ቀጥታ፡

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ የሚመራንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል

ሆሳዕና/ሚዛን፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምዝገባ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ካርድ በመውሰድ የሚመራንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የሆሳዕና እና የሚዛን አማን ከተሞች ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ጠቅላላ ምርጫውን ግንቦት 24 ቀን 2018 ለማካሄድ ቀን ተወስኖ፣ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራት በመከናወን ላይ ነው።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው አስራት ሽፈራሁና ወጣት እስራኤል አብይ የመራጭነት የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። 

አቶ መላኩ ደበበ እና ወጣት ትግስት በየነ የተባሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው የምርጫ ካርድ የመውሰጃ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት መብታቸውን ለመጠቀም ካርድ ለመውሰድ በምርጫ ጣቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቤ ታደሰ እና መሐመድ ሸምሱ በበኩላቸው፤ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብትን ለመጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ ካርድ በመውሰድ በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀት ይገባል ነው ያሉት።

ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ መሳተፍ የሚያስቸለውን ካርድ መያዙን የተናገረው ደግሞ ወጣት ሮቤል ኃይሌ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም