ሪያል ሶሲዬዳድ ለስፔን ጥሎ ማለፍ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሪያል ሶሲዬዳድ ለስፔን ጥሎ ማለፍ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ (ኮፓ ዴል ሬይ) የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ሪያል ሶሲዬዳድ አትሌቲኮ ቢልባኦን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአኖኤታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ኦያርዛባል በ87ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ሁለቱ ቡድኖች ተመጣጣኝ ፉክክር አድርገዋል።
ሪያል ሶሲዬዳድ በድምር ውጤት 2 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል።
የባስኩ ክለብ በመጀመሪያው ጨዋታ 1 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።
ሪያል ሶሲዬዳድ በፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ይጫወታል።
የፍጻሜው ጨዋታ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ባርሴሎናን በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።