ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በክልሉ ግብርናን በማዘመን በተከናወኑ ተግባራት ምርትና ምርታማነት እያደገ መጥቷል-ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Apr 6, 2026 19
አሶሳ፤መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርናን በማዘመን በተከናወኑ ተግባራት ምርትና ምርታማነት እያደገ መምጣቱን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ። 10ኛው ክልላዊ የግብርና ልማት አጋር አካላት የግንኙነት ካውንስል ጉባኤ፣የ2017/18 የመኸር ምርት አፈጻጸም እና የ2018/19 የመኸር ምርት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እንዳሉት፥ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን እየተመዘገበ ያለው ለውጥ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ የኢኮኖሚ አቅሙን እንዲያሳድግ አድርጓል። አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየተከናወነ የሚገኘው የግብርና ሥራ ሰፋፊ ማሳዎችን በዘር ከመሸፈን ባለፈ ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉን ተናግረዋል። በክልሉ በሌማት ትሩፋት፣በአረንጓዴ አሻራ፣በሩዝ፣ በስንዴና በተፋሰስ ልማት እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል። መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ያከናወናቸው የመስኖ ግንባታዎች እና ዘርፉን የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በበኩላቸው፤ በ2017/18 የመኸር እርሻ 55 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አስታውቀዋል። በ2018/2019 የመኸር እርሻ በክልሉ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬትን በማልማት ከ70 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት ዕቅድ መያዙን ኃላፊው ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘርፉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ወዳጅነት ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት ትሰራለች
Apr 6, 2026 44
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ በኢትዮጵያ የኳታር መንግስት አምባሳደር ሰአድ ሙባረክ አል-ናይሚ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሁለቱ አመራሮች በቆይታቸው በኢንቨስትመንት መስፋፋት እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በሚሰሩ የልማት ስራዎች ዙሪያ በዝርዝር መክረዋል። በተለይም የኳታሩ ሹራ ካውንስል (Shura Council) ከብልፅግና ፓርቲ እና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚችልባቸው መንገዶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎችንና እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ለአምባሳደሩ አብራርተዋል። በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የግብርና ምርታማነት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያላቸውን ጉልህ ሚና በዝርዝር አንስተዋል። አምባሳደር ሰአድ ሙባረክ አል-ናይሚ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እየተመዘገበ ያለው ውጤት አመርቂ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም ሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገችውን የተሟላ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ተገማች፣ ግልጽና ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፈጠሩን አመልክተዋል። አምባሳደሩ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተገኝተው ባደረጉት ምልከታ የልማት ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን መታዘባቸውንም ገልጸዋል። በተጨማሪም አቶ አደም ፋራህ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለአምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል። ኢትዮጵያ ለሰፊ ኢንቨስትመንትና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያላትን ቁርጠኝነትም በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል። የኳታር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አቶ አደም ፋራህ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ወዳጅነት ይበልጥ በማሳደግ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትና ለቀጣናዊ መረጋጋት በቁርጠኝነት መስራቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን አቀናጅቶ በመምራት ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Apr 6, 2026 119
ሀዋሳ ፤መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፡- ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን አቀናጅቶ በመምራት ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ዘሃራ ሁመድ ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያና አጎራባች ክልሎች የመንግስታት ግንኙነት መድረክ በሃዋሳ እየተካሄደ ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ዘሃራ ሁመድ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በጠበቀና አቀናጅቶ በመምራት ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተከናውነዋል ። በመሆኑም መደበኛ የመንግስታት ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚረዳ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት አዋጅ ተደንግጎ እየተሰራበት ነው ብለዋል። የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት የህዝቦችን ግንኙነትና ትስስር በማጠናከር በመንግስታት መካከል ያሉ የጋራ ግንኙነቶችን በአጋርነትና በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ተቋማዊ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ጤናማ የፌደራል ስርዓት ለመገንባት፣ ህገ-መንግስታዊ መሰረትን ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም ቀጣይነቱን ለማስጠበቅ እንደሚያግዝም ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የመንግስታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ በበኩላቸው ተቋማቱ የተረጋገጠ የርስ በርስ ግንኙነቶችን በማጎልበት የጋራ ልማትን የሚያጠናክሩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የዛሬው መድረክ ዋና ዓላማም ከዚህ ቀደም በተደረጉ መድረኮች የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በመሙላት የመንግስታትና የህዝቦችን ግንኙነትን ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በመርህ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የትብብር ስርዓት በማጎልበት ለፌደራላዊ ስርዓቱ ቀጣይነት ክልሎች የድርሻቸውን እንዲወጡ እንደሚያስችል ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት የመንግስታትን ግንኙነት በማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መገኘታቸውን የገለጹት ደግሞ የሲዳማ ክልል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ናቸው። የዘንድሮ የግንኙነት መድረክም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተቃረበ ጊዜ የሚካሄድ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። "የትብብር ፌዴራሊዝም ሞዴል እና የመንግስታት ግንኙነት በህብረ-ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ" በሚል ርእስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው። በመድረኩም አፈ-ጉባኤዎች፣ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የህግ አማካሪዎችና የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ119 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ ነው
Apr 6, 2026 68
ጊምቢ፣ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ከ119 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ መሆኑን የዞኑ የኅብረት ሥራ ማህበራት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጽሕፈት ቤት የምርት ግብዓትና አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ተሰፋዬ ታሲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለ2018/19 የምርት ዘመን የመኸር እርሻ 235 ሺህ 572 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሰራ ይገኛል። እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ 119 ሺህ 731 ኩንታል ማዳበሪያ በዞኑ መድረሱን ገልጸው ከደረሰው ውስጥ 18 ሺህ 849 ኩንታል በላይ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ ጋር ደርሷል ብለዋል። ስርጭቱ በዞኑ በሚገኙ አራት ዩኒየኖችና በየደረጃው ባሉ የኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት እየተከናወነ መሆኑ ጠቁመዋል። የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በወቅቱ መከናወኑን የገለጹት ቡድን መሪው፤ የአቅርቦት ሂደቱም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ እንዲከፋፈል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የላሎ አሳቢ ወረዳ አርሶ አደር ኦላኒ ሀብታሙ፤ ለዘንድሮ የእርሻ ሥራ የሚውል ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የእርሻ ሥራቸውን በተሟላ ዝግጅት ለማከናወን እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል። የጊምቢ ወረዳ አርሶ አደር ቡልቲ ኑሩ በበኩላቸው፤ ማዳበሪያው በኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት በጊዜ መሰራጨቱ አሁን ያለውን ዝናብ በመጠቀም የመሬት ዝግጅት ሥራቸውን አስቀድመው እንዲያጠናቅቁና የተሻለ ምርት እንዲያገኙ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኢ- ተገማችና ተለዋዋጭ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ቀደም ብላ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቷን የግብርና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።
የለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው- ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
Apr 6, 2026 92
ቦንጋ፤ መጋቢት 28/2018(ኢዜአ)፦ የለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል ። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ መጋቢት 24/2010 ዓ.ም የዴሞክራሲ መሰረት የተቀመጠበትና የመደመር እሳቤ የተበሰረበት ታሪካዊ እለት መሆኑን ገልጸዋል። የለውጡ ሂደት የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም ችግሮችን ወደ አድል በመቀየር በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ተናግረዋል። በብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች በመመራት የህዝብን ተጠቃሚነት እውን ማድርግና ምርታማነትን ማሳደግ የተቻለበት መሆኑን ገልጸዋል። በከተሞችም ይሁን በገጠር የቆዩ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ በመስጠት እድገትና ማንሰራራት እውን እንዲሆን የተሰራበት ስኬታማ የለውጥ አመታት መሆኑን አንስተዋል። የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዳሻው ከበደ፤ በለውጡ ዓመታት እንደ ሀገር የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎችም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና ሌሎችንም መጀመር መቻሉ በቀጣይ ትልቅ ሀገራዊ ተስፋ የሰነቀ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይበልጥ መትጋት ይኖረብናል ብለዋል። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተክለአብ ቡሎ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች የተገኙት በህዝቡ ጠንካራ ትብብር መሆኑን አንስተው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንሰራለን ብለዋል። በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ፖለቲካ

መጋቢት 24 ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለማሸጋገር የለውጥ ንጋት የፈነጠቀበት ታላቅ ዕለት ነው - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
Apr 6, 2026 152
ሐረር፤ መጋቢት 28/2018(ኢዜአ) ፦ መጋቢት 24 ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለማሸጋገር የለውጥ ንጋት የፈነጠቀበት ታላቅ ዕለት ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። በለውጡ የተገኙ ድሎችና ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በሐረር ከተማ ተካሂዷል። በዚሁ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በክልሉ ከገጠርና ከከተማ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎችም ተሳታፊ ሆነዋል። በኢማም አህመድ ስታድየም ለድጋፉ ለተገኘው ህዝብ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት ታላላቅ ሀገራዊና ክልላዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል። እለቱ በተለያዩ የልማት መስኮች ድል ለማስመዝገብ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዚህም ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ብሔራዊ መግባባት የተፈጠረበት ሀገረ መንግስት በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የለውጡ ዓመታት ጠንካራ የአመራር ውህደት የተፈጠረበትና ከፍተኛ የልማት መነሳሳት የታየበት መሆኑን ገልጸው፤ የህዝብ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ነው ብለዋል። በዚህም የለውጡ መንግስት ሀገር መምራት ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች እመርታዎች መመዝገባቸውንም አመልክተዋል። አገሪቷ የጀመረችውን ሁሉ አቀፍ የልማት ስራዎችን ህዝቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከመንግስት ጎን በመሆን እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ለመራጭነት የሚያበቃውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባም ጥሪ አስተላልፈዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በበኩላቸው የለውጡ መሐንዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ አመራር የመጡበት መጋቢት 24 በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን በሕዝብ ትግልና መስዋዕትነት የመጣ የድል ፍሬ ነው ብለዋል። መጋቢት 24 በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ጭቆናና ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት ከህዝባችን ጫንቃ ላይ የተነሳበት፤ በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ እይታ አካታች፣ ህብረ ብሄራዊ፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት የተጠናከረበት ነው ሲሉም ተናግረዋል። አቶ ጌቱ አክለውም እለቱ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማዕከል ያደረገ የመደመር መንግስት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት የሀገረ መንግስት ግንባታ በይፋ የተጀመረበት ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።
የክልሉን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የጸጥታ ሀይሉ የህግ ማስከበር ተግባሩን በላቀ ሁኔታ እየተወጣ ነው
Apr 6, 2026 157
ባህርዳር፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታን አስተማማኝ ለማድረግ የጸጥታ ሀይሉ የህግ ማስከበር ተግባሩን በላቀ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለፁ። የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በየደረጃው ለሚገኙ የፖሊስ አመራሮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖሊስ አባላት ሚና እና ስነ-ምግባር ላይ በማተኮር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማካሔድ ጀምሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እንዳሉት የክልሉን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የጸጥታ ሀይሉ የህግ ማስከበር ተግባሩን በላቀ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑንም አስረድተዋል። ህዝብ በመረጠው መንግስት መመራት እንዲችል ምርጫ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው የሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫ መሆኑንም አንስተዋል። ይህን እውን ለማድረግም ፖሊስ ገለልተኛነቱን በጠበቀ አግባብ ምርጫው ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። የፀጥታ ሀይሉ የምርጫ ሂደቱን ስኬታማ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ምርጫውን በተጀመረው አግባብ በስኬት ለማከናወን በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ስልጠናው ባህርዳርን ጨምሮ በስድስት ማዕከላት የተጀመረ ሲሆን በምርጫ ዙሪያ በተዘጋጁ ሰነዶች እየተሰጠም ይገኛል።
በክልሉ በመደመር እሳቤ በመመራት የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Apr 6, 2026 206
ሚዛን አማን፤ መጋቢት 28/ 2018 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመደመር እሳቤ በመመራት የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ። የለውጡን ስምንተኛ ዓመት የሚዘክር የድጋፍ ሰልፍ በሚዛን አማን ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዕለቱም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ፍቅሬ አማን፤ የለውጡ ትሩፋት የሆነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተመሰረተ በኋላ በክልሉ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸዋል። በመደመር እሳቤ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በማጠናከር የሕዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የመጡ ውጤቶችን በማስፋት፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሕዝቡ ተሳትፎ ጉልህ መሆኑን ጠቁመዋል። የኮሪደር ልማት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ተግባራት የዕድገት ጉዞው ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ሕዝቡ ለሀገር ልዕልና በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው፤ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የተስፋ መነሻና የብልጽግና ጉዞ መሠረት የተጣለበት ታሪካዊ ቀን መሆኑን ገልጸዋል። በለውጡ ዓመታት መንግሥት ያለፉ ስብራቶችን እየጠገነ መምጣቱን የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ ሕዝብን ባሳተፈ ተግባር የተመዘገቡ ውጤቶች የዞኑን ተጠቃሚነት ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። በተለይም የዞኑን እምቅ የተፈጥሮ ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ ልማት የመቀየር ሥራ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አክለዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት አቶ አማኑኤል ዘለቀ፤ በከተማዋ እየታዩ ያሉ የልማት ውጤቶች የለውጡ ፍሬዎች መሆናቸውን ገልጸው፣ ለተጨማሪ ስኬት ከመንግሥት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ሌላዋ የሰልፉ ታዳሚ ወይዘሮ ሚሚ ወልደሰንበት በበኩላቸው፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታቸው ከሚጠበቀው በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ አሻራቸውን ለማሳረፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በጠቅላላ ምርጫው ለሀገር የሚበጅ የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ ወስደናል- የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች
Apr 6, 2026 148
አምቦ፣ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫው ሀገርን የሚያሻግር ሀሳብ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ማሳወቁ ይታወሳል። ቦርዱ ቀደም ሲል ያወጣውን የምርጫ ካርድ የመውሰጃ ጊዜ ሰሌዳ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማራዘሙ ይታወሳል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች፤ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም፣ ለሀገር ሰላምና ልማት መቀጠል የተሻለ ሀሳብ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ካርድ መውሰዳቸውንና በተለያዩ መንገዶች የሚደረጉ የምርጫ ክርክሮችን እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዘሮ ኦልአንቱ ባንቲ በምርጫው የሴቶች እኩልነትና ነፃነትን ለማስከበር የሚሰራ የፖለቲካ ፓርቲን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል። ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ያሸጋግራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት በጉጉት እየጠበቁ መሆኑንም ተናግረዋል። በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለሀገራዊ እድገት የበኩላቸውን ለመወጣት የሚያበቃቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው ነዋሪ አቶ አበበ በቃና ናቸው። እንደ ሀገር የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል ሁሉም ሰው በተሰጠው ተጨማሪ ቀን የመራጭነት ካርዱን እንዲወስድም ከልምዳቸው መክረዋል። ዲሞክራሲያዊና የበለጸገች ሀገርን ለመገንባት በምርጫ ሂደት መሳተፍ የዜግነት ግዴታ ነው ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ሳራ ማሞ ናቸው። በምርጫው ሰላማዊና ፍትሐዊ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡና ለዚህም የምርጫ ካርድ በመውሰድ የፈለጉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በሐረሪ ክልል በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
Apr 6, 2026 204
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ለውጡ እውን መሆን የጀመረበትን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የከተማና የገጠር ወረዳዎች ነዋሪዎች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ በኢማም አህመድ ስታዲየም እየተካሄደ ነው። በስታዲየሙ የተገኙ ተሳታፊዎች የለውጡን ጉዞ የሚደግፉና ለቀጣይ ስኬቶች ያላቸውን ዝግጁነት የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ከተደመጡት መፈክሮች መካከልም ፦ "ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!" "እሳቤያችን ዘመን ተሻጋሪ፣ ተግባራችን ትውልድ ቀያሪ!" " ሐረርን ከቀደምት ከተማነት ወደ ብልፅግና ተምሳሌትነት እናሸጋግራለን!" የሚሉ ይገኙበታል። ሰልፈኞቹ መጋቢት 24 በኢትዮጵያ እውነተኛ የዲሞክራሲ ግንባታ የተረጋገጠበትና ሀገሪቱን የማላቅ ጉዞ የተጀመረበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።
የለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
Apr 6, 2026 253
ቦንጋ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። የድጋፍ ሰልፍ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና ስኬቶችን በመደገፍ ቀጣይነት እንዲኖራቸው መልእክቶች እየተላለፉበት ይገኛል። “የመጋቢት 24 ለውጥ ለአዲሱ ትውልድ ተስፋ ለሀገራችን አዲስ ተስፋ ”፣ የመጋቢት 24 የኢትዮጵያ ብልፅግና ጉዞ የተጀመረበት ታሪካዊ ቀን”፣ "ባለፉት ዓመታት በፈተናዎች ውስጥ የጸናች በስኬቶች የደመቀች ኢትዮጵያን ገንብተናል" የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶች በድጋፍ ሰልፉ ላይ እየተላለፉ ነው። በድጋፍ ሰልፉ ላይ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የከተማው ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ።
የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት የሚያስቀጥል የፖሊሲ አማራጭ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ካርድ ወስደናል -ወጣቶች
Apr 5, 2026 1007
ጭሮ፤መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡-በጠቅላላ ምርጫው የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት የሚያስቀጥል የፖሊሲ አማራጭ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሂርና ከተማ ወጣቶች ተናገሩ። የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ቀነ ገደቡ ሳይጠናቀቅ በመራጭነት ተመዝግበው ካርድ እንዲወስዱ ወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል። የምርጫ ሂደቱን አስመልክተው የሂርና ከተማ ወጣቶች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንደ ሀገር የተገኙ ልማቶችን አጠናክሮ የሚያስቀጥል የፖሊሲ አማራጭ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስደዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡ ወጣቶች መካከል ወጣት ያሲን አህመዲን እንዳለው በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እየተሳተፈ ነው። በሀገሪቱ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ ልማቶችን ለማስቀጠልና ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲጠናከር በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ለማበርከት የምርጫ ካርድ መውሰዱን ተናግሯል። ሌሎችም የምርጫ ካርድ በመውሰድ የዜግነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መክሯል። ወጣቶች በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ለዲሞክራሲ ግንባታና ለሀገር እድገት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የጠየቀው ደግሞ ወጣት ዝያድ ያሲን ነው። ለምርጫው ፍትሀዊነትና ሰላማዊነት የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለመምረጥ የሚያስችለውን ካርድ በወቅቱ መውሰዱን ተናግሯል። የመራጭነት ካርድ ያልወሰዱ ወጣቶች የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ሳይጠናቀቅ ተመዝግበው ካርድ እንዲወስዱ መክሯል። ሌላኛዋ የከተማው ነዋሪ ወጣት ሮዛ ያሲን በበኩሏ የበለፀገች ሀገር ለመገንባት በምርጫ በንቃት መሳተፍ ወሳኝ መሆኑን አስረድታለች። በገጠርና ከተሞች እየተስተዋለ ያለው ፈጣን ልማት ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረጉን ገልፃ ልማቱን ለማስቀጠል ይበጃል የምትለውን ፓርቲ ለመምረጥ ከወዲሁ የምርጫ ካርድ ወስጃለሁ ነው ያለችው። ለመራጮች ምዝገባ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ሳይጠናቀቅ ህብረተሰቡ የምርጫ ካርድ እንዲውስድ ወጣቶቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ማህበራዊ
በአፍሪካ ለአደጋ ስጋት ምላሽ አህጉራዊ አቅምን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Apr 6, 2026 131
አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ) ፦ 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም አህጉራዊ ጉባኤ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ገለጹ። ኮሚሽነሩ ጉባኤውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት፤ ጉባኤው በዋናነት በአፍሪካ አህጉር የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና የአደጋ ሥጋት ፋይናንስ አቅምን ለማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ይመክራል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ እንዲሁም በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ላይ ያከናወነቻቸው ስኬታማ ተግባራት በመሪነት እንዲታይ በማድረጋቸው፣ ጉባኤውን እንድታስተናግድ መመረጧንም አስታውሰዋል። በዚሁ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ 300 ተሳታፊዎች ይታደማሉ ። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ አደጋዎች ቢጨምሩም፣ ዓለም አቀፍ አጋርነትና ድጋፍ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። አፍሪካ ለችግሮቿ የራሷን መፍትሄ ለማበጀት በራሷ የሰው ኃይል፣ ዕውቀትና የሀብት አቅም የሚመራ ተቋም እንደሚያስፈልጋትም ገልጸዋል። በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ሥር የሚገኘው የአፍሪካ አደጋ ሥጋት አቅም ቡድን ለዚህ ተጠቃሽ ተቋም መሆኑን አብራርተዋል። በቀጣይ ቀናት የሚካሄደው አህጉራዊ ጉባኤ አፍሪካ መር የአደጋ ስጋት ምላሽ አቅምን ማጠናከር ላይ በስፋት እንደሚመክር ጠቁመዋል። የውጭ እርዳታ ጥገኝነት አስተሳሰብን መለወጥ፤ በፋይናንስ አቅም ላይ የአባል ሀገራትን መዋጮ ማሳደግ፤ ተቋማዊ ቁመናን በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አብራርተዋል። በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ እንግዶች በቆይታቸው በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች፣ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትና ሌሎች ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
በአማራ ክልል ከ20 ሺህ ለሚበልጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና እየተሰጠ ነው
Apr 6, 2026 64
ደሴ፤ መጋቢት 28/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል ከ20 ሺህ ለሚበልጡ መምህርናን እና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመምህራንና ለትምህርት አመራሮች እየተሰጠ ያለው የሙያ ፍቃድ ምዘና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል። በተጨማሪም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል፣ የመምህራንንና የትምህርት አመራሩን ብቃት ለማሳደግ እና ስነ- ምግባርን ለማሻሻልም ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። በዛሬው እለትም በክልሉ በ535 ምዘና ማዕከላት ከ20 ሺህ 400 የሚበልጡ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ መመዘኛ ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑንም አስታውቀዋል። በምዘናው ወቅት መምህራንና አመራሮቹ ላይ ያታዩትን ክፍተቶች በመለየት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥም ነው አቶ ደምስ የተናገሩት። በምዘናው የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡት ደግሞ የሙያ ፍቃድ ከማገኘት ባለፈ የደረጃ እድገት ሲኖር ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችልም ነው የጠቀሱት። በየዓመቱ ተመሳሳይ ምዘና የሚካሔድ ሲሆን በዘንድሮው ምዘና ያለተካተቱ በቀጣይ አመት እድሉ እንደሚኖር ነው ያብራሩት። ምዘናው በሁሉም አካባቢዎች በስኬት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው ለአስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል። የዘንድሮው የመማር መስተማር ሥራ በተሻለ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተማሪዎች በ12ኛ፣ 8ኛ እና 6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡም ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በክልሉ የ12ኛ ክፍል የ'ኦንላይን' ፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው
Apr 6, 2026 91
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 28/2018(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የ'ኦንላይን' ፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ ካሳሁን ገላና (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በወረቀትና በ'ኦንላይን' ሲሰጥ የነበረውን ፈተና ዘንድሮ በ'ኦንላይን' ለመፈተን መታቀዱን ገልጸዋል። በዚህም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በክልሉ ብሔራዊ ፈተናውን የሚወስዱ 180 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ'ኦንላይን' እንዲፈተኑ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል። እስካሁን ባለው ሂደትም ከ180 በላይ የፈተና ጣቢያዎች ተለይተው የተቋቋሙ ሲሆን፤ በቀሪ ወረዳዎችና ዞኖችም የፈተና ጣቢያዎችን የማደራጀት ሥራው ቀጥሏል ብለዋል። በፈተና ጣቢያዎቹ ተጨማሪ ኮምፒውተሮችን የማሟላትና የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ዝርጋታም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ተፈታኝ ተማሪዎች ከ'ሲስተሙ' ጋር እንዲላመዱ የሙከራ ፈተናዎች በ'ኦንላይን' እየተሰጣቸው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አክለዋል። ፈተናው በየወረዳው በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥም ጠቁመዋል። የ'ኦንላይን' ፈተናው ዘመናዊና ውጤታማ ከመሆኑም ባለፈ ተማሪዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ሳይርቁ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ጣቢያዎች በተረጋጋ ስሜት ለፈተና እንዲቀመጡ እንደሚረዳቸውም አመልክተዋል። በተጨማሪም የ'ኦንላይን' ፈተናው "ዲጂታል 2030" እቅድን እውን ለማድረግና የዲጂታል ትምህርትን ለማስፋፋት ትልቅ መሰረት እንደሚጥልም አመልክተዋል።
ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ወቅቱን የዋጀ ነው
Apr 5, 2026 233
አዲስ አበባ፤መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡-ሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጮች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚስማማና ወቅቱ የሚጠይቃቸው መሆናቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የትራንስፖርት አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ድረስ መሆኑ ተገልጿል። ብስክሌቶቹ በሞባይል መተግበሪያ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የጂፒኤስ ሲስተም የሚጠቀሙ መሆኑ በመርሀ ግብሩ ተመላክቷል። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የትራንስፖርት አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። "የብስክሌት መጋራት" የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወቅቱን የዋጀ ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው፤ ለሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የብስክሌት መጋራት የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፤ ሚኒስቴሩ በሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰማሩ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ያብባል አዲስ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ የሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በኮሪደር ልማቱ ከ240 ኪሎ ሜትር በላይ የብስክሌት መንገድ መሰራቱን ጠቁመው፤ መሰረተ ልማቱንም በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መጽደቁንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ስድስት የሚሆኑ የብስክሌት ኦፐሬተሮች ቅድመ ምዝገባ በማድረግ የዝግጅት ስራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዘርፉ የትራንስፖርት አገልግሎትን በጉልህ የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም አካባቢዎች ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸውም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል። የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት በተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን መገንዘብ መቻሉን ያመለከቱት የአዲስ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ሳተና ዋሬ ናቸው። ለአገልግሎቱ የሚውለው መተግበሪያም በራስ አቅም በሀገር ልጆች መልማቱን ጠቁመዋል። አገልግሎቱ የፋይዳ ቁጥር በማስገባት መጠቀም የሚቻል ሲሆን፤ ክፍያውም በዲጂታል መንገድ በሞባይል የሚፈጸም መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስፋት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በደንብ ቁጥር 183/2017 የብስክሌት መጋራት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ ማጽደቁ ይታወሳል።
ኢኮኖሚ
በክልሉ ግብርናን በማዘመን በተከናወኑ ተግባራት ምርትና ምርታማነት እያደገ መጥቷል-ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Apr 6, 2026 19
አሶሳ፤መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርናን በማዘመን በተከናወኑ ተግባራት ምርትና ምርታማነት እያደገ መምጣቱን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ። 10ኛው ክልላዊ የግብርና ልማት አጋር አካላት የግንኙነት ካውንስል ጉባኤ፣የ2017/18 የመኸር ምርት አፈጻጸም እና የ2018/19 የመኸር ምርት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እንዳሉት፥ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን እየተመዘገበ ያለው ለውጥ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ የኢኮኖሚ አቅሙን እንዲያሳድግ አድርጓል። አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየተከናወነ የሚገኘው የግብርና ሥራ ሰፋፊ ማሳዎችን በዘር ከመሸፈን ባለፈ ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉን ተናግረዋል። በክልሉ በሌማት ትሩፋት፣በአረንጓዴ አሻራ፣በሩዝ፣ በስንዴና በተፋሰስ ልማት እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል። መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ያከናወናቸው የመስኖ ግንባታዎች እና ዘርፉን የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በበኩላቸው፤ በ2017/18 የመኸር እርሻ 55 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አስታውቀዋል። በ2018/2019 የመኸር እርሻ በክልሉ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬትን በማልማት ከ70 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት ዕቅድ መያዙን ኃላፊው ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘርፉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ወዳጅነት ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት ትሰራለች
Apr 6, 2026 44
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ በኢትዮጵያ የኳታር መንግስት አምባሳደር ሰአድ ሙባረክ አል-ናይሚ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሁለቱ አመራሮች በቆይታቸው በኢንቨስትመንት መስፋፋት እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በሚሰሩ የልማት ስራዎች ዙሪያ በዝርዝር መክረዋል። በተለይም የኳታሩ ሹራ ካውንስል (Shura Council) ከብልፅግና ፓርቲ እና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚችልባቸው መንገዶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎችንና እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ለአምባሳደሩ አብራርተዋል። በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የግብርና ምርታማነት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያላቸውን ጉልህ ሚና በዝርዝር አንስተዋል። አምባሳደር ሰአድ ሙባረክ አል-ናይሚ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እየተመዘገበ ያለው ውጤት አመርቂ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም ሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገችውን የተሟላ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ተገማች፣ ግልጽና ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፈጠሩን አመልክተዋል። አምባሳደሩ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተገኝተው ባደረጉት ምልከታ የልማት ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን መታዘባቸውንም ገልጸዋል። በተጨማሪም አቶ አደም ፋራህ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለአምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል። ኢትዮጵያ ለሰፊ ኢንቨስትመንትና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያላትን ቁርጠኝነትም በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል። የኳታር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አቶ አደም ፋራህ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ወዳጅነት ይበልጥ በማሳደግ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትና ለቀጣናዊ መረጋጋት በቁርጠኝነት መስራቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ119 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ ነው
Apr 6, 2026 68
ጊምቢ፣ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ከ119 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ መሆኑን የዞኑ የኅብረት ሥራ ማህበራት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጽሕፈት ቤት የምርት ግብዓትና አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ተሰፋዬ ታሲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለ2018/19 የምርት ዘመን የመኸር እርሻ 235 ሺህ 572 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሰራ ይገኛል። እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ 119 ሺህ 731 ኩንታል ማዳበሪያ በዞኑ መድረሱን ገልጸው ከደረሰው ውስጥ 18 ሺህ 849 ኩንታል በላይ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ ጋር ደርሷል ብለዋል። ስርጭቱ በዞኑ በሚገኙ አራት ዩኒየኖችና በየደረጃው ባሉ የኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት እየተከናወነ መሆኑ ጠቁመዋል። የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በወቅቱ መከናወኑን የገለጹት ቡድን መሪው፤ የአቅርቦት ሂደቱም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ እንዲከፋፈል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የላሎ አሳቢ ወረዳ አርሶ አደር ኦላኒ ሀብታሙ፤ ለዘንድሮ የእርሻ ሥራ የሚውል ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የእርሻ ሥራቸውን በተሟላ ዝግጅት ለማከናወን እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል። የጊምቢ ወረዳ አርሶ አደር ቡልቲ ኑሩ በበኩላቸው፤ ማዳበሪያው በኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት በጊዜ መሰራጨቱ አሁን ያለውን ዝናብ በመጠቀም የመሬት ዝግጅት ሥራቸውን አስቀድመው እንዲያጠናቅቁና የተሻለ ምርት እንዲያገኙ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኢ- ተገማችና ተለዋዋጭ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ቀደም ብላ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቷን የግብርና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።
የለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው- ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
Apr 6, 2026 92
ቦንጋ፤ መጋቢት 28/2018(ኢዜአ)፦ የለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል ። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ መጋቢት 24/2010 ዓ.ም የዴሞክራሲ መሰረት የተቀመጠበትና የመደመር እሳቤ የተበሰረበት ታሪካዊ እለት መሆኑን ገልጸዋል። የለውጡ ሂደት የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም ችግሮችን ወደ አድል በመቀየር በሁሉም ዘርፎች ትልልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ተናግረዋል። በብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች በመመራት የህዝብን ተጠቃሚነት እውን ማድርግና ምርታማነትን ማሳደግ የተቻለበት መሆኑን ገልጸዋል። በከተሞችም ይሁን በገጠር የቆዩ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ በመስጠት እድገትና ማንሰራራት እውን እንዲሆን የተሰራበት ስኬታማ የለውጥ አመታት መሆኑን አንስተዋል። የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዳሻው ከበደ፤ በለውጡ ዓመታት እንደ ሀገር የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎችም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና ሌሎችንም መጀመር መቻሉ በቀጣይ ትልቅ ሀገራዊ ተስፋ የሰነቀ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይበልጥ መትጋት ይኖረብናል ብለዋል። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተክለአብ ቡሎ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች የተገኙት በህዝቡ ጠንካራ ትብብር መሆኑን አንስተው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንሰራለን ብለዋል። በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቷል
Apr 4, 2026 258
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው "የአፈር ለምነትንና ጤናማነትን ማስጠበቅ ለግብርና ሽግግር" በሚል መሪ ሃሳብ 14ኛው ዙር ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ተካሂዷል። በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አክበር ጩፎ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል። የአፈር ለምነትና ጤናማነትን መጠበቅ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድግ በመሆኑ ለግብርና ዘርፍ ምርምሮች ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን በዘርፉ የተሰማሩ ተመራማሪዎችን በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ ከ79 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ከ50 በላይ የምርምር፣ 54 የማህበረሰብ ተኮር እንዲሁም ከ14 በላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውድነህ ቶማስ(ዶ/ር) ናቸው። በዩኒቨርሲቲው ያለውን ዕውቀት ከሀብት ጋር ለማቀናጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በዚህም የዘንድሮው 14ኛው ዓመታዊ የምርምር ኮንፍረንስ የአፈር ጤንነትና ምርታማነት ላይ አተኩሮ መዘጋጀቱን ጠቁመው በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራንና ባለሙያዎች ቅንጅታቸውን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል አበክረው መስራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲው የአፈር ሳይንስ ጥናት ፕሮፌሰር ፋኑኤል ላዕከማርያም ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት በአፈር ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮች ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር የሰው፣ የአካባቢ እና የእንስሳትን ጤና ለማስጠበቅ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። በጥናታዊ ጽሁፋቸው የአፈር እርጥበትን ማስጠበቅ፣ አሲዳማነትን መቀነስ፣ ምርታማነትን መጨመርና ካርቦንን አምቆ የመያዝ አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም የተለያዩ ጥናቶች መስራታቸውን ጠቁመው ይህም መንግስት ዘርፉን ለማሻሻል የጀመረውን ውጥን የሚደግፍ በመሆኑ ወደ አርሶ አደሮች በማምጣት እንደሚተገበርም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝና የአየር ንብረጥ ለውጥ መቋቋም ፕሮግራም ዳይሬክተር አወቀ ሙሉዓለም(ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋማቸው የሀገሪቱን ግብርና ለማሻገር በጥናት የተደገፈ ስራ በመስራት የግብርናን ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ለማሳካት እየተጋ መሆኑን በመጥቀስ ለስራው ውጤታማነት ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከቤተሰብ ፍጆታ ያለፈ ትርፍ ምርት በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ገበያን በማረጋጋት በኩል አበርክቶ እንዲኖረው ትልቅ ድርሻ መወጣቱን አመልክተዋል። በመድረኩ ከ10 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ሙያዊ ውይይት ተደርጎ የፖሊሲ አቅጣጫ የማመላከት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በምርምር ስራዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት ይጠናከራል
Apr 4, 2026 421
ሰመራ፣መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ) ፡-በምርምር ስራዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ዓሊ ተናገሩ። በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀ የአደጋ ተጋላጭ ማህበረሰብ ዝግጁነትና መቋቋም ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ ተካሄዷል። በመድረኩ ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት፤ የምርምር ስራዎችን በማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይገባል። የምርምር ውጤቶቹ ማህበረሰቡን ከማንቃትና ተጋላጭ እንዳይሆኑ ከማድረግ አኳያ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል። በተለይም ተመራማሪዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የአካባቢውን ችግር ተረድተው እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተው በአካባቢው የሚገነቡ ህንፃዎች ጭምር ግምት ውስጥ ሊገቡ እንደሚገባም አመልክተዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በበኩላቸው፤ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ዝግጅት ማድረጉ የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ውሳኔ ሰጪ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ፣ ፖሊሲዎችን ማጤንና የህንፃ ግንባታ ደረጃ ግልፅ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልክተው እያከናወኑ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር ሊጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው የምርምር ግኝቶችን በየጊዜው በማውጣት ለሚመለከታቸው አካላት ማጋራት ይገባል ብለዋል። በመድረኩም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ በያዝነው ዓመት መድኃኒት የማምረት አቅሟን ከ50 በመቶ በላይ ታደርሳለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Apr 4, 2026 139
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ መድኃኒት የማምረት አቅሟን፣ በ2018 ዓ.ም ከ50 እስከ 55 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ሀገር ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት፣ አፍሪካ ለከፍተኛ አደጋ ትጋለጣለች የሚል ግምት በበለጸጉት ሀገራት በኩል የነበረ ቢሆንም፣ ያ ሳይሆን መቅረቱን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ወረርሽኙ በሽታን አስቀድሞ የመከላከል ዝግጁነት ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶ ማለፉን ተናግረዋል። በወቅቱ መንግስት በምግብ፣ በልብስ እና በመድኃኒት ዘርፎች ራስን መቻል አለብን የሚል ግልጽ አቅጣጫ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል። በዚህም በምግቡ ዘርፍ ስንዴን ጨምሮ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ በመድኃኒት በኩል ግን በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ አለመታየቱን ጠቁመዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማምረት የምትችለው መድኃኒት ስምንት በመቶ ብቻ እንደነበርም አስታውሰዋል። በቂ የመድኃኒት ምርት ማምረት አለመቻሉ፣ ሻጮች የግዢ መድኃኒት መያዛቸውና የግሉ ዘርፍ በምርት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ እምብዛም ፍላጎት አለማሳየቱ በመንግስት በኩል ትልቅ ቁጭት እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። በምግብ፣ በልብስና በመድኃኒት ራሱን ያልቻለ ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እንደሌለው ጠቅሰው፣ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማምረት የምትችለው የመድኃኒት ድርሻ ቀደም ሲል ከነበረበት ስምንት በመቶ አሁን ላይ ወደ 44 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። በቅርብ ጊዜያት የሚመረቁ ፋብሪካዎችን ታሳቢ በማድረግም በተያዘው ዓመት የማምረት አቅሙ ከ50 እስከ 55 በመቶ እንደሚደርስም አስታውቀዋል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ቢያንስ መድኃኒትና ክትባትን በራሷ አቅም እንድታመርት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በአንጋፋው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም የተመረቀው ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ከፍተኛ ወጪ የወጣበት መሆኑን ጠቁመው፣ ለማዕከሉ ለመድኃኒትና ክትባት ምርት መሠረት የሚጥሉ ዕውቀቶችን መያዙንም አመልክተዋል። በኮቪድ ወቅት የናሙና ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላክ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አዲሱ የምርምር ማዕከል እንዲህ ያሉ ምርመራዎችን እዚሁ የማከናወን አቅም እንዳለው ገልጸዋል። ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ክፍሎችን እንዲሁም የመድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ ማዕከልን ያካተተ ሲሆን፤ ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድም እንደ ዋልታ የሚያገለግል መሆኑን አመልክተዋል። ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር ረገድ ማዕከሉ በመድኃኒት ምርት ራስን ለመቻልና ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በጥረትና በትጋት ከሰራን ሀገርን ማሳደግና ማበልጸግ እንደሚቻል ይህ ማዕከል ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤት እየተገኘ ነው
Apr 4, 2026 111
ደሴ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) አስታወቁ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እና በስታርታፕ ፖሊሲ አዋጅ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሁለንተናዊ እድገትን ለማፋጠን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። ባለፉት ዓመታት ለዚህ አጋዥ የሆኑ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እቅድን በስኬት ለማጠናቀቅ ማስቻሉን አውስተዋል። በተለይም በሪፎርም ማሻሻያዎችና በተቋማት ግንባታ፣ በመሠረተ ልማትና በሰው ኃይል ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነትና በዲጂታል ክፍያ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ በጤና፣ በግብርና እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በማበረታታትና ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግ፣ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ መሪ እንድትሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። ለዚህ ውጤታማነትም ሚኒስቴሩ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ የዛሬው መድረክም የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አወል ሰይድ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ዩኒቨርሲቲው የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲውን የውስጥ አሠራር በቴክኖሎጂ ከመደገፍ ባለፈ፣ የሌሎች ተቋማትን አቅም በመገንባት የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ እንዲሳካ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሀገር እድገት መሠረት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎታል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት አገልግሎቱን ማዘመን መቻሉንና ሂደቱን በጥናትና ምርምር እያገዙ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በመድረኩ ከወሎ፣ ከመቅደላ አምባ፣ ከወልድያ፣ ከራያ እና ከሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ስፖርት
በኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ይጫወታሉ
Apr 5, 2026 362
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን በዌስትሃም ዩናይትድ ለንደን ስታዲየም ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ማንችስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን እና ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛሉ። የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሚያዚያ 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳሉ። 154 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤፍኤ ካፕ የዓለማችን አንጋፋው የእግር ኳስ ውድድር ነው።
ሊድስ ዩናይትድ ከ39 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Apr 5, 2026 219
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን በመለያ ምት አሸንፏል። ማምሻውን በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዎ ታናካ በ26ኛው ደቂቃ በጨዋታ እና ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን በ75ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ያስቆጠሯቸው ግቦች ሊድስ ዩናይትድን መሪ አድርጓል። ጨዋታው በሊድስ ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ማቴውስ ፈርናንዴዝ በ93ኛው እና አክሴል ዲሳሲ በ96ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ሆኗል። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በመጠናቀቁ 30 ደቂቃ ተጨምሯል። በጭማሪ ሰዓት አሸናፊው ባለመለየቱ ምክንያት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል። በዚሁ መሰረት ሊድስ ዩናይትድ 4 ለ 2 በማሸነፍ ከ39 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ዌስትሃም ዩናይትድ ዩናይትድ ከ35 ዓመታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ ህልሙ አልተሳካም። ጨዋታውን ተከትሎ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ተጠናቋል። ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ እና ሳውዝሃምፕተን ለግማሽ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።
ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ
Apr 5, 2026 273
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የተገናኙት ሀዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 2 አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታው የተካሄደው 10 ሠዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ነው። በዚሁ ጨዋታም ያሬድ ብሩክ እና ሽመልስ በቀለ ለሐዋሳ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። እንዲሁም ነጻነት ገ/መድኅን እና ዳዊት ገብሩ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል። ቀደም ብሎ 9 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።
ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን አሸንፏል
Apr 5, 2026 136
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል። 9 ሠዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ሁለቱም እስከ እረፍት ድረስ ያለምንም ግብ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል። ከእረፍት መልስ ዳዊት ተፈራ እና ሮሆቦት ሰላሎ ለነጌሌ አርሲ እንዲሁም ዳዋ ሁቴሳ ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ውጤቱን ተከትሎም ነጌሌ አርሲ በ41 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አዳማ ከተማ በ33 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ ከካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ የደን አያያዝ ስራዎችን እያከናወነች ነው
Apr 4, 2026 149
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ ዘላቂ የመሬትና የደን አስተዳደር ልምዶችን እያሳደገች መሆኑን የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገለጹ። ዶክተር አደፍርስ ወርቁ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የካርበን ክምችት መኖሩን በማንሳት፤ አብላጫው በደን ሀብት ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ ሀገሪቱ ከካርበን ሽያጭ የምታገኘው ገቢ እንዲጨምር የጎላ ሚና እየተጫዎተ እንዳለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ የብዝሃ ህይወት ባለቤት በመሆኗ የተሻለ የካርበን ክምችት ለመያዝ የሚያስችል ተስማሚ ሥነ-ምህዳር እንዳላት ዶክተር አደፍርስ ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአየር ንብረትና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈች መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ካርበንን ከአየር ላይ በማስወገድ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መንገድ እንዲከማች እያደረገ ነው ብለዋል። ቀደም ሲል በደን መመንጠርና ባልተገባ የመሬት አያያዝ ምክንያት ወደ ህዋ ይለቀቅ የነበረውን ሙቀት አማቂ ጋዝ መከላከል የሚያስችሉ ተግባራት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካይነት እየተተገበሩ እንዳለ አስረድተዋል። በዚህም ከካርበን ግብይት መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ ዘላቂ የመሬት እና የደን አሥተዳደር ልምዶችን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ሁለተኛው ደግሞ እጽዋት በሚተከሉበት ወቅት ቀደም ሲል ወደ ህዋ የሄደውን ካርበን አምቀው የሚመልሱበትን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ እና ከልቀት የተጠበቀውን ካርበን ገበያ ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እያከናወነች ባለችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት የካርበን ሽያጭን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑንና ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር የግዢ ውል ስምምነት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም የኖርዌይ መንግስት እንደመነሻ የ75 ሚሊዮን ዶላር የካርበን ግዢ እንዲሁም የዓለም ባንክም እንዲሁ የግዢ ውል ማሰሩን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ኖርዌይ እና የዓለም ባንክ ሊገዙት ከሚፈልጉት በላይ ካርበን ማመንጨቷን ጠቁመው፤ እስከ አንድ ቢሊየን ዶላር ሊያመጣ የሚችል ካርበን ሀብት መኖሩን ገልጸዋል። በዓለም ገበያ ላይ ለካርበን ግዢ የሚመደበውን ከፍተኛ ሀብት ወደ ኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ ማምጣት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በዓለም ላይ ያለውን የካርበን ፋይናንስ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከማጠናከር ባለፈ ሰነዶች የማደራጀትና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለዲጂታልና ታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው
Apr 3, 2026 385
አዳማ ፤መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎትን ከማስፋት ባሻገር ለዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ ቴሌኮም በአዳማ ከተማ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል በመገንባት በዛሬው እለት አገልግሎት አስጀምሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ በኢትዮጵያ የዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአዳማ ከተማ ተገንብቶ በዛሬው እለት ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከልም የዚሁ ልማት ጥረት አካል መሆኑን ጠቁመዋል። የአዳማው ማእከል በአንድ ጊዜ 12 ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የሚያደርግ አቅም እንዳለው ተናግረው በሌሎች አካባቢዎችም የማስፋት እቅድ መኖሩን ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ከፈጣንና ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ ለዲጂታልና የታዳሽ ሃይል ልማት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በዚህም መሰረት አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀ ማድረጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ፤ የስማርት አዳማ ፕሮጀክት ተቀርፆ አሰራርና አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ሂደት የኢትዮ ቴሌኮም አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በከተማዋ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ይኖራል
Apr 3, 2026 94
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጠንና ሥርጭት የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም የበልግ ዝናብ በመጠንና ስርጭት ከፍተኛ ድርሻ የሚወስድበት ወቅት መሆኑን ገልጿል። በዚህም በመጪው ሚያዚያ ወር በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከቀደሙት ሁለት የበልግ ወራት በመጠንና ሥርጭት የተሻለ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር አስታውቋል። ይህም የአየር ጠባይ ሁኔታ የበልግ አብቃይና ተጠቃሚ አካባቢዎች ለሚያከናውኑት የግብርና ሥራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል ብሏል ኢንስቲትዩቱ በመግለጫው። በተለይም በተያዘው የመጋቢት ወር የሚስተዋለው ተከታታይ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ በቡቃያና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች ምርታማነት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል። በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚጠበቀው እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለቦረና፣ ጉጂና መሰል ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ሰብል ልማት፣ ግጦሽ መሬትና የውሃ አቅርቦት ወሳኝ መሆኑንም አመላክቷል። በዚህም የበልግ አብቃይ አካባቢ አርሶና አርብቶ አደሮች ማሳቸውን በማዘጋጀት የሚጠበቀውን አመቺ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለመጠቀም ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። በበልግ ዝናብ መዋዠቅ አዝማሚያ ምክንያት ዝናብ አጠር የሆኑ አካባቢዎች የሚያጋጥማቸውን ተከታታይ ደረቃማ ሁኔታ ለመቋቋም እርጥበትን በማሳ ማቆየት የሚያስችል ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ኢንስቲትዩቱ አስውገንዝቧል። በሌላ በኩል በአንዳንድ አካባቢዎች በሚኖር ከባድ ዝናብ ሊፈጠር ከሚችል የመሬት መንሸራተት፣ የአፈር መሸርሸርና ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል።
የክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው
Apr 3, 2026 98
ባህር ዳር፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በለውጡ ዓመታት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከእለት ወደ እለት ስኬታማ እየሆነ መምጣቱ እየተመሰከረለት ነው። በመርሃ ግብሩ በብዛትና እና በአይነት መጠነ ሰፊ ችግኞች ተከላ መካሄዱን ለአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፤ ለደን ሽፋን መጨመር ብሎም የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ እያስቻለ ነው። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ መሰሉ ብርሃኑ ለኢዜአ እንዳሉት፤በለውጡ ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዘርፉን ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው። መርሃ ግብሩ ለአካባቢ ጥበቃና ለአየር ንብረት ለውጥ መሻሻል፤ ለደን ሽፋን መጨመር እና የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል። መርሃ ግብሩ ተግባራዊ መደረጉ በክልሉ 13 ነጥብ 9 በመቶ የነበረውን የደን ሽፋን ወደ 18 ነጥብ 9 በመቶ ለማስደግ እንደተቻለም ነው የተናገሩት። በነዚሁ የለውጥ አመታት በ22 ሺህ 189 ተፋሰሶች ላይ በተካሔደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርታማነት ለማሳደግ ያስቻለ መሆኑንም አብራርተዋል። የአረንጓደ ልማቱ በተለይም ለንብ ማነብ፣ ለእንስሳት እርባታና ለፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 233
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 539
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 227
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 325
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሐተታዎች
የጤና ነገር ...
Apr 3, 2026 2048
በዮሐንስ ደርበው የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። የኒውትሬሽን ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የሰው ልጅ የሰውነት ክፍል 60 በመቶው ውኃ እንደመሆኑ ለተስተካከለ ጤና ሚዛን መጠበቅ በቂ ውኃ መጠጣት ይገባል። ውኃን በትክክለኛው መጠንና ጊዜ መውሰድ ከተቻለ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን 50 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ነገር ግን ሰውነት የሚፈልገውን የውኃ መጠን በአግባቡ ካላገኘ ለዕለታዊ እና በጊዜ ሂደት ሥር ለሚሰድዱ ህመሞች የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምርም ያነሳሉ። ለመሆኑ ሰውነት የሚፈልገውና በቂ የውኃ መጠን የሚባለው መጠኑ ስንት ነው? በቂ ውኃ አለመጠጣትስ የሚያስከትለው ችግር ምንድን ነው? በሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ የኒውትሬሽን መምህር፣ ተመራማሪ እና ደራሲ ይሁኔ አየለ ምላሽ አላቸው። አንድ ሰው የሚያስፈልገው የውኃ መጠን በዕድሜ፣ ጾታ፣ በሥራ ባሕርይ፣ በመኖርያ አካባቢ፣ እንደ ጤና ሁኔታው እና እንደ ሰውነት ክብደቱ እንደሚወሰንም በምላሻቸው አስገንዝበዋል። ለምሳሌ የስኳር ታማሚዎች፣ የምታጠባ እናት፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ብዙ አድካሚና ላብ የሚያወጡ፣ በሞቃታማ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቀን 3 ሊትር ውኃ መጠጣት አለባቸው ይላሉ። በአማካይ ግን በቀን አንድ ሰው ከ2 እስከ 3 ሊትር ውኃ መጠጣት እንደሚጠበቅበት ይገልጻሉ። ጤናማ ሕይወት የሚመሠረተው ከውኃ ነው፤ ለምሳሌ ውኃማውን 60 በመቶ የሰውነት ክፍል ሚዛን ለማስጠበቅ የግድ አስፈላጊውን መጠን ውኃ መጠጣት እንደሚገባ ይመክራሉ። በሰውነት ውስጥ የሚካሄደው ሕይወታዊ ሂደት (ባዮሎጂካል ፕሮሰስ) ውኃን መሠረት ያደረገ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለምሳሌ ለተስተካከለ የሥርዓተ-ምግብ ሂደት፣ ቆሻሻን ከሰውነት አጣርቶ ለማስወጣት፣ የአጥንት መገጣጠሚያ ሥራን ለማስተካከል እና ለሌሎችም በርካታ የሰውነት ክፍሎች የተሳለጠ ተግባር ውኃ ቁልፍ መሆኑን አንስተዋል። ይህን ተከትሎም ውኃ ካሎሪ አልባው መድኃኒት (ተፈጥሯዊው መድኃኒት) እስከመባል መድረሱን ነው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያስረዱት። ሰውነት የሚያስፈልገውን ያህል ውኃ አለመጠጣት ግን ድካም ያስከትላል፤ ለማየት፣ ለመንቀሳቀስ፣ ለመሥራት፣ ለማሰብ፣ ለመረጋጋት . . . አያስችልምና ሲሉ ያብራራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ ሰው ውኃ የመጠማት መጠኑ ከአራት በመቶ በላይ ከሆነ ለሞት ሊጋለጥ እንደሚችልም ጠቅሰዋል። ውኃ አለመጠጣት፤ የጨጓራ ህመምን በማባባስ ማስገሳት፣ የቆዳ ድርቀትና ግርጣት፣ የኩላሊት ህመም ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ያደርጋል ነው ያሉት። ከምግብ በፊት 30 ደቂቃ ቀድሞ ውኃ መጠጣት ውፍረትን ለመቀነስ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። በቂ ውኃ ከመጠጣት በተጨማሪ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ማዘውተር እንደሚመከርም ገልጸዋል። የፈላ ውኃ እና የዝናብ ውኃን በብዛት መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድና በኩላሊት ላይም ጫና እንደሚፈጥር አመላክተዋል። ለተስተካከለ ጤናማ ሕይወት የግድ ውኃ መጠጣትን ልማድ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ። #ውኃ_መጠጣት #ጤና #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency
ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች
Apr 3, 2026 2125
በዮሐንስ ደርበው የለውጡ መንግሥት ኢትዮጵያን ማሥተዳደር ከጀመረ እነሆ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ 8 ዓመት ሞላው። በእነዚህ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊ ዘርፉ በዲፕሎማሲውና በሌሎችም መስኮች የተለያዩ ስኬቶች ተከናውነዋል። በእነዚህ ጥቂት ዓመታትም ለማሳካት ቀርቶ ለማሳብ የማይደፈሩ ብዙ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። የተገኙት ስኬቶች ከጊዜያቸው የፈጠኑ ናቸው። ለዚህም ሕዝቡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በነቂስ እየወጣ አድናቆቱን ገልጿል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሰጡት የሰላ አመራርነትና ቁርጠኝነትም አክብሮቱንና ምሥጋናውን ገልጿል። የለውጡ መንግሥት አካሄድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የልማት ፕሮጀክቶችም በይበልጥ ተስፋፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆሙም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ባስተጋቧቸው መልዕክቶቻቸው አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በለውጡ መንግሥት ለማሳካት ቀርቶ ለማሰብ የማይደፈሩ ተግባራት ተከናውነዋል። ከእነዚህ ከፍተኛ ጥቅም ከተገኘባቸው የታሪክ እጥፋትን ካሠረጹ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹን ቀጥለን በወፍ በረር እንዳሥሣለን። ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ሥልጣኔ - በምርጫ ካርድ መምረጥ የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። • የኮሪደር ልማት እንደምናውቀው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነትና ልዩ ትኩረት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከሁሉም አስቀድሞ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። አሁን ላይ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የበርካታ ከተሞችን ገጽታ የቀየሩ አስደማሚ ሥራዎች ተከናውነውበታል። ይህም በገጠር ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ለዘመናት አሮጌ ገጽታዋን ይዛ ያሸለበችውን አዲስ አበባ እንደ አዲስ የፈጠራትም ይኸው ፕሮጀክት ነው። አሁን ላይ መዲናይቱ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን ለውጥ ዐይተው ዝም ማለት አልቻሉም። ከመደመማቸው አንጻር የዘወትር አጀንዳቸውም እያደረጓት ይገኛሉ። ይህንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ነው ማለታቸው ይታወሳል። ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑንንም አስረድተዋል። ከለውጡ መንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ለማሳደግም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ድርብርብ ፕሮጀክት ነው የኮሪደር ልማት። • የበጋ መስኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የለውጡ መንግሥት ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ለዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አንዱ ማሳኪያ ሥልት አድርጎ እየተጋ ይገኛል። የበጋ መስኖ ስንዴ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ ማስገባት አቁማ መላክ እንድትጀምር ያስቻለ ኢኒሼቲቭ ነው። በዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችና በሜካናይዜሽን ታግዞ በስፋት እየተሠራበትም ይገኛል። ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በምርታማነት ማደግና የሥራ ዕድል በመፍጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል። የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብም ከፍተኛ ውጤት ተገኝቶበታል። ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ላይ ባሳየችው ትጋት፤ ፍጆታዋን በራሷ ዐቅም የሸፈነችው፣ ስንዴን ከውጭ ማስገባትን ያቆመችው፤ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችው በለውጡ መንግሥት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ በመሸለም ለጥረታቸው ዕውቅና መስጠቱም ይታወሳል። • መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል አንድ ጉዳይን ለማስፈጸም እዚያም እዚህም መንከራተት የግድ ነበር። በዚህ አያበቃምና ወረፋውም ሌላ ችግር ነው። መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ባካሄዳቸው ሕዝባዊ ውይይቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉልን የሚሉ እሮሮዎች በረከቱ። መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል ሥራ ወደ ተግባር አሥገባ። በዚህም መሠረት ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ ጀመረ። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነውም አሉ። ለዚህ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ የሆነውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስጀመራቸውንም ገለጹ። እንግዲህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በመሰብሰብ በቴክኖሎጂ ታግዘው በተሳለጠ ሂደት እንዲሰጡ በማድረግ የተገልጋይን እንግልት፣ ገንዘብ እና ጊዜ መቀነስ ያስቻለ አሠራር ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት ተደርጎም ይወሰዳል። በየከተሞቹም እየተስፋፋ ነው። • አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ አይ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው በቁጭት በተለያዩ መድረኮች ያነሳሉ። ለዚህም መፍትሔ ዘይደው ተቋማትን ከማቋቋም ጀምሮ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ተግተዋል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ ለመጓዝ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቋመች። የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ በመክፈት በግብርናው፣ በጤናው እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠርም በሂደት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት ቀይሮ ወደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ሕንፃ በተዛወረበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የሚታይ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ የሮቦቶችን ሶፍትዌር ብቻ ሳይሆን ውጫዊ የአካል ክፍልን (ሃርድዌር) መሥራት ጀምሯል ብለዋል። ድሮን ማምረት ብቻ ሳይሆን የማነጋገር ዐቅም እየፈጠረ ያለ ተቋም መሆኑንም አንስተዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደር አሠራርን የሚከተል መሆኑን ጠቁመው፤ በርካታ ምርቶችን አውጥቷል ማለታቸው ይታወቃል። ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮሉሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን ሲሉ ማስገንዘባቸውም ይታወሳል። • የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው። በዚህ ሂደት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊታአውራሪነት ይጠቀሳል። በተደራጀና ተቋማዊ ሆኖ ባልተቆራረጠ አካሄድ እየተከናወነ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተተከሉ ችግኞችም በየዘርፉ ተጠቃሚነት አድጓል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል። • የሌማት ትሩፋት ከመጋቢት ሥጦታዎች አንዱ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ነው። የምርት አቅርቦትን በማስፋት ለተረጋጋ ግብይት እና ለተመጣጠነ ሥርዓተ-ምግብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይም ይገኛል። ኢኒሼቲቩ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለሀገራዊ የሥርዓተ-ምግብ መሻሻል ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ነው። የዋጋ ንረትን በማረጋጋት፣ የምርት ስብጥርን በማሳደግና በዘላቂነት በማቅረብ ረገድም የጎላ ሚና አለው። የግድ ሰፋፊ መሬት መፈለግ ሳያሻ በትንሽ ቦታ ብዙ በማምረት ፍጆታን ከመሸፈን አልፎ ኢኮኖሚን በመደጎም እና የሥራ ዕድል በመፍጠርም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። • የቱሪስት መዳረሻ ልማት ቅርሶች እንዲጠገኑ፣ አዳዲስ ሎጂዎች እንዲገነቡ፣ በመዳረሻ ስፍራዎች መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ያስቻሉ ተግባራት በለውጡ መንግሥት ተከናውነዋል፤ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ እና ስኬታማ ኢኒሼቲቭ ነው። በዚህ ሂደት ከሐሳብ አመንጭነት ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የጻፉትን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ጭምር ለቅርስ ጥገናና ለቤተ-መጻሕፍት ግንባታ እንዲውል አድርገዋል። በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት፤ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደ ተግባር አስገብተዋል። በእነዚህ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። አማራጭ የቱሪስት መዳረሻም ሆነዋል። • የተቋማት ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪል ሐሳብ በተካሄደው የዐበይት ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ኮንፈረንስ ላይ፤ የተቋማት ግንባታና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ብለዋል። በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው ሲሉም አስገንዝበዋል በወቅቱ። ዘመን የማይለውጣቸው ዘላቂ ጠንካራ ሃገራዊ ተቋማትን በመገንባት ረገድ ብዙ ርቀት መጓዝም ተችሏል። በመሆኑም የመንግሥት ተቋማት ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲሆኑ በማድረግ እና ሥርዓት በተለዋወጠ ቁጥር የማይፈርሱ ወይም የሚሻገሩ ተቋማት መገንባት ተችሏል። ይህ ትጋት ተጠናክሮም ቀጥሏል።
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3647
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 413
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 4, 2026 1078
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 20 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ መሆኗን ገልጸው፤ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፣ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ፣ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ብለዋል። ፈጣን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሠራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ ዐቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው ከፍተዋል። በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል በወቅቱ። የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከል ማከተቱን አብራርተዋል። ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። • የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የከተማችንን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል። በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋልም ነው ያሉት። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል ሲሉም ገልፀዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአፋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል። በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት፤ ለሌሎች በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሠነድ እንደሚሆን አመላክተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የጸጥታና ደኅንነት ተቋሞቻችን ችግርን ወደ ዕድል እንዲቀየሩ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጨምና ከትናንት ዕዳዎች ተላቀን፣ የዛሬ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ለነገው ትውልድ የምትመጥን ሀገር ለመገንባት በዓላማ ጽናት እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል። • ስለ መጋቢት 24 መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የመጣውን የለውጡን መንግሥት የሚደግፉ ሕዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ሰልፎች ላይም መንግሥት ባለፉት ሥምንት ዓመታት ያመጣቸውን ለውጦች እና የተገኙ ስኬቶችን የሚያወሱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) ለሰጡት ስኬታማ አመራርነት የሚያሞግሱና የሚያመሠግኑ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝባዊ ግፊትና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው ብለዋል። ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብሏል። የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች ሲልም ገልጿል። ይህን ለውጥ ዕውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፤ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም ነው ያለው። • የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ሕንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ጽሕፈት ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል ብሏል። የ1954 የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ሲልም አስገንዝቧል ጽሕፈት ቤቱ።
ባሳለፍነው ሳምንት
Mar 28, 2026 478
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • የ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን እና የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ሎጁ የዛሬ 50 እና 60 ዓመት መሠራት የነበረበት ቢሆንም፤ አሁን ስለዘገየን አንቆጭም ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ስለሠራንም አንረካም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሩጫችን ገና ብዙ እንደሆነ፣ አፋር ገና እንዳልተነካ አስበን ይህን ጅማሮ ይበልጥ በማላቅ ለማስቀጠል እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቃና ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነም ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸውን ፋይዳም አንስተዋል። • ኢትዮጵያ በማላቦው ጉባዔ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ማላቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉባዔው ከመጋቢት 18 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። • የልማት ሥራዎች ጉብኝት በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎሉና ግንባታቸው እየተፋጠኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት እና የአየር መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ሲሉም በወቅቱ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት የሀገር ሀብት ፈስሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የመገጭ ግድብ ምስክር መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይህ ሞዴል መንደር በአካባቢው ለረጅም ዓመታት የቆየውን የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ጥያቄ በተግባር መልሷል ብለዋል። በሀገራችን ከተማው ብቻ ሳይሆን ገጠሩም እኩል እየተዋበ፣ በልማት እየተገነባና በዕድገት ፍኖት ላይ በጽኑ መሠረት እየተራመደ ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ትልቁ ማሳያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። • "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ በአዲስ አበባ 4ኛው "Invest in Ethiopia 2026" የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይሆን አጋርነትን ነው፤ እርዳታን ሳይሆን ኢንቨስትመንትን ነው! ለባለ ሀብቶች ምቹ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ለችሎታ እና ለዕድል በሯን ወለል አድርጋ መክፈቷንም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን በፍጥነት ወደ ከፍታ እየገሠገሠች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ የዕድገት ጉዞ፤ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያ ለእናንተ ዝግጁ የሆነ፣ በዕድሎችና በስኬቶች የተሞላ ታላቅ የኢንቨስትመንት መሶብ አላት፤ ኑ አብረን እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል! • የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫም፤ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። በዚህም ከክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀሌ እና በአዲስ አበባ ከ22 ጊዜ በላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ ሂደቱን በክልሉ ለማካሄድ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው፤ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም አስረድተዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 193
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 876
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል የነዳጅ ብክነትን ለመቀነስ ምን ዓይነት ብልኀት መጠቀም ይመከራል? ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3808
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2578
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8366
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6854
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች
Apr 5, 2026 4262
በዮሐንስ ደርበው ✍️ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች - የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው። ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እንደመሆኗ ብዙ ናት። ይህን ሁሉም ሀገራት ስለማያገኙት ዕድለኛም ናት፤ የእኛም ስለሆነች መታደል ነው። የተለያየ የኑሮ ዘይቤ፣ ባህል እንዲሁም ሁሉንም የዐየር ፀባይ ዐቅፋለች። ደግሞም ልዩ ልዩ የተፈጥሮ አቀማመጥ በልዩነት የተቸራት። አሥረጂ ማቅረብ ቢያሻ በሀገሪቱ ከፍተኛ ከሆነው ስሜን ተራራዎች እስከ ዝቅተኛው ስፍራ ዳሎል ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ መጥቀስ ሁነኛ ምሥክር ነው። ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ✍️ የተፈጥሮ ችሮታ ለኢትዮጵያ ከብዙ ሥጦታዎቿ መካከል ብሔራዊ ፓርኮችን ብቻ ብናነሳ… የኢትዮጵያ የዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን በጀት መድቦ በቀጥታ በሥሩ 11 ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሁለት የዱር እንስሣት መጠለያዎች ያሥተዳድራል። እነሱም፡- 📌 ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ገራይሌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ሃላይደጌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም 👉 ባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ እና 👉 ሲንቂሌ የቆርኬዎች መጠለያዎች ናቸው። ብሔራዊ ፓርኮቹና የዱር እንስሣት መጠለያዎቹ የሀገሬው ሀብት ናቸውና፤ እየተንከባከቡ መጠቀም ይገባል። ✍️ መንግሥት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ከላይ የተገለጹትን ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችንም፤ ከቤት እንስሣት ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ ከልቅ ግጦሽ እንዲሁም ከሕገ-ወጥ ዐደን ለመጠበቅ መንግሥት ብዙ ገንዘብ ያወጣል። የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ዐቅርቦትንም ያሟላል። ይህም ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ይመሠክራል። በሌላ በኩል የላሊበላ አብያተክርስቲያናት፣ ሶፍዑመር ዋሻን እና የፋሲል አብያተ መንግሥትን ጨምሮ በየክልሎች የሚገኙ ቅርሶችን በመጠገንም እንዲሁ እየተጋ ነው። ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎቹ አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ማድረጉም ትኩረቱን ያሳያል። በዚህ ሂደት በየአካባቢው ፀጋዎችን ዕየለየ በርካታ መዳረሻዎችንና የጎብኝ ማረፊዎችን አልምቷል፤ እያለማም ነው። እነዚህም በኢኮኖሚው ብሎም በሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍ ያለ ሚና እያበረከቱ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት፤ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተሠሩ መዳረሻዎችን ለአብነት ብንጠቅስ፤ ‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች ናቸው። የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው። ኢትዮጵያ ዛሬ ነገንም እየሠራች ነውና፤ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጭውን ትውልድ ባገናዘበ ሁኔታ እየተሳለጡ ነው። በአፍሪካ መዲና በአንድነት እና የወዳጅነት ፓርኮች ጅማሮውን ያደረገው የዘርፉ ልማት፤ ወደ ወንጪ ኢኮቱሪዝም፣ ጎርጎራ፣ ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሸበሌ ሪዞርት፣ ሶፍዑመር ዋሻ፣ ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ የዝሆኖች ዳና ሎጂ፣ የኒዒን ሌ ፓልም ሎጂ ድረስ ወዘተ… ዘልቋል። እንደቀጠለም ነው። እነዚህም ፀጋን ለይቶ ወደ ሃብት በመቀየር ሂደት በመንግሥት ብርታት የለሙ መዳረሻዎች ናቸው። መንግሥት ነባር መዳረሻዎችን በመጠገንና በማደሥ፤ አዳዲስ መዳረሻ በመገንባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም አልሠሠተም፤ ብዙ እየሠጠ ነው። ✍️ ከቱሪዝም ዘርፍ አንጻር የሕብረተሰቡ ሚና ቱሪዝም በተፈጥሮው ከበርካታ ጉዳዮች ጋር ይተሣሠራል። በእጅጉ ሰላም ይሻል፤ የሰላም ባለቤት ደግሞ ሕዝቡ ነው። ዘርፉ የቅርሶችንና መዳረሻዎችን ልማትና እንክብካቤም ይሻል። ለዘርፉ የሚሰጥ ትኩረት ሀገርንም፤ ሕዝብንም ይጠቅማል፤ ጥቅሙ ከዕለት ጉርስ እስከ ጥሪት ይዘልቃል። በዚህ ሂደት ሕዝቡ በየአካባቢው ያሉ ብሔራዊ ፓርኮችን፣ ቅርሶችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን የኔ ብሎ መጠበቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ፡- ብሔራዊ ፓርክ ወይም በመዳረሻ ላይ ጉዳት ቢደርስ በቀጥታ ተጎጂው የአካባቢው ነዋሪ ነው። ምክንያቱም ቱሪስት ካልሄደና ገቢ ካልተገኘ ገቢ ይደርቃልና።
የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስን የታደገው ሀገራዊ ለውጥ
Apr 4, 2026 240
የስልጣኔ መነሻ የጥበብ መፍለቂያ የሆነችው የምስራቋ ፈርጥ ሀረር የንግድ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ትስስር ማዕከል ሆና በትውልድ ቅብብሎሽ ከአንድ ሺህ አመታት በላይ የተሻገረች እድሜ ጠገብ ከተማ ነች። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርትና የንግድ ማዕከል የነበረችው ከተማዋ በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ እንዲሁም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶችን የያዘች ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ነች። ከእነዚህ ቅርሶች መካከል ጥንታዊ የስነ-ህንፃ የጥበብ፣ የከተማ ፕላን፣ ባህላዊ የመሬት አጠቃቀም፤ አካባቢያዊ መስተጋብርና የስልጠኔ መገለጫ በሚል እኤአ በ2006 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በአለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ቅርስ ይጠቀሳል፡፡ ቅርሱ ምንም እንኳን በኪነ ህንፃ ጥበብ በላቁ በአርቆ አሳቢ አባቶች እንዳይፈርስና ሚዛኑን ጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ በተመረጠ ድንጋይ እና አፈር በልዩ ጥበብ የተገነባ ቢሆንም በጥበቃና እንክብካቤ ጉድለት ምክንያት ከግማሽ ምዕተ አመታት በላይ እድሜን ባስቆጠረው ቅርስ ላይ አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል። በቅርሱ ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍሎች የህገ-ወጥ ግንባታዎች መበራከትና በሌሎች ምክንያቶች በደረሰበት ጉዳት የጥንት ስልጣኔ ምልክት የሆነው አለም አቀፉ የጀጎል ቅርስ ከዩኔስኮ የአለም ቅርስነት እስከመሰረዝ የደረሰ አደጋ ተደቅኖበት ነበር። ሆኖም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአዲስ እሳቤ፤ በተደመረ አቅምና በላቀ ቁርጠኝነት፤ ህዝብን በማሳተፍ ከመንግስት ምንም አይነት በጀት ሳይመደብለት ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማልማት ተቻለ። አሁን ላይ እነኛ በሸራና በጨርቅ በተሰሩ ህገወጥ ግንባታዎች ተወሮ የነበረው 3ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጀጎል ግንብ ዙሪያ በአበቦችና ቅርሱን በሚያስውቡ ስራዎች ደምቀዋል። በዚህም አባቶች ከዘመኑ ቀድመው ዛሬም ድረስ ግርምትን በሚያጭር ጥበብ አንፀው ያኖሩት ይህንን የሀገር ሀብት በመታደግ ትውልዱን ከታሪክ ተወቃሽነት ወደ ዳግም ታሪክ ሰሪነት እንዲሸጋገር ማድረግ ተችሏል። ስራውም የትላንትን መሰረት ሳያናጋ፤ የቀድሞ አባቶችን ጥበብና ስልጣኔ ሳይጋፋና ሳይዘነጋ ጥንታዊውን ከዘመናዊ ጋር አዋህዶ ቅርስ መገኛ ለሆኑ ሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት በሚሆን ደረጃ አስደናቂ ስራ ተከናወነ። የአካባቢውን ሀብትና እውቀት በመጠቀም እውን የተደረገው ይህ ስራ በእያንዳንዱ የሀረሪ ጥንታዊ ቤቶች በሚገኙ የታሪክ አሻራዎችና የባህል መገለጫዎች እንዲደምቅም ሆኗል። ይህ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ቅርሱን ከአደጋ ከመታደግ ባለፈ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከግለሰብ እስከ ማህበራትና የዳያስፖራ አባላት ድረስ ሁሉም በያገባኛል ስሜት አሻራውን ያኖረበት ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት ነው። ይህም በቅርሱ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲጎለብት በማድረግ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ያስቻለና ቀደም ሲል የነበሩ የግለኝነት አስተሳሰቦችን በመቅረፍ የወል እሳቤ እውን የሆነበት ፕሮጀክት ሆኖ ታይቷል። ዛሬ ላይ እነኛ የቆሻሻ መጣያ የነበሩ እና በአካባቢው ለማለፍ ከባድ የነበሩ የጀጎል መንገዶች ፀድተው ውብ ሆነዋል። ይዘታቸውን ለቀው የነበሩ ቅርሶችም የአለም ቅርስነት ክብርና መስፈርትን በሚመጥን ደረጃ ታድሰዋል። ዛሬ የጀጎል ነዋሪ እንደቀድሞ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ሳይሆን መኖርን የሚመርጥባት የወጣውም መመለስን የሚመኝባት ምቹ አካባቢ ሆናለች። የመቻል ምልክት የትብብር ውጤትና የአብሮነት ጉልበት በተግባር የታየበት የጁገል መልሶ ልማት ጥንታውን መንደር ለነዋሪዎች ምቹ ለጎብኚዎች ተመራጭ የጉብኝት ስፍራ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል። በለውጡ መንግስት በአዲስ መልክና ቀለም የተዋበው ጀጎል የሀረርን ቀደምት ስልጣኔ እየመሰከረ የሀገርንም ገፅታ እየገነባ ይገኛል።