ቀጥታ፡

በገዥ ትርክት የሚመራ ተግባቦት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው-ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦በገዥ ትርክት የሚመራ ተግባቦት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው በብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ''ውጤታማ ተግባቦት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ'' በሚል መሪ ሃሳብ የስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ለጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና የኮሙዩኒኬሽን ሙያተኞች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚሰጠው ስልጠናም ከዛሬ ሰኔ 5 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።

በብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በመድረኩ፤ ትርክት የአንድ ማህበረሰብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ የሚቃኝበት የአስተሳሰብ ውቅር ነው ብለዋል።

በዚህም በገዥ ትርክት የሚመራ የአመራርና ሙያተኛ ተግባቦት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።


 

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ ስኬታማ ተግባቦት የውጤታማ መሪ መለያ መሆኑን ተናግረዋል።

የጤና ዘርፍ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥም ሀገራዊና ጂኦፖለቲካዊ ሥነ-ምኅዳርን ያገናዘበ ጠንካራ ተግባቦት እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በበኩላቸው፥የጤና ዘርፍ ሙያተኞች ውጤታማ ተግባቦት የህብረተሰብ ደህንነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የኢትዮጵያ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ስኬታማ ለውጥ በጤናው ዘርፍ የፈጠረውን እመርታዊ ለውጥ ውጤታማ ተግባቦት መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በጤና ዘርፍ በአክሞ ማዳንና በሽታ በመከላከል የተገነቡ ውጤታማ አቅሞችን ማጠናከር የሚያስችል ተቋማዊ ተግባቦት እየተፈጠረ ነው ያሉት ደግሞ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዲላሂ ናቸው።


 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሳፍንት ተፈራ በበኩላቸው፥በሕትመትና ሁነት ዝግጅት ገዥ ትርክትን መገንባት የሚያስችሉ ይዘቶች ተቀርጸው እየተሰራባቸው ይገኛል ብለዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም