ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Oct 13, 2026 20
አርባምንጭ፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡-በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ። በአርባምንጭ ከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት የተካሄደ የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ዛሬ ተመርቋል።   በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ሥራ ፕሮጀክት አስተባባሪ አንዷለም ገሠሠ እንደገለጹት በሀገሪቱ በ88 ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል። በዚሁ መሠረት ባለፉት አምስት ዓመታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዜጎችን በትምህርት፣ በጤናና በሌሎችም የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል። የአርባምንጭ ከተማ የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታም የዚሁ አንድ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ወገኖችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ በቢሮውና በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ትብብር የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ። ትምህርት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና ጉልህ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የተገነባው ትምህርት ቤት በዕውቀት የታነጸ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት አስተዋጽኦው የላቀ ነው ብለዋል። የትምህርት ተደራሽነት ለማስፋፋትና ጥራቱን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ለትምህርት ልማት ስራ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል ።   የአርባምንጭ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ሊዲያ ከንቲባ በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ግንባታ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል። ትምህርት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ጉልህ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቤተ ሙከራና በቤተመጻሕፍት እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።  
የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት መካከለኛ የሰው ኃይል በማፍራት ላይ ማተኮር አለባቸው
Oct 13, 2026 29
ጎንደር፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡-የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ከኢንተርፕረነር ሺፕ ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀምሯል።   የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል። ለዚህም የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት አዲሱን የስልጠናና ስርዓተ ትምህርት በተግባር በመተርጎም ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ወጣቱን ትውልድ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በዕውቀትና ክህሎት በማነጽ የስራ እድል ፈጣሪና ተጠቃሚ እንዲሆን የመምህራን የስራ ተነሳሽነትና ርብርብ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል። ፈጣን ሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ የሚቻለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ላይ አተኩሮ በመስራት መሆኑን ጠቁመው አስተዳደሩም ለዘርፉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።   የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮንን በበኩላቸው፤ ስልጠናው በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በጎንደር ቀጠና የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን ለማብቃት ያለመ ነው። ለ10 ቀናት በሚቆየው ስልጠናም ፖሊሲውን በማሳወቅ፣ ሙያን ወደ ቢዝነስ በመቀየር፣ በመደራጀት አብሮ የመስራት ስነ-ምግባርና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በማተኮር ይሰጣል ብለዋል። ስልጠናው የተግባቦት፣ የቡድን ስራ፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የችግር አፈታትና የውሳኔ ሰጪነት ክህሎቶችን ለማዳበር ያስችላል ያሉት ደግሞ ስልጠናውን በመስጠት ላይ የነበሩት አቶ ጌታቸው አለባቸው ናቸው። ከሰልጣኞቹ መካከል መምህር ባዬ ከበደ፤ ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ የአሰልጣኝነት ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተመሳሳይ ስልጠናዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሐሮማያ እና ሐዋሳ እየተሰጠ መሆኑም በዚሁ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡
 ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ተቋማዊ ብቃቱን ለማሳደግ በቅንጅት እየሰራ ነው 
Oct 13, 2026 43
ጅማ፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ተቋማዊ ብቃትና የተማሪዎች ክህሎት ለማሳደግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ከአፍሪካን ዲጂታል ኢኖቬሽን ኤንድ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ጋር በቴክኖሎጂ ልማት፣ በስልጠናና በሙያ ምክር አገልግሎት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ዛሬ ስምምነት አድርጓል።   ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመማር ማስተማርና ለምርምር ለማዋል አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዩች ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማስፋፋት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ነው። ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ብቁ ከማድረግ ባሻገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የተካኑ ዜጎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም አክለዋል። በተለይም በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለጥሩ ዓላማ የመጠቀም ልምድ እንዲዳብር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ስልጠናዎችን ተደራሽ የማድረግ ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።   የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ማዕከል ዳይሬክተር መሀመድ ሙንታዝ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ አካዳሚው በዩኒቨርሲቲው እየሰጠ ያለው ስልጠና በቀጣይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ለማሳደግ ጉልህ ሚና አለው። የአፍሪካን ዲጂታል ኢኖቬሽን ኤንድ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ሸጋው አናጋው በበኩላቸው፣ አካዳሚው ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቴክኖሎጂ ልማት፣ በስልጠናና በማማከር ላይ ለመስራት መስማማቱን ገልጸዋል።   ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመማር ማስተማርና ለምርምር በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማገዝ ያለመ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አበረታች ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋሙና ለዘርፉ የሚያግዝ ፖሊሲ መውጣቱ የቴክኖሎጂ ልማቱን ለማሳለጥ የሚያስችሉ አስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው ብለዋል። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋገጡ
Oct 13, 2026 105
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዓመታዊው ስብስባ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችንም እያካሄደ ነው።   ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሊድ መሐመድ ባላማ ጋር ተወያይተዋል። የሁለቱ ሀገራት ማዕከላዊ ባንኮች ገዥዎች ውይይት በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የሀገራቱን የፋይናንስ ሥርዓቶች ይበልጥ ለማቀራረብና ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
የሚታይ

የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ግንባታና ለሕዝቦች አብሮነት ታላቅ ሀገራዊ ኃይል ናቸው 
Oct 13, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ግንባታ፣ ለሕዝቦች አብሮነት እንዲሁም አንድነት ታላቅ አቅም መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት 45ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ታሪክ፣ ባህል፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ቅርሶችና የምኅንድስና ጥበባት ግንባታ ታሪካዊና ዘላቂ ሚና አበርክታለች። ቤተ ክርስቲያኗ ለዘመናት የትምህርት፣ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ማዕከል ሆና በማገልገል ለሀገር ነፃነትና ለሕዝቦች አብሮነት ፈር ቀዳጅ ሆና መዝለቋንም አብራርተዋል። አባቶች፣ እናቶች በነበራቸው ጽኑ መንፈሳዊ ተጋድሎና እምነት ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አሻራ ማኖራቸውን በማስታወስ፣ የአሁኑ ትውልድም ይህንን አርዓያነት በመከተል ሀገራዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በጋራ የሚያስተሳስራቸው ዋና መሠረት ኢትዮጵያዊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።   የሃይማኖት ተቋማት የሀገር ግንባታና የሰላም መሠረት መሆናቸውን በመግለጽ፤ ይህን አበርክቷቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። መንፈሳዊ አባቶች፣ ካህናት፣ ሊቃውንትና ምዕመናን የተሰጣቸውን አደራ በመወጣት ዘላቂ ሰላምን በማጽናት፣ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ድህነትና ኋላቀርነትን በማስወገድ በኩል አዎንታዊ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ ሰበካ ጉባዔው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡ የጉባኤው ዋነኛ ዓላማ ፍቅርን በማስፈን፣ አብሮነትን ለማጠናከር እና ተግቶ ለመስራት ቁርጠኝነት የሚታደስበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዚሁ ወቅት፤ ሰበካ ጉባዔው የ2018 ዓ.ም አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ገምግሞ የ2019 ዓ.ም የስራ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለዋል። የምዕመናንን የአገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት እንዲሁም በኢኮኖሚ የበለጸገችና የተጠናከረች ተቋም ለመገንባት የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በቤተ-ክህነት ደረጃ የተለያዩ የልማትና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል። የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ሲስተም፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ሲስተም እና የድረ ገጽ መግቢያ ፓርታል ተጠናቅቀው ተመርቀዋል።
የኢትዮጵያና ሩሲያ የግብርና ንግድ ትብብር የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ የምርታማነት አቅምን ለመገንባት ያግዛል
Oct 13, 2026 203
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያና ሩሲያ የግብርና ንግድ ትብብር የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ የምርታማነት አቅም ለመገንባት እንደሚያግዝ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በኢዜአ አዘጋጅነት “የሩሲያና የኢትዮጵያ የግብርና ንግድ አጋርነት፤ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂና የምግብ ዋስትና” በሚል መሪ ሐሳብ የኢትዮ-ሩሲያ የግብርና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ማፋጠን፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስርን ማስፋት እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሀገራት የትብብር መስኮች መሆናቸው ተነስቷል።   የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሰብል ንግድ ማስፋፊያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዌይሳ ጋረደው፤ የኢትዮጵያ ግብርና የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ እመርታዊ የዕድገት ጉዞ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ዕድገት እየተመዘገበ የሚገኘውም በግብዓት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እንዲሁም በጥናትና ምርምር ታግዞ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ የትብብር ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የሩሲያ የንግድ ተወካይ ያሮስላቭ ታራሲዩክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሩሲያና ኢትዮጵያ በንግድና በግብርና ልማት ያላቸውን ትብብር እያሳደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።   ሩሲያ ከኢትዮጵያ ቡናን፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን እንደምትረከብ፣ ኢትዮጵያም ከሩሲያ የአፈር ማዳበሪያና የምግብ ዘይት እንደምታስገባ አስታውቀዋል። የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በግብርናና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን እያሰፋ መሆኑንም ጠቁመዋል። ይህም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ ዳርእስከዳር ታዬ፤ የአፍሪካ ዲያስፖራ በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር በማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።   ዲያስፖራው ያካበተውን ልምድና እውቀት ወደ አፍሪካ በማሸጋገር በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፀደቀ አባተ(ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን በማሻሻል የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አቅሟን እያጎለበተች መሆኑን ገልጸዋል።   በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው የግብርና ንግድ ትብብርም ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል። የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማቀነባበር አቅም ማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን የፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኩባንያ የሀገር ውስጥ ኃላፊ ሀብታሙ ሚሊዮን ገልጸዋል።   ሩሲያ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ያካበተችውን የቴክኖሎጂ አቅም፣ እውቀትና ልምድ ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማጋራት ለዘርፉ ዕድገት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንዳለባት አሳስበዋል። የኢትዮ-ሩሲያ የግብርና ትብብር በንግድ ልውውጥ ብቻ ሳይወሰን በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በምርት ማቀነባበር የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የጣና ፎረም ታዳሚዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል
Oct 13, 2026 105
ባህርዳር፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው የጣና ፎረም ታዳሚዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ፎረሙን ለማዘጋጀት እየተደረገ ባለው ዝግጅትና የኮሙኒኬሽን ስራዎች ላይ በማተኮር ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በባህርዳር ከተማ የሚካሔደው የጣና ፎረምን ስኬታማ በሆነ መንገድ ለማጠናቀቅ የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል። ፎረሙ የኢትዮጵያን ገጽታ በሚገነባና እድገቷን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ የሚካሔድ መሆኑን ተናግረዋል። የጣና ፎረም አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው ጥበብና አመራር ለመፍታት የሚካሄድ መሆኑንም አክለዋል። በባህርዳር ከተማ እስካሁን የተካሄዱ 11 የፎረሙ ስብሰባዎችም በአህጉሩ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ለመሪዎች ጉባኤ የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህም በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን እድገትና ልማትን በማፋጠን ላይ በመምከር የመፍትሄ ሃሳቦችንና የቀጣይ እቅጣጫዎች እንዲመነጩ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም አፍሪካ ያላትን ሃብት ተጠቅማ እንዳትለማ እንቅፋት በሆኑ ህገ- ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር ላይ በመወያየት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ማመላከት እንደተቻለ አመልክተዋል። “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን የዘንድሮው የ12ኛው የጣና ፎረም በአፍሪካ ሰላም፣ መረጋጋትና እድገት ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለመላው የጥቁር ህዝቦች ነጻነት እንደታገለችው ሁሉ ዛሬም የራሷን ልማትና እድገት በማረጋገጥ ወደ አህጉሩ አባል ሀገራት እንዲስፋፋ የበኩሏን ኃላፊነት እየተወጣች እንደምትገኝ አስረድተዋል። በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ለፎረሙ የሚመጡ የአፍሪካ መሪዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። 12ኛው የጣና ፎረም በባህርዳር ከተማ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
በትግራይ ተቋርጦ የቆየው የትጥቅ ማስፈታትና ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ሂደት (DDR) እንደገና ተጀመረ
Oct 12, 2026 304
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2 /2019(ኢዜአ)፦ከታጠቁ ኃይሎች በመውጣት ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስ የሚፈልጉ ወጣቶች በመቀሌ እየተመዘገቡ እንደሚገኙ ተገለጸ። በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የትጥቅ ማስፈታት፣ ከታጠቁ ኃይሎች መውጣትና ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስን ያካተተው የDDR ሂደት እንደገና መጀመሩ ተሰምቷል። በሂደቱ መቀጠል፣ ከጦርነት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ የሚፈልጉ ታጣቂዎች የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በመቀሌ በሚገኘው የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የምዝገባ ማዕከል በመቅረብ እየተመዘገቡ መሆኑ ተገልጿል። በምዝገባው ሂደት ከሚሳተፉ አንዳንድ የታጠቁ ወጣቶች እንደገለጹት፣ በአካባቢያቸው ለሚገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ክፍሎች መሣሪያዎቻቸውን ካስረከቡ በኋላ ወደ መቀሌ በመምጣት ለምዝገባ ቀርበዋል። የDDR ሂደቱ እንደገና መጀመሩ፣ በጦርነት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ከወታደራዊ ኑሮ በመውጣት የተረጋጋ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት እንዲመሠርቱ አዲስ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ በተለይም በቀደመው ግጭት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የትግራይ ወጣቶች ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ የሚያስችሏቸውን አማራጮች እንዲጠቀሙና የወደፊት ሕይወታቸውን እንደገና እንዲገነቡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። የDDR ሂደቱ ዋና ዓላማ ታጣቂዎች ከታጠቁ ኃይሎች በመውጣት ወደ መደበኛ ማኅበራዊ ኑሮ እንዲመለሱ፣ በሰላም ግንባታና በልማት ሥራዎች እንዲሳተፉ ማስቻል ነው። ይህንን ዓላማ ለማሳካት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የተለያዩ ተቋማትና ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ቅንጅትና ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ ተጠቁሟል። በምዝገባው ወቅት ያነጋገርናቸው አንዳንድ ታጣቂዎች የDDR ሂደቱ እንደገና መጀመሩ ከታጠቀ ኑሮ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመሸጋገር አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በተያያዘም የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በመቀሌ በሚገኙት የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽንና የሰሜን እዝ ማዕከል በመቅረብ እንዲመዘገቡ ለሚፈልጉ ታጣቂዎች ጥሪ ማቅረቡ ተገልጿል።
የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የትውልዱ የጋራ ጥያቄና ሀገራዊ አጀንዳችን ነው - የፓርቲ አመራሮች
Oct 12, 2026 261
አዳማ፣ ጥቅምት 02/2019 (ኢዜአ) ፦ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የትውልዱ የጋራ ጥያቄና ሀገራዊ አጀንዳችን ነው ሲሉ የተለያዩ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ተናገሩ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርእይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባሕር በር ጉዳይን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና መቀጠል አትችልም ማለታቸው ይታወሳል። በመሆኑም የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የትውልዱ የጋራ ጥያቄና ሀገራዊ አጀንዳችን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ፓስተር በየነ ደሳለኝ፤ ኢትዮጵያ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ የሁላችንም ቁጭት በመሆኑ ወደ ቀደመ ባለቤትነቷ እንድትመለስ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷን በማይታወቅ መልኩ ድንገት ያጣችው ቢሆንም ታሪክን፣ ህጋዊነትንና ቅርበትን መሰረት በማድረግ በዚህ ትውልድ ይመለሳል ብለዋል ። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጉዳይ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባለፈም የሉአላዊነቷና የህልውናዋ መሰረት መሆኑን ገልጸው ጥያቄውም ምላሽ ማግኘት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። በተለይ በቀጣናው ያለውን አሁናዊ የኃይል አሰላለፍ ለመዋጀት እና ብሔራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ የባሕር በር ጥቅሙ ምትክ የለሽ እንደሆነ አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር የመንግስት ምስረታ ላይ ባደረጉት ንግግር የባህር በር ባለቤትነት በሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲመለስ እንደሚሰራ ማንሳታቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲም በቅርበት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሀብታሙ ተሰማ፤ የባሕር በር ተጠቃሚነት የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እና ምጣኔ ሃብታዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ ሁላችንም እንረባረባለን ብለዋል። የባሕር በር ባለቤትነት መብትን ለማረጋገጥ የመደመር መንግሥት በሰጥቶ መቀበል የዲፕሎማሲ መርህ መስራቱ ሊደነቅ የሚገባው ስለመሆኑም አንስተዋል። የአዲስ ትውልድ ፓርቲ አባል ወጣት ቦንቱ አብርሃም፤ የባሕር በር ጉዳይ የዜጎች ቁጭትና ለዓመታት ሲብሰለሰል የቆየ ጥያቄ በመሆኑ በዚህ ትውልድ ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል የሚል ጽኑ እምነት እንዳላት ገልፃለች። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ የጋራ ጥያቄና ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን አንስታ በጉዳዩ ላይ የመንግስትን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቃ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ጠንካራ አቋም ይዘን እንሰራለን ብላለች።
ጠመንጃ የሚያስነሳና ጫካ የሚያስገባ ምንም አይነት ምክንያት የለም - የቀድሞ ታጣቂዎች
Oct 12, 2026 274
ገንዳውኃ፣ ጥቅምት 02/2019ዓ/ም (ኢዜአ) ፦ ጠመንጃ የሚያስነሳና ጫካ የሚያስገባ ምንም አይነት ምክንያት የሌለ መሆኑን በመረዳት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን መጥተናል ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ገለጹ። በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በጫካ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች የሰላምን ጥሪ በመቀበል መጥተዋል። ‎የቀድሞ ታጣቂዎቹ በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ በመግባት በአካባቢው ህዝብ ላይ በፈፀሙት በደል መጸጸታቸውን ተናግረዋል።   ከታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ተልእኮ በመቀበል ጉዳት አድርሰናል፤ በደልም ፈፅመናል ያሉት የቀድሞ ታጣቂዎቹ በድርጊታቸው መጸጸታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ጊዜ ጠመንጃ የሚያስነሳና ጫካ የሚያስገባ ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ በአግባቡ ተገንዘበናል በማለት ለፈፀሙት ጥፋት ይቅርታቸውን ጠይቀዋል። በመሆኑም በቀጣይ የልማት አርበኛና የሰላም አምባሳደር በመሆን የበደልነውን ህዝብ ለመካስ በመዘጋጀት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን መጥተናል ብለዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደረሰ አዱኛ፤ በጥፋታቸው ተጸጽተው የሰላምን እድል በመጠቀም የመጡ የቀድሞ ታጣቂዎችን አመስግነዋል።   በዞኑ አሁንም በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላምን ጥሪ ተቀብለው እንዲመጡ ጥሪ በማቅረብ ለመጡት አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ የሚደረግ መሆኑን ገልጸው በልማት ህዝብን መካስ እንዲዘጋጁ አስገንዝበዋል። የመተማ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ምክትል ኃላፊ አቶ አስፋው ውበት፤ የሰላምን ጥሪ ተቀብለው የመጡትን በማመስገን በጫካ የቀሩ ሌሎች ታጣቂዎችም ይህንኑ እድል እንዲጠቀሙ መክረዋል።
የመደመር መንግስት የተለማቸው የልማት ዕቅዶች የህዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው
Oct 12, 2026 241
አሶሳ፤ ጥቅምት 2//2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት በቀጣይ ዓመታት ለማከናወን የተለማቸው የልማት ዕቅዶች ህዝቡን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ትልቅ ሀገር፤ትልቅ ህዝብ፤ታላቅ ርዕይ ነዋሪዎቹ እንደገለፁት፤ የመደመር መንግሥት በሚቀጥሉት ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግዙፍ የልማት ግቦችና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው። የልማት ዕቅዶቹ በሚቀጥሉት ዓመታት ውስጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ አስራት ወልደአማኑኤል፤ የመደመር መንግሥት ያቀዳቸው ግቦች ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና በጠንካራ አንድነት ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። የመደመር መንግሥት በቀጣዮቹ ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግዙፍ የልማት ግቦች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በተግባር የሚያረጋግጡና ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ እንደሚሆኑም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።   ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ኢብራሂም አዙቤር በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በምርጫ የህዝብ ይሁንታን ያገኘ መንግሥት በመሆኑ በሚሰራቸው የልማት ሥራዎች ጠንካራ የህዝብ ንቅናቄን መፍጠር ይችላል ብለዋል። የመደመር መንግሥት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ በተግባር ያሳየ ነው ያሉት ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጉደታ ነጋሳ ናቸው።   መንግሥት በቀጣይ ዓመታት ለመተግባር የተለማቸውን የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ግዙፍ የልማት ተግባራትን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለበት እና ህብረተሰቡም ከመንግሥት ጎን በመሆን የልማቱ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆን እንዳለበትም አመልክተዋል።      

ማህበራዊ
በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Oct 13, 2026 20
አርባምንጭ፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡-በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ። በአርባምንጭ ከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት የተካሄደ የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ዛሬ ተመርቋል።   በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ሥራ ፕሮጀክት አስተባባሪ አንዷለም ገሠሠ እንደገለጹት በሀገሪቱ በ88 ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል። በዚሁ መሠረት ባለፉት አምስት ዓመታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዜጎችን በትምህርት፣ በጤናና በሌሎችም የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል። የአርባምንጭ ከተማ የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታም የዚሁ አንድ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ወገኖችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው የአሰፋ ጨቦ መታሰቢያ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ በቢሮውና በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ትብብር የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ። ትምህርት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና ጉልህ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የተገነባው ትምህርት ቤት በዕውቀት የታነጸ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት አስተዋጽኦው የላቀ ነው ብለዋል። የትምህርት ተደራሽነት ለማስፋፋትና ጥራቱን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ለትምህርት ልማት ስራ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል ።   የአርባምንጭ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ሊዲያ ከንቲባ በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ግንባታ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል። ትምህርት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ጉልህ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቤተ ሙከራና በቤተመጻሕፍት እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።  
የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ግንባታና ለሕዝቦች አብሮነት ታላቅ ሀገራዊ ኃይል ናቸው 
Oct 13, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ግንባታ፣ ለሕዝቦች አብሮነት እንዲሁም አንድነት ታላቅ አቅም መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት 45ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ታሪክ፣ ባህል፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ቅርሶችና የምኅንድስና ጥበባት ግንባታ ታሪካዊና ዘላቂ ሚና አበርክታለች። ቤተ ክርስቲያኗ ለዘመናት የትምህርት፣ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ማዕከል ሆና በማገልገል ለሀገር ነፃነትና ለሕዝቦች አብሮነት ፈር ቀዳጅ ሆና መዝለቋንም አብራርተዋል። አባቶች፣ እናቶች በነበራቸው ጽኑ መንፈሳዊ ተጋድሎና እምነት ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አሻራ ማኖራቸውን በማስታወስ፣ የአሁኑ ትውልድም ይህንን አርዓያነት በመከተል ሀገራዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በጋራ የሚያስተሳስራቸው ዋና መሠረት ኢትዮጵያዊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።   የሃይማኖት ተቋማት የሀገር ግንባታና የሰላም መሠረት መሆናቸውን በመግለጽ፤ ይህን አበርክቷቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። መንፈሳዊ አባቶች፣ ካህናት፣ ሊቃውንትና ምዕመናን የተሰጣቸውን አደራ በመወጣት ዘላቂ ሰላምን በማጽናት፣ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ድህነትና ኋላቀርነትን በማስወገድ በኩል አዎንታዊ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ ሰበካ ጉባዔው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡ የጉባኤው ዋነኛ ዓላማ ፍቅርን በማስፈን፣ አብሮነትን ለማጠናከር እና ተግቶ ለመስራት ቁርጠኝነት የሚታደስበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዚሁ ወቅት፤ ሰበካ ጉባዔው የ2018 ዓ.ም አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ገምግሞ የ2019 ዓ.ም የስራ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለዋል። የምዕመናንን የአገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት እንዲሁም በኢኮኖሚ የበለጸገችና የተጠናከረች ተቋም ለመገንባት የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በቤተ-ክህነት ደረጃ የተለያዩ የልማትና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል። የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ሲስተም፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ሲስተም እና የድረ ገጽ መግቢያ ፓርታል ተጠናቅቀው ተመርቀዋል።
በኢትዮጵያ መድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው
Oct 13, 2026 158
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የመድህን አገልግሎት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ የኢትዮጵያ መድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ዳይሬክተር በላይ ቱሉ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዲሱ የመድህን አዋጅ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አልፎ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል። በኢትዮጵያ የመድህን አገልግሎት ባለፉት 30 ዓመታት ዕድገት እያሳየ ቢሆንም ከሀገሪቱ አቅምና ከዓለም አቀፍ ደረጃ አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የመድህን አገልግሎት ዕድገት የሚለካው ለኢኮኖሚው በሚያበረክተው አስተዋጽኦ፣ የመድህን አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብዛት እና በአገልግሎቶቹ አይነት መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም መለኪያዎች አነስተኛ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ካላት የኢኮኖሚ አቅም፣ መድህን የመግዛት ፍላጎት ካለው ህዝብ ቁጥርና ተመሳሳይ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የመድህን አገልግሎት ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚያበረክተው በዓለም 6 ነጥብ 5 በመቶ፣ በአፍሪካ 3 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም በሰብ-ሰሃራን አፍሪካ 2 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ እንዳለው ገልጸው፤ በኢትዮጵያ 0 ነጥብ 3 በመቶ አስተዋጽኦ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። የመድህን ዘርፉ ለውጭ ገበያ ዝግ ሆኖ መቆየቱ፣ ዘርፉን መቆጣጠር፣ ማሳደግና መምራት የሚችል ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁን ለማውጣት ገፊ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። የአገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነትን ለማሻሻል በሰው ሀይልና በቴክኖሎጂ ማዘመን እንደሚገባ ገልጸው፤ ያላትን ዕምቅ አቅም ጥቅም ላይ ማዋል ያስችላል ብለዋል። በተመሳሳይ ስራ የተለየ ውጤት መጠበቅ እንደማይቻል ገልጸው፤ የህይወት መድህን ከጠቅላላ የመድህን አገልግሎት እንዲያድግ ማድረግ የሚያስችል አሰራር ይፈጥራል ብለዋል። በአፍሪካ የመድህን አገልግሎትን በማዕከላዊ ባንኮች የሚቆጣጠሩት ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 ሀገራት ብቻ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ሌሎች ራሱን የቻለ የመድህን ተቆጣጣሪ ባለስልጣን አልያም ከጡረታ ተቋም ጋር ተቀናጅቶ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ለዚህም በኢትዮጵያ የመድህን አገልግሎት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ የመድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በአዋጁ መሰረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ከተጨማሪ ሀላፊነት ጋር ይዞ በገለልተኝነት ይቋቋማል ብለዋል። አዲሱ የመድህን አዋጅ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አልፎ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል ያሉት አቶ በላይ፤ ለመድህን ተቋማት ዕድገት በትጋት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በመሆኑም ለመድህን ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፤ ውጤታማነታቸውንም ይቆጣጠራል፣ ለኢንዱስትሪው ዕድገት በሚበጅ መንገድ እንዲመሩ ጤናማነታቸውን ይቆጣጠራል ብለዋል። የመድህን አዋጁ ከማክሮ ኢኮኖሚ፣ ከቁጥጥር ስርዓቱ እና ከገበያው የሚመነጩ የዘርፉን ችግሮች መፍታት እንዲችል ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። የሕይወት ኢንሹራንስ የሀገራትን የኢኮኖሚ ዕድገትና የዜጎችን የኢኮኖሚ ደረጃ ማሳያ መሆኑን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ገና በመነሳት ላይ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የንብረት ኢንሹራንስ 94 በመቶ ድርሻውን መያዙን በመጥቀስ፤ የሕይወት ኢንሹራንስ ቢያንስ 40 በመቶ መድረስ እንዳለበት ገልጸዋል። በአጠቃላይ የመድህን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ዋጋ በመቀነስ ላይ ከተመሰረተ ውድድር ወደ አገልግሎት ጥራትና አይነት ማተኮር ይገባል፤ አዋጁ ለዚህም አጋዥ ይሆናል ብለዋል።
በመደመር መንግሥት እሳቤ በመመራት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሕዝብን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ይሰራል
Oct 13, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በመደመር መንግሥት እሳቤ በመመራት በቀጣዮቹ አምስት አመታት የሕዝብን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት በላቀ መልኩ ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ገለጹ፡፡ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ራዕይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብን ይሁንታ በማግኘት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ቀደም ብሎ እንዲሁም መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም አዲሱን የመደመር መንግሥት መመስረቱ ይታወቃል። በየደረጃው በተካሄዱት የመደመር መንግሥት ምስረታ ጉባኤዎች አዲሶቹ የምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የካቢኔ አባላት የሥራ ኃላፊነታቸውን በመረከብ በይፋ ሥራ ጀምረዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ተሿሚ የካቢኔ አባላትም፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሕዝብን አደራ በላቀ የኃላፊነት መንፈስ በመቀበል የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። በመደመር መንግሥት እሳቤ በመመራት የመዲናዋን እድገት የሚያፋጥኑና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን በቁርጠኝነት እንደሚተገብሩ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፤ ቢሮው በመደመር መንግሥት እሳቤ ሰላምንና ጸጥታን ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ የከተማዋን ሰላም እና ጸጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ፣ የዕቅዶቹን ውጤታማነት በዜጎች የዕለት ተዕለት እርካታ አንጻር እንደሚገመገምም ገልጸዋል። የወንጀል መከላከል አቅምን ለማሳደግና የኅብረተሰቡን ደህንነት በብቃት ለመጠበቅ ሕዝብን በማሳተፍና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡ በመደመር መንግሥት እሳቤ መሠረት ዕቅዶቻችንን ከልሰን የሕዝብ ተጠቃሚነትና የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ላይ በሰፊው እንሠራለን ብለዋል። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማርያም በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት ዋናው መለኪያ የዜጎች እርካታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ሥራዎቻችን የሚገመገሙት ዜጎች ምን ያህል ተጠቃሚ ሆነዋል እንዲሁም በአገልግሎቶቻችን ምን ያህል እርካታ አግኝተዋል ከሚሉ መመዘኛዎች አንጻር ነው ሲሉ አመላክተዋል። የሚሠሩት ሥራዎች በሙሉ ለብሔራዊ አቅምና ለኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽኑ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ በግራንድ ስትራቴጂው መሠረት ዕቅዶች መከለሳቸውን አስታውቀዋል። ሥራዎች በዲጂታላይዜሽን ታግዘው በፍጥነት፣ በጥራት እና በተደራሽነት እንደሚፈጸሙም አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ፤ በመደመር መንግሥት እሳቤ እና አሠራር መሠረት የንግድ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የቁጥጥር ሥራዎችን በዲጂታል ታግዞ ለማከናወን ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል። በንግድ ቢሮ የሚሰጡ አገልግሎቶች በሙሉ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት እንደሚሰጡና ዜጎችም በተሰጣቸው አገልግሎት እርካታቸውን የሚገልጹበት አሠራር መዘርጋቱንም አክለዋል። በማኑዋል ይካሄድ የነበረው በር ለበር የቁጥጥር ሥራ አሁን ላይ ቅልጥፍናን በሚያስገኙ አዳዲስ የዲጂታል (ኢ-ፎርማት) ሥርዓቶች እንደሚታገዝም የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋገጡ
Oct 13, 2026 105
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዓመታዊው ስብስባ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችንም እያካሄደ ነው።   ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሊድ መሐመድ ባላማ ጋር ተወያይተዋል። የሁለቱ ሀገራት ማዕከላዊ ባንኮች ገዥዎች ውይይት በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የሀገራቱን የፋይናንስ ሥርዓቶች ይበልጥ ለማቀራረብና ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ
Oct 13, 2026 97
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ145 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነትን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አከናውኗል።   ምክር ቤቱ በስብስባው በመንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ145.8 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ ፤ የብድሩ ዓላማ የአዲስ አበባን የኃይል ማስተላለፊያ መረብ ለማጠናከር፣ አዳዲስ የኃይል ጣቢያዎችን መገንባትና ነባሮቹን ማሻሻል እንዲሁም የመሬት ውስጥ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) አስተማማኝና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ የብድር ስምምነቱ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። ብድሩ ቀላልና አነስተኛ የገንዘብ ጫና የሚፈጥር ተብሎ የተገለጸ ሲሆን የስድስት ዓመት የእፎይታ ጊዜን ጨምሮ በ 31 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተብራርቷል። የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትሩ አያይዘውም ብድሩ ከሀገሪቱ የብድር አሰጣጥና አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣምና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን አመልክተዋል። ምክር ቤቱ በመንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኃይል ዘርፍ ማሻሻያ፣ ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተፈረመውን የ145.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ ቀላል የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅን፤ አዋጅ ቁጥር 1441/2019 አድርጎ በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።
የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠንካራ አጋርነት የሚጠይቅ በመሆኑ የድርሻችንን እየተወጣን ነው
Oct 13, 2026 185
ሰመራ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የባህር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠንካራ አጋርነት የሚጠይቅ በመሆኑ የድርሻችንን እየተወጣን ነው ሲሉ በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ ከባህር በር እንድትርቅ የተደረገበት ታሪካዊ ሂደት ሕጋዊ መሠረት የሌለውና የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት ለንግድ ሚዛን መዛባትና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከባድ ጫና መፍጠሩን ያነሱት ፓርቲዎቹ፣ ችግሩን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። የባህር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የዜጎችን ንቁ ተሳትፎና ይበልጥም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠንካራ አጋርነት የሚጠይቅ በመሆኑ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ይህ ጥረት ልዩነት የሌለበት አገራዊ አጀንዳ መሆኑንም አረጋግጠዋል። የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ መሐመድ አወል ወግሪስ፤ ኢትዮጵያን ከባህር በር እንድትርቅ ለማድረግ የተሄደበት መንገድ ሕጋዊ መሠረት የሌለውና ታሪካዊ ፍትሐዊነትን የካደ በመሆኑ፣ ይህንን ታሪካዊ ስህተት በማረም ሂደቱን ለማሳካት እንታገላለን ብለዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር መኖር ቀጠናዊ ተደማጭነቷን ከፍ ለማድረግና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን በመጠቆም፤ ይህንን ለማሳካት የተሄደበት የ"ሰጥቶ መቀበል" የዲፕሎማሲ መርህ ሙሉ በሙሉ የሚደገፍና ብልህነት የተሞላበት መሆኑንም አብራርተዋል። የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የገቢ ረሱ ዞን አስተባባሪ አቶ መሐመድ ኢስማኤል በበኩላቸው፤ ከባህር በር መራቃችን ያስከተለውን ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ጉዳት በመረዳት፣ ለሀገራችን የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ቅርብ በሆነ ስትራቴጂካዊ ርቀት ላይ ብትገኝም፣ ለዓመታት ተነጥላና ተገልላ መቆየቷ ፍጹም አግባብነት የሌለውና የታሪክ ስህተት እንደነበር አቶ መሐመድ ገልጸዋል። ይህንን ብሔራዊ ጉዳይ ለመፍታት እየተሄደበት ያለው ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እጅግ የሚደነቅ በመሆኑ ፓርቲያቸው ከምንጊዜውም በላይ ለስኬታማነቱ በንቃት እንደሚሠራ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ ሀገሪቱ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት ክፍያዎች የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ልማት ለማዋል ያስችላል ብለዋል።
በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ
Oct 13, 2026 135
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳይ ሃይሉ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደመር መንግስት ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት የህዝብን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ህዝብን በማሳተፍ በተደመረ አቅም ይሰራል። በተለይ የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በአጭርና በረዥም ጊዜ የሚከናወኑትን ለይቶ ወደሥራ እንደሚገባ ገልጸው፣ ፈጣን ምላሽ ለሚፈልጉት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት በርብርብ ይሰራል ብለዋል። የክልሉ መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ህዝቡ የሚያደርገው ተሳትፎና ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክተዋል። በክልሉ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የልማት ፀጋዎችን በአግባቡ ለይቶ መጠቀም ሌላው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም ርዕስ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። መንግስት ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የህዝቡ ኑሮ እየተሻሻለ ከመምጣቱ ባለፈ የክልሉን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን እያገዘ መሆኑንም አስታውቀዋል።   በቀጣይም የክልሉን ህዝብ የልማት ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ጠንካራ ተቋማትን ከመገንባት ባለፈ አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። የወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን ጨምሮ በክልሉ የልማት ሥራዎች በቅንጅት እንደሚከናወኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል። የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠርና ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለይቶ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል። በመድረኩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም የተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት መካከለኛ የሰው ኃይል በማፍራት ላይ ማተኮር አለባቸው
Oct 13, 2026 29
ጎንደር፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡-የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ከኢንተርፕረነር ሺፕ ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀምሯል።   የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል። ለዚህም የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተቋማት አዲሱን የስልጠናና ስርዓተ ትምህርት በተግባር በመተርጎም ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ወጣቱን ትውልድ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በዕውቀትና ክህሎት በማነጽ የስራ እድል ፈጣሪና ተጠቃሚ እንዲሆን የመምህራን የስራ ተነሳሽነትና ርብርብ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል። ፈጣን ሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ የሚቻለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ላይ አተኩሮ በመስራት መሆኑን ጠቁመው አስተዳደሩም ለዘርፉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።   የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮንን በበኩላቸው፤ ስልጠናው በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በጎንደር ቀጠና የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን ለማብቃት ያለመ ነው። ለ10 ቀናት በሚቆየው ስልጠናም ፖሊሲውን በማሳወቅ፣ ሙያን ወደ ቢዝነስ በመቀየር፣ በመደራጀት አብሮ የመስራት ስነ-ምግባርና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በማተኮር ይሰጣል ብለዋል። ስልጠናው የተግባቦት፣ የቡድን ስራ፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የችግር አፈታትና የውሳኔ ሰጪነት ክህሎቶችን ለማዳበር ያስችላል ያሉት ደግሞ ስልጠናውን በመስጠት ላይ የነበሩት አቶ ጌታቸው አለባቸው ናቸው። ከሰልጣኞቹ መካከል መምህር ባዬ ከበደ፤ ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ የአሰልጣኝነት ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተመሳሳይ ስልጠናዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሐሮማያ እና ሐዋሳ እየተሰጠ መሆኑም በዚሁ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡
 ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ተቋማዊ ብቃቱን ለማሳደግ በቅንጅት እየሰራ ነው 
Oct 13, 2026 43
ጅማ፣ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ተቋማዊ ብቃትና የተማሪዎች ክህሎት ለማሳደግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ከአፍሪካን ዲጂታል ኢኖቬሽን ኤንድ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ጋር በቴክኖሎጂ ልማት፣ በስልጠናና በሙያ ምክር አገልግሎት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ዛሬ ስምምነት አድርጓል።   ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመማር ማስተማርና ለምርምር ለማዋል አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዩች ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማስፋፋት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ነው። ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ብቁ ከማድረግ ባሻገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የተካኑ ዜጎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም አክለዋል። በተለይም በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለጥሩ ዓላማ የመጠቀም ልምድ እንዲዳብር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ስልጠናዎችን ተደራሽ የማድረግ ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።   የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ማዕከል ዳይሬክተር መሀመድ ሙንታዝ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ አካዳሚው በዩኒቨርሲቲው እየሰጠ ያለው ስልጠና በቀጣይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ለማሳደግ ጉልህ ሚና አለው። የአፍሪካን ዲጂታል ኢኖቬሽን ኤንድ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ሸጋው አናጋው በበኩላቸው፣ አካዳሚው ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቴክኖሎጂ ልማት፣ በስልጠናና በማማከር ላይ ለመስራት መስማማቱን ገልጸዋል።   ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመማር ማስተማርና ለምርምር በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማገዝ ያለመ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አበረታች ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋሙና ለዘርፉ የሚያግዝ ፖሊሲ መውጣቱ የቴክኖሎጂ ልማቱን ለማሳለጥ የሚያስችሉ አስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው ብለዋል። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
በሶማሌ ክልል የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ስራ እየተካሄደ ነው
Oct 12, 2026 277
ጅግጅጋ፣ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ስራ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ አስታወቁ። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በክልሉ ሶስተኛ የሆነውን ጅግጅጋ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማምሻውን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል ።   ርዕሰ መስተዳድሩ በሥነሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት መሶብ የአንድ ማዕከል ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎቶት ለመስጠት እያስቻለ ነው ። በዚህም በወረዳዎችና በከተማ አስተዳድሮች ማእከላቱን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ግዜና ወጪ ለመቀነስና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ሻፊ አህመድ በበኩላቸው በማዕከሉ 11 አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች በዲጂታል የታገዙ መሆናቸውን ጠቁመው በዚህም የህብረተሰቡ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት እንደሚያገኝ አስታውቀዋል።   ከዚሁ ጎን ለጎን በጅግጅጋ ከተማ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች በይፋ ስራ ጀምረዋል ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በሺር አህመድ በከተማው የተተከሉ የደህንነት ካሜራዎች የህዝቡን ጸጥታና ሠላም ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል። በተለይም ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ለሚከናወኑ ተግባራት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥሩና የፖሊስን ስራ የሚያዘምኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አስተማማኝ የሳይበር ምህዳር መገንባት ወሳኝ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Oct 12, 2026 106
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ዲጂታል ደኅንነት እና ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አስተማማኝ የሳይበር ምህዳር መገንባት ወሳኝ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ንቁ ዜጋ ደኅንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቅምት 01 እስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከበረውን ሰባተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር በይፋ አስጀምረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር በማፋጠን፣ የቴክኖሎጂ አቅሟን በማጠናከርና የዜጎችን ዲጂታል ደኅንነት እና ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ንቁ ዜጋ መፍጠርና አስተማማኝ የሳይበር ምህዳር መገንባት ወሳኝ ነው። በዘመናችን የቴክኖሎጂ እድገት የሀገራትን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ እድገት እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚወስን ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን አንስተዋል። ስለሆነም ኢትዮጵያም በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ መድረክ ተወዳዳሪ ለመሆን ለዘርፉ ስትራቴጂያዊ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ የጥልቅ ዳታ ትንተና፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ኳንተም ኮምፒውቲንግና ዘመናዊ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማቶች የዓለምን ኢኮኖሚና የአስተዳደር ሥርዓት እየቀየሩ መሆኑን ገልጸዋል። የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ የፈጠራ አቅምን ማሳደግና ፈጣን የመዋቅር ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።   የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ሀገሪቱን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሸጋገር ጠንካራ መሠረት መጣሉን ጠቅሰው፤ በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር እድገት፣ በቴሌኮም ዘርፍ የውድድር እድል መስፋፋት፣ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች መጎልበትና የመንግሥት አገልግሎቶችን በኦንላይን ማድረስ ረገድ የተገኙ ውጤቶች ለቀጣዩ ምዕራፍ መሠረት መሆናቸውን አንስተዋል። አሁን የሀገሪቷን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚወስነው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬታማ እንዲሆን አስተማማኝ የሳይበር ደኅንነት መኖር የግድ መሆኑን አስገንዝበዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ80 በመቶ በላይ የሳይበር ጥቃቶች ከሰዎች የግንዛቤ እጥረት፣ ከግዴለሽነትና ከስህተት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ይህም የሰው ልጅ ንቃተ ሕሊናና ዝግጁነት ከቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ጋር ተደምሮ የሳይበር ደኅንነት ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያመለክታል ብለዋል። በመሆኑም ዜጎች በስልካቸው፣ በኮምፒውተራቸውና በሥራ ቦታቸው የሚያደርጉት ጥንቃቄ ለሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል። መንግሥት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ውስጥ የሕፃናትን የኦንላይን ጥበቃ በማካተት ሀገራዊ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲዘረጋ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ተናግረዋል። በ2016 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በጸደቀው ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት ፖሊሲ የሕፃናትን የኦንላይን መብት የሚጠብቁና ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የሚያግዙ አቅጣጫዎች መካተታቸውን ገልጸዋል። ጠንካራ፣ አስተማማኝና ደኅንነቱ የተጠበቀ የሳይበር ምህዳር መገንባት የሁሉም ዜጋ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።   የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፤ የሳይበር ጥቃቶች መጠንና ውስብስብነት እየጨመረ በመምጣቱ በግለሰቦች፣ በተቋማትና በሀገራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል። በኢትዮጵያም በ2018 ዓ.ም ብቻ ከ71 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ሪፖርት መደረጋቸውን ገልጸዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሀገሪቱን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በአሠራር ሥርዓት ዘርፎች ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑም አስረድተዋል። በተለይም በቅርቡ የጸደቀው የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት አዋጅ ባንኮችን፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና የኃይል ተቋማትን ጨምሮ ወሳኝ ተቋማት የሚያጋጥሟቸውን የሳይበር ስጋቶች ለመከላከልና አገልግሎታቸው ሳይቋረጥ እንዲቀጥል የሚያስችል አቅም ለመገንባት የሚያግዝ ነው ብለዋል።        
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል
Oct 13, 2026 130
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከሩዋንዳ ጋር ያካሂዳል። ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይከናወናል። ሁለቱ ሀገራት መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም በኪጋሊ ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። የሩዋንዳዋ ኡዛዬሴንጋ ሊድያ በራሷ ላይ ግቡን አስቆጥራለች። ውጤቱን ተከትሎ በቻለው ለሜቻ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አስፍቷል። ሉሲዎቹ ከመጀመሪያው ጨዋታ መልስ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት ዝግጅቱን አድርጓል። ብሔራዊ ቡድኑ ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በድሬዳዋ ስታዲየም አከናውኗል። ቡድኑ በጥሩ ሞራል እና ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በአንድሬ ካሳ ሙቡንጎ የሚመራው የሩዋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምዱን ትናንት በድሬዳዋ ስታዲየም አድርጓል። ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፉ ሶስተኛውን ዙር የሚቀላቀሉ ሲሆን ከታንዛንያ እና ቦትስዋና አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ። በአምስት ዙሮች በሚካሄደው ማጣሪያ ሁለት ሀገራት አፍሪካን ወክለው በኦሊምፒክ ውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ። በአጠቃላይ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ 12 ሀገራት የሚሳተፉ ይሆናል።
ኮቨንተሪ ሲቲ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ድል አስመዘገበ
Oct 13, 2026 110
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኮቨንተሪ ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 4 ለ 1 ረትቷል። ትናንት ማምሻውን በኮቨንተሪ ቢውሊዲንግ ሶሳይቲ አሬና በተካሄደው ጨዋታ ሲዲኪ ቼሪፍ፣ ኤሊስ ሲምስ፣ ስቴፈን ሙፉኒ እና ጃክ ሩዶኒ (ፍጹም ቅጣት ምት) የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ስቬን ቦትማን ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በጨዋታው ኒውካስትል ብልጫ ወስዶ ቢጫወትም ኮቨንተሪ ሲቲ የግብ እድሎችን በሚገባ በመጠቀም የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል። በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በስድስት ነጥብ ደረጃውን ከ19ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ጨዋታውን ተከትሎ ስድስተኛ ሳምንት ተጠናቋል። የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል
Oct 13, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ (League Phase) ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ምሽት አራት ሰዓት ላይ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም የፈረንሳዩን ክለብ ሊል ያስተናግዳል። የባለፈው የውድድር ዓመት የፍጻሜ ተፈላሚ አርሰናል በመጀመሪያ ጨዋታው ናፖሊን 1 ለ 0 አሸንፏል። ተጋጣሚው ሊል በበኩሉ በሪያል ቤቲስ የ3 ለ 2 ሽንፈት አስተናግዷል። ባለሜዳው አርሰናል ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። በሌላኛው መርሐ ግብር አትሌቲኮ ማድሪድ ከማንችስተር ዩናይትድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ይጫወታሉ። አትሌቲኮ ማድሪድ በመጀመሪያ ጨዋታው በሊቨርፑል የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዷል። ማንችስተር ዩናይትድ የአዘርባጃኑን ሳባህን 4 ለ 0 ረትቷል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። ጋላታሳራይ ከባርሴሎና ምሽት አራት ሰዓት ላይ በራምስ ፓርክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በመጀመሪያ መርሐ ግብር ጋላታሳራይ በስፖርቲንግ ሊዝበን የ3 ለ 1 ሽንፈት ሲቀምስ ባርሴሎና ፌይኖርድን 5 ለ 1 አሸንፏል። የኖርዌይ ቫይኪንግ ባየር ሙኒክን ምሽት አራት ሰዓት ላይ በላይስ አሬና ያስተናግዳል። ቫይኪንግ በመጀመሪያ ጨዋታው በስቱትጋርት 3 ለ 1 ተሸንፏል። ተጋጣሚው ባየር ሙኒክ የኖርዌውን ቦዶ ግሊምት 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፉ አይዘነጋም። የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ባየር ሙኒክ በሁለተኛው ጨዋታ ሌላኛውን የኖርዌይ ክለብ ይገጥማል። ኢንተር ሚላን ከክለብ ብሩዥ፣ ቪያሪያል ከናፖሊ እና አርቢ ላይፕዚግ ከፒኤስቪ አይንድሆቨን በተመሳሳይ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ሌንስ ከስፖርቲንግ ሊዝበንና ሳባህ ከስላቪያ ፕራግ በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የብሩንዲ አቻውን አሸነፈ
Oct 12, 2026 136
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ብሩንዲን 3 ለ 0 ረትቷል። ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘሚካኤል ምንያህል፣ አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ እድሉን አስፍቷል። ብሔራዊ ቡድኑን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ ከዩጋንዳ ጋር ያከናውናል። በምድቡ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የብሩንዲ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከማጣሪያው ተሰናብቷል። ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ከምድቡ አንደኛ መውጣት ወይም ከሶስቱ ምድቦች ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ። 17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው
Oct 13, 2026 112
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው ብለዋል።   ‎ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ሲሉም ገልጸዋል። ‎‎እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነውም ብለዋል።   በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለመተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል ሲሉም ገልጸዋል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው
Oct 12, 2026 94
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2 /2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኗን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከ192 አባል ሀገራት የመጡ ሳይንቲስቶች፣ ውሳኔ ሰጪዎች፣ የሚቲዎሮሎጂ ባለሙያዎች እና የዘርፉ ተመራማሪዎች የተገኙበትንና ከጥቅምት 2 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን ዓለም አቀፍ ፎረም ማካሄድ ጀምሯል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የአረንጓዴ ኢኮኖሚ አቅም እየገነባች ነው። በዚህም መንግሥት የአየር ንብረት ተለዋዋጭነትን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመተግበር የታዳሽ ኃይል ምንጮችን እያስፋፋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉንም አመልክተዋል። የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መንግሥታት አቀፍ ባለሙያዎች ፓናል ሰባተኛው የግምገማ ሪፖርት ውስጥ ለፖሊሲ አውጪዎች ተግባራዊ መፍትሔዎች እንዲቀርቡ፣ በታዳጊ ሀገራት ያሉ የመረጃ ክፍተቶች እንዲሞሉና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን በትክክል ለመለየት እንዲረዳ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የሙቀት መጨመርና የዝናብ ሁኔታ መለዋወጥ እየተባባሱ ነው ብለዋል።   አህጉሪቱ ለዓለም አቀፍ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀት ያላት አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ግን ከፍተኛ ተጋላጭ መሆኗን አስረድተዋል። ለዚህም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን፣ የአየር ንብረት መረጃ አገልግሎቶችን፣ የምልከታ መረቦችንና የምርምር አቅሞችን ማሳደግ የሕብረተሰቡን ሕይወት ለመታደግና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በኢንስቲትዩቱ አማካይነት የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ምልከታ መረቦችን በማስፋፋት፣ የትንበያ አገልግሎቶችን በማሻሻል እንዲሁም የአየር ንብረት ምርምርን በመደገፍ ለቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮች የላቀ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ጠቁመዋል። የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መንግሥታት አቀፍ ባለሙያዎች ፓናል ሪፖርቶች ለመንግሥታት፣ ለተመራማሪዎችና ለልማት አጋሮች የአየር ንብረት ስጋቶችን በትክክል ለመረዳትና ውጤታማ ምላሾችን ለማዘጋጀት ጠቃሚ መሠረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል። በሰባተኛው የግምገማ ዙር የሚካሄዱ ውይይቶች ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለፖሊሲ አውጪዎችና ለማኅበረሰቡ የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዙ ተናግረዋል።  
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ ነው
Oct 9, 2026 264
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት ገለጸ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች የተራቆቱ መሬቶችን በማገገም ጉልህ ፋይዳ እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩም የግብርና ምርታማነትን በማገዝ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያስገኘ ዓለም አቀፍ ተነሳሽነት ነው።   በኢትዮጵያ ደን ልማት የተፈጥሮ ደን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ካብታሙ ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ደን የአካባቢ መራቆትና የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በመጠበቅ ለግብርና ምርታማነት ጉልህ ጠቀሜታ አለው። የደን ሽፋን ዕድገትም አየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ብርቅዬ እንስሳትና የብዝኅ ሕይወት ደኅንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለደን ልማት የሰጠው ትኩረት የአካባቢ ተጽዕኖ ውጤታማነትን በማሻሻል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ዜጎች በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ተያያዥ የልማት መስኮች የሚሰማሩበትን ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራም 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረውን ደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉን አስታውሰዋል።   የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን ጥበቃ ውጤታማነትን በማላቅ የተስተካከለ ሥነ-ምኅዳርና የብዝኅ ሕይወት እንዲፈጠር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተለይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እፅዋት ልማትን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት እየጣለ መሆኑን አብራርተዋል። የህብረተሰቡን የደን ጥበቃና እንክብካቤ ባህል በማሻሻል የደን አስተዳደር ሥርዓት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ደን ልማትም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ፣ የደን ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና እንዲለማ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። በተጨማሪም የደን ውጤቶች ምርታማነትን በማሻሻል የደን ሀብት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነትን በማላቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሆኗል
Oct 7, 2026 242
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት አርዓያ የሆነ ታላቅ ተግባር መሆኑን የዘርፉ ሙያተኞች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይን አንግባ በትኩረት እየሰራችባቸው ከሚገኙ ውጤታማ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል አረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን ለመከላከል፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት በአርንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ተክላለች። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 56 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ መሬቶችን አረንጓዴ ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም ይህ መርሀ ግብር የመሬት መሸርሸርን እንዲቀንስ፣ ስነ ምህዳራን መጠበቅ እንዳስቻለም መግለጻቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት የደን ፎረም ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ዶክተር ጁሊያት ቢያኦ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የደን ሽፋንን ለመጨመር የሚከናወኑ ተግባራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱም ገልጸዋል። የደን መራቆትን ለመቅረፍና የመሬት ገጽታ ለመጠበቅ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የዘርፉን ተዋንያን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ነድፎ ባለፉት ዓመታት በመተግበር የአረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ያከናወነው ተግባር ውጤት ማስመዝገቡንም አክለዋል።   የአፍሪካ የደን ፎረም የደን ተመራማሪ የሆኑት ዶሪስ ሙታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአካባቢ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያከናወነቻቸው ውጤታማ ተግባራት ከደን ሽፋን መመናመን ጋር ተያይዞ የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን በመከላከል በኩል ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት በዘርፉ በትኩረት ከተሰራ ታሪክ መቀየር እንደሚቻል ለዓለም ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል። እንደ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አይነት ፕሮጀክት ነድፎ መተግበር ፋይዳው አካባቢን በደን ከመሸፈን በላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በመሆኑም መሰል ምሳሌ የሚሆን ተግባር ሰዎች በምቹ ስነ ምህዳር እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥርና ምርታማነትን የሚያሳድግ አርዓያነት ያለው ተግባር እንደሆነም ነው ዶሪስ ሙታ ( ዶ/ር) የገለጹት።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አይኤምኤፍ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልግ ገለጸ
Oct 13, 2026 91
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ ማስፋት እንደሚፈልግ አስታወቀ። የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከስብሰባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የፊሲካል ጉዳዮች ክፍል እና ከገንዘብና ካፒታል ገበያዎች የስራ ክፍል ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርጓል።   ከአይኤምፊ ፊስካል ጉዳዮች ዘርፍ ጋር በተካሄደው ውይይት፣ ለገንዘብ ሚኒስቴር በሚደረጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ድርጅቱ ለሚኒስቴሩ እየሰጠ የሚገኘውን የቴክኒክ ድጋፍ አፈጻጸም ተገምግሟል። በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሪፎርም አጀንዳዎች መሠረት በቀጣይ ተጨማሪ ድጋፍ የሚደረግባቸውን ዕድሎችና የትብብር መስኮች ላይ ምክክር ተደርጓል። በተያያዘም፣ ከተቋሙ የገንዘብና ካፒታል ገበያዎች የስራ ክፍል ጋር በተካሄደው ውይይት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ድጋፎች ላይ ያተኮረ ነው። ውይይቱ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኩል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እየተደረገ ያለውን የቴክኒክ ድጋፍ ያካተተ ነው። የተቋሙን የማስፈጸም አቅም የበለጠ ለማጠናከርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጀመረውን የሪፎርም አጀንዳ ለማጠናከር የሚያስችሉ ተጨማሪ የድጋፍ መስኮችን የመለየት ሥራ ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ ከስብሰባው ጎን ለጎን የተለያዩ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ  
Sep 21, 2026 1151
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1175
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 1074
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሐተታዎች
የጣና ፎረም ሂደቱና ውጤቱ
Oct 12, 2026 176
የጣና ፎረም ሂደቱና ውጤቱ ምን ይመስላል? የአፍሪካ መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራንና ሌሎችንም በአንድ መድረክ በማሰባሰብ እንዲመክሩ በማሰብ የተቋቋመው ጣና ፎረም ለአህጉራዊ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሁም ለጠንካራ የትብብር ግንኙነት ወሳኝ መድረክ ሆኗል። በዚህም የጣና ፎረም ላለፉት አስራ አንድ ተከታታይ አመታት ተካሂዶ ዘንድሮም 12ኛው መድረክ በውቢቷ ባህር ዳር ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል። በአፍሪካ ግጭትን መከላከል፣ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ ማበጀት ላይ የሚያተኩረው መድረክ አፍሪካ ችግሮቿን በራሷ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ለተግባራዊነቱ ለመትጋት የሚያስችል ነው። በመሆኑም በየአመቱ የሚካሄደው የጣና ፎረም ዓላማ በአፍሪካ የሰላም ፖሊሲዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ የአህጉሪቱን ድምፅ ማጠናከር፣ የክልላዊ ትብብርን ማሳደግና የሚነሱ ሀሳቦች ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ይሆናል። በዚሁ መሰረትም የዘንድሮው የጣና ፎረም “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፡ የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” የሚል መሪ ሃሳብ በማንገብ በጣና ሀይቅ ዳርቻ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። ከ250 በላይ እንግዶች በሚታደሙበት ፎረም ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የተቋማት ሃላፊዎች፣ የቀድሞ መሪዎች የሚገኙ ሲሆን ለጉባኤው መሳካትም ኢትዮጵያ የተሟላ ዝግጅት ማድረጓ ታውቋል። በአህጉሪቷ የሚስተዋሉ ግጭቶችን መከላከል፣ ሰላምና ደኅንነትም ማስጠበቅ እንዲሁም ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነትን ማጠናከር ይሆናል። በተለይም በአገራት መካከል በቀጥታ፣ በግልጽና በጥልቀት የውይይት አውዶችን በማስፋት በጋራ መስራትን የሚያበረታታ ነው። በፎረሙ ላይ የሚነሱ ጥልቅ ትንታኔዎችና የተለያዩ ምክረ ሐሳቦች ለፖሊሲ ግብአት፣ ለተቋማዊ ለውጥና ለተግባት ተኮር እንቅስቃሴዎች ጉልህ ፋይዳ የሚኖረው መሆኑ ይታመናል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ የሰላም፣ የደኅንነትና የፖለቲካ መድረኮች ላይ በሚኖራት ተሳትፎ የተደራጀና የተቀናጀ አቋም በመያዝ ለመቅረብ ጣና ፎረም ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የጣና ፎረም የግጭት መፍትሔ አስፈጻሚ ተቋም ባይሆንም፣ ውሳኔ ሰጪዎች አዲስ አቅጣጫ እንዲያዩ፣ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጥሩና ለቀጣይ እርምጃዎች መሠረት እንዲያኖሩ የሚያግዝ መሆኑም ይታመናል። የጣና ፎረም ያለፉት 11 መድርኮች የአፍሪካ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በመምከር የመፍትሄ አመላካች ሃሳቦች የሚነሱበት ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። በመድረኮቹ ከአፍሪካ የውስጥ ግጭቶችና የሰላም ግንባታ እስከ ክልላዊ ትብብር፣ የዓለም የኃይል ሚዛን፣ የኢኮኖሚ ልማትና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጥቅሞችና ተፅእኖዎቻቸው ላይ የጋራ ግንዛቤ የመያዝ እድል ተፈጥሯል። የሰላምን ጉዳይ ከፖለቲካ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከአስተዳደርና ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ጋር አስተሳስሮ በማየት የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተመላክተውበታል። የ11ኛው ጣና ፎረም፣ “አፍሪካ በለውጥ ላይ ባለ የዓለም ሥርዓት” (Africa in an Evolving Global Order) በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የአገራት መሪዎች፣ ቀድሞ መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችና ሌሎችም ታድመውበት በስኬት ተከናውኗል። በፎረሙ ከተነሱት አበይት ጉዳዮች መካከልም በአፍሪካ ሕብረት፣ በኢጋድ እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል የሰላምና ደኅንነት ቅንጅትን የማጠናከር። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማምጣት እንዲሁም እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥና የዘመኑ ክስተትና በፍጥነት እየደገ የመጣው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ያተኮረ ነበር። በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪና በኃይል ልማትና ቀጣናዊ ትስስርን በተመለከተም በስፋት ተመክሮበታል። በመሆኑም የጣና ፎረም የውይይትና የፖሊሲ ሐሳቦች ማፍለቂያ እንዲሁም የምክረ ሐሳብና መፍትሄዎች ማመላከቻ መድርክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የአፍሪካ መሪዎች፣ ምሁራን፣ ዲፕሎማቶችና የተለያዩ የፖለቲካና ማህበራዊ እንዲሁም የንግድ ተቋማት ተወካዮች የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮችን በቀጥታ የሚወያዩበት የተለመደ መድረክም ሆኗል። የፎረሙ ዋና ስኬትም በአህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ የታዩ መሻሻሎች፣ የተፈቱ ችግሮችና የተተገበሩ ፖሊሲዎችን መጥቀስ ይቻላል።   በ2026 ከጥቅምት 23 እስከ 25 በባሕር ዳር የሚካሄደው 12ኛው ጣና ፎረም፣ “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፡ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል። የዘንድሮው መሪ ሃሳብ የሚያመለክተውም ለዘላቂ ሰላም የኢኮኖሚያዊ ልእልና ፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የኢንዱስትሪ አቅምና ሌሎችንም ያካተተ ነው። ከፎረሙ የሚጠበቁ አበይት ነጥቦች መካከልም አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷንና የዲጂታል አቅሟን ለራሷ ልማትና ለዜጎቿ ጥቅም እንዴት ማዋል ትችላለች? የዓለም የኃይል ሚዛን እየተቀያየረ ባለበት ሁኔታ አፍሪካ የጋራ ፍላጎቷን እንዴት ማስጠበቅ ትችላለች? የሥራ ዕድል፣ የኢንዱስትሪ እድገት፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደትን በተመለከተ የሚነሱ ጣቀሚ ሃሳቦች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የአገራት የንግድ፣ የመሠረተ ልማት፣ የሃይል ልማት ትስስርን ማጠናከርም ሌላው ትኩረት ይሆናል።  
‎ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር፤ የመደመር መንግሥት የማድረግ አቅም ማሳያ
Oct 10, 2026 425
በመንግሥቱ ዘውዴ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ ካሏት ጸጋዎች መካከል የምድር ውስጥ ሃብቶች ይገኙበታል። ሃብቶቹ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብዓት ናቸው። እጅግ የበለጸጉ የጂኦሎጂካል ማዕድናት ሀብት ያላት ኢትዮጵያ የማዕድን ሃብት በብዝኅ ኢኮኖሚ መርህ የዕድገት ሽግግርን የሚያፋጥን መሰረት እየጣለ ይገኛል። ኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ ለኢንዱስትሪና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ በጥሬ ዕቃ ግብዓትነት የሚውሉ ውድና የከበሩ እንደ ታንታለም፣ ፖታሽና ሌሎች ማዕድናት በጉያዋ የታቀፈች ምድር ናት። ማዕድናት ለሥራ ዕድል ፈጠራም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም። በመደመር መንግሥት አምስት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች መካከል የማዕድን ዘርፍ አንዱ እንዲሆን አድርጓል። ይህም የኢትዮጵያን የምድር ውስጥ እምቅ ሀብቶች ለኢኮኖሚ ዕድገት ማዋል እንደሚቻል ግልጸኝነትን የፈጠረ ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህም ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ያሉ ሀብቶችን በማልማት፣ እሴት ጨምሮ በማምረትና ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት በኩል አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፤ ሀብቶቻችንን ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር የወጪ ንግድ ገቢንና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት የመደመር መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። የዚህ ሀገራዊ ጥረት አንድ አካል የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ሥራ የጀመረው የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም የመደመር መንግሥት እምቅ የሀገር ሀብቶችን ለይቶ፣ አልምቶና አምርቶ ለውጤት ማብቃቱ አይነተኛ ምሳሌ ይሆናል። ይህ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት የተቋቋሙ የመደመር መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በጋራ በመሥራት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያል። የማዕድን ሀብቶችን በማልማትና እሴት ጨምሮ በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገበውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ዕድገትም ሁነኛ አብነት ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም አለው። ፋብሪካው በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት በመጨመርና የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በማጠናከር በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ኢትዮጵያን ቀጣናዊ ማዕከል የሚያደርግ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል። ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ በኢትዮጵያ የላቀ የእሴት ሰንሰለት እየፈጠረ ይገኛል። ይህ ፋብሪካም በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ተጨባጭ የልማት ውጤት መሆኑ እሙን ነው። የመደመር መንግሥት ኢንዱስትሪ ምርታማነትን ከማስፋፋት ባሻገር የማምረት አቅማቸው እንዲጎለብት የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል። የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ እየሆነ መጥቷል። በተለይም የወርቅ ማዕድን ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ቀጥሏል። ይህ ሀገራዊ ተነሳሽነት ሀብቶችን ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅምና ከዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንደሚያሳይም ያመላክታል። የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካውም የወርቅ ጥራትን በማስጠበቅ ለማንጠርና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደሆኑ ንጹሕ ምርት በመቀየር የጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ሁነኛ አቅም ይሆናል። የመደመር መንግሥትም ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በጥሬው ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የያዘውን ትክክለኛ የልማት አቅጣጫ ተጨባጭ ያደርገዋል። ፋብሪካውም ኢትዮጵያ በሀብቶቿ ላይ እሴት ጨምራ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ በያዘችው የኢኮኖሚ አቅጣጫ መሰረት የተገነባው ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ግልጽና ትልቅ ርዕይ ማንገቡን ያመላክታል። በተለይም ለማዕድን ልማትና ዕድገት የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የተመዘገበውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይህ ውጤታማ ተግባር በሌሎች ዘርፎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል። ትልቅ ሕዝብ ይዛ፣ ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያም የተፈጥሮ ሀብቶቿን በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪ በማልማት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ መሰረት እየጣለች ይገኛል። የብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመርም ሃብትን በጥሬው ከመሸጥ ወደ እሴት ጨምሮ ማምረት ከዚያም ከሀብት ወደ ምርት፣ ከምርት ወደ ውጭ ንግድ ተወዳዳሪነት የሚያሸጋግር ጉልህ እርምጃ ነው። በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠረውን ዕድል በማስፋት ማዕድንን ጨምሮ የብዝኅ ኢኮኖሚ አዕማዶችን በማሳደግ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢንና የሀገርን የምርት አቅም ማጠናከር የዚህ ርዕይ ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው። በርግጥም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገርነትን ከትልቅ ሕዝብ፣ ጸጋዎችን ከልማት በማሰናሰል አቅምን ወደ ውጤትና ርዕይንም ወደ ተጨባጭ የብልፅግና መሰረት እየቀየረች ይገኛል።  
የህብረ ብሔራዊነት ማህተም
Oct 10, 2026 272
በብዙ ድል ታጅቦ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ እንደ ዓይን ብሌን በስስት ከሚጠበቁ የሀገር ካስማዎች መካከል ሰንደቅ ዓላማ አንዱና ዋነኛው ነው። አይነኬ የሀገር ምልክትም ነው፤ ሰንደቅ ዓላማ። ለሀገር ምልክት የማይከፈል ዋጋ የለም። የሀገር መከላከያና ሌሎች የጸጥታ አካላት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የደረሰ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁለት፤ የሀገር ምልክት የሆኑ አትሌቶችም ደከመኝ ሳይሉ፣ ሳይታክቱና ሕመማቸውን ዋጥ አድርገው በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉለት ነው ሰንደቅ ዓላማ። ሁሉም በየመስኩ ደፋ ቀና የሚልለት የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓሉን አስመልክቶ እንደገለጸው፣ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት፣ በሀገራዊ አንድነትና በሕብረ ብሔራዊ መግባባት የሚፈጥሩበት ሀገራዊ በዓል ነው። ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና አርማ ነው። ሰንደቅ ዓላማ ለኢትዮጵያውያን የጽናታቸው፣ የሕብረታቸው፣ የሕልውናቸውና የሉዓላዊነታቸው ምልክት ነው። ሁለመናቸው ለሆነው ለዚህ ሰንደቅ ዓላማ ጸንቶ መዝለቅ ኢትዮጵያውያን የሚሰስቱት አንዳች ነገር የላቸውም። ታሪክ የሚነግረንም ይህንኑ ሀቅ ነው። የሀገር ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነት፣ የነጻነት፣ የሕዝቦች አንድነትና የክብር ምልክትም ጭምር ነው። ሰንደቅ ዓላማ የትውልዶች ታሪክ፣ የማንነት መገለጫ እንዲሁም የሀገር ሕልውና ምሰሶ መሆኑን የሚያረጋግጡ በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳስታወቀው፣ 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሐሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ይህ በምክር ቤቱ መሪነት የሚከበረው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቷ ወቅታዊ ሀገራዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ፣ በድምቀትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከበራል። ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በበርካታ ሀገራዊ ድሎችና ውጤቶች የታጀበ ነው። ከእነዚህ ሀገራዊ ድሎች መካከል ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት አጠናቃ አዲሱን የመደመር መንግሥት መመሥረቷ የመጀመሪያው ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው በአሳታፊነትና በአካታችነት ሂደት በስኬት የተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ነው። ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጸንቶ መቆየት በየትውልዱ ዜጎች የሕይወት መስዋዕትነትን ጨምሮ ውድ ዋጋ ከፍለዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ይህንን የሉዓላዊነት ምልክት ሳያጎድፉ፣ የሀገርን ዳር ድንበር ሳያስደፍሩና ነጻነትን አስከብረው ለዛሬው ትውልድ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ቀደምት የሀገር አለኝታዎች የከፈሉት መስዋዕትነት ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው። የመከላከያ ሠራዊት ለሰንደቅ ዓላማው ጸንቶ መቆም ሲባል ሕይወቱን፣ ደሙንና አካሉን የገበረ የሀገር አለኝታ ስለመሆኑ ምስክር አያሻም። ለዚህ ነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀኑን አከባበር ሂደት በተመለከተ ባስታወቀበት መልዕክቱ፣ ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበርና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩትን ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ሲል ያስገነዘበው። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተከበረበት ወቅት፣ “የሰንደቅ ዓላማ ቀን ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ፍቅርና አንድነትን የሚያድሱበት፣ የነገ ተስፋቸውን የሚያጸኑበት ነው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ የሉዓላዊነት መገለጫ ማኅተም ነው” ሲሉ መግለጻቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ እስከ መስዋዕትነት የደረሰ ዝግጁነት ያላቸውን ቀናኢነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብዙ ሀገራዊ ድሎችና ተስፋዎች ታጅቦ ነው። ኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ባስመዘገበችበት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ውጤታማ በሆነችበትና የጀመረችውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ባጠናቀቀችበት ወቅት የሚከበር ልዩ ቀን ነው። በተጨማሪም ሀገራችን በውጭም ሆነ በውስጥ የገጠሟትን ፈተናዎች በዲፕሎማሲያዊ መንገድና በአይበገሬነት መንፈሷ በጽናት እየመከተችና ውጤት እያስመዘገበች ባለችበት፣ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግልጽ፣ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በስኬት በማካሄድ አዲሱን የመደመር መንግሥት በመሠረተችበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ደግሞ እጅግ ልዩ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቿን “የባንዲራ ፕሮጀክቶች” በማለት ሰይማለች። ለዚህ ምክንያቱ፣ ሰንደቅ ዓላማ የሀገር መለያ እንደሆነው ሁሉ፣ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችም ሀገራዊ ውክልና ያላቸውና የክብር ምልክት በመሆናቸው የሀገሪቱን ታላቅነት፣ ዕድገትና የወደፊት ርዕይ ለዓለም የሚያሳዩ የልማት ውክልናዎች ናቸው። አንድ ሀገር ከነደፈቻቸው ዘመን ተሻጋሪ የልማት ዕቅዶች መካከል ግንባር ቀደም ሆነው የሚተገበሩ፣ ለሌሎች ፕሮጀክቶች አቅጣጫ የሚያሳዩና ስኬታቸው ለሌሎች መንገድ ጠራጊ የሚሆኑትም በመሆናቸው ጭምር ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ በጀት፣ ሰፊ ሽፋንና የብዙ ዜጎችን ሕይወት የመቀየር አቅም ያላቸው በመሆናቸው፣ የስኬታማነታቸው ውጤት በጠቅላላው ሀገራዊ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥራል። በባሕር ላይ ዋናዋ መርከብ ትኩረት እንደምትስበው ሁሉ፣ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን መሪዎች፣ የመገናኛ ብዙኃንንና የሕዝቡን ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡና ቅድሚያ የሚሰጠው የሀብት ድልድል የሚደረግላቸው ናቸው። ለዚህም ነው በዜጎችም ሆነ በመንግሥት ልዩ ጥበቃና ክትትል የሚደረግላቸው። ለአብነት ያህል፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች የሀገርን የልማት ቁርጠኝነት፣ አቅምና ርዕይ ለዓለም የሚገልጹ ናቸው። በሀገሪቱ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል በዜጎችም ሆነ በመንግሥት ተሳትፎና ትኩረት የሚስቡ በመሆናቸው “የባንዲራ ፕሮጀክት” ተብለው ይጠራሉ። የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምሳሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር የነጻነት ምልክት ነው። ይህ ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምሳሌ ሆኖ እንዲወሳ ያደረገው የመከላከያ ሠራዊቱና የሕዝቡ የጋራ ተጋድሎ ነው። በዓድዋ ጦርነት ወቅት በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጀውን ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት በመመከት፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በነጻነት እንዲያውለበልብ የተደረገው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጀግኖች በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር ነው። ይህ የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምልክት የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠብቆ እዚህ ደርሷል፤ ይኸው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ወደፊትም ይቀጥላል። ሀገር በውጭ ወራሪዎች በተፈተነችባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ፣ ሠራዊቱ የሰንደቅ ዓላማዋን ክብር ለማስጠበቅ ግንባሩን ለጥይት መስጠቱን አላቆመም። የሀገርን ድንበር ጥሶ ለመግባት የሚሞክር ወራሪ ኃይልን በመመከት፣ የሉዓላዊነት ምልክት የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለሚያደርግ ሠራዊት ጽናትና ለሀገር ያለውን ጽኑ ፍቅር በግልጽ ይጠቁማል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለዘለዓለም በነጻነት ከፍ ብላ የምትውለበለበው በጀግኖች የመከላከያ ሠራዊት ውድ ዋጋና መስዋዕትነት ነው። ሠራዊቱ ለሰንደቅ ዓላማው መጽናት የከፈለውና እየከፈለው ያለው መስዋዕትነት የሀገርን ሕልውና የማስቀጠል፣ የሕዝቦችን ሰላም የማረጋገጥና ታሪካዊ ክብሯን የመጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ አደራ ስላለበት ጭምር ነው። ይህንን መስዋዕትነት ማወቅ፣ ማክበርና ለሠራዊቱ የሚገባውን ምስጋና መስጠት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።  
የሴቶች አካታችነት ምኅዳር መስፋት፤ ኢትዮጵያን የመገንባት ፍኖት
Oct 10, 2026 182
በየጸዳወርቅ ታደለ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ርህራሔ፣ ጥንካሬ፣ ሕይወት፣ ፍቅርና ውበት የሀገርና ሴት መገለጫዎች ናቸው። በቋንቋ፣ በስያሜ፣ በታሪክና በተግባር ሲታዩ ሀገር እና ሴት አንድ የሚያደርጋቸውን ተመሳስሎሽ ያሳያሉ። ሴት የሕይወት መሠረት፣ የቤት ማዕዘንና የትውልድ አርበኛ ናት። ሴት ልጅ የተቸራት ሁለገብ ሙያ፣ ዕውቀት፣ ብልሃትና ብቃት የሀገር ግንባታ ድርሻዋን ጉልህ ያደርገዋል። ሀገር ስትጠራም በእናት ትመሰላለች። ይህ ስያሜ አባባል ብቻ አይደለም። የእናትነትን ታላቅ ባሕርይ ለሀገር የመስጠት ጥልቅ ፍቅር ነው። አንዲት ሴት ልጅን በእቅፏ እንደምታሳድግ ሁሉ፣ ሀገርም ዜጎቿን አስጠልላ የምታሳድግ ግዙፍ ጥላ ናት። ለዚህም ነው ሁለቱም የመጠለያና የደህንነት ተምሳሌቶች ናቸው የሚባሉት። ይህ ተፈጥሯዊ ሁኔታ ሴቶች በተሰማሩበት መስክ ስኬታማነታቸው የላቀ እንደሚሆኑ ያሳያል። ሴቶች ከቤታቸው አልፈው በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። ለምሳሌ እርስ በርስ በመረዳዳት፣ በባህላዊ እሴቶችና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ሚና በመወጣት የሕብረተሰብ መስተጋብር ገመድ ናቸው። በኢኮኖሚ መስክም ለሀገር የልማት መርሃ ግብሮች ስኬት ከፍተኛ ዐሻራ አላቸው። የኢትዮጵያ ሴቶችም የርኅራሔ፣ የአብሮነት መሠረትና የትውልድ ግንባታ ተምሳሌት ናቸው። ጀግንነትም የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ነጻነት በማስከበር ሂደት በተግባር ተፈትሎ የሚያልፍበት መገለጫቸው ነው። ለዚህም ከዓድዋ ድል የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ሂደት ዐሻራቸው ሕያው ነው። ዛሬም የመደመር መንግሥት ሴቶችን በከፍተኛ የመንግሥት አመራርና በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ፣ ያላቸውን ብቃትና አቅም ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ለውጥ በማዋል የሴቶችን ሚና የበለጠ የሚያጎለብት ምኅዳር ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ የወለደው የመደመር መንግሥት፣ ሴቶች ብቃታቸውን፣ ክህሎታቸውንና ተሰጧቸውን ለሀገር ግንባታ የሚያውሉበትን አስቻይ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምኅዳር ፈጥሯል። የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማጎልበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። ይህም በትምህርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በተቋም ግንባታና በውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች ላይ ሴቶች የማድረግ አቅማቸውን ማስመስከር ያስቻሉ ተግባራዊ ለውጦች እንዲመዘገቡ አድርጓል። በተለይም የመደመር መንግሥት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማጎልበት የፈጠረው ልምምድ አሳታፊና አካታች ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁልፍ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አጀንዳነት የተያዘ ነው። እነዚህና መሰል ተግባራትም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምኅዳር እየፈጠረች መሆኗን ያመላክታሉ። የመደመር መንግሥት በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች የካቢኔ አወቃቀር ለሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ድርሻ መስጠቱ ሁለገብ ሙያዊ ክህሎታቸውን ለሀገር ግንባታ እንዲያውሉ እያስቻለ ይገኛል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት በተዋቀረው አዲሱ ካቢኔ ውስጥ ከ22 የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ውስጥ 9 ሴቶች ሹመት አግኝተዋል። ይህም ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካትና የሕዝብ አደራ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አካታች ሥርዓት የመገንባት መሰረት ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካቀረቧቸው 22 ዕጩዎች ሚኒስትሮች መካከል ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር፣ ሃና አርአያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ያስሚን ወሃብረቢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር፣ ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር፣ ዓይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር እና ሰላማዊት ካሳ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በማድረግ ሹመት ሰጥቷል። እንዲሁም ዓለምጸሃይ ጳውሎስ የማዕድን ሚኒስትር፣ ሻዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሲያደርጉ ሹመቱን ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ሚኒስትሮቹም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ሕዝባዊ አደራና ኃላፊነት ተረክበዋል። ይህም ሴቶችን ከማሳተፍ በላይ የተሻገረ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም የመደመር መንግሥት አሳታፊና አካታችነት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ማጠናከሩን የሚያሳይና እጅግ የሚያኮራ ውሳኔ መሆኑን አንስተዋል። በካቢኔ አወቃቀር ውስጥ በርካታ ሴቶች መካተታቸው ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ሀገራት ጭምር ተምሳሌት መሆኑን ነው ያመለከቱት። ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ በፓርላማ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድና በከንቲባነት ጭምር ሴቶችን በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመሾም አህጉራዊና ዓለም አቀፍ አርዓያነቷን ማሳየቷንም አስታውሰዋል። በቀጣይም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚሠራ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ የሴቶችን የመፈጸም አቅምና ብቃት ለማረጋገጥ ብሎም ተጨማሪ ዕድል ለመስጠት የመደመር መንግሥት ዝግጁ ነው። የመደመር መንግሥት አካታች የዲሞክራሲ ሥርዓትን መገንባት ብቻ ሳይሆን እውን ማድረግ እንደቻለ ምስክር የሚሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ሴቶችን በማብቃት፣ በማካተትና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የተወሰዱ ትልልቅ ውሳኔዎችና ስኬታማ ሥራዎች በመደመር መንግሥት የተጀመሩ ዛሬም ወደፊትም የሚቀጥሉ ናቸው። ሴቶች የበለጸገች ኢትዮጵያን በመቅረጽ ሂደት ውስጥ ያላቸው አበርክቶ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በእርግጥም ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ለሰነቀችው ኢትዮጵያ የሁሉንም ዜጎች አቅም፣ ዕውቀትና ተሰጥኦ ለሀገር ግንባታ ማሰለፍ ማለት ነው። ከዓድዋ ድል የነፃነት ተጋድሎ እስከ ዛሬው የልማትና የለውጥ ጉዞ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ያስመዘገቡት ጀግንነትና ሁለገብ ብቃት ለዚህ ታላቅ ርዕይ ወሳኝ መሰረት ነው። የመደመር መንግሥት ሴቶችን በከፍተኛ አመራርና ውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ የጀመረው እመርታም ይህንኑ አቅም ወደ ሀገራዊ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል አካታች ምኅዳር ፈጥሯል። ስለሆነም ሴቶች በእኩልነት፣ በብቃትና በኃላፊነት የሚሳተፉባት፣ የሁሉንም ዜጎቿን አቅም የምታሰልፍና የጋራ ብልፅግናን የምታረጋግጥ ኢትዮጵያን መገንባት የዘመኑ ታሪካዊ ዐሻራ ነው። ትልቅ ሀገር የምትገነባው በትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይዋንም ወደ እውነት የምትቀይረው የሁሉንም ዜጎች አቅም በማካተት ነው።  
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ታላቅ የልማት ጉዞ ላይ ትገኛለች
Oct 13, 2026 163
ኢትዮጵያ በታሪኳ የታላቅነት፣የሥልጣኔና የሉዓላዊነት ምሳሌ ሆና የኖረች ሀገር ናት።በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የራሷን መገበያያ በጥንት ዘመን ፈጥራ፣ ፊደላትን ቀርጻ፣ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ዓለምን ያስደመሙ የኪነ ህንጻ ሥራዎችን የከወነች ኃያል ሀገር ናት። የስልጣኔ ሀገረ መንግሥት ተብለው ከሚጠቀሱት ጥቂት ሀገራት አንዷ የሆነው ኢትዮጵያ የዓለም ተቋማትን በመመስረት፣ ለግፉዓን ድምፅ በመሆን፣ በዓለም የፖለቲካ አውድ ግዘፍ የነሳውና ብዙ ለውጦችን ያመጣው የዓድዋ ድል ባለቤቷ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅስማቸውን በመስበርና በማንበርከክ ድል አድርጋ የአድዋን ታላቅ ድል ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነትና የብሥራት ምልክት አድርጋ አስረክባለች። ሆኖም ይህ ታላቅ የታሪክ ኩራትና የሉዓላዊነት ወደር የለሽ ክብር ሀገሪቱን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ብልጽግናና ተወዳዳሪነት በበቂ ሁኔታ ሳይቀይራት ለረጅም ዘመናት ቆይቷል። ታዲያ የዚህ ሁሉ የስልጣኔና የድል ውርስ ባለቤቷ ሀገር እንዴት ወደኋላ ቀረች? በተከታታይ በነበሩ የሥልጣን ሽኩቻዎች፣የውስጥ ግጭቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ምክንያት ሀገራዊ አቅምና የሰው ኃይል ለግንባታ ሳይሆን ለጥፋት ሲውል ቆይቷል። በተጨማሪም የጠንካራና ዘላቂ ተቋማት አለመገንባታቸው እንዲሁም የፖሊሲ ውሳኔዎች ከተጨባጭ የሕዝብ ፍላጎት ይልቅ በርዕዮተ-ዓለም አክራሪነት ላይ መመሥረታቸው ኢኮኖሚውንም ፖለቲካውንም በእጅጉ ጎድቶታል።ዓለም በኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በዘመናዊ ግብርና እየመጠቀች በሄደችበት ወቅት ኢትዮጵያ በባህላዊ የአመራረት ዘይቤና በውጭ እርዳታ ጥገኝነት ውስጥ ታስራ በመቆየቷ ከዓለም አቀፍ ውድድር ወደኋላ ቀርታለች።የሀገር ሀብት፣ የምሁራን እውቀት፣ የግሉ ዘርፍና የመንግሥት ጥረት ሳይቀናጁና ሳይደጋገፉ በየፊናቸው በመጓዛቸው የታሰበውን ሀገራዊ ስኬት ማምጣት ሳይቻል ቀርቷል። ይህንን የታሪክና የልማት ክፍተት ለማረቅ የተነሳው የመደመር መንግሥት የትናንትን ጥፋቶች ማረም፣ መልካም ስኬቶችን ማስቀጠልና የነገን ብልጽግና የሚያረጋግጥ አዲስ ሀገራዊ ምዕራፍ መክፈትን ዓላማ አድርጎ ተነሳ። የመጀመሪያው የትኩረት አቅጣጫ የተበታተኑ ሀገራዊ አቅሞችን ማለትም የሕዝብን፣ የመንግሥትን፣ የግሉን ዘርፍ፣ የምሁራንንና የዳያስፖራውን አቅም በማቀናጀት ለጋራ ልማት ማሰለፍ ነው። ሁለተኛው ሀገሪቱን ከእርዳታና ከተወሰኑ ዘርፎች ጥገኝነት በማውጣት ግብርናን፣ አምራች ኢንዱስትሪን፣ ማዕድንን፣ ቱሪዝምንና ዲጂታል ኢኮኖሚን የእድገት መሪ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም መተግበር ነው። ሦስተኛው ደግሞ ፕሮጀክቶች በወረቀት ላይ ብቻ ሳይቀሩ በመሬት ላይ ፈጣን፣ ጥራት ያለውና ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችል አዲስ የተቋማትና የአፈጻጸም ባህል መገንባት ነው። የተመዘገቡ ተጨባጭ ድሎች የመደመር መንግሥት በሁሉም መስክ በትልቁ ማሰብ፣ ጀምሮ መጨረስን ባህል አድርጎታል። በዚህም ኢትዮጵያ እንድታንሰራራ ያስቻሉ ግዙፍ የልማት ምዕራፎችን እያሳካ ይገኛል። በግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማትን በማስፋት በዓመት 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በማምረት በአፍሪካ ቀዳሚዋ የስንዴ አምራች ሆናለች። ራሷን ችላም ወደ ውጭ መላክ ጀምራለች። የግብርና ሜካናይዜሽንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋት የሰብል ምርትን ከ335 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማሳደግ ተችሏል። በኢኮኖሚና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የወጪ ንግድ ገቢን 11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በተጨማሪም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የ15 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን በማነቃቃት ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን መተካት ተጀምሯል።ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችንም በማምረት ላይ ትገኛለች። በማዕድን ዘርፍም አፈር የለበሱ የከበሩ ማዕድናትን እየገለጠች ወደ ጥቅም በመቀየር ላይ ናት። የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያዎች የወርቅ ፋብሪካዎችና ግዙፍ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ እየገቡ ናቸው። የመደመር መንግሥት በመሠረተ ልማትና በሜጋ ፕሮጀክቶች በኩል የትርክትና የአፈጻጸም ለውጥ ፈጥሯል። የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት፣ የማይገነባ መሰረተ ልማት የለም በሚል ከለውጡ በፊት የነበሩ የተንከባለሉ ፕሮጀክቶችን በማፋጠን አሳክቷል።ለዚህ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ከነበረበት ውስብስብ የፕሮጀክት አስተዳደር በማላቀቅ በራስ አቅም በዜጎች ደምና ላብ ለውጤት አብቅቷል። ኃይል አመንጭቶ የቀጣናው የብርሃን ማዕከል እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ ባደረጓቸው የጉባ ብስራት ሜጋ ፕሮጀክቶችም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን፣ የነዳጅ ማጣሪያ፣ የጋዝ ማምረቻ፣ የሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል ማብለያ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ገብተዋል። ኢትዮጵያ በመደመር ነገን የተሻለ የማድረግ ሀገራዊ ዕይታ በኮሪደር ልማት ከተማና ገጠሩን ወደ ዘመናዊ የኑሮና የሥራ ማዕከልነት እየቀየረች ትገኛለች።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ ከአዲስ አበባ በጀመረው የከተማ የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበትና የኑሮ ደረጃ በእጅጉ አሻሽሏል።በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ እየተገነባ ነው።ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መፍጠር ተችሏል። በቱሪዝምና በሀገር ገጽታ ግንባታ በኩል የገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ሀብቶችን ወደ ላቀ የኢኮኖሚና የቱሪዝም አቅም ቀይረዋል።የመደመር መንግሥት የቀጣይ ጉዞ ርዕይ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመች፣ በራሷ አቅም የምትተማመንና በቀጣናው፣በአፍሪካና በዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር ማድረግ ነው። በመጀመሪያ በምግብ ራስን በመቻል፣ የወጪ ንግድ አቅምን በማሳደግና ከውጭ ጫናዎች ነፃ የሆነ ጠንካራ የፋይናንስና የኢንዱስትሪ መሠረት በመገንባት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው። በሁለተኛ ደረጃ በሰላማዊ የፖለቲካ ባህል አማካይነት ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የተደመረ ሀገራዊ የፖለቲካ ካፒታል የተፈጠረባትና የሕግ የበላይነት የጸናባት ሀገር ማድረግ ነው። ከጎረቤት ሀገራት ጋርም በልማት፣ በኃይል አቅርቦትና በሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲ ጠንካራ ትስስር የመፍጠር ትልሞችን ማስቀጠል ላይ የመደመር መንግሥት አበክሮ እየሠራ ይገኛል። የባሕር በርና የንግድ ወጪ አማራጮችን በፍትሐዊነትና በሕጋዊ መንገድ ማረጋገጥ ነው። በአራተኛ ደረጃ ጥራት ያለው ትምህርት፣የጤና ሽፋንና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማስፋት ለነገዋ ዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት የመደመር መንግሥት ዋና አጀንዳ ነው። የኢትዮጵያ ታላቅ የልማት ጉዞ የትናንት ህልሞችን ወደ ዛሬ ተጨባጭ ድል የመቀየር ሁለንትናዊ ጉዞ ነው።የመደመር መንግሥት ርዕይ ኢትዮጵያን የትናንት ታሪኳን የምትመለከት ብቻ ሳትሆን፣ የነገው ብልጽግናዋ አስተማማኝ የሆነ፣ ዜጎቿ በክብርና በፍትህ የሚኖሩባት ባለታሪክና ባለድል ሀገር አድርጎ ለማስረከብ የትውልድ አደራን በመፈጸም ላይ ይገኛል።
ፈተናን ወደ ዘላቂ ስኬት-በመደመር እሳቤ የተገለጠ ሀገራዊ አቅም
Oct 12, 2026 302
የአንድ ሀገር ታላቅነትና ብልፅግና የሚለካው በገጠሟት ፈተናዎች ስፋት ሳይሆን፣ እነዚያን ፈተናዎች ወደ ልማትና ዘላቂ ስኬት ለመቀየር በሚወሰዱ ቆራጥ ሀገራዊ እርምጃዎች ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ አያሌ መዋቅራዊ፣ጂኦፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን አልፋ የተጓዘች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፤በአሁኑ ወቅት የነበሩባትን ማነቆዎች ወደ አዲስ ዕድል በመቀየር ላይ ትገኛለች። ይህ ሂደት በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በመሬት ላይ በሚታዩ ዘለቄታዊ ታላላቅ ፕሮጀክቶችና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች እውን እየሆነ ይገኛል። ይህ አዲስ የተግባር ምዕራፍ ደግሞ የሀገሪቱን ዕድገትና ትውልድ ተሻጋሪ ጉዞ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የተነደፈው የመደመር እሳቤ ቀጥተኛ ነጸብራቅ ነው። የመደመር ፍልስፍና የነበሩ በጎ እሴቶችንና ስኬቶችን ይዞ መቀጠልን፣ጉድለቶችን ማስተካከልን እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ማመንጨትን እንደ ስትራቴጂ የሚይዝ በመሆኑ፣በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችና መዋቅራዊ ማሻሻያዎችም ይህንን እሳቤ በተግባር ያረጋገጡ ናቸው። ለዘመናት ያጋጠሙትን የምግብ ዋስትና ችግሮች፣ የምንዛሬ እጥረትና የገበያ መዛባቶች ለመቅረፍ የተወሰዱት አገራዊ እርምጃዎች የዚሁ ችግርን ወደ እድል የመቀየር ስትራቴጂ ዋና ማሳያ ናቸው። ኢትዮጵያ ለዘመናት የስንዴ እህልን ከውጭ ለማስገባት ታወጣ የነበረውን በዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረትና አገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትልቅ ታሪካዊ እመርታ አስመዝግቧል። ሀገሪቱ አሁን ላይ የስንዴ ምርትን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማብቃት ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ገበያ ኤክስፖርት ማድረግ ወደምትችልበት ደረጃ ተሸጋግራለች። በቅርብ የምርት ዘመናት ኢትዮጵያ 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በማምረት በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር ለመሆን የበቃች ሲሆን፣ ይህ ስኬት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ከአቮካዶና ሆርቲካልቸር እስከ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ያሉ አዳዲስ አቅሞችን በመጠቀምና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር የሀገር ውስጥ አምራቾች ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር እንዲገናኙና አገራዊ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲያድግ አስችሏል። ይህም የመደመር እሳቤ የሀገር ውስጥ አቅምን በመጠቀም የውጭ ጥገኝነትን እንዴት እንደሚቀንስ በተግባር ያሳየበት ተጨባጭ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል የተፈጥሮ ሀብትንና የከተሞችን አቅም ጥቅም ላይ ማዋል ባለመቻሉ ሲፈጠሩ የነበሩትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅፋቶች ለመፍታት አዳዲስ ሀገራዊ የልማት ሞዴሎች በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በዚህም ከተሞችን የዘመናዊና ጤናማ አኗኗር ማሳያ ማድረግ ተችሏል።በዋና ዋና ከተሞች የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች፣ ነባር መጨናነቆችን፣ የመሰረተ ልማት እጥረቶችንና የከተማ አስተዳደር ጉድለቶችን በመቅረፍ ከተሞችን ዘመናዊ፣ ፅዱ፣ እና ለኑሮ ተስማሚ አድርገዋቸዋል። ይህም የከተሞችን ውበትና ደረጃ ከማሳደግ ባሻገር ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ በገበታ ፕሮጀክቶች አማካይነት ያልተነኩ የተፈጥሮ ውበቶችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ሀብትነት በመቀየር እንደ ወንጪ፣ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ሀላላ ኬላ እና ደምቢ ኢኮ-ሎጂ ያሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። ይህ የልማት ግንባታ ከመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን በህዝባዊ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የታገዘ በመሆኑ የመደመርን የሀብት አጠቃቀም ጥበብ በግልጽ ያሳያል።በተለይም በክረምት ወራት የተከናወኑ በሺዎች የሚቆጠሩ አቅመ-ደካሞችን ቤቶች ማደስ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት የመንግስትን ከፍተኛ በጀት በማስቀረት የላቀ የካፒታል አቅም መፍጠር ችሏል። የአንድ ሀገር የእድገት ጉዞ የሚረጋገጠው የማህበረሰቡን አስተሳሰብ፣ የፖለቲካ ባህል እና የማህበራዊ ትስስር እሴቶችን በአዲስ መልክ በመገንባት እንደሆነ የመደመር እሳቤ በጥብቅ ያሰምርበታል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ እውነታ ውስጥ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ሀገራዊ ምክክር ሀገሪቱን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆም እየተተገበሩ ያሉ ተጨማሪ የመዋቅርና የአስተሳሰብ አምዶች ናቸው። የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበራዊ ካፒታል ግንባታ እና የወጣትነት ሀይልን ለሀገር ግንባታ የማዋል ፍልስፍና በተግባር የገለጠ ስራ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ልዩነቶችን በኃይል፣በግጭት እና በጠመንጃ የመፍታት አደገኛ ልማድን በማስወገድ፤ በሰለጠነ፣ አሳታፊ እና በውይይት የማመን ባህል የመተካት ትልቅ መሰረት ተጥሏል። ይህም ቀጣይነት ላለው ሀገረ-መንግሥት ግንባታ እና ዘላቂ ሰላም የሚጠቅም የፖለቲካ ባህል ሽግግር የፈጠረ ሲሆን፣ ልዩነቶችን በመደመር ውበት የመቀየር ጥበብ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የገጠሟትን ዘመናዊና ታሪካዊ ፈተናዎች ወደ ልማትና ወደ ዘላቂ ስኬት የመቀየር ትልቅ አቅም እንዳላት በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በመደመር ፍልስፍና የሚመሩት እነዚህ ፕሮጀክቶች እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የምታደርገውን የማንሰራራት ጉዞ እውን የሚያደርጉ ናቸው። የኢትዮጵያ ነገ ብሩህ የሚሆነው ፈተናዎች በሌሉበት ሳይሆን፣ ያሉትን ፈተናዎች በመደመር እሳቤ ወደ ተሻገረ ዕድል የመቀየር አቅሟ እንደሆነ ይህ ታሪካዊ ጉዞ ይመሰክራል።
የትግራይ ክልልን የሰላም እና የልማት ማዕከልነት የማረጋገጥ ጉዞ
Oct 11, 2026 260
ከትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ሰብዓዊ ድጋፍ፦ የትግራይ ክልልን የሰላም እና የልማት ማዕከልነት የማረጋገጥ ጉዞ የሕወሓት ቡድን አጥፊ አካሄድ የትግራይ ክልልን ሕዝብ ሰላም፣ ደህንነትና የወደፊት ተስፋ አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ቡድኑ ከሕዝብ ሰላማዊ ሕይወት ይልቅ የራሱን ቡድናዊ ጥቅም በማስቀደሙ ምክንያት፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዳይረጋገጥና ሕዝቡም ወደ መደበኛ ሕይወቱ እንዳይመለስ ትልቅ እንቅፋት ሲሆን ቆይቷል። በተለይም ወጣቶችን በግዳጅ ወደ ጦርነት መውሰዱ፣ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማራቁና የሚፈጽማቸው ኢ-ሰብዓዊ ተግባራት በሕዝብ ላይ የሚያደርሳቸው ከባድ በደሎች ናቸው። የትግራይ ክልል ሕዝብ ከማንኛውም ጊዜ በላይ የሰላምን አስፈላጊነት በጽኑ ይረዳል። የወጣቶችም ፍላጎት በጦርነት ማለቅ ሳይሆን በትምህርት፣ በሥራና በልማት የተሞላ ተስፋ ያለው የወደፊት ዕድል ማግኘት ነው። የማንኛውም ቡድን ጥቅም ከሕዝብ ሕይወትና ከዜጎች መጻኢ ዕድል በላይ ሊበልጥ አይችልምና። የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ክልል ልክ እንደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሰላም፣ የልማትና የዕድገት ማዕከል እንዲሆን የሚያደርገው ጥረት በተግባራዊ እርምጃዎች የታጀበ ነው። ለዚህም ለሰላም በሩን ክፍት በማድረግ፣ በትዕግሥትና በሆደ ሰፊነት መንቀሳቀስ እንዲሁም ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ በመሆን ለዘላቂ ሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አረጋግጧል። ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ገብተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ የቅበላ ማዕከላትን ማዘጋጀቱ በአብነት የሚጠቀስ ነው። በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የተዘጋጁት የተሃድሶ ቅበላ ማዕከላት ታጣቂዎች ከጦርነት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲሸጋገሩ ዕድል ፈጥሯል፣ አሁንም እየፈጠረ ይገኛል። ይህም የግጭት አዙሪትን ለመስበር፣ የሰው ሕይወትን ለመታደግና ለልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው። በተመሳሳይ በአላማጣ ከተማ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች በፌዴራል መንግሥት ወጪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ መጀመሩ የሕዝቡን አስቸኳይ ፍላጎት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ያሳያል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ድጋፉን ማድረስ መቻሉ ዜጎች በችግር ውስጥ ሲሆኑ ፈጥኖ የመድረስና የሰብዓዊ ኃላፊነትን የመወጣት አስፈላጊነት በእጅጉ ያጎላል። በሕወሓት ህገ ወጥ ተግባር በረራው ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የአውሮፕላን በረራ እንደገና መጀመሩ ሌላው ተጨባጭ እርምጃ ነው። የትራንስፖርት ግንኙነት መመለስ የሰዎችን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ፣ የንግድና የሥራ ግንኙነቶችን ለማጠናከር፣ ለቤተሰብና ማህበራዊ ግንኙነትን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ጠቃሚ ነው። የተቋረጡ አገልግሎቶች መመለስ ለሰላም ግንባታና ለልማት የሚያስፈልገውን መሠረትም በእጅጉ ያጠናክራል። በአጠቃላይ በትግራይ የተሃድሶ ማዕከላት መዘጋጀት፣ ለተጎጂ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ መድረስና የአየር በረራ ዳግም መጀመር የሚያሳዩት አንድ ወሳኝ መልዕክት አለ፤ ሰላም በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ይገነባል። ይህ የክልሉ ሕዝብ ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለስ፣ ልጆቹ በሰላም እንዲማሩ፣ ወጣቶቹ በሥራና በልማት እንዲሳተፉ እና ክልሉ ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ጋር በእኩልነት እንዲያድግ በመንግሥት በኩል የሚደረገውን ያላሰለሰ ጥረት የሚያረጋግጡ ናቸው። የሰላምን ዕድል መጠቀም የሕዝብን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ህልውና፣ አንድነትና የጋራ የወደፊት ተስፋ ለማጠናከር ወሳኝ ነው።
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Oct 10, 2026 219
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት እጩ የካቢኔ አባላትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ሹመታቸውን አጸድቀዋል። የካቢኔ አባላቱ ሹመት ህዝብን የማገልገል አቅምና ፍላጎት፤ የትምህርት ዝግጁነት፣ የስራ ልምድና አጠቃላይ ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ ነው። እንደ አጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የከፍታ ምዕራፍ የማሸጋገር አደራና ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቀጣይ በላቀ የስራ አፈፃፀም የሀገርን እድገት የማስቀጠልና በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት በሚታይ ለውጥ ለማምጣት መትጋትም ይጠበቅባቸዋል። በተቋማት ቀጣይነት፣ በሥርዓት ግንባታና በሕዝብ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ በመመሥረት የሀገር ግንባታን ሂደት ማስቀጠል የመደመር መንግስት አበይት ትኩረቱ አድርጎ እንደሚሰራም ይጠበቃል። የተቋማት ስኬት የሚለካው ለሕዝብ በሚሰጡት ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ውጤታማ አገልግሎት በመሆኑ ሚኒስትሮቹ በዚሁ ልክ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን የሚተጉ መሆን ይኖርባቸዋል። የመደመር መንግስት የካቢኔ አባላት እጩዎችም የመፈጸም አቅምና ፍላጎት፣ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እንደ መሠረታዊ መስፈርቶች ተወስደው የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን በመዘጋጀት መሆኑን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል። የመንግስት ሹመት “የሚዝናኑበት ሳይሆን የሚሰሩበት” ከፍተኛ የሕዝብ አደራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የካቢኔ አባላት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል እንዲተጉም አሳስበዋል። የመደመር መንግስት ሀገር የመምራት እድልም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የማስቀጠል፣ የተቋማትን ግንባታ የማጠናከር፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማስቀጠል ይሆናል።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር 
Oct 9, 2026 201
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 373
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 256
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 263
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108844
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 82239
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60075
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57677
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40908
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40845
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40256
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38753
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108844
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 82239
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60075
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57677
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የሸማ ጥበብ-የጋሞዎች ባህላዊ ማንነት እና የኢኮኖሚ መሠረት
Oct 11, 2026 212
አርባ ምንጭ፤ ጥቅምት 1 /2019 (ኢዜአ):- የሸማ ጥበብ-- የጋሞዎች ባህላዊ ማንነት እና የኢኮኖሚ መሠረት በሳሙኤል አየነው (ኢዜአ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ) በኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ጥበባት ታሪክ ውስጥ የጋሞ ማኅበረሰብ የሸማ ሥራ ልዩና የጎላ ስፍራ አለው። ከጥንት ጀምሮ ከጥጥ ምርት ጋር የተሳሰረው ይህ ዕውቀት፣ ልብስን ከመልበስ ፍላጎት አልፎ የትውልድ ማንነት፣ የውበት መግለጫ እና የታሪክ ማኅደር ሆኖ ዘልቋል። በጥጥ ፈትል ላይ በሚያርፉ ደማቅ ቀለማትና ልዩ ንድፎች የሚታወቀው የጋሞ የሸማ ጥበብ፣ እንደ «ዱንጉዛ» ያሉ የክብር አልባሳትን ለአለም በማስተዋወቅ አርባ ምንጭንና አካባቢዋን "የጥበብ ምድር" የሚያስብል እና የታሪክ ባለቤት አድርጓቸዋል። የጋሞ የሸማ ጥበብ ተራ የሙያ ክህሎት ሳይሆን በቤተሰብ አባላት የጋራ ድርሻና ትብብር የሚከናወን፣ ትውልድ ከትውልድ የሚወርሰው ሕያው ባህላዊ እሴት ነው። ሴቶች ጥጥ በመፍተል፣ ወንዶች በዕውቀታቸው በመሸመን፣ ህፃናት ደግሞ በመደወር የሚካፈሉበት ይህ የሙያ ክፍፍል ማኅበራዊ ትስስርን ያጠናክራል። ከባህላዊ መግለጫነቱ ባሻገር የጋሞዎች የሸማ ጥበብ ለአካባቢውና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት የሀብት ምንጭ ነው። ሙሉ በሙሉ በእጅ በሚከናወነውና ሳይበረዝ በቆየው በዚህ ሀገር በቀል ጥበብ የተመረቱ አልባሳትና ብርድ ልብሶች፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፈው በዘመናዊ ዲዛይኖች በመታገዝ በአውሮፓና በአሜሪካ ገበያዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትን አትርፈዋል። ይህም ጥበቡ ለብዙዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው አድርጎታል። በሀገራችን ከሚታወቁ ሀገር በቀል ዕውቀቶች መካከል አንዱ የጋሞዎች መገለጫ የሆነው የሸማ ጥበብ ነው። የሸማ ጥበብ ደግሞ ከጥጥ ምርት የሚሠራ በመሆኑ ጋሞዎች ከጥጥ ምርት ጋር ያላቸው ቁርኝት ከጥንት ጀምሮ የዘለቀ ነው። ጥጥ ለጋሞዎች ከልብስ እስከ ጉርስ፣ ከጉርስ እስከ ውርስ በመሆን ትውልድ ተሻግሮ እያገለገለ የሚገኝ ሀብት ነው። በተለያየ መልክ በመሠራቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ዜጎችን ቀልብ እያማለለ ያለው የሸማ ጥበብ "ጋሞ የጥበብ ምድር" ተብሎ እንዲጠራም ምክንያት ሆኗል። ይህን ተከትሎ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ1890ዎቹ የጥበብ አልባሳት እንዲሠሩላቸው በሚል አፄ ምኒልክ በቁጥር 50 የሚሆኑ የሸማ ጥበብ ያላቸውን ጋሞዎች ከዶርዜ አካባቢ ወደ መሐል ሀገር እንደወሰዷቸው ይነገራል። በዚህ መልክ የሸማ ጥበብና ዕውቀቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ መሐል ሀገር እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች የተስፋፋ ሲሆን፣ የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካም ይህን ፀጋ ተከትሎ ሊመሠረት ችሏል። በግብርና ልማት እና በሽመና የሚተዳደረው የጋሞ ማህበረሰብ በማሳው ጥጥን በስፋት ማምረት ከህልውናው ጋር የተያያዘ በመሆኑ ዛሬም ድረስ በአካባቢው ጥጥ በስፋት እየተመረተ ይገኛል። የጋሞዎች የሸማ ጥበብ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ስፍራ ያለው፣ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረና ማንነትን የሚገልጽ ሀገር በቀል ዕውቀት ነው። በጥጥ ከሚሠሩ ባህላዊ አልባሳት መካከል አንዱ የማንነታቸው መገለጫ የሆነው ‹‹ዱንጉዛ›› ነው። ይህም የጋሞ ማህበረሰብ ታዋቂና የክብር ልብስ ሲሆን፣ ቀይ፣ ጥቁርና ቢጫ የመሳሰሉ ደማቅ ቀለሞችንና ልዩ ንድፎችን የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እንደ ቁሌ፣ አሰራ፣ ፈርዣ፣ ቡሉኮ፣ ጋቢ፣ ኩታ፣ ባርኔጣ እና ያኖ የመሳሰሉ የተለያዩ የባህል ልብሶችና ብርድ ልብሶች ይመረታሉ። ልብሶቹ ውበትን ከማንጸባረቅ ባለፈ እንደ "ዮ ማስቃላ" ባሉ የዘመን መለወጫ በዓላት ከፍተኛ ቦታ አላቸው። የሸማ ጥበብ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ የቱሪዝም መሳቢያ እና የጋሞ ህዝብ የኢኮኖሚ መሠረት በመሆኑ ልጆች ከወላጆች የሚወርሱት ነገር ቢኖር አንዱ የሸማ ጥበብ ነው። የሸማ ሥራ የሚከናወነው እንደ ቤተሰብ የሥራ ድርሻ በመከፋፈል ሲሆን፣ በዚህም ሴቶች ጥጥ በመፍተል፣ ወንዶች በመሸመን እንዲሁም ልጆች በመደወር ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። የሸማ ጥበቡን ልዩ የሚያደርገው በእጅ ብቻ የሚሠራ፣ ያልተበረዘና ያልተከለሰ ሀገር በቀል ሀብት መሆኑ ነው። ይህም በአሁኑ ሰዓት በዘመናዊ ዲዛይን በመታገዝ ከሀገር ውስጥ እስከ አውሮፓና አሜሪካ ገበያዎች በስፋት የሚገኝ ሲሆን፣ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ የራሱን ድርሻ እያበረከተ ይገኛል። በቅርቡ 6ኛው አለም አቀፍ የጥጥ ቀን ''ጥጥ ለበጎነት፡ በንግድ፣ እሴት በመጨመር እና በትብብር የበለጸገ ሕይወትን መገንባት'' በሚል መሪ ሐሳብ በታሽከንት፣ ኡዝቤኪስታን የተከበረ ሲሆን የጥጥ ምርትን ከጥሬ ዕቃነት ባሻገር እሴት በመጨመር ወደ ከፍተኛ ውጤት ማሸጋገርን፣ የዓለም አቀፍ ንግድ ዕድሎችን ማስፋፋትን እና የአምራች ማኅበረሰቦችን የኢኮኖሚ ተደራሽነት ማሳደግን ያለመ ውይይት በማካሄድ መጠናቀቁ ይታወሳል።
የከተሞች ትንሳኤ ምሥጢር - የመደመር መንግሥት 
Oct 9, 2026 207
በታዬ ለማ 👉አዲስ አበባ ዳግም አብባለች ጎህ ሲቀድ በአዲስ አበባ ላይ የሚወጣው ፀሐይ ዛሬ ሌላ ከተማ ያበራል። ሰፋፊ መንገዶቿ ላይ ብርሃን ሲያርፍ፣ በእግረኛ መንገዶቿ ላይ የማለዳ ተጓዦች ሲተላለፉ፣ በወንዞቿ ዳርቻ የተሠሩ ፓርኮች አረንጓዴ ሲለብሱ ማየት ይቻላል። ይህች ከተማ እንደ ስሟ አዲስ ሆናለች። ይህ ለውጥ ግን ድንገት የመጣ አይደለም፤ በትልቅ ቁጭት የተገነባ የትውልድ ተሻጋሪ አሻራ ነው፡፡ 👉አገር እየተቀየረች ነው የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት አገርን የሚቀይሩና ኢትዮጵያን ወደ ፊት ያራመዱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል። በኢኮኖሚው ዘርፍ ታሪካዊ ውጤት ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ የምታስገባ አገር መሆኗ ቀርቶ ዛሬ ወደ ውጭ የምትልክ ሆናለች። በኢንዱስትሪው ዘርፍም ትልቅ ድል ተገኝቷል፤ ቀደም ሲል ብዙ የውጭ ምንዛሬ ያስወጡ የነበሩ ምርቶች አሁን እዚሁ ይመረታሉ፤ በዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። በማዕድን ዘርፍ እስከ ዛሬ ታይቶ በማያውቅ መንገድ የኢትዮጵያ ማዕድናት እንዲወጡ እየተደረገ ነው፤ አገሪቱም ከዚህ ሀብቷ ተጠቃሚ እየሆነች ነው። በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሠሩት ሥራዎች አስደናቂ ናቸው፤ መንግሥት በቴክኖሎጂ የተገነባች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ያሳያሉ። በቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ «ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» በተሰኙ ማዕቀፎች አስደናቂ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህ ሳቢያ አብዛኞቹ የአገሪቱ ክፍሎች በአስደናቂ ሁኔታ ተቀይረዋል። ታሪካቸው ተለውጦ አዲስ መልክ የያዙት እነዚህ ስፍራዎች ለዜጎቻቸው ኑሮ የተመቹ ከመሆናቸውም በላይ የውጭ አገር ዜጎች ጭምር ሊጎበኟቸው የሚናፍቋቸው ከተሞች እየሆኑ ነው። ከእነዚህ ሁሉ መካከል እንደ ስሟ በመደመር መንግሥት ዘመን አዲስ መሆን የቻለችው አዲስ አበባ ጎልታ ትታያለች። 👉«ውብ አበባ» የተባለችው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛው የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ይህንኑ እውነታ አንስተዋል። ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ በጀመሩት ጥረት ለመኖሪያ የተመቹ፣ ለንግድና ለኮንፈረንስ የተስማሙ፣ ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱም እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል። «ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነት እንጂ ባዶ ምኞት ተደርጎ አይወሰድም» ብለዋል። አያይዘውም የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጎብኚዎችን «ኑ ወደ እኔ» እያለ የሚጣራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት እውነት ነው። 👉ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ይህ ጥሪ ምን ያህል ትልቅ ለውጥ እንደሆነ ለመረዳት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና፣ የአፍሪካም የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና ለዘመናት በአገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቦታ ይዛ ኖራለች። ይሁን እንጂ እድገቷ ከደረጃዋ ጋር ፈጽሞ አይጣጣምም ነበር። በአብዛኞቹ የከተማዋ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀና ከተሽከርካሪ መንገድ የተለየ የእግረኛ መንገድ አልነበረም። እግረኛው ከመኪና ጋር እየተጋፋ ይጓዝ ነበር፤ መንገዶቿም ለትራፊክ አደጋና ለእግረኞች እንግልት ዋና ምክንያት ነበሩ። የመንገድ ዳር መብራቶች ካሉበት ቦታ ይልቅ የሌሉበት አካባቢዎች በርከት ይሉ ነበር፤ በርካታ አደባባዮችና መንገዶችም ከፍተኛ ጥገና ይፈልጉ ነበር። ዘመናዊና አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴዎችን የሚያበረታቱ መንገዶች ደግሞ ጨርሶ የሚታሰቡ አልነበሩም። ሌላው ጎልቶ የሚታይ ክፍተት የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች እጥረት ነበር። ነዋሪው ነፃ ጊዜውን የሚያሳልፍበት ሰፊ ቦታ አልነበረውም። በከተማዋ ውስጥ አቋርጠው የሚያልፉ በርካታ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎችም ተንከባካቢ በማጣታቸው በቆሻሻ ተሞልተው የአካባቢ ጥበቃ ሥጋት ሆነው፣ የበሽታ ምንጭና የደህንነት ስጋትም ነበሩ፡፡ እንደ ካዛንቺስና አራት ኪሎ ባሉ የከተማዋ እምብርት ሰፈሮች ውስጥ በአንድ ወቅት ተደራርበው የቆሙ አሮጌ የጭቃ ቤቶች፣ ጠባብ ጥጋጥጎች እና የታጨቁ መንደሮች የተለመደ ገጽታ ነበሩ። የዘመናት ታሪክ የተሸከሙ ሕንፃዎችና መኖሪያዎች ተገቢውን እድሳትና እንክብካቤ ሳያገኙ በጊዜ ሲሸረሸሩ ኖረዋል። ከተማዋ ወጥ የሆነ የውበትና የቀለም መመሪያ ስላልነበራት ገጽታዋ የተበታተነ ነበር፤ የታሪካዊ ስፍራዎችና የሐውልቶች ዙሪያም በቂ ጽዳትና ብርሃን አላገኘም ነበር። ዛሬ ግን ያ ገጽታ ወደ ታሪክነት እየተሸጋገረ ነው። እነዚሁ ሰፈሮች በዘመናዊ ዕቅድ ተቃኝተው፣ ታሪካዊ ሕንፃዎቻቸው ታድሰውና ተጠብቀው፣ በተዋሃደ የቀለምና የዲዛይን ቅንብር አዲስ መልክ እየያዙ ነው። ሐውልቶችና ታሪካዊ ስፍራዎች በጽዳትና በምሽት ብርሃን ተውበው፣ ለነዋሪው ኩራት ለጎብኚውም መስህብ ሆነው ይታያሉ። 👉ትንሳኤ ዛሬ ግን ታሪኩ ተቀይሯል። አዲስ አበባ የትናንት ገጽታዋን በማይታመን ሁኔታ እየቀየረች ነው። ነዋሪው ለውጡን እያጣጣመው ነው፤ ዓለምም አድናቆቱን እየገለጸ ነው። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ላትመለስ ተሰናብታለች። መዓዛዋ ተቀይሯል፤ ደስ የማይል ገጽታዋና ሽታዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዷል። አዲስ አበባ በእርግጥም አዲስ ሆናለች። 👉የመደመር መንግሥት ለአዲስ አበባ ትንሳኤ ሆኗታል። ዛሬ እንደ ስሟ አዲስ ሆና ተገንብታለች። በኮሪደር ልማቷ፣ በስማርት ሲቲ ግንባታዋና በሰው ተኮር ልማቶቿ ለዜጎቿ ምቹ እየሆነች፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በትክክል እያረጋገጠች ትገኛለች። የኮሪደር ልማት አዲስ አበባን ከጊዜው ጋር የሚመጥንና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት ባለቤት ያደረገ ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ፕሮጀክቱ መንገድን ከማሻሻል ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይሯል። 👉ከመንገድ እስከ እግረኛ የከተማዋ ዋና ዋና አውታሮች ሰፊና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው እንደገና ተገንብተዋል። ተሽከርካሪዎች ቀልጣፋ ፍሰት አግኝተዋል፤ የትራፊክ እንግልትም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቀሏል። ቀደም ሲል ትኩረት ተነፍጎት የነበረው እግረኛ አሁን ትክክለኛውን የመራመጃ ቦታ አግኝቷል። የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተዋል፤ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መተላለፊያዎች፣ ንጹሕና ውብ የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የብስክሌት መጋለቢያ መስመሮች ተካተዋል። ዜጎች ደኅንነታቸው በተጠበቀ፣ ምቹ በሆነ አካባቢ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ምሽት ሲመጣም ከተማዋ አትደበዝዝም። ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ የመብራት ሥርዓቶች፣ የዲጂታል መረጃ መስጫ ሰሌዳዎችና ውብ የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማቶች ውበቷንና ደኅንነቷን ይጨምራሉ። ይህ የተቀናጀ ልማት አዲስ አበባን የነዋሪዎቿን ፍላጎት የምታሟላ፣ ለኑሮና ለሥራ ምቹ፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በሥራ ያረጋገጠች ዘመናዊ ከተማ አድርጓታል። 👉ወንዞችና አረንጓዴ ስፍራዎች በአንድ ወቅት የቆሻሻ መጣያና የከተማዋ ሥጋት የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎችና ክፍት ቦታዎች ዛሬ የከተማዋ ዋነኛ የመስህብ ሀብትና የጽዳት ማዕከል ሆነዋል። በከተማዋ ማዕከልና አካባቢ የሚያልፉ ጥንታዊ ወንዞች ከቆሻሻ ተነጥለው የተፈጥሮ ፍሰታቸውን ጠብቀው እንዲፈሱ ተደርገዋል። ዳርቻዎቻቸው በድንጋይና በኮንክሪት ግድግዳዎች ተጠብቀው ከጎርፍ ሥጋት ነፃ ሆነዋል። በወንዝ ዳርቻዎች ላይ የተገነቡት ውብ ፓርኮች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎችና የስፖርት ማዕከላት ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ሁለንተናዊ የዕረፍትና የመዝናኛ አማራጭ ፈጥረዋል። የዛፎችና አረንጓዴ ተክሎች መብዛት የከተማዋን የአየር ጥራት አሻሽሏል፤ የሙቀት መጠኑን አመጣጥኖ የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳሩ እንደገና እንዲያንሰራራ አድርጓል። በዚህም አዲስ አበባ አረንጓዴ፣ ንጹሕና ለኑሮ እጅግ ተስማሚ ሆናለች። 👉ሰላምና ደኅንነት የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበትና ገጽታ ብቻ አልቀየረም፤ ወንጀልን በመከላከልም ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው። ፍትሕ ሚኒስቴር «የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በወንጀል መከላከልና ደኅንነት ማረጋገጥ ላይ ያለው ሚና» በሚል ርዕስ ባካሄደው ጥናት ይህንኑ አመልክቷል። በተለይ ለጎዳና ወንጀል ምቹ የነበሩ ስፍራዎች እንዲጠፉ በማድረግ አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ ዕድል መፍጠሩን ጥናቱ ያሳያል። 👉ጉዞው ይቀጥላል ታላቅ ሕዝብን የሚመጥን ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ፣ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ይበልጥ የማደስ ተግባሯን አጠናክራ ትቀጥላለች። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለመምራት በተመረጡበት ወቅት ያረጋገጡትም ይህንኑ ነው። በቀጣዮቹ ዓመታት አዲስ አበባን ይበልጥ ጽዱ፣ ሳቢ፣ ምቹና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የማድረጉ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው በማለት አፅንኦት ሰጥታዋል። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ተሰናብታለች። ዛሬ የምትታየው አዲስ አበባ ደግሞ ገና ጅማሬዋ ላይ ናት። 👉አዲስ አበባ የለኮሰችው የልማት ችቦ በሁሉም ይበራል ከአዲስ አበባ የተነሳው የልማት ብርሃን በዚያው አልተወሰነም፤ ወደ ሁሉም የአገሪቱ ማዕዘናት እየተሰራጨ ነው። በመዲናዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፓርኮችና የከተማ እድሳት ልምድ ወደ ሌሎች ከተሞች ተሸጋግሮ፣ ዛሬ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያሉ ከተሞች አዲስ መልክ እየያዙ ይገኛሉ። የመደመር መንግሥት የሚያከናውነው ልማት ማንንም ወደ ኋላ የማይተው፣ ሁሉንም አካባቢዎች በእኩል ዓይን የሚያይና ያቀፈ ነው። በ«ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» ማዕቀፎች በተለያዩ ክልሎች የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ በየከተማው የሚታዩ ዘመናዊ መንገዶችና የመዝናኛ ስፍራዎች፣ እንዲሁም በገጠር የሚካሄዱ የግብርና እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች አንድ እውነት ይናገራሉ፤ ልማቱ የአንድ ከተማ ሳይሆን የመላው አገር መሆኑን። አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች አርአያ ሆና ስትቆም፣ ሌሎች ከተሞችም በየፊናቸው አብበው የአገሪቱን ውበት እያበዙ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በአንድ ማዕከል ብቻ የምታደምቅ ሳትሆን፣ በሁሉም ማዕዘኗ የምታበራ፣ ዜጎቿም በየትኛውም ቦታ የልማቱ ተካፋይና ተጠቃሚ የሆኑባት አገር እየሆነች ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም