ቀጥታ፡

በምርጫው ድምጽ በመስጠት የዜግነትና የዴሞክራሲ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል

ጊምቢ/መቱ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር የተሻለ ሐሳብና አማራጭ ይዞ የቀረበን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስደው መዘጋጀታቸውን የምዕራብ ወለጋ እና የኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ለሀገርና ለሕዝብ የሚበጅ ሐሳብ ይዞ የሚመጣን አካል ለመምረጥ፣ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።


 

የመቱ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ቀሲስ ታከለ ዳዲ፤ ምርጫ መንግሥት የሚመሠረትበት ሂደት መሆኑን ገልጸው፣ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ሂደት መሳተፍ የዜግነትና የዴሞክራሲ መብት መሆኑን ተናግረዋል።

የመቱ ከተማ ነዋሪዎቹ ወይዘሮ የኋላሸት አዳሙና አቶ አወል አብዱ፤ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ጠቅሰው ለሀገር ዕድገት ይሠራል ብለው ያመኑበትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት እየተጠባበቁ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የጊምቢ ከተማ ነዋሪው አቶ ደገፋ ጂሬኛ፣ የሕዝብን ሁለንተናዊ ልማት የሚያረጋግጥ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውንና ክርክሮችን በንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪው አቶ ታረቀኝ ሞሲሳ፤ በምርጫው በመሳተፍ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ መምረጥ የዜግነት ግዴታችን ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም