ቡናማዎቹ በሊጉ ደረጃቸውን አሻሽለዋል - ኢዜአ አማርኛ
ቡናማዎቹ በሊጉ ደረጃቸውን አሻሽለዋል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢኒያም ጌታቸው በ47ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ35 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን በ28 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 15ኛ ዝቅ ብሏል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።