ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአማራ ክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት በቅንጅት መስራታቸው በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ ነው
Nov 6, 2025 44
ባሕር ዳር፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት በላቀ ቅንጅት መስራታቸው በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው አስታወቁ። የክልሉ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በባሕርዳር ከተማ እየገመገመ ነው። በግምገማው መድረክ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው እንደገለጹት፤ የዳኝነትና የፍትህ አካላት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተቀናጅተው በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ። የተቋማቱ ቅንጅትም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያና ፍትህ ቢሮ ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋማቱ ነጻነትና ገለልተኝነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ስራቸውን በተቀናጀ ትብብር በመስራታቸው የክልሉን የፍትህ ስርዓት ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። በዚህም በዳኝነትና ፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በትብብር በመሙላትና ጥንካሬዎቻቸውን በማስቀጠል መሰረታዊ ለውጥ እያመጡ መሆኑን አስታውቀዋል። የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ በማዘመን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግም የሰው ሃብት አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት። ይህም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ለወጭና እንግልት ሳይዳረጉ የርቀት ክርክሮችንና ቅሬታ የሚያቀርቡበት ስርዓት መዘርጋት እንዳስቻለም አንስተዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በበኩላቸው፤ የፍትህና ዳኝነት አካላት በቅንጅትና ትብብር መስራታቸው ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። ማረሚያ ቤቶች የፍርድ ውሳኔ ያገኙ ዜጎችን በአግባቡ በማረምና በመልካም ስነ ምግባር የማነፅ ተግባር ላይ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር ሃብታሙ ሲሳይ ናቸው። ተቋማቱ በቅንጅትና ትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ያለው አሰራር መዘርጋቱ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀን በሚቆየው መድረክ የክልሉ የዳኝነትና ፍትህ ተቋማት አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በደብረ ብርሃን ከተማ 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ነው
Nov 6, 2025 55
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 27/ 2018 (ኢዜአ) ፡- በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ወጣትና ስፖርት መምሪያ ገለጸ። በከተማው እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀደም ሲል በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 16 የመኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል። በዘህ ወቅት በመምሪያው የወጣቶች አደረጃጀት ማካተትና ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ አወቀ ሀይለማሪያም እንዳመለከቱት፤ በከተማው እየተከናወነ ያለው የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እየተከናወነ ነው። በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የደም ልገሳ፣ 117 አዲስ መኖሪያ ቤቶችን የመገንባትና ያረጁ ቤቶችን የመጠገን ስራን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንደሚከናወኑ አንስተዋል። በዚህም 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተመልክቷል። የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ በለጥሽ ግርማ በበኩላቸው፤ በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሴቶችና አረጋውያን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዛሬ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት 16 የመኖሪያ ቤቶች የዚሁ አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ በሀይሉ ገብረህይወት እንዳሉት ፤ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በራስ አቅም በመርዳት ችግራቸወን መፍታት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተንከባካቢና ደጋፊ የሌላቸውን ወገኖች በማገዝ የተጀመረው አገልግሎት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። የመኖሪያ ቤት እድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የወረዳው አርሶ አደሮች የውሃ አማራጮችን በመጠቀም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሰማርተዋል
Nov 6, 2025 131
ሮቤ ፤ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-በአካባቢያቸው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴን እያለሙ መሆናቸውን የባሌ ዞን ጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ። በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ከጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል ሼህ አህመድ ከድር በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው የወንዝ ውሃን በሞተር ፓምፕ በመሳብ ባለፉት ሦስት ዓመታት ስንዴንና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬ በማፈራረቅ በማልማት ተጠቃሚ እየሆኑ ናቸው ። ዘንድሮም አንድ ሄክታር መሬታቸውን በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ወደ ስራ መግባታቸውንና ከዚህም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። ከዚህ በፊት የዝናብ ወቅትን ብቻ በመጠበቅ ከሚያለሙት ሰብል የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን እንዳልቻሉ ያስታወሱት ደግሞ ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ከማል አብዱ ናቸው። ባለፉት አመታት በተሰማሩበት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በመሰማራታቸው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ማደጉን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኘውን ወንዝ በሞተር ፓምፕ በመሳብ ከሌሎች የአካባቢያቸው አርሶ አደሮች ጋር በኩታገጠም አሰራር ስንዴንና ሌሎች ገቢ የሚያስገኙ ሰብሎችን እያለሙ መሆናቸውን አመልክተዋል። የጋሠራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ተፈራ በበኩላቸው የወረዳው አርሶ አደር የዝናብ ውሃን ብቻ ጠብቆ ከሚያካሄደው የሰብል ልማት በተጓዳኝ በበጋውም ወቅት መስኖን በመጠቀም ስንዴንና ሌሎች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልይ መሐመድ በበኩላቸው በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል ። እስከ አሁን በተደረገው የሥራ እንቅስቃሴም ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ማልማት ተችሏል። የበጋ መስኖ ስንዴን ውጤታማ ለማድረግ 2ሺህ የሚሆኑ የውኃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች በረዥም ጊዜ ብድር በልማቱ ለተሳተፉ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን እንዲሁ። በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት በተለያዩ ሰብሎችና አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ ከሚገኘው ከ183 ሺህ ሄክታር ከሚበልጥ መሬት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገልጿል።
የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ታላቅ አየር ኃይል እየተገነባ ነው -ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
Nov 6, 2025 116
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 27/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ታላቅ አየር ኃይል እየተገነባ ነው ሲሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ። ዋና አዛዡ ከቢሾፍቱ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር 90ኛ ዓመት የአየር ኃይል የምስረታ ቀን አከባበርን አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያ አየር ኃይል በየዘመናቱ የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ አኩሪ ገድል መፈፀሙን ዋና አዛዡ ገልፀዋል። አሁንም የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥንና የሕዝባችን መመኪያ የሆነ ተቋም እየተገነባ ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነት እና የአንድነት ምልክት "በሚል መሪ ሐሳብ 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብርም አስታውቀዋል። የምስረታ ቀኑ በአቪዬሽን ኤክስፖ፣ በአየር ትርኢት እና በሌሎችም ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገልጿል። የምስረታ ቀኑ ለሀገር፣ ለተቋም ብሎም ለቢሾፍቱ ከተማ እድገትና የገፅታ ግንባታ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ ከተማውን በማስዋብና ሰላሟን በመጠበቅ ነዋሪዎች ንቁ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያላቸውን ፖሊሲዎች መተግበር ይገባል
Nov 6, 2025 83
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያላቸው ፖሊሲዎች መተግበር እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ ገለጹ። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ(POA)፣ በቻይና የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ እና የትብብር፣ የውይይትና የጥናት ማዕከል ትብብር የተዘጋጀው የቻይና አፍሪካ ስትራቴጂክ የትብብር ዓውደ ጥናት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመድረኩ የቻይና የሥራ ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የተለያዩ ዘርፎች ኮሚሽነሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ፤ በአፍሪካ እና በቻይና መካከል ያለው አጋርነት ወሳኝ ነው ብለዋል። የዩኒዶ ተልዕኮም ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ማስፈን መሆኑን ጠቁመው፤ ዘላቂነት ያለውን የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ፖሊሲ ትግበራ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የኢኮኖሚ አማካሪ አሊ ዘፋር በበኩላቸው፤ መድረኩ ከቻይናና አፍሪካ በተጓዳኝ የኃይል ልማት ትብብርን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ልማት መሠረት መሆኑን አንስተው፤ ለመላው አፍሪካውያን የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከ2025 እስከ 2030 ባለው ጊዜ 75 በመቶ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳካት ዒላማ መሰነቋን አውስተው፤ ከዚህ ውስጥ 95 በመቶው ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ኢትዮጵያን በታዳሽ ኃይል ግንባር ቀደም ከሆኑ ሀገሮች ተርታ እንደሚያሰልፋት ገልጸዋል። ቻይና ከራሷ ተሞክሮ በመነሳት የአፍሪካን የታዳሽ ኃይል ለማሳደግ አስተዋፅዖ ማድረግ እንደምትችል ጠቁመዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን አብሮነት ማጠናከርና ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የቻይና ተነሳሽነት ከአፍሪካ ልማት ፍላጎት ጋር የተዛመደ መሆኑን ጠቁመው፤ ለአብነትም የኃይል ዘርፉን የጠቀሱት ደግሞ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ኢነርጂ ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ሳምሶን መክብብ(ዶ/ር) ናቸው። ይህን የተቀመጠ ግብ ለማሳካት በኢንዱስትሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና በመንግሥት የሚደረጉትን ሁሉንም ጥረቶች ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
ፖለቲካ

ለዘላቂ ሰላም ግንባታና ለልማት ስራዎች መጠናከር ከክልሉ መንግስት ጋር ተቀራርበን እየሰራን ነው -የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
Nov 6, 2025 97
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ለዘላቂ ሰላም ግንባታና ለልማት ስራዎች መጠናከር ከክልሉ መንግስት ጋር ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑን የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮች በክልሉ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰላም እና ልማት እንዲኖር ከክልሉ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ለሰላምና ጸጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለክልሉ መንግስት አስፈላጊ ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል። የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ፤ የምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች በየቀበሌው ያለውን ሁኔታ በመከታተል ሰላምን ለማስፈን የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ከሰላም ጋር በተያያዘ ለውይይት የሚቀርቡ ጉዳዮች ካሲኖሩም ሀሳቦቹን በመለየት ወደ ምክር ቤቱ በማምጣት ውይይት ተደርጎበት ለመፍትሄው በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ችግሮችም ሲያጋጥሙ ለመንግስት አካላት በግልጽ በማቅረብ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን ገልጸው መንግስትም ከምክር ቤቱ የሚሰጡትን አስተያየቶች ተቀብሎ እየተገበረ መሆኑን አስረድተዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ አቶ ታሪኩ ድምበሩ በበኩላቸው፤ ሰላምን በማጽናት ሂደት የፖለቲካ ተዋናዮች ድርሻ አላቸው ብለዋል። የጋራ ምክር ቤቱ በተለይም የጸጥታ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎችን በመለየት ቅድሚያ ትኩረት የሚፈልጉ እንዲሁም መሻሻል በታየባቸው ደግሞ ሰላምን ዘላቂ ከማድረግ አንጻር ከመንግስት ጋር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤት 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘ ምክር ቤት መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያና ሩሲያ ግንኙነትን ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ያለመ ምክክር ተካሄደ
Nov 5, 2025 288
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 26/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነቶችን ወደ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ያለመ ምክክር ተካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የፋይናንስ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ሥራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ምክትል ሀላፊ ማክሲም ኤስ ኦሬሽኪን እና ከሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፥በተለያዩ ስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል። በተጨማሪም በዘላቂ ልማት፣ በቀጣናዊ ደኅንነት እና በጋራ ልማት ላይ መምከራቸው ተገልጿል። ሚኒስትር ጌዲዮን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ሩሲያ በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ላደረገችው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አመሥግነዋል። በቀጣይም በግብርና፣በማኑፋክቸሪንግ፣ በአይሲቲ፣ በማዕድን ልማት፣ በብረታ ብረት፣ በኢነርጂ መሠረተ ልማት፣ በኑክሊየር እና ሌሎች ዘርፎች በትብብር መሥራት የሚቻልባቸው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች መኖራቸውን አስገንዝበዋል።
የሕዳሴ ግድብ የአካባቢውን ጂኦ ፖለቲካዊ አሰላለፍ የቀየረና የዲፕሎማሲ መስኩን ስኬታማ ስራ ያረጋገጠ ነው
Nov 5, 2025 188
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአካባቢውን ጂኦ ፖለቲካዊ አሰላለፍ የቀየረና የዲፕሎማሲ መስኩን ስኬታማ ተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ምሁራን ገለጹ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፖለቲክስና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ እና የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አየለ በከሪ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ማንኛውም ሉዓላዊ ሀገር ያለውን የተፈጥሮ ሀብት አልምቶ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳለው አስታውቀዋል፡፡ ምሁራኑ ኢትዮጵያ ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ በሃብቶቿ የመጠቀም መብት እንዳላት ጠቅሰው፤ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የሚደረጉ ተግባራት መጠናከር አለባቸው ብለዋል። የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አየለ በከሪ፤ ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው ፕሮጀክቶች ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ ዜጎችን ከድህነት ለማውጣት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፖለቲክስና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ይሰነዘሩባት የነበሩ ጫናዎችን ለመቋቋም ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ማከናወኗን አስታውሰዋል፡፡ በመንግስትና በዜጎች ትብብር የተከናወኑ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎች ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ሲያራምዱ የነበሩ አካላትን ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ አድርጓል ነው ያሉት። ፕሮፌሰር አየለ በከሪ ኢትዮጵያ የታላቁን የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዓለም አቀፍ ሕግን አክብራ ማጠናቀቋንም ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የተከተለችው አካሄድ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት ማንም ሊያስቆመው እንደማይችል ያሳየ መሆኑን አመልክተው፤ ይህም ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን ነው የጠቀሱት። ግብጽ የዓባይን ወንዝ በበላይነት የመቆጣጠር ፍላጎቷ ማብቃቱን በመገንዘቧ የቀይ ባህር መድረክ የሚል ቡድን ማቋቋሟን ተናግረዋል፡፡ ግብጽ በመድረኩ በመታገዝ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ጉዳይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳይኖራት ጥረት እያደረገች መሆኑን አንስተዋል። ይህንኑ እንቅስቃሴ ለመመከት የተጠናከሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ ነው ያነሱት። ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአካባቢው ያለውን የጂኦ ፖለቲካዊ አሰላለፍ የቀየረና በዲፕሎማሲ መስክ የተገኘውን ድል ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማረጋገጥ በዲፕሎማሲው መስክ ያከናወነቻችው ተግባራት ውጤታማ እንዳደረጓት ነው የተናገሩት።
የምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው ግዳጆች ሁሉ በጀግንነት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት የሀገሩ ዳር ድንበርና የሉአላዊነቷ ዘብ ሆኖ ቆሟል
Nov 5, 2025 203
ሐረር፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው ግዳጆች ሁሉ በጀግንነት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት የሀገሩ ዳር ድንበርና የሉአላዊነቷ ዘብ ሆኖ መቆሙ ተገልጿል። በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ፤ በምስራቅ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርቶ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እየተወጣ ይገኛል። በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው አልሸባብ ሾልኮ በመግባት የኢትዮጵያ የልማትና የሰላም እንከን እንዳይሆን ዕዙ አስተማማኝ መከታ ሆኖ ሌት ከቀን ግዳጁን እየተወጣ መሆኑ ይታወቃል። በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ 305ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ማርሼት ፈለገ፤ ዕዙ በተሰማራባቸው ግዳጆች ሁሉ በጀግንነት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት የሀገሩ ዳር ድንበርና የሉአላዊነቷ ዘብ ሆኖ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የቀጠናውን ሠላም የማረጋገጥና የምስራቁን የሀገሪቷን አካባቢዎች ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ በማድረግና ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲከናወኑ ሌት ከቀን በመቆም ተልዕኮውን በላቀ ብቃትና በቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኮሩ አባላት በቀጣናው የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሀይሎችን ተከታትለው እርምጃ በመውሰድ በአካባቢው ምንም አይነት ስጋት እንዳይኖር እየሰሩ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በምስራቅ ኢትዮጵያ አገልግሎት የጀመሩ እና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ምንም አይነት መሰናክል እንዳይገጥማቸው ኮሩ በአስተማማኝ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የዕዙ የ28ኛ ክፍለጦር 2ኛ ሬጅመንት 1ኛ ሻምበል አዛዥ መቶ አለቃ ጌታሰው ጋሻው በበኩላቸው፤ዕዙ በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው አል ሸባብ፣ ሌሎች የውጭ ጠላቶች ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት ስጋት እንዳይሆኑ ግዳጅና ሃላፊነቱን በላቀ ብቃት እየተወጣ መሆኑን አንስተው ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የዕዙ የ27ኛ ክፍለጦር ዘመቻ መኮንን መቶ አለቃ ጌታ መሳይ ዳዊት፤ዕዙ ለሀገሩ ዳር ድንበርና ለሉአላዊነቷ መከበር በጀግንነት፣ በላቀ ብቃትና በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የኤፒሲ ብረት ለበስ አዛዥ መቶ አለቃ ደጀኔ አበበ በበኩላቸው ዕዙ በምስራቅ ኢትዮጵያና በድንበር አካባቢዎች አስተማማኝ መከታ ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጣ የሚችል ትንኮሳ ካጋጠመ ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ የሚችል፤ በየትኛውም ስፍራ እና የአየር ሁኔታ ግዳጁን በላቀ ብቃት የሚወጣ አስተማማኝና ጠንካራ ሰራዊት ተገንብቷል ሲሉም አረጋግጠዋል።
በዞኑ የተዘረጋው የቀበሌ አደረጃጀት የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እያገዘ ነው
Nov 5, 2025 167
አዳማ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ሸዋ ዞን የተዘረጋው የቀበሌ አደረጃጀት ህብረተሰቡ የመንግስት አገልግሎቶችን በቅርበት እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እያገዘ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አባቡ ዋቆ ገለፁ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ህዝቡን በቅርበት በማገልገል አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት ዘርግቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በቅርቡ በተካሄደው የክልሉ መንግስት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ የቀበሌ አደረጃጀቶቹ በትክክል የኢኮኖሚ ሽግግር የሚረጋገጥባቸው ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውን አንስተዋል። እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የቀበሌ አደረጃጀቶች ህዝቡ አገልግሎት የሚሰጠው፣ ልማት የሚያሳልጥለት አስተዳደር በቅርበት እንዲያገኝ ማድረግ አስችሏል ሲሉም ተናግረዋል። በዚሁ መነሻነት ኢዜአ ያነጋገራቸው የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አባቡ ዋቆ እንደገለፁት የቀበሌ አደረጃጀቱ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎትና የልማት ጥያቄዎችን በቅርበት ለመመለስ ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው። በተለይም ከዚህ ቀደም የገጠሩ ህዝብ ከመሬት፣ ከፍትህና ሌሎች ጉዳዮች ጋር የተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳና ከተማ በመመላለስ አላስፈላጊ ወጪ እና የስራ ጊዜን የሚሻማ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። የቀበሌ አደረጃጀቶቹ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። በዚህም በህዝብና በባለሃብቶች ተሳትፎ እንዲሁም በመንግስት አቅም የቀበሌ ጽሕፈት ቤቶች ግንባታን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። የቀበሌ መዋቅሩ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ባሻገር ዘላቂ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈንም ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው በዚህ ወቅትም ዞኑ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል። በዚህ ወቅትም በተለያየ ምክንያት በ59 ቀበሌዎች ጉዳት የደረሰባቸው የመብራት እና የመሰረተ ልማት ተቋማት ጥገና ተደርጎ ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል ነው ያሉት። በተመሳሳይም የቀበሌ አደረጃጀቱ የገቢ አሰባሰብ አቅምን ለማሳደግ እያገዘ መሆኑን አንስተው በገጠሩ አካባቢ የቤተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መሰረት እየጣለ መሆኑንም ተናግረዋል። በምስራቅ ሸዋ ዞን የተደራጁ 302 ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን በእነዚህ ቀበሌዎች የተሟላ የሰው ሀይል ተመድቦ ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን የጥፋት እቅድ በማምከን ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን- የመንግስት ሰራተኞች
Nov 4, 2025 275
ወልዲያ ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች ገለጹ። "የውጭ ባዳ እና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የውይይት መድረክ አካሂደዋል። በውይይቱ መድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሲሳይ አለሙ እና አቶ አበራ አብርሃ፤ ለኢትዮጵያ መልካም ነገር የማያስቡ እና የማይመኙ ታሪካዊ ጠላቶች በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለጥፋት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም የውስጥ ባንዳዎችን ተልእኮ ፈፃሚ በማድረግ የልማት ስራዎች እንዲደናቀፉ እና በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲደፈርስ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ጭምር ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ አሰፋ፤ የባንዳዎችና ባዳዎች የጥፋት ሙከራና እንቅስቃሴ በሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ እና በጸጥታ ሃይሉ ጥብቅ ቁጥጥር እየመከነ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት የህዝቡ በተለይም የመንግስት ሰራተኛው እገዛና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው-ምሁራን
Nov 4, 2025 274
ድሬደዋ፤ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦በአሻጥር ያጣነውን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ። የባሕር በር ጉዳይ የሕልውናና ሀገርን የማስቀጠል ተቀዳሚ አጀንዳ መሆኑንም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የመንግሥት አቋምና አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ የተደረገበት መንገድ እና ውሳኔ ተፈትሾ ተጨባጭ ማስረጃ መታጣቱን ማንሳታቸው ይታወሳል። የባሕር በር ጉዳይ የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን በጉዳዩ ላይ አነጋግሯል። የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ ሐይሉ እንዳሉት፥ በአሻጥር ያጣነው የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው ብለዋል። ሀገራችን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄዋ በታሪክም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ተቀባይነት ያለው የሕልውና ጥያቄ ነው ያሉት ደግሞ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምሕር አቶ ዋኬና አፍካላ ናቸው። ይህን ታሪካዊና ሕጋዊ መብቷን በዲፕሎማሲያዊ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ ለማግኘት መንግስት የጀመራቸው ተግባራት እና ውሳኔዎች ወሳኝ እርምጃ መሆናቸውን አንስተዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ ሐይሉ አክለው እንደገለፁት፥ ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተነጠለችበት መንገድ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ የሚመላለስ አሁናዊ የሕልውና ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል። የሀገርን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ፣ዕድገትና ሕልውና ለማረጋገጥ የመንግስት አቋምና እየተጓዘበት ያለው መንገድ ትክክለኛና ወቅታዊ ነው ብለዋል። ከ130 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ እና ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት አገር ባሕር ተዘግቶባት ሕልውናዋን ማስቀጠል አይቻልም የሚሉት ደግሞ መምሕርና የአፍሪካ ቀንድ ፀሐፊ አቶ ዋኬና አፍካላ ናቸው። የባሕር በር ጥያቄን በአለምአቀፍ ሕጎችና በጋራ የመልማት ተቀዳሚ ዲፕሎማሲያዊ መርሕ ከዳር ለማድረስ የተቀናጀ ጥረቱ መጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ፥ የሕልውና ጥያቄ የሆነውን የባሕር በር የማግኘት ጉዞ በማሳካት ረገድ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ጭምር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ብለዋል። በተለይም የኢትዮጵያን መልማትና ማደግ ባገኙት አጋጣሚ የሚያጠለሹት ግብፅን የመሳሰሉ ታሪካዊ ባላንጣ ሀገራትን መልዕክቶች በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ በማጋለጥ የሀገራችንን በጋራ የመልማት ተቀዳሚ መርሕን ማሳወቅ ላይ መረባረብ ይገባናል ብለዋል።

ማህበራዊ
በአማራ ክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት በቅንጅት መስራታቸው በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ ነው
Nov 6, 2025 44
ባሕር ዳር፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት በላቀ ቅንጅት መስራታቸው በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው አስታወቁ። የክልሉ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በባሕርዳር ከተማ እየገመገመ ነው። በግምገማው መድረክ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው እንደገለጹት፤ የዳኝነትና የፍትህ አካላት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተቀናጅተው በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ። የተቋማቱ ቅንጅትም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያና ፍትህ ቢሮ ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋማቱ ነጻነትና ገለልተኝነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ስራቸውን በተቀናጀ ትብብር በመስራታቸው የክልሉን የፍትህ ስርዓት ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። በዚህም በዳኝነትና ፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በትብብር በመሙላትና ጥንካሬዎቻቸውን በማስቀጠል መሰረታዊ ለውጥ እያመጡ መሆኑን አስታውቀዋል። የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ በማዘመን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግም የሰው ሃብት አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት። ይህም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ለወጭና እንግልት ሳይዳረጉ የርቀት ክርክሮችንና ቅሬታ የሚያቀርቡበት ስርዓት መዘርጋት እንዳስቻለም አንስተዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በበኩላቸው፤ የፍትህና ዳኝነት አካላት በቅንጅትና ትብብር መስራታቸው ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። ማረሚያ ቤቶች የፍርድ ውሳኔ ያገኙ ዜጎችን በአግባቡ በማረምና በመልካም ስነ ምግባር የማነፅ ተግባር ላይ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር ሃብታሙ ሲሳይ ናቸው። ተቋማቱ በቅንጅትና ትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ያለው አሰራር መዘርጋቱ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀን በሚቆየው መድረክ የክልሉ የዳኝነትና ፍትህ ተቋማት አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በደብረ ብርሃን ከተማ 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ነው
Nov 6, 2025 55
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 27/ 2018 (ኢዜአ) ፡- በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ወጣትና ስፖርት መምሪያ ገለጸ። በከተማው እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀደም ሲል በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 16 የመኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል። በዘህ ወቅት በመምሪያው የወጣቶች አደረጃጀት ማካተትና ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ አወቀ ሀይለማሪያም እንዳመለከቱት፤ በከተማው እየተከናወነ ያለው የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እየተከናወነ ነው። በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የደም ልገሳ፣ 117 አዲስ መኖሪያ ቤቶችን የመገንባትና ያረጁ ቤቶችን የመጠገን ስራን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንደሚከናወኑ አንስተዋል። በዚህም 85 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተመልክቷል። የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ በለጥሽ ግርማ በበኩላቸው፤ በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሴቶችና አረጋውያን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዛሬ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት 16 የመኖሪያ ቤቶች የዚሁ አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ በሀይሉ ገብረህይወት እንዳሉት ፤ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በራስ አቅም በመርዳት ችግራቸወን መፍታት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተንከባካቢና ደጋፊ የሌላቸውን ወገኖች በማገዝ የተጀመረው አገልግሎት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። የመኖሪያ ቤት እድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋ በጥናትና ምርምር በማገዝ ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ ነው
Nov 6, 2025 57
አምቦ ፤ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋ በጥናትና ምርምር በማገዝ ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችል ተግባር በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድሕን የባሕል ጥናትና ምርምር ማዕከል ከኦሮሞ ምርምር ማሕበር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ የሕብረተሰቡን ባሕልና ቋንቋ በምርምር በመደገፍ የበለጠ ማሳደግ ዓላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። በዚሁ ወቅት የኦሮሞ ምርምር ማሕበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተፈሪ ቡዛየሁ (ዶ/ር )፤ የኦሮሞን ባሕል እና ቋንቋ በጥናትና ምርምር በማገዝ የበለጠ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በተለይም የገዳ ስርዓትን ማዕከል ባደረገ መልኩ የኦሮሞን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ የበለጠ ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል። ዛሬ የተፈረመው ስምምነትም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ተናግረው ስምምነቱ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። በጋራ ምርምር እና ጥናቶችን ማካሄድ፣ የምርምር ጉባኤዎችን ማዘጋጀት እና የልምድ ልውውጦችን ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። ማሕበሩ በእነዚሕ ጉዳዮች ላይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከሎሬት ጸጋዬ ገብረመድሕን የባሕል ጥናትና ምርምር ማዕከል በተጨማሪ ከሌሎችም ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለመስራት ማቀዱንም ገልጸዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን ማሾ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ስምምነቱ ባሕል እና ቋንቋን የሚያሳድጉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በጋራ ማከናወን እና ጥቅም ላይ ማዋል ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ስምምነቱ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድሕን የባሕል ጥናትና ምርምር ማዕከል ይበልጥ እንዲያድግ እድል የሚፈጥርለት መሆኑን አስረድተዋል። የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ሳሙኤል ለይኩን (ዶ/ር) ፤ ከማሕበሩ ጋር የተደረገው ስምምነት ሁሉን አቀፍ የባሕል እና ቋንቋ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል። ማዕከሉ በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባሕልና በኪነ-ጥበብ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስምምነቱም የተጀመሩ ስራዎችን ለማፋጠን ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።
በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት ውጤቶች ተገኝተዋል
Nov 6, 2025 84
ጂንካ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት ውጤቶች መገኘታቸውን የክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል። በክልሉ የወባ መከላከል ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል እና የፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ መና መኩሪያ በክልሉ በክረምት ወራት የወባ ስርጭት ከፍ ብሎ መታየቱን አንስተዋል። ሆኖም ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የወባ ስርጭትን ለመቀነስና ለመቆጣጠር የተሳኩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል። በክልሉ በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች የወባ ስርጭቱ ከፍ ብሎ መታየቱን ጠቅሰው፥ በእነዚህ አካባቢዎች ህብረተሰቡንና አጋር ድርጅቶችን ያሳተፈ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በንቅናቄ መሰራቱን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም በክልሉ በወባ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ጠቁመው በሽታውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል። በቢሮው የበሽታ መከላከል ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ካሳዬ በበኩላቸው፤ በክልሉ በመጀመርያው ሩብ ዓመት የጤና አጋሮችን በማስተባበር የወባ ስርጭቱ ከፍ ብሎ በታየባቸው አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ በኬሚካል የተነከረ የአልጋ አጎበር መሰራጨቱን ተናግረዋል። በ488ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የነበሩ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራ ተሰርቷል ብለዋል። በተጨማሪም የወባ በሽታ ስርጭት ከፍ ብሎ በሚታይባቸው 10 ወረዳዎች የቤት ለቤት የፀረ-ወባ ኬሚካል ርጭት መከናወኑንም ጠቁመዋል። በአጠቃላይ በመጀመርያው ሩብ ዓመት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከወባ በሽታ መጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
የወረዳው አርሶ አደሮች የውሃ አማራጮችን በመጠቀም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሰማርተዋል
Nov 6, 2025 131
ሮቤ ፤ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-በአካባቢያቸው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴን እያለሙ መሆናቸውን የባሌ ዞን ጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ። በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ከጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል ሼህ አህመድ ከድር በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው የወንዝ ውሃን በሞተር ፓምፕ በመሳብ ባለፉት ሦስት ዓመታት ስንዴንና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬ በማፈራረቅ በማልማት ተጠቃሚ እየሆኑ ናቸው ። ዘንድሮም አንድ ሄክታር መሬታቸውን በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ወደ ስራ መግባታቸውንና ከዚህም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። ከዚህ በፊት የዝናብ ወቅትን ብቻ በመጠበቅ ከሚያለሙት ሰብል የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን እንዳልቻሉ ያስታወሱት ደግሞ ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ከማል አብዱ ናቸው። ባለፉት አመታት በተሰማሩበት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በመሰማራታቸው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ማደጉን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኘውን ወንዝ በሞተር ፓምፕ በመሳብ ከሌሎች የአካባቢያቸው አርሶ አደሮች ጋር በኩታገጠም አሰራር ስንዴንና ሌሎች ገቢ የሚያስገኙ ሰብሎችን እያለሙ መሆናቸውን አመልክተዋል። የጋሠራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ተፈራ በበኩላቸው የወረዳው አርሶ አደር የዝናብ ውሃን ብቻ ጠብቆ ከሚያካሄደው የሰብል ልማት በተጓዳኝ በበጋውም ወቅት መስኖን በመጠቀም ስንዴንና ሌሎች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልይ መሐመድ በበኩላቸው በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል ። እስከ አሁን በተደረገው የሥራ እንቅስቃሴም ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ማልማት ተችሏል። የበጋ መስኖ ስንዴን ውጤታማ ለማድረግ 2ሺህ የሚሆኑ የውኃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች በረዥም ጊዜ ብድር በልማቱ ለተሳተፉ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን እንዲሁ። በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት በተለያዩ ሰብሎችና አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ ከሚገኘው ከ183 ሺህ ሄክታር ከሚበልጥ መሬት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያላቸውን ፖሊሲዎች መተግበር ይገባል
Nov 6, 2025 83
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያላቸው ፖሊሲዎች መተግበር እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ ገለጹ። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ(POA)፣ በቻይና የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ እና የትብብር፣ የውይይትና የጥናት ማዕከል ትብብር የተዘጋጀው የቻይና አፍሪካ ስትራቴጂክ የትብብር ዓውደ ጥናት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመድረኩ የቻይና የሥራ ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የተለያዩ ዘርፎች ኮሚሽነሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ፤ በአፍሪካ እና በቻይና መካከል ያለው አጋርነት ወሳኝ ነው ብለዋል። የዩኒዶ ተልዕኮም ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ማስፈን መሆኑን ጠቁመው፤ ዘላቂነት ያለውን የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ፖሊሲ ትግበራ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የኢኮኖሚ አማካሪ አሊ ዘፋር በበኩላቸው፤ መድረኩ ከቻይናና አፍሪካ በተጓዳኝ የኃይል ልማት ትብብርን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ልማት መሠረት መሆኑን አንስተው፤ ለመላው አፍሪካውያን የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከ2025 እስከ 2030 ባለው ጊዜ 75 በመቶ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳካት ዒላማ መሰነቋን አውስተው፤ ከዚህ ውስጥ 95 በመቶው ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ኢትዮጵያን በታዳሽ ኃይል ግንባር ቀደም ከሆኑ ሀገሮች ተርታ እንደሚያሰልፋት ገልጸዋል። ቻይና ከራሷ ተሞክሮ በመነሳት የአፍሪካን የታዳሽ ኃይል ለማሳደግ አስተዋፅዖ ማድረግ እንደምትችል ጠቁመዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን አብሮነት ማጠናከርና ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የቻይና ተነሳሽነት ከአፍሪካ ልማት ፍላጎት ጋር የተዛመደ መሆኑን ጠቁመው፤ ለአብነትም የኃይል ዘርፉን የጠቀሱት ደግሞ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ኢነርጂ ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ሳምሶን መክብብ(ዶ/ር) ናቸው። ይህን የተቀመጠ ግብ ለማሳካት በኢንዱስትሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና በመንግሥት የሚደረጉትን ሁሉንም ጥረቶች ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
የቻይና አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ትብብር በምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ነው
Nov 6, 2025 100
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ የቻይና አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትብብር በምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያሳየ መምጣቱ ተገለጸ። በቻይና የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እና የውይይት የጥናትና ትብብር ማዕከል ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ(POA) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የቻይና የሥራ ኃላፊዎች የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የተለያዩ ዘርፎች ኮሚሽነሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሲኤ) የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የፋይናንስና አስተዳደር ዳይሬክተር ስቴቨን ካሪንጊ(ዶ/ር) የቻይና አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ትብብር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለሚገኝባት አፍሪካ ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። በአፍሪካ የኢንተርኔት መሰረተ ልማትና ተደራሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፤ አሁን ካለው ፍላጎት አኳያ በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማሳለጥ የሃይል አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማት እጥረትና የሰለጠነ የሰው ሃይል ውስንነቶች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። ኮሚሽኑ ሀገራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እያደረጉ ያለው ጥረት በገበያ ማፈላለግና በቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ቻይና የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ልማትና ዲጂታላይዜሽን ላይ እያደረገች የሚገኘው አስተዋጽኦ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና ለሀገራት ምጣኔ ሃብት ዕድገት የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል። በቻይና አፍሪካ ልማት ፈንድ የኢትዮጵያ ቢሮ ተወካይ ሊ ሺባኦ፤ ቻይና ለአፍሪካ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ድጋፍ እያደረገች መሆኑንም አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዘላቂ የኃይል ልማት በመፍጠር ለዲጂታል ኢኮኖሚው የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገች መሆኑንም ጠቅሰዋል። በቻይና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አካዳሚ የደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ሊዩ ዩኢ እንደተናገሩት፤ የቻይና አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ትብብር እያደገ መጥቷል። የቻይና ምጣኔ ሀብት ዕድገት መሠረቱ ዲጂታል መሠረተ ልማትና የኢንዱስትሪ መስፋፋት መሆኑን ጠቅሰው፤ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ሀገራቸው ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት የሚጥሉትን የኔትወርክ የክላውድ ግንባታን በማስፋት አፍሪካን እያስተሳሰረች መሆኑን ጠቁመዋል። ቻይናና አፍሪካ ዲጂታል ስነ ምህዳር ላይ ትብብራቸውን የበለጠ የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ እየተተገበሩ መሆኑንም አንስተዋል። በቻይና ብሄራዊ ልማትና ለውጥ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ትብብር ከፍተኛ ተመራማሪ ዚኢ ሊንካን(ዶ/ር)፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል። በቻይና የሰው ሰራሽ አስተውሎት በፖሊሲ ተደግፎ በተለያዩ ዘርፎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ ኢንዱስትሪ ፈጣንና ውጤታማ መሆኑን አብራርተዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በግብር፣ በኢንዱስትሪ አገልግሎትና በሌሎችም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት እየታየ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራትን ከቻይና ጋር እያደረጉ ባለው የዲጂታል ኢኮኖሚ ትብብር የኢኮኖሚ ዕድገታቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።
በቻይና እና አፍሪካ መካከል የሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ትብብር እየተጠናከረ መጥቷል
Nov 6, 2025 66
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ በቻይና እና አፍሪካ መካከል የሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ልማት ዲፓርትመንት ፖሊሲ ኦፊሰር ቢያትሪስ ኢጉሉ ገለጹ። በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (POA)፣ በቻይና የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ እና የውይይት፣ የጥናትና የትብብር ማዕከል ትብብር የተዘጋጀው የቻይና አፍሪካ ስትራቴጂክ የትብብር ዓውደ ጥናት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ልማት ዲፓርትመንት ፖሊሲ ኦፊሰር ቢያትሪስ ኢጉሉ እንዳሉት፤ ቻይና በአፍሪካ ያላት ኢንቨስትመንት ለበርካታ አፍሪካውያን ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ በኢንቨስትመንቱ ከስራ ዕድል ባለፈ ቻይናዊያን ባለሙያዎች ለአፍሪካዊያን እውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዕድል እየፈጠሩ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በቻይናና አፍሪካ ግብርና ትብብር ማዕቀፍ የስልጠና መርሃ ግብር 10 ሺህ አፍሪካዊያን ባለሙያዎች በግብርና ሜካናይዜሽን፣ መስኖ ልማት፣ ግብርና ማቀነባበር ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተዳደር ላይ ስልጠና መሰጠቱን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ በብሉ ኢኮኖሚ መስክም ዘላቂ ዓሳ ሀብት ልማት ፣የውሃ ዳርቻዎች መሰረተ ልማት እና በውሃ ሀብት ልማት ላይ የአፍሪካ እና ቻይና ትብብር ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል። ቻይናና አፍሪካ በሃይል እና ኢንዱስትሪ ልማት ላይም ያላቸው አጋርነት ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ቢያትሪስ ገለጻ፤ እነዚህ የትብብር መስኮች በቻይና እና አፍሪካ መካከል የሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ትብብር እንዲጠናከር እያደረጉ ነው፡፡ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ አቅም ግንባታ ለአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ክዌንቲን ዎዶን በበኩላቸው፤ በአፍሪካ ያሉ ኢንዱስትሪዎች የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት እጥረት አሁንም ችግር እንደሚያጋጥም ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በአፍሪካ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በሚጠበቀው ደረጃ ስልጠናዎች ማካሄድ ላይ ባለመሰራቱ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ቁጥር ዝቅተኛ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በዚህ ዙሪያ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ወደ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚገቡ ሰልጣኞች ቁጥር እንዲጨምር ማድረግ፣ በመስኩ የማበረታቻ አሰራሮችን በመዘርጋት የዘርፉን እምቅ አቅም በተሻለ መልኩ ለመጠቀም መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞችን አቅም መገንባት፣ ለአሰልጣኞች ሳቢ የሆኑ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባ አመልክተው፤ ዘመኑ የደረሰበትን የስልጠና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። በቻይና ቤጂንግጓ ኖርማል ዩኒቨርስቲ የኤጁኬሸናል ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ዲን ማ ኒንግ (ፕ/ር) በበኩላቸው፤ በቻይና ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) በሰፊው ጥቅም ላይ መዋሉን ገልጸዋል። ይህም የትምህርት ጥራቱ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለጥናት ምርምርና ፈጠራ በግብዓትነት እያገለገለ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም ተጠቃሽ ውጤቶች እየተገኙ ነው ብለዋል፡፡ ቻይና እና አፍሪካ በትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት የበለጠ እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ተኪ ምርቶችና የተለያዩ ዘርፎችን የሚደግፉ ቴክኖሎጂዎች እየተመረቱ ነው
Nov 6, 2025 58
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ተኪ ምርቶችና የተለያዩ ዘርፎችን የሚደግፉ ቴክኖሎጂዎችን እያመረቱ መሆኑ የፈጠራ ባለሙያዎች ገለጹ። "ክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም" በሀገሪቱ ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራን እና የሰው ኃይል ክህሎት ማጎልበትን በተመለከተ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካይነት የሚመራ ሀገራዊ ተነሳሽነት ነው። ይህ ፕሮግራም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን (TVET) ከዘመኑ የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋር በማጣጣም ወጣቶች ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለማስቻል ያለመም ነው። የክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ብሩክ ሰለሞን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር መቀየር የሚችሉበት ምህዳር እየተፈጠረ ነው። በዚህም የግል ዘርፉና የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፎም እየጨመረ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በመስኩ የተሻለ አቅም እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በፕሮግራሙ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ዜጎች በማሰባሰብ የሥልጠና፣ የግብዓት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፋይናንስ ድጋፍ ከማመቻቸት ጨምሮ የገበያ ትስስር የመፍጠር ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል። በመጀመሪያው ዙር ከ400 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነው ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎች መመረታቸውን ተናግረው፤ በፕሮግራሙ ሁለተኛ ዙር በተኪ ምርቶች ላይ 152 ወጣቶች 99 ቴክኖሎጂዎችን እያለሙ ነው ብለዋል። በፕሮግራሙ በተሰጠው ድጋፍ በግብርና፣ ጤና፣ ደህንነት፣ አገልግሎት የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች መሰራታቸውንም ተናግረዋል። ለአብነትም በአፋርና ሶማሌ ክልሎች በሰፋፊ እርሻዎች ላይ የውሃና ማዳበሪያ አጠቃቀምን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መተግበሩን ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያዊያን የተመረቱ ቴክኖሎጂዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሮች ላይም ከፍተኛ ውጤቶች መገኘታቸውንም አንስተዋል። በቴክኖሎጂና በተኪ ምርት ስራ ከተሰማሩት የፈጠራ ባለሙያዎች መካከል ሄዋን አሊ፤ በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ባገኘችው ድጋፍ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመደራጀት ከውጭ የሚገቡ ማሽኖችን እያመረቱ መሆኑን ገልጻለች። የእንስሳት መኖ ማቀነባበር የሚያስችሉ አምስት መሳሪያዎችን ማምረት መቻላቸውንም ተናግራለች። ማቀነባበሪያው የእንስሳት ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ እገዛ እንደሚያደርግ አብራርታለች። በሮቦቲክስና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ የተሰማራው ወጣት ሁነኛው ዘሩ በበኩሉ የግብርናና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በሮቦት በመታገዝ ማከናወን የሚያስችል ቴክኖሎጂ መስራቱን ጠቅሷል። በሮቦቲክስና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የስራ እድሎችን ለመፍጠር ከሌሎች ወጣቶች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል። የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረቻ መሳሪያ እያመረተ የሚገኘው አቤኔዘር ተከስተ፤ ማሽኑ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለቤት ውስጥ መገልገያ የሚውሉ ፕላስቲክ ምርቶች ለማምረት እንደሚያስችል ይናገራል። ይህም የፕላስቲክ ምርቶችን በመልሶ መጠቀም የስራ እድልን ለማስፋት እንደሚረዳም ገልፅዋል፡፡ በጤና ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት ያደረገችው ወጣት ነቢሃ ነስሩ፤ በጤና ተቋማት ተኝቶ ታካሚዎች አስቸኳይ እርዳታ በሚፈልጉበት ወቅት የህክምና ባለሙያዎችን በቀላሉ መጥራት እንዲችሉ እገዛ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሰርታ በጤና ተቋም ጥቅም ላይ እንዲውል እየሰራች መሆኑን ጠቅሳለች። ወጣቶች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወደ እድሎች ለመቀየር መስራት ይኖርብናል ብላለች።
ዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዎችን በማከናወን አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር እያስተዋወቀ ነው
Nov 4, 2025 262
ሮቤ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፡- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በማከናወን አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር እያስተዋወቀ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ተመራማሪዎችን ያሳተፈ የምርምር ማዕከላት የመስክ ምልከታን ዛሬ አካሄዷል። በመስክ ምልከታው ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወንድሙ እንዳሉት ፤ ተቋሙ የአርሶ አደሩን ችግር ማዕከል ያደረጉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ነው። የስንዴ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልና በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በምርምር ለመለየት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በአርሶ አደሩ አቅራቢያ የምርምር ጣቢያዎችን በመክፈት አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 200 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ ማሳ ላይ በኩታ ገጠም አስተራረስ ለተደራጁ አርሶ አደሮች ዝርያን በማላመድ፣ በአረም ቁጥጥርና በሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በተጨማሪም ለአርሶ አደሩ የምርጥ ዘር አቅርቦትና ሌሎች የግብርና ድጋፎችን ከማድረግ በተጓዳኝ በእፅዋት በሽታ ቁጥጥርና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ተግባር ተኮር ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑንም አንስተዋል። አርሶ አደሩንና የዘርፉ ባለሙያዎችን ያገናኘው የመስክ ምልከታ የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል። ከምሥራቅ ባሌ ዞን የመጡት አርሶ አደር ዘውዴ ጉታ፤ በስንዴ ሰብል ልማት የመሳተፍ የረጅም ዓመት ልምድ ቢኖራቸውም በምርጥ ዘር አጠቃቀም ልምድ ማነስ ምክንያት በሄክታር ከ20 ኩንታል ያልበለጠ ስንዴ ሲያመርቱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ። ከሦስት ዓመታት ወዲህ ግን በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ያገኙትን የስንዴ ምርጥ ዘር መጠቀም በመጀመራቸው በአንድ ሄክታር እስከ 70 ኩንታል ስንዴ ማምረት መጀመራቸውን አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው በተወሰነ መሬት ላይ እያከናወነ ከሚገኘው የስንዴ፣ የባቄላ፣ የጤፍና የሌሎች የሰብል ዝርያዎች ብዜት ብዙ ልምድ መቅሰማቸውን የገለጹት ደግሞ ከምዕራብ አርሲ ዞን የመጡት ከማል አልይ ናቸው። የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ አርሶ አደር አሚኖ አማን በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በተለያየ ጊዜ ምርጥ ዘርና ሌሎች ድጋፎችን አድርጎልናል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በሚያደርግልን ድጋፍም ምርትና ምርታማነታችንን እያሻሻልን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል። በመስክ ምልከታው ላይ ከባሌ ዞን፣ ምሥራቅ ባሌና ምዕራብ አርሲ ዞን የተውጣጡ አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ ነው
Nov 4, 2025 194
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ዜጎች የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምኅዳር እየፈጠረ የሚገኝ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ ልማት መርሃ ግብር አካል መሆኑ ይታዎሳል። በ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት የተጀመረው መርሃ ግብርም ዜጎች መሠረታዊ ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት የሚያዳብሩበትን የበይነ-መረብ (ኦንላይን) የስልጠና ምኅዳር ፈጥሯል። በተነሳሽነቱም በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ፣ በአንድሮይድና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልጠና መስኮች ዜጎች ያለምንም ክፍያ ባሉበት ቦታ በበይነ-መረብ የስልጠና እንዲከታተሉ እያደረገ ይገኛል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳው የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነትም ዜጎች በዲጂታል ዓለም ውስጥ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ፤ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች የመንግስትን አገልግሎቶች በማሳለጥ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። የ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳ ቁልፍ የዜጎች ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት ልማት መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ትግበራ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ በመገንባት በቁልፍ መሳሪያነት እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠና ከጀመረበት አንስቶም በፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ፣ ዳታ ሳይንስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊያን ላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ነው ብለዋል። በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ ከሚገኙ ዜጎች ውስጥም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው ሰርትፊኬት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል። የኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብሩም የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መርሃ ግብሩም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል በማፍራት አገልግሎት አሰጣጦችን በማዘመን በር እንደከፈተም ገልጸዋል። በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት መጨረሻም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎችን 4 ሚሊየን ለማድረስ ከክልልና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ኢትዮጵያዊያንም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናን ባሉበት ቦታ በመመዝገብ የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት አቅማቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የዲጂታል መታወቂያ በተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ የሚያስችል የአገልግሎት ማዕከላትን የማስፋት ስራ እየተከናወነ ነው
Nov 2, 2025 342
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ):-የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን በተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ የሚያስችል የአገልግሎት ማዕከላት ማስፋት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ገለጹ፡፡ እስካሁን ከ27 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ለሁሉም ነዋሪዎች ዲጂታል መታወቂያን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። የምዝገባ አገልግሎቱን በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ለማዳረስ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የአገልግሎት ማዕከላት በማስፋት ምዝገባ እያካሄደ ነው። በተጨማሪም አገልግሎቱ ወደ ሩቅ አካባቢዎች እንዲደርስ በተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች (Mobile Registration Units) አማካኝነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከአምስት ሺህ በላይ የመመዝገቢያ ማሽኖች አገልግሎት ላይ ናቸው ያሉት አስተባባሪው፤ ከ27 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል ብለዋል። እስከ በጀት ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የመመዝገቢያ ማሽኖቹን ቁጥር ወደ 10 ሺህ በማሳደግ ተደራሽነትን ለማስፋት መታቀዱን ገልጸዋል። በአጠቃላይ በዓመቱ ውስጥ 60 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመዝገብ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማሳካት ጠንካራ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አስረድተዋል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማሳደግ፣ የገንዘብ ማጭበርበርን በመቀነስ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።
ስፖርት
የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው
Nov 6, 2025 93
ቁሊቶ፤ጥቅምት 27/2018 (ኢዜአ)፡- የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የዞኑ አስተዳደር ገለፀ፡፡ የስታዲየሙን የግንባታ ሂደት በተመለከተ ለኢዜአ ማብራሪያ የሰጡት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ከድር ቆሮቾ እንደገለፁት፤ በማህበረሰብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለው የቁሊቶ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡ ግንባታውን በሶስት ምዕራፎች ለማጠናቀቅ ታስቦ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ጠቁመው የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የእግር ኳስ ሜዳውን ሰው ሰራሽ ሳር የማልበስ፤ ደረጃውን የጠበቀ የመሮጫ መምና የተመልካች መቀመጫ የመግጠም ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የቁሊቶ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተመደበለትም አስረድተዋል፡፡ የስታዲየሙ ግንባታ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ነው ያስረዱት፡፡ የስታዲየሙ የእግር ኳስ ሜዳውና የመሮጫ ትራኩ ግንባታ በፊፋ እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አማካኝነት በተደረገ ምዘና በጥሩ ሂደት ላይ እየተከናወነ እንደሆነ ግብረ መልስ እንደተሰጠም ገልጸዋል፡፡ ከስታዲየሙ ግንባታ ጎን ለጎንም እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችሉ የሆቴሎች ግንባታ ለማከናወን ከባለሀብቶች ጋር መግባባት ላይ መደረሱንም ገልፀዋል፡፡ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ስራው በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።
ማንችስተር ሲቲ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን አሸነፈ
Nov 6, 2025 86
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን 4 ለ 1 አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፊል ፎደን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አርሊንግ ሃላንድ እና ራያን ቼርኪ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ዋልዴማር አንቶን ለዶርትሙንድ ግቧን አስቆጥሯል። ፎደን በጨዋታው ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል። ሃላንድ ዘንድሮ በሁሉም ውድድሮች ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 18 ከፍ አድርጓል። ድሉን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ10 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሰባት ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። በሌሎች ጨዋታዎች ባርሴሎና ከክለብ ብሩዥ ጋር ሶስት አቻ ተለያይቷል። ጃኮብ ፎርብስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኒኮሎ ትሬሶልዲ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ፌራን ቶሬስ፣ ላሚን ያማል እና የክለብ ብሩዡ ክሪስቶስ ዞሊስ በራሱ ላይ ግቦቹን ለባርሴሎና ግቦቹን አስቆጥረዋል። ኒውካስትል ዩናይትድ በዳን በርን እና ጆኢሊንተን ግቦች አትሌቲኮ ቢልባኦን 2 ለ 0 አሸንፏል። በሳንሲሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢንተር ሚላን ካይራት አልማቲን 2 ለ 1 አሸንፏል። ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ካርሎስ አጉስቶ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ኦፍሪ አራድ ለካይራት ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ጋላታሳራይ አያክስን 3 ለ 0፣ ባየር ሌቨርኩሰን ቤኔፊካን እና አትላንታ ማርሴይን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ካራባግ እና ቼልሲ አቻ ተለያዩ
Nov 5, 2025 125
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ካራባግ እና ቼልሲ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በቶፊክ ባህራሞቭ አዲና ሬስሪፐብሊክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊያንድሮ አንድራዴ በጨዋታ እና ማርኮ ያንኮቪች በፍጹም ቅጣት ምት ለካራባግ ግቦቹን አስቆጥረዋል። እስቴቫኦ እና አሌሃንድሮ ጋርናቾ ለቼልሲ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ እና ካራባግ በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 10ኛ እና 12ኛ ደረጃን ይዘዋል። በሌላኛው ጨዋታ ፓፎስ ቪያሪያልን 1 ለ 0 አሸንፏል። ዴሪክ ላካሰን የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች በህዳር ወር መጀመሪያ ይካሄዳሉ
Nov 5, 2025 118
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ደልድል ዛሬ ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ፣ መቀሌ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ፣ ምድረገነት ሽሬ ከመቻል፣ ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ መድን፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከነጌሌ አርሲ፣ ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ እና አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ። ሀላባ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ፣ ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከደሴ ከተማ፣ ሐረር ከተማ ከአቃቂ ክፍለ ከተማ፣ ንብ ከየካ ክፍለ ከተማ እና ቤንችማጂ ቡና ከጋሞ ጨንቻ ሌሎች የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ከህዳር 2 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ጨዋታዎቹ አዲስ አበባ ስታዲየም፣ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ እና ጅማ ስታዲየም ይደረጋሉ። በመጀመሪያው ዙር ውድድር የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ብቻ የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊ ቡድኖች በሁለተኛው ዙር ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ጋር በመቀላቀል ይጫወታሉ። ወላይታ ድቻ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ነው። የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚያሸንፍ ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
አካባቢ ጥበቃ
የባሌ ህዝብ ከገዳ ሥርዓት በወረሰው አስተምህሮ እና ዕሴት የተፈጥሮ ሃብቶችን በመጠበቅ አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገ ህዝብ ነው
Nov 5, 2025 153
ሮቤ ፤ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ የባሌ ህዝብ ከገዳ ሥርዓት በወረሰው አስተምህሮ እና ዕሴት የተፈጥሮ ኃብቶችን በመጠበቅ አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገ ህዝብ ነው ሲሉ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ካነሱዋቸው ሀሳቦች መካከል የባሌ ህዝብ ከተፈጥሮ ሀብት ጋር ያለው መስተጋብር አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ “የባሌ ሕዝብ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የጋራ የተፈጥሮ ሀብቶችን ጠብቆ በማቆየቱ ሊመሰገን ይገባል” ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዞኑ ህዝብ ያቀረቡት ምስጋናና አክብሮት የተፈጥሮ ጸጋዎችን በመንከባከብ ይበልጥ አልምቶ ለመጠቀም የሚያነሳሳ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የሃገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ገልጸዋል፡፡ ከሮቤ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች መካከል አቶ ተማም ጀማል፣ በተፈጥሮ ጸጋዎች የታደለው የባሌ ዞን የበርካታ ብዝሀ ህይወት ባለቤት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የቱሪዝም መዳረሻ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሐረና ጥብቅ ደንና ሌሎች ውብና ማራኪ መልካም ገጽታን የተላበሰ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እንዳለው ጠቅሰው ፓርኩ የተለያዩ ብርቅዬ የዱር እንስሳትና አዕዋፋት መገኛ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርኩ ልማትና ብዝሀ ህይወት ጥበቃ የሰጡት ትኩረት ብሎም ለዞኑ ህዝብ ያቀረቡት ክብርና ምስጋና በታሪክ የሚታወስና ለዘላቂ ጥበቃ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡ በተለይ ለዘመናት ሳይለማ የተረሳው የሶፍ ኡመር ዋሻ የኢትዮጵያን ታላቅነትና መልካም ገጽታ ለአለም ህዝብ ጭምር የሚያስተዋውቅ ሌላ ቅርስ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ አማን ሐጂ አብዶ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለዞኑ ህዝብ ያቀረቡት ምስጋናና አክብሮት የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የደን ቅሪቶችን ይበልጥ በመንከባከብ አልምቶ ለመጠቀም የሚያነሳሳ እንደሆነም አመልክተዋል። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ መምህራንም የአገር ሽማግሌዎችን ሀሳብ በመጋራት የጋራ የተፈጥሮ ሀብቶችን በመንከባከብ ለዛሬ ላቆየው የባሌ ህዝብ በመንግስት የቀረበው እውቅናና ክብር ለዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አዎንታዊ አንድምታ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በተለይም በጥብቅ ደኖች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር በመደራጀት ደኑን በመጠበቅ ከስነ-ምህዳሩ ከሚያገኙት ጥቅም በተጓዳኝ ከካርቦን ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መምጣታቸው የጥበቃውን ተግባር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ መምህርና ተመራማሪ ኡመር አብደላ፣ የባሌ ህዝብ ከገዳ ሥርዓት በወረሰው አስተምህሮትና ዕሴት የተፈጥሮ ኃብቶችን በመጠበቅ አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገ ህዝብ መሆኑን ተናግረዋል ። በተለይ የአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በቋሚ ቅርስነት መመዝገቡን ገልፀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክና በውስጡ የሚገኙ የብዝሀ ህይወት ስብጥሮች ማህበረሰቡ ጠብቆ ያቆየው ሃብት መሆኑን አመልክተዋል። የባሌ ህዝብ የተፈጥሮ ኃብቱን በመንከባከብ ለትውልድ በማቆየቱ ከመንግሥት የተሰጠው እውቅና የጥበቃውን ሥራ ይበልጥ ውጤታማና ዘላቂ የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላው የዘርፉ መምህርና ተመራማሪ አብዱልፈታህ አብዱ ናቸው። የተሰጠው እውቅናም የህዝቡ ብቻ ሳይሆን በዘርፉ ይስተዋሉ በነበሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ ሲለግሱ ለቆዩት የዘርፉ ምሁራንን ጭምር የሚያነሳሳ መሆኑን አስታውሰዋል።
የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃን የልማት አጀንዳቸው የትኩረት ማዕከል ሊያደርጉ ይገባል- ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ
Nov 4, 2025 216
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃና እንክብካቤን እንደ ልማት አጀንዳ በመያዝ መስራት እንደሚገባቸው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው ላለፉት ሁለት ቀናት በባለሙያዎች ደረጃ ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል። “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” በመሪ መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎችና ቀጣይ እርምጃዎች የሚመክር ነው። የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ከጸጋ ባሻገር የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፣ የምግብ ዋስትና እና የባህል ማንነት መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። ብዝሃ ህይወት እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች የዓለም ተፈጥሮ ሀብት ዘቦች ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል። ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የእንስሳትና እጽዋት መኖሪያ ቦታ መውደም እና የተለያዩ ዝርያዎች መጥፋት የብዝሃ ህይወት ሀብቶች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አፍሪካውያን ብዝሃ ህይወትን የአህጉሪቱ የልማት አጀንዳ ምሰሶ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ነው ያሉት። በአጀንዳ 2063 የበለጸገች እና ሰላማዊ አፍሪካን የመፍጠር ህልም ሊሳካ የሚችለው በዜጎች ትጋትና በዘላቂ አካባቢ ጥበቃና አስተዳደር መሆኑንም አመልክተዋል። አህጉራዊ አጀንዳዎችን ለማሳካት የፖሊሲ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ እንዲሁም ወጣቶችና ሀገር በቀል ማህበረሰቦችን በብዝሃ ህይወት ጥበቃ የመሪነት ሚና እንዲወጡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት ንግግራቸውን ወደ ተጨባጭ ስራ እና ወደሚለካ ውጤት በመቀየርና የአካባቢ ስነ ምህዳርን በመጠበቅ መጻኢውን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ እንዲሰሩ አስገንዝበዋል። አፍሪካን በዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ እና ዘላቂ አጠቃቀም መሪ እናድርጋት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ነገር እናስረክብ ሲሉም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል። በጉባኤው ላይ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ ነገ በመሪዎች ደረጃ በሚደረግ ስብሰባ ይጠናቀቃል። ጉባኤው ለአፍሪካ ብዝሃ ህይወት መመናመን፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ብክለት የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው
Nov 4, 2025 198
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ የምታከናውናቸው ተግባራት ከቀጣናው ባሻገር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምሳሌ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የስነ-ምህዳርና ባዮ-ዳይቨርሲቲ ዋና የቴክኒክ አማካሪ ዶለይ ጸሪንግ ገለጹ፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የስነ-ምህዳርና ባዮ-ዳይቨርሲቲ ዋና የቴክኒክ አማካሪ ዶለይ ጸሪንግ ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ስነ-ምህዳርና ብዝሃ ህይወት የታደለች ሀገር ናት ብለዋል፡፡ የብዝሃ ህይወት እና ስነ-ምህዳር ጥበቃ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ወሳኝ ሚና እንደሚያበረክት ጠቁመው፤ ተቋማቸው በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ የዓለም ሀገራት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በብሔራዊ ፓርኮች ጥበቃን በማጠናከር እና አዳዲስ ስፍራዎችን በማልማት ለብዙ አይነት የዱር እንስሳትና ዕፅዋት ወሳኝ መኖሪያ እያለማች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በትላልቅ የደን ልማት እያከናወነች ያለው ተግባር ከአፍሪካ ቀንድ አልፎ በዓለም አቀፉ ደረጃ ግንባር ቀደም እንደሚያደርጋት ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራዎች ቀጣዩን ትውልድ ጭምር ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና ከብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ጋር ለማስተሳሰር እየወሰደቻቸው ያሉ እርምጃዎች የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ረገድ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ከቀጣናው ባሻገር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያ የምታከናውነውን የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን እንደሚያግዝም አረጋግጠዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በቀጣናው የሚገኙትን ሥነ-ምህዳሮችና የብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ ከመንግሥት፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ተመራማሪ (ዶ/ር) ፋኑዔል ከበደ በበኩላቸው፤ የዱር እንስሳት ለቱሪዝም መስህብነትና ለሌሎችም ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የእነዚህን እንስሳት መኖሪያ የመጠበቅ ስራን በትኩረት እየሰራች መሆኑን ጠቁመው በዚህም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ በዚህም በርካታ የዱር እንስሳት አሁን ላይ ወደ ነባር ቀዬያቸው እየተመለሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እየጨመረ ይሄዳል
Nov 3, 2025 245
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአየሩ ሁኔታ እንደሚቀያየር አስታውቋል። በደብረ ብርሃን፣አርሲ ሮቤ፣አዳባ፣ደሴ፣ባሌ ሮቤ፣አዲስ አበባ፣አደሌ፣አምባ ማሪያም፣ ኮምቦልቻ፣ አንኮበር በአብዛኛው ቀናቶች ላይ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል። የበጋ ወቅት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑት የደቡብ፣ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል። በሌላ በኩል አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በመካከለኛው፣የምስራቅ እና ደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚሄድ የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። የመኽር ሰብል አብቃይ በሆኑት የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በወሩ ያለው እርጥበት ዘግይተው ለተዘሩት፣ የእድገት ጊዜያቸውን ላልጨረሱ ሰብሎች፣ለቋሚ ተክሎችና ፍራፍሬዎች የውሃ ፍላጎት ለማሟላት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጿል። ያለው እርጥበት ለእንስሳት መኖም አዎንታዊ አበርክቶ እንዳለው ጠቁሟል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበጋ እርጥበት ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው የሚጠበቅ ሲሆን የተቀሩት ተፋሰሶች ዝቅተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል ብሏል። አብዛኛው የባሮ አኮቦ፣ኦሞ ጊቤ፣ገናሌ ዳዋ፣ኦጋዴን፣ በመካከለኛው እና በታችኛው ስምጥ ሸለቆ፣ዋቤ ሸበሌ የተሻለ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። አብዛኛው አፋር ደናክል፣አዋሽ፣ተከዜ፣መረብ ጋሽ እንዲሁም አይሻ ተፋሰሶች ላይ ደረቅ የአየር ሁኔታ ጠባይ ተጽዕኖ ስር እንደሚወድቁ የአየር ትንበያ ያሳያል ብሏል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ መሪዎች ብዝሃ ህይወትን ከብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸው ጋር ማስተሳሰር ይገባቸዋል -አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ
Nov 6, 2025 92
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ መሪዎች የብዝሃ ህይወት አጀንዳን ከብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸው ጋር በማቆራኘት ሊተገብሩ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ገለጹ። ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ በመሪዎች ደረጃ በተደረገ ስብስባ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ የሀገራት መሪዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ጉባኤው አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠበቅ በጀመረችው ጉዞ ውስጥ ታሪካዊ ሁነት መሆኑን ገልጸዋል። ከኮንጎ ጥብቅ ደን እስከ ደቡብ አፍሪካው የኬፕ የአበባ ሀብት ቀጣና በአህጉሪቷ የሚገኙ ተፈጥሯዊ ምህዳሮች የህይወት፣ ባህል እና የኢኮኖሚ እድገት ምንጮች መሆናቸውን አመልክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብክለት እና ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም በአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ላይ ስጋቶችን እንደደቀኑ ተናግረዋል። የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ያስፈልጋል ያሉት አምባሳደሯ ለዘርፉ የሚያስፈልገውን መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከአባል ሀገራት፣ ከቀጣናዊ ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን የአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ስትራቴጂ ከአጀንዳ 2063 እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በተጣጠመ መልኩ እንዲተገበር በትብብር እንደሚሰራ ነው የገለጹት። ብዝሃ ህይወት እንደ ተጓዳኝ ጉዳይ ሳይሆን ለአፍሪካ ሰላም፣ አይበገሬነት እና ዘላቂ ልማት ባለው ቁልፍ ድርሻ ሊታይ እንደሚገባ ጠቅሰው በዚህ ረገድም የአፍሪካ መሪዎች ብዝሃ ህይወት ከብሄራዊ ፖሊሲዎች ጋር ማስተሳሰር እንዳለባቸው አሳስበዋል። ወጣቶች እና ሀገር በቀል ማህበረሰቦችን ማብቃት እንዲሁ በፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዓለም አቀፍ እኩልነት ለማስፈን መትጋት ትኩረት እንደሚያሻቸው ነው ያነሱት። የአፍሪካ ብልፅግና አረንጓዴ፣ ሁሉን አቀፍ እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። የጋቦሮኒው ጉባኤ የአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ድንጋጌ ቀጣይ ለሚመጡ ትውልዶች መሰረት የሚጥል እንደሚሆንም ገልጸዋል። ጉባኤው በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎችና ቀጣይ እርምጃዎች በዋናነት መምከሩን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሄይቲ እና ጃማይካ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ የበርካቶች ሕይዎት አለፈ
Oct 31, 2025 358
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡-በሄይቲ እና ጃማይካ የተከሰተው ‘ሃሪኬን ሜሊሳ’ የተሰኘው ወጀብና ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ እስካሁን የ49 ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል። በሄይቲ የ30 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን እና ከ20 በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። እስካሁን ያሉበት ሁኔታ ያልታወቁ ሰዎችን የመፈለጉ ሥራም መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ ለአልጄዚራ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመላክተዋል። እንዲሁም የአውሎ ነፋሱ ሰለባ በሆነችው ሌላኛው ሀገር ጃማይካ የ19 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል። እስካሁን ከተመዘገቡት በጣም ኃይለኛ የአትላንቲክ አውሎ ነፋሶች አንዱ እንደሆነ የተነገረለት ሃሪኬን ሜሊሳ በሠዓት 295 ኪሎ ሜትር እንደሚከንፍ ተገልጿል። አውሎ ነፋሱ የጃማይካን ምዕራባዊ ክልል በመምታት አስከፊ ጉዳት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሃሪኬን ሜሊሳ በካሪቢያን ቀጣና ኩባ፣ሄይቲ እና ጃማይካ በሰው ሕይወት እንዲሁም በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። ይህን ተከትሎም በካሪቢያን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ውጭ መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል። የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን ለመመለስና አካባቢዎቹንም የማጽዳት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
የአፍሪካ ህብረት የ30 ቢሊዮን ዶላር የአቪዬሽን መሰረተ ልማት የኢንቨስትመንት እቅድ ይፋ አደረገ
Oct 31, 2025 280
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ማዘመንን አላማ ያደረገ የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርጓል። ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ የነበረው ሶስተኛው የአፍሪካ መሰረተ ልማት ፋይናንስ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአንጎላ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ጆአኦ ሎሬንቾ፣ የህብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የአየር መንገዶች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ከጉባኤው ጎን ለጎን በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ አማካኝነት የአህጉሪቷን አቪዬሽን መሰረተ ልማት በፋይናንስ በመደገፍ እና በማዘመን የተቀናጀ የአየር አገልግሎት እና ነጻ እንቅስቃሴን መፍጠር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተከናውኗል። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ በመድረኩ ላይ በአየር ትራንስፖርት ገበያው አማካኝነት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ለማዘመን የሚውል የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። እቅዱ አፍሪካ በቀጣይ 10 ዓመት የአቪዬሽን ዘርፉን ለማሻሻል የሚያስፈልጋትን ከ25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በአፍሪካ እ.አ.አ በ2024 160 ሚሊዮን የነበረው የመንገደኞች መጠን እ.አ.አ በ2050 ወደ 500 ሚሊዮን ገደማ እንደሚደርስ የገለጸው ህብረቱ ኢንቨስትመንቱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና አቅምን ለማጎልበት እንደሚያስችል አመልክቷል። በኢንቨስትመንት እቅዱ አማካኝነት ገንዘቡ ለአውሮፕላን ማረፊያ፣ አውሮፕላን ጣቢያ እና ጥገና ማዕከላት መሰረተ ልማት፣ የአቪዬሽን ስርዓቶች ማዘመን፣ ለሰው ኃይል ልማት፣ ለቁጥጥር ስራ፣ ለቴክኖሎጂ እና ተጓዳኝ ስራዎች እንደሚውል ተገልጿል። የአፍሪካ ህብረት 10 ቢሊዮን ዶላሩን ከአፍሪካ መንግስታት፣ ከቀጣናዊ የልማት ባንኮች እና ከባለቡዙ ወገን አጋሮች ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቋል። ቀሪው 20 ቢሊዮን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አጋሮች፣ የሉዓላዊ ሀብት ፈንዶች (sovereign wealth funds) እና የጡረታ ፈንዶችን ጨምሮ ከግል እና የተቋማት ኢንቨስተሮች ለማግኘት መታሰቡን ነው ያመለከተው። የሀብት ማሰባሰቡ የሚከናወነው በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ማዕቀፍ ሲሆን የ30 ቢሊዮን ዶላሩ ከእ.አ.አ 2025 እስከ 2035 ለሚተገበሩ ስራዎች የሚውል ነው። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ አቪዬሽን የትራንስፖርት አማራጭ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ትስስር ስትራቴጂካዊ ሞተር እንዲሁም የአጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ቁልፍ አቅም ነው ብለዋል። በኢንቨስትመንት እቅዱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት መመዘኛዎችን ባሟላ እና ከካርቦን ልህቀት ነጻ በሆነ መልኩ እንደሚገነቡ አመልክተዋል። ህብረቱ ዘመናዊ፣ ውጤታማ እና ዘላቂ የአቪዬሽን ኔትወርክ በመፍጠር ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር፣ የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት ስር እንዲሰድ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲያድግ በቁርጠኝነት ይሰራል ነው ያሉት።
ለአህጉሪቷ ለዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው
Oct 24, 2025 553
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-ለአህጉሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ የአባል አገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በዓሳ ሀብት፣ በገጠር ልማት፣ በውሃ፣ በአካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው የሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም የማላቦ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2014 እስከ 2025) መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው የካምፓላ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2035) ጸድቋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አባል ሀገራት የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም የግብርና ግብዓቶችንና ምርጥ ዘርን መጠበቀ እንዲሁም ብዝሃ ህይወትን ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውሃ ኃብትን ከማሳደግ አኳያም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ - ኒፓድ የግብርና፣ የምግብ ዋስትና እና የአካባቢ ዘላቂነት ዳይሬክተር ኤስቴሪን ፎታቦንግ የካምፓላ አጀንዳ (2026–2035) በአፍሪካ የግብርና-ምግብ ሥርዓቶች ላይ የለውጥ ምዕራፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ ከአጀንዳው ግቦች መካከልም ዘላቂ የምግብ ምርትን፣ አግሮ-ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እና ንግድን ማጠናከር፣ ለግብርና-ምግብ ሥርዓት ለውጥ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስን ማሳደግ ብሎም የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ የካምፓላ አጀንዳ ስትራቴጂ እንዲሳከ ምቹ ሁኔታዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡ የዩጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የአምስተኛው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ ፍሬድ ብዊኖ ክያኩላጋ የካምፓላ አጀንዳ የእንስሳት ሃብትን ማሳደግ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡ በዚህም ለእንስሳትና ለዓሳ እርባታ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የእንስሳት መኖ ማሳደግ፣ ለእንስሳት ጤና እንዲሁም የዘረመል መሻሻልም ከትኩረት መስኮች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ የካምፓላ አጀንዳ የአፍሪካ ግብርና ልማት መርሃ ግብር ታላላቅ ግቦች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ሐተታዎች
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት
Nov 3, 2025 317
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ያላቸው ታሪካዊ ወዳጅነት በርካታ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት በአራተኛው ክፍለ ዘመን እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአክሱም ንጉስ ኢዛና ወቅት ኢትዮጵያ ከምስራቅ ሮም መንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ እና ሃይማኖታዊ ግንኙነት እንደነበራት ይነገራል። 15ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው በሰነድ የተደገፈ የኢትዮጵያ እና አውሮፓ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ግንኙነቶች የተደረጉበት ወቅት ነው። እ.አ.አ በ1441 የኢትዮጵያ ልዑክ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤት (The Council of Florence) ስብስባ ላይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት እና አውሮፓ መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ግንኙነት እንደሆነ ታሪክ ያወሳል። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑካን ወደ ሮም፣ ቬኒስ እና ሊዝበን ጉብኝቶችን አድርገዋል። ከዛ በኋላ ባሉ ክፍለ ዘመናት በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ሀገራት መካከል በርካታ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ እንቅስቃሴዎች እና የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። እ.አ.አ 1975 ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ማህበረሰብ ጋር ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመረችበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት (በቀድሞ አጠራሩ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ) እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 28 1975 በቶጎ ሎሜ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ የሎሜ ድንጋጌ እየተባለ ይጠራል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያ እና ለአውሮፓ ህብረት ትብብር መሰረት የጣለ ታሪካዊ ሁነት ነው። የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ ትብብር፣ የልማት ድጋፍ እና የወጪ ንግድ የስምምነቱ አበይት ማዕቀፎች ናቸው። የሎሜ ስምምነት አራት ጊዜ ማሻሻያ ተደርጎበታል። ማሻሻያዎቹ ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በፖለቲካ፣ ዴሞክራሲ፣ ኢንዱስትሪ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ቀጣናዊ ትስስርን ጨምሮ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ ማስፋትን ያለሙ ናቸው። እ.አ.አ በ2000 የሎሜ ስምምነት ወደ ኮቶኑ ስምምነት ተሸጋገረ። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በቤኒን ኮቶኑ አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ተፈራረሙ። የኮቶኑ ስምምነት የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ያስቀጠለ ነው። የፖለቲካ ምክክሮች፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶች አካቷል። ስምምነቱ ሁለት ጊዜ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ሲሆን እ.አ.አ በ2020 ማዕቀፉ እስከ እ.አ.አ 2024 እንዲቀጥል ተወስኗል። እ.አ.አ በ2023 በሶሞአ በተደረገ ውይይት የድህረ ኮቱኑ ስምምነት የተባለለት ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት እና አውሮፓ ህብረት መካከል ተፈርሟል።ኢትዮጵያ የዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ናት። እ.አ.አ በ2016 የተፈረመው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ስትራቴጂካ ትስስር ማዕቀፍ ስምምነት የበለጠ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ያጸና ነው። የአውሮፓ ህብረት ያቋቋመው የአውሮፓ ቡድን በኢትዮጵያ (Team Europe in Ethiopia) ህብረቱን፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና 21 የህብረቱ አባል ሀገራትን አቅፎ የያዘ ነው። ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት መካከል 21ዱ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ውክልና አላቸው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ሰላም እና ፀጥታ፣ የምግብ ስርዓት፣ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የግሉ ዘርፍ ልማት እና ትራንስፖርት ጨምሮ በሌሎች መስኮች ትብብር አላቸው። የአውሮፓ ህብረት በኮቶኑ ስምምነት የነበረውን የአውሮፓ የልማት ፈንድ ድጋፍ በመተካት ከእ.አ.አ 2021 እስከ 2027 የሚቆይ የፋይናንስ ማዕቀፍ እየተገበረ ይገኛል። 629 ሚሊዮን ዩሮ ፈሰስ የሚደረግበት ይህ ማዕቀፍ ከአውሮፓ ህብረት ተቋማት እና አባል ሀገራት አስተዋጽኦ የሚገኝ ሲሆን በየዓመቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለሚከናወኑ ስራዎች የሚውል ነው። ታዳሽ ኢነርጂ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ዘላቂ የስርዓተ ምግብ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ የሰው ሀብት ልማት፣ የፍልሰት አስተዳደር እና ሰላም ግንባታ ድጋፍ የሚደረግባቸአው መስኮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ትብብር ውስጥ የሚጠቀሱ አንኳር ጉዳዮች አሉ። ከቅርቡ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ወደ ቤልጂየም ብራሰልስ በማምራት ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከርና ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ከውይይቱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። "ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" በአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን የሚመራ የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ ኢኒሼቲቭ ሲሆን ህብረቱ ከተለያዩ ሀገራት በዲጂታላይዜሽን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በስርዓተ ምግብ፣ በጤና፣ በዘላቂ ግብርና፣ በሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በቁልፍ ዘርፎች ያለውን ትብብር እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው። ስምምነቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ ገልጸዋል። በተጨማሪም ስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች እ.አ.አ በ2016 ለተፈራረሙት የስትራቴጂክ ትስስር የጋራ ድንጋጌ አዲስ አቅም እንደሚፈጥርም ተመላክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሳምንት ለ2025 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ ግብር የ90 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት በአዲስ አበባ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው። በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብስባ ላይ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከስበሰባው ጎን ለጎን ከአውሮፓ የኢንቨስትመንት ባንክ ከዓለም አቀፍ አጋርነት ዳይሬክተር ቱራያ ትሪኪ ጋር መክረው ነበር። በወቅቱ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP III) ሶስተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ የሚውል የ110 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር ተፈራርመውታል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የ240 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል። ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን ልማት በተለያዩ ወሳኝ ዘርፎች ለማጠናከር የሚውል ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም የጋራ ምክክር በአዲስ አበባ ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ የጋራ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሁለቱ ወገኖች በህዳር ወር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተመሳሳይ የጋራ የምክክር መድረክ ማድረጋቸው አይዘነጋም። በ2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት በጤና ዘርፍ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ ያተኮረ የ20 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ዲፕሎማሲያዊ ትስስሩ ሁለቱ ወገኖች በሰኔ ወር 2008 ዓ.ም ከተፈራረሙት የስትራቴጂክ የጋራ ድንጋጌ በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረሙ የሁለቱን አካላት ግንኙነት ለማጠናከር እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጌዛ ስትራመር፣ የፈረንሳይ የወጪ ንግድ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር መልዕክተኛ ኒኮላስ ፎርሲየር፣ የሜዴፍ ኢንተርናሽናል ምክትል ፕሬዝዳንት ፋብሪስ ላሳች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች እና የንግድ መሪዎች ተገኝተዋል። ፎረሙ በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከርና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በዝርዝር አስረድተዋል። ሪፎርሙ የግል ኢንቨስመንት መሳብ እና ኢትዮጵያ ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ያላትን ትስስር የበለጠ ማጠናከርን ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ትብብር እያደገ መምጣቱን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረም በኢትዮጵያ ተቋማትና በአውሮፓ ኩባንያዎች መካከል በኢኖቬሽን፣ በእሴት መጨመርና የጋራ ብልጽግናን መደገፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጎልበት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ገልጿል። ፎረሙ የፈረንሳይ ድርጅቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚሰራ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በሚደግፈው ሜዴፍ ኢንተርናሽናል እና በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በአራት የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በአቪዬሽን፤ በታዳሽ ኃይል፤ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት እና በዲጂታል ቴሌኮሙኒኬሽን ላይ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረምም ይህንን እያደገ ያለ ትብብር ያሳያልም ተብሏል። የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት ከግማሽ ክፍለ ዘመናት በላይ ጸንቶ የቆየ ወዳጅነት ነው። የሁለቱ ወገኖች ትብብር በአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት ላለው ግንኙነት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
የብዙዎች ቤት…
Oct 27, 2025 476
እስካሁን በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት ከ81 በላይ የአጥቢ እንስሣት፣ ከ450 በላይ የአዕዋፍ እና ከ400 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች መኖሪያ ነው። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የአዕዋፍ ዝርያዎች በዚህ ሥፍራ ብቻ ይገኛሉ፤ ከአምስቱ መካከል በተለይም የአንዷ ዝርያ ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተመራማሪዎችንና ጎብኚዎች ቀልብ መሳቡ ይጠቀሳል። ከአካባቢው ተፈጥሯዊ አቀማመጥና የአየር ሁኔታ ጋር መጣጣም የቻሉ የቆላ እፅዋት (ዛፎች) በምቾት በስፋት እንደሚገኙበትም ይገለጻል። የተመሠረተው በ1958 ዓ.ም ሲሆን፤ ስፉቱም 591 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፤ በቁጥርም ሆነ በሥብጥር የብዙዎች መኖሪያ የሆነው ይህ ሥፍራ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ይሰኛል። መንግሥት በሰጠው ትኩረት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ እንስሣቱም ሆኑ እፅዋቱ እየኖሩ ነው፤ ከሕገ ወጥ ድርጊትም እንዲጠበቁ ማድረግ መቻሉን የፓርኩ ኃላፊ አደም መሐመድ ለኢዜአ አረጋግጠዋል። በፓርኩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም ለ247 ወገኖች ቋሚ እና ለ2 ሺህ 535 ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ዓመትም በ1 ሺህ 751 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች እንደተጎበኘ ኃላፊው ገልጸዋል።
የክህሎቶች ልማት፤ የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
Oct 15, 2025 857
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ። ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል። ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው። የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። አህጉራዊ የንግድ ማዕቀፉ በሙሉ አቅሙ ሲተገበር የአፍሪካ ሀገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ መጠን 50 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያፋጥንና አህጉሪቷ ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ ልካ መልሳ ያለቀላቸውን ምርቶች በከፍተኛ ወጪ ከመግዛት ተላቃ ጥሬ ምርቶቿን በከፍተኛ ጥራት ወደ ማምረት ያሸጋግራታል። ይህ ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር እድል አፍሪካውያን በጋራ እንዲለሙ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያሳድጉ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ እና የማይበገር ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እነዚህ ሁላ ተስፋ ሰጪ አቅሞች የሚቃረን አንድ የማይካድ ሐቅ አፍሪካ ውስጥ አለ ይህ እውነት የአፍሪካን የእድገት አቅም በሚፈለገው መልኩ የሚመግብ የክህሎቶች እና የስራ ክፍተት ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ከ10 እስከ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ። ይሁንና በአህጉሪቷ በዓመቱ የሚፈጠረው መደበኛ ስራ 3 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ ከአፍሪካ ወጣቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ገደማው ስራ አጥ (Unemployment) ወይም ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) ውስጥ ነው። ይህ ስራ አለማግኘት ያለው በአፍሪካ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ክህሎት ያለው ሰው አጠረን እያሉበት ባሉበት ወቅት መሆኑ ትልቅ ጥያቄን ያስነሳል። በትምህርት ስርዓቱ እና በገበያው ፍላጎት መካከል እንዴት እንደዚህ አይነት አለመጣጣም ሊመጣ ቻለ? የሚል። በትምህርት እና በኢንዱስትሪው መካከል ባለው ያለመተሳሰር ችግር ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምርታማነት (productivity) ታጣላች። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ፈተናው የአቅም ሳይሆን ትምህርት እና ስራን፣ ፖሊሲ እና ተግባርን እና ስልጠናን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተሳሰር መስመር አለመዘርጋቱ ነው። በአፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት እየሰሩ ያሉት ከኢንዱስትሪው ርቀው ነው ማለት ይቻላል ይህም ተመራቂዎች የስራ ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት እና አቅም እንዳይታጠቁ አድርጓል። ሌላኛው ፈተና በአፍሪካ የተንሰራፋው ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ነው። አንዳንድ ጥናቶች የአፍሪካን ኢ-መደበኛ የኢኮኖሚ ድርሻ እስከ 85 በመቶ ያደርሱታል። ይህም ዜጎች ክህሎታቸውን እንዳያሳድጉ እና የብቃት ማረጋገጫን እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል። የአፍሪካን ክህሎት ምህዳር በመቀየር የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር አበይት ትኩረቱ ያደረገ ሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። “አፍሪካውያንን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያፋጥኑበትን ክህሎቶች ማስታጠቅ” የሳምንቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሁነቱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው። በሁነቱ መክፈቻ ላይ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የልማት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራን፣ ኢኖቬተሮች፣ የወጣት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ተሳትፈውበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክህሎቶች ለሀገራዊ ግቦችና ለአህጉራዊ የ2063 የልማት አጀንዳዎች መሳካት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ናቸው። ኢትዮጵያ ለክህሎት ልማት በሰጠችው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው ብለዋል። ክህሎት መር የፖሊሲ እርምጃችን ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የስራ ፈጣሪነት ባህልን በንቃት እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እና እድገት እንዲያመጡ የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እያመቻቸ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው የህዝባችንን አቅም ወደ ውጤታማ፣ አሳታፊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ የሥራ ኃይል መለወጥ አለብን ብለዋል። ክህሎት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የክህሎት ልማት ለአሳታፊ ዕድገትና ለተገቢ የሥራ ዕድሎች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። አባል ሀገራት ሀገራዊ ለውጦችን ከአህጉራዊ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተሻለ፣ ፈጣን እና ይበልጥ አሳታፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የለውጥ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። የፖሊሲ ወጥነትን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ክህሎት ክፍተትን መሙላት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለክህሎት ልማት መጠቀም እና በአጀንዳ 2063 አማካኝነት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ላይ ውይይት ይደረጋል። በሳምንቱ የሚኒስትሮች እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች፣ የክህሎት አውደ ርዕዮች እና የገበያ ትስስር ሁነቶች እንዲሁም የወጣቶች እና የስራ ፈጣሪዎች ፎረም እንደሚካሄድ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፎረሙ የአፍሪካ ኢኖቬተሮች የስራ ውጤቶች ይቀርቡበታል። የክህሎቶች ሳምንት ተሳታፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና በኢኖሼሽን ማዕከላት ውስጥ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ይጎበኛሉ። ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ ክህሎት ልማት አስመልክቶ የጋራ አቋም መገለጫ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ለአህጉሪቷ የኢንዱስትሪ እና ክህሎት አጀንዳ ተጨባጭ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል። የመጀመሪያው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት እ.አ.አ ኦክቶበር 2024 በጋና አክራ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ክህሎቶች ፈተናዎች ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ምህዳሩን ለመቀየር አህጉሪቷ በዘርፉ አብዮት ያስፈልጋታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን የስነ ህዝብ ትሩፋት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ክህሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል መቀየር ይገባል። ይህን ለማድረግ የተቀናጀ እና አህጉር አቀፍ ጥረት ያስፈልጋል። የሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ስኬት የሚለካው በንግግሮች እና በጋራ መግለጫዎች ሳይሆን ራዕዮቹን በአፍሪካ ትምህርት ተቋማት፣ ስልጠና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች በተጨባጭ በመቀየር እና ውጤት በማምጣት ነው። በዚህ ረገድም መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአፍሪካን የክህሎት ልማት መጻኢ ጊዜ በውድድር፣ በፈጠራ እና አሳታፊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊገነቡ ይገባል። አፍሪካ ወጣቶቿ በክህሎት እና በእውቀት ከታጠቁ አፍሪካ የተለመቻቸውን ግዙፍ እቅዶች እና ትላልቅ ውጥኖች ባጠረ ጊዜ እንዲሳኩ ያስችላል።
ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ በሀገሩ ህልሙን እውን ያደረገው ወጣት...
Oct 9, 2025 825
ሐረር ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ተወልዶ ያደገው ነስረዲን አህመድ፤ በውጭ ሀገር ሰርቶ መለወጥን በማሰብ ከአመታት በፊት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ እንቅስቃሴ ጀመረ። የመጓዝ እቅዱም ተሳካለትና በዱባይ ለስምንት ዓመታት በስራ ላይ ማሳለፉን ያስታውሳል፤ በበረሃው ምድር ሌት ተቀን በስራ እየደከመ ህይወቱን ሊለውጥለት የሚችል ገንዘብ ለመያዝ ቢጥርም ባሰበው ልክ ሊሳካለት አልቻለም። በመሆኑም ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ሰርቶ የመለወጥ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ስራ ገባ። ከበረሃው ንዳድ ወጥቶ በሀገሩ ሰርቶና አልምቶ መለወጥን የሰነቀው ነስረዲን በሀረር የንብ ማነብ ስራን ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንደሆነው ያስታውሳል። በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት ሌት ከቀን መስራት ከቻልን የማናሳካው ነገር አይኖርም የሚለው ወጣቱ አሁን በሀገሩና በወንዙ በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን ይናገራል። የነስረዲን የንብ ማነብ ስራ የተጀመረው በጥቂት ቀፎዎች የነበረ ቢሆንም በስድስት ወራት ውስጥ ግን 50 ቀፎዎች ማድረስ መቻሉን ያስታውሳል። በሀገሬ ህልሜ እውን እየሆነ ነው የሚለው ወጣቱ የንብ ማነብ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ላይ የንብ ቀፎዎቹን 300 ሲያደርስ ለ30 የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ፈጥሯል። በአረብ ሀገር የቆየባቸውን ዓመታት በቁጭት የሚያስታውሰው ነስረዲን መልፋትና መድከም ከተቻለ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ ይላል። ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የስኬት መንገድን ጀምሬያለሁ በቀጣይም ጠንክሬ እሰራለሁ ብሏል። በቀጣይ ከንብ ማነብም ባለፈ የማር ማቀነባበርያ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የማቋቋም ትልም እንዳለው ተናግሮ ለዚህም እንደሚተጋ አረጋግጧል። በዚሁ የልማት ፕሮጀክት ላይ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ሸዊብ መሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ያለምንም ስራ ተቀምጦ መሽቶ ይነጋ እንደነበር አስታውሶ አሁን እያገኘ ባለው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየረዳ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት በድሪ ሙሳም፤ በነስረዲን ጥረት እርሱን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ስራ የተፈጠረላቸው በመሆኑ ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን አንስቶ በቀጣይ እርሱም የራሱን ተመሳሳይ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል። በሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የንብ እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢብሳ ዩስፍ፤ የነስረዲን ጥረትና የአጭር ጊዜ ስኬት ለሌሎች ወጣቶችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ የማር ምርታማነትን ለማጎልበት በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ የንብ መንደር በመመስረት ዘርፉን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 1776
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2145
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3008
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 3108
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 1055
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 727
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6566
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5040
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ባሕር በር -የታሪክና የእድገት ስብራት ወጌሻ
Nov 5, 2025 228
ባሕር በር የታሪክ እና የእድገት ስብራት ወጌሻ በቀደሰ ተክሌ የምሥራቅ አፍሪካዋ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ስሟ ገኖ እንዲነሳ ካደረጓት መካከል የሰው ዘር መገኛነት፣ የራሷ የሆነ የአስተዳደር ሥርዓት፣ የዘመን አቆጣጠር፣ ቋንቋና ፊደል ያላት ሉዓላዊት ሀገር መሆኗ ተጠቃሽ ነው ። የገናና የጥበብ ባለቤት መሆኗን አክሱም እና ላሊበላ ዛሬም ቆመው ይመሰክሩላታል። በጥንት ጊዜ ወደብ የስልጣኔ ተጽዕኖ ፈጣሪነት መገለጫ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያም ስሟ ጎልቶ ይነሳ ነበር። ወደብ ዓለምን እርስ በእርስ ከማስተሳሰር ባለፈ የግብይት የጀርባ አጥንት ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፤ ዛሬም እያገለገለ ይገኛል። ሀገራት አዋጭ የንግድ ስትራቴጂ ቀይሰው የተለያዩ ወደቦችን የመጠቀም ልምዳቸው በታሪክ ውስጥ ጎልቶ የሚነሳ ነው። የንግድ ሥርዓታቸውን በወደብና በየብስ ከሚያከናውኑ የዓለም ሀገራት መካከል ደግሞ ኢትዮጵያ አንዷ ናት። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመነ መንግስታት የተለያዩ ወደቦችን በባለቤትነት አስተዳድራለች። ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስከ ደርግ መንግስት ድረስ አዱሊስ፣ አሰብ፣ ዘይላ፣ ምጽዋና ሌሎች ወደቦችን ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ትገለገል ነበር። ይሕ የኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነት ታሪክ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ የዘለቀ እንደነበር በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሰቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምሕርት ክፍል መምሕር አጥናፉ ምትኩ ይናገራሉ። ወደብ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ እንደሆነም አውስተዋል። በታሪክ ኩነት ውስጥ የተፈጠረ ሴራና ተንኮል ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። ይሕም ከሆነ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። በዚሕም ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ብር እየከፈለች የወጪ እና ገቢ ንግድን የማንቀሳቀስ እዳ ተጭኖባታል። ይሕም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ጉዳዮች አንዱ ሆኖ ዛሬ ድረስ ዘልቋል። የወደብ አገልግሎት ነጻነት ማጣት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መጨመር፣ ማዳበሪያን ጨምሮ አስፈላጊ ግብአቶች መዘግየትና በወቅቱ አለመድረስ፣ በዚሕም የሰብል ልማት ስራዎች ላይ ችግሮች መስተዋል ከባሕር በር ባለቤትነት እጦት ጋር የመያያዝ እድላቸው ሰፊ ነው። እነዚሕ ችግሮች ደግሞ ተደማምረው ለኑሮ ውድነት መፈጠር አስተዋጾኦ ይኖራቸዋል ማለት ይቻላል። በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠረው ስብራት እያስከተለ ያለው ጉዳት አሁን ላይ ለኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ በታሪካዊ ዳራ መሠረት መጠገን ያስፈልጋል። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ከ130 ሚሊዮን ያሻቀበ የሕዝብ ቁጥር፣ የኢኮኖሚ ዕድገትና ሀገራዊ የቆዳ ስፋት ገፊ ምክንያቶች ከሚባሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ከዚሕ ቀደም የነበረው የሀገሪቱ ባሕር በር ባለቤትነት ማስረጃ ዛሬ ላይ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። መንግሥት የጀመረው የባሕር በር ባለቤት የመሆን ጥያቄ በመሬት ተዘግቶ የመኖር ታሪክ እንዲያበቃ የሚያደርግና በዓለም አቀፍ ሕግ ተፈጥሮን በጋራ ተጠቅሞ የመልማት መብትን የሚያስጠብቅ መሆኑ እውን ነው። ለሦስት አስርት ዓመታት ታፍኖ የቆየው የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ የመንግስት ቁርጠኝነት እንዳለ ሆኖ ዜጎችም አጥብቀው በመያዝ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መስራት ይጠበቃል። የሀገርና የሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆነው የባሕር በር እስኪሳካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት ከሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚጠበቅ መምሕር አጥናፉ ይገልጻሉ። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆን የታሪኳና ዕድገቷ ወጌሻ ነው ያሉት መምሕር አጥናፉ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለመጠቀም የሚያስችላት ታሪካዊ መብት አላት። ይሕን ታሪካዊ መብቷን የምታረጋግጥበት ትልቁ መሣሪያ ደግሞ ያላት ጠንካራ የዲፕሎማቲክ አቅሟ ነው። ከዓለም ሀገራት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ተናግሮ ለማሳመን እውነታን ለመግለጽ የሚያስችላት ነው። ይሕንንም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓለም ፊት አረጋግጣለች። ይሕን የሕዳሴ ድል በቀይ ባሕር ላይ የማትደግምበት ምንም ምክንያት አይኖርም። በተለይ ኢትዮጵያ ያላት የጋራ ተጠቃሚነት መርሕ በዓለም ላይ ተቀባይነት ያለውን ሀሳብ ይዛ እንድትቀርብ እያስቻላት ይገኛል። ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጠው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ ተፈጥሮን ተባብሮ በማልማት እንጠቀም የሚል መሠረት ያለው ነው። መምሕር ይስሐቅ ንጉሤ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሰቲ የምጣኔ ሀብት መምሕር ሲሆኑ የባሕር በር ጉዳይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማጠንጠኛ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ የባሕር በር ማጣቷ በፈጣን ዕድገቷ ላይ መሰናክል ሆኖ መዝለቁን ተናግረዋል። በተለይ የዓለም ሀገራት ከፍተኛው የንግድ፣ የኢኮኖሚና ሀብት እንቅስቃሴ የሚታይበት እና የሀገራት የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት የቀይ ባሕር ቀጠና ላይ ያለውን አብሮ የመስራትና ከማደግ ዕድል ኢትዮጵያ ያለአግባብ መገለሏን ያነሳሉ።ይሕም በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትና በሌሎች ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደሆነ ነው ያገለጹት። የባሕር በር ጥያቄ የምጣኔ ሀብት ዕድገትን በማሳለጥ ሀገሪቱ ከልመና ለመውጣት ያላትን ዕድል እንድትወስን ያስችላታል የሚሉት መምሕሩ ፤ለስኬቱም የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማጠናከር እንደሚገባም ነው የገለጹት። እንደ መምሕሩ ገለጻ ከዓለም አቀፍ መርሆችና ስምምነቶች እንዲሁም ካለን መልከአ ምድራዊ አቀማመጥና ታሪክ አንጻር ለኢትዮጵያ የባሕር በር ተገቢ ነው። ይሕ እንዲሳካም መንግስት ካሳየው ቁርጠኝነት በተጨማሪ ሁሉም በተቀናጀ መንገድ የሚያደርገውን ጥረት ማጠናከር ይኖርበታል። መንግስት የዘመናት የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የባሕር በር ጉዳይ በግልጽና በይፋ መረጃ በመስጠት ዓለም አቀፍ አጀንዳ እንዲሆንም ጭምር እያደረገ ያለውን ጥረትንም አድንቀዋል። ታሪክ በኩነቶች መካከል መጥፎም መልካም ሆኖ ያልፋል። በታሪክ የባሕር በር ባለቤትነታችን የገጠመውን ስብራት ለመጠገን የሚያስችል ወጌሻ ያስፈልጋል። በታሪክ ሂደት መልካሙ ወደ መጥፎ ሁኔታ እንደሚቀየር ሁሉ የተበላሸን ወደ መልካም የመቀየር ዕጣ ፈንታ ያለው የዛሬው ትውልድ ላይ ነው። ለእዚሕ ደግሞ ትውልዱ በሕዳሴው ግድብ ከመንግስት ጎን ሆኖ ያሳየውን አንድነትና ሕብረት በባሕር በርም መድገም አለበት። ታሪካዊ ዳራን፣ ዲፕሎማሲን፣ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታና ሕግን ተከትሎ በአብሮነት ከተሰራ ያኔ የተበላሸው ይቃናል፤ ያጣነውን እናገኛለን። "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" ዓይነት እንስሳዊ ግብር በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊሰማ አይገባም፤ መሰማትም አይኖርበትም። ኢትዮጵያ ብታደግ ለቀጣናው ኩራት፤ ለአፍሪካም ልዕልና እንጂ ጥፋት የሚያስከትል እንዳልሆነ መገንዘብና የትብብር ልማትና ዕድገትን ባሕል ማድረግ ሊለመድ ይገባል። ሰላም!
የዳሰነቾች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ''
Oct 30, 2025 872
የዳሰነች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ'' (በጣፋጩ ሰለሞን ከጂንካ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ዳሰነቾች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በአብሮነት ተጎዳኝተው ይኖራሉ። የብሔረሰቡ አባላት ዋነኛ መተዳደሪያ ከብት እርባታ ሲሆን፤ ከከብት እርባታው ጐን ለጐን በዝቅተኛ ደረጃ በግብርናና በዓሳ ማስገር ስራ ይተዳደራሉ፡፡ ዳሰነቾች በሰሜን ከሐመር፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ በምስራቅ ከቦረና በስተ ምዕራብ ደግሞ ከኛንጋቶም ማህበረሰብ ተጎራብተው ይኖራሉ። ዳሰነቾች ከኩሽቲክ የቋንቋ ነገድ የሚመዘዝ ''አፍ ዳሰነች'' የተሰኘ የመግባቢያ ቋንቋም አላቸው። ዳሰነቾች የተለየ የአለባበስ፣ የአጋጌጥ፣ የቤት አሰራር እና የባህላዊ የሙዚቃ ስልተ ምትን ጨምሮ አስደማሚ ባህሎች እና ማራኪ የመልክዓ ምድር አቀማመጥን የታደሉ ናቸው። ዳሰነቾች ከሚታወቁባቸው አስደማሚ ባህሎች ውስጥ አንዱ የሆነው አለመግባባቶችን በውይይት የሚፈቱበት የ''ጀለባ''ስርዓት ተጠቃሽ ነው። ይህ ስርዓት ግጭቱ ቂምና ቁርሾ በማይሻገርበት መልኩ በዘላቂነት የማስወገድ አቅም ያለው ሲሆን የማይናወጥ ሰላምና ወንድማዊ ትስስር እንዲጠናከርም ሚናው የጎላ ነው። ዕሴቱ የዳሰነቾች የአኗኗር ቁመና የሚለካበትና የሚመዘንበት መጻኢንም የሚተለምበትም ጭምር ነው። ስለሆነም በዳሰነቾች ዘንድ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል ነው የሚባለው። የባህሉ ተመራማሪ ሊዮን አርሎት 'ጀለባ'' የተሰኘው ባህላዊ ዳኝነት ከአካባቢው ሰላም አልፎ ለቀጠናው ወንድማማችነት መጠናከር ትልቅ ሚና ያለው የፍትህ ስርዓት መሆኑን ያነሳሉ። በ''በጀለባ'' ስርዓት ባህላዊ የዳኝነት አሰጣጥ እርከኖች እንዳሉ ጠቅሰው፥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ''ኖሞ'' የተሰኙ ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው በማቅናት የግጭቱን መንስኤ በማጣራት ''ቶሎል'' ለተሰኙ ሌሎች ሽማግሌዎች የሚያሳውቁበት አሰራርም አላቸው። እንደ ግጭቱ ቅለትና ክብደት ''ቶሎል'' በተሰኙ ሽማግሌዎች ተለይቶ ቀለል ያለው ''ካባና'' በተሰኙ ዳኞች ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን፥ ጉዳዩ ከበድ ያለ ከሆነ ደግሞ የመጨረሻው ውሳኔ ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች ይሰጣል። ከነፍስ ማጥፋት በስተቀር ሁሉም ውሳኔዎች ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች እልባት ያገኛሉ። የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲከሰት ግን ጉዳዩን ለመንግሥት አሳልፎ በመስጠት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል ። ነፍስ ያጠፋው ሰው የእርምት ጊዜውን አጠናቆ ማህበረሰቡን ለመቀላቀል ሲወስን ባህላዊ የዕርቅ ስነ-ስርዓት ተዘጋጅቶ በዳይና ተበዳይ ይቅር የሚባባሉበትም ስርዓት እንዳለ የባህሉ ተመራማሪ ይናገራሉ። በዳሰነቾች ባህል ልዩነቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በዘላቂነት መንገድ የመፍታት ዘመናትን የተሻገረ ድንቅ ዕሴት መኖሩን የሚያነሱት የብሔረሰቡ አባል አሸቴ ነካሲያ፤ “በዳሰነች ብሔረሰብ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል'' ይላሉ። በዳሰነቾች አለመግባባቶች በውይይት የሚፈቱበት ስርዓት እንዳለ ጠቅሰው፥ ''ናብ'' በተሰኘው የዳኝነት ስፍራ አለመግባባቶች ውለው ሳያድሩ እልባት ያገኛሉ ብለዋል። ሌላው የብሔረሰቡ አባል ሎቶያቡስ ሎኪሰሬሬ በበኩላቸው የባህል መሪዎች የተጣላን ማስታረቅ፣ ትውልዱን የመግራትና በስነ-ምግባር የማነፅ ኃላፊነት እንዳላቸው ጠቅሰዋል። ''ማንም ሰው ከባህል መሪዎች ትዕዛዝ አያፈነግጥም'' የሚሉት አቶ ሎቶያቡስ፥ ሁሉም እርስ በእርስ በመከባበር እና ችግሮች ሲኖሩ በውይይት በመፍታት አብሮነቱን ያጠናክራል ብለዋል። ወጣቱ ለባህል መሪዎች ታዛዥ ነው የሚሉት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ የብሔረሰቡ አባል ሎሲያ ሎብቻ ወጣቶች ለአካባቢው ሰላም ዘብ እንዲቆሙ፣ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በፍቅር እንዲኖሩ በማስተማር ወጣቱን በስነ-ምግባር የማነፅ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው የዳሰነች ህዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ከወረዳው አልፎ ለቀጠናው ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። የብሔረሰቡ ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት ትውልዱን በመግራት በስነ- ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲፈጠር እንዳደረገም አስረድተዋል። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርና ተመራማሪ አጎናፍር ሰለሞን፤ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቶች ለዘመናዊው የፍትህ ስርዓት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ቅጣት በመጣል ጥፋተኝነት እንዲሰማ የሚያደርጉ ሳይሆኑ፤ እውነተኛ ይቅርታን የሚያሰፍኑና ለአብሮነት የሚበጁ ዕንቁ ባህሎች እንደሆኑም አብራርተዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹ በግለሰብ ተጠቃሚነት ላይ ሳይሆን በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ በመሆናቸው ከዘመናዊው የፍትህ ስርዓት በይበልጥ ለአብሮነት መጠናከር አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹም ለሀገራዊ መግባባት ሚናቸው የላቀ በመሆኑ፥ እሴቶቹ ተጠብቀው፣ ለምተውና ጎልብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ መስራት እንደሚገባም መክረዋል። ሀገራችን ቂምና ቁርሾን የወለዱ ያለመግባባቶች በዘላቂነት በሰለጠነና ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ሁሉንም ያሳተፈ ስራ እየሰራች እንደሆነ ያነሱት መምህርና ተመራማሪው አጎናፍር ሰለሞን ዕሴቶቹ በማህበረሰቡ ዘንድ ካላቸው ተቀባይነት እንዲሁም ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ከማገዝ አንጻር ጉልህ ሚና ስለሚኖራቸው መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።