የሲሸልስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና ዳያስፖራ ሚኒስትር ባሪ ፎር በ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሲሸልስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና ዳያስፖራ ሚኒስትር ባሪ ፎር በ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018(ኢዜአ)፦ የሲሸልስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና ዳያስፖራ ሚኒስትር ባሪ ፎር በ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፋ የተለያዩ የሕብረቱ አባል ሀገራት የልዑካን ቡድን አባላት ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።
የሲሸልስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና ዳያስፖራ ሚኒስትር ባሪ ፎር በ49ኛው የሕብረቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል መላኩ በዳዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ "የአፍሪካ አጀንዳ 2063ትን ለማሳካት ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓት ማንበር" በሚል መሪ ሀሳብ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት ዋና መስሪያ ቤት ይካሄዳል።
ነገ በሚካሄደው የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የሕብረቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ሊቀ መንበርና የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት በአፍሪካ ሕብረት የ2026 የዓመቱ መሪ ሀሳብ ትግበራና አፈፃፀምን በተመለከተ በቀረበው ሪፖርት ላይ በጥልቀት ይመክራል።
የአፍሪካ ሕብረት ስምምነቶች በቅልጥፍና በሚጸድቁበትና ገቢራዊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በአጀንዳ 2063 ትግበራ ዙሪያ በቀረበው የኮሚቴው ሪፖርት ላይ ይወያያል።