ቀጥታ፡

የጋምቤላ ክልልን ሰላም በማጽናት የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት የማሳደግ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ክልልን ሰላም በማጽናት የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ ገለጹ።

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ዘመን፣ 5ኛ የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር በመፍታት፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የተጀመሩ የልማት እቅዶችን ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን በማውጣት በአግባቡ እንዲተገበሩ ከማድረግ ባለፈ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት መፈጸማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤታ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀና በሚካሔደው ጉባኤ የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር፣ የኦዲትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕቅድ ክንውን አድምጦ ውይይት ያደርጋል።

በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ፣ በማስፈጸሚያ በጀት፣ በተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ከመርሐ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም