ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል

አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 1 / 2018 (ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ (Inter-Continental Dialogue among Political Parties - ICDPP) ላይ ለመሳተፍ ሴኡል፣ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል።


 

ከሴፕቴምበር 6 እስከ 9 ቀን 2026 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ፣ ኤሽያ፣ አውሮፓ፣ ላቲን አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የተወጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአሁን ወቅት የተሳታፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ መርሃ ግብር እየተደረገ ይገኛል።

ጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የጋራ ግንዛቤ እና ትብብር ማጠናከርን ዋና አላማው አድርጎ የተነሳ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም