ቀጥታ፡

በስሉጥ ከተማ ስሉጥ አገልግሎት- አዲስ መሶብ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5 / 2018 (ኢዜአ)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ከታየው አስደማሚ የከተሜነት ትራንስፎርሜሽን ጎን ለጎን የሕብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ሰው ተኮር ስራዎች ተሰርቷል፤ እየተሰሩም ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ ውስጥ የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት ስር-ነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣትም መጠነ ሰፊ የሆነ የመሰረተ-ልማት እና የሰው ኃይል ልማት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ዕድገቷን እና ስሉጥ ከተማነቷን (Smart-city) የሚመጥን አገልግሎት ለማቅረብ ቴክኖሎጂን ተግባር ላይ የማዋል ሂደት አጠናክራ ይዛለች፡፡ ይኸውም የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ቀዳሚው ተጠቃሽ ነው፡፡


 

አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ በማድረግ የሕብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ቀን ከሌሊት እየተሰራ ይገኛል፤ የላቀ ውጤትም ተመዝግቦበታል፡፡

እስካሁን በማዕከል እና በዘጠኝ ክፍለ-ከተሞች እንዲሁም በተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የተደራጀ፣ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግባቸው፣ የበቁ የሰው ኃይል የተሟላላቸው ማዕከሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በቴክኖሎጂ በታገዘ በተደረገ ዳሰሳ እንደሚያሳየው ተገልጋዩ ከ99 በመቶ በላይ እርካታ ያመላክታል፡፡ ቀሪ ሁለት ክፍለ ከተሞችም ግንባታቸው ተጠናቅቆ በጥቂት ቀናት አገልግሎት ይጀምራሉ፡፡


 

የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለትን ታሪክ ለማድረግ በቁርጠኝነት ተተግብሮ፣ የሕብተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ እንደሚሰራ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም