ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት ነው
Apr 9, 2026 549
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን የጎበኙ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ተሳታፊዎች ዛሬ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ጎብኝተዋል፡፡ ከጎብኚዎቹ መካከል ጅቡቲያዊው ኢሳም አብዱልሃኪም፤ በመጀመሪያ የሰው ልጅ መገኛ ወደ ሆነችው ታሪካዊት አገር ኢትዮጵያ በመምጣቴ እጅግ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በጣም በርካታ ታሪኮችን የያዘ ሆኖ ማግኘታቸውን አመልክተው፤ በዚህም እጅግ መደነቃቸውን ተናግረዋል። ታሪኩ ኢትዮጵያዊያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል። ዛንቢያዊቷ መሲ ችሉ በበኩላቸው፤ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ከተባበርን ከጦርነት ባሸገር በልማትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል የሚያረጋግጥ ነው። የዓድዋ ድል ትክክለኛ የአመራር ብቃትና የህዝብ ቁርጠኝነት የታየበት የጀግንነት ታሪክ ነው ያሉት ደግሞ ሱዳናዊው እስማዔል አሊ ናቸው፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚኖራቸውን የክትትልና ድጋፍ ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Apr 9, 2026 735
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚኖራቸውን የክትትልና ድጋፍ ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሳበ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል። በዚሁ ጊዜ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል ብለዋል። ባለሥልጣኑም የሲቪል ማህበረሰብ የድርጅቶች ምዝገባና ቁጥጥር፣ ለሀገር ልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሕዊና ዴሞክራሲያዊነትም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም፤ ባለስልጣኑ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምዝገባና ክትትል የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራትን ጠይቀዋል። በተጨማሪም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫና በሀገር የልማትና ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ጋር የተያያዙ አስተያየትና ጥያቄዎችን አቅርበዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፤ ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው ተቋማዊ የለውጥ እርምጃ ለሰቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል። የባለስልጣኑ አገልግሎቶችን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ መታቀዱን አመልክተው፤ የተወሰኑ አገልግሎቶችን ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለማሳደግ ‘ቅን ልብ’ የተሰኘ መተግበሪያ ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚደረገውን ክትትል ለማጠናከር ውጤታማና ስጋትን መሰረት ያደረገ የመሰክ ምልከታ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ከክልሎች ሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ምክር ቤቶች ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድርጅቶቹን ሚና ለማጎልበት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችንም አብራርተዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው፤ ከምዝገባ ጀምሮ ወደ ስራ የተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ክትትል ለማጠናከር የተሰሩ ስራዎቸን አብራርተዋል። የምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በምርጫው ሂደት ገለልተኛና ነጻ ሆነው በስፋት እንዲሰሩ የሚደረገው ክትትል ማጠናከር ያሰፈልጋል ብለዋል። ባለስልጣኑ በዲጂታላይዜሽንና በሰው ሀይል አቅም ግንባታ፣ የበጎ ፍቃደኝነት ስራዎችን ለማጎልበትና የምዝገባና ሂደቱን በጥንቃቄ ለማካሄድ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን አንስተዋል። ድርጅቶቹ በተቋቋሙበት ዓላማ መሰረት እየሰሩ መሆናቸውን እንዲሁም ጠንካራ አገሪቷን የሚመጥኑ ድርጅቶችን ለማስፋፋት መስራት ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተፈራረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የሀገራቱን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው
Apr 9, 2026 620
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተፈራረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የሀገራቱን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል። በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና ፣ በንግድ ፣ በዲጂታል መታወቂያ እና በቱሪዝም ዘርፎች የተፈረሙት እነዚህ ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። እነዚህ የመግባቢያ ስምምነቶች የሁለቱን ሀገራት ሰፊ አቅም በመደመር ወደ ብልጽግና ለምናደርገው የጋራ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ እንደሆኑም ገልጿል።
ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
Apr 9, 2026 201
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሳይ ሰለሞን በ91ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ስድስተኛ ድሉን አስመዘግቧል። በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ29 ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 17ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን፣ ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ፍላጎት ለማሳካት የታለመውን የጥፋት መንገድ በመተው የሰላም አማራጭ ተቀብለናል - ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን የቀድሞ አመራር አባላት
Apr 9, 2026 616
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- ቀደም ሲል ሲከተሉት የቆዩት የጥፋት መንገድ አገርንና ሕዝብን የሚጎዳና የታሪካዊ ጠላቶችን ፍላጎት ለማሳካት ያለመ በመሆኑ የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን የቀድሞ አመራር አባላት ገለጹ። በጥፋት ቡድኑ ተታለው ጫካ የገቡ ወንድሞቻቸውም ወደ ሠላም አማራጭ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። እጃቸውን በሠላም ለመንግስት የሰጡ የጽንፈኛ ቡድኑ የቀድሞ አመራር አባላት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ እስከአሁን ሲከተሉት የቆዩት መንገድ ለክልሉ ህዝብ አንዳች ጥቅም እንደሌለው በመረዳታቸው የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል። በጫካ ቆይታቸው የተረዱት እውነታ "ለሕዝብ እንታገላለን" በሚል መፈክር ሽፋን የቀድሞ ሕወሃትና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችን ፍላጎት ለማሳካት የተጠለፈ ትግል መሆኑንና ሕዝብን ለጥፋት ለመዳረግ ያለመ አካሄድ መሆኑን ተገንዝበዋል። እጃቸውን በሰላም ከሰጡት ራሱን አፋብን ብሎ ከሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን አመራሮች መካከል የቀድሞ የኮር ፖሊት መምሪያ ኃላፊ ጌራወርቅ ዳኛው፤ የአማራ ሕዝብ ዘላቂ ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው በሰላማዊ መንገድ መታገል ብቻ በመሆኑ ሰላማዊ አማራጭን ለመከተል ወስኛለሁ ብሏል። የጽንፈኛ ቡድኑ አመራሮች ከክልሉም ሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የልማት ፍላጎት በተጻራሪ በመቆም ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተባብረው ጥፋት በማድረስ ላይ ናቸው ያለው ጌራወርቅ፤ በማህበራዊ እሴቶችና መሰረተ ልማቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጸመው ጥቃት ከጀርባው የጥፋት ሴራ እንዳለው አመላካች መሆኑን ተናግሯል። ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን የቀድሞ አመራር አባል ሀምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙልዬ በበኩሉ፤ የጽንፈኛው ቡድን አመራሮች ከሕዝብ ፍላጎት ይልቅ ለኢትዮጵያ ጠላቶችና ለግል ጥቅማቸው እየሰሩ መሆኑን ጠቁሟል። ለጽንፈኛው ቡድን የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ የትግል አጋርን በመፈረጅ የማሸማቀቅና አልፎም ሰበብ ፈልጎ የማስወገድ ተግባር እንደሚፈጸም አስረድቷል። እነርሱ ልጆቻቸውን ውጭ ልከው እያስተማሩ የደሃ ልጆችን ግን ለመስዋዕትነት እየዳረጉ ነው ሲል ሀምሳ አለቃ ፍቅሩ አብራርቷል። ሌላው የቡድኑ የቀድሞ አመራር አባል እና ኮር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር አየነው አስፋው እንደገለጸው፤ ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን አመራሮች ፍላጎት ትግሉን በማራዘም የራሳቸውን ሀብት ማካበት ላይ ማተኮር ነው። ለትግል በሚል የተጀመረው ዓላማ የሕዝብን የልማትና የእድገት ፍላጎት የሚያደናቅፍ፣ አንዳች ፋይዳ የሌለው መሆኑን መረዳቱን አመልክቶ፤ ለህዝብ ጥቅም እንቆማለን የሚሉት የጥፋት ቡድኑ አመራር አባላት ቤት በመስራት፣ ተሽከርካሪ በመግዛትና ሀብት በማካበት መጠመዳቸውን ገልጿል። በጥፋት በድኑ ራሱን የሸዋ ፋኖ ጠቅላይ ግዛት ብሎ የሚጠራው የቀድሞ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማንነገረው መለሰ እንደገለጸው፤ የግለሰቦችን የሥልጣን ፍላጎት ለማርካት የሚደረገው እንቅስቃሴ ሀገርን ከመጉዳት የዘለለ ፋይዳ የለውም። የቡድኑ አመራሮች ምንም ዓይነት ግልጽ ፖለቲካዊ እውቀት፣ መርህና ዝግጁነት የሌላቸው መሆኑን ጠቅሶ፤ ሕዝቡ የቡድኑን እውነተኛ ማንነት ሊገነዘብ እንደሚገባም አሳስቧል። ይህ አካሄድ ሕዝብም የማይደግፈው ውጤት የማያመጣ መሆኑን መረዳቱን ጠቅሶ፤ ሰላማዊ አማራጨ በመቀበል ለመጓዝ መምረጡን ተናግሯል። የመረጡት የሰላም አማራጭ የጥፋት ተልዕኮ ሳራዘም በክልሉ ሰላም ግንባታ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሆነ አስገንዝበዋል። በዚህም እኛ የሰላም አብሪ ሆነናል ያሉት የቀድሞው ጽንፈኛ ቡድን አመራር አባላት፤ በቀጣይም ቀሪ በጫካ የሚገኙ ወንድሞቻችን የመንግስትን የሰላም አማራጭ በመቀበል ለአማራ ህዝብና ለኢትዮጵያ ሰላም መስራት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ፖለቲካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ
Apr 9, 2026 377
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ዛሬ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሁለትዮሽ ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል። በቆይታችን ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ አከናውነናል ብለዋል። እነዚህ ውይይቶች እና የተፈረሙት ስምምነቶች ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ፣ የቆዩ ግንኙነቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ብለዋል።
ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ለማድረግ የሚያግዝ አስቻይ የደኅንነት ዝግጅት ተደርጓል
Apr 9, 2026 369
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018(ኢዜአ) ፦በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ጠንካራ መንግሥት መመስረት የሚያግዝ አስቻይ የደኅንነት ዝግጅት መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሎች ገለጹ፡፡ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ የምርጫ ደኅንነት ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር አካሂዷል። በዚሁ ወቅት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የህዝባችንን የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ አስቻይ የደኅንነት ዝግጅት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ዜጎች ሰላማዊና ነፃ ምርጫ በማድረግ ጠንካራ መንግሥት መመስረት የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የደኅንነትና ፀጥታ ተቋማት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሉ እንደገለጹት፤ እያንዳንዱ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ ከሚደረግ ሁነት ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የሚያመጣው ወሳኝ ነገር አለ። ለዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉንም የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት የያዘ ዕቅድ በማውጣት ካለፉት ስምንት ወራት ጀምሮ ሰፋፊ ተግባራትን በማከናወን ወደ ተግባር መገባቱን አስረድተዋል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት የተካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫም የፀጥታና ሌሎች ፈታኝ ጉዳዮችን በማለፍ ሉዓላዊ አንድነትን የሚያስቀጥል መንግሥት ለመመስረት ያስቻለ እንደነበር አስታውሰዋል። የዘንድሮው ምርጫም ኢትዮጵያ ባለፈችባቸው ወሳኝ ምዕራፎች ውስጥ በዜጎች ይሁንታ የተመሰረተ ጠንካራ መንግሥት ለመመስረት ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን አስገንዝበዋል። ከኢትዮጵያ ህልውና ጋር የተቆራኙትን የዓባይ ተጠቃሚነትን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን መሆኑን ጠቁመው፤ የቀይ ባሕር ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥም ፍትሕዊና ሕጋዊ ጥያቄ እያቀረበች መሆኗን አንስተዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በህዝብ ይሁንታ ጠንካራ መንግሥት መመስረት የሚያስችል አስቻይ የምርጫ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች በቴክኖሎጂና በበጎ ሥነ-ምግባር የተካኑ ሙያተኞች ሰልጥነው ስምሪት መውሰዳቸውን አስረድተዋል። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድም ሰላማዊና ፍትሕዊ ምርጫ ለማካሄድ በሙያዊ ክህሎትና ሥነ-ምግባር ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሙያተኛ ስምሪት መሰጠቱን አስታውቀዋል። የምርጫ ሰላማዊነትን ለማስጠበቅም የድሮን፣ የፀረ-ድሮንና የኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃን በመሰብሰብና በመተንተን ለውሳኔ ሰጪ አካል በፍጥነት ማቅረብ የሚያስችል የላቀ ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ (ዶ/ር)፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ተዓማኒ፣ ፍትሕዊና ዴሞክራሲያዊነት የሚያስጠብቅ የደኅንነት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ለዚህም በምርጫው ሂደት ሊከሰቱ የሚችሉ የደኅንነት ስጋቶችን በመዳሰስ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን በማጥናት ሰፊ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል። ከፌዴራል እስከ ታችኛው ድረስ ባሉ መዋቅሮች በጥናት የተጠናቀሩና የሚጠናቀሩ መረጃዎችንም በመሰብሰብ፣ በመተንተንና ለውሳኔ ሰጪ አካል በማቅረብ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የምርጫ ሂደቱን የደኅንነት ሁኔታ ለማስጠበቅም የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ለአገልግሎቱ ሙያተኞች ወሳኝ ስልጠና በመስጠት አቅም እየገነባ እንደሚገኝ አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ስልጠናም ከምርጫ ባሻገር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስጠበቅ የመረጃ ኦፊሰሮችን በማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት ማሳደግ፣ መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ጠንካራ የመረጃ ኪነ-ሙያና በዕውቀትና ክህሎት የተካነ የሰው ሃብት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም ወቅታዊና አሁናዊ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ አሰላለፎችን፣ ስጋትና መልካም አጋጣሚዎችን በተገቢው መንገድ በመተንተን ምላሽ የሚሰጥ ብቁ የሰው ሃይል መገንባት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በምርጫ ደኅንነት የተሰጠው ስልጠናም የዚሁ ተግባር አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነትና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Apr 9, 2026 439
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነትና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ለገቡት የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ አቀባበል አድርገዋል። ይሄንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ፤ በድንቅ ህዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው በማለት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነትና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ ብለዋል። በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ፣ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት፤ ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
በለውጡ ዓመታት የተገኙ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የድርሻችንን እንወጣለን-የሰመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች
Apr 9, 2026 306
ሰመራ፣ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ) ፡-በለውጡ ዓመታት የተገኙ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡ የሰመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት በማስመልከት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሠመራ ስታዲየም በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተሳተፉ የሰመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ አሃው ሻሚ እንደተናገሩት ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍና ትሩፋቶቹን ለማስቀጠል በድጋፍ ሰልፉ ተሳትፈዋል። ለውጡ እውነተኛ ፌዴራሊዝምን በመተግበር የህዝቦች አንድነት የተጠናከረበት መሆኑን ገልፀው ከዚህ ጎን ለጎን በለውጡ ዓመታት ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ሁለንተናዊ ልማት መከናወኑን ገልፀዋል። ሌላዋ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ ወይዘሮ መዲና መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት በስምንት የለውጡ ዓመታት የተሰሩ ስራዎች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ ናቸው። ይህም ከተረጂነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት መሰረት የሚጥሉና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በለውጡ አመታት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በተለይ የከተሞች የኮሪደር ልማት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ተጨማሪ አቅም መፍጠራቸውን አንስተዋል። አቶ መሐመድ ያዮ በበኩላቸው ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የህዝብን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። ይህም የህብረተሰቡን ልማት የማስቀጠል ተነሳሽነትን የፈጠረና በመተባበር መለወጥ እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን ገልጸው፤ እሳቸውም ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአፍሪካ ኩራት ነው
Apr 9, 2026 370
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ኩራት ነው ሲሉ የብሩንዲ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሽሚዬ ገለጹ። ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንዳይሽሚዬ ዛሬ በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጉብኝት አድርገዋል። ከጉብኝታቸው በኋላም ከመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል። ፕሬዚዳንቱ በውይይታቸው ላይ፤ ብሩንዲ የሰላም ዕጦት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰላም በማስከበር ረገድ ላበረከተው ሚናና ለከፈለው መስዋዕትነት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ ሰራዊት መሆኑንም በማንሳት አድናቆታቸውን ገልፀዋል። የሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሰራዊት አባላት በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ላይ በጋራ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወናቸውን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ ለብሩንዲ ሰራዊት በስልጠና እና በተለያዩ ድጋፎች ስታደርግ የቆየችውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል። በርካታ የብሩንዲ ሰራዊት አባላትም በኢትዮጵያ ስልጠና በመውሰድና አቅማቸውን በመገንባት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በመጥቀስ፤ አሁንም የብሩንዲ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድጋፍና ልምድ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ፕሬዚዳንቱ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) በበኩላቸው፤ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥብቅ አጋርነት የሚያሳይ ጉልህ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። ጉብኝቱ ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ሙያዊ ልምዶችን ለመለዋወጥ ወሳኝ አጋጣሚ መሆኑንም አክልዋል። በተለይም በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ተቋማት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ መስኮችና በጋራ ወታደራዊ ስልጠናዎች ላይ በትኩረት ለመስራት ዝግጁነት መኖሩንም ጠቁመዋል። ይህ ትብብርም የሁለቱን ሀገራት የጋራ ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለቀጣናዊ ሰላም መጠበቅ ያለውን አህጉራዊ ኃላፊነት በጋራ ለመወጣት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ማህበራዊ
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት ነው
Apr 9, 2026 549
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን የጎበኙ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ተሳታፊዎች ዛሬ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ጎብኝተዋል፡፡ ከጎብኚዎቹ መካከል ጅቡቲያዊው ኢሳም አብዱልሃኪም፤ በመጀመሪያ የሰው ልጅ መገኛ ወደ ሆነችው ታሪካዊት አገር ኢትዮጵያ በመምጣቴ እጅግ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በጣም በርካታ ታሪኮችን የያዘ ሆኖ ማግኘታቸውን አመልክተው፤ በዚህም እጅግ መደነቃቸውን ተናግረዋል። ታሪኩ ኢትዮጵያዊያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል። ዛንቢያዊቷ መሲ ችሉ በበኩላቸው፤ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ከተባበርን ከጦርነት ባሸገር በልማትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል የሚያረጋግጥ ነው። የዓድዋ ድል ትክክለኛ የአመራር ብቃትና የህዝብ ቁርጠኝነት የታየበት የጀግንነት ታሪክ ነው ያሉት ደግሞ ሱዳናዊው እስማዔል አሊ ናቸው፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ
Apr 9, 2026 145
አሶሳ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለበዓል የሚሆን ዱቄት፣ ዘይትና ሌሎች ምግብ ነክ ቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ የትንሣኤ በዓልን የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመርዳት እና በመተሳሰብ ማሳለፍ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። ወቅቱ የመረዳዳት ባህላችንን የበለጠ ማጠናከር እንዳለብን የሚያመላክት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዓሉን ሁሉም በደስታ እንዲያሳልፍ እንደዚህ አይነት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።
የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየምን ጉበኙ
Apr 9, 2026 175
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየምን ጉብኝተዋል። የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየም ጉብኝት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል። በታላቁ ቤተ-መንግስት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት፤ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ መዘከራቸውንም አስታውቋል።
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ
Apr 9, 2026 168
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ) ፦ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናቸዋል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክም አስጎብኝተናቸዋል ሲሉ ገልጸዋል። በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለነበረዎት ቆይታ እያመሰገንኩ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ብለዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ከብሔራዊ ልማት አጀንዳ ጋር የተቀናጀ አደጋን የመቋቋም አቅም እየገነባች ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 9, 2026 224
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ከብሔራዊ ልማት አጀንዳ ጋር የተቀናጀ አደጋን በራስ የመቋቋም አቅም በመገንባት ረገድ ለአፍሪካ የተግባር ምሳሌ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲና ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጉባኤው ባደረጉት ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ቢጨምርም ዓለም አቀፋዊ ትብብርና መደጋገፍ እየላላ መጥቷል ብለዋል። በኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ለውጦች ለሰብዓዊ ምላሽ የሚውል የድጋፍ ሀብት መቀነሱን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አደጋ ጠንቅቃ ከመገንዘብ ባለፈ የጉዳቱ ገፈት ቀማሽ በመሆኗ የመቋቋም አቅምን የሚያጠክሩ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሯን ገልጸዋል። የረጅም ጊዜ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት እና የአየር ንብረት መቋቋም ልማት ስትራቴጂን በመቅረጽ ለሀገራዊ እድገት እና ለዓለም አቀፋዊ ምላሽ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን ጠቅሰዋል። ሀገር በቀል ፖሊሲዎችን በሁሉም መስኮች በውጤታማነት እየተገበረች ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ከብሔራዊ የልማት አጀንዳዎች ጋር የተቀናጀ የአደጋ መቋቋም አቅም እየገነባች ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኮሪደር ልማት፣ የታዳሽ ኃይል እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት አደጋን በራስ አቅም የመቋቋምና በፈተና የማትበገር ሀገር የመገንባት ወሳኝ አምዶች መሆናቸውንም አስረድተዋል። ዘላቂ መጻኢ እድልን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ በማንሳት፥ ከኢትዮጵያ አልፎ ፋይዳና ተሞክሮነታቸው ለአፍሪካ እንደሚተርፍ ገልጸዋል። ከዚህ አኳያ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አህጉሪቱ በሳይንስና በፈጠራ በመታገዝ በጋራ የመስራትና ችግሮችን የመቋቋም አቅምን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ተቋሙ አፍሪካውያን ከአደጋ በኋላ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለአደጋ ቀድሞ ወደ መዘጋጀት እንዲሸጋገሩ እያገዘ መሆኑን ጠቅሰው፥ በአጀንዳ 2063 ራሷን የቻለች፣ የማትበገርና የተባበረች አፍሪካን ለመገንባት ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቅሰዋል። የመቋቋም አቅምን ለመገንባት በሀገራት፣ በተቋማት እና በዘርፎች መካከል ያለውን ትብብር፣ መተማመን፣ መደጋገፍና የጋራ አመራርን ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል። ለዚህ ደግሞ አፍሪካ ግዙፍ አቅም፣ ሀብት፣ እውቀት እንዳላት ገልጸው፥ የሚያስፈልገን በአንድነት እና በዓላማ መነሳት ብቻ ነው ብለዋል። ከአደጋ ስጋት ወደ አይበገሬነት የሚደረገው ጉዞ ራዕይን፣ ቁርጠኝነትን እና ቀጣይነት ያለው እርምጃን እንደሚጠይቅም አንስተዋል። የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም የአፍሪካ የአንድነትና የሉዓላዊነት ምሰሶ በመሆኑ የያዘው ግብ እንዲሳካ የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ ዘላቂ ፋይናንስ እና ጠንካራ ቴክኒካዊ አቅም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለመፍታት ሀገራት ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል
Apr 9, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት በመፍታት ከውጭ ጥገኝነት ለማውጣት ሀገራት ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። ኢትዮጵያ የምታስተናግደው16ኛው የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አህጉራዊ ጉባኤ "ለሉዓላዊነት መተባበር" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አባል ሀገራትና ታዛቢዎች እንዲሁም የዘርፉ ተዋንያን የሚሳተፉበት ጉባኤው በአፍሪካውያን መካከል ትብብርና አጋርነትን በመፍጠር አህጉራዊ የአደጋ ሥጋትን የመከላከልና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርን ያለመ ነው። ጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም፣ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ለመስጠት እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አፍሪካ መር መፍትሔ ማፈላለግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክርና የጋራ መግባባት መፍጠር ያስችላል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት እንደ አፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ያሉ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት አለባቸው። በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣው ማህበራዊ፣ ኢኮናሚያዊና የስነ-ምህዳር ለውጥ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም ብለዋል። አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ቢሆንም አምስት በመቶ ጥቅል አህጉራዊ ሀብቷን እያሳጣት መሆኑን ገልጸዋል። አሕጉራዊ ችግሮች አህጉራዊ መፍትሔ እንደሚሹ ገልጸው፤ የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለአፍሪካ ችግሮች ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ብለዋል። አሕጉራዊ ማዕቀፎችና ፖሊሲዎች ከዚህ ጋር መጣጣም እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ ችግሩን በዘላቂነት በራስ አቅም ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት ይገባል ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት መካከል ያለው ትብብር በማሳደግ የፋይናንስ አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። ከተናጠል እርምጃ ይልቅ በአባል ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከርና ወደ ተግባር መቀየር ይገባል ያሉት ምክትል ሊቀ መንበሯ፤ አህጉራዊ የትኩረት መስኮች ላይ መተባበር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ከውጭ በሚመጣ ፋይናንስ ጥገኛ መሆን እንደሌለባት ጠቅሰው፤ ለአፍሪካ መፍትሔ ሀገር በቀል ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል። ግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት አካታችነት የምርጫ ጉዳይ አይደለም ያሉት ምክትል ሊቀ መንበሯ፤ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ማሳተፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ለትንሳኤ በዓል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ነው- ሸማቾች
Apr 9, 2026 120
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018(ኢዜአ)፡- በመዲናዋ ለትንሳኤ በዓል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ሸማቾች ገለጹ። ኢዜአ ለበዓል ፍጆታ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት ምን እንደሚመስል የህብረት ስራ ዩኒየኖችና ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የመሸጫ ሱቆች እና መደብሮች ቅኝት አድርጓል፡፡ ቅኝት ባደረገባቸው የሸማች ህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች ለበዓል ፍጆታ የሚያስፈልጉ ምርቶች ማቅረባቸውንና ህብረተሰቡም ሲገበያይ መመልከት ችሏል። የብርሃን ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ይታየው ታደለ ለኢዜአ እንደገለጹት ለትንሳኤ በዓል ተፈላጊ የሆኑ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለማቅረብ ቀደም ተብሎ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ከአምራቾች ጋር ትስሰር በመፍጠርና በዩንዮኖች በኩል ያለ ደላላ ጣልቃ ገብነት በቂ ምርት ወደ ህብረት ስራ ማሀበራት ማስገባት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ለትንሳኤ በዓል ዘይት ዱቄት፤ ሽንኩርት ፤እንቁላል እና ሌሎችም ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በስፋት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ አውቶቡስ ተራ ሁለገብ ሸማች ሃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም አስማረ በበኩላቸው፤ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የባልትና ውጤቶችን ጨምሮ ሌሎችን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየተከፋፈለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የብስራት ለጉለሌ ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ ሞገስ መንገሻ በዩኒየኑ ባሉት 10 መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቶቹን ለመሰረታዊ ማህበራትና ለህብረት ስራ ማህበራቱ በጅምላ እየተከፋፈለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በማህበራቱ ሲሸምቱ ያገኘናቸው ሸማቾች በበኩላቸው፤ ለበዓሉ ተፈላጊ የሆኑ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ካነጋርናቸው ሸማቾች መካከል ወይዘሮ ዓለም ለገሰ እንዳሉት ከዘይት ጀምሮ ለበዓል ተፈላጊ የሚባሉ ሽንኩርትና የተለያዩ ግብዓቶች በተመጣጠነ ዋጋ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላኛዋ ሸማች ወይዘሮ ጤና ይበልጣል በበኩላቸው በሸማቾች በኩል ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶችን ማግኘታቸውን አንስተዋል፡፡ መንግሥት በህብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር ያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ፍሬህይወት አባይነህ እና ብዙአየሁ አበበ ናቸው፡፡
የምስራቅ ቦረና ዞን የነዳጅና የግብርና ምርቶችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ አካላትን የመቆጣጠር ተግባሩን አጠናክሯል
Apr 9, 2026 97
ነገሌ ቦረና፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- የምስራቅ ቦረና ዞን የነዳጅና የግብርና ምርቶችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ አካላትን የመቆጣጠር ተግባር ማጠናከሩን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በህገወጥ የነዳጅና የግብርና ምርቶች ዝውውር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በነገሌ ቦረና ከተማ ተካሄዷል፡፡ በዚሁ ወቅት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን፤ በዞኑ የሚገኙ አንዳንድ ነጋዴዎች በአቋራጭ ለመበልጸግ ምርት በመደበቅ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ ይገኛሉ። በተለይም ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ በህገወጥ መልኩ ነዳጅን የሚያዘዋውሩ አካላት መኖራቸውም ተረጋግጧል ብለዋል። ለዚህም የዞኑ አስተዳደር ግብረ ኃይል አቋቁሞ ከማደያ ውጭ ነዳጅ በሚሸጡ ህገወጦች ላይ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን በተደረገው ጥረትም በርካታ የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውን፣ የተወሰኑ የንግድ ቤቶች ባለቤቶችም በቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡ ያልተገባ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም ህገወጥ የምርት እና የሸቀጦች ዝውውር ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ያልተገባ ድርጊት ሲፈጽሙ የተገኙ የመንግስት ሰራተኞችም ተጠያቂ እየተደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል። የዞኑ ንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገልማ ገልገሎ፤ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ከዞን አስተዳደር፣ ከንግድ፣ ከአቃቤ ህግ፣ ከፖሊስና ከሌሎችም ተቋማት የተውጣጣ የክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ምርት የደበቁ፣ ፍትሀዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና በኮንትሮባንድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም 177 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 62 ግለሰቦች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ፍትሀዊ ያልሆነ ዋጋ በሚጨምሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። የነዳጅ ምርት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ቅድሚያ ማግኘት የሚገባቸው አካላት እንዲያገኙ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪው አቶ ግዛቸው ካሳ፤ በህገወጦች ላይ የተጀመረው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ሌላዋ የመድረኩ ተሳታፊ ወይዘሮ አይናለም አየለ በበኩላቸው፤ የዞኑ አስተዳደር ህገወጥነት ላይ የጀመረው ቁጥጥር ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የክፍያ ስርዓቱ የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቱን በማዘመን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው
Apr 9, 2026 88
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮ-ቴሌኮም ያስጀመረው የክፍያ ስርዓት የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎትን በማዘመን የሀገርን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑ ተገለጸ። ኢትዮ-ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ ዲጂታል የክፍያ ስርዓት ዛሬ አስጀምሯል። የዲጂታል ክፍያ ስርዓቱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ አባሲመል በቱሉ ዲምቱ ዋና የክፍያ ጣቢያ አስጀምረዋል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮ-ቴሌኮም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ቀልጣፋ፣ ምቹና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት በማቅረብ የፋይናንስ ዘርፉን እየደገፈ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህም የሀገርን ልማት ዘላቂና አካታች ለማድረግ የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል። ኢንተርፕራይዙ በቀን ከ32 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ እንደመሆኑ፣ አዲሱ የ"ቶሎ" ዲጂታል ክፍያ አሠራር ጊዜን ከመቆጠብ ባሻገር የአገልግሎት ጥራትንና የመንገድ ደኅንነት ቁጥጥርን ማረጋገጥ የሚያስችል ነው። በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር የሚገኘው ይህ ተቋም፣ አገልግሎቱን 100 በመቶ ዲጂታል ለማድረግና አረንጓዴ ኢነርጂን ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝም ተመላክቷል። ዛሬ የተጀመረው የዲጂታል ክፍያ መርሃ ግብርም የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት በማሳለጥ የሀገርን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይህም ደንበኞች ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀ ካርድ ተጠቅመው ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ አባሲመል በበኩላቸው፤ ካሁን ቀደም ወረቀት መሰረት ያደረገ ክፍያ ስርዓት ይከናወን እንደነበረ ገልፀዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ዛሬ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል። "ቶሎ" የተሰኘ የክፍያ ስርዓት ሶፍትዌር መልማቱን አመልክተው፤ ይህም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ከቴሌ ብር ጋር በማስተሳሰር ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት መጀመሩ አብስረዋል። በዚህም ደንበኞች የተዘጋጀውን ካርድ በመጠቀም ክፍያ እንዲፈፅሙ በማስቻል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተናግረዋል። የክፍያ ስርዓቱ የመንግሥት አገልግሎቶችን በማዘመን ግልጽና የአሰራር ቅልጥፍና የሰፈነበት የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል። ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ አብሮ መስራት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።
ዲጂታል ኢንሼቲቩ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን ያለው ፋይዳን በመገንዘብ በባለቤትነት መንፈስ ሊተገበር ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Apr 9, 2026 171
ባህርዳር፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሉ አመራር ዲጂታል ኢንሼቲቩ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን ያለው ፋይዳ በመገንዘብ በባለቤትነት መንፈስ ሊተገብረው እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አሳሰቡ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያና ኢትዮ ኮደርስ አፈጻጸም ያለበትን ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል። ርዕሰ መስተዳድር አረጋ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት የመንግስት ተቋማትን አሰራር ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ የዲጂታል አሰራርን መተግበር ይገባል ብለዋል። በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያና ኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቮች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። አመራሩም ኢንሼቲቮቹ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን ያላቸውን ፋይዳ በመገንዘብ በባለቤትነት መንፈስ ሊተገብራቸው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የትምህርትና ጤና ሴክተር ሰራተኞችን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አመልክተዋል። የዲጂታል ትግበራው አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት በተሟላ ሁኔታ መተግበር አለበት ብለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው እየተተገበሩ የሚገኙት ኢንሸቲቮች የክልሉን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያፋጥኑ ሞተሮች መሆናቸውን ተናግረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በርካታ ተቋማት በአንድ ማእከል አገልግሎታቸውን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ይነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ማስቻሉን አክለዋል። ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያን እስካሁን 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች መውሰዳቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይ ሦስት ወራትም ቀሪ ግቦችን ለማሳካት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማሪያም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኢትዮ ኮደርስና የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት እንደሚያስችሉ አስረድተዋል። በመድረኩ ላይ ዘርፎቹን የሚመሩ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ የፈጣን መንገድ የክፍያ ሥርዓትን በቴሌ ብር ማከናወን የሚያስችል ዲጂታል የክፍያ ስርዓት አስጀመረ
Apr 9, 2026 253
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ የፈጣን መንገድ የክፍያ ሥርዓትን በቴሌ ብር አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ዲጂታል የክፍያ ስርዓት አስጀመረ። ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ የፈጣን መንገድ የክፍያ ሥርዓትን በቴሌ ብር ማከናወን የሚያስችለውን ዲጂታል የክፍያ ስርዓት የማስጀመር መርሀ ግብር በቱሉ ዲምቱ ዋና የክፍያ ጣቢያ እያካሄደ ነው። የክፍያ ስርዓቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ አባሲመል በቱሉ ዲምቱ ዋና የክፍያ ጣቢያ አስጀምረዋል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮ-ቴሌኮም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ቀልጣፋ፣ ምቹና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት በማቅረብ የፋይናንስ ዘርፉን እየደገፈ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህም የሀገርን ልማት ዘላቂና አካታች ለማድረግ የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል። ዛሬ የተጀመረው አገልግሎት የትራንስፖርት ዘርፉ በተሻለ ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይህም ደንበኞች ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀ ካርድ ተጠቅመው ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ አባሲመል በበኩላቸው፤ ካሁን ቀደም ወረቀትን መሰረት ያደረገ ክፍያ ስርዓት ይከናወን እንደነበር ገልፀዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ አገልግሎቱን ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ዛሬ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል። "ቶሎ" የተሰኘ የክፍያ ስርዓት ሶፍትዌር መልማቱን አመልክተው፤ በዚህም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ከቴሌ ብር ጋር በማስተሳሰር ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት መጀመሩን አብስረዋል። በዚህም ደንበኞች የተዘጋጀ ካርድ በመጠቀም ክፍያ እንዲፈፅሙ በማስቻል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተናግረዋል። ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ አብሮ መስራት የሚያስችል የፊርማ ስምምነት ስነ-ስርአትም አካሂደዋል።
በክልሉ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል
Apr 9, 2026 95
ባህርዳር ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋት ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠትና ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን መሀመድ (ዶ/ር) ገለጹ። በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያና የኢትዮ ኮደርስ አፈጻጸም ያለበትን ሁኔታ የሚገመግም መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን መሀመድ (ዶ/ር)፤ በክልሉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተመረጡ ከተሞች ተጀምሮ ለሌሎች አካባቢዎችም ሞዴል በሚሆን መልኩ እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል። የፋይዳ የዲጂታል መታወቂያና የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ተደራሽ በማድረግ ረገድም ጥሩ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልጸዋል። በክልሉ እስካሁን 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መውሰዳቸውንም ለአብነት ጠቅሰዋል። እነዚህ አገልግሎቶች ተግባራዊ መደረጋቸው ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል አስችሏል ብለዋል። በቀጣይም አገልግሎቶቹን ተደራሽነት የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል። በመድረኩ ላይ በክልሉ የሚገኙ ዘርፉን የሚመሩ የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ስፖርት
ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
Apr 9, 2026 201
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሳይ ሰለሞን በ91ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ስድስተኛ ድሉን አስመዘግቧል። በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ29 ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 17ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን፣ ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ሀዲያ ሆሳዕና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
Apr 9, 2026 91
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄኖክ አርፊጮ በ11ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ጎሏን አስቆጥሯል። ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ስምንተኛ ድሉን አስመዝግቧል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ22 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
Apr 9, 2026 81
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንተ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምኞት ደበበ በ67ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን የጨዋታዎች ብዛት ወደ ዘጠኝ አድርሷል። በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ41 ነጥብ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብሏል። በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ
Apr 9, 2026 85
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪቲካ ጅማ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ጎል ነገሌ አርሲ መሪ ሆኗል። ከእረፍት መልስ ብሩክ በላቸው በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ለኢትዮጵያ መድን አንድ ነጥብ አስገኝቷል። አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ የማድረግ እድል አልተጠቀመም። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ29 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። መድን ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የሕብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ የታየበት በአፍሪካ ቀዳሚ ኢንሼቲቭ ነው
Apr 9, 2026 67
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ የታየበት በአፍሪካ ቀዳሚ ኢንሼቲቭ መሆኑን የብሄራዊ አረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አህጉራዊ ጉባኤ "ለሉዓላዊነት መተባበር" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አባል ሀገራትና ታዛቢዎች እንዲሁም የዘርፉ ተዋንያን የሚሳተፉበት ጉባኤው በአፍሪካውያን መካከል ትብብርና አጋርነትን በመፍጠር አህጉራዊ የአደጋ ሥጋትን የመከላከልና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርን ያለመ ነው። ጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም፣ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ለመስጠት እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አፍሪካ መር መፍትሔ ማፈላለግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክርና የጋራ መግባባት መፍጠር ያስችላል። የብሄራዊ አረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) በመድረኩ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬትና ለአፍሪካ ያላትን ተሞክሮ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ምዕራፍ 50 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ስታቅድ በወቅቱ ምሁራን ሳይቀሩ ዕቅዱ ሊሳካ አይችልም የሚል ጥርጣሬ እንደነበራቸው አስታውሰዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እሳቤ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተራቆተ መሬትን እንዲያገግም ማድረግ ሥነ-ምህዳሩን መመለስ እና ለግብርናና ከተማ ልማት ምቹ ከባቢ መፍጠር ነው ብለዋል። በዚህም የተለያዩ ሀገር በቀል እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል የኢትዮጵያን ምድር አረንጓዴ ማልበስ መጀመሩን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከቀጣይነት ያለው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃን በማጠናከር የግብርና ሥራዎች ምቹ ሥነ-ምህዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ የመላው ኢትዮጵያውያንና ተቋማት ትብብር የጋራ ውጤት ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ ከጠቅላይ ማኒስትሩ ጀምሮ የሁሉም አመራር ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ተሞክሮ ሆኗል ብለዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀው፣ ኬንያ በአስር ዓመት ውስጥ 15 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ተሞክሮ መውሰዷን ተናግረዋል።
ለአየር ንብረት ለውጥ የማትበገር አፍሪካን ለመገንባት አህጉራዊ አንድነታችን ወሳኝ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 9, 2026 171
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- ለአየር ንብረት ለውጥ የማትበገር አፍሪካን ለመገንባት አህጉራዊ አንድነታችን ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በሰው ልጅ መገኛዋ ኢትዮጵያ፣ በአፍሪካውያን መሰባሰቢያ አዲስ አበባ፣16ኛውን የአፍሪካ የሥጋት መከላከል ዐቅም ጉባኤ (ARC-COP16) በይፋ አስጀምረናል ብለዋል። አህጉራችን በአየር ንብረት ለውጥ ክፉኛ እየተፈተነች ትገኛለች ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ሆኖም ይህ ፈተና ተስፋችንን የሚያጨልም፣ ጉዟችንን የሚገታ አይሆንም ሲሉም ገልጸዋል። በእልህ፣ በቁጭትና በእንችላለን ኅብረት አንድነታችንን የምናጠናክርበት አጋጣሚ ነው። እኛ አፍሪካውያን ከአደጋ በኋላ ለሚመጣ ርዳታ እጅ ከመዘርጋት ይልቅ፣ አደጋን ቀድሞ መከላከልና በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍትሔ መዘጋጀት የህልውናችን መሠረት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ራዕይ ሰንቃ፣ ክንዷን አበርትታ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ዐቅም እየገነባች መሆኑን ገልጸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የምድርን ገጽታ እየቀየርን መሆኑንም ተናግረዋል። በምግብ ሉዓላዊነት ንቅናቄ ራሳችንን ለመቻል እየተጋን ነው። በታዳሽ ኃይል ልማትም የአህጉራዊ ትሥሥር ገመድ እየሆንን ነው ብለዋል። ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በበዙበት፣ በአንጻሩ ዓለም አቀፋዊ ድጋፎች በቀነሱበት በዚህ ወቅት፣ የአፍሪካ ሥጋትን የመከላከል ዐቅም (African Risk Capacity-ARC) የመሰሉ አህጉራዊ ተቋሞቻችንን ማጠናከር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የአደጋ ሥጋትን በጥናት መለየት፣ ቀድሞ መከላከል፣ ችግር ሲከሠትም በአፍሪካዊ ዐቅም ምላሽ መስጠት ይገባል። ኢትዮጵያም ለዚህ የአፍሪካውያን ሌላኛው የሉዓላዊነት ግብ መሳካት በአርአያነት ትተጋለች ብለዋል።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ለአፍሪካ ምሳሌ ናቸው
Apr 8, 2026 504
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ፣ በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከልና ምላሽ ለአፍሪካውያን ምሳሌ የሆኑ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገኝ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አህጉራዊ ጉባኤ "ለሉዓላዊነት መተባበር" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተካሄደ ነው። 39 የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አባል ሀገራትና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን እየተሳተፉበት የሚገኘው ይህ ጉባኤ፤ በአፍሪካውያን መካከል ትብብርና አጋርነትን በመፍጠር አህጉራዊ የአደጋ ሥጋትን የመከላከልና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርን ያለመ ነው። የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካውያን የምግብ ሉዓላዊነትን በራሳቸው አቅም ለማረጋገጥ ለጋራ ግብ የሚተባበሩበት ወሳኝ ወቅት ላይ ናቸው፡፡ የአፍሪካ የአደጋ ሥጋት አቅም አህጉራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ለማሳካት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የተቀናጀ የአደጋ ሥጋት ምላሽ መስጠት የሚያስችል አህጉራዊ የፋይናንስ አቅም መገንባት ይገባል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ግቦችን በማሳካት የምንመኛትን አፍሪካ ለመገንባት የሀገራት ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ቀዳሚ አጀንዳ መደረጉን ገልጸው፤ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር የተሟላ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አቅም ተገንብቷል ብለዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ አረንጓዴ አሻራ፣ መስኖ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የታዳሽ ኃይል እና ሌሎችም ኢንሼቲቮች የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመከላከል እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመመከት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥና የአደጋ ምላሽ በመስጠት ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ እየሆነች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ያሳየችው ስኬት ጉባኤውን ለማስተናገድ ተመራጭ እንዳደረጋትም ኮሚሽነሩ አንስተዋል። የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በማሟላትና የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ያስመዘገበቻቸውን ተሞክሮዎች የምታጋራበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሥርዓት ለመገንባት የተገበረቻቸው ኢኒሼቲቮች የምግብ ሉዓላዊነትን እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማሳካት እንደሚያስችሉ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ የሚሰሩ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የአየር ንብረት ለውጥን መከላከልና የአደጋ ምላሽ በመስጠት ለአፍሪካውያን ምሳሌ የሆኑ የተግባር ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው
Apr 8, 2026 153
አሶሳ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ዑራ ወረዳ የችግኝ ጣቢያዎች በመገኘት ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ዝግጅትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ ብሎም እንደ ሀገር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የልማት ስራው ዘንድሮም ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተው ለዚህም በክልሉ በቂ የችግኝ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን በጉብኝታችን አረጋግጠናል ብለዋል። ከዚህ ፊት የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ደረጃ እና በወረዳው በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችንም ርእሰ መስተዳድሩ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 358
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 276
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 574
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 264
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሐተታዎች
የጤና ነገር ...
Apr 3, 2026 2089
በዮሐንስ ደርበው የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። የኒውትሬሽን ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የሰው ልጅ የሰውነት ክፍል 60 በመቶው ውኃ እንደመሆኑ ለተስተካከለ ጤና ሚዛን መጠበቅ በቂ ውኃ መጠጣት ይገባል። ውኃን በትክክለኛው መጠንና ጊዜ መውሰድ ከተቻለ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን 50 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ነገር ግን ሰውነት የሚፈልገውን የውኃ መጠን በአግባቡ ካላገኘ ለዕለታዊ እና በጊዜ ሂደት ሥር ለሚሰድዱ ህመሞች የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምርም ያነሳሉ። ለመሆኑ ሰውነት የሚፈልገውና በቂ የውኃ መጠን የሚባለው መጠኑ ስንት ነው? በቂ ውኃ አለመጠጣትስ የሚያስከትለው ችግር ምንድን ነው? በሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ የኒውትሬሽን መምህር፣ ተመራማሪ እና ደራሲ ይሁኔ አየለ ምላሽ አላቸው። አንድ ሰው የሚያስፈልገው የውኃ መጠን በዕድሜ፣ ጾታ፣ በሥራ ባሕርይ፣ በመኖርያ አካባቢ፣ እንደ ጤና ሁኔታው እና እንደ ሰውነት ክብደቱ እንደሚወሰንም በምላሻቸው አስገንዝበዋል። ለምሳሌ የስኳር ታማሚዎች፣ የምታጠባ እናት፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ብዙ አድካሚና ላብ የሚያወጡ፣ በሞቃታማ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቀን 3 ሊትር ውኃ መጠጣት አለባቸው ይላሉ። በአማካይ ግን በቀን አንድ ሰው ከ2 እስከ 3 ሊትር ውኃ መጠጣት እንደሚጠበቅበት ይገልጻሉ። ጤናማ ሕይወት የሚመሠረተው ከውኃ ነው፤ ለምሳሌ ውኃማውን 60 በመቶ የሰውነት ክፍል ሚዛን ለማስጠበቅ የግድ አስፈላጊውን መጠን ውኃ መጠጣት እንደሚገባ ይመክራሉ። በሰውነት ውስጥ የሚካሄደው ሕይወታዊ ሂደት (ባዮሎጂካል ፕሮሰስ) ውኃን መሠረት ያደረገ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለምሳሌ ለተስተካከለ የሥርዓተ-ምግብ ሂደት፣ ቆሻሻን ከሰውነት አጣርቶ ለማስወጣት፣ የአጥንት መገጣጠሚያ ሥራን ለማስተካከል እና ለሌሎችም በርካታ የሰውነት ክፍሎች የተሳለጠ ተግባር ውኃ ቁልፍ መሆኑን አንስተዋል። ይህን ተከትሎም ውኃ ካሎሪ አልባው መድኃኒት (ተፈጥሯዊው መድኃኒት) እስከመባል መድረሱን ነው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያስረዱት። ሰውነት የሚያስፈልገውን ያህል ውኃ አለመጠጣት ግን ድካም ያስከትላል፤ ለማየት፣ ለመንቀሳቀስ፣ ለመሥራት፣ ለማሰብ፣ ለመረጋጋት . . . አያስችልምና ሲሉ ያብራራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ ሰው ውኃ የመጠማት መጠኑ ከአራት በመቶ በላይ ከሆነ ለሞት ሊጋለጥ እንደሚችልም ጠቅሰዋል። ውኃ አለመጠጣት፤ የጨጓራ ህመምን በማባባስ ማስገሳት፣ የቆዳ ድርቀትና ግርጣት፣ የኩላሊት ህመም ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ያደርጋል ነው ያሉት። ከምግብ በፊት 30 ደቂቃ ቀድሞ ውኃ መጠጣት ውፍረትን ለመቀነስ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። በቂ ውኃ ከመጠጣት በተጨማሪ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ማዘውተር እንደሚመከርም ገልጸዋል። የፈላ ውኃ እና የዝናብ ውኃን በብዛት መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድና በኩላሊት ላይም ጫና እንደሚፈጥር አመላክተዋል። ለተስተካከለ ጤናማ ሕይወት የግድ ውኃ መጠጣትን ልማድ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ። #ውኃ_መጠጣት #ጤና #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency
ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች
Apr 3, 2026 2190
በዮሐንስ ደርበው የለውጡ መንግሥት ኢትዮጵያን ማሥተዳደር ከጀመረ እነሆ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ 8 ዓመት ሞላው። በእነዚህ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊ ዘርፉ በዲፕሎማሲውና በሌሎችም መስኮች የተለያዩ ስኬቶች ተከናውነዋል። በእነዚህ ጥቂት ዓመታትም ለማሳካት ቀርቶ ለማሳብ የማይደፈሩ ብዙ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። የተገኙት ስኬቶች ከጊዜያቸው የፈጠኑ ናቸው። ለዚህም ሕዝቡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በነቂስ እየወጣ አድናቆቱን ገልጿል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሰጡት የሰላ አመራርነትና ቁርጠኝነትም አክብሮቱንና ምሥጋናውን ገልጿል። የለውጡ መንግሥት አካሄድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የልማት ፕሮጀክቶችም በይበልጥ ተስፋፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆሙም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ባስተጋቧቸው መልዕክቶቻቸው አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በለውጡ መንግሥት ለማሳካት ቀርቶ ለማሰብ የማይደፈሩ ተግባራት ተከናውነዋል። ከእነዚህ ከፍተኛ ጥቅም ከተገኘባቸው የታሪክ እጥፋትን ካሠረጹ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹን ቀጥለን በወፍ በረር እንዳሥሣለን። ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ሥልጣኔ - በምርጫ ካርድ መምረጥ የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። • የኮሪደር ልማት እንደምናውቀው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነትና ልዩ ትኩረት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከሁሉም አስቀድሞ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። አሁን ላይ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የበርካታ ከተሞችን ገጽታ የቀየሩ አስደማሚ ሥራዎች ተከናውነውበታል። ይህም በገጠር ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ለዘመናት አሮጌ ገጽታዋን ይዛ ያሸለበችውን አዲስ አበባ እንደ አዲስ የፈጠራትም ይኸው ፕሮጀክት ነው። አሁን ላይ መዲናይቱ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን ለውጥ ዐይተው ዝም ማለት አልቻሉም። ከመደመማቸው አንጻር የዘወትር አጀንዳቸውም እያደረጓት ይገኛሉ። ይህንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ነው ማለታቸው ይታወሳል። ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑንንም አስረድተዋል። ከለውጡ መንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ለማሳደግም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ድርብርብ ፕሮጀክት ነው የኮሪደር ልማት። • የበጋ መስኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የለውጡ መንግሥት ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ለዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አንዱ ማሳኪያ ሥልት አድርጎ እየተጋ ይገኛል። የበጋ መስኖ ስንዴ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ ማስገባት አቁማ መላክ እንድትጀምር ያስቻለ ኢኒሼቲቭ ነው። በዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችና በሜካናይዜሽን ታግዞ በስፋት እየተሠራበትም ይገኛል። ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በምርታማነት ማደግና የሥራ ዕድል በመፍጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል። የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብም ከፍተኛ ውጤት ተገኝቶበታል። ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ላይ ባሳየችው ትጋት፤ ፍጆታዋን በራሷ ዐቅም የሸፈነችው፣ ስንዴን ከውጭ ማስገባትን ያቆመችው፤ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችው በለውጡ መንግሥት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ በመሸለም ለጥረታቸው ዕውቅና መስጠቱም ይታወሳል። • መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል አንድ ጉዳይን ለማስፈጸም እዚያም እዚህም መንከራተት የግድ ነበር። በዚህ አያበቃምና ወረፋውም ሌላ ችግር ነው። መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ባካሄዳቸው ሕዝባዊ ውይይቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉልን የሚሉ እሮሮዎች በረከቱ። መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል ሥራ ወደ ተግባር አሥገባ። በዚህም መሠረት ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ ጀመረ። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነውም አሉ። ለዚህ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ የሆነውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስጀመራቸውንም ገለጹ። እንግዲህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በመሰብሰብ በቴክኖሎጂ ታግዘው በተሳለጠ ሂደት እንዲሰጡ በማድረግ የተገልጋይን እንግልት፣ ገንዘብ እና ጊዜ መቀነስ ያስቻለ አሠራር ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት ተደርጎም ይወሰዳል። በየከተሞቹም እየተስፋፋ ነው። • አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ አይ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው በቁጭት በተለያዩ መድረኮች ያነሳሉ። ለዚህም መፍትሔ ዘይደው ተቋማትን ከማቋቋም ጀምሮ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ተግተዋል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ ለመጓዝ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቋመች። የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ በመክፈት በግብርናው፣ በጤናው እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠርም በሂደት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት ቀይሮ ወደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ሕንፃ በተዛወረበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የሚታይ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ የሮቦቶችን ሶፍትዌር ብቻ ሳይሆን ውጫዊ የአካል ክፍልን (ሃርድዌር) መሥራት ጀምሯል ብለዋል። ድሮን ማምረት ብቻ ሳይሆን የማነጋገር ዐቅም እየፈጠረ ያለ ተቋም መሆኑንም አንስተዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደር አሠራርን የሚከተል መሆኑን ጠቁመው፤ በርካታ ምርቶችን አውጥቷል ማለታቸው ይታወቃል። ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮሉሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን ሲሉ ማስገንዘባቸውም ይታወሳል። • የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው። በዚህ ሂደት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊታአውራሪነት ይጠቀሳል። በተደራጀና ተቋማዊ ሆኖ ባልተቆራረጠ አካሄድ እየተከናወነ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተተከሉ ችግኞችም በየዘርፉ ተጠቃሚነት አድጓል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል። • የሌማት ትሩፋት ከመጋቢት ሥጦታዎች አንዱ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ነው። የምርት አቅርቦትን በማስፋት ለተረጋጋ ግብይት እና ለተመጣጠነ ሥርዓተ-ምግብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይም ይገኛል። ኢኒሼቲቩ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለሀገራዊ የሥርዓተ-ምግብ መሻሻል ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ነው። የዋጋ ንረትን በማረጋጋት፣ የምርት ስብጥርን በማሳደግና በዘላቂነት በማቅረብ ረገድም የጎላ ሚና አለው። የግድ ሰፋፊ መሬት መፈለግ ሳያሻ በትንሽ ቦታ ብዙ በማምረት ፍጆታን ከመሸፈን አልፎ ኢኮኖሚን በመደጎም እና የሥራ ዕድል በመፍጠርም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። • የቱሪስት መዳረሻ ልማት ቅርሶች እንዲጠገኑ፣ አዳዲስ ሎጂዎች እንዲገነቡ፣ በመዳረሻ ስፍራዎች መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ያስቻሉ ተግባራት በለውጡ መንግሥት ተከናውነዋል፤ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ እና ስኬታማ ኢኒሼቲቭ ነው። በዚህ ሂደት ከሐሳብ አመንጭነት ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የጻፉትን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ጭምር ለቅርስ ጥገናና ለቤተ-መጻሕፍት ግንባታ እንዲውል አድርገዋል። በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት፤ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደ ተግባር አስገብተዋል። በእነዚህ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። አማራጭ የቱሪስት መዳረሻም ሆነዋል። • የተቋማት ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪል ሐሳብ በተካሄደው የዐበይት ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ኮንፈረንስ ላይ፤ የተቋማት ግንባታና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ብለዋል። በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው ሲሉም አስገንዝበዋል በወቅቱ። ዘመን የማይለውጣቸው ዘላቂ ጠንካራ ሃገራዊ ተቋማትን በመገንባት ረገድ ብዙ ርቀት መጓዝም ተችሏል። በመሆኑም የመንግሥት ተቋማት ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲሆኑ በማድረግ እና ሥርዓት በተለዋወጠ ቁጥር የማይፈርሱ ወይም የሚሻገሩ ተቋማት መገንባት ተችሏል። ይህ ትጋት ተጠናክሮም ቀጥሏል።
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3696
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 445
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
ትንታኔዎች
ከፓን አፍሪካኒዝም እስከ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት - የኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የስድስት አስርት ዓመታት የዲፕሎማሲ ጉዞ
Apr 9, 2026 412
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያና የብሩንዲ ግንኙነት የሚጀምረው አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ለመውጣት በምትታገልበት ወሳኝ ወቅት እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት እንደመሆኗ፣ ብሩንዲ እ.ኤ.አ በ1962 ከቤልጂየም ቅኝ አገዛዝ ወጥታ ነፃነቷን ስታገኝ ግንኙነታቸውን በይፋ ከጀመሩ የመጀመሪያዎቹ አገራት ተርታ ትመደባለች። ይህ ግንኙነት በወቅቱ በነበረው የፓን-አፍሪካዊነት መንፈስ እና አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካዊ ችግሮች በሚለው መርህ ላይ የቆመ ነበር። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ምስረታ ላይ የነበራቸው የጋራ ተሳትፎ ለዘመናት ለዘለቀው ወንድማማችነት ጠንካራ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አዳዲስ ከቅኝ ግዛት ነፃ የሚወጡ የአፍሪካ ሀገራትን ወደ አህጉራዊው መድረክ ለማምጣት በነበራቸው ራዕይ መሰረት፣ ከብሩንዲ የመጀመሪያው ንጉሥ ምዋሚ ምዋቡትሳ አራተኛ ጋር የጠበቀ ግንኙነት መስርተዋል። ግንኙነቱ በይፋ ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በኋላም (እ.አ.አ 1963) ብሩንዲ በአዲስ አበባ በተመሰረተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) ላይ በመስራች አባልነት እንድትሳተፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች። በወቅቱ የነበረው የሀገራቱ ግንኙነት በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል እና በቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነበር። በወቅቱ ይደረጉ በነበሩ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብስባዎች ላይ ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ አህጉራዊ አጀንዳዎችን በጋራ አንጸባርቀዋል። ኢትዮጵያ በብሩንዲ የሰላም ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውታለች። በተለይም በብሩንዲ የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ጥረት እና በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (AMIB) ውስጥ የኢትዮጵያ ሰራዊት ቀዳሚ ተሳትፎ ነበረው። ልዑኩ በአፍሪካ ህብረት ታሪክ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ በአህጉሪቱ የተመራና የተደራጀ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንደሆነ ይወሳል። ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሞዛምቢክ ጋር በመሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ልካለች። ሰራዊቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲከበር ማድረግ፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ (DDR) ላይ ትልቅ ስራ ሰርቷል። ኢትዮጵያ በወታደራዊ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲው ረገድም ንቁ ተሳትፎ አድርጋለች። የአሩሻ የሰላም ስምምነት እንዲሳካ እና በብሩንዲ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች በኢጋድ (IGAD) እና በአፍሪካ ህብረት በኩል ጫና ሲያደርጉና ሲያሸማግሉ ቆይተዋል። በብሩንዲ በተለያዩ ቡድኖች መካከል እምነት እንዲገነባ ኢትዮጵያ እንደ ገለልተኛ እና ታማኝ አደራዳሪ ትታይ ነበር። ተልዕኮው ስራውን አጠናቆ ወደ ተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (ONUB) ሲቀየርም የኢትዮጵያ ሰራዊት እዛው በመቆየት ለሰላሙ ዘላቂነት አስተዋፅኦ ማድረጉን ቀጥሏል። ይህም ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ይህም በሁለቱ ሀገራት ትብብር ውስጥ በትልቁ የሚነሳ እና የሚወሳ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም እና በፖለቲካዊ ወዳጅነት ላይ መሰረት አድርጎ የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት ወደ ተለያዩ መስኮች እየሰፋ መጥቷል። እ.አ.አ በ1970ዎቹ መጀመሪያ በሀገራቱ መካከል የተፈረሙ የንግድ እና የባህልን ትብብር የማጠናከር የጋራ መግባቢያ ሰነዶች የዚሁ ማሳያ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በሀገራቱ መካከል የተደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና የጋራ ስብሰባዎች ግንኙነቱን ከማጠናከር ባለፈ የትብብር አድማሱን ማስፋትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን ማየት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2023 በብሩንዲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ብሩንዲ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ አቪዬሽን እና ቀጣናዊ ሰላም ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው። በጉብኝቱ ወቅት ብሩንዲ የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት እና የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ በስፋት ለመተግበር ያላትን ፍላጎት አሳይታለች። የሁለትዮሽ ውይይቱ የተለያዩ ውጤቶች የተገኙበት ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን የሚያቀላጥፉ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ውሳኔ ተላልፏል። ኢትዮጵያ ለብሩንዲ በቴክኒክ እና በሙያ ስልጠና (TVET) ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች። የሀገራቱ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን (JMC) በየጊዜው እየተገናኘ ስምምነቶችን እንዲከታተል መመሪያ ተሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውይይቱ በተጨማሪ ግብርና እና ኢንዱስትሪን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2023ቱ የብሩንዲ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ በዋና ማሳያነት የሚጠቀስ ነው። የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ እ.አ.አ በ2021 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለብሩንዲ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ችግኞችን በስጦታ አበርክተው ነበር። ይህም ሀገራቱ በግብርና እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያላችውን ፍላጎት የሚያሳይ ነበር። በፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ወቅት የመጀመሪያ የኢትዮ-ብሩንዲ የመጀመሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባ ተደርጓል። በወቅቱ በግብርና፣ በቱሪዝም እና በትምህርት ዘርፍ አዳዲስ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። እ.አ.አ በ2023 የብሩንዲ ፓርላማ የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) በህግ አፀደቀ (Ratified)፤ ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ተደርጎ ተቆጠረ። ኢትዮጵያ ብሩንዲ ስምምነቱን እንድታጸድቅ ድጋፍ አድርጋለች። ይህም የሀገራቱን የውሃ ትብብር የበለጠ ያጸና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። የቀድሞው የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል። ይህም በሀገራቱ የከፍተኛ አመራሮች የጉብኝት ልውውጦች ውስጥ የሚጠቀስ ነው። ከንኩሩንዚዛ ጉብኝት ሁለት ዓመታት በኋላ እ.አ.አ በ2014 ብሩንዲ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ከፍታለች። ይህም የሀገራቱን ትብብር ለማጠናከር የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ ከብሩንዲ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ስራ የሚሸፍነው በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ በተለያዩ ጊዜያት ተደራራቢ ታክስን ማስቀረት፣ በኢንቨስትመንት፣ አየር ትራንስፖርት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመከላከያ እና ፀጥታ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲሁም ባህልና ስፖርት ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈራርመዋል። ጉብኝቶችና ስምምነቶች ኢትዮጵያና ብሩንዲ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር በማሳለጥ እና የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው ሚና ወሳኝ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያና የብሩንዲ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን (Joint Ministerial Commission - JMC) መጋቢት 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሄዷል። ስብስባውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ፣ የቀጣናዊ ትስስርና የልማት ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና በጋራ መርተውታል። በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የዘርፍ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በስብስባው ማብቂያ የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ተፈርመዋል። ስምምነቶቹም በዋናነት በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር (በተለይም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ)፣ በግብርና ምርታማነት፣ በአቪዬሽን እና በቀጣናዊ ደህንነት ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ስብስባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) መርህ መሰረት በማድረግ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር፣ የመሰረተ ልማት ግንኙነቶችን ማስፋፋት እና በአባይ ተፋሰስ የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈረም በስኬት ተጠናቋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ እና የብሩንዲን ትብብር የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል ነው። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሁለቱን ሀገራት ትብብር ከማጠናከር ባለፈ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትስስር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። የኢትዮጵያ እና የብሩንዲ መጻኢ የሁለትዮሽ ትብብር በሁለገብ ዘርፎች ላይ ያተኮረና ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚሸጋገርበት ወቅት እንደሚሆን ይጠበቃል። የፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጉብኝት እና የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽኑ ውሳኔዎች፣ ለቀጣዮቹ ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚኖረው ጠንካራ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትስስር መጠናከር ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 4, 2026 1118
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 20 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ መሆኗን ገልጸው፤ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፣ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ፣ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ብለዋል። ፈጣን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሠራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ ዐቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው ከፍተዋል። በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል በወቅቱ። የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከል ማከተቱን አብራርተዋል። ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። • የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የከተማችንን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል። በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋልም ነው ያሉት። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል ሲሉም ገልፀዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአፋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል። በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት፤ ለሌሎች በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሠነድ እንደሚሆን አመላክተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የጸጥታና ደኅንነት ተቋሞቻችን ችግርን ወደ ዕድል እንዲቀየሩ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጨምና ከትናንት ዕዳዎች ተላቀን፣ የዛሬ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ለነገው ትውልድ የምትመጥን ሀገር ለመገንባት በዓላማ ጽናት እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል። • ስለ መጋቢት 24 መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የመጣውን የለውጡን መንግሥት የሚደግፉ ሕዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ሰልፎች ላይም መንግሥት ባለፉት ሥምንት ዓመታት ያመጣቸውን ለውጦች እና የተገኙ ስኬቶችን የሚያወሱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) ለሰጡት ስኬታማ አመራርነት የሚያሞግሱና የሚያመሠግኑ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝባዊ ግፊትና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው ብለዋል። ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብሏል። የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች ሲልም ገልጿል። ይህን ለውጥ ዕውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፤ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም ነው ያለው። • የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ሕንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ጽሕፈት ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል ብሏል። የ1954 የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ሲልም አስገንዝቧል ጽሕፈት ቤቱ።
ባሳለፍነው ሳምንት
Mar 28, 2026 517
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • የ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን እና የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ሎጁ የዛሬ 50 እና 60 ዓመት መሠራት የነበረበት ቢሆንም፤ አሁን ስለዘገየን አንቆጭም ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ስለሠራንም አንረካም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሩጫችን ገና ብዙ እንደሆነ፣ አፋር ገና እንዳልተነካ አስበን ይህን ጅማሮ ይበልጥ በማላቅ ለማስቀጠል እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቃና ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነም ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸውን ፋይዳም አንስተዋል። • ኢትዮጵያ በማላቦው ጉባዔ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ማላቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉባዔው ከመጋቢት 18 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። • የልማት ሥራዎች ጉብኝት በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎሉና ግንባታቸው እየተፋጠኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት እና የአየር መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ሲሉም በወቅቱ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት የሀገር ሀብት ፈስሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የመገጭ ግድብ ምስክር መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይህ ሞዴል መንደር በአካባቢው ለረጅም ዓመታት የቆየውን የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ጥያቄ በተግባር መልሷል ብለዋል። በሀገራችን ከተማው ብቻ ሳይሆን ገጠሩም እኩል እየተዋበ፣ በልማት እየተገነባና በዕድገት ፍኖት ላይ በጽኑ መሠረት እየተራመደ ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ትልቁ ማሳያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። • "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ በአዲስ አበባ 4ኛው "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይሆን አጋርነትን ነው፤ እርዳታን ሳይሆን ኢንቨስትመንትን ነው! ለባለ ሀብቶች ምቹ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ለችሎታ እና ለዕድል በሯን ወለል አድርጋ መክፈቷንም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን በፍጥነት ወደ ከፍታ እየገሠገሠች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ የዕድገት ጉዞ፤ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያ ለእናንተ ዝግጁ የሆነ፣ በዕድሎችና በስኬቶች የተሞላ ታላቅ የኢንቨስትመንት መሶብ አላት፤ ኑ አብረን እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል! • የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫም፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። በዚህም ከክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀሌ እና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ ሂደቱን በክልሉ ለማካሄድ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው፤ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም አስረድተዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 225
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3838
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2605
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8397
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6887
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች
Apr 5, 2026 4438
በዮሐንስ ደርበው ✍️ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች - የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው። ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እንደመሆኗ ብዙ ናት። ይህን ሁሉም ሀገራት ስለማያገኙት ዕድለኛም ናት፤ የእኛም ስለሆነች መታደል ነው። የተለያየ የኑሮ ዘይቤ፣ ባህል እንዲሁም ሁሉንም የዐየር ፀባይ ዐቅፋለች። ደግሞም ልዩ ልዩ የተፈጥሮ አቀማመጥ በልዩነት የተቸራት። አሥረጂ ማቅረብ ቢያሻ በሀገሪቱ ከፍተኛ ከሆነው ስሜን ተራራዎች እስከ ዝቅተኛው ስፍራ ዳሎል ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ መጥቀስ ሁነኛ ምሥክር ነው። ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ✍️ የተፈጥሮ ችሮታ ለኢትዮጵያ ከብዙ ሥጦታዎቿ መካከል ብሔራዊ ፓርኮችን ብቻ ብናነሳ… የኢትዮጵያ የዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን በጀት መድቦ በቀጥታ በሥሩ 11 ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሁለት የዱር እንስሣት መጠለያዎች ያሥተዳድራል። እነሱም፡- 📌 ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ገራይሌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ሃላይደጌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም 👉 ባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ እና 👉 ሲንቂሌ የቆርኬዎች መጠለያዎች ናቸው። ብሔራዊ ፓርኮቹና የዱር እንስሣት መጠለያዎቹ የሀገሬው ሀብት ናቸውና፤ እየተንከባከቡ መጠቀም ይገባል። ✍️ መንግሥት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ከላይ የተገለጹትን ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችንም፤ ከቤት እንስሣት ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ ከልቅ ግጦሽ እንዲሁም ከሕገ-ወጥ ዐደን ለመጠበቅ መንግሥት ብዙ ገንዘብ ያወጣል። የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ዐቅርቦትንም ያሟላል። ይህም ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ይመሠክራል። በሌላ በኩል የላሊበላ አብያተክርስቲያናት፣ ሶፍዑመር ዋሻን እና የፋሲል አብያተ መንግሥትን ጨምሮ በየክልሎች የሚገኙ ቅርሶችን በመጠገንም እንዲሁ እየተጋ ነው። ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎቹ አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ማድረጉም ትኩረቱን ያሳያል። በዚህ ሂደት በየአካባቢው ፀጋዎችን ዕየለየ በርካታ መዳረሻዎችንና የጎብኝ ማረፊዎችን አልምቷል፤ እያለማም ነው። እነዚህም በኢኮኖሚው ብሎም በሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍ ያለ ሚና እያበረከቱ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት፤ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተሠሩ መዳረሻዎችን ለአብነት ብንጠቅስ፤ ‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች ናቸው። የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው። ኢትዮጵያ ዛሬ ነገንም እየሠራች ነውና፤ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጭውን ትውልድ ባገናዘበ ሁኔታ እየተሳለጡ ነው። በአፍሪካ መዲና በአንድነት እና የወዳጅነት ፓርኮች ጅማሮውን ያደረገው የዘርፉ ልማት፤ ወደ ወንጪ ኢኮቱሪዝም፣ ጎርጎራ፣ ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሸበሌ ሪዞርት፣ ሶፍዑመር ዋሻ፣ ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ የዝሆኖች ዳና ሎጂ፣ የኒዒን ሌ ፓልም ሎጂ ድረስ ወዘተ… ዘልቋል። እንደቀጠለም ነው። እነዚህም ፀጋን ለይቶ ወደ ሃብት በመቀየር ሂደት በመንግሥት ብርታት የለሙ መዳረሻዎች ናቸው። መንግሥት ነባር መዳረሻዎችን በመጠገንና በማደሥ፤ አዳዲስ መዳረሻ በመገንባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም አልሠሠተም፤ ብዙ እየሠጠ ነው። ✍️ ከቱሪዝም ዘርፍ አንጻር የሕብረተሰቡ ሚና ቱሪዝም በተፈጥሮው ከበርካታ ጉዳዮች ጋር ይተሣሠራል። በእጅጉ ሰላም ይሻል፤ የሰላም ባለቤት ደግሞ ሕዝቡ ነው። ዘርፉ የቅርሶችንና መዳረሻዎችን ልማትና እንክብካቤም ይሻል። ለዘርፉ የሚሰጥ ትኩረት ሀገርንም፤ ሕዝብንም ይጠቅማል፤ ጥቅሙ ከዕለት ጉርስ እስከ ጥሪት ይዘልቃል። በዚህ ሂደት ሕዝቡ በየአካባቢው ያሉ ብሔራዊ ፓርኮችን፣ ቅርሶችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን የኔ ብሎ መጠበቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ፡- ብሔራዊ ፓርክ ወይም በመዳረሻ ላይ ጉዳት ቢደርስ በቀጥታ ተጎጂው የአካባቢው ነዋሪ ነው። ምክንያቱም ቱሪስት ካልሄደና ገቢ ካልተገኘ ገቢ ይደርቃልና።
የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስን የታደገው ሀገራዊ ለውጥ
Apr 4, 2026 305
የስልጣኔ መነሻ የጥበብ መፍለቂያ የሆነችው የምስራቋ ፈርጥ ሀረር የንግድ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ትስስር ማዕከል ሆና በትውልድ ቅብብሎሽ ከአንድ ሺህ አመታት በላይ የተሻገረች እድሜ ጠገብ ከተማ ነች። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርትና የንግድ ማዕከል የነበረችው ከተማዋ በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ እንዲሁም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶችን የያዘች ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ነች። ከእነዚህ ቅርሶች መካከል ጥንታዊ የስነ-ህንፃ የጥበብ፣ የከተማ ፕላን፣ ባህላዊ የመሬት አጠቃቀም፤ አካባቢያዊ መስተጋብርና የስልጠኔ መገለጫ በሚል እኤአ በ2006 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በአለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ቅርስ ይጠቀሳል፡፡ ቅርሱ ምንም እንኳን በኪነ ህንፃ ጥበብ በላቁ በአርቆ አሳቢ አባቶች እንዳይፈርስና ሚዛኑን ጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ በተመረጠ ድንጋይ እና አፈር በልዩ ጥበብ የተገነባ ቢሆንም በጥበቃና እንክብካቤ ጉድለት ምክንያት ከግማሽ ምዕተ አመታት በላይ እድሜን ባስቆጠረው ቅርስ ላይ አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል። በቅርሱ ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍሎች የህገ-ወጥ ግንባታዎች መበራከትና በሌሎች ምክንያቶች በደረሰበት ጉዳት የጥንት ስልጣኔ ምልክት የሆነው አለም አቀፉ የጀጎል ቅርስ ከዩኔስኮ የአለም ቅርስነት እስከመሰረዝ የደረሰ አደጋ ተደቅኖበት ነበር። ሆኖም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአዲስ እሳቤ፤ በተደመረ አቅምና በላቀ ቁርጠኝነት፤ ህዝብን በማሳተፍ ከመንግስት ምንም አይነት በጀት ሳይመደብለት ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማልማት ተቻለ። አሁን ላይ እነኛ በሸራና በጨርቅ በተሰሩ ህገወጥ ግንባታዎች ተወሮ የነበረው 3ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጀጎል ግንብ ዙሪያ በአበቦችና ቅርሱን በሚያስውቡ ስራዎች ደምቀዋል። በዚህም አባቶች ከዘመኑ ቀድመው ዛሬም ድረስ ግርምትን በሚያጭር ጥበብ አንፀው ያኖሩት ይህንን የሀገር ሀብት በመታደግ ትውልዱን ከታሪክ ተወቃሽነት ወደ ዳግም ታሪክ ሰሪነት እንዲሸጋገር ማድረግ ተችሏል። ስራውም የትላንትን መሰረት ሳያናጋ፤ የቀድሞ አባቶችን ጥበብና ስልጣኔ ሳይጋፋና ሳይዘነጋ ጥንታዊውን ከዘመናዊ ጋር አዋህዶ ቅርስ መገኛ ለሆኑ ሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት በሚሆን ደረጃ አስደናቂ ስራ ተከናወነ። የአካባቢውን ሀብትና እውቀት በመጠቀም እውን የተደረገው ይህ ስራ በእያንዳንዱ የሀረሪ ጥንታዊ ቤቶች በሚገኙ የታሪክ አሻራዎችና የባህል መገለጫዎች እንዲደምቅም ሆኗል። ይህ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ቅርሱን ከአደጋ ከመታደግ ባለፈ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከግለሰብ እስከ ማህበራትና የዳያስፖራ አባላት ድረስ ሁሉም በያገባኛል ስሜት አሻራውን ያኖረበት ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት ነው። ይህም በቅርሱ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲጎለብት በማድረግ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ያስቻለና ቀደም ሲል የነበሩ የግለኝነት አስተሳሰቦችን በመቅረፍ የወል እሳቤ እውን የሆነበት ፕሮጀክት ሆኖ ታይቷል። ዛሬ ላይ እነኛ የቆሻሻ መጣያ የነበሩ እና በአካባቢው ለማለፍ ከባድ የነበሩ የጀጎል መንገዶች ፀድተው ውብ ሆነዋል። ይዘታቸውን ለቀው የነበሩ ቅርሶችም የአለም ቅርስነት ክብርና መስፈርትን በሚመጥን ደረጃ ታድሰዋል። ዛሬ የጀጎል ነዋሪ እንደቀድሞ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ሳይሆን መኖርን የሚመርጥባት የወጣውም መመለስን የሚመኝባት ምቹ አካባቢ ሆናለች። የመቻል ምልክት የትብብር ውጤትና የአብሮነት ጉልበት በተግባር የታየበት የጁገል መልሶ ልማት ጥንታውን መንደር ለነዋሪዎች ምቹ ለጎብኚዎች ተመራጭ የጉብኝት ስፍራ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል። በለውጡ መንግስት በአዲስ መልክና ቀለም የተዋበው ጀጎል የሀረርን ቀደምት ስልጣኔ እየመሰከረ የሀገርንም ገፅታ እየገነባ ይገኛል።