አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን አገኘ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁል ሲቲ እና አስቶንቪላ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በኤምኬ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አስቶንቪላ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ባለሜዳው ሁል ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ የተሻለ ነበር።
አስቶንቪላ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ በሰባት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ በሊጉ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል።
አስቶንቪላ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘ ሲሆን 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። እስከ አሁን በሊጉ ምንም ግብ አላስቆጠረም።
በአራተኛ ሳምንት ሁል ሲቲ ከቼልሲ፣ አስቶንቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ዛሬ በሊጉ ከተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች መካከል አምስቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።