ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ማንችስተር ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን በማሸነፍ በሊጉ መሪነት ቀጥሏል
Sep 5, 2026 69
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በ26ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። የ26 ዓመቱ አጥቂ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሶስት አድርሷል። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ በጨዋታው ላይ በተጋጣሚው ተፈትኗል። ተጋጣሚው ኮቨንተሪ ሲቲ ግብ ሊያስቆጥርባቸው የሚችልባቸውን ግልጽ እድሎችን አምክኗል። በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ከቼልሲ ወደ ማንችስተር ሲቲ የተዘዋወረው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ በመሪነነቱ ቀጥሏል። ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኮቨንተሪ ሲቲ ያለ ምንም ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በአራተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከከተማ ተቀናቃኙ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርገው የደርቢ ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው። ኮቨንተሪ ሲቲ ከብራይተን ጋር የሚጫወት ይሆናል። በሌሎች መርሐ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፏል። ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ብራይተን ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ሁል ሲቲ ከአስቶንቪላ በኤምኬኤም ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 5, 2026 98
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የማይነጣጠል ታሪካዊ ቁርኝት ያላትና የባሕር በር ጥያቄዋም የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከጥንት ጀምሮ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ግዛት ወሰን አካል ሆኖ መኖሩን አውስተዋል። ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎችም የራሳቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም በቀይ ባሕር በኩል እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ ይነግዱ እንደነበር አውስተዋል። ከ1950ዎቹ በኋላም አሰብና ምፅዋ የኢትዮጵያ ዋና የባሕር በር ወደቦች ሆነው ማገልገላቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም የኢህአዴግ መንግሥት ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት በሌለው ሁኔታ፣ ያለምንም የሕዝብ ውይይትና ያለ በቂ ጥናት በድንገተኛ ውሳኔ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ ማድረጉንም አብራርተዋል። ለሀገርና ለሕዝብ ኃላፊነት በማይሰማው መንግሥት የተፈጸመው ይህ የጥፋት ውሳኔ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ መፍጠሩን ጠቁመዋል። በባሕር ንግድ በተሳሰረች ዓለም ውስጥ 130 ሚሊዮን ሕዝብን ይዞ ያለ ምንም የባሕር መውጫ ረጅም ጉዞ ማሰብ አይቻልም ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ። የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በቁጭት የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁን ያለው መንግሥት ኃላፊነት የሚሰማው በመሆኑ የባሕር በር አጀንዳን ፊት ለፊት ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል። የባሕር በር ለንግድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን ከጥቃት ለመከላከልም ወሳኝ የብሔራዊ ደህንነት ዓምድ ነው ብለዋል። አክለውም የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ትውልድ የማይተወው የህልውና አጀንዳ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል። በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ ሀገራት የሕዝብ ብዛትና ኢኮኖሚ ተደምሮ የኢትዮጵያን ግማሽ አቅም እንኳ እንደማይደርስ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መምጣት ለእነዚህ ሀገራትም ትሩፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል። ቀጣናው የኃያላን ሀገራት መራኮቻና የተለዋዋጭ ሁኔታዎች ሰለባ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ አኳያ የቀጣናው ሀገራት በጋራ መልማት የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል ። የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመቀነስ በኢኮኖሚና በታሪክ የተሳሰረውን ሕዝባቸውን ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአካባቢው ግዙፍ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅስ መሆኗ ፋይዳው ድንበር ዘለል ነው ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ፥ ከባሕር በር ተነጥላ ልትኖር ስለማትችል የአካባቢው ሀገራት የመውጫ በር ሊሰጧት ይገባል ነው ያሉት። ይህ ካልሆነ ግን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር ያላት በመሆኗ በጊዜ ሂደት በተፈጥሯዊ መንገድ የታፈነው ጥያቄ መፈንዳቱ አይቀሬ ነው ብለዋል። ይህ እንዳይሆን የቀጣናው ሀገራት በሰላማዊ መንገድ የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመከላከልና ሀብትን በጋራ በመጠቀም መርህ ለኢትዮጵያ የባሕር በር በማመቻቸት የጋራ ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ ጉብኝት
Sep 5, 2026 88
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ። የሰላም ሚኒስቴር ሀገር በቀል ዕውቀትና ባህላዊ ሀብቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አድርገዋል።   የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከልምድ ልውውጥና ውይይቱ ባለፈ በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።   የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ሕንፃ ግንባታ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል።
የአየር መንገዱ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ
Sep 5, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎብኝተዋል። ሰራተኞቹ ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተመልክተዋል። እንዲሁም የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችንም ጎብኝተዋል።   በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው፤ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የአዲስ በባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።  
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኢንዱስትሪ ዘርፍ በመጣው ለውጥ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል
Sep 5, 2026 96
ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 30/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኢንዱስትሪ ዘርፍ በተመዘገበው ስኬት በርካታ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን "የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ልህቀት፣ ለከፍተኛ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛር በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል።   በማዕከላት የገቡ መካከለኛና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ምርታማነታቸው ከማደጉ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቅሰዋል። ባዛርና ኤግዚቢሽኑም አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ከማድረግ ባሻገር የገበያ ትስስር በመፍጠር የጎላ ሚና እንዳለው አስታውቀዋል። በዘርፉ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራም እንዲሁ።   ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አቅሙን በማጎልበት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በማጠናከርና የኢንቨስትመንት ምህዳሩን በማስፋት ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት ደግሞ የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን ብርሃኑ (ኢ/ር) ናቸው። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 አልሚ ባለሀብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውንና ከ4 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውቀዋል።
የሚታይ

ተመድ የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ አጸደቀ
Sep 4, 2026 1013
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ፤ የአፍሪካን እውነተኛና ትክክለኛ መልክዓ-ምድራዊ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ በይፋ አጽድቋል። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የተላለፈው በአፍሪካ ህብረት ስም በቶጎ አቅራቢነት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ ዓላማውም ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተዘጋጀውን የተዛባ የካርታ አሰራር እንዲያከትም ማድረግ ነው። በውሳኔው መሠረት፣ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለውና ለአፍሪካ አህጉር ትክክለኛ ያልሆነ ስፋት ይሰጥ የነበረው የሜርካቶር ካርታ ከስራ ውጪ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል። በምትኩ ደግሞ እንደ እ.ኤ.አ. በ2018 ይፋ የሆነውና የምድርን ትክክለኛ መጠንና ድርሻ የሚያንጸባርቀው "ኢኩዋል አርዝ"(Equal Earth) የመሳሰሉ ዘመናዊ እና እኩል አቀራረብ ያላቸው የካርታ ቀመሮች በስራ ላይ ይውላሉ። ይህ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ 164 ሀገራት የውሳኔ ሀሳቡ እንዲፀድቅ ድጋፍ ሰጥተዋል። የተለመደውና የድሮው ካርታ የተሰራው እ.አ.አ በ1569 በደች (ፍሌሚሽ) ካርታ ሰሪ በጄራርዱስ ሜርካቶር ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በወቅቱ ለባህር ዳር መርከበኞች ማሰሻነት እንዲያገለግል ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ካርታ ከምድር ወገብ (Equator) እየራቀ ሲኬድ የመሬትን ስፋት እያጋነነ የሚያሳይ በመሆኑ፣ የምድር ወገብ አቅራቢያ የሚገኙ አካባቢዎችን በዕይታ በእጅጉ እንዲቀንሱ አድርጓል። በዚህ የተዛባ የካርታ አሰራር ምክንያት አፍሪካ ከግሪንላንድ ደሴት ጋር ተቀራራቢ መጠን እንዳላት ሆና ስትታይ ቆይታለች። አፍሪካ ከግሪንላንድ በ14 እጥፍ የምትበልጥ ትልቅ አህጉር መሆኗ ይታወቃል። የዘመቻው ደጋፊዎች እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኞች ይህንን እርምጃ በዓለም አቀፍ የትምህርት ስርዓት እና የካርታ ስራ ውስጥ ለዘመናት የዘለቀውን የምዕራባውያን አድሎአዊ እይታ ለማስተካከል የተወሰደ ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ አድርገው እንደወሰዱት የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ጥራትንና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ - ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Sep 4, 2026 872
ሆሳዕና፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማህበረሰቡ ተሳትፎ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ። "ዘላቂ የትምህርት ጥራት ፤ ለላቀ የመማር ውጤትና ለብልፅግና " በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሦስተኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ማህበረሰቡን በማሳተፍ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ።   በክልሉ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ መሰራቱንና በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤት ለማስመዝገብ መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። ለዚህም በዘንድሮ ሀገራዊና ክልላዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት መሻሻል በማሳየቱ ውጤቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በበኩላቸው፣ የመማር ማስተማር ሥራውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማገዝ የተወዳዳሪነት አቅምን ያሳድጋል ብለዋል።   ለዚህም በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን 61 ነጥብ 4 በመቶ ለሚሆኑ የ12 ክፍል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናን በዲጂታል ታግዞ በኦን ላይን ለመስጠት መቻሉን ጠቅሰዋል። በቀጣይ የትምህርት ዘመንም ፈተናውን በኦን ላይን የሚወስዱ ተማሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ ትምህርት ቤቶችን በግብዓት የማሟላት ሥራው በልዩ ትኩረት እንደሚመራ ተናግረዋል። የከምባታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳዊት አሹሮ በዞኑ ማህበረሰቡን በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።   በተያዘው የትምህርት ዘመንም በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄና በትምህርት ቤት ምገባ ማህበረሰቡን በማሳተፍ ውጤቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል። በህብረተሰቡ ተሳትፎም ስምንት አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለትምህርት ዘመኑ ዝግጁ መደረጋቸውን አመልክተዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ በክልሉ በዘንድሮ ብሔራዊና ክልላዊ ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷል፡፡ ሽልማትና እውቅና ከተሰጣቸው መካከል በሆሳዕና ከተማ የሊች ጎጎ አዳሪ ልህቀት ትምህርት ቤት ተማሪ ሮቤል ጌታቸው በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 590 ነጥብ 08 በማምጣቱ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቶታል። የተሰጠው ሽልማትና እውቅናም በቀጣይ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ጠንክሮ በመማር ውጤታማነቱን ለማስቀጠል መነቃቃት እንደፈጠረለት ተናግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Sep 4, 2026 931
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጣልያን መንግሥት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስመልክቶ ለአስተዳደሩ እና ለጣልያን ሕዝብ የተሰማቸውን ልባዊ የደስታ መግለጫ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጣልያን በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጠንካራ እና አርቆ አሳቢ መሪነት በዘመናዊቷ የጣሊያን ሪፐብሊክ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ መረጋጋትን ማስፈኑን አመልክተዋል። የሜሎኒ ጽናትና ቀጣይነት ያለው ትጋት ዓለም አቀፍ መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባሻገር፣ በኢትዮጵያ እና በጣልያን መካከል የቆየውን ሁሉን አቀፍ እና ጥልቅ ትብብር ይበልጥ ማጠናከሩን ገልጸዋል። ሁለቱ ሀገራት በመከባበር ላይ ለተመሰረተው የጋራ ትብብራቸው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለጣልያን መንግሥትና ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 5, 2026 98
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የማይነጣጠል ታሪካዊ ቁርኝት ያላትና የባሕር በር ጥያቄዋም የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከጥንት ጀምሮ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ግዛት ወሰን አካል ሆኖ መኖሩን አውስተዋል። ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎችም የራሳቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም በቀይ ባሕር በኩል እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ ይነግዱ እንደነበር አውስተዋል። ከ1950ዎቹ በኋላም አሰብና ምፅዋ የኢትዮጵያ ዋና የባሕር በር ወደቦች ሆነው ማገልገላቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም የኢህአዴግ መንግሥት ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት በሌለው ሁኔታ፣ ያለምንም የሕዝብ ውይይትና ያለ በቂ ጥናት በድንገተኛ ውሳኔ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ ማድረጉንም አብራርተዋል። ለሀገርና ለሕዝብ ኃላፊነት በማይሰማው መንግሥት የተፈጸመው ይህ የጥፋት ውሳኔ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ መፍጠሩን ጠቁመዋል። በባሕር ንግድ በተሳሰረች ዓለም ውስጥ 130 ሚሊዮን ሕዝብን ይዞ ያለ ምንም የባሕር መውጫ ረጅም ጉዞ ማሰብ አይቻልም ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ። የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በቁጭት የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁን ያለው መንግሥት ኃላፊነት የሚሰማው በመሆኑ የባሕር በር አጀንዳን ፊት ለፊት ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል። የባሕር በር ለንግድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን ከጥቃት ለመከላከልም ወሳኝ የብሔራዊ ደህንነት ዓምድ ነው ብለዋል። አክለውም የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ትውልድ የማይተወው የህልውና አጀንዳ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል። በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ ሀገራት የሕዝብ ብዛትና ኢኮኖሚ ተደምሮ የኢትዮጵያን ግማሽ አቅም እንኳ እንደማይደርስ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መምጣት ለእነዚህ ሀገራትም ትሩፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል። ቀጣናው የኃያላን ሀገራት መራኮቻና የተለዋዋጭ ሁኔታዎች ሰለባ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ አኳያ የቀጣናው ሀገራት በጋራ መልማት የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል ። የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመቀነስ በኢኮኖሚና በታሪክ የተሳሰረውን ሕዝባቸውን ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአካባቢው ግዙፍ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅስ መሆኗ ፋይዳው ድንበር ዘለል ነው ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ፥ ከባሕር በር ተነጥላ ልትኖር ስለማትችል የአካባቢው ሀገራት የመውጫ በር ሊሰጧት ይገባል ነው ያሉት። ይህ ካልሆነ ግን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር ያላት በመሆኗ በጊዜ ሂደት በተፈጥሯዊ መንገድ የታፈነው ጥያቄ መፈንዳቱ አይቀሬ ነው ብለዋል። ይህ እንዳይሆን የቀጣናው ሀገራት በሰላማዊ መንገድ የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመከላከልና ሀብትን በጋራ በመጠቀም መርህ ለኢትዮጵያ የባሕር በር በማመቻቸት የጋራ ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ተመድ የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ አጸደቀ
Sep 4, 2026 1013
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ፤ የአፍሪካን እውነተኛና ትክክለኛ መልክዓ-ምድራዊ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ በይፋ አጽድቋል። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የተላለፈው በአፍሪካ ህብረት ስም በቶጎ አቅራቢነት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ ዓላማውም ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተዘጋጀውን የተዛባ የካርታ አሰራር እንዲያከትም ማድረግ ነው። በውሳኔው መሠረት፣ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለውና ለአፍሪካ አህጉር ትክክለኛ ያልሆነ ስፋት ይሰጥ የነበረው የሜርካቶር ካርታ ከስራ ውጪ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል። በምትኩ ደግሞ እንደ እ.ኤ.አ. በ2018 ይፋ የሆነውና የምድርን ትክክለኛ መጠንና ድርሻ የሚያንጸባርቀው "ኢኩዋል አርዝ"(Equal Earth) የመሳሰሉ ዘመናዊ እና እኩል አቀራረብ ያላቸው የካርታ ቀመሮች በስራ ላይ ይውላሉ። ይህ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ 164 ሀገራት የውሳኔ ሀሳቡ እንዲፀድቅ ድጋፍ ሰጥተዋል። የተለመደውና የድሮው ካርታ የተሰራው እ.አ.አ በ1569 በደች (ፍሌሚሽ) ካርታ ሰሪ በጄራርዱስ ሜርካቶር ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በወቅቱ ለባህር ዳር መርከበኞች ማሰሻነት እንዲያገለግል ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ካርታ ከምድር ወገብ (Equator) እየራቀ ሲኬድ የመሬትን ስፋት እያጋነነ የሚያሳይ በመሆኑ፣ የምድር ወገብ አቅራቢያ የሚገኙ አካባቢዎችን በዕይታ በእጅጉ እንዲቀንሱ አድርጓል። በዚህ የተዛባ የካርታ አሰራር ምክንያት አፍሪካ ከግሪንላንድ ደሴት ጋር ተቀራራቢ መጠን እንዳላት ሆና ስትታይ ቆይታለች። አፍሪካ ከግሪንላንድ በ14 እጥፍ የምትበልጥ ትልቅ አህጉር መሆኗ ይታወቃል። የዘመቻው ደጋፊዎች እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኞች ይህንን እርምጃ በዓለም አቀፍ የትምህርት ስርዓት እና የካርታ ስራ ውስጥ ለዘመናት የዘለቀውን የምዕራባውያን አድሎአዊ እይታ ለማስተካከል የተወሰደ ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ አድርገው እንደወሰዱት የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Sep 4, 2026 931
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጣልያን መንግሥት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስመልክቶ ለአስተዳደሩ እና ለጣልያን ሕዝብ የተሰማቸውን ልባዊ የደስታ መግለጫ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጣልያን በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጠንካራ እና አርቆ አሳቢ መሪነት በዘመናዊቷ የጣሊያን ሪፐብሊክ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ መረጋጋትን ማስፈኑን አመልክተዋል። የሜሎኒ ጽናትና ቀጣይነት ያለው ትጋት ዓለም አቀፍ መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባሻገር፣ በኢትዮጵያ እና በጣልያን መካከል የቆየውን ሁሉን አቀፍ እና ጥልቅ ትብብር ይበልጥ ማጠናከሩን ገልጸዋል። ሁለቱ ሀገራት በመከባበር ላይ ለተመሰረተው የጋራ ትብብራቸው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለጣልያን መንግሥትና ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።
የህዳሴ ግድብን ያሳካው ትውልድ የባህር በር ጥያቄንም ማሳካቱ የማይቀር ነው
Sep 4, 2026 933
ሰቆጣ፤ ነሃሴ 29/2018(ኢዜአ) ፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ታሪክ የሰራው ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትን ማሳካቱ የማይቀር ነው ሲሉ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ገለጹ። ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው የፋይናንስ አቅምና ጉልበት ለዓመታት በጽናት የገነቡት የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ኃይል እያመነጨ፣ ዓሳ እየተመረተበት እና የአካባቢውን መልካዐ ምድር አስውቦ የቱሪስት መስህብ ጭምር ሆኗል። የዚህ ታሪካዊ ስኬት ባለቤት የሆነው የአሁኑ ትውልድ በሁሉም ረገድ የኢትዮጵያን ስኬት፣ ክብርና ልእልና ለማስጠበቅ በትጋት መስራቱን ቀጥሏል። በቅርበትም፣ በመልክዐ ምድርም ይሁን በታሪክ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ባለቤትነቷን እውን ማድረግ የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነ ብርሃን፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገበት ሴራ ስንቆጭበት የኖርንበት ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የወደቦች ባለቤት እንደነበረችና ገቢና ወጪ ምርቶችን በቀላሉ ታንቀሳቅስ እንደነበር በማስታወስ ለምን እንዳጣነው እስካሁንም ግልጽ አይደለም ብለዋል። የባህር በር ባለቤትና የባህር ሃይል የነበራት ኢትዮጵያ ለምን እንዳጣች ማንም የማያውቀውና ጉዳዩ እንዳይነሳ ተጽእኖ ይደረግ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ግን የትውልድ ጥያቄ ሆኖ በመምጣቱ ኮርተናል ብለዋል። በመሆኑም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ታሪክ የሰራው ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትን ማሳካቱ የማይቀር መሆኑን እርግጠኛ ነኝ ሲሉም ተናግረዋል። ሌላኛው የቀድሞ ሰራዊት አባል መቶ አለቃ አበባው ገብረእግዚአብሔር፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት በብዙ መልኩ እስካሁንም የተሻገረ ችግር የፈጠረባት መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የሀገር ህልውና ጉዳይ እና የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ መነሳቱና የባህር በር ባለቤትነት የግድ መሆኑ የሁላችንም ጽኑ አቋም ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከአባይና ከቀይ ባህር ነጥሎ ማየት የማይታሰብ መሆኑን የገለጹት መቶ አለቃ አበባው፤ የባህር በር ባለቤትነታችን የማይቀር በመሆኑ ለዚህም በትብብርና በአብሮነት ለሀገራችን መስራታችን ይቀጥላል ብለዋል።
በደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምን አፅንቶ በማዝለቅ የልማት ስራው እንዲፋጠን የድርሻችንን እንወጣለን-ነጋዴዎች
Sep 4, 2026 867
ደብረ ብርሃን፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- በደብረ ብርሃን ከተማ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጀመሩ የልማት ተግባራት ተጠናከረው እንዲቀጥሉ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የአስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በወቅታዊ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ በከተማዋ ከሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ ውይይት አካሂዷል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ተስፋዬ እሸቴ እንደገለጹት፤ በከተማዋ እየተረጋገጠ የመጣውን ሰላም አፅንቶ ለማዝለቅ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ ይጠይቃል። በከተማዋ አሁን የተገኝው ሰላም ዘላቂ እንዲሆንና የልማት ጥያቄዎቻቸው ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ የድርሻቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል። ሌላዋ የመድረኩ ተሳታፊ ወይዘሮ ሰርካለም ተሾመ፤ የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ከሚመለከተው አካል ጋር በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ አስከባሪ አካላት አጋልጦ በመስጠት ወንጀልን በጋራ ለመከላከል የተጀመረውን ስራ ከማገዝ አንፃር የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በህብረተሰብ ተሳትፎ የብሎክ አደረጃጀትን መሰረት አድርጎ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል በተጀመረው አሰራር ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ አውላቸው ለገሰ ናቸው።   የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በበኩላቸው፤ የከተማዋን ሰላምና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ህዝቡ የሚያነሳውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ለመመለስ በከተማዋ የመሰረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ልማቱን ለማፋጠን የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የፀጥታ ኃይሉ ወንጀልን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡና የፀጥታ ሀይሉ ተቀናጅተው ወንጀልን እየተከላከሉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ገብረመስቀል ቦጋለ ናቸው። ከዚህ ውስጥም የንግዱ ማህበረሰብ በሆቴሎች አልጋ የሚይዙ እንግዶችን በአግባቡ በመመዝገብ ለፀጥታ ኃይሉ በማሳወቅ የጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። በተካሄደው የውይይት መድረክ ከከተማዋ የተውጣጡ የአገልግሎት ሰጪና የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ተሳትፈዋል።  
የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው
Sep 4, 2026 975
መተማ፤ ነሐሴ29/2018(ኢዜአ) ፦ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም በጫካ የሚገኙ የታጠቁ አካላት ለመንግስት የሰላም ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት እድሉን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መክረዋል። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትጥቅ ይዘው በየጫካው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቃቸውን በመፍታት ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል። በተሳሳተ መንገድ በትጥቅ እንቅስቃሴ የነበሩ በርካታ ወጣቶች እውነታውን በመረዳት በህዝብ ላይ እገታና ዘረፋ አንፈፅምም በማለት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እየመጡም ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የመንግስትን የሰላምን ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው ሌሎችም ይህንኑ መልካም መንገድ እንዲከተሉ መክረዋል። የመንግሥትን የሰላም ጥረትና ቁርጠኝነት በማድነቅ የታጠቁ አካላት ይህንን መልካም እድል በመጠቀም ትጥቃቸውን በመፍታት ለሰላምና ልማት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። በምእራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የሚኖሩት የኃይማኖት አባት ሊቀ ህሩያን እያሱ ገዳሙ እና መጋቤ ብርሃን ዘላለም አዲሱ፤ የመንግስት ሆደ ሰፊነትና ለሰላም የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጥረት አድንቀዋል። በዚህም መሰረት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን አንስተው ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ እንዲከተሉ መክረዋል። በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ተጨማሪ ህይወት ሳይጠፋና ንብረት ሳይወድም የተሰጠውን የሰላም እድል በመጠቀም ለህዝባቸው እፎይታን መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የሀገር ሽማግሌው አቶ ደርቤ ጫኔ፤ ለሰላም የሚደረግ ጥረት ጀግንነትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው ለመንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥረትና ሰላምን መርጠው እየመጡ ላሉ ታጣቂዎች አመስግነዋል። በመሆኑ በጫካ የቀሩ ታጣቂዎች የህዝቡን ፍላጎትና የመንግሥትን የሰላም ጥረት ትርጉም በመስጠት ከጥፋት ወጥተው ሰላምን መርጠው ህዝቡን እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል። በመሆኑም ይቅር ባይነትን በማስቀደም ወደ ሰላም መንገድ መመለስ እና ይህንን እድል መጠቀም ለህዝብና ለሀገር በማሰብ የሚፈፀም በመሆኑ የሰላም ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
Sep 3, 2026 1145
ባህር ዳር ነሐሴ 28/2018;(ኢዜአ) ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ሙዚየም መገንባቱ የህዝቡን የፍትህ እሴትና በህግ የበላይነት ከማሳየት ባሻገር ተቋማት ለለውጥ ያላቸውን መነሳሳት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የፍትህ አስተዳደር ታሪክ ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ በመሆኑም ለአዲሱ ትውልድ እሴትና ተደማሪ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ አሻራ ላስቀመጡና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለምረቃ እንዲበቃ ላደረጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።   የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የሙዚየሙ መገንባት በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ትልቅ እሴት የሚሆን ነው ብለዋል። በካታሎግና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘውን የአገራችን የፍትህ ታሪክ ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያውቁና ለምርምር ግባአት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለምአንተ አግደው፤ ሙዚየሙ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ አስተዳደር የነበሩ የፍትህ ታሪኮችን ሰንዶ በመያዝ የተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ለህግ ማሻሻያ፣ ለፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻና ለሌሎችም የጥናትና ምርምር ስራዎች ትልቅ አቅምና ግብአት ይሆናል ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩና ሌላ ቦታ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ ብርቅዬ የፍትህ ሰነዶች የሚገኙበት ነው ብለዋል። እነዚህን ታሪካዊ መረጃዎች ከተለያዩ ቦታዎች ለማሰባሰብ ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው አጠቃላይ የሙዚየሙ ግንባታ አላማ የህዝቡን የፍትህ ስርዓት ታሪክ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። በፍትሕ ሙዚየም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ማህበራዊ
የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ ጉብኝት
Sep 5, 2026 88
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ። የሰላም ሚኒስቴር ሀገር በቀል ዕውቀትና ባህላዊ ሀብቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አድርገዋል።   የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከልምድ ልውውጥና ውይይቱ ባለፈ በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።   የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ሕንፃ ግንባታ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል።
ኢትዮ - ቴሌኮም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 5, 2026 165
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮ-ቴሌኮም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን በጎተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ - ቴሌኮም 25ኛ ዓመቱን ለያዘው "ስለ እናት" በጎ አድራጎት ድርጅት የ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብና ዓለምገና ለሚገኘው ውህደት ቅድመ አንደኛና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ የተማሪ መማሪያ ደብተር ለግሷል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የኩባንያውን ድጋፍ በ"ስለ እናት" በጎ አድራጎት ድርጅት እና ውህደት ቅድመ አንደኛና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው አበርክተዋል።   ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኩባንያው ከመደበኛ ሥራዎቹ ባሻገር የሰዎችን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል። በአዲስ አበባ የተካሄደው የበጎ አድራጎት ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት መርሃ ግብርም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ድጋፍ የሚካሄድበት መሆኑን ገልጸዋል። ከሃምሳ በላይ የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በተፈጠረው በትብብር የመስራት ሁኔታም ከ22 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት የሚከናወኑ ሰው ተኮር የድጋፍ ሥራዎችን ታሳቢ በማድረግም በስምንት ዓመታት ውስጥ ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ያስቻሉ ድጋፎች መደረጋቸውን አስረድተዋል። ዘንድሮም በአዲስ አበባ ለ"ስለ እናት" በጎ አድራጎት ድርጅት እና ዓለምገና ለሚገኘው ውህደት ቅድመ አንደኛና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል። የ"ስለ እናት" በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ያሬድ አብዱ በበኩላቸው፤ ኢትዮ ቴሌኮም ከአምስት ዓመታት በፊት ጀምሮ በተከታታይ እያደረገላቸው ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ሌሎች ተቋማትም የኢትዮ-ቴሌኮምን የሰብዓዊ ድጋፍ አርዓያነት በመከተል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ለውህደት ቅድመ አንደኛና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ባበረከቱበት ወቅት፤ የትምህርት ተቋማት በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መፍጠሪያ ማዕከላት ናቸው ብለዋል። ለዚህም በዘንድሮው ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የሚውል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የደብተር ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል። የውህደት ቅድመ አንደኛና መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስራችና የአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አበበ የኋላወርቅ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮ-ቴሌኮም ለትምህርት ቤቱ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመረዳዳት እሴት እንዲጎለብት እያደረገ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Sep 5, 2026 184
አሶሳ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማቃለል የመረዳዳት እሴት እንዲጎለብት እያደረገ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ቡልድግሉ ወረዳ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት እና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማቃለል የመረዳዳት እሴት እንዲጎለብት እያደረገ ነው። በክልሉ በክረምት ወራት ከበጎ ፍቃደኞች በተጨማሪ የክልሉ የመንግስት ተቋማት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል። በዘንድሮው ክረምት ከ200 በላይ አዳዲስ የቤት ግንባታዎች እና ከ50 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ለመጠገን ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤትም በቡልድግሉ ወረዳ አምስት የአቅመ ደካሞች ቤቶችን እያስገነባ እንደሚገኝ ገልጸው፥ በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የስራ አፈጻጸም በየጊዜው በመገምገም ውጤታማ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ወቅቱ የትምህርት ዘመን የሚጀመርበት በመሆኑ ለተማሪዎች የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በሰዓቱ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚያደርግና የወላጆችን ጫና የሚቀንስ መሆኑን ገልጸዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወረዳው 200 ለሚሆኑ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳር እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ለ200 ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች ውጤት ተገኝቷል
Sep 5, 2026 102
ሀረር፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መገኘቱን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ። የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዓመታዊ የክልል ጉባዔ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው። መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከብቁ የሰው ኃይል ጋር በማቀናጀት ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራ ማከናወን ተችሏል። የአገልግሎት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ዘመናዊ የፖሊሲና ፕሮግራም፣ አዋጅና ደንብ እንዲሁም መመሪያና ስታንዳርድ በመቅረጽ ለተግባራዊነቱ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በተለይም የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል። በተለይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ በተደረገው ውጤታማ የሪፎርም እርምጃ ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በመቅረፍ የአገልግሎት እርካታን እያሳደገ መሆኑንም ገልጸዋል። የተጀመረውን ስራ በዘላቂነትና በውጤታማነት ለማሳደግ የአመራር ቁርጠኝነትና የቴክኖሎጂ ትግበራ ቀጣይነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የተቋማት አቅም ግንባታን በማጠናከር፣ የሰው ኃይልን ከቴክኖሎጂ ጋር የማብቃት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የሐረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጆርዳን ይስሃቅ በበኩላቸው በክልሉ በአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። በተለይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አሰራርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል ። የማህበረሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄ በመመለስ ጥራትና ቅልጥፍናን በመጨመርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በማስቀረት የአገልግሎት እርካታን ማሳደግ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል። መድረኩም የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ መደላድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስና የክልል ቢሮ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በፌደራልና በክልሎች 2018 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 እቅድ ላይ በመወያየት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል።
ኢኮኖሚ
የአየር መንገዱ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ
Sep 5, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎብኝተዋል። ሰራተኞቹ ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተመልክተዋል። እንዲሁም የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችንም ጎብኝተዋል።   በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው፤ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የአዲስ በባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።  
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኢንዱስትሪ ዘርፍ በመጣው ለውጥ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል
Sep 5, 2026 96
ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 30/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኢንዱስትሪ ዘርፍ በተመዘገበው ስኬት በርካታ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን "የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ልህቀት፣ ለከፍተኛ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛር በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል።   በማዕከላት የገቡ መካከለኛና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ምርታማነታቸው ከማደጉ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቅሰዋል። ባዛርና ኤግዚቢሽኑም አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ከማድረግ ባሻገር የገበያ ትስስር በመፍጠር የጎላ ሚና እንዳለው አስታውቀዋል። በዘርፉ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራም እንዲሁ።   ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አቅሙን በማጎልበት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በማጠናከርና የኢንቨስትመንት ምህዳሩን በማስፋት ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት ደግሞ የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን ብርሃኑ (ኢ/ር) ናቸው። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 አልሚ ባለሀብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውንና ከ4 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውቀዋል።
በነቀምቴ ከተማ ከ 21 ሺህ 800 በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ
Sep 5, 2026 93
ነቀምቴ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በነቀምቴ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት 21 ሺ 840 ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የከተማው የስራ እድል ፈጠራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገለጸ። የነቀምቴ ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አሰፋ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ14 ሺሕ በላይ ሥራ አጥ ወጣቶችን በተለያዩ የሙያ መስኮች በማሰማራትተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ከብድር አቅርቦት ጋር ተያይዞ ወጣቶች የተመቻቸላቸውን የሥራ ዕድል እንዲጠቀሙ በተደረገው ጥረትም በበጀት ዓመቱ 289 ሚሊዮን ብር ብድር መመቻቸቱን ጠቁመዋል። በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣቶች የተበደሩትን ገንዘብ በየጊዜው እንዲመልሱ ለማስቻል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከ88 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመለስ መቻሉንም ገልጸዋል። በ2019 የበጀት አመትም የወጣቶችን የሥራ እድል ፈጠራ ለማስፋፋት፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና የወጣቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ነው አቶ ብርሃኑ የገለጹት። የአካባቢው ወጣቶች የሥራ ባህላቸውን በማሳደግ በሀገር ግንባታ የበኩላቸውን አሻራ እንዲያኖሩም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው በተለያዩ ዘርፎች 21 ሺሕ 840 ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚደረጉም ተናግረዋል። የስራ እድል እየተመቻቸላቸው ያሉ ወጣቶች እንደተናገሩትም የከተማው አስተዳደር ለወጣቶች የሰጠው ትኩረት አስደሳች መሆኑን ገልጸው፤ በስራ እድሉ ተጠቅመው ራሳቸውን እንደሚለውጡ ተናግረዋል። ወጣት ሙሉጌታ ተስፋዬ፣ በተገኘልኝ የብድር ድጋፍ አነስተኛ የእንስሳት ማድለብ ሥራ ጀምሬያለሁ ብሏል። ዛሬ ለራሴ ገቢ ከመፍጠር ባሻገር ለሌሎች ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥሬያለሁ ብሏል። ወጣት ሀና አሰጠው በበኩሏ፣ በተሰጠኝ የሙያ ሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ የልብስ ስፌት ሥራ ጀምሬ በመስራት ቤተሰቤን እየደገፍኩ ነው ብላለች። የተፈጠረልን ዕድል ለብዙ ወጣቶች ተስፋ ሆኗል ያለችው ወጣቷ በዚህ የስራ እድል መጠቀም ይገባናል ብላለች።
በጋምቤላ ክልል አነስተኛ መስኖዎችንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ከ49 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል
Sep 5, 2026 140
ጋምቤላ ፤ ነሐሴ 30/ 2018 (ኢዜአ) ፦ በጋምቤላ ክልል የተለያዩ የውሃ አማራጮችንና አነስተኛ መስኖዎች በመጠቀም ከ49 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ስራ መገባቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮ ኃላፊው አቶ አንድሮው ቱት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ ያለውን በመስኖ የመልማት አቅም በመጠቀም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራው በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው። የውሃ ሸሽ/ እርጥበታማ አፈር/ እና አነስተኛ የመስኖ ልማትን የሚያስተባብር የአመራርና የባለሙያዎች ቡድን የመስክ ስምሪት መደረጉንም ገልፀዋል። በክልሉ በዝናብ ብቻ ሳይወሰን በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ በመስኖ በማልማት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጡን ጉዳይ በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። በክልሉ 2019 የበጋ መስኖ ልማት የውሃ ሸሽ/እርጥበታማ አፈረን/፣ 15 አነስተኛ የመስኖ ተቋማትን፣ 256 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችንና ሌሎች የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ከ49 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እየተሰራ ነው ብለዋል። ከመስኖ ልማቱ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰብል ፣የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለመሰብስብ መታቀዱንም ተናግረዋል። በበጋው መስኖ ለማልማት የታቀደው መሬት ከቀዳሚው ዓመት በ15 ሺህ ሄክታር መሬት ብልጫ እንደሚኖረው ኃላፊው ገልፀዋል። ከመጪው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለሚካሄደው የውሃ ሸሽ/ እርጥበታማ አፈርን/ እና ሌሎች የመስኖ አማራጮች ለመጠቀም ንቅናቄ የሚፈጥር የአመራርና የባለሙያዎች ቡድን ወደ ዞኖችና ወረዳዎች መሰማራቱንም ተናግረዋል። በጋምቤላ ክልል ባሮን ጨምሮ አራት ታላላቅ ወንዞችና ሌሎች የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ከ780 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት የሚያስችል አቅም እንዳለ በጥናት መለየቱም ተገልጿል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ አስችሏል - ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 5, 2026 95
ጎንደር፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መሥተዳድሩ አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ዛሬ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት የአገልግሎት አሠጣጥ ሪፎርም አካል በመሆን ዘልማዳዊ እና እንግልት የበዛበትን አሠራር እየቀየረ ነው ብለዋል። የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል በማሠባሠብ፣ በማደራጀት፣ ዲጂታል በማድረግ፣ ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሻሻል እያገዘ መሆኑንም አስረድተዋል። በክልሉ ስድስት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ተገልጋይን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የነበረውን እንግልት የበዛበት አሠራር ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ እየቀረ መሆኑን አንስተዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተሻለ ተደራሽነትን፣ የላቀ ቅልጥፍናን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ መኾኑንም አንስተዋል። አገልግሎቱ የመንግሥት ተቋማትን በማቀናጀት፣ የእርስ በእርስ የመረጃ ልውውጣቸውን በማቀላጠፍ ለደንበኞች እርካታ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። የጎንደር መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሕንጻ የከተማዋን ቀደምት የኪነ- ሕንጻ ጥበብ በጠበቀ መንገድ በጥራት ተገንብቶ የተጠናቀቀ መሆኑንም አብራርተዋል። በቀጣይም በኮምቦልቻ፣ በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ እንደሚጀምሩም ነው የተናገሩት። በ2019 በጀት ዓመትም በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎትን የማስፋፋት ስራ እንደሚሠራም አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያዘመነ ነው - ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ
Sep 4, 2026 149
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ ገለጹ። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ደንበኞች በዘመናዊ ዲጂታል አማራጭ የሚገለገሉበት የዲጂታል መተግበሪያ ዛሬ አስመረቋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያሳልጥ የባሕር ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። በዚህም የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሀገሪቱ የሎጂስቲክስ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት አሰራር እየተገበረ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋሙ ለአፍሪካ ብቸኛ እና ታሪካዊ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ሆኖ መቆየቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅትም ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን አዲስ አሰራር ስርዓት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። ዛሬ የተመረቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ደንበኞች እንግልት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እንዲሁም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን የሚያፋጥን እንደሆነ አስታውቀዋል። በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የሚጠናቀቁ ትላልቅ አዳዲስ ሲስተሞች እየተገነቡ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል። በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተቋሙን ከዓለም አቀፍ አሰራሮች ጋር እኩል የሚያሰልፉ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የቦርድ አባልና የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ፤ የሎጂስቲክስ ሥርዓቱን የሚያዘምን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህም መንግሥት የየብስ ትራንስፖርት፣ የባቡርና የደረቅ ወደብ መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ የመርከቦች ቁጥር እንዲበራከት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ አቅም ለማጎልበት ከሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በተጨማሪም የባሕር በር ባለቤትነት ምላሽ ለማረጋገጥ በዋና አጀንዳነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተመረቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂም አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሳለጥ ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቅልጥፍናን ለማሳለጥ የቴክኖሎጂ አሠራር ወሳኝ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራሆል ጣፋ ናቸው። የኢትዮጵያ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂንና የሎጂስቲክስ ዘርፍ ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማዘመንና አሠራሩን ዲጂታላይዝ የሚያደርጉ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል መተግበሪያውም ግልጽ፣ ፈጣንና ዘመናዊ አሠራር ሥርዓትን ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ የሀገሪቱን የልማት ጉዞ የሚያፋጥን የሰው ሃይል የማፍራት ድርሻውን ያጠናክራል
Sep 4, 2026 132
ሃዋሳ ፤ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ) ፡-የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ገበያ መር አዳዲስ ፕሮግራሞች በመክፈት የሀገሪቱን የልማት ጉዞ የሚያፋጥን የሰው ሃይል የማፍራት ድርሻውን እንደሚያጠናክር አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ በ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና በቀጣይ እቅዶችና አቅጣጫዎች ላይ በሃዋሳ መክሯል።   የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ ገበያ መር የሆኑ 11 አዳዲስ ፕሮግራሞችን በመክፈትና የተማሪዎች የቅበላ አቅሙን በማሳደግ የሀገሪቱን የልማት ጉዞ የሚያፋጥን የሰው ሃይል በማፍራት የበኩሉን እየተወጣ ነው ። ለዚህም አቅርቦት መር የነበረውን የስልጠና ሂደት ወደ ፍላጎት መር በመቀየር ዘመኑን የዋጁ የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሳይበር ሴኩሪቲ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና በባዮ ሜዲካል ቴክኖሎጂ ጥናትን መሰረት በማድረግ የስልጠና ዘርፎች መከፈታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንተርፕራይዝ ልማት ተግባራቱን ለማሳካት ከ17ዐ በላይ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር መፈጠሩንም አመልክተዋል። በበጀት አመቱም ከ40 በላይ የምርምር ስራዎችን በማድረግ ለፖሊሲ ግብአትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያግዙ እንዲሁም ተኪ ምርቶችን ለማምረት አቅም የመፍጠር ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል። በቀጣይም በኢንስቲትዩቱ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ መሰረት በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ችግር ፈቺ የፈጠራ ማእከላት የማድረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።   በምክትል ከንቲባ ማእረግ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ቸርነት ፍላቴ በበኩላቸው በከተማው በተከናወኑ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማትና ባለሙያዎች በፈጠራ ስራ ጉልህ ድርሻ አበርክተዋል ብለዋል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ያወጧቸው የሰው ሀይልና የምርምር ስራዎች በከተማዋ እድገት የራሳቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን ጠቁመዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በኢንስቲትዩቱ የቴክስታይልና አፓሬል ፋሽን ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ዲን መረርቱ ዋቁማ (ዶ/ር) እንደገለፁት ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ሃይል ለማፍራት በመደበኛና በአጫጭር ስልጠናዎች በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ፋሽን ቴክኖሎጂው የሚፈልገውንና ዘመኑን የዋጁ ፕሮግራሞችን በመክፈት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ከዘርፉ የሚገኙ ጥቅሞችን የማሳደጉ ስራ እንደሚጠናከር አመላክተዋል ። በመድረኩ በቀረቡ የውይይት መነሻ ሰነዶችና የተቋሙ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።          
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው
Sep 4, 2026 182
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኗን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ። ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት፣ የቀጣናውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ በጋራ ለመቅረጽ ያለመ አውደ ጥናት መካሄድ ጀምሯል።   የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣን ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚን፣ መንግሥታትንና የሰውን አቅም እየቀረጸ ይገኛል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ኃይል መሆኑንም ገልጸዋል። የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራትም የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ አማራጭን በአግባቡ በመጠቀም የኢኮኖሚ ውህደትን ማፋጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል። ለዚህም የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም እና የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተጠቃሚነት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተው፤ ዘርፉ በፍጥነት ለውጥ እያስመዘገበ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። ስለሆነም ሀገራት ይህ ተግባር የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴክኖሎጂ የተሻለ እየሰራች መሆኑንም ጠቁመዋል። ኤ አይ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ዘርፉን ለመምራት ኢንስቲትዩት በማቋቋም አበረታች ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም መሆኑንም አብራርተዋል። የኢጋድ አባል ሀገራቱ የተናበበ ፖሊሲ እንዲኖራቸውና የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይ ከቀጣናው የተውጣጡ ወጣቶችን የሚያሰለጥን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።   በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከተማ ኃይሌ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢኮኖሚ እድገትን የሚያፋጥን ብዝኅ ምርታማነት አቅም መገንቢያ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለቀጣናዊ ትብብር፣ ለጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ ለዲጂታል መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም ለጥናትና ፈጠራ ኢንቨስትመንት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ልማት ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና በመገንዘብ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም የኢጋድ አባል ሀገራትን እና አጠቃላይ አፍሪካን የሚጠቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።  
ስፖርት
ማንችስተር ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን በማሸነፍ በሊጉ መሪነት ቀጥሏል
Sep 5, 2026 69
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በ26ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። የ26 ዓመቱ አጥቂ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሶስት አድርሷል። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ በጨዋታው ላይ በተጋጣሚው ተፈትኗል። ተጋጣሚው ኮቨንተሪ ሲቲ ግብ ሊያስቆጥርባቸው የሚችልባቸውን ግልጽ እድሎችን አምክኗል። በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ከቼልሲ ወደ ማንችስተር ሲቲ የተዘዋወረው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ በመሪነነቱ ቀጥሏል። ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኮቨንተሪ ሲቲ ያለ ምንም ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በአራተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከከተማ ተቀናቃኙ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርገው የደርቢ ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው። ኮቨንተሪ ሲቲ ከብራይተን ጋር የሚጫወት ይሆናል። በሌሎች መርሐ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፏል። ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ብራይተን ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ሁል ሲቲ ከአስቶንቪላ በኤምኬኤም ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲዳማ ቡና ከኤግሎንስ ጋር ይጫወታል
Sep 5, 2026 153
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በ2026/27 የካፍ ሻምፒዮንስ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ሲዳማ ቡና ከቻዱ ኤግሎንስ ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል። ጨዋታው ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 ላይ በኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ስታዲየም ይካሄዳል። ሲዳማ ቡና በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የበቃው የ2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ነው። በ1999 ዓ.ም የተቋቋመው ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና ለማጣሪያ ጨዋታው በሃዋሳ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቶ በተያዘው ሳምንት ወደ ስፍራው አቅንቷል። ቡድኑ ስብስቡን ለማጠናከር በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፣ የተጫዋቾችንም ውል አድሷል። ቢኒያም በላይ፣ ውብሸት ክፍሌ፣ ኤፍሬም ታምራት፣ ይገዙ ቦጋለ እና ዩጋንዳዊው ካሊድ አውቾ ከፈረሙት ተጫዋቾች መካከል ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ሲዳማ ቡና የአምበሉን ያሬድ ባየህ፣ መስፈን ታፈሰ እና ደስታ ደሙን የመሳሰሉ የቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል። ተጋጣሚው ኤግሎንስ ባለፈው የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የቻድ ፕሪሚየር ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ በአህጉራዊ መድረኩ ላይ ይሳተፋል። ኤግሎንስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እ.አ.አ በ2015 የተመሰረተው ኤግሎንስ የወቅቱ አሰልጣኝ አማን አዱም ቱኒያ ናቸው። የሊጉ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው አጥቂው ፋቢየን ጄዳኑም እና ምርጥ ግብ ጠባቂ የተባለው ቢርዌ ማንጋና የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ናቸው። የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል እና ከብሩንዲው አይግል ኑዋር አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ከኮቨንተሪ ሲቲ ጋር ይጫወታል
Sep 5, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በኢትሃድ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በሚካሄደው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ አዲስ አዳጊውን ኮቨንተሪ ሲቲ ያስተናግዳል። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። በሁለቱ የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው ኮቨንተሪ ሲቲ ያለ ምንም ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። ክለቦቹ ከዚህ ቀደም 10 ጊዜ በሊጉ ተገናኝተው በተመሳሳይ አራት ጊዜ ድል ቀንቷቸዋል። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ በ2001ነው። በወቅቱ ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ክለቦቹ ከ25 ዓመታት በኋላ ዳግም በሊጉ ይገናኛሉ። ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ የሊጉን መሪነት የሚያጠናክር ሲሆን ኮቨንተሪ ሲቲ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። በሌላኛው መርሐ ግብር ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ኖቲንግሃም ፎረስት በአንድ ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያለ ምንም ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ሁለቱም ክለቦች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። በዝውውር መስኮቱ ከ300 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያወጣው ቶተንሃም ደካማ ጅማሮ ያሳየ ሲሆን በሊጉ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ይፋለማል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ሁል ሲቲ አስቶንቪላን በኤምኬኤም ስታዲየም ጨዋታውን ያከናውናል። አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። አስቶንቪላ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁል ሲቲ በመልካም ጅማሮው ለመቀጠል አስቶንቪላ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። በሌሎች መርሐ ግብሮች ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ 11 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ኒውካስትል ዩናይትድ ከቦርንማውዝ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን በመከላከል ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው - የአፍሪካ ህብረት
Sep 5, 2026 133
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችን ለመመከትና ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የአፍሪካ ህብረት የዘላቂ ከባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሃርሰን ንያምቤ ገለጹ። ዳይሬክተሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አረንጓዴ አሻራ ንጹህ አየርን ጨምሮ ሌሎች ስነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ከማስገኘቱም በላይ፣ የካርበን ልቀትን በመቀነስ የአየር ሙቀት መጨመርን ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል። የተራቆተ መሬትንና የአካባቢ ስነ ምህዳር እንዲያገግም በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አመልክተዋል። በጥቅሉ ሲታይ የአረንጓዴ አሻራ በርካታ ሁለገብ ጥቅሞች ያሉት ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ መሆኑንም አንስተዋል። የአፍሪካ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተግባራት ላይ የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባቸው የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በዚህ ረገድም በአካባቢ ጥበቃ ላሉባቸው ተግዳሮቶች መፍትሄ ለማበጀት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ መውሰድ እንደሚችሉ ነው የገለጹት። ኢትዮጵያም ስኬታማ ተሞክሮዎቿን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማካፈል ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለባት ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
‎የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 394
‎አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ ‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። ‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። ‎መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። ‎የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። ‎በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። ‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። ‎በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ‎ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።  
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 695
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በአፍሪካ አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
Sep 2, 2026 533
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትንና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓም ተገልጿል። የአፍሪካ ቀጣና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ይፋ የተደረገ ሲሆን እስከ 2027 እያንዳንዱን ሰው በአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና በተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከተመድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቢሮና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የተቀናጀ አይነተ ብዙ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል።   የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀና አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም ወቅታዊና ተገቢ ነው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎችን አደጋዎችን በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ሴቶችና ህፃናት ጨምሮ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የአደጋው ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበትና ተቋማዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓን ጠቅሰው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስና ሌሎችም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ማንም ሀገር ብቻውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስትራቴጂን ውጤታማ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራትና የተለያዩ አጋር አካላት ጋር በአይነተ ብዙ የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።   በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዘላቂ አካባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቤ፤ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ማህበረሰቡን አደጋን የመቋቋም አቅም መገንባትና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2027 እያንዳንዱን ሰው ከአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል አደጋዎች መጠበቅ የሚለውን ግብ ለማሳካት ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጎርፍና የተራዘመ ደርቅ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ፣ እና በሌሎች አደጋዎች ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን በመግለጽ፤ አፍሪካውያን ውስጣዊ ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። አደጋ ድንበር የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በአይነቱ ብዙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአባል ሀገራቱን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ቢሮ ዳይሬክተር ኤግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአመራር ቁርጠኝነት እያደገ በመምጣቱ መሻሻል እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነትና በተወሳሰበ ሁኔታ ተባብሰው ቀጥለዋል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመቆጣጠር የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በሀገራት የተቀናጀ አሰራር መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የ2027 ግብ ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በመግለፅ፤ በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ግንባታ ዘላቂና እምነት የሚጣልባቸው መሆን አለባቸው ብለዋል። በአፍሪካውያን መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ በመጥቀስ፤ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 200
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1609
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1265
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1541
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 394
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል።   በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል።   3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች።   የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።  
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 560
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል።   ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች።   ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል።   ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 556
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 755
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
ለኢትዮጵያ የቤት ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስምምነት
Sep 4, 2026 226
የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ፈጣን እየሆነ በመምጣቱ እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመሄዱ፣የዜጎችን የቤት ባለቤትነትን ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት አንዱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት የነበረው የቤት አቅርቦት በመንግሥት ትከሻ ላይ ብቻ የወደቀ በመሆኑ፣ ካለው ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ቀርጾ በካቢኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ፖሊሲው የዕድገቱን ፍጥነት እና የከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሥራዎች ለዚህ ሰፊ ራዕይ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታውሰዋል።   ይህንኑ ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት አጠቃላይ ዝግጅት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አሁን ላይ አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂንና የረጅም ጊዜ የቤት ብድር ሥርዓትን በማስተዋወቅ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲሱ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ በካቢኔ መጽደቁንና በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አጋርነት መዋቅሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ፍላጎታቸውን የሚያስተናግድ አዲስ የፋይናንስ አሠራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ሰዎች ቤት በቀጥታ መግዛት ካልቻሉ በመንግሥት በሚመቻቸው አዲስ የሞርጌጅ ሥርዓት አማካኝነት ከገቢያቸው ላይ እየከፈሉ በረጅም ጊዜ ሂደት የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል ይፈጠራል ብለዋል። ይህ ግብ የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የሚሳካ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የሞርጌጅ ሥርዓት የቤት ፍላጎትን ለማሟላት የቀረበ ሌላኛው አማራጭ ሆኗል። የቤት መግዣ ብድር ሥርዓት (ሞርጌጅ) ማለት አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ በብድር አግኝቶ፣ ያንን የተበደረውን ገንዘብ ከነወለዱ በረጅም ዓመታት መልሶ የሚከፍልበት የፋይናንስ አሠራር ነው። ይህ አሠራር አቅማቸው ውስን ለሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በወር በወር እየከፈሉ የቤት ባለቤት የመሆን ልዩ ዕድል ይፈጥራል። የከፍተኛ የቤት ኪራይ ወጪን በማስቀረት ዜጎች በየወሩ የሚከፍሉት ገንዘብ በራሳቸው ንብረት ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ያደርጋል። ይህንን ታላቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በሀገሪቱ የመጀመሪያው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈጽሟል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅዖ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ገልጸዋል። ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።   የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ በሰጡት አስተያየት፣ ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የከተሞች ልማት ላይ የግል ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ጠንካራ የቤት ፋይናንስ ገበያ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ቁልፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ እንዲጀመር እንዲሁም ሂደቱ ላይ ክትትል በማድረግ እያከናወኑት ላለው ሥራና አመራር ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ የፋይናንስ ማዕቀፍ አማካኝነት ዜጎች ሙሉ የቤት መግዣ ገንዘብ እስኪኖራቸው ሳይጠብቁ በባንክ ብድር የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይደረጋል።ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ ሳይሆን በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ይከናወናል። የሞርጌጅ ፋይናንስ ሥርዓቱ የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ ቁልፍ የሚባል ነው። መንግሥት ብቻውን ሊያከናውነው የሚችለውን ግዙፍ የልማት ጫና፣የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር በጋራ መወጣት እንደሚቻል የዛሬው ስምምነት ግልጽ ማሳያ ነው። የ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ፈንድ እና የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ዕቅድ እውን መሆን፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥንና ሁሉንም ዜጎች አካታች የልማት ባለቤት የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኮሪደር ልማት እና የነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 4, 2026 154
በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መጻኢውን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መሰረት የሚጥሉ ናቸው። ከእነዚህ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሀገሪቱን ከተሞች ገጽታና የነዋሪዎቿን የኑሮ ዘይቤ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት መርሃ ግብር ነው። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ስልጡን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው ስኬትና የፈጠረው አርአያነት አሁን ላይ አዲስ አበባን አልፎ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበትና ገጽታ ባለፈ የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለ እና የነገዋን ሀገር ዛሬ ላይ የመቅረጽ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። በኮሪደር ልማቱ ለእግረኛ እና ለአካል ጉዳተኞች ፈታኝ የነበሩ መንገዶች ዛሬ ሰፊና ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ንጣፎችና የብስክሌት መስመሮች ተተክተዋል።   በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህ ጥራት ያላቸው መሠረተ-ልማቶች የነገውን ጤናማ እና ማህበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። የኮሪደር ልማት የከተሞችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ዘመናዊነት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና የደህንነት ካሜራዎች የታገዙ ከተሞች በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ በር በመክፈታቸው፣ የ24 ሰዓት የስራ ባህልን በመፍጠር ለአያሌ ወጣቶችና አነስተኛ ነጋዴዎች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። በሌላ በኩል፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ልማት ኢትዮጵያን ወደ ቋሚ የኮንፈረንስ፣ የንግድ እና የባህል ቱሪዝም መዳረሻነት እየቀየራትም ይገኛል። በተለይም የከተሞችን ማህበራዊ መስተጋብርና የሕዝቡን አንድነት በማጠናከር ረገድ የኮሪደር ልማቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው። በልማቱ የተፈጠረው የጋራ ትስስር የነገዋን ጠንካራ፣ ሰላማዊና በአብሮነት የታነጸች ሀገር ለመገንባት እንደ ትልቅ ማህበራዊ መሰረት ያገለግላል። የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ያደገችና አሰራሯ የዘመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተሳስሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።   ስራው ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በማከናወን ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የስማርት ከተማ መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት አብሮ እየተዘረጋ ይገኛል። በተጨማሪም ከኮሪደር ልማት ጋር እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች ከተሞች ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋትና ሙቀት በመከላከል ለትውልዱ ንጹህና ጽዱ መኖሪያን አካባቢን ለማስረከብና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እያስቻለ ነው። በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአንድ ከተማ ገጽታ ማሻሻል ባሻገር፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ክልል ከተሞች ላይ በመስፋፋት ሀገራዊ ለውጥ ፈጥሯል ማለት ያስችላል። የዚህ ዘርፈ ብዙ የልማት ፍሬ ዛሬ ላይ የኑሮ ዘይቤን እያሻሻለ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ለወደፊቱ ትውልድም የኩራት ምንጭ የሆነ ዘላቂ ሀብት ሆኖ ይሸጋገራል። ዛሬ በጥራትና ውብ ሆነው እየተሰሩ ያሉ መንገዶች፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶች የነገዋ ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ ስልጡንና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ራዕይን እውን የሚያደርጉ ናቸው።
የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚና
Sep 3, 2026 168
የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል። ይህ የተኪ ምርት ስራ ጅማሮ በዋናነት ያነጣጠረው በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ በማስቀረት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የተበታተኑ የማምረት ሙከራዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር ለመቀየር ይፋዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ስትራቴጂ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለትግበራው መፋጠን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደ ትልቅ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።   ሀገራዊ ንቅናቄው በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ለጀመረው ብሔራዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ትልቅ አቅም የፈጠረ ነው። የስትራቴጂው መውጣት እና ወደ ተግባር መግባት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማስገኘት ጀምሯል። ትልቁ እና ዋነኛው ፋይዳም የውጭ ምንዛሬን ማዳን ሲሆን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህ መነቃቃት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የፋብሪካዎችን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ጋር በማስተሳሰር የአቅርቦት ሰንሰለቱን አጠናክሮታል። ይህንኑ ሀገራዊ ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ላይ የዘርፉን ስልታዊ ጠቀሜታ በተደጋጋሚ አንስተዋል። በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል በመጥቀስ፣ የሀገር ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ኢትዮጵያን የምግብ እጥረት እንደታደጋት ገልጸዋል። ተኪ ምርት ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይወጣባቸው የነበሩ የድንጋይ ከሰል እና የችፑድ ምርቶች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ በስፋት እየተመረቱ መሆናቸውን አንስተዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥራትን መሰረት አድርገው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተኪ ምርት ስራዎች ያገኘውን ስኬት ይበልጥ ለማስፋት እና ዘላቂ ለማድረግ አዳዲስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ግቦችን አስቀምጧል።   የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ወደ 49 ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባውን ወደ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም ስኬት አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ምርቶቻቸውን ያለ ደላላ ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የዲጂታል የገበያ ትስስር ፕላትፎርም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል። ወደፊትም ከቀላል የሸማች ዕቃዎች ባለፈ እንደ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካሎች እና ብረታብረት ያሉ አስራ አምስት ስልታዊ የከባድ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመተካት ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ ወጪ ንግድ ገቢን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ተወዳዳሪ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ተሰንቋል። በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የተኪ ምርት ስራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ምርታማነት እያሸጋገረ የሚገኝ ስልታዊ እርምጃም ነው። በጥናት የተለዩት 96 ቁልፍ ስልታዊ ምርቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ለሀገር በቀል እውቀትና ለፈጠራ ስራዎች ሰፊ በር ከመክፈቱም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ላይ ያላትን የድርድር እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል።
የቀይ ባህር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ሚና
Aug 29, 2026 853
(በሙሴ መለሰ) በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ አብዛኛው ወጪና ገቢ ሸቀጦች በባህር በር በኩል የሚተላለፉ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች ወይም የሎጂስቲክስ መስተጓጎሎች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ማሳረፉ የማይቀር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ የተከሰተውን የጸጥታ ቸግር ተከትሎ የተለያዩ የዓለም ሃገራት የቀይባህር መስመር ከባቤል ሜንደብ እስከ ስዊዝ ቦይ ድረስ ያለው ደህንነት አሳስቧቸዋል። ይሄንን ስጋት ለማቃለልም ሆነ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሃገራት በቀጣናው ካሉ የባህር ተጋሪ መንግስታት ጋር በመሆን የመሰረቷቸውን የጦር ሰፈሮች ቢያጠናክሩም አሁንም ቀጣናው በባህር ላይ ውንብድና፣ በህገ-ወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለስጋት የተጋለጠ ሆኖ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከቀይ ባህር ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ መሆኑን በጽኑ የምታምነው ኢትዮጵያ፣ ድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ የባለብዙ ወገን ውይይቶች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ ታበረክታለች። በተለይም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እንዲሁም የባህር ላይ ወንጀሎችን በጋራ ለመመከት የቀጣናው ሀገራት የተቀናጀ ምላሽ እንዲኖራቸው ድጋፍ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያላት መልክዐ ምድራዊ ትስስር እና የፀጥታ አጋርነት በቀይ ባህር ቀጣና መረጋጋት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በቀጣናው የሚከሰቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግሮች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የትብብር አማራጭን ተከትላ እየሰራች ትገኛለች። የአፍሪካ ቀንድና የቀይባሕር ደኅንነት ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ በቀጣናው ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ በሚደረጉ የማሪታይምና የደኅንነት ውይይቶች ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሰፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስትራቴጂያዊ የንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ በግልጽ ታይቷል። በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አምስተኛው የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባህር ላይ ህግ ማስከበር ውይይት (Maritime Law Enforcement Dialogue) ላይ፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅሞችን የሚያስጠብቅ ተሳትፎ አድርጓል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያላትን ሚና እና ባለቤትነት አሳይቷል። ለኢትዮጵያ የባህር በር ደህንነት የህልውና ጉዳይ ነው። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ተወካይ ካፒቴን ክብሩ መስፍን እንደገለጹት፣ የባሕር ላይ ሰላም መደፍረስ በቀጥታ የአገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ይነካል። አብዛኛው የሀገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ በባህር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚከሰቱ የባሕር ላይ ውንብድናዎችና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የንግድ ፍሰቱን እንዳያስተጓጉሉ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ካፒቴን ክብሩ አክለውም፣ የመርከቦች መድን ዋስትና መናርና የሸቀጦች መዘግየት የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንዳይፈታተኑ፣ ጠንካራና የተቀናጀ የባህር ላይ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ለመመከት ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ግንባር ቀደም ናት። በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር በመቀናጀት "ብሔራዊ የማሪታይም መረጃ ማዕከል" (National Maritime Information Centre) ለመመስረት ያቀደችው ስትራቴጂ፣ ሀገሪቱ ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚያሳይ ነው። መረጃን በጋራ መለዋወጥና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ለዚህ ስኬት ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች። በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ-ሰላጤ የሚስተዋሉ እንደ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሕገ-ወጥ አሳ ማጥመድ ያሉ ስጋቶች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ቀጣናዊ ኃይሎች ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC) የቀጣናው አስተባባሪ ሞስታፋ ኤልባና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አስተማማኝና የተረጋጉ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በቀይ ባህር ቀጣና ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC)፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅርበት በመሥራት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ያላትን የመሪነት ሚና በታሪካዊ ኃላፊነትና በሕግ አግባብ እያስጠበቀች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የባህር ኃሃይልን ጨምሮ በጥብቅ ዲሲፕሊኑ እና በመፈጸም አቅሙ የሚታወቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይሄ ሰራዊት በተለያየ ጊዜ ችግር ላጋጠማቸው ሃገራት ባሳየው የሰላም ማስከበር ሚናው በውጤታማነቱ የተመሰከረለትም ነው። የቀጣናውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሃይል አስፈላጊ ስለሆነም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሃገራት የኢትዮጵያን የባህር ላይ ህልውና በበጎ ይመለከቱታል። ለዚህም በቅርቡ በአንድ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የባብኤል ሜንደብን እና የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ሃገራቸው በቂ አቅም ስለሌላት የሌሎች እገዛ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የጅቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፋይናስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ ገለጻ አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አመላካች የሚሆኑት ያለ አግባብ ከባህሩ የተገፋችውና መብቷን የምትጠይቀው ኢትዮጵያ ያላት ዘርፈ ብዙ ዓቅም ለቀጣናውም ለራሷም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያላት መሆኑን ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 12702
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22151
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15185
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20926
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105825
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80192
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58534
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56140
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40064
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 39977
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39440
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37924
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105825
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80192
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58534
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56140
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 1026
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።   በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።   በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 848
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም