ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Mar 10, 2026 28
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በክልሉ የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው የግብርና ሚኒስቴር "በሴቶች ላይ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ ለሀገር ብልጽግና መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ኹነቶች አክብሯል።   በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ የጀርባ አጥንት በሆነው ግብርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የሀገርን ምርታማነት ከማሳደግ አኳያ የሴቶች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ግብርና እና የሴቶች ተሳትፎ የማይነጣጠሉ በመሆናቸው በዘርፉ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።   ሴቶችን በቴክኖሎጂ እና በፋይናንስ ተደራሽ ማድረግ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው መስራት፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ስራዎችን በትኩረት ማከናወን ሚኒስቴሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አብራርተዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ኸይረዲን በበኩላቸው፣ መንግስት ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራትም የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ገነት አብደላ፤ ሴቶች ለሀገር እድገትና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡   ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሴቶችን ማብቃትና መደገፍ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡ በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ የተገነባው የህጻናት ማቆያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ሴት አምራቾች ምርቶቻቸውን ለገበያ ያቀረቡበት ልዩ ኤግዚቢሽንም ተከናውኗል።
ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል
Mar 10, 2026 37
ደብረ ብርሃን፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ምርጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ በተግባር የሚረጋገጥበት ነው በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ። ይህንኑ ተከትሎ ኢዜአ በደብረ ብርሀን ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ ፍርዴ ወርቄ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።   በዚህም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን ምርጫ ክልል 02 ምርጫ ጣቢያ “ሀ"-1 ለመራጭነት ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በምርጫ የሚመሰረት መንግስት ሰላምና ልማትን ያረጋግጣል ብዬ ስለማምን በዘንድሮው ምርጫ ለመሳተፍ ተመዝግቤ ካርድ ወስጃለሁ ያሉት ደግሞ ሌላው የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አቶ ጌታቸው በቀለ ናቸው። ምዝገባው በዲጂታል ጭምር ታግዞ መካሄዱ ሂደቱን እንዳቀለለው ጠቁመው የወሰዱትን ካርድ ተጠቅመው በምርጫው ቀን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።   ለሀገር ልማትና ሰላም ግንባታ ይበጃል ያልኩትን የፖለቲካ ፓርቲ ለይቼ ለመምረጥ የሚያስችለኝን የመራጭነት ካርድ በመውሰዴ ተደስቻለሁ ያሉት ደግሞ ወይዘሮ አዲስ መላኩ ናቸው። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአካባቢያቸው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሆስፒታሎች የሚውል ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመድኃኒትና ሕክምና ግብዓቶች አበረከተ
Mar 10, 2026 37
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለአምስት የመንግስት ሆስፒታሎች የሚውል ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ አበርክቷል። በጾም ወቅት የተቸገሩትን በመርዳትና በጎ ሥራን በማከናወን የሚታየው መደጋገፍ ሊጠናከር ይገባል-የሃይማኖት አባቶች በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አማካኝነት የተበረከተው ድጋፍ በዑስታዝ አቡበከር አህመድ አስተባባሪነት ከሙስሊም ኤይድ አሜሪካ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በድጋፍ ርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።   ድጋፎቹም ለአቦምሳ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ጭናክሰን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚውሉ ናቸው። በዚሁ ወቅት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንደገለጹት፤ ምክር ቤቱ ኃይማኖታዊ ግዴታን በመወጣት በዜጎች ማህበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በንቃት እየተሳተፈ ነው።   ለአምስቱ ሆስፒታሎች የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍም የረመዳን ወር የመተሳሰብና የመደጋገፍ መሆኑን በተግባር እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ ለሆስፒታሎቹ የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ ለጤና ተቋማት ተጨማሪ አቅም መሆኑን በመግለጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ህብረተሰቡ በልማት ስራዎች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት መነቃቃት ፈጥሯል
Mar 10, 2026 42
ሐረር፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀረሪ ክልል ጉብኝት በክልሉ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እየሰጡት ያለው ጥቅም በተግባር የተረጋገጠበት እና ህብረተሰቡ ለልማቱ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት መነቃቃት የሚፈጥር ነው ሲሉ የሐረር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ትናንት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሐረር ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፤ ጉብኝቱ የልማት ሥራዎች በተግባር ለዜጎች እየሰጡት ያለውን ጠቀሜታ የተመለከቱበትና በቀጣይ ለላቀ ሥራ የሚያዘጋጅ ነው ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል መምህር ደረጀ ተስፋዬ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የፕሮጀክቶችን ክንውን እንዲሁም ለህዝብ እየሰጡት ያለውን አገልግሎት የገመገመ ስለመሆኑ አንስተዋል።   በቀጣይም የልማት ሥራዎች በተሻለ ፍጥነት እንዲከናወኑና ህብረተሰቡም የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት ምቹ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማና የገጠሩን ገጽታ እየቀየረው መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም የክልሉን እድገት ለማፋጠን በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ የሐረር ከተማን ውብና ጽዱ ከማድረግ ባለፈ ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች ምቹ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ አቶ ደመቀ ካሳዬ ናቸው።   በክልሉ በልማት ሥራዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ደስታ እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት መነቃቃት በመፍጠር ይህን ተግባር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ጉብኝት ለአካባቢው ተስፋን የሰነቀና ልማት እንዲጠናከር መነቃቃትን የፈጠረ ነው ያለችው ደግሞ ወጣት ሄለን ሲራጅ ናት።   "በተለይ የኮሪደር ልማት ለወጣቶች የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ያሰፋና ተጠቃሚነትን እያጎለበተ ነው" ያለችው ወጣቷ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረር የልማት ሥራዎችን በመጎብኘታቸው ምስጋና አቅርባለች። በክልሉ ሶፊ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ማወርዲ ሙህየዲን በበኩሏ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አካባቢያችን መጥተው መጎብኘታቸው ለገጠሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያል፤ በዚህም ተደስቻለሁ" ብላለች።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በየአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለወጣቶች ተስፋን መሰነቁን ተናግራለች።
በክልሉ የግብርና አቅምን በመለየት የተከናወኑ የአሰራር ማሻሻያዎች ውጤት አምጥተዋል
Mar 10, 2026 39
ዲላ ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና አቅምን በጥናት በመለየት የተከናወኑ የአሰራር ማሻሻያዎች እና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ትግበራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በክልሉ የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት "በምርምር የታገዘ ግብርና፣ የበለፀገ ማኅበረሰብ፣ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው አውደ ጥናት በዲላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።   በአውደ ጥናቱ በሰብል፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የተሰሩ 1 ሺህ 107 የምርምር ሥራዎች ቀርበው የሚገመገሙ መሆኑ ተመላክቷል። በወቅቱም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በክልሉ የግብርና ሽግግርን ለማፋጠን ጥናትና ምርምርን መሠረት ያደረጉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በተለይም የክልሉን የግብርና አቅም በመለየት የተከናወኑ የአሠራር ማሻሻያዎችና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ትግበራዎች ውጤት ማምጣታቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም በክልሉ በሩዝ ልማት የተመዘገበውን ውጤት ለአብነት በመጥቀስ፣ መሰል ውጤታማ የምርምር ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፍቃዱ ግርማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የግብርና ምርምርን ከሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች ጋር በማጣጣም በተከናወኑ ተግባራት ስኬት መገኘቱን ገልጸዋል።   በተለይም በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች ግብርናውን ለማሻገር የሚያስችሉ ተጨማሪ አቅሞችን መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል። ግብርናው ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አጋዥ ኃይል ሆኖ በመውጣት ሽግግሩን እንዲመራም እየተከናወኑ ያሉ የምርምር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዞኑ በቡናና በእንሰት ልማት ላይ የታየው ለውጥ በሰብሎቹ ላይ የተካሄዱ የምርምር ሥራዎች ውጤታማ በመሆናቸው የመጣ ነው ብለዋል።   በተለይም በቡና ልማት ረገድ በምርምር ግኝቶች ላይ ተመስርተው የወጡ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ በሄክታር በአማካይ 5 ኩንታል የነበረውን የቡና ምርት ወደ 11 ኩንታል ማሳደጉን አስረድተዋል። ይሁን እንጂ የአፈር አሲዳማነት ዛሬም የዞኑ የግብርና ልማት ማነቆ መሆኑን በመጥቀስ፣ በዚህ ረገድ የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአውደ ጥናቱ ዓላማ የተቀናጁ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት የተሻለ የግብርና ልማትን ማረጋገጥ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዮት መብራቴ (ዶ/ር) ናቸው።   ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ የግብርና ምርታማነትን እያገዘ መሆኑን ገልጸው፤ በተያዘው ዓመት በ470 ሄክታር የአርሶ አደር ማሳ ላይ ሰርቶ በማሳየት የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦትን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል።
የሚታይ

የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል 
Mar 10, 2026 62
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር የህክምና ግብዓቶችንና መሳሪያዎችን መደገፍ የሚያስችል የሶስት ዓመት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። በሸገር ከተማ የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት በተከናወኑ ተግባራት ውጤት እየተገኘ ነው በስምምነቱ መሰረት ከአጋር አካላት ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚቆይ የ282 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የህክምና ግብዓት ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ይህ ድጋፍ የእናቶች፣ የህፃናት እና የቤተሰብ ምጣኔ ግብዓት አቅርቦት ማሳደግ የሚያስችል ሲሆን የሕክምናውን ዘርፍ ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎችን የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡   የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለፉት ጊዜያት በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋትም አመርቂ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በመንግስት በጤና ተቋማት ለእናቶች የሚሰጠው የቅድመ ወሊድ እና የድህረ ወሊድ ነፃ የህክምና አገልግሎት ለዚህ እመርታ ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረው ለመንግስት ቁርጠኝነት መሳካት የማህበረሰቡ እና የአጋር አካላት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ሚኒስትሯ አክለዋል።   በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ክርስቲን ፐረን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ወሳኝ አጋር ሀገር መሆኗን ጠቁመው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የጤና ትብብር እየጠነከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ ያስመዘገበችውን ውጤት ለማበረታታት የታለመ መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች የአጋር ድርጅት ተወካዮችም በመንግስት በኩል የጤናውን ዘርፍ ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራ ይጠናከራል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Mar 10, 2026 59
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ዓመታት የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠል ከግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን "በተቀናጀና ቀጣይነት ባለው የድጋፍ ማዕቀፍ አምራቿንና ምርታማዋን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንፈጥራለን" በሚል መሪ ሃሳብ ክልል አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም በወላይታ ሶዶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።   በፎረሙ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሩ በኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመቅረፍ አልሚ ባለሃብቶችን ማበረታታትና መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠል ከግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ጋር በቅንጅት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ክልሉ ያለውን ዕምቅ የኢንቨስትመንት አቅም በመጠቀም የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የግሉ ባለሀብት ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ባሉን አቅሞችና ዕድሎች ዙሪያ በመወያየት ክልሉ ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንዲችል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል።   የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አፀደ አይዛ በበኩላቸው በክልሉ 82 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 1ሺህ 826 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተው በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል። ክልሉ ከተመሰረተ በኃላ ከ49 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 536 የኢቨስትመንት ፕሮጀክቶች በኢንቨስትመንት ቦርድ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ አገልግሎት መስፋፋት ጉልህ ሚና እያበረከቱ መሆኑን ገልጸው በክልሉ ያለውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ማልማት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ተገቢው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ስትራቴጂካዊ አቅም ይፈጥራል
Mar 10, 2026 130
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ስትራቴጂካዊ አቅም እንደሚፈጥር በመከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮንን ገለጹ። ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሰራዊት ማህበር ቀይ ባሕርና የባሕር በር ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መብት በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት እያካሄደ ነው። በመከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መመሪያ ሃላፊ ጄኔራል ይመር መኮንን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ከአክሱም ስልጣኔ ጀምሮ አዱሊስና ዛይላ የኢትዮጵያ የንግድና የባህል በር ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበር ታሪክ የሚያስረዳው ሀቅ ነው።   ይህ ታሪካዊ ሀቅ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ያላት ጥያቄ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ፍላጎት ሳይሆን ከሉዓላዊነትና ከብሔራዊ ህልውናዋ ጋር የተጋመደ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ከባሕር በር እንድትገለል መደረጉ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማነቆ መሆኑን ገልጸው የባህር በር ጥያቄው ምላሽ ማግኘት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብሎም ለቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ በአካባቢው የሚታዩ የፀጥታ ስጋቶችን በጋራ መከላከል የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅም የሚፈር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የጋራ ተጠቃሚነትንና ቀጣናዊ ውህደትን መሰረት ያደረገ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡   የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የጋራ ተጠቃሚነት ትብብር፡ በቀጣናው ሰላምና የመሰረተ ልማት ትስስርን በማጠናከር የምስራቅ አፍሪካን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ የነቃ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ጠቁመው ለዚህም የማህበሩ አባላት ጠንካራ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።   የብሔራዊ የኢትዮጵያ ሰራዊት ማህበር ፕሬዝዳንት ሀምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ በበኩላቸው፤ የማህበሩ አባላት በሀገር ጉዳይ ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የባሕር በር ጥያቄም በሰለማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ ማህበሩ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደሚወጣም አረጋግጠዋል።
ምርጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ በተግባር የሚረጋገጥበት ነው
Mar 10, 2026 177
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የመንግሥት የስልጣን ምንጭ ህዝብ መሆኑን በተግባር የሚረጋገጥበት መሆኑን ምሁራን ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመከናወን ላይ ነው። መራጮችም በዲጂታል "ምርጫዬ" መተግበሪያና በየምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ድምፅ መስጠት የሚያስቻለቸውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የምርጫ ምልክትና የርዕዮተ ዓለማቸውን በማስተዋወቅ ላይ ናቸው። የሕግና የምጣኔ ሃብት ምሁራን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን በማጠናከር ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን የሚጠቀሙበት መድረክ ነው።   የሕግ መምህርና ተመራማሪ ማናየ ዘገየ(ዶ/ር)፤ ምርጫ የመንግሥት የስልጣን ምንጭ ህዝብ መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ የጋራ መድረክ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ ውስንነቶች ቢስተዋልባቸውም መራጩ ዜጋ የሚሰጠው ድምፅ የመንግሥት ስልጣን ህዝብ መሆኑን በተግባር ሲታይ መቆየቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያንም ዘንድሮ በሚከናወነው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀኛል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ በመስጠት ለስኬታማ የስልጣን ሽግግር ውጤታማነት ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ገልጸዋል። በምርጫ ሂደቱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መራጩ ህዝብ ለምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሕዊነት ገንቢ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚኖርባቸውም አስገንዝበዋል።   ሌላኛው የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ገመቺስ መርሻ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምርጫ የምቹ ፖለቲካ ምኅዳርን በማስፋት ለዴሞክራሲ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። የፖለቲካ ምኅዳርን በማስፋት ዜጎች በምርጫ ሂደት ሕገ-መንግስታዊ የመምረጥና መመረጥ መብታቸውን የሚያንጸባርቁበትን ሁኔታ ለመፍጠርም የምርጫ ተዋናዮች ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የህዝብን አንድነትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስቀደም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስጠበቅ በኃላፊነት መንፈስ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ምርጫ የዴሞክራሲ ባህል መገንቢያ ቁልፍ መሳሪያ ነው ያሉት ምሁራኑ፤ ነፃ፣ ገለልተኛና ፍትሕዊ ምርጫን ማስፈጸም ሲቻል የህዝብና መንግሥትን ጤናማ መስተጋብር ለመፍጠር መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል
Mar 10, 2026 37
ደብረ ብርሃን፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ምርጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ በተግባር የሚረጋገጥበት ነው በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ። ይህንኑ ተከትሎ ኢዜአ በደብረ ብርሀን ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ ፍርዴ ወርቄ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።   በዚህም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን ምርጫ ክልል 02 ምርጫ ጣቢያ “ሀ"-1 ለመራጭነት ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በምርጫ የሚመሰረት መንግስት ሰላምና ልማትን ያረጋግጣል ብዬ ስለማምን በዘንድሮው ምርጫ ለመሳተፍ ተመዝግቤ ካርድ ወስጃለሁ ያሉት ደግሞ ሌላው የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አቶ ጌታቸው በቀለ ናቸው። ምዝገባው በዲጂታል ጭምር ታግዞ መካሄዱ ሂደቱን እንዳቀለለው ጠቁመው የወሰዱትን ካርድ ተጠቅመው በምርጫው ቀን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።   ለሀገር ልማትና ሰላም ግንባታ ይበጃል ያልኩትን የፖለቲካ ፓርቲ ለይቼ ለመምረጥ የሚያስችለኝን የመራጭነት ካርድ በመውሰዴ ተደስቻለሁ ያሉት ደግሞ ወይዘሮ አዲስ መላኩ ናቸው። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአካባቢያቸው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ገዢ ትርክትን በማስረፅ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በማፍራት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የድርሻችንን እንወጣለን- መምህራን
Mar 10, 2026 55
ደሴ ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ ገዢ ትርክትን በማስረፅ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በማፍራት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ በደሴ ከተማ የሚገኙ መምህራን ገለጹ። ትውልዱ በሀገር ሰላምና ልማት ውስጥ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር የድርሻችንን እንወጣለን- የሀይማኖት አባቶች የደሴ ከተማ አስተዳደር "ለሰላም ዘብ እንቆማለን፣ የልማት አርበኛም እንሆናለን" በሚል መሪ ሀሳብ ከመምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄዷል።   የውይይቱ ተሳታፊ መምህር ተስፋዬ ከበደ ፤ ሰላም ለሁሉም አስፈላጊ በመሆኑ ከመማር ማስተማር ሥራቸው በተጓዳኝ ለከተማው ዘላቂ ሰላምና ልማት የበኩላችንን ድርሻ እየተወጣን ነው ብለዋል።   መምህራን ለሀገር ተረካቢው ትውልድ ገዢ ትርክትን በማስረፅ ፣ ሰላምና ልማትን ከማረጋገጥ ባሻገር በተለይ እንደ ሀገር የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። መንግስት በአሁኑ ወቅት ሰላምን ለማምጣት የሰጠውን ሰፊ እድል ያደነቁት መምህሩ ትውልዱ የሰላም ኃይል በመሆን ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መጠናከር እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፍም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት። ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ መምህር ወንድምነህ ይልማ፤ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ከማነጽ ባሻገር ለከተማዋ ሰላምና ልማት የድርሻቸውን ለመወጣት በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑን ይገልፃሉ።   በተለይ አሰባሳቢ ትርክት ላይ በመመስረት የተማሪዎችንና የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስር እንዲሰድ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ''አንድነታችንን ጠብቀን ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የድርሻችንን እንወጣለን" ያሉት ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊ መምህርት አልማዝ አለባቸው ናቸው።   ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢያችንን ሰላም ተደራጅተን በመጠበቅ በከተማዋ የሰፈነውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የምናደርገውን አስተዋጽኦ እናጠናክራለን ብለዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በመድረኩ እንደገለፁት፣ ከማሕበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰላምን ዘላቂ ለማድረግና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል እየተሰራ ነው። መምህራንም ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለመፍጠር ከሚያደርጉት ጥረት ባሻገር ለከተማው ሰላምና ልማት የድርሻቸውን ማበርከት መቻላቸው የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።   በቀጣይም የጋራ ትርክትን በመገንባት፣ ለአንድነት፣ ለሰላምና ለልማት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩም የክልል፣ የከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በክልሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው
Mar 9, 2026 125
ባህር ዳር፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በመራጭነት፣ በተመራጭነትና በታዛቢነት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርዳችንን ወስደናል - የምርጫ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የክልሉ ሴቶች በምርጫው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑና የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ የማንቃት ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን የሚያስከብርና ፍላጎታቸውን የሚያሟላ የፖለቲካ ፓርቲን ለይተው እንዲመርጡ ለማስቻል ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።   በተመራጭነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግም ውጤታማና ሞዴል የሆኑ ሴቶች በፈለጉት ፓርቲ ተመልምለው እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም አመልክተዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ በቢሮው በኩል ይህንኑ ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ የንቅናቄ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ዕድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱ ሁሉም ሴቶች የምርጫ ካርዳቸውን በመውሰድ የሚፈልጉትን በመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ አስገንዝበዋል።
አብን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Mar 9, 2026 131
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ለስኬታማነቱ በቅንጅት እየተሠራ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። በምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጣችው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውንና ማኒፌስቶዎቻቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዕጩዎቻቸውን በማስመዝገብ የምርጫ ክርክር እያካሄዱ ነው። በተጨማሪም ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ ሂደት በይፋ ተጀምሯል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ አብን ካለፈባቸው በርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ወጥቶ አሁን ላይ ራሱን ለውድድር እያዘጋጀ ይገኛል። አብን በምርጫው ለመሳተፍ የሚያደርገው ጥረት በአማራ ክልል ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎች ጭምር ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በመሆኑም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ደጋፊዎቹን በማስተባበርና ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጠናከር በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ ለመሆን በትኩረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ምርጫው ስኬታማና ተዓማኒ እንዲሆን መንግሥት፣ ሕዝቡና የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራና በቅንጅት በመስራት የሚጠበቅባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም መንግሥት ሁሉም ፓርቲዎች በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹና አስተማማኝ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠሩን እንዲያጠናክር አንስተዋል። መገናኛ ብዙኃንም ለሁሉም ተፎካካሪ ኃይሎች እኩልና ፍትሐዊ የሆኑ የብሮድካስት መድረኮችን በማመቻቸት የድርሻቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች ኢትዮጵያ ወደ ላቀ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንድትሸጋገር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖራቸውም ሊቀመንበሩ አብራርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የሐሳብ ልዕልናን በማስቀደም ተጨባጭና ለሀገር የሚጠቅሙ አማራጭ ዕቅዶቻቸውን ለመራጩ ሕዝብ ማቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ፓርቲያቸው አሁን ላይ የተፈጠሩትን የፖለቲካ ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም፣ ሂደቱ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ድርጅታዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችለንን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል-ነዋሪዎች
Mar 8, 2026 170
ነጌሌ ቦረና ፤የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ድምጻቸውን ለመስጠት ከወዲሁ መዘጋጀታቸውን በምስራቅ ቦረና ዞን የነጌሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባሰቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከትናንት የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ መጀመሩ ይታወሳል። በዚሁ መርሃ ግብር መሰረት ኢዜአ በነጌሌ ቦረና ከተማ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ካርድ ሲወስዱ ያገኛቸውን ነዋሪዎች አነጋግሯል። ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ጉራቻ ጃተኒ በሰጡት አስተያየት በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ከወዲሁ ተዘጋጅተዋል። ለዚህም የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ጠቅሰው ድምጻቸውንም ለሀገር ልማትና እድገት ይሰራል ብለው ላመኑበት ፓርቲ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የጎቢቻ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ቱራ ሊበን በበኩላቸው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ የዜግነትና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ለመጠቀም የመራጭነት ካርድ እንደወሰዱ ተናግረዋል። ምርጫ የሀገረ መንግሥት ግንባታን ለማጽናት ወሳኝ በመሆኑ እዚህ ላይ አተኩሮ ለሚሰራ ፓርቲ ድምጼን እሰጣለሁ ብለዋል። ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአከባቢያቸውን ሠላም ነቅተው በመጠበቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አስታውቀዋል። ሌላኛው የመራጭነት ካርድ መውሰዱን የሚናገረው የከተማው ነዋሪ ወጣት ማሙሽ ፈይሳ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የሚተላለፈውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር በአግባቡ በመከታተል ለሚደግፈው ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል። ክርክሩ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድና በምርጫው ለመሳተፍና ድምጽ ለመስጠት እንዳነሳሳውም አክሏል። የነገሌ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ አባይነህ ወርቁ በዞኑና በነጌሌ ቦረና ከተማ በሚገኙ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። የመራጮች የምዝገባ ሂደቱንም 167 የምርጫ አስተባባሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን 668 ምርጫ አስፈጻሚዎችም ምዝገባውን እያስፈጸሙ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።።      
ብሔራዊ ጥቅምን ለታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ አካል ሊሆኑ አይገባም - በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Mar 8, 2026 185
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ ብሔራዊ ጥቅምን ለታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ አውድ ውስጥ ባለድርሻ አካል ሊሆኑ እንደማይገባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች፣ በቀይ ባህርና የባህር በር ጥያቄ፣ ምርጫ 2018 በተመለከተና በሌሎች ጉዳዮች ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ቀይ ባህር ያለ ኢትዮጵያ ህዝብ ፈቃድና ይሁንታ በፖለቲካ ሴራ ያጣነው የተፈጥሮ ሃብታችን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ተፈጥሯዊ፣ ህጋዊ እና መልክዓምድራዊ መብቷን መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ይህንን ታሪካዊ ሀብት ማጣት በአሁኑ ትውልድ ዘንድ ከፍተኛ የቁጭት ስሜት ፈጥሯል። መንግስት ይህንን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስና ኢትዮጵያ ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስከበር የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ስልቶችን በመከተል ረጅም ርቀት ተጉዟል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ለኢትዮጵያ የዓባይ ውሃና ቀይ ባህር ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቿ ናቸው። ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት በሌለው አግባብ በሴራ እንድታጣው መደረጉን አንስተው፤ ይህ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመ ታላቅ በደል ነው ብለዋል። ከዚህ አኳያ መንግስት የባህር በር ጥያቄን ሀገራዊ አጀንዳ አድርጎ ማምጣቱን አብን በአዎንታ የሚቀበለውና የሚደግፈው አካሄድ መሆኑንም ገልጸዋል። በወቅቱ በድፍረት የተወሰነ የፖለቲካ ውሳኔ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመ ታሪካዊ በደልና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ ታሪካዊ ስህተት እንደሆነም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በታሪክና በተፈጥሮ ያላትን የባህር በር የማግኘት መብት ዳግም የሚያረጋግጥላት ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ አብንም ይህንን ፍትሃዊ ጥያቄ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ስለሆነም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለታሪካዊ ጠላቶች አሳልፈው ለመስጠት የሚሰሩ የፖለቲካ ኃይሎች በፖለቲካው አውድ ውስጥ ባለድርሻ አካል መሆን እንደሌለባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃ ለኤሌትሪክ ሃይል ማመንጫነት በመገደብ ተጠቃሚነቷን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ማረጋገጧን አንስተው፤ የባህር በር ጥያቄ ላይም በጋራ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያ የልማት ጥረቶቿ እንዲደናቀፉ ሌት ተቀን እንደሚሰሩ ያመለከቱት ሊቀ መንበሩ፤ ኢትዮጵያውያን ግን የጋራ ጠላቶቻቸውን ሴራ በፅናት የመከቱበት ፕሮጀክት ነው ብለዋል። አሁን ላይ ከእነዚህ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች በላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሌላ ምንም ዓይነት አጀንዳ እንደሌለ አረጋግጠዋል።

ማህበራዊ
በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Mar 10, 2026 28
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በክልሉ የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው የግብርና ሚኒስቴር "በሴቶች ላይ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ ለሀገር ብልጽግና መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ኹነቶች አክብሯል።   በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ የጀርባ አጥንት በሆነው ግብርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የሀገርን ምርታማነት ከማሳደግ አኳያ የሴቶች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ግብርና እና የሴቶች ተሳትፎ የማይነጣጠሉ በመሆናቸው በዘርፉ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።   ሴቶችን በቴክኖሎጂ እና በፋይናንስ ተደራሽ ማድረግ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው መስራት፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ስራዎችን በትኩረት ማከናወን ሚኒስቴሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አብራርተዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ኸይረዲን በበኩላቸው፣ መንግስት ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራትም የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ገነት አብደላ፤ ሴቶች ለሀገር እድገትና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡   ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሴቶችን ማብቃትና መደገፍ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡ በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ የተገነባው የህጻናት ማቆያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ሴት አምራቾች ምርቶቻቸውን ለገበያ ያቀረቡበት ልዩ ኤግዚቢሽንም ተከናውኗል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሆስፒታሎች የሚውል ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመድኃኒትና ሕክምና ግብዓቶች አበረከተ
Mar 10, 2026 37
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለአምስት የመንግስት ሆስፒታሎች የሚውል ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ አበርክቷል። በጾም ወቅት የተቸገሩትን በመርዳትና በጎ ሥራን በማከናወን የሚታየው መደጋገፍ ሊጠናከር ይገባል-የሃይማኖት አባቶች በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አማካኝነት የተበረከተው ድጋፍ በዑስታዝ አቡበከር አህመድ አስተባባሪነት ከሙስሊም ኤይድ አሜሪካ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በድጋፍ ርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።   ድጋፎቹም ለአቦምሳ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ጭናክሰን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚውሉ ናቸው። በዚሁ ወቅት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንደገለጹት፤ ምክር ቤቱ ኃይማኖታዊ ግዴታን በመወጣት በዜጎች ማህበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በንቃት እየተሳተፈ ነው።   ለአምስቱ ሆስፒታሎች የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍም የረመዳን ወር የመተሳሰብና የመደጋገፍ መሆኑን በተግባር እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ ለሆስፒታሎቹ የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ ለጤና ተቋማት ተጨማሪ አቅም መሆኑን በመግለጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል 
Mar 10, 2026 62
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር የህክምና ግብዓቶችንና መሳሪያዎችን መደገፍ የሚያስችል የሶስት ዓመት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። በሸገር ከተማ የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት በተከናወኑ ተግባራት ውጤት እየተገኘ ነው በስምምነቱ መሰረት ከአጋር አካላት ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚቆይ የ282 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የህክምና ግብዓት ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ይህ ድጋፍ የእናቶች፣ የህፃናት እና የቤተሰብ ምጣኔ ግብዓት አቅርቦት ማሳደግ የሚያስችል ሲሆን የሕክምናውን ዘርፍ ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎችን የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡   የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለፉት ጊዜያት በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋትም አመርቂ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በመንግስት በጤና ተቋማት ለእናቶች የሚሰጠው የቅድመ ወሊድ እና የድህረ ወሊድ ነፃ የህክምና አገልግሎት ለዚህ እመርታ ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረው ለመንግስት ቁርጠኝነት መሳካት የማህበረሰቡ እና የአጋር አካላት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ሚኒስትሯ አክለዋል።   በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ክርስቲን ፐረን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ወሳኝ አጋር ሀገር መሆኗን ጠቁመው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የጤና ትብብር እየጠነከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ ያስመዘገበችውን ውጤት ለማበረታታት የታለመ መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች የአጋር ድርጅት ተወካዮችም በመንግስት በኩል የጤናውን ዘርፍ ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።
በጾም ወቅት የተቸገሩትን በመርዳትና በጎ ሥራን በማከናወን የሚታየው መደጋገፍ ሊጠናከር ይገባል-የሃይማኖት አባቶች
Mar 10, 2026 70
ቦንጋ ፤የመጋቢት 1/2018 (ኢዜአ) ፦በአቢይና በታላቁ ረመዳን የጾም ወቅት የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያለን በማካፈልና በጎ ሥራዎችን በማከናወን የምናሳየውን መደጋገፍ የሁሌም ተግባር ልናደርገው ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ። በሃይማኖት ብዝሀነት የምትታወቅ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች ለዘመናት አብረው ተቻችለውና ተከባበርው የኖሩባት ሀገር ናት። ሀገራዊ አንድነት እና ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሀይማኖቶች አብሮ የመኖር ውጤት ነው። የአቢይ ጸም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት፤ ታላቁ የረመዳን ጾም ደግሞ በእስልምና እምነትና ተከታዮቻቸው ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። እንደአሁኑ ክርስቲያኑም ሆነ ሙስሊሙ በአንድ ጊዜ ሲጾሙ ደግሞ በሃይማኖቶቹ መካከል ያለው የአንድነትና የመከባበር መንፈስ ይበልጥ ይጠናክራል። አጻሟቱ ካላቸው ሃይማኖታዊ ፋይዳ በሻገር ለሀገርና ለህዝቦች አንድነት፣ ለማህበራዊ ትስስር እና እርስ በርስ መደጋገፍ ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን የየእምነቶቹ አባቶች ይገልጻሉ። በቦንጋ ከተማ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኦርቶዶክስና የእስልምና እምነት አባቶች እንደገለፁት የአቢይና የረመዳን ፆም ወቅት መረዳዳትና መተሳሰብ የሚጎላበት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባት መጋቤ ሀይማኖት እሸቱ በላይ እንዳሉት፣ አቢይ ፆም በእምነቱ ተከታዮችና በቤተከርስቲያኒቷ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ፆም ከምግብና መጠጥ ብቻ መከልከል ሳይሆን ከክፉ ሀሳብና ተግባር መራቅ ጭምር መሆኑን አንስተው የጾም ወቅትን ለሀገርና ለህዝብ ሰላም አበክሮ ከመጸለይ ባለፈ በመተሳሳብ፣ በመደጋገፍና በፍቅር ማሳለፍ እንደሚገባ ገልፀዋል። በመሆኑም የእምነቱ ተከታዮች የተቸገሩትን በመርዳት፣ ካለ ላይ በማካፈልና በጎ ተግባራትን በማጠናከር ማሳለፍ እንዳለባቸው ጠቅሰው፣ እነዚህን መልካም ተግባራት በፆም ወቅት ብቻ ሳይሆን የሁሌም ባህል ልናደርጋቸው ይገባል ብለዋል። ያለምንም ልዩነት ከሁሉም ጋር በፍቅርና በአንድነት መኖር እንደሚገባ ጠቁመው፣ ከመለያየትና ከክፉ ነገር በመራቅ ለሀገር ሰላምና ልማት ተግቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የቦንጋ አንሷር መስጂድ ኢማም ሼህ ኢብራሒም አባጀበል በበኩላቸው፣ ታላቁ የረመዳን ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ፤ ከጾምና ጸሎት ባለፈ አንድነትና ፍቅርየሚጎላበት ነው ብለዋል። በእስልምና እምነት አብሮነት፣ መረዳዳትና መቀራራብን ማጠናከር ትልቅ ቦታ እንዳለው ገልጸው፣ ህዝበ ሙስሊሙ እነዚህን መልካም ተግባራት ከረመዳን ወር በኋላም ይበልጥ ማጠናከር አለበት ብለዋል። ረመዳን የሰላም ወር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ለሀገር ሰላም አብዝቶ ከመጸለይ ባለፈ፣ እርስ በርስ መደጋገፍን በማሳደግ አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።      
ኢኮኖሚ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ህብረተሰቡ በልማት ስራዎች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት መነቃቃት ፈጥሯል
Mar 10, 2026 42
ሐረር፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀረሪ ክልል ጉብኝት በክልሉ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እየሰጡት ያለው ጥቅም በተግባር የተረጋገጠበት እና ህብረተሰቡ ለልማቱ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት መነቃቃት የሚፈጥር ነው ሲሉ የሐረር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ትናንት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሐረር ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፤ ጉብኝቱ የልማት ሥራዎች በተግባር ለዜጎች እየሰጡት ያለውን ጠቀሜታ የተመለከቱበትና በቀጣይ ለላቀ ሥራ የሚያዘጋጅ ነው ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል መምህር ደረጀ ተስፋዬ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የፕሮጀክቶችን ክንውን እንዲሁም ለህዝብ እየሰጡት ያለውን አገልግሎት የገመገመ ስለመሆኑ አንስተዋል።   በቀጣይም የልማት ሥራዎች በተሻለ ፍጥነት እንዲከናወኑና ህብረተሰቡም የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብት ምቹ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማና የገጠሩን ገጽታ እየቀየረው መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም የክልሉን እድገት ለማፋጠን በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ የሐረር ከተማን ውብና ጽዱ ከማድረግ ባለፈ ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች ምቹ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ አቶ ደመቀ ካሳዬ ናቸው።   በክልሉ በልማት ሥራዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ደስታ እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት መነቃቃት በመፍጠር ይህን ተግባር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ጉብኝት ለአካባቢው ተስፋን የሰነቀና ልማት እንዲጠናከር መነቃቃትን የፈጠረ ነው ያለችው ደግሞ ወጣት ሄለን ሲራጅ ናት።   "በተለይ የኮሪደር ልማት ለወጣቶች የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ያሰፋና ተጠቃሚነትን እያጎለበተ ነው" ያለችው ወጣቷ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረር የልማት ሥራዎችን በመጎብኘታቸው ምስጋና አቅርባለች። በክልሉ ሶፊ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ማወርዲ ሙህየዲን በበኩሏ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አካባቢያችን መጥተው መጎብኘታቸው ለገጠሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያል፤ በዚህም ተደስቻለሁ" ብላለች።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በየአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለወጣቶች ተስፋን መሰነቁን ተናግራለች።
በክልሉ የግብርና አቅምን በመለየት የተከናወኑ የአሰራር ማሻሻያዎች ውጤት አምጥተዋል
Mar 10, 2026 39
ዲላ ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና አቅምን በጥናት በመለየት የተከናወኑ የአሰራር ማሻሻያዎች እና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ትግበራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በክልሉ የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት "በምርምር የታገዘ ግብርና፣ የበለፀገ ማኅበረሰብ፣ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው አውደ ጥናት በዲላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።   በአውደ ጥናቱ በሰብል፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የተሰሩ 1 ሺህ 107 የምርምር ሥራዎች ቀርበው የሚገመገሙ መሆኑ ተመላክቷል። በወቅቱም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በክልሉ የግብርና ሽግግርን ለማፋጠን ጥናትና ምርምርን መሠረት ያደረጉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በተለይም የክልሉን የግብርና አቅም በመለየት የተከናወኑ የአሠራር ማሻሻያዎችና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ትግበራዎች ውጤት ማምጣታቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም በክልሉ በሩዝ ልማት የተመዘገበውን ውጤት ለአብነት በመጥቀስ፣ መሰል ውጤታማ የምርምር ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፍቃዱ ግርማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የግብርና ምርምርን ከሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች ጋር በማጣጣም በተከናወኑ ተግባራት ስኬት መገኘቱን ገልጸዋል።   በተለይም በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች ግብርናውን ለማሻገር የሚያስችሉ ተጨማሪ አቅሞችን መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል። ግብርናው ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አጋዥ ኃይል ሆኖ በመውጣት ሽግግሩን እንዲመራም እየተከናወኑ ያሉ የምርምር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዞኑ በቡናና በእንሰት ልማት ላይ የታየው ለውጥ በሰብሎቹ ላይ የተካሄዱ የምርምር ሥራዎች ውጤታማ በመሆናቸው የመጣ ነው ብለዋል።   በተለይም በቡና ልማት ረገድ በምርምር ግኝቶች ላይ ተመስርተው የወጡ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ በሄክታር በአማካይ 5 ኩንታል የነበረውን የቡና ምርት ወደ 11 ኩንታል ማሳደጉን አስረድተዋል። ይሁን እንጂ የአፈር አሲዳማነት ዛሬም የዞኑ የግብርና ልማት ማነቆ መሆኑን በመጥቀስ፣ በዚህ ረገድ የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአውደ ጥናቱ ዓላማ የተቀናጁ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት የተሻለ የግብርና ልማትን ማረጋገጥ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዮት መብራቴ (ዶ/ር) ናቸው።   ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ የግብርና ምርታማነትን እያገዘ መሆኑን ገልጸው፤ በተያዘው ዓመት በ470 ሄክታር የአርሶ አደር ማሳ ላይ ሰርቶ በማሳየት የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦትን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል።
በክልሉ የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው
Mar 10, 2026 63
ሆሳእና፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በዘርፉ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ መድረክ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባበሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ኡስማን ሱሩር በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርምር ሥራዎች ለተጠቃሚው በመድረሳቸው በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው፡፡ የግብርና ምርምር ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማላመድና ዘመናዊ የእርሻ አስተዳደር ዘዴዎችን በማስተዋወቅ የዘርፉን ምርታማነት እያሳደጉ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም በሽታና ድርቅን ተቋቁመው የተሻለ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን፣ የቅመማቅመም ምርቶች እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለአርሶ አደሮች የማቅረብ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግብርናን በማዘመን ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግርን ከግብ ለማድረስ ተመራማሪዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፣ ማባዛትና ማሰራጨት ላይ ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፀጋዬ ተረፈ በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥን ተቋቁመው የተሻለ ምርት በሚሰጡ ዝርያዎች ላይ ምርምር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምርምር ውጤቶች ለአርሶ አደሮች ደርሰው በተጨባጭ ማሳ ላይ እንዲተገበሩ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በቅርበት እየሰራን ነው ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አድሩና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ መደረጋቸውን ገልጸዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚቆየው መድረክ ከተለያዩ ተቋማት የቀረቡ ከ265 በላይ የምርምር ሥራዎች እንደሚገመገሙ ተመላክቷል።
በኦሮሚያ ክልል የተሻሻሉና የአካባቢን ስነ-ምህዳር ታሳቢ ያደረጉ የቡና ችግኞች ይተከላሉ
Mar 10, 2026 107
ሮቤ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የተሻሻሉና የአካባቢን ስነ-ምህዳር ታሳቢ ያደረጉ የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የቡናና ፍራፍሬ ዘርፍ አስተባባሪ መሐመድሳኒ አሚን ገለጹ። አቶ መሐመድሳኒ አሚን በክልሉ ባለፉት ዓመታት የቡና ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ሲናወኑ መቆየታቸውንና በተያዘው የበልግ የዝናብ ወቅት የተዘጋጁ የቡና ችግኞችን ከ300ሺህ በሄክታር በሚበልጥ አዲስ መሬት ላይ ይለማሉ ብለዋል። የቡና ዝርያዎቹ ከግብርና ምርምር ተቋማት የተለቀቁ እንዲሁም የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከግምት ያስገቡ እና የተሻለ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውንም ለኢዜአ ገልጸዋል። ስራውን ስኬታማ ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ የግብርና ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። በክልሉ ባሌ ዞን የቡና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሙአዊያ ፉአድ ናቸው። ከግብርና ምርምር ማዕከላት የወጡ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በስፋት መትከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህን ዝርያዎች በመጠቀም ባለፉት ሰባት ወራት በወረዳዎቹ በተደረገው እንቅስቃሴ ከ41 ሚሊየን በላይ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ያላቸው ችግኞች ማዘጋጀት መቻሉን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት በዞኑ እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ በመጠቀም የቡና ችግኝ ተከላ መጀመሩን ገልጸው በዚህም 5ሺህ 700 ሔክታር አዲስ መሬት እንደሚለማ አስታውቀዋል። በልማቱም ከ20 ሺህ በላይ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን ጠቁመው የቡና ችግኝ ተከላውም ከአዲስ መሬት በተጨማሪ ያረጁና ከምርት ውጭ የሆኑ የቡና ተክሎችን በመንቀል ጭምር በምትኩ ተከላው እንደሚካሄድ አመልክተዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በክልሎቹ የከተሞች አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር ውጤት እያመጣ ነው
Mar 10, 2026 99
አዳማ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የከተሞች አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ። የክልሎቹ የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች ለኢዜአ እንደገለጹት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና የተገልጋይነት እርካታን ለማሳደግ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጨምር ኃይሌ እንደገለጹት፤ በክልሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ከወረቀት ንክኪ ነፃ በማድረግ ወደ ዲጂታል ስርዓት ለማስገባት ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል። በተለይም በመሬት፣ በግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር እንዲሁም የገቢዎችን ዘርፍ ጨምሮ 55 የሚሆኑ አገልግሎቶች በዲጂታል መንገድ መሰጠት መጀመሩን ተናግረዋል። የዲጂታል አገልግሎቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ በሆሳዕና፣ በቡታጂራ፣ በወልቂጤ፣ በዱራሜ፣ በወራቤ፣ በአላባ ቁሊቶና በሳጃ ከተሞች የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ16 ከተሞች በዲጂታል ዘዴ የታገዘ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን ወደ 24 ከተሞች ለማሳደግ የተጀመረው ስራ ይጠናከራል ብለዋል። አቶ ጨምር አክለውም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሶፍትዌሮችን በማቅረብ እና የዲጂታላይዜሽን ስራውን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ይህም የመረጃ አያያዝን ከማዘመኑም ባለፈ፣ ፋይል ለመፈለግ ይባክን የነበረውን ጊዜና የተገልጋዮችን ቅሬታ መቀነስ መቻሉን፣ እንዲሁም የሊዝ እዳ መረጃን በአግባቡ ለማወቅና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።   በተመሳሳይም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተማ ልማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ቢፍቱ ጎሹ፤ በክልሉ ከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በመሬት እና በገቢዎች ዘርፍ ያሉ ፋይሎችን ወደ ሶፍት ኮፒ የመቀየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በስምንት ማዕከላት ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል። በአሶሳ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ለመጀመር የግንባታና የፋይሎችን መረጃ ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ኢንጂነር ቢፍቱ አክለዋል።
የተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የዜጎች ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ሆነዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Mar 10, 2026 86
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018 (ኢዜአ)፡- የተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመንግሥት አገልግሎት አፈፃፀም ቁልፍ የክዋኔ ማመላከቻ እና የዜጎች ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ሆነዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጎብኝተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላም በሐረር ከተማ የተቋቋመው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር አቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል። አክለውም በሐረር የመሶብ ማዕከል 8 ተቋማት በ24 የአገልግሎት መስኮቶች 67 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ ለተገልጋይ ያቀርባል ብለዋል።   ይኸው ሀገራዊ አፈፃፀም የመንግሥት አገልግሎትን ብቃት፣ ተደራሽነት እና የዜጎች እርካታ በማሻሻል፣ በተቋማት መካከል የተበታተነ አገልግሎትን በመቀነስ፣ ኅብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት የሚያጠፋውን ጊዜ እና ገንዘብ መቀነስ አስችሏልም ነው ያሉት። ‎በመላው ሀገራችን የመሶብ ሥነ-ዘዴ፤ መንግሥት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ያለውን ጽኑ ዐቋም በሚያመላክት መንገድ እየተስፋፋ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመንግሥት አገልግሎት አፈፃፀም ቁልፍ የክዋኔ ማመላከቻ እና አጠቃላይ የዜጎች ተጠቃሚነት ማጎልበቻ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል።
በአማራ ክልል ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Mar 9, 2026 128
ባህርዳር፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት የሚያሳድጉ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዓመታዊ ክልላዊ የግብርና ምርምር ስራዎች አውደ ጥናት በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።   የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ደረጀ ማንደፍሮ በወቅቱ እንደገለጹት የ25 ዓመት የአሻጋሪ ዕድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ተገብቷል። በመሆኑም በክልሉ የሚገኙ እምቅ አቅሞችን ለማልማት በሚደረገው ጥረት ተመራማሪዎች፣ ምሁራንና ተባባሪ አካላት በተቀናጀ መልኩ መስራት ይኖርብናል ብለዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የምርምር ስራዎች አማካይ የሰብል ምርትማነት በሄክታር ከ10 ኩንታል ወደ 32 ኩንታል ማደጉን ጠቅሰው በተለይም የስንዴ ምርታማነት ከፍተኛ ማንሰራራት እያሳየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት የሚያሳድጉና ችግሮችን የሚፈቱ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። በምርምር አበረታች ውጤቶች ቢመዘገብም የአፈር አሲዳማነት፣ የግብርና መካናይዜሽን ዕጥረት፣ የድህረ ምርት ብክነትና ሌሎች ችግሮች እየተፈቱ መሄድ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።   የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሰማኽኝ አስረዴ(ዶ/ር)፤ ኢንስቲትዩቱ ባለፉት ዓመታት የአርሶ አደሩን ኑሮ ሊቀይሩ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ የምርምር ስራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል። በዚህም በሰብልና እንስሳት ልማት፤ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በደን ልማት ስኬታማ ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተው በምግብ ሳይንስና በባዮ ቴክኖሎጂ የተገኙ ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ ግብርናውን ለማዘመን አሁን ላይ 960 የተለያዩ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አንስተው 371 የሚሆኑትን ዘንድሮ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ተናግረዋል።   የአማራ ክልል የዩኒቨሲቲዎች ፎረም ዋና ጸሀፊ ተወካይ ጀጃው ደማሙ(ዶ/ር)፤ በበኩላቸው ከግብርና ምርምርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአርሶ አደሩን ኑሮ የሚቀይሩና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርምር ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው አንስተዋል።    
ኢንስቲትዩቱ በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ተደራሽ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው
Mar 9, 2026 182
ወልቂጤ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በግብርናው ዘርፍ በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ተደራሽ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ በወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ዝርያቸው የተሻሻሉ ጊደሮችና ኮርማዎችን ለሞዴል አርሶ አደሮችና በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራት የማስተላለፍ እና የመስክ ምልከታ መርሃ ግብር አካሂዷል። በወቅቱም የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ድሪባ ገለቴ(ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ በ23 የምርምር እና በ712 የአገልግሎት ማዕከላት አዳዲስ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።   በሀገሪቱ አሁን ላይ ከ271 በላይ የምርምር ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ የሀገሪቱን እድገት ማፋጠን የሚያስችሉ በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፉ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ኢንስቲትዩቱ በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ተደራሽ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል እና የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ ኢያሱ ተረፈ በግብርና ምርምር የተገኘው ስኬትና ማንሰራራት ቀጣይነት እንዲኖረው የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።   ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት በክልሉ የወተት ምርታማነት 675 ሚሊየን ሊትር ላይ መድረሱን ጠቁመው በዘንድሮ ዓመት 744 ሚሊየን ሊትር ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው የምርምር ስራዎች በዞኑ የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የማሳደግ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የገለፁት ደግሞ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማ ናቸው።   የለውጡ መንግስት ለግብርና ልማት በሰጠው ትኩረት የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተግባራዊ መደረጉ የእንስሳት ልማቱን በግብዓትና በአዳዲስ አሰራር ለማገዝ አስችሏል ብለዋል። የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ቤተል ነክር በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር መፍታት የሚያስችሉ የተለያዩ የግብርና ምርምር ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰዋል።   ለዓመታት የምርምርና ብዜት ሥራ ሲከናወንባቸው የነበሩ የተሻሻሉ የኮርማ፣ የጊደርና የዶሮ ዝርያዎችን ለሞዴል አርሶ አደሮች እና በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራት እንዲሰጡ መደረጉንም ተናገረዋል።   የሶዶ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር አድማሱ ግዛው፤ ከእርሻ ሥራቸው ጎን ለጎን ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞቹን በማርባት ከሚያገኙት ምርት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ገቢያቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።   በምርምር ማእከሉ የተሰጧቸው ዝርያቸው የተሻሻሉ ዶሮዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግላቸው የገለፁት ደግሞ በአበሽጌ ወረዳ የጣጤሳ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ መውደድ ሰርጉ ናቸው። በወልቂጤ ከተማ ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶችን በማርባት በቀን 60 ሊትር ወተት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እያደረጉ መሆናቸውን ያነሱት ደሳለኝ ዘበርጋ(ዶ/ር) ናቸው።   በዘንድሮ ዓመትም ከምርምር ማእከሉ ዝርያቸው የተሻሻሉ ጊደሮችን ማግኘታቸውን ነው የገለጹት።
ስፖርት
ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ
Mar 10, 2026 56
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1 /2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ልደታ ክፍለ ከተማን 4 ለ 2 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። ማህሌት ምትኩ ቀሪዋን ጎል ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ሄለን ጌታቸው እና ይታገሱ ተገኘወርቅ ለልደታ ክፍለ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሀትሪክ የሰራችው ዳግማዊት ሰለሞን የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች። በሊጉ 16ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ49 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። ከተከታዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለው ልዩነት በሁለት ነጥብ ቀጥሏል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በ15 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። የኢትዮ ኤሌክትሪኳ አጥቂ ዳግማዊት ሰለሞን በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ 22 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቷን አጠናክራለች። ዛሬ በተደረገ የ18ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ አትላንታ ከባየር ሙኒክ ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
Mar 10, 2026 89
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል።   በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ምሽት 5 ሠዓት ላይ አትላንታ ከባየር ሙኒክ በቤርጋሞ ስታዲየም ይጫወታሉ።   አትላንታ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በደርሶ መልስ 4 ለ 3 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል። ባየር ሙኒክ በሊግ እርከን ምዕራፍ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ ገብቷል። እ.አ.አ የ2024 የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አትላንታ እና የሦስት ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊጉ አሸናፊ ባየር ሙኒክ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።   በሌላኛው መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና ምሽት 5 ሠዓት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ኒውካስትል በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የአዘርባጃኑን ካራባግን በደርሶ መልስ 9 ለ 3 በመርታት ጥሎ ማለፍ ገብቷል። ተጋጣሚው ባርሴሎና በ16 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ መግባቱ ይታወቃል።   በራምስ ፓርክ ስታዲየም ጋላታሳራይ ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በራምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ። የቱርክዬው ጋላታሳራይ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ጁቬንቱስን በድምር ውጤት 7 ለ 5 በማሸነፍ ጥሎ ማለፍ መግባቱ ይታወቃል። ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ በቀጥታ 16 ውስጥ ገብቷል። ክለቦቹ በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ተገናኝተው ጋላታሳራይ 1 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።   በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም አትሌቲኮ ማድሪድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር ምሽት 5 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። አትሌቲኮ ማድሪድ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የቤልጂየሙን ክለብ ብሩዥ በደርሶ መልስ 7 ለ 4 አሸንፏል። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ17 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብቷል። የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስኬቶች ጤናማ የአካባቢ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር አስችለዋል
Mar 9, 2026 104
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስኬቶች ጤናማ የአካባቢ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር ማስቻላቸውን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ተምሳሌታዊ ተግባር ነው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ በሁለተኛው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ ፈጠራና የሕግ ተከባሪነት ስኬታማ ስራ ተሰርቷል። የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስኬቶችም የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ለፅዱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል። የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የፕላስቲክ፣ የአፈር፣ የውሃ፣ የአየርና የድምፅ ብክለትን በመከላከል የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል። በንቅናቄው መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ15 ሚሊየን በላይ ከሚሆን ህዝብ ጋር የገፅ ለገፅ መድረክ በመፍጠር የአካባቢ ጥበቃና ፅዱ አካባቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠቱን አንስተዋል። በመገናኛ ብዙሃንም ከ50 ሚሊየን በላይ ህዝብ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ በአካባቢ ላይ የሚደርስ ብክለትን መቀነስ የሚያስችል የዕውቀት፤ የግንዛቤና የሕግ ማስከበር ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል። በዚህም በሁለት ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የዜጎችን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማሳደግ ፅዱና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል መሰረት መጣሉን ጠቅሰዋል። በቀጣይም 3ኛ ዙር የፅዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በ3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የለውጡን ዓመታትን የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስኬቶች በማጽናት ባህል ይሰራል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተተገበሩ የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የገጠርና ከተማ ኮሪደር ልማት ስኬቶች የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ለፅዱ ኢትዮጵያ ግንባታ ወሳኝ ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ስራ የፍሳሽ አወጋገድና የቆሻሻ አያያዝን በማዘመን ዜጎችን ፅዱ የመኖሪያ ምኅዳር በማጎናጸፍ የወንዞችን ጤናማነት የሚያስጠብቅ ተምሳሌታዊ የልማት ስኬት መሆኑንም ተናግረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃና የእርከን ሥራ የሥነ-ምኅዳር ደኅንነትን በማስጠበቅ ገንቢ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል። በሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታም ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሰሩ የግሉን ዘርፍ ማበረታታት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አመላክተዋል።
‎በጋምቤላ ክልል የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ 
Mar 9, 2026 141
ጋምቤላ ፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። በክልሉ ኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመከላከል ጤናማ የገበያ ሥርአት ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል ‎‎በክልሉ በዘንድሮው ዓመት እየተካሄደ ባለው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች የማጠናከሪያ መርሃ ግብር በጎግ ወረዳ እየተካሔደ ነው። ‎‎ርዕሰ መስተዳደሯ አለሚቱ ኡሞድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የጎላ ድርሻ አላቸው።   ‎‎ይህን ታሳቢ በማድረግ በተራቆቱ አካባቢዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጠናከር በክልሉ የተጀመረውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት መስራቱ ይቀጥላል ብለዋል። ‎በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፋሰስ ልማትና የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የአካባቢ መራቆትንና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል በኩል እመርታዊ ለውጥ እንዲመጣ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። ‎‎በመሆኑም የተጀመረው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ይገባዋል ብለዋል። ‎በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ‎የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ ለተቀመጠው ግብ መሳካት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች የላቀ አበርክቶ አላቸው።   ‎‎ባለፉት አመታት ለተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች በተሰጠው ትኩረት የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙና የግብርና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል። ‎‎በመሆኑም የተፈጥሮ ሃብትን መሠረት ያደረገ የግብርና ልማትን ለማስፋት የተጀመረው ጥረት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ‎‎የጋምቤላ ክልልም ለግብርና ልማት የተመቸ ስነ ምህዳር ያለው አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ሃብት በአግባቡ አልምቶ ከመጠቀም አንፃር የቅንጅት ስራዎች እንደሚጠናከሩ ገልፀዋል። ‎በክልሉ ሲከናወን በቆየው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የአፈር እርጥበታማነትንና ለምነትን በማሻሻል የሰብል ምርታማነትን እያሳደገ ይገኛል ያሉት ደግሞ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድሮው ቱት ናቸው። ‎‎በክልሉ የተፋሰስ ልማትን በማጠናከር የከርሰ ምድርና የገፀ ምድርን የውሃ ሀብት በማሻሻል የግብርና ልማቱን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት። ‎‎በክልሉ በዘንድሮዉ የተፋሰስ ልማት ስራ በሁሉም ወረዳዎች በ101 ተፋሰሶች፤ 64 ሺህ ሄክታር የተራቆተ መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል ።
የአባያና ጫሞ ሀይቆችን ከስጋት መታደግ የሚያስችል የተቀናጀና በጥናት የተደገፈ ስራ ይሰራል
Mar 7, 2026 152
አርባ ምንጭ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦ የስምጥ ሸለቆ ተፋሰስ የሆኑ የአባያና ጫሞ ሀይቆችን ከስጋት ለመታደግ የተቀናጀና በጥናት የተደገፈ ስራ እንደሚሰራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የአባያና ጫሞ ሀይቆች የሚያስከትሉትን ተጽእኖ መቀነስ የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት የአባያና ጫሞ ሀይቆችን በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ከፀጋነት ወደ ስጋትነት እየተቀየሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።   በተለይ በጋሞ፣ በጋርዱላ፣ በኮንሶና በቡርጂ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ እንዲሁም በተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይ አደጋ እያስከተሉ ይገኛሉ ብለዋል። በመሆኑም ሐይቆቹን ከስጋት ለመታደግ የተቀናጀና በጥናት የተደገፈ ስራ እንደሚጠናከር ገልጸዋል፡፡ ተፋሰሶቹ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር፣ የፍራፍሬ፣ የብዝሃ ህይወት የቱሪዝምና የቀጣናዊ ልማት ማሳለጫዎች መሆናቸውን ጠቅሰው ከስጋት ወደ ሀብት ምንጭነት ለመቀየር የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። በውሃው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉን ችግሮች ለመቅረፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የክልሉ መንግስት የበኩሉን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል።   የማዕድን ሚኒስትርና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በበኩላቸው የአባያና ጫሞ ሃይቆችን በዘላቂነት መጠቀም ለሃገር ሁለንተናዊ ብልጽግና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ በአርባ ምንጭና አካባቢው መልከ ብዙ ፀጋዎች መኖራቸውን ጠቅሰው የሀይቆቹን ትሩፋት ለማጉላት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በአግባቡ ሊከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል። በተገኙ ጥናቶች መሠረት የተፋሰሶቹን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ፕሮግራሞች፣ ስትራቴጂዎችና ፕሮጀክቶች ተቀርጸው መተግበር እንዳለባቸውም አመልክተዋል።   የአባያና ጫሞ ሀይቆች የውሃ መጠን መጨመር፣ የተፋሰሱ ወንዞች ሙላትና ደለል ከፍተኛ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎችን እያስከተሉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አብደላ ከማል(ዶ/ር) ናቸው። የአባያና ጫሞ እንዲሁም ሌሎች ተፋሰሶች በተቀናጀ ሁኔታ ካልተመሩ ተጽዕኖው ከሀይቆቹ ዳርቻ አልፎ ሰፊ ቦታዎችን ሊያዳርስ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡንም ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲው በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመከላከል የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። በመድረኩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎችና ተመራማሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም እየተሳተፉ ነው።
የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ተምሳሌታዊ ተግባር ነው
Mar 7, 2026 112
አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አርአያ የሚሆን ስራ እያከናወነች እንደምትገኝ የዓለም ባንክ ከፍተኛ የግብርና ባለሙያ ቲም ሮበርትሰን ገለጹ። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አስተማማኝ የግብርና ሥርዓት መገንባት ይጠበቅባቸዋል ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባትና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነች ትገኛለች። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን ማምረት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የስንዴ ምርታማነት፣ የኢትዮጵያ የማዳበሪያ እና የጤናማ አፈር ፍኖተ ካርታ፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን የመስኖ ስራዎች ማስፋትና የተራቆቱ መሬቶችን በአካባቢ ጥበቃ ስራ ወደ ነባር ይዞታቸው መመለስ ከተከናወኑ ተግባር መካከል ይጠቀሳሉ። የዓለም ባንክ ከፍተኛ የግብርና ባለሙያ ቲም ሮበርትሰን ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እየገነባች ያለችው አቅም የሚደነቅ መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነች እንደሚገኝ ጠቅሰው እንደ አረንጓዴ አሻራ ባሉ ኢኒሼቲቮች የቀጣናው ሀገራት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የዘርፉ ስኬቶች ለማስፋት መንግስት፣ ቀጣናዊ ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጣናው የሚገኙ ሀገራት በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ያላቸውን አቅም የበለጠ ማጠናከር እንደሚኖርባቸውም ነው ባለሙያው የገለጹት። በዚህ ረገድ የዓለም ባንክ ከመንግስታት ጋር የግሉ ዘርፍ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ያለውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግና በተለይም ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኢኖቬሽን፣ ዲጂታል መፍትሄዎች፣ ዘላቂ የኢነርጂ አጠቃቀም እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ነው ያነሱት። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የዓለም የግብርና ፋይናንስ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን ገልጸው ሀገራት ፋይናንስ በዘላቂነት የሚያመጡ አጋርነቶችን መፍጠር እንዳለባቸው መክረዋል። ለዚህ ተቋማት ትስስራቸውን ማጠናከር፣ አማራጭ ፋይናንስ መፈለግ፣ እሴት መጨመር ትኩረት መስጠት እና ለጋራ ግብ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 60
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።   በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 88
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ደኅንነት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 5, 2026 129
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የኢጋድ የሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ውይይቱን ያደረጉት የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) በመወከል ነው። ውይይቱ ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው። ሁለቱ ወገኖች የጋራ የተግባር ምላሽ ለመስጠት እና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ 
Mar 2, 2026 239
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል።   የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል።   የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 288
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።      
   የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 288
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን።   የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው።   የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።   የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።   የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 724
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ።   በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 322
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር
Feb 24, 2026 428
(በአየለ ያረጋል) ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፤ ኢትዮጵያና እስራኤል። የሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረው ግንኙነት አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች የተጠናከረ ሆኖ ይገኛል። የሀገራቱ ግንኙነት ግን እንደየስርዓተ መንግስታቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባህሪ መልኩን እየለዋወጠ እና ውጣ ውረዶችን እያለፈ የተሻገረና ጠንካራ መሆኑም ይታወቃል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪካዊ ገጽታ፦ ሃገራቱ የግንኙነታቸው ትርክት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በንግሥተ ሳባ እና በንጉሥ ሰለሞን ዘመነ መንግስት እንደሆነ አፈ ታሪክ ያስረዳል። ይህ አፈ-ታሪካዊ እርሾ ከኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ጋርም ቀጥሏል። በመካከለኛው እና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ሃይማኖትና ንግድ ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አስተሳስሯል። በተለይም ዴር ሱልጣንን ጨምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት መኖር የሁለቱን ሀገራት ባህላዊ ተጋምዶሽ አጎልብቷል። ይህ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ከእስራኤል ሀገረ መንግስት ዳግም መመስረት በኋላም በዘመናዊት ኢትዮጰያ ታሪክም ቀጥሏል። የኢትዮ እስራኤል ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፦ የዘመናዊ የኢትዮ-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተወጠነው በአውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ1956 ሲሆን በ1961 ይፋዊ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል። በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግስት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ ጥቅምን ያማከለና የወቅቱን የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አድርጓል። በንጉሳዊ ስርዓተ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ሌሎች የልማት ቴክኒካል ድጋፍ የደረሰ ወዳጅነት ነበራቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በእስራኤለና አረቦች ጦርነት ሳቢያ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል። ያም ሆኖ በግልጽም ሆነ የህቡዕ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ይወሳል። መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በደርግ መንግስት መጨረሻ ዓመታት (በአውሮፓውያኑ 1989) የኢትዮ-እስራኤል ይፋዊ ግንኙነት ዳግም ተጀምሯል። የ"ኦፕሬሽን ሙሴ" (1984) እና "ኦፕሬሽን ሰለሞን" (1991) የተሰኙ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የማጓጓዝ ተልዕኮዎችም በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ስምምነት የተካሄዱ መሆናቸውን ልብ ይሏል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም) ጀምሮ ደግሞ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጥሏል። በፈረንጆቹ 1992 ኢትዮጵያ በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፍታለች። በፈረንጆቹ 2003 ኢትዮጵያና እስራኤል የኢንቨስትመቶች ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1996 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2004) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አሪኤል ሻሮን ጋር ያደረጉት ታሪካዊ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሳድጎታል። ጉብኝቱን ተከትሎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ያጠናከሩ የተለያዩ ስምምነቶች ተደርገዋል። በተለይም በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከፍ ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትና ፀረ ሽብር ጉዳዮች እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥና የድንበር ጥበቃ ቴክኖሎጂ በትብብር ለመስራት መሰረት ጥለዋል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአዲስ አበባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም መክረዋል። በተመሳሳይ በፈረንጆቹ በ2017 የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ጎብኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በየራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ቆመዋል። በዓለም አቀፍ መድረኮች አንዳቸው ለሌላው ድምጽ በመስጠት ተደጋግፈዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ለብሔረታዊ ጥቅሞቿ መጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እስራኤል አሉታዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይልቁንም እስራኤል ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ እንደ መግቢያ ሁነኛ በር አድርጋ ትቆጥራለች። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮ-አስራኤል ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴካዊ አጋርነት አድጓል። በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በእስራኤል ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ደግሞ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ እንዲታደስ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ታሪካዊ የተሰኘውን ምክክር አድረገዋል። መሪዎቹ በሰጡት ገለጻም በአምስት ነጥቦች ላይ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በውሃ፣ በመስኖ፣ በጤና እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ መፈራረማቸውን አውስተው ነበር። በግብርና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምተው እንደነበርም እንዲሁ። ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ፦ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ልማት በመለወጥ የንግድና ኢንቨስመንት ግንኙነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አከናውነዋል። የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እየጎለበተ መጥቷል። ለአብነትም የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል። በማዕድን ዘርፍ (በፖታሽ)፣ በማምረቻ ዘርፍ( በጨርቃጨርቅ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች) እንዲሁም በጤናና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ ነው። በተለይም በግሪን ሃውስ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በፋርማሲዩቲካል (የመድኃኒት) ዘርፎች ሁነኛ ተሳትፎ አድርገዋል። በተመሳሳይ በንግድ ልውውጥ ረገድ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ እስራኤል በስፋት ትልካለች። በአንጻሩ እስራኤል የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የግብርና ግብዓቶችን (ማዳበሪያና ኬሚካሎች)፣ የሕክምና መሣሪያዎችን እና የደህንነት ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረቅ አካባቢ ግብርና ስመጥር የሆነችው እስራኤል በዘርፉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት አጋር ስትሆን በዘመናዊ መስኖ፣ የአቮካዶና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት እርባታ እና የወተት ምርታማነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች በጎ ተሳትፎ ታደርጋለች። በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወዳጅነት መጠናከር ቤተ-እስራኤላውያን እንደ ድልድይ አገልግለዋል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ160 ሺህ በላይ መሰረታቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላዊያን ዜጎች አሉ። እነዚህ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ሁነኛ ድልድይ ሆነዋል። በተለይም በእስራኤል የሰለጠኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በማስቻል በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በንግድ ስራ ረገድ ውጤታማ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ፈጥጠሯል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸውን ከፍ አድርጎታል። የፕሬዝዳንት ሔርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሃገራት የጸና ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጎለብት እንደሚሆን ይጠበቃል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ የሚያጠናክሩበት ምቹ ሁኔታም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1147
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል።   ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር።   ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ።   ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ   ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ   ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።   ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው።   መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ 
Jan 1, 2026 1151
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው።   በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል።   ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ   ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 3640
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2424
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8219
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6704
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60535
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54470
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35043
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32620
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 27767
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 26846
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26367
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26067
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60535
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54470
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35043
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32620
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 450
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ።   እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል።   የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል።   በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል።   ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል።   በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡
ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት
Feb 26, 2026 420
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያደርሰዋል።   ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት አዘርባጃን እ.አ.አ በ1991 ነጻነቷን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። የሀገራቱ ግንኙነት ከእ.አ.አ 1990ዎች መግቢያ አንስቶ እያደገ መጥቷል። አዘርባጃን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ኤምባሲ የከፈተች ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር እንዲጠናከር በር ከፍቷል። በቱርክዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስራ የሚሸፍን ሲሆን ፖለቲካ፣ ትምህርት እና ባህል ሀገራቱ ካላቸው የትብብር መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።   የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል በባለብዙ ወገን መድረክ በገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) መድረክ በትብብር እየሰሩ መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2019 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 18ኛው የገለልተኛ ሃገራት ንቅናቄ (ናም) ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ 120 አባል ሃገራትን ያቀፈና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓለም ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። በሀገራቱ መካከል ተከታታይ የሆኑ የባህል ልውውጥ መድረኮች ተካሄደዋል። ለዚህም እ.አ.አ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአዘርባጃን የትምህርት እድል አግኝተው ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢኮኖሚ አንጻር እ.አ.አ በ2017 በአዘርባጃን የተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ፎረም ተጠቃሽ ነው። በወቅቱ ጨርቃጨርቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በወቅቱ ሀገራቱ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ምጣኔ ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ባለስልጣናት መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እያደጉ መጥተዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአዘርባጃን ጉብኝት ማድረጋቸወ ይታወሳል። ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም እንዲሁ። ምክክሩ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍና በትብብር መንፈስ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም በወቅቱ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር በነበራቸው ውይይት የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ መክረዋል። በውይይቱም በመረጃ፣ በፀጥታና ደህንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም መስማማታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው ይታወሳል።   እ.አ.አ በ2017 በወቅቱ የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኤልማር ማማድያሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቋሚነት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ማኅበራዊ ፈጠራ ተቋም ሊቀ መንበር ኦልቪ ሜዲዬቭ የብሔራዊ ቤተመንግሥት እና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል። ኦልቪ ሜዲዬቭ በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል።   የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ የተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን የምትልካቸው ምርቶች ብዝኀነትን ለማሳደግና ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ሰሊጥ፣ የተቆላ ቡና፣ ተልባ፣ የፍየል እና የበግ ሥጋን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡   በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ንግድ ትብብር ላይ ያተኮረው ሶስተኛ የኢትዮ-አዘርባጃን የውይይት መድረክ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ከውይይቱ በኋላ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል። 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) በህዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን መካሄዱ ይታወቃል። በጉባኤው ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጋለች። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑክ ከአዘርባጃን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ሀገራቱ በአካባቢ ጥበቃ፣ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገራቱ መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደረጉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ትምህርት እና ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሻሉ።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ እንደሚታይ አንስቷል። የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝትም የዚሁ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጉብኝት በመሪ ደረጃ የሚደረግ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር የቅርብ ዓመታት ውይይቶች እና ጉብኝቶች ማሳያ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም