ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዳበረ አብሮነት የከተማዋን ምሳሌትነት እያደመቀ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመተሳሰብ የዳበረ አብሮነት የከተማዋን ምሳሌትነት እያደመቀ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢፍጣር መርሐ-ግብር አክሂዷል።

የአሥተዳደሩ ‎ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደ ከተማ አሥተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በማስታወስ በጋራ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ማዘጋጀቱ ትልቅ ደስታ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።


 

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የእምነት ልዩነት ያልገደበው ተሳስቦና ተረዳድቶ በአንድነት የመኖር ጥበብ የከተማዋን ተምሳሌትነት እያደመቀ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።

የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓቱም የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ያለውን ጠንካራ ትስስር በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል።

በቀጣይም መሰል የመደጋገፍና መረዳዳት ዕሴቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በኢፍጣር መርሐ-ግብሩ ላይ የተሳተፉት የእምነቱ ተከታዮችም በከተማ አሥተዳደሩ ለተደረገላቸው ዝግጅት ምሥጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም