ቀጥታ፡

ኒውካስትል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ሪያል ሶሲዬዳድ ለስፔን ጥሎ ማለፍ ፍጻሜ አለፈ

የሊጉ መሪ አርሰናል ድል ሲቀናው ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጥሏል

በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ጎርደን በፍጹም ቅጣት ምት እና ዊሊያም ኦሱላ በጨዋታ ግቦቹን አስቆጥረዋል።



ተቀይሮ የገባው ኦሱላ በ90ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ካሲሚሮ ለማንችስተር ዩናይትድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የኒውካስትሉ ጃኮብ ራምሴይ በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።



ማንችስተር ዩናይትድ ያገኘውን የተጫዋች ብልጫ መጠቀም አልቻለም።

ኒውካስትል ዩናይትድ የቁጥር ብልጫ ቢወሰድበትም ባሳየው ጥንካሬ ሶስቶ ነጥብ አግኝቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ዩናይትድ በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር የመጀመሪያ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በውድድር ዓመቱም ለስድስተኛ ጊዜ ተሸንፏል።



ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኒውካስትል ዩናይትድ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ 11ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም