አማራጭ ሀሳቦቻችንን ለማቅረብ የሚያስችሉ የሚዲያ አማራጮች ተመቻችተውልናል - ኢዜአ አማርኛ
አማራጭ ሀሳቦቻችንን ለማቅረብ የሚያስችሉ የሚዲያ አማራጮች ተመቻችተውልናል
ሰመራ፣መጋቢት 23/2018(ኢዜአ)፦በምርጫው ሂደት በንቃት እየተሳተፉ የፓርቲያቸውን አማራጭ ሐሳቦች ለማድረሰ የሚያስችሉ የሚዲያ አማራጮች እንደተመቻቸላቸው የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) ገለጸ።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ብዝሃነትን ባስተናገደ መልኩ የክርክር መድረኮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ሃንፈሬ መሐመድ ለኢዜአ እንደገለፁት፥የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊና ነፃ በሆነ መልኩ በጥሩ የፖለቲካ ምህዳር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለጠቅላላ ምርጫው ነፃ ክርክር በማድረግ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ባለው ሰላማዊ ሁኔታ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምንም ዓይነት እንከን ያልገጠማቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።
የዘንድሮው ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖርና በድምፁ መወሰን እንዲችል ሂደቱ ጥሩ መሆኑን አውስተው ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የራሳችንን ሚና እየተወጣን ነው ብለዋል።
የምርጫ ህጉን በተከተለ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።