አርእስተ ዜና
የ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሚያጸና መልኩ ለማሳካት የአመራሩ ትጋትና የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
Jul 18, 2025 66
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-የ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሚያጸና መልኩ ለማሳካት የአመራሩ ትጋትና የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ። የመንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት አቅድ የግምገማ መድረክ በፌደራል ተቋማት አመራሮች ደረጃ ተካሂዷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በዚሁ ወቅት፥ በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የላቀ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል። በግብርናው ዘርፍ፣ በማዕድን እና በቡና ወጪ ንግድ፣ በተኪ ምርት እና በሌሎች ዘርፎች በታሪክ ከፍተኛ ውጤት መምጣቱን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅም የኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ድል መሆኑን ተናግረዋል። የተመዘገቡ ስኬቶች በቅንጅት የመጡ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ሀገርና ህዝብን የሚያኮሩ እና ለአዳዲስ ድል እንድንነሳ ስንቅ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ አስደናቂ እመርታዎች መመዝገባቸውን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅም በራስ አቅም ብሔራዊ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ምሳሌ፣ የጀግንነትና የወል ትርክት አምድ፣ የኢትዮጵያውያን የይቻላል ትጋት ማሳያ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ በአምራች ኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ልህቀት ወሳኝ ስኬቶች መጥተዋል ነው ያሉት። መንግሥት ጥራት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማስቀጠል ለአምራች ዘርፉ የፋይናንስ አቅርቦትን ማጠናከሩንም አውስተዋል። በቀጣይም ሙስናን የመከላከል፣ ዘላቂ ሰላምን የማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል። በኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎችን በማድረግ ለውጥ ቢመጣም በፌደራልና በክልሎች መካከል የተናበበ አሰራርና አፈጻጸም ባለመኖሩ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)፥ የዘንድሮው ሀገራዊ እቅድ የ2017 በጀት ዓመት ስኬቶችን፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ተሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ጥራት ያለው ስኬት ለማስመዝገብ መታቀዱንም ጠቁመዋል። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግም የፌደራል ተቋማትና ክልሎች ወጥ የሆነ አሰራርን እንዲተገብሩና የተሳለጠ ምህዳር እንዲፈጥሩ ይደረጋል ነው ያሉት። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ በሰጡት ማጠቃለያ፥ መንግሥት የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ በልማት እያጸና እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ለዚህም በ2018 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ አዳዲስ እመርታዎችን ለማስመዝገብ ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል ነው ያሉት። ሀገራዊ ዕቅዱ ታላላቅ ስኬቶችን ያለመ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ በከፍታ ለማስቀጠል የአመራሩ የሌት ተቀን ትጋት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። በእቅዱ ላይ መግባባት ፈጥሮ በአርዓያነት መስራት፣ የመንግሥት ሰራተኛውን፣ የግሉን ዘርፍ እና የህዝቡን ተሳትፎ በጉልህ በማሳደግ መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል። በሌላ በኩል ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለወል ትርክት መጠናከር ሁሉም መስራት አለበት ነው ያሉት።
በክልሉ የንግዱ ማህበረሰብ የዘርፉን ሥራ በፍትሃዊነት በማሳለጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን - እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Jul 18, 2025 63
ሆስዕና ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግዱ ማህበረሰብ የዘርፉን ሥራ በፍትሃዊነት በማሳለጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የ2017 ማጠቃለያ ጉባኤና የንግድ ሳምንት ባዛር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል ፡፡   በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የሸማቹን ፍላጎትና የአምራቹን አቅርቦት በማጣጣም የንግዱን ሥርዓት ፍትሐዊና የተሳለጠ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን ለማስፈን ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና እጥረትን ለማስቀረት በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ፡፡ የንግዱን ማህበረሰብ ችግር ለይቶ ለመፍታትና ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የንግዱ ማህበረሰብም ህብረት በመፍጠር ለትላልቅ ሥራዎች ልምድ ማዳበር እንዳለባቸውን ጠቁመዋል፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው፤ የንግድ ሥርዓቱን ሕጋዊና ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ የቁጥጥር ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።   በዚህም ባለፈው የበጀት ዓመት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አመልክተው፤ ‎ለአብነት በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ300 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር መዋሉንና ህግን የተላለፉ ማደያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። ‎አምራችና ሸማችን በማቀራረብ ገበያን በማረጋጋትና ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓትን በመዘርጋትም እንዲሁ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ ‎በተለይ በከተሞች የሰንበት ገበያዎችን ቁጥራቸውን በማሳደግ አምራቹና ሸማቹ በቀጥታ እንዲገናኙ ማድረግ እንደተቻለ አብራርተዋል ። ከባዛሩ ተሳታፊዎች መካከል ከሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ የመጡት አቶ አብደላ ሀሰን፤ በተሰማሩበት የንብ ማነብ ሥራ የሚያገኙትን የማር ምርት በራሳቸው ሱቅና ባዛሮች ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርቡ ጠቅሰው፤ በተለይ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ከተጀመረ በኋላ ሥራቸውን በስፋትና በዘመናዊ መንገድ መከወን እንደቻሉ ተናግረዋል።   ‎ዘንድሮ ብቻ ሰብስበው ባቀረቡት የማር ምርት 950 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውንም አውስተዋል። ‎በጉራጌ ዞን አድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ግብይት ክፍል አስተባባሪ ወይዘሮ ዐባይነሽ ኪሮስ ፤ ዩኒየኑ ከአባላት ግብዐት በመሰብሰብ የተጣራ የኑግ ዘይት እያመረተ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ጠቁመው፤ የአካባቢውን ገበያ በማረጋጋትም አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሚገኝ አብራርተዋል።   በመርሀ ግብሩ ላይ የተቋማት አመራሮችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉ ሲሆን፤ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሴክተሩ አደረጃጀቶች የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ህዝበ ሙስሊሙ እድሉን ሊጠቀም ይገባል
Jul 18, 2025 61
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ)፡- ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ መሪዎቹን የመወሰን እድሉን እንዲጠቀም የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ በድሩ ኑሩ፤ የመጅሊስ ምርጫን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ኡስታዝ በድሩ ኑሩ፤ በመግለጫቸው ቦርዱ ምርጫውን የተሳካ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱን አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የመወሰን እድሉን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል። እጩ የመለየትና ጥቆማ የመስጠቱ ሂደት ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን የኡለማዎች ምርጫ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል ብለዋል። በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ በንቃት በመሳተፍ ሊመሩ የሚችሉ በቂ ልምድና እውቀት ያላቸውን አመራሮች እንዲመርጥ መልዕክት አስተላልፈዋል። በምክር ቤቱ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ፀሐፊ መሃዲ ሸምሱ፤ በክልሉ የመጅሊስ ምርጫ ምዝገባ ከተጀመረ ወዲህ በርካቶች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን አስታውሰው በቀሩት ጥቂት ቀናት ሌሎችም ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም እድሜው 18 ዓመት የሞላው ሙስሊም መመዝገብ እንደሚችል ተመልክቷል።  
የአካል ጉዳተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ረቂቅ የፖሊሲ ሰነድ ተዘጋጅቷል
Jul 18, 2025 57
አዳማ ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አካታች ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ የፖሊሲ ሠነድ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ረቂቅ ፖሊሲ ሠነድ ዝግጅት ግብዓት ለማሰባሰብ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ዛሬ በአዳማ ተካሄዷል። በወቅቱም የሚኒስቴሩ የህግ አማካሪ አቶ ደረጄ ተግበሉ እንደገለፁት፤ የአካል ጉዳተኞችን መሰረታዊ መብቶች በማስከበርና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። በመሆኑም የፖሊሲ ዝግጅት ማድረግ ማስፈለጉንና ዋና ዓላማውም የአካል ጉዳተኞችን የእኩል እድል ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ የፖሊሲ እርምጃዎችን ለመውሰድ መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዱ አካል ጉዳተኞች በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልፀው ለ5ኛ ጊዜ የግብዓት ማሰባሰብ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄዷል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማህበራዊ ልማት፣ የባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) መንግስት አካል ጉዳተኞች የልማቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።   የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው ሀገሪቱ እስካሁን የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ፖሊሲ ስለሌላት የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስከበር ሳይቻል መቆየቱን አስታውሰዋል። መንግስት የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲ ለማውጣት ቁርጠኛ አቋም መያዙን አድንቀው ፖሊሲው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚያስገኝም አመልክተዋል።   በመድረኩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ እንዲሁም የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የሚታይ

መገናኛ ብዙሃን የጋራ ትርክትን ለማስረጽ የጀመሩትን ውጤታማ ተግባራት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Jul 18, 2025 90
  አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-መገናኛ ብዙሃን የጋራ ትርክትን ለማስረጽ የጀመሩትን ውጤታማ ተግባራትን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከተቋሙ ባለሞያዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ኢዜአ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀገራዊ አጀንዳዎችና ለሪፎርም ስራዎች ስኬት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና እያደረገች ላለችው ስኬታማ ጉዞ መሳለጥ፣ የህብረ-ብሔራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ትርክትን ብሎም የሀገረ መንግስት ግንባታን ከማስረጽ አኳያ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮርም በኢኮኖሚ፣ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ዲፕሎማሲና ዘላቂ የሰላም ግንባታ ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በርካታ ስራዎችን መስራቱን ተናግረዋል፡፡ መገናኛ ብዙሃን መንግስት ትኩረት ያደረገባቸውን ትላልቅ ጉዳዮች ማጉላት እንዳለባቸው ጠቁመው፤የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚመረቁበት ዓመት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሀገራዊ ምርጫ፣ወሳኝ የሰላም ጉዳዮች፣ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዕድገት የሚጠበቅበት ብሎም ሌሎችም ተግባራት የሚከናወኑበት በጀት አመት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን የምታረጋግጥበት ዓመት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቢቂላ፤ መገናኛ ብዙሃንም እነዚህን አጀንዳዎች ጨምሮ ሌሎችንም ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ አባል ሚሊዮን ተረፈ በበኩላቸው፥ ኢዜአ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማስረጽ ረገድ እምርታ ያላቸው ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።   ተቋሙ ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ሀገራዊ ተልእኮውን ይበልጥ በብቃት ለመወጣት መስራት እንዳለበትም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፤ ኢዜአ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡   ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ቀጣናዊና አካባቢያዊ ጉዳዮችና ሀገራዊ ምክክር ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎችን ለማስረጽ በእቅድ ከያዛቸው ዋና ዋና የትኩረት መስኮች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ፣የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት፣ዲፕሎማሲና ሌሎች ሀገራዊ አጀንዳዎችን በዲጂታል አማራጮችና የተለያዩ የይዘት ስራዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በጥልቀት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በዲጂታል አማራጮች በተለያዩ ቋንቋዎች የገጽታ ግንባታ ስራዎችን መሥራት ከዋነኛ የትኩረት መስኮች መካከል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማጎልበት ያስችላል-በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Jul 18, 2025 57
  አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እውቀትን በማስፋፋት፣የግለሰቦችንና የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበት ቁልፍ ዓላማው መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር "በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ረቂቅ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ "በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተገኙ ስኬቶች ላይ ተመስርቶ አዳዲስ የዲጂታል እድገቶች ላይ ያተኮረ ነው። ስትራቴጂው አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ስማርት ከተሞችን፣ ድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ ፣ ዲጂታል ሉዓላዊነትን የመሳሰሉ ጽንሰ ሃሳቦችን በማካተት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። ስትራቴጂው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለሚፈጥሩ የስራ እድሎች፣ አካታች እና ፍትሃዊ ልማትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዓላማ ማድረጉንም ተናግረዋል። የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋት እና የተቋም አቅምን በመገንባት የግለሰቦችን እንዲሁም የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበት የስትራቴጂው ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን፣ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ተደራሽነትን ማሳደግ እና ኢትዮጵያን ለዲጂታል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ማድረግ ከስትራቴጂው ዓላማዎች መካከል እንደሚካተቱ አክለዋል። አገራዊ ዳታዎችንና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎችን እና አገራዊ የልማት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን የዲጂታል ልማት ምሰሶዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችን የለየ መሆኑንም አብራርተዋል። የአይሲቲ ማህበር ፕሬዝዳንት ይልቃል አባተ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ስትራቴጂው ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ እያከናወነች ያለውን ስራ በሰፊው ለመተግበር የሚያስችል ነው።   በተጨማሪም ዜጎች በዲጂታል ዓለም ተፎካካሪ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አክለዋል። ስትራቴጂው ኢትዮጵያን የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ እንደሚያስችል የተናገሩት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢትዮጵያ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ባህሩ ዘይኑ ናቸው።  
በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 18, 2025 54
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ከለውጡ ወዲህ በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።   ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት፤ በሁለንተናዊ ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ መገንባት ይገባል ብለዋል። ይህን ከማረጋገጥ አኳያ ጥራት ያለው ትምህርት አይነተኛ ሚና እንደሚያበረክት ገልጸዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ አመታት በትምህርት ዘርፍ ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገብ መቻሉንም አመላክተዋል፡፡ በመዲናዋ ከለውጡ ወዲህ 110 የሚሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ 30 ሺህ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች፣ 334 የትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትና ሌሎች የትምህርት መሰረተ ልማቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመትም 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለምረቃ መብቃታቸውን ተናግረዋል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል 14 የሚሆኑት አዳዲስ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በእርጅና ለመማር ማስተማር ምቹ ያልነበሩና የማስፋፊያ ግንባታ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡   ሁለንተናዊ ብልጽግናን ያለትውልድ ግንባታ ማሰብ አይቻልም ያሉት ከንቲባዋ፤ በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በተሰጠው ትኩረት የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አመላክተው፤ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ትምህርት የአገራት እድገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ በዚህ መነሻነት ከተማ አስተዳደሩ ያከናወናቸው የትምህርት ማሻሻያ ርምጃዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል።   ፕሮጀክቶቹ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነት ከማረጋገጥ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚያበረክቱ ነው የገለጹት። በምርቃት ስነ ስርዓቱ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የባህል ቡድኑ ወደተለያዩ የአለም ሀገራት የሚያደርገው ጉዞ የኢትዮጵያን ህያው ባህል በማስተዋወቅ አዲስ ምእራፍ የሚከፍት ነው
Jul 18, 2025 58
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):- የባህል ቡድኑ ወደተለያዩ የአለም ሀገራት የሚያደርገው ጉዞ የኢትዮጵያን ህያው ባህል በማስተዋወቅ አዲስ ምእራፍ የሚከፍት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ። "ኪን ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ብስራት" የተሰኘ የኢትዮጵያን ባህል ለአለም የሚያስተዋውቅ የባህል ቡድን ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራት ጉዞ እንደሚያደርግም ተገልጿል ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እና የሻኩራ ፕሮዳክሽን ስራ አስኪያጅ አርቲስት ካሙዙ ካሳ ሁነቱን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ሁነቱ የኢትዮጵያን ህያው ባህል ለአለም ህዝብ በማስተዋወቅ አዲስ ምእራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል። ኪነጥበብ የአንድን ሀገር እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው፤ ሁነቱ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው የኢትዮጵያን የባህል ዲፕሎማሲ ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም ጠቁመዋል። መንግስት ኪነጥበብ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ሰፋፊ ስራ መስራቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት እንዲሁም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አመላክተዋል። የጉዞው የመጀመሪያ መዳረሻ ቻይና መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ወደተለያዩ ሀገራት ጉዞውን እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በርካታ የኪነጥበብ ሀብት ያላት ሀገር ናት ብለዋል። ሁነቱ የኢትዮጵያን ባህል በአለም አቀፍ ደረጃ በጉልህ የሚያስተዋውቅ መሆኑን በመግለጽ። በሁነቱ የባህል ትርኢት፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች ትርኢት እንዲሁም ከሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት መሆኑን ተናግረዋል። ላለፉት አራት ወራት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ መቆየቱን የገለጹት ደግሞ የሻኩራ ፕሮዳክሽን ስራ አስኪያጅ አርቲስት ካሙዙ ካሳ ናቸው። በሁነቱ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ባህል፣ አመጋገብና ባህላዊ አለባበሶች እንደሚቀርቡበት ተናግረዋል። የባህል ቡድኑ እሁድ ሀምሌ 13 ጉዞውን ወደ ቻይና በማድረግ እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
መገናኛ ብዙሃን የጋራ ትርክትን ለማስረጽ የጀመሩትን ውጤታማ ተግባራት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Jul 18, 2025 90
  አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-መገናኛ ብዙሃን የጋራ ትርክትን ለማስረጽ የጀመሩትን ውጤታማ ተግባራትን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከተቋሙ ባለሞያዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ኢዜአ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀገራዊ አጀንዳዎችና ለሪፎርም ስራዎች ስኬት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና እያደረገች ላለችው ስኬታማ ጉዞ መሳለጥ፣ የህብረ-ብሔራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ትርክትን ብሎም የሀገረ መንግስት ግንባታን ከማስረጽ አኳያ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮርም በኢኮኖሚ፣ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ዲፕሎማሲና ዘላቂ የሰላም ግንባታ ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በርካታ ስራዎችን መስራቱን ተናግረዋል፡፡ መገናኛ ብዙሃን መንግስት ትኩረት ያደረገባቸውን ትላልቅ ጉዳዮች ማጉላት እንዳለባቸው ጠቁመው፤የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚመረቁበት ዓመት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሀገራዊ ምርጫ፣ወሳኝ የሰላም ጉዳዮች፣ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዕድገት የሚጠበቅበት ብሎም ሌሎችም ተግባራት የሚከናወኑበት በጀት አመት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን የምታረጋግጥበት ዓመት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቢቂላ፤ መገናኛ ብዙሃንም እነዚህን አጀንዳዎች ጨምሮ ሌሎችንም ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ አባል ሚሊዮን ተረፈ በበኩላቸው፥ ኢዜአ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማስረጽ ረገድ እምርታ ያላቸው ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።   ተቋሙ ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ሀገራዊ ተልእኮውን ይበልጥ በብቃት ለመወጣት መስራት እንዳለበትም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፤ ኢዜአ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡   ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ቀጣናዊና አካባቢያዊ ጉዳዮችና ሀገራዊ ምክክር ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎችን ለማስረጽ በእቅድ ከያዛቸው ዋና ዋና የትኩረት መስኮች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ፣የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት፣ዲፕሎማሲና ሌሎች ሀገራዊ አጀንዳዎችን በዲጂታል አማራጮችና የተለያዩ የይዘት ስራዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በጥልቀት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በዲጂታል አማራጮች በተለያዩ ቋንቋዎች የገጽታ ግንባታ ስራዎችን መሥራት ከዋነኛ የትኩረት መስኮች መካከል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ ይገኛል
Jul 18, 2025 95
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):- በሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ተሰጥቷል። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በአገራዊ ምክክር ሂደቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ለማሳተፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለዚህም የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር በሕግ ጥላ ስር ያሉ ዜጎች በምክክር ሂደቱ ተሳታፊ መሆን በሚችሉበት ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱም በህግ ጥላ ስር ያሉ ዜጎችን ማሳተፍ ገንቢ ሚና እንዳለው የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል። በቀጣይም በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤት ያሉ ዜጎችን ተሳታፊ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን አቶ ጥበቡ በመግለጫቸው አብራርተዋል። በዚህም በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አብዛኞቹ በአገራዊ ምክክር ሂደቱ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል። እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፓርቲዎች ቅደመ ሁኔታ በማስቀመጥ በምክክር ሂደቱ ከመሳተፍ መታቀባቸውን ተከትሎ ኮሚሽኑ ውይይት ማድረጉን ጠቅሰው፤ በዚህም ገንቢ ሀሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። በምክክሩ ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳተፉ የቆዩ ፓርቲዎችን ወደ ምክክሩ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ኮሚሽኑ በምክክሩ የሴቶች ተሳትፎን ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህንንም ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን አስረድተዋል። ኮሚሽኑ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ጋር ባደረገው ውይይት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸውን እንዲወጡ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ጠቅሰዋል።
የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔ ነገ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል
Jul 18, 2025 62
አዳማ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለፀ። የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱራህማን ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳመላከቱት በጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ። የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የጨፌው ፅህፈት ቤት ሥራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንደሚፀድቅ አፈ ጉባዔዋ ገልጸዋል። በጉባኤው የሰላም እና የፀጥታ ጉዳይ፣ የልማት ሥራዎች ክንውን፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ዋነኛ የትኩረት ጉዳዮች መሆናቸውንም አፈጉባዔዋ አስታውቀዋል። እንዲሁም የኦዲት ግኝት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዓመቱ እቅድና አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት አስታውቀዋል። የጨፌው ቋሚ ኮሚቴዎች የድጋፍና ክትትል አፈጻጸም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል። በተጨማሪም ጉባዔው በሁለት ቀናት ውሎው የ2018 የክልሉ በጀት እና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ወይዘሮ ሰአዳ ተናግረዋል።
የብሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ የሳሄል ቀጣና ልዩ ልዑክ ሆነው ተሾሙ
Jul 17, 2025 123
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆኣኦ ሎሬንቾ የብሩንዲውን ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬን የሳሄል ቀጣና ልዩ ልዑክ ሆነው እንዲያገለግሉ መርጠዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ህብረት የወጣቶች፣ ሰላም እና ደህንነት አጀንዳ ልዩ አስተባባሪም ናቸው። ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የሳሄል ቀጣና የደህንነትና ሰብዓዊ ፈተናዎች የመፍታት የፖለቲካ ተልዕኮን መቀበላቸውን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል። ልዩ ልዑክ ሆነው የተመረጡት ፕሬዝዳንቱ ህብረቱ በሳሄል ቀጣና ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ በአዲስ መልክ የጀመራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ይመራሉ። በተሰጣቸው ኃላፊነት ከመንግስታት፣ ቀጣናዊ ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይቶች እንዲደረጉ፣ መግባባት እንዲፈጠርና ዘላቂ ሰላምና ደህንነት የሚያመጡ ስትራቴጂዎችን የመደገፍ እና የመተግበር ስራዎችን ያከናውናሉ። የልዩ ልዑኩ ሚና ውስብስቡን የሳሄል ቀጣና ቀውሶች ሁሉን በማሳተፍ እና የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ እንደሆነ ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ጆኣኦ ሎሬንቾ የብሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ የካበተ የፖለቲካ ልምድ ያላቸውና ጠንካራ የፓንአፍሪካ ተሟጋች እንደሆኑ ገልጸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጡ ሙሉ እምነቴ ነው ብለዋል። የልዩ ልዑኩ ሹመት የአፍሪካ ህብረት ለቀጣናዊ ትስስር፣ ለሰላም ግንባታና በአፍሪካ የተኩስ ድምጽ እንዳይሰማ የማድረግ ትልቅ ራዕይ እንዲሳካ ያለውን ጽኑ አቋም እንደሚያሳይም ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ ሁሉም የአፍሪካ ህብረት አደረጃጀቶች፣ አባል ሀገራት እና የልማት አጋሮች የልዩ ልዑኩን የሳሄል ቀጣና ስራ እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን የፖለቲካ ተሳትፎ ያሳድጋል
Jul 17, 2025 144
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፦ የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን የፖለቲካ ተሳትፎ እንደሚያሳድግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ዛሬ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ማሻሻያ የተደረገበትን የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን አፅድቋል። በዚሁ አዋጅ 26 አንቀፆች እንደተሻሻሉ የተገለጸ ሲሆን፥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።   በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ፥ የአዋጁን የማሻሻያ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል። በዚሁ ጊዜ አዋጁ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አሳታፊ፣ ዴሞክራሲያዊና ግልፅ በሆነ መልኩ ማካሄድ እንዲያስችል መሻሻሉን አንስተዋል። ማሻሻያ ከተደረገባቸው አንቀፆች መካከል የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች የምርጫ ተሳትፎ፣ የቅሬታ አቀራረብ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች የፋይናንስ ምንጭና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ይገኙበታል ብለዋል።   የምክር ቤቱ አባላትም የማሻሻያ አዋጁ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን የፖለቲካ ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ የምርጫ ስራውን በቴክኖሎጂ ለማገዝ እንደሚያስችል አንስተዋል። ይሁንና በማሻሻያ አዋጁ ላይ በምርጫ ጣቢያዎች የነበረው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንዲቀር መደረጉ ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እውነቱ አለነ በሰጡት ምላሽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባሉት ከ50ሺህ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን ማቋቋም አስፈላጊነቱ እምብዛም መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም ቅሬታ ከምርጫ ክልል ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የሚቀርቡበት አማራጭ አዋጭ መሆኑ እንደታመነበት አስረድተዋል።   በሌላ በኩል የማሻሻያ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመሰራረትን በተመለከተ ማሻሻያ ለምን እንዳልተደረገበትም የምክር ቤቱ አባላት አስንተዋል። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ በሰጡት ምላሽም የፖለቲካ ፓርቲዎች በፈለጉት መንገድ የመደራጀት መብት ሕገ-መንግስታዊ መሆኑን አብራርተዋል። የተሻሻለው አዋጅ የምርጫ ሥራን በተሻለ መልኩ መምራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን በመግለጽ። ውስብስብ የሆነውን የምርጫ ሂደት በቴክኖሎጂ በማገዝ ግልፅ፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ ምርጫ ማካሄድ እንደሚያስችልም አስረድተዋል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ማሻሻያ አዋጅን በሁለት ተቃውሞ በአራት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ ለማፋጠን ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል - ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)
Jul 17, 2025 195
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ ለማፋጠን በጥናት ላይ የተመሰረተና የተደራጀ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ገለፁ። የለውጡ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች አካታችና ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር ስር እየሰደደ፥ ሀገራዊ ኢኮኖሚውም በከፍተኛ ሁኔታ እያንሰራራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ለኢዜአ አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች በኢትዮጵያ ምህዳሩ እየሰፋ እና እየተረጋጋ የመጣ አካታች የፖለቲካ ስርዓት እየተገነባ ነው። የሀገርን ህልውና የሚፈታተኑ የፍትሐዊነትና የእኩልነት አለመኖር ስብራቶችን በመጠገን፥ ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ አንድነት አስተማማኝ መሰረት መጣሉን አንስተዋል። በተቃውሞ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ በመንግስት መዋቅር ገብተው እንዲሰሩ መደረጉ፣ በሀገራዊ ምክክር ችግሮችን ለመፍታት ወደ ሥራ መገባቱና የሽግግር ፍትሕ ለዘላቂ ሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።   በሌላ በኩል ስርዓታዊ ልህቀት ማምጣት የሚያስችሉ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲ እና የጸጥታ ተቋማት መገንባታቸውንም ነው ሚኒስትሩ ያነሱት። የለውጡ መንግሥት በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይልና በአመራር ጠንካራ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት መገንባቱ፥ ከየትኛውም አቅጣጫ በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት በሩቁ የሚያስቀር አስተማማኝ አቅም እንዲፈጠር አስችሏል ብለዋል። በሀገረ መንግስቱ ላይ አደጋ ደቅነው የነበሩ ቡድኖች መንግሥት በፈጠረው አቅም፣ ዓለም አቀፍ ሁኔታው በመቀየሩና በራሳቸው የተሳሳተ አካሄድ ከነበሩበት እብሪት ወርደው ህልውናቸው ወደማክተም እየሄደ ነው ሲሉም ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያን የጸጥታ ኃይሎች የሚገዳደር ኃይል የለም ነው ያሉት። መንግሥት ለሀሳብ የበላይነት ዋጋ በመስጠቱ፣ የወል ትርክትን እየገነባ በመሆኑ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርምን በመተግበሩ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እየፈታ በመሆኑና ህግን በማስከበሩ ተጨባጭ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሌብነትና ብልሹ አሰራርን የማይሸከም ስርዓት በመገንባት የመንግስት አገልግሎትን የማዘመን ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ሆና በልማት ስራዎች ስኬት ማስመዝገቧን ገልጸው፥ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችና በብዝሃ ዘርፍ ልማት ሀገራዊ ኢኮኖሚው በአካታችነት እያንሰራራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። መንግሥት በቀጣይ ኢ-ተገማችና ቅፅበታዊ ዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገና ችግሮችን በመቅረፍ ድሎችን ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ሀገርን ከማንሰራራት ወደ ተሟላ ብልጽግና ለማሸጋገርም በተለወጠ ሀገራዊ ዕይታ ለአዳዲስ እመርታዎች መዘጋጀቱንም አረጋግጠዋል። መገናኛ ብዙሃንም አካታች የፖለቲካ ስርዓቱ ይበልጥ እንዲጎለብት፣ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ እንዲጠናከር በጥናትና በተደራጀ መረጃ ተደራሽነት አጋዥ ሚናቸውን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል።
በክልሉ እንደሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ አበረታችሥራዎች እየተከናወኑ ነው - አቶ አደም ፋራህ
Jul 17, 2025 141
ሐረር፤ሐምሌ 10/2017 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል እንደሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በሐረሪ ክልል በዘጠኙም ወረዳዎች የተገነቡ የፓርቲ ጽሕፈት ቤቶችን መርቀው ከፍተዋል።   በዚህ ወቅት አቶ አደም ፋራህ፤ ከለውጡ ወዲህ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ እድገት መመዝገብ እንደተቻለ መመልከታቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም በክልሉ እንደሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም የአመራሩና የህዝብ አንድነት ወሳኝ ሚና እያበረከተ መሆኑን አመላክተዋል። በዘጠኙም ወረዳዎች ወጪ ቆጣቢ መሰረት ባደረገ መልኩ የተገነቡ ህንፃዎች የፓርቲውን የፕሮጀክት አመራር ስርዓትን በተግባር የገለጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው፤ እንደሀገር የተመዘገቡ ታላላቅ ድሎች የብልፅግና ፓርቲ ፖሊሲዎች ትክክለኛነትና ህዝባዊ ቅቡልነቶች ማሳያ መሆናቸውን አንስተዋል። እንደ ክልልም አደጋ ውስጥ የነበረው በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ በመደመር እሳቤና በአመራር አንድነትና ቁጭት የተሰራውንም ጠቅሰዋል።   የሕዝቡ የልማት ጥያቄ በመመለስ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውና የኮሪደር ልማትም አበረታች መሆኑን አንስተዋል። በምረቃ መርሃ ግብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።  
የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገና የታክስ መሰረትን የሚያሰፋ ነው-ምክር ቤቱ
Jul 17, 2025 193
