ቀጥታ፡

ማሊ እና ዛምቢያ አቻ ተለያዩ  

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታ ማሊ እና ዛምቢያ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ላሲን ሲናዮኮ በ61ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ማሊን መሪ ሆና ነበር። 

ይሁንና ፓትሰን ዳካ በ92ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ለዛምቢያ ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝታለች። 

ማሊ በ41ኛው ደቂቃ ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት ኤል ቢላል ቱሬ አምክኖታል።

ውጤቱን ተከትሎ ማሊ እና ዛምቢያ በውድድሩ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። 

በምድብ አንድ ትናንት አዘጋጇ ሞሮኮ ኮሞሮስን 2 ለ 0 በማሸነፍ በሶስት ነጥብ ምድቡን እየመራች ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም