ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
አረንጓዴ ዐሻራ - የመደመር እሳቤ አንዱ ማሳያ
Jul 28, 2026 179
በየዓመቱ እያደገ የመጣው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በተጨባጭ ውጤት እየታጀበ የቀጠለ ሆኗል። ዐቅምን በመሰብሰብ በመደመር ዕሳቤ እየተከናወነ ያለው ይህ ኢኒሼቲቭ በረከቱ ብዙ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነትና አመራር ሰጪነት በ2011ዓ.ም የተጀመረው ይህ መርሃ-ግብር ዛሬ ላይ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ውጤትም እየተመዘገበበት ነው። እንደየአካባቢው ሥነ-ምኅዳር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸውን ችግኞች፣ ለደን ሽፋን፣ ለከተማ ውበትና ለማረፊያ ጥላ የሚሆኑ የአፈር መከላትን የሚያስቀሩ ችግኞችን መትከል ባህል እየሆነም ነው። የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 184 ላይ እንደተጠቀሰው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ዋና ግብ የገጠርና የከተማ አረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ በማድረግ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና አስተዋጽዖ ማድረግ ነው። ይህ መርሃ-ግብር በ2011 ዓ.ም ከመጀመሩ በፊት በ 2010 ዓ.ም. የነበረው ሀገር አቀፍ የደን ሽፋን 17 ነጥብ 2 በመቶ ነበር ። በአንድ ሰው 40 ችግኝ (40 ዛፎች በነፍስወከፍ) በሚል መሪ ቃል በአንድ ቀን የተከናወነውን የአንድ ጀምበር የ 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ ተከላን ጨምሮ በተከናወነ መርሃ-ግብር የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ የሀገራችንን የደን ሽፋን በ2016 ዓ.ም 23 ነጥብ 6 በመቶ አድርሶታል። የተለያዩ ክፍላተ-ዓለማት አንድም በከፋ ቅዝቃዜ እንዲሁም መደበኛ የኑሮ ሁኔታን በሚያናጋ አደገኛ ሙቀት ብሎም በድንገተኛ ጎርፍ እና ሰደድ እሳት በሚታመሱበት ጊዜ፤ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ቀድሞ ለማረቅ አንዱ መፍትሔ አረንጓዴ ዐሻራን በስፋት ማከናወን መሆኑ ይታመናል። ባለፉት ዓመታት በብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን ርብርብ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፤ ውጤቱንም ሕዝቡ ዐይቷል። በሕዝቡ ዘንድ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ ጭምር ተደርጎ በመወሰዱ የተሳታፊዎች ቁጥርና የሚተከለው ችግኝ በየዓመቱ እየጨመረ ሊሄድ ችሏል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ጥቅሙ የሚታይ የሚጨበጥ ሆኗል። የመሬት ምርታማነትንም አሳድጓል። ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፊት (በ2010 ዓ.ም) በሔክታር የሚመረተው ስንዴ 22 ኩንታል፣ በቆሎ 30 ኩንታል፣ ጤፍ 17 ኩንታል እንዲሁም ገብስ 23 ኩንታል ነበር። ከኢንሼቲቩ ትግበራ በኋላ ደግሞ (በ2017 ዓ.ም) ስንዴ በሔክታር 36 ኩንታል፣ በቆሎ 46 ኩንታል፣ ጤፍ 20 ኩንታል፣ ገብስ 30 ኩንታል ማምረት ተችሏል። በዚህም መሠረት በ2017 ዓ.ም 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 280 ሚሊየን ኩንታል ማምረት ተችሏል። ስንዴን በትጋት በማምረትም ከውጭ ለማስገባት ይወጣ የነበረን 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት ተችሏል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፍራፍሬ ልማት ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። በዚህም ገበያውን ከማረጋጋት ባለፈ ሕብረተሰቡ (አምራቹ) ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ በዚያው ልክ እንዲያድግ አስችሏል። ይህም ኢትዮጵያም በአፍሪካ አቮካዶን በቀዳሚነት ወደ ውጭ የምትልክ ሁለተኛዋ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ጠቀሜታ ዘርፈ-ብዙ ነው። የተፈጥሮ ስነ-ምህዳርን ከመጠበቅ ባለፈ በሁሉም መንገድ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ነው። ከአረንጓዴ ዐሻራ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የባለድርሻ አካላት እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር፣ በክረምት ወራት የሚተከሉ ችግኞችን በበጋ ወራት በአግባቡ መንከባከብ ከቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ማስጀመራቸው ይታወቃል። በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ከ8 ቢሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ በሆኑበት በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በተለያዩ ዘርፎች የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በቀጥታ ለሕዝቡ ጥቅም የቆመ ሰው ተኮር መርሃ-ግብር መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ስለዚህ በቀጣይ ሕብረተሰቡ በመደመር ዕሳቤ በዚህ ኢኒሼቲቭ ላይ ያለጠባቂነት በንቃት የመሳተፍ ባሕሉን በማሳደግ ተጠቃሚነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መትጋት ይጠበቅበታል።
የበጋ መስኖ ስንዴ፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ የግብርና ዘርፍ እመርታ!!
Jul 28, 2026 148
በሚኪያስ ጎቡ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ አምድ፣ ሕዝብ የኑሮ መሠረትና የምግብ ዋስትና ማዕዘን ነው። በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ሆኖ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግብርናን ከኢንዱስትሪ፣ ከማዕድን፣ ከቱሪዝም እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር በመጣመር ወሳኝ የዕድገት ምሰሶ የሚሆንበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም በሰብል፣ በእንስሳት እና በሌሎች ዘርፎች እመርታዊ ውጤቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል። በዚህ ዘርፍ ከተመዘገቡ አስደናቂ ለውጦች መካከል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አዲስ የዕድገት ፍኖት ከፍቷል። ለዓመታት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚያስፈልገውን ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ስታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ በስትራቴጂካዊ የግብርና ማሻሻያዎች፣ በመስኖ ልማት ማስፋፋት፣ በሜካናይዜሽን እና በአርሶና አርብቶ አደሮች አደረጃጀት የስንዴ ምርቷን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችላለች። ይህ ለውጥ የገቢ ምርትን ከመተካት ባሻገር በምግብ ራስን መቻል፣ ለውጭ ንግድ አቅም እና ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት አዲስ ዕድል ፈጥሯል። የስንዴ ምርታማነትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ዘንድ የይቻላል መንፈስን በማጎልበት የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ አቅም ፈጥሯል። ከዚህም በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና ሥርዓት በመገንባት ለአፍሪካና ለቀጣናው ሀገራት የልማት ተሞክሮ አስገኝቷል። የምርትና የምርታማነት አብዮት በክረምት ዝናብ ላይ ብቻ ተንተርሶ የቆየው የኢትዮጵያ ግብርና አሁን ዘመናዊ የአመራረት ምኅዋር ውስጥ ገብቷል። ይህም በቆላማ፣ በደጋማ እና በወንዝ ዳርቻ የሚገኙ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወደ ምርታማ የስንዴ ማሳዎች ቀይሯል። የስንዴ ምርታማነት አብዮትም በመስኖ፣ በሜካናይዜሽን፣ በተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎች እና በአርሶና አርብቶ አደሮች የተቀናጀ ጥረት የምርታማነትን ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ አሻሽሏል። በዚህም ኢትዮጵያ ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታስገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል። ይህ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የግብርናን ገጽታ የቀየረ የምርትና የምርታማነት አብዮት ነው። ፖሊሲ፣ ቴክኖሎጂ፣ መስኖ እና የአርሶና አርብቶ አደሩ ትጋት ሲጣመሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያጎናጽፍ አቅም መፍጠር እንደሚቻል የሚያሳይ የልማት ተሞክሮ ሆኗል። የክላስተር ግብርና፤ የሜካናይዜሽን ስኬት እመርታ!! የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ስኬት ከውጤታማ የአሠራር ዘዴዎች መካከል የክላስተር ግብርናና የሜካናይዜሽን አጠቃቀም ዋነኛ ምሰሶዎች ናቸው። ባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን በማደራጀት ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ እና የሰብል ጥበቃ ግብዓቶችን በወቅቱና በተደራጀ መንገድ እንዲያገኙ አስችሏል። የሜካናይዜሽን መስፋፋት ባህላዊ በሰው ጉልበትና በእንስሳት ኃይል የተመሠረተውን አሠራር በዘመናዊ ማሽነሪዎች በመተካት የማሳ ዝግጅትን፣ የዘር አዘራርን እና የምርት አሰባሰብን ውጤታማ አድርጓል። ትራክተርና ኮምባይነር አጠቃቀም የጊዜና የጉልበት ብክነትን ከመቀነሱ ባሻገር በምርት ስብሰባ ወቅት የሚደርሰውን ብክነት በመቀነስ የምርት ጥራትና መጠን እንዲጨምር አስችሏል። የክላስተር ግብርናና የሜካናይዜሽን ሥርዓት የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ከተለመደው የኑሮ ግብርና ወደ ተወዳዳሪ የንግድና የኢንዱስትሪ ግብዓት ምንጭነት እንዲሸጋገር በማድረግ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ አወንታዊ ተፅዕኖ፡- የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ለውጥ አምጥቷል። በተለይም የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መስፋፋቱ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በመተካት የምግብ ራስን የመቻል ግብን እያሳለጠ ይገኛል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የንግድ ሚዛንን በማሻሻል ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንዲፈጠር ዕድል ከፍቷል። በሌላ በኩል የስንዴ ምርት መጨመሩ የምግብ አቅርቦትን በማረጋጋትና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በማጎልበት የአርሶና አርብቶ አደሩን ምርታማነት የበለጠ ለማጠናከር እያስቻለ ነው። የይቻላል ተምሳሌቱ፤ የበጋ ስንዴ ምርታማነት፡- የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት የግብርና ስኬት ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ አብዮትም ነው። ለዘመናት ስንዴን ከውጭ ማስገባት የማይቀር የሚመስለውን እሳቤ በመስበር ከጥገኝነት የመላቀቅ መንፈስን አጎልብቷል። በመስኖ የተደገፈ ዓመቱን ሙሉ የማምረት ባህልን በማስፋፋትም ለሌሎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተነሳሽነት ፈጥሯል። ከአፍሪካ ቀዳሚነት ወደ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ፡- የስንዴ ልማቱ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ አቅም በመፍጠር በአፍሪካ ቀዳሚ አምራች ሀገር አድርጓታል። የመስኖ ልማት መስፋፋትና ቆላማ አካባቢዎችን ወደ ምርታማ የስንዴ ማሳዎች መቀየር ለኢኮኖሚው ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለአፍሪካ የተግባር ምሳሌ፡- የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለምሥራቅ አፍሪካና ለመላው አህጉሪቱ በምግብ ራስን መቻል እንደሚቻል በተግባር አሳይቷል። የውጭ የስንዴ ገቢ ምርት ጥገኝነትን በማስቀረት በአፍሪካ ምድር የምግብ ሉዓላዊነት ሊረጋገጥ እንደሚችል ተጨባጭ ውጤት አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች እንደገለጹት፤ ከስንዴ እርዳታና ከውጭ ጥገኝነት መላቀቅ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በሀገር ውስጥ ምርት ማረጋገጥ እና መሬትና የመስኖ ውኃን በአግባቡ በመጠቀም ኢትዮጵያን ከምርት ተቀባይነት ወደ አምራችነትና ወደ ላኪነት ማሸጋገር እየተቻለ ነው። ማጠቃለያ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በኢትዮጵያ የተመዘገበ የግብርና ስኬት ብቻ አይደለም፤ የአስተሳሰብ፣ የፖሊሲ፣ የቴክኖሎጂ እና የሀገራዊ ቁርጠኝነት ፍሬ የሆነ የልማት አብዮት ነው። ለዘመናት የውጭ ጥገኝነት ምልክት ሆኖ የቆየውን የስንዴ አቅርቦት ችግር በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ኢትዮጵያ ከአስመጪነት ወደ ላኪነት የምትሸጋገርበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍታለች። ይህ ስኬት የአንድ የግብርና ፕሮጀክት ውጤት ብቻ ሳይሆን መሬትን፣ ውኃን፣ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂን እና የአርሶ አደሩን ትጋት በአንድ ራዕይ ያስተሳሰረ የብልፅግና ሞዴል መሆኑን አሳይቷል። በተለይም የክላስተር ግብርና፣ የመስኖ ልማት፣ የሜካናይዜሽን መስፋፋት እና የተሻሻሉ የምርት ቴክኖሎጂዎች ተቀናጅተው ሲተገበሩ ግብርና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገር ኢኮኖሚን የመቀየር አቅም እንዳለው በተግባር አረጋግጧል። ከዚህ በኋላ የሚጠበቀው ይህንን ስኬት በማስቀጠል የጥራት ማሻሻያን፣ የእሴት ጭማሪ ኢንዱስትሪዎችን፣ የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነትን እና የግብርና ዲጂታላይዜሽንን በማጠናከር ስንዴን ከምግብ ዋስትና ባሻገር የውጭ ምንዛሬ፣ የኢንዱስትሪ ግብዓት እና የሀገራዊ ኢኮኖሚ መረጋጋት ስትራቴጂያዊ ምሰሶ ማድረግ ነው። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የኢትዮጵያን ይቻላል መንፈስ በማሳየት የምግብ ራስን መቻልን ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን፣ የውጭ ምንዛሬ አቅምን፣ የአፍሪካ የልማት ተምሳሌትነትን እና የቀጣይ ትውልድ የብልፅግና መሠረትን እየገነባ ነው። በዚህም የተገኘው የግብርና ድል የአንድ ወቅት የምርት ጭማሪ ሳይሆን የኢትዮጵያን የዕድገት ታሪክ የሚቀይርና ለአፍሪካም አዲስ የልማት አድማስ የሚከፍት ዘላቂ ስኬት ሆኖ ይቀጥላል።
በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
Jul 28, 2026 168
ባህር ዳር፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ። የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ "ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ" በሚል መሪ ቃል የ2018 አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል። የቢሮ ኃላፊው መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ። ቢሮው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ100 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል። የተሰበሰበው ገቢ ለክልሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት በማዋል በራስ የመልማት አቅም ለመገንባት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ነው የተናገሩት። ቢሮው ከባህዳር ዩኒቨርሲቲና ከኢትዮ-ቴሌኮም ኩባንያ ጋር በመተባበር በዲጂታል ግብር የመክፈል ስርአት መዘርጋቱ ለዘርፉ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማበረከቱን አስረድተዋል። ይህም ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው ግብር በመክፈል ፈጣን፣ ተአማኒነት ያለውና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም እሸቴ በበኩላቸው፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 91 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል። በተሰበሰበው ገቢም በከተማዋ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን በማከናወን የህዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚውል እንደሆነም አስረድተዋል። በ2019 በጀት ዓመትም የግብር አሰባሰብ ስርአቱን ይበልጥ ግልጽ፣ ፍትሐዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ለማድረግ በተሻለ መንገድ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል። በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይም ለምስጉን ግብር ከፋዮችና ከፍተኛ ገቢ ለሰበሰቡ ተቋማት እውቅና የመስጠት ስነ ስርአት ተካሂዷል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የሦስት ሀገራት አምባሳደሮችን አሰናበቱ
Jul 28, 2026 229
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የሦስት ሀገራት አምባሳደሮችን አሰናበቱ። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ፣ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክርቲንሰን እና የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አሰናብተዋል። አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ሁለገብ ግንኙነቶችና ትብብርን ለማጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፕሬዝዳንቱ ምሥጋና አቅርበዋል። ፕሬዚዳንቱ አምባሳደሮቹ ከኢትዮጵያ ጋር ላላቸው የቆየ አጋርነት ላሳዩት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸው፣ ለቀጣይ ሥራዎቻቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታላቅ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ናት። በኢትዮጵያ በቆዩበት የሦስት ዓመታት የሥራ ዘመን በርካታ ውድ የሆኑ ተሞክሮ የቀሰምኩበት ነው ያሉት አምባሳደሯ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ሚናዋን በአግባቡ እየተወጣች መሆኑን አድንቀዋል። ፊንላንድ እና ኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በገጠር የንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በግብርና እና በዲጂታል የመሬት ምዝገባ ዘርፎች የቆየ ትብብር እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ዘመናዊ እና ፈጣን ሽግግር አድንቀው፤ ይህም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በፈጠራ፣ በስታርት አፕ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኢንቨትምነት ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት የፊላንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵየ እንዲሰማሩ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመው፤ እንደ ኖኪያ እና ቫይሳላ ያሉት ኩባንያዎችን በማሳያነት አንስተዋል። የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክርስቲንሰን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል። ኢትዮጵያና ኖርዌይ በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ፣ በደን ልማት ዘርፎች ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል። የአረንጓዴ አሻራ፣ የደን ጥበቃ ሥራዎችና በኢትዮጵያ ኑሮን ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራትን ኖርዌይ መደገፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል። የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ፤ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን ያደረጉትን ታሪካዊ ጉብኝት በማስታወስ፤ በጉብኝቱ ወቅት ከተደረሱት ስምምነቶች መካከል ብዙዎቹ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን እያሰፉ ሲሄድ፣ ተጨማሪ የህንድ ኢንቨስትመንቶች ወደ አገሪቷ እንደሚመጡም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት በዘርፉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል
Jul 28, 2026 248
ዲላ፣ ሐምሌ 21/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ልዩ ትኩረት በዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠሩም በላይ ቆይታችን እንድናራዝም አድርጎናል ሲሉ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች ገለጹ። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የመጡት ቱሪስቶች በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት በኢትዮጵያ ባዩት የመዳረሻ ልማት፣ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጥራት እና በህዝቡ እንግዳ አቀባበል መደሰታቸውን ቱሪስቶቹ ገልጸዋል። ከስፔን የመጡት ዶክተር አና ፕካሶ ለኢዜአ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው አዲስ አበባን፣ ባህር ዳርን እንዲሁም የጌዴኦ ዞንን በጎበኙበት ወቅት ለቱሪስቶች እጅግ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተመልክተዋል። በጎበኟቸው የመዳረሻ ስፍራዎች ኢትዮጵያ የብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች እና የባህላዊ እሴቶች ባለቤት መሆኗን ለመረዳት መቻላቸውንም ጠቅሰዋል። በተለይ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራት፣ በመዳረሻ ልማት እንዲሁም በህዝቡ እንግዳ አቀባበል መደሰታቸውን አንስተው፣ በዚህም የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም መወሰናቸውን ተናግረዋል። በጌዴኦ ባህላዊ መልከዓ ምድር ውስጥ በተመለከቱት አስደናቂ የአካባቢ ጥበቃ ባህል መደነቃቸውን የገለጹት ደግሞ ከጣሊያን የመጡት ጎብኚ ኢንጅነር ሆሴ አንቶኒዮ ናቸው። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለሚደረጉ ጥረቶች እንደ ትልቅ ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን አመልክተው፣ በኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት የተከናወኑ ተግባራት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ አናቤል ሮዲጌዝ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያዩዋቸው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ቱሪስቶችን ለመሳብ ከፍተኛ አቅም ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል። የጌዴኦ ባህላዊ መልከዓ ምድርን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ባዩት ነገር መደሰታቸውን ጠቁመው፣ እንዲህ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን የበለጠ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ዘርፉን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባም አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ቆይታቸውን እንዲያራዘሙ ማድረጉን ያነሱት ደግሞ ከስፔን የመጡት ካሮሊና ኢዩስካስ ናቸው። በቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ባዩት ነገር መደነቃቸውን በመግለጽ፣ እንዲህ ዓይነት አካባቢዎችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል። የጌዴኦ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም ግብይትና ፕሮሞሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በደቻ በበኩላቸው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዞኑ ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። በተለይም የይርጋጨፌ ቡና ባህላዊ ዝግጅትና ልዩ ጣዕሙ በርካቶች ዞኑን መዳረሻ እንዲያደርጉ ማስቻሉን ጠቁመዋል። በአዲሱ በጀት ዓመትም ከ2 ሺህ የሚልቁ የውጭ እና ከ40 ሺህ በላይ የሚደርሱ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ለመቀበል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል። ለዚህም በአሁኑ ወቅት ነባር እና አዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በመለየትና በማልማት፣ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖለቲካ

የአፍሪካ ህብረት በዘላቂነት ራሱን ለመቻል የፋይናንስ ነጻነትና መዋቅራዊ ሪፎርም ወሳኝ ነው
Jul 28, 2026 203
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን ችግሮች በራሱ የሚፈታና የልማት አጀንዳዎቹን በውጤታማነት የሚያስፈጽም እንዲሆን የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥና የመዋቅራዊ ሪፎርም ሂደቶችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በዚህ ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ስብሰባው በህብረቱ በጀት፣ በፋይናንስ ራስን መቻል፣ በመዋቅራዊ ሪፎርምና በሌሎች አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት በራሱ አቅም የሚመራና የአህጉሪቱን የልማት አጀንዳዎች በውጤታማነት የሚያስፈጽም እንዲሆን አባል ሀገራት የህብረቱን በጀት በራሳቸው አቅም የመሸፈን ቁርጠኝነት ሊያሳዩ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በስብሰባው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር መግለጻቸውን አስታውሰዋል። አፍሪካ በሰላምና ደህንነት፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት በርካታ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመው፤ እነዚህን በውጤታማነት ለማስፈጸም የአፍሪካ ህብረት በፋይናንስ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ተቋም መሆን እንዳለበት ገልጸዋል። አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አህጉር መሆኗን በመጥቀስም፣ ሀብቷን ለጋራ ጥቅም ለማዋል በትብብርና በጋራ አሰራር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ያመለከቱት አምባሳደር ነብያት፤ ይህም በኢትዮጵያ የቀረበ ቁልፍ መልዕክት መሆኑን ጠቁመዋል። በስብሰባው በበጀት፣ በፋይናንስ ራስን መቻልና በመዋቅራዊ ሪፎርም ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች የህብረቱን የገንዘብ አቅም የሚያጠናክሩ ዘላቂ የፋይናንስ መሰረት የሚፈጥሩ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል። አምባሳደር ነብያት አክለው እንደገለጹት፣ አጀንዳ 2063 የአፍሪካ ህብረት የረጅም ጊዜ የልማት ርዕይ ሲሆን፣ የሰላምና ደህንነት፣ የሰዎች ነጻ እንቅስቃሴ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች አህጉራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮችን ያካተተ ነው ብለዋል። የልማት አጀንዳዎቹ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎች እየተገመገሙ የአፈጻጸም ሂደታቸውንም በቀጣይነት የሚከታተለው መሆኑን ጠቁመው፤ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ከሚያጸድቃቸው ምክረ ሀሳቦች በመነሳት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የመጨረሻ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ገልጸዋል። አፍሪካ ሙሉ ነጻነቷን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ ነጻነት እውን መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለዚህም አባል ሀገራት የጋራ ተቋማቸው ለሆነው የአፍሪካ ህብረት በቂ የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስና የራሱን አጀንዳዎች በራሱ አቅም የሚያስፈጽም ተቋም እንዲሆን የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አምባሳደር ነብያት አንስተዋል።
ኢትዮጵያና አዘርባጃን ለጋራ ልማትና ብልጽግና ትብብራቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 28, 2026 211
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና አዘርባጃን በተለያዩ ዘርፎች ለጋራ ልማትና ብልጽግና ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከአዘርባጃን ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፤ የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። አፈ-ጉባኤው ለአዘርባጃን ልዑካን ቡድን ስለ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹና አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠሯንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎችንና አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ሥራዎችን ከማከናወኗ ባሻገር አልሚዎችን የሚደግፍ ፖሊሲ ቀርጻ እየተገበረች እንደሚገኝ የጠቀሱት አፈ ጉባኤው፤ ሀገሪቱ በግብርና፣ በማዕድንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም እንዳላት አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ስኬታማ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዷንና አገራዊ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት ገለልተኛ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ምክክር ላይ መሆኗን ገልጸዋል። አያይዘውም ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር በተለያዩ መስኮች ለጋራ ብልጽግና ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። የአዘርባጃን ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተለያዩ ጊዜያት በአዘርባጃን ያደረጓቸው ጉብኝቶች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። አዘርባጃን በትምህርት፣ በአቅም ግንባታና በግብርና ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በትምህርት ዕድል ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈረም ጠቁመዋል። የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያጸና መሆኑን ጠቅሰው፤ አዘርባጃን ለዚህ ስኬት በቁርጠኝነት እንደምትሠራና ከተለያዩ የትብብር መስኮች በተጨማሪ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ዲሞክራሲን ለማፅናትና የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻል እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 28, 2026 179
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ ዲሞክራሲን ለማፅናትና የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻል እየተከናወኑ የሚገኙ ስኬታማ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ። በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል። በዚህ ወቅት አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፓርቲውን በአሰራር፣ በሰው ሀይል እና በአደረጃጀት የማጠናከር ስራ ተሰርቷል። በበጀት አመቱ ዲሞክራሲን ለማፅናት መሰረት የጣሉ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል። ገዥ ትርክትን በመገንባት ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ አዎንታዊ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተሻለ አፈጻጸም እንዲተገበር በቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሰራር መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል። ስራዎችን በማቀናጀት በተለይም የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት፣ የገበያ መረጋጋትን በማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። እንዲሁም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ ስራዎች እንደሚሰሩም አብራርተዋል። በተለይም ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪክ ማህበራት ጋር የቅንጅት ስራዎች በማስቀጠል ስኬቶችን የበለጠ ማላቅ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል። የተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎች ባህል እንዲሆን ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የማጠናከር ስራም መጠናከር አለበት ነው ያሉት። ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት እየተደረጉ የሚገኙ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። “አዲሱ በጀት ዓመት ህዝቡን ይበልጥ የምናገለግልበት፣ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርጉ ስራዎችን አጠናክረን ለማስቀጠል የክትትልና ድጋፍ ተግባራት የሚጠናከሩበት ይሆናል” ሲሉም ገልጸዋል። የታቀዱ ግቦችን ለማሳካት በየደረጃው የሚገኘው አመራር በቁርጠኝነትና በከፍተኛ ትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ አሰባሳቢና ገዥ ትርክት በመገንባት ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጽናት ረገድ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል-ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
Jul 28, 2026 230
ሮቤ፣ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አሰባሳቢና ገዥ ትርክት በመገንባት ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጽናት ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ 'ውጤታማ ተግባቦት ለጠንካራ ፓርቲ' በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶች ላይ የሚመክር መድረክ በባሌ ሮቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ አሰባሳቢና ገዥ ትርክት በመገንባት ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጽናት ረገድ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። የፖለቲካ ምህዳሩን አካታች፣አሳታፊና የሃሳብ ብዝሃነት የሚንሸራሸርበት በማድረግ እንዲሁም የዳበረ የዴሞክራሲ ስርአት በመገንባት ሂደት ጠንካራ መሰረት እያኖረ መሆኑንም ገልጸዋል። በፓርቲው አባላትና አመራሮች መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲሁም የገዥ ትርክት ግንባታ እንዲጠናከር ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በተጨማሪም ከቤተሰብ ጀምሮ በሀገር ደረጃ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ስለመከናወናቸው አንስተው በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉ ተናግረዋል። አካታች፣ አቃፊና አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲኖር የሚያስችሉ ተግባራት በህዝብ ግንኙነት ዘርፉና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መከናወናቸውንም አብራርተዋል። "ብልጽግና ፓርቲ ብቻውን ሀገር ለመለወጥ የተነሳ አይደለም" ያሉት ዶ/ር ቢቂላ፤ በሀገር ጉዳይ በመደመር እሳቤ አካታችና አሳታፊ የሆነ አዲስ የፖለቲካ እሳቤ እንዲጎለብት አድርጓል ብለዋል። በ2018 የበጀት ዓመት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊ፣ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ መካሄዱም ትልቅ ሀገራዊ ስኬት መሆኑን አንስተዋል። በምርጫው ህዝቡ ለብልጽግና ፓርቲ በሰጠው ይሁንታ መሰረት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት መንግሥት በመመስረት በላቀ መልኩ ህዝባዊ አደራውን ለመወጣት መዘጋጀቱንም ተናግረዋል። በዚህም መሰረት በሚቀጥሉት አምስት አመታት ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ለመስራት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዚምባብዌ እና ቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
Jul 28, 2026 231
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ) ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው 49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ከዚምባብዌ አቻቸው ከፕሮፌሰር አሞን ሙርዊራ ጋር ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ እና ዚምባብዌ ጠንካራ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸው እና በአፍሪካ ሕብረት፣ በፓንአፍሪካኒዝምና በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ ምልከታ እንዳላቸው በውይይቱ ወቅት ተገልጿል። ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር በተለያዩ ዘርፎች የተለዋወጧቸው የትብብር ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማካሄድ ተስማምተዋል። በተመሳሳይ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቤኒን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሪን አሞሪ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። ሚኒስትሮቹ ሁለቱ ሀገራት ከአሁን በፊት የተፈራረሟቸውን ሥምምነቶች ወደ ተግባር በሚለውጡባቸው አግባቦች ዙሪያ ሐሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፣ ቤኒን ከኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ልምድ ለመቅሰም ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሯ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ተመካካሪዎች የሚያቀርቧቸው ሃሳቦች በሚገባ እየተሰነዱ ነው - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Jul 28, 2026 237
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ እስካሁን ተመካካሪዎች የመከሩባቸው ጉዳዮችና ያቀረቧቸው ሃሳቦች በሚገባ እየተሰነዱ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የምክከሩን የእስካሁን ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ላለፉት ሁለት ቀናት አራት ሺህ ተሳታፊዎች በጥቃቅን ቡድን ተከፋፍለው(በ 50 ቡድን) አስር አስር በመሆን በተሰጣቸው አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ የመከሩባቸው ጉዳዮችም እየተሰነዱ መሆኑንና ተመካካሪዎች የሚያቀርቧቸው ሃሳቦች በሚገባ እየተሰነዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው የምክከር ሂደት(የጥቃቅን ቡድን) ወደ ንዑስ ቡድን ተሻጋግሮ በሚገባ ምክክር እንደሚደረግም ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡ በምክክሩ ሁሉም ተመካካሪዎች ሃሳባቸውን በነጻነት እና በግልጽ እያቀረቡ እንደሚገኙ ገልጸው እስካሁን ያለቀና የተወሰነ ነገር አለመኖሩን አብራርተዋል፡፡ ሀሳቦች እየተቀራረቡ ቢሆንም ነገር ግን ውሳኔ የሚቀርብበት ምዕራፍ ላይ ገና አልተደረሰም ሲሉም አስታውቀዋል፡፡ የፊታችን ሰኞ የ250ዎቹ (ስልታዊ ቡድን) ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ 500ዎቹ እንሸጋገራለን የሚል እምነት እንዳላቸውም ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጠቁመዋል፡፡ ተመካካሪዎች ይህንን ታሪካዊ ሂደት በሚገባ እንዲጠቀሙበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡ የኮሚሽኑ ዓላማ ሁሉም በእኩልነት እንዲነጋገር መሆኑን ጠቁመውም የምክክሩ ስነ ዘዴ ሁሉም እኩል አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
አካታችና አሳታፊ የሆነው ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ አቅም ይፈጥራል
Jul 28, 2026 223
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አካታችና አሳታፊ የሆነው ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ስምንት የምክክር አጀንዳዎችን በመለየት ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። ሁሉንም አሳታፊ ያደረገው ይህ የምክክር መድረክ ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ በመመካከር መፍትሄ ለማበጀት ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኗል። ተመካካሪ አቶ ተስፋዬ ያዴሳ እንደገለጹት፤ የምክክር መድረኩ ሁሉንም ያሳተፈና አካታች በመሆኑ በጋራ መግባባት ሀገርን ማስቀጠል እንደምንችል ያየንበት አጋጣሚ ነው፡፡ ቀደም ሲል ልንግባባባቸው ያልቻልናቸውን ነገሮች በሰፊው እየተወያየንባቸውና እየተግባባንባቸው እንገኛለን ያሉ ሲሆን፤ ምክክሩ ሀሳባችንንና የማህበረሰባችንን ፍላጎት ያለምንም ገደብ በነጻነት እንድንገልጽ ሰፊ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡ ምክክሩ ውስጣዊ ስሜታችንንና አመለካከታችንን ያለምንም ገደብ እንድንገልጽ ዕድል የፈጠረና ተስፋ ሰጪ ሂደት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተመካካሪ ሙሉነሽ ዋቅቶላ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ክልሎች ባለፈ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ ነው። የምክክር መድረኩ አሳታፊነትና አካታችነት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል። ሌላኛው ተመካካሪ ሳሙኤል ብርሀኑ፤ ሀገራዊ ምክክሩ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁሞ፤ ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመመካከር መፍታት የሚያስችል እንደሆነም ተናግሯል፡፡ የምክክር መድረኩ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች በአንድነትና በግልጽነት ተነጋግረው እንዲተማመኑ በማድረግ ለሀገራችን ዘላቂነት ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው ያሉት ደግሞ ተመካካሪ በየነ ሶሎ ናቸው። ሁሉንም በአንድ ልብ ያቀራረበና ወደ ዘላቂ መፍትሔ የሚያሸጋግር ምክክር እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ማህበራዊ
በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት በዘርፉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል
Jul 28, 2026 248
ዲላ፣ ሐምሌ 21/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ልዩ ትኩረት በዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠሩም በላይ ቆይታችን እንድናራዝም አድርጎናል ሲሉ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች ገለጹ። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የመጡት ቱሪስቶች በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት በኢትዮጵያ ባዩት የመዳረሻ ልማት፣ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጥራት እና በህዝቡ እንግዳ አቀባበል መደሰታቸውን ቱሪስቶቹ ገልጸዋል። ከስፔን የመጡት ዶክተር አና ፕካሶ ለኢዜአ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው አዲስ አበባን፣ ባህር ዳርን እንዲሁም የጌዴኦ ዞንን በጎበኙበት ወቅት ለቱሪስቶች እጅግ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተመልክተዋል። በጎበኟቸው የመዳረሻ ስፍራዎች ኢትዮጵያ የብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች እና የባህላዊ እሴቶች ባለቤት መሆኗን ለመረዳት መቻላቸውንም ጠቅሰዋል። በተለይ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራት፣ በመዳረሻ ልማት እንዲሁም በህዝቡ እንግዳ አቀባበል መደሰታቸውን አንስተው፣ በዚህም የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም መወሰናቸውን ተናግረዋል። በጌዴኦ ባህላዊ መልከዓ ምድር ውስጥ በተመለከቱት አስደናቂ የአካባቢ ጥበቃ ባህል መደነቃቸውን የገለጹት ደግሞ ከጣሊያን የመጡት ጎብኚ ኢንጅነር ሆሴ አንቶኒዮ ናቸው። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለሚደረጉ ጥረቶች እንደ ትልቅ ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን አመልክተው፣ በኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት የተከናወኑ ተግባራት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ አናቤል ሮዲጌዝ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያዩዋቸው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ቱሪስቶችን ለመሳብ ከፍተኛ አቅም ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል። የጌዴኦ ባህላዊ መልከዓ ምድርን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ባዩት ነገር መደሰታቸውን ጠቁመው፣ እንዲህ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን የበለጠ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ዘርፉን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባም አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ልማት የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ቆይታቸውን እንዲያራዘሙ ማድረጉን ያነሱት ደግሞ ከስፔን የመጡት ካሮሊና ኢዩስካስ ናቸው። በቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ባዩት ነገር መደነቃቸውን በመግለጽ፣ እንዲህ ዓይነት አካባቢዎችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል። የጌዴኦ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም ግብይትና ፕሮሞሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በደቻ በበኩላቸው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዞኑ ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። በተለይም የይርጋጨፌ ቡና ባህላዊ ዝግጅትና ልዩ ጣዕሙ በርካቶች ዞኑን መዳረሻ እንዲያደርጉ ማስቻሉን ጠቁመዋል። በአዲሱ በጀት ዓመትም ከ2 ሺህ የሚልቁ የውጭ እና ከ40 ሺህ በላይ የሚደርሱ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ለመቀበል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል። ለዚህም በአሁኑ ወቅት ነባር እና አዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በመለየትና በማልማት፣ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ በሚሆኑ መዝገቦች ላይ ውሳኔ አሳልፏል
Jul 28, 2026 149
ቦንጋ ፤ ሀምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ በሚሆኑ የወንጀልና የፍትሐ ብሔር መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን ገለጸ ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት በዛሬው ውሎው የክልሉን መንግሥት የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድና ረቂቅ በጀት፣ እንዲሁም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የአፈጻጸም ሪፖርቶችና ጠቋሚ ዕቅዶች አድምጧል። በወቅቱም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቆጭቶ ገብረማርያም፤ ፍርድ ቤቱ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ በሚሆኑ የወንጀልና የፍትሐ ብሔር መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል። የዳኝነት ሥርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የማጥራት አቅምን በማሳደግ፣ በበጀት ዓመቱ የቀረቡ መዝገቦች ውሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ የፋይሎችን መጨናነቅ ማስቀረት መቻሉን አስረድተዋል። ጉዳዮችን በተቀመጠው የጊዜ ስታንዳርድ ውስጥ የመወሰን አቅምን ለማሳደግ የተሠራው ሥራ ውጤታማ እንደነበርም ተናግረዋል። የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት የኦዲት ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ የተሻሉ ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ ናቸው። ከክልሉ ምክር ቤት ኦዲት አስመላሽ ግብረ ኃይል ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ የኦዲት ማስመለስ ሥራውን ከ70 በመቶ በላይ ማድረስ እንደተቻለ ገልጸው በክዋኔ ኦዲት ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም እንደሚሰራም ጠቁመዋል። በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ምክር ቤቱና አስፈጻሚ አካላት በቅንጅት በሠሩት ሥራ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። በቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፎች የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል፣ የሥራ ዕድልን ከግብርና ሜካናይዜሽን ጋር ማያያዝ፣ እንዲሁም በኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል። ያልተጠናቀቁ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ማጠናቀቅን ጨምሮ፣ የገቢ አማራጮችን ማስፋፋት ላይ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ጅምሮች መጠናከር እንዳለባቸውም አመልክተዋል። ምክር ቤቱ የቀረበውን ሪፖርት ተወያይቶ በማፅደቅ ሲያካሂድ የቆየውን 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለምክር ቤት አባላት ዕውቅና በመስጠት አጠናቋል።
የጥበብ ዘርፉን አበርክቶ የሚያጎሉ ስራዎችን በጥናትና ምርምር የማገዝ ተግባር እየተከናወነ ነው
Jul 28, 2026 163
ባህር ዳር፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥበብ ዘርፉን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለውን አበርክቶ ለማጉላት የሚያስችሉ ስራዎችን በጥናትና ምርምር የማገዝ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለፀ። በዘርፉ የሚሰማሩ ወጣት ሴቶች እያጋጠማቸው ባለው ተግዳሮትና መፍትሔ አመላካች ጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ተካሄዷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት፤ የጥበብ ዘርፍ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያለውን የላቀ አበርክቶ በአግባቡ መጠቀም ይገባል። በዚህም ጥበብ ከመዝናኛነት ባለፈ የማኅበረሰብ ግንኙነትን በማጠናከር ለሰላም ግንባታና ለዘላቂ ልማት ለማዋል እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተለይም የኪነ-ጥበብ እና ዕደ-ጥበብ ዘርፉ ለበርካታ ወገኖች የሥራ ዕድል ፈጠራ እያገዘ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዚህ ቀደም ዘርፉን በጥናትና ምርምር በማገዝ በኩል ክፍተት እንደነበረ አንስተው፤ አሁን ላይ አበርክቶውን የበለጠ ለማሳደግ መንግሥት በሰጠው ትኩረት መሠረት በምርምር ታግዞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ወጣት ሴት የጥበብ ባለሙያዎች ወደ ጥበብ ዘርፉ ለመግባትና ከገቡ በኋላም በሙያው የመዝለቅ ችግር እንደሚስተዋል አመልክተዋል። በመሆኑም የተጠቀሱትንና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ የፈጠራ አቅማቸውን በመጠቀም የተሻለ አበርክቶ እንዲኖራቸው የማድረግ ተግባራት በቅንጅት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም የጥበብ ዘርፉ ኢኮኖሚውን በዘላቂነት መደገፍ እንዲችል በጥናትና ምርምር የታገዘ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አንስተው፤ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ብሎም የጥናት ፕሮጀክቱ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ በበኩላቸው፤ በሀገራችን በዘርፉ የሚሰማሩ ወጣት ሴቶች የተለያዩ ተግዳሮቶች እየገጠማቸው መሆኑ በተደረገው ጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል። በዚህም በቤተሰብም ሆነ በማኅበረሰቡ ዘንድ በሚስተዋል ያልተገባ ጫና በዘርፉ የሚሳተፉ ሴቶች ተሳትፎ በሚፈለገው ልክ ማደግ እንዳልቻለ አንስተዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዝ ጥናት መካሄዱን አንስተው፤ ጥናቱ በአምስት ክልሎች 500 የሚደርሱ ተሳታፊዎችን በመድረስ የተዘጋጀ መሆኑን አክለዋል። በሦስት ዓመታት በተካሄደው ጥናትም 13 ተመራማሪዎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው፤ የጥናት ውጤቱም ለፖሊሲ አውጪዎች ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል። ጥናቱ በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆንም ሚዲያውን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አመልክተዋል። በመድረኩ የክልል አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የጥበብ ሰዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች ለከተማዋ ዕድገት ጉልህ ሚና እያበረከቱ ነው
Jul 28, 2026 104
ወልቂጤ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ በወልቂጤ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የከተማዋን ዕድገት እያፈጠኑ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ገለጹ። በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትእና የድልድይ ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች በዘላቂነት የሚመልሱ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ነው ያስታወቀው ። የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት እየተከናወኑ ነው። በከተማዋ የኮሪደር ልማት፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ዝርጋታ፣ጤናና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የበርካታ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የነዋሪውን የልማት ጥያቄ በዘላቂነት ከመመለስ ባለፈ የከተማዋን ዕድገት እያፈጠኑ እንደሚገኙ ነው ያስረዱት ። ይህም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማጠናከር ከተማዋን ተመራጭ እያደረጋት መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ ሙራድ ለበርካቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል ። ለአገልግሎት የበቁትን ጨምሮ አስተዳደሩ የሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በበኩላቸው፤ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እንዲቻል የተሻለ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዞኑ በ2018 በጀት አመት በህብረተሰብ ተሳትፎ በተገኘ ከ620 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻልና አዳዲስ ግንባታዎች ማከናወን መቻሉንም ነው የገለጹት። ይህም ለመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ ኑርድዋን ዱላ እና ወይዘሮ አነኋት ያሰና በበኩላቸው ፤ነዋሪው ለረጅም ጊዜ ሲነሳቸው የነበሩ የመንገድ እና ሌሎችም መሰረተ ልማት ጥያቄዎች በመመለሳቸው ተጠቃሚ አድርጎናል ነው የሚሉት። አስተዳደሩ ህዝቡ የሚያቀርባቸውን የልማት ጥያቄዎች በማዳመጥ እየሰጠ ያለው ምላሽ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ነው የተናገሩት። ለአብነትም በአካባቢው ለረዥም ጊዜ ሲቀርብ ለነበረው የድልድይ ግንባታ ፈጣን ምላሸ መሰጠቱ በውሃ ሙላት ምክንያት ይጠፋ የነበረው የሰው ህይወትን በማስቀረት እፎይታን የሰጠ እንደሆነም አመልክተዋል።
ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
Jul 28, 2026 168
ባህር ዳር፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ። የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ "ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ" በሚል መሪ ቃል የ2018 አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል። የቢሮ ኃላፊው መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ። ቢሮው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ100 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል። የተሰበሰበው ገቢ ለክልሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት በማዋል በራስ የመልማት አቅም ለመገንባት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ነው የተናገሩት። ቢሮው ከባህዳር ዩኒቨርሲቲና ከኢትዮ-ቴሌኮም ኩባንያ ጋር በመተባበር በዲጂታል ግብር የመክፈል ስርአት መዘርጋቱ ለዘርፉ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማበረከቱን አስረድተዋል። ይህም ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው ግብር በመክፈል ፈጣን፣ ተአማኒነት ያለውና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም እሸቴ በበኩላቸው፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 91 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል። በተሰበሰበው ገቢም በከተማዋ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን በማከናወን የህዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚውል እንደሆነም አስረድተዋል። በ2019 በጀት ዓመትም የግብር አሰባሰብ ስርአቱን ይበልጥ ግልጽ፣ ፍትሐዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ለማድረግ በተሻለ መንገድ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል። በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይም ለምስጉን ግብር ከፋዮችና ከፍተኛ ገቢ ለሰበሰቡ ተቋማት እውቅና የመስጠት ስነ ስርአት ተካሂዷል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ177ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈን ተችሏል
Jul 28, 2026 113
ደብረ ብርሃን፤ ሐምሌ 21/ 2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተያዘው ክረምት ከ177 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ ወይዘሮ ሁሉምታየ ዘነበ እንደገለፁት፤ በዚህም በ2018/19 የመኸር ምርት ዘመን 563 ሺህ 336 ሄክታር መሬት በሰብል ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል። ባጠቃላይ ከሚለማው ማሳ ውስጥም ከ308 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን በኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ በመጠቀም በጤፍ ፣ ስንዴ ፣ ማሽላ፣ በቄላና ማሾ ሰብሎች ለማልማት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አስካሁን በተደረገው ጥረትም 196 ሺህ 417 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ177 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል። የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎችም አርሶ አደሩ የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴን፣ሌሎች የተሻሻሉ አሰራሮችንና ግብአትን ተጠቅመው በመዝራት ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በተጨማሪም ዝናቡ ዘግይቶ በጣለባቸው አካባቢዎች ፈጥነው የሚደርሱ ሰብሎችን እንዲዘራና በማሳው ዳር እና ዳር ውሃን አቅቦ የሚያቆይ ጉድጓድ በመቆፈር እንዲጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በዞኑ የሞረትና ጅሩ ወረዳ አርሶ አደር የሆኑት መዝገቡ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ስድስት ሄክታር መሬታቸውን በኩታ ገጠም በማረስ በስንዴ፣በጤፍና በጥራጥሬ ሰብሎች ሸፍነዋል። በአሁኑ ወቅትም ቡቃያውን መንከባከብ መጀመራቸውን ነው የተናገሩት። ሌላው የዚሁ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ማሙሽ በቀለ በበኩላቸው፤ያለው የዝናብ ስርጭት ጥሩ በመሆኑ ሶስት ሄክታር መሬታቸውን በሰንዴ ሰብል መሸፈን መቻላቸውን አስረድተዋል። ምርታማነታቸውን ለማሳደግም የሚያስፈልጋቸውን ማዳበሪያና ምርጥ ዘርን በወቅቱ ማግኘት በመቻላቸው ፈጥነው ወደ ዘር ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል። በዞኑ ከመኸር እርሻ 20 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በክልሉ የቡና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ከፍ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል
Jul 28, 2026 170
ሚዛን አማን፣ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቡና ልማትን በማስፋፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከፍ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኮጁአብ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ከቡና የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍ ለማድረግ ልማቱን የማስፋፋትና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በዚህም በክረምቱ ወራት ከ25 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞችን ለመትከል ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል። የቡና ልማቱን ለማሳካት ዝርያቸው የተሻሻሉና ለደጋና ቆላማ አየር ንብረት ተስማሚነታቸው በምርምር የተረጋገጡ ችግኞች ለአርሶ አደሩ መሰራጨታቸውን ጠቁመዋል። የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለምርት የሚደርሱ እና ከነባሩ የቡና ዝርያ በእጥፍ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ልማቱን ለማሳካትም ሙያዊ ድጋፋና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ አርሶ አደር ሰሎሞን ብርሃኔ ከቡና የሚያገኙትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያላቸውን የቡና ማሳ በየዓመቱ እያስፋፉ መሆኑን ገልጸዋል። አምና ከወረዳው ያገኙትን አንድ ሺህ "ኬ1" የተሰኘ ምርጥ የቡና ችግኝ መትከላቸውንና ዘንድሮም ተግባሩን በማስቀጠል አንድ ሺህ ችግኞችን ለመትከል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ነባሩን የቡና ዝርያ በምርምር በተገኙ የቡና ዝርያዎች እየተኩ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር ጢሞቴዎስ ከሮ እና ታደሰ እጅጉ ናቸው። ቡናን ከማልማት ባሻገር ጥራቱን ለማስጠበቅ በግብርና ባለሙያ ትምህርት ታግዘው እየሠሩ መሆናቸውን አመልክተዋል። ያላቸው ማሳ ላይ በየዓመቱ አዳዲስ ችግኞችን እየተከሉ የቡና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ትኩረት መስጠታቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 614 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና እየለማ መሆኑ ታውቋል።
ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር ለጠንካራ ኢኮኖሚ ግንባታ ሚናውን እየተወጣ ነው
Jul 28, 2026 118
ጅማ ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር አገልግሎት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ። በጅማ ከተማ በዛሬዉ ዕለት የገጠር ካዳስተር ስፍር የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሂዷል። በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ ፣ የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ሀላፊ መሠረት አሰፋ እና ሌሎችም የዞን እና የወረዳ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ በወቅቱ እንደገለጹት ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ የመሬት አስተዳደር ትልቅ ሚና አለው። ይህንን ከግብ ለማድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር አገልግሎት ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። በክልሉ የተሰራው የካዳስተር ስራም ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል። ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር አገልግሎትን በማሳካት ወደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የመቀየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ። የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ሀላፊ መሠረት አሰፋ በበኩላቸዉ የመሬት ካዳስተር አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን አስገኝቷል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ አርሶ አደሮችን ወደ ኢንቨስትመንት ማሸጋገር ፣ የመሬት ብክነትን ማስቀረትና ግልፅና ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ። በክልሉ በ21 ዞኖች ለ4 ሚሊዮን 69 ሺህ 179 አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን አስታውቀዋል። የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው የካዳስተር አገልግሎት የዞኑን ገቢ ከማሳደግ በተጨማሪ ኢንቨስትመንትን እያጠናከረ ነዉ ብለዋል። ግልፅነትን በማስፈን ሀብትን በአግባቡ መጠቀም ያስቻለ መሆኑንም አመልክተዋል። የጅማ ዞን መሬት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አብዱልሀሚድ ሀጂ በዞኑ የተጀመረዉ የመሬት ካዳስተር አገልግሎት በርካታ ጠቀሜታ ማስገኘቱን ጠቁመው በ20 ወረዳዎች እና በ513 ቀበሌዎች መሬት በካዳስተር መሰፈሩን ተናግረዋል። በዚህም ለ397 ሺህ 647 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን ገልፀዋል። የካዳስተር አገልግሎት የአርሶ አደሩን የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር በማሻሻል ግንዛቤን ማሳደጉንም አክለዋል። በጅማ ዞን የሰኮሩ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዝናብ አባ ጎጀም ሁለት ሄክታር መሬታቸዉ ተሰፍሮ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘታቸዉን ተናግረዉ አገልግሎቱ መሬታቸውን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳገዛቸዉ ጠቅሰዋል። ሌላዉ የሊሙ ሰቃ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ፋሪስ መሀሙድ መሬት ወደ ካዳስተር መግባቱ ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸዉ በባለቤትነት ዙሪያ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን መፍታቱን ገልፀዉ የይዞታ ማረጋገጫ በማግኘቴ ተደስቻለሁ ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ ዲጂታል መተግበሪያዎች ገቢራዊ ተደርገዋል
Jul 28, 2026 223
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦በነዳጅና ኢነርጂ ዘርፍ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ግልጽ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ ዲጂታል መተግበሪያዎች ገቢራዊ መደረጋቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን የነዳጅ ግብይቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥርዓት መቆጣጠር የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን አስመርቋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ተቋማትን በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ በማደራጀት ምቹ የሥራ ከባቢና ቀልጣፋ አሠራር መዘርጋት ይገባል፡፡ ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሠራር ሥርዓት ለተቋማዊ ግንባታ የጎላ ሚና እንዳለው በመግለጽ፤ የዲጂታል አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ዘርፉን አሠራር ይበልጥ ማዘመንና ግልጽነትን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ተመርቀው ሥራ ላይ የሚውሉት የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የላቀና ቀልጣፋ አገልግሎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ገቢራዊ የተደረጉት የዲጂታል መተግበሪያዎች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካል መሆናቸውን ገልጸው፤ ተቋማዊ አሠራርን በቴክኖሎጂ ማዘመን ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡ የነዳጅ ዘርፉን ብልሹ አሠራር በሕጋዊ የአሠራር ሥርዓት ከመቆጣጠር ባሻገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተቀናጀ የነዳጅ ሥርዓት አበረታች ሥራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን የበለጠ ግልጽነትን ለማስፈን ከ300 በላይ ዝርዝርና 47 ጥቅል አገልግሎቶችን በዲጂታል አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ብለዋል፡፡ የመንግሥት መሻትና የሕዝብ ፍላጎት የሚሳካው አገልግሎቶችን ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ መደገፍ ሲቻል መሆኑን በማንሳት፤ የዲጂታል መተግበሪያዎች የዚህ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባለሥልጣኑ ያለማቸው የዲጂታል መተግበሪያዎች ለተቋም ግንባታ መሠረት ይጥላሉ ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ለተጀመረው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የነዳጅ አቅርቦት ግብይትና ሥርጭት የተቋማትን አቅም መገንባት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ የዲጂታል መተግበሪያው በነዳጅ ዘርፍ 29 አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ፣ በኢነርጂ ዘርፍ 36 አገልግሎቶችን በከፊል በዲጂታል ቴክኖሎጂ መስጠት ተጀምሯል ብለዋል፡፡
ኤጀንሲው የጀመራቸውን የዲጂታል አሰራሮች አጠናክሮ ይቀጥላል
Jul 28, 2026 119
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጀመራቸውን የዲጂታል አሰራሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ የኤጀንሲውን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክቶ ዋና ዳይሬክተሩ ዮሴፍ ንጉሤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ኤጀንሲው በ2018 በጀት ዓመት ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ተገልጋዮች 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የኩነትና የነዋሪነት አገልግሎቶች መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የሞትና የጉዲፈቻ ምዝገባዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ለስታትስቲክስ፣ ለፖሊሲ ቀረጻና ለአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዜጎች የልደት ምዝገባቸውን በ90 ቀናት ውስጥ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርበዋል። ኤጀንሲው የኩነት ምዝገባ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በጤና ተቋማትና በፍርድ ቤቶች የአንድ መስኮት አሰራርን ማስፋቱን ገልጸዋል። በዚህም 94 በመቶ የወቅታዊ የልደት ምዝገባዎች በጤና ተቋማት በተቋቋሙ የአንድ መስኮት ማዕከላት መከናወናቸውን፤ የፍቺና የጉዲፈቻ ምዝገባዎችም በፍርድ ቤቶች በተቀናጀ አገልግሎት 100 በመቶ መከናወናቸውን ጠቁመዋል። ከአገልግሎት ዘመናዊነት አንጻርም ኤጀንሲው በአካል በመገኘት የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ዲጂታል አሰራር ማሸጋገር መጀመሩን ጠቁመው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዚህም የልደት፣ የያላገባ ማስረጃና የመታወቂያ አገልግሎቶች ተገልጋዮች ወደ ቢሮ ሳይመጡ በዲጂታል ካሉበት ሆነው እንዲጠይቁ የሚያስችል ስርዓት መጀመሩን አስታውቀዋል። ኦንላይን አገልግሎቱ ከተጀመረ በኋላ 8 ሺህ 872 ተገልጋዮች ወደ ቢሮ ሳይመጡ አገልግሎት ማግኘታቸውንም ገልጸዋል። ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የነዋሪነት መታወቂያን የማስተሳሰር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉንና፤ ይህም የዜጎችን ማንነት በአንድ መለያ ለማረጋገጥና የሐሰተኛ ሰነዶችን አጠቃቀም ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በ2018 በጀት ዓመት 1 ሚሊየን 828 ሺህ 846 ተገልጋዮች በኤጀንሲው በኩል የፋይዳ ምዝገባ ማጠናቀቃቸውን፤ ፋይዳ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 8 ሚሊየን ያህል ተጠቃሚዎች በኤጀንሲው በኩል መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም 12 ሚሊየን የሚደርሱ የነዋሪነት ሰነዶች በዲጂታል ስርዓት እንዲቀመጡ መደረጋቸውን ገልጸው ይህም የሰነድ መጥፋትንና የመረጃ አያያዝ ችግሮችን በመቀነስ የአገልግሎት ጥራትን አሻሽሏል ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ በተከታታይ እያደገ መምጣቱንና ይህም የአገልግሎቱ ተደራሽነትና ቅልጥፍና መሻሻሉን እንደሚያመላክት ገልጸዋል። በ2019 በጀት ዓመት የሞት ምዝገባን ወደ ጤና ተቋማትና ሌሎች የማህበረሰብ ተቋማት ማስፋት፣ የመታወቂያ ህትመትን ወደ ወረዳ ማውረድና የኦንላይን አገልግሎቱን ማስፋት ዋና ዕቅዶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ኤጀንሲው በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የአገልግሎት አፈጻጸም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እውቅና እና ሽልማት ማግኘቱንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው
Jul 26, 2026 265
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ገለጹ። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የማሰልጠኛ እና የምርምር ዘመናዊ የላቀ ላብራቶሪ ስራ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ፤የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ፣የመከላከያ ሰራዊት ጀነራል መኮንኖች፣የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። ላቦራቶሪው በ20 ሺህ 850 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ለስልጠና እና ምርምር የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል። ላቦራቶሪው በውስጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የሳይበር፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣የአውቶሜሽን፣የኮሙኒኬሽን እና ኤሌክትሮኒክስ፣የነርሲንግ ሲሙሌሽን ላብራቶሪዎች በውስጡ ማካተቱ ተመላክቷል። በተጨማሪም ላቦራቶሪው ዘመናዊ የሶላር ስርዓት እና ዘመናዊ መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ተመላክቷል። የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በላቦራቶሪው መሰረተ ልማቱ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ማዋል ብቻውን በቂ አይደለም ብለዋል። ይልቁንም እውቀትን ወደ ሙያዊ ብቃት፣ምርምርን ወደ ፈጠራ እንዲሁም ፈጠራን ለሀገራችን አገልግሎት ወደሚውሉ ተግባራዊ መፍትሄዎች የሚቀይር አዲስ የትምህርት የሳይንስ እና ተቋማዊ አቅም የተከፈተበት ታላቅ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል። የዚህ የልህቀት ምእራፍ መሰረት በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መካከል ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ታሪካዊ ወዳጅነት ቀደም ሲል ከነበሩት ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር አሁን ላይ የሁለቱን ሀገራት ሀገራዊ ደህንነት፣ቴክኖሎጂያዊ ሽግግርና የተቋማትን ዘመናዊነት ወደሚያጎለብት የላቀ ምእራፍ መሸጋገሩን ጠቁመዋል። የላቦራቶሪ ማእከሉ በቁሳቁስ ድጋፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በእውቀት ሽግግር ፣በሳይንሳዊ ምርምር እና በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ትውልድን የሚቀርጽ መሆኑን ጠቁመዋል። ላቦራቶሪው የመከላከያ ሰራዊቱን ሁለንተናዊ የዘመናዊነት ጉዞ የሚያፋጥን የተቋሙን የቴክኖሎጂና ምርምር መሰረት የሚያጎለብት እና የወደፊት ሀገራዊ ደህንነት በጽኑ መሰረት ላይ የሚጥል ታላቅ እርምጃ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ዘላቂ ወዳጅነት የሚያሳይ ታሪካዊ ምልክት ነው
Jul 26, 2026 248
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ዘላቂ ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነትን የሚያሳይ ታሪካዊ ምልክት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ ገለጹ። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የማሰልጠኛ እና የምርምር ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ ስራ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። ላቦራቶሪው በ20 ሺህ 850 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ለስልጠና እና ምርምር የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ፕሮጀክቱ በእውቀት፣ በፈጠራና በሰው ኃብት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለዘላቂ ልማትና ለብሔራዊ ደህንነት መሠረት መሆኑን የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል። ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግሥት ላሳየው ድጋፍና ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል። ይህም በሁለቱ ወንድማማች ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነትና የጋራ የልማት ራዕይ የሚያሳይ ተጨማሪ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። ላቦራቶሪው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የሳይበር ደህንነት፣ የመገናኛ ምህንድስና፣ የአውቶሜሽንና የቁጥጥር ሥርዓቶች፣ የኃይል ምህንድስና፣ የ3ዲ ዲዛይን፣ የፕሮቶታይፕ ልማት እና የነርሲንግ ሲሙሌሽን ዘርፎችን የሚያካትቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው መገልገያዎችን መያዙን ተናግረዋል። ይህም ለከፍተኛ ትምህርት፣ ለሳይንሳዊ ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ለምርት ልማት፣ ለምህንድስና መፍትሔዎችና ለቴክኖሎጂ ሽግግር የተቀናጀ መድረክ እንደሚፈጥር አንስተዋል። በተጨማሪም ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኢንዱስትሪ፣በመንግሥት ተቋማትና በዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል የምርምርና የፈጠራ ትብብርን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመዋል። የማዕከሉ ስኬት በተገጠሙ መሣሪያዎች ሳይሆን በሚያፈራቸው ብቁ ባለሙያዎች፣ በሚያመነጨው ምርምር፣ በሚፈጥረው ፈጠራና ለሀገር የሚያበረክተው ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንደሚለካ ገልጸዋል።
ስፖርት
ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ መስራት ይገባል
Jul 26, 2026 224
ሀዋሳ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተወዳዳሪና ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሠረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። እ.አ.አ. በ1957 የተመሰረተው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስራች ከነበሩ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ትልቅ አሻራ አሳርፋለች። የአፍሪካ እግር ኳስ በዓለም መድረክ የሚገባውን ቦታ እንዲይዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉት የካፍ ፕሬዝዳንት የነበሩት የይድነቃቸው ተሰማ ሀገር ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ያሉባትም ናት። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ያኖረችውን አሻራና የቀደመ ገናና ታሪክ በማንሳት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧም ይታወቃል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እና የክለቡ ተጫዋች ሁሴን ጠሃ፤ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በመሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሏት አንስተው ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ዕድሎችን ለመጠቀም ብዙ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የ2018ቱ የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እንደገለጸው፤ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ሌላው ዓለም የሚሰራውን መስራት መቻል አለብን ። የስፖርት መሰረተ ልማትና የታዳጊ ስልጠና ማዕከላትን ማጠናከር፤ የምልመላ ስርዓትና የውድድር ዕድሎችን ማስፋት ቀዳሚዎች መሆናቸውን አንስቷል። ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች የሚፈሩባቸው ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የሚደረጉ ስልጠናዎችና ውድድሮች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አክሏል። አሰልጣኞችን ልምድ ባላቸው ሀገራት ማስተማር፣ ወጥ የሆነ የስልጠና ማኑዋል ማዘጋጀትና ሳይንሳዊ የሆነ የምልመላ ስርዓት መዘርጋት ሌላው ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስቷል። መንግስት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቡ በስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ መነሳሳትን እንደሚፈጥር የጠቀሰው አሰልጣኝ ያሬድ ዕድሉን መጠቀም ይገባናል ሲል ገልጿል። ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ህልም ይዞ እየሰራ ያለው የክለቡ ከ20 ዓመት በታች የግራ መስመር አጥቂ ሁሴን ጠሃ በበኩሉ፤ ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጠር ታዳጊዎችና የስልጠና ሜዳዎች ሊጠናከሩ ይገባል ነው ያለው።
የርገን ክሎፕ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
Jul 24, 2026 290
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የርገን ክሎፕን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል። የ59 ዓመቱ ጀርመናዊ የአራት ዓመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱ አሰልጣኙን እስከ 2030 የዓለም ዋንጫ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸው ነው። ክሎፕ በቦታው የተኩት በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጀርመን በ32ቱ ዙር በፓራጓይ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ከሆነች በኋላ ከኃላፊነታቸው የለቀቁትን ጁሊያን ናጌልስማንን በመተካት ነው። ከሊቨርፑል የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የሬድ ቡል ሳልስበርግ የዓለም እግር ኳስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ክሎፕ፣ የጀርመን እግር ኳስን እንደገና ወደ ቀደመ ገናናነቱ የመመለስ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ክሎፕ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም. በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ (Uefa Nations League) ከኔዘርላንድስ ጋር ያደርጋሉ።
የዓለም አትሌቲክስ የአትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን አፀደቀ
Jul 23, 2026 303
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ የኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ (women’s only) የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዛሬ ማፅደቁን ይፋ አድርጓል። አትሌት ትዕግስት እ.አ.አ አፕሪል 26 / 2026 በለንደን ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በመግባት እ.አ.አ በ2025 በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በዘጠኝ ሴኮንድ በማሻሻል አሸንፋለች። የዓለም አትሌቲክስ የአትሌቷን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረ ወሰን ዛሬ ማፅደቁን አስታውቋል። የሴቶች ብቻ (women’s only) የዓለም ክብረ ወሰን ሴቶች ብቻ በሮጡበት ውድድር ብቻ የተመዘገበ የዓለም ፈጣን ሰዓት ማለት ነው። የዚህ የዓለም ክብረ ወሰን አመዘጋገብ በሴቶች ውድድር ላይ የወንድ አሯሯጮች ወይም ወንዶች ተቀላቅለው ሲሮጡ (አጠቃላይ ሩጫ) ከሚመዘገበው የዓለም ክብረ ወሰን ጋር የሚለያይ ነው። ወንዶች በሴቶች ውድድር ላይ መኖራቸው የውድድሩን አዝማሚያ እና ሴቶች የሚያስመዘግቡት ሰዓት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። ሴት እና ወንድ ተደባልቀው በሚሮጡበት አጠቃላይ የሴቶች ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን (Overall women's world record) የያዘችው ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕጌቲች ናት። ሩት እ.አ.አ በ2024 በቺካጎ ማራቶን 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ጨብጣለች። የዓለም አትሌቲክስ ከአትሌት ትዕግስት በተጨማሪ ሰባት የዓለም ክብረ ወሰኖችን ማጽደቁን አስታውቋል። እውቅናና ፈቃድ በተሰጣቸው ውድድሮች ላይ ማሸነፍ፣ የውድድር ሜዳዎቹ የሚፈለገውን መስፈርት ያሟሉ መሆንና አትሌቶች በአበረታች ቅመም ምርምራ ውጤት ጤነኛ መሆናቸው መረጋገጥ አትሌቶች የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት የሚሆኑባቸው ዋነኛ ቅደመ-ሁኔታዎች ናቸው።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ - የመደመር እሳቤ አንዱ ማሳያ
Jul 28, 2026 179
በየዓመቱ እያደገ የመጣው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በተጨባጭ ውጤት እየታጀበ የቀጠለ ሆኗል። ዐቅምን በመሰብሰብ በመደመር ዕሳቤ እየተከናወነ ያለው ይህ ኢኒሼቲቭ በረከቱ ብዙ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነትና አመራር ሰጪነት በ2011ዓ.ም የተጀመረው ይህ መርሃ-ግብር ዛሬ ላይ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ውጤትም እየተመዘገበበት ነው። እንደየአካባቢው ሥነ-ምኅዳር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸውን ችግኞች፣ ለደን ሽፋን፣ ለከተማ ውበትና ለማረፊያ ጥላ የሚሆኑ የአፈር መከላትን የሚያስቀሩ ችግኞችን መትከል ባህል እየሆነም ነው። የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 184 ላይ እንደተጠቀሰው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ዋና ግብ የገጠርና የከተማ አረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ በማድረግ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና አስተዋጽዖ ማድረግ ነው። ይህ መርሃ-ግብር በ2011 ዓ.ም ከመጀመሩ በፊት በ 2010 ዓ.ም. የነበረው ሀገር አቀፍ የደን ሽፋን 17 ነጥብ 2 በመቶ ነበር ። በአንድ ሰው 40 ችግኝ (40 ዛፎች በነፍስወከፍ) በሚል መሪ ቃል በአንድ ቀን የተከናወነውን የአንድ ጀምበር የ 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ ተከላን ጨምሮ በተከናወነ መርሃ-ግብር የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ የሀገራችንን የደን ሽፋን በ2016 ዓ.ም 23 ነጥብ 6 በመቶ አድርሶታል። የተለያዩ ክፍላተ-ዓለማት አንድም በከፋ ቅዝቃዜ እንዲሁም መደበኛ የኑሮ ሁኔታን በሚያናጋ አደገኛ ሙቀት ብሎም በድንገተኛ ጎርፍ እና ሰደድ እሳት በሚታመሱበት ጊዜ፤ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ቀድሞ ለማረቅ አንዱ መፍትሔ አረንጓዴ ዐሻራን በስፋት ማከናወን መሆኑ ይታመናል። ባለፉት ዓመታት በብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን ርብርብ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፤ ውጤቱንም ሕዝቡ ዐይቷል። በሕዝቡ ዘንድ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ ጭምር ተደርጎ በመወሰዱ የተሳታፊዎች ቁጥርና የሚተከለው ችግኝ በየዓመቱ እየጨመረ ሊሄድ ችሏል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ጥቅሙ የሚታይ የሚጨበጥ ሆኗል። የመሬት ምርታማነትንም አሳድጓል። ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፊት (በ2010 ዓ.ም) በሔክታር የሚመረተው ስንዴ 22 ኩንታል፣ በቆሎ 30 ኩንታል፣ ጤፍ 17 ኩንታል እንዲሁም ገብስ 23 ኩንታል ነበር። ከኢንሼቲቩ ትግበራ በኋላ ደግሞ (በ2017 ዓ.ም) ስንዴ በሔክታር 36 ኩንታል፣ በቆሎ 46 ኩንታል፣ ጤፍ 20 ኩንታል፣ ገብስ 30 ኩንታል ማምረት ተችሏል። በዚህም መሠረት በ2017 ዓ.ም 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 280 ሚሊየን ኩንታል ማምረት ተችሏል። ስንዴን በትጋት በማምረትም ከውጭ ለማስገባት ይወጣ የነበረን 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት ተችሏል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፍራፍሬ ልማት ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። በዚህም ገበያውን ከማረጋጋት ባለፈ ሕብረተሰቡ (አምራቹ) ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ በዚያው ልክ እንዲያድግ አስችሏል። ይህም ኢትዮጵያም በአፍሪካ አቮካዶን በቀዳሚነት ወደ ውጭ የምትልክ ሁለተኛዋ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ጠቀሜታ ዘርፈ-ብዙ ነው። የተፈጥሮ ስነ-ምህዳርን ከመጠበቅ ባለፈ በሁሉም መንገድ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ነው። ከአረንጓዴ ዐሻራ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የባለድርሻ አካላት እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር፣ በክረምት ወራት የሚተከሉ ችግኞችን በበጋ ወራት በአግባቡ መንከባከብ ከቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ማስጀመራቸው ይታወቃል። በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ከ8 ቢሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ በሆኑበት በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በተለያዩ ዘርፎች የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በቀጥታ ለሕዝቡ ጥቅም የቆመ ሰው ተኮር መርሃ-ግብር መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ስለዚህ በቀጣይ ሕብረተሰቡ በመደመር ዕሳቤ በዚህ ኢኒሼቲቭ ላይ ያለጠባቂነት በንቃት የመሳተፍ ባሕሉን በማሳደግ ተጠቃሚነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መትጋት ይጠበቅበታል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ሉዓላዊነትና ለዘላቂ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው
Jul 28, 2026 104
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ሉዓላዊነትና ለዘላቂ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳአ ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል። በመርሃ ግብሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች ተሳትፈውበታል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እንዳሉት፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተተከሉ ያሉ ችግኞች ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ እያበረከቱ ይገኛሉ። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች የአካባቢን ሥነ-ምሕዳር ከመጠበቅ ባሻገር፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የኢንስቲትዩቱ ባለሙያ የሆኑት በሻነ ጣሰው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተጀመረ ጀምሮ ኢንስቲትዩቱ አሻራውን ሲያሳርፍ መቆየቱን ተናግረዋል። ችግኞችን ከመትከል ባሻገር የመንከባከብና አርሶ አደሩን የመደገፍ ሥራ በኢንስቲትዩቱ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል። እየተተከሉ ያሉ የፍራፍሬ ተክሎች የአካባቢውን ሥነ-ምሕዳር ከመጠበቅ ባሻገር፣ የአርሶ አደሩን የምግብ ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ቢቂላ ለሜሳ በበኩላቸው፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የተተከለው የአቮካዶ ምርት፣ ኅብረተሰቡ ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ተጠቃሚ እያደረገው እንደሚገኝ ተናግረዋል። የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው፤ እስካሁን ድረስ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዞኑ 500 ሄክታር መሬት በአቮካዶ የተሸፈነ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ክረምት ይህንን ወደ 700 ሄክታር ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ባጠቃላይ በዞኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ተከትሎ የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ምርትና ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳደጉት አመልክተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለመጪው ትውልድ ሥነ-ምሕዳሩ የተጠበቀና ምቹ አካባቢን የማሸጋገር ተግባር መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ሲኒየር ዳይሬክተር ደሳለኝ ድጉማ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል በአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ላይ ትኩረት በመስጠት በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም የአቮካዶ ምርትን በክላስተር በማዘጋጀት ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል ዛፎችን በመትከል ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው
Jul 28, 2026 101
አምቦ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ) :-የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በሦስት ሄክታር መሬት ላይ ሀገር በቀል ዛፎችንና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የማኅበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ባይሳ ለታ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን እያሳለጠ ይገኛል። በዚህም ዩኒቨርሲቲው በሦስት ሄክታር መሬት ላይ ሀገር በቀል ዛፎችንና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታውቀዋል። ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በራሱ ችግኝ ጣቢያዎች ያዘጋጃቸውን የተለያዩ ችግኞች ከመትከል ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ ሲያቀርብ መቆየቱን ጠቁመዋል። ዛሬ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ በመገኘትና ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራውን ማኖሩን ተናግረዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ብዙነሽ ሚደቅሳ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በራሱ ማዕከል ዝርያቸው እየተመናመኑ የመጡ ሀገር በቀል ዛፎችን በምርምር እያባዛ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው ከምርምር ማዕከሉ የወጡትን ችግኞች ለአካባቢው ማኅበረሰብ በማቅረብ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በተሻለ ሁኔታ እየተወጣ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በመርሃ ግብሩ የሚተከሉ ችግኞች የፓፓያ፣ የአቮካዶ፣ የሙዝ እና የሌሎች ፍራፍሬዎች ዝርያዎች መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ ዋና ዳይሬክተር ንጉሤ በቀለ (ዶ/ር) ናቸው። በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የተተከሉ ችግኞችን በማረም፣ በመኮትኮትና በመጠበቅ ውብና ጽዱ የሆነች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የዜግነት ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በዘላቂነት ለማስቀጠል ችግኞችን መንከባከብ ይገባል
Jul 28, 2026 113
ቃሉ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያስገኝ ያለውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዘላቂ ለማድረግ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ የክልሉ ግብርና ቢሮ አሳሰበ። የደቡብ ወሎ ዞን የዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በቃሉ ወረዳ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ እና ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ የማይተካ ድርሻ እያበረከተ ነው። መርሃ- ግብሩ የደን ሽፋንን ለማሳደግና የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ እያስገኝ ያለውን ጠቀሜታ ዘላቂ ለማድረግም በ260 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም የተተከሉ ችግኞችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍ ለማድረግም ህብረተሰቡ የእንክብካቤ ስራው ላይም ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ነው ጥሪ ያቀረቡት። የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው፣ በዞኑ 40 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 230 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተገኙ ውጤቶችን በተጨባጭ በመገንዘቡ የፍራፍሬ ችግኝን በስፋት እየተከለ መሆኑንም ተናግረዋል። የችግኝ ተከላ ስራው በተፋሰሶች፣ በወል መሬቶች፣ በአርሶ አደሩ ማሳና በሌሎች ቦታዎች በስፋት እየተካሔደ መሆኑን ጠቁመዋል። በየዓመቱ የተተከሉት ችግኞች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረጉ በመሆናቸው የእንክብካቤ ሰራ ላይ እንደሚሳተፉ ያነሱት ደግም የቃሉ ወረዳ 019 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሀዋ እንድሪስ ናቸው። ግማሽ ሄክታር መሬታቸውን በፍራፍሬ ችግኝ በመሸፈንም ከልማቱ እያገኙ ያለውን ጥቅም ለማሳደግ በትጋት እንደሚሰሩም ነው ያረጋገጡት። ሌላው የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ምርታማነትን ለማሳደግና የእንስሳት መኖን በበቂ ሁኔታ ለማግኝት እንዳስቻላቸው ነው የተናገሩት። በማስጀመሪያ ስነ ስርአቱ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አፍሪካ ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት በመላቀቅ የውስጥ የገቢ አቅሟን በአግባቡ መጠቀም ይጠበቅባታል
Jul 28, 2026 176
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ዘላቂ ልማቷን ለማረጋገጥ ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት ተላቃ የውስጥ የገቢ አቅሟን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክሌቨር ጋቴቴ ገለጹ። 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ይከናወናል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማና፣ የአባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች በስብሰባው መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክሌቨር ጋቴቴ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የጂኦፖለቲካ ውጥረቶች፣ የግጭቶች መበራከት፣ የብድር ክፍያ ጫና እና የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በአህጉሪቷ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። እነዚህን ፈተናዎች ለመወጣት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አባል ሀገራት የታክስ ስርዓታቸውን እንዲያዘምኑ ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ የሀገር ውስጥ ካፒታል ገበያዎችን እንዲያጠናክሩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። አህጉሪቷ በየዓመቱ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሳቢያ በርካታ ገንዘብ እንደምታጣና የታክስ መሰብሰብ አቅሟም ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቷ 16 በመቶ ብቻ መሆኑን አመልክተው፤ ይህ አሰራር በአስቸኳይ መለወጥ እንዳለበትም ተናግረዋል። በግብርና፣ በኃይል፣ በኢንዱስትሪ እና በአየር ንብረት መከላከል የተቀናጀ ፖሊሲና አሰራር መከተል እንደሚገባ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ቁጠባና ኢንቨስትመንትን ለአህጉሪቱ ልማት ማዋል እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማሸሽን መግታት እንደሚገባ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ እርስ በርስ ንግድ 17 በመቶ ብቻ ሲሆን፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሙሉ በሙሉ ሲተገበር በ2045 የውስጥ ንግድን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የመረጃ ስርዓቶችን ለማዘመንና ዲጂታል መሠረተ-ልማቶችን ለማስፋፋት መዋዕለ-ነዋይ ማፍሰስ እንደሚገባም ገልጸዋል።
አፍሪካ አጀንዳዎቿን ለማስፈጸም የራሷን ሀብት መጠቀም ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት
Jul 28, 2026 129
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ አጀንዳዎቿን ለማስፈጸምና ግቦቿን ለማሳካት የራሷን ሀብት መጠቀም ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባት የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማና ገለጹ። 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ስብሰባው እየተደረገ ያለው “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማና አፍሪካ በጋራ ጉዳዮቿ ላይ በአንድ ድምፅና በተባበረ ክንድ መቆም እንዳለባት አስገንዝበዋል። ሚኒስትሩ አፍሪካውያን ሁለንተናዊ ጥቅሟን ለማረጋገጥ በፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የጋራ አንድነት መገንባት አለባት ብለዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ የአፍሪካ ሀገራት የጋራ አቋም የያዙባቸውና የህብረቱ ማዕቀፎች በሚገባ መተግበርና አፈጻጸማቸውን መከታተል እንደሚገባም አመልክተዋል። ማዕቀፎቹ የአፍሪካን ፍላጎት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስከበር ዋና መደላድል መሆናቸውን ነው የገለጹት። የህብረቱን ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ በተመለከተ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ አፍሪካ የራሷን አጀንዳዎች ለማስፈጸምና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ነፃነቷን ለማስጠበቅ የራሷን ሀብት መጠቀም ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት ብለዋል ሚኒስትሩ። በዚህ ረገድም የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ ድጋፋቸውን ማድረግ እንዳለባቸው ነው ጨምረው የተናገሩት። ስምምነት እና መግባባት (Consensus) የፖለቲካ ብስለት እንጂ የድክመት ምልክት እንዳልሆነ ጠቁመው ይህም የአፍሪካ ሀገራትን የሚያቀራርቧቸውን የጋራ እሴቶች እንዲፈልጉ የሚያስችል ዋና መሳሪ ነው ብለዋል። የተያዙ አጀንዳዎችንና የተገቡ ቃል ኪዳኖችን ለአፍሪካውያን ህይወት ለውጥ ወደሚያመጡ ተጨባጭ ውጤቶች መቀየር እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ ሀገራት የልማት ግቦችን የሚያሳኩ የአሰራር ማዕቀፎችን በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል
Jul 28, 2026 126
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት አህጉራዊ የልማት ግቦችን እውን የሚያደርጉ ስምምነቶችን በአፋጣኝ አፅድቀው ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት አፍሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ የሚመጡ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በሙሉ አቅሟ እየተጋፈጠች ነው። የግጭቱ መቀስቀስ የዓለም አቀፍ የአቅርቦት መስመሮችን በማስተጓጎሉ ምክንያት የነዳጅ፣ የሸቀጣሸቀጥ እና የመሰረታዊ ቁሳቁሶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሻቅብ ማድረጉን ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ጉዳዩን በጥልቀት ሲመረምሩት እንደቆዩና የዚህ ቀውስ ዳፋ ለበርካታ አመታት አብሮን ሊቆይ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን አብራርተዋል። በሌላ በኩል በአህጉሪቱ እየተስፋፋ ያለው የሽብርተኝነት አደጋ እና የጤና ስጋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሊቀ መንበሩ አውስተዋል። በሳህል ቀጣና ባደረጉት ጉብኝት የሰብአዊ ሁኔታዎችን መመልከትና ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ቀጣናዊ ትብብር ለማጠናከር ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) እያከናወነ ላለው ስራ ላይ አባል ሀገራት ድጋፋቸውን እንዲያጠናከሩም ጠይቀዋል። ሊቀ መንበሩ በአፍሪካ ህብረት የበጀት እና አደረጃጀት ላይ በሰጡት ማብራሪያም የ2027 የበጀት ረቂቅ 797 ሚሊየን 893 ሺህ 884 ዶላር መሆኑን ይፋ አድርገዋል። ይህ በጀት ከአባል ሀገራት መደበኛ መዋጮ እና በዓለም አቀፍ አጋሮች የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመዋል። የአጀንዳ 2063 ሁለተኛውን የ10 ዓመት እቅድ ለማስፈጸም ወደ ሁለት ቢሊየን ዶላር ገደማ ፋይናንስ እንደሚያስፈልግ ነው ሊቀ መንበሩ ያስረዱት። ኮሚሽኑ ለአፍሪካ ልማት የሚሆን የግል እና የህዝብ ካፒታልን መሳብ የሚያስችሉ ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሚናውን እንደሚወጣም ተናግረዋል። አባል ሀገራትም የህብረቱን የልማት ግቦች እውን ለማድረግ ቁልፍ የሆኑ ህጋዊ ስምምነቶችንና ሰነዶችን በፍጥነት እንዲያፀድቁ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 20502
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ሐተታዎች
የበጋ መስኖ ስንዴ፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ የግብርና ዘርፍ እመርታ!!
Jul 28, 2026 148
በሚኪያስ ጎቡ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ አምድ፣ ሕዝብ የኑሮ መሠረትና የምግብ ዋስትና ማዕዘን ነው። በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ሆኖ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግብርናን ከኢንዱስትሪ፣ ከማዕድን፣ ከቱሪዝም እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር በመጣመር ወሳኝ የዕድገት ምሰሶ የሚሆንበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም በሰብል፣ በእንስሳት እና በሌሎች ዘርፎች እመርታዊ ውጤቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል። በዚህ ዘርፍ ከተመዘገቡ አስደናቂ ለውጦች መካከል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አዲስ የዕድገት ፍኖት ከፍቷል። ለዓመታት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚያስፈልገውን ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ስታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ በስትራቴጂካዊ የግብርና ማሻሻያዎች፣ በመስኖ ልማት ማስፋፋት፣ በሜካናይዜሽን እና በአርሶና አርብቶ አደሮች አደረጃጀት የስንዴ ምርቷን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችላለች። ይህ ለውጥ የገቢ ምርትን ከመተካት ባሻገር በምግብ ራስን መቻል፣ ለውጭ ንግድ አቅም እና ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት አዲስ ዕድል ፈጥሯል። የስንዴ ምርታማነትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ዘንድ የይቻላል መንፈስን በማጎልበት የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ አቅም ፈጥሯል። ከዚህም በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና ሥርዓት በመገንባት ለአፍሪካና ለቀጣናው ሀገራት የልማት ተሞክሮ አስገኝቷል። የምርትና የምርታማነት አብዮት በክረምት ዝናብ ላይ ብቻ ተንተርሶ የቆየው የኢትዮጵያ ግብርና አሁን ዘመናዊ የአመራረት ምኅዋር ውስጥ ገብቷል። ይህም በቆላማ፣ በደጋማ እና በወንዝ ዳርቻ የሚገኙ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወደ ምርታማ የስንዴ ማሳዎች ቀይሯል። የስንዴ ምርታማነት አብዮትም በመስኖ፣ በሜካናይዜሽን፣ በተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎች እና በአርሶና አርብቶ አደሮች የተቀናጀ ጥረት የምርታማነትን ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ አሻሽሏል። በዚህም ኢትዮጵያ ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታስገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል። ይህ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የግብርናን ገጽታ የቀየረ የምርትና የምርታማነት አብዮት ነው። ፖሊሲ፣ ቴክኖሎጂ፣ መስኖ እና የአርሶና አርብቶ አደሩ ትጋት ሲጣመሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያጎናጽፍ አቅም መፍጠር እንደሚቻል የሚያሳይ የልማት ተሞክሮ ሆኗል። የክላስተር ግብርና፤ የሜካናይዜሽን ስኬት እመርታ!! የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ስኬት ከውጤታማ የአሠራር ዘዴዎች መካከል የክላስተር ግብርናና የሜካናይዜሽን አጠቃቀም ዋነኛ ምሰሶዎች ናቸው። ባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን በማደራጀት ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ እና የሰብል ጥበቃ ግብዓቶችን በወቅቱና በተደራጀ መንገድ እንዲያገኙ አስችሏል። የሜካናይዜሽን መስፋፋት ባህላዊ በሰው ጉልበትና በእንስሳት ኃይል የተመሠረተውን አሠራር በዘመናዊ ማሽነሪዎች በመተካት የማሳ ዝግጅትን፣ የዘር አዘራርን እና የምርት አሰባሰብን ውጤታማ አድርጓል። ትራክተርና ኮምባይነር አጠቃቀም የጊዜና የጉልበት ብክነትን ከመቀነሱ ባሻገር በምርት ስብሰባ ወቅት የሚደርሰውን ብክነት በመቀነስ የምርት ጥራትና መጠን እንዲጨምር አስችሏል። የክላስተር ግብርናና የሜካናይዜሽን ሥርዓት የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ከተለመደው የኑሮ ግብርና ወደ ተወዳዳሪ የንግድና የኢንዱስትሪ ግብዓት ምንጭነት እንዲሸጋገር በማድረግ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ አወንታዊ ተፅዕኖ፡- የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ለውጥ አምጥቷል። በተለይም የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መስፋፋቱ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በመተካት የምግብ ራስን የመቻል ግብን እያሳለጠ ይገኛል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የንግድ ሚዛንን በማሻሻል ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንዲፈጠር ዕድል ከፍቷል። በሌላ በኩል የስንዴ ምርት መጨመሩ የምግብ አቅርቦትን በማረጋጋትና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በማጎልበት የአርሶና አርብቶ አደሩን ምርታማነት የበለጠ ለማጠናከር እያስቻለ ነው። የይቻላል ተምሳሌቱ፤ የበጋ ስንዴ ምርታማነት፡- የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት የግብርና ስኬት ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ አብዮትም ነው። ለዘመናት ስንዴን ከውጭ ማስገባት የማይቀር የሚመስለውን እሳቤ በመስበር ከጥገኝነት የመላቀቅ መንፈስን አጎልብቷል። በመስኖ የተደገፈ ዓመቱን ሙሉ የማምረት ባህልን በማስፋፋትም ለሌሎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተነሳሽነት ፈጥሯል። ከአፍሪካ ቀዳሚነት ወደ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ፡- የስንዴ ልማቱ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ አቅም በመፍጠር በአፍሪካ ቀዳሚ አምራች ሀገር አድርጓታል። የመስኖ ልማት መስፋፋትና ቆላማ አካባቢዎችን ወደ ምርታማ የስንዴ ማሳዎች መቀየር ለኢኮኖሚው ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለአፍሪካ የተግባር ምሳሌ፡- የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለምሥራቅ አፍሪካና ለመላው አህጉሪቱ በምግብ ራስን መቻል እንደሚቻል በተግባር አሳይቷል። የውጭ የስንዴ ገቢ ምርት ጥገኝነትን በማስቀረት በአፍሪካ ምድር የምግብ ሉዓላዊነት ሊረጋገጥ እንደሚችል ተጨባጭ ውጤት አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች እንደገለጹት፤ ከስንዴ እርዳታና ከውጭ ጥገኝነት መላቀቅ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በሀገር ውስጥ ምርት ማረጋገጥ እና መሬትና የመስኖ ውኃን በአግባቡ በመጠቀም ኢትዮጵያን ከምርት ተቀባይነት ወደ አምራችነትና ወደ ላኪነት ማሸጋገር እየተቻለ ነው። ማጠቃለያ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በኢትዮጵያ የተመዘገበ የግብርና ስኬት ብቻ አይደለም፤ የአስተሳሰብ፣ የፖሊሲ፣ የቴክኖሎጂ እና የሀገራዊ ቁርጠኝነት ፍሬ የሆነ የልማት አብዮት ነው። ለዘመናት የውጭ ጥገኝነት ምልክት ሆኖ የቆየውን የስንዴ አቅርቦት ችግር በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ኢትዮጵያ ከአስመጪነት ወደ ላኪነት የምትሸጋገርበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍታለች። ይህ ስኬት የአንድ የግብርና ፕሮጀክት ውጤት ብቻ ሳይሆን መሬትን፣ ውኃን፣ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂን እና የአርሶ አደሩን ትጋት በአንድ ራዕይ ያስተሳሰረ የብልፅግና ሞዴል መሆኑን አሳይቷል። በተለይም የክላስተር ግብርና፣ የመስኖ ልማት፣ የሜካናይዜሽን መስፋፋት እና የተሻሻሉ የምርት ቴክኖሎጂዎች ተቀናጅተው ሲተገበሩ ግብርና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገር ኢኮኖሚን የመቀየር አቅም እንዳለው በተግባር አረጋግጧል። ከዚህ በኋላ የሚጠበቀው ይህንን ስኬት በማስቀጠል የጥራት ማሻሻያን፣ የእሴት ጭማሪ ኢንዱስትሪዎችን፣ የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነትን እና የግብርና ዲጂታላይዜሽንን በማጠናከር ስንዴን ከምግብ ዋስትና ባሻገር የውጭ ምንዛሬ፣ የኢንዱስትሪ ግብዓት እና የሀገራዊ ኢኮኖሚ መረጋጋት ስትራቴጂያዊ ምሰሶ ማድረግ ነው። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የኢትዮጵያን ይቻላል መንፈስ በማሳየት የምግብ ራስን መቻልን ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን፣ የውጭ ምንዛሬ አቅምን፣ የአፍሪካ የልማት ተምሳሌትነትን እና የቀጣይ ትውልድ የብልፅግና መሠረትን እየገነባ ነው። በዚህም የተገኘው የግብርና ድል የአንድ ወቅት የምርት ጭማሪ ሳይሆን የኢትዮጵያን የዕድገት ታሪክ የሚቀይርና ለአፍሪካም አዲስ የልማት አድማስ የሚከፍት ዘላቂ ስኬት ሆኖ ይቀጥላል።
የባሕር በር ፣ የኢትዮጵያውያን የልማትና የሕልውና ጥያቄ
Jul 26, 2026 274
የባሕር በር ፣ የኢትዮጵያውያን የልማትና የሕልውና ጥያቄ በዜናው ፈንቴ እንደ መግቢያ፡- የባሕር በር የአንድ ሀገር የውኃ ዳርቻ ባለቤትነት መገለጫ ብቻ አይደለም፤ የንግድ ደም ስር፣ የኢኮኖሚ አምድ፣ ፍኖተ ስልጣኔ፣ የባህል መስተጋብርና የጂኦፖለቲካ ኃይል እንጂ። የዓለም ታላላቅ የሥልጣኔ መሰረት የሆኑ ከተሞች የውኃማ አካላትን ጠርዝ ተንተርሰው የተቆረቆሩ ናቸው። ባሕር የውሃ ስፋት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ የንግድ ማሳለጫ፣ የደህንነት ዋስትና የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ነው። የዓለም 80 በመቶ የንግድ ልውውጥ በባህር ላይ ይከወናል፤ በዓመቱ በአማካኝ እስከ 12 ቢሊዮን ቶን ጭነት ይጓጓዛል፤ የባሕር በር ያላቸው ሀገራት በፈጣን ዕድገት፣ በወጭ ንግድ፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋትና በቀጣናዊ ተፅዕኖ የተሻለ አቅም መገንባት ይችላሉ፤ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ደግሞ ለከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ፣ ለንግድ መጓተትና ለውጭ ጥገኝነትን ይጋለጣሉ፡፡ ለዚህም ነው የባሕር በር የአንድ ሀገርና ዜጎች የህልውና ጉዳይ ነው የሚባለው። ይህ እውነታ በኢትዮጵያ በግልጽ ይንጸባረቃል፤ በአፍሪካ ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያላት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ በኃይል ልማትና በዲጂታል ኢኮኖሚ እየተለወጠች ነገር ግን የባሕር በር የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ተለዋዋጭ በሆነው የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ትልቅ የሕዝብ ቁጥርና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ለምትመራው ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የህልውና ፍትሕ እንጂ ቅንጦት አይደለም፡፡ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ልማትም ዋስትና። ቀይ ባሕር አውሮፓን፣ ኤዥያና አፍሪካን የሚያገናኝ፤ የስዌዝ ቦይን ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር የሚያስተሳስር፣ የዓለምን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ የዓለም ወሳኝ የባሕር መስመር ነው። በዚህ ወሳኝ ጂኦ ስትራቴጂክ ቀጣና የሚገኝ ሀገር አስተማማኝ የባሕር በር ያስፈልገዋል። ኢትዮጵያም ይገባታል፤ የታሪክ፣ የጂኦግራፊ፣ ነባራዊ ሁኔታና የተፈጥሮ ሚዛን ወደ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ያጋደለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ለሺህ ዘመናት የተሻገረ በአክሱም ስልጣኔ ዓለምን የናኘ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ እንደነበራት የአደባባይ ሐቅ ነው። የአዱሊስ ወደብም አፍ አውጥቶ ይናገራል፤ ከመካከለኛው ዘመን እስከ ቅርቡ አሰብ ወደብ ኢትዮጵያና የባሕር በር የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሆነው ቆይተዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሲቪልና የአካባቢ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከዓባይና የቀይ ባሕር ውሃዎች ጋር የተቆራኘ መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡ የባሕር በር የሀገር ብሔራዊ ጥቅም አንጓ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የተገለለችበት መንገድ የሚያስቆጭና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተፈፀመ በደል ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ የወቅቱ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልክዓ-ምድራዊ ማስረጃዎች እንዳሉት ያብራራሉ። ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ተመራጭ መንግሥትና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ያልተሰጠው የሽፍታ ስብስብ ኤርትራን በማስገንጠል ኢትዮጵያን የባሕር በር አልባ አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ይህንን ሕገ ወጥና በሀገር ላይ የተፈጸመ ክህደት ሲያብራሩ "ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበትን ውሳኔ ማን ወሰነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ሲቀጥሉም "ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔውን ዶክመንት ብናነብ የለም፣ ካቢኔው አያውቅም። አይ የለም ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብንወስድ ምክር ቤትም አልነበረም፣ ምክር ቤቱም አላወቀም። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ ይሆናል እንዳይባል አልወሰነም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነውን፣ ተወካዮቹ ያላዩትን፣ ቢያንስ ቢያንስ አስፈጻሚው ካቢኔ ያላየውን ውሳኔ ማን ወሰነው? ማጣትን የሚያክል ነገር ያጣንበት መንገድ ሕጋዊነት ችግር እንዳለው የሚያሳየው፣ ተቋሞች አልገቡበትም" በማለት ውሳኔው ሕዝባዊና ተቋማዊ ውክልና ባልነበረው ስብስብ የተወሰነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ባንዳና ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ኢ-ፍትሐዊ በደል ፈፅመዋል። ይህም ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በፍጥነት እያደገች ያለች ኢኮኖሚ ያላትና በቀጣናው የሰላምና የደኅንነት ዋና ተዋናይ የሆነችውን ኢትዮጵያ ያላቋረጠ የጂኦፖለቲካ ፈተና ውስጥ አስገብቷታል። በዚህ አውድ ውስጥ የቀረበው የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሌላ ሀገርን ግዛት ለመውሰድ ወይም ሉዓላዊነትን ለመጋፋት የቀረበ ጥያቄ አይደለም። ይልቁንም በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ጥቅም፣ በቀጣናዊ ትብብር እና በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች መሠረት ሁሉንም ወገኖች የሚጠቅም ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የቀረበ የልማትና የሕልውና አጀንዳ ነው። የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ከኢኮኖሚ ጥቅም በላይ የሀገር ዘላቂ ዕድገት፣ የቀጣናው ትስስር እና የብሔራዊ ሕልውና ጉዳይ ነው። ስለዚህም ጥያቄው ታሪካዊ እውነታን፣ ሕጋዊ መሠረትን፣ ጂኦግራፊያዊ እውነታን እና የጋራ ቀጣናዊ ጥቅምን በሚያጣምር መንገድ መታየት ያለበት ስትራቴጂካዊ ጉዳይ እንጂ የግጭት ወይም የመስፋፋት የፖለቲካ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም። 👉ባሕር፤ የታሪካችን አካል፣ የወደፊታችንም መሠረት የኢትዮጵያ ከባሕር ጋር ያላት ትስስር ከዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ከሥልጣኔዋ መነሻ ጋር የተቆራኘ የአደባባይ ሐቅ ነው። የአክሱም ሥልጣኔ በአዱሊስ ወደብ በኩል ከሮማ፣ ከግብፅ፣ ከሕንድ፣ ከዓረቡ ዓለምና ከሩቅ ምሥራቅ ጋር የንግድና የሥልጣኔ ትስስር መፍጠሩ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው። በዚህ ወደብ አማካኝነት ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ቅመማ ቅመሞችና ሌሎች የንግድ ሸቀጦች ወደ ዓለም ገበያ ይደርሱ እንደነበርም ታሪክ ያስረዳል። በዚህ ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪና ዓለም አቀፍ የውሃ ተደራዳሪ ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የብሔራዊ ጥቅም ማጠንጠኛ ነው። ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከባሕር ጋር የነበራት ታሪካዊ ትስስር በተለያዩ የፖለቲካ ለውጦች ቢቋረጥም፣ በሕዝብ የልብ ማህደረ ውስጥ ያለው ስፍራ አልተሸረሸረም። ኢትዮጵያ በታሪኳ አሰብን፣ ምጽዋንና ሌሎች ወደቦችን ተጠቅማ ከቀጣናውና ከዓለም ጋር ሰፊ የንግድ ትስስር የፈጠረች ሀገር ናት። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ አዲስ ፍላጎት ወይም አዲስ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪክ፣ ኢኮኖሚና ጂኦግራፊያዊ እውነታ ጋር የተቆራኘ ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪዬሽን፣ በዲጂታል ኢኮኖሚና በኃይል ልማት ዘርፎች ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች። ይሁን እንጂ ይህ የኢኮኖሚ መስፋፋት ውጤታማ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና የተረጋጋ የባሕር በር ተደራሽነት ካልተደገፈ ሙሉ አቅሙን ማሳየት አይችልም። በዚህ ምክንያት የባሕር በር ጉዳይ የታሪክ ትውስታ ብቻ ሳይሆን፣ የዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልጽግና መሠረት ሆኗል። በመሆኑም የባሕር በር ጉዳይ የትናንትን ታሪክ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለማጠናከር፣ የንግድ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የቀጣናዊ ትብብርን ለማስፋትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። ከዚህ አንጻር በቀይ ባሕር አካባቢ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ኢትዮጵያ ከባሕር ተደራሽነት ውጭ መሆኗ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና በቀጣናዊ ተወዳዳሪነት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በተረጋጋ የውይይትና የትብብር መንገዶች መፍትሔ የሚሻ ስትራቴጂክ ጉዳይ መሆኑን ያሳያል። 👉የባሕር በር፤ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የልማትና የሕልውና ጥያቄ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአንድ ሀገር ጥንካሬ በወታደራዊ ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ በኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት፣ በንግድ ትስስር፣ በሎጂስቲክስ ቅልጥፍናና ዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነት ይለካል። በዚህ መለኪያ የባሕር በር ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የልማት መሠረታዊ መስፈርት ሆኖ ይታያል። በዚህ አውድ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ታሪካዊ እውነታን፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥንና ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎችን ያጣመረ የልማት ጉዳይ መሆኑን ምሁራን ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ለዚህ ጥያቄ መፍትሔ ለማግኘት የምታደርገው ጥረትም በሰላማዊ ውይይት፣ በዲፕሎማሲ፣ በጋራ ጥቅምና በቀጣናዊ ትብብር ላይ የተመሠረተ ነው። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በአፍሪካ በፍጥነት እያደገች ያለች፣ በአቪዬሽን፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኃይልና በዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየገነባች ያለች ኢትዮጵያ፣ ይህን የልማት እመርታ በተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና በተረጋጋ የባሕር በር ተደራሽነት ካልደገፈች ሙሉ አቅሟን ማሳካት አትችልም። በዚህ ምክንያት የባሕር በር ጉዳይ የአንድ ወደብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ የንግድ ተወዳዳሪነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና ጉዳይ ነው። እንደዚሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ጥያቄ የጦርነት ወይም የመስፋፋት ሳይሆን፣ በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ጥቅምና በቀጣናዊ ትብብር መሠረት መፍትሔ የሚፈልግ የልማትና የሕልውና ጉዳይ ነው። 👉የኢኮኖሚ እመርታና የባሕር በር ትስስር በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ በብዝኅ ኢኮኖሚ ሥርዓት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን አስመዝግባለች። የግብርና ምርት ጨምሯል፣ የኢንዱስትሪ ማምረት አቅም ጎልብቷል፣ የማዕድን ሀብቶች ወደ ውጭ ገበያ እየቀረቡ ሲሆን፣ የቱሪዝምና የዲጂታል ኢኮኖሚ መስፋፋትም አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ከፍቷል። ይሁን እንጂ ይህ እመርታ ተወዳዳሪና ዘላቂ ሊሆን የሚችለው ከተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና ከአስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ጋር ሲተሳሰር ነው። የግብርና ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ውጤቶች፣ የማዕድን ሀብቶችና ሌሎች ወደ ዓለም ገበያ በፍጥነትና በወጪ ቆጣቢነት እንዲደርሱ የባሕር በር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ የኢትዮጵያና የቀይ ባሕር ትስስር ከሀገረ መንግሥቷ ታሪክ ጋር የተቆራኘ ሲሆን፣ የባሕር በር ጉዳይም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ቁልፍ አጀንዳ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለወደብና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት ብቻ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓ፣ የባሕር በር ጉዳዩ ከኢኮኖሚ ጋር ያለውን ቀጥተኛ ትስስር ያሳያል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም እንደሚጠቁሙት፣ አስተማማኝ የባሕር በርና አማራጭ የወደብ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማስቀጠል የሚያስፈልግ መሠረታዊ ፍላጎት ነው። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ የአንድ ዘርፍ ፍላጎት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን፣ የንግድ መስፋፋትንና የዘላቂ ብልጽግና ጉዞን የሚወስን ስትራቴጂካዊ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው። 👉ከታሪካዊ መብት ወደ የጋራ ብልፅግና፤ ምላሽ የሚሻው የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ!! የኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ የትናንትን ታሪክ ለማስታወስ ብቻ የቀረበ አይደለም፤ የነገውን የቀጣናው ኢኮኖሚ፣ የንግድ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚወስን ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት ፉክክርን ሳይሆን ትብብርን ከመረጡ፣ ወደቦች የአንድ ሀገር ብቻ ሳይሆኑ የቀጣናውን የጋራ ዕድገት ማስፈንጠሪያ መድረኮች ይሆናሉ። በዚህ እሳቤም የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀይ ባሕር ቀጣና፣ ለአፍሪካ ቀንድ እና ለቀጣናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት የሚያስችል ዕድል ነው። የምጣኔ ሀብት ምሁር ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) እንደሚገልጹትም፣ የኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነትን ይሻል፤ ይህ አለመኖሩ ግን የንግድ ተወዳዳሪነትን በመገደብ በሀገሪቱ ኢኮኖሚና በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ ቀጥተኛ ጫና ያሳድራል። ስለዚህ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የግዛት መስፋፋት ሳይሆን፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሀገር ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማረጋገጥ፣ የንግድ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግና የቀጣናዊ የጋራ ብልፅግናን ለማጠናከር የሚቀርብ የልማትና የሕልውና ጥያቄ ነው። 👉የቀይ ባሕር ጂኦፖለቲካ፤ የዓለም ትኩረት ለምን በቀጣናው ላይ ነው? የቀይ ባሕር ከውሃ አካልነቱ ባሻገር የዓለም ኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ ወሳኝ ማዕከል ነው። ከሕንድ ውቅያኖስ እስከ ሜዲትራኒያን የሚዘረጋው ይህ የባሕር መስመር የእስያን፣ የአፍሪካንና የአውሮፓን ኢኮኖሚዎች የሚያገናኝ ዋነኛ የዓለም የንግድ መተላለፊያ ነው። በዚህ ቀጣና የሚያልፉ መርከቦች ሸቀጦችን ብቻ ሳይሆን የኃይል አቅርቦትን፣ የምግብ ዋስትናንና የዓለም ኢኮኖሚ ቀጣይነትንም ይሸከማሉ። ስለዚህም የቀይ ባሕር ደህንነት የአንድ ቀጣና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆኗል። በቀጣናው የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል የነዳጅና የምግብ ዋጋ፣ የመጓጓዣ ወጪ እንዲሁም የዓለም የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ ስለዚህ ዓለም የቀይ ባሕርን በልዩ ትኩረት ትከታተላለች። 👉ኢትዮጵያ፤ የቀጣናው ተፈጥሯዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ለሦስት አስርት ዓመታት ከቀይ ባሕር ዳርቻ ተገልላ ብትቆይም፣ የቀጣናው ትልቁ ኢኮኖሚ፣ ገበያና የሰው ኃይል ማዕከል ሆና ቀጥላለች። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ፣ ጠንካራ የአየር መጓጓዣ ትስስር፣ ትልልቅ የኃይል ፕሮጀክቶችና እየሰፋ ያለ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያላት ሀገር፣ በቀይ ባሕር ጂኦ-ኢኮኖሚ ውስጥ ማዕከላዊ ሚና እንዳይኖራት ማሰብ አይቻልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ፍላጎት ወደ ባሕር መድረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣናው ዘላቂ የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚያገለግል አስተማማኝና ተመጣጣኝ የባሕር በር ተደራሽነት ማረጋገጥ ነው። ይህም ለጎረቤት ሀገራት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የሥራ ዕድልና የመሠረተ ልማት መስፋፋትን በማፋጠን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር እድል ይፈጥራል። 👉ከታሪክ ወደ የጋራ ጥቅም የቀይ ባሕር ቀጣና በታሪክ ዘመናት የሥልጣኔ፣ የንግድና የባህል መገናኛ ሆኖ ቆይቷል። ከአክሱም ጀምሮ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ድረስ የባሕር በር ከሀገሪቱ ኢኮኖሚና ታሪክ ጋር የተሳሰረ ተፈጥሯዊ አካል ነው። ይህን ታሪክ ማስታወስም ያለፉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ ሳይሆን፣ የዛሬውን ጉዳይ በትክክለኛ ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አውድ ለመረዳት ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከታሪካዊ መብት ባሻገር፣ ከኢኮኖሚ ዕድገት፣ ከሕዝብ ብዛት፣ ከቀጣናዊ ትስስርና ከጋራ ብልፅግና አንፃር ሊታይ ይገባል። ዘላቂ መፍትሔም በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በጋራ ጥቅም፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በተቋማዊ ውይይት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለመላው የቀይ ባሕር ቀጣና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ሊሆን ይገባል። 👉የወደፊቷ ኢትዮጵያ፤ ከብሉ ኢኮኖሚ ጋር የተሳሰረ ርዕይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ፣ ከዚያም ወደ እሴት ጨማሪ ምርትና ዲጂታል ኢኮኖሚ እየተሸጋገረ ነው። ይህ ሽግግር ዘላቂ እንዲሆን ግን ውጤታማ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ወሳኝ ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ የባሕር በር አጀንዳ የፖለቲካ ክርክር ሳይሆን የትውልድ የልማት ራዕይ ነው። በሕግ፣ በዲፕሎማሲና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ኢትዮጵያን ከዓለም ገበያ በተሻለ ሁኔታ ያገናኛል፤ ለቀጣናውም መረጋጋትና የጋራ ብልፅግና መሠረት ይሆናል። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ዕድገትና የብሉ ኢኮኖሚ የወደፊት ራዕይ አካል ነው። 👉መደምደሚያ፡ የባሕር በር ጉዳይ፤ የግጭት ሳይሆን የጋራ ብልፅግና መንገድ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ ያለፈውን ታሪክ ለመመለስ ብቻ የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን፣ የወደፊቱን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚወስን ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ነው። የባሕር በር ተደራሽነት የሌላ ሀገር ጥቅምን በመጉዳት ሳይሆን፣ በጋራ ጥቅም፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በቀጣናዊ ልማት ላይ የተመሠረተ የዕድገት መንገድ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሀገራት ብልፅግና በመገፋፋት ሳይሆን በመተባበርና በጋራ ዕድገት ይገነባል። ስለዚህ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር፣ ለንግድ መስፋፋትና ለዘላቂ ሰላም አዲስ ዕድል የሚከፍት ነው። ከአክሱም ሥልጣኔ ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የቆየው ታሪካዊ ትስስር ከዘመኑ የሕዝብ ብዛት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገትና ከቀጣናዊ ሚና ጋር ተያይዞ አዲስ ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት አግኝቷል። ስለሆነም አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ማረጋገጥ የዛሬው ትውልድ የልማት ራዕይና የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህም በጽኑ ሀገራዊ አንድነት፣ በበሰለ ዲፕሎማሲ፣ በውይይትና በጋራ ጥቅም መርህ ሊመራ ይገባል። በመጨረሻም የባሕር በር የትናንት ትዝታ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ የነገ ብልፅግና፣ የቀጣናው የጋራ ልማትና የአፍሪካ ተስፋ መንገድ ነው። የባሕር በር የኢትዮጵያ የነገ ብልፅግና መንገድ እንጂ የትናንት ትዝታ ብቻ አይደለም!!
ምግቤን ከደጄ፤ የከተማ ግብርና አዲሱ የምግብ ዋስትና መሰረት
Jul 25, 2026 318
በመቅደስ ወልዴ መግቢያ፡- ዛሬ ዓለም በፈጣን የከተሜነት ሽግግር ውስጥ ትገኛለች። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ፣ ከተሞችን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የኑሮ ማዕከላት እያደረጓቸው ነው። ይህ ሽግግር አዳዲስ የልማት ዕድሎችን ቢፈጥርም፣ ከምግብ አቅርቦት እስከ የኑሮ ውድነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ እስከ የሥራ ፈጠራ ድረስ ያሉ አዳዲስ ፈተናዎችንም አስከትሏል። በተለይም በታዳጊ ሀገራት የከተሞች መስፋፋት የምግብ ዋስትናን ከልማት ፖሊሲዎች ማዕከል ላይ አስቀምጦታል። በ2050 ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሦስተኛው በከተሞች እንደሚኖር የሚጠበቀው እውነታ፣ ከተሞች ምግባቸውን ለማረጋገጥ አዳዲስና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል። ኢትዮጵያም ከዚህ ዓለም አቀፋዊ ሽግግር ውጭ አይደለችም። የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የገበያ መረጋጋትና የኑሮ ውድነት አዳዲስ የፖሊሲ ጉዳዮች ሆነው ተነስተዋል። በዚህ ዐውድ ውስጥ የከተማ ግብርና ባዶ ቦታን ወደ ምርት፣ ቆሻሻን ወደ ማዳበሪያ፣ ሸማቹን ወደ አምራች የሚቀይር ዘመናዊና ዘላቂ የልማት መንገድ ሆኖ እየጎለበተ ነው። የከተማ ግብርና፤ ምንነቱና ጠቀሜታው የከተማ ግብርና በከተማ ውስጥ በሚገኙ አነስተኛ ቦታዎች፣ በመኖሪያ ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በበረንዳ ስፍራዎች ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ቀላል የምርት ዘዴዎችን በመጠቀም አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንስሳት፣ ዓሳና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን የማምረት ሥርዓት ነው። ቀደም ሲል ግብርና የገጠር ብቻ ተደርጎ ይታሰብ የነበረው አመለካከት ዛሬ በእጅጉ ተለውጧል። በከተሞች የሚገኙ ጠባብ ስፍራዎች እንኳን ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የልማት መስኮች ሆነዋል። በቤት ዙሪያ ይደረግ የነበረው ቀላል የጓሮ አትክልት ልማትም ዛሬ ለሺዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ ገበያን የሚያረጋጋና የሀገር ኢኮኖሚን የሚደግፍ ዘርፍ ሆኗል። ከተሞችን ውብና አረንጓዴ ከማድረጉ ባሻገር፣ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ፣ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙና ለአካባቢ ጥበቃ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። እንዲሁም የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብና ሌሎች አነስተኛ የግብርና ሥራዎች የቤተሰብን ምግብ ከማሟላት ባለፈ ገበያውን በማረጋጋት ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የከተማ ግብርና ለምን አስፈለገ? የግብርና ልማት ዛሬ በገጠር አርሶ አደሮች ጥረት ብቻ የሚገደብ አይደለም። የከተሞችን እምቅ ሀብት በመጠቀምና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማቀናጀት የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የሚቻልበት ውጤታማ መንገድ መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ተሞክሮዎችም የከተማ ግብርና የከተሞችን ገበያ በማረጋጋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የከተማ ቆሻሻን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየርና የከተሞችን አረንጓዴነት በማጎልበት ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ በተግባር አሳይተዋል። የከተማ ግብርና፤ ከጓሮ ልማት ወደ ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ቀደም ሲል በቤት ጓሮ የሚከናወን ቀላል የአትክልት ልማት ተደርጎ ይታይ የነበረው የከተማ ግብርና፣ ዛሬ የምግብ ዋስትናን፣ የገበያ መረጋጋትን፣ የሥራ ፈጠራንና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን የሚያጠናክር ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ሆኖ ተቀይሯል። በአነስተኛ ቦታዎች፣ በቤት ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በባዶ መሬቶች ላይ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ሀብት፣ የንብ እርባታና ሌሎች የግብርና ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ። "ምግቤን ከደጄ" የሚለው ሀገራዊ ንቅናቄም የከተማ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እስከ የገበያ መረጋጋት የከተማ ግብርና ከሚያስገኛቸው ትልልቅ ጥቅሞች መካከል ዋነኛው የምግብ ምርትን ለተጠቃሚው በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪና በተሻለ ጥራት ማድረስ መቻሉ ነው። በከተማ ውስጥ የሚመረቱ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ እንቁላልና ወተት ረጅም ርቀት ሳይጓዙ በቀጥታ ለገበያ ስለሚቀርቡ ትኩስነታቸውን ይጠብቃሉ፤ የመጓጓዣ ወጪንም በእጅጉ ይቀንሳሉ። በሌላ በኩል ቤተሰቦች በጓሯቸው የሚያመርቱት ምርት የዕለት ተዕለት የምግብ ወጪያቸውን በመቀነስ የምግብ ዋስትናቸውን ያጠናክራል። ከቤተሰብ ፍጆታ በላይ የሚተርፈው ምርት ደግሞ ወደ ገበያ በመግባት የምግብ አቅርቦትን ያሳድጋል፤ በዚህም የዋጋ ንረትን በመቀነስ የገበያ መረጋጋትን ለማስፈን የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። የአረንጓዴ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ የከተማ ግብርና የምግብ ምርትን ከማሳደግ ባለፈ፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የከተማ ኢኮኖሚን የሚያነቃቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሠረትን የሚያጠናክር ዘርፍ ሆኗል። በአዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ሀብትና በንብ ማነብ የተሰማሩ በርካታ ወጣቶችና ሴቶች ቋሚ የገቢ ምንጭ እያገኙ ይገኛሉ። ይህም የከተማ ግብርና የቤተሰብ የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር የሥራ አጥነትን ለመቀነስና የከተማ ኢኮኖሚን ለማጠናከር እያበረከተ ያለውን ጉልህ አስተዋፅኦ ያሳያል። አካባቢን ከመጠበቅ እስከ የከተሞችን ውበት የከተማ ግብርና የሥነ-ምህዳር ጠቀሜታውም ከፍተኛ ነው። ከቤት የሚወጡ ኦርጋኒክ ቆሻሻዎችን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየር የአፈር ለምነትን ያሻሽላል፤ በተመሳሳይ ጊዜም የከተማ ጽዳትን ያጠናክራል። ከዚህ በተጨማሪ የአረንጓዴ ስፍራዎች መስፋፋት የከተሞችን የሙቀት መጠን በመቀነስ፣ የአየር ጥራትን በማሻሻልና ለነዋሪዎች ጤናማና ምቹ የኑሮ አካባቢ በመፍጠር ለከተማ ዘላቂነት የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ማጠቃለያ የከተማ ግብርና የኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት የልማት አቅጣጫ መሆኑን በተግባር አረጋግጧል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጀምሮ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የሥራ ፈጠራን ማስፋፋት፣ የከተሞችን ውበት ማጎልበትና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ድረስ ያለው ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ ነው። ስለሆነም ለከተማ ግብርና የሚስማሙ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍን ማጠናከር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻልና በከተማ ፕላን ውስጥ ለግብርና ተስማሚ ቦታዎችን በቋሚነት መመደብ ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው። ከተሞች የምግብ ፍጆታቸውን በራሳቸው የማምረት አቅም እያዳበሩ ሲሄዱ፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ዋስትና፣ ጠንካራ አረንጓዴ ኢኮኖሚና ተወዳዳሪ የከተማ ልማት ስኬታማ ትልም ይበልጥ ይፋጠናል። ከደጃችን የሚጀምረው ምርት፤ ለሀገር ዕድገት የሚሆን ትልቅ አቅም ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ፤ ከሥነ-ምኅዳር ዘብ እስከ ዓለም የልማት ተምሳሌት
Jul 23, 2026 542
በመጽሔት አንለይ በወሳኝ ሀገራዊ የልማት ውይይቶች ላይ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸው፣ በዚህም በርካታ ሚሊየን ሄክታር መሬት መታደሱ እንዲሁም የተመዘገበ የደን ሽፋን በአበይት ጉዳይነት ይነሳሉ። ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአርሶ አደሩ ምርታማነት ማደግ፣ የወጣቱ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን፣ የእናቶች የኑሮ መሻሻልና የተፈጥሮ ሃብት መጠበቅ መቻሉ እንዲሁም የአየር ንብረት መዛባትን ማስተካከልና የደን ሽፋንን ማሳደጉ ለመርሃ ግብሩ ውጤታማነት በአብነትነት ይጠቀሳሉ። በዚህ አተያይ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከተራ የችግኝ ተከላ ዘመቻ ባሻገር በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ልማት ዘርፎች መዋቅራዊ ለውጥ በማምጣት አንጸባራቂ ውጤት እያሰገኘ ነው። የዓለም አየር ንብረት ጉዳይ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ አፍሪካ የችግሩ ተጠቂ ብቻ ሳትሆን ለመፍትሄውም የራሷን ልምድና አቅም ማበርከት እንደምትችል እያሳየች ይገኛል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ንቅናቄም ለአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት አዲስ የተግባር ልምድ እየሆነ መጥቷል። የአረንጓዴ ዐሻራው ልዩነት በተተከሉ ችግኞች ቁጥር ብቻ አይለካም። በተራቆቱ መሬቶች ላይ የተመለሰው ሕይወት፣ በገጠር የተፈጠሩ የኢኮኖሚ ዕድሎች፣ የተጠበቁ የውሃ ሀብቶችና ለወደፊት ትውልድ የተገነባው የአካባቢ መሠረት ዋናው ውጤቱ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፤ ከርዕይ ወደ ተግባር!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በሀገራዊ ለውጥ ማግስት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሕዝባዊ ተሳትፎ የተጀመረ ሲሆን፤ እስካሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። ከዚህ በፊት የነበረው የተፈጥሮ ሃብት መራቆት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ብቻ ሳይሆን በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይም ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ ነበር። የአፈር መሸርሸር፣ የደን መጥፋትና የድርቅ ተጋላጭነቶችም የገጠር ሥነ-ምኅዳራዊ ሕይወትን ሲፈታተኑ ቆይተዋል። ይህን ምላሽ ለመስጠትም የአረንጓዴ ዐሻራ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማትና የደን ሽፋንን ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የአረንጓዴ አሻራ የኢኮኖሚ ዐሻራ፡- የአረንጓዴ ዐሻራ ትርጉም በአካባቢ ጥበቃ ብቻ አይወሰንም። በኢኮኖሚውም ውስጥ አዲስ የልማት መንገድ እየፈጠረ ይገኛል። በጥምር ግብርና (Agroforestry) አማካኝነት ቡና፣ ፍራፍሬና ሌሎች የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ከደን ልማት ጋር እንዲሰናሰሉ አድርጓል። ይህም የገቢ ምንጭን ከማስፋት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ አስተዋፅዖ አድርጓል። በተለይ የቡና ዘርፍ ከሚሊዮን ወደ ቢሊዮን ዶላር ደረጃ መሻገሩ የዚህ ጥምረት ውጤት አንዱ ማሳያ ነው። የአቮካዶ ምርት ለወጪ ንግድ የፈጠረው ዕድልም አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ውጤታማነት አብነት ሆኗል። በሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች ላይ የመጣው ዕድገት ኢትዮጵያን በዓለም ገበያ የተሻለ ተወዳዳሪ የምትሆንበትን ዕድል ፈጥሯል። ከአፈር ጥበቃ እስከ ምግብ ዋስትና፡- የአረንጓዴ ዐሻራ በአፈር ጤናማነት ላይ ያመጣው ለውጥ የግብርና ምርታማነትን ከፍ አድርጓል። የአፈር ኦርጋኒክ ካርቦን መጨመር፣ የውሃ ማቆየት አቅም መሻሻልና የተፋሰስ ልማት በኢትዮጵያ የመስኖ ልማትና የምግብ ምርት ዕድገት መሠረት ጥለዋል። የስንዴ ምርታማነት ዕድገት እና የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስኬታማ ጉዞም የአረንጓዴ ዐሻራ ተጠቃሽ ውጤቶች ናቸው። የተፈጥሮ ጋሻነት፡- ኢትዮጵያ ለድርቅ፣ ለጎርፍና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ዛፎችና ስሮቻቸው አፈርን በመያዝ መሸርሸርን ይቀንሳሉ፤ የውሃ ሃብቶችን ጠብቆ በማቆየትና በማሻሻል የድርቅ ተጋላጭነትን የመቋቋም አቅም እየገነባ ነው። በተለይም በርካታ የኃይል ማመንጫ ግድቦችንና የውሃ ሃብቶችን ከደለል አደጋ ለመጠበቅ የደን ልማት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቀልበስ የተፈጥሮ ጋሻነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። የትውልድ ሐውልትና የልማት ውርስ የሆነው አረንጓዴ ዐሻራ!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በአንድ ወቅት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻም፣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፈውበታል። ይህም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ታሪክ በመፃፍ በልማት መስክ አስደናቂ የትብብር መንፈስ እንዲገነቡ አስችሏል። የመርሃ ግብሩ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ የደን ውድመትን በመከላከል የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ፣ የድርቅና የበረሃማነት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተፅዕኖ መቋቋም አዲስ የዲፕሎማሲ ሚና!! በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የአፍሪካ ዋና ጥያቄ የአየር ንብረት ፍትሐዊነት ነው። አህጉሪቱ በአነስተኛ የካርቦን ልቀት ላይ ብትገኝም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከባድ ጫናን እየተጋፈጠች ይገኛል። በዚህ አውድ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራን እንደ ሀገራዊ ፕሮጀክት በመውሰድ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር የሚጋራ ተሞክሮ ፈጥራለች። የአፍሪካ አህጉራዊ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱም ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎና አመራር ያሳየ ክስተት ነው። ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት ማዕከል እንድትሆን ከማገዙም በላይ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረኮችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም በተግባር አሳይቷል። ማጠቃለያ፡- የተተከለ ችግኝ፣ የተገነባ ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ ''ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በዚህ ዓመት ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምቷል። በዚሁ ወቅትም ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ወደ 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በፅናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ዘንድሮም የተያዘውን የስምንት ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት በሚደረገው ብሔራዊ የንቅናቄ ስራ ላይ በሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ የወደፊት የዕድገትና ብልፅግና ማሳኪያ የልማት ትልም እንጂ። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም ከአንድ ችግኝ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የደረሰ የሀገር ተሞክሮ ነው። የተተከሉት ችግኞች ዛሬ የአካባቢ ጥበቃ ዘብ ሲሆኑ፣ ነገ ደግሞ የኢኮኖሚ ዕድል፣ የምግብ ዋስትና፣ የኃይል ዘላቂነትና የትውልድ ተስፋ ይሆናሉ። የተተከለው ችግኝ ነገ የሚሆነው ዛፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ጋሻና ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሕያው ቅርስ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ ዛሬ የሚተከል ተስፋ፣ ነገ የሚሰበሰብ ብልፅግና ነው፤ ተስፋን እንትከል!!!
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 503
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 643
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4624
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 3788
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 10847
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20989
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14017
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 19772
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም - የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ በኢትዮጵያ!!
Jul 27, 2026 425
በቤተልሔም ባህሩ መግቢያ፡- ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ሥልጣኔ መነሻ፣ የታሪክ መዝገብና የቱባ ባህል ሀብት ካስማ ምድር መሆኗ የአደባባይ ሃቅ ነው። የሺህ ዓመታት ታሪኮች፣ በዘመናት የተገነቡ ዕድሜ ጠገብ የሕንፃ አሻራዎች፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ባህላዊ እሴቶችና በዓላት ኢትዮጵያን በዓለም የቱሪዝም ካርታ ላይ ልዩ ስፍራ የሚያስይዙ መለያ ምልከቶቿ ናቸው። እንደ የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የአልነጃሺ መስጂድ፣ የሐረር ጀጎል እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የሃይማኖታዊ ትውፊትና የአርክቴክቸር ብልጽግና ሕያው ምስክሮች ናቸው። በተጨማሪም መስቀል፣ ጥምቀት፣ የገዳ ሥርዓት፣ አሸንዳ/አሸንድዬ፣ ኢሬቻ፣ ፊቼ ጨምበላላ እና ጊፋታ የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትም ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳቡ የማይዳሰሱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ የኢትዮጵያ ውድ ሃብቶች ናቸው። እነኝህ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶች በዓለም አቀፍ ዕውቅናም የተቸራቸው ናቸው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 16 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ማስመዝገብ ችላለች። በቅርቡ የተመዘገቡት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የሐረር ሸዋል ኢድ ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝብ ያበረከተቻቸው አዳዲስ የመስህብ ትሩፋቶች ናቸው። እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም ላይ ከማጉላት ባሻገር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን በመሳብ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በብዝኅ ተፈጥሮ፣ ታሪክና ባህል የታደለች ሀገር ብትሆንም ለረጅም ጊዜ እነዚህን ዕምቅ ሃብቶች በዘመናዊ የቱሪዝም አቀራረብ ለማልማት፣ ለዓለም አቀፍ ገበያ በብቃት ለማስተዋወቅና ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር የሚገባውን ያህል ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል። በመሆኑም የቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን እውነተኛ አቅም በሚመጥን ደረጃ መጠቀም ሳይቻል ቆይቷል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በኢትዮጵያ በተተገበረው ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ አምድ እንዲሆን በመደረጉ ልዩ ትኩረት አግኝቷል። ይህም ዘርፉ ከተለምዷዊ አካሄድ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ልማት፣ ወደ ከፍተኛ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸጋገርበትን መሰረት ጥሏል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተተገበሩት "የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ለውጥ ወሳኝ ምዕራፍ ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል የታደሉ ስፍራዎችን በዘመናዊ መንገድ በማልማት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ማራኪ መዳረሻዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት አድጓል፣ የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል፣ የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ መልክ እያገኘ መጥቷል። ዛሬ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጫ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምንጭ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ ዋና ሞተር በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የዓለም ቅርሶች ማዕከል ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከ16 በላይ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያስመዘገበች በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት። ከሚዳሰሱት ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የፋሲል ግቢና የጎንደር ቤተ መንግስት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የታችኛው ኦሞና የአዋሽ ሸለቆዎች፣ የሐረር ጁገል ግንብ እንዲሁም የባሌና የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች ይገኙበታል። ከማይዳሰሱት ቅርሶች ደግሞ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የጥምቀት በዓል፣ የፊቼ ጨምበላላና የገዳ ሥርዓት ተጠቃሽ ናቸው። ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ቅርሶች በተሻለ ሁኔታ የመጠበቅና የማደስ ሥራዎች የሚሰሩበትን ዕድል ፈጥሯል። በተመሳሳይም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተወዳዳሪና ማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ የሚያስችል ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ሶስቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ገበታ ለሸገር - የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየረ የለውጥ ጥንስስ!! የገበታ ለሸገር መርሃ ግብር የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ በመቀየር የቱሪዝም ስበት ማዕከልነቷን ያጎለበተ የለውጥ ምዕራፍ ነው። በመርሃ ግብሩ የተገነቡት የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች፣ የሳይንስ ሙዚየምና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከተማዋን ከዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ባሻገር ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስ ቱሪዝምና የመዝናኛ ጉብኝት ማዕከል እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የተተገበሩት የከተማ ኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለበርካታ ዓመታት ችላ የተባሉ ስፍራዎችን ወደ አረንጓዴ፣ ዘመናዊ እና ለሁሉም ተደራሽ የመዝናኛ ከባቢነት ቀይረዋል። ይህም ከተማዋን ለጎብኚዎች ይበልጥ ማራኪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለነዋሪዎች ጤናማ፣ ንጹህና ምቹ የከተማ ምኅዳር መፍጠር አስችሏል። ገበታ ለሸገር የአዲስ አበባን የከተማ ውበት በማሳደግ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን በማበራከት የቱሪዝም ዕድገትን ያፋጠነ ብቻ ሳይሆን፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ያሻሻለና የዘመናዊ ከተማ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስኬታማ ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር - ከገበታ ለሸገር የተቀዳ የሀገር በረከት!! ገበታ ለሀገር መርሃ ግብር በገበታ ለሸገር የተጀመረውን የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ወደ መላው ሀገር በማስፋት፣ በየክልሉ የሚገኙ ዕምቅ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶችን ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች የቀየረ ትልቅ የልማት ፕሮጀክት ነው። በዚህ ማዕቀፍ የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም፣ የጎርጎራ፣ የኮይሻና ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች በመገንባታቸው የክልሎችን የቱሪዝም አቅም በእጅጉ በማሳደግ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች አዳዲስና ማራኪ የጉብኝት መዳረሻዎችን ፈጥረዋል። በተመሳሳይም ፕሮጀክቶቹ በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የመንገድ፣ የመስተንግዶ፣ የመዝናኛና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች በስፋት እንዲገነቡ አስችለዋል። ይህም የቱሪዝም ጥቅም በተወሰኑ ከተሞች ብቻ እንዳይገደብ በማድረግ፣ የአካባቢ ኢኮኖሚን በማነቃቃት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የክልሎችን የልማት ተጠቃሚነት በማሳደግ የቱሪዝም ዕድገትን ወደ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ የቀየረ ውጤታማ ፕሮጀክት ሆኗል። ገበታ ለትውልድ - የቱሪዝም ልማትን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋገረ የአገልግሎት ዘርፍ እመርታ!! ገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር የተጀመረውን የቱሪዝም ልማት በማስቀጠል፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት ከመጠበቅ ጋር በማጣጣም ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት ያስቻለ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። መርሃ ግብሩ የቱሪዝም ልማትን ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር ለትውልድ የሚተርፍ ሃብት የመጠበቅ እሳቤ ጋር አሰናስሎታል። በዚህ ማዕቀፍ በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርትን ጨምሮ፣ የሸበሌ፣ የሎጎ ሐይቅ ሪዞርቶችና የሀሮ ደንዲ ኢኮ ሎጅ ተጠናቀው ወደ ሥራ ገብተዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ የልማት ሥራዎችም ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ አቅም ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስፋፋት፣ አገልግሎትን ወደ ዓለምአቀፍ ደረጃ በማሳደግና የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። በተመሳሳይም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ በማሳለጥም ገንቢ ሚና እየተወጡ ይገኛል። የኮሪደር ልማትና አዳዲስ የቱሪዝም ትስስሮች በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እየተስፋፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበት እያፈካ ይገኛል። በዚህም የከተሞችን መሠረተ ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራን፣ የመዝናኛና የእግረኛ መንገዶችን በስፋት በማልማት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ የከተማ ምኅዳር ፈጥሯል። ይህ ልማት የከተሞችን ውበት ከማሳደግ ባለፈ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማትን በማጠናከር፣ የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘምና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ዘርፉን ወደ ከፍተኛ የዕድገት ምዕራፍ አሸጋግሯል። የኮንፍረንስ ቱሪዝም (MICE) የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ውብ፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ከተማ በማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን ከተማ ወደ ቀዳሚ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ቀይሯታል። አዲስ ዓለም ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የሳይንስ ሙዚየምና ሌሎች ዘመናዊ መዳረሻዎች በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ተቋማትን በማፍራት ከተማዋን ለሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ ኤግዚቢሽኖችና ትላልቅ የንግድ መድረኮች ተመራጭ አድርጓታል። ለአብነትም የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) እና መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት ማስተናገድ ተችሏል። በተለይም የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ምቹ መድረክ ፈጥሯል። ይህም የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ገጽታ ከማጎልበት ባለፈ የቱሪዝም ማስተዋወቅን በዲጂታል ዘመን ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግሮታል። የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም መርሃ ግብርም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በአዲስ አበባ የሚያልፉ ትራንዚት መንገደኞችን ከመሸጋገሪያነት ብቻ ወደ ጎብኚነት ለመቀየር አስፈላጊ ዕድል ፈጥሯል። በዚህም መዲናዋን ከቱሪስት መሸጋገሪያነት ወደ ቱሪዝም ማዕከልነት ቀይሯታል። በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማትም ውብና ማራኪ የከተሜነት ገጽታን በመፍጠር፣ መንገደኞች በቆይታቸው የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ዘመናዊ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ አስችሏል። ይህም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘም ባለፈ፣ የመስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የባህልና የንግድ አገልግሎቶችን በማነቃቃት ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲፈጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል። በዚህም ከታሪካዊ ቅርሶች ባሻገር የባህል፣ የተፈጥሮ፣ የኢኮ ቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋፋት፣ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በተሻለ ሁኔታ እንድትጠቀም መንገድ ከፍተዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎች መስፋፋት የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደጉ ባለፈ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲጠናከር በማድረግ ዜጎች የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች እንዲያውቁና እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ይህም የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭን በማስፋፋትና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጨምረውን አስተዋጽኦ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አበርክቶ እያስገኘ ነው። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በኢኮ ቱሪዝም፣ በባህል ውጤቶች ንግድና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል። በመሆኑም ቱሪዝም ከመዝናኛ ዘርፍ ባሻገር የልማት፣ የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ ለውጥ ማስፈንጠሪያ ምሰሶ እየሆነ መጥቷል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሃብቶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ጋር በማስተሳሰር፣ በኮሪደር ልማት፣ በተሻሻለ የአገልግሎትና በዓለም አቀፍ የማስተዋወቅ ስራዎች በቱሪዝም ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች። የተቀናጀው የልማት አቅጣጫ ሀገሪቱ ለዘመናት የያዘቻቸውን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም፣ የሥራ ዕድልና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ እየቀየረ ይገኛል። ዛሬ ቱሪዝም የኢኮኖሚ አንድ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል፣ የባህልና ታሪክ መዳረሻ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ሀገር ለማድረግ የሚያግዝ ስትራቴጂያዊ አቅም ሆኗል። ይህም ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የባህል ትስስርና የዓለም አቀፍ ተሳትፎ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። በተለይም የዲጂታል ዘመን የቱሪዝም ዘርፉን ለማስተዋወቅ ዕድሎችን የሚያሰፋ በመሆነኑ ይህንኑ በመጠቀም፣ እንደ አይሾ ስፒድና ዲላን ፔጅ ያሉ ዓለም አቀፍ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ውብ ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክ ለዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ትኩረት እያሳደጉ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ከጉብኝት ዘርፍ ባሻገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀገር ገጽታ ግንባታና የዓለም አቀፍ ትስስር መሣሪያ በማድረግ ወደ አዲስ የቱሪዝም ዘመን እየተሸጋገረች ትገኛለች። ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የብልፅግና ዘመን የኢኮኖሚ መሰሶነቱን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል።
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 7190
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers