ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአማራ ክልል በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል
Feb 27, 2026 15
ባህርዳር፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ። በክልሉ በተለይም በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ለኢዜአ ገልጸዋል። ወጣት መሳይ ታምራት በባህር ዳር ከተማ የዶሮ ጫጩት ማሳደግ እና ማከፈልፈል ስራ ላይ በማህበር ተደራጅቶ ወደ ሥራ ከገባ አንድ ዓመት ሆኖታል። በከተማ አስተዳደሩ በተደረገላቸው ሁለት ሼዶች ድጋፍ በአምስት ዙር የተረከቧቸውን የአንድ ቀን ጫጩቶች በማሳደግ ከ19 ሺህ በላይ ቄብ ዶሮዎችን ለአርቢዎች ማከፋፈላቸውን ገልጿል። ከአንድ አመት በፊት በ275 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል የጀመሩት ስራ አሁን ለይ በፍጥነት በማደጉ የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸወን አረጋግጧል። በቀጣይ ጠንክረው በመስራትና በመቆጠብ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ማሽን በመግዛት የእንቁላል ጣይና የሥጋ ዶሮዎችን በማስፈልፈል ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን አመልክቷል። ወጣት ዮሴፍ ፈቃዱ በበኩሉ ሰባት ሆነው በመደራጀት በተደረገላቸው የሼድና የአንድ ቀን ጫጩት ድጋፍ ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጿል። ከአንዳሳ የግብርናና የእንስሳት ምርምር ማእከል ተረክበው ያሳደጓቸውን ከሰባት ሺህ በላይ ቄብ ዶሮዎች በሰቆጣ፣ ጎንደርና ፍኖተሰላም አካባቢ ለሚገኙ አርቢዎች በማሰራጨት የተሻለ ገቢ ማግኘታቸውን ተናግሯል። አሁን ላይ አራት ሺህ የአንድ ቀን ጫጩቶችን ተረክበው በማሳደግ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው በቀጣይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በማርባት ተጠቃሚነታቸውን ለማስፋት እየሰሩ መሆኑን አብራርቷል። በአማራ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ የእንስሳት ባለሙያ ሙላቱ ዳኘው እንዳሉት የሌማት ትሩፋት በዶሮ ልማት፣ በወተትና አሳ ሀብት ልማት ዘርፉ ከፍተኛ ወጤት እያስመዘገበ ነው። በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊየን የአንድ ቀን ዶሮ ጫጩቶችን ለአሳዳጊዎች ለማሰራጨት ታቅዶ በተደረገ ጥረት እስካሁን ከሰባት ሚሊየን በላይ ጫጩቶችን ለሶስት ሺህ 439 አሳዳጊዎች ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል። በክልሉ ባለፉት 7 ወራት ከሰባት ሚሊየን በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶችን ለአሳዳጊዎች ማስረከብ መቻሉንም አመልክተዋል። የዶሮ እርባታ ዘርፍ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና ዘላቂ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ኢንስቲትዩቱ የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና ተጓዳኝ ስራዎች እያከናወነ ነው
Feb 27, 2026 22
አዳማ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ቦጋለ ለኢዜአ እንደገለጹት የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት በዓሣ ዝርያ ማሻሻያ ላይ ኢንስቲትዩቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በተለይ እየተተገበረ ያለውን የዓሣ ልማት ኢንሼቲቭ ለማሳካት ምርቱን የሚጨምሩ ዝርያዎችን በስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በክልሉ የውሃ አካላት በሙሉ የዓሣ ምርት መያዝ አለባቸው የሚል ግብ ተቀምጦ በዝርያ ማሻሻያ ላይ የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል። ኢንስቲትዩቱ በምርምር ማዕከላቱ የዓሣ ጫጩት የማባዛት ስራ እየሰራ መሆኑንና የተባዙ የዓሣ ጫጩቶችን ለአርሶ አደሩ በነፃ እየተሰራጨ መሆኑንም አክለዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ1 ሚሊየን በላይ የዓሣ ጫጩቶች መሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል። በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 5 ሚሊየን የዓሣ ጫጩቶች ለማሰራጨት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የባቱ የዓሣ ምርምር ማዕከልን ጨምሮ በኢንስቲትዩቱ ስር በሚገኙ የምርምር ማዕከላት ብዛት ያላቸው የዓሣ ጫጩት ዝርያዎች መባዛታቸውን ጠቁመው የዓሣ ጫጩት ብዜት ስራው በቤተ ሙከራና በኩሬ እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል። ከዝርያ ማሻሻያ ስራዎች በተጓዳኝ ከዓሣ እርባታ ጋር በተያያዘ የእውቀትና የአሰራር ክህሎት ስልጠናና አቅም ግንባታም እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ በሀገር ደረጃ የተያዘውን በምግብ ራስን የመቻልና የስነ ምግብ ስርዓትን ለማስረፅ የዓሣ ሀብት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የጎላ ሚና አለው ብለዋል። በዚህም የህፃናት የአእምሮ እድገት እንዲጎለብት፣ የመቀንጨርና መቀጨጭ ችግሮችን ለመቅረፍ ዓሣ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ተወያዩ
Feb 27, 2026 30
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአዘርባጃን ባደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ላደረጉላቸው ሞቅ ያለ እና የተከበረ አቀባበል ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት የሀገራቱ አጋርነት በየጊዜው እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል። የትብብር ዘርፎቹ ለሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር መሠረት የጣሉ ሲሆን፣ ዛሬ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በተደረገው ጥልቅ ውይይትም ግንኙነቱን እና ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። የሀገራቱ መሪዎች በዛሬው ዕለትም በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ክርክሮች ለሀገርና ህዝብ በሚጠቅሙ የፖሊሲ አጀንዳዎች ላይ ሊያተኩሩ ይገባል- ምሁራን
Feb 27, 2026 32
ሮቤ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፡-የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ክርክሮች ለሀገርና ህዝብ በሚጠቅሙ የፖሊሲ አጀንዳዎች ላይ ያተኮሩ መሆን እንዳለባቸው የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውንና ስትራቴጂዎቻቸውን በመገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ ማስተዋወቅ ጀምረዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጎላ ሚና እንዳላቸው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገልጸዋል። ፓርቲዎች በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ከጥላቻ ንግግሮች መራቅና ሀሳባቸውን በሰለጠነ መንገድ መግለጽ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያግዛል ነው ያሉት ምሁራኑ። ፓርቲዎቹ የሚያቀርቧቸው አማራጭ ሀሳቦች ወደ መሬት ሊወርዱ የሚችሉና ሀገርን የሚያሻግሩ ሊሆኑ እንደሚገባም አንስተዋል። በዩኒቨርስቲው የስነ ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት መምህርና ተመራማሪ መቅደስ መስፍን እንዳሉት፣ ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቅሰቀሳ ወቅት በከፍተኛ ኃላፊነት ሊሳተፉ ይገባል። ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ ለሀገር የሚበጅና ሊያሻግር የሚችል አማራጭ ፖሊሲና ስትራቴጂያቸውን በሰለጠነ መልኩ ሊያንጸባርቁ ይገባል ብለዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የምርጫ ሥነ-ምግባር ሕጉን ባከበረ መልኩ መንቀሳቀስ አለባቸው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና ሥነ- ተግባቦት ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ኡመር መሐመድኑር ናቸው። በአሁን ጊዜ ፓርቲዎቹ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አማራጮች አያደረጉት ያለው ክርክር በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው በመከባበር ላይ የተመሰረተ ሲሆን ነው ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የጂኦግራፊና አካባቢ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ተስፋዬ ፈዬ (ረዳት ፕሮፌሰር) በበኩላቸው የፓርቲዎች ንግግርም ሆነ ተግባር ህዝብን ያከበረ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ የሚያነሱት አማራጭ ሀሳብ ሕብረተሰቡ በቀላሉ ሊረዳው በሚችለው አግባብ መቅረብ እንዳለበትም አንስተዋል። በምርጫው ቅስቀሳና ክርክር ወቅት የሀገርን አንድነትና ሉአላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ንግግርም ሆነ ተግባር መፈጸም ተገቢ እንዳልሆነ በመረዳት ፓርቲዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ረዳት ፕሮፌሰሩ ያስገነዘቡት። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የተቀናጁ የጠለፋ ጥቃቶችን በተመለከተ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት
Feb 27, 2026 62
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የዜጎችንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ ተደጋጋሚ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ለማህበረሰቡ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። በተለይ ከዋትስአፕና ከቴሌግራም አካዉንቶች ጠለፋ መስፋፋትን ተከትሎ በቅርቡም የጥንቃቄ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወቃል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም ሰባተኛውን ጠቅላላ የምርጫ ሂደትን ተገን በማድረግ፣ አጥፊዎች ስልታቸውን ይበልጥ በማወሳሰብ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኝ አስተዳደሩ በሚደርሱት መረጃዎችና የሳይበር ደህንነት ትንተናዎች ማረጋገጥ ችሏል። ይህ ጥቃት በተለይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በርቀት ሆነዉ በዲጂታል አማራጮች የሚማሩ ግለሰቦችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ፣ መላው የዋትስአፕ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ሊያውቃቸው የሚገቡ የጥቃት ስልቶችና የመከላከያ መንገዶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ የመረጃ መንታፊዎች የሚጠቀሙባቸዉ ዋና ዋና የጠለፋ ስልቶች 1. የምርጫ ሂደትን እና የፖለቲካ ኩነቶችን ለሴራ መጠቀም፦ አጥፊዎቹ የሀገራዊ የምርጫ ወቅት መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የዜጎችን የፖለቲካ ፍላጎትና ስሜት ለጥቃት መቹ አጋጣሚ አድርገዉ እየተጠቀሙ ይገኛል፦ የምርጫ ደጋፊ በመምሰል፦ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊ በመምሰልና የፓርቲዎችን አርማ (Logo) በመጠቀም "ለፓርቲያችን ድጋፍዎን እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ይግለጹ" ወይም "የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ" የሚሉ አሳሳች መልዕክቶችን ይልካሉ። የምርጫ መረጃ አቅራቢ በመምሰል፦ "የምርጫ ጣቢያዎትን ለማወቅ"፣ "የዕጩዎችን ዝርዝር ለማየት" ወይም "የምርጫ ውጤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት" የሚሉ አሳሳች ማስፈንጠሪያዎችን (Links) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የዋትስአፕ አካውንት በቁጥጥራቸው ስር ያውላሉ። 2. ተከታታይ ጠለፋ እና የማንነት ስርቆት: ይህ ስልት እጅግ አደገኛ የሆነው ጥቃቱ የሚመጣው ከሚታወቅና ከቅርብ ሰው በመሆኑ ነው። የአንድ ግለሰብ አካውንት አንዴ ከተጠለፈ በኋላ አጥፊዎቹ የሚከተሉትን ድርጊቶች ይፈጽማሉ፦ የገንዘብ ማጭበርበር፦ የተጠለፈውን ሰው ማንነት በመጠቀም በስልክ አድራሻ ዝርዝሩ ውስጥ ላሉ ወዳጆች "ድንገተኛ የጤና ችግር አጋጥሞኝ ነው" ወይም "ከምርጫ ስራ ጋር በተያያዘ ገንዘብ በአስቸኳይ አስፈልጎኝ ነው" በማለት የባንክ አካውንት በመላክ ከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ይፈጽማሉ። ተጨማሪ ጠለፋ፦ ለሌሎች የሥራ ባልደረቦችና ኃላፊዎች አሳሳች ሊንኮችን በመላክ የጥቃቱን ሰለባ ያስፋፋሉ። በዚህም ወሳኝ የሆኑ የመንግስት እና የተቋማዊ መረጃዎችን የመስረቅና የማጥፋት ስጋት ይፈጥራሉ። 3. ተማሪዎችን እና የከፍተኛ ትምህርት ተከታታዮችን ኢላማ ማድረግ፦ በውጭ ሀገር የሚማሩ ወይም በኢንተርኔት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ዜጎችን ኢላማ በማድረግ፤ ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ የተላከ በማስመስል (ለቪዛ እድሳት፣ ለትምህርት ክፍያ ቅናሽ ወይም ለፈተና መረጃ በሚል ሰበብ) ሊንኮችን ይልካሉ። ተማሪዎቹ መረጃቸውን ሲያስገቡ የግል መረጃቸውና የዋትስአፕ አካውንታቸው ወዲያውኑ ይረበሻል። 4. የባለ 6-አሃዝ ኮድ ማጭበርበር: አጥፊዎች የእርስዎን ስልክ ቁጥር በመጠቀም በሌላ ስልክ ዋትስአፕ ለመክፈት ይሞክሩና ወደ እርስዎ ስልክ በቴክስት (SMS) የሚመጣውን ባለ 6-አሃዝ ኮድ፤ "በስህተት ወደ አንተ የተላከ ኮድ ስለሆነ እባክህ መልሰህ ላክልኝ" በማለት ይጠይቃሉ። ይህንን ኮድ አሳልፈው ከሰጡ አካውንትዎ ወዲያውኑ ይጠለፋል። ራስን እና ተቋምን ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች 1. ባለሁለት-ደረጃ ማረጋገጫን ያብሩ፦ ይህ አካውንትዎን ከጠለፋ ለመጠበቅ ቁልፍ መከላከያ ነው። እንዴት ይበራል? WhatsApp Settings > Account > Two-step verification > Turn On በመግባት የራስዎን ሚስጥራዊ ባለ 6-አሃዝ ቁጥር (PIN) እና የኢሜይል አድራሻ ያስገቡ። 2. የማረጋገጫ ኮድን በምንም ምክንያት አያጋሩ፦ ወደ ስልክዎ በሜሴጅ የሚላክን የዋትስአፕ ማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለምንም አይነት አካል (ለጓደኛም ሆነ ለቤተሰብ) አሳልፈው አይስጡ። 3. አጠራጣሪ ሊንኮችን (Links) አይጫኑ፦ በተለይ ከምርጫና ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከማይታወቅም ሆነ ከሚታወቅ ሰው የሚላኩልዎትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመጫንዎ በፊት ትክክለኛነቱን በሌላ የመገናኛ ዘዴ ያረጋግጡ። 4. የገንዘብ ጥያቄን በመደበኛ ስልክ ያረጋግጡ፦ ማንኛውም ሰው በዋትስአፕ በኩል የገንዘብ እርዳታ ሲጠይቅዎት፣ አካውንቱ ተጠልፎ ሊሆን ስለሚችል ገንዘብ ከመላክዎ በፊት በመደበኛ ስልክ በመደወል ድምፁን ሰምተው ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ። 5. የመረጃ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ወሳኝ የሆኑ ሀገራዊ እና ተቋማዊ መረጃዎችን በዋትስአፕ ከመለዋወጥ መቆጠብ አለባቸው። ለሥራ ጉዳይ ደህንነታቸው የተረጋገጡ (Secure) የውስጥ መገናኛ ዘዴዎችን መጠቀም ይመከራል። አካውንትዎ ከተጠለፈ ምን ማድረግ አለብዎት? ወዲያውኑ ድጋሚ ለመመዝገብ ይሞክሩ፦ የዋትስአፕ መተግበሪያዎን አጥፍተው (Uninstall) እንደገና በመጫን ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡ። በSMS የሚላክልዎትን ኮድ ሲያስገቡ አጥፊው ከእርስዎ አካውንት በራስ-ሰር እንዲወጣ (Log out) ይደረጋል። ለወዳጅ ዘመዶችዎ መልዕክት ያስተላልፉ፦ አካውንትዎ ተጠልፎ እንደነበር በመደበኛ ስልክ ወይም በሌሎች አማራጮች በማሳወቅ፣ ከእርስዎ ስም ለሚመጣ ማንኛውም የገንዘብም ሆነ የሊንክ ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጡ ያስጠነቅቁ። ሪፖርት ያድርጉ፦ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊ ከሆኑ ወይም ጥቃቱ ተቋማዊ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ ጉዳዩን ወዲያውኑ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሪፖርት ያድርጉ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገሪቱን የሳይበር ምህዳር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ለሳይበር ሌቦች በር እንዳይከፍት ያሳስባል። ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የካቲት 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
ፖለቲካ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው
Feb 27, 2026 38
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። የኢዜማ፣ የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የአብን ፓርቲ አመራሮች ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የሁሉንም አካላት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እንዳሉት፥ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የምርጫው ሂደት ስኬታማነት ወሳኝ ነው። በሂደቱም መራጩ ሕዝብ፣ ገዥው ፓርቲ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ ምርጫ ቦርድና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የየራሳቸው የጋራና የተናጠል ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ትልቁ ዓላማችን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሆን አለበት ያሉት አርክቴክት ዮሐንስ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካልና ዜጋ ሕግን በማክበር ሀገራዊ ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር አበራ በቀለ በበኩላቸው የዘንድሮው ምርጫ ለኢትዮጵያ የተረጋጋ ፖለቲካዊና ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ጠንካራ መሠረት የምናኖርበት ነው ብለዋል። በምርጫው የሚያሸንፍ ሐሳብ ይዘን እንቀርባለን ያሉት አቶ አበራ ምርጫው ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዲሞክራሲ ምዕራፍ የሚያሻግር ወሳኝ የታሪክ አጋጣሚ መሆኑን አስገንዝበዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሥራ አስፈጻሚ አባል የሱፍ ኢብራሂም፥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር በዲሞክራሲያዊ ምርጫና በሀሳብ የበላይነት ብቻ መሆን እንዳለበት ፓርቲያቸው በጽኑ እንደሚያምን ገልጸዋል። ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እጅግ ሰፊ ዝግጅትን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ከማኒፌስቶ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ አማራጭ ሐሳብን የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚጠይቅ አስረድተዋል። ምርጫ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ አካል በመሆኑ፥ ፓርቲያቸው ለሀገር ወሳኝ በሆነው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የፖርቹጋል አምባሳደርን አሰናበቱ
Feb 26, 2026 98
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊሳ ፋራጎሶ አሰናብተዋል። በዚሁ ወቅት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፤ አምባሳደሯ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በተለያዩ ዘርፎች የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም አምባሳደሯ በቱሪዝም፣ በባህልና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድ የነበራቸው ከፍተኛ ሚና በቀጣይ የትብብር መስኮችም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ተሰናባቿ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊሳ ፋራጎሶ በበኩላቸው፤ የኢትዮ-ፖርቹጋል ግንኙነት ከ500 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ወዳጅነትን ያሳለፈ ነው ብለዋል። ባለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ የስራ ቆይታቸውም በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በቱሪዝምና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች ትስስሩን ማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን እንዳከናወኑ ገልጸዋል። የሀገራቱ ተቋማዊ ግንኙነት መጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት አምባሳደሯ፤ በአዲስ አበባና በፖርቶ ከተሞች መካከል የሚካሄደው የቀጥታ የአየር በረራ አገልግሎትም ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል። የአየር በረራ አገልግሎቱም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የሀገራቱን የትምህርትና የባህል ትብብር መስክ ይበልጥ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም የሁለትዮሽ ትብብሩን ይበልጥ ለማሳደግ በሀገራቱ የሚገኙ ሃብቶችንና የልማት ዕድሎችን የሚያስተዋውቁ የምክክር መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በተለይም በአውሮፓ ሕብረት የግሎባል ጌትዌይ ማዕቀፍ ሥር የንግድ ፎረም ለመፍጠር የተጀመረው ጥረት ለቀጣይ ትብብሮች ተስፋ ሰጪ እንደሚሆኑ አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ
Feb 26, 2026 95
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል። ይኅው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያስታወቀው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውም ተገልጿል። በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።
በሁሉም የልማት መስኮች የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና ሀገራዊ ዕድገትን ያፋጠኑ ስኬቶች ተመዝግበዋል
Feb 26, 2026 75
ቦንጋ/ሚዛን፤የካቲት19/2018 (ኢዜአ)፡-ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም የልማት መስኮች የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑ የልማት ስኬቶችን በተግባር ማስመዝገቡ ተገለጸ። ፓርቲው ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክቱ የሆነውን የስንዴ ነዶ እና ማኒፌስቶውን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሚዛን አማን እና ቦንጋ ከተሞች ዛሬ ለህዝብና ለደጋፊዎቹ አስተዋውቋል። በቦንጋ ከተማ በተካሄደ መድረክ ላይ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፣ ብልጽግና ባለፉት ዓመታት እዳን ወደ ምንዳ በመቀየር በፈጠራና በፍጥነት እሳቤ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። ፓርቲው የተከተለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ዕሳቤ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት ድህነት ወጥታት በልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ለመሸጋገር የሚያስችላት መሆኑን ጠቅሰዋል። በፓርቲው መሪነት ባለፉት ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስኬቶች መመዝገባቸውንና ይህም ተጠናከሮ መቀጠሉን ነው የተናገሩት። በማህበራዊ ዘርፍም ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን በማከናወን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ትችሏል ብለዋል። በዞኑ ሰፊ የልማት ሀብት ቢኖርም ትኩረት ባለመሰጠቱ ህዝቡ ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል ያሉት አስተዳዳሪው፣ በፓርቲው መሪነት በዞኑ ልማትን ለማፋጠን በተሰራው ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነው የስንዴ ነዶ የአብሮነት፣ የጥንካሬ፣ የአንድነትና በምግብ ራስን የመቻል መሆኑን ጠቁመው፣ ፓርቲውን መምረጥ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ማስቀጠል ነው ብለዋል። በብልጽግና ፓርቲ የካፋ ዞን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ሀይሌ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ብልፅግና ፓርቲ እንደሀገር የገጠሙ ስብራቶችን በመጠገንና ልማትን በማስቀጠል ዜጎችን ተጠቀሚ እያደረገ ይገኛል። በካፋ ዞን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስመዝገብ በትኩረት በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት እየመጣ ነው ያሉት ሀላፊው፣ በዚህም የዞኑ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መጥቷል ብለዋል። ዞኑ በልማት ወደኋላ ቀርቶ እንደነበረ አቶ አጥናፉ አስታውሰው፣ በፓርቲው መሪነት ይህን ለመቀየር የተወሰደ እርምጃ ህዝብን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዜና በሚዛን አማን ከተማ በተከሄደ መድረክ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንዳሉት ፓርቲው የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑ የልማት ሥራዎችን በተጨባጭ እያከናወነ ይገኛል። ምርጫ ለአንድ ሀገር ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ በመሆኑ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል። በፓርቲው መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችና አዳዲስ እሳቤዎች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የልማት ተምሳሌት የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። "ብልጽግና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡና ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑ የልማት ሥራዎችን በተጨባጭ ያስመዘገበና ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ዓልሞ የሚሰራ ነው" ሲሉ አክለዋል። ዞኑ ከሀገራዊ ለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚ መሆኑን የገለጹት አስተዳዳሪው፣ በብዝሃ ኢኮኖሚ እይታ የተገነባው የደንቢ ኢኮ ሎጅ ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል ፓርቲው ድህነትን ለማሸነፍ በግብርና ዘርፍ የጀመራቸው ኢኒሼቲቮች ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበባቸው በመሆኑ የማኅበረሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ ነው ብለዋል። ብልጽግና የኢኮኖሚ አማራጭ መፍጠሩ በአካባቢያችን ያሉ አንጡራ ሀብቶችን አውጥቶ ለመጠቀም አስችሏል ያሉት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የቤንች ሸኮ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን ናቸው። በቦንጋና በሚዛን አማን ከተማ በተካሄዱ መድረኮች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የገነባችው አስተማማኝ ሠራዊት በቀጣናው ያላትን የሠላም አለኝታነት የሚያጸና ነው
Feb 26, 2026 89
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የገነባችው አስተማማኝ ሠራዊት በቀጣናው ያላትን የሠላም አለኝታነት የሚያጸና መሆኑን የቀድሞው የአየር ወለድ አዛዥና ወደር የሌለው የኢትዮጵያ የጦር ሜዳ ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ገለጹ፡፡ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በተከበረበት ወቅት፣ ከኢትዮጵያ ባለፈ የቀጣናውንና የአፍሪካን ነጻነትና ሰላም ዛሬም እንደትናንቱ የሚያስከብር አስተማማኝ ኤሊት ፎርስ ተገንብቷል ብለዋል፡፡ የሠራዊቱ የተሟላ ዝግጁነት በድፍን አፍሪካ ሰላም እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቀጣናው ላሉ ሀገራትም አለኝታና መከታ እንደሚሆን ገልጸዋል። የቀድሞው የአየር ወለድ አዛዥና ወደር የሌለው የኢትዮጵያ የጦር ሜዳ ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ወታደራዊ ሳይንስን፣ ስነ-ልቦናዊ ግንባታን እና የአካል ብቃትን መሠረት አድርጎ የተገነባ ሠራዊት ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። ስልጠና የድል በር መክፈቻ ቁልፍ ነው ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ሠራዊት ጥራት ያለው፣ በሁሉም መልኩ የተዘጋጀ አስተማማኝ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል። በ65ኛው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የምስረታ በዓል የተመለከቱት የሠራዊቱ ትርኢትም በሁኔታዎች የማይበገር ወሳኝ ኃይል መገንባቱን ያሳየ ነው ብለዋል። "በሕይወት ኖሬ የኢትዮጵያ ሠራዊት በዚህ መልኩ ተገንብቶ በማየቴ እንደገና እንደተወለድኩ ነው የቆጠርኩት" ሲሉም ነው የገለጹት። ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገነባችው ኃይል የራሷን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ የአካባቢው ሀገራት ጭምር የሚታመኑበትና ዋስትና የሚሆናቸው ኃይል ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ሠራዊት ቁመና እና ጥንካሬ ያደነቁት ብርጋዴር ጀኔራሉ፥ ይህም ሀገራችን በቀጣናው ያላትን የሠላም አለኝታነት የሚያጸና መሆኑን ገልጸዋል። ሠራዊቱ ሁሉንም አቀፍ እውቀትና ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቀ በመሆኑ በአየር፣ በባህር፣ በየብስ እንዲሁም በየትኛውም አውድና የመሬት ገፅ ድል አብሳሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ አክለውም ኢትየጵያ ተግባርና ኃላፊነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ በሥነ-ምግባር የታነጸና ከራሷ አልፎ ለአፍሪካውያን ሠላም ዋስትና የሚሆን ሠራዊት መገንባቷን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምጽዋ ጫፍ በባህር ላይ የሚያጋጥሙ ሽብሮችን የሚያስቀር ኤሊት ፎርስ መገንባቱን መግለጻቸው ይታወቃል። ተቋም የምንገነባው፣ ኤሊት ፎርስ የምንገነባው፤ በቀጣናችን ውጊያና ሽብር እንዳይፈጠር ነው፤ ሲፈጠርም በአጠረ ጊዜ ለመቋጨት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ይህን አይነት ተቋም በመገንባቷ የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ሀገራት እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ማህበራዊ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናወኑ
Feb 27, 2026 58
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከአዘርባጃን ፕሬዝደንት ኢልሃም አልየቭ ጋር ከሚያደርጉት ውይይቱ ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል። እነዚህ ሀውልቶች የህዝቡን የማይበገር አንድነት የሚወክሉ ሲሆን፤ ለአዘርባጃን አንድነት መስዋዕትነት ለከፈሉ ሁሉ ያለንን ጥልቅ ክብር መግለጽ እንወዳለን ሲልም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
ትውልዱ ራሱን በሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን የጥበብ ስራዎች ውስጥ በማየት የሀገሩን አርት ለማሳደግ መትጋት አለበት
Feb 26, 2026 92
አምቦ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ትውልዱ ራሱን በሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን የጥበብ ስራዎች ውስጥ በማየት የሀገሩን አርት ለማሳደግ ጠንክሮ መስራት አለበት ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) አስገነዘቡ። የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን የትውልድ ስፍራ ያስገነባው ትምህርት ቤትም ለምረቃ መብቃቱ ተመልክቷል። የሎሬቱን 20ኛ ዓመት ህልፈተ ህይወት መርሃ ግብርን መነሻውን በአዲስ አበባ ራስ መኮንን ድልድይ (70 ደረጃ) ከሚገኘው የሎሬቱ መታሰቢያ ሐውልት ጋር በማድረግ ወደ ሎሬቱ ትውልድ ከተማ አምቦ በማቅናት በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ-ጥበብና ስነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው በዋነኝነት ሀገር ለጥበብ ሰዎች ያላትን ክብር ለመግለፅ ነው ብለዋል። እንዲሁም የሎሬቱን የጥበብ ትሩፋትና በጎ አሻራ ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑንም አመልክተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም “የአሁኑ ትውልድ ራሱን በሎሬቱ የጥበብ ስራዎች ውስጥ በማየት የሀገሩን አርት ለማሳደግ ጠንክሮ መስራት አለበት” ብለዋል። ሚኒስቴሩ ከዚህ በኋላ በየዓመቱ የሎሬት ፀጋዬን የአርት ስራዎች የሚዘክርና የሚያሳዩ ስራዎችን በቋሚነት ለመስራት ማቀዱንም ይፋ አድርገዋል። በዛሬው ዕለትም በሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን 20ኛ የዕረፍት መታሰቢያ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው የኢፈ-ቦሩ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል። የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ትምህርት ቤቱን ከማስገንባት ባለፈ፣ ለተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደት ግብዓት የሚሆኑ ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርጓል። በዚህም መሠረት ለትምህርት ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ላፕቶፖች፣ ፕሪንተሮችና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስ በስጦታ መልክ አበርክተዋል። የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደራራ ከተማ በበኩላቸው ሎሬቱ የሀገራችንን አርት ለዓለም ያስተዋወቁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ቢሮው መሰል የጥበብ ሰዎችን ለማፍራት የሚያስቸሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው ይህንንም ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት አርቲስቶችም የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን አርአያነት በመውሰድ፣ የሀገራችንን ጥበብ አሁን ካለበት ለማሳደግ ተባብረው እንደሚሰሩም ገልጸዋል። አርቲስት አበበ ባልቻ እንደገለፀው፤ የሎሬቱ የጥበብ ሥራዎች በርካታ አርቲስቶችን በማፍራት በሀገራችን የጥበብ እድገት ውስጥ የማይረሳ አሻራ አኑረዋል። አርቲስቱ አክሎም በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስም የተሰየመውን የኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሌሎች አርቲስቶችን በማስተባበር በየዓመቱ በመምጣት አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብሏል። ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የኢትዮጵያን ጥበብ ከማሳደግ ባለፈ የአፍሪካ የጥበብ እድገት በዓለም መድረክ እንዲታይ ያደረገ መሆኑን የገለፀው ደግሞ አርቲስት ተፈሪ አለሙ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያን እንድንወድ ያደረገ ታላቅ አርቲስት ነው ሲልም ገልጿል።
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከአጋር አካላት ጋር የተቀናጀ ሥራ እየተከናወነ ነው
Feb 26, 2026 101
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከአጋር አካላት ጋር የተቀናጀ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በካንሰር ምርምር ላይ የሚያተኩረውን የelse korner center fore cancer care (EKC 2) ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍን በመጠናቀቅ ሁለተኛውን ምዕራፍ ይፋ አድርጓል፡፡ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን የሴቶችን የካንሰር ሕክምና አገልግሎት በየአካባቢው ተደራሽ ማድረግ፣ ስለ ጡት እና ማህፀን በር ካንሰር ግንዛቤን ማሳደግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን በዚሁ ወቅት፤ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከመከሰታቸው በፊት በቅድመ ጥንቃቄ መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በሰዎች ላይ የሚያስከትሉትን ማኅበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ለመግታት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል፡፡ መንግስት የበሽታዎቹን ስርጭት ለመግታት ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ባሻገር ሌሎች ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ጥንቃቄ ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የካንሰርና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርምር ክፍል አስተባባሪ ዶክተር አዳሙ አዲሴ በበኩላቸው፤ የካንሰር በሽታ በአፍሪካ ደረጃ አሳሳቢነቱ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመዋል። ይህንን ለመቅረፍ ኮሌጁ ችግር ፈቺ በሆኑ ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንና የኤልሳ ክሮነር የካንሰር ሕክምና ማዕከል ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ቢሳ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በተለይ በእናቶች ላይ የሚከሰቱ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ለመቀነስ ትልቅ ሚና አለው። ቀደም ሲል በተመረጡ ሆስፒታሎች ብቻ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት አሁን በፕሮጀክቱ አማካኝነት ወደ ጤና ጣቢያዎች ዝቅ እንዲል መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
በድሬደዋ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ተደራሽነትና አገልግሎቶች ይጠናከራሉ - ከንቲባ ከድር ጁሃር
Feb 26, 2026 107
ድሬደዋ፣ የካቲት 19/2018(ኢዜአ):- በድሬደዋ ለተገልጋዩ ፈጣንና ተደራሽ የፍርድ አገልግሎት በመስጠት ወሳኝ ሚና እያበረከቱ የሚገኙ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ይጠናከራሉ ሲሉ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ። በድሬደዋ አስተደዳር የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ምክርቤት የማቋቋምና ለባህላዊ ፍርድ ቤቶች ዕውቅና የመስጠት ስነስርአት ዛሬ በይፋ ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንዳሉት፤ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ጫና እያቃለሉ ናቸው። የፍትህ አገልግሎቱ እንዲሻሻል እያከናወኑ ያሉትን አበረታች ተግባራት ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚመሩበት የህግ ማዕቀፍ በአስተዳደሩ ምክርቤት ፀድቆ ወደ ስራ መገባቱንም አስታውሰዋል። በመሆኑም ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የምክርቤቱ መቋቋም ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል ። የድሬደዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ በበኩላቸው የባህላዊ ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት የአሰራር ስነስርአት ማህበረሰቡን ተደራሽ በማድረግ የፍትህ አገልግሎት እንዲያገኝና ማህበራዊ መስተጋብር እንዲጠናከር እያስቻሉ መሆኑን አንስተዋል። ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚለያቸውን ድንበርና አሰራር በመለየት የሚፈለገውን ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግላቸው በማስታወቅ። የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ባህላዊ ህጎችና እሴቶችን በመጠበቅና የማህበረሰቡን መስተጋብር በማጠናከር የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን የስራ ጫና እያቃለሉ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የድሬደዋ አስተዳደር የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት አቶ ነጂብ ኢድሪስ ናቸው። በተጨማሪም የሃብትና የጊዜ ብክነትን በመከላከል ምርታማነት ይበልጥ እንዲጎለብት አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የተሰጣቸው ዕውቅና በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ነው አቶ ነጂብ የተናገሩት። የኃይማኖት አባቶችና ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ኡጋዞች፣ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተመሰረተው የባህላዊ ፍርድ ቤት ምክርቤት አባላት መሆናቸውን በስነስርዓቱ ላይ ተመልክቷል።
ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል
Feb 27, 2026 15
ባህርዳር፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ። በክልሉ በተለይም በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ለኢዜአ ገልጸዋል። ወጣት መሳይ ታምራት በባህር ዳር ከተማ የዶሮ ጫጩት ማሳደግ እና ማከፈልፈል ስራ ላይ በማህበር ተደራጅቶ ወደ ሥራ ከገባ አንድ ዓመት ሆኖታል። በከተማ አስተዳደሩ በተደረገላቸው ሁለት ሼዶች ድጋፍ በአምስት ዙር የተረከቧቸውን የአንድ ቀን ጫጩቶች በማሳደግ ከ19 ሺህ በላይ ቄብ ዶሮዎችን ለአርቢዎች ማከፋፈላቸውን ገልጿል። ከአንድ አመት በፊት በ275 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል የጀመሩት ስራ አሁን ለይ በፍጥነት በማደጉ የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸወን አረጋግጧል። በቀጣይ ጠንክረው በመስራትና በመቆጠብ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ማሽን በመግዛት የእንቁላል ጣይና የሥጋ ዶሮዎችን በማስፈልፈል ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን አመልክቷል። ወጣት ዮሴፍ ፈቃዱ በበኩሉ ሰባት ሆነው በመደራጀት በተደረገላቸው የሼድና የአንድ ቀን ጫጩት ድጋፍ ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጿል። ከአንዳሳ የግብርናና የእንስሳት ምርምር ማእከል ተረክበው ያሳደጓቸውን ከሰባት ሺህ በላይ ቄብ ዶሮዎች በሰቆጣ፣ ጎንደርና ፍኖተሰላም አካባቢ ለሚገኙ አርቢዎች በማሰራጨት የተሻለ ገቢ ማግኘታቸውን ተናግሯል። አሁን ላይ አራት ሺህ የአንድ ቀን ጫጩቶችን ተረክበው በማሳደግ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው በቀጣይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በማርባት ተጠቃሚነታቸውን ለማስፋት እየሰሩ መሆኑን አብራርቷል። በአማራ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ የእንስሳት ባለሙያ ሙላቱ ዳኘው እንዳሉት የሌማት ትሩፋት በዶሮ ልማት፣ በወተትና አሳ ሀብት ልማት ዘርፉ ከፍተኛ ወጤት እያስመዘገበ ነው። በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊየን የአንድ ቀን ዶሮ ጫጩቶችን ለአሳዳጊዎች ለማሰራጨት ታቅዶ በተደረገ ጥረት እስካሁን ከሰባት ሚሊየን በላይ ጫጩቶችን ለሶስት ሺህ 439 አሳዳጊዎች ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል። በክልሉ ባለፉት 7 ወራት ከሰባት ሚሊየን በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶችን ለአሳዳጊዎች ማስረከብ መቻሉንም አመልክተዋል። የዶሮ እርባታ ዘርፍ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና ዘላቂ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰፈነው ሰላም የሕዝብ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ዕድል ፈጥሯል
Feb 27, 2026 49
ጊምቢ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰፈነው ሰላም የሕዝብ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። የዞኑ አመራሮች በዞኑ ውስጥ ግንባታቸው እየተከናወነ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል። በአመራሮቹ ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል በቤጊ ወረዳ ኮቦር ከተማ የሚገኘው የግብርና ልማት ማዕከል፣ የእንስሳት እርባታና የንብ ማነብ ማዕከላት እንዲሁም የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው። የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተሊላ ተረፋ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዓመታት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች የዞኑ ነዋሪዎች የሚያነሱትን የልማት ጥያቄዎች የመመለስ ከፍተኛ አቅም እንዳላቸውም ገልጸው በዞኑ የሰፈነው ሰላም ለልማት ስራዎች መፋጠን እገዛ አድርጓል ብለዋል። በተለይም በግብርና ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ ኢኒሼቲቮች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኅብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሸል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆኑንም ገልጸዋል። በቀጣይም በዞኑ የተመዘገቡ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ህዝቡን ያሳተፈ የሰላምና የልማት ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል። በዞኑ በግንባታ ላይ ከሚገኙ መሰረተ ልማቶች መካከል መንገድ፣ ድልድይ፣ የመስኖ አውታር፣ የትምህርትና የጤና ተቋማት እንደሚገኙበትና በተያዘው የበጀት ዓመት ለአገልግሎት ለማብቃት ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።
ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ የሆርቲካልቸር ምርቶች ከ288 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል
Feb 27, 2026 51
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ የሆርቲካልቸር ምርቶች ከ288 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። ግብርና ሚኒስቴር በሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት የ2018 በጀት ዓመት የሰባት ወራት የኤክስፖርት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው። በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ እንዳሉት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ሰባት ወራት ከሆርቲካልቸር ምርቶች የወጪ ንግድ ከ288 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ገቢው ወደ ተለያዩ ሀገራት ከተላኩ የአበባ እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና ጥራትን በማስጠበቅ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። የግብርና ልማትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ ዘመናዊ የእርሻ ልማት ስራዎችን የማስፋፋት ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ባለሀብቶች የሚገጥማቸውን ችግሮች በመቅረፍ የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በአማራ ክልል የሰላም አማራጭን የተቀበሉ የቀድሞ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ
Feb 26, 2026 94
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ የሰላም አማራጭ ተቀብለው የተመለሱ እና በተለያዩ የመንግሥት መዋቅር ስር ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞው የመንግሥት ሰራተኞች ወደ መንግሥት ስራቸው እንዲመለሱ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት ባካሔደው 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው የሰላም አማራጭን ተቀብለው በተመለሱና ቀደም ሲል በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች ሲያገለግሉ በነበሩ ሠራተኞች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። የክልሉ መንግሥት ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማረጋገጥ ባለው ጽኑ ቁርጠኝነት፣ ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ አካላት በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በመንግሥት ጥሪ፣ በድርድርና በውይይት የሰላም አማራጭን መርጠው የተመለሱና የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ምክር ቤቱ ወስኗል። ይህ ውሳኔ የክልሉ መንግሥት ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታትና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። በቀጣይም ለክልሉ ዕድገትና አንድነት መሰል የሰላም ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢንስቲትዩቱ የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና ተጓዳኝ ስራዎች እያከናወነ ነው
Feb 27, 2026 22
አዳማ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ቦጋለ ለኢዜአ እንደገለጹት የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት በዓሣ ዝርያ ማሻሻያ ላይ ኢንስቲትዩቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በተለይ እየተተገበረ ያለውን የዓሣ ልማት ኢንሼቲቭ ለማሳካት ምርቱን የሚጨምሩ ዝርያዎችን በስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በክልሉ የውሃ አካላት በሙሉ የዓሣ ምርት መያዝ አለባቸው የሚል ግብ ተቀምጦ በዝርያ ማሻሻያ ላይ የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል። ኢንስቲትዩቱ በምርምር ማዕከላቱ የዓሣ ጫጩት የማባዛት ስራ እየሰራ መሆኑንና የተባዙ የዓሣ ጫጩቶችን ለአርሶ አደሩ በነፃ እየተሰራጨ መሆኑንም አክለዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ1 ሚሊየን በላይ የዓሣ ጫጩቶች መሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል። በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 5 ሚሊየን የዓሣ ጫጩቶች ለማሰራጨት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የባቱ የዓሣ ምርምር ማዕከልን ጨምሮ በኢንስቲትዩቱ ስር በሚገኙ የምርምር ማዕከላት ብዛት ያላቸው የዓሣ ጫጩት ዝርያዎች መባዛታቸውን ጠቁመው የዓሣ ጫጩት ብዜት ስራው በቤተ ሙከራና በኩሬ እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል። ከዝርያ ማሻሻያ ስራዎች በተጓዳኝ ከዓሣ እርባታ ጋር በተያያዘ የእውቀትና የአሰራር ክህሎት ስልጠናና አቅም ግንባታም እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ በሀገር ደረጃ የተያዘውን በምግብ ራስን የመቻልና የስነ ምግብ ስርዓትን ለማስረፅ የዓሣ ሀብት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የጎላ ሚና አለው ብለዋል። በዚህም የህፃናት የአእምሮ እድገት እንዲጎለብት፣ የመቀንጨርና መቀጨጭ ችግሮችን ለመቅረፍ ዓሣ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የተቀናጁ የጠለፋ ጥቃቶችን በተመለከተ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት
Feb 27, 2026 62
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የዜጎችንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ ተደጋጋሚ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ለማህበረሰቡ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። በተለይ ከዋትስአፕና ከቴሌግራም አካዉንቶች ጠለፋ መስፋፋትን ተከትሎ በቅርቡም የጥንቃቄ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወቃል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም ሰባተኛውን ጠቅላላ የምርጫ ሂደትን ተገን በማድረግ፣ አጥፊዎች ስልታቸውን ይበልጥ በማወሳሰብ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኝ አስተዳደሩ በሚደርሱት መረጃዎችና የሳይበር ደህንነት ትንተናዎች ማረጋገጥ ችሏል። ይህ ጥቃት በተለይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በርቀት ሆነዉ በዲጂታል አማራጮች የሚማሩ ግለሰቦችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ፣ መላው የዋትስአፕ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ሊያውቃቸው የሚገቡ የጥቃት ስልቶችና የመከላከያ መንገዶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ የመረጃ መንታፊዎች የሚጠቀሙባቸዉ ዋና ዋና የጠለፋ ስልቶች 1. የምርጫ ሂደትን እና የፖለቲካ ኩነቶችን ለሴራ መጠቀም፦ አጥፊዎቹ የሀገራዊ የምርጫ ወቅት መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የዜጎችን የፖለቲካ ፍላጎትና ስሜት ለጥቃት መቹ አጋጣሚ አድርገዉ እየተጠቀሙ ይገኛል፦ የምርጫ ደጋፊ በመምሰል፦ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊ በመምሰልና የፓርቲዎችን አርማ (Logo) በመጠቀም "ለፓርቲያችን ድጋፍዎን እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ይግለጹ" ወይም "የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ" የሚሉ አሳሳች መልዕክቶችን ይልካሉ። የምርጫ መረጃ አቅራቢ በመምሰል፦ "የምርጫ ጣቢያዎትን ለማወቅ"፣ "የዕጩዎችን ዝርዝር ለማየት" ወይም "የምርጫ ውጤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት" የሚሉ አሳሳች ማስፈንጠሪያዎችን (Links) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የዋትስአፕ አካውንት በቁጥጥራቸው ስር ያውላሉ። 2. ተከታታይ ጠለፋ እና የማንነት ስርቆት: ይህ ስልት እጅግ አደገኛ የሆነው ጥቃቱ የሚመጣው ከሚታወቅና ከቅርብ ሰው በመሆኑ ነው። የአንድ ግለሰብ አካውንት አንዴ ከተጠለፈ በኋላ አጥፊዎቹ የሚከተሉትን ድርጊቶች ይፈጽማሉ፦ የገንዘብ ማጭበርበር፦ የተጠለፈውን ሰው ማንነት በመጠቀም በስልክ አድራሻ ዝርዝሩ ውስጥ ላሉ ወዳጆች "ድንገተኛ የጤና ችግር አጋጥሞኝ ነው" ወይም "ከምርጫ ስራ ጋር በተያያዘ ገንዘብ በአስቸኳይ አስፈልጎኝ ነው" በማለት የባንክ አካውንት በመላክ ከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ይፈጽማሉ። ተጨማሪ ጠለፋ፦ ለሌሎች የሥራ ባልደረቦችና ኃላፊዎች አሳሳች ሊንኮችን በመላክ የጥቃቱን ሰለባ ያስፋፋሉ። በዚህም ወሳኝ የሆኑ የመንግስት እና የተቋማዊ መረጃዎችን የመስረቅና የማጥፋት ስጋት ይፈጥራሉ። 3. ተማሪዎችን እና የከፍተኛ ትምህርት ተከታታዮችን ኢላማ ማድረግ፦ በውጭ ሀገር የሚማሩ ወይም በኢንተርኔት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ዜጎችን ኢላማ በማድረግ፤ ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ የተላከ በማስመስል (ለቪዛ እድሳት፣ ለትምህርት ክፍያ ቅናሽ ወይም ለፈተና መረጃ በሚል ሰበብ) ሊንኮችን ይልካሉ። ተማሪዎቹ መረጃቸውን ሲያስገቡ የግል መረጃቸውና የዋትስአፕ አካውንታቸው ወዲያውኑ ይረበሻል። 4. የባለ 6-አሃዝ ኮድ ማጭበርበር: አጥፊዎች የእርስዎን ስልክ ቁጥር በመጠቀም በሌላ ስልክ ዋትስአፕ ለመክፈት ይሞክሩና ወደ እርስዎ ስልክ በቴክስት (SMS) የሚመጣውን ባለ 6-አሃዝ ኮድ፤ "በስህተት ወደ አንተ የተላከ ኮድ ስለሆነ እባክህ መልሰህ ላክልኝ" በማለት ይጠይቃሉ። ይህንን ኮድ አሳልፈው ከሰጡ አካውንትዎ ወዲያውኑ ይጠለፋል። ራስን እና ተቋምን ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች 1. ባለሁለት-ደረጃ ማረጋገጫን ያብሩ፦ ይህ አካውንትዎን ከጠለፋ ለመጠበቅ ቁልፍ መከላከያ ነው። እንዴት ይበራል? WhatsApp Settings > Account > Two-step verification > Turn On በመግባት የራስዎን ሚስጥራዊ ባለ 6-አሃዝ ቁጥር (PIN) እና የኢሜይል አድራሻ ያስገቡ። 2. የማረጋገጫ ኮድን በምንም ምክንያት አያጋሩ፦ ወደ ስልክዎ በሜሴጅ የሚላክን የዋትስአፕ ማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለምንም አይነት አካል (ለጓደኛም ሆነ ለቤተሰብ) አሳልፈው አይስጡ። 3. አጠራጣሪ ሊንኮችን (Links) አይጫኑ፦ በተለይ ከምርጫና ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከማይታወቅም ሆነ ከሚታወቅ ሰው የሚላኩልዎትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመጫንዎ በፊት ትክክለኛነቱን በሌላ የመገናኛ ዘዴ ያረጋግጡ። 4. የገንዘብ ጥያቄን በመደበኛ ስልክ ያረጋግጡ፦ ማንኛውም ሰው በዋትስአፕ በኩል የገንዘብ እርዳታ ሲጠይቅዎት፣ አካውንቱ ተጠልፎ ሊሆን ስለሚችል ገንዘብ ከመላክዎ በፊት በመደበኛ ስልክ በመደወል ድምፁን ሰምተው ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ። 5. የመረጃ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ወሳኝ የሆኑ ሀገራዊ እና ተቋማዊ መረጃዎችን በዋትስአፕ ከመለዋወጥ መቆጠብ አለባቸው። ለሥራ ጉዳይ ደህንነታቸው የተረጋገጡ (Secure) የውስጥ መገናኛ ዘዴዎችን መጠቀም ይመከራል። አካውንትዎ ከተጠለፈ ምን ማድረግ አለብዎት? ወዲያውኑ ድጋሚ ለመመዝገብ ይሞክሩ፦ የዋትስአፕ መተግበሪያዎን አጥፍተው (Uninstall) እንደገና በመጫን ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡ። በSMS የሚላክልዎትን ኮድ ሲያስገቡ አጥፊው ከእርስዎ አካውንት በራስ-ሰር እንዲወጣ (Log out) ይደረጋል። ለወዳጅ ዘመዶችዎ መልዕክት ያስተላልፉ፦ አካውንትዎ ተጠልፎ እንደነበር በመደበኛ ስልክ ወይም በሌሎች አማራጮች በማሳወቅ፣ ከእርስዎ ስም ለሚመጣ ማንኛውም የገንዘብም ሆነ የሊንክ ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጡ ያስጠነቅቁ። ሪፖርት ያድርጉ፦ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊ ከሆኑ ወይም ጥቃቱ ተቋማዊ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ ጉዳዩን ወዲያውኑ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሪፖርት ያድርጉ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገሪቱን የሳይበር ምህዳር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ለሳይበር ሌቦች በር እንዳይከፍት ያሳስባል። ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የካቲት 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቶቹን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ አድርጓል
Feb 26, 2026 133
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ሥርዓት ለማቀላጠፍና ቁጥጥሩን ለማዘመን አገልግሎቶቹን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማድረጉን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በርካታ ውጤታማ የዲጂታላይዜሽን ተግባራትን አከናውናለች። ይህንንም አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችለው ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ዲጂታል ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ነው በዲጂታል 2025 በርካታ ተቋማት አገልግሎታቸውን ያዘመኑ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዲጂታል የተደገፈ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የጉምሩክ ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ ዲጂታል 2025 ተከትሎ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ አተኩሮ በርካታ ውጤታማ ተግባራት በማከናወን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ተችሏል፡፡፡ በአሁኑ ወቅት ነጋዴዎች በማንኛውም ቦታ ሆነው የጉምሩክ ሥርዓትን መፈጸም የሚችሉበት የተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት መዘርጋት መቻሉን አስታውቀዋል። ከ70 በላይ ተቋማትን በአንድ ላይ የሚያገናኘው የኤሌክትሮኒክ ሲንግል ዊንዶው ፕላትፎርም ተግባራዊ መድረጉን አንስተው፤ ይህም የንግድ ስራን ለማቀላጠፍ ትልቅ እመርታ መሆኑን ተናግረዋል። የኮሚሽኑን የክትትል አቅም ለማሳደግ ስማርት ቦርደር ማኔጅመንት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ሲሉም አንስተዋል፡፡ የኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ሲስተምን በመጠቀም ጭነቶች ካለባቸው መስመር እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ካሜራዎች በተለያዩ ስልታዊ ቦታዎች ላይ ተተክለው ውጤታማ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ኮሚሽኑ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከባንኮችና ከሌሎች ፈቃጅና ተቆጣጣሪ ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂ ትስስር መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የታክስ ሥርዓትም የኢ-ፋይሊንግ እና የኢ-ፔይመንት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ ውለዋል ብለዋል። እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ በአሁኑ ወቅት በጂቡቲ የሚገኙ ሁለት ቅርንጫፎችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ያሉ 15 ቅርንጫፎች በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የ24 ሰዓት አገልግሎት በቴክኖሎጂ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ይህ መጠነ ሰፊ የዲጂታላይዜሽን ስራ የገቢና ወጪ ንግዱን ከማሳለጡ ባለፈ፣ የህግ ማስከበር ስራውን በቴክኖሎጂ የታገዘና ግልጽ አሰራረን ተግባራዊ በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ አስታውቀዋል።
እያደገ የመጣው የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል
Feb 26, 2026 59
ደብረ ማርቆስ ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን እያደገ የመጣው የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት የዜጎች ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱ ተገለጸ። የገጠር መሬትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ-አደሮች፤ አማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀማቸው የደን ጭፍጨፋን መቀነስ፣ ጤናቸውን መጠበቅና ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። የጎዛምን ወረዳ ደሳ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ጌታቸው አንሙት፣ የባዮጋዝ ቴክኖሎጂን በመገንባት ለምግብ ማብሰያና ለመብራት አገልግሎት መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል። ይህም ቀደም ሲል ለማገዶና ለናፍጣ ሳወጣ የነበረውን ወጪ ቆጥቦልኛል ብለዋል። አማራጭ የኢነርጂ ቴክኖሎጂው የእርሳቸውንና ቤተሰባቸውን ጤና እንዲጠብቁ ከማድረግ ባለፈ ማገዶ ፍለጋ ጫካ በመሄድ ይደረስባቸው የነበረውን እንግልት መቀነሱን ገልጸዋል። አርሶ አደር ጌታሁነኝ ብርሃን በበኩላቸው፣ ከባዮጋዝ የሚገኘውን ተረፈ ምርት እንደ ማዳበሪያ በመጠቀማቸው የአትክልትና ሰብል ምርታማነታቸው መጨመሩን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂውን ለተለያዩ አገለግሎቶች እያዋሉት መሆኑንና በዚህም በኑሯቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን አንስተዋል። የእነደድ ወረዳ ነዋሪ ዘውዲቱ ጥላሁን፣ ዘመናዊና ሀይል ቆጣቢ ምድጃዎችን መጠቀም መጀመራቸው ከዚህ ቀደም በእሳት ነበልባልና በጭስ ምክንያት ይደርስባቸው ከነበረው የጤና መታወክ እንደታደጋቸው ገልጸዋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ሃላፊ ፍሬው ካሴ እንደገለጹት፤ በዞኑ አማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማስፋት የአርሶአደሩን ኑሮ ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው። በ2018 በጀት ዓመት ከ44ሺህ በላይ የተለያዩ የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰው፣አሁን ላይ ከ34 ሺ በላይ ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ከአማራጭ የሃይል ቴክኖሎጂዎች ውስጥ 21 ሺህ 243ቱ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች፣ 13 ሺህ 451ዱ በጸሃይ ሃይል የሚሰሩና 261ዱ የባዮጋዝ ቴክኖሎጂ ግንባታ ይገኙበታል ብለዋል። በቴክኖሎጂዎቹ ከ140 ሺ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና በዚህም የደን ጭፍጨፋን መከላከልና የሕብረተሰቡን ጤና መጠበቅ እንደተቻለ አመልክተዋል። በዞኑ እስካሁን አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የተለያዩ የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆናቸውን የመምሪያው መረጃ ያመለክታል።
ስፖርት
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
Feb 27, 2026 130
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በዎልቭስ እና አስቶንቪላ መካከል ይካሄዳል። ጨዋታው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በሞልኒው ስታዲየም ይደረጋል። ዎልቭስ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። አስቶንቪላ በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ22ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 21 ጨዋታዎች ዎልቭስ ሰባት ጊዜ ሲያሸንፍ አስቶንቪላ በስምንቱ አሸንፏል። በስድስቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ ላይ ዎልቭስ 33 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ አስቶንቪላ 41 ጎሎችን አስቆጥሯል። ክለቦቹ ዘንድሮ በሊጉ የመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ አስቶንቪላ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ዎልቭስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። አስቶንቪላ ካሸነፈ በሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያገኛል። የ46 ዓመቱ ክሬግ ፖውሰን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታል
Feb 27, 2026 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሲዳማ ቡና በሊጉ 14 ጨዋታዎችን አድርጎ በአምስቱ ሲያሸንፍ ስድስት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። በ14 ጨዋታዎች ላይ 14 ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ግቦችን አስተናግዷል። ቡድኑ በ18 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ እስከአሁን ባደረጋቸው 14 ጨዋታዎች በ11ዱ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በሁለት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 37 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ አምስት ጎሎችን አስተናግዷል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ቡድኖች ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዘገብ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋል። በሌላኛው መርሐ-ግብር መቻል ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። መቻል 14 ጨዋታዎችን አከናውኖ በዘጠኙ ድል ሲቀናው ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 23 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ግቦች ተቆጥረውበታል። መቻል በ30 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች መካከል ስምንቱን ያሸነፈው ሃዋሳ ከተማ በበኩሉ በሁለቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ አራት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 23 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 10 ግቦችን አስተናግዷል። ሃዋሳ ከተማ በ28 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ቡድኖች ከ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የአቻ ውጤት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ። ሸገር ከተማ ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ። ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ
Feb 27, 2026 62
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ፋሲል ከነማ በሊጉ 20 ጨዋታዎች አድርጎ ስምንት ጊዜ ድል ሲቀናው በሶስቱ ተሸንፏል። በዘጠኝ ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 15 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 11 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ ካከናወናቸው 20 ጨዋታዎች መካከል ሶስቱን ብቻ ያሸነፈው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስምንቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ዘጠኝ ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል። በ20 ጨዋታዎች 13 ግቦችን ሲያስቆጥር 22 ጎሎችን አስተናግዷል። ወልዋሎ በ18 ነጥብ 19ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፉም። ቡድኖቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር በሁለተኛ ሳምንት ተገናኝተው ፋሲል ከነማ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በሌላኛው መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሀዲያ ሆሳዕና በ24 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። በ20ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና በባህርዳር ከተማ 1 ለ 0 ተሸንፏል። ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይጫወታሉ። ምድረ ገነት ሽሬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ምድረ ገነት ሽሬ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ24 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል የራቀው ምድረ ገነት ሽሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ባህርዳር ከተማ በ27 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። አርባምንጭ ከተማ በ13 ነጥብ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባህር ዳር ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል።
ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ
Feb 26, 2026 87
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራምኬል ጀምስ በ87ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ26 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 5ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ነገሌ አርሲ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ-ግብር መቻል እና መቀሌ 70 እንደርታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። መቀሌ 70 እንደርታ በ22 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። መቻል በ31 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 ሲረታ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የመሬት እንቅስቃሴ አደጋዎችን ለመቀነስ የመከታተያ ማዕከላት ማስፋፋት ያስፈልጋል - የዘርፉ ምሁራን
Feb 26, 2026 101
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ የመሬትመንቀጥቀጥና የእሳተ ገሞራ አደጋዎችን ለመቀነስ የመከታተያ ማዕከላት ማስፋትና የህዝብን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የመሬት መንቀጥቀጥና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አደጋ በኢትዮጵያ ስጋትና መፍትሔዎች" በሚል መሪ ሃሳብ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው። በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በተሰናዳው መድረክ የታደሙት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሀንስ፤ ምሁራን በሀገራቸው ጉዳይ ያላቸውን ሚና ማላቅ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም በተለያዩ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ለሕትመትና ተደራሽነት እንዲበቁ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚኖራቸውን መፍትሔ አመላካች የጥናትና ምርምር ሥራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የጂኦ-ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ፤ የመሬት እንቅስቃሴ በተፈጥሮ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ብለዋል። በመሬትና በብዝኅ ህይወት ላይ የሚፈጥረው የገጽታ ለውጥም በህዝብ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ አኗኗር ሥርዓት ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሚከሰቱ የመሬት እንቅስቃሴዎችንም በመከታተል በተለያዩ ጊዜያት ህዝቡን የማስገንዘብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት መንቀጥቀጥና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አደጋዎችን አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም የማዕከላትን መረጃ ማጠናቀር አቅም ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። የምህንድስና የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት የጂኦቴክኒክ ኢንጅነሪንግ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አስራት ወርቁ በበኩላቸው፤ የመሬት እንቅስቃሴ አደጋዎችን ለመቀነስ የግንባታ ጥራትን ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል። የህንፃና ተያያዥ መሰረተ ልማት ገንቢ ተቋማትና መሃንዲሶችም ከመሬት ሳይንስ ተመራማሪዎች ጋር በመቀናጀት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ማህበራዊ ገጽታን አስመልክቶ ጽሁፍ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ተገኝ ገብረእግዚአብሔር፤ የስምጥ ሸለቆ የከተሜነት መስፋፋት ለመሬት እንቅስቃሴ አደጋ ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል ብለዋል። ለዚህም የሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር የቅድመ ማስጠንቀቂያና የመሠረተ ልማት ጥራትን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
ለብሔራዊ ፓርኮችና ጥብቅ ሥፍራዎች ልማት የተሰጠው ትኩረት ከቱሪዝም ዘርፉ የበለጠ ለመጠቀም ያስችላል
Feb 26, 2026 172
ባህር ዳር ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡-ለብሔራዊ ፓርኮችና ጥብቅ ሥፍራዎች ልማት የተሰጠው ትኩረት ከቱሪዝም ዘርፉ የበለጠ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ በሀገሪቱ 29 ብሔራዊ ፓርኮችና 87 ዓይነት ጥብቅ ስፍራዎች ይገኛሉ ብለዋል። የጥብቅ ስፍራዎችን ማስፋፋት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ ጨበራ ጩርጩራ፣ አዋሽ እና ባሌ ብሔራዊ ፓርኮች ያሉ ሥፍራዎች ላይ የተሰሩ የልማት ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንም እንዲሁ። በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የሚታየውን ልዩ የዱር እንስሳት እንቅስቃሴ ለቱሪዝም መስህብነት ለማዋል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ነው ያብራሩት። በፓርኮች ውስጥ የሚስተዋሉትን ልቅ የእንስሳት ግጦሽ፣ የደን ጭፍጨፋ፣ ሕገ-ወጥ አደንና የእርሻ መስፋፋት ችግሮችን ለማስወገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ብለዋል። መንግስት የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት ረገድ የሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፉ በፍጥነት እያደገ እንዲመጣ ማስቻሉንም ገለጸዋል። የአማራ ክልል አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው፤ በክልሉ የእንሰሳትና የብዝሃ ሕይወት የመጠበቅ ስራ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚስተዋሉ ሰደድ እሳት፣ ህገወጥ እርሻ፣ ደን ጭፍጨፋ፣ ሕገ-ወጥ አደንና መሰል ተግባራትን ሕብረተሰቡን በማስተባበር የመጠበቅ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ፓርኩ ለአካባቢው ማሕብረሰብ ያለውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት ቀደም ሲል 136 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የነበረውን የፓርኩ ይዞታ ወደ 412 ስኩዌር ኪሎ ሜትር እንዲሰፋ መደረጉን አስታውሰዋል። ፓርኩን የማስፋት ስራ በዩኔስኮ መመዝገብ ስላለበት ይህንኑ ተግባር እውን ለማድረግ በጥናት ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ተዘጋጅቶ መቅረቡን ተናግረዋል። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማማው ዘገየ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ በምርምርና በማሕበረሰብ አገልግሎት ፓርኩን እያገዘ ነው። የቱሪዝምና ቅርስ አስተዳደር የትምህርት ክፍል በመክፈት ተማሪዎች በተግባር የታገዘ ትምህርት እንዲወስዱ ከማድረግ ባሻገር ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሃብቱን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀደም ሲል የተካሄደው የይዞታ ማስፋት ስራ የአካባቢውን ማሕበረሰብ የበለጠ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደረገ ነው ያሉት ደግሞ የፓርኩ የሕግ ማስከበር ቡድን መሪ ሲሳይ ሰለሞን ናቸው። በማስፋት ስራውም ቀደም ሲል ያልተካተቱ ሥፍራዎች መካተታቸውን ጠቅሰው፤ ለዩኔስኮ የቀረበው ሰነድ ሲፀድቅ የፓርኩን ዓለም አቀፍ እውቅና ያሳድጋል ብለዋል።
በሀዋሳ በፕላስቲክ ከረጢት ምትክ አማራጭ ምርቶችን የመጠቀም ልምድ እየዳበረ ነው
Feb 26, 2026 214
ሀዋሳ ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- በሀዋሳ ከተማ በፕላስቲክ ከረጢት ምትክ አማራጭ ምርቶችን የመጠቀም ልምድ እየዳበረ መምጣቱን የከተማ አስተዳደሩ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሠረት እንደ ሀገር ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት፣ ወደ ሀገር ማስገባት፣ መሸጥና መጠቀም ላይ ክልከላ ተደርጓል፡፡ አዲስ አበባ በንፅህና አጠባበቅ ረገድ እያከናወነች ያለው ሥራ በአርዓያነት ይጠቀሳል ባልተገባ መልኩ የሚጣሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች /ፌስታል/ አካባቢን በመበከል፣ የውሃ መስመሮችን በመዝጋት፣ በተለይ ሳይበሰብሱ ለብዙ ዓመታት በመቆየት የስነ ምህዳር ጠንቅ እንደሆኑ ሳይንሳዊ ምርምሮች ያወሳሉ። በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት አጠቃቀምን ለመገደብና ለመከልከል ባለፉት ዓመታት በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን ክልከላው በዋናነት የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና የህዝብን ጤና ለመጠበቅ ያለመ መሆኑም ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ በሀዋሳ ከተማም ክልከላው ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በህብረተሰቡ ዘንድ በፕላስቲክ ከረጢት ምትክ አማራጭ ምርቶች የመጠቀም ልምድ እየዳበረ መምጣቱን የጽህፈቱ ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሹምባሻ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ ጽህፈት ቤቱም ክልከላውን ከማስተግበር ጎን ለጎን ምትክ ምርቶች በስፋት ለሕብረተሰቡ እንዲቀርቡ እየሰራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ 15 ድርጅቶች ምትክ የወረቀት ከረጢቶችን በማምረት ሥራ ላይ በመሰማራታቸው አዋጁን ከመተግበር ባለፈ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል ብለዋል። የኤሊያና ፔፐር ፓኬጂንግ ኤንድ ማኑፋክቸሪንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ሞገስ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው የወረቀት ከረጢቶችን በስፋት የማምረት ስራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ አዋጁ ስነ ምሕዳሩን ከመጠበቅ ባለፈ በዘርፉ ተጨማሪ የገበያ ዕድል በማስገኘት ሰፊ አስተዋጽኦ አበርክቷል ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅትም 85 ወጣቶችን በማሰልጠን የስራ እድል ለመፍጠር የተቻለ ሲሆን በቀን እስከ 15 ሺህ የወረቀት ከረጢቶችን እያመረቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሱፐር ማርኬት ሥራ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ ፀሐይ ይርዳው በበኩላቸው፤ የጨርቅ ከረጢቶችና ካርቶኖችን በመጠቀም ደንበኞቻቸውን እያስተናገዱ እንደሚገኙ ይገልፃሉ። ከዚሁ በተጨማሪም ማህበረሰቡ አምኖበት የወረቅ ምርቶቹን እንዲጠቀም ለማድረግም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰሩ መሆኑን ነው ያነሱት። በሆቴል ሥራ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ ልደት ማሩፋ፤ የፕላስቲክ ከረጢት ክልከላው ሀዋሳን ፅዱ ከማድረግ ባለፈ ሀይቁን ከብክለት ሥጋት ነፃ የሚያደርግ በመሆኑ በደስታ እንደተቀበሉት ገልፀዋል፡፡ ለቤታቸው በሚሸምቱት ዕቃም ሆነ በሆቴል አገልግሎታቸው አማራጭ ምርቶችን ብቻ እየተጠቀሙ መሆኑን ተናግረው የክልከላ አዋጁ ተግባራዊ እንዲሆንና ፅዱ ከተማን ለመፍጠር ሁሉም መተባበር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በታዳሽ ኃይል ለዓለም የስኬት አርዓያ ሆናለች -የሮማኒያ አምባሳደር
Feb 25, 2026 119
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በታዳሽ ኃይል ለዓለም የስኬት አርዓያ ሆናለች ሲሉ በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር ጁሊያ ፓታኪ ገለጹ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጣናውን በሀይል በማስተሳሰር ረገድም ጉልህ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት ባለፉት ዓመታት በተገበረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ችላለች። ይህ ተግባርም የዓለም የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል የተስተካከለ ምህዳርን ለመፍጠር ጉልህ ሚና አለው። ኢትዮጵያ በዚህ ተግባሯም ዓለም አቀፍ እውቅናዎችን አግኝታለች። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር ጁሊያ ፓታኪ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ልማት ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ስኬቶች ሀገሪቷን በዓለም ላይ እውቅና እያስገኘላት መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ድንቅ የአካባቢ ጥበቃ ስራ መሆኑን ጠቁመዋል፤የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መረጃዎችን እያስፋፋን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ ስኬቶች ሀገሪቷን በአረንጓዴ ልማት፣ በታዳሽ ሀይል ስራዎች ለሌሎች ሀገራት አርዓያ አድርጓታል ብለዋል። አምባሳደሯ አክለውም ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና ላይ መሆኗን ጠቁመው፤ በአዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተመዘገቡ ያሉ የልማት ውጤቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ የልማት እንቅስቃሳም በሌሎች የክልል ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑን ጠቁመዋል። የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አዲስ አበባን እውነተኛ የአፍሪካ መዲናነቷን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው በአፍሪካ ልዩ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል። ግድቡ ቀጣናውን በሀይል በማስተሳሰር ረገድም ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢጋድ እና ተመድ ትብብር ለቀጣናዊ ሰላም
Feb 26, 2026 80
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን የጋራ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የኢጋድ የደቡብ ሱዳን ልዩ ልዑክ አምባሳደር ሙሳ ጃማ አሊ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጉዋንግ ኮንግ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። ልዩ ልዑኮቹ በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት በተለይም በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት የአምስት አባል ሀገራት ኮሚቴ (AU C5) እና ኢጋድ ያደረጉት የጋራ ጉባኤ የተገኙ ውጤቶች ላይም መክረዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ መረጋጋት እና ቀጣናዊ ትብብር እውን እንዲሆን ያላቸውን ቅንጅት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢጋድ እና ሩሲያ በትብብር መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
Feb 24, 2026 165
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ሩሲያ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ አጋርነት ዳይሬክተር ታትያና ዶቭጋሌንኮ ጋር በተቋሙ መቀመጫ ጅቡቲ ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ኢጋድ እና ሩሲያ በፖሊሲና ደኅንነት፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን፣ ሳይንስ እና ትምህርት ዘርፎች ትብብር ማጎልበት የሚያስችላቸውን ስምምነት እና የድርጊት መርሐ-ግብር ተፈራርመዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ተቀራርበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ህብረት እና ሳዑዲ አረቢያ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ
Feb 23, 2026 118
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ሳዑዲ አረቢያ በሰላም፣ ልማት እና ዲፕሎማሲ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ ቢን አብዱልከሪም ኤል- ከሀርጂ(ኢ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ አፍሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ለረጅም ጊዜ የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው ትብብሩ በጥልቅ የባህል፣ የኢኮኖሚና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ላይ የተመሰረተ መሆኑን አውስተዋል። ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ ያላትን ዘላቂ ትብብር እና በአህጉሪቱ እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት አልፎም በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ያላትን ገንቢ ሚና አድንቀዋል። ሳዑዲ አረቢያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመቀናጀት በሊቢያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች እያሳየች ያለውን የዲፕሎማሲ ድጋፍ እና ተሳትፎ አዎንታዊ መሆኑን አመልክተዋል። የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ ቢን አብዱልከሪም ኤል- ከሀርጂ በበኩላቸው የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ በልማት፣ በሰላም እና በባለብዙ ወገን ትብብር ያለውን የመሪነት ሚና አንስተዋል። ሳዑዲ አረቢያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ልማት፣ ሰላም፣ ደህንነት እና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች የአፍሪካ ህብረትና ሳዑዲ አረቢያ ያላቸውን ግንኙነት በጋራ መከባበር መንፈስ፣ በወዳጅነት እና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ በመመስረት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ ፍላጎት ማሳየታቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የፈጠረውን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው
Feb 21, 2026 178
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን የንግድ ትስስር ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለ አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የስምምነቱ ትግበራ የንግድ መሰናክሎችን በማስቀረት የሀገራትን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነው። እስካሁን 50 ሀገራት ፈርመው ያጸደቁት ይህ የንግድ ቀጣና፤ በዲጂታል የኢኮኖሚ ዕድገት የፋይናንስ ቴክኖሎጂን በማስፋት የአኅጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በማዘመንና የገንዘብ ዝውውርን በማቀላጠፍ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ተዳራሽ ለማድረግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዘርግቷል የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲሱ ገጽታ፤ ከአማራጭ ማጣት ወደ መዳረሻዎች ብዛት በኢትዮጵያ ለግል ዘርፉ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ኢኮኖሚው እየተነቃቃ ነው የአፍሪካን የተፈጥሮ ሃብትም በተሻለ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነት በማልማት የመሰረተ ልማት፣ የዋጋ ግሽበትና የንግድ መሰናክሎችን ለመቀነስ አይነተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል። በዚህም አባል ሀገራት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን በማፋጠን የእርስበርስ የንግድ ልውውጥን ማሳለጥ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን ዕድል ለመጠቀም የግሉ ዘርፍና የአባል ሀገራት መንግሥታት የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረትም የአባል ሀገራት ኢንቨስትመንትን የሚያነቃቃ የኢንቨስትመንት ጥበቃ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድተዋል። የስምምነቱ የኢንቨስትመንት ጥበቃም የአፍሪካን በመተማመን ላይ የተመሰረተ የእርስበርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።
ሐተታዎች
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 159
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 189
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 634
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 971
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 178
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር
Feb 24, 2026 289
(በአየለ ያረጋል) ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፤ ኢትዮጵያና እስራኤል። የሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረው ግንኙነት አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች የተጠናከረ ሆኖ ይገኛል። የሀገራቱ ግንኙነት ግን እንደየስርዓተ መንግስታቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባህሪ መልኩን እየለዋወጠ እና ውጣ ውረዶችን እያለፈ የተሻገረና ጠንካራ መሆኑም ይታወቃል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪካዊ ገጽታ፦ ሃገራቱ የግንኙነታቸው ትርክት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በንግሥተ ሳባ እና በንጉሥ ሰለሞን ዘመነ መንግስት እንደሆነ አፈ ታሪክ ያስረዳል። ይህ አፈ-ታሪካዊ እርሾ ከኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ጋርም ቀጥሏል። በመካከለኛው እና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ሃይማኖትና ንግድ ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አስተሳስሯል። በተለይም ዴር ሱልጣንን ጨምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት መኖር የሁለቱን ሀገራት ባህላዊ ተጋምዶሽ አጎልብቷል። ይህ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ከእስራኤል ሀገረ መንግስት ዳግም መመስረት በኋላም በዘመናዊት ኢትዮጰያ ታሪክም ቀጥሏል። የኢትዮ እስራኤል ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፦ የዘመናዊ የኢትዮ-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተወጠነው በአውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ1956 ሲሆን በ1961 ይፋዊ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል። በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግስት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ ጥቅምን ያማከለና የወቅቱን የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አድርጓል። በንጉሳዊ ስርዓተ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ሌሎች የልማት ቴክኒካል ድጋፍ የደረሰ ወዳጅነት ነበራቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በእስራኤለና አረቦች ጦርነት ሳቢያ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል። ያም ሆኖ በግልጽም ሆነ የህቡዕ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ይወሳል። መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በደርግ መንግስት መጨረሻ ዓመታት (በአውሮፓውያኑ 1989) የኢትዮ-እስራኤል ይፋዊ ግንኙነት ዳግም ተጀምሯል። የ"ኦፕሬሽን ሙሴ" (1984) እና "ኦፕሬሽን ሰለሞን" (1991) የተሰኙ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የማጓጓዝ ተልዕኮዎችም በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ስምምነት የተካሄዱ መሆናቸውን ልብ ይሏል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም) ጀምሮ ደግሞ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጥሏል። በፈረንጆቹ 1992 ኢትዮጵያ በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፍታለች። በፈረንጆቹ 2003 ኢትዮጵያና እስራኤል የኢንቨስትመቶች ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1996 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2004) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አሪኤል ሻሮን ጋር ያደረጉት ታሪካዊ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሳድጎታል። ጉብኝቱን ተከትሎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ያጠናከሩ የተለያዩ ስምምነቶች ተደርገዋል። በተለይም በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከፍ ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትና ፀረ ሽብር ጉዳዮች እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥና የድንበር ጥበቃ ቴክኖሎጂ በትብብር ለመስራት መሰረት ጥለዋል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአዲስ አበባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም መክረዋል። በተመሳሳይ በፈረንጆቹ በ2017 የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ጎብኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በየራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ቆመዋል። በዓለም አቀፍ መድረኮች አንዳቸው ለሌላው ድምጽ በመስጠት ተደጋግፈዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ለብሔረታዊ ጥቅሞቿ መጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እስራኤል አሉታዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይልቁንም እስራኤል ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ እንደ መግቢያ ሁነኛ በር አድርጋ ትቆጥራለች። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮ-አስራኤል ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴካዊ አጋርነት አድጓል። በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በእስራኤል ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ደግሞ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ እንዲታደስ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ታሪካዊ የተሰኘውን ምክክር አድረገዋል። መሪዎቹ በሰጡት ገለጻም በአምስት ነጥቦች ላይ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በውሃ፣ በመስኖ፣ በጤና እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ መፈራረማቸውን አውስተው ነበር። በግብርና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምተው እንደነበርም እንዲሁ። ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ፦ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ልማት በመለወጥ የንግድና ኢንቨስመንት ግንኙነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አከናውነዋል። የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እየጎለበተ መጥቷል። ለአብነትም የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል። በማዕድን ዘርፍ (በፖታሽ)፣ በማምረቻ ዘርፍ( በጨርቃጨርቅ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች) እንዲሁም በጤናና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ ነው። በተለይም በግሪን ሃውስ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በፋርማሲዩቲካል (የመድኃኒት) ዘርፎች ሁነኛ ተሳትፎ አድርገዋል። በተመሳሳይ በንግድ ልውውጥ ረገድ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ እስራኤል በስፋት ትልካለች። በአንጻሩ እስራኤል የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የግብርና ግብዓቶችን (ማዳበሪያና ኬሚካሎች)፣ የሕክምና መሣሪያዎችን እና የደህንነት ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረቅ አካባቢ ግብርና ስመጥር የሆነችው እስራኤል በዘርፉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት አጋር ስትሆን በዘመናዊ መስኖ፣ የአቮካዶና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት እርባታ እና የወተት ምርታማነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች በጎ ተሳትፎ ታደርጋለች። በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወዳጅነት መጠናከር ቤተ-እስራኤላውያን እንደ ድልድይ አገልግለዋል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ160 ሺህ በላይ መሰረታቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላዊያን ዜጎች አሉ። እነዚህ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ሁነኛ ድልድይ ሆነዋል። በተለይም በእስራኤል የሰለጠኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በማስቻል በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በንግድ ስራ ረገድ ውጤታማ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ፈጥጠሯል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸውን ከፍ አድርጎታል። የፕሬዝዳንት ሔርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሃገራት የጸና ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጎለብት እንደሚሆን ይጠበቃል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ የሚያጠናክሩበት ምቹ ሁኔታም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1044
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 1008
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3521
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2343
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8136
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6620
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት
Feb 26, 2026 192
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያደርሰዋል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት አዘርባጃን እ.አ.አ በ1991 ነጻነቷን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። የሀገራቱ ግንኙነት ከእ.አ.አ 1990ዎች መግቢያ አንስቶ እያደገ መጥቷል። አዘርባጃን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ኤምባሲ የከፈተች ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር እንዲጠናከር በር ከፍቷል። በቱርክዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስራ የሚሸፍን ሲሆን ፖለቲካ፣ ትምህርት እና ባህል ሀገራቱ ካላቸው የትብብር መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል በባለብዙ ወገን መድረክ በገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) መድረክ በትብብር እየሰሩ መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2019 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 18ኛው የገለልተኛ ሃገራት ንቅናቄ (ናም) ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ 120 አባል ሃገራትን ያቀፈና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓለም ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። በሀገራቱ መካከል ተከታታይ የሆኑ የባህል ልውውጥ መድረኮች ተካሄደዋል። ለዚህም እ.አ.አ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአዘርባጃን የትምህርት እድል አግኝተው ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢኮኖሚ አንጻር እ.አ.አ በ2017 በአዘርባጃን የተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ፎረም ተጠቃሽ ነው። በወቅቱ ጨርቃጨርቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በወቅቱ ሀገራቱ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ምጣኔ ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ባለስልጣናት መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እያደጉ መጥተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአዘርባጃን ጉብኝት ማድረጋቸወ ይታወሳል። ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም እንዲሁ። ምክክሩ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍና በትብብር መንፈስ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም በወቅቱ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር በነበራቸው ውይይት የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ መክረዋል። በውይይቱም በመረጃ፣ በፀጥታና ደህንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም መስማማታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ2017 በወቅቱ የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኤልማር ማማድያሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቋሚነት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ማኅበራዊ ፈጠራ ተቋም ሊቀ መንበር ኦልቪ ሜዲዬቭ የብሔራዊ ቤተመንግሥት እና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል። ኦልቪ ሜዲዬቭ በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ የተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን የምትልካቸው ምርቶች ብዝኀነትን ለማሳደግና ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ሰሊጥ፣ የተቆላ ቡና፣ ተልባ፣ የፍየል እና የበግ ሥጋን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ንግድ ትብብር ላይ ያተኮረው ሶስተኛ የኢትዮ-አዘርባጃን የውይይት መድረክ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ከውይይቱ በኋላ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል። 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) በህዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን መካሄዱ ይታወቃል። በጉባኤው ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጋለች። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑክ ከአዘርባጃን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ሀገራቱ በአካባቢ ጥበቃ፣ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገራቱ መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደረጉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ትምህርት እና ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ እንደሚታይ አንስቷል። የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝትም የዚሁ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጉብኝት በመሪ ደረጃ የሚደረግ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር የቅርብ ዓመታት ውይይቶች እና ጉብኝቶች ማሳያ ናቸው።
የኢትዮጵያ የስኬት ጉዞ …
Feb 26, 2026 162
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በየዘርፉ እያስመዘገበቻቸው የሚገኙት ስኬቶች በተለያዩ የዓለም መድረኮች በምሳሌነት እያስጠቀሳት ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በአምስቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አምዶቿ ማለትም በግብርና፣ በኢንዳስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ቀጥለን እንዳሥሣለን። የስንዴ ምርታማነት ስኬት ኢትዮጵያ በግብርና በተለይ በሌማት ትሩፋት እና በስንዴ ልማት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ስኬት ያስመዘገበችባቸው መስኮች ናቸው። ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ታወጣ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከለውጡ መንግስት ወዲህ ግን በተለይ ለስንዴ ልማት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የግብርና ሜካናይዜሽን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን በከፍተኛ መጠን ማሳደግ በመቻሉ ከራስ ፍላጎት ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ ትገኛለች። ይህ ውጤታማነቷም በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጭምር እውቅና አስችሯታል። ለስንዴ ምርት እና ምርታማነት ማደግ ዘመናዊ የመስኖ ሥርዓቶች፣ የኩታ ገጠም አስተራረስ ዜዴ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን ስልቶችና የግብርና ኢኒሼቲቮች በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። በዚህ መነሻነት ነው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት ለአፍሪካ አርዓያነት ያለው መሆኑንና በስንዴ ልማት ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበችው ለውጥ ከፍተኛ መነሳሳት መፍጠሩን ጠቅሰዋል። ይህን የኢትዮጵያን ውጤታማነት መነሻ በማድረግም የአፍሪካ ሀገራት እንዲተገብሩት መክረዋል። በተመሳሳይ በ2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ መሸለማቸው ይታወቃል። ሽልማቱ በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ትጋት፣ ፈጣን፣ ተለዋዋጭና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት ስኬት የግብርናው አብዮት ማሳያ ሲሆን፤ ራስን መቻል እና ለአፍሪካ መብቃትን ያለመ ነው። ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በሰላም ግንባታ፣ ግጭት አፈታት እና አኅጉራዊ ትሥሥር ረገድ ሚናዋን እየተወጣች ያለችው ኢትዮጵያ፤ በዲፕሎማሲው መድረክም ተደማጭነቷ እያደገ መጥቷል። በሰላም ማስከበር፣ አረንጓዴ ዐሻራና በሌሎች ዐበይት ጉዳዮች ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት በዓለም መድረኮች ስሟ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን፣ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ፣ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው፣ የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የሌሎች ሀገራት ባልሥልጣናት የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝቶች የሀገሪቱን የጂኦ ፖለቲካዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ብሎም የዲፕሎማሲ ተደማጭነት እያደገ መምጣት ያሳያሉ። ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ በዓለም መድረክ የአፍሪካ ድምጽ እየሆነች ትገኛለች። አረንጓዴ ዐሻራ - ሌላኛው የኢትዮጵያ ስኬት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሐምሌ 2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፤ እስከአሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። በ2011 ዓ.ም 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፤ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ በተከናወነው ሥራ አሁን ላይ ከ23 በመቶ በላይ ደርሷል። በኢትዮጵያ በተካሄደው 2ኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራው ዕውቅና ተችሮታል። በተጨማሪም በ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዋን ኢትዮጵያ ባስተዋወቀችበት ወቅት፤ የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ መሆኑንም በምሳሌነት ጠቅሰውታል። ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ችግኝ በመስጠት የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን አሳይታለች። ይህም "አረንጓዴ ዲፕሎማሲ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትን ለማዳበር አስተዋጽኦ አበርክቷል። የግዙፍ (ሜጋ) ፕሮጀክቶች ግንባታና ምረቃ በወርሃ ጳጉሜን 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የኢነርጂ ትሥሥር ውጥን ትልቅ የምሥራች ነው። የጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ የሚያገኙት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትም ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግር የሕዳሴ ግድብ የአፍሪካ ራስን የመቻል ምልክት እና የኢትዮጵያ አይበገሬነት ተምሳሌት መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የኒውክሌር ማበልጸጊያ እንደሚገነባ፣ የጋዝ ፋብሪካ እንደሚመረቅ፣ የነዳጅ ማጣሪያ ዕውን እንደሚሆን፣ በአፍሪካ ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚገነባ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታ እንደሚከናወን ጉባ ላይ ማብሠራቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም በሶማሌ ክልል የጋዝ ፋብሪካ ተመርቋል፣ የቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም ተጀምሯል። የሌሎች መሠረተ ልማቶች ግንባታ እና የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። እየተገነባ ያለው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫም ለኢነርጂ አቅርቦት ዕድገት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት መገለጹ ይታወሳል። የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማዘመን ሥራዎች የኮሪደር ልማት ኢኒሼቲቮች የትራንስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንዲዘምኑ፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ፣ የንግድ ተቋማት አሰራር እንዲዘምን፣ አምፊ ቴአትርን ጨምሮ የኪነ-ጥበብ መሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ግንባታ እንዲከናወን የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ የክልል ከተሞችን ከማስዋብ ባለፈ ዜጎች በንጹህ አካባቢ እንዲኖሩ አስችሏል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እ.አ.አ በ2025 ስለ አዲስ አበባ ሲናገሩ፤ ከተማዋን ጊዜ ወስደው መመልከታቸውንና ከፍተኛ መሻሻል እንዳዩ መግለጻቸው አንዱ ማሳያ ነው። የኬንያ የፓርላማ አባል ጁኔት መሐመድም አዲስ አበባን የአፍሪካ አዲሷ ዱባይ ሲሉ አድንቀው፤ አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ምሳሌ መሆኑንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ዲፕሎማቶች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲሁም የልማት አጋሮች ለአዲስ አበባ የከተማ መዘመንና ለውጥ ምስክርነታቸውን መስጠታቸው አይዘነጋም። በሰው ሠራሽ አስተውሎት ረገድ ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከአምስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቁማ ወደ ሥራ ገብታለች። በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠም ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ ባካሄደው መድረክ ላይ፤ ፈጥነን ልጆቻችንን ካዘጋጀን ሰው ሠራሽ አስተውሎትን እንደ ተለያዩ ምርቶች በቀላሉ መጠቀም እንችላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የምትገነባው የኤ አይ ዩኒቨርሲቲም የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ብዙ ችግሮችን ይፈታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረት እየጣለች መሆኗንም አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ዘመኑን የዋጀ ዕይታ ለዲጂታል ዘመን ለውጦች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንም ይፈጥራል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያን በዲጂታል ዘርፉ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የማሸጋገር ዐቅም አላቸው። ኢትዮጵያ - የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል የአፍሪካ አቪዬሽን ምልክት የሆነው ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ኢትዮጵያን ከቀሪው ዓለም እና አፍሪካን ርስ በርስ በማገናኘት በኩል የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ነው። የአየር መንገዱ የመንገደኞች እና የካርጎ አገልግሎቶች የንግድ፣ የቱሪዝም እና ዓለምአቀፍ የቢዝነስ ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተም ይገኛል። በተያዝው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽም አየር መንገዱ 10 ነጥብ 64 ሚሊየን ሰዎችን ማጓጓዝ መቻሉ ለመሪነቱ ትልቅ ማሳያ ሆኖ ይወሰዳል። በሌላ በኩል በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው ቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀምሯል። የዚህ ግንባታ መጀመር ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን የመሪነት ሚና አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁነኛ ሚና አለው። ሌላኛው የኢትዮጵያ ስኬት - ቱሪዝም ኢትዮጵያ በታሪክ፣ ባህል፣ በተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች የታደለች ናት። እነዚህም ጎብኚዎችንና ተመራማሪዎችን መሳባቸውን ቀጥለዋል። መንግሥት እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ ወስዶ እየሠራበት በሚገኘው የቱሪዝም ዘርፍ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት፤ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ አማካኝነት የተከናወኑ ሥራዎች የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እያሳደጉም ይገኛሉ። በቅርቡ በሶማሌ ክልል የተመረቀው እና የገበታ ለትውልድ ሥራ አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት የዚሁ ሥራ ማሳያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምረቃው ወቅት፤ ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምሥራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ሥራ ነው ማለታቸው ይታወሳል። በአዲስ አበባ የሚገኙት የወዳጅነት ዐደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና ሌሎችም ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሆነዋል። የኮሪደር ልማቱም የመዲናዋን መልክ በአዲስ ሁኔታ በመግለጥ ጎብኚዎችን እየሳበ ነው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በዲፕሎማሲ፣ በኢኖቬሽን፣ በመሠረተ ልማት፣ በከተማ ማዘመንና ኮሪደር ልማት፣ ቱሪዝምን ጨምሮ በሌሎች መስኮች ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች የራሷን መጻኢ ጊዜ ብሩኅነት ያመላክታሉ። የኢትዮጵያ ስኬቶች ብሎም ስትራቴጂካዊ ራዕይ ጊዜውን የሚመጥን ዕድገትን በትጋትና በጋራ ትብብር የመሥራት ውጤትን የሚያሳዩ ናቸው። ኢትዮጵያ ለዛሬ ብቻ እየሠራች አይደለም፤ ቀጣይ ለሚመጡ ትውልዶች መሠረት እየጣለችም እንጂ።