የሊጉ መሪ አርሰናል ድል ሲቀናው ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ድል ሲቀናው ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን በመካሄድ ላይ ናቸው።
በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሰናል ቡካዮ ሳካ በዘጠነኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ነጥቡን ወደ 67 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አንቶዋን ሴሜንዮ እና ሮድሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሞርጋን ጊብስ-ዋይት እና ኤልዮት አንደርሰን ለፎረስት ጎሎቹን አሳርፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ በ60 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ውሃ ሰማያዊዎቹ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያላቸው የነጥብ ልዩነት በነበረበት ወደ ሰባት ከፍ ብሏል።
ሲቲ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ ጥሏል።
ቼልሲ አስቶንቪላን ከሜዳው ውጪ 4 ለ 1 አሸንፏል።
ጆአኦ ፔድሮ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።ኮል ፓልመር ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ዳግላስ ሉዊስ ለአስቶንቪላ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ48 ነጥብ አምስተኛ፣ አስቶንቪላ በ51 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሌላኛው ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ በክሪሴንሲዮ ሳመርቪል ጎል ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል።