ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት ተከናውነዋል

ጅግጅጋ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  ሙስጠፌ መሀመድ አስታወቁ።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።


 

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ  መሀመድ  የክልሉ መንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ  በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ።

በተለይም በሰላምና በልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ።

በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በድህነት ቅንሳ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የሚመጡ አደጋዎች ቅነሳ ከፍተኛ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

በክልሉ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው የፍትህ አካላትን አቅም ለመገንባት በተደረገ ጥረት  የፍትህ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን አስችሏል ሲሉ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም