ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
አዲስ ስፖርት ፓርክ የመደመር እሳቤና ተግባር የታየበት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 4, 2026 141
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦‎ አዲስ ስፖርት ፓርክ የመደመር እሳቤና ተግባር የተገናኙበት ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዲስ ስፖርት ፓርክ ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፓርኩ የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ልማት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ልማት ያለ ሰብአዊ ልማት ምልዑ ሊሆን እንደማይችል ጠቁመው፣ የስፖርት መሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች የዚሁ የሰው ተኮር ልማት ተግባር ማሳያ መሆናቸውን አመልክተዋል። የመደመር መንግሥት ዋና እሳቤም ሁሉን አቀፍ ልማትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ መሆኑንና ዛሬ የተመረቀው ፓርክም ይህ እሳቤና ተግባር የተገናኙበት ትልቅ የስፖርት አውድ መሆኑን አስገንዝበዋል።   ፓርኩ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሁሉም ስፖርቶች መሠረተ ልማት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎችን አሟልቶ የተገነባ ነው ብለዋል። ይህም ስፍራ ለወጣቶች መወዳደሪያና ለታዳጊዎች መጎልበቻ ከመሆኑ ባለፈ፣ ለሀገራቸው ትልቅ ክብር ያመጡ የስፖርት ፈርጦች ሐውልት የቆመበት የጀግኖች አምባ ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ መዘጋጀቱን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት። በተለይም በፓርኩ ውስጥ የጀግኖች ገጽታ ከነጽናታቸውና ከነአርዓያነታቸው፣ እንዲሁም ፊታቸው ላይ ከተጻፈው የሀገር ፍቅር ጋር ተደምሮ በሐውልት መታሰቢያነት መቆሙን አንስተዋል። ሐውልቶቹ ለኢትዮጵያ የሮጡ እግሮችንና ለሀገር የተከፈለ ውድ ዋጋን በሚዘክር መልኩ በክብር ተቀርጸው የተቀመጡ መሆናቸውንም እንዲሁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል እያከበረና ኃላፊነቱን እየተወጣ ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። ቃል ተግባር እየሆነ አዲስ አበባም እየተቀየረች፣ ኢትዮጵያም ወደ ክብር ማማ እየገሰገሰች ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 4, 2026 89
ከመጋቢት 20 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ መሆኗን ገልጸው፤ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፣ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ፣ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ብለዋል። ፈጣን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሠራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ ዐቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው ከፍተዋል። ‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል በወቅቱ። ‎የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከል ማከተቱን አብራርተዋል። ‎ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። • የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)‎ የከተማችንን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል። ‎በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋልም ነው ያሉት። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል ሲሉም ገልፀዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአፋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል። በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት፤ ለሌሎች በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሠነድ እንደሚሆን አመላክተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የጸጥታና ደኅንነት ተቋሞቻችን ችግርን ወደ ዕድል እንዲቀየሩ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጨምና ከትናንት ዕዳዎች ተላቀን፣ የዛሬ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ለነገው ትውልድ የምትመጥን ሀገር ለመገንባት በዓላማ ጽናት እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል። • ስለ መጋቢት 24 መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የመጣውን የለውጡን መንግሥት የሚደግፉ ሕዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ሰልፎች ላይም መንግሥት ባለፉት ሥምንት ዓመታት ያመጣቸውን ለውጦች እና የተገኙ ስኬቶችን የሚያወሱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) ለሰጡት ስኬታማ አመራርነት የሚያሞግሱና የሚያመሠግኑ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝባዊ ግፊትና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው ብለዋል። ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብሏል። የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች ሲልም ገልጿል። ይህን ለውጥ ዕውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፤ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም ነው ያለው። • የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ሕንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ጽሕፈት ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል ብሏል። የ1954 የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ሲልም አስገንዝቧል ጽሕፈት ቤቱ።
ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ወቅቱን የዋጀ ነው
Apr 4, 2026 71
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጭ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚስማማና ወቅቱን የዋጀ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ድረስ መሆኑም ተገልጿል። ብስክሌቶቹ በሞባይል መተግበሪያ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የጂፒኤስ ሲስተም እንደሚጠቀሙም በመርሀ ግብሩ ላይ ተመላክቷል። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የትራንስፖርት አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወቅቱን የዋጀ ምላሽ መሆኑንም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው፤ ለሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፤ ሚኒስቴሩ በሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰማሩ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ያብባል አዲስ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ የሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በኮሪደር ልማቱ ከ240 ኪሎ ሜትር በላይ የብስክሌት መንገድ መሰራቱን ጠቁመው፤ መሰረተ ልማቱንም በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መጽደቁንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ስድስት የሚሆኑ የብስክሌት ኦፕሬተሮች ቅድመ ምዝገባ በማድረግ የዝግጅት ስራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዘርፉ የትራንስፖርት አገልግሎትን በጉልህ የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም አካባቢዎች ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸውም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት በተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን መገንዘብ መቻሉን ያመለከቱት የአዲስ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ሳተና ዋሬ ናቸው። ለአገልግሎቱ የሚውለው መተግበሪያም በራስ አቅም በሀገር ልጆች መልማቱን ጠቁመዋል። አገልግሎቱ የፋይዳ ቁጥር በማስገባት መጠቀም የሚቻል ሲሆን፤ ክፍያውም በዲጂታል መንገድ በሞባይል የሚፈጸም መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስፋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በደንብ ቁጥር 183/2017 የብስክሌት መጋራት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ ማጽደቁ ይታወሳል።  
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚያስኬዱ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችል አቅም እየገነባች ነው
Apr 4, 2026 67
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚያስኬዱ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችል አቅም እየገነባች መሆኑን የዘርፉ ተዋናዮች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያደረገችው ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር የሜዲካል ቱሪዝምን የሚያሳልጥ መሆኑም ተመላክቷል። በአዲስ አበባ እየተካሄዱ የሚገኙት ሁለተኛው የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን እንዲሁም 10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለም አቀፍ የሕክምና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይና ጉባኤ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ስኬቶች አጉልተው አሳይተዋል።   በኤግዚቢሽኑ የተሳተፉ የሕክምና መሣሪያ አምራቾችና አስመጪዎች እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የጤና ዘርፉን ለማዘመን በሰጠችው ልዩ ትኩረት ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ የማይታሰቡ ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት ውጤታማ ሕክምና መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል። የበርለ ኦፍ ሜዲካል ካምፓኒ ተወካይ ዶክተር ኪሩቤል ክፍሌ፥ የኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ እያሳየ ያለው እድገት እጅግ ፈጣንና አስገራሚ መሆኑን ገልጸዋል። ቀደም ሲል ትኩረቱ በተላላፊ በሽታዎች ላይ ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ሆስፒታሎች ውስብስብ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችሉ ትልልቅ ማሽኖችን ታጥቀዋል ብለዋል። ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዜጎች ለሕክምና ወደ ውጭ ለመሄድ ይገደዱባቸው የነበሩ ህክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አቅም በመፍጠር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያድን ጠቅሰዋል።   የቻይናው ሰንሼን ማኑፋክቸሪንግ ድርጅት የኢትዮጵያ ካንትሪ ማናጀር አማኑኤል ሽጉጥ በበኩላቸው፤ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙና የሐኪሞችን ሥራ የሚያቀሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንጻር በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርገውና የሜዲካል ቱሪዝምን የሚያሳልጥ መሆኑን ገልጸዋል። ‎በዓለም አቀፍ የሕክምና ኤግዚቢሽኖች በኢትዮጵያ መካሄድ መጀመራቸውም ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።   መንግሥት ለጤናው ዘርፍ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ድጋፍና ለሕክምና መሣሪያዎች ግዢ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ላይ ቅድሚያ መስጠቱ ለዚህ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ ከዓለም ኢንተርናሽናል ፒኤልሲ የመጣው የባዮ ማዲካል ኢንጂነር አስቻለው አሸናፊ ናቸው። በተጨማሪም የሕክምና መሣሪያዎች በጥብቅ ቁጥጥር እንዲገቡ መደረጉ ጥራታቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስችሏል ብለዋል። በቀጣይም በሀገር ውስጥ ያለውን የማምረት አቅም በመጠቀም ወደ ማምረቱ ሥራ ይበልጥ መግባት ለዘርፉ እድገት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሚታይ

አዲስ ስፖርት ፓርክ የጀግኖች መዘከሪያ እና የትውልድ መገንቢያ ስጦታ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 4, 2026 129
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ አዲስ ስፖርት ፓርክ የጀግኖቻችን ክብር ህያው የሚሆንበት፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በጤናማ ትውልድ የምንገነባበት ታላቅ ስጦታ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውና በዓለም መድረክ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ ጀግኖች አትሌቶች መታሰቢያ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባው አዲስ ስፖርት ፓርክ ዛሬ ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ጀግኖች አትሌቶች በተገኙበት ፓርኩ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማዋ እምብርት በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ማዕከል፣ ሁሉንም ዓይነት የስፖርት ዘርፎች ያካተተ ነው ብለዋል። ፓርኩ የነገዋን ኢትዮጵያ በአካልና በሞራል የታነጸ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ለጀግኖች አትሌቶች የክብር መግለጫ፣ ለወጣቶች የተስፋ ምንጭ፣ ለልጆች ደግሞ የደስታ ስጦታ ሆኖ መቅረቡን አመልክተዋል። የፓርኩ ልዩ ገጽታ በኦሎምፒክ መድረክ የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት የኢትዮጵያን ስም ላስጠሩ 15 የምንግዜም እንቁ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የቆመው የክብር ሐውልት እንደሆነም አንስተዋል። ይህም ጀግኖችን በቁም ለማመስገንና ለተተኪው ታዳጊ ትውልድ እኔም እችላለሁ የሚል ትልቅ የስነ-ልቦና ተነሳሽነት ለመፍጠር ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ነው ከንቲባዋ የገለጹት። ፓርኩ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚመጥን መልኩ የተገነባ ሲሆን፣ ለባለሙያዎችና ለወጣቶች የኦሎምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የመዋኛ ገንዳዎች፣ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎችን መያዙን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ስፖርትን የዘወትር የሕይወት ዘይቤ ለማድረግ የሚያግዙ ዘመናዊ የቤት ውስጥና የውጪ ጂም፣ የዌልነስ ሴንተር (Wellness Center) እና የ800 ሜትር የመሮጫ ትራክ ተካትተውበታል። ለልጆችና ለታዳጊዎች ደግሞ እንደ እድሜያቸው የተዘጋጁ ዘመናዊና ባህላዊ የመጫወቻ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎችና የአሸዋ ላይ ስፖርት ሜዳዎች ተገንብተዋል። መሠረተ ልማቶቹ ህጻናት በአካልና በአዕምሮ እንዲያድጉ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ላይ ገልጸዋል። ይህ የልማት ፕሮጀክት ከስፖርት ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጠናክራል ያሉት ከንቲባዋ በተለይም ለካዛንችስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች የተገነቡ የሴራሚክ መሸጫ ሱቆች፣ የዜጎችን ኑሮና ስራ ከልማቱ ጋር ለማስተሳሰር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተጨማሪም 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ቤዝመንት የመኪና ማቆሚያ፣ የአውቶቡስ ተርሚናል፣ እስከ 3 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግድ ሰፊ ፕላዛ እና ምቹ ሬስቶራንቶች ፓርኩን ለቤተሰብና ለጎብኚዎች ተመራጭ እንደሚያደርጉት ነው ያብራሩት። ፓርኩ ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተሰናስሎ የተሰራ በመሆኑ፣ የአረንጓዴ ልማት መናፈሻውና የውሃ ፋውንቴኑ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ አረንጓዴ ከተማ ለማድረግ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ስፖርት ፓርክ የፅናትና የብልጽግና ምልክት መሆኑን ገልጸው ከተማዋን ውብና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው የከተማዋን የኮሪደር ልማትና የከተማ እድሳት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል
Apr 4, 2026 140
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው የከተማዋን የኮሪደር ልማትና የከተማ እድሳት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ዛሬ በይፋ መርቀው መክፈታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል። ‎በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክት፤ የኦሎምፒክ ደረጃን ያሟላ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎችን እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን፣ ዘመናዊ የቤት እና የዉጪ ጂም ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ከማህበረሰብ አገልግሎቶች ጋር አቀናጅቶ የያዘ ነው።   ልማቱ ሁሉንም የእድሜ ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣ የልጆች መጫወቻዎችን፣ እንደ እድሜያቸው የተከፋፈሉ መዋኛ ገንዳዎች፣ የአሸዋ ላይ የእጅ እና የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን እና የጤና ማዕከልን አካቷል። በኦሎምፒክ መድረክ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶች በፓርኩ መሐል መቆማቸው፤ የጀግኖቻችንን ታሪክ ሕያው ከማድረግ ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ስፖርተኞች ታላቅ ተምሳሌት ይሆናሉ።   ከስፖርታዊ አገልግሎቶች ባሻገር፣ ፕሮጀክቱ 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ፕላዛ ከሬስቶራንቶች እና ካፌዎች ጋር፣ 300 መኪናዎችን በአንዴ የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ እና በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን አካትቷል። ከወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፣ ነዋሪዎችን በመዝናኛም ሆነ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘመናዊና ሁለገብ የከተማ ፕላን ማሳያ ነው። ‎ ይህ ያለመችውን የምታሳካዋ፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ገጽታ ነው!
ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Apr 4, 2026 231
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል።   በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ መገንባቱንም አመልክተዋል።   የእውነተኛ ልማት ማዕከል ማህበረሰቡ ላይ መሆን አለበት በሚል እምነት፣ ይህ ፕሮጀክት ከላቀ የስፖርት አገልግሎት ባለፈ በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ አቅም የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆችን እንዲሁም 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ መያዙንም ነው የገለጹት። በተጨማሪም በአንዴ 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ ያለውና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፤ ንፁህና ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የጀመርነውን ቁርጠኝነት ጉልህ ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል። ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
አዲስ ስፖርት ፓርክ ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ሆነ
Apr 4, 2026 178
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በፈጣን የግንባታ አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውና ለከተማዋ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ ያለው አዲስ ስፖርት ፓርክ ተጠናቆ ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ፕሮጀክቱ መንግሥት ለዜጎች ጤና እና ለከተማዋ ዘመናዊ ገጽታ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት እንደሆነም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፣ ከግንባታ ፕሮጀክትነት ባለፈ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ መገለጫ መሆኑን አመልክቷል።   ማዕከሉ የከተማዋን ነዋሪዎችና ጎብኝዎችን ፍላጎት በሚያረካ መልኩ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ የተገነባ እንደሆነ ተገልጿል። በፓርኩ ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና መሰረተ ልማቶች መካከል የኦሎምፒክ ደረጃን የሚያሟላ የመዋኛ ገንዳ፣ የ800 ሜትር የሩጫ ትራክ፣ እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች ይገኙበታል። ከነዚህም በተጨማሪ ለሕፃናት መጫወቻ የሚሆኑ ስፍራዎችና ልዩ የአሸዋ ሜዳዎች ለማህበረሰቡ ዕረፍት እንዲውሉ ተዘጋጅተዋል። የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃትና የሀገር ባለውለታዎችን ለመዘከር፣ በዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ መድረክ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አንጋፋ አትሌቶች የክብር ሐውልቶች በፓርኩ ውስጥ መቆማቸው ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል።   ይህም ስፍራው የስፖርት ማዘውተሪያ ብቻ ሳይሆን የታሪክና የጀግንነት መዘከሪያ እንዲሆን ያደርገዋል። ማዕከሉ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ ለንግዱ ማህበረሰብ ሰፊ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆች ተካተውበታል። በተጨማሪም በአንድ ጊዜ 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ መገንባቱ፣ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ተራዘመ
Apr 4, 2026 464
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሲያከናውን የቆየውን የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታወቀ። ቦርዱ ቀደም ሲል ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲከናወን መታቀዱን አስታውሷል። የምዝገባ ሂደቱን በቴክኖሎጂ ለማገዝ በወጣው ዕቅድ መሠረትም የዕጩዎች ምዝገባ በአሁኑ ወቅት መጠናቀቁንና የመራጮች ምዝገባ ደግሞ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሲከናወን መቆየቱን ገልጿል። ሆኖም በምዝገባ ሂደቱ ወቅት በተወሰኑ አካባቢዎች በቴክኖሎጂ የታገዘውን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ የኔትወርክ አቅርቦት ችግር ማጋጠሙን ቦርዱ ገልጿል። ይህንን ተግዳሮት በመቅረፍ ሂደቱን አስተማማኝና ቀልጣፋ ለማድረግ የተጠቀመውን ተጨማሪ ጊዜ ለማካካስ የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል። በተጨማሪም አስተማማኝ የኔትወርክ አቅርቦት ይኖራቸዋል ተብለው በታሰቡ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የኔትወርክ መቋረጥ በማጋጠሙ፣ ሂደቱን ወደ ማኑዋል (በእጅ) አሠራር በመቀየር ረገድ የባከነውን ጊዜ ለመተካት መወሰኑን በመግለጫው አመልክቷል። በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በነበረ የትራንስፖርት ችግር ምክንያት የምዝገባ ቁሳቁሶች በወቅቱ ባለመድረሳቸው ለተፈጠረው መዘግየት ምላሽ ለመስጠት፣ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባው ሁለት የበዓል ቀናትን ሳይጨምር እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ማድረጉን አስታውቋል።
መጋቢት 24 የሶማሌ ክልል ህዝብ ትክክለኛ ውክልና ያገኘበትና አዲስ የፖለቲካ ባህል የታየበት ዕለት ነው
Apr 4, 2026 278
ጅግጅጋ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ መጋቢት 24 የሶማሌ ክልል ህዝብ ትክክለኛ ውክልና ያገኘበትና አዲስ የፖለቲካ ባህል የታየበት ዕለት ነው ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገለጸ። የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ መጋቢት 24 የሶማሌ ክልል ህዝብ ትክክለኛ ውክልና ያገኘበትና አዲስ የፖለቲካ ልምምድ የጀመረበት ዕለት ነው ብለዋል። ከለውጡ የሶማሌ ክልል የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ችግሮች የነበሩበት መሆኑን አስታውሰው ከለውጡ ወዲህ ለችግሮቹ መፍትሄ በመገኘቱ በክልሉ አሁን ላይ ውጤታማ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። በለውጡ ዓመታት በተከናወኑ ሪፎርሞች በክልሉ ሁለንተናዊ ልማት እየተረጋገጠ መሆኑን ገልፀው ከአግላይና ከፋፋይ የፖለቲካ ሥርዓት በመውጣት አዲስ የፖለቲካ ባህል መታየቱንም አክለዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስትና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር በመስራት ላይ እንደሚገኙ አንስተው በክልሉ በተፈጠረው ምቹ የፖለቲካ ምህዳር በጠቅላላ ምርጫው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩም ገልጸዋል። በጸጥታና በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውንና የማጠናከር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን በመጥቀስ በቀጣይም በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን በተገቢው መንገድ መጠቀም የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። በክልሉ ተግባራዊ የተደረጉ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው ህብረተሰቡን በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ተጠቃሚ የማድረግ ተግባራት ይጠናከራሉ ብለዋል። ክልሉን የቱሪዝም የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች በውጤታማነት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው ማህበረሰቡን ከተረጂነት ለማውጣት የተጀመሩ የግብርና ልማት ሥራዎች የበለጠ እንደሚጠናከሩም አረጋግጠዋል።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ የሚመራንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
Apr 4, 2026 306
ሆሳዕና/ሚዛን፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምዝገባ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ካርድ በመውሰድ የሚመራንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የሆሳዕና እና የሚዛን አማን ከተሞች ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ጠቅላላ ምርጫውን ግንቦት 24 ቀን 2018 ለማካሄድ ቀን ተወስኖ፣ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራት በመከናወን ላይ ነው። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው አስራት ሽፈራሁና ወጣት እስራኤል አብይ የመራጭነት የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። አቶ መላኩ ደበበ እና ወጣት ትግስት በየነ የተባሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው የምርጫ ካርድ የመውሰጃ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት መብታቸውን ለመጠቀም ካርድ ለመውሰድ በምርጫ ጣቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይም የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቤ ታደሰ እና መሐመድ ሸምሱ በበኩላቸው፤ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብትን ለመጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ ካርድ በመውሰድ በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀት ይገባል ነው ያሉት። ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ መሳተፍ የሚያስቸለውን ካርድ መያዙን የተናገረው ደግሞ ወጣት ሮቤል ኃይሌ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ነው።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን
Apr 4, 2026 194
አዳማ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን አስታወቀ። ፌዴሬሽኑ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎችን ለማሰማራት ያዘጋጀው የአሰልጣኞች ሥልጠና መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።   የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ትዕግሥት ተረፈ እንደገለጹት፤ ሴቶች በምርጫ ሂደት ያላቸው ተሳትፎ ከጎለበተ ፍትሐዊ፣ ነፃና አሳታፊ የምርጫ ምኅዳር ለመፍጠር መሠረታዊ ነው። "ሴቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ በመጠቀም የሚጫወቱት ሚና ትልቅ ነው" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቷ፤ ከቤተሰብ ማስተዳደር ጀምሮ እስከ ፖለቲካ ተሳትፎ ድረስ ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል። ፌዴሬሽኑ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ግንዛቤ ለመፍጠርና በታዛቢነት ለመሳተፍ ፈቃድ ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል። እስካሁንም እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ለበርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን ጠቅሰው፤ በመላ ሀገሪቱ ታዛቢዎችን ለማሰማራት ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል። የዛሬው መድረክም ከኦሮሚያ ክልልና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አመራሮችና አባላትን ያሳተፈ መሆኑን ጠቅሰዋል። የምርጫ ታዛቢዎች የሕዝብ አመኔታን ለመጨመር፣ የአፈጻጸም ጉድለቶችን ለማሻሻልና የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል። የሴቶች ማኅበራት የታዛቢነት ሚናቸውን መወጣታቸው ምርጫው ተዓማኒ እንዲሆንና የዴሞክራሲ ባህል እንዲጠናከር እንደሚረዳም አክለዋል።   የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ እጸገነት ሙሉጌታ በሰጡት አስተያየት፤ ሴቶች በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሚናቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ገልጸዋል። ሌላዋ የመድረኩ ተሳታፊ ወይዘሮ መስከረም አንበሴ በበኩላቸው፤ ሥልጠናው በምርጫ ሥነ-ምግባርና በታዛቢነት መርሆዎች ላይ ያጠነጠነ በመሆኑ የተጣለባቸውን ሕዝባዊ አደራ በኃላፊነት ለመወጣት አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።   በየደረጃው የሚገኙ ሴቶች በምርጫው ዕለት በየምርጫ ጣቢያው በመገኘት ለመብታቸው የሚቆሙ ዕጩዎችን እንዲመርጡና ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።  
በጠቅላላ ምርጫው የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል- የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች
Apr 4, 2026 213
አርባምንጭ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፡- በጠቅላላ ምርጫው የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል ሲሉ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ነዋሪዎቹ ለመራጮች ምዝገባ የተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ነዋሪዎች በቀሪው ጊዜ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ መውሰድ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች በምርጫው የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችል ካርድ ወስደናል ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ተረፈ አልበኔ እንዳሉት በምርጫው ለመሳተፍ ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ስልጣን የሚያዘው በምርጫ ብቻ በመሆኑ የሚበጀኝን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ነው ያሉት። የጊዜ ሰሌዳው እየተጠናቀቀ በመሆኑ ካርድ ያልወሰዱ በቀሩት ጥቂት ቀናት ካርድ መውሰድ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። ወ/ሮ አሰለፈች አሽኔ በበኩላቸው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ እና ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል። አቶ ማሩ ሞታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መተግበሪያ በመጠቀም በኦን ላይን መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የመራጮች የምዝገባ ሂደት እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ቦርዱ ካወጣው መርሃ ግብር መረዳት እንደሚቻል ገልፀው ካርድ ያልወሰዱ ነዋሪዎች በቀሪው ጊዜ ሊወስዱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።    
በምርጫው ድምጽ በመስጠት የዜግነትና የዴሞክራሲ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል
Apr 4, 2026 239
ጊምቢ/መቱ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር የተሻለ ሐሳብና አማራጭ ይዞ የቀረበን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስደው መዘጋጀታቸውን የምዕራብ ወለጋ እና የኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ለሀገርና ለሕዝብ የሚበጅ ሐሳብ ይዞ የሚመጣን አካል ለመምረጥ፣ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።   የመቱ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ቀሲስ ታከለ ዳዲ፤ ምርጫ መንግሥት የሚመሠረትበት ሂደት መሆኑን ገልጸው፣ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ሂደት መሳተፍ የዜግነትና የዴሞክራሲ መብት መሆኑን ተናግረዋል። የመቱ ከተማ ነዋሪዎቹ ወይዘሮ የኋላሸት አዳሙና አቶ አወል አብዱ፤ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ጠቅሰው ለሀገር ዕድገት ይሠራል ብለው ያመኑበትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት እየተጠባበቁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የጊምቢ ከተማ ነዋሪው አቶ ደገፋ ጂሬኛ፣ የሕዝብን ሁለንተናዊ ልማት የሚያረጋግጥ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውንና ክርክሮችን በንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ጠቁመዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪው አቶ ታረቀኝ ሞሲሳ፤ በምርጫው በመሳተፍ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ መምረጥ የዜግነት ግዴታችን ነው ብለዋል።
ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሀገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥና ምርጫውን ለማሳካት የሚያስችል አቅም ገንብቷል
Apr 4, 2026 342
አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሀገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥና ምርጫውን ለማሳካት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም መገንባቱን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ። የፀጥታና መረጃ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የክልል ርዕሳነ- መስተዳደሮች የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሀገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥና ሰባተኛውን ምርጫ በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ጉብኝት ማድረጋቸውን አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡ በጉብኝቱ የተሳተፉ የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ-መስተዳድሮች በሰጡት አስተያየት፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ በቦታና በጊዜ ሳይገደብ መረጃዎችን የመሰብሰብና የመተንተን ብቃቱ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡   የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በየትኛውም ስፍራ የሚከሰቱ ማናቸውም የፀጥታና ደኅንነት ስጋቶችን በመለየት ተንትኖ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥበት የማድረግ አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ትኩረት በመስጠት በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና ድኅረ- ምርጫ ወቅት የደኅንነት ስጋቶች ቢያጋጥሙ ቀድሞ ለመለየትና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረጉን በጉብኝታቸው ወቅት ማረጋገጣቸውን አብራርተዋል፡፡ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም የተለያዩ ተዋንያን ሚናም ወሳኝነት ስላለው ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡ "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሀሳብ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል።   በመድረኩም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮችና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር በሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር እያደረግን ነው
Apr 4, 2026 273
ጅማ ፤መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በማስቀደም በሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር እያደረጉ መሆኑን የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ሃላፊዎች ተናገሩ። የለውጡ መንግስት ባለፉት ዓመታት በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ስኬቶችን በተግባር ያረጋገጠበት ስኬታማ አመት መሆኑን በብዙ ማሳየዎች መግለጽ ይቻላል። የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ሰላማዊ ትግል እያደረጉ እና የመንግስት ተቋማትን የመምራት እድል የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በማስቀደም በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር እያደረጉ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች ገልጸዋል። የሸካ ዞን የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሀይሉ ተስፋዬ፤ ከለውጡ በፊት በፖለቲካው ለመሳተፍ ባደረጉት ጥረት በጠላትነት ተፈርጀውና ተገፍተው መቆየታቸውን አስታውሰው በለውጡ በተፈጠረው ምቹ ምህዳር በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ቢኖርም በሀገር ብሄራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ላይ የጋራ አቋም ያላቸው መሆኑን አንስተው ከማይገባ ተቃርኖ እና የጠላትነት እሳቤ በመውጣት በሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር እያደረግን እንገኛለን ብለዋል። በተፈጠረው ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር በሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር እያደረግን ለዘንድሮውም ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስተባባሪ አቶ ሰለሞን መኮንን፤ ለውጡ በተለይም የፖለቲካውን ምህዳር በማስፋት እና አሳታፊ በማድረግ የሚታይና ተጨባጭ ውጤት የመጣበት ሆኗል ብለዋል። በፖለቲካ ፉክክሩ በሀገር ብሄራዊ ጥቅም ላይ የጋራ አቋም መኖሩን አንስተው ከገዢው ፓርቲ ጋር ስለ ሀገር እና የዜጎች ጉዳይ ላይ ተቀራርበን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያደገ እንዲመጣ ኢዜማ የበኩሉን መወጣቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚያስኬዱ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችል አቅም እየገነባች ነው
Apr 4, 2026 67
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚያስኬዱ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችል አቅም እየገነባች መሆኑን የዘርፉ ተዋናዮች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያደረገችው ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር የሜዲካል ቱሪዝምን የሚያሳልጥ መሆኑም ተመላክቷል። በአዲስ አበባ እየተካሄዱ የሚገኙት ሁለተኛው የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን እንዲሁም 10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለም አቀፍ የሕክምና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይና ጉባኤ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ስኬቶች አጉልተው አሳይተዋል።   በኤግዚቢሽኑ የተሳተፉ የሕክምና መሣሪያ አምራቾችና አስመጪዎች እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የጤና ዘርፉን ለማዘመን በሰጠችው ልዩ ትኩረት ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ የማይታሰቡ ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት ውጤታማ ሕክምና መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል። የበርለ ኦፍ ሜዲካል ካምፓኒ ተወካይ ዶክተር ኪሩቤል ክፍሌ፥ የኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ እያሳየ ያለው እድገት እጅግ ፈጣንና አስገራሚ መሆኑን ገልጸዋል። ቀደም ሲል ትኩረቱ በተላላፊ በሽታዎች ላይ ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ሆስፒታሎች ውስብስብ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ መስጠት የሚያስችሉ ትልልቅ ማሽኖችን ታጥቀዋል ብለዋል። ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዜጎች ለሕክምና ወደ ውጭ ለመሄድ ይገደዱባቸው የነበሩ ህክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አቅም በመፍጠር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያድን ጠቅሰዋል።   የቻይናው ሰንሼን ማኑፋክቸሪንግ ድርጅት የኢትዮጵያ ካንትሪ ማናጀር አማኑኤል ሽጉጥ በበኩላቸው፤ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙና የሐኪሞችን ሥራ የሚያቀሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንጻር በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርገውና የሜዲካል ቱሪዝምን የሚያሳልጥ መሆኑን ገልጸዋል። ‎በዓለም አቀፍ የሕክምና ኤግዚቢሽኖች በኢትዮጵያ መካሄድ መጀመራቸውም ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።   መንግሥት ለጤናው ዘርፍ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ድጋፍና ለሕክምና መሣሪያዎች ግዢ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ላይ ቅድሚያ መስጠቱ ለዚህ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ ከዓለም ኢንተርናሽናል ፒኤልሲ የመጣው የባዮ ማዲካል ኢንጂነር አስቻለው አሸናፊ ናቸው። በተጨማሪም የሕክምና መሣሪያዎች በጥብቅ ቁጥጥር እንዲገቡ መደረጉ ጥራታቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስችሏል ብለዋል። በቀጣይም በሀገር ውስጥ ያለውን የማምረት አቅም በመጠቀም ወደ ማምረቱ ሥራ ይበልጥ መግባት ለዘርፉ እድገት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው የከተማዋን የኮሪደር ልማትና የከተማ እድሳት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል
Apr 4, 2026 140
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው የከተማዋን የኮሪደር ልማትና የከተማ እድሳት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ዛሬ በይፋ መርቀው መክፈታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል። ‎በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክት፤ የኦሎምፒክ ደረጃን ያሟላ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎችን እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን፣ ዘመናዊ የቤት እና የዉጪ ጂም ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ከማህበረሰብ አገልግሎቶች ጋር አቀናጅቶ የያዘ ነው።   ልማቱ ሁሉንም የእድሜ ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣ የልጆች መጫወቻዎችን፣ እንደ እድሜያቸው የተከፋፈሉ መዋኛ ገንዳዎች፣ የአሸዋ ላይ የእጅ እና የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን እና የጤና ማዕከልን አካቷል። በኦሎምፒክ መድረክ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶች በፓርኩ መሐል መቆማቸው፤ የጀግኖቻችንን ታሪክ ሕያው ከማድረግ ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ስፖርተኞች ታላቅ ተምሳሌት ይሆናሉ።   ከስፖርታዊ አገልግሎቶች ባሻገር፣ ፕሮጀክቱ 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ፕላዛ ከሬስቶራንቶች እና ካፌዎች ጋር፣ 300 መኪናዎችን በአንዴ የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ እና በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን አካትቷል። ከወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፣ ነዋሪዎችን በመዝናኛም ሆነ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘመናዊና ሁለገብ የከተማ ፕላን ማሳያ ነው። ‎ ይህ ያለመችውን የምታሳካዋ፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ገጽታ ነው!
አዲስ ስፖርት ፓርክ ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ሆነ
Apr 4, 2026 178
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በፈጣን የግንባታ አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውና ለከተማዋ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ ያለው አዲስ ስፖርት ፓርክ ተጠናቆ ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ፕሮጀክቱ መንግሥት ለዜጎች ጤና እና ለከተማዋ ዘመናዊ ገጽታ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት እንደሆነም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፣ ከግንባታ ፕሮጀክትነት ባለፈ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ መገለጫ መሆኑን አመልክቷል።   ማዕከሉ የከተማዋን ነዋሪዎችና ጎብኝዎችን ፍላጎት በሚያረካ መልኩ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ የተገነባ እንደሆነ ተገልጿል። በፓርኩ ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና መሰረተ ልማቶች መካከል የኦሎምፒክ ደረጃን የሚያሟላ የመዋኛ ገንዳ፣ የ800 ሜትር የሩጫ ትራክ፣ እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች ይገኙበታል። ከነዚህም በተጨማሪ ለሕፃናት መጫወቻ የሚሆኑ ስፍራዎችና ልዩ የአሸዋ ሜዳዎች ለማህበረሰቡ ዕረፍት እንዲውሉ ተዘጋጅተዋል። የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃትና የሀገር ባለውለታዎችን ለመዘከር፣ በዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ መድረክ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አንጋፋ አትሌቶች የክብር ሐውልቶች በፓርኩ ውስጥ መቆማቸው ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል።   ይህም ስፍራው የስፖርት ማዘውተሪያ ብቻ ሳይሆን የታሪክና የጀግንነት መዘከሪያ እንዲሆን ያደርገዋል። ማዕከሉ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ ለንግዱ ማህበረሰብ ሰፊ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆች ተካተውበታል። በተጨማሪም በአንድ ጊዜ 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ መገንባቱ፣ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከልን መርቀው ከፈቱ
Apr 4, 2026 159
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል። ‎የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ማካተቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ተቋሙ ለድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድ እንደ ማገር ሆኖ ያገለግላል ብለዋል። ‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢኮኖሚ
አዲስ ስፖርት ፓርክ የመደመር እሳቤና ተግባር የታየበት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 4, 2026 141
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦‎ አዲስ ስፖርት ፓርክ የመደመር እሳቤና ተግባር የተገናኙበት ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዲስ ስፖርት ፓርክ ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፓርኩ የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ልማት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ልማት ያለ ሰብአዊ ልማት ምልዑ ሊሆን እንደማይችል ጠቁመው፣ የስፖርት መሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች የዚሁ የሰው ተኮር ልማት ተግባር ማሳያ መሆናቸውን አመልክተዋል። የመደመር መንግሥት ዋና እሳቤም ሁሉን አቀፍ ልማትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ መሆኑንና ዛሬ የተመረቀው ፓርክም ይህ እሳቤና ተግባር የተገናኙበት ትልቅ የስፖርት አውድ መሆኑን አስገንዝበዋል።   ፓርኩ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሁሉም ስፖርቶች መሠረተ ልማት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎችን አሟልቶ የተገነባ ነው ብለዋል። ይህም ስፍራ ለወጣቶች መወዳደሪያና ለታዳጊዎች መጎልበቻ ከመሆኑ ባለፈ፣ ለሀገራቸው ትልቅ ክብር ያመጡ የስፖርት ፈርጦች ሐውልት የቆመበት የጀግኖች አምባ ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ መዘጋጀቱን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት። በተለይም በፓርኩ ውስጥ የጀግኖች ገጽታ ከነጽናታቸውና ከነአርዓያነታቸው፣ እንዲሁም ፊታቸው ላይ ከተጻፈው የሀገር ፍቅር ጋር ተደምሮ በሐውልት መታሰቢያነት መቆሙን አንስተዋል። ሐውልቶቹ ለኢትዮጵያ የሮጡ እግሮችንና ለሀገር የተከፈለ ውድ ዋጋን በሚዘክር መልኩ በክብር ተቀርጸው የተቀመጡ መሆናቸውንም እንዲሁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል እያከበረና ኃላፊነቱን እየተወጣ ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። ቃል ተግባር እየሆነ አዲስ አበባም እየተቀየረች፣ ኢትዮጵያም ወደ ክብር ማማ እየገሰገሰች ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ወቅቱን የዋጀ ነው
Apr 4, 2026 71
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጭ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚስማማና ወቅቱን የዋጀ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ድረስ መሆኑም ተገልጿል። ብስክሌቶቹ በሞባይል መተግበሪያ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የጂፒኤስ ሲስተም እንደሚጠቀሙም በመርሀ ግብሩ ላይ ተመላክቷል። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የትራንስፖርት አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወቅቱን የዋጀ ምላሽ መሆኑንም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው፤ ለሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፤ ሚኒስቴሩ በሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰማሩ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ያብባል አዲስ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ የሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በኮሪደር ልማቱ ከ240 ኪሎ ሜትር በላይ የብስክሌት መንገድ መሰራቱን ጠቁመው፤ መሰረተ ልማቱንም በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መጽደቁንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ስድስት የሚሆኑ የብስክሌት ኦፕሬተሮች ቅድመ ምዝገባ በማድረግ የዝግጅት ስራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዘርፉ የትራንስፖርት አገልግሎትን በጉልህ የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም አካባቢዎች ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸውም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት በተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን መገንዘብ መቻሉን ያመለከቱት የአዲስ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ሳተና ዋሬ ናቸው። ለአገልግሎቱ የሚውለው መተግበሪያም በራስ አቅም በሀገር ልጆች መልማቱን ጠቁመዋል። አገልግሎቱ የፋይዳ ቁጥር በማስገባት መጠቀም የሚቻል ሲሆን፤ ክፍያውም በዲጂታል መንገድ በሞባይል የሚፈጸም መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስፋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በደንብ ቁጥር 183/2017 የብስክሌት መጋራት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ ማጽደቁ ይታወሳል።  
ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች እየተሰራች ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 
Apr 4, 2026 71
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ የማጽናት እና የመስራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ ስፖርት ፓርክ ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ግንባታ ስራ ሁለት መሰረታዊ ምሰሶዎችን መያዝ እንዳለበት ገልጸው፤ ትናንትን በወጉ እና በቅጡ የሚያስታውስ ነገን የሚሰራ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። በአድዋ ሙዚየም የአባቶቻችንን ጀግንነት እና ነጻነታችንን እንደምናስታውሰው ሁሉ ነገን የምንሰራው በልጆቻችን ነው ብለዋል። መንግስት የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ 35 ሺህ መዋዕለ ህጻናትን ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ጠቅሰው ዓላማውም የተሻለ ዝግጁነት ያለው ትውልድ መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል። የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ግብ ነገን የሚሰራ ትውልድ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ነው ያመለከቱት። የሀገር ግንባታ እና የሰው ልማት የሚቆራኘው በአካዳሚክ እውቀት በሚገኝ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ መስተጋብር ጭምር ነው ብለዋል። አዲስ ስፖርት ፓርክ እንደ አበበ ቢቂላ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ደራርቱ ቱሉ እና ጥሩነሽ ዲባባ ያሉበትን ሐውልቶች መያዙን ጠቅሰው፤ አትሌቶቹ ለትውልድ ምሳሌ የሆኑና ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ያስጠሩ መሆናቸውን አንስተዋል። ለአትሌቶቹ ሐውልቱ የቆመላቸው በህይወት እያሉ ማክበር ስለሚገባም ነው ብለዋል። ፓርኩ በሁሉም መስክ ህጻናት እና ታዳጊዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችሉ ስፍራዎችን መያዙንና ይህም ትውልዱ ከአትሌቶቹ እንዲማር መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል ነው ያሉት። ህጻናቱ አትሌቶቹን መሆን እየተመኙ ተግተው ከሰሩ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ የሚያስጠሩ አትሌቶችን ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል። ሳንዘራ ማጨድ አይቻልም ፣ መዋዕለ ንዋያ ሳናፈስ ውጤት መጠበቅ ከንቱ ምኞት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስመጥር ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደ አዲስ ስፖርት ፓርክ አይነት መሰረተ ልማቶች ወሳኝ መሆናቸውን አብራርተዋል። የስፖርት ፓርኩ በተለያዩ ስፖርቶች ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማቶች መያዙን ጠቅሰው፤ ይህም ለታዳጊዎች ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል። ህጻናት ፓርኮች፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች እና ንጹህ ስፍራዎችን እያዩ ካደጉ ሌላ ሀገር መሄድን መመኘት ትተው በሀገር መኩራትና መስራት እያደገ እንደሚሄድ ገልጸዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያ እንደምትገነባ ገልጸው፤ በሁሉም መስኮች ትናንት እና ነገን በማስተሳሰር ሀገርን መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ አብዛኛው ህዝቧ ወጣት በመሆኑ ተግቶ መስራት እና ራስን በእውቀት ማበልጸግ ከታቸለ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካን የመደገፍ ትቅል እድል እንዳለ አንስተዋል። በክህሎት እና ብቃት ሰዎች ተሰርተው የሚያድጉበት መሰረተ ልማት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ አሁን ላይ የሚሰሩ ስራዎች የነገዋን ኢትዮጵያ እና ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውንም አመልክተዋል። የአዲስ ስፖርት ፓርክ የካዛንችስ መለወጥ እና ማበብን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው ፓርኩ ትውልድ የሚሰራበት ቦታ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እየተሰራች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ኢትዮጵያን የማጽናት እና የመስራት ተግባር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ነው ያስረዱት። ኢትዮጵያን በመስራት ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Apr 4, 2026 231
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል።   በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ መገንባቱንም አመልክተዋል።   የእውነተኛ ልማት ማዕከል ማህበረሰቡ ላይ መሆን አለበት በሚል እምነት፣ ይህ ፕሮጀክት ከላቀ የስፖርት አገልግሎት ባለፈ በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ አቅም የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆችን እንዲሁም 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ መያዙንም ነው የገለጹት። በተጨማሪም በአንዴ 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ ያለውና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፤ ንፁህና ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የጀመርነውን ቁርጠኝነት ጉልህ ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል። ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቷል
Apr 4, 2026 178
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው "የአፈር ለምነትንና ጤናማነትን ማስጠበቅ ለግብርና ሽግግር" በሚል መሪ ሃሳብ 14ኛው ዙር ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ተካሂዷል። በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አክበር ጩፎ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል። የአፈር ለምነትና ጤናማነትን መጠበቅ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድግ በመሆኑ ለግብርና ዘርፍ ምርምሮች ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን በዘርፉ የተሰማሩ ተመራማሪዎችን በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡   ዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ ከ79 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ከ50 በላይ የምርምር፣ 54 የማህበረሰብ ተኮር እንዲሁም ከ14 በላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውድነህ ቶማስ(ዶ/ር) ናቸው። በዩኒቨርሲቲው ያለውን ዕውቀት ከሀብት ጋር ለማቀናጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በዚህም የዘንድሮው 14ኛው ዓመታዊ የምርምር ኮንፍረንስ የአፈር ጤንነትና ምርታማነት ላይ አተኩሮ መዘጋጀቱን ጠቁመው በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራንና ባለሙያዎች ቅንጅታቸውን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል አበክረው መስራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል።   በዩኒቨርሲቲው የአፈር ሳይንስ ጥናት ፕሮፌሰር ፋኑኤል ላዕከማርያም ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት በአፈር ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮች ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር የሰው፣ የአካባቢ እና የእንስሳትን ጤና ለማስጠበቅ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። በጥናታዊ ጽሁፋቸው የአፈር እርጥበትን ማስጠበቅ፣ አሲዳማነትን መቀነስ፣ ምርታማነትን መጨመርና ካርቦንን አምቆ የመያዝ አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም የተለያዩ ጥናቶች መስራታቸውን ጠቁመው ይህም መንግስት ዘርፉን ለማሻሻል የጀመረውን ውጥን የሚደግፍ በመሆኑ ወደ አርሶ አደሮች በማምጣት እንደሚተገበርም አስረድተዋል።   በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝና የአየር ንብረጥ ለውጥ መቋቋም ፕሮግራም ዳይሬክተር አወቀ ሙሉዓለም(ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋማቸው የሀገሪቱን ግብርና ለማሻገር በጥናት የተደገፈ ስራ በመስራት የግብርናን ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ለማሳካት እየተጋ መሆኑን በመጥቀስ ለስራው ውጤታማነት ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከቤተሰብ ፍጆታ ያለፈ ትርፍ ምርት በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ገበያን በማረጋጋት በኩል አበርክቶ እንዲኖረው ትልቅ ድርሻ መወጣቱን አመልክተዋል። በመድረኩ ከ10 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ሙያዊ ውይይት ተደርጎ የፖሊሲ አቅጣጫ የማመላከት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በምርምር ስራዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት ይጠናከራል
Apr 4, 2026 204
ሰመራ፣መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ) ፡-በምርምር ስራዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ዓሊ ተናገሩ። በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀ የአደጋ ተጋላጭ ማህበረሰብ ዝግጁነትና መቋቋም ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ ተካሄዷል።   በመድረኩ ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት፤ የምርምር ስራዎችን በማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይገባል። የምርምር ውጤቶቹ ማህበረሰቡን ከማንቃትና ተጋላጭ እንዳይሆኑ ከማድረግ አኳያ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል። በተለይም ተመራማሪዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የአካባቢውን ችግር ተረድተው እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተው በአካባቢው የሚገነቡ ህንፃዎች ጭምር ግምት ውስጥ ሊገቡ እንደሚገባም አመልክተዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በበኩላቸው፤ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ዝግጅት ማድረጉ የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።   የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ውሳኔ ሰጪ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ፣ ፖሊሲዎችን ማጤንና የህንፃ ግንባታ ደረጃ ግልፅ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልክተው እያከናወኑ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር ሊጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው የምርምር ግኝቶችን በየጊዜው በማውጣት ለሚመለከታቸው አካላት ማጋራት ይገባል ብለዋል። በመድረኩም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።  
ኢትዮጵያ በያዝነው ዓመት መድኃኒት የማምረት አቅሟን ከ50 በመቶ በላይ ታደርሳለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Apr 4, 2026 108
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ መድኃኒት የማምረት አቅሟን፣ በ2018 ዓ.ም ከ50 እስከ 55 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ሀገር ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት፣ አፍሪካ ለከፍተኛ አደጋ ትጋለጣለች የሚል ግምት በበለጸጉት ሀገራት በኩል የነበረ ቢሆንም፣ ያ ሳይሆን መቅረቱን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ወረርሽኙ በሽታን አስቀድሞ የመከላከል ዝግጁነት ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶ ማለፉን ተናግረዋል።   በወቅቱ መንግስት በምግብ፣ በልብስ እና በመድኃኒት ዘርፎች ራስን መቻል አለብን የሚል ግልጽ አቅጣጫ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል። በዚህም በምግቡ ዘርፍ ስንዴን ጨምሮ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ በመድኃኒት በኩል ግን በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ አለመታየቱን ጠቁመዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማምረት የምትችለው መድኃኒት ስምንት በመቶ ብቻ እንደነበርም አስታውሰዋል። በቂ የመድኃኒት ምርት ማምረት አለመቻሉ፣ ሻጮች የግዢ መድኃኒት መያዛቸውና የግሉ ዘርፍ በምርት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ እምብዛም ፍላጎት አለማሳየቱ በመንግስት በኩል ትልቅ ቁጭት እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። በምግብ፣ በልብስና በመድኃኒት ራሱን ያልቻለ ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እንደሌለው ጠቅሰው፣ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን አመልክተዋል።   ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማምረት የምትችለው የመድኃኒት ድርሻ ቀደም ሲል ከነበረበት ስምንት በመቶ አሁን ላይ ወደ 44 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። በቅርብ ጊዜያት የሚመረቁ ፋብሪካዎችን ታሳቢ በማድረግም በተያዘው ዓመት የማምረት አቅሙ ከ50 እስከ 55 በመቶ እንደሚደርስም አስታውቀዋል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ቢያንስ መድኃኒትና ክትባትን በራሷ አቅም እንድታመርት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በአንጋፋው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም የተመረቀው ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ከፍተኛ ወጪ የወጣበት መሆኑን ጠቁመው፣ ለማዕከሉ ለመድኃኒትና ክትባት ምርት መሠረት የሚጥሉ ዕውቀቶችን መያዙንም አመልክተዋል። በኮቪድ ወቅት የናሙና ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላክ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አዲሱ የምርምር ማዕከል እንዲህ ያሉ ምርመራዎችን እዚሁ የማከናወን አቅም እንዳለው ገልጸዋል። ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ክፍሎችን እንዲሁም የመድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ ማዕከልን ያካተተ ሲሆን፤ ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድም እንደ ዋልታ የሚያገለግል መሆኑን አመልክተዋል። ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር ረገድ ማዕከሉ በመድኃኒት ምርት ራስን ለመቻልና ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በጥረትና በትጋት ከሰራን ሀገርን ማሳደግና ማበልጸግ እንደሚቻል ይህ ማዕከል ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤት እየተገኘ ነው
Apr 4, 2026 82
ደሴ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) አስታወቁ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እና በስታርታፕ ፖሊሲ አዋጅ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።   ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሁለንተናዊ እድገትን ለማፋጠን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። ባለፉት ዓመታት ለዚህ አጋዥ የሆኑ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እቅድን በስኬት ለማጠናቀቅ ማስቻሉን አውስተዋል። በተለይም በሪፎርም ማሻሻያዎችና በተቋማት ግንባታ፣ በመሠረተ ልማትና በሰው ኃይል ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነትና በዲጂታል ክፍያ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ በጤና፣ በግብርና እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በማበረታታትና ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግ፣ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ መሪ እንድትሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። ለዚህ ውጤታማነትም ሚኒስቴሩ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ የዛሬው መድረክም የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አወል ሰይድ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ዩኒቨርሲቲው የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲውን የውስጥ አሠራር በቴክኖሎጂ ከመደገፍ ባለፈ፣ የሌሎች ተቋማትን አቅም በመገንባት የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ እንዲሳካ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሀገር እድገት መሠረት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎታል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት አገልግሎቱን ማዘመን መቻሉንና ሂደቱን በጥናትና ምርምር እያገዙ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በመድረኩ ከወሎ፣ ከመቅደላ አምባ፣ ከወልድያ፣ ከራያ እና ከሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ስፖርት
ሲዳማ ቡና በመሪነት ግስጋሴው ቀጥሏል
Apr 4, 2026 76
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ያለው በ25ኛ ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 48 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ሃዋሳ ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ከፍ ማድረግ ችሏል። ቡድኑ በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት 13 ደርሰዋል። በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ23 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አላሸነፈም። የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው በሊጉ ከመረብ ላይ ያሳረፋቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 11 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1፣ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አዲስ ስፖርት ፓርክ የጀግኖች መዘከሪያ እና የትውልድ መገንቢያ ስጦታ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 4, 2026 129
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ አዲስ ስፖርት ፓርክ የጀግኖቻችን ክብር ህያው የሚሆንበት፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በጤናማ ትውልድ የምንገነባበት ታላቅ ስጦታ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውና በዓለም መድረክ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ ጀግኖች አትሌቶች መታሰቢያ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባው አዲስ ስፖርት ፓርክ ዛሬ ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ጀግኖች አትሌቶች በተገኙበት ፓርኩ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማዋ እምብርት በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ማዕከል፣ ሁሉንም ዓይነት የስፖርት ዘርፎች ያካተተ ነው ብለዋል። ፓርኩ የነገዋን ኢትዮጵያ በአካልና በሞራል የታነጸ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ለጀግኖች አትሌቶች የክብር መግለጫ፣ ለወጣቶች የተስፋ ምንጭ፣ ለልጆች ደግሞ የደስታ ስጦታ ሆኖ መቅረቡን አመልክተዋል። የፓርኩ ልዩ ገጽታ በኦሎምፒክ መድረክ የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት የኢትዮጵያን ስም ላስጠሩ 15 የምንግዜም እንቁ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የቆመው የክብር ሐውልት እንደሆነም አንስተዋል። ይህም ጀግኖችን በቁም ለማመስገንና ለተተኪው ታዳጊ ትውልድ እኔም እችላለሁ የሚል ትልቅ የስነ-ልቦና ተነሳሽነት ለመፍጠር ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ነው ከንቲባዋ የገለጹት። ፓርኩ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚመጥን መልኩ የተገነባ ሲሆን፣ ለባለሙያዎችና ለወጣቶች የኦሎምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የመዋኛ ገንዳዎች፣ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎችን መያዙን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ስፖርትን የዘወትር የሕይወት ዘይቤ ለማድረግ የሚያግዙ ዘመናዊ የቤት ውስጥና የውጪ ጂም፣ የዌልነስ ሴንተር (Wellness Center) እና የ800 ሜትር የመሮጫ ትራክ ተካትተውበታል። ለልጆችና ለታዳጊዎች ደግሞ እንደ እድሜያቸው የተዘጋጁ ዘመናዊና ባህላዊ የመጫወቻ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎችና የአሸዋ ላይ ስፖርት ሜዳዎች ተገንብተዋል። መሠረተ ልማቶቹ ህጻናት በአካልና በአዕምሮ እንዲያድጉ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ላይ ገልጸዋል። ይህ የልማት ፕሮጀክት ከስፖርት ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጠናክራል ያሉት ከንቲባዋ በተለይም ለካዛንችስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች የተገነቡ የሴራሚክ መሸጫ ሱቆች፣ የዜጎችን ኑሮና ስራ ከልማቱ ጋር ለማስተሳሰር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተጨማሪም 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ቤዝመንት የመኪና ማቆሚያ፣ የአውቶቡስ ተርሚናል፣ እስከ 3 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግድ ሰፊ ፕላዛ እና ምቹ ሬስቶራንቶች ፓርኩን ለቤተሰብና ለጎብኚዎች ተመራጭ እንደሚያደርጉት ነው ያብራሩት። ፓርኩ ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተሰናስሎ የተሰራ በመሆኑ፣ የአረንጓዴ ልማት መናፈሻውና የውሃ ፋውንቴኑ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ አረንጓዴ ከተማ ለማድረግ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ስፖርት ፓርክ የፅናትና የብልጽግና ምልክት መሆኑን ገልጸው ከተማዋን ውብና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ ከካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ የደን አያያዝ ስራዎችን እያከናወነች ነው
Apr 4, 2026 119
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ ዘላቂ የመሬትና የደን አስተዳደር ልምዶችን እያሳደገች መሆኑን የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገለጹ። ዶክተር አደፍርስ ወርቁ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የካርበን ክምችት መኖሩን በማንሳት፤ አብላጫው በደን ሀብት ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ ሀገሪቱ ከካርበን ሽያጭ የምታገኘው ገቢ እንዲጨምር የጎላ ሚና እየተጫዎተ እንዳለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ የብዝሃ ህይወት ባለቤት በመሆኗ የተሻለ የካርበን ክምችት ለመያዝ የሚያስችል ተስማሚ ሥነ-ምህዳር እንዳላት ዶክተር አደፍርስ ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአየር ንብረትና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈች መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ካርበንን ከአየር ላይ በማስወገድ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መንገድ እንዲከማች እያደረገ ነው ብለዋል። ቀደም ሲል በደን መመንጠርና ባልተገባ የመሬት አያያዝ ምክንያት ወደ ህዋ ይለቀቅ የነበረውን ሙቀት አማቂ ጋዝ መከላከል የሚያስችሉ ተግባራት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካይነት እየተተገበሩ እንዳለ አስረድተዋል። በዚህም ከካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ ዘላቂ የመሬት እና የደን አሥተዳደር ልምዶችን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ሁለተኛው ደግሞ እጽዋት በሚተከሉበት ወቅት ቀደም ሲል ወደ ህዋ የሄደውን ካርበን አምቀው የሚመልሱበትን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ እና ከልቀት የተጠበቀውን ካርበን ገበያ ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እያከናወነች ባለችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት የካርበን ሽያጭን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑንና ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር የግዢ ውል ስምምነት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም የኖርዌይ መንግስት እንደመነሻ የ75 ሚሊዮን ዶላር የካርበን ግዢ እንዲሁም የዓለም ባንክም እንዲሁ የግዢ ውል ማሰሩን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ኖርዌይ እና የዓለም ባንክ ሊገዙት ከሚፈልጉት በላይ ካርበን ማመንጨቷን ጠቁመው፤ እስከ አንድ ቢሊየን ዶላር ሊያመጣ የሚችል ካርበን ሀብት መኖሩን ገልጸዋል። በዓለም ገበያ ላይ ለካርበን ግዢ የሚመደበውን ከፍተኛ ሀብት ወደ ኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ ማምጣት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በዓለም ላይ ያለውን የካርበን ፋይናንስ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከማጠናከር ባለፈ ሰነዶች የማደራጀትና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።          
ኢትዮ ቴሌኮም ለዲጂታልና ታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው
Apr 3, 2026 367
አዳማ ፤መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎትን ከማስፋት ባሻገር ለዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ ቴሌኮም በአዳማ ከተማ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል በመገንባት በዛሬው እለት አገልግሎት አስጀምሯል።   በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ በኢትዮጵያ የዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአዳማ ከተማ ተገንብቶ በዛሬው እለት ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከልም የዚሁ ልማት ጥረት አካል መሆኑን ጠቁመዋል። የአዳማው ማእከል በአንድ ጊዜ 12 ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የሚያደርግ አቅም እንዳለው ተናግረው በሌሎች አካባቢዎችም የማስፋት እቅድ መኖሩን ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ከፈጣንና ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ ለዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።   በዚህም መሰረት አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀ ማድረጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ፤ የስማርት አዳማ ፕሮጀክት ተቀርፆ አሰራርና አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ሂደት የኢትዮ ቴሌኮም አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በከተማዋ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ይኖራል
Apr 3, 2026 76
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጠንና ሥርጭት የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም የበልግ ዝናብ በመጠንና ስርጭት ከፍተኛ ድርሻ የሚወስድበት ወቅት መሆኑን ገልጿል። በዚህም በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከቀደሙት ሁለት የበልግ ወራት በመጠንና ሥርጭት የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር አስታውቋል። ይህም የአየር ጠባይ ሁኔታ የበልግ አብቃይና ተጠቃሚ አካባቢዎች ለሚያከናውኑት የግብርና ሥራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል ብሏል ኢንስቲትዩቱ በመግለጫው። በተለይም በተያዘው የመጋቢት ወር የሚስተዋለው ተከታታይ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ በቡቃያና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች ምርታማነት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል። በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚጠበቀው እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለቦረና፣ ጉጂና መሰል ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ሰብል ልማት፣ ግጦሽ መሬትና የውሃ አቅርቦት ወሳኝ መሆኑንም አመላክቷል። በዚህም የበልግ አብቃይ አካባቢ አርሶና አርብቶ አደሮች ማሳቸውን በማዘጋጀት የሚጠበቀውን አመቺ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለመጠቀም ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። በበልግ ዝናብ መዋዠቅ አዝማሚያ ምክንያት ዝናብ አጠር የሆኑ አካባቢዎች የሚያጋጥማቸውን ተከታታይ ደረቃማ ሁኔታ ለመቋቋም እርጥበትን በማሳ ማቆየት የሚያስችል ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ኢንስቲትዩቱ አስውገንዝቧል። በሌላ በኩል በአንዳንድ አካባቢዎች በሚኖር ከባድ ዝናብ ሊፈጠር ከሚችል የመሬት መንሸራተት፣ የአፈር መሸርሸርና ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል።
የክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው
Apr 3, 2026 83
ባህር ዳር፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በለውጡ ዓመታት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከእለት ወደ እለት ስኬታማ እየሆነ መምጣቱ እየተመሰከረለት ነው። በመርሃ ግብሩ በብዛትና እና በአይነት መጠነ ሰፊ ችግኞች ተከላ መካሄዱን ለአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፤ ለደን ሽፋን መጨመር ብሎም የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ እያስቻለ ነው። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ መሰሉ ብርሃኑ ለኢዜአ እንዳሉት፤በለውጡ ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዘርፉን ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው። መርሃ ግብሩ ለአካባቢ ጥበቃና ለአየር ንብረት ለውጥ መሻሻል፤ ለደን ሽፋን መጨመር እና የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል። መርሃ ግብሩ ተግባራዊ መደረጉ በክልሉ 13 ነጥብ 9 በመቶ የነበረውን የደን ሽፋን ወደ 18 ነጥብ 9 በመቶ ለማስደግ እንደተቻለም ነው የተናገሩት። በነዚሁ የለውጥ አመታት በ22 ሺህ 189 ተፋሰሶች ላይ በተካሔደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርታማነት ለማሳደግ ያስቻለ መሆኑንም አብራርተዋል። የአረንጓደ ልማቱ በተለይም ለንብ ማነብ፣ ለእንስሳት እርባታና ለፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 205
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 524
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት።   ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው 
Mar 22, 2026 213
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሐተታዎች
የጤና ነገር ...
Apr 3, 2026 1065
በዮሐንስ ደርበው የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። የኒውትሬሽን ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የሰው ልጅ የሰውነት ክፍል 60 በመቶው ውኃ እንደመሆኑ ለተስተካከለ ጤና ሚዛን መጠበቅ በቂ ውኃ መጠጣት ይገባል። ውኃን በትክክለኛው መጠንና ጊዜ መውሰድ ከተቻለ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን 50 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ነገር ግን ሰውነት የሚፈልገውን የውኃ መጠን በአግባቡ ካላገኘ ለዕለታዊ እና በጊዜ ሂደት ሥር ለሚሰድዱ ህመሞች የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምርም ያነሳሉ። ለመሆኑ ሰውነት የሚፈልገውና በቂ የውኃ መጠን የሚባለው መጠኑ ስንት ነው? በቂ ውኃ አለመጠጣትስ የሚያስከትለው ችግር ምንድን ነው? በሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ የኒውትሬሽን መምህር፣ ተመራማሪ እና ደራሲ ይሁኔ አየለ ምላሽ አላቸው። አንድ ሰው የሚያስፈልገው የውኃ መጠን በዕድሜ፣ ጾታ፣ በሥራ ባሕርይ፣ በመኖርያ አካባቢ፣ እንደ ጤና ሁኔታው እና እንደ ሰውነት ክብደቱ እንደሚወሰንም በምላሻቸው አስገንዝበዋል። ለምሳሌ የስኳር ታማሚዎች፣ የምታጠባ እናት፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ብዙ አድካሚና ላብ የሚያወጡ፣ በሞቃታማ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቀን 3 ሊትር ውኃ መጠጣት አለባቸው ይላሉ። በአማካይ ግን በቀን አንድ ሰው ከ2 እስከ 3 ሊትር ውኃ መጠጣት እንደሚጠበቅበት ይገልጻሉ። ጤናማ ሕይወት የሚመሠረተው ከውኃ ነው፤ ለምሳሌ ውኃማውን 60 በመቶ የሰውነት ክፍል ሚዛን ለማስጠበቅ የግድ አስፈላጊውን መጠን ውኃ መጠጣት እንደሚገባ ይመክራሉ። በሰውነት ውስጥ የሚካሄደው ሕይወታዊ ሂደት (ባዮሎጂካል ፕሮሰስ) ውኃን መሠረት ያደረገ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለምሳሌ ለተስተካከለ የሥርዓተ-ምግብ ሂደት፣ ቆሻሻን ከሰውነት አጣርቶ ለማስወጣት፣ የአጥንት መገጣጠሚያ ሥራን ለማስተካከል እና ለሌሎችም በርካታ የሰውነት ክፍሎች የተሳለጠ ተግባር ውኃ ቁልፍ መሆኑን አንስተዋል። ይህን ተከትሎም ውኃ ካሎሪ አልባው መድኃኒት (ተፈጥሯዊው መድኃኒት) እስከመባል መድረሱን ነው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያስረዱት። ሰውነት የሚያስፈልገውን ያህል ውኃ አለመጠጣት ግን ድካም ያስከትላል፤ ለማየት፣ ለመንቀሳቀስ፣ ለመሥራት፣ ለማሰብ፣ ለመረጋጋት . . . አያስችልምና ሲሉ ያብራራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ ሰው ውኃ የመጠማት መጠኑ ከአራት በመቶ በላይ ከሆነ ለሞት ሊጋለጥ እንደሚችልም ጠቅሰዋል። ውኃ አለመጠጣት፤ የጨጓራ ህመምን በማባባስ ማስገሳት፣ የቆዳ ድርቀትና ግርጣት፣ የኩላሊት ህመም ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ያደርጋል ነው ያሉት። ከምግብ በፊት 30 ደቂቃ ቀድሞ ውኃ መጠጣት ውፍረትን ለመቀነስ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። በቂ ውኃ ከመጠጣት በተጨማሪ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ማዘውተር እንደሚመከርም ገልጸዋል። የፈላ ውኃ እና የዝናብ ውኃን በብዛት መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድና በኩላሊት ላይም ጫና እንደሚፈጥር አመላክተዋል። ለተስተካከለ ጤናማ ሕይወት የግድ ውኃ መጠጣትን ልማድ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ። #ውኃ_መጠጣት #ጤና #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency
ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች
Apr 3, 2026 1517
በዮሐንስ ደርበው የለውጡ መንግሥት ኢትዮጵያን ማሥተዳደር ከጀመረ እነሆ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ 8 ዓመት ሞላው። በእነዚህ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊ ዘርፉ በዲፕሎማሲውና በሌሎችም መስኮች የተለያዩ ስኬቶች ተከናውነዋል። በእነዚህ ጥቂት ዓመታትም ለማሳካት ቀርቶ ለማሳብ የማይደፈሩ ብዙ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። የተገኙት ስኬቶች ከጊዜያቸው የፈጠኑ ናቸው። ለዚህም ሕዝቡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በነቂስ እየወጣ አድናቆቱን ገልጿል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሰጡት የሰላ አመራርነትና ቁርጠኝነትም አክብሮቱንና ምሥጋናውን ገልጿል። የለውጡ መንግሥት አካሄድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የልማት ፕሮጀክቶችም በይበልጥ ተስፋፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆሙም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ባስተጋቧቸው መልዕክቶቻቸው አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በለውጡ መንግሥት ለማሳካት ቀርቶ ለማሰብ የማይደፈሩ ተግባራት ተከናውነዋል። ከእነዚህ ከፍተኛ ጥቅም ከተገኘባቸው የታሪክ እጥፋትን ካሠረጹ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹን ቀጥለን በወፍ በረር እንዳሥሣለን። ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ሥልጣኔ - በምርጫ ካርድ መምረጥ የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። • የኮሪደር ልማት እንደምናውቀው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነትና ልዩ ትኩረት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከሁሉም አስቀድሞ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። አሁን ላይ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የበርካታ ከተሞችን ገጽታ የቀየሩ አስደማሚ ሥራዎች ተከናውነውበታል። ይህም በገጠር ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ለዘመናት አሮጌ ገጽታዋን ይዛ ያሸለበችውን አዲስ አበባ እንደ አዲስ የፈጠራትም ይኸው ፕሮጀክት ነው። አሁን ላይ መዲናይቱ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን ለውጥ ዐይተው ዝም ማለት አልቻሉም። ከመደመማቸው አንጻር የዘወትር አጀንዳቸውም እያደረጓት ይገኛሉ። ይህንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ነው ማለታቸው ይታወሳል። ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑንንም አስረድተዋል። ከለውጡ መንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ለማሳደግም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ድርብርብ ፕሮጀክት ነው የኮሪደር ልማት። • የበጋ መስኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የለውጡ መንግሥት ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ለዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አንዱ ማሳኪያ ሥልት አድርጎ እየተጋ ይገኛል። የበጋ መስኖ ስንዴ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ ማስገባት አቁማ መላክ እንድትጀምር ያስቻለ ኢኒሼቲቭ ነው። በዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችና በሜካናይዜሽን ታግዞ በስፋት እየተሠራበትም ይገኛል። ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በምርታማነት ማደግና የሥራ ዕድል በመፍጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል። የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብም ከፍተኛ ውጤት ተገኝቶበታል። ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ላይ ባሳየችው ትጋት፤ ፍጆታዋን በራሷ ዐቅም የሸፈነችው፣ ስንዴን ከውጭ ማስገባትን ያቆመችው፤ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችው በለውጡ መንግሥት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ በመሸለም ለጥረታቸው ዕውቅና መስጠቱም ይታወሳል። • መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል አንድ ጉዳይን ለማስፈጸም እዚያም እዚህም መንከራተት የግድ ነበር። በዚህ አያበቃምና ወረፋውም ሌላ ችግር ነው። መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ባካሄዳቸው ሕዝባዊ ውይይቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉልን የሚሉ እሮሮዎች በረከቱ። መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል ሥራ ወደ ተግባር አሥገባ። በዚህም መሠረት ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ ጀመረ። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነውም አሉ። ለዚህ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ የሆነውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስጀመራቸውንም ገለጹ። እንግዲህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በመሰብሰብ በቴክኖሎጂ ታግዘው በተሳለጠ ሂደት እንዲሰጡ በማድረግ የተገልጋይን እንግልት፣ ገንዘብ እና ጊዜ መቀነስ ያስቻለ አሠራር ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት ተደርጎም ይወሰዳል። በየከተሞቹም እየተስፋፋ ነው። • አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ አይ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው በቁጭት በተለያዩ መድረኮች ያነሳሉ። ለዚህም መፍትሔ ዘይደው ተቋማትን ከማቋቋም ጀምሮ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ተግተዋል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ ለመጓዝ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቋመች። የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ በመክፈት በግብርናው፣ በጤናው እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠርም በሂደት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት ቀይሮ ወደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ሕንፃ በተዛወረበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የሚታይ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ የሮቦቶችን ሶፍትዌር ብቻ ሳይሆን ውጫዊ የአካል ክፍልን (ሃርድዌር) መሥራት ጀምሯል ብለዋል። ድሮን ማምረት ብቻ ሳይሆን የማነጋገር ዐቅም እየፈጠረ ያለ ተቋም መሆኑንም አንስተዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደር አሠራርን የሚከተል መሆኑን ጠቁመው፤ በርካታ ምርቶችን አውጥቷል ማለታቸው ይታወቃል። ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮሉሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን ሲሉ ማስገንዘባቸውም ይታወሳል። • የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው። በዚህ ሂደት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊታአውራሪነት ይጠቀሳል። በተደራጀና ተቋማዊ ሆኖ ባልተቆራረጠ አካሄድ እየተከናወነ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተተከሉ ችግኞችም በየዘርፉ ተጠቃሚነት አድጓል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል። • የሌማት ትሩፋት ከመጋቢት ሥጦታዎች አንዱ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ነው። የምርት አቅርቦትን በማስፋት ለተረጋጋ ግብይት እና ለተመጣጠነ ሥርዓተ-ምግብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይም ይገኛል። ኢኒሼቲቩ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለሀገራዊ የሥርዓተ-ምግብ መሻሻል ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ነው። የዋጋ ንረትን በማረጋጋት፣ የምርት ስብጥርን በማሳደግና በዘላቂነት በማቅረብ ረገድም የጎላ ሚና አለው። የግድ ሰፋፊ መሬት መፈለግ ሳያሻ በትንሽ ቦታ ብዙ በማምረት ፍጆታን ከመሸፈን አልፎ ኢኮኖሚን በመደጎም እና የሥራ ዕድል በመፍጠርም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። • የቱሪስት መዳረሻ ልማት ቅርሶች እንዲጠገኑ፣ አዳዲስ ሎጂዎች እንዲገነቡ፣ በመዳረሻ ስፍራዎች መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ያስቻሉ ተግባራት በለውጡ መንግሥት ተከናውነዋል፤ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ እና ስኬታማ ኢኒሼቲቭ ነው። በዚህ ሂደት ከሐሳብ አመንጭነት ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የጻፉትን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ጭምር ለቅርስ ጥገናና ለቤተ-መጻሕፍት ግንባታ እንዲውል አድርገዋል። በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት፤ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደ ተግባር አስገብተዋል። በእነዚህ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። አማራጭ የቱሪስት መዳረሻም ሆነዋል። • የተቋማት ግንባታ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪል ሐሳብ በተካሄደው የዐበይት ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ኮንፈረንስ ላይ፤ የተቋማት ግንባታና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ብለዋል። በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው ሲሉም አስገንዝበዋል በወቅቱ። ዘመን የማይለውጣቸው ዘላቂ ጠንካራ ሃገራዊ ተቋማትን በመገንባት ረገድ ብዙ ርቀት መጓዝም ተችሏል። በመሆኑም የመንግሥት ተቋማት ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲሆኑ በማድረግ እና ሥርዓት በተለዋወጠ ቁጥር የማይፈርሱ ወይም የሚሻገሩ ተቋማት መገንባት ተችሏል። ይህ ትጋት ተጠናክሮም ቀጥሏል።
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3449
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ 
Mar 2, 2026 407
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል።   የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል።   የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 4, 2026 89
ከመጋቢት 20 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ መሆኗን ገልጸው፤ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፣ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ፣ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ብለዋል። ፈጣን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሠራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ ዐቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው ከፍተዋል። ‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል በወቅቱ። ‎የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከል ማከተቱን አብራርተዋል። ‎ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። • የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)‎ የከተማችንን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል። ‎በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋልም ነው ያሉት። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል ሲሉም ገልፀዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአፋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል። በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት፤ ለሌሎች በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሠነድ እንደሚሆን አመላክተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የጸጥታና ደኅንነት ተቋሞቻችን ችግርን ወደ ዕድል እንዲቀየሩ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጨምና ከትናንት ዕዳዎች ተላቀን፣ የዛሬ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ለነገው ትውልድ የምትመጥን ሀገር ለመገንባት በዓላማ ጽናት እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል። • ስለ መጋቢት 24 መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የመጣውን የለውጡን መንግሥት የሚደግፉ ሕዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ሰልፎች ላይም መንግሥት ባለፉት ሥምንት ዓመታት ያመጣቸውን ለውጦች እና የተገኙ ስኬቶችን የሚያወሱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) ለሰጡት ስኬታማ አመራርነት የሚያሞግሱና የሚያመሠግኑ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝባዊ ግፊትና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው ብለዋል። ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብሏል። የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች ሲልም ገልጿል። ይህን ለውጥ ዕውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፤ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም ነው ያለው። • የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ሕንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ጽሕፈት ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል ብሏል። የ1954 የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ሲልም አስገንዝቧል ጽሕፈት ቤቱ።
ባሳለፍነው ሳምንት
Mar 28, 2026 355
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ‎የ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን እና የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ሎጁ የዛሬ 50 እና 60 ዓመት መሠራት የነበረበት ቢሆንም፤ አሁን ስለዘገየን አንቆጭም ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ስለሠራንም አንረካም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሩጫችን ገና ብዙ እንደሆነ፣ አፋር ገና እንዳልተነካ አስበን ይህን ጅማሮ ይበልጥ በማላቅ ለማስቀጠል እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቃና ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነም ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸውን ፋይዳም አንስተዋል። • ኢትዮጵያ በማላቦው ጉባዔ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ማላቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉባዔው ከመጋቢት 18 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። • የልማት ሥራዎች ጉብኝት በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎሉና ግንባታቸው እየተፋጠኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት እና የአየር መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ሲሉም በወቅቱ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት የሀገር ሀብት ፈስሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የመገጭ ግድብ ምስክር መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይህ ሞዴል መንደር በአካባቢው ለረጅም ዓመታት የቆየውን የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ጥያቄ በተግባር መልሷል ብለዋል። በሀገራችን ከተማው ብቻ ሳይሆን ገጠሩም እኩል እየተዋበ፣ በልማት እየተገነባና በዕድገት ፍኖት ላይ በጽኑ መሠረት እየተራመደ ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ትልቁ ማሳያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። • "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ በአዲስ አበባ 4ኛው "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይሆን አጋርነትን ነው፤ እርዳታን ሳይሆን ኢንቨስትመንትን ነው! ለባለ ሀብቶች ምቹ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ለችሎታ እና ለዕድል በሯን ወለል አድርጋ መክፈቷንም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን በፍጥነት ወደ ከፍታ እየገሠገሠች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ የዕድገት ጉዞ፤ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያ ለእናንተ ዝግጁ የሆነ፣ በዕድሎችና በስኬቶች የተሞላ ታላቅ የኢንቨስትመንት መሶብ አላት፤ ኑ አብረን እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል! • የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫም፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። በዚህም ከክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀሌ እና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ ሂደቱን በክልሉ ለማካሄድ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው፤ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም አስረድተዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 183
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 859
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል የነዳጅ ብክነትን ለመቀነስ ምን ዓይነት ብልኀት መጠቀም ይመከራል? ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 3801
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2572
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8358
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6847
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60755
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54724
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35252
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32857
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 27902
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 27090
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26597
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26218
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60755
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54724
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35252
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32857
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስን የታደገው ሀገራዊ ለውጥ
Apr 4, 2026 218
የስልጣኔ መነሻ የጥበብ መፍለቂያ የሆነችው የምስራቋ ፈርጥ ሀረር የንግድ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ትስስር ማዕከል ሆና በትውልድ ቅብብሎሽ ከአንድ ሺህ አመታት በላይ የተሻገረች እድሜ ጠገብ ከተማ ነች። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርትና የንግድ ማዕከል የነበረችው ከተማዋ በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ እንዲሁም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶችን የያዘች ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ነች። ከእነዚህ ቅርሶች መካከል ጥንታዊ የስነ-ህንፃ የጥበብ፣ የከተማ ፕላን፣ ባህላዊ የመሬት አጠቃቀም፤ አካባቢያዊ መስተጋብርና የስልጠኔ መገለጫ በሚል እኤአ በ2006 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በአለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ቅርስ ይጠቀሳል፡፡   ቅርሱ ምንም እንኳን በኪነ ህንፃ ጥበብ በላቁ በአርቆ አሳቢ አባቶች እንዳይፈርስና ሚዛኑን ጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ በተመረጠ ድንጋይ እና አፈር በልዩ ጥበብ የተገነባ ቢሆንም በጥበቃና እንክብካቤ ጉድለት ምክንያት ከግማሽ ምዕተ አመታት በላይ እድሜን ባስቆጠረው ቅርስ ላይ አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል። በቅርሱ ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍሎች የህገ-ወጥ ግንባታዎች መበራከትና በሌሎች ምክንያቶች በደረሰበት ጉዳት የጥንት ስልጣኔ ምልክት የሆነው አለም አቀፉ የጀጎል ቅርስ ከዩኔስኮ የአለም ቅርስነት እስከመሰረዝ የደረሰ አደጋ ተደቅኖበት ነበር። ሆኖም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአዲስ እሳቤ፤ በተደመረ አቅምና በላቀ ቁርጠኝነት፤ ህዝብን በማሳተፍ ከመንግስት ምንም አይነት በጀት ሳይመደብለት ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማልማት ተቻለ። አሁን ላይ እነኛ በሸራና በጨርቅ በተሰሩ ህገወጥ ግንባታዎች ተወሮ የነበረው 3ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጀጎል ግንብ ዙሪያ በአበቦችና ቅርሱን በሚያስውቡ ስራዎች ደምቀዋል።   በዚህም አባቶች ከዘመኑ ቀድመው ዛሬም ድረስ ግርምትን በሚያጭር ጥበብ አንፀው ያኖሩት ይህንን የሀገር ሀብት በመታደግ ትውልዱን ከታሪክ ተወቃሽነት ወደ ዳግም ታሪክ ሰሪነት እንዲሸጋገር ማድረግ ተችሏል። ስራውም የትላንትን መሰረት ሳያናጋ፤ የቀድሞ አባቶችን ጥበብና ስልጣኔ ሳይጋፋና ሳይዘነጋ ጥንታዊውን ከዘመናዊ ጋር አዋህዶ ቅርስ መገኛ ለሆኑ ሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት በሚሆን ደረጃ አስደናቂ ስራ ተከናወነ። የአካባቢውን ሀብትና እውቀት በመጠቀም እውን የተደረገው ይህ ስራ በእያንዳንዱ የሀረሪ ጥንታዊ ቤቶች በሚገኙ የታሪክ አሻራዎችና የባህል መገለጫዎች እንዲደምቅም ሆኗል። ይህ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ቅርሱን ከአደጋ ከመታደግ ባለፈ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከግለሰብ እስከ ማህበራትና የዳያስፖራ አባላት ድረስ ሁሉም በያገባኛል ስሜት አሻራውን ያኖረበት ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት ነው። ይህም በቅርሱ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲጎለብት በማድረግ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ያስቻለና ቀደም ሲል የነበሩ የግለኝነት አስተሳሰቦችን በመቅረፍ የወል እሳቤ እውን የሆነበት ፕሮጀክት ሆኖ ታይቷል።   ዛሬ ላይ እነኛ የቆሻሻ መጣያ የነበሩ እና በአካባቢው ለማለፍ ከባድ የነበሩ የጀጎል መንገዶች ፀድተው ውብ ሆነዋል። ይዘታቸውን ለቀው የነበሩ ቅርሶችም የአለም ቅርስነት ክብርና መስፈርትን በሚመጥን ደረጃ ታድሰዋል። ዛሬ የጀጎል ነዋሪ እንደቀድሞ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ሳይሆን መኖርን የሚመርጥባት የወጣውም መመለስን የሚመኝባት ምቹ አካባቢ ሆናለች። የመቻል ምልክት የትብብር ውጤትና የአብሮነት ጉልበት በተግባር የታየበት የጁገል መልሶ ልማት ጥንታውን መንደር ለነዋሪዎች ምቹ ለጎብኚዎች ተመራጭ የጉብኝት ስፍራ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል። በለውጡ መንግስት በአዲስ መልክና ቀለም የተዋበው ጀጎል የሀረርን ቀደምት ስልጣኔ እየመሰከረ የሀገርንም ገፅታ እየገነባ ይገኛል።
የለውጡ ትሩፋት - ግብርናን የሚያሻግረው ዕይታ
Apr 3, 2026 93
የለውጡ ትሩፋት - ግብርናን የሚያሻግረው ዕይታ በአሸናፊ በድዬ በኢትዮጵያ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ልዩ ቀን ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ዕለቱ አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበትና ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ የተጀመረበት ነው። ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች መሠረታዊ ውጤቶችን እያስመዘገበችም ትገኛለች። በተለይ በሀገር አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም መሰረት ፈጣን፣ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። ለዚህም ነው ዕድገቱን ፈጣንና ተከታታይ ለማድረግ አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ተለይተው ወደ ሥራ የተገባው። እነዚህ ዘርፎች ኢኮኖሚው በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ እንዳይቀርና በማንኛውም ዓለም አቀፋዊ ጫና ውስጥ የማይናወጥ ጽኑ መሠረት እንዲኖረው ያደርጋል። በተለይም ግብርናው ለኢንዱስትሪው ግብዓት ሲያቀርብ፣ ቴክኖሎጂው ደግሞ የግብርናውን ምርታማነት ሲያሳልጥ፣ ማዕድንና ቱሪዝም ደግሞ ለሌሎች ዘርፎች መስፋፋት ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሬ ሲያመነጭ የተቀናጀ የሰንሰለት አሰራር መዘርጋት ይችላል። በዚህ መሠረት፣ ከለወጡ ወዲህ የሀገሪቷን የኢኮኖሚ ገጽታ እየቀየሩ ያሉትን እነዚህን ዘርፎችና የታሪካዊ ቀኗን ትሩፋት በወፍ በረር እንመለከታለን። 1. ግብርና ፦ የስንዴ አብዮት ግብርናው አሁንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው። ከለውጥ ማግስት በኋላ ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣትና በቴክኖሎጂ በመታገዝ በዘርፉ ታሪክ ቀያሪ ስኬት እየተመዘገበ ይገኛል። የዚህ ስኬት ዋነኛ ማሳያ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያተረፈው የኢትዮጵያ የስንዴ አብዮት ነው። 👉የቀድሞ ቅኝት፦ የዳራ እውነታዎችና የጥገኝነት ቀንበር ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የኢትዮጵያ ግብርና ገጽታ በእድገት ማነቆዎች የተጠፈረ ነበር። ኢትዮጵያ ሰፊ ለም መሬት፣ አመቺ የአየር ንብረትና ብዙ የሰው ኃይል እያላት ለዓመታዊ የፍጆታ ፍላጎቷ የሚሆን በቂ ስንዴ ማምረት አቅቷት ለዓመታት ቆይታለች። በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ በሚደርስ የውጭ ምንዛሬ ስንዴ በመግዛት ከውጭ ለማስገባት ትገደድ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪኳ ነው። የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ኢትዮጵያ የማምረት አቅም እያላት ለውጪ ምንዛሪ ወጪ ዳርጓት ቆይቷል፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሚፈጠሩ የዋጋ መዋዠቆችና ጂኦ-ፖለቲካዊ ቀውሶች ተጋለጭነቷን አስፍቶት እንደነበር የሚታይ እውነት ነው። 👉የለውጡ ስትራቴጂና ቁርጠኝነት የስኬት ጅማሮ ይህ ቢያንስ በስንዴ ጥገኛ አድርጎን የቆየው ተግዳሮት ታሪክ በሚቀይር መልኩ አዲስ ምዕራፍ ያስከፈተው መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነትና ያላሰለሰ ክትትል የተጀመረው የተቀናጀ ጥረት የኢትዮጵያን ግብርና ከነበረበት ተግዳሮት አላቆ ዘመናዊና ውጤታማ ምዕራፍ ያሸጋገረው ጉዞ ጀምሯል። ለዚህ በአብነት የሚጠቀሰው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስትራቴጂ ነው። በ2011 ዓ.ም በሙከራ ደረጃ በ3 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ብቻ የተጀመረው የመስኖ ስንዴ ልማት፣ ዘንድሮ አራት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል፡፡ የምርት መጠኑም ከ100 ሺህ ኩንታል ወደ 175 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኸር፣ በበልግና በመስኖ የሚለማው መሬት ስፋት ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ካለው ጋር ሲነጻጸር እምርታዊ ለውጥ ማሳየቱን ማስተዋል ይቻላል። በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች ሆናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ዓመት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢኮኖሚው ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር መሆኗን መግለጻቸውን ይታወሳል። ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የጀመረችው ስትራቴጂያዊ ንቅናቄ በሀገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የምርት ዕድገት አስመዝግቧል። ይህም የዘርፉን ጉዞ ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ አላቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙ እጥፍ እንዲልቅና ለሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነት ዋነኛ መሰረት እንዲሆን አስችሎታል። 👉የምግብ ሉዓላዊነትና የሀገር ክብር ዛሬ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ ከማስገባት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ ስንዴ ለውጭ ገበያ መላክ የጀመረችበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ይህም የለወጡ ትሩፋት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬን በማዳን፣ በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያን ተደራዳሪነትና ክብር ከፍ አድርጓል። በተጨማሪም እንደ አረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋትና መሰል መርሃ-ግብሮች በዘርፉ እምርታዊ ለውጥ እያመጡ ይገኛሉ። 2. ኢንዱስትሪ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይም አምራች ኢንዱስትሪው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ የሀገር ውስጥ ምርትን በመተካትና ለውጭ ገበያ የሚሆን ጥራት ያለው ምርት በማቅረብ ላይ ያተኮረ ነው። በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አማካኝነት ከዚህ ቀደም ተዘግተው የነበሩ በርካታ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ተመልሰዋል። የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን (እንደ ሲሚንቶና ብረት) በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም በማደጉ የግንባታ ዘርፉን አነቃቅቷል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመነትን በመሳብ ለሺዎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። 3. ማዕድን ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በሳይንሳዊ መንገድ በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ግኝቷን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ትልቅ ርብርብ እየተደረገ ነው። የወርቅ፣ የድንጋይ ከሰልና የሌሎች ማዕድናት ምርት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። በተለይ የድንጋይ ከሰልን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ቀንሷል። በዘርፉ ሕገ-ወጥ ዝውውርን በመቆጣጠርና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት የመንግሥት ገቢ እንዲያድግ ተደርጓል። 4. ቱሪዝም ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመጪነትና ተግባራዊ ስራዎች ቱሪዝም በአዲስ መልክ የተወለደና ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ዘርፍ ሆኗል። ቀደም ሲል በታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ላይ ብቻ ተወስኖ የቆየው እንቅስቃሴ፣ አሁን ላይ ሰው ሰራሽ መስህቦችን በማካተት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አረጋግጧል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተገነቡት አንድነት፣ እንጦጦና ወዳጅነት ፓርኮች የአዲስ አበባን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ከመቀየራቸውም በላይ ለከተማ ቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። በ"ገበታ ለሀገር" መርሃ-ግብር የተገነቡትና በቅርቡ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት እንደ ወንጪ (Eco-Tourism)፣ ጎርጎራ ያሉ መዳረሻዎች የሀገሪቷን የቱሪዝም ሀብት ወደ ክልሎች በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ስኬት አስመዝግበዋል። በቅርቡ ተመርቆ ወደ ሥራ የገባው የታላቁ ቤተ-መንግሥት የቱሪስት መዳረሻ እና በ"ገበታ ለትውልድ" ስር እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ዘርፉን ይበልጥ አጠናክረውታል። አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና በመሆኗ፣ በትላልቅ ስብሰባዎች አማካኝነት የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ያስታወቁት፤ አዲስ አበባን የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ በርካታ የልማት ሥራዎችና ሜጋ ፕሮጀክቶች ፍሬ ማፍራት በመጀመራቸው፣ በከተማዋ የሚካሄዱ ኩነቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነው። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 150 የሚሆኑ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኹነቶች በአዲስ አበባ የተካሄዱ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን መግለጻቸው ይታወቃል። ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የቱሪስት ፍሰት ጋር ተያይዞ ባለፉት ስድስት ወራት 155 ቢሊየን ብር ወደ ኢኮኖሚው ፈሰስ መደረጉን የገለጹ ሲሆን፤ መዲናዋን የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ለኹነቶቹ መጨመር በተጨባጭ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ናቸው ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በክልሎች ከተሞች እየተሰሩ ያሉት የኮሪደር ልማቶች ከተማዎቹን ልዩና ውብ ከማድረጋቸው ባሻገር ለቱሪስት መስህብ ሆነዋል። 5. ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ/ዲጂታል ኢኮኖሚ ይህ ዘርፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያደርግ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ለውጥ ወዲህ የደመቀ የለውጥ ሞተር ነው። የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስኬቶች በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶች (ፓስፖርት፣ ንግድ ፈቃድና ታክስ ክፍያ) በበይነ-መረብ በመሆናቸው ሌብነትንና እንግልትን ይቀንሳሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በ"ፋይዳ" መታወቂያ የታቀፉ ሲሆን፤ በ"ቴሌ ብር"ና መሰል አማራጮች የገንዘብ ዝውውር መዘመን ችሏል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ ሥራ መግባት የአገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ጨምሯል። የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ራዕይ የ2025 ስኬትን መሠረት በማድረግ አሁን ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በስፋት የመጠቀም ግብ ወዳለው ቀጣይ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። በ"ኢትዮ-ኮደሮች" መርሃ-ግብር አምስት ሚሊዮን ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት ለማሰልጠን እየተሠራ ያለው ሥራ ወጣቶችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እያደረገም ይገኛል። እነዚህ አምስት ምሰሶዎች ተነጣጥለው የሚታዩ ሳይሆን አንዱ ሌላውን የሚደግፉ ናቸው። ይህ ታሪካዊ ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ማማ የሚያሸጋግር ስትራቴጂ ነው። የነገዋ ኢትዮጵያ በራሷ የምትመገብና ለሌሎችም የምትተርፍ ጠንካራ ሀገር መሆኗን ያረጋገጠ ታርካዊ ክንውን ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም