ቀጥታ፡

ቼልሲ ፖርት ቫሌ ላይ ሰባት ግቦች አስቆጥሮ በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተሻገረ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቼልሲ ፖርት ቫሌን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

 

ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆሬል ሃቶ፣ ጆአኦ ፔድሮ፣ ቶሲን አዳራቢዮ፣ አንድሬይ ሳንቶስ፣ እስቴቫኦ ዊሊያን፣ አሌሃንድሮ ጋርናቾ እና የፖርት ቫሌው ጆርዳን ላውረንስ-ጋብርኤል በራሱ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጋርናቾ ግቧን ያስቆጠረው በፍጹም ቅጣት ምት ነው።

በጨዋታው ላይ ቼልሲ ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል።

 

የስምንት ጊዜ የኤፍኤ ካፕ አሸናፊው ቼልሲ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።

በእንግሊዝ ሊግ ሶስተኛ እርከን ( ሊግ ዋን) የሚገኘው ፖርት ቫሌ ጉዞ ከሩብ ፍጻሜው ሊሻገር አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም