ቀጥታ፡

የክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው

ባህር ዳር፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በለውጡ ዓመታት የተተገበረው  የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር  የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከእለት ወደ እለት ስኬታማ እየሆነ መምጣቱ እየተመሰከረለት ነው።

በመርሃ ግብሩ በብዛትና እና በአይነት መጠነ ሰፊ ችግኞች ተከላ መካሄዱን ለአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፤ ለደን ሽፋን መጨመር ብሎም የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ እያስቻለ ነው።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ መሰሉ ብርሃኑ ለኢዜአ እንዳሉት፤በለውጡ ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዘርፉን ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው።

መርሃ ግብሩ ለአካባቢ ጥበቃና ለአየር ንብረት ለውጥ መሻሻል፤ ለደን ሽፋን መጨመር እና የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።

መርሃ ግብሩ ተግባራዊ መደረጉ በክልሉ  13 ነጥብ 9 በመቶ የነበረውን የደን ሽፋን  ወደ 18 ነጥብ 9 በመቶ ለማስደግ እንደተቻለም ነው የተናገሩት።

በነዚሁ የለውጥ አመታት በ22 ሺህ 189 ተፋሰሶች ላይ በተካሔደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርታማነት ለማሳደግ ያስቻለ መሆኑንም አብራርተዋል።

የአረንጓደ ልማቱ በተለይም ለንብ ማነብ፣ ለእንስሳት እርባታና ለፍራፍሬ ልማት  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም