ቀጥታ፡

ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ መርሐ ግብር ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት ማምሻውን በቶሮንቶ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ ጆቮ ሉኪች በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቦሲኒያ መሪ ሆናለች።

ከእረፍት መልስ  ተቀይሮ የገባው ካይል ላሪን በ78ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ግብ ካናዳን አቻ አድርጓል።

ካናዳ በጨዋታው ብልጫ ብትወስድም ተጨማሪ ጎሎች ማስቆጠር አልቻለችም።

ከዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ካናዳ በውድድር ተሳትፎዋ ታሪክ የመጀመሪያ ነጥቧን አግኝታለች።

ቦሲኒያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ አንድ ነጥብ አግኝታለች።

ከጨዋታው በፊት በቶሮንቶ ስታዲየም የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

በዚሁ ምድብ ኳታር ከስዊዘርላንድ ነገ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በሳንፍራስሲስኮ ቤይ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም