ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል
Oct 5, 2026 14
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ ለተደጋጋሚ ጊዜያት የኢትዮጵያን ለውጦች የሚገፋቸው ቁጭት እንደነበር አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓትን የመገንባት ሙከራዎች የቁጭት ችግር ባይኖርባቸውም የእፎይታና የስክነት ችግር ይስተዋልባቸው እንደነበር አስረድተዋል። የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለኢትዮጵያ የሚሆነውን አዋጭ መንገድ መርጦ፣ ፈትኖና አረጋግጦ ኢትዮጵያዊ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል አቅም እንደነበርም ገልጸዋል። በዚህም የየወቅቱ መሪዎች ከሚያዋጣው መንገድ ይልቅ አቋራጩን ሲመርጡ በመኖራቸው የኢትዮጵያን ችግር ለሌሎች ተቀድቶ በተሰፋ የውጭ ሀገር እሳቤ ለመፍታት ሲሞክሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ምንጩን የሚረሳ ወንዝ ይደርቃል እንዲሉ መሰረቱን፣ ባህሉን፣ ልማዱን፣ ሀገራዊ እሳቤውን በማሽቀንጠር የሚጀምር የሥልጣኔ ጉዞም ሩቅ ሊጓዝ አይችልም ሲሉም ነው ያስገነዘቡት። ለዚህም ባለፉት ስምንት ዓመታት በሥልጣኔ ጉዟችን ለሚገጥሙን ፈተናዎችና እንቅፋቶች መሻገሪያ የሚሆን የጥበብ ወረት እንዳለን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል። ኢትዮጵያዊ እሳቤ እንደነበረን አረጋግጠናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ይህም የመደመር እሳቤ ነው ብለዋል። የአውሮፓ ሥልጣኔ የተገነባው በአውሮፓዊ ባህል፣ የኤስያ ሥልጣኔም በኤስያዊ ባህል በተስማማው በኮንፊሺየስ እሳቤ ላይ ተመስርቶ መሆኑን አስገንዝበዋል። ባለፉት ዓመታት የሌሎችን ተሞክሮ ከራሳችን ጋር ስናስማማ ቆይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል ብለዋል። የምንኮራባቸው ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ በመደመር እሳቤ የተቀኙ እንደነበሩ በመገንዘብ በለውጡ ጊዜ የተሞከሩ ተግባራት አስደናቂ ውጤት ማምጣት እንደቻሉም አብራርተዋል። ከፋፋይና ጠባብ እሳቤዎችን በሕብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲተኩ የተደረገው የሀገር በቀል እሳቤ ሙከራ ፍሬ እያፈራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Oct 5, 2026 19
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ስኬት እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በቀጣናውና በሕዝቦች መካከል ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ ብልጽግና እንዲሰፍን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ፈጣን የጂኦፖለቲካ ለውጦችን በመገንዘብ ከቀድሞ ልምዶቿ በመማር በቂ ዝግጅት ማድረግ አለባት
Oct 5, 2026 24
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በአካባቢዋና በዓለም የሚታዩ ፈጣን የጂኦፖለቲካ ለውጦችን በመገንዘብ ከቀድሞ ልምዶቿ በመማር በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተከናውኗል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የምትገኝበት ምስራቅ አፍሪካና የቀይ ባህር ቀጣና ከፍተኛ የጂኦፖለቲካ ለውጥ እያስተናገደ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ከፈተና ባሻገር እድልም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። የቀይ ባህርና የህንድ ውቅያኖስ መገናኛ፣ የባብ ኤል መንደብ የባህር መስመር እና የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ቀጣናውን የዓለም አቀፍ የሀያላን ፉክክር ማዕከል እያደረገው መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ሳያሳድር ሊያልፍ እንደማይችል ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሀያላን ፉክክር የቀጣናውን የፖለቲካ ሁኔታ መቀየሩንም ተናግረዋል፡፡ አቅም በነበረን ወቅት የራሳችንን ጉዳይ ራሳችን ወስነናል፤ በተዳከምን ጊዜ ግን ሌሎች በእኛ ላይ ወስነውብናል ብለዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአሁኑ የዓለም ሥርዓት ለውጥ ወቅት ፈጥና መንቃት፣ የራሷን አቅም መገንባትና የሀገራዊ ጉዳዮቿን በራሷ አቅም ለመወሰን መዘጋጀት እንደሚገባት አስገንዝበዋል። በማዕበል የምትናጥ ዓለም ውስጥ እስከምን ለመጓዝ ተዘጋጅተናል? ሲሉ ያነሱት ጥያቄ፣ ከሚመጡ ፈተናዎች ጋር በጥንካሬ ለመጋፈጥ የሀገሪቱ ዝግጁነት ወሳኝ መሆኑን ያመላክታል።
በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው
Oct 5, 2026 24
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ በመፈጸም ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፤ ካለፉት የታሪክ ተሞክሮዎች በመማር የዓለምን ፈጣን ለውጥ ቀድሞ መረዳትና ለሚመጣው ዘመን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀት ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ዓለም በተከታታይ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን በማካሄድ የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ አቅሟን ስታሳድግ፣ ለእነዚህ ለውጦች ራሳቸውን ያዘጋጁ ሀገራት የአብዮቶቹ ተዋናዮች መሆን መቻላቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች ከእነዚህ ለውጦች በበቂ ሁኔታ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን ጠቅሰው፣ በተለይ በጦርነትና በውስጣዊ ግጭት የተነሳ ከዓለም የለውጥ ጉዞ ጋር በተመጣጣኝ ሁኔታ መጓዝ እንዳልቻለች አስታውሰዋል። ቀድሞ አለመዘጋጀት እንደሀገር የሚያስከፍለውን ዋጋ ለማሳየትም የጣሊያን ዳግም ወረራን በምሳሌነት አንስተዋል። በዓድዋ ጦርነት የተሸነፈው የጣሊያን ሀይል አራት አስርት ዓመታት ያህል የሚቆይ ዝግጅት ካደረገ በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በአንጻሩ ከዓድዋ ድል በኋላ በበቂ ሁኔታ ሳትዘጋጅ መቆየቷ በማይጨው ጦርነት ከተለወጠው የጦር ቴክኖሎጂ ጋር እንድትጋጠም መገደዷን ገልጸዋል። በወቅቱ ወራሪው ሀይል 450 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ይዞ ሲመጣ፣ ኢትዮጵያ ከ12 በማይበልጡ ወታደራዊ ያልሆኑ አነስተኛ አውሮፕላኖች ለመጋፈጥ መገደዷንም ነው ያነሱት። በመሆኑም ካለፉት የታሪክ ተሞክሮዎች በመማር የዓለምን ፈጣን ለውጥ ቀድሞ መረዳትና ለሚመጣው ዘመን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ገልጸዋል። አንድ እንቅፋት አንዴ መመታት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ደጋግሞ መመታት ግን የጤና እንዳልሆነ በመጥቀስም ያለፈውን በመረዳት የተሻለ ዝግጅት ማድረግ የሀገሪቱን ቀጣይ ጉዞ ለማሳካት ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ዛሬ የት ላይ እንዳለች በመገምገም የሚመጡ ለውጦችን ቀድማ በመጠበቅና በመዘጋጀት በዓለም የለውጥ ጉዞ ውስጥ ተዋናይ ሆና መቀጠል እንዳለባትም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያውያን ሀገር አጽንተው ለትውልድ ማስተላለፍ የቻሉት በመደመር እሳቤ ነው 
Oct 5, 2026 27
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በመቋቋም ሀገር አጽንተው ለትውልድ ማስተላለፍ የቻሉት በመደመር እሳቤ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ የ2010 ዓ.ም ለውጥን ያመጣው በአዲስ ትውልድ ውስጥ ያለው ዓለምን አሸንፎ የመጓዝ ፍላጎት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ለውጦች የሚገፋቸው ሀገር ወደኋላ ስትቀርና ዓለም ወደፊት ሲራመድ የሚፈጠር ቁጭት እንደነበር ጠቁመው፤ ከባዱ ነገር ይህንን ቁጭት በተገቢው ስርዓት የማስተናገድ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል። ቁጭት መነሻ እንጂ መድረሻም ሆነ ማድረሻ እንደማይሆን ገልጸው፤ ማድረሻው ሥርዓት ሲሆን መዳረሻው ደግሞ ስልጣኔ መሆኑን ተናግረዋል። ቁጭት ስርዓትን እንዲወልድ ሰክኖ ማሰብ፣ ማሰላሰል፣ መመርመር፣ መሞከር፣ የተሻለውን መምረጥና ማሻሻል አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሥርዓት በአንድ ጀምበር ተገንብቶ እንደማያልቅና ይልቁንም በሂደት የሚፈጠር፣ ትዕግስት እና ትጋትን እኩል የሚጠይቅ፣ ጥበብ እና ስክነትንም አጣምሮ የያዘ እንደሆነም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ስርዓትን የመገንባት ሙከራዎች የቁጭት ችግር እንዳልነበረባቸው ገልፀው፤ በአንጻሩ ግን በአንድ በኩል የእፎይታ እና የስክነት ችግር እንደሚስተዋልባቸው ጠቁመዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ለአዲስ ሀሳብ ዝግ የመሆን ጠባይ በሰፊው እንደሚታይም በንግግራቸው አንስተዋል። ነባራዊውን ዓለም ተገንዝቦ ለኢትዮጵያ የሚሆነውን አዋጭ መንገድ መርጦ፣ ያንን መንገድ ፈትኖ እና አረጋግጦ ኢትዮጵያዊ ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል ዝግጁነት እንደሚያንስም ጨምረው አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የየወቅቱ መሪዎች ከሚያወጣው መንገድ ይልቅ አቋራጩን ሲመርጡ መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የሀገራችንን ችግር በውጭ ሀገር እሳቤ ለመፍታት ሲጣደፉ መቆየታቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያን ከዚህ አዙሪት ለማውጣት ብዙ ጥረቶች መደረጋቸውን ጠቁመው፤ በስልጣኔ ጉዟችን ውስጥ ለሚገጥሙን እንቅፋቶች መሻገሪያ የሚሆን የጥበብ ወረት መኖሩን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። ፈተናዎች ያልበገሩት፣ ችግሮች ያልበጠሱት፣ ርዕዮተ ዓለሞች ያልቀየሩት፣ የውጭ ወራሪዎች ያልሰበሩት ኢትዮጵያዊነት ሊገኝ የቻለው ኢትዮጵያውያን በመደመር መንገድ ስለሚጓዙ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ይህም ብዝሃነትን ከአንድነት፣ የእምነት ልዩነትን ከእሴት ትስስር፣ አካባቢነትን ከሀገር፣ የግል ፍላጎትን ከቡድን፣ ትናንትን ከዛሬ፣ አቅምን ከአቋም ደምረው ስለሚጓዙ እንደሆነም ነው የተናገሩት። ያለንን የስልጣኔ ወረት ይዘን፣ የስረ መንግስትነት እሴታችንን አዘምነን፣ በሀገር በቀል እሳቤ ላይ የታነጸ ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ እንዳንገነባ የሚከለክለን ማንም የለም ብለዋል። በትውልድ ቅብብሎሽ የደለበውን ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ወረት ፈልፍለን፣ ከባህር ማዶ የምናገኛቸውን ጠቃሚ ጥበቦች ከኢትዮጵያዊ እሳቤ ጋር በማጣጣም ስልጣኔ መገንባት እንችላለን ሲሉም ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት የሌሎችን ተሞክሮ መርምሮ ከራሳችን ጋር እንዲስማሙ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፤ መደመር የኢትዮጵያ ስልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል ማረጋገጥ መቻሉን አንስተዋል። የምንኮራባቸው ስልጣኔዎቻችን ሁሉ በመደመር እሳቤ የተቃኙ እንደነበሩ መታወቅ መቻሉን ጠቁመው፤ በለውጡ ጊዜ የተሞከሩ ተግባራት አስደናቂ ውጤት ማምጣታቸውንና ከፋፋይ እና ጠባብ እሳቤዎች በህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲተኩ ተደርገው ፍሬ ማፍራት መቻላቸውን አስታውቀዋል።
የሚታይ

አለመግባባቶችን በጠብመንጃ ለመፍታት የሚደረግ አካሄድ ተገቢ አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Oct 5, 2026 30
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት እየተቻለ በጠብመንጃ ለመፍታት የሚደረግ አካሄድ ተገቢ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ ፈተናዎች ወደኋላ የሚጎትቷት ሀገር አይደለችም ብለዋል። ለአብነትም በምግብ እራሷን ለመቻል ያደረገችው ጥረት ከራሷ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል የግብርና እመርታዊ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጸዋል። ዛሬ ላይም የኢትዮጵያን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን ያለን አማራጭ በዓላማ በመጽናት ሀገርን የሚለውጡ ስራዎችን መስራት ሀገራዊ ግዴታችን እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። የምክር ቤት አባላትም የኢትዮጵያን ስልጣኔ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጠንካራ ርዕይ በመሰነቅ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የብዝሃ ስልጣኔ፣ አስደናቂ ታሪኮችና እሴቶች ያላት ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ድንቅ ሀብቶችን በማልማት የተጀመሩ ልማቶችን ማስቀጠል ላይ ክፍተት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያን ዕድገት በማፋጠን የድኅነት ተጋላጭነትን ማስወገድ እንደሚገባ በመጠቆም፤ አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት እየተቻለ በጠብመንጃ ለመፍታት የሚደረግ አካሄድ ተገቢ እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ሌሎች ሀገራትን ሊመግብ የሚችል የእርሻ መሬትና ልዩ ልዩ የሰብል አይነቶች ያላት ሀገር ሆና ሳለ በምግብ ራሷን ለመቻል ፈተና ሆኖባት እንደቆየም አስታውሰዋል። ለዚህም ኢትዮጵያዊያን በጋራና በትብብር ያሉብንን ችግሮች ቀርፈን የሰለጠነች ሀገርን መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል። ድህነትን ማሸነፍ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የትምህርትና ጤና ተደራሽነት፣ ለኢንቨስተሮች ብድር ማመቻቸት፣ ቀልጣፋ ትራንስፖርትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ተደራሽነትም የቀጣይ ግቦች መሆናቸውን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ዘላቂ ችግር የሚፈታው ኢትዮጵያ ስልጣኔ ስትገነባ ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሀገርን ስልጣኔ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን ለአንድ ዓላማ በጋራ መስራትና መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የሰለጠነች ኢትዮጵያን በመገንባት ሀገሪቱን የምታሳድግ ብቻ ሳይሆን ዓለምን የምትቀይር ኢትዮጵያን መፍጠር ለነገ የማንለው የቤት ስራችን ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም -ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ
Oct 5, 2026 33
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም ሲሉ ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ በመልዕክታቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በድጋሚ በመመረጥዎ የተሰማኝን ደስታ ልገልፅ እወዳለሁ ብለዋል። የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም ሲሉ ተናግረዋል። ታሪካዊቷ ሀገር ኢትዮጵያን ያገለግሉ ዘንድ የተሳካና ፍሬያማ የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታችውን ገልጸዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ

ማህበራዊ
አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት አለበት 
Oct 5, 2026 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሁሉም ዜጎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶች አባቶችና እናቶች ለሀገር እድገትና አንድነት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። በጫካ የሚገኙ የታጠቁ አካላት ይህንን ታሪካዊ እድል በመጠቀም ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቅሬታ ያላቸው ወገኖችም የይቅርታን መንፈስ ተላብሰው በሀገር ግንባታ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔራዊ ጥቅም ላይ በጋራ የመቆም እና በአማራጭ ሀሳቦች የመፎካከር ባህልን ማሳደግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት እንዳለበት ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፤ የዛሬ ወጣቶች በሩቅ አሳቢነት ነጋቸውን እንዲቀርጹ አሳስበዋል። የትናንት ወጣቶች ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአብዮታዊ የትግል ስልትና ከባንዳነት ልምምድ በመራቅ የተጣሉትን ለማስታረቅና የሸሹትን ለመመለስ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሀገር አባቶችና እናቶችም ለነገዋ ኢትዮጵያ ታላቅነትና ስልጣኔ በመጸለይ ታሪካቸውን ማውረስና ትውልዱን መገንባት እንደሚገባቸው ገልጸዋል። "ትናንት አልፏል፤ ነገም ገና አልደረሰም፤ ዛሬ ግን ምቹ ሆኖ ቀርቧል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬን በትጋት በመስራት ትናንትን ማስተካከል እና የፈለግነውን ዓይነት ብሩህ መንገድ መቅረጽ እንደሚቻል አስገንዝበዋል። ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኖረው ቆይታ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመጠየቅና ከመደገፍ ባሻገር የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ የህዝቡን ህይወት ምን ያህል እንደለወጡና የመደመር ስልጣኔን ምን ያህል እንዳሳኩ በቅርበት እንዲከታተልና እንዲመራም አደራ ብለዋል።
ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኩል ስንራመድ ብቻ ነው
Oct 5, 2026 35
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኩል ስንራመድ ብቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምርጫ አካሂደን፣ በህጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው፣ በድምጻቸው መንግስት ለማጽናት በተግባር ለታመኑ ዜጎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል። ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ፣ የዲሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ያሳለፍነው ምርጫ እንደማንኛውም ህዝባዊ ምርጫ ተካሄደ ተብሎ ብቻ የሚገለጽ የሰርክ ኹነት አልነበረም ብለዋል። ዜጎች በምርጫው ፈቃዱን ሊሰጥ የቻለው በብዙ ውዥንብሮች መካከል አልፎ እንደነበርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል። በየጫካው የሸመቁበት፣ በየሚዲያው እያዋከቡት፣ በአሉባልታ እያስፈራሩት፣ በብዙ ፈተናዎች መካከል አልፎ ህልውናውን ለማጽናት ህዝቡ ፈቅዶ መርጧል ብለዋል። አጠቃላይ ሂደቱ የዴሞክራሲ ባህል መሰረቱ እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ አሳይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ወደፊት ታሪክ በደማቅ ብዕር እንደሚጽፈው፣ ትውልድም ደጋግሞ እንደሚዘክረው ጥርጥር የለኝም በማለት ገልጸዋል። ማንኛውም ምርጫ አሸናፊ እና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖረው ይችላል፤ ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል። ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኪል ስንራመድ ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፤ ዛሬ ዘመኑ ተቀይሯል ነገሮች እንደ ድሮ አይደሉም ብለዋል። ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ ዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እንደሚለዋወጡ ጠቅሰው፤ ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ወዲህ የዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መልኮች በፈጣን ለውጥ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። ዓለም በጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎቿ ምክንያት መልክ እና ጠባይዋ መቀያየሯን ጠቁመው፤ አይገመቴነት የዘመኑ ዋነኛ መገለጫ እየሆነ ነው፤ ቋሚ አሰላለፍ ማየት ብርቅ ሆኗል ብለዋል። የባለብዙ ዓለም ዋልታ ሊወለድ በሚታገልበት በዚህ ወቅት ጎራ መርጦ ማንም እንደማይቆምና የትኛውም ፖለቲካዊ እሳቤ በዓለም ላይ እንደሚነግስ ከግምት በዘለለ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻልም አስገንዝበዋል። ታሪክ ወደ የትኛው አዲስ ምዕራፍ እንደሚያደርሰን በግልጽ በማይታወቅበት መንታ መንገድ ላይ እንገኛለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲስ ነገር ዕዳም፣ ምንዳም አለው፤ ዕዳ እና ምንዳው ግን ለሁሉም እኩል አይደለም ነው ያሉት። መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው፣ የሚመጣውን አዲስ ነገር ከወዲሁ ገምተው፣ በጥንቃቄ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ መሆኑን ጠቁመው፤ በአንጻሩ ዘግተው እና ተዘናግተው ለሚቆዩ ደካሞች ዕዳው እልፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የሀገራችን አርሶ አደርም «መጪው ክረምት የሚጠቅመው ላረሰው ገበሬ ነው» እንደሚል ገልጸው፤ ከሁለቱ አማራጮች ለሀገራችን የሚበጀውን መንገድ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቁ አደራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ለሆነው የወል ትርክት ግንባታ ተገቢ ትኩረት ይሰጠዋል
Oct 5, 2026 49
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ለሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ለሆነው የወል ትርክት ግንባታ ተገቢ ትኩረት እንደሚሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሄዷል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ የተጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የታለመለት ግብ እንዲመታ ይደረጋል ብለዋል። ለዚህም የመደመር መንግሥት ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ያለበት የበጀት አካሄድን በመከተል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ለሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ የሆነው ለወል ትርክት ተገቢው ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል። ምርታማነትን በሁሉም መስክ ለማላቅ ይሰራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የሰላም ሁኔታችንን የበለጠ ለማጽናት የውይይትና የይቅርታን መንገድ እንከተላለን ብለዋል። የተጠናከረ የጸጥታና የደህንነት ዝግጅትና ክትትል እንዲሁም ስምሪት በአስተማማኝ መሰረት የማነጽና የመገንባት ሥራ እንደሚከናወንም አስረድተዋል። የመገናኛ ብዙኅን ምህዳርንም ሕግን፣ ሀገራዊ እሴቶችንና ፍላጎቶችን ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀስ የማድረግ ሥራ በትኩረት እንደሚሰራበት አንስተዋል።
ሙስናን፣የዘመድ አሰራርን ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መራር እርምጃዎችን ይወስዳል 
Oct 5, 2026 37
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርን፣ ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስት መረር ያሉ እርምጃዎችን ይወስዳል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርን፣ ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስት መረር ያሉ እርምጃዎችን ይወስዳል ብለዋል። እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ ዘመናዊ አሰራሮችን እስከ ታችኛው እርከን በማድረስና የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ለማዘመን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። የመኖሪያ ቤት ችግሮችን ከስሩ ለመፍታትም አዳዲስ አካሄዶችን እንከተላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የተገኙ ተሞክሮዎችን በማላቅ ጭምር የቤት ልማት መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ተናግረዋል። በዚህም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጤታማነትን በማሳደግ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ጊዜና ገንዘብ በሚቆጥብ በተጠናከረና ፈጣን አሰራር እንደሚተገብርም አብራርተዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ለአንዴ እንኳን ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን ማስቀጠል ችላለች
Oct 5, 2026 51
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሃብት አልምተን እንዳንጠቀም ሲያጋጥሙን የነበሩ ጫናዎችን በመሻገር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ችላለች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማፋጠን የሚያስችል መሰረት ተጥሏል ብለዋል። ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው ስኬታማ ዓመታትም ፈተናዎችን በብስለት በማለፍ ሀገርን የሚቀይሩ የልማት ትሩፋቶች የተከናወኑበት መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት በቁርጠኝነት በሰራው ስራም ጠንካራ የፖለቲካልና ኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት መቻሉን ተናግረዋል። ዓለም ጀርባውን ሲያዞርብንና ፍርደ ገምድልነቱን ደግሞ ደጋግሞ ሲያሳየን ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ለአንዴ እንኳን ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን ማስቀጠል እንደቻለችም አስረድተዋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሃብት አልምታ እንዳትጠቀም ሲያጋጥሙ የነበሩ ጫናዎችን በመሻገር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ እንደተቻለ አክለዋል።
ከተሞቻችን ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቱሪዝም የተስማሙና ተምሳሌት በመሆን የሚጠቀሱ እየሆኑ ነው 
Oct 5, 2026 63
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ከተሞቻችን ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቱሪዝም የተስማሙና ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱ እየሆኑ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ዓመታት ተረስተው የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶች ተጠግነውና ተሻሽለው ለጎብኚዎች ክፍት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት የማይታወቁ የሀገሪቱ ሀብቶች ታድሰውና ለነገው ዘመን ተዘጋጅተው ተጨማሪ ሀብት ማመንጨት ጀምረዋል ነው ያሉት። ዛሬ ከተማና ገጠሩ እኩል እየተቀየረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ ጥረት ማድረግ ጀምረዋል ሲሉ ገልጸዋል። በዚህም ለመኖሪያ የተመቹ፣ ለንግድና ኮንፈረንስ የተስማሙ፣ ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመው ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነት እንጂ ባዶ ምኞት ተደርጎ አይወሰድም ነው ያሉት። የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጎብኚዎችን ኑ ወደ እኔ እያለ ሲጠራ፤ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የምርት ባህላችንን ሲያድሰው፤ የማዕድን ልማታችን የዘመናት የወጪ ንግዳችንን በአጭር ጊዜ መብለጥ ሲችል አይተናል ሲሉም ተናገርዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በንግግራቸው በአረንጓዴ አሻራ ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ስንተክል የተራቆቱ ሜዳዎቻችን አረንጓዴ ለበሱ፤ ተጠርጎ የሚሸሸው አፈር ባለበት ተገደበ ሲሉም አክለዋል። የበጋ መስኖ ልማት የኢትዮጵያን የስንዴና የሩዝ ታሪክ መቀየሩን ጠቁመው በሌማት ትሩፋት የወተት፣ የዶሮና የዕንቁላል ምርቶች እንደጨመረና ይህም በምግብ ራስን የመቻል ግብ ሩቅ እንዳልሆነ ጠቁሞናል ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል የኢትዮጵያን የአገልግሎት አሰጣጥ መልክ ማስተካከሉን ጠቁመው ፋይዳ አዲሱን ዲጂታል ማንነት ማጠናከሩን፣ የወንዝ ዳር ልማት የኢትዮጵያን የውሃ እሳቤ መቀየሩን እንዲሁም የገበታ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ነባር መልኮች በአዲስ መልክ ሲገልጡ በአይናችን አይተናል ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በእመርታ ወደፊት ትቀጥላለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Oct 5, 2026 98
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ በእመርታ ወደፊት ትቀጥላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል። አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ብዙ ፈተናዎችን በጽናት ማለፏን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እድገት እና መስፈንጠር ያልተዋጠላቸው የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ሀገሪቱን ለማሰናከል እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የውስጥ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አይችሏትም ከህልሟ ማንም አያሰናክላትም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ፍላጎቶቿን በራሷ አቅም እና ጉልበት ማሳካት እንደምትችል ማረጋገጧንም አመልክተዋል። መንግስት ጠንካራና አይበገሬ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስርዓት እየገነባ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ችግሮችና ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ ያሰበችው ቦታ መድረስ እንደምትችል አመልክተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ለህዝብ የገባውን ቃል እንዲያሳካ ድጋፋችንን እናጠናክራል- ነዋሪዎች
Oct 5, 2026 113
ድሬደዋ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን እንዲያደርግ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምስረታና ለከተማዋ እድገትና መልካም አስተዳደር መስፈን ያላቸውን ተሳትፎ አስመልክተው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ አስተዳደሩ በምርጫ ወቅት የገባውን ቃል ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተዋል። ከነዋሪዎች መካከል አቶ ዳንኤል ብርሃነ እንደተናገሩት፤ አዲሱ አስተዳደር የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በላቀ ደረጃ እንዲፈጽም የድርሻቸውን ይወጣሉ። ወይዘሮ ኤደን የሺጥላ እና አቶ ረመዳን ደስታ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጥያቄን ለመመለስ እና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀው፣ ለዚህም የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አክለዋል። አስተዳደሩ ያዋቀራቸው የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በዕውቀት እና በሥራ ልምድ ብቁ መሆናቸውን መረዳታቸውንም ነው የገለጹት። የሚፈልጉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤቶች ለማምጣትም በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል። የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄዎች የመለሱ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲሱ አስተዳደር አበክሮ መስራት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው የሳይንስ ባህል ግንባታን የሚያጠናክሩ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
Oct 5, 2026 97
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታዳጊዎች ላይ በትኩረት በመስራት የሳይንስ ባህል ግንባታን የሚያጠናክሩ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ገለፁ። ዩኒቨርሲቲው የዲጂታላይዜሽን ዘርፉን የሚመሩ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው የታዳጊዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት የሚያሳድጉ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። ዩኒቨርሲቲው በክረምት ወቅት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን አንስተው፤ ባለው የስቴም ማዕከልም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የተማሩትን በተግባር የሚያዩበትና የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ተማሪዎች የሚጎበኙት የሳይንስ ሙዚየምም የሳይንስ ክህሎትን ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የልህቀት ማዕከላት ፈጠራን የሚያበረታቱ በመሆናቸው በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩና ወደ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገሩ የፈጠራ ስራዎች መኖራቸውን አስረድተዋል። የዩኒቨርሲቲው የኢኖቬሽንና ኢንኩቤሽን ማዕከልም የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብና ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያሉ ተሰጥኦ ያላቸውን ሰዎች ሀሳብ ወደስታርት አፕ ለመቀየር ብሎም ሀብት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል። በስኬት የተጠናቀቀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራም ለምርምር ተቋማት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፣ ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።   የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ደበበ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሳይንስ ባህል ግንባታ ላይ ለዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። የስቴም ትምህርቶችን ከዚህ ቀደም ከዘጠነኛ ክፍል ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው፤ የሳይንስ ባህል ግንባታውን ወደታችኛው የትምህርት ደረጃ ለማስፋት በማሰብ በአሁኑ ወቅት ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች መካተታቸውን አስረድተዋል። በቅርቡም የማህበረሰብ ትምህርት ቤት መክፈቱ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ ተማሪዎች ሳይንስና ቴክኖሎጂን እንዲገነዘቡ የሚያስችል ነው ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን የሳይንስ ሙዚየም ተማሪዎችን እንደላቦራቶሪ እገዛ እያደረገ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የዲጂታላይዜሽን ዘርፉን የሚመሩ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሰው ኃይል ልማት ላይ እየሰራ ነው ብለዋል።    
ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል
Oct 3, 2026 158
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዜጎች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማጠናከር ተግባራዊ የተደረገ ፕሮግራም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ5 ሚሊየን የኮደርስ መርሐ ግብር ወደ 7 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ስዩም መንገሻ እንደገለጹት፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ የስኬት ጉዞ በዋናነት ትልቁ የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ነው። የኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሲጀመር አምስት ሚሊዮን ዜጎችን ስልጠና እንዲወስዱ መታቀዱን አንስተው፤ ከታቀደው በላይ ለማሳካት በመቻሉ ሰባት ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 5 ነጥብ 4 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በዚህም ክህሎታቸውን ማሳደግና በኦን ላይን የስራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበታቸውን ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠናው መሰረታዊ ነው፤ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ መንደርደሪያ፣ መስፈንጠሪያ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድጉ ተግባራትን እያከናወነች መሆን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ዲጂታላይዜሽን በማስፋፋት ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውንም ገልጸዋል። የዲጂታል ክህሎት ሀገርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ግብዓት በመሆኑ በዘርፉ ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለጹት። የኢትዮ ኮደርስ ዜጎች የዲጂታል ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸው፤ በቀጣይም እንደዚሀ አይነት ስልጠናዎች በላቀ ደረጃ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።   በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርትአፕ ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት አብይ ታደሰ በበኩሉ በኢትዮ ኮደርስና በሌሎች ኢኒሼቲቮች ስታርት አፖችን መደገፍ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። የኮደርስ ስልጠና መሰረታዊ ክህሎትን ለማስጨበጥና የስራ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በኤ. ይ ዘርፍ የወጣቶችን ክህሎት የሚያዳብሩ ወደ ስታርት አፕ እንዲገቡ የሚያስችሉ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ነው የገለጸው። ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ክህሎታቸውን ማሳደጋቸው ለስራ ፈጠራና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል። በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይበር ሴኪዩሪቲ ኦዲተር ማርታ ሀዲስ አራቱንም ኮርሶች መውሰዳቸውንና በዘርፉ የነበራቸውን እውቀት ለማዳበር እንደጠቀማቸው ገልጸዋል። ኢኒሼቲቩ ለወጣቶች በጣም ትልቅ እድል ነው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን፣ ክህሎትን ለማሳደግ ከወቅቱ ጋር ለመራመድ መሰረታዊ ስልጠና ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ የታገዙ ስራዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ኮርሶቹ ለቀጣይ የስራ እድሎችና ሙያን ለማሳደግ መሰረት ነው ሲሉም ተናግረዋል።    
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ ነው
Oct 1, 2026 299
አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2019(ኢዜአ)፡-የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ባላት ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በሁሉም መስክ የሀገርን ማንሰራራት የሚያበስር እመርታዊ ውጤት እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የ50 ዓመታት የምርምር፣ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ጉዞን እና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።   ለሦስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ማጠናቀቂያም የኢትዮጵያ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ማበልፀጊያ ኢንስቲትዩት የቡራዩ ተሰጥኦ ልማት ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን አስመርቋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችን በማሰልጠን የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል የሰው ኃይል እያፈራ ነው። በትምህርት ቤቱ ሥልጠና የሚሰጣቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችም ከፍተኛ የማሰብ፣ የማገናዘብና የመተንተን አቅማቸውን ታሳቢ ባደረጉ መስፈርቶች ተመልምለው የሚሰለጥኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ታዳጊዎች የፈጠራ ክህሎትና ልዩ ተሰጧቸውን በማበልጸግ ችግር ፈቺ የመፍትሔ ውጤቶችን የሚያፈልቁበት ወሳኝ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ተመራቂዎችም በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው ንድፈ ሃሳብን ከተግባር ተኮር ያቀናጀ ዕውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላትም ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያበለጽጉበትን ዕድል በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው፤ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ተፈጥሯዊ ተሰጥኦቸውን በተግባር ልምምድ የታገዘ ሥልጠና የሚያገኙበትን የዕውቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ማክዳ ወርቅሸት፤ ትምህርት ቤቱ ልዩ ተሰጥኦቸውን የሚያበለጽጉበትን ወሳኝ ትምህርትና ሥልጠና ዕድል ሰጥቶናል ብላለች። የሥልጠና ቆይታቸውም የልዩ ተሰጥኦ ዕውቀትና ክህሎታቸውን በማበልጸግ ከዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነትን እንደሚያጎለብትላቸው ገልጻለች። የኢትዮጵያ ዲጂታል ልማት የቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጧቸውን የምናጎለብትበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሮልናል ያለው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት በተሻለ አበበ ነው። በአሁኑ ወቅት የክረምት ሥልጠናዎችና ልዩ ልዩ የፈጠራ ማሳያ መድረኮች በርካታ ዕድሎችን በመፍጠር ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጿል። ወጣቶችም የኢንተርኔት አክሰስንና አዳዲስ ዕድሎችን በመጠቀም የራስን ጥረት ማዕከል በማድረግ አዳዲስ ሶፍትዌሮችን በማልማት ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።  
በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው 
Oct 1, 2026 217
ሸገር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላቱ ለኢሬቻ በዓል አከባበር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በሚገኘው የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው። የዲያስፖራ አባላቱ በኢንስቲትዩቱ በተከናወኑ የዲጂታል ልማት ስራዎቹ መደመማቸውንም ገልጸዋል።   ከአሜሪካ የመጡት ዶክተር ተመስገን ሻሾ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመለከቱት ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለተተኪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው። "ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተደገፈች ያለችበት ወቅት በመሆኑ፣ ሀገራችን ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከውጭ ይገቡ የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የጀመረችው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ነው" ብለዋል።   በተለይም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲደገፉና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ያደነቁት ዶክተር ተመስገን፤ አሁን የተጀመሩት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በተሻለ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ተመስገን፤ በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራቸው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።   ከደቡብ አፍሪካ የመጡት አቶ ኡመር ኡስማን በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወኑት ተግባራት ትውልዱ በሀገሩ ሰርቶ እንዲለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል። በኦሮሚያ ክልል በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ አስተማማኝ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአስተማማኝ የዕድገት መስመር ላይ የምትገኝ መሆኗን በመጠቆም፣ ዲያስፖራው በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።   በተመሳሳይ ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ሌንሴ ለሜሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳሉት፤ ጉብኝቱ በየዓመቱ በኢሬቻ ሳምንት በክልሉ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት ባህል አካል ነው።   አክለውም በኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ለነገዋ ሀገር ተስፋ የሚሆኑበትን አሰራር መመልከታቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።   ይህም ከፍተኛ የዕውቀት ብቃት (IQ) ያላቸውን ተማሪዎች በማፍራት ሀገራቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን ያብራሩት አቶ አሚን፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በሀገራችን እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ በተግባር በማሳየት አባላቱ ሀገራቸውን በዕውቀትም ሆነ በኢንቨስትመንት ለመደገፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲሸልስን በድጋሚ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ
Oct 3, 2026 241
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊ ሰለሞን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት በአጠቃላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። እሙሽ ዳንኤል ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታገናኝ ቱሪስት ለማ፣ ቤተልሄም መንተሎ፣ ቤተልሄም በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና የሲሸልሷ አሻንታ ማሪ በራሷ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል። ሀገራቱ ከቀናት በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ 16 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የበላይነቱን አሳይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛል። የወዳጅነት ጨዋታዎቹም የዚህ ዝግጅት አካል ናቸው። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል
Oct 3, 2026 175
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታውን ዛሬ ያከናውናል። ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል። በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅቱን እያደረገ ነው። ቡድኑ የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናውነዋል። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ ተካሄደ
Oct 1, 2026 247
ቢሾፍቱ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ተካሂዷል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል።   በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ጅራታ ሌሊሳ (ከሸገር) 1ኛ፤ አትሌት ለሚ ተሾመ (ከሸገር) 2ኛ፤ አትሌት አቤል ቼቤት (ከኡጋንዳ) 3ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል። እንዲሁም በሴቶች አትሌት ብርነሽ ደሴ (ከፀዳይ ባንክ) 1ኛ በመውጣት የ2019 የ2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል።   በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ ባደረጉት ንግግር፣ ኢሬቻ ፍቅርንና አንድነትን በማጠናከር ለብሔራዊ መግባባት መሠረት በመጣል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ይህንን በስፖርት በማስደገፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የመግባባት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ እናሳድጋለን ብለዋል።   የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ ሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሀገሪቱን ቱሪዝም እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የቢሾፍቱ ከተማም ከምንጊዜውም በላይ ዘንድሮ የኢሬቻ እንግዶችን ለመቀበል በኮሪዶር ልማት አጊጣ እየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል።
2ኛው የኢሬቻ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል
Oct 1, 2026 181
ቢሾፍቱ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓል ዋዜማን በማስመልከት የተዘጋጀው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ፡ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ፣ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦችን አንድ ላይ የሚያመጣ እንዲሁም መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል።   በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 162
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።      
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን እያጎለበተ ነው
Oct 1, 2026 188
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን በማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል። በተለይም የከተሞችን ሁለንተናዊ ጽዳትና ውበት ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምኅዳር ድኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የጽዱ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ ምኅዳርን በማጎናጸፍ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻና መሰል ውጤታማ የልማት ሥራዎችን የሚያፋጥን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንም የሕብረተሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጽዱ ኢትዮጵያን ግብ የሚያሳካ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ባህልን የሚያጎለብት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያው ዙር "ውበት ይንቃ፤ ብክለት ይብቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የብክለት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ "ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ባህልን ማጠናከር የሚያስችል መሰረት መጣል እንደተቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም ለ3 ወራት የሚቆይ 3ኛ ዙር ''የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል። በየዓመቱ የሚካሄዱት የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የማኅበረሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማጎልበት ተቋማት በብክለት መከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው ብለዋል። መርሐ ግብሩም የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትና መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ በውጤታማነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይም ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥና ብክለትን ለመከላከል የተቀናጁ የአካባቢ የጽዳትና ውበት ጥበቃ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።    
የኤልኒኖ ክስተት ተጽዕኖዎችን ለመከላከል መዘጋጀት ይገባል
Sep 29, 2026 245
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ ክስተት የሚያመጣቸውን መልካም እድሎች ለመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኤልኒኖ ክስተት ከጥቅምት ወር ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጠnነከረ ይሄዳል። ኤልኒኖ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች እንዲሁም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ የደቡብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እና ስርጭት እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ከጥቅምት ጀምሮ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት በተለይም ለሱማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ ለጉጂ፣ ለቦረና፣ ለሲዳማ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም ዝናብ ከወዲሁ የመስኖ ስራዎችንና የተለያዩ የግብርና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለአርብቶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በማሻሻል በእንስሳት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ህንድ ውቅያኖስም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቀ ይገኛል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኤልኒኖ ክስተት እና የህንድ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመር በአንድ ጊዜ በሚጣመሩበት ወቅት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አማራ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከመደበኛ በላይ በሚኖረውና ተደጋጋሚነት ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በዋቢ ሸበሌ እና በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት እድሉ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል ከወዲሁ በዋቢ ሸበሌ፣ በኦጋዴን እና በገናሌ ዳዋ አካባቢዎች የተቀናጀ የወንዝ አመራር ስርዓትን መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው የበጋ ወቅት ከመደበኛ በላይ የሚኖረው የዝናብ መጠን ያለው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ለማህበረሰቡ ተደጋጋሚነት ያለው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀጣናው የታዳሽ ኃይል ማዕከል
Sep 27, 2026 480
ኢትዮጵያ በውሃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል ሀብቶቿ ለታዳሽ ኃይል ልማት እጅግ ግዙፍ አቅም ያላት ሀገር ስትሆን፤ የመደመር መንግስት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በብቃት በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማልማት ረገድ ያከናወነው ስራ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ከራሷ አልፎ ለጎረቤት አገራት በማዳረስ ቀጣናውን በኢነርጂ የማስተሳሰር ስትራቴጂካዊ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። እንደ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ ላሉ አገራት የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የምስራቅ አፍሪካን አገራት በኢነርጂ በማስተሳሰር በጋራ ማደግ እንደሚገባ ያሳየ ነው።ይህ የሃይል ትብብር የአፍሪካን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ እና በቀጣናው የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት ሆኖ ቀጥሏል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ  
Sep 21, 2026 910
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1028
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 925
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1108
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
በሀገር ግንባታ ላይ እየጎለበተ የመጣው የወጣቶች ተሳትፎ
Oct 5, 2026 75
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተከናወኑ ሀገራዊ ሂደቶች ወጣቶች በፖለቲካና በምርጫ፣ በሀገራዊ ምክክር፣ በቴክኖሎጂ እና በሥራ ፈጠራ፣ በስፖርት፣ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በሰላም ግንባታና በበጎ ፈቃደኝነት የሚያሳዩት ተሳትፎ እየጎላ መጥቷል። ይህ ሁኔታ ወጣቶች በሀገራዊ ልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ውስጥ ሀሳብ የሚያመነጩ፣ በውሳኔዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉና በዛው ልክ ተጠቃሚነታቸውንም እያረጋገጡ የሚሄዱ የዛሬ ተዋናዮች የነገ ደግሞ ተረካቢዎች መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል። ለዚህ ደግሞ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የታየው ሰፊ የወጣቶች ተሳትፎ ነው። በምርጫው ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈዋል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሰፊውን ድርሻ ወጣቶች ሊይዙት እንደሚችልም ይታመናል። የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከሚጎለብትባቸው ሂደቶች መካከል ምርጫ አንዱ ነው። በዚህ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ ወጣቶች በተመራጭነት፣ በመራጭነት፣ በምርጫ አስተባባሪነትና አስፈጻሚነት፣ በፖለቲካዊ ውይይቶችና በተለያዩ የሕዝብ ተሳትፎ መድረኮች ላይ በንቃት መሳተፋቸው ወጣቶች በሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ አሳይተዋል። ይህም ወጣቶች የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደቱን ከሩቅ የሚመለከቱ ሳይሆኑ በሂደቱ ውስጥ በቀጥታ የሚሳተፉ ዜጎች መሆናቸውን ያሳያል። ሀገራዊ ምክክር፤ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ የታየበት ሀገራዊ ሁነት የወጣቶች ተሳትፎ በምርጫ ብቻ ሳይወሰን በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በግልጽ ተንጸባርቋል። በሀገራዊ ምክክሩ ከተካተቱ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ወጣቶች ዋነኞቹ ነበር። ባገኙት ዕድልም የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተመለከቱ በርካታ አጀንዳዎችን በማቅረብ ተሳትፏቸውን አጠናቀዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዓላማ በጋራ የሚያገናኙ ጉዳዮችን በውይይት መለየት፣ በልዩነቶች ላይ መነጋገርና በሀገር ደረጃ መግባባት የሚፈጥሩ መፍትሔዎችን ማፈላለግ ነው። በዚህ ሂደት ወጣቶች መሳተፋቸው በዲሞክራሲያዊ ውይይትና በሰላማዊ የሀሳብ ልውውጥ ውስጥ ያላቸውን ሚና ያሳያል። በመሆኑም ሀገራዊ ምክክር ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበትና ሀሳባቸውን የሚያንጸባርቁበት መድረክ መፈጠሩን ያሳያል። ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጠራ የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ተሳተፎ እና ተጠቃሚነት በግልጽ ካሳየባቸው ዘርፎች መካከል የቴክኖሎጂ ዘርፍ አንዱ እና ዋነኛው ነው። በዚህ ዘርፍ ላይ የወጣቶች ተጠቃሚነት በቴክኖሎጂ ፈጠራም የታጀበ ነው። የዲጂታል ዘመኑ ለወጣቶች አዳዲስ የተሳትፎ መድረኮችን ፈጥሯል። በኮዲንግ፣ በሶፍትዌር ልማት፣ በዲጂታል አገልግሎት፣ በፊንቴክ፣ በኢ-ኮሜርስና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ወጣቶች አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅና መፍትሔዎችን በማቅረብም ጭምር። መንግሥት የወጣቶችን በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሳደግ ካለው መሻት የተነሳ የ5 ሚሊየን ኮደሮች ፕሮግራም ነድፎ በመተግበር ውጤት አስመዝግቧል። ወጣቶችን በኮዲንግና በዲጂታል ክህሎት ለማብቃት የተሄደበት ርቀት እና የተመዘገበው ውጤት ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። ይህ ተሳትፎ ወጣቶች ቴክኖሎጂን ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ቴክኖሎጂን ወደ መፍጠር እንዲሸጋገሩ፣ ችግሮችን የሚፈቱና ሥራ የሚፈጥሩ ምቹ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂን ለስራ ዕድል ፈጠራ ወጣቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በዚህም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መጥቷል። ወጣቶች ቴክኖሎጂን ለግብርና፣ ለአግሮ-ቢዝነስ፣ ለማምረቻው ዘርፍ፣ በኢ-ኮሜርስ እና ለአገልግሎት ዘርፎች ዕድገት በማዋል በኩል የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱም ናቸው። ይህም የወጣቶች ሚና ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነትና ወደ ንቁ ኢኮኖሚያዊ ተዋናይነት እየተሸጋገረ መምጣቱን ያመለክታል። ስፖርት፤ የወጣቶች ተሳትፎ ሌላው መድረክ የመደመር መንግሥት በአእምሮም በአካልም የጎለበተ ትውልድ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚኖረውን አበርክቶ በውል በመረዳቱ ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሆኑ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል። እየሰራም ይገኛል። ስፖርት ወጣቶች ሀገራዊ ተሳትፏቸውን የሚያጎለብቱበት እና ሀገራቸውን በዓለም የውድድር መድረኮች ላይ የሚወክሉበትና የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው። የስፖርት ተሳትፎ ከውድድርና ውጤት ባለፈ የቡድን ሥራ፣ የመከባበር፣ የደንብ ማክበርና የሰላማዊ ውድድር እሴቶችን የሚያጎለብት በመሆኑ ለዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታም አስተዋጽኦ አለው። ባህልና ኪነ-ጥበብ፤ የወጣቶች የሀሳብ መግለጫ ወጣቶች በባህልና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ እያሰፉ ነው። በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በቲያትር፣ በስዕልና በሌሎች የፈጠራ ዘርፎች የሚሳተፉ ወጣቶች የራሳቸውን ሀሳብና እይታ ለማህበረሰቡ እያቀረቡ የሌሎችንም እየወሰዱ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የራሳቸውን ጠጠር እንዲያኖሩ ዕድል የሚፈጥሩ አውዶች ናቸው። ኪነ-ጥበብ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ፣ ልዩነቶችን ለማቀራረብና የጋራ እሴቶችን ለማጠናከር ከሚያገለግሉ መድረኮች አንዱ በመሆኑ፣ የወጣቶች በዚህ ዘርፍ መሳተፍ ለሀገራዊ ማንነትና ለማህበራዊ ትስስር ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ነው። ሰላም ግንባታና በጎ ፈቃደኝነት፤ ለማህበረሰብ ተሳትፎ የወጣቶች ሀገራዊ ተሳትፎ በሰላም ግንባታና በበጎ ፈቃደኝነትም ጭምር ይገለጻል። በተለያዩ የሰላም ማስፈን፣ የማህበረሰብ ውይይት፣ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ድጋፍ ሥራዎች ወጣቶች በበጎ ፈቃድ የሚሳተፉባቸው ዘርፎች ናቸው። ይህ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ለሀገር ጉዳይ መቆም እንደሚችሉ ያሳያል። በጎ ፈቃደኝነት በተለይ የዜግነት ተሳትፎን በተግባር የሚያሳይ መስክ ነው። ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለማህበረሰቡ በማበርከት የጋራ ችግሮችን በጋራ መፍታት እንደሚቻል በተግባር ያሳያሉ። ይህም የዜጎችን ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎን የሚያጠናክር ነው። ይህ ሁለንተናዊ የወጣቶች ተሳትፎ ለሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውጤታማነት አይነተኛ ሚና አለው። የመደመር መንግስት በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ሂደት ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገር ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ ተጠቃሚነታቸውንም እንዲያረጋግጡ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ወጣቶች ይህን ትልቅ ዕድል በመጠቀም ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከመጠቀም ባለፈ ለሀገር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። ይህን ዕድል በሚገባ ከተጠቀሙበት የኢትዮጵያ ወጣቶች የነገ ተስፋ ብቻ ሳይሆኑ በዛሬው የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ አሻራቸውን ማኖር ያስችላቸዋል። የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ብቻ ሳይሆን በሀገራዊ ልማት፣ በሰላም፣ በማህበራዊ ትስስርና በፈጠራ ዘርፎች እየሰፋ የመጣ ግልጽ እውነታ ነው። ይህን ተሳትፎ በተጠናከረ መንገድ ለማስቀጠል ዛሬ የሚመሰረተው የመደመር መንግስት ግልጽ አቅጣጫ ይከተላል።  
የታላቅ ሕዝብ ድምጽ - የጠንካራ ሀገረ መንግሥት መሠረት
Oct 5, 2026 99
የታላቅ ሕዝብ ድምጽ - የጠንካራ ሀገረ መንግሥት መሠረት ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ታላቅነት መታወቂያዋ፣ ግዙፍ ሕዝብ ጌጧ፣ አርቆ አሳቢ ርዕይ ደግሞ የጉዞዋ ኮከብ የሆነላት ኢትዮጵያ፣ በየዘመናቱ እንደ ተራራ የተደቀኑባትን መሰናክሎች ሁሉ ተሻግራ የልማትና የብልፅግና ጉዞዋን በጽናት ዘልቃለች። ዛሬም የጀመረቻቸውን ሀገራዊ የዕድገት ርምጃዎች አጠናክራ ለመቀጠል በታሪክ ማዕዘን ላይ ቆማለች። ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያሸጋግራትን መሪ የመምረጥ ባለቤትነትና ሥልጣን ለሕዝብ የተረጋገጠበት፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም የዚህ ሀገራዊ ጉዞ ጉልህና ወሳኝ ምዕራፍ ሆኖ በታሪክ ማኅደር ሰፍሯል። 👉የታላቅ ሕዝብ ውሳኔ ትልቅነት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተከናወነው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው፣ ይበጀናል ላሉት ፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት ሰጥተዋል። በምርጫው 42 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል። ይህ ተሳትፎም ምርጫውን በአገር ውስጥ የፖለቲካ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ከተመዘገበባቸው ምርጫዎች ተርታ አሰልፎታል። የምርጫው ስኬት በቁጥር ብዛት ብቻ አይለካም። ዜጎች የአየር ንብረት ተጽዕኖና የጊዜ ገደብ ሳይበግራቸው እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ይህም ሕዝቡ ለሀገራዊ ዕጣ ፈንታው ያለውን ጥልቅ የኃላፊነት ስሜት፣ ትዕግሥትና ጽናት በተግባር የመሰከረበት፣ የታላቅነቱንም ምስክር ለዓለም ያሳየበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው። የሕዝቡን ድምጽ ተከትሎም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 ወንበሮችን በማግኘት የአብዛኛውን ሕዝብ ይሁንታ በማግኘት ማሸነፉን ይፋ አድርጓል። 👉ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ተወካዮቹን የመምረጡ ዋና ዋና ጥቅሞች ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ተወካዮቹን መምረጡ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ እንደ ዓለት የጸና መሠረት ነው። የመንግሥት ጥንካሬ ምንጩ የሕዝብ ድጋፍና ይሁንታ ነው። የዜጎችን ይሁንታ ያገኘ መንግሥት ተቋማትን ለመገንባት፣ ሕግን ለማስከበርና ሀገራዊ አንድነትን ለማጽናት የሚያስፈልገውን ሞራላዊና ሕጋዊ መሠረት ይጨብጣል። ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ የመንግሥትን ሕጋዊ ተቀባይነት ያጎላል፤ መንግሥትም "ሕዝብ የሰጠኝ አደራ ነው" ብሎ በሙሉ ልብ ፖሊሲዎቹን ይተገብራል፤ ዜጎችም ለወጡ ሕጎችና ውሳኔዎች ይበልጥ ይተባበራሉ። ምርጫው የዴሞክራሲን ባህል በሕዝብ ልብ ውስጥ ይተክላል። ዜጎች ድምጻቸው ወሳኝ መሆኑን በዓይናቸው ሲያዩ፣ የሥልጣን ምንጭ ሕዝብ መሆኑን በልምድ ይገነዘባሉ። ይህ ልምድ ለመጪዎቹ ምርጫዎች ጠንካራ ፋና ሆኖ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ የሥልጣን ሽግግርን አገራዊ ባህል ያደርጋል። ከልዩ ልዩ ክልሎች፣ ማኅበረሰቦችና ሃይማኖቶች የተውጣጡ ዜጎች በአንድ ቀን፣ ለአንድ ዓላማ ወደ ምርጫ ጣቢያ መትመማቸውም "የጋራ ሀገር፣ የጋራ ዕጣ ፈንታ" የሚለውን ፅኑ ስሜት ያጎለብታል። በመሰረቱ በካርዱ የመረጠ ዜጋ የመረጠውን መንግሥት የመከታተል፣ የመጠየቅና የመተቸት ሞራላዊ መብት ይጎናጸፋል። መንግሥትም ለመረጠው ሕዝብ የመመለስ ኃላፊነት ይሸከማል። ይህ የጋራ ተጠያቂነት የጤናማ የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነት የጀርባ አጥንት ነው። ግጭትና አለመግባባት በምርጫ ሳጥን ሲፈታም የሥልጣን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መልስ ያገኛል፤ ይህም ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ዋስትና ነው። በመጨረሻም ብዙ ሕዝብ የተሳተፈበት ምርጫ የሀገርን ዓለም አቀፍ ገጽታና ተዓማኒነት ያንጻል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ አጋሮች፣ ለኢንቨስተሮችና ለልማት ተባባሪዎች ያላትን ተዓማኒነት ከፍ ያደርጋል፤ የተረጋጋችና በሕዝብ ድጋፍ የምትመራ አገርም ለኢንቨስትመንትና ለትብብር ተመራጭ ናትና። 👉ከሕዝቡ ጠቀሜታ አኳያ ምርጫ ለሕዝቡ የመብት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የጥቅሙም መሣሪያ ነው። ሕዝብ ሕልሙን፣ ፍላጎቱንና ምኞቱን እውን ያደርግልኛል ብሎ ያመነውን ፓርቲ መምረጡ ተገቢውን ምላሽ እንደሚያገኝ በማመን ነው። አሸናፊው ፓርቲም የሕዝብን ጥያቄዎች የመመለስ ቃል በትከሻው ላይ ይሸከማል። በዚህም ሕዝብ ፍላጎቱን የሚያስቀድም መንግሥት ያገኛል። መንገድ፣ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ የሥራ ዕድልና የኑሮ ውድነትን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት ጥያቄዎች በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የመንግሥት ዕቅድ እምብርት እንዲሆኑ ድምጽ ተሰጥቷል። ይህም የልማትና የአገልግሎት ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበትን በር ይከፍታል። ድምጹ ዋጋ እንዳለው ያየ ዜጋ ተስፋውና ተሳትፎው ይለመልማል። ዛሬ የሚጣሉ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረቶችም ለልጆቻችንና ለመጪው ትውልድ የተረጋጋችና የበለጸገች አገር ቅርስ ሆነው ይተላለፋሉ። 👉የመደመር መንግሥት ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የሰጠው ድምጽ ውጤትን ከማብሰር ያለፈ፣ ከባድ አደራ የተሸከመ ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ማግኘቱ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጠለት ብልፅግና ፓርቲ፣ ዛሬ መንግሥት የሚመሠርተው ይህንኑ የሕዝብ አደራ በመሸከም ነው። ዛሬ ለሕዝቡ ቃል የገባውን በተግባር የሚተረጉምበትን ፍኖተ ካርታ የሚያሳይበት ነው። ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ እና የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥም ተከታታይ ድሎችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው። ከድሎቹ ቀዳሚው የትውልድ ቃል ኪዳን የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም፣ ገንዘብና ጥረት የገነቡት ይህ ግድብ ተጠናቅቆ ተመርቋል። በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ ሆኖም ለአገር ብርሃንን፣ ለሕዝብ ተስፋን፣ ለቀጣናውም የትብብር ዕድልን ይዞ ቆሟል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ ተሰልፈው ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአገርን ገጽታ ቀይረዋል። ስንዴን ከውጭ በማስገባት ትታወቅ የነበረች አገር፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ራሷን ወደ መቻል መንገድ ገብታለች። በኮሪደር ልማት የአዲስ አበባና የሌሎች ከተሞች ገጽታ ተለውጧል፤ ሕዝብም በንጹህ፣ ውብና ለኑሮ ምቹ አካባቢ የመኖር መብቱን እያጣጣመ ነው። በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ለመገንባትና ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተጀመሩ ርምጃዎችም የአገሪቱን የነገ ከፍታ ያበስራሉ። ሕዝብ አብላጫ ድምጹን የሰጠው ይህንን የስኬት ጉዞ አይቶ፣ ከዚህ የበለጠ ያደርሰናል ብሎ በማመን ነው። ስለዚህ የዛሬው ድምጽ ለፓርቲው ከዕውቅና ባለፈ፣ የጀመራቸውን ሥራዎች ወደ ከፍታ ለማድረስ የሚጓዝበት ስንቅ ነው። የተገኙት ድሎች የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆኑ ለቀጣይ ታላቅ ርምጃ የተቀመጡ መሠረቶች ናቸው። ፓርቲውም ይህንን የድል ጉዞ ሳይቋረጥ የማስቀጠል፣ ከፍ የማድረግና የማላቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ዛሬ የሚመሰረተው የመደመር መንግሥት ሕዝብ በድምጹ በሰጠው ይሁንታ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ሥራዎች ሳይቆራረጡ እንዲቀጥሉ፣ ግልጽ የአምስት ዓመት የአመራር አቅጣጫም እንዲኖር ያስችላል። ከሕዝብ፣ አደራ የተረከበው መንግሥት ሕዝቡ ያስቀመጠውን አደራ ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚለውጥበት ጊዜ ይመጣል። በኑሮ ማሻሻያ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በፍትሐዊ ተጠቃሚነት የተገቡ ቃሎች ወደ ተግባር ይለወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሕዝብ እምነቱን አብላጫ ድምጽ በመስጠት ያረጋገጠው ፓርቲም ይህንን እምነት በውጤት የመመለስ ድርብ ኃላፊነት አለበት። ጠንካራ ሀገር ከመገንባት አኳያም፣ ሕዝባዊ ይሁንታ ያለው መንግሥት፣ ጠንካራ ተቋማትና ንቁ ዜጋ ሲገናኙ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ይገነባል። ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ መርጧል፤ አሁን ደግሞ ምርጫው የዘራውን ተስፋ በሥራ የማጽናት ኃላፊነት ብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት ነው። ያለፉት ድሎች ለቀጣዮቹ ስኬቶች መወጣጫ ደረጃ ሆነው፣ ሕዝብና መንግሥት በመተማመን ላይ የተመሠረተ የጋራ ጉዞ ሲያደርጉ፣ ኢትዮጵያ ታላቅ ሕዝቧን እና ታላቅ ርዕይዋን የሚመጥን ከፍታ ላይ ትደርሳለች።
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 112
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 98
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ አየር ኃይል - የማድረግ አቅም ዳርቻ
Oct 5, 2026 83
በብዙ መውጣትና መውረድ፣ ውስጥ አልፏል። በውድ መስዋዕትነት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አስከብሯል። በሁለት አሳዛኝና አስገራሚ አጋጣሚዎች የመፍረስ አደጋ ተደቅኖበት ነበር፤ አሳዛኙ በጣሊያን ወረራ ወቅት ወድሞ ከጥቅም ውጭ መሆኑ ነው። ሁለተኛውና አስገራሚው ነገር ደግሞ በ1983 ዓ.ም መንበረ ስልጣኑን በሀይል የተቆጣጠረው ጸረ ኢትዮጵያው ሕወሓት የባህር ኃይሉን ሙሉ በሙሉ በመበታተን የአየር ኃይሉን በማዳከም ለሀገሩ ያለውን ጥላቻ የገለጠበት የታሪክ አጋጣሚ ነው። የመፍረስ አደጋዎችን በማለፍ የማንሰራራት ዘመንን ዋጅቷል። የቀጣናው የሰላም ዘብ፣ የደህንነት ዋስትና መሆኑን በጀግንነት እያሳየ ድፍን 90 ዓመታትን ተሻግሯል፤ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር ኃይል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ “ኢሕአዴግ ሀገሪቱን ሲቆጣጠር በጠቅላላ ነው የተበተነው፤ ኢትዮጵያ መልሳ ማግኘት የማትችላቸው ንብረቶች ወደ ጎረቤት ሀገር ተበትነዋል።” ብለዋል። ሕገወጡ ሕወሓት ምድረ በዳ ያደረገው አየር ሀይል ዛሬ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግሮ ድል የማብሰር ምልክት ሆኗል። የጠንካራና አይበገሬ ተቋማት፣ የሉዓላዊነት ዋስትና የድል አድራጊነት አውራ ሆኗል። “ሰማዩ የእኛ ነው” በሚል መሪ ሀሳቡ እንደ ስሙ እያደረ ነው። የቀጣናው አስተማማኝ የሰላም ዘብ ነው የኢትዮጵያ አየር ኃይል። የአውሮፕላን አብራሪዎችና ቴክኒሻኖችን ማሰልጠኛ ማዕከል፣ ለሌሎች የሚተርፍ የጥገና አቅም ገንብቷል፤ መለዋወጫዎችን ያመርታል። ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የታጠቁ የሰማይ ላይ ንጉሶችን አፍርቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሰው ልጅ የማድረግ አቅምና ብቃት የታየበት፣ የዳበረ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ የዋለበት የቴክኖሎጂም፣ የምርምርም፣ የውጊያም፣ የሰላምም ተቋም ሆኗል። ነገን መዋጀት፣ ኢትዮጵያን ማፅናትና ማስቀጠል የግብሩ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ልጆች የጀመሩት ለውጥ በትናንሽ ሙከራዎች ሸብረክ የማይል በጽኑ መሰረተ ላይ የመገንባቱ ማረጋገጫ ማህተም ጭምር። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በ1928 ዓ.ም ሲቋቋም የመጀመሪየው አዛዣ ሻለቃ ሚሽካ ባቢቼፍ ነበሩ። የመጀመሪያዋ የጦር አውሮፕላን ደግሞ "ንስረ ተፈሪ" /Nessre Tafari/ የተሰኘችው ባለሁለት ክንፍ የፈረንሳይ ስሪት Potez 25-ናት። ኢትዮጵያ ከብዙ የዓለም ሀገራት በፊት ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ባንክና መሰል ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ስትጀምር የኢፌዴሪ አየር ኃይል አንዱ ነበር። የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት አርማ፣ የሉዓላዊነትና የደህንነት ማረጋገጫ ማህተም መሆኑን በሰማይ ላይ ነግሦ በተግባር አረጋግጧል፤ እያረጋገጠም ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ የአየር ክልል በአስተማማኝነት በመጠበቅ የሰማይ ንግሥናውን ተቆናጧል። የኢትዮጵያ የታላቅነት ማንፀሪያ ሆኖም ያገለግላል። ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ “90 ዓመታትን በተሻገረው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ታሪክ ውስጥ የሀገርን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል፤ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል በደምና በአጥንታቸው ሀገር ያጸኑ ጀግኖቻችንን አፍርቷል” ብለዋል። የለውጡ መንግሥት አየር ኃይሉን ከመፍረስ ታድጎ በውጊያ መሰረተ ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታና ትጥቅ በማሟላት ኢትዮጵያን የሚመጥን ተቋም ገንብቷል። የኢፌዴሪ አየር ኃይልን በሁሉም ረገድ በማዘመንና ሁለንተናዊ ብቃቱን በማሳደግ የመከላከያ ሠራዊቱ ጠንካራ ክንድ፣ የሉዓላዊነት ዘብ፣ የኢትዮጵያውያን ኩራት ማድረግ ተችሏል። አየር ኃይል ከ1969 – 1970 ዓ.ም በተካሄደው የእናት አገር ጥሪ /የኦጋዴን ጦርነት/ የእብሪተኛውን የዚያድ ባሬ ወራሪ ጦር ግብዓተ መሬት በማፋጠን የፈጸመው ጀብዱ በዓለም ወታደራዊ ኢላማና ስኬት ታሪክ እጅግ አስደናቂ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። እንደነ ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ባሉ ወደር የለሽ የአየር ላይ ቀዛፊዎች በቁጥር የላቀና ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶችን የታጠቀው የሶማሊያ አየር ኃይል ላይ የአየር የበላይነት በመውሰድ መቅሰፍት አውርደውበታል። ይህ ኢትዮጵያውያን በኩራት የሚናገሩለት ገናና ታሪክ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል እንደ ታሪኩ ማደር የሚያስችለው ቅኝት ውስጥ ገብቷል፤ በጠላቶች የተቃጣበትን የመፍረስ አደጋ በጣጥሶ ወጥቷል። የአባቶቹ ልጅ መሆኑን አሳይቷል። ዛሬ እጅግ በረቀቁና በቴክኖሎጂ በዳበሩ የጦር ጄቶችና ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅሙን ገንብቷል። በጠላት ላይ ኢላማውን የጠበቀ ከፍተኛ አደጋ መፍጠር የሚችሉ ምስጉን ባለሙያዎችን አፍርቷል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው እንደሚሉት፤ የአየር ኃይል የጥገና፣ የማምረትና የቴክኖሎጂ አቅም በአፍሪካውያን ጭምር የተመሰከረለት አስደናቂ ለውጥ ውጤት አምጥቷል። በአፍሪካ ካሉ ትልልቅ የአቬዬሽን ኢንዱስትሪዎች አንዱ ሆኗል፤ በዕውቀት በቴክኖሎጂና ራስን በመቻል አቅም ልቆ ተገኝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል “የኢትዮጵያን አንድነትና ነጻነት ሊገዳደሩ የሚፈልጉ ሀይሎች አቅሟን አይተው እንዲገቱ፤ ከሞከሩም እንዲቀጡ የማድረግ ሀገራዊ አቅም ገንብቷል። ጥቁር አንበሳ ማሸነፍ እንጂ መሸነፍ አያውቅም፤ እናም አትሞክሩት፤ ሰላምን ማጽናት እንፈልጋለን ደፍሮ የሚሞክር ካለ ግን ግብዓተ መሬቱን እናፋጥናለን።” በማለት ኢትዮጵያ ግዙፍ ተቋም መገንባቷን አብስረዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ላይ የተደረገው ስር ነቀል ሪፎርም የኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥገና፣ የሰው አልባ አውሮፕላን ምርት፣ የመለዋወጫና ሌሎች የማምረቻ ፋብሪካዎች አቅም በፍጥነት አድጓል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል የማድረግ አቅም ጨምሯል፤ የትብብር ስምምነት በመፈራረም በጋራ ለመስራት የሚፈልጉ ሀገሮችም ተበራክተዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፤ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስከብር አየር ኃይል መገንባት እንደሚቻል የተረዳነው፣ ዐይናችንን የገለጥነው፣ ወደ ተግባር የገባነው ከሪፎርሙ በኋላ ነው ይላሉ። ሪፎርሙ ቴክኖሎጂ እንዲታጠቅና እንዲያለማ፣ ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀም በማድረግ ብዙ ሀብት እንዲያፈራ የማይገለጹ አቅሞችን እንዲገነባ ማድረጉንም አንስተዋል። “የማምረት አቅማችን ከአምናው ዘንድሮ ጨምሯል” የሚሉት ምክትል አዛዡ፤ በቀን ከ20 ያልበለጡ ምርቶችን ከማምረት አሁን 350 ተሸጋግሯል፤ አንዳንድ መለዋወጫዎችን በቀን እስከ 3 ሺህ 500 የማምረት አቅም ገንብቷል፤ በኢትዮጵያ አየር ኃይል እርካታ የሚባል ነገር የለም፤ አይፈቀድምም። በድል ላይ ድል መጎናጸፍ፤ የኢትዮጵያን ሀያልነት ማወጅ የግቡ መዳረሻ ነው። ስሙ በተነሳ ቁጥር ከኢትዮጵያ ውድቀት ጋር የሚቆራኘው ሕገ ወጡ ሕወሓት፤ ኢትዮጵያ ባህር በር አልቦ፣ ዜጎቿን የመልክዓ ምድር እስረኛ አድርጓል። ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አድማስ ተሻጋሪ ነው፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ አይወሰንም፤ ህንድ ውቅያኖስ ይደርሳል፤ መሰረታዊ፣ ታሪካዊና ህጋዊ የባህር በር ባለቤትነቷ ምላሽ ማግኘት አለበት። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚመጠን አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን መትጋት ደግሞ የአየር ኃይል አድማስ ተሻጋሪ የዘወትር ግብር ነው። ኢትዮጵያን የመታደግ፣ ኢትዮጵያን የማኩራት፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት ተቋማዊ አርማው ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር አስቀጥሏል። ኢትዮጵያ “ማህጸን ለምለም ናት” የሚለውን በገቢር እየኖረ ሰማዩን እያሰሰ አውሮፕላኑ እየተንደቀደቀ … የኢትዮጵያውያንን ልብ እያሞቀ … ቀጥሏል፤ ንሥርነቱን በተግባር እየገለጠ ወዳጆቹን እያስደመመ፣ ጠላቶቹን እያኮሰመነ ይቀጥላል።  
ከፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት
Oct 5, 2026 82
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፡- ከፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ ኢትዮጵያ ረጅም የፖለቲካ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ ይህ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች በፖለቲካዊ መገለል፣ በአለመተማመን፣ በአለመግባባትና በግጭት የተቆራረጠ መንገድ አልፏል። የፖለቲካ ስርዓቱ ውስጥ የሀገሪቱ ህዝቦች፣ ክልሎችና የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች በእኩልነት እንዲሳተፉ የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠርም ብዙ ፈተናዎች አልፈዋል። ከብዙ ልፋት በኋላ በሀገሪቷ የመጣው ለውጥ የተሻለ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት፣ ምህዳሩን በማስፋትና ልዩነቶችን በሃሳብ ክርክር ለመፍታት የሚያስችል አዲስ የፖለቲካ አውድ ፈጥሯል። ይህም ከቆየው የፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት የሚወስድ መልካም እድሎችን ይዞ የመጣ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የፖለቲካ ተሳትፎ በመስፋቱ የፖለቲካ አውዱ የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት ማድረግ አስችሏል። የሀገር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ፣ የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት እንዲሆን የሚያስችል የፖለቲካ አውድ መፈጠር አስችሏል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተወሰኑ ክልሎች “አጋር” እየተባሉ በሀገራቸው ጉዳይ እንዳይወስኑ እና እኩል ተሳታፊ እንዳይሆኑ ተገድበው ቆይተዋል። አሁን ላይ ግን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል ተሳትፎና ድምጽ እንዲኖራቸው ተደርጓል። በዴሞክራሲ ሥርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚኖራቸው ሚና መንግሥትን መቃወም ብቻ አይደለም። አማራጭ ፖሊሲዎችን ማቅረብ፣ ለህዝብ የተሻለ አማራጭ ማቅረብና በሀገር ጉዳይ ላይ ገንቢ ሚና መጫወትም ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ረገድ ባለፉት ጥቂት አመታት በሃሳብ የበላይነት የሚመራና ክርክር የሚደረግበት እድል መኖሩ በተግባር ታይቷል። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም በመንግሥት አመራር ውስጥ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው ተቋማትን የመምራትና ህዝብን የማገልገል ዕድል ማግኘት ችለዋል። በአንድ ሀገር ውስጥ የፓርቲዎች እንዲሁም የመንግስት መምጣትና መሄድ የማይቀርና የተለመደ ነው፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ግን ከግለሰቦችና ከፓርቲዎች በላይ ቆመው ለህግ፣ ለፍትሕና ለህዝብ ጥቅም መስራት አለባቸው። በመሆኑም በኢትዮጵያ መሰረቶች በመጠናከራቸው የዴሞክራሲ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ የታቸለበት እድል ተፈጥሯል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እድገትና የሀገረ መንግስት ግንባታ በአንድ ፓርቲ ወይም በአንድ መንግሥት ብቻ የሚጠናቀቅ አይደለም። የሁሉም ዜጎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የክልሎች፣ የዴሞክራሲ ተቋማትና የሲቪክ ማህበራት የጋራ አጀንዳ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል።  
የኢትዮጵያ የፅናት ጉዞ እና የካይሮ የጥፋት እጆች
Oct 4, 2026 334
ታሪክ ደጋግሞ እንደሚያስተምረን፤ የኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት እና በቀጣናው ላይ የሚኖራት አዎንታዊ ተፅዕኖ ማደግ በካይሮ የፖለቲካ ሊሂቃን ዘንድ እንደ ስጋት ሲቆጠር ኖሯል።የዓባይን ውሃ በብቸኝነት የመቆጣጠር የቆየ ስትራቴጂ የምትከተለው ግብፅ፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም እና በኢኮኖሚ ጠንካራ ሀገር ሆና እንዳትወጣ ለማድረግ ያልፈነቀለችው ድንጋይ፣ ያልተጠቀመችበት የጂኦፖለቲካዊ ሴራ አልነበረም። ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያን በውስጥ ባንዳዎች እና ቅጥረኞች በፋይናንስና በመሳሪያ በመደገፍ ሀገሪቱን ለማዳከም የተሄደባቸው መንገዶች በሙሉ በኢትዮጵያውያን አይበገሬነት እና በሉዓላዊነት ላይ ባላቸው የማይናወጥ ጽናት ምክንያት መና ቀርተዋል። በቅርቡ ደግሞ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ እና ወደ ሥራ መግባት፣ ያንን የቆየውን የቅኝ ግዛት ውል እና "እኔ ብቻ ልጠቀም" የሚለውን አግላይ እሳቤ ላይመለስ አክሽፎታል። በቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ወይም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢትዮጵያን ማንበርከክ ያልቻለችው ካይሮ፣ አሁን ላይ የስልት ለውጥ በማድረግ የውክልና ጦርነት ስትራቴጂን በሰፊው ማካሄድ ጀምራለች። ለዚህ እኩይ አላማዋ ደግሞ በአስመራ የሚገኘውን የሻዕቢያ አስተዳደር እንደ ፈጻሚ አካል መጠቀም ከጀመረች ሰነባብታለች። ሁለቱን ወገኖች ያገናኛቸው የጋራ ፍላጎት ልማት ወይም የህዝቦች እድገት ሳይሆን፤ "ኢትዮጵያን የማዳከም፣ የማተራመስ እና በቀጣናው አቅም አልባ የማድረግ" እኩይ ግብ ነው። የዚህ ያልተቀደሰ ጋብቻ ዋና ስትራቴጂ፡ኢትዮጵያ ሁልጊዜም በውስጥ ግጭትና አለመረጋጋት እንድትጠመድ ማድረግ። ሀገሪቱ ትኩረቷን እና ሀብቷን ወደ ጸጥታ ማስከበር እንድታዞር በማድረግ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን አቅም ማዳከም።የሀገሪቱን የመከላከል አቅም ለመበታተን በተለያዩ አቅጣጫዎች የጸጥታ ስጋት መፍጠር ናቸው። በአሁኑ ወቅት ይህ ጣልቃ ገብነት በግልጽ በሚታይ ደረጃ ላይ ደርሷል። የኤርትራ ሠራዊት የውስጥ ታጣቂዎችን በመደገፍ፣ በቀጥታ በጦርነት በመሳተፍ የጸጥታ ስጋት በመፍጠር እና የፌደራል መንግሥቱን ለማዳከም እየሰራ ይገኛል። ይህም ግብፅ በስተጀርባ ሆና በገንዘብ፣ በመሳሪያ እና በዲፕሎማሲ የምታግዘው ግልጽ የውክልና ጦርነት አካል ነው። ነገር ግን ታለቋ ኢትዮጵያ የሉዓላዊነቷን ወሰን እና የብሔራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውንም አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ሴራዎች በዝምታ እንደማትመለከት በተግባር እያሳየች ትገኛለች። የውስጥ ሰላሟን ከመጠበቅ ጎን ለጎን፣ የውጭ ኃይላትን ድብቅ ሴራ የሚያከሽፉ ጠንካራ የዲፕሎማሲ እና የመከላከል እርምጃዎችንም ወስዳለች። በብሔራዊ ደህንነት ላይ አደጋ በሚደቅኑ ተግባራት ላይ በቀጥታ የተሳተፉ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከሀገር እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን፤ በአስመራ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተደርጓል።በተመሳሳይ ሁኔታ ከግብፅ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና ድብቅ ጣልቃ ገብነት በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ሀገር ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ጠንካራ መልዕክት አዘል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። ከዲፕሎማሲያዊ ውሳኔዎቹ ባሻገር፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የገቡትን እና በካይሮ እና በአስመራ የተላኩትን የሻዕቢያ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም የውስጥ ቅጥረኞችን የማጽዳት ስራንም በተሳካ ሁኔታ እያከናወነች ትገኛለች። ኢትዮጵያን በታሪክ አጋጣሚ ሁሉ በቀጥታ ወታደራዊ ወራራ ለመፈጸም ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጋ ያልተሳካላት ግብጽ አስመራን እየላከች የሄደችበት የሴራ ቀመር ዛሬ ላይ መንቀሳቀስ የሚችል አይደለም። ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ አይደለችም። የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ የውስጥ ድክመቷን ተደግፎ የፈለጉትን ሴራ የሚያስኬዱባት ደካማ ሀገር አይደለችም። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የናይልን የውሃ ፖለቲካ የበላይነት በቋሚነት ቀይሮታል። ሀገሪቱ በቀጣናው የኢነርጂ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ሆና ብቅ ብላለች።የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊ የውጊያና የቴክኖሎጂ አቅም በመታጠቅ የሀገርን ሉዓላዊነት በጽኑ መደብ ላይ ገንብቷል፤ ማንኛውንም የውስጥና የውጭ ስጋት በከፍተኛ አቅም የመመከት፤ ሲያስፈልግም የማጥቃት ሙሉ ብቃት አለው። በመሆኑም ካይሮ እና አስመራ በጋራ የሸረቡት የማተራመስና የውክልና ጦርነት ሴራ የዛሬዋን ኢትዮጵያ አዲስ እውነታና ቁርጠኝነት ባላገናዘበ ስሁት ስልት ላይ የተመሠረተ ነው። ቀደም ሲል በታሪክ አጋጣሚዎች በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች የተጎነጎኑ ጥምረቶች ሁሉ በኢትዮጵያውያን አይበገሬነት መና እንደቀሩት ሁሉ፣ አሁንም በካይሮ ታቅዶ በአስመራ የሚፈጸመው እኩይ ድራማ የታሰበበት ግብ ሳይደርስ በጽኑ የኢትዮጵያ ክንድ የሚከሽፍ እና የትም የማይደርስ መሆኑ የማይቀር ሀቅ ነው።
ለአፍሪካ ተምሳሌት ከሆነ ምርጫ እስከ መንግሥት ምሥረታ
Oct 4, 2026 415
✍️ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ የአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በግጭትና በተቋማዊ ድክመት የተፈተነ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ምርጫን በሰላም ማካሄድ፣ የሕዝብን ድምፅ ማክበር፣ ውጤትን በተቋማዊ መንገድ ማስተናገድ እና ወደ ሕጋዊ መንግሥት ምሥረታ መሸጋገር እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዚህ ረገድ ለአፍሪካ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ ጠንካራና ገለልተኛ ተቋማት መፍጠሯን፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነጻነት ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መምረጣቸውን፣ በዚህም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የቋመጡ አካላትን ሴራ ማክሸፋቸውን አሳይቷል። ኢትዮጵያ ነገ የምትጀምረው አዲስ ምእራፍ ከሕዝብ ድምፅ ወደ ሥልጣን፣ ከሥልጣን ወደ አደራ፣ ከአደራ ወደ ተግባር የሚወስድ የዴሞክራሲ ሂደት ነው። ከእያንዳንዱ ድምፅ ጀርባ አንድ ዜጋ አለ፤ ከእያንዳንዱ ዜጋ ጀርባ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ ሕልም፣ አንድ ተስፋ እና አንድ የነገ ርዕይ አለ። ሕዝቡ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ከ52 ሺህ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰልፎ ድምፁን ሲሰጥ በካርዱ ላይ የሰፈረውን የመረጠውን ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገሩ የሚያስበውን ተስፋ ነው። ኢትዮጵያውያን መንግሥታቸውን መርጠዋል። አዲሱ መንግሥት ደግሞ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ነገ በይፋ ሥራውን ይጀምራል።ኢትዮጵያውያን ጓጉተው ሲጠብቁት የነበረው ቀን ደርሷል።ጨበክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት ምስረታ ተካሂዷል። በነገው ዕለት ደግሞ ነገ አዲሱ የፓርላማ የሥራ ዘመን መክፈቻና የመንግሥት ምስረታ ይካሄዳል። የዚህ መንግስት ምስረታ ጉዞ የጀመረው ግንቦት 24 በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው። ሕዝብ ድምፁን ሲሰጥ ሥልጣንን ብቻ አይሰጥም፤ አደራ ይሰጣል። መንግሥት ሲመሠረትም የሚያገኘው የሥልጣን ወንበር ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እምነትን የሚሸከም ከባድ ኃላፊነት ነው። ኢትዮጵያ በነገው ዕለት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝብ በድምፁ ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ መንግሥት ምሥረታ በማሸጋገር አዲስ ምዕራፍ ትጀምራለች። ይህም ኢትዮጵያ በሰላማዊ፣ በሕጋዊና በተቋማዊ መንገድ የመንግሥትን ሥልጣን የምታሸጋግር ሀገር መሆኗን የምታሳይበት ታሪካዊ ክስተት ነው። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግርና የልዩነት አፈታት ሁልጊዜ በሰላማዊ የሀሳብ የበላይነትና በዴሞክራሲያዊ ፉክክር አልተመራም። የኃይል አማራጭ ብዙ ጊዜ ተሞክሯል። ይህም ብዙ ችግር ወልዷል። ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግርን አባክኗል። ሀገርን በአብዮት ፍዳ ደፍቋታል።ዛሬ ግን በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ መሠረት ላይ የዴሞክራሲ ድልድይ ፈጥሮ የተካሄደው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይህን የቆየ የፖለቲካ መጥፎ ልማድ በመሻገር ሀገሪቱ ወደ ሰለጠነ የሀሳብ ፖለቲካና ወደ ዘመናዊ የመንግሥት ግንባታ እየተሻገረች መሆኗን አሳይቷል። የዚህ ለውጥ ትልቁ መሠረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተሳትፈዋል። ምርጫው እንዳይሳካ በጠላት የተሞከሩ ከባድ ፈተናዎችን አልፈው፣ ማስፈራሪያና እንግልትን በጽናት ተሻግረው ከማለዳ እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው፣ ቁርና ሐሩር ሳይበግራቸው ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መርጠዋል። ሕዝቡ ለመረጠው መንግሥት የሰጠው ባዶ ካርድ ሳይሆን የሚፈጸም አደራም ነው። ኢትዮጵያ ነገ የምትጀምረው አዲስ ምእራፍ ከሕዝብ ድምፅ ወደ ሥልጣን፣ ከሥልጣን ወደ አደራ፣ ከአደራ ወደ ተግባር የሚወስድ የዴሞክራሲ ሂደት ነው። ከእያንዳንዱ ድምፅ ጀርባ አንድ ዜጋ አለ፤ ከእያንዳንዱ ዜጋ ጀርባ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ ሕልም፣ አንድ ተስፋ እና አንድ የነገ ርዕይ አለ።ሕዝቡ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ከ52 ሺህ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰልፎ ድምፁን ሲሰጥ በካርዱ ላይ የሰፈረውን የመረጠውን ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገሩ የሚያስበውን ተስፋ ነው። “የትኛው ፖሊሲ የተሻለ ነው? የትኛውን አቅጣጫ እመርጣለሁ? ምን ዓይነት መንግሥት እፈልጋለሁ? ለልጆቼ ምን ዓይነት ኢትዮጵያን አስረክባለሁ?” የሚሉ ጥያቄዎችን አስቦ ነው ድምፅ የሰጠው። በዚህ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች መሳተፋቸውም ይህንን የሕዝብ ምርጫ ለመወሰን ሰፊ የፖለቲካ አማራጭ ፈጥሯል። ስለዚህ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊነት በአንድ ፓርቲ ድል ብቻ የሚጠቃለል አይደለም። የዴሞክራሲ ሂደቱ ራሱ አሸናፊ ሆኗል። ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግር ሁልጊዜ በሰላማዊ የሀሳብ ውድድር የተመራ አልነበረም። የኃይል አማራጭ ብዙ ጊዜ በዴሞክራሲ የሚመራ ፖለቲካ ውሳኔን ተክቷል። ሰባተኛው ምርጫ ግን አዲስ መንገድ አሳይቷል። ሥልጣን በኃይል ሳይሆን በሕዝብ ፈቃድና ምርጫ እንደሚመጣ አረጋግጧል። ይህም ለአፍሪካ ቀንድና ለመላው አፍሪካ ምሳሌ ሆኗል። የአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በግጭትና በተቋማዊ ድክመት የተፈተነ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ምርጫን በሰላም ማካሄድ፣ የሕዝብን ድምፅ ማክበር፣ ውጤትን በተቋማዊ መንገድ ማስተናገድ እና ወደ ሕጋዊ መንግሥት ምሥረታ መሸጋገር እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዚህ ረገድ ለአፍሪካ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ ጠንካራና ገለልተኛ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ መፍጠሯን፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነጻነት ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መምረጣቸውን፣ በዚህም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የቋመጡ አካላትን ሴራ ማክሸፋቸውን አሳይቷል። ምርጫው እንዳይሳካ ብዙ የሴራ ድር በጠላትና በባንዳ ተተብትቦ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ “ምርጫው ራሱ የጠላት ኢላማ ነበር” ምክንያቱም የምርጫው መሳካት የሚያሳፍራቸው ብዙ የስሁት መንገደኞች ነበሩ፤ ከግጭት የሚያተርፉ የደም ነጋዴዎችም ነበሩ፣ በኃይል ሥልጣን መናጠቅ የሚመኙ ከንቱ ሕልመኞችም ነበሩ።ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ለፕሮፓጋንዳም ሆነ በጠላት ለተደቀነባቸው አፈሙዝ ሳይበገሩ ድምፅ ሰጥተዋል። ከማለዳ እስከ እኩለ ሌሊት በጽናት ተሰልፈው ሀገርን ለማሻገር ይበጀናል ያሉትን መርጠዋል። በዚህም ጠላት ሲያፍር ኢትዮጵያ ግን አሸንፋለች። ይህ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የፖለቲካ ባህል ላይ ትልቅ ለውጥ ነው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሌላኛው ድል የሚለካው በውጤቱ ብቻ አይደለም፤ በፖለቲካዊ ተሳትፎ ስፋትና በአካታች ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ባሳረፈው ጉልህ አሻራም ጭምር ነው።በዚህ ምርጫ ከ42 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች በምርጫ ሜዳው ተሳትፈዋል። ይህም የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ለተለያዩ ሐሳቦች፣ አማራጮችና የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች በር የከፈተ መሆኑን ያሳያል። የዚህ ምርጫ ልዩ ገጽታ ግን በተወዳዳሪዎቹ ቁጥር ብቻ አይወሰንም። ከዚያ በላይ፣ ገዥው ፓርቲ ለተፎካካሪዎች የበለጠ የመወዳደሪያ ዕድል እንዲፈጠር ያደረገው ውሳኔ በራሱ ግዙፍ የፖለቲካ ትርጉም አለው። ብልፅግና ፓርቲ 15 በመቶ የምክር ቤት ወንበሮችን በሚያስገኙ የምርጫ ክልሎች ላይ እንዳይወዳደር መወሰኑ፣ ለሌሎች ፓርቲዎች የተለየ የፉክክር ሜዳ የፈጠረ እርምጃ ነበር። በሌላ አገላለጽ፣ ገዥው ፓርቲ የራሱን የምርጫ ዕድል በመገደብ ሌሎች የፖለቲካ ድምፆች ወደ ምክር ቤቱ እንዲገቡ ተጨማሪ ቦታ ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ውሳኔ ሲያብራሩ፣ ዓላማው ብዙ ድምፆች ወደ ፓርላማ እንዲገቡና አካታች ዴሞክራሲ እንዲጠናከር ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። በእርግጥም ይህ አንዱ የዴሞክራሲ ጥንካሬ መለኪያ ነው። ይህ ውሳኔ በምርጫ ወቅት የተወዳዳሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ የተደረገ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ፓርላማ የተለያዩ የሕዝብ ሐሳቦች የሚወከሉበት የበለጠ ውክልና ያለው መድረክ ለማድረግ የተወሰደ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው። ምርጫው የአንድን ፓርቲ ድል ብቻ ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ ሂደት ብዝሃ ድምፆች እንዲሰሙ ዕድል የፈጠረ ነው። በዚህ ረገድ የሰባተኛው ምርጫ ዋና ትርጉም ከምርጫ ውጤቱ በላይ ነው። 15 በመቶውን የምርጫ ሜዳ ለሌሎች ተወዳዳሪዎች መተው ደግሞ የአካታችነት መርህን በተግባር ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ሆኗል። ይህ በየትኛውም አፍሪካ ሀገር ያልተደረገ ነው። ብዙ ድምፆች ወደ ፓርላማ ሲገቡ፣ ዴሞክራሲም የበለጠ ይሰፋል። ይህም የሰባተኛው ምርጫ ከውጤቱ በላይ የሚታይበት ሌላኛው ድል ነው። አዲስ የሚመሠረተው መንግሥትም የበርካታ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የሚሳተፉበት አካታች መንግሥት ነው። የምርጫ ድል የመንግሥት አደራ ነው። የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ድምፅ አግኝቶ መንግሥት የመመሥረት ሕጋዊ መብት አግኝቷል። ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በሆነው የ501 የምርጫ ክልሎች ውጤት መሠረትም 438 የፌዴራል ፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፏል። ግን የምርጫ ድል የምክር ቤት ወንበርን በማሸነፍ ቢጀምርም በዚህ አያበቃም። ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር መፈጸም ቅቡልነትን ያጸናል። ይህም ነገ የሚመሠረተው መንግሥት የሚጠብቀው ትልቁ ኃላፊነት ነው። ሕዝቡ መርጧል። አሁን ደግሞ አዲሱ መንግሥት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ነገ በይፋ ሥራውን ይጀምራል። በመንግሥት ምሥረታው ከመራጩ ወደ ተመራጩ የሚሸጋገረው የአደራ ኪዳንም ይህ ነው። ቅቡልነት ያለው ሕጋዊ መንግሥት በምርጫ ይመሠረታል። የሚጸናው ግን በሥራ ውጤቱ ነው። የጠንካራ መንግሥትነት መለያውም በሕዝብ የተጣለበትን እምነትና አደራ የሚወጣ፣ ጠንካራ ተቋማትን የገነባ፣ ሕግን ያስከበረ፣ ተፎካካሪ ሐሳቦች የሚደመጡበት እና የሕዝብን ጥያቄ በተጨባጭ ውጤት የሚመልስ መንግሥት ሲሆን ነው። ስለዚህ ነገ የሚመሠረተው መንግሥት በምርጫ ማኒፌስቶው የገባውን ቃልና በሕዝብ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት የአምሥት ዓመት ጉዞውን በተግባር የሚጀምር መሆን አለበት። ይህ እንደሚሆን ደግሞ ብዙ እርሾዎች አሉት። አሁን የተመረጠው መንግሥት ባለፉት አምሥት ዓመታት ለሕዝብ ቃል ገብቶ ባሳካቸው ድሎች ዳግም ዕድል የተሰጠው ነው። በምግብ ራስን የመቻል ግብን በማሳካት ተረጅነትን አስቀርቷል። ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሕዝብ ቃል በገባው መሠረት አሳክቷል። ሕዝብን ያማረረውን የሌብነትና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል የመሶብ አገልግሎትን በመላ ሀገሪቱ አስጀምሯል። የኑሮ ውድነትን ለማቃለልም ምርትና ምርታማነትን በብዙ እጥፍ በማሳደግ እና የተበላሸ የገበያ ሰንሰለትን በማስተካከል ወሳኝ ለውጥ አምጥቷል። ታላቋን ኢትዮጵያን የሚመጥኑ የክብርና የሉዓላዊነቷ ዘብ የሆኑ የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን ገንብቷል። በታላቅ ርዕይ በመመራትም ኢትዮጵያን ከኩስመና የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ወደ ተደማጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከፍታ አሸጋግሯታል። በቱሪዝም ልማት የኢትዮጵያን መልክ አድምቋል።በከተሞች ኮሪደር ልማት ጉስቁልናን አስወግዶ ከተሞችን ውብ የመዝናኛ፣ የሥራና የምቹ መኖሪያ ማዕከል እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ከቀደሟት እኩል እንድትራመድ እያደረገ ይገኛል። ማዕድኗን ገልጣ ወደ ሀብት እንድትቀይር በውጤት የታጀበ መንገድን ጀምሯል። በኢንዱስትሪ ረገድም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ስትራቴጂክ ምርቶች እንድትተካ ጠንካራ መሠረት ጥሏል። የሕዝብን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስም ባለፉት ዓመታት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቤቶች ከመገንባት ባለፈ በሚቀጥሉት አምሥት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተጨማሪ ቤቶችን እንደሚገነባ በማብሰር ወደ ሥራ ገብቷል። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያን ለዘመናት ከኖረችበት ውስብስብ የመከራ አዙሪት ተላቃ ጠንካራ ብሔራዊ መግባባትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲኖራት ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የገባውን ቃል በተግባር ፈጽሟል። አራት ዓመት ተኩል የፈጀ ሀገራዊ ምክክር በማካሄድ በወሳኝ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ኢትዮጵያውያን መግባባት ላይ እንዲደርሱ በማድረግ አዲስ ታሪክ ጽፏል። እንዲሁም ኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገቷን የሚመኙትም ሆኑ የማይመኙትን የምታጓጓ ሀገር እንድትሆን አስችሏል። ይህ ጉዞ በአዲሱ መንግሥት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሰላምን ማጽናት፣ ሕግን ማስከበር፣ ለሌብነት የማይመች አሠራርን ማጠናከር፣ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት፣ የኑሮ ውድነትን መግራት፣ የሕዝብን ኑሮ በተጨባጭ መለወጥ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መሻቶች ማሳካትና ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አካታችነትን ያረጋገጠችና ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች የአፍሪካ ተምሳሌት ሀገርን መገንባት ለአዲሱ መንግሥት ከሕዝብ የተሰጡ አደራዎች ናቸው። መንግሥት አደራውን እንዲወጣ ደግሞ የሕዝብ፣ የግሉ ዘርፍ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ መገናኛ ብዙኃንና የእያንዳንዱ ተቋም የተደመረ ትጋት ወሳኝ ነው። ይህ ከተሳካ፣ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ባህል ብቻ ሳይሆን በሕጋዊ የሥልጣን መሠረት፣ የሕዝብን አደራ በመወጣት፣ በአካታች መንግሥትና በልማት ድል የአፍሪካ ሞዴል መሆኗን በተግባር ታረጋግጣለች።
ልዩ ዘገባዎች
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 112
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 98
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 113
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
Oct 5, 2026 116
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ የዛሬው እለት ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ ታሪኳ ሌላ አዲስ ምዕራፍ የምትከፍትበት ታሪካዊ እለት ነው። በግንቦት ወር የተካሄደው ምርጫ፣ የሕዝብ ድምፅና ውሳኔ ወደ ተጨባጭ የመንግሥት ምስረታ የተሸጋገረበት ወቅት ላይ ይገኛል። የሕዝብ ድምፅ ድምር ውጤት መንግስት የሚመሰረትበትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጽኑ መሰረት የያዘበት አዲስ የታሪክ ምእራፍ ተከፍቷል። የምርጫ ሂደት በራሱ የሚጠናቀቀው የምርጫ ውጤት በመገለጹ ብቻ ባለመሆኑ የሕዝብ ውሳኔ በተቋማት በኩል ተግባራዊ ሲሆንና የሕዝብን የልማትና የአገልግሎት ፍላጎት ማስተናገድና ምላሽ መስጠት የሚችል መንግስት ሲመሰረት ነው። በዚሁ መሰረትም ባሳለፍነው ሳምንት ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ክልሎች የመንግሥት ምስረታ ሂደታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ ገብተዋል። በዛሬው እለት ደግሞ የፌዴራል መንግስት የሚመሰረትበት፤ አዲሱ ፓርላማ ሥራውን በይፋ የሚጀምርበትና አዲስ የፌዴራል መንግሥት የሚመሠረትበት ታሪካዊ እለት ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የተለያዩ የፖለቲካ ሥርዓቶችንና የለውጥ ወቅቶችን አሳልፋለች። በእያንዳንዱ ዘመን የሀገሪቱ ፖለቲካ በሕዝቡ ፍላጎት፣ በሀገራዊ ጥቅምና በዘመኑ ተግዳሮቶች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ የታየበት አጋጣሚ የበዛ ነበር ማለት ይቻላል። የዛሬው የመንግስት ምስረታ ግን ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፃቸውን በነፃነት የሰጡበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ድምር ውጤት ነው። በመሆኑም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የቆዩ የፖለቲካ ስብራቶችን በማከም የኢትዮጵያን የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚተልምና ቀጣይ መዳረሻዋን የሚወስን ይሆናል። ታላቋን ኢትዮጵያ ለመምራት ትልቅ ርዕይ የሰነቀ መንግስት የግድ በመሆኑ እንደ ሀገር የተያዙ እቅዶችን በተደመረ አቅም በማሳካት እድገትና ማንሰራራቷን ማስቀጠል ይገባል። በመሆኑም አዲሱ መንግሥት በምርጫ ወቅት ለህዝብ የገባውን ቃል በማክበር ለተግባራዊነቱ መትጋት ይጠበቅበታል። የህዝብን አደራ በአግባቡ በመወጣት ቃልን በተግባር መፈፀም የግድ ይላል። የዜጎች የሥራ ዕድል፣ የኑሮ ውድነት፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ፣ የልማት ፍላጎት፣ የፍትሕ አገልግሎትና የመንግሥት ተጠያቂነት የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎች ናቸው። ፓርላማውም ሕግ ከማውጣት ባሻገር የመንግሥትን አፈጻጸም መከታተል፣ ተጠያቂነትን ማረጋገጥና የዜጎችን ድምፅ ወደ ፖሊሲና የሕግ አቅጣጫ መቀየር ይጠበቅበታል። በዚህ መልኩ የሚቀጥለው ፓርላማ የዴሞክራሲ ሥርዓቱን በማጠናከር የህዝብ የልማት መሰረቶች ተጠናክረው የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል። የሕዝብ ድምፅ የሥልጣን ምንጭና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት የሚያኖር መሆኑ ይታወቃል። በህዝብ ድምጽ የተሰጠ ሃላፊነት ደግሞ ተጠያቂነት ጭምር ያለበት አደራ ነው። በመሆኑም አዲሱ መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለዘላቂ ሰላምና ልማት፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የህግ የበላይነት መስራት ይጠበቅበታል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108433
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81575
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59865
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57466
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40788
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40715
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40138
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38628
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108433
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81575
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59865
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57466
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ኢትዮጵያ እና ቡና
Sep 30, 2026 325
ኢትዮጵያ- ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የተገኘውና በዓለም ላይ የተስፋፋው ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ በብዛት የሚጠጣ ተፈለጊና ተወዳጅ ምርት በመሆን የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሮት ይገኛል። በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ የአርሶ አደሮች የዓለምን 80 በመቶ ቡና እንደሚያመርቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ ቪትናም እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ አገሮች ሲሆኑ ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በመሆኑም የቡናን ዓለም አቀፍ ግብይትና ተፈላጊነት እንዲሁም የተጠቃሚዎች ብዛት መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 1 የዓለም የቡና ቀን አድርጎ ሰይሞታል። በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያው የዓለም የቡና ቀን እ.ኤ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመከበር ላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቡና ለኢትዮጵያዊያን የገቢ ምንጭ ብሎም የባህል መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ፣ የአብሮነት ማሳያ፣ የማኅበራዊ ትስስርና የውይይት መድረክም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በልዩ ልዩ የጣዕም የሚገለጽና በእጅጉም ተፈላጊ ምርት በመሆኑ በተለይም በአርሶ አደሮች ህይወትና አጠቃላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው። በአንዳንድ አካባቢዎች ቡና ተፈልቶ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ዙር የመጠጣት ልምድም አለ። ምንም እንኳን አጠራራቸውና ከእያንዳንዱ ዙር ጋር የሚያያዙ ትርጓሜዎች በአካባቢው ባህል መሠረት የሚለያይ ቢሆንም የመጀመሪያው “አቦል”፣ ሁለተኛው “ቶና” እንዲሁም ሶስተኛው “በረካ” እየተባለ ይጠራል። የዚህ የቡና ስነ ስርአት ዋነኛ ዓላማ በተደጋጋሚ መጠጣት ሳይሆን በአንድነት መቆየትን፣ ለሌላው ጊዜ መስጠትንና የማኅበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ የባህል ምልክቶች ናቸው። ከቡናው ጋር የሚቀርብ (የቡና ቁርስ) እንደየ ሁኔታው ፋንዲሻ፣ ቆሎ፣ ዳቦ ወይም ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦች የሚቀርቡ ሲሆን እጣን አጭሶ በመመራረቅ የሚጠጣም ይሆናል። በዘመናዊው ዓለም ቡና የንግድ፣ የሥራና የመዝናኛ አካል ሆኗል። በቡና ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎችና በዘመናዊ የቡና ማቅረቢያ ሥፍራዎች ሰዎች ይገናኛሉ። ሆኖም በኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩ ትርጉም ከጣዕምና ከንግድ በላይ ይዘልቃል። ከቤት እስከ ጎረቤት ፤ ከታሪክ እስከ ትውልድ የቆየ ትስስር ያለው የኢትዮጵያን ልዩ መገለጫ ባህል ነው። የቡና ባህላዊ ሥነ ሥርዓትን በማስተዋወቅ እንዲሁም የቡና ታሪክን ከተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮ በማሳየት የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርስ ለዓለም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡና የባህል ይዘቱ እንዳለ ሆኖ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆን ለእድገትና ማንሰራራት ሁነኛ መሰረት እየሆነ ይገኛል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቡና ቀን የቡና ዘርፍ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማድረግ “ቡና የዘላቂ መፍትሄ አካል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።
የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ
Sep 29, 2026 240
ጋምቤላ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ የጋምቤላ ክልል በሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውሃ ሀብት፣ ደኖች፣ የሣር ምድሩና በዱር እንስሳትና ብዝሃ ሕይወት እምቅ ሃብት ያለው መሆኑ ይታወቃል። የአኙዋሃና የማጃንግ የተፈጥሮ ሃብቶች ለልዩ የቱሪዝም መስህቦች ሆነው ይጠቀሳሉ።   በተለይም ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በሰፊ የሳር ሜዳዎች፣ በውሃ አካላትና በተለያዩ የዱር እንስሳት የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ነው። የዱር እንስሳት ጉብኝት፣ የአዕዋፍ እይታ፣ የተፈጥሮ ጉዞና አጠቃላይ የኢኮ-ቱሪዝም ሃብት ፓርኩ የታደለ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወንዞችና ረግረጋማ መሬቶች፣ የደን ሃብት ከሰዎች አኗኗርና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ጋር በማሰናሰል የቱሪዝም ሃብት ማድረግ ተችሏል።   በመሆኑም ጋምቤላ ያለውን የተፈጥሮና የባህል እምቅ ሃብት በዘላቂነት በማልማት፣ የተፈጥሮ ጥበቃን ከቱሪዝም ልማት ጋር በማስተሳሰር ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት አዲስ አቅም መፍጠር እየተቻለ ነው። የባዮስፌር ሪዘርቭ ዋና ዓላማ ተፈጥሮን ከሰው ልጅ የኢኮኖሚና የኑሮ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የዘላቂ ልማትና የምርምር ከባቢን መፍጠር በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና የማጃንግ የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ሊመዘገብ ችሏል። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ምድር ያካለለ ሲሆን በውስጡ በርካታ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ።   በጥብቅ ደኑ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ የዕፅዋት፣ ከ327 የሚልቁ የአእዋፍ፣ ከ86 በላይ አጥቢና ተሳቢ የእንስሳት ዝርያዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ የተፈጥሮ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውና ተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ፣ የዱር እንስሳት ሃብት ኮሪደር እና የዘላቂ ልማት ማዕከል ነው ማለት ይቻላል። የአካባቢው ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር ተስማምቶ በመኖር የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ለትውልድ ጠብቆ በማቆየት ረገድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው።   በ225 ሺህ 490 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የማጃንግ የተፈጥሮ ደንም በውስጡ 550 የዕፅዋት ዝርያዎች፣ 33 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች እንዲሁም 130 የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዝቅተኛና ከፍተኛ መልክአ ምድርን አካቶ የያዘው ጥብቅ የተፈጥሮ ሃብቱ በተለይም ለንብ ማነብና ለፍራፍሬ ልማት እጅግ ተመራጭ አካባቢ ነው። የጋምቤላ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለምግብ ዋስትና እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ ወሳኝ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም