ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በጉራጌ ዞን ተፈጥሮዊ እና ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብ እየዋሉ ነው
Sep 4, 2026 11
ወልቂጤ፣ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-በጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብ እየዋሉ መሆኑን የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ። የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በዞኑ ተሸፍነው የቆዩ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮዊ ቅርሶች በመደመር መንግስት እሳቤ ለምተው ለቱሪስት መስህብነት እየዋሉ ነው። የቱሪስት ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ለማዋል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ለአብነትም በዞኑ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን እንዲሁም መስህቦችን በማስተዋወቅና የገጠር ኮሪደርን ከጀፎረ ባህላዊ እሴት ጋር በማስተሳሰር ለቱሪዝም ልማቱ መዋል መቻሉን ጠቁመዋል። ይህም የቱሪስቶችን ቁጥርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ማገዙን ገልጸዋል። በዚህም በ2018 በጀት ዓመት ዞኑ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች መጎብኘታቸውና ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል። በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ፣ ባህል እና ሃገር በቀል ልማት ማዕከል ዳይሬክተር ፀጋማርያም ዱላ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶችንና እሴቶችን በማልማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳቸውን ለማጉላት የሚደረገውን ጥረት በጥናትና ምርምር እያገዘ ነው። ይህም ቅርሶች የሚጠበቁበት እና ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች በስፋት የሚጎበኙበትን አቅም እያሳደገው መጥቷል ብለዋል። የጉራጌ ባህላዊ እሴት የሆነው ጀፎረን በገጠር ኮሪደር ይበልጥ እንዲለማ መደረጉና መተዋወቁ ቱሪስቶች በብዛት ወደ አካባቢው እንዲመጡ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ አቶ ወንድሙ ብሩ ናቸው። ይህም በቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰዎች የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ከ 10 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው
Sep 4, 2026 28
ባህርዳር ፤ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን ለማቃለል በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ አለው። በአማራ ክልል ለሚያጋጥመው የምርጥ ዘር እጥረት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና የአካባቢውን የስነ-ምህዳር ሁኔታ ያገናዘበ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ትኩረቱን በሀገር ውስጥ የዘር ብዜት ላይ አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ይህ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረው የዘር ብዜት ስራም የውጭ ዘር ጥገኝነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ ለቀጣዩ ምርት ዘመን ገበሬው ጥራት ያለውና በሽታን የመቋቋም አቅሙ የጎለበተ የሰብል ዘር በቅርበትና በወቅቱ እንዲያገኝ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው። በዚህም ከምርምር የወጡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በ2018/2019 የምርት ዘመን በኩታ ገጠም እርሻ ዘር የማባዛት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በምርት ዘመኑ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ እየተባዙ ያሉት የበቆሎ፣ የስንዴ፣ የጤፍ፣ የሩዝ፣ የአኩሪ አተርና ሌሎች የተሻሻሉ የሰብል ዘሮች እንደሆኑም አመልክተዋል። የዘር ብዜት ስራው በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ፣ በግል ዘር አባዥዎች፣ በዩኒየኖች፣ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽንና ሌሎች ዘር አባዢ ድርጅቶች እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በምርት ዘመኑ 267 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ምርጥ ዘር ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ይህም የክልሉን የምርጥ ዘር እጥረት በማቃለል ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኘው የዕድገት ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ በሪሁን እንዳሉት ዩኔየኑ በ360 ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ፣ የበቆሎና ባቄላ ሰብሎች የምርጥ ዘር ብዜት ስራ እያከናወነ ነው። የዘር ብዜት ተግባሩን እያከናወነ ያለው ከ4 ሺህ 100 አርሶ አደሮች ጋር የኮንትራት እርሻ የውል ስምምነት በመፈፀም መሆኑንም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል። ዩኔየኑ ባለፈው የምርት ዘመን አባዝቶ ከሰበሰበው ከሰባት ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተሻለ ይሰበስባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን የእንስሳት ጤናን በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል
Sep 4, 2026 29
ጂንካ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኦሞ ዞን የእንስሳት ዝርያን በማሻሻልና ጤንነታቸውን በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ምንላርገው አዲሱ ለኢዜአ እንዳሉት በዞኑ ካለው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት የሚገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና የእንስሳቱን ጤና መጠበቅ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው። በአሁኑ ወቅትም የእንስሳት ጤናን ለመጠበቅ የእንስሳት ክትባት በዞኑ ባሉ ስድስት ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በዘመቻ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በዘመቻ እየተሰጠ ያለው ክትባት አባሰንጋ፣ አባ ጎርባ፣ ጉርብርብ፣ የዳልጋ ከብቶች የሳንባ በሽታ፣ የዶሮ ፈንግል እንዲሁም የበግና ፍየሎች በሽታን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በግ፣ ፍየል፣ የዳልጋ ከብቶችና ዶሮን ጨምሮ ወደ 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ እንስሳት በተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድን አማካኝነት በዘመቻ ክትባት እንደሚሰጥ ገልጸው፣ ለዘመቻው የተለያዩ ተቋማት አስተዋጾ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል። በዞኑ በናፀማይ ወረዳ እንጨቴ ቀበሌ እየተሰጠ ባለው የእንስሳት ክትባት ተጠቃሚ ከሆኑ አርብቶ አደሮች መካከል ኦይታ ሞርዴ እንዳሉት፣ መንግስት ከብቶቻቸውን በነጻ እንዲያስከትቡ ማመቻቸቱ ጤናቸውን ለመጠበቅ አግዟቸዋል። አቶ ባካ ዋልታ የተባሉ ሌላው የቀበሌው ነዋሪ በበኩላቸው፣ መንግስት ለከብቶቻቸው የሕክምና አገልግሎትን በአቅራቢያቸው ከመስጠት ባለፈ በዘመቻ መከተቡ ከብቶቻቸውን ከጉዳት ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በዞኑ 14 ሚሊዮን የሚጠጉ ከብቶችን በመደበኛና በዘመቻ መልክ ለመከተብ መታቀዱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
ለኢትዮጵያ የቤት ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስምምነት
Sep 4, 2026 62
የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ፈጣን እየሆነ በመምጣቱ እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመሄዱ፣የዜጎችን የቤት ባለቤትነትን ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት አንዱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት የነበረው የቤት አቅርቦት በመንግሥት ትከሻ ላይ ብቻ የወደቀ በመሆኑ፣ ካለው ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ቀርጾ በካቢኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ፖሊሲው የዕድገቱን ፍጥነት እና የከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሥራዎች ለዚህ ሰፊ ራዕይ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታውሰዋል። ይህንኑ ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት አጠቃላይ ዝግጅት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አሁን ላይ አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂንና የረጅም ጊዜ የቤት ብድር ሥርዓትን በማስተዋወቅ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲሱ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ በካቢኔ መጽደቁንና በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አጋርነት መዋቅሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ፍላጎታቸውን የሚያስተናግድ አዲስ የፋይናንስ አሠራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ሰዎች ቤት በቀጥታ መግዛት ካልቻሉ በመንግሥት በሚመቻቸው አዲስ የሞርጌጅ ሥርዓት አማካኝነት ከገቢያቸው ላይ እየከፈሉ በረጅም ጊዜ ሂደት የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል ይፈጠራል ብለዋል። ይህ ግብ የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የሚሳካ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የሞርጌጅ ሥርዓት የቤት ፍላጎትን ለማሟላት የቀረበ ሌላኛው አማራጭ ሆኗል። የቤት መግዣ ብድር ሥርዓት (ሞርጌጅ) ማለት አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ በብድር አግኝቶ፣ ያንን የተበደረውን ገንዘብ ከነወለዱ በረጅም ዓመታት መልሶ የሚከፍልበት የፋይናንስ አሠራር ነው። ይህ አሠራር አቅማቸው ውስን ለሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በወር በወር እየከፈሉ የቤት ባለቤት የመሆን ልዩ ዕድል ይፈጥራል። የከፍተኛ የቤት ኪራይ ወጪን በማስቀረት ዜጎች በየወሩ የሚከፍሉት ገንዘብ በራሳቸው ንብረት ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ያደርጋል። ይህንን ታላቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በሀገሪቱ የመጀመሪያው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈጽሟል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅዖ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ገልጸዋል። ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ በሰጡት አስተያየት፣ ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የከተሞች ልማት ላይ የግል ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ጠንካራ የቤት ፋይናንስ ገበያ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ቁልፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ እንዲጀመር እንዲሁም ሂደቱ ላይ ክትትል በማድረግ እያከናወኑት ላለው ሥራና አመራር ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ የፋይናንስ ማዕቀፍ አማካኝነት ዜጎች ሙሉ የቤት መግዣ ገንዘብ እስኪኖራቸው ሳይጠብቁ በባንክ ብድር የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይደረጋል።ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ ሳይሆን በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ይከናወናል። የሞርጌጅ ፋይናንስ ሥርዓቱ የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ ቁልፍ የሚባል ነው። መንግሥት ብቻውን ሊያከናውነው የሚችለውን ግዙፍ የልማት ጫና፣የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር በጋራ መወጣት እንደሚቻል የዛሬው ስምምነት ግልጽ ማሳያ ነው። የ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ፈንድ እና የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ዕቅድ እውን መሆን፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥንና ሁሉንም ዜጎች አካታች የልማት ባለቤት የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የልማት ስራዎችን እያፋጠነ ነው
Sep 4, 2026 71
ሸገር፣ ነሐሴ 29/2018(ኢዜአ)፡- በሸገር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩን ከፍተኛ የፋይናንስ ወጪ በማዳን የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማፋጠን ማስቻሉን የከተማው የገንዘብ ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የሸገር ከተማ አስተዳደር የሚነሱ ሰፊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ፍላጎቶችን በመንግሥት መደበኛ የበጀት አቅም ብቻ ማሟላት የማይቻል በመሆኑ፣ የኅብረተሰቡንና የልዩ ልዩ አካላትን ጉልበት፣ እውቀትና ሀብት ባቀናጀ መልኩ ማስተባበር አስፈላጊ ሆኗል። በዚህም መሠረት በከተማ ደረጃ የሚካሄዱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በዋናነት የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ፣ የማህበረሰብ ጤናና ትምህርት ድጋፎች እንዲሁም የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ትኩረት አድርገው ሲከናወኑ ቆይተዋል። እነዚህ ተግባራት በመደበኛ የጨረታና ኮንትራት አሰራር ቢፈጸሙ ኖሮ ከከተማው ካፒታልና መደበኛ በጀት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ነበሩ። አሁን ላይ የበጎ ፈቃደኞችን፣ የወጣቶችንና የባለሀብቶችን ተሳትፎ በማጎልበት የተካሄዱት እንቅስቃሴዎች የከተማዋን በጀት ከመቆጠባቸው ባሻገር፣ የተመደበውን ውስን የመንግሥት ሀብት ለሌሎች ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ለማዋልና የአገልግሎት ተዳራሽነትን ለማፋጠን ማስቻላቸው ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ድሳሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የተከናወነው የተቀናጀ የክረምት የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸው፤ መርሃ ግብሩ ስኬታማ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ይገኛል። በመንግሥት የበጀት አቅም ብቻ ሊሸፈኑ የማይችሉ ሰፋፊ የልማት ተግባራት በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው መከናወናቸውን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ ይህም በከተማዋ የሚኖሩ ድጋፍ ፈላጊ ወገኖችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ለማቃለል ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው ባለፈው የበጀት ዓመት ከታቀደው በላይ ከፍተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ በዚህም የ25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ተግባራት ለማከናወን ታቅዶ 28 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ግምት የሚያወጣ የልማትና የድጋፍ ሥራ ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል። በያዝነው የበጀት ዓመትም በ105 የሥራ ዘርፎች 29 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አቶ ወርቅነህ ጠቁመዋል። የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው በርካታ የልማት ተግባራትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ያስቻለ መሆኑን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ ይህም ሕዝብንና መንግሥትን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ከማገዙ ባሻገር ፈጣንና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም መፍጠሩን አስረድተዋል። ማዕድ የማጋራት፣ የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ጨምሮ የመጠጥ ውሃ፣ የድልድይ፣ የጠጠርና ኮብልስቶን መንገድ ግንባታ እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና የመገንባት ተግባራት በሰፊው እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው የተሳኩት የልማት ሥራዎች የከተማውን መደበኛ በጀት ከመታደጋቸው ባሻገር፣ አስተዳደሩ የፋይናንስ አቅሙን ለሌሎች ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ተጨማሪ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲያውል ትልቅ ዕድል መፍጠራቸውን አቶ ወርቅነህ ገልጸዋል።
ፖለቲካ
የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው
Sep 4, 2026 106
መተማ፤ ነሐሴ29/2018(ኢዜአ) ፦ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም በጫካ የሚገኙ የታጠቁ አካላት ለመንግስት የሰላም ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት እድሉን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መክረዋል። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትጥቅ ይዘው በየጫካው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቃቸውን በመፍታት ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል። በተሳሳተ መንገድ በትጥቅ እንቅስቃሴ የነበሩ በርካታ ወጣቶች እውነታውን በመረዳት በህዝብ ላይ እገታና ዘረፋ አንፈፅምም በማለት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እየመጡም ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የመንግስትን የሰላምን ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው ሌሎችም ይህንኑ መልካም መንገድ እንዲከተሉ መክረዋል። የመንግሥትን የሰላም ጥረትና ቁርጠኝነት በማድነቅ የታጠቁ አካላት ይህንን መልካም እድል በመጠቀም ትጥቃቸውን በመፍታት ለሰላምና ልማት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። በምእራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የሚኖሩት የኃይማኖት አባት ሊቀ ህሩያን እያሱ ገዳሙ እና መጋቤ ብርሃን ዘላለም አዲሱ፤ የመንግስት ሆደ ሰፊነትና ለሰላም የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጥረት አድንቀዋል። በዚህም መሰረት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን አንስተው ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ እንዲከተሉ መክረዋል። በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ተጨማሪ ህይወት ሳይጠፋና ንብረት ሳይወድም የተሰጠውን የሰላም እድል በመጠቀም ለህዝባቸው እፎይታን መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የሀገር ሽማግሌው አቶ ደርቤ ጫኔ፤ ለሰላም የሚደረግ ጥረት ጀግንነትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው ለመንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥረትና ሰላምን መርጠው እየመጡ ላሉ ታጣቂዎች አመስግነዋል። በመሆኑ በጫካ የቀሩ ታጣቂዎች የህዝቡን ፍላጎትና የመንግሥትን የሰላም ጥረት ትርጉም በመስጠት ከጥፋት ወጥተው ሰላምን መርጠው ህዝቡን እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል። በመሆኑም ይቅር ባይነትን በማስቀደም ወደ ሰላም መንገድ መመለስ እና ይህንን እድል መጠቀም ለህዝብና ለሀገር በማሰብ የሚፈፀም በመሆኑ የሰላም ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
Sep 3, 2026 321
ባህር ዳር ነሐሴ 28/2018;(ኢዜአ) ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ሙዚየም መገንባቱ የህዝቡን የፍትህ እሴትና በህግ የበላይነት ከማሳየት ባሻገር ተቋማት ለለውጥ ያላቸውን መነሳሳት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የፍትህ አስተዳደር ታሪክ ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ በመሆኑም ለአዲሱ ትውልድ እሴትና ተደማሪ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ አሻራ ላስቀመጡና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለምረቃ እንዲበቃ ላደረጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የሙዚየሙ መገንባት በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ትልቅ እሴት የሚሆን ነው ብለዋል። በካታሎግና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘውን የአገራችን የፍትህ ታሪክ ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያውቁና ለምርምር ግባአት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለምአንተ አግደው፤ ሙዚየሙ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ አስተዳደር የነበሩ የፍትህ ታሪኮችን ሰንዶ በመያዝ የተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ለህግ ማሻሻያ፣ ለፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻና ለሌሎችም የጥናትና ምርምር ስራዎች ትልቅ አቅምና ግብአት ይሆናል ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩና ሌላ ቦታ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ ብርቅዬ የፍትህ ሰነዶች የሚገኙበት ነው ብለዋል። እነዚህን ታሪካዊ መረጃዎች ከተለያዩ ቦታዎች ለማሰባሰብ ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው አጠቃላይ የሙዚየሙ ግንባታ አላማ የህዝቡን የፍትህ ስርዓት ታሪክ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። በፍትሕ ሙዚየም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ ነው-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 3, 2026 352
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ መሆኑን አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የማሳካት ጉዞዋ በየትኛውም የጥፋት ጥምረት ሊከሽፍ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ፅምዶ በሚል የጋራ ዓላማ በሌለው ተራ የጥፋት ኃይሎች ስብስብም ሆነ ለሌሎች ትላልቅ ኃይሎች ጫና የምትበገር ጠንካራ ሀገር አለመሆኗን ገልጸው፤ ይህ በታሪኳም ሆነ በአሁናዊ ጉዞዋ የታየ ተጨባጭ ሀቅ ነው ብለዋል። አሁን ፅምዶ በሚል የጥፋት ጥምረት የተሳሰቡት ኃይሎችም የጋራ ዓላማ የሌላቸውና አጭር ርቀት እንኳ አብረው መጓዝ የማይችሉና እርስ በርስ የሚጋጭ አጀንዳን ያነገቡ ተራ ስብስብ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚያቆማት ኃይል የለም ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤እነዚህ ትናንሽና አቅመ ቢስ ቡድኖች የጀመሩት የጥፋት መንገድም የትም እንደማያደርሳቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል - ቲቦር ናዥ
Sep 3, 2026 436
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ገለጹ። ከቀይ ባህር ጋር ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ ተገቢና ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑንም አመልክተዋል። ቲቦር ናዥ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ግብጽ በአባይ ተፋሰስ ላይ ምንም አይነት የውሃ ድርሻ ሳይኖራት ለዘመናት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ስትጠቀም መቆየቷን አውስተዋል። ግብጽ የዓባይ ወንዝ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖረኝ ይገባል በሚል የምትከተለው አካሄድ ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ ካለው የቀጣናው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም መሆኑንም ገልጸዋል። ግብፅ አዲሱን እውነታ መቀበል አለባት ያሉት የቀድሞው ዲፕሎማት፤ የኢትዮጵያን ፈጣን ዕድገትና በቀጣናው እየተቀየረ ያለውን የኃይል ሚዛንም አንስተዋል። የቀጣናው ፖለቲካዊ ገጽታ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ ግብፅ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የኃይል ሚዛን መፈጠሩንና ኢትዮጵያም እጅጉን ማደጓን ልትገነዘብ እንደሚገባ አስምረውበታል። ግብፅ የድርድር አቀራረቧን ዳግም በመመርመርና አዲስ እና አዎንታዊ አመለካከት ይዛ ወደ ንግግር ጠረጴዛው ከተመለሰች ዘላቂና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻልም ነው ያነሱት። የሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብቶችን የመጠቀም መብት እውቅና መስጠት ላይ የተመሰረቱ ውይይቶች የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ተናግረዋል። ቲቦር ናዥ የኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም ራስ ወዳድነት ወይም በግብፅ ላይ የህልውና አደጋ ተደርጎ መታየት የለበትም ሲሉ አስገንዝበዋል። አገራት የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት ይጠቀማሉ። ሁሉንም ነገር በእውነታው ላይ ቆመን እንመልከት ብለዋል። ቲቦር ናዥ አያይዘውም፤ ግብፅ ስለ ዓባይ ከምታነሳው አቋም በተቃራኒው፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር እንዳትደርስ የያዘቸውን አቋም ምክንያታዊነት የጎደለው መሆኑን አንስተዋል። ግብፅ የቀይ ባህር ዳርቻ ሀገራት ብቻ የባህር አስተዳደር ጉዳይ ይመለከታቸዋል የምትል ከሆነ፣ በአባይ ተፋሰስ መጠቀም ያለባቸው የውሃ ድርሻ ያላቸው ሀገራት ብቻ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ከእውነታ ጋር የማይጣጣመውን ይህን የግብጽን አቋም የግብዝነት ድርጊት ሲሉ ተችተውታል። የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዠ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተም ሀሳባቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን የባህር ላይ ታሪክ በማስታወስ፣ ሀገሪቱ በወቅቱ የራሷ የባህር ኃይል (ኔቪ)፣ የባህር ኃይል ማዕከል እና በባህር ኃይል ውስጥ ያገለግሉ የነበሩ የኢትዮጵያ አድሚራሎች እንደነበሯትም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት እጅግ አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ሀገሪቱ አሁን የምታደርገውን የባህር በር የማግኘት ጥረት ለቀይ ባህር ካላት ታሪካዊ ግንኙነት ጋር አያይዘውታል። የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ መሆኑን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ የጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች በሚገባ መረዳት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው
Sep 3, 2026 376
ቦንጋ፤ ነሐሴ28/2018(ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራት የኢኮኖሚ እድገትና ደህንነት መረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ። የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻና በአንድ ወቅት ስሟም ከሀያላን ሀገራት ተርታ የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር አካባቢ የነበራት ተሰሚነትና የወደብ ባለቤትነት ለገናናነቷ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ በታሪክ አጋጣሚ የቀይ ባህር ባለቤት ከነበረችበት ከተነጠለች ጀምሮ የራሷ የባህር በር በማጣቷ ለበርካታ ችግሮች ተዳርጋ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ያለቸው ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቢኖራትም ወደብ አልባ መሆኗ በእድገቷና በኢኮኖሚዋ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮባታል። ይህን ታሪክ በመቀየር ኢትዮጵያን በቀጣናው ሀገራት ወደነበረችበት ከፍታ ለመመለስ የባህር በር ባለቤትነትን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዘሪሁን ያሬድ፣ የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ባለቤትነት ኢትዮጵያ በቀጣናውና በአሁጉሩ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ ነው። የአካባቢውን ሀገራት የህዝብ ለሕዝብ ትስስር በማጠናከር ቀጣናዊ ውሕደትን ለመፍጠር፣ ሰላምን ለማጽናትና የጋራ እድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። የባህር በር መኖር ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት ለሀገር ልማት እንድታውል ያደርጋል ያሉት መምህሩ፣ የወጪና ገቢ ምርቶችን በቀላሉ በማሳለጥ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷንም እንደሚያሳድግ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን በዲፕሎማሲዊ መንገድ የጀመረችው ጥያቄ መልካዓ ምድራዊና ሕጋዊ መሠረት ያለው በመሆኑ የዜጎችን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም መምህሩ ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሰለሞን ማሞ በበኩላቸው፣ ቀይ ባህር ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዲፕሎማሲዊ መስክ ትልቅ ቁርኝት የነበረውና የሕልውናዋ መሠረት መሆኑንም ገልፀዋል። በወቅቱ ኢትዮጵያን በዓለም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ዘርፎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አራት ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡ የባህር በር ማጣት በተዘጋ ቤት ውስጥ እንደመኖር መሆኑን የጠቀሱት መምህሩ፣ መልሶ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የሚደረገው ጥረት የመላው ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን በጋራ ተደጋግፎ ለማደግ ካለው ፋይዳ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መከበር ትልቅ ዋጋ እንዳለውና የኢትዮጵያም ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሕገ-ወጡ ሕወሓት ቡድን የሚደርስብንን ግፍ ለማስቆም የጀመርነውን ትግል እናጠናክራለን - የትግራይ ክልል ተወላጆች
Sep 3, 2026 543
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በትግራይ ክልል ሕገ-ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆም በቡድኑ ላይ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገለጹ። በአሁኑ ወቅት ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ወጣቶች ለሌላ አሳልፎ መሸጥን ጨምሮ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ በማካሄድ ከፍተኛ ግፍና መከራ እያደረሰ ይገኛል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የክልሉ ተወላጆች መካከል አቶ ኹሉፍ አጽአሊ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል ወጣቶች ወደ ማይፈልጉት ጦርነት እንዲገቡ እየተገደዱ ነው። ወጣቶች ይህንን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በመሸሽ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ ባሕርና በረሃ እየገቡ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም እኛ አንድነታችንን በማጠናከር ሕገ ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ማስቆም አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ለምለም ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በሕገ ወጡ ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል እናቶች በለቅሶና መከራ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በጣም ኢ-ሰብአዊ መሆኑን በመግለጽ ሕገ ወጡን ቡድን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል ማጠናከር አለብን ያሉት ደግሞ ሌላኛው የክልሉ ተወላጅ ተካ ገብሩ ናቸው። ሰውን ያለፍላጎቱ ለጦርነት እንዲሰማራ ማድረግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተካ፣ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁበት የሰብዓዊነት እሴት በክልሉ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ዲፕሎማሲ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ ላይ ያተኮረው የአሰፋ አብዩ (ዶ/ር) መጽሐፍ ተመረቀ
Sep 2, 2026 586
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ(ዶ/ር) የዲፕሎማሲ ሥራ በአፍሪካ ቀንድ ለሚካሄደው የሰላም ግንባታ ሂደት ያለውን ቁልፍ ሚና አስመልክቶ የጻፉት አዲስ መጽሐፍ ተመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደው የመጽሐፉ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ማኅበረሰብ፣የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ምሁራን ተገኝተዋል። ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ስትራቴጂ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ተሞክሮና ፈተናዎቹ (Diplomacy As A Peace Building Strategy:-Approaches and challenges in the Horn Africa) የተመረቀው መጽሐፍ ርዕስ ነው። የመጽሐፉን ዳሰሳ ያቀረቡት የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደገለጹት፤ የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ያለውን ፋይዳ አጉልቶ ማሳየት ነው፡፡ ፀሐፊው በዳበረ ሙያዊ ልምድ፣ የአመራርነት ክህሎት፣ በትምህርት ባገኙት እውቀትና ጥልቅ ጥናት ታግዘው ያዘጋጁት መጽሐፍ መሆኑን ከንባባቸው መገንዘባቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ዲፕሎማሲ ከሰላም ግንባታ ባሻገር ብሔራዊ ጥቅምና ደኀንነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ማሣሪያ መሆኑ በትኩረት እንደተተነተነ ጠቁመዋል፡፡ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ግጭቶችንና ጦርነቶችን መፍታት ብቻ ሳይሆን፤ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ በመጽሐፉ በሚገባ መብራራቱ የጥንካሬው ማሳያ ነው ብለዋል። ሌላኛው የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት መምህር ባዩልኝ ዘመድአገኘሁ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን አጉልቶ ማሳየቱ ጠንካራ ጎኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሰላም ጉዳዮችንና የዲፕሎማሲ ፅንሰ-ሐሳቦችን አስተሳስሮ በማንሳት መፍትሔ እንደሚጠቁም አብራርተዋል። መጽሐፉ ወቅታዊ የሆኑ አህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ ክስተቶችና ግጭቶችን በማጣቀስ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋሉ ችግሮች በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ፖሊሲ አውጪዎች 21 ምክረ-ሐሳቦችን በግብዓትነት ማቅረቡ የይዘት ጥንካሬውን አጉልቶ እንደሚያሳይ ዶክተር ባዩልኝ አመልክተዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳሰሳ ያቀረቡት አምባሳደር ሽብሩ ማሞ፤ መጽሐፉ ሰላም፣ዲፕሎማሲና ደኀንነት ከድንበር ግጭት ጋር ያላቸውን ትስስር በሚገባ የሚያነሳ መሆኑን ጠቁመዋል። የሀገራችን ዲፕሎማቶች፣የፀጥታና ደኀንነት አባላት፣ ጥናትና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ግንባታ ጥረቶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ ወሳኝ የሆኑ የሰላም፣ ግጭትና ዲፕሎማሲ ጽንሰ-ሐሳቦችን በሚገባ እንዳነሳ ጠቅሰዋል፡፡ በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት የሚታዩ የድንበር ወሰን ችግሮች የፀጥታና ደኅንነት ስጋት እንደሚፈጥሩ በመግለጽ፤ መጽሐፉ ለባለድርሻ አካለት ግብዓት እንደሚሆን አመልክተዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ድንበሮች ጥናት ግብረ-ኃይል አስተባባሪ አምባሳደር ኢብራሂም አድሪስ በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ክፍተት በሆኑት የድንበር ግጭት ፣ ሰላምና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑ ጠቅሰው፤ በዲፕሎማሲ ፣ፀጥታና ደኀንነት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና አመራሮች ጠቃሚ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይ በዲፕሎማሲና የሰላም ግንባታ ዘርፎች የካበተ ሥራ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎችም መጽሐፍ ለመጻፍ እንዲነሳሱ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ (ዶ/ር) በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተልዕኮ ሥምሪት ያገኙት ልምድና ተሞክሮ እንዲሁም የፒኤችዲ ድግሪ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፍ መጽሐፉን ለማዘጋጀት መነሻ እንደሆናቸው ጠቁመዋል። ከዝግጅት እስከ ሕትመት ባለው ሂደት ተሳትፎ ላደረጉት አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከመጽሐፉ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ 100 ሺህ ብር ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት መስዕዋትነት ለሚከፍለው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም 100 ሺህ ብር ደግሞ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በስምሪት ላይ እያሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚያበረክቱ በመድረኩ ላይ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የህዳሴ ግድብ ግንባታን ያሳካ ታሪካዊ ትውልድ የባህር በር ጥያቄንም ያሳካል
Sep 2, 2026 568
ደሴ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት አለበት ሲሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገለጹ። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለረጅም ዘመናት የቀይ ባህር ዳርቻዎችና ወደቦች ባለቤት ሆና የቆየች ቢሆንም፣ በየጊዜው በነበሩ የታሪክ አጋጣሚዎችና ጂኦፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የህዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣው ኢኮኖሚ እና የመልክዐ ምድራዊ አካባቢዋ ተፈጥሯዊ ቁርኝት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የባህር በር መብቷን እንደገና እንድታስከብር የሚያስገድድ መሆኑም ይታወቃል። የአርበኞች ማህበር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የቀድሞ የሰራዊት አባላት፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ምሁራንና ሌሎችም ይህ ታሪካዊና ህጋዊ እውነት በትውልዶች መካከል ሳይደበዝዝ እንዲቀጥል የነበራቸውን ድርሻ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ወሎ ዞን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጽህፈት ቤት አባላት፤ በቀይ ባህር ቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ የሚያስቆጭ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ መደረጉ በሴራ የተፈፀመ የባንዳነት ተግባር መሆኑን ያነሱት አርበኞቹ አሁን ላይ ይህንን የቆየ ስብራት ለመጠገን በመደመር መንግስትና በህዝቡ የተጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። የጽሕፈት ቤቱ ፀሐፊ ተተኪ አርበኛ አየለ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገበት ምክንያት እስካሁን ለማንም ግልጽ ያልሆነና የምንቆጭበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት እንዳለበት አንስተዋል። በዚህ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው ለስኬቱም የሁላችንም ሀገራዊ አደራ እና ሃላፊነት አለብን ብለዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተዘግቶባት መዝለቅ የማትችልና የህልውናዋ ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄው መልስ ሊያገኝ እንደሚገባም ገልጸዋል። የማህበሩ አባል አቶ ማሞ አያሌው እና ሃምሳ አለቃ አለማየሁ አበበ፤ ለኢትዮጵያ የባህር በር ቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን የትውልዱ መረዳት አስደናቂነት አንስተው ለተግባራዊነቱ በጋራ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ እና የቀይ ባህር መልክዓ ምድራዊ ቁርኝት ከጥንት ጀምሮ ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን አንስተው በዚህ ዘመን የባህር በር የምትነፈግበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ቀይ ባህርን ለመነጠል የተሄደበት ርቀት የሴራ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ያነሱት ሌላኛው የማህበሩ አባል ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ ኢትዮጵያ ታሪኳን አድሳ የባህር በር ባለቤት የምትሆንበት ጊዜ ብዙም እሩቅ ሊሆን አይችልም ብለዋል። በወቅቱ የነበሩ ፖለቲከኞች የሰሩት ታሪካዊ ስህተት ኢትዮጵያን አሁን ላይ ብዙ ዋጋ እያስከፈላት መሆኑን የሚናገሩት ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ የባህር በር ባለቤትነቷ እውን እንዲሆን በመስራት ታራካችንን የምናድስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በታሪክ፣ በመልክዐ ምድርና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ተገቢ ጥያቄ መሆኑም ተናግረዋል።

ማህበራዊ
በጉራጌ ዞን ተፈጥሮዊ እና ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብ እየዋሉ ነው
Sep 4, 2026 11
ወልቂጤ፣ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-በጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብ እየዋሉ መሆኑን የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ። የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በዞኑ ተሸፍነው የቆዩ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮዊ ቅርሶች በመደመር መንግስት እሳቤ ለምተው ለቱሪስት መስህብነት እየዋሉ ነው። የቱሪስት ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ለማዋል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ለአብነትም በዞኑ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን እንዲሁም መስህቦችን በማስተዋወቅና የገጠር ኮሪደርን ከጀፎረ ባህላዊ እሴት ጋር በማስተሳሰር ለቱሪዝም ልማቱ መዋል መቻሉን ጠቁመዋል። ይህም የቱሪስቶችን ቁጥርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ማገዙን ገልጸዋል። በዚህም በ2018 በጀት ዓመት ዞኑ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች መጎብኘታቸውና ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል። በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ፣ ባህል እና ሃገር በቀል ልማት ማዕከል ዳይሬክተር ፀጋማርያም ዱላ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶችንና እሴቶችን በማልማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳቸውን ለማጉላት የሚደረገውን ጥረት በጥናትና ምርምር እያገዘ ነው። ይህም ቅርሶች የሚጠበቁበት እና ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች በስፋት የሚጎበኙበትን አቅም እያሳደገው መጥቷል ብለዋል። የጉራጌ ባህላዊ እሴት የሆነው ጀፎረን በገጠር ኮሪደር ይበልጥ እንዲለማ መደረጉና መተዋወቁ ቱሪስቶች በብዛት ወደ አካባቢው እንዲመጡ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ አቶ ወንድሙ ብሩ ናቸው። ይህም በቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰዎች የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን የእንስሳት ጤናን በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል
Sep 4, 2026 29
ጂንካ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኦሞ ዞን የእንስሳት ዝርያን በማሻሻልና ጤንነታቸውን በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ምንላርገው አዲሱ ለኢዜአ እንዳሉት በዞኑ ካለው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት የሚገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻልና የእንስሳቱን ጤና መጠበቅ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው። በአሁኑ ወቅትም የእንስሳት ጤናን ለመጠበቅ የእንስሳት ክትባት በዞኑ ባሉ ስድስት ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በዘመቻ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በዘመቻ እየተሰጠ ያለው ክትባት አባሰንጋ፣ አባ ጎርባ፣ ጉርብርብ፣ የዳልጋ ከብቶች የሳንባ በሽታ፣ የዶሮ ፈንግል እንዲሁም የበግና ፍየሎች በሽታን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በግ፣ ፍየል፣ የዳልጋ ከብቶችና ዶሮን ጨምሮ ወደ 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ እንስሳት በተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድን አማካኝነት በዘመቻ ክትባት እንደሚሰጥ ገልጸው፣ ለዘመቻው የተለያዩ ተቋማት አስተዋጾ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል። በዞኑ በናፀማይ ወረዳ እንጨቴ ቀበሌ እየተሰጠ ባለው የእንስሳት ክትባት ተጠቃሚ ከሆኑ አርብቶ አደሮች መካከል ኦይታ ሞርዴ እንዳሉት፣ መንግስት ከብቶቻቸውን በነጻ እንዲያስከትቡ ማመቻቸቱ ጤናቸውን ለመጠበቅ አግዟቸዋል። አቶ ባካ ዋልታ የተባሉ ሌላው የቀበሌው ነዋሪ በበኩላቸው፣ መንግስት ለከብቶቻቸው የሕክምና አገልግሎትን በአቅራቢያቸው ከመስጠት ባለፈ በዘመቻ መከተቡ ከብቶቻቸውን ከጉዳት ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በዞኑ 14 ሚሊዮን የሚጠጉ ከብቶችን በመደበኛና በዘመቻ መልክ ለመከተብ መታቀዱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የልማት ስራዎችን እያፋጠነ ነው
Sep 4, 2026 71
ሸገር፣ ነሐሴ 29/2018(ኢዜአ)፡- በሸገር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩን ከፍተኛ የፋይናንስ ወጪ በማዳን የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማፋጠን ማስቻሉን የከተማው የገንዘብ ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የሸገር ከተማ አስተዳደር የሚነሱ ሰፊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ፍላጎቶችን በመንግሥት መደበኛ የበጀት አቅም ብቻ ማሟላት የማይቻል በመሆኑ፣ የኅብረተሰቡንና የልዩ ልዩ አካላትን ጉልበት፣ እውቀትና ሀብት ባቀናጀ መልኩ ማስተባበር አስፈላጊ ሆኗል። በዚህም መሠረት በከተማ ደረጃ የሚካሄዱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በዋናነት የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ፣ የማህበረሰብ ጤናና ትምህርት ድጋፎች እንዲሁም የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ትኩረት አድርገው ሲከናወኑ ቆይተዋል። እነዚህ ተግባራት በመደበኛ የጨረታና ኮንትራት አሰራር ቢፈጸሙ ኖሮ ከከተማው ካፒታልና መደበኛ በጀት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ነበሩ። አሁን ላይ የበጎ ፈቃደኞችን፣ የወጣቶችንና የባለሀብቶችን ተሳትፎ በማጎልበት የተካሄዱት እንቅስቃሴዎች የከተማዋን በጀት ከመቆጠባቸው ባሻገር፣ የተመደበውን ውስን የመንግሥት ሀብት ለሌሎች ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ለማዋልና የአገልግሎት ተዳራሽነትን ለማፋጠን ማስቻላቸው ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ድሳሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የተከናወነው የተቀናጀ የክረምት የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸው፤ መርሃ ግብሩ ስኬታማ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ይገኛል። በመንግሥት የበጀት አቅም ብቻ ሊሸፈኑ የማይችሉ ሰፋፊ የልማት ተግባራት በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው መከናወናቸውን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ ይህም በከተማዋ የሚኖሩ ድጋፍ ፈላጊ ወገኖችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ለማቃለል ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው ባለፈው የበጀት ዓመት ከታቀደው በላይ ከፍተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ በዚህም የ25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ተግባራት ለማከናወን ታቅዶ 28 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ግምት የሚያወጣ የልማትና የድጋፍ ሥራ ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል። በያዝነው የበጀት ዓመትም በ105 የሥራ ዘርፎች 29 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አቶ ወርቅነህ ጠቁመዋል። የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው በርካታ የልማት ተግባራትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ያስቻለ መሆኑን ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ ይህም ሕዝብንና መንግሥትን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ከማገዙ ባሻገር ፈጣንና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም መፍጠሩን አስረድተዋል። ማዕድ የማጋራት፣ የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ጨምሮ የመጠጥ ውሃ፣ የድልድይ፣ የጠጠርና ኮብልስቶን መንገድ ግንባታ እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና የመገንባት ተግባራት በሰፊው እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው የተሳኩት የልማት ሥራዎች የከተማውን መደበኛ በጀት ከመታደጋቸው ባሻገር፣ አስተዳደሩ የፋይናንስ አቅሙን ለሌሎች ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ተጨማሪ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲያውል ትልቅ ዕድል መፍጠራቸውን አቶ ወርቅነህ ገልጸዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ማህበራዊ ችግራችን ተቃሏል-በአምቦ ከተማ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች
Sep 4, 2026 67
አምቦ፤ ነሐሴ 29/2018(ኢዜአ)፡- በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተደረገላቸው ድጋፍ ማህበራዊ ችግራቸውን እንዳቃለለላቸው በአምቦ ከተማ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ተናገሩ። በኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚካሄደው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዋናነት አቅመ ደካሞችን፣ አረጋውያንን እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂና በጊዜያዊ ድጋፎች ለማገዝ የሚከናወን አገር አቀፍ እንቅስቃሴ ነው። በአምቦ ከተማም በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ በባለሙያዎችና በባለሀብቶች አስተባባሪነት በየክረምቱ የሚከናወኑት የቤት እድሳት፣ የምግብና የቁስ ድጋፍ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም የነፃ ህክምና አገልግሎቶች የብዙ ነዋሪዎችን የኑሮ ጫና ሲያቃልሉ ቆይተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለረጅም ዓመታት ያረጁ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ በመኖራቸው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደነበር አንስተዋል። አሁን ላይ አዲስ ቤት ተሰርቶላቸው የተሟላ ኑሮ መኖር መጀመራቸውን ይገልጻሉ። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ዘውዴ ደበሌ ይኖሩበት የነበረው ቤት ከክረምት ዝናብም ሆነ ከበጋ ፀሐይ የማይከላከልላቸው እንደነበር ጠቅሰው፤ ይህም ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸው እንደቆየ ተናግረዋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው እንደ አዲስ መገንባቱ በመጀመሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው ህብረተሰቡ የነበረውን ጥንታዊ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ዕሴት እንደገና የሚያነቃቃ በመሆኑ በስፋት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል። ባጋጠማቸው የአካል ጉዳት ሰርተው ልጆቻቸውን የማስተዳደር አቅማቸው ተዳክሞ በችግር ውስጥ መቆየታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አቶ ኤቢሳ አብዲሳ ናቸው። ሊፈርስ ከደረሰ ቤት ውስጥ በስጋት ይኖሩ እንደነበር ያነሱት አቶ ኤቢሳ፣ የከተማው አስተዳደር በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አዲስ ቤት ሰርቶ በመስጠቱ በአሁኑ ወቅት ከተጋረጠባቸው ስጋት መላቀቃቸውን ተናግረዋል። የአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ሙለታ በበኩላቸው በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 59 የሥራ ዘርፎች ተለይተው ወደ እንቅስቃሴ መገባቱን ገልጸዋል። በነዚህ ተግባራትም ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው በአጠቃላይ 91 ሺህ 529 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። በበጎ ፈቃድ ዘመቻው ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ከማደስና ከመገንባት ጀምሮ የጤና፣ የትምህርት፣ የአካባቢ ጥበቃና የግብርና ሥራዎች በዋናነት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ዘመቻ የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን የጠቀሱት ሃላፊው፤ በዚህም 255 ሚሊዮን 181 ሺህ 448 ብር የሚገመቱ የተለያዩ የማህበረሰብ ልማትና የድጋፍ ሥራዎች መከናወናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል ከ 10 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው
Sep 4, 2026 28
ባህርዳር ፤ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን ለማቃለል በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ አለው። በአማራ ክልል ለሚያጋጥመው የምርጥ ዘር እጥረት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና የአካባቢውን የስነ-ምህዳር ሁኔታ ያገናዘበ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ትኩረቱን በሀገር ውስጥ የዘር ብዜት ላይ አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ይህ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረው የዘር ብዜት ስራም የውጭ ዘር ጥገኝነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ ለቀጣዩ ምርት ዘመን ገበሬው ጥራት ያለውና በሽታን የመቋቋም አቅሙ የጎለበተ የሰብል ዘር በቅርበትና በወቅቱ እንዲያገኝ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው። በዚህም ከምርምር የወጡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በ2018/2019 የምርት ዘመን በኩታ ገጠም እርሻ ዘር የማባዛት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በምርት ዘመኑ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ እየተባዙ ያሉት የበቆሎ፣ የስንዴ፣ የጤፍ፣ የሩዝ፣ የአኩሪ አተርና ሌሎች የተሻሻሉ የሰብል ዘሮች እንደሆኑም አመልክተዋል። የዘር ብዜት ስራው በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ፣ በግል ዘር አባዥዎች፣ በዩኒየኖች፣ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽንና ሌሎች ዘር አባዢ ድርጅቶች እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በምርት ዘመኑ 267 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ምርጥ ዘር ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ይህም የክልሉን የምርጥ ዘር እጥረት በማቃለል ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኘው የዕድገት ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ በሪሁን እንዳሉት ዩኔየኑ በ360 ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ፣ የበቆሎና ባቄላ ሰብሎች የምርጥ ዘር ብዜት ስራ እያከናወነ ነው። የዘር ብዜት ተግባሩን እያከናወነ ያለው ከ4 ሺህ 100 አርሶ አደሮች ጋር የኮንትራት እርሻ የውል ስምምነት በመፈፀም መሆኑንም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል። ዩኔየኑ ባለፈው የምርት ዘመን አባዝቶ ከሰበሰበው ከሰባት ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተሻለ ይሰበስባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
በሲዳማ ክልል የህዝብን የልማት ጥያቄ የመመለሱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Sep 3, 2026 270
ሀዋሳ፣ ነሀሴ 28/2018 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልሱ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ቡድን በምስራቃዊና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። ርዕሰ መስተዳድሩ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ እና ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም አክለዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ታስቦ እየተገነባ የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ለማጠናቀቅም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የልኡካን ቡድኑ የአርቤጎና እና የቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘውና በሎጊታ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የባሬ ድልድይ እንዲሁም የቡራ ወረዳ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ በዚሁ ወቅት ከጎበኙዋቸው የልማት ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የክልሉ መንግሥት የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ ፕሮጀክቶችን እውን የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በቡራ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው የአስተዳደር ሕንፃም የመንግሥት አገልግሎትን ምቹና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመስጠት እንደሚያስችል ነው ያመለከቱት። በቡራ ወረዳ ዳለቻ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ባንጫ ባዲሶ በበኩላቸው፣ የአርቤጎና እና ቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የባሬ ድልድይ መሠራቱ ቀደም ሲል ወንዙን ለመሻገር ይገጥም የነበረውን ችግር እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል። ወንዙ በሚሞላበት ወቅት በርካቶች ለመሻገር ሲሞክሩ በደራሽ ውኃ ይወሰዱ እንደነበር አስታውሰው፣ የድልድዩ ግንባታ ትልቅ እፎይታ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። ሌላው የአርቤጎና ወረዳ ሚቂቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ፌኦ ሲዱ በበኩላቸው፣ የድልድዩ መገንባት ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማውጣትና የሚፈልጉትን ሸምተው ለመመለስ ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንደፈታላቸው ገልጸዋል። በጉብኝቱ ላይ የክልሉ፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 3, 2026 297
አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። አገልግሎቱ መንግሥት ሃገራዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገባውን ቃል ወደ ተግባር እየለወጠ ይገኛል ብሏል። ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና የዜጎቿን ሕይወት ከፍ ለማድረግ በምታደርገው ያልተቋረጠ ርብርብ፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያበስሩ ታሪካዊ ምዕራፎች እውን እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። መንግሥት ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስልታዊ ፖሊሲዎችን በመንደፍና በመተግበር በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት የዚህ አበይት ርዕይ አንዱ ማሳያ ነው ሲልም አገልግሎቱ አብራርቷል። በ100 ቢሊየን ብር ካፒታል የሚቋቋመውና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ያካተተው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ፣ በባንክ ዘርፍ ያለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን በመቅረፍ ለዜጎች አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ይፈጥራል ብሏል። አገልግሎቱ ይህ ታሪካዊ ስምምነት መንግሥት በተመጣጣኝ ዋጋ የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን ለማቅረብ ያስቀመጠውን ግብ በግንባር ቀደምትነት የሚያሳካ መሆኑን ገልጿል። ስምምነቱ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ፍላጎት እውን በማድረግ ረገድ የሚታዩ ማነቆዎችን በመስበር፣ የበርካቶችን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ማኅበራዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያሻሽል የመንግሥት ቁርጠኝነትን ያረጋገጠ ቁልፍ ርምጃ መሆኑንም ጠቅሷል። ይህ ስኬት ብቻውን የቆመ አይደለም፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሜጋ ፕሮጀክቶች የተመዘገቡት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ድሎች ቀጣይ ምዕራፍ አካል ነው። የመደመር መንግሥት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በስፋት በማካተትና የገበያ ሥርዓቱን በማዘመን አገራዊ የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር የልማት ጉዞው መሠረት አድርጎ ቀጥሏል። እንደ ሀገር እየተመዘገበ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የዋጋ ግሽበት አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሰውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ መንግሥት በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት በመመደብ በነዳጅ፣ በመሠረታዊ ፍጆታዎች እና በግብርና ግብአቶች ላይ ከፍተኛ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። ከዚህ የዕለት ኑሮ ማቃለያ ሥራ ባሻገር የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ማሻሻልና ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎል። በዚህም ቃል በተግባር እየተለወጠ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ የመገንባት ጽኑ ፍላጎቱ በሁሉም መስክ በተግባር እየተፈጸመ ቀጥሏል ብሏል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአዳማ ከተማ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ አድርጓል
Sep 3, 2026 134
አዳማ ፤ነሐሴ 28/2018(ኢዜአ )፡-የአዳማ ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ማድረጉን የአስተዳደሩ ከንቲባ ሃይሉ ጀልዴ ገለፁ። በከተማዋ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ባለሃብቶች የተሳተፉበት ፎረም ተካሄዷል ። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ እንደገለፁት፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በስፋት ለማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በዋናነት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል። የሕዝብ ወይም የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ ለማድረግ ዋናው ትኩረት የተደረገው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ ነው ብለዋል። በዚህም በከተማዋ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሐሲያ ኢሳ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ምርቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብና የተኪ ምርቶችን ለማሳደግ በተደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። በዚህም ዘርፉ የግንባታና የፍጆታ ምርቶችን በማምረት ገበያውን ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የጎላ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ የኢንቨስተሮች ፎረም አስተባባሪ አቶ ፈይሳ አራርሳ በበኩላቸው፤ ፎረሙ በባለሀብቶችና በአስተዳሩ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር የመሠረተ ልማትና የመሬት አቅርቦት ጥያቄዎችን በትብብር ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የከተማዋን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳለጥና የባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ከፎረሙ ተሳታፊዎች መካከል የኩሩፍቱ የወረቀት ፋብሪካ ተወካይ አቶ ሲሳይ ጌታቸው፤ መንግሥት ባለሀብቶች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማስቻል የኢንቨስትመንት መሬትና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በወቅቱ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገት መሳሪያ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 3, 2026 325
ባህርዳር ፤ ነሃሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገትና የመወዳደሪያ መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ "የኤሌክትሮኒክስ መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የፓናል የውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። ርዕሰ መስተዳደሩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ በክልሉ ፈጠራና ቴክኖሎጂን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳለጫ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። በአማራ ክልል "ዲጂታል አማራ" በሚል በ25 ዓመቱ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ቴክኖሎጂ እንደ ልማት መዳረሻ መፍጠሪያ ተደርጎ ተይዟል ብለዋል። በ25 ዓመቱ ስትራቴጂክ ግብ ላይ በ2042 የአማራ ክልል ዋነኛ ሀብት፤ የአገልግሎት መስጫ እና የኢኮኖሚ የዕድገት ምንጭ ቴክኖሎጂ እንዲሆን ይሠራል ነው ያሉት። በዚህም ዘርፉን የሚመራውን ተቋም በአዲስ በማደራጀት፣ አሰራሮችን በመዘርጋትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን አስረድተዋል። በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን የታገዘ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል። በቀጣይም ተቋማት ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባር ላይ አተኩረው እንዲሰሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አስገንዝበዋል። የኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶር) በበኩላቸው፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ በትኩረት በመስራት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ማሳካት ተችሏል ብለዋል። ባለፈው አፈጻጻም የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመርም አሁን ላይ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን በማሟላት የዲጂታል ግብይት፣ ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ የመንግስት አገልግሎትና ጉልበት የቀነሰ አመራረት እውን በማድረግ ለውጥ መመዝገቡንም አስረድተዋል። ይህም የሰው ኃይሉን በኢትዮ ኮደርስ በማሰልጠን ጭምር በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ውጤታማና በዓለም አቀፍ ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በአገራችን የሚገኘው ወጣት ኃይል ራሱን በቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት በማነጽ እየመጣ ያለውን ዓለም አቀፍ ውድድር ለማሸነፍ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱም የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶች አውደ ርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል
Sep 3, 2026 353
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ኩባንያው ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በ2019 ዓ.ም የደንበኞቹን ቁጥር ለማሳደግ፣ ገቢውን ለማሳደግ እና የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት በርካታ ግቦችን ማቀዱን አስታውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በመግለጫው እንደተናገሩት በ2019 በጀት ዓመት የቴሌኮም መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የ5G እና 4G የኔትወርክ ተደራሽነትን ለማሳደግ ታቅዷል። ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ የሚያንቀሳቅሱ አዳዲስ አሰራሮችና አገልግሎቶች እንደሚተገበሩ ተናግረው፤ 295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል። በ2019 ዕቅድ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 628 ተጨማሪ አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች የሚገነቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 605 ያህሉ በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎችና የቴሌኮም አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች መሆኑን አብራርተዋል። የ4G አገልግሎት ለተጨማሪ 300 ከተሞች ተደራሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም የአገልግሎቱን ተደራሽነት 95 በመቶ ያደርሰዋል ብለዋል። የ5G አገልግሎት ለተጨማሪ 40 ከተሞች እንደሚዳረስና በአጠቃላይ የ5G ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥር ወደ 83 ከፍ ይላል ብለዋል። ተቋሙ ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 20 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል የገመድ አልባ ሞባይል ኔትወርክ አቅም በመፍጠር፣ አጠቃላይ የማስተናገድ አቅሙን ወደ 135 ነጥብ 7 ሚሊዮን ያሳድጋል ብለዋል። በፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎት ላይ የሚታዩ የአገልግሎት መቋረጦችን ለማስወገድና የአገልግሎት ጥራትን ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ 150 ሺህ ደንበኞችን የተሻለ የፋይበር ቴክኖሎጂ የማዛወር ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል። በከተሞች የሚገኘውን የፋይበር መስመር በመጨመር 300 ኪሎ ሜትር በማስፋፋት አጠቃላይ አቅሙን ከ15 ሺህ ኪሎሜትር በላይ ከፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቀዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ያስቀመጣቸውን እነዚህን ግቦች ለማሳካት የቴክኖሎጂ አጋርነቱን እንደሚያጠናክር እና በሰው ሃይል ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
በአማራ ክልል ዲጂታል 2030ን በተሳካ መልኩ እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው
Sep 3, 2026 132
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ዲጂታል 2030ን በተሳካ መልኩ እውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ። በባሕር ዳር ከተማ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ተከፍቷል። በአውደ ርዕዩ የመክፈቻ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው እንደገለጹት፤ የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ በክልሉ ዲጂታል 2030 ን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ማሳየትና ማስተዋወቅ ነው። አውደ ርዕዩ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የፈጠራ ሥራዎቻቸውንና የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ለሕዝብና ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡበት ዕድል እንደሚፈጥርላቸው አብራርተዋል። ይህም የቴክኖሎጂ ፈጠራን በማስፋፋት የተያዘውን ሀገራዊና ክልላዊ የዲጂታላይዜሽን ግብ ለማሳካት እየተሠራ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል። በተጨማሪም በኤግዚቢሽኑ በተለያዩ ተቋማት የለሙ 35 የተለያዩ ዲጂታል ሥርዓቶች (Digital Systems) በይፋ ተመርቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።
ስፖርት
ሊቨርፑል በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት ከኤፕስዊች ታውን ጋር ይጫወታል
Sep 4, 2026 85
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ኤፕስዊች ታውን ከሊቨርፑል በፖርትማን ሮድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያገኘው ኤፕስዊች ታውን 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሊቨርፑል በሁለት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ13ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ሊቨርፑል ሰባት ጊዜ ሲያሸንፍ ኤፕስዊች ታውን ሁለት ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ሊቨርፑል በ12 ጨዋታዎች ላይ 26 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ኤፕስዊች ታውን ዘጠኝ ጎሎችን አስቆጥሯል። ክለቦቹ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ ጃንዋሪ 2025 ሲሆን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል 4 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ባለሜዳው ኤፕስዊች ታውን በሁለተኛ ሳምንት በማንችስተር ዩናይትድ ካጋጠመው የ5 ለ 2 ሽንፈት አገግሞ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል። በሁለቱም የሊጉ ጨዋታዎች አቻ የወጣው ሊቨርፑል የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ መርሐ ግብር እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው
Sep 2, 2026 287
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ምርጦች ዕውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ጳጉሜን 3 እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሊግ አንድ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እንዲሁም ምስጉን ዳኛ እና ረዳት ዳኞች ሽልማት ይበረከታል። የሽልማት ስነ ሥርዓቱ የሚካሄድበት ቦታ በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ማንችስተር ሲቲ የቼልሲውን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ተስማማ
Sep 1, 2026 290
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ ማብቂያ ቀን የቼልሲውን አማካይ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። የ25 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አማካይ ከቤንፊካ በ107 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቼልሲ የተቀላቀለው እ.አ.አ በ2023 ነበር። ተጫዋቹ ቼልሲ ከፉልሃም ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ከሉተን ጋር በካራባኦ ካፕ እንዲሁም ከብራይተን ጋር በተደረገው የሊጉ መርሐ ግብር አልተጫወተም። ይህ ዝውውር ሊቨርፑል ባለፈው ዓመት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማጠናቀቂያ ቀን የኒውካስትል ዩናይትዱን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ከከፈለው የእንግሊዝ ክብረ ወሰን ክፍያ እኩል መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል። ፈርናንዴዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ ማምራት እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሲሆን፣ በኢትሃድ ከቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ጋር እንደገና ይገናኛል። ተጫዋቹ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ የሕክምና ምርመራዎችን አድርጎ ዝውውሩን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቼልሲ አርጀንቲናውን አማካይ የሚተካ ሌላ ተጫዋች ለማስፈረም እየሰሩ ይገኛሉ። ክለቡ የሮማውን ማኑ ኮኔ እና የሞናኮውን ላሚን ካማራን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ ሌሎች አማካዮችንም እየተመለከተ ይገኛል።
አርሰናል ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
Sep 1, 2026 329
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል አስቶንቪላ 1 ለ ዐ አሸንፏል። ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ በ59ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። የ24 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እምብዛም ግልጽ የግብ እድሎች ባልተፈጠሩበት ጨዋታ አርሰናል ያገኘውን የግብ እድል በሚገባ ተጠቅሟል። አስቶንቪላ ወደ አርሰናል የግብ ክልል በተደጋጋሚ ጊዜ ቢደርስም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ተስኖታል። በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ብሩኖ ጉማራይሽ ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ተከታታይ ድሉን አግኝቷል። በአንጻሩ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ያጣው አስቶንቪላ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል። አስቶንቪላ በሁለቱ የሊግ ጨዋታዎች ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ከአዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ጋር ይጫወታል። በለንደን ደርቢ አርሰናል ከቼልሲ የሚያደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው። የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 318
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 619
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በአፍሪካ አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
Sep 2, 2026 479
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትንና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓም ተገልጿል። የአፍሪካ ቀጣና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ይፋ የተደረገ ሲሆን እስከ 2027 እያንዳንዱን ሰው በአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና በተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከተመድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቢሮና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የተቀናጀ አይነተ ብዙ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀና አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም ወቅታዊና ተገቢ ነው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎችን አደጋዎችን በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ሴቶችና ህፃናት ጨምሮ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የአደጋው ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበትና ተቋማዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓን ጠቅሰው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስና ሌሎችም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ማንም ሀገር ብቻውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስትራቴጂን ውጤታማ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራትና የተለያዩ አጋር አካላት ጋር በአይነተ ብዙ የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዘላቂ አካባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቤ፤ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ማህበረሰቡን አደጋን የመቋቋም አቅም መገንባትና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2027 እያንዳንዱን ሰው ከአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል አደጋዎች መጠበቅ የሚለውን ግብ ለማሳካት ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጎርፍና የተራዘመ ደርቅ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ፣ እና በሌሎች አደጋዎች ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን በመግለጽ፤ አፍሪካውያን ውስጣዊ ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። አደጋ ድንበር የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በአይነቱ ብዙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአባል ሀገራቱን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ቢሮ ዳይሬክተር ኤግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአመራር ቁርጠኝነት እያደገ በመምጣቱ መሻሻል እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነትና በተወሳሰበ ሁኔታ ተባብሰው ቀጥለዋል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመቆጣጠር የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በሀገራት የተቀናጀ አሰራር መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የ2027 ግብ ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በመግለፅ፤ በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ግንባታ ዘላቂና እምነት የሚጣልባቸው መሆን አለባቸው ብለዋል። በአፍሪካውያን መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ በመጥቀስ፤ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል - የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
Sep 1, 2026 217
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና ዘላቂ የኢንቨስትመንት እድል የሚያሰፋ የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታውቀ። የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ካሳሁን ማሞ፤ ምክር ቤቱ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ፎረምና ኤግዚቢሽኑም ፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና የአረንጓዴ ቢዝነስ ኩባንያዎችና አልሚዎች በተሳተፉበት ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማላቅ ዘላቂ ሥነ-ምህዳራዊ ዕይታን ያማከለ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት እንዲጎለብት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ረገድ ከጀርመን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት እና ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የአረንጓዴ ልማትና ዘላቂነት ማዕከል ማቋቋሙን አመልክተዋል። የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽንም ጤናማ ሥነ-ምኅዳርን የተከተለ የታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን በማጠናከር የዘርፉ ተዋናዮች ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። መድረኩም በአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትንና ሥራ ፈጣሪዎችን በማገናኘት አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ዘላቂ ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማላቅም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል። በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት የሊዌይ የፕሮግራም ማኔጀር ሔለን ጌታው በበኩላቸው፤ መድረኩ ከአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው ብለዋል። ፎረሙም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎችን የፋይናንስ፣ የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ተግዳሮቶች በመለየት መፍትሔ የሚመላከትበት ጠቃሚ መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የገበያ ትስስርና የድጋፍ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አክለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 100
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1562
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1219
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1496
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 311
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል። በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል። 3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች። የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 514
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች። ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 511
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 710
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
ለኢትዮጵያ የቤት ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስምምነት
Sep 4, 2026 62
የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ፈጣን እየሆነ በመምጣቱ እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመሄዱ፣የዜጎችን የቤት ባለቤትነትን ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት አንዱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት የነበረው የቤት አቅርቦት በመንግሥት ትከሻ ላይ ብቻ የወደቀ በመሆኑ፣ ካለው ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ቀርጾ በካቢኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ፖሊሲው የዕድገቱን ፍጥነት እና የከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሥራዎች ለዚህ ሰፊ ራዕይ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታውሰዋል። ይህንኑ ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት አጠቃላይ ዝግጅት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አሁን ላይ አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂንና የረጅም ጊዜ የቤት ብድር ሥርዓትን በማስተዋወቅ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲሱ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ በካቢኔ መጽደቁንና በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አጋርነት መዋቅሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ፍላጎታቸውን የሚያስተናግድ አዲስ የፋይናንስ አሠራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ሰዎች ቤት በቀጥታ መግዛት ካልቻሉ በመንግሥት በሚመቻቸው አዲስ የሞርጌጅ ሥርዓት አማካኝነት ከገቢያቸው ላይ እየከፈሉ በረጅም ጊዜ ሂደት የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል ይፈጠራል ብለዋል። ይህ ግብ የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የሚሳካ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የሞርጌጅ ሥርዓት የቤት ፍላጎትን ለማሟላት የቀረበ ሌላኛው አማራጭ ሆኗል። የቤት መግዣ ብድር ሥርዓት (ሞርጌጅ) ማለት አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ በብድር አግኝቶ፣ ያንን የተበደረውን ገንዘብ ከነወለዱ በረጅም ዓመታት መልሶ የሚከፍልበት የፋይናንስ አሠራር ነው። ይህ አሠራር አቅማቸው ውስን ለሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በወር በወር እየከፈሉ የቤት ባለቤት የመሆን ልዩ ዕድል ይፈጥራል። የከፍተኛ የቤት ኪራይ ወጪን በማስቀረት ዜጎች በየወሩ የሚከፍሉት ገንዘብ በራሳቸው ንብረት ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ያደርጋል። ይህንን ታላቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በሀገሪቱ የመጀመሪያው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈጽሟል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅዖ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ገልጸዋል። ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ በሰጡት አስተያየት፣ ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የከተሞች ልማት ላይ የግል ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ጠንካራ የቤት ፋይናንስ ገበያ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ቁልፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ እንዲጀመር እንዲሁም ሂደቱ ላይ ክትትል በማድረግ እያከናወኑት ላለው ሥራና አመራር ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ የፋይናንስ ማዕቀፍ አማካኝነት ዜጎች ሙሉ የቤት መግዣ ገንዘብ እስኪኖራቸው ሳይጠብቁ በባንክ ብድር የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይደረጋል።ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ ሳይሆን በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ይከናወናል። የሞርጌጅ ፋይናንስ ሥርዓቱ የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ ቁልፍ የሚባል ነው። መንግሥት ብቻውን ሊያከናውነው የሚችለውን ግዙፍ የልማት ጫና፣የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር በጋራ መወጣት እንደሚቻል የዛሬው ስምምነት ግልጽ ማሳያ ነው። የ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ፈንድ እና የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ዕቅድ እውን መሆን፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥንና ሁሉንም ዜጎች አካታች የልማት ባለቤት የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኮሪደር ልማት እና የነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 4, 2026 89
በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መጻኢውን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መሰረት የሚጥሉ ናቸው። ከእነዚህ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሀገሪቱን ከተሞች ገጽታና የነዋሪዎቿን የኑሮ ዘይቤ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት መርሃ ግብር ነው። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ስልጡን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው ስኬትና የፈጠረው አርአያነት አሁን ላይ አዲስ አበባን አልፎ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበትና ገጽታ ባለፈ የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለ እና የነገዋን ሀገር ዛሬ ላይ የመቅረጽ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። በኮሪደር ልማቱ ለእግረኛ እና ለአካል ጉዳተኞች ፈታኝ የነበሩ መንገዶች ዛሬ ሰፊና ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ንጣፎችና የብስክሌት መስመሮች ተተክተዋል። በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህ ጥራት ያላቸው መሠረተ-ልማቶች የነገውን ጤናማ እና ማህበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። የኮሪደር ልማት የከተሞችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ዘመናዊነት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና የደህንነት ካሜራዎች የታገዙ ከተሞች በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ በር በመክፈታቸው፣ የ24 ሰዓት የስራ ባህልን በመፍጠር ለአያሌ ወጣቶችና አነስተኛ ነጋዴዎች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። በሌላ በኩል፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ልማት ኢትዮጵያን ወደ ቋሚ የኮንፈረንስ፣ የንግድ እና የባህል ቱሪዝም መዳረሻነት እየቀየራትም ይገኛል። በተለይም የከተሞችን ማህበራዊ መስተጋብርና የሕዝቡን አንድነት በማጠናከር ረገድ የኮሪደር ልማቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው። በልማቱ የተፈጠረው የጋራ ትስስር የነገዋን ጠንካራ፣ ሰላማዊና በአብሮነት የታነጸች ሀገር ለመገንባት እንደ ትልቅ ማህበራዊ መሰረት ያገለግላል። የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ያደገችና አሰራሯ የዘመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተሳስሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ስራው ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በማከናወን ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የስማርት ከተማ መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት አብሮ እየተዘረጋ ይገኛል። በተጨማሪም ከኮሪደር ልማት ጋር እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች ከተሞች ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋትና ሙቀት በመከላከል ለትውልዱ ንጹህና ጽዱ መኖሪያን አካባቢን ለማስረከብና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እያስቻለ ነው። በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአንድ ከተማ ገጽታ ማሻሻል ባሻገር፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ክልል ከተሞች ላይ በመስፋፋት ሀገራዊ ለውጥ ፈጥሯል ማለት ያስችላል። የዚህ ዘርፈ ብዙ የልማት ፍሬ ዛሬ ላይ የኑሮ ዘይቤን እያሻሻለ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ለወደፊቱ ትውልድም የኩራት ምንጭ የሆነ ዘላቂ ሀብት ሆኖ ይሸጋገራል። ዛሬ በጥራትና ውብ ሆነው እየተሰሩ ያሉ መንገዶች፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶች የነገዋ ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ ስልጡንና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ራዕይን እውን የሚያደርጉ ናቸው።
የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚና
Sep 3, 2026 123
የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል። ይህ የተኪ ምርት ስራ ጅማሮ በዋናነት ያነጣጠረው በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ በማስቀረት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የተበታተኑ የማምረት ሙከራዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር ለመቀየር ይፋዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ስትራቴጂ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለትግበራው መፋጠን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደ ትልቅ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ሀገራዊ ንቅናቄው በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ለጀመረው ብሔራዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ትልቅ አቅም የፈጠረ ነው። የስትራቴጂው መውጣት እና ወደ ተግባር መግባት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማስገኘት ጀምሯል። ትልቁ እና ዋነኛው ፋይዳም የውጭ ምንዛሬን ማዳን ሲሆን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህ መነቃቃት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የፋብሪካዎችን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ጋር በማስተሳሰር የአቅርቦት ሰንሰለቱን አጠናክሮታል። ይህንኑ ሀገራዊ ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ላይ የዘርፉን ስልታዊ ጠቀሜታ በተደጋጋሚ አንስተዋል። በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል በመጥቀስ፣ የሀገር ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ኢትዮጵያን የምግብ እጥረት እንደታደጋት ገልጸዋል። ተኪ ምርት ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይወጣባቸው የነበሩ የድንጋይ ከሰል እና የችፑድ ምርቶች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ በስፋት እየተመረቱ መሆናቸውን አንስተዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥራትን መሰረት አድርገው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተኪ ምርት ስራዎች ያገኘውን ስኬት ይበልጥ ለማስፋት እና ዘላቂ ለማድረግ አዳዲስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ግቦችን አስቀምጧል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ወደ 49 ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባውን ወደ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም ስኬት አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ምርቶቻቸውን ያለ ደላላ ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የዲጂታል የገበያ ትስስር ፕላትፎርም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል። ወደፊትም ከቀላል የሸማች ዕቃዎች ባለፈ እንደ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካሎች እና ብረታብረት ያሉ አስራ አምስት ስልታዊ የከባድ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመተካት ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ ወጪ ንግድ ገቢን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ተወዳዳሪ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ተሰንቋል። በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የተኪ ምርት ስራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ምርታማነት እያሸጋገረ የሚገኝ ስልታዊ እርምጃም ነው። በጥናት የተለዩት 96 ቁልፍ ስልታዊ ምርቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ለሀገር በቀል እውቀትና ለፈጠራ ስራዎች ሰፊ በር ከመክፈቱም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ላይ ያላትን የድርድር እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል።
የቀይ ባህር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ሚና
Aug 29, 2026 804
(በሙሴ መለሰ) በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ አብዛኛው ወጪና ገቢ ሸቀጦች በባህር በር በኩል የሚተላለፉ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች ወይም የሎጂስቲክስ መስተጓጎሎች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ማሳረፉ የማይቀር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ የተከሰተውን የጸጥታ ቸግር ተከትሎ የተለያዩ የዓለም ሃገራት የቀይባህር መስመር ከባቤል ሜንደብ እስከ ስዊዝ ቦይ ድረስ ያለው ደህንነት አሳስቧቸዋል። ይሄንን ስጋት ለማቃለልም ሆነ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሃገራት በቀጣናው ካሉ የባህር ተጋሪ መንግስታት ጋር በመሆን የመሰረቷቸውን የጦር ሰፈሮች ቢያጠናክሩም አሁንም ቀጣናው በባህር ላይ ውንብድና፣ በህገ-ወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለስጋት የተጋለጠ ሆኖ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከቀይ ባህር ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ መሆኑን በጽኑ የምታምነው ኢትዮጵያ፣ ድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ የባለብዙ ወገን ውይይቶች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ ታበረክታለች። በተለይም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እንዲሁም የባህር ላይ ወንጀሎችን በጋራ ለመመከት የቀጣናው ሀገራት የተቀናጀ ምላሽ እንዲኖራቸው ድጋፍ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያላት መልክዐ ምድራዊ ትስስር እና የፀጥታ አጋርነት በቀይ ባህር ቀጣና መረጋጋት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በቀጣናው የሚከሰቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግሮች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የትብብር አማራጭን ተከትላ እየሰራች ትገኛለች። የአፍሪካ ቀንድና የቀይባሕር ደኅንነት ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ በቀጣናው ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ በሚደረጉ የማሪታይምና የደኅንነት ውይይቶች ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሰፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስትራቴጂያዊ የንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ በግልጽ ታይቷል። በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አምስተኛው የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባህር ላይ ህግ ማስከበር ውይይት (Maritime Law Enforcement Dialogue) ላይ፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅሞችን የሚያስጠብቅ ተሳትፎ አድርጓል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያላትን ሚና እና ባለቤትነት አሳይቷል። ለኢትዮጵያ የባህር በር ደህንነት የህልውና ጉዳይ ነው። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ተወካይ ካፒቴን ክብሩ መስፍን እንደገለጹት፣ የባሕር ላይ ሰላም መደፍረስ በቀጥታ የአገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ይነካል። አብዛኛው የሀገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ በባህር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚከሰቱ የባሕር ላይ ውንብድናዎችና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የንግድ ፍሰቱን እንዳያስተጓጉሉ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ካፒቴን ክብሩ አክለውም፣ የመርከቦች መድን ዋስትና መናርና የሸቀጦች መዘግየት የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንዳይፈታተኑ፣ ጠንካራና የተቀናጀ የባህር ላይ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ለመመከት ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ግንባር ቀደም ናት። በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር በመቀናጀት "ብሔራዊ የማሪታይም መረጃ ማዕከል" (National Maritime Information Centre) ለመመስረት ያቀደችው ስትራቴጂ፣ ሀገሪቱ ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚያሳይ ነው። መረጃን በጋራ መለዋወጥና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ለዚህ ስኬት ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች። በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ-ሰላጤ የሚስተዋሉ እንደ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሕገ-ወጥ አሳ ማጥመድ ያሉ ስጋቶች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ቀጣናዊ ኃይሎች ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC) የቀጣናው አስተባባሪ ሞስታፋ ኤልባና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አስተማማኝና የተረጋጉ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በቀይ ባህር ቀጣና ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC)፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅርበት በመሥራት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ያላትን የመሪነት ሚና በታሪካዊ ኃላፊነትና በሕግ አግባብ እያስጠበቀች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የባህር ኃሃይልን ጨምሮ በጥብቅ ዲሲፕሊኑ እና በመፈጸም አቅሙ የሚታወቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይሄ ሰራዊት በተለያየ ጊዜ ችግር ላጋጠማቸው ሃገራት ባሳየው የሰላም ማስከበር ሚናው በውጤታማነቱ የተመሰከረለትም ነው። የቀጣናውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሃይል አስፈላጊ ስለሆነም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሃገራት የኢትዮጵያን የባህር ላይ ህልውና በበጎ ይመለከቱታል። ለዚህም በቅርቡ በአንድ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የባብኤል ሜንደብን እና የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ሃገራቸው በቂ አቅም ስለሌላት የሌሎች እገዛ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የጅቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፋይናስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ ገለጻ አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አመላካች የሚሆኑት ያለ አግባብ ከባህሩ የተገፋችውና መብቷን የምትጠይቀው ኢትዮጵያ ያላት ዘርፈ ብዙ ዓቅም ለቀጣናውም ለራሷም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያላት መሆኑን ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12622
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22107
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15141
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20882
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 945
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 805
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።