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2017 (ኢዜአ)፦ የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገና የታክስ መሰረትን የሚያሰፋ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን አፅድቋል። በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ የማሻሻያ አዋጁን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል። ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የገቢ ግብር አዋጅ ዲጂታል ኢኮኖሚውን ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን አውስተዋል። በአሁኑ ወቅት በአዋጁ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ከዲጂታል ኢኮኖሚው ጋር የተጣጣመ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።   የታክስ መሰረትን በማስፋት የመንግስትን የገቢ መሰብሰብ አቅም ለማሳደግ እንዲሁም የታክስ ማጭበርበርን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባላት የማሻሻያ አዋጁን በተመለከተ ግልፅ ያልሆኑላቸውን ጉዳዮች በማንሳት፥ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፥ የማሻሻያ አዋጁ ከሁለት ዓመታት በላይ የፈጀ ጥናት እንደተደረገበትና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት መዘጋጀቱን አስታውሰዋል። ተለዋዋጭ የሆነውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የገቢ ግብር እንደ ሀገር ለታቀደው የኢኮኖሚ እድገት እውን መሆኑ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዉ፣ ለዚህ ደግሞ አዋጁን ማሻሻል ተገቢና አስፈላጊ ነው ብለዋል። መንግስት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንና ከገቢ ግብር አሰባሰብ ጋር ተያይዞ የሚፈጥረው ጫና አለመኖሩንም አረጋግጠዋል። የማሻሻያ አዋጁ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማበረታታት፣ የታክስ ማጭበርበርን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል። ምክር ቤቱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁን በአምስት ተቃውሞ፣ በ12 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅንም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ማህበራዊ
የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ህዝበ ሙስሊሙ እድሉን ሊጠቀም ይገባል
Jul 18, 2025 61
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ)፡- ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ መሪዎቹን የመወሰን እድሉን እንዲጠቀም የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ በድሩ ኑሩ፤ የመጅሊስ ምርጫን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ኡስታዝ በድሩ ኑሩ፤ በመግለጫቸው ቦርዱ ምርጫውን የተሳካ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱን አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮችን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የመወሰን እድሉን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል። እጩ የመለየትና ጥቆማ የመስጠቱ ሂደት ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን የኡለማዎች ምርጫ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል ብለዋል። በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ በንቃት በመሳተፍ ሊመሩ የሚችሉ በቂ ልምድና እውቀት ያላቸውን አመራሮች እንዲመርጥ መልዕክት አስተላልፈዋል። በምክር ቤቱ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ፀሐፊ መሃዲ ሸምሱ፤ በክልሉ የመጅሊስ ምርጫ ምዝገባ ከተጀመረ ወዲህ በርካቶች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን አስታውሰው በቀሩት ጥቂት ቀናት ሌሎችም ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም እድሜው 18 ዓመት የሞላው ሙስሊም መመዝገብ እንደሚችል ተመልክቷል።  
የአካል ጉዳተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ረቂቅ የፖሊሲ ሰነድ ተዘጋጅቷል
Jul 18, 2025 57
አዳማ ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አካታች ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ የፖሊሲ ሠነድ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ረቂቅ ፖሊሲ ሠነድ ዝግጅት ግብዓት ለማሰባሰብ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ዛሬ በአዳማ ተካሄዷል። በወቅቱም የሚኒስቴሩ የህግ አማካሪ አቶ ደረጄ ተግበሉ እንደገለፁት፤ የአካል ጉዳተኞችን መሰረታዊ መብቶች በማስከበርና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። በመሆኑም የፖሊሲ ዝግጅት ማድረግ ማስፈለጉንና ዋና ዓላማውም የአካል ጉዳተኞችን የእኩል እድል ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ የፖሊሲ እርምጃዎችን ለመውሰድ መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዱ አካል ጉዳተኞች በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልፀው ለ5ኛ ጊዜ የግብዓት ማሰባሰብ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄዷል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማህበራዊ ልማት፣ የባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) መንግስት አካል ጉዳተኞች የልማቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።   የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው ሀገሪቱ እስካሁን የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ፖሊሲ ስለሌላት የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስከበር ሳይቻል መቆየቱን አስታውሰዋል። መንግስት የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲ ለማውጣት ቁርጠኛ አቋም መያዙን አድንቀው ፖሊሲው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚያስገኝም አመልክተዋል።   በመድረኩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ እንዲሁም የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በክልሉ መስህቦችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ
Jul 18, 2025 55
ባሕርዳር፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):- በአማራ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መስህቦችን ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የስራ ክንውን የግምገማ መድረክ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄዷል።   በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ12 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና ከ27 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ክልሉን ጎብኝተዋል። ባለድርሻ አካላትን፣ የቢሮውን መዋቅር ከላይ እስከታች በማቀናጀትና መገናኛ ብዙሃንን በአግባቡ በመጠቀም በተከናወነው የማስተዋወቅ ስራ የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቀት ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።በተለይም የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የቱሪዝም ፍሰቱ ከታቀደው በላይ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል የታየበት እንደሆነም አመልክተዋል። የክልሉን ዕምቅ የባህልና የቱሪዝም አቅም በማስተዋወቅና መዳረሻዎችን በማልማት የተከናወነው ስራ ጨምሮ በበጀት ዓመቱ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ አስታውቀዋል። የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ፤ በባህል ልማትና እሴት ግንባታ በኩልም ሰፊ ስራ ተከናውኗል ብለዋል። በተለይም በክልሉ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበሩ የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ የእንግጫ ተከላና የቡሄ በዓላትን የቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ስራ በስፋት መከናወኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።
በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 18, 2025 54
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ከለውጡ ወዲህ በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።   ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት፤ በሁለንተናዊ ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ መገንባት ይገባል ብለዋል። ይህን ከማረጋገጥ አኳያ ጥራት ያለው ትምህርት አይነተኛ ሚና እንደሚያበረክት ገልጸዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ አመታት በትምህርት ዘርፍ ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገብ መቻሉንም አመላክተዋል፡፡ በመዲናዋ ከለውጡ ወዲህ 110 የሚሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ 30 ሺህ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች፣ 334 የትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትና ሌሎች የትምህርት መሰረተ ልማቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመትም 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለምረቃ መብቃታቸውን ተናግረዋል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል 14 የሚሆኑት አዳዲስ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በእርጅና ለመማር ማስተማር ምቹ ያልነበሩና የማስፋፊያ ግንባታ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡   ሁለንተናዊ ብልጽግናን ያለትውልድ ግንባታ ማሰብ አይቻልም ያሉት ከንቲባዋ፤ በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በተሰጠው ትኩረት የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አመላክተው፤ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ትምህርት የአገራት እድገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ በዚህ መነሻነት ከተማ አስተዳደሩ ያከናወናቸው የትምህርት ማሻሻያ ርምጃዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል።   ፕሮጀክቶቹ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነት ከማረጋገጥ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚያበረክቱ ነው የገለጹት። በምርቃት ስነ ስርዓቱ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢኮኖሚ
የ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሚያጸና መልኩ ለማሳካት የአመራሩ ትጋትና የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
Jul 18, 2025 66
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-የ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሚያጸና መልኩ ለማሳካት የአመራሩ ትጋትና የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ። የመንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት አቅድ የግምገማ መድረክ በፌደራል ተቋማት አመራሮች ደረጃ ተካሂዷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በዚሁ ወቅት፥ በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የላቀ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል። በግብርናው ዘርፍ፣ በማዕድን እና በቡና ወጪ ንግድ፣ በተኪ ምርት እና በሌሎች ዘርፎች በታሪክ ከፍተኛ ውጤት መምጣቱን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅም የኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ድል መሆኑን ተናግረዋል። የተመዘገቡ ስኬቶች በቅንጅት የመጡ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ሀገርና ህዝብን የሚያኮሩ እና ለአዳዲስ ድል እንድንነሳ ስንቅ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ አስደናቂ እመርታዎች መመዝገባቸውን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅም በራስ አቅም ብሔራዊ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ምሳሌ፣ የጀግንነትና የወል ትርክት አምድ፣ የኢትዮጵያውያን የይቻላል ትጋት ማሳያ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ በአምራች ኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ልህቀት ወሳኝ ስኬቶች መጥተዋል ነው ያሉት። መንግሥት ጥራት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማስቀጠል ለአምራች ዘርፉ የፋይናንስ አቅርቦትን ማጠናከሩንም አውስተዋል። በቀጣይም ሙስናን የመከላከል፣ ዘላቂ ሰላምን የማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል። በኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎችን በማድረግ ለውጥ ቢመጣም በፌደራልና በክልሎች መካከል የተናበበ አሰራርና አፈጻጸም ባለመኖሩ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)፥ የዘንድሮው ሀገራዊ እቅድ የ2017 በጀት ዓመት ስኬቶችን፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ተሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ጥራት ያለው ስኬት ለማስመዝገብ መታቀዱንም ጠቁመዋል። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግም የፌደራል ተቋማትና ክልሎች ወጥ የሆነ አሰራርን እንዲተገብሩና የተሳለጠ ምህዳር እንዲፈጥሩ ይደረጋል ነው ያሉት። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ በሰጡት ማጠቃለያ፥ መንግሥት የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ በልማት እያጸና እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ለዚህም በ2018 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ አዳዲስ እመርታዎችን ለማስመዝገብ ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል ነው ያሉት። ሀገራዊ ዕቅዱ ታላላቅ ስኬቶችን ያለመ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ በከፍታ ለማስቀጠል የአመራሩ የሌት ተቀን ትጋት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። በእቅዱ ላይ መግባባት ፈጥሮ በአርዓያነት መስራት፣ የመንግሥት ሰራተኛውን፣ የግሉን ዘርፍ እና የህዝቡን ተሳትፎ በጉልህ በማሳደግ መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል። በሌላ በኩል ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለወል ትርክት መጠናከር ሁሉም መስራት አለበት ነው ያሉት።
በክልሉ የንግዱ ማህበረሰብ የዘርፉን ሥራ በፍትሃዊነት በማሳለጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን - እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Jul 18, 2025 63
ሆስዕና ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግዱ ማህበረሰብ የዘርፉን ሥራ በፍትሃዊነት በማሳለጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የ2017 ማጠቃለያ ጉባኤና የንግድ ሳምንት ባዛር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል ፡፡   በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የሸማቹን ፍላጎትና የአምራቹን አቅርቦት በማጣጣም የንግዱን ሥርዓት ፍትሐዊና የተሳለጠ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን ለማስፈን ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና እጥረትን ለማስቀረት በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ፡፡ የንግዱን ማህበረሰብ ችግር ለይቶ ለመፍታትና ተወዳዳሪ እንዲሆን እንሰራለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የንግዱ ማህበረሰብም ህብረት በመፍጠር ለትላልቅ ሥራዎች ልምድ ማዳበር እንዳለባቸውን ጠቁመዋል፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው፤ የንግድ ሥርዓቱን ሕጋዊና ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ የቁጥጥር ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።   በዚህም ባለፈው የበጀት ዓመት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አመልክተው፤ ‎ለአብነት በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ300 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር መዋሉንና ህግን የተላለፉ ማደያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። ‎አምራችና ሸማችን በማቀራረብ ገበያን በማረጋጋትና ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓትን በመዘርጋትም እንዲሁ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ ‎በተለይ በከተሞች የሰንበት ገበያዎችን ቁጥራቸውን በማሳደግ አምራቹና ሸማቹ በቀጥታ እንዲገናኙ ማድረግ እንደተቻለ አብራርተዋል ። ከባዛሩ ተሳታፊዎች መካከል ከሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ የመጡት አቶ አብደላ ሀሰን፤ በተሰማሩበት የንብ ማነብ ሥራ የሚያገኙትን የማር ምርት በራሳቸው ሱቅና ባዛሮች ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርቡ ጠቅሰው፤ በተለይ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ከተጀመረ በኋላ ሥራቸውን በስፋትና በዘመናዊ መንገድ መከወን እንደቻሉ ተናግረዋል።   ‎ዘንድሮ ብቻ ሰብስበው ባቀረቡት የማር ምርት 950 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውንም አውስተዋል። ‎በጉራጌ ዞን አድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ግብይት ክፍል አስተባባሪ ወይዘሮ ዐባይነሽ ኪሮስ ፤ ዩኒየኑ ከአባላት ግብዐት በመሰብሰብ የተጣራ የኑግ ዘይት እያመረተ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ጠቁመው፤ የአካባቢውን ገበያ በማረጋጋትም አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሚገኝ አብራርተዋል።   በመርሀ ግብሩ ላይ የተቋማት አመራሮችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉ ሲሆን፤ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሴክተሩ አደረጃጀቶች የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚዘጋጁ ኤግዚቢሽን እና ባዛሮች የአምራች እና የሸማቹን የገበያ ትስስር እያጠናከሩ ነው
Jul 18, 2025 59
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-በከተማ አስተዳደሩ የሚዘጋጁ ኤግዚቢሽን እና ባዛር የአምራች እና የሸማቹን የገበያ ትስስር እያጠናከሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሃቢባ ሲራጅ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ያዘጋጀውና ከሃምሌ 7 እስከ ሃምሌ 11/2017 ዓ/ም በኤግዚቢሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው እለት ተጠናቋል።     የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሃቢባ ሲራጅ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ቢሮው የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ የንግድ ስርአቱን ቀልጣፋ እንዲሆን አምራች እና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት በኩል ውጤታማ ስራ መሰራቱን ለአብነት አንስተዋል፡፡ 2ኛው ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንና ባዛርም የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ለ5 ቀናት በቆየው ኤግዚቢሽን እና ባዛር የአገር ውስጥ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለህብረተሰቡ ትልቅ ፋይዳ ማስገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት መፈጸማቸውን አንስተው ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑንም አስታውቀዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍስሃ ጥበቡ በበኩላቸው፤ ባዛሩ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ ትስስር የተፈጠረበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡   ቢሮው አቅራቢዎችና ሸማቾች በቀጥታ የሚገበያዩበት ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ከሸማቾች መካከል አልማዝ አበበ እንደገለጸችው ከባዛሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በመግዛት ተጠቃሚ መሆኗን ተናግራለች፡፡   ምርታቸውን በባዛሩ ያቀረቡት አቶ ደረጀ ጋሪ በበኩላቸው፤ ባዛሩ መዘጋጀቱ ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡    
በዞኑ አርሶ አደሮች አሲዳማ አፈርን በማከም ምርታማነታቸውን ማሳደግ ችለዋል
Jul 18, 2025 63
ደብረማርቆስ፤ ሐምሌ 11 /2017(ኢዜአ)፡ - በምሥራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች አሲዳማ አፈርን በኖራ አክመው የእርሻ ማሳቸውን በማልማት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻላቸው ተገለጸ። ዘንድሮ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል ትኩረት ከተሰጠው ጉዳይ አሲዳማ አፈርን በማከም ማልማት እንደሆነ የዞኑ ግብርና መምሪያ አመልክቷል። ከ248 ሄክታር በላይ መሬት በኖራ ለማከም ታቅዶ እስካሁን ከ48ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ በማቅረብ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ መበተኑን መምሪያው ጠቅሷል። አርሶ አደር መልሳቸው ያዜ በዞኑ የማቻከል ወረዳ የቅዳማን ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ በአሲዳማ አፈር የተጠቃ አንድ ሄክታር የእርሻ ማሳቸውን በኖራ በማከም ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። ይህም የመሬታቸውን ለምነት በመጨመሩ በሄክታር ከአምስት ኩንታል በላይ የምርት ጭማሪ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በተያዘው የመኸር ወቅትም ተግባሩን ለማስቀጠል ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል። በአነደድ ወረዳ የጉዳለማ ቀበሌ አርሶ አደር ተመስጌን ክብረት በበኩላቸው፤ ግማሽ ሄክታር ማሳቸውን በኖራ በማከም የአፈሩ ለምነት እንዲመለስ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ቀደም ሲል በአሲድ የተጠቃው ማሳቸው ምርቱ መቀነሱን አውስተው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጠቃው ማሳቸው በኖራ አክመው በመዝራት የጤፍና የስንዴ ምርታቸው ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።ያገኙትን ጥቅም ለማሳደግም ከዘር በፊት ቀደም ብለው ኖራ በመበተን ማከማቸውን አንስተዋል። የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አበበ መኮንን እንደገለጹት፤ ዘንድሮ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል ትኩረት ከተሰጠው ጉዳይ አሲዳማ አፈርን በማከም ማልማት ነው።   ለዚህም በዞኑ ከ248 ሄክታር በላይ መሬት በኖራ ለማከም ታቅዶ እስካሁን ከ48ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ በማቅረብ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ መበተኑን ተናግረዋል። አርሶ አደሮችን በማሳተፍ እየተካሄደ ያለው አሲዳማ አፈርን በኖራ የማከም ተግባር ውጤታማነቱ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል። ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ እንደሚያመልክተው፤ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017/2018 የምርት ዘመን ከ642 ሺህ ሄክታር በላይ በሰብል ዘር በመሸፈን ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማጎልበት ያስችላል-በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Jul 18, 2025 57
  አዲስ አበባ፤ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):-የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እውቀትን በማስፋፋት፣የግለሰቦችንና የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበት ቁልፍ ዓላማው መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር "በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ረቂቅ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ "በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተገኙ ስኬቶች ላይ ተመስርቶ አዳዲስ የዲጂታል እድገቶች ላይ ያተኮረ ነው። ስትራቴጂው አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ስማርት ከተሞችን፣ ድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ ፣ ዲጂታል ሉዓላዊነትን የመሳሰሉ ጽንሰ ሃሳቦችን በማካተት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። ስትራቴጂው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለሚፈጥሩ የስራ እድሎች፣ አካታች እና ፍትሃዊ ልማትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዓላማ ማድረጉንም ተናግረዋል። የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋት እና የተቋም አቅምን በመገንባት የግለሰቦችን እንዲሁም የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበት የስትራቴጂው ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን፣ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ተደራሽነትን ማሳደግ እና ኢትዮጵያን ለዲጂታል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ማድረግ ከስትራቴጂው ዓላማዎች መካከል እንደሚካተቱ አክለዋል። አገራዊ ዳታዎችንና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎችን እና አገራዊ የልማት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን የዲጂታል ልማት ምሰሶዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችን የለየ መሆኑንም አብራርተዋል። የአይሲቲ ማህበር ፕሬዝዳንት ይልቃል አባተ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ስትራቴጂው ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ እያከናወነች ያለውን ስራ በሰፊው ለመተግበር የሚያስችል ነው።   በተጨማሪም ዜጎች በዲጂታል ዓለም ተፎካካሪ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አክለዋል። ስትራቴጂው ኢትዮጵያን የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ እንደሚያስችል የተናገሩት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢትዮጵያ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ባህሩ ዘይኑ ናቸው።  
በኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ
Jul 18, 2025 77
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ተገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠናን ሐምሌ 2016 ዓ.ም ማስጀመራቸው ይታወሳል። ስልጠናው በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ ለኢዜአ እንደገለጹት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወሳኝ ከሆኑ መሰረቶች አንዱ የዲጂታል ስነ-ምህዳሩን ማስፋት መሆኑን አንስተዋል፡፡ የዲጂታል ስነ ምህዳሩን ከሚያሰፉ ስራዎች መካከልም ዋነኛው የክህሎት ግንባታ መሆኑን ገልጸው፤ በዘርፉ እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ማፍራት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በዚህም እስካሁን ባለው የስልጠናው ሂደት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የኮደርስ ስልጠናን እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 900ሺህ የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ሀገራዊ ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ ክልሎችም የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ለመወጣት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በዚህም የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መኖራቸውን ነው ስዩም መንገሻ ጨምረው የገለጹት። የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ንቁ ተሳታፊ እና አምራች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያገኙበት መሆኑንም ገልጸዋል። በተያዘው ክረምት ወቅትም ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በትምህርት ቤቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስልጠናውን በመውሰድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መልእክት አስተላልፈዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋት፣ የተቋማት የመፈጸም አቅም ማጎልበትን ዓላማ ያደረገ ነው - ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Jul 18, 2025 99
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋት፣ የግለሰቦችንና የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበትን ቁልፍ ዓላማ ያደረገ መሆኑን የኢኖቬሸን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር "በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ረቂቅ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።   ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተገኙ ስኬቶች ላይ ተመስርቶ አዳዲስ የዲጂታል እድገቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ስትራቴጂው ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል የህዝብ መሰረተ ልማት እስከ ስማርት ከተሞች፣ ድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ፣ ዲጂታል ሉዓላዊነት የመሳሰሉ ጽንሰ ሃስቦችን አካቶ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ስትራቴጂው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለሚፈጠሩ የስራ እድሎች፣ አካታችና ፍትሃዊ ልማትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን አላማ አድርጎ የተነደፈ መሆኑንም ተናግረዋል።   የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋትና የተቋም አቅምን በመገንባት የግለሰቦችን እንዲሁም የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጎልበት ከስትራቴጂው ዋና አላማዎች መካከል እንደሆነም ገልጸዋል። አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን፣ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ተደራሽነትን ማሳደግ እና ኢትዮጵያን ለዲጂታል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ማድረግ ከስትራቴጂው ዓላማዎች መካከል መሆኑንም አክለዋል። ሀገራዊ ዳታዎችንና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎችን እንዲሁም ሀገራዊ የልማት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን የዲጂታል ልማቱ ምሰሶዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችን የለየ መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ውህደት ዕድገትን እያስመዘገበች ነው 
Jul 15, 2025 238
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 8/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የዲጂታል ውህደት ዕድገትን እያስመዘገበች ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። 25ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የተሳተፉት ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ የዲጂታል ውህደት በመፍጠር በኩል ጠንካራ የዲጂታል ግስጋሴ ላይ መሆኗን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዲጅታል ግስጋሴ ከአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ፖሊሲ ማትሪክስ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ጠቁመዋል። የአፍሪካ ቀንድ ዲጅታል ውህደትን እውን ከማድረግ አንጻር ሀገራቱ ጥሩ አፈጻጸም እያስመዘገቡ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ኢትዮጵያ የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው መካከል አንዷ መሆኗን ነው የገለጹት፡፡ ኢትዮጵያ ያደረገችው ሪፎርም የቴሌኮም ዘርፎችን ነፃ ማድረግ፣የግል መረጃ ጥበቃ እና የሳይበር ደህንነት ህጎችን ማውጣት፣የፋይበር መሠረተ ልማትን ማስፋፋት መቻሉን ገልጸዋል። እንዲሁም ከ19 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በዲጂታል መታወቂያ ስርዓት መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። አክለውም፥ ከ54 ሚሊዮን በላይ የቴሌብር ተጠቃሚዎች መኖራቸውን እና 4.6 ትሪሊዮን ብር የግብይት መጠን መፈጸሙ ኢትዮጵያ በፋይናንሺያል አካታችነት ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል ብለዋል። የቀጣናውን የሀይል ትስስር አስፈላጊነት ገልጸው፥አጋር አካላት ለሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አመስግነዋል።
ስፖርት
የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል
Jul 18, 2025 61
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ):- በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ናይጄሪያ ከዛምቢያ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ይጫወታሉ። የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በምድብ ሁለት በሰባት ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዛ ሩብ ፍጻሜ ገብታለች። ተጋጣሚዋ ዛምቢያ በምድብ ሁለት በሰባት ነጥብ ሁለተኛ በመሆን ስምንት ውስጥ ገብታለች። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫው ሲገናኙ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው። እ.አ.አ በ2022 በሞሮኮ በተካሄደው 12ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ ባደረጉት ጨዋታ ዛምቢያ ናይጄሪያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ጋና እ.አ.አ በ2018 ባዘጋጀችው 11ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሁለት ተገናኝተው ናይጄሪያ ዛምቢያን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ረታለች። በናሚቢያ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2014 በተካሄደው 9ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ተገናኝተው ናይጄሪያ 6 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። በሶስቱ ጨዋታዎች ናይጄሪያ 11 ግቦችን ስታስቆጥር ዛምቢያ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው 1 ጎል ብቻ ነው። በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች ተመጣጣኝ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ናይጄሪያ የማሸነፍ ቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች። የጨዋታው አሸናፊ በግማሽ ፍጻሜው ከደቡብ አፍሪካ እና ሴኔጋል አሸናፊ ጋር ይጫወታል። ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፕሪስን ሙላይ አብደላ ስታዲየም የሚካሄደው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ማሊን ያገናኛል።   ሞሮኮ በምድብ በሰባት ነጥብ አንደኛ ደረጃን በመያዝ፣ ማሊ በምድብ ሶስት በአራት ነጥብ ምርጥ ሶስተኛ በመሆን ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል። ሁለቱ ቡድኖች በውድድር እና የወዳጅነት ጨዋታዎች ከዚህ ቀደም ሰባት ጊዜ ተገናኝተው በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፉ ሶስት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ሞሮኮ 10 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ማሊ 9 ጎሎችን አስቆጥራለች። በዛሬው ጨዋታ ሞሮኮ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ እንደምትወስድ የሚጠበቅ ሲሆን ማሊ የመልሶ ማጥቃት እና የፈጣን ሽግግር እንቅስቃሴ ይዛ ወደ ሜዳ ትገባላች ተብሎ ይጠበቃል። ሞሮኮ የማሸነፍ የቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች። የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በግማሽ ፍጻሜው ከአልጄሪያ እና ጋና አሸናፊ ጋር ይገናኛል።
ስፔን እና ስዊዘርላንድ በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት ይፋለማሉ
Jul 18, 2025 60
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ):- 14ኛው የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ሶስተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ዛሬ በስፔን እና ስዊዘርላንድ መካከል ይካሄዳል። ጨዋታው በዋንክዶርፍ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ይደረጋል። ስፔን በምድብ ሁለት ዘጠኝ ነጥብ በማግኘት የምድቧ መሪ ሆና ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። በምድብ አንድ የነበረችው የውድድሩ አዘጋጅ ስዊዘርላንድ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስምንት ውስጥ ገብታለች። ሁለቱ ቡድኖች እስከ አሁን ስድስት ጊዜ ተገናኝተው ስፔን አምስት ጊዜ ስታሸንፍ ስዊዘርላንድ አንድ ጊዜ ድል ቀንቷታል። ስፔን በጨዋታዎቹ 25 ግቦችን ስታስቆጥር ስዊዘርላንድ 8 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፋለች። እ.አ.አ በ2023 በአውሮፓ የሴቶች የኔሽንስ ሊግ ውድድር ስፔን ስዊዘርላንድን 7 ለ 1 ያሸነፈችበት ጨዋታ በሀገራቱ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከፍተኛ የግብ መጠን የተቆጠረበት ሆኖ ተመዝግቧል። ስፔን ስዊዘርላንድን ባሸነፈችባቸው ጨዋታዎች በአማካይ አራት ግቦችን አስቆጥራለች። ሁለቱ ሀገራት ያላቸው የእርስ በእርስ ግንኙነት ስፔን ከፍተኛውን ብልጫ ትወስዳለች። በውድድሩ ላይ አራተኛ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ስፔን ትልቁ ውጤቷ እ.አ.አ በ2022 እንግሊዝ ባሰናዳችው 13ኛው የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ የደረሰችበት ነው። በአንጻሩ ለሶስተኛ ጊዜ እየተሳተፈች ያለው ስዊዘርላንድ ከምድቡ ስታልፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዛሬው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ስፔን የማሸነፍ የቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች። የጨዋታው አሸናፊ በግማሽ ፍጻሜው ከፈረንሳይ እና ጀርመን አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
የአፍሪካ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሶስተኛ ቀን ውሎ 
Jul 18, 2025 69
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ)፦ ናይጄሪያ አቢኩታ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው አምስት የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ። ከቀኑ 6 ሰዓት ከ55 በ400 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ፍፃሜ ገነት አየለ እና ባንቻአለም ቢክስ ይሳተፋሉ። ምሽት 12 ሰዓት ከ55 በሚደረገው የ100 ሜትር መሰናክል ሴት ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ትዕግስት ባንቲይደሩ ኢትዮጵያን ወክላ ትወዳደራለች። በ400 ሜትር ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት 30 ላይ የሚካሄድ ሲሆን አጃይባ አሊዬ ትሳተፋለች። ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ20 ላይ በ3000 ሜትር ወንዶች ከ18 ዓመት በታች ፍፃሜ አብርሃም ገብረእግዚአብሔር የሚወዳደር ይሆናል። ምሽት 2 ሰዓት ከ40 ላይ በሚደረገው የ4x100 ሜትር ሴት ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ሰላማዊት ኮከብ፣ ደሚቱ ሽፈራሁ፣ አጃይባ አሊዬ እና ትግስት ባንቲይደሩ ተሳታፊ ናቸው። በውድድሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ እየጠበቀች ነው። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው እስከ አሁን ሶስት የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎች ማግኘቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ሀገር ለማውረስ ለሚደረገው ጥረት የላቀ አበርክቶ አለው
Jul 18, 2025 68
ጋምቤላ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ሀገር ለማውረስ ለሚደረገው ጥረት የላቀ አበርክቶ እንዳለው ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጋምቤላ ሪጅን የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ሃሳብ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አካሂደዋል፡፡   የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሳይመን ሙን(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት እተከናወነ ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ሀገርን ለማውረስ ለሚደረገው ጥረት የላቀ አበርክቶ አለው ብለዋል፡፡ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሀገር የተያዘውን ግብ ማሳካት እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጋምቤላ ሪጅን የሥራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ዛሬ በጋምቤላ ከተማ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ብለዋል፡፡ ሌሎች ተቋማትም ይህንኑ አርዓያ በመከተል በክረምቱ ወራት በሚከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል፡፡   የጋምቤላ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አማረ ገብረመድህን በወቅቱ እንዳሉት የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የሁሉንም ተቋማት የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡ አገልግሎቱ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት እንደሀገር በተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ላይ በትኩረት ሲሳተፍ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማትም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር የተራቆቱና የተጎዱ አካባቢዎች ላይ ችግኞችን እየተከሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ችግኝ መትከል ብቻ ግብ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ ዛሬ የተተከሉትን ችግኞች ከእንስሳት ንክኪ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱም ተናግረዋል፡፡   ከሪጅኑ ሰራተኞች መካከል አቶ ይርጋለም ገነቴ እና አቶ አበበ ለማ በሰጡት አስተያየት በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ችግኝ በመትከል አሻራችንን በማሳረፋችን ተደስተናል ብለዋል፡፡   ዛሬ የተከሏቸውን ችግኞች ተንከባክበው ለጽድቀት እንደሚያበቁ ጠቅሰው በቀጣዮቹ የክረምቱ ወራት የጀመሩትን የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለተግባር ተኮር የግብርና ትምህርት ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው- ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)
Jul 17, 2025 117
ባሕርዳር፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እየተሰጠ ላለው ተግባር ተኮር የግብርና ትምህርት ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በባህር ዳር ከተማ ፋሲሎ 2ኛ ደረጃ እና መስከረም 16 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ በትምህርት ቤቶች የሚከናወን የችግኝ ተከላ ስራ የአየርን ንብረት ሚዛንን ለመጠበቅ ከማገዝ ባለፈ ለምግብነትና ለውበት የሚሆን ነው። በተለይ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እየተሰጠ ላለው ተግባር ተኮር የግብርና ትምህርት በተሞክሮነት እንደሚያገለግል ገልጸዋል። በመሆኑም እንደቢሮ የተተከለው ችግኝ ፀድቆ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል አስፈላጊው ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ተናግረዋል።   ትምህርት ቤቶችን አረንጓዴና ሳቢ ማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ማራኪና ተማሪዎች እንዲጓጉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ያሉት ደግሞ በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የቢሮው ባለሙያ ወይዘሮ ህብስቴ ካሴ ናቸው። ከመትከለ ባለፈ መንከባከብና እንዲጸድቁ ማድረግ የክረምት ስራዎች አንዱ አካል እንደሆነ ገልጸዋል። ሌላኛው የቢሮው ባለሙያ አቶ ጌታነህ መንግስት፤ በትምህርት ቤቶች የሚከናወን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የትምህርት ቤቶችን የምገባ መረሃ-ግብር ለማሳለጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አፕልና ማንጎን ጨምሮ ሌሎችም ለምግብነት ጭምር የሚያገለግሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆናቸውን አመልክተዋል። ዋናው ግብ እንዲጸድቁ ማስቻል መሆኑን አንስተው፤ ለዚህ ደግሞ እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኛ የተከለውን ችግኝ የመከታተል ኃላፊነቱን መወጣት አለብን ብለዋል።
አረንጓዴ አሻራ ምቹ፣ ውብና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሀገርን ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ተግባር ነው
Jul 16, 2025 135
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እያካሄደችው የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምቹ፣ ውብና ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የማይበገር ሀገርን ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ተግባር መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል። በዚህም የተለያዩ ተቋማትና ህብረተሰብ ክፍሎች በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች አሻራቸውን በማሳረፍ ላይ ይገኛሉ። ዛሬ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራር አባላትና ሰራተኞች፣ ከፌዴራል ስፖርት ማህበራት፣ ከኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት አመራር አባላትና ሰራተኞች ጋር በመተባበር በገላን ስታዲዬም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ምቹና ውብ አካባቢን በመፍጠር ለመጪው ትውልድ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የማይበገር ሀገርን የማስረከብ ተግባር ነው። ይህንን እውን ለማድረግ ወጣቱ እያደረገ ያለውን አበርክቶና ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡   ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ የተሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል እየሆኑ መምጣታቸውን የተናገሩት ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሀመድ ናቸው።   ይህም ዛሬ በተግባር የታየበት መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች ጸድቀው የታለመው አላማ እንዲሳካ እንሰራለን ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በበኩላቸው እንደገለጹት ፌዴሬሽኑ ለአረንጓዴ አሻራ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።   የሸገር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ናስር ሁሴን፤ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ችግኞችን መትከል ስፖርተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ባህል እንዲያደርጉና እንዲንከባከቡ ለማስቻል ነው ብለዋል።   ከተሳታፊዎች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪ ወጣት በድሉ በቀለ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወጣት ቡሳሞ ሞንደ እንዳሉት በየዓመቱ በሚካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።     ችግኞችን መትከልና እስከ ጽድቀታቸው ድረስ መንከባከብ ከሁሉም ሰው የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል።
በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በጣለው ከባድ ዝናብ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ ነው
Jul 16, 2025 112
አፋር፤ ሐምሌ 9/2017(ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በጣለው ከባድ ዝናብ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሸን አስታወቀ፡፡ በክልሉ በትናንትናው እለት ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሎጀስቲክስ ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር አሊ መሀመድ፤ ክስተቱን በማስመልከት ለኢዜአ መረጃ ሰጥተዋል። በክልሉ አፍዴራ ወረዳ በትናንትናው እለት ነፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱንና ብዙዎችን ማፈናቀሉንም ተናግረዋል።   በአደጋው ምክንያት በ32 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ22 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው፤ ተጎጂዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። በአደጋው ከ2 ሺህ 500 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን አንስተው ፤ አምስት የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቅሰዋል። ክስተቱን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ፣ አልባሳትና የፍራሽ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰው፤ ቀጣይነት ያለው እገዛና ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለአደጋው አስቸኳይ ምላሽ የሚሰጥ ከተለያዩ አካላት የተዋቀረ ግብረ ሃይል መቋቋሙን ተናግረው ፤ ቅንጅታዊ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከወረዳው አስተዳደር፣ ከጸጥታ ሃይል፣ በየደረጃው ካለው አመራርና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት አልፏል- የሕንድ ፖሊስ
Jun 12, 2025 1132
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ፖሊስ አስታወቀ። በሕንድ 242 መንገደኞችን ይዞ በህንድ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል አህመዳባድ ከተማ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን ጋትዊክ ለማምራት በተነሳበት ቅፅበት በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ተከስክሷል። በቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ውስጥ 169 ህንዳውያን፣ 53 የብሪታኒያ ዜጎች፣ 7 ፖርቹጋላዊ እና አንድ ካናዳዊ ነበሩ።   በአደጋው የተረፈ ሰው ለማግኘት የሚቻልበት እድል እጅጉን የጠበበ ነው ሲል የአህመዳባድ ፖሊስ ኃላፊ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጾ ነበር። ይሁንና ማምሻውን በወጣ መረጃ የ40 ዓመት የህንድ እና ብሪታኒያዊ ጥምር ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩማር ራሜሽ ከአደጋው መትረፉ ተጠቁሟል። እስከ አሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የአውሮፕላኑ አካል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ወድቆ ቢያንስ አምስት የህክምና ተማሪዎች መሞታቸውን እና 50 ገደማ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አደጋው ቃል ከሚገልጸው በላይ ልብ የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በአደጋው ለተጎዱ በሙሉ ልባዊ ሀዘናቸውን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኮሚሽኑ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ ይሰራል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 12, 2025 1418
አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫው በማድረግ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ዛሬ ትውውቅ እና ቆይታ አድርገዋል። ሊቀ-መንበሩ በስልጣን ጊዜያቸው ሊያሳኳቸው ስላቀዷቸው ተቋማዊ ግቦችና ቅድሚያ ሰጥተው ለመፈጸም ያሳቧቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በሰላም፣ ደህንነት፣ ልማትና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል። መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሰላምና ደህንነት የኮሚሽኑ ዋንኛ የትኩረት ማዕከል መሆኑን አመልክተዋል። ኢ-ሕገ መንግስታዊ የመንግስት ለውጦች በአፍሪካ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን ተናግረዋል።   የአፍሪካ ህብረት መሰል ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም ሰላምን በማስፈንና የዴሞክራሲ ስርዓትን በማረጋገጥ የህብረቱ አባል ሀገራትን ሉዓላዊነት እና ደህንነት መጠበቅ ላይ አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት። ሊቀ-መንበሩ በገለጻቸው ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካን ድምጽ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሻ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ውስጥ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር ቁልፍ ግብ መሆኑን ጠቅሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት በጽኑ ሁኔታ እንደሚሟገት አመልክተዋል። ሊቀ-መንበሩ የፀጥታው ምክር ቤት አሁናዊ መዋቅር የታሪክ ኢ-ፍትሃዊነት በማለት የገለጹት ሲሆን አፍሪካ በዓለም አስተዳደር የሚገባትን ትክክለኛ ስፍራ በሚገልጽ ሁኔታ ምክር ቤቱ ማሻሻያ ሊደርግበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚና ሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በአፍሪካ ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ማሳለጥ ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል። የህብረቱ ኮሚሽን ከቀጣናዊ ኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወጥነት ባለው መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሊቀ-መንበሩ በአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አማካኝነት ወረርሽኝን የመከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱንም አንስተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር በየሶስት ወር ጊዜ ቆይታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሙሳ ፋቂ ማህማትን በመተካት የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ያላትን የአፈጻጸም ሪፖርቶች ማቅረብ ጀመረች
May 10, 2025 1079
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ በፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው። በጋምቢያ ባንጁል የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሔደ ባለው ስብሰባ ላይ በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ልኡኩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀምሯል።   ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብአዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል። በኮሚሽኑ መርሃ-ግብር መሰረትም ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት እንደሆነም ተገልጿል።
በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
Apr 23, 2025 1707
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ)፦በዛሬው እለት በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። እንደ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘገባ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የኢስታንቡል እና ጎረቤት አካባቢ ነዋሪዎች በፍርሃት የመኖሪያ ህንጻቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል። በሌላም በኩል ረፋዱ ላይ በኢስታምቡል አቅራቢያ የባህር ዳርቻ ቡዩኪክሚ የተባለ ስፍራ ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አናዶሉ የዜና ወኪል የሃገሪቱን የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። በአደጋው ምንም የተመዘገበ ጉዳት እንዳልተከሰተ የጠቀሰው ዘገባው ነዋሪዎች የዚህ ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲገጥም የተጎዱ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳይገቡ የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪዎችን እንዳይጠቀሙና ሌሎች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ባለስልጣኑ ማስተላለፉም ተገልጿል። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንና ለዜጎችም መልካም ሁኔታ እንዲገጥማቸው መመኘታቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ከሃገሪቱ የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣንና ከሚመለከታቸው አካላት መረጃዎችን በመቀበል በቅርበት እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ሐተታዎች
የህንድ የፈጠራ ማዕከል - ባንጋሎሩ
Jul 2, 2025 622
ቤተልሄም ባህሩ(ኢዜአ) የዴልሂና አግራ ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ቀጣይ መዳረሻችን ባንጋሎሩ ከተማ ልንጓዝ ስንሰናዳ አብዛኛው የጋዜጠኛ ልዑክ ያሳሰበው እንደሰም የምታቀልጠውን የአግራ ፀሀይና ሙቀት በባንጋሎሩም ታገኘን ይሆን? የሚለው ነበር። ሆኖም ከዴልሂ ኢንድራ ጋንዲ አየር ማረፊያ ተነስተን ለሶስት ሰዓት ከተቃረበ በረራ በኋላ ያገኘናት ባንጋሎሩ የተለየች ሆነን አገኘናት። ባንጋሎሩ ቀዝቀዝ ባለ አየር ነበር እንግዶቿን የተቀበለችን። በዕለቱ ከክፍሎቻችን ወጥተን በጋራ ወደአየር ማረፊያ የሚወስደንን ትራንስፖርት ስንጠባበቅ ከጋዜጠኛ ቡድኑ ስድስት አባላት ከአጠገባችን እንዳልነበሩ አስተዋልን። የት ጋር እንደተነጣጠልን አላስታውስም። በዚህ ምክንያት ግን የእለቱ ጉዟችን ተሰርዞ ከተማዋን ለማየት ስንዘዋወር የማውቀው ዓይነት እንጂ የተለየ ሙቀት አላስተናገድኩም። የ13 ወር ፀጋ በመባል የምትታወቀው አገሬ ኢትዮጵያ ከዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባላት የመልከዓ ምድር አቀማመጥና ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ሙቀቱንም፣ ቅዝቃዜውንም ማወቃችን እንደዚህ ለአለ አጋጣሚ መልካም ስሜት ይፈጥራል። በተወሰነ ደረጃ በህንድ ያጋጠመኝ የአየር ባህሪ ከአገሬ ጋር ቢመሳሰልብኝ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ስራ አጃኢብ ብዬ እንዳልፍ አድርጎኛል። ባንጋሎሩ ከተማ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ማዕከል በመሆኗ የህንድ ሲልከን ቫሊ በመባል ትታወቃለች። ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስፍራዎችም ከመገለጫዎቿ መካከል ናቸው። የጠፈር ጠበብቶቹ - ባንጋሎሩ ደርሰን በመጀመሪያ ያየነው ዓለም በስፔስ ሳይንስ እየሰራች ያለችውና እያስመዘገበችው የምትገኘው ውጤት ማሳያ የሆነውን የህንድ ስፔስ ምርምር ድርጅትን ነው። ተቋሙ የህንድ መንግስት የስፔስ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን፤ ዶክተር ቪክራም ሳራብሃይ በተሰኙ ባለራዕይ በ1962 የተወጠነና አሁን ላይ በዘርፉ ተገዳዳሪ መሆን የቻለ ነው። የተቋሙ ዓላማ የስፔስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመተግበር ለተለያዩ አገራዊ ጥቅሞች ማዋል መሆኑን ተከትሎ የሳተላይት ማምጠቂያ መሳሪያዎችን የማምረት ስራን ጨምሮ ከአገሩ አልፎ ለሌሎች አገራትም በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የተደረገልን ገለፃ አብዛኛውን ጋዜጠኛ ያስደመመ ነበር ከገለፃ በኋላ በጋዜጠኞች የተነሳው ሃሳብም ህንድ በስፔስ ዘርፍ ያላት ልምድና ያከናወነችው ተግባር በቀጣይም ልትሰራ የወጠነቻቸው ሃሳቦች የአገሪቱን መዳረሻ የተለሙ በአገራቸው እንዲተገበር የሚናፍቁት መሆኑን ነው። ተቋሙ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን የሚያጠናክር መሆኑን ከተደረገልን ገለፃ ተገንዝበናል።   በሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግና አስተዳደር ምሁራንን በማስተማር እያበረከተ ያለው የህንድ የሳይንስ ኢንስቲትዩት በባንጋሎሩ ከጎበኘናቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎችን የሚያስተምርና ከተቋማት ጋርም በዘርፉ የሚሰራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከጅማ፣ በተግባር ለመቀየር ሲታትሩ የስታርት አፖችን የምርት ውጤቶቻቸውን ሲፈትሹና ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። በኢትዮጵያም አሁን ላይ ለስታርት አፖች በተሰጠው ትኩረትና በተፈጠረው ምቹ ስነ ምህዳር የፈጠራ ውጤቶች እያደጉና እየተበራከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እንደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት የተማሪዎችን ፈጠራ ወደ ውጤት ለመቀየር እየተጉ መሆኑና የስታርት አፕ ኤግዚቢሽንና የሰመር ቡት ካምፖች ፈጠራን ምን ያህል እያበራከቱ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ወደ አዕምሮዬ የመጣ የአገሬው ህዝብ በውጤት የታጀበ ጥረት ነው።   ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በባዩቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው ባዮኮንም ከባላንጎሩ የጉብኝት መዳረሻችን መካከል የሆነና አስፈላጊ መድሀኒቶችን የሚያመርትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይም እየሰራ ያለ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠቃሚ ናቸው። ከ120 በላይ በሆኑ አገራት ለስኳርና ካንሰር ህመም የሚያገለገሉ መድሀኒቶችን በማምረትና በማሰራጨት ለህሙማን ፈውስና ለጤናው ዘርፍ ስርዓት አስተዋፅኦ እያበረከተም ይገኛል። የተቋሙ ላቦራቶሪና ዘመኑን የዋጀና ደረጃውን የጠበቀ ማምረቻ ፋብሪካን መጎብኘቴ አለም በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የባንጋሎሩ ቤተመንግስት - ይህን ቤተ መንግስት ማስቃኘቴን ከመጀመሬ በፊት በስፍራው ካስገረመኝ ነገር ላወጋችሁ ወደድኩ። ቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ያቀናነው በእለተ ሰኞ ነበር። ሆኖም ምድረ ግቢውን ቃኝተን ስለህንፃው ሰምተን ከመመለስ ውጪ ወደ ውስጥ አልዘለቅንም። ለምን? ለሚለው ምላሹ በዚህ ስፍራ "ሰኞ የእረፍት ቀን ናት" ነው። እንዴት ካላችሁ ቤተ መንግስቱ ቅዳሜና እሁድ በበርካታ ሰዎች የሚጎበኝ መሆኑን ተከትሎ በስፍራው ለሚሰሩ ሰራተኞች የእረፍት ቀናቸው ሰኞ በመሆኑ ነው። የቤተ መንግስቱ ምድረ ግቢ ሰፊና ልምላሜ የተላበሰ ሲሆን፤ የሚያምርና ለዓይን የሚስብ ኪነ ህንፃ ያለው ነው። አሰራሩና ውጥኑም እንደሚከተለው ነው። በዎዲየር ስርወ መንግስት ንጉስ ቻማራጃ ዋዲያር ወደ እንግሊዝ ባደረጉት ጉዞ በለንደን ዊንሶር ግንብ ይደነቃል። ተደንቆም አልቀረ የባንጋሎሩ ቤተ መንግስትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባል። ይህ ቤተ መንግስት በተወሰነ መልኩ የመካከለኛው ዘመን የኖርማንሲና የእንግሊዝ ግንቦችን ይመስላል።   ቪድሃና ሶውዳ የካራንታካ ህግ አውጪ አካል መናገሻ በጉብኝታችን ያየነው ሌላው መዳረሻ ስፍራችን ነው። የህግ አውጪና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የያዘው ይህ ህንፃ ህንድ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በራሷ መሀንዲስ የሰራችው የመጀመሪያው ህንፃ መሆኑ ተገልፆልናል። የህንፃ ግንባታ ጥበብ ማሳያ፣ የፖለቲካ መናገሻ እንዲሁም የባህል ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል።   እንደአጠቃላይ በቆይታዬ የተመለከትኩት የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ማበረታቻ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራ ኢትዮጵያ እያከናወነች ካለው የኮሪደር ልማትና ስታርት አፕን የማበረታታት ብሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ምቹነት ስራዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ነው። በህንድና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ፤ ለሁለት ሺህ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያሳያል። የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአክሱም ስርወ መንግስት ኢትዮጵያና ህንድ በአዱሊስ ወደብ በኩል የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመምና ሐርን ከህንድ ትገበይ ነበር። ህንድ ደግሞ ወርቅና የዝሆን ጥርስን ከኢትዮጵያ ትሸምት ነበር። ህንድ ከንግድ ልውውጥ ባሻገር በኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ግንባታ ላይ አሻራዋን አኑራለች። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍም ትልቅ አበርክቶ ያላት አገር ናት። ህንድ ነፃነቷን ካገኘችበት እኤአ 1948 አንስቶ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ህንድ ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ ያገኘሁት የአምራች ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወኑ ያሉት ንቅናቄ ነው። ህንድ እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት "ሜድ ኢን ኢንዲያ" በሚል ለአስር ዓመት የተገበረችውና በርካታ ለውጥ የተመዘገበበት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ካለውና የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግን ዓላማ ካደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጋር የተመሳሰለ ነው። ንቅናቄ በኢትዮጵያ መተግበሩ ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና ገቢ ምርት በመተካት በኩል ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑም ይታወቃል። በህንድ ተዘዋውሬ በተመለከትካቸው ከተማዎች ባሉ ጎዳናዎች ከታዘብኩት ነገር ሰዎች ከሱቅ ለሚገበያዩት ነገር ሳይቀር በዲጂታል መንገድ ክፍያ መፈፀማቸውን ነው። በባጃጅና በሞተር የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘትም ጭምር ሞባይሉን በመጠቀም “ይህ ቦታ የት ነው?” ሳይል ያሻዎት ስፍራ መድረስም ሌላው ትዝብቴ ነው። ይህ ነገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትኩረት አግኝተው እየተሰራባቸው ካሉት የዲጂታል ክፍያና ዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቆይታችን ልክ እንደአትሌቶቻችን ሁሉ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ የሚያስነሳውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝናና ክብር ለማስተዋል ችያለሁ። ፀጉረ ልውጥ መሆናችንን የተገነዘቡ በገበያ ማዕከላት የሚያገኙን እንዲሁም በምንጎበኛቸው ተቋማት የምንተዋወቃቸው ህንዳውያን "ከየት ናችሁ?" ብለው ሲጠይቁ፤ ለእኔና አንድ ከሌላ መገናኛ ብዙሃን የሄድን "ከኢትዮጵያዊ" ስንል የሚከተልልን ምላሽ "አሃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ" የሚል ነው። ይህም አየር መንገዱ ስሙ ከኢትዮጵያ ተሰናስሎ የሚጠራ የአገሪቷ መታወቂያ ተቋም መሆኑን ያስገነዘበኝ ነው። ከህንዳውያን ጋር ብቻ ሳይሆን አብረን ከተጓዝን ጋዜጠኞች አንዱ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእናንተ የብቻ ሳይሆን እኛንም እንደራሳችን ሆኖ እያገለገለን ያለ የጋራ አየር መንገዳችን ነው" ሲል ነው የገለፀው። ይሄ ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ኩራት ብቻ ሳይሆን መለያ ምልክትም ጭምር መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነው። በቀናት ቆይታዬ በእንግዳ አክባሪነታቸውና በለገሱን ፍቅርና እንክብካቤ ከአገሬ የራቅኩ ያህል ሳይሰማኝ ብቸኝነትን ሳላስተናግድ እንደውም እየናፈኳቸው እንድመለስ ላደረጉኝ ህንዳውያን በከበረ ሰላምታ ላመሰግን እወዳለሁ።
ውበትና ትጋት በህንድ
Jun 27, 2025 549
በቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ) በልጅነቴ እያየሁ ያደግኳቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች የህንድ ናቸው። ይህ ደግሞ ከአገራችን አርቲስቶች በላይ የህንድ የፊልም ተዋንያኑን ስም ለመለየት አስችሎኛል። የህፃንነት ዘመኔን የሚያስታውሱኝን ፊልሞች ከትዝታ ማህደሬ እያወጣሁ ከመተረክ በስተቀር ህንድን የማይበት አጋጣሚ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚያን በህንድ ፊልም የማደንቃቸውን የምደመምባቸውን የህንዳውያንን ሶስት ከተሞች ለመጎብኘት ከተመረጡ ከሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች መካከል መሆን ድንገቴ ሆነብኝ። እኔም ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ የጋዜጠኞች ልዑካን ህንድ ከልጅነት ትዝታቸው ጋር የተሳሰረ አንዳች ነገር አለው። ህንድ በፊልሞቿ የሚያቋት ስለመሆኑ ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው በዶርሻን የቴሌቪዥን ጣቢያ ውይይት ላይ ሲያነሱ ሰምቻለሁ። በዓለም ላይ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚዋ ህንድ የብዝሃ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት አገር ናት። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኪነ ጥበብ ስራዎቿ በዓለም ላይ ትታወቃለች። ለጉብኝት ከተጋበዙት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አባል ሆኜ በዴልሂ፣ አግራና ባንጋሎሩ ከተሞች በተጓዝንባቸው ስፍራዎች ሁሉ የታዘብኩት ህንዳዊያን በስራና ትጋት ላይ መሆናቸውን ነው። ሁሉም ነገውን ለማሳመር የራሱን ድርሻ ለማኖር፤ ለሀገሩ እድገትና ልማት አሻራውን ለማኖር እንደሚታትር መረዳት ይቻላል።   ባረፍንበት ሆቴል ያሉ ሰራተኞች፣ በገበያ ስፍራ የምናገኛቸው ሰዎች እንዲሁም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሀገራቸው እድገትና ልማት ብሎም ነጋቸውን ለማሳመር የራሳቸውን ድርሻ ለማኖር ይታትራሉ። አብሬ ከነበርኳቸው ጋዜጠኞች ጋር ስናወጋ የምናነሳው በከተማዋ በተጓዝንባቸው ጎዳናዎች የምናየው የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በየተቋማት የሚታትሩ ሰራተኞች እንዲሁም በንግድ የተሰማሩ ሰዎች ደፋ ቀና ማለት ለአገር የሚያደርጉትን ልፋት ነው። አንድ ቀን በጋራ ሆነን ወደገበያ ስፍራ ስናቀና በፍጥነት የሚደርሱ ምግቦች ተመግበው ለመሄድ የሚፋጠኑ ህንዳውያንን ያየ የጋዜጠኛ ቡድኑ አባል መሰል ልምድና ጊዜ አጠቃቀም በአፍሪካም ሊለመድ የሚገባውና የአህጉራችንን የስራ ባህልና እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ ለአገሬው ህዝብ ታታሪነት እንደማሳያ አድርጌ ላነሳው ወደድኩ። በሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ አዲስ ሰው ሲያዩ ለማገዝ አና ስለነገሮች ለማስረዳት የሚፈጥኑ ዜጎችን ተመልክቻለሁ። በተጓዝኩባቸው ከተማዎች ያየኋቸውን ስፍራዎች ከማስታወሻዬ እየነቀስኩ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በቅድሚያ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የስድስት ሰዓት ተኩል በረራ በማድረግ የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረግናትን ዴልሂን እንቃኛለን። ዴልሂ- ታሪካዊ ህንፃዎችን ከአዲሶቹ ጋር አጣምራ የያዘች ጥንታዊ ስልጣኔን ከዘመናዊው ጋር አዋህዳ የምታንፀባርቅ ከተማ ናት። በከተማዋ በተዘዋወርንባቸው ስፍራዎች ሁሉ ከጎዳናዎቿ እስከ ህንፃዎቿ ምድረ ግቢ ድረስ በእፅዋት የተሞላችና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት የሰጠች መሆኗን በግልፅ ያሳየች ከተማ ናት። በዴልሂ ብቻም ሳይሆን በተዘዋወርንባቸው በሶስቱም ከተሞች ጎዳና ስንጓዝ ያየናቸው ግዙፍ ዛፎች ትናንት አገሪቷ ለእፅዋት የሰጠችው ትኩረት ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ አስተዋልኩ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንዲሁም በኮሪደር ልማት ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ካመጡት ለውጥ ባለፈ ለወደፊት የሚኖራቸውንም መዳረሻ አሻግሬ ለማየት አስችሎኛል። አሰላሳዮቹ - በዴልሂ ቆይታችን በመጀመሪያ ያቀናነው ጥናቶችን በመስራትና ውይይቶችን በማድረግ በኩል አበርክቶ እያደረገ ያለውን ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ አሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ነው። ተቋሙ በአገር ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የመስራት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ከኢኮኖሚና እድገት ባለፈ በኢነርጂ፣ አካባቢ፣ በደህንነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑና ለውሳኔ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በማመንጨት የአገሪቷን ህዝብና መንግስት እያገዘ ይገኛል። ከተቋሙ አባላት ጋር ባደረግነው ቆይታ ለራስ ችግር የራስ መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት አንስተዋል። የአፍሪካ አገራት ትብብር የአህጉሪቷን ልዕልና ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተነስቷል። የአሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን አባላቱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ጨርሰን በቀጣይ ያመራነው በህንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ባሉ አገራት ጭምር በባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ላይ አሻራ እያኖረ ወዳለው ራይትስ ወደተሰኘው ተቋም ነው። የህንድ የባቡር መንገድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት (Rail India Technical and Economic Service) የተሰኘው ይህ ተቋም ላለፉት 51 ዓመታት በባቡር መንገድ ጠበብቶች አማካኝነት በህንድና በመላው ዓለም ባሉ 62 አገራት በዘርፉ ሲሰራ ቆይቷል።   የእጅ ጥበብ ገበያ - ቀጣይ መዳረሻችን ደግሞ ዲል ሃት ኢና የተሰኘው የባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያዎች መገኛ ወደ ሆነው ገበያ ነው። ገበያው ባይገበዩበትም ዞረው እንዲቃኙ የሚያስገድድ አንዳች ድምቀትን የተላበሰ መሆኑን ባደረኩት ቆይታ አስተውያለሁ። የንግድ ማህበር የሆነው የህንድ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ሲአይ አይ) በዴልሂ ቆይታችን ካየናቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው። ተቋሙ የንግድ፣ ፖለቲካ፣ የትምህርትና የሲቪል ማህበረሰብ አመራር አባላትን በጋራ በማሰለፍ ዓለም አቀፍና የኢንዱስትሪ አጀንዳዎችን እንዲቀርፁ የሚሰራ ነው። አደጋን የሚቋቋም መሰረተ ልማት ጥምረት (CDRI) በነበረን ቆይታ ጥምረቱ ከአገራት፣ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችና መርሃግብሮች፣ ከፋይናንስና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የአየር ንብረትና የአደጋ ስጋትን የሚቋቋም መሰረተ ልማት አስተዳደር ላይ እየሰራ መሆኑን ተገንዝበናል። ጥምረቱ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም፣ በተቋማትና ህብረተሰብ አቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ይሰራል። ጥምረቱ 46 አባል አገራትና ስምንት አጋር ድርጅቶች ያሉበት ሲሆን፤ አገራትና ዓለም አቀፍ አካላትን በማስተባበር የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የጥናትና ፈጠራዎች ውጤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበትም ነው።   የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዴልሂ(IIT Delhi) ሌላው የጉብኝት መዳረሻችን ነበር። ኢንስቲትዩቱ በኢንጂነሪንግና ሳይንስ ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በርካታ ሰዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ችለናል። ብሄራዊ ሙዝየም - በኒው ዴልሂ የሚገኘው የህንድ ብሄራዊ ሙዚየም በአገሪቱ ያለ ትልቁ ሙዚየም ሲሆን፤ በጉብኝታችን ወቅት ለዘመናት የቆየች ቅሪተ አካልን ጨምሮ፣ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶችና የታሪክ አሻራ ማሳያ ስራዎችን ቀርበው ይጎበኙበታል። በዴልሂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደረገልን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባልና ውይይት ህንድና አፍሪካ የጠነከረ ቁርኝት ያላቸውና በንግድ አጋርነትት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑ ተመላክቷል። በተደረገልን ገለፃ ህንድና የአፍሪካ የንግድ መጠን 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው።   ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ፋርማሲዩቲካል ፣ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ፣ ማዕድን እና የባንክ ዘርፎችን ያላት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ወደ 75 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መድረሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ከህንድ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷም ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተነስቷል። ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በባህል ትስስር ጭምርም የተጋመደ መሆኑ ተመላክቷል። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቱ ካሉ አገራት ጋር የምታደርገው ትብብርና ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነስቷል። አግራ- የህንድ ታሪክ፣ ባህልና ኪነ ህንፃ መገለጫ በሆነችው አግራ ተገኝተን የጎበኘነው ህንድ ስትነሳ ስሙ ተያይዞ የሚነሳውን ታጅ መሃልን ነው። ታጅ መሃል በእምነ በረድ የተሰራ ውብ ኪነ ህንፃ ሲሆን፤ ንጉስ ሻህ ጃሃን ከሌሎች ሚስቶቹ ሁሉ አስበልጦ ለሚወዳት ሚስቱ ሙምታዝ መሀል ክብር ሲል የገነባው ድንቅ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ታጅ መሃልን ስንጎበኝ የነበረው ሙቀት ሀይለኛ ቢሆንም ላባችን እየተንቆረቆረ ንጉሱ ለፋርስ ልዕልቷ ሚስቱ የነበረውን ፍቅር በተመለከተ በአስጎብኚያችን የሚሰጠንን ማብራሪያ ስናደምጥና የፍቅር ሃያልነትን ስናደንቅ ነበር። በዴልሂ ከጉብኝታችን ባሻገር በኢንዲያን ጌትና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም በከተማዋ ጎዳናዎች ተዘዋውረን የህዝቡን ፍቅርና ተባባሪነት አይተናል። በተለይ ቦታ የጠፋን መሄድ ያሰብንበት ቦታ እንዳለ የሚያመላክት ፍንጭ በግርታችን ያስተዋሉ ከመሰላቸው "እዚህ መሄድ ፈልገህ ነው ይህን እዚህ ማግኘት ትችላለህ" የሚል ጥቁምታ በመስጠት እንግዳ ተቀባይነትና ሰው አክባሪነታቸውን ይገልፁልሃል። በዴልሂና አግራ የነበረንን ጉብኝትና ትዝታ እያሰላሰልን ቀጣይ መዳረሻ ያደረግናት ባንጋሎሩ ከተማን ነው። ባንጋሎሩ ቀጣይ ትረካችን ይሆናል።    
ስራዋን በውጤታማነት በማስቀጠል ለሌሎች ወጣቶችም መትረፍ የቻለችው ወጣት
May 22, 2025 1086
ብርሃኑ ፍቃዱ - ከሰቆጣ ኢዜአ በ2013 ዓ.ም የልብስ ስፌት ስራ የጀመረችው ወጣት ማህደር አስማረ፤ ነዋሪቷ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ሰቆጣ ከተማ ነው። ስራዋን በውጤታማነት የቀጠለችው ወጣት ከአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስታ ወደ ሶስት የልብስ ስፌት መኪና የደረሰች ሲሆን ካፒታሏንም ከዓመት ዓመት በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስራዋን ለመጀመርም ባጠራቀመችው አነስተኛ ገንዘብ ቤት ተከራይታ ነበር። ከልብስ ስፌት መኪናው በተጨማሪ የሌዘርና የጥልፍ ማሽኖችን በማስመጣት የፋሽንና ዲዛይን ስራና ማሰልጠኛ ማዕከል በመክፈት ለሌሎች ወጣቶች መትረፍ የቻለችበትን አቅም ገንብታለች።   የማሰልጠኛ ማዕከሉን ለመክፈት እስከ 500 ሺህ ብር ወጪ ማድረጓን የገለፀችው ወጣት ማህደር፤ 30 ተማሪዎችን ተቀብላ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የምዝገባና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃለች። "ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሴትነቴም ሆነ ሌላ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም" የምትለው ወጣት ማህደር ፤ የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከልን ከማስፋት ባለፈ በቀጣይ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልፃለች። ወጣት መሰረት ጌታቸው በማህደር የልብስ ስፌትና የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከል ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆናለች።   ከድርጅቱ በቂ የልብስ ስፌት ሙያ፣ ልምድና እውቀት መቅሰሟንና ለዚህም ማህደር እውቀቷንና ልምዷን ሳትሰስት በማከፈሏ ብቁ ሰራተኛ እንድትሆን አድርጋታለች ። የማሰልጠኛ ማዕከሉ በከተማዋ መከፈቱ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት በመሆን ሰርተው የሚለወጡበት እድል የከፈተ ነው በማለት ትገልጻለች። ከወጣት ማህደር ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ጠንክሮ መስራትንና ቁርጠኝነትን ትምህርት ወስጃለሁ ያለችው ወጣት መሰረት ፤ በልብስ ስፌት ዘርፍ ላይም ውጤታማ ለመሆን እየተጋች መሆኑን ትናግራለች። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ዲያቆን ኪዳነ ማርያም ገብረህይወት፤ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ለይተው ከተንቀሳቀሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ወጣት ማህደር ትልቅ አርአያ ናት ይላሉ።   ለአብነትም እንደ ወጣት ማህደር ያሉ ታታሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት በስራ እድል ፈጠራ ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። የወጣቷን አርአያነት ለማስፋት በቀጣይ የብድር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ እንደሚያበረታቱ አረጋግጠዋል። ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በባለፉት ወራት ለ11 ሺህ ሰዎች የስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አውስተዋል።      
የኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን ምጣኔ ቅነሳ ስኬቶች እና ቀሪ የቤት ስራዎች
May 13, 2025 1206
የዓለም የጤና ድርጅት (ደብሊውኤችኦ) የ2025 ዓለም የጤና ቀንን እ.አ.አ አፕሪል 7, 2025 አክብሯል። የዘንድሮው ዓመት የቀኑ መሪ ሀሳብ “ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ፣ ለመጻኢው ብሩህ ጊዜ” የሚል ነው። የዓለም የጤና ጉዳዮች የበላይ አካል የሆነው ደብሊውኤችኦ መሪ ሀሳቡን መሰረተ በማድረግ ዓመቱን ሙሉ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ አስመልክቶ ንቅናቄ ያደርጋል። በኢትዮጵያም የዓለም የጤና ቀን ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው እንጦጦ ፓርክ “ ከቃል ያለፈ የተግባር ምላሽ” በተሰኘ ሁነት ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች፣ የጤና ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሁነቱን በጋራ አዘጋጅተውታል። በእንጦጦ ፓርክ የነበረው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ሁነቱን አስቦ ከመዋል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ለእናቶች እና ህጻናት ሞት ቅነሳ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን ገልጿል። የእናቶች እና ህጻናት ጤና የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብት፣ የማህበራዊ ልማት እና የብሔራዊ ልማት ጉዳይም ጭምር እንደሆነ የዘንድሮው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ እናቶች መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጡ ነበር። ኢትዮጵያ ይሄን አሃዝ በመቀየር የራሷን ታሪክ ፅፋለች። በአሁኑ ሰዓት የእናቶች ሞት ምጣኔ ከ100 ሺህ እናቶች ወደ 195 ዝቅ ብሏል። ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ኢትዮጵያ በጤናው ስርዓት፣ የሰው ኃይል ስልጠና እና የአገልግሎት አቅርቦት ላይ እያደረገች ያለውን ዘላቂ ኢንቨስትመንት እንደሚያሳይ ድርጅቱ ገልጿል። ይሁንና አሁንም በኢትዮጵያ በየአመቱ በአማካይ 8 ሺህ ገደማ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር እንደሚሞቱ መረጃው ያመለክታል። በእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ እየተደረገው ያለው ዓመታዊ ንቅናቄ ለለውጦች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ቀሪ የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ እንደሚገባ የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሰው ኃይል ስልጠናን በማስፋት፣ የእናቶች እና ህጻናት ክብካቤን ማሻሻል፣ በዲጂታል መሳሪያዎች አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር ላይ መልካም ስራዎች ቢያከናውንም አሁንም የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ድርጅቱ አሳስቧል። የጤና መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥርን መጨመር ሌሎች ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው ብሏል። የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓትን ማጠናከር ሌላኛው በድርጅቱ የቀረበ ምክር ሀሳብ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቤጆይ ናምቢያር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ያለው የእናቶች እና ህጻናት ሞት አሳሳቢ እንደሆነና ጠንካራ ምላሽ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል። በዘላቂ ልማት ግቦች እ.አ.አ በ2030 ከ100 ሺህ እናቶች የሚሞቱን ወደ 70 ዝቅ የማድረግ ግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት ለማሳካት እየሄዱበት ያለው ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከተቀመጠው ግብ አንጻር ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በዓለም የፋይናንስ ፈተናዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በግልጽ ያሳየች ሀገር መሆኗ ተገልጿል። ዓለም በተግባር የታገዘ ምላሽ ከሰጠ መከላከል የሚቻሉ የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ማስቀረት ሊሳካ የማይችል ህልም አይደለም። ከእንጦጦ ፓርክ ጎዳናዎች አንስቶ በሀገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ የጤና ማዕከላት የእናቶች እና ህጻናትን ሞትን ለመቀነስ የሚወሰዱ እያንዳንዱ እርምጃዎች የወደፊቱን የዓለም መጻኢ ጊዜ ብሩህ የማድረግን ራዕይን የሚያሳካ ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ጽሁፉን ቋጭቷል።
ትንታኔዎች
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 3571
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች።   የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።   ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።    
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት 
Dec 16, 2024 2923
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ​ ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። ​​​ አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። ​​​ አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ​​​ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ​​​ ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። ​​​ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ​ እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት
Dec 13, 2024 3114
    የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድምታ ከቀንዱ ሀገራት የተሻገረ ነው። የቀጣናው ሀገራት ትስስርና ትብብርም እንደዚያው። በነዚህ ሀገራት መካከል የሚፈጠር መቃረን የሚያሳድረው ተጽዕኖም አድማስ ዘለል ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የግንኙነት መሻከር ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር በቀጣናው ስውርና ገሀድ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎችን ያሳሰበና ያስጨነቀ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። በቱርክዬ ርዕሰ ከተማ አንካራ የተደረሰው የኢትዮ-ሶማልያ ሥምምነት ግን ለበርካቶች እፎይታን ይዞ መጥቷል። ከኢትዮጵያና ሶማልያ ጋር መልካም ወዳጅነት ያላት ቱርክዬ የሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት ከጀመረች ውላ አድራለች። ምንም እንኳ ጥረትና ድካሟ በተደጋጋሚ ሳይሳካ ቢቆይም ካለፈ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚኒስትሮች ደረጃ ለማረቅ ተግታለች። በሦስተኛው ዙር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረገው ድርድር ግን ፍሬ አፍርቶላታል። ቱርክዬ እየተገነባ ባለው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ጎልተው እየወጡ ካሉ ኃያላን ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በአፍሪካ ውስጥ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነትም እያደገ መምጣቱ ይታወቃል-በተለይ በአፍሪካ ቀንድ። ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊና ዘርፈ ብዙ ትስስር ጠንካራ የሚባል ነው። ቱርክዬ ከቻይና ቀጥላ በኢትዮጵያ ግዙፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሀገር ናት። ከኢኮኖሚያዊ ቁርኝቱ ባሻገር ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያላቸው ትብብርም የላቀ ነው። ቱርክዬ ከሶማልያ ጋር ያላት አጋርነትም እየተጠናከረ የመጣ ነው። እናም የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ለቱርክዬ ሳንካ ነበር። ስለዚህ የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት በአንካራው ድርድር ዲፕሎማሲያዊ እልባት ማግኘቱ ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወሳኝ እርምጃ ሆኖላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአንካራ ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የቀንዱን ውጥረት አርግቧል። ስምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል። በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት መስማማት ችላለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማልያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የወደብ አማራጮችን በስፋት ለመጠቀም ለምትፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያና የሶማልያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በጉርብትና ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰሩ ወንድማማቾች እና እህታማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል። ይልቁንስ ሶማልያን ከአሸባሪዎች ለመከላከልና ሠላሟን ለማረጋገጥ ሲባል በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር የተሳሰረ መሆኑን ነው ግልጽ ያደረጉት። ኢትዮጵያ ለጋራ ሠላምና ልማት ከሶማልያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድም ለዚህ ሀቅ ጠንካራ እማኝነታቸውን ሰጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱ ሠላም መጠበቅ ለዓመታት የከፈለውን ዋጋ መቼም አይዘነጋም ሲሉ የሚገባውን ክብር አጎናጽፈውታል። ሶማልያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሠላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። ​ በጥቅሉ የአንካራው የአቋም መግለጫ የሁለቱን አገራት የጋራ አሸናፊነት ያንጸባረቀ ነው። ለዘመናት በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ፈጽሞ የተዘነጋ እና የማይታሰብ ይመስል የነበረውን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ በድፍረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ያስቻለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከሃገር አልፎ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ትስስር ጭምር ወሳኝ መሆኑ መግባባት የተደረሰበት ሆኗል። በተለያዩ አሰራሮች እና አግባቦች፣ በሠላማዊ መንገድ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ መግባባት የፈጠረ ነው። ይህን ሥምምነት ዕውን ለማድረግ በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ድርድሮች በማካሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መግባባት ችለዋል። በዚህ ረገድ ቱርክዬ ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለማገዝ ኃላፊነት መውሰዷ ደግሞ ዘላቂነት እንዲኖረው እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ነው። ኢትዮጵያና ሶማልያ በአንካራ የደረሱት ስምምነት ከአውሮፓ ኅብረት እስከ አፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እስከ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት አድናቆት የቸሩት ሆኗል። ይህ ስምምነት የሁለት አገራት ስምምነት ብቻ አይደለም። የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካ የመፍጠር ህልም አካልም ጭምር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የውዳሴው መነሻና መድረሻውም ደግሞ ስምምነቱ የአፍሪካ ቀንድን ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ወደ አህጉራዊ ትብብር የሚወስድ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሥምምነቱ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመባቱ በፊት ለቀንዱ አገራት የቀረበ ሥጦታ ነው። እናም የአንካራው ስምምነት ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ባለፈ አንድምታው ቀጣናውን የተሻገረ በመሆኑ የአፍሪካውያንና የወዳጅ ሀገራት በቅን መንፈስ የተቃኘ ድጋፍ ያሻዋል።   ሠላም!
ህዳሴ - በመስዋዕትነት የተገነባ ነገ
Nov 2, 2024 4219
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የኢትዮጵያውያን በጋራ የመቻል ትምህርት ነው። የወል ዕውነታቸው፣ የወል አቅማቸው፣ የጋራ ተስፋቸው በግልጽ የተንጸባረቀበት የአይበገሬነት ምልክት ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን እንዴት በጋራ መገንባት እንደሚችሉ በሚገባ ያሳዩበት ዳግማዊ አድዋ ነው - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ። አድዋ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የተዋደቁበት ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢኮኖሚ ሉአላዊነት የደም ዋጋ የተከፈለበት የትውልዱ የብሄራዊነት ማሳያ ነው። ህዳሴን ዕውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ከሴራ ዘመቻዎች እስከ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የደረሱ እንቅፋቶችን አልፋለች። በተለይም የግድቡ ግንባታ ወደማይቀበለስበት ደረጃ በደረሰባቸው ያለፉት 6 ዓመታት ፈተናዎቹ በርትተው ነበር። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተጓጉዘው እንዳይደርሱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት እንዳያመርቱና እንዳያቀርቡ በተለየዩ ቦታዎች ጥቃቶች ይሰነዘሩ ነበር። ቢሆንም ግን የማያባሩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የተንኮል ወጥመዶች በጣጥሶ ለማለፍ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወታቸውን ጭምር ገብረው ነገን ዛሬ መስራትን በህዳሴ ዕውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በርካታ መስዋዕትነት መከፈሉን ተናግረዋል።   ኢትዮጵያ ሁሌም በጋራ የመልማት እሳቤ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ታላቁ ህዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ልጆች ከአፍሪካ ለአፍሪካ የተሰጠ ገጸ በረከት እንዲሁም ጣፋጭ ፍሬውም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለተፋሰሱ አገራትም ብስራት መሆኑን ነው ያስረዱት። የታላቁ የኢትዮጵየ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አኩሪ ደረጃ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ከገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀታቸው ባሻገር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 2864
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 2470
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 3938
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል።     በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል።   የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 48845
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 44186
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 28182
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25546
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 23756
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 21880
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 21745
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 21372
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 48845
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 44186
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 28182
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25546
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ከሮም እስከ አዲስ አበባ 
Jul 11, 2025 374
ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ይካሔዳል። የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ኢንቨስትመንት እና ፋይናንስ፣ የምግብ ስርዓት ሽግግር ሁለንተናዊነትና የተገቡ ቃሎችን ከመፈጸም አንጻር ያለውን የተጠያቂነት ስርዓት ማጠናከር ጉባኤው ትኩረት ያሚያደርግባቸው ሀሳቦች ናቸው። ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተምግብ ጉባኤ በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም በጣልያን ሮም የተካሄደው የመጀመሪያ የተመድ ስርዓት ምግብ ላይ የተገቡ ቃሎች ትግበራ ሂደትን መነሻ በማድረግ የሚካሄድ ነው። በመጀመሪያው ጉባኤ ላይ የ182 ሀገራት ተወካዮች፣ 21 የሀገራት መሪዎች እና 126 ሚኒስትሮችን ጨምሮ 3 ሺህ 300 ተሳታፊዎች ታድመውበታል። በጉባኤው ላይ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሀገራት እና ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ስድስት የትኩረት አቅጣጫዎችን ይፋ አድርገው ነበር።   የምግብ ስርዓት ስትራቴጂዎችን ከብሄራዊ ፖሊሲዎች ጋር ማስተሳሰር፣ ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓት አስተዳደር መገንባት፣ በጥናት፣ ዳታ፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ ሁሉን አቀፍ የእቅድ ዝግጅት እና ትግበራን ማጠናከር፣ በምግብ ስርዓት ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የአጭርና የረጅም ጊዜ የአነስተኛ ወለድ የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ከትኩረት አቅጣጫዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ። ኢንቨስትመንት፣ የበጀት ድጋፍ እና የእዳ አስተዳደር ሌላኛው የትኩረት መስክ ነው። በጉባኤው ላይ 300 ገደማ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የምግብ ስርዓት ሽግግርን እውን ለማድረግ ቃል መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል። በተለይም እ.አ.አ 2030 የማይበገር፣ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የምግብ ስርዓት መገንባት እንዲሁም ምግብ ለሁሉም የሚለውን ግብ ለማሳካት ጥረት እንደሚያደርጉ ሀገራት ቃል ገብተዋል።   ሁሉን አሳታፊ ነው በሚል አድናቆት ያገኘው ጉባኤው በስርዓት ምግብ ላይ ግንዛቤን ከማሳደግ እና አቅምን ከመገንባት አንጻር ውጤታማ እንደነበር ይነሳል። የምግብ ስርዓት ሽግግር አንገብጋቢና ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ እንደሆነም በጉባኤው ተወስቷል። ኢትዮጵያም በስርዓተ-ምግብ ጉባኤው ላይ የነበራት ተሳትፎ ስኬታማ ነበር። በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ውጤታማ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳዩ ልምደችን አቅርባለች። በጉባኤው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና በስርዓተ ምግብ ሽግግር ለማምጣት እየወሰደች ባለው የፖሊሲ እርምጃና ውጤቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገውም ነበር። ኢትዮጵያ የኩታ ገጠም እርሻን በማስፋፋት፣ ለየስነ ምህዳሩ ተስማሚ የሆኑ የተሻሻሉ ዝርያዎችን፣ አነስተኛ ቴክኖሎጂዎችንና ሌሎች ግብአቶችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለኢኮኖሚው ዕድገት የላቀ አበርክቶ እንዲኖረው እየሰራች መሆኑንም አንስተዋል።   በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ መስኖ በተለይም በበጋ ስንዴ ምርት እና በሌማት ትሩፋት እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን ለጉባኤው አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የስራ እድል ፈጠራን ለማበረታታትም ሆነ በስርዓተ-ምግብ ሽግግር ለማድረግ አዲስና የተለየ የፋይናንስ ሞዴል ያስፋልጋል በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል። ዘላቂና አካታች የስርዓተ ምግብ ሽግግር አቅጣጫዎች ጥሩ አፈጻጸም የታየባቸው ቢሆንም በፋይናንስ አቅርቦት፣ በዓለም አቀፍ ትብብር፣ በአየር ንብረት ለውጥና በሰው ሰራሽ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቋቋም በትብብር በመስራት በኩል በርካታ ችግሮች መስተዋላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ የገለጹት። በመሆኑም ሀገሮች በስርዓተ ምግብ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በአነስተኛ እርሻ ስር-ነቀል ለውጥ በማምጣት ሽግግሩን ማፋጠን እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፅንኦት አንስተዋል። ለዚህም የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎን እንዲያሳድጉና ለግብርና ቴክኖሎጂ መስፋፋት እንዲሰሩ ጠይቀዋል ። ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ-ምግብ ጉባኤ የመጀመሪያውን ጉባኤ መነሻ በማድረግ በተለያዩ አጀንዳዎች ይመክራል። ቀዳሚ ትኩረቱ ከመጀመሪያው ጉባኤው በኋላ የምግብ ስርዓትን አስመለክቶ ያሉ ለውጦች ምንድን ናቸው? የሚለው ነው። በጉባኤው ላይ ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን አስመልክቶ ያገኟቸውን ስኬቶች እና የጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ። በተለይም የምግብ ስርዓት ሽግግሩ ሁለንተናዊነት እና ሁሉን አሳታፊነት ዋንኛ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ሁለተኛው የጉባኤው አጀንዳ በመንግስታት፣ የምግብ አምራቾች፣ የንግድ ማህበረሰቡ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን አጋርነት ማጠናከር ነው። የባለድርሻ አካላት ትብብር መጠናከር የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንዳለው ታምኖበታል። በተጨማሪም ሀገራት እና ተቋማት በሮሙ ጉባኤ የገቧቸው ቃሎች የደረሱበትን ደረጃ የሚገመገም ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎም ይጠበቃል። ለምግብ ስርዓት ሽግግር የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት እና የኢንቨስትመንት መጠንን መጨመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ጉባኤው ይመክራል። ለምግብ ስርዓት ሽግግር ስራዎች በአነስተኛ ወለድ የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ፣ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀም እና ሀገር በቀል የፋይናንስ መሰብሰብ አቅምን ማጎልበት ላይ ምክክሮች ይደረጋሉ ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በሮም በነበረው ጉባኤው ላይ ይፋ ያደረጓቸው ስድስት የትኩረት መስኮች አፈጻጸም ግምገማ ሌላኛው አጀንዳ ነው። በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ የሚካሄደው ሁለተኛው የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ የሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ አርሶ አደሮች፣ አምራቾች እና የምግብ ስርዓት ሽግግር ተዋንያንን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። በጉባኤው ላይ ከዋናው ሁነት ጎን ለጎን የምግብ ስርዓት ትራስፎርሜሽን እና የስርዓተ ምግብ ሽግግርን አስመልክቶ በርካታ የጎንዮሽ ስብስባዎች ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ በምግብ ስርዓት ሽግግር ያከናወናቸውን ስራዎች አስመልክቶም በጉባኤው ተሳታፊዎች የመስክ ምልከታ ይደረጋል። ኢትዮጵያ በስርዓት ምግብ ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እና በግብርናው ዘርፍ ባደረጋቻቸው ሀገር በቀል ሪፎርሞች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች ጉባኤውን እንድታስተናግድ የተመረጥችባቸው ምክንያቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር እየተወጣች ያለው የመሪነት ሚና እና በማደግ ላይ ከሚገኙ ሀገራት በስርዓተ ምግብ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መሆኗ ተመድ ዓለም አቀፉን ከፍተኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲያደርግ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግርን ለማሳካት እያከናወነች ባለው ተግባር ዙሪያ ተሞክሮዋን ለዓለም ማህበረሰብ የማስገንዘብ ስራ ታከናውናለች። ተባባሪ አዘጋጇ ጣልያን እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በምግብ ስርዓት ሽግግር ውጤታማ ተሞክሮ ያላት ሀገር ናት። የደቡብ አውሮፓዊቷ ሀገር ከኢትዮዮጵያ ጋር በመሆን ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን እየሰራችም ትገኛለች። ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ተሳታፊዎች ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እየጠበቀች ትገኛለች።  
በቻይና ይህም አለ!
Jul 8, 2025 384
  በአብነት ታደሰ በርግጥ ከዓለማችን የጥንት ስልጣኔ ምድሮች አንዷ ናት- ቻይና። በታሪክ ገጾች ‘የግኝት ምድር’(Land of Invention) የሚል ተቀፅላ የሰፈረላት የሺህ ዘመናት ባለታሪክ ሀገር። የጥንት ቻይኖች አያሌ ‘ግኝቶችን’ ለዓለም አካፍለዋል። ወረቀት ፈብርከው ዘመናቸውን ጽፈዋል፣ ማተሚያ ቁስ ፈጥረው አትመዋል፤ ኮምፓስ ፈልስመው አቅጣጫ ጠቁመዋል።በ221 ዓመተ-ዓለም አንድ ወጥ ስርወ መንግስት መስርተው በሀገረ መንግስት የታሪክ ዑደት ከፍታንም ዝቅታንም አይተዋል። በቻይና አያሌ ስርወ መንግስታት ተፈራርቀዋል። ቻይናውያን ክፉውንም ደጉንም ችለው አልፋዋል። የሕዝቡ ጽናት፣ ጥበብ፣ ቱባ ባህል፣ ታሪክና ብልሃት በቻይና ግንብ ይመሰላል። ግንቡም ዝም ብሎ የጡብ ክምር አይደለም፤ የመሰረተ-ጽኑነታቸው ትዕምርት(symbol) እንጂ። ሲሶውን ሕዝቧ በያንግትዝ ወንዝ ተፋሰስ ጉያ አቅፋ፣ ጥንተ ማንነቷን ሸክፋ ዕልፍ ዘመናትን ተሻግራለች። የቻይና ስርወ መንግስታት ከስመው የዛሬዋ ኮሚኒስት ሪፐብሊክ ቻይና ከተመሰረተች ገና አንድ ምዕተ ዓመቷ ነው። ቅድመ ልደተ ክርስቶት በ221 ዓመተ-ዓለም የተመሰረተው ወጥ-ስርዎ መንግስት በመልከ ብዙ ምክንያቶች ተዳከመ። በፈረንጆቹ 1912 የመጨረሻው የቻይና ስርዎ መንግስት ተንኮታኮተ። ዘመናዊቷ የቻይና ሪፐብሊክ በዚህ ዘመን ተመሰረተች። ዳሩ ለውጡ አልጋ በአልጋ አልሆነም። ለሺህ ዘመን የጽኑ ስርዓተ መንግስት ባለቤቷ ሀገር ቻይና በአስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ታመሰች። ወረራንም፣ ዕልቂትንም አስተናገደች። በዘመኑ ማኦ ዘዶንግ የሚባል ባለራዕይ መሪ በቻይና ምድር ተነሳ። አርቆ አሰበ፤ ሀሳቡንም አሰረጸ፤ በዓላማ ጸንቶ ክፉ ዘመን ተሻገረ። ማኦ እና ተከታዮቹ ለቻይና ትንሳኤ ታተሩ። በጽናት ታገሉ። ለመስዕዋትነት ቆርጠው ተነሱ፤ ዋጋም ከፈሉ። በአውሮፓዊኑ ዘመን አቆጣጣር በ1949 የዛሬዋን የቻይና ሕዝባዊ ኮሚኒስት ሪፐብሊክ መሰረተ። ሃሳቡን ወደ ፖሊሲ ቀየረ፤ ተገበረውም። ቻይናን በኢንዱስትሪና ግብርና ምርት በንቅናቄ የማስፈንጠር ፕሮግራምንም (Great Leap Forward) ገቢራዊ አደረገ። ሆኖም ፖሊሲው በአንዴ ፍሬ አላፈራም። በወቅቱ በተፈጥሯዊና በሌሎች ምክንያቶች ቻይና በረሀብ ጠኔ ተመታች። ቻይናዊያን ተራቡ፤ ጎረቤት ሀገራትን ደጅ ጠኑ፤ ታላቁን ረሀብ መሻገር ያልቻሉ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናዊያን በረሀብ አለቁ። በቻንግሻ የሚገኘው የማኦ ዘዶንግ ግዙፍ ሐውልት መራራ ጽዋን ተጎነጩ። የሀገሪቷ መሪ ማኦ ዘዶንግ በወቅቱ ፈተና ተስፋ ሳይቆርጥ ሀገር አሻጋሪ ፖሊሲውን ገቢራዊ አደረገ። ልመናን ለትውልድ ላለማውረስ፣ ንቅዘትን(ሙስናን) ነውር የሚያደርግ ስርዓት አጸና። ስራን ወንጌል፤ ሙስናን ወንጀል ያደረገ ጽኑ ስርዓተ መንግስት ገነባ። ከራሷ አልፋ ለዓለም የተረፈችዋን የዛሬዋን ቻይና በጽኑ መሰረት ላይ አነበረ። የዛሬዋ ቻይና ከዓለማችን ቁንጮ ልዕለ ሃያል ሀገራት አንዷ ናት። ከራሷ አልፋ ለዓለም ተርፋለች፤ የቻይና ቴክኖሎጂ ምጥቀትና ርቀት ዓለም ጉድ አሰኝቷል። በቅርቡ ሀገረ ቻይናን ከጎበኙ ጋዜጠኞች አንዷ ሆኜ ‘መልክዓ ቻይና’ን በወፍ በረር ቃኘሁ። በዚህ ማስታወሻዬ በቻይና የቴክኖሎጂ ልህቀትና ምጥቀት ላይ ብቻ አተኩራለሁ። ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ባላት፣ በ14 ሀገራት በምትዋሰነው፣ በአንድ ኮሚኒስት ፓርቲ በምትመራው ሀገር ቻይና በነበረኝ የ15 ቀናት ቆይታ ቻይና እንደ ጥንተ ታሪኳ ሁሉ በዘመኑ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ ያላትን የመራቀቅ ጥግ ታዘብኩ። ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን የመቅደም እሽቅድድሟ ‘አጃይብ’ ያሰኛል። በሀገሪቷ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ እና በማዕከላዊ ቻይዋ በምትገኘው የሁናን ግዛት ዋና ከተማ ቻንግሻ ምልከታዬ ቻይና ’ከተባለላት በላይ’ የቴክኖሎጂ ምጥቀቷ አስደንቆኛል። ምናልባትም የመጀመሪያ ጉዞዬ መሆኑም ነገሩን በአንክሮት እንድመለከት ሳያስገድደኝ አልቀረም። የሀገሪቷ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ እና ጥንታዊቷ ቻንግሻ ከ22 ሚለዮን የሚልቅ ህዝብ በጉያዋ የታቀፈችው ታላቋ ቤጂንግ ከተማ ከዓለማችን ግንባር ቀደም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህል፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከላት አንዷ ናት። የአዲስ አበባ እህት ከተማ በዚህ ወቅት ሞቃታማ አየር ጸባት አላት። ቤጂንግ የ21ኛው ክፍል ዘመን የኪነ ህንፃና ክትመት ቴክኖሎጂ ያበበች ብቻ አይደለችም፤ ይልቁኑም በዛፎች ሀመልማላዊ ገጽታ የተላበሰች ውብ መዲና እንጂ። በሕንፃዎችም፣ በዛፎችም የተደነነች ከተማ። በተፈጥሮ የበቀሉ የሚመስሉ ሰማይ ታካኪ ሕንጻዎች፤ የመንገድ መሰረተ ልማት ስፋት፣ ጽዳትና ጥራት ‘ኩልል’ ያለች፣ ‘ምልል’ የምታደርግ ከተማ ያደርጋታል። ቤጂንግ ከተማ ከዘመናችን አስደናቂ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዱ በሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) ሕይወትና ኑሮን እንዴት እንዳቃለለ የቤጂንግ የዕለት ከዕለት ክዋኔ ሁነኛ ማሳያ ነው። ቻይኖች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ተጠበዋል፤ መጠበብ ብቻም ሳይሆን ኑባሬያቸውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት መር አድርገዋል። ከሮቦት መስተንግዶ እስከ ሰው ሰራሽ ፀሐይ መራቀቅ ይስተዋላል።   ካረፍኩበት ሆቴል (15ኛ ወለል ላይ ከሚገኘው መኝታ ክፍሌ) ሆኜ ያዘዝኩት ምግብ በቅጽበት አስተናጋጇ ‘ከች’ ብላ ትደውላለች። ፍጥነቷ ስትገረም፤ አስተናጋጆች ሮቦቶች መሆናቸውን ስትመለከት ይበልጥ ትደነቃለለህ። በክፍሌ ውስጥ ማብሪያ ማጥፊያ ስጫን መጋረጃው ሲከፈት መደንገጤን አልሸሽግም፣ ከምሽቱ 3 ሰዓት ፀሐይ አለመጥለቋን ስመለከት ‘የቻይና ሰው ሰራሽ ፀሐይ ወጣች እንዴ?’ ማለቴ አልቀረም። በነገራችን ላይ የቻይና የሰው ሰራሽ ፀሐይ ሳይንሳዊ ፈጠራ ሁለት ግዜ ተሞክሮ ያለምንም እንከን እንደሚሰራ ነግረውናል። የሰው ሰራሽ ፀሐዩ ሃይድሮጅን እና ዱተሪየም ጋዞችን እንደ ሀይል ማመንጫ ነዳጅነት በመጠቀም ንጹህ ኢነርጂን ለማመንጨት ታስቦ ዲዛይን እንደተደረገና ሰው ሰራሽ ፀሐይ በርሐን ከተፈጥሮ ፀሐይ 13 እጥፍ ያክል ሙቀት እንደሚያመነጭም ሰምተን ተደንቀናል። የቻይና ሰው ሰራሽ ፀሐይ ፕሮጀክት የሥራ ሰዓትን ከ13 ሰዓት ወደ 24 ሰዓት ለመጨመርና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብ የሰነቀ ነው። በቻይና በሰዉ ቅርፅ የተሰሩ ሮቦቶች በእግር ኳስ ጨዋታዎች ተወዳጅነት አትርፈዋል። ቤጂንግ የሚገኘው ሂዩማኖይድ የተሰኘ የሮቦት ቡድን የሰራቸው ሮቦቶች አመርቂ ውጤት ከራቀው የሀገሪቷ እግር ኳስ ቡድን ይልቅ የሀገሬውን ቀልብ እንደሳቡ ይነገራል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት በታገዘ የሮቦቶች ውድድር አያሌ ቻይናዊያን ይታደማሉ። ሮቦቶቹ በጨዋታ መሐል ቢወድቁ በራሳቸውን ይነሳሉ፤ ቢጎዱም ከሜዳ የሚወጡበት ስርዓት ተዘርግቷል። የታላቋ ቻይና ሰዎች ቴክኖሎጂን ከችግር መፍቻነት ወደ መዝናኛነትም አልቀውታል። በሀገራችን እንደ አዲስ ቴክኖሎጂ በንግዱ ስርዓት ውስጥ እየተዋወቀ ያለው የፈጣን ምላሽ መለያ ወይም ኪው አር ኮድ(Quick Response code) በቻይና ዕለታዊ ከዋኔዎች ቅንጦት አይደለም። በቻይና ማንኛውም ግልጋሎት በዚህ በዲጂታል ስርዓት ይከወናል። እንደሌሎች ስልጡን ሀገራት ሁሉ በንክኪ የሚደረግ ገንዘብ ዝውውር ቀርቷል። በቤጂንግ ጎዳናዎች በኪው አር ኮድ(QR Code) በሚንቀሳቀሱ ሞተር ሳይክሎችን በየመንገዱ ተሰድረዋል፤ የፈለገ መንገደኛ ሳይክሎችን በመጠቀም ወደ ፈለገበት ስፍራ ተንቀሳቅሶ ክፍያውን በኪው አር ኮድ ከፍሎ ይሄዳል። ሌላውም እንዲሁ። በአዲስ አበባ መኖሪያ ሰፈሬ የነበሩ ሳይክሎኝ ከደጃችን ደብዛቸው እንደጠፋ ሳስብ በቻይኖች ብልሃት፣ ታማኝነትና የከተሜነት ልህቀት ቀናሁ። በርግጥ በቻይና ኪው አር(QR) ኮድ ለተገለገልንበት መክፈያ ብቻ ሳይሆን ለልመናም መዋሉን ሲመለከቱ ፈገግ ሊሉ ይችላሉ። በቻይና ይህም አለ በማለት። በርግጥ በቤጂንግ የሰው እጅ ከሚያይ ይልቅ ጆሮቸውን ቢቆጥርጣቸው የሚሰሙ የማይመስሉ አዛውንቶች ሳይቀር በስራ ላይ ተጠምደው ይስተዋላሉ። ከቻይናውያን ጋር ለመግባባት በተለይም በንግድ ማዕከላት የቻይንኛ ቋንቋ መረዳት ግድ ይላል። “ሃው ማቺ፣ ጉዳ ጉዳ፤ ሺሼ፣ ኢ፣ አር…” እና መሰል ቃላት ማወቅ ይበጃል። ከዚህ ባለፈ በምልክት መግባባት አልያም በቋንቋ ተርጓሚ መተግበሪያ መጠቀም ያሻል። የቻይና ሰራሽ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርቶች በራሳቸው ብራንድ፣ ቋንቋና መልክ እየተመረቱ በተመጣጣሽ ዋጋ ለህዝቦቿ ተደራሽ እየተደረጉ ነው። የቻይና የራስ-በቅነት ጥረት ያስቀናል። በቴክኖሎጂ፣ በባሕልና በኢኮኖሚ ተጽዕኖ ተላቀው በራሳቸው ለመቆም የሄዱበት ርቀት ግሩም ነው። ግብይቶች በራሳቸው ገንዘብ ብቻ ይከወናል። በወቅቱ ምንዛሬ አንድ የአሜሪካ ዶላር ሰባት የቻይና ገንዘብ(ዩዋን) ነው። ከምዕራባዊያን ማህበራዊ ትስስር ገጾች(ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ) በሕግ በማገድ የራሳቸውን መተግበሪያ አበልጽገው ገቢራዊ አድርገዋል። ‘ዊቻት’ የተሰኘው መተግበሪያ ሁሉም ቻይናውያን መገልገያ ነው።   ከቤጂንግ ሌላ ያስደነቀችኝ ጥንታዊቷ ቻንግሻ ከተማ ነች። ቻንግሻ ስመ-ብዙ ነች። ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ ዕድሜ ጠገቧ የሁናን ግዛት ርዕሰ መዲና ቻንግሻ ‘የከዋክብት ከተማ’ ትሰኛለች። በነገራችን ላይ ማኦ ዘዶንግ ትውልዱ ሁናን ግዛት ውስጥ ነው። ቻንግሻ በስራ ከተማነቷ ‘የማታንቀላፋው መዲና’ ትባላለች። በመዝናኛ ስፍራነቷ ‘የተዝናኖት መነሃሪያ’ የሚል ተቀጥላ ስም አላት። ‘የሚዲያ ጥበብ’ ስፍራም ትሰኛለች። በኢንዱስትሪ፣ በጥንታዊ ሐውልቶች፣ አብያተ መቅደሶች፣ ታሪካዊ ስፍራዎች መገኛ በመሆኗ በቱሪስቶች ተወዳጅ ከተማ ናት። ትናንትና ዛሬን ያዋደደች፣ ታሪክና ባህል ባዛነቀችዋ ቻንግሻ የአምስት ቀናት ቆይታዬ ብዙ ገጽታዋ አስደምሞኛል። የሻንግ ወንዝን ተንተርሳ፣ በተራራማ፣ በሜዳማና ኮረብታማ መልክዓ ምድር በማዛነቅ የተቆረቆረች በመሆኗ የስብት ማዕከል ሆናለች። እንደ ቤጂንግ በደን የተከበበች፣ በዘመነኛ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እና በታሪካዊ ኪነ ሕንጻዎች የተጌጠች ከተማ ናት። ከዚህ ባሻገር የአምራች ኢንዱስትሪዎች መናገሻም ናት። የምቹ ከተሜነትና ጠንካራ የስራ ባህል በግላጭ የሚስተዋልባት ከተማ። የዓለማችን ገዙፉ በጣም ሞቃታማ አየር ጸባይ ባላት ቻንግሻ ሌት ከቀን ይሰራል። ፋብሪካዎቿ አይተኙም። ሌትና ቀኑ የሚታወቀው በሰዓት ብቻ እንጂ የስራና የንግድ ድባቡ እኩል ነው። ብርሃናማዋ ቻንግሻ ‘የቻይዊያን መስቀል’ በተሰኘው በቀይ በተቀለመው መስቀልም ትታወቃለች። በርግጥ ከዓለማችን ግዙፍ ማማዎች አንዱ የሆነው ሕንጻም መገኛ ናች። በጥቅሉ የቻይና ጉብኝት ትዝብቴ የገናና ታሪክ ባለቤቷ ሀገር ከባድ ውጣ ውረዶችን አልፋ ዛሬ ዓለምን እየቀደመች መሆኑን ሳስብ፤ እንደቻይና ሁሉ የሺ ዘመናት ገናና ታሪክና አኩሪ ገድል ያላት ኢትዮጵያስ የሚል ተጠየቅ እንዳውጠነጥን አድርጎኛል። ቻይናዊያን የዘመን የፈተና ቋጠሮዎቻቸውን ፈታተው ከዛሬ ከፍታ ሰገነት ላይ ወጥተዋል። ከዛሬም በበለጠ ነገን በጽኑ መሰረት ላይ እየገነቡ ነው። እኛስ? ብዬ ሳስብ በቁጭትና በተስፋ ተዋጥኩ! ሰላም!
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም