ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና ከኤግሎንስ ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና የቻዱ ኤግሎንስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ጨዋታው ማምሻውን በኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ስታዲየም ተካሄዷል።

ሲዳማ ቡና ግብ ማስቆጠር ባይችልም መልካም የሚባል እንቅስቃሴ አድርጓል።


የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል እና ከብሩንዲው አይግል ኑዋር አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ሁለቱም ክለቦች በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሲወዳደሩ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም