ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ
Mar 29, 2026 94
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ከመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቋል። በሻምፒዮናው ላይ 36 ክለቦች፣ ተቋማት፣ 9 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ 621 ወንድ፣ 436 ሴት በድምሩ 1057 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።   ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው። በውድድሩ ማብቂያ ቀን 10 የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል።   ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሻምፒዮናው አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን አጠናቋል። መቻል ሁለተኛ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው መጨረሳቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በሻምፒዮናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ለክለቦች እና አትሌቶች የተዘጋጁ የገንዘብ፣ የዋንጫና ሜዳሊያ ሽልማቶችን አበርክተዋል። ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ለማካሄድ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታውቋል።   ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን (Time Tronics) በሻምፒዮናው ላይ ተግባራዊ ሆኗል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።
ዋልያዎቹ ከሞሮኮ መልስ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን አድርገዋል
Mar 29, 2026 77
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ የመጀመሪያ ልምምዱን ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም ሰርቷል።   በአባቱ ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት ምክንያት በመጀመሪያው ጨዋታ ያልነበረው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጋቶቾ ፓኖም ስብስቡን ተቀላቅሎ ልምምድ አድርጓል። የዋልያዎቹ ተጋጣሚ የሆኑት ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድሬዳዋ መግባታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።   የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ሞሮኮ ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 አሸንፋለች።   በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ ወደ ምድብ ድልድል መግባቱን ያረጋግጣል።   36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድን ጎበኙ
Mar 29, 2026 88
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል አይሳይታ ከተማ የሚገኘውን የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድን ጎበኙ፡፡ በአፋር ክልል በአይሳይታ ከተማ የሚገኙት የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድ እርስ በእርስ የተሳሰረ ጥንታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ቅርሶች ናቸው።   በተለምዶ "ቀይ ፎቅ" ተብሎ የሚጠራው ቤተ-መንግሥቱ ሱልጣል አሊሚራህ ሐንፍሬ ወደ ሥልጣን በመጡ በአምስት ዓመታቸው በ1940 ዓ.ም የተመሠረተ ነው። ቤተ መንግሥቱ ለረጅም ጊዜ በእድሜ ብዛት ፈራርሶ የቆዬ ሲሆን፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ ታድሶ አሁን ላይ የሱልጣኑ መቀመጫና ሙዚየም ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በመስጅዱና በቤተ-መንግሥቱ ዙሪያ ያለው አካባቢ ለበርካታ ዓመታት የሱልጣንነት ሹመት የሚከናወንበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የሱልጣን አሊሚራህ መስጅድም መሠረቱ በሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ የተጣለ ቢሆንም ግንባታው ሳይጠናቀቅ ቆይቷል። ከሠላሳ ዓመታት በኋላ ግንባታው ተጠናቆ በቅርቡ ተመርቋል።   መስጅዱ በኢትዮጵያ ደረጃ በስፋቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለትና የአካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ታሪካዊ ቅርስ ነው። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!  
Mar 29, 2026 2050
በዮሐንስ ደርበው የሥልጣኔ ቁንጮ -በምርጫ ካርድ መሪን መምረጥ! በያዝነው ዓመት ወርኃ ግንቦት በባተ 24ኛው ቀን ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ቀን ቆርጣለች። ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ወደ ትግበራ ምዕራፍ ገብታለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን፤ ቀሪ ሥራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን ገልጿል። ለዚህም የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ መግባታቸው በአሥረጂነት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ መሰጠቱ፤የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች በኦንላይን ሥርዓት በታዛቢነት መመዝገባቸውን አስረድቷል። በኢዜአ ዐይን …! በገበታ ለሀገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የጤና ነገር … እንዲሁም ዐለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት መጥተው ፈቃድ የሚወስዱበት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሠለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች አሠማርቷል። ለመራጮች ምዝገባ የተዘጋጁ 46 ሺህ 757 ጣቢያዎች እና ተጨማሪ በርካታ ንዑስ ጣቢያዎችም ተሠናድተዋል። እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ፤ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮው ምርጫ ለውድድር ተመዝግበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ 73 ዕጩዎች በግል ለውድድር መቅረባቸው ተገልጿል። ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ የሚከናወነው ሁሉም ፓርቲ ሕግን አክብሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደሆነ ያስማማል። የምርጫው ስኬት የሚረጋገጠውም ቦርዱ ለብቻው በሚያደርገው ጥረት ሳይሆን፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዕኩል ኃላፊነቱን መወጣት ሲችል መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰባት ምዕራፎችና በ30 አንቀጾች የቀረበውን የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ፈርመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሂደት የዜጎችን ተሳትፎ ለማበረታታት “ምርጫችን ነው-ሀገር ያለኛ” የተሰኘ የምርጫ ኅብረ-ዝማሬ ማስመረቁ ይታወቃል። በዚሁ ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ኅብረ-ዝማሬው አካታች ተሣትፎን ለማበረታታት መሠናዳቱን አስገንዝበዋል። የልዩ ልዩ ድምጾች ኅብራዊነት ያለውን የጋራ ጥንካሬ በማሳየት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዜጎችን ተሳትፎ ማጎልበት የኅብረ-ዝማሬው ዓላማ መሆኑም ተገልጿል። በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫም “የሀገር ካስማ” የተሰኘ ኅብረ-ዝማሬ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ምዝገባው እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይቀጥላል። የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ የሚገኘውም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ ነው። ከአጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ያህሉ የዲጂታል የመራጮች ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ቦርዱ ማሳወቁ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ በተከናወነ የመራጮች ምዝገባ ከ28 ሚሊየን 365 ሺህ 310 በላይ መራጮች ተመዝግበዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 37(7) ላይ ቦርዱ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክቶችን አቀማመጥ፣ ቅደም ተከተልና እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ግልጽ በሆነ መንገድ በመመሪያ እንደሚወስን ይደነግጋል። በዚህም መሠረት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ባሳለፍነው መጋቢት 14 ቀን በይፋ አስጀምሯል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት የሚከናወነው በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክት አቀማመጥን የሚወሥነው የዕጣ ማውጣት ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የዓየር ሠዓት ድልድል የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል። በዚህም መሠረት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የዓየር ሠዓት ተድልድሎላቸዋል። የሠዓት ድልድሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና ፖሊሲዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ የግል ዕጩዎችም አማራጭ ሐሳባቻቸውን እንዲያጋሩና የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ብሎም ከመራጩ ጋር እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ ነው። ይፋ በተደረገው ነፃ የዓየር ሠዓት የተመዘገቡ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች በኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ ይጠበቃል። በአጠቃላይ በምርጫ ካርድ መሪን መምረጥ ከሥልጣኔ ቁንጮዎች አንዱ ሆኖ ይነሳል። የመራጮች ምዝገባ ሂደትም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራርን እንዲያጠናክሩ ብሎም በካርዳቸው ይሁንታ የሚመራቸውን መምረጫ ቁልፍ ነው። ኢትዮጵያ በወሳኝ የምርጫ ወቅት ላይ ናትና፤ ለስኬታማነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #የመራጮች_ምዝገባ #በኢዜአ_ዐይን
የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ያስችላል
Mar 29, 2026 133
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ገንቢ ሚና እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ገለጹ፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ሕጎችና ደረጃዎች ዴስክ ኃላፊ ወንደሰን ታደሰ፤ ኢትዮጵያ የውኃ፣ የደን፣ የዓየር ንብረት አገልግሎት፣ የቁጥጥርና ቱሪዝም ሥርዓተ-ምኅዳር ብትታደልም በሚገባት ልክ አልተጠቀመችም ብለዋል።   የሥርዓተ-ምኅዳር ጉዳዮች በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ጉዳዮች በከፍተኛ ጫና ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።   የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ በአገልግሎቱ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች መካከል የጋራ መግባባትን በመፍጠር ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስችልም አስረድተዋል። የፋርም አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሸዊት አማኑኤል በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን የብዝኃ ሕይወት ሃብቶች ለሕብረተሰቡ ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የባሌ አካባቢ ማኅበረሰብ ተፈጥሮን በመንከባከብ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ተጠቃሚ መሆን መጀመሩን ገልጸው፤ ይህ በሁሉም አካባቢዎች መስፋት እንዳለበት አመላክተዋል። መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራና በአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገቡን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝኃ ሕይወት ሀብት ይበልጥ መለየትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡   በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ሀብትና ሀይድሮሎጂ መምህር ዓለምአየሁ አባተ (ዶ/ር)፤ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ማኅበረሰቡ የሠራበትን እንዲያገኝ በማድረግ የተጠናከረ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡ በባሌ ኢኮሎጂ በ20 ወረዳዎች በመሰማራት እየሠሩ መሆኑን የገለጹት የፋርም አፍሪካ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ፈይሳ አሰፋ፤ በኢትዮጵያ የካርበን ክፍያ መጀመሩ የሕብረተሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ተነሳሽነት ያሳድጋል ብለዋል፡፡ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጁ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የብዝኃ ሕይወት ሀብት ጠብቃ እንድትቆይና ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል ሲሉም አስገንዝበዋል።
የሚታይ

ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያበረታታ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረጓ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጓታል
Mar 29, 2026 240
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የአረንጓዴና የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያበረታታ የተሟላ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረጓ በቀጣናው ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዳደረጋት ተገለጸ። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የፖሊሲ ጥናት ማዕከል ኃላፊና በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አማካሪ አሊ ዛፋር፤ የሀገሪቱ የኃይል አቅርቦት ምንጭ የሆነው ታዳሽ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል።   በተለይም ከውኃ ሀብት የሚመነጨው ኃይል የኢንዱስትሪ ልማትን በማሳለጥ ሀገራዊ የልማት ግቦችን በማሳካት ኢትዮጵያን ከቀጣናው ሀገራት ጋር በኃይል ያስተሳስራል ሲሉም ለኢዜአ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረገችው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም የዋጋ ግሽበት መቀነሱንና የውጭ ምንዛሬ ክምችት መሻሻሉን አንስተዋል።   በቀጣናው ዝቅተኛ የኃይል አቅርቦት ዋጋ ያላት፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ እና መንግሥት ለዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳራሻ እንዳደረጋትም አመላክተዋል። ሀገሪቱ ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ የምታደርገውን ጥረት በመጥቀስ፤ መንግሥት በታዳሽ ኃይል የሚመራ አረንጓዴ ልማትን ለማረጋገጥ ያለውን ጽኑ አቋም አድንቀዋል፡፡   ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት ትልቅ ትኩረት በመስጠት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲበረታቱ እያደረገች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢ ጥበቃና በታዳሽ ኃይል ልማት ግንባር ቀደም መሆኗን ጠቅሰው፤ ሌሎች ሀገራት ሊማሩበት የሚገባ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 397
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት።   ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል
Mar 28, 2026 356
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተንዳሆ መስኖ ልማት የማጠናቀቂያ እና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ መርቀዋል።   የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለእኛ ሉዓላዊነት ማለት ዳር ድንበርን ከመጠበቅ ባሻገር፣ የዜጎችን አንገት የሚያስደፋውን የልመና እጅ ሰብሮ በራስ ምርት መቆም ነው ብለዋል። የአፋር ሕዝብ ለዘመናት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በንቃትና በጀግንነት ሲጠብቅ የኖረ የቁርጥ ቀን የሀገር ባለውለታ መሆኑንም አውስተዋል። ለምርቃት የበቃው የተንዳሆ መስኖ ልማት የማጠናቀቂያ እና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ትግላችን የድል ዓርማ ነው ብለዋል። ለዓመታት ተጓትቶ፣ ተስፋ አስቆርጦና የጎርፍ ሥጋት ሆኖ የቆየውን ግድብ፣ በቆራጥ አመራርና በፈጣን አፈጻጸም ወደ ልማት አውታር መቀየሩን ተናግረዋል። ይህ ፕሮጀክት ለምድራችን በረከት፣ ለሕዝባችን የብልጽግና ምንጭ እንዲሆን ዳግም ተወልዷል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እውነተኛ ነጻነትና ምሉዕ ክብር የሚረጋገጠው በራስ ማሳ ላይ በሚለማ ሰብል፣ በራስ ጉልበት በሚገራ ውኃና ከማንም እጅ በማይጠበቅ የዜጎች የዕለት ጉርስ መሆኑንም አመልክተዋል።   የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተነሣነውም የዜጋን ክብርና የሀገርን የህልውና መሠረት ለማጽናት ነው የዚህ ዋናዎቹ ዐቅሞቻችን ደግሞ ያልተነካው የበረሃ ለም አፈራችን፣ ውኃችን፣ ትጉህ ሕዝባችንና የመስኖ አውታሮቻችን ናቸው ብለዋል። ለእኛ መስኖ ማለት የዝናብ ጠባቂነትን ታሪክ መዝጋት ነው፤ መስኖ ተለዋዋጭ የሆነውን የዓለም ጂኦ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥረት የምንቋቋምበት ብቸኛውና አስተማማኙ መከታችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። የቆላማ አካባቢዎቻችንን እምቅ ሀብት ማልማትና የዜጎቻችንን ሕይወት በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ማሣለጥ የወደፊት ዕጣ ፈንታችንን የመወሰን ጉዳይ እንደሆነም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት። ቃልን በተግባር፣ ሐሳብን በውጤት እየለወጥን፣ አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩንና ባለ ሀብቱን ያስተሣሠረ የልማት ሠንሰለት በመፍጠር፣ ኢትዮጵያን በምግብ ራሷን የቻለች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የምትተርፍ የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለዋል።
የፌዴራል መንግሥት ተንዳሆን ከችግር አውጥቶ ወደ ልማት አውታር መልሶታል - ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ
Mar 28, 2026 305
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል መንግሥት ተንዳሆን ከችግርና ስጋት አውጥቶ የአፋርን ክልል ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የልማት አውታር መልሶታል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል የተንዳሆ መስኖ መሠረተ ልማት ማጠናቀቂያና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክትን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።   የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የተንዳሆ የመስኖ ፕሮጀክት ዱብቲ፣ የሠመራ ሎጊያ ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ ስድስት ወረዳዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የአፋር ሕዝብ በአዋሽ ወንዝ ጎርፍና በድርቅ በውሃ እጥረት ጉዳት ሲደርስበት መቆየቱን አንስተው፤ አሁን ግን ችግሩ እየተቀረፈ ነው ብለዋል። የተንዳሆ ግድብ ውሃ ሲሞላ የማስተንፈሻ ቦዩ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ የተስተካከለ ስላልነበር ማህበረሰቡ ላይ ትልቅ የጎርፍ ስጋት ሆኖ እንደነበር አስታውሰዋል። በመሆኑም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አፋርን ከጎርፍ አደጋ እየታደገና የውሃ አቅምን በመጠቀም የውሃ እጥረትን እየፈታ መሆኑን ተናግረዋል።   ለፌደራል መንግሥቱ ትልቅ አድናቆት አለኝ ያሉት ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ፤ በቢሊየን ሀብት አውጥቶ ተንዳሆን ወደዚህ ደረጃ ማድረሱ ቀላል አይደለም ነው ያሉት። በአፋር ክልል በርካታ የቆላማ ልማትና የመስኖ ግድቦች እየተገነቡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም የፌዴራል መንግሥቱን አመሥግነዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ሕዝቡን ያሳተፉ የፀጥታ ማስከበር ሥራ እየተከናወነ ነው
Mar 29, 2026 288
ገንዳውኃ፤ መጋቢት20/2018 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ጎንደር ዞን ሕዝቡን ያሳተፉ የፀጥታ ማስከበር ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ። በዞኑ በወቅታዊ የሰላምና ልማት ተግባራት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በገንዳ ውኃ ከተማ ተካሂዷል። የአማራ ክልል የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ ተሾመ አግማስ በዚሁ ወቅት፤ በዞኑ አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ የልማትና የፀጥታ ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።   ከሰላም ማስፈን ሥራ ጎን ለጎን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ ለመጨረስና አዳዲስ የልማት ሥራዎችን ለማስጀመር የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉንም አንስተዋል። ሕዝቡ የልማት ሥራዎችን ከጸጥታ ማስከበር ተግባር ጋር በማጣመር ለማስኬድ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች እንዲጠናከሩም ጠቀዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እያሱ ይላቅ በበኩላቸው፤ በእያንዳንዱ ተግባር የሕዝቡን ተሳትፎ በማረጋገጥ የሰላሙና የልማቱ ባለቤት ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎም በዞኑ ያለው ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንና ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከናወነ ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዳበረ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ነው
Mar 28, 2026 513
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፉክክር በማድረግ ለዳበረ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት መድረክ ነው ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል። የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አማራጭ ሃሳቦችን ለህዝብ በማቅረብ ድምፅ ማግኘት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እያደረጉ ነው። በሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫም ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፉክክር በማድረግ ለኢትዮጵያ የዳበረ የመድበለ ፓርቲ ባህል ግንባታ እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ዋና ጸኃፊ ዋሲሁን ተስፋዬ፤ የኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ወሳኝ የልምምድ ዕድል እንዳለው ተናግረዋል። ይህም ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፉክክር በማድረግ የዳበረ የመድበለ ፓርቲ ምኅዳር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ገንቢ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አንስተዋል። ለአብነትም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) በራሱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ዴሞክራሲያዊ የአመራር ለውጥ ማድረጉን አስረድተዋል። የፖርቲው ውስጠ-ዴሞክራሲም የሀገርን የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ለማጠናከር ጉልህ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል።   የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት(ኢዴሕ) ሊቀመንበር ገብሩ በርሔ፤ መንግስት ሰፊ የፖለቲካ ምኅዳር እንዲፈጠር በማድረግ አስደናቂ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትም የፓርቲዎችን ሚዛናዊነት ማስጠበቅ የሚያስችል ምቹ የድጋፍና ክትትል ሥርዓት መፍጠሩን ገልጸዋል። ፓርቲያቸውም የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፉክክር ባህል በማጎልበት ለመድበለ ፓርቲ ግንባታ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ አንተዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስቻይ ሁኔታ ፈጥሮ እየሰራ ነው ያሉት ደግሞ የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍትሕዓለው ዓባይ ናቸው።   በዚህም ሰላም ለኢትዮጵያ የፓርቲዎች ጥምረት በሕዝብ ተወካዮችና በክልል ምክር ቤቶች የሚወከሉ ዕጩዎችን በማቅረብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የፉክክር ሂደትም አማራጭ የፖሊሲ ሀሳባቸውን በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ለህዝብ በማቅረብ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እየተጠቀሙበት እንደሚገኝ ተናግረዋል። በህዝብ ይሁንታ የተመሰረተ መንግስት በማቋቋም ጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ለመገንባት ዜጎች በምርጫ ሂደት የሚሰጡት ድምፅ ከፍተኛ ዋጋ እንዳለውም ጠቁመዋል። ለዚህም የፓርቲዎቻቸውን አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች የምርጫን ዋጋ በማስገንዘብ የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። መራጩ ህዝብም የምርጫ ካርድ በማውጣት ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምፅ መስጠት የሚያስችል ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።  
የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመደብላቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል
Mar 28, 2026 410
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመደብላቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በመጠቀም ፕሮግራሞቻቸውን በአግባቡ ማስተዋወቅ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስገነዘበ። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት ድልድል የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በዚሁ ወቅት፤ ቦርዱ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ ለፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት ድልድል ማድረግ ነው ብለዋል።   ይህ የነፃ የአየር ሰዓት ድልድል የሚካሄደውም ቦርዱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመሆን ባበለጸገው አዲስ ሲስተም መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ አሰራር የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን ሀሳብ፣ ፖሊሲ እና ፕሮግራም ለመራጩ ህዝብ እንዲያስተዋውቁ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ፓርቲዎች የሚመደብላቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተለይም ፓርቲዎቹ ባስመዘገቧቸው ሴት እና አካል ጉዳተኛ ዕጩዎች ብዛት ልክ ተጨማሪ ነፃ የአየር ሰዓት የሚፈቅድ አዋጅ በመፅደቁ፤ አሰራሩ በዚህ ምርጫ ተግባራዊ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው፤ ነፃ የአየር ሰዓቱ መራጩ ህዝብ ድምፅ በሚሰጥበት ወቅት በዕውቀት ላይ ተመስርቶ እንዲወስን ያስችላል ብለዋል።   ነፃ የአየር ሰዓቱ ለ47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች በዕጣ ድልድል እንደሚደረግ ተናግረዋል። የዘንድሮው ድልድል ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው፤ ይህም በ50 መገናኛ ብዙሃን (በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በጋዜጣ) የሚስተናገድ ይሆናልም ብለዋል። ይህ ድልድል ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው፣ ፓርቲዎች የአየር ሰዓቱን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ አስገንዝበዋል። መገናኛ ብዙሃንም ለፓርቲዎቹ አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት አጠቃቀም ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓላት ቀናትን ሳይጨምር ከመጋቢት 23 እስከ ግንቦት19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተገልጿል።
በምርጫው በንቃት በመሳተፍ የሚወክለንን ለመምረጥ ካርድ እየወሰድን ነው
Mar 28, 2026 330
ቡታጅራ ፤መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ የሚወክለንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ካርድ እየወሰድን ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፣ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን፤ ለዚሁ ተግባር የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ዝግጅቶች መካከል ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ። ኢዜአ በቡታጅራ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ። በከተማዋ የእርንዛፍ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ባህርነሽ መሀመድ፤ "የመራጭነት ካርድ በመውሰድ የሚጠቅመኝን ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ" ብለዋል። የምርጫ ካርድ መያዝ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም እንዲችሉ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ፣ ሁሉም የምርጫ ካርድ መያዝ እንዳለበትም ይመክራሉ። ሌላኛው የከተማዋ የ02 ቀበሌ ነዋሪ አቶ ቢራቱ ጠረጋ በበኩላቸው፤ የሕዝብን የልማት ፍላጎትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፓርቲ ለመለየት የምርጫ ክርክሮችን በንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ጠቁመዋል።   የአካል ጉዳተኛ የሆኑት አቶ ቢራቱ፤ በምርጫው አካል ጉዳተኞችን በትምህርትና በሥራ እድል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ ፓርቲ እንደሚመርጡ ተናግረዋል።   በከተማዋ የ04 ሸባብ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ከድጃ ሳሉሲን እና የ03 ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሪት መለሰች ተካም እንዲሁ፤ የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልስ ፓርቲ ለመምረጥ ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።   የካርድ አሰጣጥ ሂደቱም ምቹ እና ቀልጣፋ መሆኑን ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልል 1 አስፈጻሚ አቶ እስጢፋኖስ ፍቃዱ፤ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መራጮች እየተመዘገቡ መሆኑን አረጋግጠዋል። በምርጫ ክልሉ በሚገኙ 87 የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የአባል ሃገራቱን ጥቅም ለማስከበር መትጋት ይጠበቅበታል
Mar 27, 2026 815
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የተቋቋመለትን አላማ እንዲያሳካ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ነጻነቱን ጠብቆ መጓዝ እንደሚገባው በቤልጂየም፣ ኔዘርላንድስ እና ሉክስምበርግ (ቤኔሉክስ) አገራት እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ገለጹ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት (ኦ ኤስ ፒ ኤስ ) የመሪዎች ጉባኤ ነገ ይጀምራል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ በርካታ የሀገራት መሪዎች በጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ። የድርጅቱ የመሪዎች ጉባኤ ቅድመ ስብስባ ዛሬ ተካሄዷል።   በስብሰባው ላይ በቤልጂየም፣ ኔዘርላንድስ እና ሉክስምበርግ (ቤኔሉክስ) አገራት እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ተገኝተዋል። አምባሳደር እሸቴ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ለአባል ሀገራቱም ሆነ ለመላው ዓለም ወሳኝ አስተዋጾኦ ማድረግ እንዲችል ራሱን በገንዘብ እና በመዋቅር ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል። አስቸጋሪ በሆነው የዓለም ተቀያያሪ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ድርጅቱ የአባል ሀገራቱ ጥቅም እንዲከበር በትጋት መስራት እንዳለበት አመልክተዋል። አምባሳደር እሸቴ በተለይ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ድርጅቱ እ.አ.አ በ1975 ከቅኝ ግዛት በኋላ የተመሰረተ እና በቅኝ ግዛት ሲጎዱ ለነበሩ የአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት አለኝታ እንዲሆን ታስቦ የተመሰረተ መሆኑን አስታውሰው ኢትዮጵያ ለዚህ ድርጅት መጠናከር ትኩረት ሰጥታ እንደምትንቀሳቀስ አስረድተዋል። ባለፉት ጊዜያት የድርጅቱ በጀት በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ይሸፈን እንደነበረ ገልጸው ድርጅቱ የተቋቋመለትን አላማ እንዲያሳካ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ነጻነቱን ጠብቆ መጓዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ አባል ሀገራቱ የሚጠበቅባቸውን የገንዘብ መዋጮ መክፍል እንደሚገባቸው ነው ያሳሰቡት።   በቅድመ ጉባኤ ስብሰባው የበርካታ ሀገራት ተወካዮች ድርጅቱ እያበረከተ ያለውን የማይተካ አስተዋጾኦ በማድነቅ የተሻለ ጠንካራ ሆኖ በሚወጣበት ጉዳይ ላይም ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። በአባል ሀገሪቱ ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ፣ የወጣቶችን አቅም በሚገባ መጠቀም ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ያለን ትስስር በማሳደግ ለሁለንተናዊ እድገት መጠቀም የሚሉት በስፋት የተንሸራሸሩ ሀሳቦች ናቸው። በአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ያለውን ድህነት በማጥፋት ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማፋጠንን አላማ በማድረግ የተመሰረተው ድርጅቱ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት አይነተኛ የትብብር ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ነው። ከአውሮፓ ሀገራት ጋር ያለው የንግድ፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ አስተዳደር እና ሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብር ደግሞ የደቡብ- ሰሜን ትስስርን በማጠናከር ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የክርክር መድረክ መራጩ ህዝብ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድምፅ እንዲሰጥ ምቹ መደላድል ይፈጥራል
Mar 27, 2026 608
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ወጥ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ መራጩ ህዝብ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድምፅ እንዲሰጥ ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባዘጋጀው የመጀመሪያው የክርክር መድረክ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት(ሰላም)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ብልፅግና ፓርቲ ተሳትፈዋል።   የክርክር መድረኩን አምስቱ የቦርዱ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በይፋ አስጀምረውታል። በዚሁ ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ የክርክር መድረኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭና ፕሮግራሞቻቸውን ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለህዝብ የሚያደርሱበት ነው ብለዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን ለህዝብ የሚያደርሱበትን ወጥ የሆነ የክርክር መድረክ ለማመቻችት በርካታ የሙከራ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል። የክርክር መድረኩ መራጩ ህዝብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አማራጭ ሃሳቦች በማጤን በዕውቀትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ድምፅ እንዲሰጥ ማድረግ የሚስችል መሆኑን ገልጸዋል።   በምርጫ ክርክር የዝግጅት ምዕራፉ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጫቸውን ለህዝብ የሚያደርሱባቸው ርዕሰ ጉዳዮች በገለልተኛ ሙያተኞች ጥናት መካሄዱንም አስታውሰዋል። በተጨማሪም በክሩክሩ ወቅት የሚቀርቡ አሃዛዊ መረጃዎችና ሀሳቦች ትክክለኝነት የሚመዝኑና የሚያጣሩ ባለሙያዎች እንዲካተቱ መደረጉንም አንስተዋል። በክርክር መድረኩም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንዲገኙ በማድረግ ለዲሞክራሲ ምኅዳር መጎልበት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታችነተና አሳታፊነትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ህዝብ በቀረቡት የማኑዋልና ዲጂታል አማራጮች ድምፅ መስጠት የሚያስችለውን ካርድ በስፋት እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የክርክር መድረኩም መራጩ ህዝብ ድምፅ መስጫ ካርድ እንዲወስድ ከፍተኛ መነቃቃት እንደሚፈጥር ሰብሳቢዋ ጨምረው ገልጸዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተናል
Mar 27, 2026 534
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን፤ ሌሎች አስፈላጊ የምርጫ ቅድመ ዝግጅቶችም እየተከናወኑ ይገኛሉ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች እንደገለጹት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በዝግጅት ላይ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወጣት መዲና መሀመድ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ እንደ ዜጋ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የሚጠበቅባትን ድርሻ መወጣቷን ገልጻለች። ዘንድሮ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ ማውጣቷን ገልጻ፤ የወጣቱን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል የምለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለው ብላለች። ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ በበኩሉ፤ በምርጫው ወጣቱን ጨምሮ የዜጎችን ተጠቃሚነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ለሚሰራ ፓርቲ ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ ሲል ገልጿል። የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚችለውን ፓርቲ ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ ወስዶ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን የተናገረው ደግሞ ወጣት ኢሳ ሰኢድ ነው፡፡ ሌላኛዋ ወጣት የተመኝ አስማማው በበኩሏ፤ ምርጫው የዲሞክራሲ መብት ተጠቃሚነትን የምናረጋግጥበት መንገድ በመሆኑ ያስተዳድረኛል የምለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ብላለች፡፡   የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት በረከት ቢርቢርሳ፤ ማህበሩ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ላይ ወጣቶች የተሻለ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማስተባበር ሚናውን ሲወጣ መቆየቱን አንስቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በመስራት በምርጫው አስተዋጿቸውን እንዲያበረክቱ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ማህበራዊ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድን ጎበኙ
Mar 29, 2026 88
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል አይሳይታ ከተማ የሚገኘውን የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድን ጎበኙ፡፡ በአፋር ክልል በአይሳይታ ከተማ የሚገኙት የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ ቤተ-መንግሥት እና መስጅድ እርስ በእርስ የተሳሰረ ጥንታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ቅርሶች ናቸው።   በተለምዶ "ቀይ ፎቅ" ተብሎ የሚጠራው ቤተ-መንግሥቱ ሱልጣል አሊሚራህ ሐንፍሬ ወደ ሥልጣን በመጡ በአምስት ዓመታቸው በ1940 ዓ.ም የተመሠረተ ነው። ቤተ መንግሥቱ ለረጅም ጊዜ በእድሜ ብዛት ፈራርሶ የቆዬ ሲሆን፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ ታድሶ አሁን ላይ የሱልጣኑ መቀመጫና ሙዚየም ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በመስጅዱና በቤተ-መንግሥቱ ዙሪያ ያለው አካባቢ ለበርካታ ዓመታት የሱልጣንነት ሹመት የሚከናወንበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የሱልጣን አሊሚራህ መስጅድም መሠረቱ በሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ የተጣለ ቢሆንም ግንባታው ሳይጠናቀቅ ቆይቷል። ከሠላሳ ዓመታት በኋላ ግንባታው ተጠናቆ በቅርቡ ተመርቋል።   መስጅዱ በኢትዮጵያ ደረጃ በስፋቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለትና የአካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ታሪካዊ ቅርስ ነው። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በኦሮሚያ ክልል ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግና የከተማ ፕላንን ለማስጠበቅ ያግዛል የተባለ ደንብ መተግበር ጀመረ   
Mar 29, 2026 227
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ የከተማ ፕላንን ለማስጠበቅና ከተሜነትን ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለ ደንብ መተግበር መጀመሩ ተገለጸ። በክልሉ ካቢኔ ሕገ-ወጥ የከተማ ቤትን ሕጋዊ ለማድረግ የጸደቀውን ደንብ መነሻ በማድረግ የክልሉ መሬት ቢሮ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የክልሉ መሬት ቢሮ ኃላፊ መሰረት አሰፋ በዚሁ ወቅት፤ እንደ ክልል መሬትን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር የመሬት አጠቃቀም ፕላን መተግበሩን እና የካዳስተር ሥርዓትን ወደ ትግበራ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን በሚፈለገው መልኩ መተግበር እንዳይቻል የከተሞች ሕገ-ወጥ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅፋት መፍጠሩን አንስተዋል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በተለይም ችግሩ ስር የሰደደባቸውን ከተሞች በጥናት በመለየት ሕገ-ወጥ መኖሪያ ቤትን ሕጋዊ ለማድረግ የሚያስችል ደንብ በክልሉ ካቢኔ መጽደቁን አስረድተዋል። ደንቡ በክልሉ ከተሞች ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ የከተማ ፕላንን ለማስጠበቅና ከተሜነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግም አመልክተዋል። በሌላ በኩል ሸገር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን ቀድመው መተግበር በመቻላቸው ደንቡ በእነዚህ ከተሞች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን አረጋግጠዋል። ከተሞቹ ዘመናዊ የመሬት አያያዝ የካዳስተር ሥርዓትን እያጠናቀቁ በመሆኑ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥን በዲጂታል መንገድ እያከናወኑ ስለመሆኑ ገልጸዋል። ይህም ከተሞቹ ፈጣን ዕድገት ላይ እንዲገኙ ከማስቻል ባለፈ የገቢ አሰባሰብ ዐቅማቸውን በማሳደግ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲፋጠን ማገዙን ነው ያስረዱት።   የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ ጉዮ ዋሪዮ በበኩላቸው፤ ደንቡ ከ2005 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን ጊዜ የሚያካልል መሆኑን አስገንዝበዋል። ከዚህም ባለፈ የከተማ ፕላን በምንም መልኩ የማይጣስ፤ ቆይታውም ከሁለት ዓመት ያልበለጠ ሲሆን ደንቡ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ደንብ ለመጠቀም የሚያመለክት ማንኛውም ሰው በአንድ ከተማ ውስጥ ከአንድ ሕገ-ወጥ ግንባታ ያልበለጠ ያለው ሰው ብቻ እንዲሆን የሚያስገድድ መሆኑንም አመልክተዋል። ሌላው የከተማውን ዝቅተኛ መመዘኛ መስፈርት ከግምት ባስገባ መልኩ ለመኖሪያ ቤት የሚሰጥ ቦታ ስፋት ብቻ እንዲጠቀም የሚደረግ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት።
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤቶች ተመዝግበዋል
Mar 29, 2026 152
አዳማ፤ መጋቢት 20/2018(ኢዜአ)፡- የሴቶችን ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን ገለጹ። የኦሮሚያ ሴት አመራር አባላት ፎረም በአዳማ ተካሂዷል። የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔና የፎረሙ ሰብሳቢ ሰዓዳ አብዱራህማን በዚሁ ወቅት፤ ሴቶች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ በተጓዳኝ የፖለቲካ ተሳትፏቸው እንዲጠናከር በተደረገው ጥረት ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። በሥራ ላይ ባለው የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛው የሥራ ዘመን 46 በመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በክልሉ በሕግ ተርጓሚና ሥራ አስፈፃሚ ዕርከኖች የሴቶች ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱንም አመላክተዋል። ፎረሙ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ፎረሙ ሴቶች በሀገር ግንባታ ረገድ እየተወጡ ያሉትን ሚና ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማስቻል ረገድ የድርሻውን እየተወጣ ነው ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ መብራት ባጫ ናቸው።   የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ዐቅም በማጎልበት ረገድ ፎረሙ የሴቶች የማስፈፀም ዐቅም እንዲዳብር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በዚህም ሴቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 43 በመቶ ለፓርላማ እንዲሁም 42 በመቶ ለጨፌ ኦሮሚያ በዕጩነት መቅረባቸውን ጠቁመዋል። በተያዘው በጀት ዓመት የዜግነት አገልግሎት እስካሁን 156 ሺህ የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባትና በመጠገን ዐቅም የሌላቸው እናቶችንና አጋረጋውያንን ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል ነው ያሉት።
ፌስቲቫሉ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበትና አብሮነት የሚደምቅበት ነው
Mar 29, 2026 82
ሐረር፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት፣ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕሴትና አብሮነት የሚደምቅበት ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል "የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ በሐረር ከተማ ተጀምሯል፡፡   ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በወቅቱ እንዳሉት፤ የኅብረ-ብሔራዊ አንድነትና አብሮነት መጠበቅና መረጋገጥ የባህል ስፖርቶችን አጉልቶ ለማሳየት ጠቃሚ ነው። የበለጠ እንዲጎለብትም መንግሥት ልዩ ትኩረት እንደሰጠው ተናግረዋል፡፡ የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ መክዩ መሀመድ በበኩላቸው፤ መንግሥት የባህል ስፖርትን ቀጣናዊ ትስስርን ለማምጣት፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር እየሠራበት ነው ብለዋል።   ኢትዮጵያ የ2026 የአፍሪካ የባህል ስፖርት ፌስቲቫልን የማስተናገድ ዕድል ማግኘቷንም አውስተዋል። ይህን ዕድል በመጠቀምም የባህል ስፖርቶቻችንን ለአፍሪካ እህት ወንድሞቻችን ለማስተዋወቅ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል። በሀገሪቱ ከ293 በላይ የተመዘገቡ ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች እንዳሉ በጥናት መለየቱን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጅ የጨዋታ ሕግና ሥርዓት ተዘርግቶላቸው ለውድድር የበቁት ከ11 የስፖርት ዓይነቶች እንደማይበልጡ ጠቁመው፤ በቀጣይ ይህን ለማስፋት እንደሚሠራ አመላክተዋል። የባህል ስፖርት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በዘላቂነት በማጠናከር ረገድ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት የገለፁት ደግሞ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሕይወት መሀመድ ናቸው፡፡ በሐረር ከተማ የተጀመረው የባህል ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ለ8 ቀናት እንደሚቆይና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፎ እንደሚያደርጉበት ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያበረታታ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረጓ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጓታል
Mar 29, 2026 240
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የአረንጓዴና የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያበረታታ የተሟላ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረጓ በቀጣናው ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዳደረጋት ተገለጸ። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የፖሊሲ ጥናት ማዕከል ኃላፊና በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አማካሪ አሊ ዛፋር፤ የሀገሪቱ የኃይል አቅርቦት ምንጭ የሆነው ታዳሽ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል።   በተለይም ከውኃ ሀብት የሚመነጨው ኃይል የኢንዱስትሪ ልማትን በማሳለጥ ሀገራዊ የልማት ግቦችን በማሳካት ኢትዮጵያን ከቀጣናው ሀገራት ጋር በኃይል ያስተሳስራል ሲሉም ለኢዜአ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረገችው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም የዋጋ ግሽበት መቀነሱንና የውጭ ምንዛሬ ክምችት መሻሻሉን አንስተዋል።   በቀጣናው ዝቅተኛ የኃይል አቅርቦት ዋጋ ያላት፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ እና መንግሥት ለዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳራሻ እንዳደረጋትም አመላክተዋል። ሀገሪቱ ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ የምታደርገውን ጥረት በመጥቀስ፤ መንግሥት በታዳሽ ኃይል የሚመራ አረንጓዴ ልማትን ለማረጋገጥ ያለውን ጽኑ አቋም አድንቀዋል፡፡   ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት ትልቅ ትኩረት በመስጠት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲበረታቱ እያደረገች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢ ጥበቃና በታዳሽ ኃይል ልማት ግንባር ቀደም መሆኗን ጠቅሰው፤ ሌሎች ሀገራት ሊማሩበት የሚገባ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሚናውን እየተወጣ ነው
Mar 29, 2026 96
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዘአ)፡- የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን የተለያዩ አምራቾች ገለጹ፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል። በዚሁ ወቅት የጎበዝ የፀሐይ ኃይል ሶላር ሴል ማምረቻ ሥራ አስኪያጅ በረከት ኃይሉ፤ ምርታቸውን በዋናነት ለአሜሪካ ገበያ እንዲሁም ወደ ካናዳ፣ ቬትናም እና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል።   ድርጅቱ ለ300 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው፤ በመንግሥት እየተደረገ ያለው ድጋፍ የማምረት ዐቅማቸውን እንዳሳደገው ለኢዜአ ገልጸዋል። የዳቺ ማኑፋክቸሪንግ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ቢንያም ዮሐንስ በበኩላቸው ድርጅቱ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ወደ ምርት መግባቱን አውስተው፤ በአራት ፋብሪካዎች 46 ዓይነት የታሸጉ ምግቦችን እያመረተ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።   ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከመደገፍ ባለፈ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት ረገድ የበኩሉን አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። መንግሥት እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትልም የድርጅቱን የማምረት ዐቅም እንዳሳደገው አረጋግጠዋል። ድርጅታቸው የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችንና አልባሳትን እያመረተ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ የሀብቴ ጋርመንት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ሐይማኖት ሙሉጌታ ናቸው።   ከሀገር ውስጥ አቅርቦት ባለፈ፤ ምርቶቻቸውን ጋና፣ ላይቤሪያ እና ቡሩንዲን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ሀገራት እየላኩ መሆናቸውን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ 400 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፤ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሠራተኞችን ቁጥር በ50 በመቶ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። የካይት ማኑፋክቸሪንግ የግዢና ሽያጭ ኃላፊ አሸናፊ ፀጋ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ የተለያዩ የምርት ማሸጊያዎችን በማምረት ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እያቀረበ ነው ብለዋል።   እስካሁን ለ220 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል። መንግሥት የመሬትና የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ እያደረገ ያለው ድጋፍ ድርጅቱ የማምረት ዐቅሙን እንዲያሳድግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።
የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል
Mar 28, 2026 356
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተንዳሆ መስኖ ልማት የማጠናቀቂያ እና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ መርቀዋል።   የአፋር ሕዝብ በረሃውን በማለምለምና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመገንባት አለኝታነቱን ዳግም እያደሰ ይገኛል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለእኛ ሉዓላዊነት ማለት ዳር ድንበርን ከመጠበቅ ባሻገር፣ የዜጎችን አንገት የሚያስደፋውን የልመና እጅ ሰብሮ በራስ ምርት መቆም ነው ብለዋል። የአፋር ሕዝብ ለዘመናት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በንቃትና በጀግንነት ሲጠብቅ የኖረ የቁርጥ ቀን የሀገር ባለውለታ መሆኑንም አውስተዋል። ለምርቃት የበቃው የተንዳሆ መስኖ ልማት የማጠናቀቂያ እና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ትግላችን የድል ዓርማ ነው ብለዋል። ለዓመታት ተጓትቶ፣ ተስፋ አስቆርጦና የጎርፍ ሥጋት ሆኖ የቆየውን ግድብ፣ በቆራጥ አመራርና በፈጣን አፈጻጸም ወደ ልማት አውታር መቀየሩን ተናግረዋል። ይህ ፕሮጀክት ለምድራችን በረከት፣ ለሕዝባችን የብልጽግና ምንጭ እንዲሆን ዳግም ተወልዷል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እውነተኛ ነጻነትና ምሉዕ ክብር የሚረጋገጠው በራስ ማሳ ላይ በሚለማ ሰብል፣ በራስ ጉልበት በሚገራ ውኃና ከማንም እጅ በማይጠበቅ የዜጎች የዕለት ጉርስ መሆኑንም አመልክተዋል።   የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተነሣነውም የዜጋን ክብርና የሀገርን የህልውና መሠረት ለማጽናት ነው የዚህ ዋናዎቹ ዐቅሞቻችን ደግሞ ያልተነካው የበረሃ ለም አፈራችን፣ ውኃችን፣ ትጉህ ሕዝባችንና የመስኖ አውታሮቻችን ናቸው ብለዋል። ለእኛ መስኖ ማለት የዝናብ ጠባቂነትን ታሪክ መዝጋት ነው፤ መስኖ ተለዋዋጭ የሆነውን የዓለም ጂኦ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥረት የምንቋቋምበት ብቸኛውና አስተማማኙ መከታችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። የቆላማ አካባቢዎቻችንን እምቅ ሀብት ማልማትና የዜጎቻችንን ሕይወት በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ማሣለጥ የወደፊት ዕጣ ፈንታችንን የመወሰን ጉዳይ እንደሆነም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት። ቃልን በተግባር፣ ሐሳብን በውጤት እየለወጥን፣ አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩንና ባለ ሀብቱን ያስተሣሠረ የልማት ሠንሰለት በመፍጠር፣ ኢትዮጵያን በምግብ ራሷን የቻለች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የምትተርፍ የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለዋል።
የፌዴራል መንግሥት ተንዳሆን ከችግር አውጥቶ ወደ ልማት አውታር መልሶታል - ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ
Mar 28, 2026 305
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል መንግሥት ተንዳሆን ከችግርና ስጋት አውጥቶ የአፋርን ክልል ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የልማት አውታር መልሶታል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል የተንዳሆ መስኖ መሠረተ ልማት ማጠናቀቂያና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክትን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።   የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የተንዳሆ የመስኖ ፕሮጀክት ዱብቲ፣ የሠመራ ሎጊያ ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ ስድስት ወረዳዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የአፋር ሕዝብ በአዋሽ ወንዝ ጎርፍና በድርቅ በውሃ እጥረት ጉዳት ሲደርስበት መቆየቱን አንስተው፤ አሁን ግን ችግሩ እየተቀረፈ ነው ብለዋል። የተንዳሆ ግድብ ውሃ ሲሞላ የማስተንፈሻ ቦዩ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ የተስተካከለ ስላልነበር ማህበረሰቡ ላይ ትልቅ የጎርፍ ስጋት ሆኖ እንደነበር አስታውሰዋል። በመሆኑም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አፋርን ከጎርፍ አደጋ እየታደገና የውሃ አቅምን በመጠቀም የውሃ እጥረትን እየፈታ መሆኑን ተናግረዋል።   ለፌደራል መንግሥቱ ትልቅ አድናቆት አለኝ ያሉት ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ፤ በቢሊየን ሀብት አውጥቶ ተንዳሆን ወደዚህ ደረጃ ማድረሱ ቀላል አይደለም ነው ያሉት። በአፋር ክልል በርካታ የቆላማ ልማትና የመስኖ ግድቦች እየተገነቡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም የፌዴራል መንግሥቱን አመሥግነዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የዲጂታል ፋይናንስ የማጭበርበር ወንጀሎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመግታት ቅንጅታዊ አሰራሮች ይጠናከራሉ
Mar 28, 2026 134
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ የማጭበርበር ወንጀሎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመግታት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የፍትህ ሚኒስትር ሃና አርአያስላሴ ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እና የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበርን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።   "ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ስርዓት ለሀገር ዕድገት" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው አውደ ጥናት ላይ የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል። የፍትህ ሚኒስትር ሃና አርአያስላሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ተግባራዊ በተደረገው የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤቶች ተገኝተዋል።   ዲጂታል ስትራቴጂ 2025ን ጨምሮ በዲጂታል 2030 ለዲጂታል ፋይናንስ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸው ይህም ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የዲጂታል ፋይናንስ ደህንነትን ለማስጠበቅና ከማጭበርበር ወንጀሎች ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህንንም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራሮች እንደሚጠናከሩ አመልክተው፤ የፍትህ አካላት፣ የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን ጨምሮ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው ብለዋል።   የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፤ አውደ ጥናቱ የዲጂታል ፋይናንስ የማጭበርበር ወንጀለኞችን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ለማቀናጀት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል። በአውደ ጥናቱ የጥናት ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ የመፍትሔ ሃሳቦች ቀርበው በባለድርሻ አካላት ውይይት እንደሚደረግባቸውም ተናግረዋል። የህግ ክፍተቶችን መለየትና የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር ሌላው የአውደ ጥናቱ ዓላማ መሆኑንም አስረድተዋል።
የኮደርስ ስልጠና ዲጂታል የፈጠራ ስራዎችን ለማሳደግ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Mar 28, 2026 107
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ዲጂታል የስራ ፈጠራ እድሎችን እና የፈጠራ ስራዎችን በማስፋት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን እያሳደገ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአምስት ሚሊየን የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና በተለይም ወጣቶች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን የሚያሳድግ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ከራሳቸው አልፈው ለሀገራቸው የዲጂታል ልማት ስትራቴጂ ትግበራ አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ስልጠናው የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ የአኗኗር ዘይቤን የሚያሳልጡ ክህሎቶችን ለማጎልበት ያስችላል። በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች ያላቸውን ክህሎት በማሳደግ ወደ ፈጠራ ስራዎች እንዲሸጋገሩ እገዛ አድርጓል ብለዋል። ይህም የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ወደ እውቀት መር ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግር አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። በትምህርት፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች በዲጂታል ስርዓት እንዲታገዙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል።   በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የአይ ሲቲ ዳይሬክተር ናኦል አንበሴ በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ተማሪዎችና ሰራተኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ተጨማሪ ክህሎትን ለማጎልበት የሚረዳ በመሆኑ ዜጎች እድሉን በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።   የአይሲ ቲ ባለሙያዋ ጥሩ መልካም ስልጠናው በየትኛውም ሙያ የተሰማሩ ዜጎች ስራቸውን ለማሻሻል ያለውን ሚና ገልጻለች።   ተማሪ ባዩሽ ተስፋዬ እና ከደቡብ ሱዳን የትምህርት ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ የሆነው ላዱሊ ሞሪ ስልጠናው ከዲጂታል ዘመን ጋር አብሮ ለመራመድ ክህሎትን ለማሳደግ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኢኮኖሚው ምሶሶ እንዲሆን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምር የመደገፍ ተግባራቸውን ማጠናከር አለባቸው
Mar 27, 2026 429
ሮቤ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምር የመደገፍ ተግባራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ላይ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችና ግኝቶች ላሏቸው ወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን ተግባር ተኮር ሥልጠና በማጠናቀቅ የእውቅና መርሐ ግብር አካሄዷል።   በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምር የመደገፍ ተግባራቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል። ሚኒስቴሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የኢኮኖሚው ምሶሶ እንዲሆን በሀገር ደረጃ የተቀረጸውን ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አክለዋል። በተለይ ክህሎትና አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብና ግኝት ያላቸውን ወጣቶች በማወዳደር ፕሮጀክቶቻቸው በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና የፈጠራ ምህዳርን በማስፋትና በዘርፉ የዳበረ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ለውጦች መታየታቸውን አመልክተዋል። በተለይ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች በሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረታታ "ስታርት አፕ አክት" የተሰኘ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖረውና የፋይናንስ ድጋፍ በማግኘት ወደ ኢኮኖሚ እንዲቀየር እየተደረገ መሆኑን በማሳያነት አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ በማጠናከር ከወቅቱ ዓለም ዓቀፋዊ ሁኔታ ጋር የተናበበና በዘርፉ እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ያለመ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስቴሩ ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችና ግኝቶች ላሏቸው ወጣቶች ያዘጋጀው የእውቅና መድረክ የዚሁ ጥረት አካልና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።   የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ዩኒቨርሲቲው በባሌ፣ በምስራቅ ባሌና በምዕራብ አርሲ ዞኖች በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቴክኖሎጂ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመመልመል የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በዩኒቨርሲቲው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ሥልጠና ያገኙ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2017 ዓ.ም በተካሄደው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር አንደኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማትና እውቅና ማግኘታቸው የዘርፉ ትኩረት ውጤት መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብና ግኝት ያላቸው ግለሰቦች በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑና ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንዲረዱ የተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና የጥረቱ አካል መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አክለዋል። እውቅና ያገኙ የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ወጣቶች በበኩላቸው ያገኙት ተጨማሪ ዕውቀትና እውቅና የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣቶች የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ የኢትዮጵያን የወደፊት ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ በትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል
Mar 27, 2026 220
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወጣቶች የዓለምን ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት የሀገሪቷን የወደፊት ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ በትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የደረሰባቸውን አደጋ፣ የርዕዮተ ዓለምና የሀያላት አሰላለፍ ለውጥ፣ የቴክኖሎጂ ልህቀት በአፍሪካ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖና ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስትሩ በቆይታቸው የዓለም ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች ነባራዊ ሁኔታ ለታዳጊ ሀገራት ፈታኝ መሆኑን በማንሳት፤ አስቸኳይና ወሳኝ ርምጃ ይፈልጋል ብለዋል፡፡ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካውያን የህልውና ጥያቄ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ችግሩን ለመቋቋም ስልታዊ እሳቤና ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ፈተናዎችን ተጋፍጦ ለድል የሚበቃ ትውልድ ለመፍጠር ለሁኔታዎች የማይበገር የትምህርት ስርዓት መገንባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ብሎም አፍሪካውያን ማድረግ የምንችለው ትልቁ ነገር የቀጣዩን ትውልድ በትምህርት በሚገባ ማዘጋጀት ነው ብለዋል፡፡ አፍሪካ በትምህርት ራሷን ለማዘጋጀት የቀጣዩን 50 ዓመት ልትጠቀምበት ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፤ በትምህርት ስርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የዓለምን ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች ነባራዊ ሁኔታ ተቋቁሞ የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል ለመወሰን የተሟላ እውቀት፣ ብቁና ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መላመድ የሚችል ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ሪፎርም በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ መደበኛ ትምህርትን በማስፋፋት፣ የትምህርት መሰረተ ልማት በመገንባት፣ የሥርዓት ትምህርት ማሻሻያና ጥራት ማረጋገጫ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሄውም ቀጣዩን ትውልድ የማብቃት አካል መሆኑን ገልጸው፤ በራሱ የሚተማመን ሀገርን የሚጠብቅና አፍሪካ ወደፊት ሊደርስባት ከሚችል አደጋ የሚከላከል ዜጋ መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡ ትምህርት የትውልድ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት የሰጡት ሚኒስትሩ፤ ችግሩን ቀለል አድርጎ ማየት እንደማይገባ ገልጸዋል፡፡ ትምህርት ወጣቶች የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ አመዛዝነው እንዲረዱና የሌሎችን ከመኮረጅ ይልቅ በሀገር በቀል እሳቤ አዳዲስ ሀሳቦችን እንዲያመነጩ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡ ለዚህም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ በፖለቲካ፣ በፍልስፍናና በሌሎችም ዘርፎች ዓለም የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ተቋቁመው ማሻገር የሚችሉ ብቃት ያላቸው አመራሮችን ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ትምህርት ከአካዳሚክ እውቀት ባለፈ እሴቶችንና ማህበራዊ ንቃተ ህሊናን ማካተት እንዳለበት ገልጸው፤ ትምህርት ቀጣዩን ትውልድ ለማዘጋጀትና ለማስተማር ትምህርት የህልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የፖሊሲ አውጭዎች በወጣቶች ትምህርት ላይ መሰማራት የማህበራዊ ግብ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ስትራቴጂያዊ ጉዳይ መሆኑን መረዳት አለባቸው ብለዋል፡፡
ስፖርት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ
Mar 29, 2026 94
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ከመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቋል። በሻምፒዮናው ላይ 36 ክለቦች፣ ተቋማት፣ 9 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ 621 ወንድ፣ 436 ሴት በድምሩ 1057 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።   ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው። በውድድሩ ማብቂያ ቀን 10 የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል።   ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሻምፒዮናው አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን አጠናቋል። መቻል ሁለተኛ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው መጨረሳቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በሻምፒዮናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ለክለቦች እና አትሌቶች የተዘጋጁ የገንዘብ፣ የዋንጫና ሜዳሊያ ሽልማቶችን አበርክተዋል። ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ለማካሄድ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታውቋል።   ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን (Time Tronics) በሻምፒዮናው ላይ ተግባራዊ ሆኗል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።
ዋልያዎቹ ከሞሮኮ መልስ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን አድርገዋል
Mar 29, 2026 77
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ የመጀመሪያ ልምምዱን ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም ሰርቷል።   በአባቱ ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት ምክንያት በመጀመሪያው ጨዋታ ያልነበረው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጋቶቾ ፓኖም ስብስቡን ተቀላቅሎ ልምምድ አድርጓል። የዋልያዎቹ ተጋጣሚ የሆኑት ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድሬዳዋ መግባታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።   የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ሞሮኮ ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 አሸንፋለች።   በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ ወደ ምድብ ድልድል መግባቱን ያረጋግጣል።   36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።
በጅማ ዞን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ተግባር እየተከናወነ ነው
Mar 29, 2026 181
ጅማ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- በሥነ-ምግባርና በአካል የበቁ ወጣቶችን ለማፍራት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ተግባር በትኩረት እያከናወነ መሆኑን የጅማ ዞን አስታውቋል።   32ኛው መላው የጅማ ዞን ስፖርት ሻምፒዮና በጅማ ከተማ መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ሻምፒዮናው በእግር ኳስ፣ በማርሻል አርት እና በሌሎች 13 የስፖርት ዓይነቶች ለ15 ቀናት መካሄዱን ይቀጥላል።   የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ ዩሱፍ ሻሮ በዚሁ ወቅት፤ ዞኑ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በመገንባትና ውድድሮችን በማዘጋጀት በሀገርና በክልል ደረጃ ተወዳዳሪ ብሎም ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየሠራ ነው ብለዋል። የጅማ ዞን ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነጉማ መኮንን እንዳሉት፤ በስፖርት ሻምፒዮናው ከሁሉም የዞንና ወረዳዎች የተውጣጡ 1 ሺህ 800 ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።   በውድድሩ ዞኑን ወክለው በክልል ደረጃ የሚሰለፉ ስፖርተኞች እንደሚመረጡም ጠቁመዋል።   ስፖርታዊ ሁነቶችን የምናካሂደው ሰላማችንን አስጠብቀን ስንቀጥል በመሆኑ፤ ለሰላም እና ለሀገር አንድነት ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት ይገባል ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል የሥራና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ባይሳ ኩማ ናቸው።
ፌስቲቫሉ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበትና አብሮነት የሚደምቅበት ነው
Mar 29, 2026 82
ሐረር፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት፣ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕሴትና አብሮነት የሚደምቅበት ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል "የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ በሐረር ከተማ ተጀምሯል፡፡   ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በወቅቱ እንዳሉት፤ የኅብረ-ብሔራዊ አንድነትና አብሮነት መጠበቅና መረጋገጥ የባህል ስፖርቶችን አጉልቶ ለማሳየት ጠቃሚ ነው። የበለጠ እንዲጎለብትም መንግሥት ልዩ ትኩረት እንደሰጠው ተናግረዋል፡፡ የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ መክዩ መሀመድ በበኩላቸው፤ መንግሥት የባህል ስፖርትን ቀጣናዊ ትስስርን ለማምጣት፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር እየሠራበት ነው ብለዋል።   ኢትዮጵያ የ2026 የአፍሪካ የባህል ስፖርት ፌስቲቫልን የማስተናገድ ዕድል ማግኘቷንም አውስተዋል። ይህን ዕድል በመጠቀምም የባህል ስፖርቶቻችንን ለአፍሪካ እህት ወንድሞቻችን ለማስተዋወቅ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል። በሀገሪቱ ከ293 በላይ የተመዘገቡ ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች እንዳሉ በጥናት መለየቱን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጅ የጨዋታ ሕግና ሥርዓት ተዘርግቶላቸው ለውድድር የበቁት ከ11 የስፖርት ዓይነቶች እንደማይበልጡ ጠቁመው፤ በቀጣይ ይህን ለማስፋት እንደሚሠራ አመላክተዋል። የባህል ስፖርት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በዘላቂነት በማጠናከር ረገድ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት የገለፁት ደግሞ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሕይወት መሀመድ ናቸው፡፡ በሐረር ከተማ የተጀመረው የባህል ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ለ8 ቀናት እንደሚቆይና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፎ እንደሚያደርጉበት ተናግረዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ያስችላል
Mar 29, 2026 133
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ገንቢ ሚና እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ገለጹ፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ሕጎችና ደረጃዎች ዴስክ ኃላፊ ወንደሰን ታደሰ፤ ኢትዮጵያ የውኃ፣ የደን፣ የዓየር ንብረት አገልግሎት፣ የቁጥጥርና ቱሪዝም ሥርዓተ-ምኅዳር ብትታደልም በሚገባት ልክ አልተጠቀመችም ብለዋል።   የሥርዓተ-ምኅዳር ጉዳዮች በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ጉዳዮች በከፍተኛ ጫና ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።   የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ በአገልግሎቱ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች መካከል የጋራ መግባባትን በመፍጠር ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስችልም አስረድተዋል። የፋርም አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሸዊት አማኑኤል በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን የብዝኃ ሕይወት ሃብቶች ለሕብረተሰቡ ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የባሌ አካባቢ ማኅበረሰብ ተፈጥሮን በመንከባከብ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ተጠቃሚ መሆን መጀመሩን ገልጸው፤ ይህ በሁሉም አካባቢዎች መስፋት እንዳለበት አመላክተዋል። መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራና በአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገቡን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝኃ ሕይወት ሀብት ይበልጥ መለየትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡   በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ሀብትና ሀይድሮሎጂ መምህር ዓለምአየሁ አባተ (ዶ/ር)፤ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ማኅበረሰቡ የሠራበትን እንዲያገኝ በማድረግ የተጠናከረ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡ በባሌ ኢኮሎጂ በ20 ወረዳዎች በመሰማራት እየሠሩ መሆኑን የገለጹት የፋርም አፍሪካ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ፈይሳ አሰፋ፤ በኢትዮጵያ የካርበን ክፍያ መጀመሩ የሕብረተሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ተነሳሽነት ያሳድጋል ብለዋል፡፡ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጁ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የብዝኃ ሕይወት ሀብት ጠብቃ እንድትቆይና ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል ሲሉም አስገንዝበዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ ነው
Mar 28, 2026 104
አምቦ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በጽህፈት ቤት የደን ልማት ባለሙያ ጉደታ ጡሪ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እየተዘጋጁ ከሚገኙ ችግኞች መካከል ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። በክረምቱ ወራት አጠቃላይ ከ94 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የችግኝ ተከላ እንደሚከናወን ገልጸው፤ የችግኝ ማፍላት ስራው በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ዝግጅቱ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል ምርታማነታቸው ከፍተኛ በሆኑና በተሻሻሉ የችግኝ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ማድረጉንም ጠቅሰዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፤ ችግኞችን የመንከባከብና የመጠበቅ ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል። የተተከሉ ችግኞች የአካባቢ ስነ-ምህዳርን ከመቀየር አንጻር ከፍተኛ ሚና ከመጫወታቸው ባለፈ፣ ደርቀው የነበሩ ኩሬዎች ዳግም ውሃ እንዲይዙ በማድረግ ለአርሶ አደሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ነው ያሉት። ባለፉት ሰባት ዓመታት በድምሩ 616 ሺህ 613 ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰው፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን ደን የመጠበቅ ባህላዊ እሴት ለአረንጓዴ ልማት ስራው ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
ለቀጣዩ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የችግኝ ዝግጅት እየተከናወነ ነው    
Mar 27, 2026 97
ሆሳዕና፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ ሻራ መርሐ-ግብር የችግኝ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ አስታውቋል።   የቢሮው ኃላፊ አብርሃም መጫ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ባለፉት 7 ዓመታት በክልሉ 450 ሺህ ሔክታር በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ማልማት ተችሏል።   በዚህም የአፈር ለምነትን በማስጠበቅ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አብራርተዋል። በዚህ ዓመትም 270 ሚሊየን የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል 80 ሺህ ሔክታር መሬትን ለማልማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራን ነው ብለዋል። ሥነ-ምኅዳርን መሠረት ያደረጉ ለምግብነትና ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውሉ ችግኞችን የማፍላትና የማዘጋጀቱ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው ያረጋገጡት።
የበልግ ዝናብ ስርጭት ለግብርና ምርታማነትና ለእንስሳት መኖ አቅርቦት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው-የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Mar 26, 2026 219
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018(ኢዜአ)፦የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ስርጭት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚከናወኑ የግብርና ስራዎች ስኬታማነትና ለእንስሳት መኖ አቅርቦት መሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ተቋሙ የአየር ጸባይ አዝማሚያዎችን፣አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን በወቅቱ ለማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው ተቋማት የማድረስ ስራውን በልዩ ትኩረት እየከወነ ይገኛል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ባለው የበልግ ወቅትም፣ በተለይም በሀገሪቱ ደቡባዊ አጋማሽ የዓመታዊ ዝናብ መጠኑ እስከ 55 በመቶ የሚሸፈንበት ዋነኛ ወቅት ነው ብለዋል። በ2018 ዓ.ም የበልግ ወቅት አብዛኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም በ55 የሚደርሱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ35 እስከ 148 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መመዝገቡን ገልጸዋል። ባለፉት ቀናት የታየው ተስፋ ሰጪ የዝናብ ስርጭት ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ጠቅሰው፥ ለበልግ እርሻ ዝግጅትና ለዘር ስራ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለሰውና ለእንስሳት የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማሻሻሉን እንዲሁም የእንስሳት መኖ ልማትን በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ ድርሻ መኖሩ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። በመጪዎቹ ሚያዝያና ግንቦት ወራትም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የበልግ ዝናብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በተለይም በደቡብና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ዝናቡ ዘግይቶ የሚወጣ በመሆኑ ለግብርናውና ለአካባቢ ጥበቃ ስራው ተጨማሪ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል። ይሁን እንጂ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ወደ ጎርፍ አደጋ ሊቀየር ስለሚችል ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 397
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት።   ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው 
Mar 22, 2026 159
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 280
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።   በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3334
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ 
Mar 2, 2026 371
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል።   የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል።   የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 428
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።      
   የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 400
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን።   የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው።   የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።   የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።   የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት
Mar 28, 2026 249
ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ‎የ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን እና የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ሎጁ የዛሬ 50 እና 60 ዓመት መሠራት የነበረበት ቢሆንም፤ አሁን ስለዘገየን አንቆጭም ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ስለሠራንም አንረካም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሩጫችን ገና ብዙ እንደሆነ፣ አፋር ገና እንዳልተነካ አስበን ይህን ጅማሮ ይበልጥ በማላቅ ለማስቀጠል እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቃና ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነም ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸውን ፋይዳም አንስተዋል። • ኢትዮጵያ በማላቦው ጉባዔ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ማላቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉባዔው ከመጋቢት 18 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። • የልማት ሥራዎች ጉብኝት በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎሉና ግንባታቸው እየተፋጠኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት እና የአየር መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ሲሉም በወቅቱ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት የሀገር ሀብት ፈስሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የመገጭ ግድብ ምስክር መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይህ ሞዴል መንደር በአካባቢው ለረጅም ዓመታት የቆየውን የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ጥያቄ በተግባር መልሷል ብለዋል። በሀገራችን ከተማው ብቻ ሳይሆን ገጠሩም እኩል እየተዋበ፣ በልማት እየተገነባና በዕድገት ፍኖት ላይ በጽኑ መሠረት እየተራመደ ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ትልቁ ማሳያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። • "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ በአዲስ አበባ 4ኛው "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይሆን አጋርነትን ነው፤ እርዳታን ሳይሆን ኢንቨስትመንትን ነው! ለባለ ሀብቶች ምቹ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ለችሎታ እና ለዕድል በሯን ወለል አድርጋ መክፈቷንም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን በፍጥነት ወደ ከፍታ እየገሠገሠች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ የዕድገት ጉዞ፤ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያ ለእናንተ ዝግጁ የሆነ፣ በዕድሎችና በስኬቶች የተሞላ ታላቅ የኢንቨስትመንት መሶብ አላት፤ ኑ አብረን እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል! • የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫም፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። በዚህም ከክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀሌ እና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ ሂደቱን በክልሉ ለማካሄድ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው፤ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም አስረድተዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 131
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 754
ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል የነዳጅ ብክነትን ለመቀነስ ምን ዓይነት ብልኀት መጠቀም ይመከራል? ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 21, 2026 230
በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ (በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት ስትወጥን የቀደመ ወረቷን፤ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን ይዛ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን ቀረጸች። ይህን ዕውን ለማድረግ ስትዘይድም የሕዝቧን የፋይናንስ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ዐቅም በመደመር መጠቀምን ሻተች። በዚህም መሠረት በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዘገበች። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኢዜአ ዐይን …! ✍️ ገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻዎችና መናፈሻዎችን ለማልማት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ገበታ ለሸገር ኢኒሼቲቭ፤ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን የሚሸፍን ነው። የሚሠራበትን ገንዘብ ለማሰባሰብም የገበታ ለሸገር የእራት ምሽት በዳግማዊ አጼ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ተዘጋጀ፤ ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። ኢኒሼቲቩ አንድነት ፓርክን ጨምሮ የእንጦጦ መናፈሻንና ሌሎች የተለያዩ መዲናዋን ያስዋቡ በረከቶችን ችሯል። ይህም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት በርካታ ቱሪስቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ለምጣኔ ሃብት ዕድገት ጉልኅ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ለዚህ ሁሉ ስኬት መነሻ የሆኑትን ጉዳዮች ያስጀመሩትም ያስፈጸሙትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሸገር የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ገበታ ለሀገር የተሰኘውን ኢኒሼቲቭ አበሠሩ። ✍️ ገበታ ለሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻን ለማልማት ያለመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። ይህም በአዲስ አበባ ከተሠራው ገበታ ለሸገር ቀጥሎ የተከናወነ ነው። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የገበታ ለሀገር ዓላማ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ የቱሪስት መስኅብ የሚሆኑና የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መሆኑን አስገንዝበዋል። በገበታ ለሀገር መርሐ-ግብር ባለሀብቶችን ጨምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት የሀገሪቱን ባለሃብቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ መርሐ-ግብሮች የተሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ውጤታማ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበታ ለሀገር ውጥን፤ እንደ ሀላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጉልተው በማሳየት ይበል ያሰኘ ውጤት አስመዝግቧል። ✍️ ገበታ ለትውልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም ገበታ ለትውልድ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ይህም ተጨማሪ መዳረሻዎች እንዲለሙ አስችሏል። በዚህ ኢኒሼቲቭ ሥር በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የመዳረሻ ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ አካባቢና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎች እየለሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የሸበሌ ሪዞርት በይፋ መርቀዋል። እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት እንደሆነም ተገልጿል። ሎጎ ሐይቅ ሪዞርትም ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረቀ ሲሆን፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኖ ቀርቧል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክርም ነው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት። የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነትና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ዕሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ሆኖ ያገለግላል። ታሪካዊ ቦታዎችና የሀገር መገለጫ መሠረተ-ልማቶች ብሔራዊ ትርክቶችንም የሚገነቡ ናቸው። በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት ብሎም በየአካባቢው የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት፣ ብዙ ጎብኚዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። እንዲሁም ነባር ቅርሶችን በማደስና በመጠገን ለትውልድ ለማሻገር ደማቅ ዐሻራ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት የመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ ዐሳይተዋል። ባለሀብቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም ሀገራቸውን የመሥራት ሚና እንደሚጠበቅባቸው አሥተምረዋል። ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ብሎም በርካታ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር በኢኮኖሚው ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግሥት ላስጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ነው። ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎችም አንዱ የሆነው ለዚህ ነው። መሠረተ-ልማቶች ከሚገነቡባቸው ጡቦች ባለፈ የነገን ሀገራዊ ማንነት፣ ራዕይ እና መዳረሻን ይበይናሉ። ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ እንኳንም ታሰቡ፤ እንኳንም ተሳኩ። ይህ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መዳረሻ ባላገኘች ነበር።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 3760
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2532
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8322
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6811
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60705
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54666
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35202
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32801
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 27867
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 27030
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26547
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26184
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60705
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54666
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35202
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32801
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በኢዜአ ዐይን …!  
Mar 29, 2026 2050
በዮሐንስ ደርበው የሥልጣኔ ቁንጮ -በምርጫ ካርድ መሪን መምረጥ! በያዝነው ዓመት ወርኃ ግንቦት በባተ 24ኛው ቀን ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ቀን ቆርጣለች። ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ወደ ትግበራ ምዕራፍ ገብታለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን፤ ቀሪ ሥራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን ገልጿል። ለዚህም የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ መግባታቸው በአሥረጂነት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ መሰጠቱ፤የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች በኦንላይን ሥርዓት በታዛቢነት መመዝገባቸውን አስረድቷል። በኢዜአ ዐይን …! በገበታ ለሀገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የጤና ነገር … እንዲሁም ዐለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት መጥተው ፈቃድ የሚወስዱበት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሠለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች አሠማርቷል። ለመራጮች ምዝገባ የተዘጋጁ 46 ሺህ 757 ጣቢያዎች እና ተጨማሪ በርካታ ንዑስ ጣቢያዎችም ተሠናድተዋል። እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ፤ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮው ምርጫ ለውድድር ተመዝግበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ 73 ዕጩዎች በግል ለውድድር መቅረባቸው ተገልጿል። ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ የሚከናወነው ሁሉም ፓርቲ ሕግን አክብሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደሆነ ያስማማል። የምርጫው ስኬት የሚረጋገጠውም ቦርዱ ለብቻው በሚያደርገው ጥረት ሳይሆን፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዕኩል ኃላፊነቱን መወጣት ሲችል መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰባት ምዕራፎችና በ30 አንቀጾች የቀረበውን የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ፈርመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሂደት የዜጎችን ተሳትፎ ለማበረታታት “ምርጫችን ነው-ሀገር ያለኛ” የተሰኘ የምርጫ ኅብረ-ዝማሬ ማስመረቁ ይታወቃል። በዚሁ ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ኅብረ-ዝማሬው አካታች ተሣትፎን ለማበረታታት መሠናዳቱን አስገንዝበዋል። የልዩ ልዩ ድምጾች ኅብራዊነት ያለውን የጋራ ጥንካሬ በማሳየት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዜጎችን ተሳትፎ ማጎልበት የኅብረ-ዝማሬው ዓላማ መሆኑም ተገልጿል። በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫም “የሀገር ካስማ” የተሰኘ ኅብረ-ዝማሬ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ምዝገባው እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይቀጥላል። የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ የሚገኘውም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ ነው። ከአጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ያህሉ የዲጂታል የመራጮች ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ቦርዱ ማሳወቁ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ በተከናወነ የመራጮች ምዝገባ ከ28 ሚሊየን 365 ሺህ 310 በላይ መራጮች ተመዝግበዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 37(7) ላይ ቦርዱ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክቶችን አቀማመጥ፣ ቅደም ተከተልና እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ግልጽ በሆነ መንገድ በመመሪያ እንደሚወስን ይደነግጋል። በዚህም መሠረት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ባሳለፍነው መጋቢት 14 ቀን በይፋ አስጀምሯል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት የሚከናወነው በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክት አቀማመጥን የሚወሥነው የዕጣ ማውጣት ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የዓየር ሠዓት ድልድል የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል። በዚህም መሠረት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የዓየር ሠዓት ተድልድሎላቸዋል። የሠዓት ድልድሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና ፖሊሲዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ የግል ዕጩዎችም አማራጭ ሐሳባቻቸውን እንዲያጋሩና የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ብሎም ከመራጩ ጋር እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ ነው። ይፋ በተደረገው ነፃ የዓየር ሠዓት የተመዘገቡ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች በኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ ይጠበቃል። በአጠቃላይ በምርጫ ካርድ መሪን መምረጥ ከሥልጣኔ ቁንጮዎች አንዱ ሆኖ ይነሳል። የመራጮች ምዝገባ ሂደትም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራርን እንዲያጠናክሩ ብሎም በካርዳቸው ይሁንታ የሚመራቸውን መምረጫ ቁልፍ ነው። ኢትዮጵያ በወሳኝ የምርጫ ወቅት ላይ ናትና፤ ለስኬታማነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #የመራጮች_ምዝገባ #በኢዜአ_ዐይን
ተከፍሎ የማያልቅ የኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ውለታ አለብን - የመናዊያን ፍልሰተኞች
Mar 19, 2026 2384
በዮሐንስ ደርበው ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለተገፉ፣ ጥላ ከለላ ለሚሹ፣ ለተከዙና ለታረዙ የሀገራት ዜጎች መጠጊያ ናት። የኢትዮጵያን ቸርነትም ከተጠለሉባት እንግዶቿ በላይ ምሥክር የለም። የኢትዮጵያን ደጅ የረገጡ ሁሉ በቆይታቸው ለተደረገላቸው ሁሉ ‘ውለታችንን በምን እንክፈል’ ሲሉ ይደመጣሉ። ከአያሌ ሀገራት በመልከ ብዙ ቀውሶች ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ የቆሰሉ ልባቸው ታክሞ፣ ዕንባቸው ታብሶና ሕይወታቸው ታድሶ ኑራቸውን አደላድለዋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በዚህም ከአፍሪካም ሆነ ከተቀረው ክፍላተ ዓለም የጦርነትና ግጭት ጥላ ያጠላባቸውና ሰላምን የተጠሙ የቀጣናው ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ሲሹ ማየት የተለመደ ነው። የየመን ዜጎች ለዚህ ማሳያ ናቸው። ኢብቲሳም ኻሊድ እና መሰል የመናዊያን ከየመን የእርስ በርስ ግጭት በኋላ የኢትዮጵያን ደጅ ረግጠው ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፍ የተድላ ኑሮ እየኖሩ ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረገችው ኢብቲሳም እንደምትለው፤ በየመን አለመረጋጋት በፈጠረው ጠባሳ እርሷና መሰሎቿ ለፍልሰት ተዳርገዋል። ለዚህ ደግሞ ምርጫቸው ኢትዮጵያ ሆነች። ወደ ኢትዮጵያም መጥተው የሀገሬው ፊት ሳይኮሰኩሳቸው በፍቅር እንደተቀበሏቸው ትናገራለች። በዚህም ዛሬ የመናዊያን ተስፋቸው ለምልሞ፣ ሕይወታቸው ሠምሮ ኢትዮጵያን እንደ እናት ቆጥረው እየኖሩ ስለመሆኑ ትናገራለች። ከ11 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ኢብቲሳም፤ በወቅቱ ቀኑ እንደጨለመባት ታወሳለች። ሰው ከቤቱ፣ ከወገኑ…ከሀገሩ ወጥቶ ወዴት ይሄዳል? በወቅቱ የነበረውን ጭንቀት ማየልም ታስታውሳለች። አሁን ግን ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ በጎነት ዐውርታ አትጠግብም። “አሁን ፍልሰተኛ አይደለሁም፤ ያለሁት በሁለተኛዋ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነውና” ትላለች። እንዲህ ባለው የረመዳን ወቅት ደግሞ የፍልሰተኞች ሁሉ ሰብሳቢ ናት። “ሁሉም ከእነ ቤተሰቡ ወደ ቤቷ እየመጣ ያፈጥራል። በዚህም በፍልሰት እንደመጡ ሳይሆን ቤተሰባዊነት ይሰማቸዋል። ከየመን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮንጎሊዝ (DRC) ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ ሰብሰብ ብለው የኢፍጣር መርሐ-ግብርን እንደሚያከናውኑም ታነሳለች። በዚህ ላይ ኢትዮጵያውያን ብርታት ናቸው ትላለች፤ ሁሌም ‘አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ነገ ጥሩ ይሆናል’ እያሉ ያበረቱናል፤ ክብርና ፍቅር ይሰጡናል ስትልም ታስረዳለች። የኢትዮጵያንና ሕዝቧን ውለታ እንዴት መክፈል ይቻላል? ኢትዮጵያን ሀገራችን ብለን ነው እየጠራን ያለነው። እንደ እንግዳ እንደ ፍልሰተኛ እራሳችንን አናስብም፤ እንደሀገሬው አንዱ እንጅ፤ የምትለው ኢብቲሳም፤ ኢትዮጵያን እንዴት ብዬ ነው የምገልጻት? እናትን መግለጽ ይቻላል? እናትን መግለጽ ከተቻለ ኢትዮጵያን በዚያ ልክ መግለጽ ይቻል ይሆናል፤ እኔ ግን አይቻለኝም በማለት ትናገራለች። “የዛሬ 11 ዓመት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት፤ የሰው ፊት አልገረፈኝም፤ ፊቱን ያዞረብኝም የለም። ኢትዮጵያውያን ደግ፣ ቅንና ደስ የምትሉ ሕዝቦች ናችሁ” ስትል ስሜቷን ትገልጻለች። ኢትዮጵያ እንደ ኒውዮርክ እያደገች ነው፤ እኛ ከመጣን በኋላ እንኳን በርካታ ለውጦች ዕያየን ነው ስትልም የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት አንስታለች። ለአብነትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በርካታ ነገሮች መስተካከላቸውን በመጠቆም፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግሥት እናመሠግናለን ብላለች። ከፍልሰተኞች ጋር በተያያዘ በርካታ ሕጎች በመሻሻላቸው፤ ዛሬ በራሴ ስም ንግድ ፈቃድ አውጥቼ እየሠራሁ ነው፤ በጨረታዎችም እወዳደራለሁ፤ የበጎ አድራጎት ማኅበር መመሥረትና መምራት ችያለሁ። እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣቸው ለውጦች ናቸው ብላለች። በምድረ ኢትዮጵያ ያለን ሁሉ ለኢትዮጵያ ዕድገት እንተባበር ስትልም ጥሪ አቅርባለች። ህልማችን ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆነን ኢትዮጵያን በማሳደግ ጥረት በንቃት መሳተፍ ነው፤ የኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ውለታ መመለስ አለብን ስትልም ትናገራለች። በኢብቲሳም ኻሊድ ቤት በተዘጋጀ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ የተሳተፈው አነስ አንዋር ለኢዜአ እንዳለው፤ ኢትዮጵያ በሯን ከፍታ አስጠልላዋለች። ከተለያዩ ሀገራት ብንመጣም ሰብሰብ ብለን ስናፈጥር፤ ማኅበራዊና ቤተሰባዊነታችን ይጠናክራል ብሏል። ብዙ ፈተናዎችን ዐይተናል፤ አልፈናቸው እዚህ ደርሰናል የሚለው አነስ፤ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት ነው” ሕዝቡ በክብር ነው የተቀበለን፤ ከምሥጋና ውጭ ምን ማለት እንችላለን? አመሥጋኞች ነን ሲል ገልጿል። እየተማርኩ ነው፤ ትምህርቴን አጠናቅቄ በሙያዬ በመሠማራት ኢትዮጵያን ማገዝ እፈልጋለሁ ብሏል። ራኪያ አሊ አብዱረዛቅ በበኩሏ በፈረንጆቹ 2011 ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷን ታወሳለች። ትምህርቷንም ተከታትላ መመረቋን ገልጻ፤ ቤተሰብ አፍርታ ሁለት ልጆችንም ወልዳ እየኖረች ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገሬ ናት፤ ሰላም አላት፤ ሕዝቡም ሰው አክባሪ ነው። ለኢትዮጵያ የተሻለ ልማት ደግሞ መተባበር ወሳኝ ስለሆነ ለዚሁ እንትጋ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች። #ፍልሰተኞች #ኢዜአ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም