማረው ይህ ቡድን የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን ያረጋገጠበት ጥፋት ፈጸመ። ሕገ ወጡ ቡድን ስምምነቱን በይፋ ከተቀበለው በኋላ ስምምነቱን የሚጥሱ ድርጊቶችን መፈጸም ቀጠለ። መሣሪያ ለማስረከብ ተስማምቶ በስምምነቱ መሠረት መሄድ አቃተው፣ እንቅፋት ፈጠረ። በትጥቅ ውስጥ የቆዩ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ማድረግ ነበረበት፣ አላደረገም። ይልቅስ ለሌላ ጥፋት ውስጥ ለውስጥ መዘጋጀቱን ተያያዘው። ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመስረት ተስማምቶ ወደ ተግባር ከተገባ በኋላ የጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን አልቀበልም በማለት ሕገ ወጥነቱን ቀጥሎ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም እና እፎይታ የሰጠውን የሰላም ስምምነት አፈረሰ። ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ትኩረት መደረግ የነበረበት የወደሙ አካባቢዎችን መገንባት፣ የተፈናቀሉትን መመለስ እና ሰብዓዊ እርዳታ ማፋጠን ላይ መሆን ሲገባው፣ ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ውጭ ይፋ በወጣ የሥልጣን ሽኩቻና የእርስ በእርስ ውንጀላ ውስጥ መዘፈቁ ለሕዝቡ ያለው ግድየለሽነት ማሳያ ሆኖ ተወሰደ። ለጥፋት ተልዕኮው ስኬት በፍጹም የዓላማም ይሁን የትግል አንድነት የለኝም ሲላቸው ከነበሩ የጥፋት ቡድኖች ጋር አበረ። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመመሳጠር ሉዓላዊነትን ለማስደፈር እና ሀገር ለማፍረስ በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ ጀመረ። ልብ ማለት የሚገባን ባህር በርን የሚያክል ጉዳይ እንደ ተራ ሸቀጥ ያየው ቡድን እንዴት ስለ ብሔራዊ ክብር እና ሉዓላዊነት ሊያስብ ይችላል? ሊሆን አይችልም። ተቃርኖ አራት፦ የሕገ ወጡ ቡድን የመጨረሻው የጥፋት ጉዞ ዓለምና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ቢቀየርም፣ ሕገ ወጡ ሕወሓት ግን አሁንም በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የትግል ስልት ተከተሏል። ቡድኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑት ባዕዳን ተልዕኮ ተቀብሎ ከሀገር ውስጥ ባንዳዎች ጋር አብሯል። ‘ጽምዶ’ ከተባለው የጥፋት ስብስብ ፊት አውራሪ በመሆን የለመደውን የተቃርኖ ጉዞ ለመቀጠል ተቅበዝብዟል። የወጣቱን የሥራ፣ የዲሞክራሲ፣ የኢኮኖሚና የዘመናዊነት ጥያቄ በትክክለኛ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ወደ ሥልጣን ለመመለስ ለሚያደርገው የቀቢጸ ተስፋ ሙከራ እያደረገ ነው። ከምርጫ ቦርድ ጋር ያለው ሕጋዊ ሰውነት የማጣት አለመግባባት እና በሕጋዊ መንገድ ራሱን ለማደስ ፈቃደኛ አለመሆኑ ቡድኑን በሕግ ፊትም ሆነ በፖለቲካዊ ምህዳሩ ውስጥ ወደ መጨረሻው የመገለልና የውድቀት ምዕራፍ መርቶታል። ዛሬ ግን ትናንት አይደለም። ኢትዮጵያ ዘመኑን በዋጀ አመራር እየተመራች ትገኛለች። ዘመኑን ሙሉ የተቃርኖ ጉዞ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን ወደ መጨረሻው የፖለቲካ ውድቀት እያመራ ነው። የሕገ ወጡ ቡድን የተቃርኖ ጉዞም የበቃል።
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 950
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 1055
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 11483
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 21366
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14393
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20145
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ከካይሮ ሴራ ጀርባ፤ የCNN ዘገባ የገለጠው የኢትዮጵያ እውነት
Aug 4, 2026 1034
ግብፅ በታሪኳ የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመጠቀም የተከተለችው ዋና ስልት "ጠንካራና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለካይሮ ስጋት ናት" የሚል ቀመርን ነው። በመሆኑም በየዘመናቱ የተነሱ የካይሮ መንግስታት ኢትዮጵያ ተረጋግታ ሀብቷን እንዳታለማ ለማድረግ ረዥም ርቀት ተጉዘዋል። በታሪክ አጋጣሚ የዓባይን መነሻ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በርካታ የወረራ ሙከራዎችን ያደረገችው ግብጽ፣ በጉንደት (1875) እና በጉራዕ (1876) በተደረጉ ታሪካዊ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጠንካራ ክንድ መራራ ሽንፈትን አስተናግዳለች። ከቀጥታ ጦርነት ከተመለሰች በኋላ ካይሮ ስልቷን ወደ "ውስጥ ለውስጥ ማበጣበጥ" ቀይራለች። ይህም የኢትዮጵያን መንግስት ትኩረትና የፋይናንስ አቅም ከልማት ፕሮጀክቶች (በተለይም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ እና መሰረተ ልማቶች) ወደ ጸጥታ ማስከበር እንዲዞር ለማድረግና ሀገሪቱን ወደማያልቅ የውስጥ ብጥብጥ ለመክተት በርካታ ሴራዎችን ስታከናውን ቆይታለች። ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨትን እንደ አማራጭ መንገድ ስትጠቀም ቆይታለች፤ እየተጠቀመችም ትገኛለች። የግብፅ የፖለቲካ ምሁራንና ዲፕሎማቶች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ “ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል” በሚል የሐሰት ትረካቸውን ሲያሰራጩና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ሲያሳስቱ ቆይተዋል። ሆኖም ግን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥበብ የተሞላበት አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ የውጭ ተፅዕኖዎችንና የውስጥ ፈተናዎችን በመሻገር ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ከፍፃሜ ማድረስ ችላለች። ይህም የመደመር እሳቤ የሆነው ፈተናን ወደ እድል የመቀየር ትልቁ ማሳያ ነው። የግድቡን እውን መሆን ተከትሎም የካይሮ ተደጋጋሚ የሀሰት ቅሬታና የተዛባ ፕሮፓጋንዳም ዘግይቶም ቢሆን እውነቱ በዓለም ፊት እየተገለጠ ይገኛል።በCNN “Connecting Africa” ወርሃዊ ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ያቀረበችው ዘገባ የዚሁ እውነት ማሳያ ነው። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2020 የቢቢሲ የኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ የሆነችው ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ፣ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገኝበት ጉባ ተገኝታ ባከናወነችው ዘገባ የካይሮን ምናባዊ ቅዥት የሚያፈርሱ ተግባራዊ እውነቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርጋለች። የምህንድስና ልህቀት እና የጋራ ልማት ማሳያ፦ CNN በዘገባው ስለ ሕዳሴ ግድብ ለዓመታት ሲነገር የቆየውን የሀሰት ሴራ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የምህንድስናና የግንባታ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን ጥረትን እውን ያደረገ የኢንጂነሪንግ ልህቀት አብነት መሆኑን አጉልቶ አሳይቷል። የግብፅ መንግስት ግድቡን “የስጋት ምንጭ” አድርጎ ለማሳየት ቢጥርም፣ የCNN ዘገባ ግን ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው የተዘረጋ የጋራ እድገት መድረክ መሆኑን አብራርቷል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር መስከረም 2025 በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በማሳደግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እያበራ መሆኑን በማሳየትም፤ ግድቡ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን በተግባር ገልጧል። የጋዜጠኛ ሩባዲሪ ዘገባ የግብፅን ተደጋጋሚ ቅሬታና ሴራ በሶስት ዋና ዋና ነጥቦች ውድቅ ያደርጋል። የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ፦ ግድቡ የታችኞቹን የተፋሰሱ ሀገራት የማይጎዳ፣ ይልቁንም የውሃ ፍሰትን በማስተካከልና ደለልን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ሚና የሚጫወት፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ፕሮጀክት መሆኑን የግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሃሳብን በማካተት ጭምር አሳይታለች። ቀጣናዊ የመደመር እሳቤ ማሳያ ፦ ግድቡ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገቢ ከማግኘቷም ባለፈ፣ የቀጣናውን ሀገራት በኃይልና በኢኮኖሚ የሚያስተሳስር ነው። ይህ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግስት እሳቤ ማለትም “በጋራ ማደግ እና እርስ በእርስ መደጋገፍ” የሚለውን ቀጣናዊ ራዕይ በተግባር የሚያረጋግጥ እንጂ ግብፅ እንደምትለው ቀጣናውን ወደ አለመረጋጋት የሚከት አለመሆኑን ያመላክታል። ሰው ተኮር የኢኮኖሚ ሽግግር፦ በCNN ዘገባ የተካተቱት የኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር (IGC) የኢትዮጵያ ኃላፊ ቴዎድሮስ መኮንን በግልጽ እንዳስቀመጡት፤ 70 በመቶው ህዝቧ ከ30 ዓመት በታች የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ከ15 ዓመታት በፊት ከነበረችበት ከአማካይ በታች የነበረ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን በአፍሪካ ከሚገኙ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች። ግድቡም ይህንን ወጣት ኃይል ወደ ዘላቂ ምርታማነት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አካል ነው። መደምደሚያ፦ በአጠቃላይ ግብፅ ግድቡን መሰረት በማድረግ የምታካሂደው የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የፖለቲካ ቁማር እንጂ ከሳይንሳዊና መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር እንደማይገናኝ የCNN ዘገባ በግልጽ አሳይቷል። በሀገር ውስጥ አቅም እና በጥበብ በተሞላ ሀገራዊ አመራር እውን የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ጊዜ የሚቀርጽ፣ የአፍሪካ ቀጣናን በኃይልና በንግድ የሚያስተሳስር የልማት ማማ እንጂ የትኛውንም ሀገር የሚጎዳ ስጋት አይደለም። የመደመር እሳቤ ያጎናፀፈው ይህ የታሪካዊ ድል ብርሃንም መላውን ቀጣና ማብራቱን ቀጥሏል።
ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ
Jul 31, 2026 1205
ዋግ ኽምራ፤ሐምሌ 24/2018 (ኢዜአ) ፦"ዓይኖቼ ማየት ባይችሉም እጆቼ ተዓምር ይሰራሉ'' -ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መለስ ጌታነህ የ62 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ አዛውንት ናቸው፤ ከጊዜ በኋላ በመጣ ችግር የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡ ቢሆንም በአካባቢው ስመ ጥር የቧንቧ ሠራተኛ ናቸው። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ገና በወጣትነት ዕድሜያቸው የቧንቧ ሥራ ሙያን ቀስመው፣ በዋግ ኽምራ በሚገኙ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ለንጹሕ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት አሻራቸውን እያሳረፉ ያሉ ትጉህ ባለሙያ ናቸው። ቆላ በመውረድ፣ ደጋ በመውጣት፣ ተራራና ሸንተረሩን ሳይበግራቸው የውሃ መስመር በመዘርጋት ህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ እንዲደርሰው እያደረጉ ያሉ አዛውንት ናቸው። ለዚህም በተደጋጋሚ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ1991 ዓ.ም የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ ሲጀምር እሳቸው በቧንቧ ባለሙያነት በቋሚነት በመቀጠር፣ የውሃ መስመር በመዘርጋትና በመጠገን የሕክምና ክፍሎች ያልተቋረጠ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ ችለዋል። ይሁን እንጂ ከዕለታት በአንድ ቀን ሥራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ወቅት ባላወቁት ምክንያት የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡበት አጋጣሚ በመከሰቱ ከቤት ለመዋል መገደዳቸውን ያወሳሉ። እንደ አቶ መለስ ገለጻ፡ “ዓይኔ ማየት ባለመቻሉ ራሴን ችዬ መንቀሳቀስ፣ እንደልቤ ሜትር ዘርግቼ ለክቼ መቁረጥና ገደል ላይ ተንጠልጥዬ የቧንቧ መስመር መዘርጋት አልችልም የሚል የተሸናፊነት ስሜት አድሮብኝ ተስፋ ቆርጬ ተቀምጬ ነበር” ይላሉ። በዚህ ወቅት ትጋታቸውንና ብርታታቸውን የሚያውቁ የሆስፒታሉ ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ዓለማየሁ ትኩ፣ ወደ ሆስፒታሉ በመውሰድና በመምከር ሥራቸውን እንዲቀጥሉ እንዳገዟቸው አውስተዋል። ቀስ በቀስም አቶ መለስ ሜትር በመዘርጋትና መጋዝ በመጨበጥ ልኬታን አስተካክለው፣ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በዳበሳ ለይተው የቧንቧ ሙያ ሥራቸውን እንደገና “ሀ” ብለው ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል። ምንም እንኳን ከወረዳ ወረዳ ተንቀሳቅሶ መሥራት ባይችሉም፣ በግለሰብ ቤቶችና ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ የቧንቧ ጥገና ሥራቸውን በብቃት እያከናወኑ ያሉ ብቁ ባለሙያ ሆነው ቀጥለዋል። በሆስፒታሉም ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ የውሃ መስመሮችን በመለየትና በአግባቡ በመጠገን፣ ለሐኪሞችና ለሕመምተኞች ወጥ የሆነ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ “አንቱ” የተባሉ ባለሙያ ሆነዋል። አቶ መለስ በቧንቧ ሥራ ሳይገደቡ፣ በራዲዮ በሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ፕሮግራሞች ባገኙት እውቀት ከአገልግሎት ውጭ የነበረውን የሆስፒታሉን የላውንድሪ (ልብስ ማጠቢያ) ማሽን በዳበሳ ጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ሆስፒታሉን ከወጪ ታድገዋል። “ብርሃን ከዓይን ብቻ ሳይሆን ከልብና ከመዳፋችንም ይገኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ምጣዶችን በመጠገንና ሌሎችንም የቴክኒክ ሥራዎች በመሥራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ጠንካራ የዕድሜ ባለፀጋ ናቸው። "የዓይን ብርሃኔን አጣሁ ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም” የሚሉት አቶ መለስ፣ አሁን ላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጣራ ላይ በመውጣት ጭምር ቧንቧ ጠግነው የሚወርዱ ባለሙያ ሆነዋል። “እኔ ሥራ ሳልሠራ ስውል ያመኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ ወጣቱ ሥራን ሳይንቅ ከሰራ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችል ምክራቸውን ለግሰዋል። ስለ ጉዳዩ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተፈራ ኃይሉ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ቢምረው እንዳሉት፡ ጋሽ መለስ የዓይን ብርሃናቸውን ቢያጡም በሙያቸው የትጋትና የ“ይቻላል” ተምሳሌት የሆኑ አዛውንት ናቸው። አዛውንቱ በሙያቸው የሆስፒታሉ የውሃ አቅርቦት እንዳይቋረጥ በማድረግ ለሕክምና ሥራ መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸው ለሌሎች ባለሙያዎች በታታሪነት፣ በሥራ ፍቅር እና በጥንካሬ አርዓያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።