ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ
Aug 27, 2026 251
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21 /2018(ኢዜአ)፦ የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ዛሬ ማምሻውን በሞናኮ ይፋ ሆኗል። ውድድሩ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት አንስቶ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ፎርማትን በማስቀረት 36 ክለቦች በ4 ቋቶች (Pots) በመከፋፈል እንዲጫወቱ የሚያደርግ አዲስ አሰራር (League Phase) መተግበር መጀመሩ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት 36ቱ ቡድኖች በ4 ቋቶች የተደለደሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ቋት 9 ክለቦች ይገኛሉ። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተደልድለዋል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ፣ ሮማ ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ፣ አስቶንቪላ፣ ፓርቶ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ሪያል ቤቲስ እና ፒኤስጂ አይንድሆቨን በቋት ሁለት የሚገኙ ክለቦች ናቸው። በቋት ሶስት ላይፕዚግ፣ ቪያሪያል፣ ናፖሊ፣ ሊል፣ ፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ቦዲ ግሊምት፣ ፊነርባቼ፣ ሻካታር ዶኔስክ እና ጋላታሳራይ ላይ ይገኛሉ። ስቱትጋርት፣ ሌንስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ ፣ ኤኢኬ አቴንስ ፣ ላስክ፣ ኮሞ፣ ቫይኪንግ እና ሳባህ በቋት አራት የተደለደሉ ክለቦች ናቸው። አንድ ክለብ በራሱ ቋት ካለ ሁለት ቡድንና በእያንዳንዱ ቋት ካሉ ሁለት ክለቦች ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። በዚህም አንድ ክለብ ስምንት ጨዋታ ያደርጋል። ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ። ቀሪዎቹ ስምንት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚገቡ ቡድኖች በሁለት የማጣሪያ ዙሮች ተጫውተው 16ት ውስጥ ይገባሉ። ከጥሎ ማለፉ አንስቶ ያለው የውድድር ፎርማት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። በዚሁ መሰረት ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከባርሴሎና፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየር ሙኒክ ፣ ባርሴሎና ከፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ በመጀመሪያው ሳምንት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የሚጠበቁ ናቸው። የጣልያኑ ኮሞ እና የአዘርባጃኑ ሳባህ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ክለቦች ናቸው።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ችግሮቻችንን ለመፍታት አግዞናል -በሃዋሳ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች
Aug 27, 2026 224
ሀዋሳ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዳገዛቸው በሃዋሳ ከተማ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡ የመደመር መንግስት እሳቤ የሆነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ በሃዋሳ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ ዓመታትን የተሻገሩ ችግሮቻቸውን በመፍታት በተስፋ እንዲኖሩ እንዳስቻላቸው ለኢዜአ ገልፀዋል። በከተማው የፋራ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ አማረች አበራ በእርጅና ያዘመመ ቤታቸው በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና በመንግስት ትብብር በአዲስ መልክ መሰራቱ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመጀመር እንዳስቻላቸው ገልጸዋል፡፡ በበጎ ፈቃዱ ያረጀ ቤታቸው ብቻ ሳይሆን ጉስቁልና የተጫጫነው ኑሯቸው እንዲቀየር የወገን አለኝታነት ከፍተኛ እገዛ እንዳረገላቸው ነው ያመለከቱት።፡ የዓይን ብርሃናቸውን አጥተው ቤት በመቀመጣቸው ለገጠማቸው ችግር በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መፍትሄ ማግኘታቸውን የጠቀሱት ደግሞ የሂጠታ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ሹቃ ፋሬሾ ናቸው። የበጎ ፈቃድ የመደጋገፍ ባህል እያደገ መምጣቱ እሳቸውን መሰል በእድሜ የገፉና በህመም ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ዜጎችን ለማገዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2011 ጀምሮ በመሳተፍ ላይ መሆኑን የገለጸው ወጣት ተመስገን ያዕቆብ፤ አቅሙን፣ ጉልበቱንና ጊዜውን አስተባብሮ አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን እያገዘ ይገኛል። በዚህም በገንዘብ የማይተመን የመንፈስ እርካታ ከማግኘት ባለፈ አገርና ህዝብን በማገዝ የዜግነት ግዴታውን እየተወጣ መሆኑንም ይናገራል። የታቦር ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት መልካሙ ሚካኤል በበኩሉ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ይናገራል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት አገራዊ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማድረግ ሰፊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ነው የገለጸው። የሃዋሳ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ90 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል ብለዋል። በዚህም 246 ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት ግብ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በ18 ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን፤ የቤት እድሳትና ግንባታ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የደም ልገሳና ሌሎችንም ተግባራት የሚያካትት መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ99 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ቀጣናዊ ትብብርና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያለመ የሕልውና ጥያቄ ነው
Aug 27, 2026 246
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ቀጣናዊ ትብብርና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጠ ያለመ ፍትሐዊና የሕልውና ጥያቄ መሆኑን በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) ገለጹ። የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለቀጣናዊና ዓለም አቀፍ የንግድ ትብብር ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የህልውና ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና የሕዝብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግም ሀገርን ከታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ መልክዓምድራዊና ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነቷ ማስታረቅ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። ስትራቴጂክ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም በትብብር ላይ የተመሰረተ ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነትን በማስጠበቅ የጋራ ዕድገትና ብልፅግናን የሚያሳልጥ የወጪና ገቢ ንግድን ለማሳለጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በተባበሩት መንግሥታት ጥናቶች መሠረት ወደብ አልባ ሀገራት ከባሕር በር ተጠቃሚ ከሆኑ ሀገራት ጋር ሲነጻጸሩ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ልዩነት እንደሚያጋጥማቸው ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነው ገቢና ወጪ ንግድ በአንድ ወደብ በኩል መከናወኑም ለሌሎች የልማት ሥራዎች ይውል የነበረው የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስወጣ ተናግረዋል። ይህም በዓለም ንግድ ሥርዓት የወጪና ገቢ ተወዳዳሪነትን በማቀጨጭ በኢንዱስትሪ፣ ኢንቨስትመንትና በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ታሪካዊ መሠረትም ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ለሺህ ዓመታት በአዱሊስ ወደብ አማካኝነት ከዓለም ጋር ሰፊ ግንኙነት ይደረግ እንደነበር አስታውሰዋል። በጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥም ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር አቅራቢያ የተፈጠረች ሀገር መሆኗ በተፈጥሯዊና መልክዓምድራዊ አመክንዮ የተደገፈ ጥያቄ መሆኑን አስረድተዋል። በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግጋትና የኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት ኢ-ሕጋዊ መንገድም የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄዋ ሕጋዊ መሠረት እንዳለው አስረጂ መሆኑን አብራርተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነትና ሕግጋትም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባሕር የመድረስና የመጠቀም መብታቸውን የሚደግፍ ድንጋጌና ማዕቀፍ መኖራቸውን አንስተዋል። አክለውም በቅርቡ በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ በተካሄደው የወደብ አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ፣ በዚህ ዘርፍ ጉልህ ውሳኔዎች መወሰናቸውን ጠቁመው፣ የአዋዛ የፖለቲካ መግለጫም መጽደቁን አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎትም የግል ጥቅምን ብቻ ለማሳካት የቀረበ ሳይሆን የጋራ ቀጣናዊ ህልውናን በማስጠበቅ ትብብርንና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያም ይህንን አቋም ለጎረቤት ሀገራት በሁለትዮሽ እንዲሁም በተለያዩ መድረኮች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እያስረዳች መሆኑንም ጠቁመዋል።
ምክክሩ ኢትዮጵያውያን አለመግባባቶችን በሐሳብ የበላይነት መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተግባር የታየበት ነው
Aug 27, 2026 237
ወልቂጤ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦የምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያውያን አለመግባባቶችን በሐሳብ የበላይነትና በጥበብ መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተግባር የታየበት መሆኑን የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያውያን በመግባባት ዘላቂ ሰላምን እውን ማድረግ የሚችሉት በኃይል አማራጭ ሳይሆን የሐሳብ የበላይነትን ባስቀደመ አካታች ውይይት ብቻ መሆኑን በተግባር ያሳየ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ነው። ተመካካሪዎቹ ልዩነቶቻቸውን በግልጽነት አቅርበው በጥበብና በመደማመጥ ለመፍታት ያደረጉት ጥረት፣ የሚነሱ አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት መፍትሔ የመስጠት ልማድ እንዲዳብር መሠረትን ይጥላል። ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያውያን አለመግባባቶችን በሐሳብ የበላይነት መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተግባር የታየበት ነው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያውያን በጋራ የመመካከርና የመወያየት ባህላቸውን በመጠቀም ውስጣዊ ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ ጉባኤው ማሳየቱን ጠቅሰዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ እስክንድር ነጋሽ ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በራሳችን ጉዳዮች ላይ በመምከር የጋራ መፍትሔ መስጠት እንደምንችል ያስገነዘበ እንደሆነም አንስተዋል። የምክክር ጉባኤው በሐሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ፣ በጠንካራ ሀገረ መንግሥት የጸናች ሃገርን በመገንባት ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል መርህ የተከተለ እንደነበረም ጠቅሰዋል። ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮችን በራሳችን አቅምና በጋራ ውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታሪካዊ ዕድልን የፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ ዳዊት ብርሃኔ ናቸው። ምክክሩ ቀጣይነት ያለው ሰላም፣ አንድነቱ የተጠበቀና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባ ሀገርን ለማንበር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ እንዳለውም አመልክተዋል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝቡ እኩል እንዲመክርና እንዲወከል በማድረጉ ሀገራዊ ስሜትን ያነቃቃና ባለቤትነትን ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ሃዲሞ ሃሰን ናቸው። ምክክሩ በሕዝቦች መካከል ያሉ የጋራ እሴቶችን በማጠናከር ረገድ ወደ ተሻለ አንድነት የሚያመጣ መሆኑን አውስተዋል።
የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል
Aug 27, 2026 244
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የውኃ ጥራት ምርመራንና ምርምርን ለማጠናከር የተገነባውን ስፔሻላይዝድ የውኃ ምርመራ ላቦራቶሪ ዛሬ አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታመና ኃይሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የውኃ ጥራትን በተሟላ መልኩ መመርመር የሕዝብ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የውኃ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም የላቀ ሚና አለው። ላቦራቶሪው የሕክምናና የውኃ ማጣሪያ ሂደቶችን በተገቢው ለመምራትና የሀገሪቱን የምርመራ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይም ለመጠጥ፣ ለመስኖና ለኢንዱስትሪ የሚውል ውኃ ተገቢውን የጥራት ደረጃ እንደሚያሟላ ለመለየት ምርመራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የውኃ ምርመራ ውጤቶችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ ለምርምርና ለዕውቀት ማከማቻ ለማዋል ያስችላል ብለዋል። አንድ የውኃ ምንጭ በአንድ ወቅት ንጹሕ መሆኑ በሌላ ወቅትም ተመሳሳይ ጥራት እንዳለው አያረጋግጥም። በመሆኑም የውኃ ጥራት በየጊዜው በመመርመር ውጤቶቹ በዳታ መልክ መመዝገብና ለተለያዩ የልማትና የምርምር ሥራዎች መዋል እንዳለበት ጠቁመዋል። በላቦራቶሪው በኩል በሀገሪቱ በተበታተነ መልኩ የሚገኙ የላቦራቶሪ አቅሞችን በማስተሳሰር፣ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በአይኤስኦ ደረጃዎች የተመሠረተ የምርመራ ሥርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን የላቦራቶሪ አቅም ለማጠናከር እንደሚሠራም ተገልጿል። በኢንስቲትዩት የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀምበርነሽ ክንፈ በበኩላቸው፣ የውኃ ናሙና እና ምርመራ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ላቦራቶሪው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ላቦራቶሪው ከውኃ ጥራት ምርመራ በተጨማሪ የውኃ ጥራት ምርምርና ሥልጠና እንዲሁም ከአቅም በላይ የሆኑ ምርመራዎችን በማከናወን እንደ ሪፈራል ላቦራቶሪ ሊያገለግል እንደሚችልም አስረድተዋል። በተጨማሪም የተፋሰስና የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የውኃ ናሙናዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲያስመረምሩና ከውኃ ጋር ተያያዥ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። ላቦራቶሪው በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር የውኃ ጥራትን ከማረጋገጥ ባለፈ የምርምር፣ የሥልጠና፣ የገቢ ማመንጫና የውኃ ዲፕሎማሲ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ሲሉም ተናግረዋል። ላቦራቶሪው በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካላዊ፣ አካላዊና ማይክሮባዮሎጂያዊ ይዘቶችን በመመርመር የውኃ ጥራትን ለማረጋገጥ ያግዛል ያሉት ደግሞ የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የስፔሻላይዝድ ላቦራቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አብዱረህማን ሰይድ ናቸው። ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ ባሉ ላቦራቶሪዎች ሊከናወኑ ያልቻሉ አንዳንድ ምርመራዎች ወደ ውጭ በመላክ ይከናወኑ እንደነበር ጠቁመው፣ የምርመራ ውጤት ለማግኘት የሚወስደውን ጊዜም ያሳጥራል ብለዋል። በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ወይም ጎጂ ማይክሮኦርጋኒዝሞች ከተፈቀደው መጠን በላይ መኖራቸው በሰው ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል፣ የውኃ ጥራትን በላቦራቶሪ መፈተሽ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
ፖለቲካ

በሰላም ማስከበር ዘርፍ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ከአካዳሚክ እውቀት ባለፈ ተግባራዊ ክህሎትንና የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ያገናዘቡ ናቸው -ሌተናል ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ
Aug 27, 2026 294
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦በሰላም ማስከበር ዘርፍ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ከአካዳሚክ እውቀት ባለፈ ተግባራዊ ክህሎትንና የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ያገናዘቡ ናቸው ሲሉ የመከላከያ ኢንስፔክተር ጄኔራል ቢሮ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ ገለጹ። በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የጋራ ዓላማን አንግቦ መስራት ወሳኝ መሆኑንም የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ ገልፀዋል። የሰላም ማስከበር ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ከተለመደው ወታደራዊ ክህሎት ባለፈ የግጭቶችን ውስብስብ ባህሪ የሚረዱና ለውይይት ቅድሚያ የሚሰጡ ሙያተኞችን ማፈራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት በሰላምና ግጭት አፈታት አስተዳደር የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የ3ኛ ዙር ተማሪዎቹን ዛሬ አስመርቋል። የመከላከያ ኢንስፔክተር ጄኔራል ቢሮ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ በሰላም ማስከበር ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችን አቅምና ሙያዊ ብቃት ማሳደግ ነው ብለዋል። እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ደረጃዎችና መልካም ተሞክሮዎች ጋር የሚጣጣም እውቀትና ክህሎት ማስታጠቅ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ኢንስቲትዩቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እና የተለያዩ ሀገራት ሠራዊት የዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በብቃት መወጣት እንዲችሉ እያዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች በቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ሰላምን፣ ውይይትንና የሰዎችን ክብር የሚያስቀድሙ መሪዎች እንዲሆኑ አሳስበዋል። የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ዘርፍ የካበተ ረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ተናግረዋል። ይህንን ልምድ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂና አሰራር ጋር በማጣመር ብቁ ሰራዊት እየተገነባ ይገኛል ብለዋል። ማዕከሉ የሀገር ውስጥ አቅምን ከመገንባት ባለፈ ከአጋር ሀገራት ጋር አብሮ በመስራት ለአለም አቀፍ ሰላም የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት አዛዥ ኮሎኔል ጌቱ ታዬ፤ በመርሃ ግብሩ በበሰላም እና ግጭት አፈታት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያጠናቀቁ ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 28 ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ትምህርቱ በመከላከያ ሚኒስቴር፣ በጃፓን መንግስትና በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ትብብር የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው የሴቶችና የውጭ ሀገራት ተማሪዎች መካተት ለፕሮግራሙ ትልቅ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል። ከተመራቂዎች መካከል ኮሎኔል ምትኩ ገመዳ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም የምታደርገውን አስተዋጽኦ አሁንም አጠናክራ እንደቀጠለች ጠቁመው ባገኙት እውቀት በተመደቡበት ማንኛውም ግጭት አፈታት ተልዕኮ ላይ ለመሰማራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሌተናል ኮሎኔል ኤልሳቤት አዳነ በበኩላቸው፤ በትምህርታቸው በወታደራዊ ዲፕሎማሲና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ሰፊ እውቀት ማገኘታቸውንና ይህም በዓለም ደረጃ ያሉ የግጭት ሁኔታዎችንና የቅድመ-መከላከል ስልቶችን በግልጽ ለመረዳት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። ያገኙት እውቀት በሚሰሩት ስራ ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና በብቃት ለመስራት እንደሚያስችላቸው በመግለጽ በትግበራው ወቅት የተማሩትን ወደ ተግባር ለመቀየር መዘጋጀታቸውን የተናገሩት ደግሞ ኮማንደር እፁብድንቅ መርሻ ናቸው። ከውጭ ሀገር ሰልጣኞች መካከል ከዩጋንዳ የመጡት ዶክተር ደቪድ ኦኮሞ ሙኙዋ እንደተናገሩት፤ ኢንስቲትዩቱ ከተማሩባቸው በርካታ የዓለም ሀገራት ተቋማት መካከል ምርጡ እንደሆነ ገልጸዋል። በአካልና በኦንላይን የተቃኘው የትምህርት አሰጣጥ ዘዴው በጣም ውጤታማና የተቀናጀ እንደነበር መስክረዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከጋራ ተጠቃሚነትም ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ወሳኝ ነው
Aug 27, 2026 265
ጅማ፤ ነሐሴ 21/2018ዓም(ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከጋራ ተጠቃሚነትም ባለፈ የቀጣናውን ሰላም በአስተማማኝ መልኩ ለማስጠበቅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። የአባይ መነሻ የሆነችውና ከቀይ ባህር በቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከሁለቱ ውሃዎች ጋር ህልውናዋ በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከጋራ የልማትና ተጠቃሚነትም ባለፈ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ወሳኝና አስፈላጊ ሀገር መሆኗ ይታመናል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሀ ምህንድስና መምህር እና ተመራማሪ ማሙዬ ቡሴር (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና መቀጠል የሌለባት በመሆኑ የባህር በር የግድ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። ከባህር በር ባለቤትነቷም ባሻገር የቀይ ባህርን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የኢትዮጵያ አስፈላጊነት አማራጭ የሌለው መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ከጋራ ተጠቃሚነትም ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል። የቀጣናው አገራት በሁለቱ ውሃዎች ዙሪያ በትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው አንስተው ኢትዮጵያን ማእከል ያላደረገ ማንኛውም እንቅስቃሴ ውጤት ሊያመጣ አይችልም ብለዋል። የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኃይል ልማት ፍላጎት መሰረት አድርጎ የተገነባ ቢሆንም በተለይም የጎረቤት አገራትን የሃይል ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በቀይ ባህርም በተመሳሳይ መርህ በትብብር መስራት የግድ መሆኑን ያነሱት ተመራማሪው በተናጠል የሚደረጉ የልማትም ይሁን የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ውጤታማ ሊሆኑ አይችሉም ሲሉ ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የሃይድሮሊክስና የውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር ዋቅጅራ ታከለ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ከራሷ ጥቅም ባለፈ ሌሎች አገራትንም ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል የልማት ትስስርን ይዞ የሚመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የቀይ ባህር ጉዳይ በትብብርና በሰላማዊ የዲፕሎማሲ አማራጭ መምራት እንደሚገባ አንስተው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው መርህ የሚደነቅ ነው ብለዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ብርሀኑ ሞሲሳ (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በቅርበት፣ በመልካአ ምድርም ይሁን በዓለም አቀፍ ህግ አሳማኝና ተቀባይነት ያለው መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ከጋራ ተጠቃሚነትም ባለፈ የባህር ላይ ወንጀሎችን ለመግታትና ሽብርተኝነትን ለመታገል የሚያስችል ቀጣናዊ አቅም መሆኑን ገልጸዋል። በሰላም ማስከበርና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና የሚታወቅ መሆኑን አንስተው፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ከጋራ ተጠቃሚነትም ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚሆን ነው ብለዋል።
የምክክር ጉባኤው ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት ብቻ የመፍታት ባህልን ያጎለብታል
Aug 27, 2026 266
ሮቤ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት ብቻ የመፍታት ባህል እንዲጎለብት ያደርጋል ሲሉ የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ለዘመናት በቆዩ ዘርፈ-ብዙ አለመግባባቶች ዙሪያ በመምከር በቀጣይ መሰል ውስብስብ ችግሮች እንዳይደገሙ ትልቅ የተግባርና የባህል ልምድ ጥሎ አልፏል። ከዚህም ዋነኛው የቱንም ያህል ጥልቅ እና ውስብስብ የሆኑ ሀገራዊ ቅሬታዎችና ልዩነቶች ቢኖሩ፣ ብቸኛውና ዘላቂው የመፍትሔ መንገድ የሐሳብ የበላይነትና በጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረግ አካታች ውይይት ብቻ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡ ነው። ሂደቱ ችግሮችን በኃይል ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ በመደማመጥ እንዲሁም የችግሮች አካል ከመሆን ይልቅ የመፍትሔው ባለቤት በመሆን መፍታት እንደሚቻል ትልቅ ትምህርትን የሰጠ ነው ። በዚሁ ጉዳይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁትም፤ የምክክር ጉባኤው ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት ብቻ የመፍታት ባህልን ያጎለብታል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ጫልቺሳ ዘውዴ፤ ጉባኤው ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እኩል እንዲመክሩና እንዲወከሉ በማድረግ ሀገራዊ ስሜትን ያነቃቃ እንዲሁም ለችግሮች መፍትሔ እንዲገኝ በር የከፈተ ነው ብለዋል። "ምክክሩ ችግሮች ምንም ያህል ጥልቅ እና ውስብስብ ቢሆኑም፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በሰለጠነ መንገድ ተቀምጦ መፍትሔ ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ ነው" ሲሉም አክለዋል። ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ኢሳ ጣህር በበኩላቸው፤ ምክክሩ የቆዩ ቅሬታዎችን እና አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ትልቅ ትምህርትን የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። ሐጂ አሬሪ ሀሰን የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ በተለይ በታሪካችን ውስጥ የነበሩ ስብራቶችን ለማቃናት፣ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የቆዩ ችግሮችን ለማስተካከል በውይይት የመፍታት ሰፊ ልምድን የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የትግራይ ህዝብ በሕገ-ወጡ ሕወሓት የሚደርስበትን ግፍና መከራ ለማስቀረት ቡድኑ ላይ የጀመረውን ትግል ሊያጠናክር ይገባል
Aug 27, 2026 370
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የሚያደርሰውን ግፍና መከራ ለማስቀረት ሕዝቡ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ እንደሚያስፈልግ የሥምረት ፓርቲ የምክር ቤት አባልና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ ጠዓመ ዓረዶም ገለጹ። አቶ ጠዓመ ዓረዶም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የሕገ-ወጡ ቡድን አፈሳና አፈና ከጥፋት አጋሩ ሻዕቢያ የተማረው የጥፋትና የጭቆና መንገድ ነው። በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር በመጣመር የሻዕቢያና የግብጽን ተልዕኮ ለማስፈጸም የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት ለማናጋት ትንኮሳ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በተለያዩ የአፋርና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የሚፈጽመው ትንኮሳ ሀገርን በማተራመስ የትግራይ ክልልን ሕዝብ ለማጎሳቆል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። የትግራይ ክልል ሕዝብ እፎይታ የሰጠውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በግልጽ በመናድ፣ በምንም ዓላማ ከማይዛመዱ ኃይሎች ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ በመፍጠር ሀገርን ለማተራመስ ሲፎክር እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ጠዓመ በማከልም፤ ሕገ-ወጡ ቡድን በበርካታ ወንጀልና ሰብዓዊ ግፍ የጨቀየ የዘራፊዎች ስብስብ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅትም በሚፈጽመው ከፍተኛ የዝርፊያና ምዝበራ ተግባር የሀገርን ሃብት እያሸሸ ነው ብለዋል። በትግራይ ክልል ሕዝብና ወጣቶች ላይ የሚፈጽመው ኢ-ሰብዓዊ እገታ፣ እስር፣ እንግልትና አፈና የሕዝብ ጉስቁልና ምንጭ የሆነ ስግብግብ ቡድን መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ከግብጽና ሻዕቢያ በሚሰፈርለት የቅጥረኝነት ተልዕኮ ኢትዮጵያን በማተራመስ ከንቱ የህልም ቅዠቱን ለማሳካት እየጣረ መሆኑንም አብራርተዋል። የትግራይ ክልል ሕዝብና ወጣቶች የሕገ-ወጡን ቡድን የጥፋት ዓላማ አምርሮ በመታገል ሰላም፣ ልማትና አብሮነትን እንደሚሹ በይፋዊ ተቃውሟቸው ድምጻቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ለዚህም እናቶች፣ ወጣቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች በቤተ-እምነቶችና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች የቡድኑን እኩይ ሴራ እየኮነኑ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ጠዓመ እንዳሉት፣ ሕገ-ወጡ ቡድን ከሕዝብ የተነጠለ የወንጀለኞች ስብስብ ነው። መንግሥት የትግራይን ሕዝብ ጦርነት ከሚያደርስበት ጉስቁልና ለመታደግ የሰጠው ከፍተኛ ትዕግስት የሚደነቅ ነው ብለዋል። በቀጣይም በሕገ-ወጡ ቡድን በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ለማስቀረት የሕግ የበላይነትን በማስከበር ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል። የሕገ-ወጡ ሕወሓት ቡድን ጠባብ ስብስብ የትግራይ ክልል ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማትና ሰላም ተቋዳሽ እንዳይሆን አበክሮ የሚሰራ ጸረ-ሕዝብ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ፓርቲያቸው በትግራይ ክልል ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተጫነውን ሕገ-ወጥ ስብስብ ለማስወገድ የጥፋት ቡድኑን የሴራ አጀንዳ የማጋለጥና የመበጣጠስ ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል። የትግራይ ክልል ሕዝብና ወጣቶች በቡድኑ ላይ የጀመሩትን ተቃውሞ በማቀጣጠል የጥፋት ቡድኑን ሕልም ማክሸፍ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ አክሽፏል - ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል
Aug 27, 2026 372
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ ማክሸፍ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ። የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ሀገራዊ የጋራ የፀጥታ መድረክ እየተካሄደ ነው። ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በጋራ ተቀናጅቶ በመስራቱ ሰላምን የሚያጸኑ ውጤቶች ተገኝተዋል። ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን፣ በየደረጃው ያለው የፖሊስ ሰራዊት፣ የፀጥታና አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ሚሊሻዎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በማቀድ መስራታቸውን አመልክተው፤ በዚህም በሀገርም ሆነ በዓለም በአርአያነት የሚጠቀስ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መካሄድ መቻሉን ተናግረዋል። ሁል ጊዜ ኢትዮጵያ በችግር እንድትቆይ ሰላሟን ለማናጋት የሚሹ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች በመገናኘት በርካታ ሴራዎችን እንደሚያቅዱ ያወሱት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ፤ እነዚያን ሴራዎች በየደረጃው ህይወታቸውን ጭምር በመክፈል እና ሴራውን በማምከን፣ የሀገርን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ዛሬ ለተደረሰበት ደረጃ መሰራቱን ተናግረዋል። መድረኩ በቀጣይም የኢትዮጵያ ጠላቶች ሰላምና ደህንነት ለማናጋት ከውስጥ ባንዳዎች እና ከውጭ ባዳዎች ጋር ተገናኝተው የሚሰሩትን ሴራ ሁሉ ለማክሸፍ፣ ሰራዊቱ አሁንም ዝግጁ መሆኑን የሚያረጋግጥበት እና ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን የሚያዘጋጅበት ነው ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የቱሪስቶች መዳረሻ ከመሆን ባለፈ ትላልቅ የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኹነቶች የሚካሄድባት ተመራጭ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። የእነዚህ ኹነቶች በሰላም እና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወኑ የፖሊስ ሰራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ከፍተኛ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አክለዋል። በቀጣይም ለሚካሄዱ ትላልቅ ሀገራዊ ኹነቶች በጋራ መወያየት፣ በጋራ ማቀድ እና በመዘጋጀት የጠላትን ሴራ እያከሸፍን በሰላም እንዲካሄዱ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የዛሬው መድረክም በዋናነት የተከናወኑትን ሥራዎች እና በእዚያ ውስጥ የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎች እና ያጋጠሙን ክፍተቶች በመለየት በቀጣይ ደግሞ ለሚኖር ተልዕኮ ከወዲሁ ለመዘጋጀት ያለመ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ጠላቶችን ሴራ በማክሸፍና የሀገሪቱን ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የጋራ ስራችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

ማህበራዊ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ችግሮቻችንን ለመፍታት አግዞናል -በሃዋሳ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች
Aug 27, 2026 224
ሀዋሳ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዳገዛቸው በሃዋሳ ከተማ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡ የመደመር መንግስት እሳቤ የሆነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ በሃዋሳ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ ዓመታትን የተሻገሩ ችግሮቻቸውን በመፍታት በተስፋ እንዲኖሩ እንዳስቻላቸው ለኢዜአ ገልፀዋል። በከተማው የፋራ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ አማረች አበራ በእርጅና ያዘመመ ቤታቸው በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና በመንግስት ትብብር በአዲስ መልክ መሰራቱ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመጀመር እንዳስቻላቸው ገልጸዋል፡፡ በበጎ ፈቃዱ ያረጀ ቤታቸው ብቻ ሳይሆን ጉስቁልና የተጫጫነው ኑሯቸው እንዲቀየር የወገን አለኝታነት ከፍተኛ እገዛ እንዳረገላቸው ነው ያመለከቱት።፡ የዓይን ብርሃናቸውን አጥተው ቤት በመቀመጣቸው ለገጠማቸው ችግር በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መፍትሄ ማግኘታቸውን የጠቀሱት ደግሞ የሂጠታ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ሹቃ ፋሬሾ ናቸው። የበጎ ፈቃድ የመደጋገፍ ባህል እያደገ መምጣቱ እሳቸውን መሰል በእድሜ የገፉና በህመም ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ዜጎችን ለማገዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2011 ጀምሮ በመሳተፍ ላይ መሆኑን የገለጸው ወጣት ተመስገን ያዕቆብ፤ አቅሙን፣ ጉልበቱንና ጊዜውን አስተባብሮ አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን እያገዘ ይገኛል። በዚህም በገንዘብ የማይተመን የመንፈስ እርካታ ከማግኘት ባለፈ አገርና ህዝብን በማገዝ የዜግነት ግዴታውን እየተወጣ መሆኑንም ይናገራል። የታቦር ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት መልካሙ ሚካኤል በበኩሉ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ይናገራል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት አገራዊ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማድረግ ሰፊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ነው የገለጸው። የሃዋሳ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ90 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል ብለዋል። በዚህም 246 ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት ግብ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በ18 ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን፤ የቤት እድሳትና ግንባታ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የደም ልገሳና ሌሎችንም ተግባራት የሚያካትት መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ99 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶችን በተሞክሮነት ያቀረበችበት ኹነት ነው
Aug 27, 2026 248
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶችን በተሞክሮነት ያቀረበችበት ስኬታማ ሁነት መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ በስኬት ተጠናቋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ለኢዜአ እንዳሉት፤ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ የኢትዮጵያ ውብ ገፅታ የተገለጠበት መድረክ ነው። ኢትዮጵያ በሽታን ለመከላከልና አክሞ ለማዳን የሚያስችል የጤና ፖሊሲ በመቅረፅ በዜጎች ጤና ላይ መሰረታዊ ለውጥ አስመዝግባለች ብለዋል። የእናቶችና ህፃናትን ሞት በመቀነስ፣ በመከታተል በቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ የጤና ስርዓት በመገንባት እመርታ መምጣቱን ገልጸዋል። በጉባዔው ኢትዮጵያ የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ ሊቀ-መንበር ሆና መመረጧን አስታውሰው፤ በጤናው ዘርፍ በዓለም መድረክ አፍሪካን ወክላ ንቁ ተሳትፎ ታደርጋለች ብለዋል። ጉባዔው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ልምዷን ያካፈለችበት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት ያረጋገጠችበት መሆኑንም ገልጸዋል። አፍሪካ የራሷን የጤና ፋይናንስ አቅም በራሷ መሸፈን መቻል እንዳለባት ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በስፋት ማምረት መጀመሯን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን ጋር በትብብር የማደግ ግቧን ለማሳካት ልምዷን አካፍላለች፤ ከሌሎችም ትማራለች ብለዋል።
በመዲናዋ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የደንብ ማስከበር ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Aug 27, 2026 241
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦በመዲናዋ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የደንብ ማስከበር እና ጥሰቶችን የመከላከል እንዲሁም የመቆጣጠር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ። ባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጸጸምና የ2019 በጀት ዓመት እቅዶች ላይ ከህዝብ ተወካዮች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከ1200 በላይ የከተማው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት ተቋሙ በ2018 በጀት አመት አፈጻጻም የላቀ ውጤት በማምጣት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸው ይህ ስኬት የተገኘው ከከተማው ነዋሪዎች በጋራ በመስራት ነው። ባለፈው በጀት ዓመት በተቋም ግንባታ፣ ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠርና የባለሙያዎችን አቅም ከመገንባት አንጻር ወጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት አመት በቴክኖሎጂ የሚመራ ተቋም መገንባት የሚያስችሉ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውንም ነው የተናገሩት። ዲጂታል የጥሪ ማእከል፣ ስማርት ኦፊስ፣ በሲሲቲቪ ካሜራ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመስጠት የከተማዋን ሰላም የሚያጠናክሩ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ መዋላቸውን ጠቅሰዋል። የደንብ ጥሰትን መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች ላይም ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን አንስተዋል። የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት የመገንባት፣ የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በስፋት መከናወናቸውንም ገልጸዋል። በውይይቱ ከተሳተፉ የመዲናዋ ነዋሪዎች መካከል ሻምበል በለጠ ጭናሾ እና አቶ ታረቀኝ ደሳለኝ የደንብ ማስከበር ስራዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን ከጉዳት ከመጠበቅ አኳያ ተጨባጭ ለውጦች መታየታቸውን አንስተዋል። የደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና መሰረተ ልማቶችን በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅ በኩል የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በክልሉ በቡሳ ጎኖፋ የመደጋገፍ እሴትን በማጎልበት ከተረጂነት የመውጣት ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ ነው
Aug 27, 2026 101
አዲስ አበባ ፤ነሃሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፡-በክልሉ በቡሳ ጎኖፋ የመደጋገፍ እሴትን በማጎልበትና ምርታማነትን በማሳደግና ከተረጂነት የመውጣት ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) ገለጹ። የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ «ከተረጂነት ወደ አምራችነት» በሚል መሪ ሐሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር)፤ በክልሉ ምርታማነትን በማሳደግ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በቡሳ ጎኖፋ የዳበረ እሴት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት ከእርዳታ ጠባቂነት በማላቀቅ ሙሉ በሙሉ ራስን ለመቻል ትኩረት መደረጉን ጠቁመዋል። ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ዜጎችን መደገፍ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውን ችለው ሕይወታቸውን መምራት እንዲችሉ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑንም አንስተዋል። የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈሪ በየና፤ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከ29 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ አባላትን በማፍራት በተጠናከረ መልኩ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ መልሶ በማቋቋም ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አክለዋል። በክልሉ ባለፉት አራት አመታት 8 ሚሊዮን ኩንታል ለትምህርት ቤቶች ምገባ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በሻሸመኔ፣ አዳማ እና ጊኒር ከተሞች ዘመናዊ የእህል ማከማቻ መጋዘኖች በመገንባታቸውን ጠቅሰው በቀጣይ እስከ ወረዳ ድረስ የማስፋት እቅድ እንዳለም አንስተዋል። በሀብት ማፍራት ረገድም በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው አሁን ላይ በ13 ትራክተሮችና 8 ኮምፓይነሮች እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የሸገር ከተማ ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ወይዘሮ ወርቅነሽ ሚደቅሳ፤ በከተማዋ ማኅበረሰቡን በማሳተፍ እና አባላትን በማፍራት ተጨባጭ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። በ2018 በጀት ዓመት በተገኘው 100 ሚሊዮን ብር በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ግብፅ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ዋጋ መክፈል አለባት-አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ
Aug 27, 2026 304
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ለምታበረክተው የ86 በመቶ የውሃ ሀብት ድርሻ ግብፅ ተገቢውን ዋጋ መክፈል እንዳለባት የቀድሞ የውሃ ሀብት ሚኒስትር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ገለጹ። ኢትዮጵያ በዓባይና በሌሎች ታላላቅ ወንዞቿ ላይ የመስኖ ግድብ በመገንባት ሁለንተናዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል የግብርና ምርታማነትን ማፋጠን እንዳለባትም አምባሳደር ሽፈራው አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿ የዘመናት ዕዳዎቿ እስኪመስሏት ድረስ ግብፅ በሸረበችው ሴራ አማካኝነት ሳትጠቀም ብትቆይም፤ ኢትዮጵያዊያን የተሸረበባቸውን ሴራ በመበጠስ በዓባይ ወንዝ ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት ብርሃን በመፈንጠቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። በአሁኑ ወቅት ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ በሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ከሀገር በመሻገር ቀጣናዊ የኢኮኖሚ በረከት ለመፍጠር ተችሏል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተፈጠረው ቀጣናዊ የኃይል ትስስርም የኢትዮጵያን በጋራ የማደግ አፍሪካዊ ርዕይን በአደባባይ የገለጠ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደት ትልም ሆኖ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ የቀድሞ የውሃ ሀብት ሚኒስትር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ግብፅ ለረጅም ዘመናት በምትከተለው ዓባይን የመቆጣጠር ፖሊሲ ምክንያት ኢትዮጵያ ዓባይን ሳትጠቀም ቆይታለች። ለረጅም ዘመናት ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የጠላትነት ትርክት ስታራምድ መቆየቷን ጠቁመው፤ በዚህም ኢትዮጵያ የዓባይን ውሃ በማልማት ሳትጠቀም ዓመታትን ማሳለፏን ተናግረዋል። በዚህ ቁጭት ኢትዮጵያውያን በሕብረ ብሔራዊ አንድነት በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ ግዙፉን ዓለም አቀፍ የኃይል ማመንጫ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን እውን ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያንን የመፈጸም አቅም በዓለም መድረክ ያሳየ ታሪካዊ የትውልድ አሻራ መሆኑን አውስተው፤ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት አስተማማኝ የውሃ ፍሰት እንዲያገኙ በማድረግ የጎርፍ አደጋንና የድርቅ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ትልቅ ጥቅም እያስገኘ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳንና ሌሎች የቀጣናው ሀገራት ጋር የፈጠረችው የኃይል ትስስርም ቀጣናዊና አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማፋጠን ጉልህ ፋይዳ እያበረከተም መሆኑን ገልጸዋል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው ቀጣናዊ የኃይል ትስስርም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ጫፍ እስከ አውሮፓ አባል ሀገራት የሚሻገር የኃይል ትስስር የማጠናከር አቅም እንዳላት ማሳያ ነው ብለዋል። የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት የአንድን ሀገር ልማትና ዕድገት ከማሳለጥ ባሻገር በትብብር የማደግ ርዕይን የሚያሳካ ወሳኝ መሠረተ ልማት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያን በታሪካዊ ጠላትነት የምትመለከትበት የግብፅ የትርክት ሴራ በአንድ በኩል የውሃ ጉዳይን ከፖለቲካ ጋር እንዲቆራኝ ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው የትብብር ሂደት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ብለዋል። በትብብር መንፈስ መሥራት ከተቻለ ኢትዮጵያ በግድቦቿ የምታከማቸውን የውሃ መጠን በመቆጣጠር የጎርፍ ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባሻገር በድርቅ ወቅት የሚጠቅም የውሃ አስተዳደር ሥርዓት ማስፋፋት እንደሚቻል ነው ያመለከቱት። ሀገራት በፍትሐዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመሥርተው አብረው ማደግ አለባቸው ያሉት አምባሳደሩ፤ ለዚህም ግብፅ ከግጭትና ከጠላትነት ትርክት በመውጣት የትብብር መንፈስን መከተል እንዳለባት አስገንዝበዋል። ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ከምታራምደው የብቻ የተጠቃሚነት ፍላጎትና አቀራረብ በመላቀቅ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ሀብታቸውን በፍትሐዊና ምክንያታዊ መንገድ እንዲጠቀሙ በትብብር መሥራት እንዳለባት ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ለምታበረክተው የ86 በመቶ የውሃ ሀብት ድርሻ ግብፅ ተገቢውን ዋጋ መክፈል እንደሚጠበቅባትም ነው የተናገሩት። በቀጣይም ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ጨምሮ በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ላይ ተጨማሪ ግድቦችን በመገንባት የኃይልና የመስኖ አቅሟን ማሳደግ እንዳለባት አምባሳደር ሽፈራው አስገንዝበዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ተጨማሪ የኃይል ማመንጫ ግድቦችንና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችላትን የሰው ኃይል፣ የገንዘብ አቅም፣ ልምድና ተሞክሮ ለማዳበር አስተዋጽኦ ማድረጉንም ጠቁመዋል። በዚህም የግብርና ምርታማነትን የበለጠ ለማሻሻል በዓባይና በሌሎች የውሃ ሀብት ወንዞቿ ላይ የመስኖ ልማትን በስፋት በማከናወን የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጡ ግድቦችን መገንባት እንደሚኖርባት አብራርተዋል። በዓባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የውሃ ሀብትን በፍትሐዊና ምክንያታዊ መንገድ መጠቀም፣ መጠበቅና በትብብር ማልማትን ያለመው የናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የጋራ የውሃ አስተዳደር ሥርዓትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። የናይል ትብብር ማዕቀፉን ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዑጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የፈረሙት ሲሆን፤ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን ደጋግመው የሚያነሱት ግብፅና ሱዳን ግን ማዕቀፉን እስካሁን አልፈረሙትም። አምባሳደር ሽፈራው እንደሚሉት፤ ግብፅና ሱዳን የናይል የትብብር ማዕቀፉን አለመፈረማቸው በቅኝ ግዛት ዘመን በብቸኝነት የመጠቀም ኢ-ፍትሐዊ አካሄድን ለማስቀጠል ከሚመነጭ ለብቻ የመጠቀም ፍላጎት ነው። በአሁኑ ወቅትም ግብፅ የናይል የጋራ ትብብር ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ እያለ በራሷ መንገድ ትብብር ለመፍጠር ጥረት የምታደርገው ፍትሐዊ የውሃ ሀብት የጋራ ተጠቃሚነትን የማትቀበል መሆኗን በገሃድ የሚገልጥ የአደባባይ ሐቅ ነው ብለዋል።
በሲዳማ ክልል ከተሞችን ይበልጥ በማዘመን ለስራና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ነው -ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Aug 27, 2026 99
ሀዋሳ፤ ነሀሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል ከተሞችን ይበልጥ በማዘመን ለስራና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በሀዋሳ፣ ይርጋለም፣ አለታ ጩኮና አለታ ወንዶ ከተሞች እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር፣ የሀይቅ ዳርቻ ልማት፣ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት፣የትምህርትና ሌሎችም መሰረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች የላቀ ስኬት እየተመዘገበባቸው ይገኛል ብለዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን ለስራ፣ ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ እና መልካም አስተዳደር የሰፈነባቸው እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛል። የሀዋሳ ኮሪደር ልማት አራተኛውን ዙር ለአገልግሎት ማብቃት እንደተቻለ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ ወንዶገነት፣ ዳዬና ለኩ ከተሞችም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሀዋሳ ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎን የሀይቅ ዳርቻ ልማት ስራ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አንስተው በተያዘለት ጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ሌት ከቀን ያለምንም እረፍት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በሲዳማ ክልል ሀዋሳን ጨምሮ ሌሎች ከተሞችንም ይበልጥ በማዘመን ለስራና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ስድስት ከተሞች የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው የሲዳማና የሀዋሳ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ወደ ስራ በመግባት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደርና የሀይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች ሀዋሳን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል መሰረት የተጣለባቸው ናቸው ብለዋል። አራተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ጠቁመው የሀይቅ ዳርቻ ልማቱንም በታቀደለት ጊዜ በጥራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሰባቱንም ቀን ለ24 ሰዓት እየተሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው በክልሉ የትምህርት ስብራትን በመጠገን የተሟላ ዕውቀትና ስብዕና የተላበሰ ዜጋን ለማፍራት በሚያስችል መልኩ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በዚህም በፌዴራል፣ በክልሉ መንግስት፣ በማህበረሰቡና አጋዥ ድርጅቶች የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻልና የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። እየተገነቡ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በትምህርት ሚኒስቴር እየተገነባ ያለውና በአለታ ጩኮ ከተማ የሚገኘው የሩፎ ዋኢኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መደረጉን ገልጸዋል። የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንገሻ ፊታሞ እንዳሉት በዞኑ የኮሪደር ልማትን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቷል። በዞኑ አለታ ወንዶን ጨምሮ በሶስት ከተሞች የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ያካተተ የኮሪደር ልማት እየተካሄደ እንደሚገኝና የአለታ ወንዶ ከተማን በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የዞኖች፣ የወረዳና የከተሞቹ አመራሮች ተገኝተዋል።
በከተማው ተግባራዊ የተደረገው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለልማትና መልካም አስተዳደር ስኬቶች አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል
Aug 27, 2026 93
ደብረ ብርሃን፤ ነሀሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡- በደብረ ብርሃን ከተማ ተግባራዊ የተደረገው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለልማትና መልካም አስተዳደር ስኬቶች አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ። የከተማ አስተዳደሩ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የተቋማት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ የውይይት መድረክ አካሄዷል። በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብእሸት እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን በልማትና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል። በተለይም በሰላም ማስፈን፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ ኢንቨስትመንትን መሳብና በሌሎች የልማት ሥራዎች አበረታች ውጤት እንዲመጣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል። አክለውም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሲቪል ሰርቪሱን ከብልሹ አሠራርና ከሙስና የጸዳ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ የተተገበሩ አዳዲስ የሪፎርም ሥራዎች የሠራተኛውን ተነሳሽነት እንዳሳደጉ ተናግረዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተደረገው ጥረት በከተማዋ ዘርፈ ብዙ የልማት ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማድረጉን አብራርተዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ መሠረት ምትክ በበኩላቸው፤ በሥራ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍና አሠራርን በማሻሻል ሕብረተሰቡን በላቀ ደረጃ ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። አክለውም የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ መሰል የመድረክ ውይይቶች አስፈላጊ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። አሠራሮችን በማሻሻል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተደረገው ጥረት ለሠራተኛው ተጨማሪ ተነሳሽነትን እንደፈጠረ የገለፁት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ አሳምነው ወልደተንሳይ ናቸው።
በክልሉ ግብርናን በማዘመን የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ሆነዋል
Aug 27, 2026 87
ጊዶሌ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርናን በማዘመን የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በጋርዱላ ዞን ያስገነባው የአርጎባ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ተመርቋል። በምረቃ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ ቦሼ ቦምቤ (ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ በመደመር መንግሥት እሳቤ የተከናወኑ የልማት ተግባራት የህዝብን ተጠቃሚነት እያሳደጉ ነው። በተለይ የመስኖ አውታር መስፋፋቱ ወቅትን ጠብቆ ብቻ ግብርናን የማከናወን ባህልን ከመቀየር ባለፈ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ገቢን ለማሳደግ ማገዙን ጠቁመዋል። የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር በበኩላቸው እንዳሉት፤ በክልሉ የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሃ ሀብቶችን በመጠቀም አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ለማሳካት እየተሰራ ነው። በዚህም በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር የመስኖ ልማትን በማስፋፋት የአርሶና አርብቶ አደሮችን የምግብ ዋስትናና ገቢ ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን ነው የገለጹት። በጋርዱላ ዞን የተገነባው የአርጎባ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው፤ ፕሮጀክቱ 180 ሄክታር መሬት በማልማት ከ800 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ግንኙነት ኪታሞ የመስኖ ፕሮጀክቱ የህዝቡን የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ ዘላቂ ጠቀሜታ እንዲኖረውም ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግ ይሠራል ብለዋል። በዞኑ የአርጎባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ንጉሤ ዳትኮ እና ካምባታ ካሊላ እንዳሉት፣ በአካባቢያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት የዝናብ ወቅት ብቻ ጠብቀው ከማልማት እንዳሻገራቸው ተናግረዋል። የመስኖ መሰረተ ልማቱን በሀላፊነት በመጠበቅ በዓመት ሦስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል
Aug 27, 2026 244
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የውኃ ጥራት ምርመራንና ምርምርን ለማጠናከር የተገነባውን ስፔሻላይዝድ የውኃ ምርመራ ላቦራቶሪ ዛሬ አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታመና ኃይሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የውኃ ጥራትን በተሟላ መልኩ መመርመር የሕዝብ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የውኃ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም የላቀ ሚና አለው። ላቦራቶሪው የሕክምናና የውኃ ማጣሪያ ሂደቶችን በተገቢው ለመምራትና የሀገሪቱን የምርመራ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይም ለመጠጥ፣ ለመስኖና ለኢንዱስትሪ የሚውል ውኃ ተገቢውን የጥራት ደረጃ እንደሚያሟላ ለመለየት ምርመራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የውኃ ምርመራ ውጤቶችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ ለምርምርና ለዕውቀት ማከማቻ ለማዋል ያስችላል ብለዋል። አንድ የውኃ ምንጭ በአንድ ወቅት ንጹሕ መሆኑ በሌላ ወቅትም ተመሳሳይ ጥራት እንዳለው አያረጋግጥም። በመሆኑም የውኃ ጥራት በየጊዜው በመመርመር ውጤቶቹ በዳታ መልክ መመዝገብና ለተለያዩ የልማትና የምርምር ሥራዎች መዋል እንዳለበት ጠቁመዋል። በላቦራቶሪው በኩል በሀገሪቱ በተበታተነ መልኩ የሚገኙ የላቦራቶሪ አቅሞችን በማስተሳሰር፣ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በአይኤስኦ ደረጃዎች የተመሠረተ የምርመራ ሥርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን የላቦራቶሪ አቅም ለማጠናከር እንደሚሠራም ተገልጿል። በኢንስቲትዩት የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀምበርነሽ ክንፈ በበኩላቸው፣ የውኃ ናሙና እና ምርመራ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ላቦራቶሪው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ላቦራቶሪው ከውኃ ጥራት ምርመራ በተጨማሪ የውኃ ጥራት ምርምርና ሥልጠና እንዲሁም ከአቅም በላይ የሆኑ ምርመራዎችን በማከናወን እንደ ሪፈራል ላቦራቶሪ ሊያገለግል እንደሚችልም አስረድተዋል። በተጨማሪም የተፋሰስና የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የውኃ ናሙናዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲያስመረምሩና ከውኃ ጋር ተያያዥ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። ላቦራቶሪው በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር የውኃ ጥራትን ከማረጋገጥ ባለፈ የምርምር፣ የሥልጠና፣ የገቢ ማመንጫና የውኃ ዲፕሎማሲ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ሲሉም ተናግረዋል። ላቦራቶሪው በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካላዊ፣ አካላዊና ማይክሮባዮሎጂያዊ ይዘቶችን በመመርመር የውኃ ጥራትን ለማረጋገጥ ያግዛል ያሉት ደግሞ የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የስፔሻላይዝድ ላቦራቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አብዱረህማን ሰይድ ናቸው። ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ ባሉ ላቦራቶሪዎች ሊከናወኑ ያልቻሉ አንዳንድ ምርመራዎች ወደ ውጭ በመላክ ይከናወኑ እንደነበር ጠቁመው፣ የምርመራ ውጤት ለማግኘት የሚወስደውን ጊዜም ያሳጥራል ብለዋል። በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ወይም ጎጂ ማይክሮኦርጋኒዝሞች ከተፈቀደው መጠን በላይ መኖራቸው በሰው ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል፣ የውኃ ጥራትን በላቦራቶሪ መፈተሽ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደኅንነት አዋጅን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ
Aug 27, 2026 288
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደኅንነት አዋጅን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችል የውይይት መድረክ መካሄዱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አስታወቀ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከቁልፍ መሰረተ ልማት አስተዳዳሪ ተቋማት ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት አዋጅ (ቁጥር 1426/2018) እና በሴክተር መለያ ስታንዳርድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በወቅቱ አዋጁን ወደ ተጨባጭ ትግበራ ለማሸጋገር የመጀመሪያውና መሠረታዊው ተግባር በወጣው ስታንዳርድ መሠረት ቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማትን መለየትና መመደብ መሆኑን ገልጸዋል። የሀገራችንን ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ከሳይበር ስጋቶችና ጥቃቶች መጠበቅ የኢትዮጵያን አጠቃላይ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ደኅንነት ከማረጋገጥ፣ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ከመጠበቅና ሀገራዊ ጽናትን ከመገንባት አንፃር ወሳኝ ሚና እንዳለው አስረድተዋል። በመድረኩ ላይ የአዋጁን አጠቃላይ ይዘት የሚያስተዋውቅ ገለጻ የቀረበ ሲሆን፣ አዋጁ ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነትን ለማጠናከር፣ የጉዳት ስጋቶችን ለመቀነስ እና ለተቋማት ጥበቃ ግልጽ የሕግ ማዕቀፍ የሚዘረጋ መሆኑ ተብራርቷል። በተጨማሪም "Critical Infrastructure and Sector Designation Standard" በሚል ርዕስ በቀረበው ገለጻ፣ ተቋማት በምን መስፈርት፣ ሂደትና የስጋት ግምገማ (Risk-based methodology) ቁልፍ ተብለው እንደሚለዩና ደረጃቸው እንደሚወሰን ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ስታንዳርዱ ተቋማት በሚሰጡት አገልግሎት ወሳኝነት፣ በስጋት ደረጃቸውና የሳይበር ጥቃት ቢደርስባቸው በሚያስከትሉት ሀገራዊ ተፅዕኖ ላይ ተመስርቶ ግልጽ አሰራርን የሚዘረጋ መሆኑ ተመልክቷል። በውይይቱ ወቅት አዋጁንና ስታንዳርዱን በውጤታማነት ወደ መሬት ለማውረድ በኢመደአ እና በቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ቅንጅታዊ አሰራር፣ የጋራ ኃላፊነትና የትብብር ማዕቀፍ ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም አዋጁ ሀገራዊ የሳይበር ጥበቃን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ገልጸው፣ ለትግበራው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የተቋሙ መረጃ አመላክቷል።
ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ያመጣቻቸውን ለውጦች ለሀገራት አካፈለች
Aug 26, 2026 151
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለተሻለ የህክምና ውሳኔ አሰጣጥ በመጠቀም ያመጣቻቸውን ለውጦች ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈል መቻሏን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ። ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለተሻለ የህክምና ውሳኔ አሰጣጥ በሰፊው እየተጠቀመች መሆኑንም ገልጸዋል። በአምስት የጤና ዘርፍ ምሰሶዎች ላይ በማተኮር ለአራት ቀናት የሚቆየው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። የመድረኩ ዋና ዋና የጤና ምሰሶዎች ዘላቂ የጤና ፋይናንስና የዲጂታል ጤና ሥርዓት፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና የሀገር ውስጥ ምርቶች አቅም ማሳደግ ናቸው። በዛሬው እለትም የጉባኤው አካል የሆነ በጤናው ዘርፍ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚና በሚል በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በርካታ የዲጂታላይዜሽንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶችን እየተጠቀመች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ለህክምና ውሳኔ አሰጣጥ ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ የወረቀት አሰራሮች በዲጂታል መተካታቸውን ገልጸው በመድረኩ ኢትዮጵያ ተሞክሮዋን አካፍላለች ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ የጤና ኤክስቴንሽን ፐሮግራም እየተገበረች መሆኑንና ይህንንም ተሞክሮ ማካፈሏን ጠቁመዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በአምስት ቋንቋ ከአንድ መቶ በላይ መመሪያዎችን ባለሙያዎች በስልክ እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በራስ የሚሰሩ እና የሚተዳደሩ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ማዋሏን አንስተው ለረጅም ጊዜ በተበታተነ መንገድ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ሲስተሞች ወደ አንድ ማምጣት መቻሉንም አክለዋል። በዚህም በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡንና አገልግሎት አሰጣጡንም ማቀላጠፉን ሚኒስትር ዴኤታዋ ጨምረው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ አገልግሎት ላይ የዋሉ የዲጂታላይዜሽንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች በህክምና ውሳኔ አሰጣጥ ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽአ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። እነዚህ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች በዘርፉ የተጠቃለሉ መረጃዎችን ለውሳኔ ሰጭ አካላት ማቅረብ እያስቻሉ መሆኑንና አጠቃላይ በጤና ስርዓቱ ላይ ትልቅ አቅም እየፈጠሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል።
የመድሀኒትና ህክምና መሣሪያዎች አቅርቦት አገልግሎት ዲጂታል ሪፎርም እውቅና አገኘ
Aug 26, 2026 251
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ለሀገሪቱ የመድሀኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ እውቅና ማግኘቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ገለጹ። አገልግሎቱ በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፉም ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት አራት ዓመታት በተተገበሩ መሠረታዊ የሪፎርም ሥራዎች በትኩረት አከናውኗል። ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል አቅርቦትን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማሸጋገር፣ የግዥ ሥርዓቱን ማዘመንና ግልጽ ማድረግ፣ የክምችትና ሥርጭት አሠራርን ማስተካከል እንዲሁም የምርቶች አቅርቦት ሰንሰለት ቅንጅትን ማጠናከር ይገኙበታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ሪፎርሙ የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማስቻሉንም አመልክተዋል። በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አጠቃላይ የግዥና የክምችት ሥርዓቱን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ማዘመን መቻሉ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንደጨመረው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበሩ አሠራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀው ይህም የደንበኞችን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሳደጉ ባሻገር አሠራሩን ወጪ ቆጣቢ ማድረጉንም ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ይህ በአገልግሎቱ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አህጉራዊ እውቅናም እያስገኘለት መሆኑን ጠቁመዋል። የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሰንሰለት የዘረጋው ቀልጣፋና ዘመናዊ ዲጂታል አሠራር አህጉራዊ ዕውቅና ያገኘ ሲሆን በቅርቡም በ5ኛው የአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት የልህቀት ሽልማት (ASCEA 2026) ከፍተኛውን የ«Gold Award» ሽልማት ማሸነፍ መቻሉንም አስታውቀዋል። ይህ ሽልማት አገልግሎቱ የሕክምና አቅርቦት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ለማስደገፍና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሠራቸው ስኬታማ ሥራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ እውቅና ወደፊት አገልግሎቱን አህጉራዊ ተወዳዳሪና ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትልቅ ብርታት እንደሚሆን አክለዋል።
ስፖርት
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ
Aug 27, 2026 251
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21 /2018(ኢዜአ)፦ የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ዛሬ ማምሻውን በሞናኮ ይፋ ሆኗል። ውድድሩ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት አንስቶ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ፎርማትን በማስቀረት 36 ክለቦች በ4 ቋቶች (Pots) በመከፋፈል እንዲጫወቱ የሚያደርግ አዲስ አሰራር (League Phase) መተግበር መጀመሩ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት 36ቱ ቡድኖች በ4 ቋቶች የተደለደሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ቋት 9 ክለቦች ይገኛሉ። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተደልድለዋል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ፣ ሮማ ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ፣ አስቶንቪላ፣ ፓርቶ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ሪያል ቤቲስ እና ፒኤስጂ አይንድሆቨን በቋት ሁለት የሚገኙ ክለቦች ናቸው። በቋት ሶስት ላይፕዚግ፣ ቪያሪያል፣ ናፖሊ፣ ሊል፣ ፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ቦዲ ግሊምት፣ ፊነርባቼ፣ ሻካታር ዶኔስክ እና ጋላታሳራይ ላይ ይገኛሉ። ስቱትጋርት፣ ሌንስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ ፣ ኤኢኬ አቴንስ ፣ ላስክ፣ ኮሞ፣ ቫይኪንግ እና ሳባህ በቋት አራት የተደለደሉ ክለቦች ናቸው። አንድ ክለብ በራሱ ቋት ካለ ሁለት ቡድንና በእያንዳንዱ ቋት ካሉ ሁለት ክለቦች ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። በዚህም አንድ ክለብ ስምንት ጨዋታ ያደርጋል። ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ። ቀሪዎቹ ስምንት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚገቡ ቡድኖች በሁለት የማጣሪያ ዙሮች ተጫውተው 16ት ውስጥ ይገባሉ። ከጥሎ ማለፉ አንስቶ ያለው የውድድር ፎርማት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። በዚሁ መሰረት ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከባርሴሎና፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየር ሙኒክ ፣ ባርሴሎና ከፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ በመጀመሪያው ሳምንት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የሚጠበቁ ናቸው። የጣልያኑ ኮሞ እና የአዘርባጃኑ ሳባህ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ክለቦች ናቸው።
ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት ሲፈልገው የነበረውን ካርሎስ ባሌባን አስፈረመ
Aug 25, 2026 330
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ዩናይትድ የካሜሮኑን አማካይ ካርሎስ ባሌባን ከብራይተን በ70 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን ዛሬ አስታውቋል። የ22 ዓመቱ ተጫዋች በኦልድ ትራፎርድ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት የተፈራረመ ሲሆን፣ እስከ እ.አ.አ 2031 በሚቆየው በዚህ ውል ላይ የክለቡ ተጨማሪ የ12 ወራት የማራዘም አማራጭ ተካቷል። ባሌባ ወደ አዲሱ ክለቡ መቀላቀሉን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፣ ለረጅም ጊዜ ለመቀላቀል ሳልመው በነበረው ማንችስተር ዩናይትድ መፈረም በመቻሌ ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል ብሏል። ከአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ጋር በመስራት እና የእሱን ልምድ በመጠቀም ብቃቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚፈልግም ገልጿል። ባሌባ በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር በክረምቱ የዝውውር መስኮት የፈረመ ሶስተኛው የአማካይ ተጫዋች ሆኗል። ዩናይትድ ቀደም ሲል አንድሬ ሳንቶስን ከቼልሲ በ48 ሚሊዮን ፓውንድ እና ዩሪ ቲሊማንስን ከአስቶንቪላ በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙ ይታወቃል።
ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል
Aug 24, 2026 347
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ቼልሲ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፏል። ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ኮል ፓልመር የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ጆአኦ ፔድሮ በ31ኛው ሴኮንድ ያስቆጠረው የዓመቱ ፈጣን ጎል ሆኖ ተመዝግቧል። ጆሹዋ ኪንግ እና ጎንዛሎ ጋርሺያ የፉልሃምን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ከአስቶንቪላ ወደ ቼልሲ የተዘዋወረው ሞርጋን ሮጀርስ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታው ጎል አስቆጥሯል። ከሪያል ማድሪድ ፉልሃምን የተቀላቀለው ጎንዛሎ ጋርሺያም የመጀመሪያ የሊግ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ጨዋታው እጅግ አዝናኝና በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ነበር። የቼልሲው አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ቀንቶታል። በአንጻሩ አዲሱ የፉልሃም አዲሱ አሰልጣኝ አርቫሎ አርቤሎአ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግዷል። ጨዋታውን ተከትሎ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል። የሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ከአርብ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ ለካፍ አስገባች
Aug 24, 2026 249
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገብታለች። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ ማስገባቱን አመልክቷል። ይህም ኢትዮጵያ ታላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን ማረጋገጧን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 26, 2026 664
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ የተከናወኑ ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ እውን ለማድረግ በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት የተገነቡ የተቀናጁ የትራንስፖርት ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎችና የንግድ ማዕከላት ምረቃ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው። ከተማ አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት የሚያገኝባቸውን በርካታ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል። ዛሬው ለምረቃ የበቁት የታክሲና የአውቶቡስ አገልግሎት ትራንስፖርት የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ዐረፍ ብሎ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ የጀመረችውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎች መካተታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎች ከነሙሉ አገልግሎታቸው ተዘጋጅተው ለሕዝብ ጥቅም ክፍት ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ከመመለስ ባሻገር የአካባቢ ጥበቃን ያማከሉ አረንጓዴ የትራንስፖርት አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡ በዚህም በመዲናዋ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለመገንባት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ከተማዋ ወደ አረንጓዴ ትራንስፖርት የምታደርገውን ሽግግር ያፋጥናሉ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ትራንስፖርትንና የግል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የመኪና ማቆሚያ አቅም ከ180 ሺህ በላይ መድረሱን ከንቲባዋ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ በእነዚህ የትራንስፖርትና የመኪና ማቆሚያ መሰረተ ልማቶች ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ብቻ እስከ አሁን ከ20 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማሪያም በበኩላቸው፤ ቢሮው ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፍጥነትና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡ መሰረተ ልማቶቹ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፉና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በውስጣቸው የንግድ ሱቆች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ አሳንሰሮችና የቲኬት መቆረጫ ቢሮዎች እንደተገነባላቸውም ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ጥበቃ ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያገዙ ነው
Aug 24, 2026 271
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ጥበቃ ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያገዙ እንደሚገኙ የክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት አስታወቀ። በክልሉ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የካርበን ሽያጭ በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተገልጿል። የኦሮሚያ ክልል ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አራርሳ ረጋሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ክልሉ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በተለይም የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን በመቀነስ የምድር ሙቀትን ለመግታትና የደን ሽፋን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመላክተዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉት ችግኞች መካከል አብዛኞቹ ጸድቀው ወደ ደንነት በመሸጋገራቸው የአካባቢውን አየር ንብረት በመጠበቅና የካርቦን ልቀትን በመቀነስ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበሩከቱ ይገኛሉ ብለዋል። ህብረተሰቡም ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ዘላቂ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር ተዘርግቶ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም አቅምን የማጠናከሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። አቶ አራርሳ ጨምረው እንደገለጹት፤ ክልሉ የደን ካርበን ንግድን በማስፋፋት በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በተደረገው ሳይንሳዊ ጥናት መሠረት አንድ ሄክታር የደን መሬት ከ10 እስከ 20 ቶን የሚደርስ ካርቦን ዳይኦክሳይድ በውስጡ የመያዝ እና የማመቅ ከፍተኛ አቅም እንዳለው አብራርተዋል። ይህም ክልሉ የሚያካሂደው የደን ልማት ለአለም አቀፉ የካርቦን ልቀት ቅነሳ ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሆነ አብራርተዋል። አቶ አራርሳ ኢትዮጵያ ከካርቦን ገበያ ገቢ ማግኘት የጀመረችበትን ታሪካዊ ሂደት ሲያብራሩ፤ የመጀመሪያው የደን ካርበን ሽያጭ እ.ኤ.አ በ2012 በባሌ ደን መጀመሩን አውስተዋል። እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥም 9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን ለገበያ በማቅረብ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል። ከሽያጩ የተገኘው ገቢም ደኑን ለጠበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ለቀጣይ የደን ልማት ስራዎች በመዋሉ የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። ድርጅቱም ከአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር በመቀናጀት እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት የተመዘገበውን 13 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የካርቦን መጠን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጁ ሆኗል። በቀጣይም የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን በሳይንሳዊ መንገድ በመንከባከብና የካርቦን ንግድን በመተግበር የአካባቢ ጥበቃውን እንዲሁም ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን የማሳደግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ውበትን ከስልጣኔ ጋር ያቆራኙ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች
Aug 23, 2026 291
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በኮሪደር እና በወንዝ ዳር ልማቶች የተገነቡት ቤተ መጽሐፍት እና የተለያዩ የመዝናኛ ስፈራዎች ለመጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋን የሰነቁ የስልጣኔ ማሳያዎች መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መዲናዋን ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ዘመናዊ ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘው ግዙፍ የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። ይህ በዋና ዋና አደባባዮች፣ መናፈሻዎች፣ መንገዶችና የወንዝ ዳርቻዎች ላይ ያተኮረው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፤ ውበትን ከጥቅም ጋር አዋህዶ የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ለውጦችን እያመጣ ነው። ኢዜአ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሉት፤ የተገነቡት የመጫወቻና የማንበቢያ ስፍራዎች የከተሜነት ምህዳሩን ከማሻሻላቸው ባሻገር ለወጣቶች የማሰላሰያና አዳዲስ ሐሳቦችን ማፍለቂያ ማዕከላት እየሆኑ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ጺዮን ጌታቸው፤ በቅርብ ዓመታት የተከናወኑት የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች አዲስ አበባን ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጋቸው ባሻገር፣ ነዋሪው አእምሮውን እያዝናና እውቀት እንዲገበይበት መንገድ መክፈታቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ግርማ አለሙ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቶቹ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉና ለአዲሱ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይም የተዘጋጁት የንባብ ማዕከላት ለተለያዩ ጥናትና ምርምሮች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ተናግረዋል። የመዲናዋ ነዋሪ ወጣት ፍራኦል ናትናኤል በበኩሉ የኮሪደር ልማቱ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በመገንባት በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብሏል። ይህም ለአገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጿል። አቶ እንዲሪስ ተሾመ እና አቶ ግርማ ንጉሴ የተባሉ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ የመዝናኛ ስፍራዎች ተገንብተዋል ብለዋል። አሁን ላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የእረፍት ጊዜ ለማሳለፍ እነዚህን አካባቢዎች ምርጫቸው ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማቶቹ፣ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍትና የመዝናኛ ስፍራዎቹ የከተማዋን ውበትና የህዝቡን የማህበራዊ ህይወት ደረጃ ያሳደጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አካባቢን ከብክለት በመጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራቱ ተግባር ይጠናከራል
Aug 21, 2026 377
ገንዳውሃ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ህብረተሰቡ አካባቢውን ከብክለት በመጠበቅና በማፅዳት ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራት ተግባርን አጠናክሮ እንዲቀጥል የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የሀገራዊ እንቅስቃሴ አካል የሆነ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ ተካሄዷል። የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መልካም ዋሲሁን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ፅዱና ውብ አካባቢን መፍጠር ለጤናማ ማኅበረሰብ ግንባታ መሠረት ነው። አካባቢን ከፕላስቲክና ከሌሎች ደረቅ እንዲሁም ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ በማድረግ ፅዱ አካባቢን መፍጠር አምራች፣ ጤናማና ውጤታማ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ለዚህም ማኅበረሰቡ የአካባቢ ፅዳት ሥራን የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳያደርግ የዘወትር ተግባርና የኑሮ ባህሉ በማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጉርባ በበኩላቸው፣ ከአካባቢ ንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሕብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንፅህና ዘወትር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል። አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ እንደ ወባ፣ ኮሌራና መሰል ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ የግልና የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ ባህል ሊደረግ ይገባል ነው ያሉት። የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ አዳነ ሀሰን እንዳሉት፣ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ለባለሀብቶች ሳቢ ለማድረግ በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብና የወጣት አደረጃጀቶች አካባቢያቸውን ሰላም ከመጠበቅ ጎን ለጎን ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። "ለነገው ሀገር ተረካቢ ሕፃናት ፅዱ ከተማን ማስረከብ የእኛ የወጣቶች ኃላፊነት ነው" ያለው ደግሞ በፅዳት ዘመቻው የተሳተፈው ወጣት ሃብታሙ አክሊሉ ነው። ከተማዋን ከፕላስቲክና ከሌሎች መርዛማ ኬሚካሎች በማፅዳት ማራኪና ለነዋሪዎቿ የምትመች ተመራጭ ከተማ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት በቀጣይም የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል። በፅዳት ዘመቻው የከተማዋ የመንገድ ዳርቻዎች፣ የገበያ ስፍራዎችና የሕዝብ መዝናኛ አካባቢዎችን ከቆሻሻ ፅዱ የማድረግ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ በየሳምንቱም የፅዳት ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል። በተካሄደው የፅዳት ዘመቻም የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1309
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1063
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1338
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1933
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 353
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች። ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 359
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 566
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ
Aug 19, 2026 468
ቡሄ በወርሃ ነሐሴ በ13ኛው ቀን ህፃናት ሆያ…. ሆዬ….! ሆ…. በሚል ዜማና ጅራፍ እያጮሁ የሚያከብሩት፤ እናቶች ለህፃናቱ ሙል ሙል ዳቦ በመስጠት እንኳን አደረሳችሁ እያሉ በድምቀት የሚያከብሩት በዓል ነው። ቡሄ ትርጓሜውም ብርሃን፣ብራ፣ ወጋግን ማለት ሲሆን ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገሪያ የተስፋ ምልክት ነው። በሀይማኖታዊ አንድምታው በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ብርሃን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ መገለጡ የሚታሰብበት ነው፤ በዚህም ደብረ ታቦር ይባላል፡፡ የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ የብርሃን ወጋገን የሚታይበት ሕፃናትና ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ «ሆያ ሆዬ» በማለት በረከትና ምርቃት የሚያፍሱበት የደስታና የፍቅር መግለጫ ነው። ህፃናትና ወጣቶች በየዕድሜያቸው ጅራፍ እያጮሁ በሕብረ ዝማሬዎች እየደመቁ በአብሮነት እና በደስታ የሚያከብሩት ትውፊታዊ በዓል ነው ቡሄ። የወጣቶችን ጉርብትና እና ማኅበራዊ ትስስር የሚያጎለብት እሴት ነው፤ በአከባበሩ ወቅት የሚንጸባረቀው የመረዳዳትና ያለውን የመካፈል ባህል ፋይዳውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሸጋገር ያስችላል። የቡሄ በዓል ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅ፣ ትውልድን በማቀራረብ እና ማኅበራዊ ትስስርን ይበልጥ በሚያጠናክር ተምሳሌትነቱ እልፍ ነው። በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከፍተኛ የቅርስ ጥናት ተመራማሪ መምህር መክብብ ገብረማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ የቡሄ በዓል የብርሃን ዘመን መምጣቱን የተስፋ ጎህ መቅደዱን ማብሰሪያ ነው፡፡ ቡሄ ከጨለማ ወደ ብርሃን ሽግግር መምጣቱን የሚያበስር በታዳጊዎች የሚዘከር የፍቅር፣ የአንድነትና የበረከት መገለጫና ተስፋ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ታዳጊዎችና ወጣቶች በበዓሉ ወቅት የሚያዜሙት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የ«ሆያ ሆዬ» ሕብረ ዜማ ለጋራ ትርክት ግንባታ ገንቢ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ በመሆኑ ማኅበራዊ ትስስርና የጋራ ዕሴቶችን ማጠናከር ያስችላል ብለዋል። ታዳጊው በሱፈቃድ አስሜ ቡሄ ከጓደኞቹ እና ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክርበት የደስታና የተስፋ በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ ቡሄ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠብቀውና ቀጣይ ሕይወቱን በአዲስ መንፈስ ለመምራት አቅም የሚፈጥርለት የብሩህ ዘመናትን ማለሚያ መሆኑን ይገልፃል። ቡሄ ከታላላቆቹ የወረሰው ከእኩዮቹ ጋር በፍቅርና በደስታ የሚያከብረው ነገን በተስፋ የሚያይበት ውብ በዓል እንደሆነ የሚናገረው ደግሞ ታዳጊው በረከት ምናለ ነው፡፡ የተጣሉ ጓደኛሞች እርቅ የሚያወርዱበት በዓል በመሆኑ ለትውልድ አንድነት እና አብሮነትን በማስተማር ረገድ ትልቅ ድርሻ አለውም ብሏል። ወጣት ያብስራ ጸጋዬ በበኩሉ ቡሄ በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጣ፤ ተራርቀው ከሚኖሩ የተለያዩ አካባቢ እኩዮቹ ጋር በአንድነት የሚያከብሩት በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ ከሁሉም ዓይነት ሕብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ታዳጊዎች የሚሰባሰቡበት፤ ሕብረ ብሔራዊነትን የሚያጠናክር የጋራ በዓል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ በኃይሉ ሞገስ ናቸው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ ማሳያ የአፍሪካውያን ኩራት - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
Aug 27, 2026 123
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከንግድ ተቋምነት ባለፈ የአፍሪካውያንን አንድነት፣ የነፃነት ታሪክና የጋራ ብልጽግና ስትራቴጂን በሰማይ ላይ የገነባ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት ተምሳሌት ነው። አህጉሪቱ ገና ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ባልተላቀቀችበትና የእርስ በእርስ ትስስር በሌለበት እ.አ.አ ከ1945 ጀምሮ የአፍሪካን ሕዝቦችና መሪዎች በማገናኘት የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አገልግሏል።ይህ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ አዲስ መንፈስ የሚለውን መፈክሩን በተግባር ያረጋገጠ ብሔራዊና አህጉራዊ ኩራትም ነው። አየር መንገዱ ለአፍሪካዊያን የጋራ ዕድገት የሚሠራ መሆኑን የሚያረጋግጠው ዋነኛው ተግባሩ፣ የገንዘብና የቴክኒክ አቅም አንሷቸው የፈረሱ ወይም የተቸገሩ የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን ብሔራዊ አየር መንገዶች በጋራ ባለቤትነት መልሶ የማቋቋምና የማጠናከር ዘላቂ ስትራቴጂው ነው። በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትርፋማና ግዙፍ ተቋም ከመሆን ባለፈ የአህጉሪቱን የአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ ለማሳደግ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የመደገፍ” ስትራቴጂካዊ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (AFRAA) እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ጋር በመተባበር በአህጉሪቱ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ እና የማኔጅመንት (የአመራር) አገልግሎት በመስጠት በርካታ አየር መንገዶችን በማቋቋምና በማጠናከር ቀዳሚውን ሚና እየተጫወተም ይገኛል። በዚህም በምዕራብ አፍሪካ ቶጎ ላይ መቀመጫውን ያደረገው አስካይ (ASKY) አየር መንገድ፣ የማላዊ አየር መንገድ፣ የዛምቢያ አየር መንገድ እና የኮንጎ አየር መንገድ የጊኒ አየር መንገድ እና ሌሎችም የአቪዬሽን ኢንቨስትመንቶች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ ጠንካራ ክንድነቱን አስመስክሯል። አየር መንገዱ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት ድርሻና ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ የአመራር፣ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ የአፍሪካ አቪዬሽን በጋራ እንዲያድግ አድርጓል። በአቪዬሽን እሴት ሰንሰለት (Aviation Value Chain) ውስጥ ያለውን መዋቅራዊ የበላይነት በመጠቀምም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች የተቀናጀ የቴክኒክና የስልጠና ድጋፍ ይሰጣል። ተቋሙ በእነዚህ አየር መንገዶች ውስጥ ስትራቴጂካዊ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ፣ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት መብትና የንግድ ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ ሙሉ የኦፕሬሽንና የማኔጅመንት ኃላፊነቱን በመውሰድ አፍሪካውያን ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የማጠናከር ስራ ሙሉ በሙሉ በፓን አፍሪካዊነት እና በእውነተኛ አፍሪካዊ የትብብር መንፈስ ላይ የተመሠረተ ታላቅ አህጉራዊ ስራ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚከተለው ሁለገብ ስትራቴጂ ግቡ የገበያ የበላይነትን መቆጣጠር ሳይሆን፣ አቪዬሽን ለሌላቸው ወይም አየር መንገዶቻቸው ለፈረሱባቸው አፍሪካውያን ወንድም ሀገራት የቴክኒክና የአመራር አቅምን ማካፈልም ነው። የአፍሪካ አየር መንገዶችን በጋራ ባለቤትነት ሲያቋቁም የኢኮኖሚ ጥቅሙን ብቻ አስልቶ ሳይሆን፣ በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት የአህጉሪቱን የሰዎችና የዕቃዎች ዝውውርን በማቀላጠፍ የጋራ አፍሪካዊ ብልጽግናን ለማምጣት በማለም ነው። ይህ አካሄድ አህጉሪቱ ከውጭ አየር መንገዶች ጥገኝነት እንድትላቀቅ የሚያደርግ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት መግለጫ ነው። የራሱን የአብራሪዎች ፣ የኢንጂነሮች እና የበረራ አስተናጋጆችን የሚያሰለጥንበትን ዘመናዊ የአቪዬሽን አካዳሚ በመገንባትም ለአቪዬሽን ዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ቁልፍ ሚናውን እየተጫወተም ይገኛል። የስልጠና እና የጥገና አቅሙ ከፍተኛ እንደመሆኑም ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የአቪዬሽን ባለሙያዎች ፣ እንዲሁም ከአህጉሪቱ ውጭ ላሉ አየር መንገዶች የስልጠና ፣የጥገና እና የቴክኒክ አገልግሎት በመስጠት የአህጉሪቱ የአቪዬሽን የጀርባ አጥንት መሆኑን አስመስክሯል። ይህ አህጉራዊ ትስስር ሀገራት የየራሳቸውን የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲያጠናክሩና በንግድ፣ በቱሪዝም እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የአፍሪካ ህብረት የአጀንዳ 2063 ራዕይ እንዲሳካ የበኩሉን ሚና ይጫወታል። በየዓመቱ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የሚያገኘው አየር መንገዱ እንደ ኤይር ባስ ኤ 350-1000 ያሉ ዘመኑን የዋጁ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት በአፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን በብቸኝነት የሚያበር ሲሆን በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ዘመናዊ የካርጎ (የጭነት) ተቋም በመገንባትም አገልግሎቱን አዘምኗል:: በመላው ዓለም 26 የሚሆኑ ታላላቅ አየር መንገዶች ያሉበት የስታር አሊያንስ አባል በመሆን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ ለሀገራችን የሚያስገኘው ገቢም ከዋነኛዎቹ የኢኮኖሚ አውታሮች ተርታ ቀዳሚው ያደርገዋል። ዓለምን ያስጨነቀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበትና ታላላቅ ዓየር መንገዶች በኪሳራ ስራ ባቆሙበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለው ቁርጠኝነትና ጠንካራ አመራር አማካኝነት በካርጎ/በጭነት አገልግሎት ለአፍሪካዊያንና ሌሎች የዓለም ሃገራት መድሃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጭነቶችን በማጓጓዝ አለኝታነቱንም ትርፋማነቱንም አረጋግጧል። ለአፍሪካውያን የሚሰራ እውነተኛ አፍሪካዊ ተቋም መሆኑን በተግባር ያረጋገጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዛሬም እንደ ትላንቱ የአህጉሪቱ የልማትና የአንድነት ድልድይ ሆኖ ቀጥሏል። አየር መንገዱ አሁንም የአፍሪካ አዲስ መንፈስ ሆኖ አህጉሪቱን ወደ ላቀ የብልጽግና እና የጋራ የከፍታ ምህዋር መምራቱን በጽናት ይቀጥላል።
ፕሬዝዳንቱ የገለጹት የኢትዮጵያ እውነት
Aug 26, 2026 766
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሔድ የቆየው የሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ማጠቃለያ በስኬት ማለቁ ተበስሯል። የውጭና የሃገራት እንግዶች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶች ኮሚሽነሮችና ተመካካሪዎች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቱ ያሰሙት ድምጽ ጆሮ ገብ ነበር። የሁሉንም ትኩረት የሳበ። ለመሆኑ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምን ብለው ነበር? በዚህ ንግግራቸውስ ምን መልዕክት አስተላለፉ? የሀገራዊ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ የማይታወቀውና ያልተለመደው የሆነበት ነው ። ይህ ምከክር ልዩነቶችን ከምክክር ይልቅ በኃይል ለመፍታት የመሞከር አባዜም ወደ ታሪክነት መሸጋገሪያው ነው ። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተረክ /political discourse/ ውስጥ በዘፈቀደ ሲገለጹ የሚሰሙት “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ፣ “ኢትዮጵያ ልትበተን ነው” ፣ “ኢትዮጵያ ልትፈርስ” ነው የሚሉና መሰል አገላለጾች የፖለቲከኞች እንጀራ መብያ እንጂ የኢትዮጵያ መንገድ መገለጫ እንዳልሆነ ያነሳሉ። ይልቁንም ኢትዮጵያን የማይገልጹና ከፍላጎታችን፣ ከሀገራዊ መሻቶቻችን ጋር አብረው የማይሄዱት እነዚህ አገላለጾች መነሻቸው ዝንታለም በሌሎች ሀሳብና ርዕይ የሚነግዱ የሀሳብ ተከታዮች እንጂ ኢትዮጵያውያን ፈጽሞ የሚናገሩት ቃል አይደለም ይላሉ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚሆነው መስቀለኛ ሳይሆን ቀጥ ያለ፣ ርቱዕ የእድገትና የህብረት መንገድ ብቻ መሆኑንም አስምረውበታል። ምክክር ማህበራዊ ባህላችን ውስጥ ያለንና የቆየ ሀብታችን ቢሆንም ይሄንን ነባር ባህል የፈተናዎቻችን መድህን የሀገር ግንባታችን ካስማ እንዲሆን መልክና ቅርጽ ተበጅቶለት ይፈጸም ዘንድ ቢያንስ በርሳቸው እድሜ እንደማያስታውሱ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የዚህን ሂደት ታሪካዊ ዋጋና ሀገራዊ ፋይዳ በማሰላሰል ለሀሳቡ እውንነት ለተጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ውጥንና ዓላማ ኢትዮጵያን ማዕከል በማድረግ ዘመንን ሊያሻግሩና ሀገርን ሊያጸኑ በሚችሉ የሀሳብ አውዶች ዙሪያ መወያየት እንደመሆኑም በመድረኩ የታየው ይሄው ነበር። በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎች፦ በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎችም መነሻቸው ይሄንኑ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ። የጋራ መሻትን ማጎልበት ቀዳሚው ሲሆን ልዩነቶችን በመሻገር የጋራ እጣፈንታንና ራዕይን የሚያጸና እውቀት የተንሸራሸረበት መድረክ መፍጠሩ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ምክክሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ስክነትና እርጋታ እንዲሸጋገሩ ያስቻለ፣ የፖለቲካ ውይይቱም ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ አስተዋይ በሆነ መንገድ እንዲመራም ያስቻለ መሆኑን ነው። ፕሬዝዳንቱ በሦስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ትልቁ ፋይዳ ደግሞ የይቅርታ እና የስርየት ጎዳና እንዲፈጠር መሰረት መጣሉ ሲሆን ከደመኝነት እና ከተቃርኖ ፖለቲካ በመውጣት በይቅርታና በመተሳሰብ የጋራ ጉዞን ለመቀጠል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ነው። የተለመደው የፖለቲካ ማጠንጠኛ ከሆነው ከአምባጓሮና ከነፍጥ በዘላቂነት በመላቀቅ የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላምና በመደማመጥ ላይ እንዲመሰረት ሃገራዊ ምክክሩ በር መክፈቱ በአራተኛነት ያነሱት ነጥብ ነው። ሌላኛው በአምስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳም በመከባበርና በሰመረ ቋንቋ፣ ከኃይለ ቃል በፀዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን ያሳየንም ነው። እንደ ሀገር ፈተና ባጋጠመን ጊዜ አንዳንድ ወዳጅ ሀገራት ከናንተ የተማርነው በህብረት ቆማችሁ ቀኝ ገዢዎችን ማንበርከክ ሆኖ ሳለ ለምን የውስጥ ጉዳያችሁን ለመፍታት ወደ ነፍጥ ታደላላችሁ? የሚል የወዳጅ ጥያቄ አዘውትሮ እንደሚቀርብም አንስተዋል። መንግስት የነበረ አካል ፣ ወደ ሽፍትነት የተለወጠበትን አጋጣሚ ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ውጥንቅጥ ችግር ሲያጋጥማቸው መቼውንም ቢሆን መውጫ መንገድ አጥተው እንደማያውቁም ጠቅሰዋል። ለዚህም ህልውናችንን የሚፈታተኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ሀገር እየጠበቅንም፣ እየመከርንም ኢትዮጵያችንን ማፅናት መቻላችን ነው ብለዋል። የዚህ መሰረቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ስልጣኔ፣ እውቀትና እውነትን አጋምዳ የያዘች በመሆኗ ችግር ሲያጋጥመን በጋራ ቆመን ጠላትን የምንመክተው የዳበረ፣ የጥንት ሀገር ስልጣኔ ባለቤት በመሆናችን ነው ይላሉ። እንደኛ የፖለቲካ እይታ ቢሆን ሌላ ድርሳን ነበረ። አጋምዶ የያዘን ግን አንዱ ጥንታዊ ሀገር ባለቤቶች በመሆናችን ነው። ሀገር ደግሞ የጋራ ላብ፣ የጋራ ደም፣ ተከሻና ጉልበት ውጤት ናት ሲሉም ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የውስጥ ችግር ባጋጠመን ወቅት፣ በአለም አቀፍ መድረክ እጅግ የማይመቹ ቃላት በኢትዮጵያ ላይ ተነጣጥረው እንደነበረ አንስተው የጋራችንን ሳይሆን የተወሰኑ የክፋት መንገድን የመረጡ ኃይሎችን ብቻ በመመልከት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ተበጥሷል፣ ወደነበረበት ለመመለስም ኢትዮጵያውያን ተስኗቸዋል በማለት ለማስተከዝ የሞከሩ እንደነበሩም አስታወሰዋል። አንዳንዶቹማ በዚህ ሀገራዊ የሀሳብ ጉባኤ ወቅት ሳይቀር የእንመካከር እንወያይ ሀሳብ ለሀሳብ እንለዋወጥ የሚለውን ጥሪ እንደ ትልቅ አጋጣሚ ከመውሰድ ይልቅ፣ ለክፋት መጠንስሻና ግጭት ማውጠንጠኛ ሊያደርጉ ሲባዝኑ መታዘባቸውን አንስተዋል። እነዚህን የመሰሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የሺህ ዓመታት ጥብቅ ማህበራዊ ሸማችንን በቅጡ ያልተረዱ፣ የህዝባችንን የውስጥ ጥንካሬ ያላወቁ ናቸው ይሏቸዋል ፕሬዝዳንቱ። እኛ ኢትዮጵያውያን የተራሮች፣ የሸለቆዎች፣ የደጋዎች፣ የወንዞች ልጆች ነን። የኢትዮጵያ ህዝብ ወንዞቹን ለመሻገርና ለመግራት የሚያስፈልገውን ትዕግስት ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። በእርግጥም አባይን የሚያቋርጥ ብቻ ሳይሆን ታሪክን የሚያሻግር ሁሉ ከነፋስና ወጀብ የበረታ ታላቅ የትዕግስት መከተሪያ ሊኖረው እንደሚገባ ያወቀ ብልህ ህዝብም ነው። ትዕግስት ስንቁ ነው። የሚሻገረውም በትዕግስተኛነትና በብርታት ነው።
ፋይዳ- ሌላው የኢትዮጵያ ዲጂታል ራዕይ የስኬት ጉዞ ማሳያ
Aug 26, 2026 133
ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዲጂታል ሥርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያም ይህን ዓለም አቀፋዊ ግስጋሴ ተቀላቅላ በዲጂታል ዘርፉ እመርታ እያሳየች ትገኛለች። በዚህም በዘመናዊ የለውጥ ጉዞ እንደ ዋና ምሰሶ የሚያገለግለው ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ አሁን ላይ የሀገሪቱ ዲጂታላይዜሽን ስኬት ጉልህ ማረጋገጫ ለመሆን በቅቷል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግር ስራ የማገዝ እና ዘመናዊ የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማት መገንባትን መነሻ በማድረግ በ2013 ዓ.ም በሙከራ ደረጃ ተጀምሯል። መንግስት እያንዳንዱ ነዋሪ በአካልም ሆነ በኦንላይን ማንነቱን በተአማኒነት ማረጋገጥ የሚችልበት ሥርዓት እንደሚያስፈልግ በመረዳት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን አስጀምሯል። ፕሮግራሙ የቅድመ-ሙከራ ስራዎችን ሲጀምር ቀደም ሲል የነበሩትን የተበታተኑ፣ ለአጭበርባሪዎች የተጋለጡ እና አንዱ ድርጅት ከሌላው ጋር መረጃ የማይለዋወጥባቸውን የቆዩ አሰራሮች በአንድ ማዕከላዊ የባዮሜትሪክ ስርዓት መተካት ዋነኛ ግብ አደረገ። ስርዓቱ ጠንካራ ህጋዊ መዋቅር እንዲኖረውም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን አስመልክቶ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይዳ መታወቂያን ተራ መለያ ሰነድ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ክብርና መብት ማረጋገጫ እንዲሁም ዘመናዊ የኢኮኖሚ ነጻነትን የሚያፋጥን የሉዓላዊነት መሣሪያ አድርገው ገልጸውታል። በተለይም በመንግስት መስሪያ ቤቶችና በግል ተቋማት ውስጥ የሚስተዋለውን የመረጃ መጭበርበር፣ አድካሚ ቢሮክራሲ እና ሙስናን ሙሉ በሙሉ በማስወገድ ረገድ ይህ ዲጂታል መሠረተ-ልማት የመፍትሔው ዋነኛ ቁልፍ መሆኑን በተደጋጋሚ አጽንኦት ሰጥተውበታል። ይህ የፋይዳ መታወቂያ ጉዞ ከኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የዲጂታል ስትራቴጂ 2030 ራዕይ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ሀገሪቱ እስከ 2030 .ድረስ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ፣ የተቀናጀ የኤሌክትሮኒክስ መንግስት አሰራር የሰፈነባት እና በዲጂታል ክፍያ የምትመራ የኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን ያቀደችውን ግብ ለማሳካት ፋይዳ እንደ ዋና የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል። ማንኛውም የዲጂታል አገልግሎት፣ የኦንላይን ንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ያለምንም እንከንና በተገቢው ፍጥነት መተግበር የሚችለው እያንዳንዱ ዜጋ ሊጭበረበር የማይችል አስተማማኝ የዲጂታል ማንነት ሲኖረው ብቻ በመሆኑ የፋይዳ ሚና ለስትራቴጂው ስኬት ወሳኝ ነው። በአሁኑ ወቅት የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም ከቀላል የፓይለት ፕሮጀክትነት ተሻግሮ፣ ወደ ትልቅ ሀገራዊ ተቋምነት ተቀይሯል። ተቋሙ ይበልጥ በራሱ እንዲንቀሳቀስና አገልግሎቱን እንዲያሰፋ «ፋይዳቨርስ» በሚል ስያሜ ራሱን የቻለ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በይፋ ተዋቅሯል። በዲጂታል መታወቂያ ስርዓ የተመዘገቡት ጠቅላላ የሰዎች ቁጥር ከ49 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘረጉ ከ12 ሺህ በላይ የባዮሜትሪክ መመዝገቢያ መሣሪያዎችን (Registration Kits) በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል የተመዘገበ ታላቅ ስኬት ነው። ከተመዘገቡት ነዋሪዎች መካከልም ከ14 ነጥብ 3 በመቶ በላይ የሚሆኑት የፕላስቲክ ካርድ ህትመታቸው ተጠናቆ በቀጥታ ማግኘት ችለዋል። ይህ የዲጂታል መታወቂያ አሰራር አሁን ላይ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር በጥብቅ በመተሳሰር የዕለት ተዕለት አገልግሎት ማረጋገጫ እየሆነ ይገኛል። እስከ አሁን ድረስ 150 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል የልማት ድርጅቶች (Integrated Agencies) የአሰራር ስርዓታቸውን ከፋይዳ ጋር ያቀናጁ ሲሆን፣ ይህም ተቋማቱ የደንበኞቻቸውን ማንነት በሴከንዶች ውስጥ በዲጂታል መንገድ እንዲያረጋግጡ አስችሏቸዋል። በዚህም ምክንያት እስከ አሁን ድረስ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ማለትም ከ194 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ማንነት ማረጋገጫ (eKYC) ፍተሻዎች በተሳካ ሁኔታ ተከናውነዋል። በፋይናንስ ዘርፍ ባንኮች አዳዲስ ደንበኞችን ለመመዝገብና የቆዩ አካውንቶችን ከፋይዳ ጋር ለማገናኘት ይህንን ቴክኖሎጂ በስፋት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ይህ የፋይዳ ዲጂታል አሰራር በሀገሪቱ ማኅበራዊ እና ፍትሃዊ አካታችነት ላይ የሚያሳድረው በጎ ተፅዕኖ እጅግ የጎላ ነው። ቀደም ሲል የመታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት በጂኦግራፊያዊ ርቀት፣ በወረቀት ቢሮክራሲ ወይም በሌሎች ማኅበራዊ ምክንያቶች ይገለሉ የነበሩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም በገጠር የሚኖሩ ዜጎች፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችና አሁን ላይ እኩል በሆነ መንገድ የመንግስትና የግል አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን በር ከፍቶላቸዋል። የዲጂታል ማንነት የዜግነት ክብርና ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ ማህበራዊ ፍትሕን የሚያሰፍን ሀገራዊ ድልድይ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። በሌላ በኩል፣ ከሀገራዊ ደህንነትና የፋይናንስ ዘርፍ ጥራት አንጻር የፋይዳ አስተዋፅኦ ወደር የለውም። የህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውርን (Money Laundering) እና ህገ-ወጥ ደላሎችን ለመግታት በባንኮችና በፋይናንስ ተቋማት የሚደረጉ ቁጥጥሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ማዕቀፍ ቀይሮታል። እያንዳንዱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከተረጋገጠ ግለሰብ ማንነት ጋር ብቻ የሚገናኝ በመሆኑ፣ የኢኮኖሚው ዘርፍ ግልፅነትና ተአማኒነት እንዲኖረው አድርጓል። ይህም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባበት ወቅት በራስ መተማመንን የሚፈጥርና ሀገሪቱን ለዓለም አቀፍ አሰራር ዝግጁ የሚያደርግ ትልቅ የቴክኖሎጂ እርምጃ ነው። የፋይዳቨርስ የወደፊት ራዕይ ይበልጥ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ ነው። ተቋሙ እድሜያቸው ለምዝገባ የደረሱ ተመዝጋቢዎችን ቁጥር 90 ሚሊዮን ለማድረስ እና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ከወላጆቻቸው መታወቂያ ጋር አገናኝቶ የመመዝገብ ልዩ አሰራርን ለማስፋት እየሰራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውንም አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት፣ ሲም ካርድ ለመግዛት፣ ፓስፖርት ለማደስ፣ የመንጃና የንግድ ፈቃድ ለማውጣት የፋይዳ ቁጥርን ብቸኛ እና ግዴታ የማድረግ ሂደትን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ተጠቃሚዎች የትኛው ተቋም የትኛውን መረጃቸውን ማየት እንዳለበት ራሳቸው መቆጣጠር የሚችሉበትን የሉዓላዊ ማንነት ቴክኖሎጂን ማጎልበት እና የግል መረጃዎችን ፍጹም ደህንነት ማረጋገጥም የስትራቴጂው አካል ነው። በአጠቃላይ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያሳየው ፈጣን እድገት፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ስኬታማነት ማሳያ ነው። ከግለሰቦች አልፎ ለባንኮች፣ ለትምህርት ተቋማት እና በሀገሪቱ ለሚኖሩ ስደተኞች ጭምር እኩል መብትና አገልግሎትን በዲጂታል መንገድ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል። ፋይዳ የኢትዮጵያን ዲጂታል ስትራቴጂ 2030 ራዕይን በማሳካት፣ ሁሉንም ዜጎች ያካተተ ፍትሃዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በዲጂታል ክፍያ የሚመራ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ ታምርት እና የኢንዱስትሪው ትንሳኤ
Aug 26, 2026 121
ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ጉዞ ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መዋቅራዊ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሀገር ውስጥ ምርትን ለማዘመን የታለመ ታላቅ ሀገራዊ መርሐ ግብር ነው። ንቅናቄው በአጭር ዓመታት ውስጥ በኢኮኖሚ ደህንነት፣ የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ አምጥቷል። ይህ ንቅናቄ በይፋ የተጀመረው በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። የንቅናቄው አላማ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ይስተዋል የነበረውን የቅንጅት ማጣት፣ የፋብሪካዎችን መዘጋት እና እጅግ ዝቅተኛ የነበረውን የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅም ለማሻሻል እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቀነስ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንቅናቄው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ትንሣኤና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት በተግባር የሚያረጋግጥ ዋና መሣሪያ ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች ላይ ገልጸዋል። አምራች ዘርፉን ማሳደግ የፖሊሲ ምርጫ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ነጻነት የማስከበር ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል። የምርት ማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከ2015 ዓ.ም አንስቶ ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመካሄድ ላይም ይገኛል። አራተኛው ዙር ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዝያ 24 እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል። በዚህ ኤክስፖ ላይ ከ270 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገበያ ትስስር ውል ተፈርሟል። በአሁኑ ወቅት ንቅናቄው ከተጀመረ ወዲህ ተዘግተው የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ፋብሪካዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የተመለሱ ሲሆን፣ ከ14 ሺህ 500 በላይ አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ እንዲሁም ከ350 በላይ አዳዲስ ግዙፍ ፋብሪካዎችም ወደ ምርት ገብተዋል። ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም 67 በመቶ የተሻገረ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ አምራቾች የምርት ድርሻም ከ30 በመቶ ወደ 45 በመቶ አድጓል። ከፋይናንስና ከምርት ዕድገት ባሻገር፣ ንቅናቄው ብዙ ቁጥር ላላቸው ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። በተጨማሪም ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በተደረገ ቅንጅት የኢንዱስትሪዎችን የቴክኖሎጂ ፍላጎት የሚያሟላ የሰለጠነ የሰው ኃይል የማፍራት ሥራ ጎን ለጎን እየተከናወነ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ የኢንዱስትሪ ምርቶችን፣ አልባሳትን እና የግብርና ማቀነባበሪያ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እስካሁን ድረስ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከንቅናቄው መጀመር አንስቶ በየዓመቱ በሚዘጋጁት የገበያ ትስስሮችም በአምራቾች እና በገዢዎች መካከል ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውል ተፈጽሟል። የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተወዳዳሪ ለማድረግ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስትቲዩትና በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አማካኝነት ለአምራቾች የቴክኒክና የሎጅስቲክስ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል። ይህም የሀገር ውስጥ ምርቶች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነትና እምነት እንዲጨምር አድርጓል። ወደፊት የመንግስት ትኩረት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢንዱስትሪ መንደሮችና የረጅም ጊዜ ብድር ማመቻቸት ላይ ያተኩራል። ለመንግስት ሰራተኞች የሚቀርቡ አልባሳት፣ ደብተሮችና የቢሮ ቁሳቁሶች በመቶ በመቶ ከሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲገዙ የሚያስገድደው አሰራር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ምርቶችን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ማድረግ የወደፊቱ ዋና አቅጣጫ ነው። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከመሸመት ወደ ማምረት እና ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል የተደረገ ትልቅ የኢኮኖሚ አብዮት በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚዋ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደሚያደርጋት ጥርጥር የለውም።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12389
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 21973
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15007
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20750
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 681
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 635
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።