ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ናቸው
Apr 1, 2026 38
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ። "ቃል በተግባር ፣ ከምርጫ እስከ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አዘጋጅነት የክልል መንግስት ቢሮዎች እና ተቋማት የተሳተፉበት ኤግዚቢሽን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል። የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ህዝብ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የለውጥ ዓመታቱ በክልሉ የነበሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍትሄ ያገኙበት እና ትክክለኛ የብልጽግና ጉዞ የተጀመረበት መሆኑንም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስትም በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራቱ ከተስፋ ወደ ተጨበጠ ብርሃን ሽግግር ለማድረግ እያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል። ከኢኮኖሚ ልማት አንጻርም በግብርናው ዘርፍ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትልቅ ውጤት መምጣቱን ጠቅሰው፤በኢንዱስትሪ፣በማዕድንና በቱሪዝም ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የክልሉ መንግስት ተነጥለው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላምን አማራጭ እንዲከተሉ በማድረግ ረገድ ትልቅ ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል። በአጠቃላይ በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንም ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉ መንግሥት የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ መሆኑን አንስተዋል። የክልሉ መንግስት በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የልማት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን የቻለበት መሆኑንም ጠቁመዋል። ኤግዚቢሽኑ ህዝቡ በመንግስት ስራዎች ላይ ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረውና የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል። በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የተገኙት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፤ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ሀገሪቱን ከጥገኝነት ወደ አምራችነት የቀየሩ ታሪካዊ ስራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንም የመንግስትን ፖሊሲዎች፣ስልቶችና የልማት ውጤቶች ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
አማራጭ ሀሳቦቻችንን ለማቅረብ የሚያስችሉ የሚዲያ አማራጮች ተመቻችተውልናል
Apr 1, 2026 54
ሰመራ፣መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦በምርጫው ሂደት በንቃት እየተሳተፉ የፓርቲያቸውን አማራጭ ሐሳቦች ለማድረሰ የሚያስችሉ የሚዲያ አማራጮች እንደተመቻቸላቸው የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) ገለጸ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ብዝሃነትን ባስተናገደ መልኩ የክርክር መድረኮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ሃንፈሬ መሐመድ ለኢዜአ እንደገለፁት፥የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊና ነፃ በሆነ መልኩ በጥሩ የፖለቲካ ምህዳር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለጠቅላላ ምርጫው ነፃ ክርክር በማድረግ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ ባለው ሰላማዊ ሁኔታ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምንም ዓይነት እንከን ያልገጠማቸው መሆኑንም አስታውቀዋል። የዘንድሮው ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖርና በድምፁ መወሰን እንዲችል ሂደቱ ጥሩ መሆኑን አውስተው ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የራሳችንን ሚና እየተወጣን ነው ብለዋል። የምርጫ ህጉን በተከተለ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ 7ኛውን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሚዛንና የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት ለመተግበር እየሠራች ነው
Apr 1, 2026 36
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ስርዓቷን ለማዘመን 7ኛውን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሚዛንና የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት ለመተግበር እየሠራች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሀፅዮን ገለጹ። የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025- (System of National Accounts 2025) የአንድን ሀገር አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወይም የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (GDP) ለመለካት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ መመሪያ ነው። የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025- 7ኛው የክፍያ ሚዛን ማኑዋል- BPM7 (Balance of Payments Manual 7th Edition) በአንድ ሀገር እና በሌላው ዓለም መካከል ያለውን የገንዘብና የንግድ ልውውጥ (የክፍያ ሚዛን) ለመመዝገብ የሚያገለግል መመሪያ ነው። የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት እና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት በክፍያ ሚዛን (BPM7) እና በ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት (SNA 2025) ላይ ያተኮረ መድረክ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሐ-ፅዮን በዚሁ ወቅት አፍሪካ እ.ኤ.አ የ2008 የብሔራዊ ሂሳብ አያያዝ ስርዓትን (SNA 2008) እና የክፍያ ሚዛን ማኑዋል (BPM6) በመተግበር ረገድ የሚደነቅ እድገት አስመዝግባለች ብለዋል። ይሁን እንጂ ከዓለም ተለዋወጭ ሁኔታ አንጻር የኢኮኖሚ ሽግግርንና መዋቅርን ሙሉ በሙሉ ለመረዳትና ለመለካት አሁንም ከፍተኛ ክፍተቶች መኖራቸውን አንስተዋል። እንደ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ኢ-መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች፣ ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶች እና መሰል ጉዳዮች በቀደሙት አሠራሮች ለመለካት አስችጋሪ መሆኑንም በአብነት ጠቅሰዋል። አዲሶቹ የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025ና 7ኛው የክፍያ ሚዛን ማኑዋል የስታትስቲክስ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የስታትስቲክስ ስርዓትን ለማዘመን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስታትስቲክስ ሥርዓቶቹን ወደ ተግባር ለማስገባት አስቀድማ ዝግጅት መጀመሯንም አንስተዋል። በኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርትን ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር መልሶ የማደራጀትና የማጣጣም ሥራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መሪነት የክፍያ ሚዛን ስታትስቲክስን የማሻሻልና የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎችን ጥራት የማሳደግ ተግባራት በትኩረት እየተተገበሩ መሆኑን አብራርተዋል። ዘመናዊ የስታትስቲክስ ሥርዓት መዘርጋቱ የአጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እምነትን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት የኢኮኖሚ ስታትስቲክስ ዳይሬክተር አዱም ጋጎሉም በበኩላቸው፣ በአህጉሪቱ የስታትስቲክስ ሥርዓቶችን ለማጠናከርና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ከአፍሪካ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት (SNA) እና የክፍያ ሚዛን (BPM7) በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በቀጣናዊ ትስስርና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተሻለ የፖሊሲ ቀረጻ እንዲኖር ያስችላሉ ነው ያሉት። በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የስታትስቲክስ መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር ጂም ቴብሬክ፤ በአፍሪካ የስታትስቲክስ ዘርፍን ለማዘመን ዓለም አቀፍ ሥርዓቶችን ታሳቢ ያደረገ ሥራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት ስለ ሀገራት ኢኮኖሚና ዓለም አቀፋዊ ትስስር አስተማማኝ መረጃ በመስጠት ረገድ ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ የለውጡ ዓመታት ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር፣ አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ተሳትፎ የታየበት ነው- ምሁራን
Apr 1, 2026 159
ሆሳዕና ፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ) ፡-በኢትዮጵያ የለውጡ ዓመታት ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር፣ አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ተናገሩ። በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሁሉም መስኮች እመርታዊ ውጤት መምጣቱ የሚታወቅ ነው። በግብርና ልማት አዳዲስ ኢኒሸቲቮችን ጨምሮ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከራስ ተርፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለበት ታሪካዊ አጋጣሚ ተፈጥሯል። በቱሪዝም፣ ማእድን፣ የኢንዱስትሪ ልማትና በዲጅታል ቴክኖሎጂም ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን መናገር ይቻላል። የለውጡ መንግስት ባለፉት ዓመታት በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ስኬቶችን በተግባር ያረጋገጠበት ስለመሆኑም በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል። በተለይም በጠላትነት፣ በመገፋፋትና አግላይነት የሚታወቀውን የፖለቲካ ምህዳር አሳታፊ፣ አካታችና ሰፊ ምህዳር የተፈጠረበት ማድረግ መቻሉን የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ። በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሙላለም ኃይለማርያም፤ ለውጡ ሲመጣ በውጭና በሀገር ውስጥ በጠላትነትና አሸባሪነት ጭምር የተፈረጁ ፖለቲከኞችን ለሰላማዊ ትግል ያሰባሰበ መሆኑ ትልቅ ውሳኔ እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በውጭም በውስጥም የነበሩ ፖለቲከኞች በተፈጠረላቸው ምቹ ምህዳር ፓርቲ መስርተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በማድርግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። በምርጫ የመንግስት ስልጣን የያዘው ገዥ ፓርቲ ለተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተቋማትን የመምራት እድል በመስጠት ጭምር አሳታፊና አካታችነቱን በተግባር ማሳየቱን ጠቅሰዋል። በዩኒቨርሲቲው በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል የሰላምና ግጭት ጥናት መምህር ጌታሁን አበራ፤ የለውጡ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት በሁሉም መስኮች የሚታዩ እና የሚጨበጡ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በተለይም በፖለቲካው መስክ የቆዩ ስብራቶችን በመጠገን ሀገራዊ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት ረገድ አበረታች ውጤቶች መጥተዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ የመጠላለፍና የጥላቻ ፖለቲካ አብቅቶ በሀገሩ ጉዳይ ሁሉም ተሳትፎና አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እድል የተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል። የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የመንግስት ተቋማትን በሃላፊነት መምራታቸው ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ የለውጡ ዓመታት ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር፣ አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ታሳትፎ የታየበት መሆኑን ምሁራኑ ተናግረዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል
Apr 1, 2026 119
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የግብርና ምርታማነት ለምግብ ሉዓላዊነትና ለሀገራዊ ክብር" በሚል መሪ ሐሳብ በለውጡ ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ እውን ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣የግብርናው ዘርፍ ከአምስቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ሆኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ረገድ ስኬት እያስገኘ ነው፡፡ እንደ የበጋ ስንዴ ምርት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ ሌማት ትሩፋት፣ ኩታ ገጠም፣ የግብርና መካናይዜሽን እንዲሁም ሌሎችም ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መንግስት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በዘርፉ ባለ አነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን በበቂ ሁኔታ አለመደገፍ፣ ገበያ ተኮር ያለመሆን እንዲሁም ዘመናዊ የግብርና ስርዓትን ባለመከተል የምርታማነት ማደግ ችግሮች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ግን ዘርፉን ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ የፖሊሲ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም ዘላቂነትን ታሳቢ ያደረገ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ መቀረጹ፣ ከፍተኛ የማዳበሪያ ድጎማ መደረጉ፣ ከቀረጥ ነፃ የሜካናይዜሽን አቅርቦትና በዲጂታል የተደገፈ የግብርና አገልግሎት መስፋፋቱ፣የተፈጥሮ ሀብትን አውቆ መጠቀም መቻሉና የመሬት ሊዝ መብት መጠናከሩ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን ገልጸው፥ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከ14 እጥፍ በላይ ማደጉን ጠቅሰዋል፡፡ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ፣በተፈጥሮ ጥበቃና ደን መልሶ ማልማት 33 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የግብርና ምርታማነት መጠን ከ56 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሰው፥ የሰብል ምርት በሶስት እጥፍ ማደጉንም ጠቁመዋል፡፡ የግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መጀመሩን ጨምሮ በዘርፉ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ይበልጥ ለመደገፍም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሠረት የግብርና ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የማከናወን ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
ፖለቲካ

በለውጡ ዓመታት የአፋር ክልል ህዝብ እምቅ ሃብቶቹን በማልማት እመርታዊ ማንሰራራት ላይ ይገኛል
Apr 1, 2026 155
ሰመራ፣መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦በለውጡ ዓመታት የአፋር ህዝብ እምቅ ሃብቶቹን በማልማት በተለይም በግብርና፣በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም እና ሌሎችም መስኮች እመርታዊ ማንሰራራት ላይ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ። በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ የመደመር መንግስት ሀገር መምራት ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ፣በኢኮኖሚና ፖለቲካዊ መስኮች እመርታዎች እየተመዘገቡ ቀጥለዋል። በተለይም ታዳጊ የሚል መለያ ተሰጥቷቸው በፖለቲካው መስክ "አጋር" እየተባሉ የነበሩ ከለውጡ በፊት የዳር ተመልካች ነበሩ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ግን ሁሉም ክልሎች በሀገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ እኩል የሚሳተፉበትና የሚወስኑበት እድል ተፈጥሮላቸዋል። በኢትዮጵያ አሳታፊ፣አካታችና ሁሉን አቀፍ የሆነ የማህበራዊ፣ ፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ምህዳር የተፈጠረላቸው መሆኑን ባለፉት ሰባት ዓመታት በተግባር ማየት ተችሏል። በዚህ አንፃር በለውጡ ዓመታት በአፋር ክልል የታየውን ሁለንተናዊ ልማትና የህዝቡን ተጠቃሚነት በተመለከተ ኢዜአ የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ አቶ መሐመድ ዓሊ ጋር ቆይታ አድርጓል። ሃላፊውም በማብራሪያቸው፥ከለውጡ በፊት የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ጉዳይ እንዳይወስን አጋር እየተባለ ተገፍቶ የኖረ መሆኑን አንስተዋል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ አሳታፊ፣ አሰባሳቢ እና የጋራ የሆነ ትርክት በመፈጠሩ የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ፖለቲካ ጉዳይ የዳር ተመልካች መሆኑ ቀርቶ እኩል ተሳታፊና ውሳኔ ሰጪ መሆን ችሏል ብለዋል። የባለፈው ስርዓት ሲያራምደው በቆየው ፖለቲካ የአፋር ክልል ህዝብ አጋር እየተባለ በሀገሩ ጉዳይ የዳር ተመልካች ሆኖ መቆየቱ የሚያስቆጭ መሆኑን አንስተው፥ የመጣው ሀገራዊ ለውጥ ለክልሉ ህዝብ ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ለውጡን ተከትሎ የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ፖለቲካ ጉዳይ የዳር ተመልካች መሆኑ ቀርቶ እኩል ተሳታፊና ውሳኔ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል። የአፋር ክልል ህዝብ በለውጡ ዓመታት እምቅ ሃብቶችን በማልማት በተለይም በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣በቱሪዝም እና ሌሎችም መስኮች እመርታዊ ማንሰራራት ላይ ይገኛል ብለዋል። የክልሉ መንግስት በነፃነት ራሱን በራሱ በማስተዳደር ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የአፋር ክልል ገና ብዙም ያልተነካ እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና የልማት አቅም ያለው በመሆኑ የልማት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
በባህር ዳር ከተማ 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታአማኒና ዴሞክራሲያዊ ሆና እንዲጠናቀቅ በትብብር እየተሰራ ነው
Apr 1, 2026 125
ባህር ዳር፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታአማኒና ዴሞክራሲያዊ ሆና እንዲጠናቀቅ በትብብር እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በባህር ዳር ምርጫ ክልል የሚሳተፋ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በባህር ዳር ምርጫ ክልል 11 ፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ከማስመዝገባቸው ባለፈ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ናቸው። የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሞላ ሁሴን በውይይት በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በከተማዋ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7 ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፖሊሲዎቻቸውን ቀርጸው ለህዝብ እያስተዋወቁ ናቸው ። ፓርቲዎቹ ምርጫው ተአማኒ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ሰብሳቢው ይህም ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል። ፓርቲዎቹ በየጊዜው እየተገናኙ ምርጫውን ስኬታማ ለማድረግ በጋራ በመምከር የመፍትሄ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ ያሉት አቶ ሞላ ከዚህ በተጓዳኝ በሰላምና በልማት ዙሪያ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ ሀገረ መንግስቱን ለማፅናትና የዴሞክራሲ ስርዓቱን ለማስፋት በሚያስችሉ ተግባራት ላይም በቅንጅት አየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተለይም መጪው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፋትሃዊ፣ የህዝብን ተሳትፎና አመኔታ ያረጋገጠ እንዲሆን በጋራ ምክር ቤቱ እየተሰራ ነው ብለዋል። ምርጫ የዴሞክራሲ ስርዓት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህም አባላቶቻቸውን በማስተማር ላይ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በምርጫ ሂደቱ ስኬቶች በጋራ በመስራትና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተነጋግሮ በመፍታት ለምርጫው የላቀ ውጤታማነት ሁሉም ፓርቲ አይተኬ ሚናውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በለውጡ መንግስት እሳቤ የተቀየሰው በሀገር ጉዳይ ተቀራርቦ የመስራት ባህልን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል
Apr 1, 2026 81
ጅማ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦በለውጡ መንግስት በመደመር እሳቤ የተቀየሰው በሀገር ጉዳይ ተቀራርቦ የመስራት ባህልን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የለውጡ መንግሥት የፖለቲካ ዕይታ ፓርቲዎች የተለያዩ አሰላለፎች እና መረዳቶች ቢኖሯቸውም ለጋራ ሀገር ብሔራዊ ጥቅምን መሰረት በማድረግ በትብብር መሥራትን ሥልጣን እስከ ማጋራት የሚገለፅ ነው። ባለፉት የለውጥ ዓመታትም ይኸው ዐቢይ እሳቤ በትብብርና በጋራ መሥራት እውን ሆኖ ወደ ተግባር መለወጡን መመልከት ተችሏል። ይህንንም አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤በለውጡ መንግስት በመደመር እሳቤ የተቀየሰው በሀገር ጉዳይ ተቀራርቦ የመስራት ባህልን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ምሁራኑ በማብራሪያቸው የለውጡ መንግስት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብትና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ለማድረግ የጀመራቸውን ስራዎችን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ደረጄ ገላሳ መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሀገር ግንባታ ሂደት በጋራ መስራቱ ለሰለጠነ ፖለቲካ መሰረት መጣሉን ተናግረዋል። ይህም ፓርቲዎቹ በፖለቲካ ርዕዮት ቢለያዩም በሀገር ጉዳይ ተቀራርበው የመስራት ባህል እንዲያዳብሩ የራሱ ድርሻ እንዳለው አክለዋል። ተግባሩም ከዚህ ቀደም የነበረን አፍርሶ የመገንባት እሳቤን በማስቀረት በመደመር እሳቤ ሀገርን የማስቀጠል መርህን መከተሉ የሚበረታታ ነው ብለዋል። የለውጡ መንግስት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመንግስት የስራ ኃላፊነቶች ላይ ማካተቱና አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት የተጀመሩ ጥረቶችም ሊጠናከሩ የሚገባቸው ተግባራት መሆናቸውን አመልክተዋል። ለሀገር የሚበጁ የተለያዩ ሀሳቦችን ወደ አንድ ማምጣት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር መሀመድ አርባኢ በበኩላቸው፥ በለውጡ ዓመታት የታዩ የፖለቲካ ምህዳሩን የማስፋት ተግባራት በሀገር ጉዳይ ተቀራርቦ መስራት እንዲለመድ መሰረት መጣላቸውን ተናግረዋል። በትብብርና በጋራ የመሥራት እሳቤው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመገፋፋት ይልቅ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ትልቅ እገዛ አድርጓል ነው ያሉት። ይህን የዴሞክራሲያዊ ልምምድን በማስቀጠል አሳታፊ የመንግስት ስርዓትን ማስቀጠል ለሀገራዊ እድገት የማይተካ ድርሻ እንዳለውም ጠቁመዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይህን መልካም ጅማሮ በማስቀጠል 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያን ጥቅም ያስቀደመ አቋም ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።
የመንግስት ያላሰለሰ የሰላም ጥረትና የታጣቂዎች በጎ ምላሽ ዘላቂ ሰላም እያመጣ ነው-ነዋሪዎች
Apr 1, 2026 124
ወልድያ፤መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦የመንግስት ያላሰለሰ የሰላም ጥረትና የታጣቂዎች በጎ ምላሽ ዘላቂ ሰላም እያመጣ መሆኑን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ። በጫካ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት ከግጭት ወጥተው የሰላምን አማራጭ ተቀብለው እንዲመጡ መንግስት ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ አመራሮችና አባሎቻቸው ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላም መጥተዋል። ከዚህ በፊት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃባ እና ሌሎችም የሰላምን መንገድ መርጠው መምጣታቸው ይታወሳል። በትናንትናው እለት ደግሞ በክልሉ የሚንቀሳቀሰውና ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ሃይል ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉዬ ከመንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ከእነ አጃቢዎቹ ላሊበላና አካባቢው ወደ ሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት በሰላም መግባቱ ይታወቃል። በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አቶ በላይ ገረመው እና አቶ ሲሳይ ጸጋዬ፤ በተለይም የመንግስት ያላሰለሰ የሰላም ጥረት ትልቅ ስኬት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ታጣቂዎችና አመራሮቻቸው ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸው በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት እውን የሚያደርግ ይሆናልም ብለዋል። በዞኑ ላሊበላ ከተማ የሚኖሩት አቶ ሲሳይ ታደሠ፤በላስታና አካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ መምጣቱ ለአካባቢው ነዋሪ ትልቅ እፎይታ መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢው ቀደም ሲል የነበረው ግጭት በነዋሪው ዘንድ ብዙ ጉዳት ማድረሱን አስታውሰው፥ በመንግስት ተደጋጋሚ ጥረት፣በህዝቡ የሰላም ጽኑ አቋም የሚፈለገው ውጤት በመምጣቱ ተደስተናል ብለዋል። ከግጭት ጥፋትና ውድመት እንጂ አንዳችም የሚመጣ ለውጥና የሚገኝ ውጤት እንደሌለ ባለፉት አመታት አይተነዋል ያሉት አቶ ሲሳይ ሁላችንም ለሰላም ዘብ መቆም አለብን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በዞኑ በመቄት ወረዳ የ029 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ በላይ ተሻለ እና በግዳን ወረዳ የሚኖሩት አቶ ዘውዱ አስራደ፤ የእርስ በርስ ግጭት ትርፉ ልማትን ማውደም፣ የወንድማማችነት ትስስርን ማበላሸትና ማህበረሰብን መጉዳት እንጂ ሌላ ትርፍ የሌለው መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የታጣቂ ቡድኖች በመንግስት የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ጊዜ ሳያጠፉ ተቀብለው በመምጣት ማህበረሰቡን በመቀላቀል በሰላም መኖርን መምረጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በዚህ ረገድ በላስታና አካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን ወታደራዊ አዛዥ የነበረው ኮማንዶ ፍቅሩ፤በትናንትናው እለት የመንግስትን ጥሪ ተቀብሎ መምጣቱ ለአካባቢው ነዋሪ እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። በጫካ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ሽፍቶች የመንግስትን የሰላም አማራጭ መቀበላቸው ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልጸው፥ ሌሎችም ወደ ሰላም እንዲመጡ ጠይቀዋል። የሰሜን ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ መብራቱ አሰፋ፤ በዞኑ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ አካላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እየገቡ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በተለይም በቡግና፣ላሊበላ፣ ላስታ፣ መቄትና ግዳን ወረዳዎች ለሚገኘው ህዝብ የሰላም እፎይታ የሰጠ ስለመሆኑ ገልጸዋል። የመንግስት ያላሰለሰ የሰላም ጥረት እንዳለ ሆኖ የአካባቢው ህዝብ ለሰላም ያሳየው ጽኑ አቋምና የሰላም ጥረት ለስኬቱ ትልቅ አቅም መሆኑን አንስተው፥ በቀጣይም መሰል ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የመጀመሪያው ዙር መድረክ መካሄድ ጀመረ
Apr 1, 2026 110
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የመጀመሪያው ዙር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መግለጹ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች፣በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ታድመዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልልና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ የውይይት መድረኮች ማዘጋጀቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ የሀገራዊ ምክክሩን የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ስራ በትግራይ ክልል ማድረግ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ባለመኖሩ የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምረናል ብለዋል። በዚህ ዙር ያልተሳተፉ የትግራይ ክልል ተሳታፊዎችን በቀጣይ ለማወያየት ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። መድረኩ አጀንዳ ከማሰባሰብ ባለፈ ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮች የሚለዩበት መሆኑንም ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አካታችና ገለልተኛ ሆኖ እንደሚሰራ ገልጸው፥ የትግራይ ክልል በምክክሩ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆን እድል መመቻቸቱን ገልጸዋል። ከጥላቻ ፍቅርን ከውዝግብ ምክክርን በማስቀደም ለሁላችንም የምትሆን ሀገር መገንባት የሚያስችል ውይይት የሚደረግበት መድረክ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ እስካሁን የአጀንዳ ማሰባሰብንና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያካሄድ መቆየቱን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን ያካሄዳቸው ውይይቶች አሳታፊ እና አካታች መሆናቸውን ገልጸዋል። ኮሚሽኑ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት ባህል እንዲሆን የማድረግ ዓላማን ይዞ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና የቀጣናውን ሰላም የሚያስጠብቅ አስተማማኝ ሠራዊት ተገንብቷል
Mar 31, 2026 574
አዲስ አበባ፤መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦በሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን ክብርና ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም የቀጣናውን ሰላም የሚያስጠብቅ አስተማማኝ ሠራዊት መገንባቱን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለጹ። የመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የለውጡ መንግሥት ተቋማዊ ግንባታን የሀገረ መንግሥት ግንባታ ዋና ምሰሶ አድርጓል። በዚህም ጠንካራና አስተማማኝ የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን መገንባት ከሀገራዊ የሪፎርም አምዶች መካከል አንዱ በማድረግ ስኬታማ ተግባራትን አከናውኗል። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ተቋማዊ አውዶች ሰፊ ሪፎርም አድርጓል። ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጣ ጥቃትን የሚመክት ብቁ የምድር ኃይል፣የአየር ኃይል፣ የሜካናይዝድ፣የባሕር ኃይል፣ የልዩ ዘመቻ እና የሳይበር ኃይል መገንባቱንም ነው ያነሱት። የሀገር ኩራት የሆነ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመገንባት ረገድ በሰው ሃይል፣በአደረጃጀትና በውጊያ ቴክኖሎጂ የላቀ የለውጥ ሥራ በማከናወን ጠንካራ ተቋማዊ ቁመና መፈጠሩንም ገልጸዋል። ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያ ግዳጁን በላቀ ብቃት የሚወጣና ጦርነትን በሩቁ የሚቀለብስ አስተማማኝ ሠራዊት እንዲኖራት አስችሏል ነው ያሉት። መከላከያን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከማስታጠቅ ባለፈ፣ ዓለም የደረሰበትን የውጊያ ቴክኖሎጂ የሚጠቀምና በአግባቡ የሚመራ ብቁ የሰው ኃይልን የማብቃት ሥራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። በወታደራዊ መሣሪያዎች ራስን ለመቻል የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካትም፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ ስኬታማ ሪፎርም በማድረግ ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲመጡ ተደርጓል ነው ያሉት። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተሰማራበት ቦታ ሁሉ የሰላም ማስከበር ግዳጆችን በብቃት በመወጣት በቀጣናው ተፈላጊ ሠራዊት መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ለቀጣናው ሠላም መረጋጋት የኢትዮጵያ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ያረጋገጠ ውጤት አስመዝግቧል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የደህንነት እና ሰላም ችግሮች በአፍሪካውያን እንደሚፈቱ ጽኑ እምነት አላት ያሉት ሚኒስትሯ፤ ለዚህም አፍሪካውያን የሰላምና ደህንነት ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ እየሠራች ነው ብለዋል። ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር በመከላከያ ጉዳዮች በትብብር ለመሥራት ስምምነቶች መደረጋቸውን በመጠቆም፥ኢትዮጵያ ልምዷን ለማካፈልና አጋርነቷን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በአቅም፣በዲሲፕሊን፣ በስነ ልቦና እና በአስተሳሰብ ከየትኛውም ወገንተኝነት የጸዳ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት መገንባቱንም ሚኒስትሯ አንስተዋል። በዚህም ሠራዊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ ሆኖ ለሕገ-መንግሥቱና ለሀገር ሉዓላዊነት ብቻ የሚቆምበት መሠረት ተጥሏል።

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድና ተጠቃሚ በማድረግ ያሳካቻቸው ውጤቶች ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷን እያሳደጉ ነው
Apr 1, 2026 86
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድና ተጠቃሚ በማድረግ ያሳካቻቸው ውጤቶች ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷን እያሳደጉ መሆኑን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን ገለጹ። ኢትዮጵያ ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ተቀብላ እያስተናገደች እንደምትገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ ቀጥሎ ሁለተኛ ሀገር ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በሰባተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል። የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ስደተኞች የልማት አጋር ሆነው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥራለች። በፈረንጆቹ 1951 የወጣውን ዓለም አቀፉን የስደተኞች ኮንቬንሽን በመተግበር ስደተኞችን በላቀ ደረጃ እየተንከባከበች መሆኑን ጠቁመው፥ ስደተኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ስደተኞች ትምህርት፣ጤና እና የምግብን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ በርካታ ተጨባጭ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተናግረዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ፥ ስደተኞች ከተቀባይ ማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን የሚያጠናክሩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው። ስደተኞች ተጠልለው በሚገኙባቸው አካባቢዎች ካለው ተቀባይ ማህበረሰብ ጋር መስተጋብራቸውን በማጠናከር በልማት እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ የስደተኞችን መብቶች በማክበር፣ ከዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሏ እንዲሁም ስደተኞችን በመንከባከብ እና ተጠቃሚ በማድረግ ያሳካቻቸው ውጤቶች ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷ እንዲጎላ እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉና ትምህርታቸውን ተከታትለው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ስደተኞች የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በመሆን ስሟን በበጎ እያስጠሩ እንደሚገኙ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፥ ይህም ለቀጣናዊ ትስስር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው
Apr 1, 2026 58
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በለውጡ ዓመታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት አንዱ በትምህርት ዘርፉ ያጋጠሙ ስብራቶችን ከመሰረቱ በመለወጥ ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ማስቻል ነው። ትምህርት ቤቶችን ማሻሻልና አዳዲስ ትምህርት በቶችን መገንባት፣ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፣ የትምህርት ግብዓት ማሟላት፣ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር እና ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት ደግሞ በዘርፉ ከተከናወኑ ተግባራት ዋነኞቹ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ካሳሁን ገላና(ዶ/ር) በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከሩን ገልጸዋል። በክልሉ በዚህ አመት የትምህርት ገበታ ላይ ያሉ 180 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን የተሻለ ነጥብ እንዲያስመዘግቡ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል። በዚህ መሰረት ከባለፉት አመታት ልምድ በመውሰድ በማጠናከሪያ ትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት አይነቶችን በመለየት ድጋፍ እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የመማር ማስተማር ሂደቱን ማጠናከር፣ ዋቢ መጽሃፍትን ማሟላት፣ ቤተ መጻህፍትና ቤተ ሙከራዎችን ማስፋትና ግብዓቶችን ማሟላት እንዲሁም ለመምህራን ስልጠና መስጠት በሰፊው ከተሰሩት መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ አሁን ላይ የመማር ማስተማር ተግባሩ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አንስተው፣ በቀሩት ወራት ደግሞ በመምህራን እገዛ ተማሪዎች በግልም ሆነ በቡድን የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚለማመዱበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል። ከዚህ በፊት ተማሪዎች መደበኛውን ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ እንደነበረ ያስታወሱት ምክትል ሀላፊው ዘንድሮ የተማሪዎችን ውጤት በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ከመስከረም ወር ጀምሮ ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል። እንዲሁም ለአዳሪና ልዩ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የበለጠ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በተለያየ ሁኔታ የማጠናከሪያና ሌሎች ድጋፎች መደረጉን ጠቅሰዋል። አጠቃላይ በክልሉ በ1ሺህ 406 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በተሻለ ሁኔታ እያዘጋጀን ነው ብለዋል። በተለይ ለሴት ተማሪዎች በጋራ ከሚደረግላቸው ድጋፍ በተጨማሪ እራሳቸው በመረጡት የትምህርት አይነት ላይ በተመረጡ መምህራን የተለየ የማጠናከሪያ ድጋፍ እያገኙ መሆኑን አንስተዋል። የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል ረገድ የወላጆች እገዛ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፣ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ከወላጅ ጋር ጥብቅ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።
በቀጣዮቹ ጊዜያት የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመመለስ በትኩረት ይሰራል-ረሻድ ከማል (ዶ/ር)
Mar 31, 2026 125
አዲስ አበባ፤መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦በቀጣዮቹ ጊዜያት የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) ገለጹ። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ምስረታ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ላለፉት ሶስት ቀናት "በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ" በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ ቆይቷል። በመርሀ ግብሩ በኮርፖሬሽኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ ህንጻዎች የተመረቁ ሲሆን፤ሀገራዊ ለውጡን መነሻ አድርጎ በተቋማዊ ሪፎርሙ የተመዘገበውን ስኬት የሚያስቃኝ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ክፍት ሆኖ ቆይቷል። በዛሬው ዕለትም የበዓሉ የማጠቃለያ መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ለተቋሙ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የበዓሉ ዓላማ በባለፉት ዓመታት የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ከክፍተቶችም ትምህርት ለመውሰድ ነው። ተቋሙ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ስኬታማ ጉዞ ማድረጉን ገልጸው፤ በተቋሙ የተከናወነው የሪፎርም ስራ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። ተቋሙ ባለፉት ሀምሳ ዓመታት በበርካታ ውጣ ውረዶች ማለፉን ገልጸው፤ ኮርፖሬሽኑ አሁን ላለበት ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ የነበራቸውን አካላት አመስግነዋል። በቀጣይም በርካታ ስራዎች በእቅድ መያዛቸውን ገልጸው፤ የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል። ኮርፖሬሽኑ ለሰው ልጅ መሰረታዊ በሆነው የቤት ፍላጎት ላይ እንደሚሰራ ገልጸው፤ ባለድርሻ አካላት ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሠላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና ማጠናከር አለባቸው
Mar 31, 2026 181
አሶሳ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሠላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና ማጠናከር እንዳለባቸው ተመላከተ። “ሠላም እና አካታች ልማትን ለማረጋገጥ የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ለአራተኛ ጊዜ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምሁራን ጉባኤ ተካሄዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማር ስራቸው ባለፈ የህዝቦችን ትስስር በሚያጠናክሩና ሰላምን በሚያፀኑ ተግባራት ላይ ማተኮር አለባቸው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሠላም እሴት ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተጠናከሩ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት። ዩኒቨርሲቲው የሚያካሄዳቸው ማህበረሰብ ተኮር የምርምር ስራዎች ለክልሉ ልማት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጨማሪ አቅም እየፈጠሩ መሆኑንም ገልጸዋል። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ከማል አብዱራሂም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የዕውቀት መፍለቂያ እና የምርምር ተቋም ከመሆን ባሻገር ለሰላም መስፈን የድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል። በተለይ በሠላም ግንባታ፣ በልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚያደርገውን ጥናትና ምርምር ወደ ተግባር በመቀየር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በመድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አስካለች አልቦሮን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎችና ምሁራን ተገኝተዋል።
ኢኮኖሚ
በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ናቸው
Apr 1, 2026 38
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ። "ቃል በተግባር ፣ ከምርጫ እስከ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አዘጋጅነት የክልል መንግስት ቢሮዎች እና ተቋማት የተሳተፉበት ኤግዚቢሽን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል። የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ህዝብ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የለውጥ ዓመታቱ በክልሉ የነበሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍትሄ ያገኙበት እና ትክክለኛ የብልጽግና ጉዞ የተጀመረበት መሆኑንም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስትም በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራቱ ከተስፋ ወደ ተጨበጠ ብርሃን ሽግግር ለማድረግ እያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል። ከኢኮኖሚ ልማት አንጻርም በግብርናው ዘርፍ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትልቅ ውጤት መምጣቱን ጠቅሰው፤በኢንዱስትሪ፣በማዕድንና በቱሪዝም ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የክልሉ መንግስት ተነጥለው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላምን አማራጭ እንዲከተሉ በማድረግ ረገድ ትልቅ ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል። በአጠቃላይ በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንም ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉ መንግሥት የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ መሆኑን አንስተዋል። የክልሉ መንግስት በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የልማት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን የቻለበት መሆኑንም ጠቁመዋል። ኤግዚቢሽኑ ህዝቡ በመንግስት ስራዎች ላይ ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረውና የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል። በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የተገኙት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፤ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ሀገሪቱን ከጥገኝነት ወደ አምራችነት የቀየሩ ታሪካዊ ስራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንም የመንግስትን ፖሊሲዎች፣ስልቶችና የልማት ውጤቶች ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል
Apr 1, 2026 119
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የግብርና ምርታማነት ለምግብ ሉዓላዊነትና ለሀገራዊ ክብር" በሚል መሪ ሐሳብ በለውጡ ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ እውን ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣የግብርናው ዘርፍ ከአምስቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ሆኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ረገድ ስኬት እያስገኘ ነው፡፡ እንደ የበጋ ስንዴ ምርት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ ሌማት ትሩፋት፣ ኩታ ገጠም፣ የግብርና መካናይዜሽን እንዲሁም ሌሎችም ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መንግስት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በዘርፉ ባለ አነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን በበቂ ሁኔታ አለመደገፍ፣ ገበያ ተኮር ያለመሆን እንዲሁም ዘመናዊ የግብርና ስርዓትን ባለመከተል የምርታማነት ማደግ ችግሮች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ግን ዘርፉን ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ የፖሊሲ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም ዘላቂነትን ታሳቢ ያደረገ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ መቀረጹ፣ ከፍተኛ የማዳበሪያ ድጎማ መደረጉ፣ ከቀረጥ ነፃ የሜካናይዜሽን አቅርቦትና በዲጂታል የተደገፈ የግብርና አገልግሎት መስፋፋቱ፣የተፈጥሮ ሀብትን አውቆ መጠቀም መቻሉና የመሬት ሊዝ መብት መጠናከሩ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኩታ ገጠም የሚታረስ መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን ገልጸው፥ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከ14 እጥፍ በላይ ማደጉን ጠቅሰዋል፡፡ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ፣በተፈጥሮ ጥበቃና ደን መልሶ ማልማት 33 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የግብርና ምርታማነት መጠን ከ56 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሰው፥ የሰብል ምርት በሶስት እጥፍ ማደጉንም ጠቁመዋል፡፡ የግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መጀመሩን ጨምሮ በዘርፉ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ይበልጥ ለመደገፍም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሠረት የግብርና ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የማከናወን ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከነበረው እጅጉን በተሻለ ለንግድ ዝግጁ ናት
Apr 1, 2026 61
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከነበረው እጅጉን በተሻለ ለንግድ ዝግጁ መሆኗን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ህንድ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13.1 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን አመልክቷል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ መሆናቸውን ገልጿል። የውጭ ምንዛሬ ተመን ሊበራላይዜሽን፣ እና የባንክና ቴሌኮም ዘርፎችን ለንግድ ማህበረሰቡ ክፍት ማድረግ የመሳሰሉ ቆራጥ እርምጃዎች ግልጽና ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፍጠራቸውን በተጨባጭ ማረጋገጡን ነው ነው ያስታወቀው። ይህም በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አማካኝነት ለዓለም አቀፍ ገበያ ምቹ መዳረሻን መፍጠሩ ተጠቅሷል። ይህ ዕድገት በሁሉም ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በግልጽ እየታየ እንደሚገኝ የገለጸው ጽህፈት ቤቱ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተንተራሰው የሀገራችንን የታዳሽ ኃይል ሀብትን በመጠቀም በሶላር ምርት እና በሃይድሮጅን ፕሮጀክቶች ላይ የተገኘው እመርታ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማዕድን ዘርፍ ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራበት እንደሚገኝ አመልክቷል። የኢንዱስትሪ ዕድገታችን አዲስ በሚገነቡት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እየተፋጠነ ሲሆን፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በልህቀት እየተመራ መሆኑ ተገልጿል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር እና በባህላዊ ቅርሶቻችን የታጀበችው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ መሆኗንም እንዲሁ። ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለላቀ አጋርነት እንጋብዛለን፤ ኢትዮጵያ ከነበረው እጅጉን በተሻለ ለንግድ ዝግጁ ናት ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪውን አቅርቧል።
ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ታሪክ ቀያሪ ስኬቶች እንድታስመዘግብ አድርጓል
Apr 1, 2026 130
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2018(ኢዜአ) ፦ ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የምርታማነት አቅም በማጎልበት የምግብ ሉዓላዊነትን እንድታረጋግጥ የሚያስችሉ ታሪክ ቀያሪ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የግብርና ምርታማነት ለምግብ ሉዓላዊነትና ለሀገራዊ ክብር" በሚል መሪ ሐሳብ በለውጡ ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ እውን ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣ ግብርናው የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ከሚደግፉ አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ሆኖ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል። በለውጡ ማግስት ዘርፉን ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ አሰራር ለማሸጋገር በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት፣ በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል ባለፈ ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ማምረት ተችሏል። በመድረኩም የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ፣ የግብርና ዘርፍ ሙያተኞችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ የግብርና ዘርፍ በምግብ ደኅንነት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በወጪ ንግድና በአየር ንብረት ላይ ግንባር ቀደም የኢኮኖሚ ድርሻ አለው ብለዋል። ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የነበረው የኢትዮጵያ የግብርና ሥርዓት በኋላቀር አሰራርና በአየር ንብረት ለውጥ ይፈተን እንደነበር አስታውሰው አዝጋሚ የምርታማነት የአስተራርስ ሥርዓቱም የግብርናው ዘርፍ ታሪክ የሚያጎደፍና ምርታማነትን የሚያቀጭጭ ሂደቶች ውስጥ ማለፉን አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስትም የግብርና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የፖሊሲና ስትራቴጂ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አንስተዋል። በዚህም ሀገራዊ ለውጡ የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያውያን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል ታሪክ ቀያሪ የምርታማነት ምዕራፍ ውስጥ ገብቷል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የተደረገው የግብርና ምርታማነት የመኸርና የበጋ መስኖ ስንዴ እመርታዊ ውጤት መገኘቱን አስታውቀዋል። የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የፖሊሲ አቅጣጫም ለዘመናት ስንዴ ሲሰፈርለት የነበረን ሀገርና ህዝብ የምግብ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ እራስን ወደ መቻል እመርታዊ ሽግግር እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል። በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ አሻራም የምግብና የሥነ- ምግብ ሥርዓትን የሚያሻሽል ውጤታማ የምርታማነት አቅም መፈጠሩን አንስተው በቀጣይም የኢትዮጵያን የተሟላ የግብርና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሠይፈ ደርቤ፥ የፓናል ውይይቱ የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የግብርናውን ጉዞና ስኬቶች ለመዳሰስ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፣ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት እንዲሁም ገፅታን መገንባትና ማስጠበቅ የኢዜአ ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ የመጋቢት 24 ዋዜማ የሚካሄደው የግብርና ምርታማነት ለምግብ ሉዓላዊነትና ሀገራዊ ክብር ወሳኝ በመሆኑም ፓናሉ መዘጋጀቱንና ቀጣይነት እንደሚኖረውም ተናግረዋል። የግብርና ምርታማነትን በመጎናጸፍ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ትርክትን የመቀየርና የተረጂነት እሳቤን የመስበር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር መድረኩን እንዳዘጋጀው አስረድተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ 7ኛውን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሚዛንና የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት ለመተግበር እየሠራች ነው
Apr 1, 2026 36
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ስርዓቷን ለማዘመን 7ኛውን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሚዛንና የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት ለመተግበር እየሠራች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሀፅዮን ገለጹ። የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025- (System of National Accounts 2025) የአንድን ሀገር አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወይም የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (GDP) ለመለካት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ መመሪያ ነው። የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025- 7ኛው የክፍያ ሚዛን ማኑዋል- BPM7 (Balance of Payments Manual 7th Edition) በአንድ ሀገር እና በሌላው ዓለም መካከል ያለውን የገንዘብና የንግድ ልውውጥ (የክፍያ ሚዛን) ለመመዝገብ የሚያገለግል መመሪያ ነው። የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት እና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት በክፍያ ሚዛን (BPM7) እና በ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት (SNA 2025) ላይ ያተኮረ መድረክ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሐ-ፅዮን በዚሁ ወቅት አፍሪካ እ.ኤ.አ የ2008 የብሔራዊ ሂሳብ አያያዝ ስርዓትን (SNA 2008) እና የክፍያ ሚዛን ማኑዋል (BPM6) በመተግበር ረገድ የሚደነቅ እድገት አስመዝግባለች ብለዋል። ይሁን እንጂ ከዓለም ተለዋወጭ ሁኔታ አንጻር የኢኮኖሚ ሽግግርንና መዋቅርን ሙሉ በሙሉ ለመረዳትና ለመለካት አሁንም ከፍተኛ ክፍተቶች መኖራቸውን አንስተዋል። እንደ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ኢ-መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች፣ ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶች እና መሰል ጉዳዮች በቀደሙት አሠራሮች ለመለካት አስችጋሪ መሆኑንም በአብነት ጠቅሰዋል። አዲሶቹ የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት 2025ና 7ኛው የክፍያ ሚዛን ማኑዋል የስታትስቲክስ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የስታትስቲክስ ስርዓትን ለማዘመን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስታትስቲክስ ሥርዓቶቹን ወደ ተግባር ለማስገባት አስቀድማ ዝግጅት መጀመሯንም አንስተዋል። በኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርትን ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር መልሶ የማደራጀትና የማጣጣም ሥራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መሪነት የክፍያ ሚዛን ስታትስቲክስን የማሻሻልና የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎችን ጥራት የማሳደግ ተግባራት በትኩረት እየተተገበሩ መሆኑን አብራርተዋል። ዘመናዊ የስታትስቲክስ ሥርዓት መዘርጋቱ የአጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እምነትን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት የኢኮኖሚ ስታትስቲክስ ዳይሬክተር አዱም ጋጎሉም በበኩላቸው፣ በአህጉሪቱ የስታትስቲክስ ሥርዓቶችን ለማጠናከርና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ከአፍሪካ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የ2025 የብሔራዊ ሂሳቦች ሥርዓት (SNA) እና የክፍያ ሚዛን (BPM7) በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በቀጣናዊ ትስስርና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተሻለ የፖሊሲ ቀረጻ እንዲኖር ያስችላሉ ነው ያሉት። በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የስታትስቲክስ መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር ጂም ቴብሬክ፤ በአፍሪካ የስታትስቲክስ ዘርፍን ለማዘመን ዓለም አቀፍ ሥርዓቶችን ታሳቢ ያደረገ ሥራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም የአፍሪካ ህብረት ስታትስቲክስ ኢንስቲትዩት ስለ ሀገራት ኢኮኖሚና ዓለም አቀፋዊ ትስስር አስተማማኝ መረጃ በመስጠት ረገድ ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋት ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ይሰራል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Apr 1, 2026 55
አሶሳ፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋት ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ። የአሶሳ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በክልሉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋት ለዜጎች ወጪ ቆጣቢ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እያስቻለ ነው። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀላል እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑንም አንስተዋል። የአሶሳ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉ በከተማዋ እየተከናወኑ ለሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች አጋዥ ከመሆን ባለፈ የዲጂታል አገልግሎትን ተደራሽ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም በበኩላቸው ማዕከሉ በከተማዋ የሚሰጡ ወሳኝ አገልግሎቶችን በማዘመን የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ ያግዛል ነው ያሉት። ማዕከሉ በአራት የክልል እና በሁለት የፌዴራል ተቋማት የተጀመረ ሲሆን 23 የተለያዩ አገልግሎችን እንደሚሰጡ ነው የተናገሩት። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመተባበር አገልግሎቶችን ይበልጥ የሚያዘምን ቴሌሳይን (teleSign) የተሰኘ ዲጂታል ሶሉሽን አስጀመረ
Mar 31, 2026 373
አዲስ አበባ፤መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር የመንግስት አገልግሎቶችን ለማዘመን ያለመ ቴሌሳይን (teleSign) የተሰኘ የዲጂታል ሶሉሽን አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕወት ታምሩ፤ኩባንያው የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግር እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶችን በስፋት እየዘረጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አዲሱ ቴሌሳይን የተሰኘው ዲጂታል ሶሉሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን አስረድተዋል። ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ውጤት አስተማማኝ የዲጂታል ማንነት ማረጋገጫንና ህጋዊ ተቀባይነት ያለውን የዲጂታል ፊርማ ስርዓት ወደ ስራ የሚያስገባ ነው ብለዋል። ይህም የመንግሥት አሠራሮችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት። አሠራሩ በተለይም አሰልቺ ቢሮክራሲን በመቀነስ፣የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳደግ እና ሀገራዊ የዲጂታል ተጠቃሚነትን በማስፈን ረገድ የላቀ ፋይዳ እንደሚኖረው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። የዲጂታል አገልግሎት መስጫው ዜጎች ያለ ምንም መልክዓ-ምድራዊ ገደብ የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል። ይህም ሀገሪቱ ወደ ሙሉ ዲጂታል መንግሥት (E-Government) የምታደርገውን ሽግግር በእጅጉ የሚያፋጥን ሲሆን፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች አገልግሎቶችን በፍጥነት፣ በብቃትና በታማኝነት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል። ኢትዮ ቴሌኮም መሰል ዘመናዊ የዲጂታል መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ሀገራዊ የዲጂታል ጉዞን የመደገፍና የማብቃት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አፅንኦት ሰጥተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፤ ሚኒስቴሩ የተጣለበትን ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን ተቋማዊ ለውጥ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አገልግሎት አሰጣጡን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ሲሆን፥የዲጂታል አገልግሎት መጀመሩም ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመቀናጀት የቴሌሳይን (teleSign) እና ዲጂታል ሞፋ (Digital MoFA) የተሰኙ ቴክኖሎጂ መር አገልግሎቶችን በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል። የዲጂታል ሥርዓቶቹ ከየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲህ አይነት ዘመናዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲናፍቁ ለነበሩ የዲያስፖራ አካላትና መላው ዜጎች ትልቅ የምስራች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በተጨማሪ ህጋዊ ተቀባይነት ያለውና የሰነዶችን ኦሪጅናልነት የሚያረጋግጥ የዲጂታል ፊርማ ስርዓትን ስራ ላይ ማዋል ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል። የላቁ የኢንክሪፕሽን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሰነዶች እንዳይለወጡና እንዳይጭበረበሩ ብሄራዊ ዋስትና መስጠት እንዲሁ። አገልግሎቱን ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር በማስተሳሰር፣ የተገልጋይ ማንነት ማረጋገጫ ስርዓት መዘርጋቱንም ጠቅሰዋል። ዲጂታል አገልግሎቱ በውጭ ጉዳይ፣በሰነዶች ማረጋገጫ እና በፍትህ ሚኒስቴር መካከል የተቀናጀ የመረጃ ፍሰት እንደሚፈጥርም አንስተዋል።
በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ተደራሽ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታን ለማሳደግ እየተሰራ ነው
Mar 31, 2026 80
ባሕርዳር፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታን ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አጋር ተቋማትን ያሳተፈ ወርክ ሾፕ በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ የቻለ ይግዛው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎች ለምተው በተቋማት ተግባራዊ እንዲሆኑ ተደርጓል። የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር፣ በመፍጠር፣ በማልማትና በማሻሻል ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ስራዎች የማዋል ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት የግብርናውን ምርታማነት ለማሳደግ፣ የማዕድንና የቱሪዝም ብሎም ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎችን ማዘመን የሚያስችሉ አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ እየተቻለ ነው ብለዋል። የዛሬው መድረክም የከፍተኛ ትምህርት እና የሌሎች ተቋማት ትስስርን የማጠናከር ዓላማ ያለው መሆኑንም አስረድተዋል። የአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ልማትን ለማረጋገጥ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በብዛትም ሆነ በጥራት መጠቀም ይገባል። በተለይም የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን በማድረግ፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየን(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፋን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በዚህም የክልሉን የገቢ አሰባሰብ ያዘመነ ውጤታማ ቴክኖሎጂ ለምቶ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ብቃት ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመጠቀም በትብብር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
ስፖርት
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ52 ዓመታት በኋላ ለዓለም ዋንጫ አለፈች
Apr 1, 2026 69
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የክፍለ አህጉራት የመጨረሻ ማጣሪያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጃማይካን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በሜክሲኮ አክሮን ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ በመጠናቀቁ ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርቷል። በጭማሪ ሰዓት የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ አክሴል ቱዋንዜቤ በ100ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። የጨዋታው ኮከብም ሆኗ ተመርጧል። በጨዋታው የማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር የተሻለ ብልጫ በመውሰድ ተጫውታለች። ውጤቱን ተከትሎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ52 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ በማለፍ ታሪክ ሰርታለች። የማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ1974 በጀርመን (በወቅቱ አጠራሯ ምዕራብ ጀርመን) አስተናጋጅነት በተካሄደው 10ኛው የዓለም ዋንጫ ነው። አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በውድድሩ ላይ ትከፈላለች። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የምትሳተፍ 10ኛ የአፍሪካ ሀገርም ሆናለች። ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ግብጽ፣ ኮትዲቯር፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጋና እና ኬፕ ቨርዴ ለዓለም ዋንጫ ያለፉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው። ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በዓለም ዋንጫው በምድብ 11 ከፖርቹጋል፣ ኡዝቤኪስታን እና ኮሎምቢያ ጋር ጨዋታዎቿን ታደርጋለች። አፍሪካ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 10 ሀገራት በዓለም ዋንጫው ታሳትፋለች። ጃማይካ ከ28 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው የመመለስ ውጥኗ አልተሳካም።
ጣልያን ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነች
Apr 1, 2026 52
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የአውሮፓ ዞን የፍጻሜ ማጣሪያ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል። ትናንት ማምሻውን በቢሊኖ ፖልጄ ስታዲየም በተካሄደውጨዋታ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና ጣልያንን 4 ለ 1 በመለያ ምት አሸንፋለች። ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ሃሪስ ታባኮቪች ለቦሲኒያ፣ ሞይስ ኪን ለጣልያን ግቦቹን አስቆጥረዋል። የጣልያኑ አሌሳንድሮ ባስቶኒ በ41ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። በጭማሪ 30 ደቂቃ ተጨማሪ ጎል ባለመቆጠሩ አሸናፊውን በመለያ ምት መለየት ግድ ሆኗል። በዚህ ቦሲኒያ 4 ለ 1 በማሸነፍ ከ12 ዓመታት በኋላ ለዓለም ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች። ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ቦሲኒያ ለሁለተኛ ጊዜ በዓለም ዋንጫው ትሳተፋለች። ጣልያን ከ20ኛው የዓለም ዋንጫ በኋላ ዓለም ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ የመመለስ ህልሟ አልተሳካም። አዙሪዎቹ ለሶስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ማለፍ አልቻሉም። በሌላኛው ጨዋታ ስዊድን ፖላንድን 3 ለ 2 አሸንፋለች። በስትሮውበሪ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ኢላንጋ፣ ጉስታፍ ላገርቢልክ እና ቪክቶር ዮኮሬሽ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የአርሰናሉ አጥቂ ዮኮሬሽ በ88ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ስዊድንን ለዓለም ዋንጫ አሳልፏታል። ኒኮላ ዛሌውስኪ እና ካሮል ስዊዴርስኪ ለፖላንድ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በፋዲል ቮክሪ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቱርክዬ ኮሶቮን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ኬረም አክቱርኮግሉ ግቧን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ቼክ ሪፐብሊክ ዴንማርክን በመለያ ምት 3 ለ 1 አሸንፋለች። ሁለቱ ቡድኖች በ12ዐ ደቂቃ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። በኢፒኢቲ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፓቬል ሱልች እና ላዲስላቭ ክሬጄቺ ለቼክ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ዮአኪም አንደርሰን እና ካስፐር ዋርትስ ሆግ ለዴንማርክ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ጨዋታው በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ በመጠናቀቁ ምክንያት ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርቷል። ላዲስላቭ ክሬጄቺ ለቼክ፣ ዋርትስ ሆግ በጭማሪ ሰዓት ግብ አስቆጥረዋል። ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት አምርተው ቼክ ሪፐብሊክ 3 ለ 1 በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ አልፋለች። ውጤቱን ተከትሎ ስዊድን፣ቱርክዬ፣ቼክ ሪፐብሊክ እና ቦሲኒያና ሄርዞጎቪና ለ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ አልፈዋል። አራቱ ሀገራት አስቀድመው በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫ ያለፉ 12 የአውሮፓ ሀገራት ተቀላቅለዋል። አውሮፓ በዓለም ዋንጫው 16 ሀገራትን ታሳትፋለች።
ኢራቅ ከ40 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ ተመልሳለች
Apr 1, 2026 54
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የክፍለ አህጉራት የፍጻሜ ማጣሪያ ኢራቅ ቦሊቪያን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ዛሬ ማለዳ ላይ በሜክሲኮ በቢቢቪኤ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሊ አል ሃማዲ እና አይማን ሁሴን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሞሰስ ፓኒያጉዋ ለቦሊቪያ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በጨዋታው ቦሊቪያ የተሻለ ብልጫ የነበራት ቢሆንም ኢራቅ ከፈጠረቻቸው ሶስት ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች መካከል ሁለቱን ወደ ግብ በመቀየር ውጤታማ ሆናለች። ግብ ያስቆጠረው የኢራቁ አይማን ሁሴን የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል። ኢራቅ ከ40 ዓመታት በኋላ ለዓለም ዋንጫ አልፋለች። የሜሶፖታሚያ አንበሶች ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተሳተፉት እ.አ.አ በ1986 ሜክሲኮ ባዘጋጀችው 11ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ነበር። ኢራቅ በውድድሩ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ትሳተፋለች። ቦሊቪያ ከ32 ዓመታት በኋላ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ ህልሟ አልተሳካም። ለመጨረሻ በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ1994 በአሜሪካ በተዘጋጀው 15ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ላይ ነው። ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በሜክሲኮ አክሮን ስታዲየም በተካሄደው የክፍለ አህጉራት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጃማይካን 1 ለ 0 በማሸነፍ ከ52 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ ተመልሳለች። በአውሮፓ ትናንት ማምሻውን የተካሄዱ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ተከትሎ ስዊድን፣ ቱርኪዬ፣ ቼክ ሪፐብሊክ እና ቦሲኒያና ሄርዞጎቪና ለዓለም ዋንጫ አልፈዋል። ጣልያን በመለያ ምት ተሸንፋ ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ የመመለስ ህልሟ ተጨናግፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ ለዓለም ዋንጫ ያለፉ ሀገራት ሙሉ ለሙሉ ተለይተዋል። 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ሮቤርቶ ዴ ዘርቢ የቶተንሃም ሆትስፐርስ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
Mar 31, 2026 151
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ ቶተንሃም ሆትስፐር ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዴ ዘርቢን በአምስት ዓመት ኮንትራት አዲሱ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ክለቡ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የቀድሞው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በቆይታቸው ደካማ ውጤት በማስመዝገባቸውና ክለቡን ለወራጅ ቀጠና ስጋት ይበልጥ ማጋለጣቸውን ተከትሎ መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል። የ46 ዓመቱ አሰልጣኝ ዴ ዘርቢ ከክለቡ አመራሮች ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት እስከ 2031 ድረስ በለንደኑ ክለብ ለመቆየት ፊርማቸውን አኑረዋል። ዴ ዘርቢ ክለቡን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ከፈርንሳዩ ማርሴይ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ ነው። በውላቸው ላይ ክለቡ ወደ ታችኛው ሊግ ቢወርድ እንኳ ኮንትራቱን የሚያቋርጥ አንቀጽ (relegation clause) አለማካተቱ፣ በአሰልጣኙ ላይ ያለውን የረጅም ጊዜ እምነት እንደሚያሳይ ተገልጿል። ዴ ዘርቢ የክለቡ አሰልጣኝ ከሆኑ በኋላ በሰጡት መግለጫ ቶተንሃምን የመሰለ ታላቅ ክለብ በመቀላቀላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። የክለቡ አመራሮች ያላቸው የወደፊት ራዕይ እና የሚከተሉት የማጥቃት እግር ኳስ ፍልስፍና ወደ ክለቡ እንዲመጡ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል። አሰልጣኙ ደጋፊዎችን የሚያስደስት ጨዋታ ለማሳየት ቃል ገብተዋል። የአሰልጣኙ አፋጣኝ እና ቀዳሚ ተግባር ቶተንሃም በዘንድሮው የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ እንዲቆይ ማድረግ ነው። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ30 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። 18ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ የሚበልጠው በአንድ ነጥብ ነው። ክለቡ ባለፉት 13 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ቀሪዎቹ ሰባት ጨዋታዎች ለአሰልጣኙ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ሮቤርቶ ዴ ዘርቢ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰንደርላንድ ጋር በ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነው። እስከ ውድድር ዘመኑ ፍጻሜ ድረስ ክለቡን በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍ ለማድረግ በሙሉ ትኩረት እና ትጋት እንደሚሰሩ አሰልጣኝ ዴ ዘርቢ አመልክተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት በምርምር ማገዝ ይገባል
Mar 31, 2026 98
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምርና በሳይንስ ማገዝ እንዳለባቸው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ገለፁ። የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የአየር ንብረት ትግበራ ፎረም የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በዚሁ ወቅት፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው ብሔራዊ ጥረት ሊኖራቸው የሚገባውን ስትራቴጂያዊ ሚና አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ሳይንሳዊ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማፍለቅ በኩል በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ስዩም አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመመከት በአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመተግበር ቀዳሚ መሆኗን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞችን መትከል እና በታዳሽ ኃይል ልማት የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለዓለም አርአያ መሆኗን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጥናትና ምርምር ስራዎቻቸው፣ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፎችንና ጆርናሎቻቸውን በአየር ንብረት ለውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው ብለዋል። ፎረሙ የፖሊሲ አውጪውንና የትምህርት ተቋማቱን የተቀናጀ ስራ የሚያጠናክር መድረክ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ጉዳዮችን በበላይነት እንደሚመራ ተቋም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የጀመረውን ቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲዎች የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችሉ ሳይንሳዊ መፍትሄዎችን በማፍለቅ በኩል ከፍተኛ ሚና አላቸው። እንደሀገር እየተተገበረ ባለው የአረንጓዴ አሻራ ልማት እና የአየር ንብረት መቋቋም አቅም ግንባታ ስራዎች ላይ የዩኒቨርሲቲዎች ተሳትፎ ከንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር የተሻገረ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል። የፎረሙ መመስረት ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ ፍለጋ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸው እንደሀገር የተጀመሩ ሥራዎችን መደገፍ የሚያስችል ነው ብለዋል።
በዞኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ለመስኖ ልማት መስፋፋት አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል
Mar 30, 2026 113
ጎንደር መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ) :-በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተካሄደው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት ስራ የከርሰ ምድር ውሃ አቅርቦትን በማሻሻል ለበጋ መስኖ ልማት መስፋፋት አመቺ ሁኔታ መፍጠሩን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራው ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ይገልፃል። የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃውም የአፈር ክለትን በመቀነስ ውሃማ አካላትና የመስኖ መሰረተ ልማት በደለል እንዳይሞሉ በማድረግ የሰብል፣ የእንስሳትና ፍራፍሬ ምርታማነትን ለማሳደግ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል። የመምሪያው ሃላፊ አቶ ንጉሴ ማለደ ለኢዜአ እንደገለጹት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተከናወነው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት የለም አፈር መከላትን በማስቀረት ለሰብል ምርታማነት ማደግ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ይህም የከርሰና ገጸ ምድር ውሃ አቅም እንዲጨምር በማድረግ አርሶ አደሩ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በመስኖ በማምረት የምግብ ሉዓላዊነቱን ለማረጋገጥ እየረዳው መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ ከአምስት ሄክታር በታች የነበረውን ዓመታዊ የመስኖ ልማት ስራ አሁን ላይ ወደ 40 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ እንዲለማ የሚያስችል ውጤት ማስገኘቱን አስረድተዋል፡፡ በዞኑ ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ተጠብቀው እየለሙ የሚገኙ ተፋሰሶች ቁጥር 955 መድረሱን ጠቁመው ይህም የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሩ እንዲሳካ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል። አሁን ላይ በንብ ማነብ፣ በእንስሳት ማድለብና በወተት ላሞች እርባታ ለተሰማሩ 1 ሺህ 350 ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮ በጋም በድግግሞሽ ከ11 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ባካሄዱት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ 57 ሺህ 370 ሄክታር የተራቆተ መሬት ላይ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ማከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ሰጠኝ አለነ እንደገለጹት በበጋው የምናከናውነው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት ስራ በመስኖ፣ በእንስሳትና በሰብል ልማት ምርታማነታቸው እንዲያድግ አስችሏል። በበጋ መስኖ በመታገዝ በአንድ ሄክታር መሬታቸው ላይ ቲማቲም፣ ሽንኩርትና ጥቅል ጎመን አምርተው ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የጭልጋ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር እሱባለው መሳፍንት በበኩላቸው በለሙ ተፋሰሶች ላይ በ15 ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ታግዘው ማር አምርተው ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የህልውናችን መሰረት መሆኑን በመገንዘባችን በልማት ቡድኖች ተደራጅተን በየዓመቱ በግልና በወል መሬቶች ላይ የእርከንና ክትር ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል፡፡
የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ያስችላል
Mar 29, 2026 226
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፡- የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ገንቢ ሚና እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ገለጹ፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ሕጎችና ደረጃዎች ዴስክ ኃላፊ ወንደሰን ታደሰ፤ ኢትዮጵያ የውኃ፣ የደን፣ የዓየር ንብረት አገልግሎት፣ የቁጥጥርና ቱሪዝም ሥርዓተ-ምኅዳር ብትታደልም በሚገባት ልክ አልተጠቀመችም ብለዋል። የሥርዓተ-ምኅዳር ጉዳዮች በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ጉዳዮች በከፍተኛ ጫና ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ በአገልግሎቱ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች መካከል የጋራ መግባባትን በመፍጠር ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስችልም አስረድተዋል። የፋርም አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሸዊት አማኑኤል በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን የብዝኃ ሕይወት ሃብቶች ለሕብረተሰቡ ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የባሌ አካባቢ ማኅበረሰብ ተፈጥሮን በመንከባከብ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ተጠቃሚ መሆን መጀመሩን ገልጸው፤ ይህ በሁሉም አካባቢዎች መስፋት እንዳለበት አመላክተዋል። መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራና በአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገቡን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝኃ ሕይወት ሀብት ይበልጥ መለየትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ሀብትና ሀይድሮሎጂ መምህር ዓለምአየሁ አባተ (ዶ/ር)፤ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ማኅበረሰቡ የሠራበትን እንዲያገኝ በማድረግ የተጠናከረ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡ በባሌ ኢኮሎጂ በ20 ወረዳዎች በመሰማራት እየሠሩ መሆኑን የገለጹት የፋርም አፍሪካ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ፈይሳ አሰፋ፤ በኢትዮጵያ የካርበን ክፍያ መጀመሩ የሕብረተሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ተነሳሽነት ያሳድጋል ብለዋል፡፡ የሥርዓተ-ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጁ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የብዝኃ ሕይወት ሀብት ጠብቃ እንድትቆይና ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል ሲሉም አስገንዝበዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ ነው
Mar 28, 2026 130
አምቦ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በጽህፈት ቤት የደን ልማት ባለሙያ ጉደታ ጡሪ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እየተዘጋጁ ከሚገኙ ችግኞች መካከል ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። በክረምቱ ወራት አጠቃላይ ከ94 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የችግኝ ተከላ እንደሚከናወን ገልጸው፤ የችግኝ ማፍላት ስራው በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ዝግጅቱ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል ምርታማነታቸው ከፍተኛ በሆኑና በተሻሻሉ የችግኝ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ማድረጉንም ጠቅሰዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፤ ችግኞችን የመንከባከብና የመጠበቅ ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል። የተተከሉ ችግኞች የአካባቢ ስነ-ምህዳርን ከመቀየር አንጻር ከፍተኛ ሚና ከመጫወታቸው ባለፈ፣ ደርቀው የነበሩ ኩሬዎች ዳግም ውሃ እንዲይዙ በማድረግ ለአርሶ አደሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ነው ያሉት። ባለፉት ሰባት ዓመታት በድምሩ 616 ሺህ 613 ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰው፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን ደን የመጠበቅ ባህላዊ እሴት ለአረንጓዴ ልማት ስራው ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 489
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 179
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 289
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 304
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3379
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 384
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 448
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 416
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት
Mar 28, 2026 273
ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • የ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን እና የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ሎጁ የዛሬ 50 እና 60 ዓመት መሠራት የነበረበት ቢሆንም፤ አሁን ስለዘገየን አንቆጭም ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ስለሠራንም አንረካም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሩጫችን ገና ብዙ እንደሆነ፣ አፋር ገና እንዳልተነካ አስበን ይህን ጅማሮ ይበልጥ በማላቅ ለማስቀጠል እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቃና ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነም ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸውን ፋይዳም አንስተዋል። • ኢትዮጵያ በማላቦው ጉባዔ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ማላቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉባዔው ከመጋቢት 18 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። • የልማት ሥራዎች ጉብኝት በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎሉና ግንባታቸው እየተፋጠኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት እና የአየር መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ሲሉም በወቅቱ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት የሀገር ሀብት ፈስሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የመገጭ ግድብ ምስክር መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይህ ሞዴል መንደር በአካባቢው ለረጅም ዓመታት የቆየውን የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ጥያቄ በተግባር መልሷል ብለዋል። በሀገራችን ከተማው ብቻ ሳይሆን ገጠሩም እኩል እየተዋበ፣ በልማት እየተገነባና በዕድገት ፍኖት ላይ በጽኑ መሠረት እየተራመደ ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ትልቁ ማሳያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። • "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ በአዲስ አበባ 4ኛው "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይሆን አጋርነትን ነው፤ እርዳታን ሳይሆን ኢንቨስትመንትን ነው! ለባለ ሀብቶች ምቹ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ለችሎታ እና ለዕድል በሯን ወለል አድርጋ መክፈቷንም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን በፍጥነት ወደ ከፍታ እየገሠገሠች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ የዕድገት ጉዞ፤ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያ ለእናንተ ዝግጁ የሆነ፣ በዕድሎችና በስኬቶች የተሞላ ታላቅ የኢንቨስትመንት መሶብ አላት፤ ኑ አብረን እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል! • የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫም፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። በዚህም ከክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀሌ እና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ ሂደቱን በክልሉ ለማካሄድ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው፤ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም አስረድተዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 155
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 780
ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል የነዳጅ ብክነትን ለመቀነስ ምን ዓይነት ብልኀት መጠቀም ይመከራል? ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 21, 2026 267
በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ (በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት ስትወጥን የቀደመ ወረቷን፤ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን ይዛ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን ቀረጸች። ይህን ዕውን ለማድረግ ስትዘይድም የሕዝቧን የፋይናንስ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ዐቅም በመደመር መጠቀምን ሻተች። በዚህም መሠረት በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዘገበች። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኢዜአ ዐይን …! ✍️ ገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻዎችና መናፈሻዎችን ለማልማት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ገበታ ለሸገር ኢኒሼቲቭ፤ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን የሚሸፍን ነው። የሚሠራበትን ገንዘብ ለማሰባሰብም የገበታ ለሸገር የእራት ምሽት በዳግማዊ አጼ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ተዘጋጀ፤ ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። ኢኒሼቲቩ አንድነት ፓርክን ጨምሮ የእንጦጦ መናፈሻንና ሌሎች የተለያዩ መዲናዋን ያስዋቡ በረከቶችን ችሯል። ይህም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት በርካታ ቱሪስቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ለምጣኔ ሃብት ዕድገት ጉልኅ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ለዚህ ሁሉ ስኬት መነሻ የሆኑትን ጉዳዮች ያስጀመሩትም ያስፈጸሙትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሸገር የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ገበታ ለሀገር የተሰኘውን ኢኒሼቲቭ አበሠሩ። ✍️ ገበታ ለሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻን ለማልማት ያለመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። ይህም በአዲስ አበባ ከተሠራው ገበታ ለሸገር ቀጥሎ የተከናወነ ነው። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የገበታ ለሀገር ዓላማ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ የቱሪስት መስኅብ የሚሆኑና የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መሆኑን አስገንዝበዋል። በገበታ ለሀገር መርሐ-ግብር ባለሀብቶችን ጨምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት የሀገሪቱን ባለሃብቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ መርሐ-ግብሮች የተሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ውጤታማ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበታ ለሀገር ውጥን፤ እንደ ሀላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጉልተው በማሳየት ይበል ያሰኘ ውጤት አስመዝግቧል። ✍️ ገበታ ለትውልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም ገበታ ለትውልድ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ይህም ተጨማሪ መዳረሻዎች እንዲለሙ አስችሏል። በዚህ ኢኒሼቲቭ ሥር በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የመዳረሻ ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ አካባቢና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎች እየለሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የሸበሌ ሪዞርት በይፋ መርቀዋል። እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት እንደሆነም ተገልጿል። ሎጎ ሐይቅ ሪዞርትም ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረቀ ሲሆን፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኖ ቀርቧል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክርም ነው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት። የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነትና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ዕሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ሆኖ ያገለግላል። ታሪካዊ ቦታዎችና የሀገር መገለጫ መሠረተ-ልማቶች ብሔራዊ ትርክቶችንም የሚገነቡ ናቸው። በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት ብሎም በየአካባቢው የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት፣ ብዙ ጎብኚዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። እንዲሁም ነባር ቅርሶችን በማደስና በመጠገን ለትውልድ ለማሻገር ደማቅ ዐሻራ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት የመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ ዐሳይተዋል። ባለሀብቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም ሀገራቸውን የመሥራት ሚና እንደሚጠበቅባቸው አሥተምረዋል። ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ብሎም በርካታ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር በኢኮኖሚው ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግሥት ላስጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ነው። ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎችም አንዱ የሆነው ለዚህ ነው። መሠረተ-ልማቶች ከሚገነቡባቸው ጡቦች ባለፈ የነገን ሀገራዊ ማንነት፣ ራዕይ እና መዳረሻን ይበይናሉ። ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ እንኳንም ታሰቡ፤ እንኳንም ተሳኩ። ይህ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መዳረሻ ባላገኘች ነበር።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3777
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2547
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8338
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6828
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 29, 2026 2860
በዮሐንስ ደርበው ሥልጣኔ - በምርጫ ካርድ መምረጥ በያዝነው ዓመት ወርኃ ግንቦት በባተ 24ኛው ቀን ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ቀን ቆርጣለች። ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ወደ ትግበራ ምዕራፍ ገብታለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን፤ ቀሪ ሥራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን ገልጿል። ለዚህም የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ መግባታቸው በአሥረጂነት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ መሰጠቱ፤የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች በኦንላይን ሥርዓት በታዛቢነት መመዝገባቸውን አስረድቷል። በኢዜአ ዐይን …! በገበታ ለሀገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የጤና ነገር … እንዲሁም ዐለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት መጥተው ፈቃድ የሚወስዱበት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሠለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች አሠማርቷል። ለመራጮች ምዝገባ የተዘጋጁ 46 ሺህ 757 ጣቢያዎች እና ተጨማሪ በርካታ ንዑስ ጣቢያዎችም ተሠናድተዋል። እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ፤ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮው ምርጫ ለውድድር ተመዝግበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ 73 ዕጩዎች በግል ለውድድር መቅረባቸው ተገልጿል። ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ የሚከናወነው ሁሉም ፓርቲ ሕግን አክብሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደሆነ ያስማማል። የምርጫው ስኬት የሚረጋገጠውም ቦርዱ ለብቻው በሚያደርገው ጥረት ሳይሆን፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዕኩል ኃላፊነቱን መወጣት ሲችል መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰባት ምዕራፎችና በ30 አንቀጾች የቀረበውን የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ፈርመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሂደት የዜጎችን ተሳትፎ ለማበረታታት “ምርጫችን ነው-ሀገር ያለኛ” የተሰኘ የምርጫ ኅብረ-ዝማሬ ማስመረቁ ይታወቃል። በዚሁ ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ኅብረ-ዝማሬው አካታች ተሣትፎን ለማበረታታት መሠናዳቱን አስገንዝበዋል። የልዩ ልዩ ድምጾች ኅብራዊነት ያለውን የጋራ ጥንካሬ በማሳየት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዜጎችን ተሳትፎ ማጎልበት የኅብረ-ዝማሬው ዓላማ መሆኑም ተገልጿል። በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫም “የሀገር ካስማ” የተሰኘ ኅብረ-ዝማሬ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ምዝገባው እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይቀጥላል። የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ የሚገኘውም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ ነው። ከአጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ያህሉ የዲጂታል የመራጮች ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ቦርዱ ማሳወቁ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ በተከናወነ የመራጮች ምዝገባ ከ28 ሚሊየን 365 ሺህ 310 በላይ መራጮች ተመዝግበዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 37(7) ላይ ቦርዱ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክቶችን አቀማመጥ፣ ቅደም ተከተልና እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ግልጽ በሆነ መንገድ በመመሪያ እንደሚወስን ይደነግጋል። በዚህም መሠረት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ባሳለፍነው መጋቢት 14 ቀን በይፋ አስጀምሯል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት የሚከናወነው በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የዕጩዎች ምሥልና የመለያ ምልክት አቀማመጥን የሚወሥነው የዕጣ ማውጣት ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የዓየር ሠዓት ድልድል የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል። በዚህም መሠረት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የዓየር ሠዓት ተድልድሎላቸዋል። የሠዓት ድልድሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና ፖሊሲዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ የግል ዕጩዎችም አማራጭ ሐሳባቻቸውን እንዲያጋሩና የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ብሎም ከመራጩ ጋር እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ ነው። ይፋ በተደረገው ነፃ የዓየር ሠዓት የተመዘገቡ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች በኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ ይጠበቃል። በአጠቃላይ በምርጫ ካርድ መሪን መምረጥ ከሥልጣኔ ቁንጮዎች አንዱ ሆኖ ይነሳል። የመራጮች ምዝገባ ሂደትም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራርን እንዲያጠናክሩ ብሎም በካርዳቸው ይሁንታ የሚመራቸውን መምረጫ ቁልፍ ነው። ኢትዮጵያ በወሳኝ የምርጫ ወቅት ላይ ናትና፤ ለስኬታማነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #የመራጮች_ምዝገባ #በኢዜአ_ዐይን
ተከፍሎ የማያልቅ የኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ውለታ አለብን - የመናዊያን ፍልሰተኞች
Mar 19, 2026 2434
በዮሐንስ ደርበው ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለተገፉ፣ ጥላ ከለላ ለሚሹ፣ ለተከዙና ለታረዙ የሀገራት ዜጎች መጠጊያ ናት። የኢትዮጵያን ቸርነትም ከተጠለሉባት እንግዶቿ በላይ ምሥክር የለም። የኢትዮጵያን ደጅ የረገጡ ሁሉ በቆይታቸው ለተደረገላቸው ሁሉ ‘ውለታችንን በምን እንክፈል’ ሲሉ ይደመጣሉ። ከአያሌ ሀገራት በመልከ ብዙ ቀውሶች ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ የቆሰሉ ልባቸው ታክሞ፣ ዕንባቸው ታብሶና ሕይወታቸው ታድሶ ኑራቸውን አደላድለዋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በዚህም ከአፍሪካም ሆነ ከተቀረው ክፍላተ ዓለም የጦርነትና ግጭት ጥላ ያጠላባቸውና ሰላምን የተጠሙ የቀጣናው ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ሲሹ ማየት የተለመደ ነው። የየመን ዜጎች ለዚህ ማሳያ ናቸው። ኢብቲሳም ኻሊድ እና መሰል የመናዊያን ከየመን የእርስ በርስ ግጭት በኋላ የኢትዮጵያን ደጅ ረግጠው ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፍ የተድላ ኑሮ እየኖሩ ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረገችው ኢብቲሳም እንደምትለው፤ በየመን አለመረጋጋት በፈጠረው ጠባሳ እርሷና መሰሎቿ ለፍልሰት ተዳርገዋል። ለዚህ ደግሞ ምርጫቸው ኢትዮጵያ ሆነች። ወደ ኢትዮጵያም መጥተው የሀገሬው ፊት ሳይኮሰኩሳቸው በፍቅር እንደተቀበሏቸው ትናገራለች። በዚህም ዛሬ የመናዊያን ተስፋቸው ለምልሞ፣ ሕይወታቸው ሠምሮ ኢትዮጵያን እንደ እናት ቆጥረው እየኖሩ ስለመሆኑ ትናገራለች። ከ11 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ኢብቲሳም፤ በወቅቱ ቀኑ እንደጨለመባት ታወሳለች። ሰው ከቤቱ፣ ከወገኑ…ከሀገሩ ወጥቶ ወዴት ይሄዳል? በወቅቱ የነበረውን ጭንቀት ማየልም ታስታውሳለች። አሁን ግን ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ በጎነት ዐውርታ አትጠግብም። “አሁን ፍልሰተኛ አይደለሁም፤ ያለሁት በሁለተኛዋ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነውና” ትላለች። እንዲህ ባለው የረመዳን ወቅት ደግሞ የፍልሰተኞች ሁሉ ሰብሳቢ ናት። “ሁሉም ከእነ ቤተሰቡ ወደ ቤቷ እየመጣ ያፈጥራል። በዚህም በፍልሰት እንደመጡ ሳይሆን ቤተሰባዊነት ይሰማቸዋል። ከየመን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮንጎሊዝ (DRC) ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ ሰብሰብ ብለው የኢፍጣር መርሐ-ግብርን እንደሚያከናውኑም ታነሳለች። በዚህ ላይ ኢትዮጵያውያን ብርታት ናቸው ትላለች፤ ሁሌም ‘አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ነገ ጥሩ ይሆናል’ እያሉ ያበረቱናል፤ ክብርና ፍቅር ይሰጡናል ስትልም ታስረዳለች። የኢትዮጵያንና ሕዝቧን ውለታ እንዴት መክፈል ይቻላል? ኢትዮጵያን ሀገራችን ብለን ነው እየጠራን ያለነው። እንደ እንግዳ እንደ ፍልሰተኛ እራሳችንን አናስብም፤ እንደሀገሬው አንዱ እንጅ፤ የምትለው ኢብቲሳም፤ ኢትዮጵያን እንዴት ብዬ ነው የምገልጻት? እናትን መግለጽ ይቻላል? እናትን መግለጽ ከተቻለ ኢትዮጵያን በዚያ ልክ መግለጽ ይቻል ይሆናል፤ እኔ ግን አይቻለኝም በማለት ትናገራለች። “የዛሬ 11 ዓመት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት፤ የሰው ፊት አልገረፈኝም፤ ፊቱን ያዞረብኝም የለም። ኢትዮጵያውያን ደግ፣ ቅንና ደስ የምትሉ ሕዝቦች ናችሁ” ስትል ስሜቷን ትገልጻለች። ኢትዮጵያ እንደ ኒውዮርክ እያደገች ነው፤ እኛ ከመጣን በኋላ እንኳን በርካታ ለውጦች ዕያየን ነው ስትልም የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት አንስታለች። ለአብነትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በርካታ ነገሮች መስተካከላቸውን በመጠቆም፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግሥት እናመሠግናለን ብላለች። ከፍልሰተኞች ጋር በተያያዘ በርካታ ሕጎች በመሻሻላቸው፤ ዛሬ በራሴ ስም ንግድ ፈቃድ አውጥቼ እየሠራሁ ነው፤ በጨረታዎችም እወዳደራለሁ፤ የበጎ አድራጎት ማኅበር መመሥረትና መምራት ችያለሁ። እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣቸው ለውጦች ናቸው ብላለች። በምድረ ኢትዮጵያ ያለን ሁሉ ለኢትዮጵያ ዕድገት እንተባበር ስትልም ጥሪ አቅርባለች። ህልማችን ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆነን ኢትዮጵያን በማሳደግ ጥረት በንቃት መሳተፍ ነው፤ የኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ውለታ መመለስ አለብን ስትልም ትናገራለች። በኢብቲሳም ኻሊድ ቤት በተዘጋጀ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ የተሳተፈው አነስ አንዋር ለኢዜአ እንዳለው፤ ኢትዮጵያ በሯን ከፍታ አስጠልላዋለች። ከተለያዩ ሀገራት ብንመጣም ሰብሰብ ብለን ስናፈጥር፤ ማኅበራዊና ቤተሰባዊነታችን ይጠናክራል ብሏል። ብዙ ፈተናዎችን ዐይተናል፤ አልፈናቸው እዚህ ደርሰናል የሚለው አነስ፤ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት ነው” ሕዝቡ በክብር ነው የተቀበለን፤ ከምሥጋና ውጭ ምን ማለት እንችላለን? አመሥጋኞች ነን ሲል ገልጿል። እየተማርኩ ነው፤ ትምህርቴን አጠናቅቄ በሙያዬ በመሠማራት ኢትዮጵያን ማገዝ እፈልጋለሁ ብሏል። ራኪያ አሊ አብዱረዛቅ በበኩሏ በፈረንጆቹ 2011 ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷን ታወሳለች። ትምህርቷንም ተከታትላ መመረቋን ገልጻ፤ ቤተሰብ አፍርታ ሁለት ልጆችንም ወልዳ እየኖረች ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገሬ ናት፤ ሰላም አላት፤ ሕዝቡም ሰው አክባሪ ነው። ለኢትዮጵያ የተሻለ ልማት ደግሞ መተባበር ወሳኝ ስለሆነ ለዚሁ እንትጋ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች። #ፍልሰተኞች #ኢዜአ